15262
ይህ ቲቃ (ታማኝ) ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
የአሜሪካ ሚስጥራዊ አገልግሎት ትራምፕ ላይ አደጋ ሊያደርስ የነበረ ግለሰብ ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።
በ20ዎቹ እድሜ ውስጥ የሚገኘው ወጣት ፍሎሪዳ በሚገኘው የፕሬዝዳንት ትራምፕ መኖሪያ ሊገባ ሲል መገደሉን አስታውቋል።
ወጣቱ ተተኳሽ ጥይት እና የእሳት አደጋ መከላከያ ይዞ እንደነበር ተገልጿል።
ግለሰቡ በማንም ላይ ጉዳት ሳያደርስ ነው ህይወቱ ያለፈው ተብሏል። #luxembourgtimes
@EyobTikuye @ThiqahEth
በኢትዮጵያ የሚገኙትን ጨምሮ ለሱዳን ስደተኞች ድጋፍ 1.6 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ተመድ አስታወቀ።
ይህ ድጋፍ የሚያካትተው ከሀገር ውጪ ተፈናቅለው በሰባት ሀገራት ለሚገኙ ሱዳናውያን ብቻ ነው ተብሏል።
ይሁን እንጂ 470 ሺሕ የሚጠጉ በድንበር አካባቢ የሚገኙና ለመውጣት የተዘጋጁ ተፈናቃዮች መካተታቸውን ድርጅቱ ገልጿል።
በዚህ የሰብዓዊ እርዳታ ጥቅል 5.9 የሱዳን ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱን አመላክቷል።
ስደተኞቹ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሊቢያ፣ ቻድ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ማዕከላዊ አፍሪካ፣ ኡጋንዳና ግብፅ እንደሚገኙ ተገልጿል። #thelibyaobserver #unnews
@EyobTikuye @ThiqahEth
"እስራኤል በመካከለኛው ምስራቅ ሰፊ ግዛት እንዲኖራት መፅሐፍ ቅዱስ የሰጣት መብት አለ" - አምባሳደሩ
"አደገኛና ፀብ አጫሪ አስተያየት ነው" - 14 የሙስሊም ሀገራት
የአረብና ሙስሊም ሀገራት በእስራኤል የሚገኙትን የአሜሪካ አምባሳደር አስተያየት አውግዘዋል።
አምባሳደር ማይክ ሁካቤ ባደረጉት ቃለ ምልልስ "እስራኤል በመካከለኛው ምሥራቅ ሰፊ ግዛት እንዲኖራት መፅሐፍ ቅዱስ የሰጣት መብት አለ" ብለዋል።
"ከግብፅ የአባይ ወንዝ እስከ ሶርያ እና ኢራቅ የኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ የግዛቷ አካል ነው" ሲሉም ተደምጠዋል።
ሳዑዲ አረቢያ፣ ፓኪስታን፣ ቱርክና ጆርዳንን ጨምሮ ሌሎች አስር የሙስሊም ሀገራት "አደገኛና ፀብ አጫሪ አስተያየት ነው" ሲሉ የሁካቤን ንግግር ተችተውታል።
ሀገራቱ "የተመድን አለማቀፍ ህግ የሚጣረስ እና የጋዛን ጦርነት የሚያባብስ ነው" በማለት ተቃውመዋል።
የእስላማዊ ምክርቤት ትብብር (OIC) እና የገልፍ ትብብር ካውንስል (GCC) በጉዳዩ ላይ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል። #france24
@EyobTikuye @ThiqahEth
በሚኒሶታ ስደተኞችን የመያዝ ዘመቻ "ተጠናቋል" ተባለ።
በአሜሪካ ታሪክ ትልቁ ነው የተባለው የስደተኞች አፈሳ በሚኒያፖሊስ ብቻ ከ2000 በላይ የኢሚግሬሽን ፖሊሶች (ICE) ተሳትፈዋል ተብሏል።
በዘመቻው በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች መያዛቸው ተገልጿል።
ድርጊቱን ለመቃወም ከወጡት ሰልፈኞች ውስጥ ሁለት አሜሪካውያን ሲገደሉ፣ ህፃናትን ጨምሮ ሌሎች ዜጎች ታስረዋል ተብሏል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰነድ አልባ ስደተኞችን ወደ መጡበት ሀገር የመመለስ ዘመቻ መጀመራቸው ከፍተኛ ተቃዋውሞ አስከትሎባቸዋል። #euronews
@EyobTikuye @ThiqahEth
ሩሲያ ዋትሳፕ መተግበሪያ ሙሉ በሙሉ ልትዘጋ ነው ተባለ።
ሞስኮ ሀገር በቀል የሆነውን ማክስ የመልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያ በመተካት በአሜሪካው የሜታ ካምፓኒ ስር የሚተዳደረው ይህ የማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያ አገልግሎት እንዳይሰጥ ወስናለች።
የሜታ ካምፓኒ ቃል አቀባይ "ከ100 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎችን መነጠል ኋላቀር እርምጃ ነው" ሲሉ አጣጥለውታል።
ሩሲያ ከቀናት በፊት የቴሌግራም የመልዕክት ልውውጥ ላይ የግል ሚስጥር ባለመጠበቅ እና በመረጃ ማጭበርበር አሰራር ገደብ ጥላለች።
ዋትስአፕ ለምን እንደሚታገድ የሩሲያ መንግስት የሰጠው ግልፅ ማብራሪያ የለም። #theguardian
@EyobTikuye @ThiqahETH
በማዳጋስካር በተከሰተው አውሎንፋስ የ20 ሰዎች ህይወት አለፈ።
የአውሎንፋሱ ፍጥነት ጨምሮ በሰዓት 250 ኪሎሜትር እንደሚሸፍን ተገልጿል።
የማዳጋስካር ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ ቶአማሲና ከፍተኛ ጉዳት አስተናግዳለች ተብሏል።
ሁለት ሦስተኛው የከተማዋ ክፍል በአደጋው መሸፈኑ ተገልጿል።
አውሎንፋሱ ከባድ እና ለቁጥጥር አዳጋች በመሆኑ የተጎጂዎችን ቁጥር ለማወቅ አስቸጋሪ ሆኗል ተብሏል። #france24
@EyobTikuye @ThiqahEth
#AddisAbaba
የመንግስት የሥራ ኃላፊው በ300 ሺሕ ብር የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በፓሊስ ተያዙ።
- የተያዙት የ300 ሺሕ ብር ቼክ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ነው።
በ300,000.00 ብር የሙስና ወንጀል የተጠረጠረን የመንግስት የስራ ኃላፊና በንግድ ስራ ላይ የተሰማራን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳውቋል፡፡
ተጠርጣሪዎች አቶ ዓለም ተ/ኃማኖት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ የግዢ ቡድን መሪ እና አቶ ሳሙኤል መላኩ የተባሉ በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ግለሰብ ናቸው ብሏል።
አቶ ዓለም ተ/ኃይማኖት በቢሯቸው ለሚፈጸመው የችግኝ ጣቢያ ግብዓቶች ጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ/ም በወጣ ጨረታ አቶ ሳሙኤል መላኩ ጨረታውን አሸንፈዋል፡፡
ተከሳሽ አቶ ሳሙኤል መላኩም ከአቶ ዓለም ተ/ኃይማኖት ጋር በቀጣይ በቢሮው በሚቀርቡ የግዢ ሂደቶች እና ጨረታዎች ላይ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ያልተገባን ድርድር በማድረግ ለቢሮው ግዢ ቡድን መሪ የ300 ሺሕ ብር ቼክ ሲሰጡ የካቲት 4 ቀን 2018 ዓ/ም እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ፓሊስ፣ ህብረተሰቡ መሰል የግዢ ስርዓቶችን ሲያከናውን ህጋዊ መንገድን መጠቀም እንዳለበት አሳስቦ፣ ነጋዴው ማህበረሰብም መብቱን በገንዘብ ሊገዛ እንደማይገባ አስገንዝቧል፡፡
@EyobTikuye @ThiqahETH
#Albania
አልባንያ 21 ተቃዋሚዎችን ስታስር፣ 16 ፓሊሶቿ ደግሞ በተቃዋሚዎቹ ጉዳት ደረሰባቸው።
የአልባን ዜጎች በዋና ከተማዋ ቲራና የፀረ-መንግስት ተቃውሞ አሰምተዋል።
በዚሁ የመብታቸውን ማንባረቂያ የተቃውሞ ሰልፍም ቢያንስ 21 ሰዎች መታሰራቸው ታውቋል።
ተቃዋሚዎቹ "ቁሳቁሶችን በመወርወር እና በመበተን ከፖሊስ አካላት ጋር መጋጨታቸው" ተገልጿል።
ሰልፉን ለመግታት በሥራ ላይ የነበሩ 16 ፖሊሶች ከተቃዋሚዎች በደረሰባቸው ጥቃት ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የአልባንያ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ ድርጊቱን አውግዞ፣ ለተከሰተው አመፅ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን ተጠያቂ አድርጓል። #voxnews
@EyobTikuye @ThiqahEth
"የሚሳዔል አቅማችን ለድርድር አይቀርብም" - ኢራን
ኢራን በባለስቲክ ሚሳዔል ዙሪያ ድርድር እንደማታደርግ አስታወቀች።
የኢራን መሪ አያቶላህ ኮሚኒ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት አሊ ሻምካኒ፣ "የባለስቲክ ሚሳዔል የቀይ መስመራችን አይደለም፣ የድርድር አካልም አይሆንም" ብለዋል።
በ47ኛ የኢራን አብዮት ክብረ በዓል ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ሻምካኒ "የሚሳዔል አቅማችን ለድርድር አይቀርብም" ሲሉ ተናግረዋል።
ይህ አስተያየት መሰጠቱ የተሰማው ኢራን እና እስራኤል ሁለተኛውን ዙር ድርድር ለማድረግ በተዘጋጁበት ወቅት ነው።
በሌላ በኩል የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ የኢራን ሚሳዔል የድርድሩ አካል እንድሆን ለመጠየቅ ዋሽንግተን ማቅናታቸው ተገልጿል።
ዋሽንግተን እና ቴህራን በቀጣይ ባለፈው ሳምንት አርብ በኦማን ያደረጉት ውይይት ውጤታማ እንደነበር ከተገለጸ በኋላ ቀጣዩን ዙር ድርድር በመጪው አርብ ለማካሄድ ቀጠሮ ይዘው መላያየታቸው ይታወሳል። #reuters #thestraightstimes
@EyobTikuye @ThiqahEth
በካናዳ ትምህርት ቤት ላይ በተፈጸመ ጥቃት 10 ሰዎች ሲገደሉ፣ 25 ቆሰሉ።
ከሟቾቹ ውስጥ አንዱ ጥቃት አድራሹ ተጠርጣሪ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል።
በተምብለር ሪጅ ከተማ በሚገኘው ትምህርት ቤት ላይ በተከፈተው ተኩስ 25 ሰዎች ቆስለው፣ ሆስፒታል መግባታቸው ተገልጿል።
ፖሊስ የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ተጨማሪ ምርመራ ማድረጉን እንደሚቀጥል አስታውቋል። #cbc #aa
@EyobTikuye @ThiqahETH
የኮሎምቢያ ፕሬዝዳንት ከግድያ ሙከራ ተረፉ።
ፕሬዚዳንት ጉስታቮ ፔድሮ ከተቃጣባቸው ግድያ ማምለጥ መቻላቸውን ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንቱ ለወራት በእፅ አዘዋዋሪዎች ኢላማ ተደርገው መቆየታቸውን ተናግረዋል።
ሙከራው የተፈጸመው ፔትሮ ከልጃቸው ጋር በሄሊኮፕተር ሲበሩ በነበረበት ወቅት ነው ተብሏል። #aljazeera
@EyobTikuye @ThiqahETH
እስራኤል የኢራን ሚሳዔል ምርት በቀጠናው ሰላም ተፅዕኖ ማሳደሩን ገለጸች።
የእስራኤል ባለሥልጣናት በኢራን የባለስቲክ ሚሳዔል ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሊፈፅሙ ይችላሉ ተብሏል።
በዋሽንግተን ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር እየተወያዩ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ የአካባቢው ደህንነት ስጋት አሁንም አለመቀረፉን ገልጸዋል።
የኔታንያሁ ጉብኝት አሜሪካ ከኢራን ጋር የምታደርገው ውይይት ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ተጠቁሟል። #foxnews
@EyobTikuye @ThiqahEth
የአብን የፓርላማ አባሉ ዶ/ር አበባው ደሳለው በመጪው ምርጫ ኢሕአፓን ወክለው ሊወዳደሩ መሆኑ ተሰማ።
የአብን የአዲስ አበባ ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት ዶ/ር ይህዓለም ታምሩም በተመሳሳይ መልኩ የፓርቲ ለውጥ አድርገው በመጪው ምርጫ እንደሚቀርቡ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ዛሬ ማክሰኞ የካቲት 3፤ 2018 ማምሻውን በበይነ መረብ በሰጠው መግለጫ ሁለቱ ቀድሞ የአብን አባላት ፓርቲውን መቀላቀላቸውን ይፋ አድርጓል።
ሁለቱ የቀድሞ የአብን አባላት ለዘንድሮው ምርጫ በእጩነት የተመዘገቡት፤ ኢሕአፓ አባል በሆነበት "ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት” በተሰኘው የፓርቲዎች ቅንጅት በኩል መሆኑን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
ባለፈው መስከረም የተመሰረተው ይህ የፓርቲዎች ቅንጅት
-ከኢሕአፓ
-መኢአድ
-አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ እና አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ አባል የሆኑበት ነው። #EthiopianInsider
@EyobTikuye @ThiqahETH
ሩሲያ የቴሌግራም መልዕክት ልውውጥ ላይ ገደብ ጣለች።
የግል መረጃ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር አለመደረጉ እና ለምዝበራ መጋለጡ ለቁጥጥሩ ቀዳሚ ምክንያት መሆኑን የሩሲያ ኮሚኒኬሽን ተቆጣጣሪ ቢሮ አስታውቋል።
ካምፓኒው መተግበሪያውን አሸባሪዎች እና ወንጀለኞች እንዳይጠቀሙበት ማድረግ አለመቻሉን ተገልጿል።
ሩሲያ በቂ ቁጥጥር አላደረጉም ያለቻቸውን
-ዩቲዩብ፣
-ፌስቡክ እና
-ኢንስታግራም ከ2019 ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ ማገዷ ይታወቃል። #bloomberg
@EyobTikuye @ThiqahETH
በኢትዮጵያ ክልል "የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የስልጠና ካምፕ መገንባቱን" ከምንጮች እና ከሳተላይት ምሥሎች ማረገጋጡን ሮይተርስ ዘግቧል።
"የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ስልጠና ትሰጥበታለች" በተባለው በዚሁ ካምፕ ውስጥ የሚገኙት አብዛኞቹ ምልምሎች "ኢትዮጵያዊ" እንደሆኑ ምንጮች ገልጸዋል ብሏል።
በዘገባው መሰረት፣ ከ2015 ዓ/ም ጀምሮ ከሱዳን ጦር ጋር እየተዋጋ ያለው "አማጺ ኃይል ስልጠና ይሰጥበታል" የተባለው ካምኙ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል "መንጌ" በተሰኘ ቦታ ከድንበር 32 ኪሜ ርቀት ላይ ይገኛል።
በኅዳር የተነሱ የሳተላይት ምሥሎች ላይ "640 ድንኳኖች" መመልከቱን፤ ካምፑ በአጠቃላይ "10 ሺሕ" ተዋጊዎችን የመያዝ አቅም እንዳለው ከሚያሳይ የዲፕሎማቲክ መልዕክት ልውውጥ መረዳቱን ዘገባው አክሏል።
"ጥቅምት ላይ የኤምሬትሱ የሎጅስቲክስ ኩባንያ 'ጎሪካ ግሩፕ' አርማ ያለባቸው የጭነት መኪናዎች በአሶሳ ከተማ አድርገው ወደ ካምፑ ሲጓዙ መመልከታቸውን ሁለት ባለስልጣናት ገልጸዋል" ሲልም ገልጿል።
"አንድ ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣንን ጨምሮ ስምንት ምንጮች፤ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሰፈሩን ግንባታ በገንዘብ እንደደገፈች፣ እንዲሁም ለቦታው የወታደራዊ አሰልጣኞችን እና የሎጅስቲክስ ድጋፍ ማቅረቧን ገልጸዋል" ሲል የሮይተርስ ዘገባ ይጠቅሳል።
ከኢትዮጵያ የደኅንነት አገልግሎት" የውስጥ ማስታወሻ ተገኘ የተባለ መረጃ ደግሞ እስከ ጥር መጀመሪያ ድረስ 4,300 የፈጥኖ ደራሽ ተዋጊዎች በስፍራው ወታደራዊ ሥልጠና እየወሰዱ እንደነበር አሳይቷል። #Reuters #Bbc
@EyobTikuye @ThiqahETH
አፍጋኒስታን በፓኪስታን ላይ የአፀፋ እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል አስታወቀች።
የአፍጋኒስታን መንግስት ፓኪስታን በአፍጋኒስታን ናንግራር እና ፓክቲካ ክልሎች ላይ በፈፀመችው ጥቃት ዜጎች መገደላቸውን ገልጿል።
የአፍጋኒስታን የአየር ክልል መጣሱን የገለፀው የታሊባን አስተዳደር ጥቃቱ ከቀጠለ ተገቢ ምላሽ እንደሚሰጥ አስጠንቅቋል።
የአፍጋኒስታን ብሄራዊ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ሉዓላዊነት የሚጥሱ አካሄዶችን እንደማይታገስ ገልጿል።
የፓኪስታን ጦር ተቀማጭነታቸውን በአፍጋኒስታን አድርገው የሽብር ድርጊት ይፈፅማሉ ባላቸው ሁለት አማፂ ሀይሎች ላይ ዘመቻ መጀመሩን አስታውቋል።
ጦሩ በሰባት ካምፖች ላይ በወሰደው እርምጃ ከ70 በላይ ተዋጊዎች መገደላቸውን ገልጿል።
ፓኪስታን እና አፍጋኒስታን ከወራት በፊት ለሳምንታት የዘለቀ ጦርነት ውስጥ ገብተው የነበረ ቢሆንም በቱርክ አማካኝነት ተኩስ ለማቆም ተስማምተዋል። #ariananews
@EyobTikuye @ThiqahEth
"ዩክሬን ከአውሮፓ አጋሮቿ ጋር በመሆን በአህጉሩ የነዳጅ እጥረት እንዲከሰት አድርጋለች" - ሀንጋሪ
ሀንጋሪ የሩሲያ ነዳጅ እገዳ ካልተነሳ የአውሮፓ ህብረት ለዩክሬን ብድር እንዳይሰጥ በሚል ተቃወመች።
የአውሮፓ ህብረት 90 ቢሊዮን ዩሮ ብድር ቢያቀርብም የህብረቱ አባል ከሆነችው ሀንጋሪ ተቃውሞ አስከትሏል።
የሀንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ፒተር ስጃርቶ በኤክስ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሑፍ፣ "ዩክሬን ከአውሮፓ አጋሮቿ ጋር በመሆን በአህጉሩ የነዳጅ እጥረት እንዲከሰት አድርጋለች" ሲሉ ወንጅለዋል።
ነዳጅ ከሩር ወደ አውሮፓ የሚገባበት "ዱርዝባ የነዳጅ ማስተላለፊያ መታገዱ የአውሮፓ እና ዩክሬንን ስምምነት ይጥሳል" በማለት ገልጸዋል። "የዱርዝባ ነዳጅ ማስተላለፊያ ሳይከፈት ለዩክሬን ብድር እንዲሰጥ አንፈቅድም" ብለዋል።
"ነዳጅ እንዳይገባ ያገደችው ዩክሬን ናት" ያሉት ስጃርቶ "ለአውሮፓ ህብረት ያላት አመለካከት የተዛባ መሆኑን ያሳያል" ብለዋል።
የአውሮፓ ኮሚሽን ለዩክሬን የመከላከያ ድጋፍ የሚያግዝ የ90 ቢሊዮን ዩሮ ብድር ያፀደቀው በጥር 2026 ነው። #foxnews
@EyobTikuye @ThiqahEth
በፈረንሳይ የአክቲቪስት ቀንቲን ዳራንቄ ግድያ ከፍተኛ ተቃውሞ አስከተለ።
ከ3,000 በላይ ተቃዋሚዎች አደባባይ የወጡ ሲሆን 11 ተቃዋሚዎች በፖሊስ ተይዘው ተወስደዋል።,ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ሰልፈኞች ከተቃውሞ እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።
የ23 አመቷ ደራንቄ በሊዮን ከተማ ተገድላ ስትገኝ ሰውነቷ ብዙ ቦታ መደብደቧን ፖሊስ ገልጿል።
ተቃዋሚዎች በበኩላቸው በመላ ሀገሪቱ ግድያውን የሚያወግዝ ሰልፍ መጥራታቸው ተገልጿል።
የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የደረንቄን ግድያ ማውገዛቸውን ተከትሎ ፕሬዚዳንት ማክሮን በፈረንሳይ የውስጥ ጉዳይ ከመግባት እንዲቆጠቡ አሳስበዋል። #upi
@EyobTikuye @ThiqahEth
"ቻይና በናይጄሪያ አሸባሪዎችን እየደገፈች ነው" - አሜሪካ
የአሜሪካ ኮንግረስ ቻይና በናይጄሪያ ቦኮሃራምን እየደገፈች ነው ሲሉ ወነጀሉ።
ሬሊ ሞሬ እና ክሪስ ስሚዝ የተባሉት የአሜሪካ ኮንግረስ አበባላት ቻይና ለህገወጥ የማዕድን ማውጣት ስራ "የጥበቃ ገንዘብ" የሚል በጀት ትመድባለች ብለዋል።
ሁለቱ አባላት "የናይጀሪያ የሃይማኖት ነፃነትና ተጠያቂነት ህግ 2026" የሚል ረቂቅ ባቀረቡበት ወቅት "ቻይና በናይጄሪያ አሸባሪዎችን እየደገፈች ነው" ሲሉ ወንጅለዋል።
"የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ህገወጥ የማዕድን ምዝበራውን ለማቆም ከናይጄሪያ መንግስት ጋር መስራት አለበት" በማለት አሳስበዋል።
የቻይና ማዕድን ፌደሬሽን ባለፈው ወር ባወጣው መግለጫ ሽብረተኝነትን ይደግፋል በሚል የሚቀርብበትን ወቀሳ ውድቅ አድርጓል። #peoplesgazette
@EyobTikuye @ThiqahETH
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በኢራን ጉዳይ ዲፕሎማሲን እንደሚመርጡ ተናገሩ።
ትራምፕ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያም ኔታንያሁ ጋር ባደረጉት ውይይት የሀይል አማራጭን እንደ ዛቻ ብቻ እንደሚጠቀሙበት ገልጸዋል።
መሪዎቹ በዋይትሃውስ በነበራቸው ውይይት ነው ድርድር መቀጠል እንዳለበት የተናገሩት ተብሏል።
ትራምፕ ኢራን ከስምምነት ላይ ካልደረሰች የኃይል አማራጭ ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል።
ሁለቱ መሪዎች በነጩ ቤተ መንግሥት ለሁለት ሰዓት ተኩል ሰፊ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል። #yenisafaq
@EyobTikuye @ThiqahETH
ግሪንላንድ "ለትራምፕ እጅ መንሻነት" ተሰጥታለች?
ኔቶ "ግሪንላንድ ለትራምፕ የእጅ መንሻ ተሰጥታለች" ከእውነት የራቀ መሆኑን ገልጿል።
በአንፃሩ በግሪንላንድ ዙሪያ የተጀመረው ውዝግብ በአሜሪካና አውሮፓ መካከል የቀጠናው ስጋት መሆኑን ገልጿል።
የኔቶ ዋና ፀሐፊ ማርክ ሩቴ ከፕ ሬዝዳንት ትራምፕ ጋር መወያየታቸው አባል ሀገራቱ ተቋሙን የበለጠ እንዲያጠናክሩ ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል።
ምንም እንኳን ኔቶ ጉዳዩን ቢያስተባብልም ትራምፕ ከሩቴ ጋር ስምምነት ካደረጉ በኋላ በያዝነው ወር መግቢያ ሊጥሉት የነበረውን ታሪፍ ማስቀረታቸው ጥርጣሬን አስከትሏል።
ዴንማርክ እና ፈረንሳይን ጨምሮ የኔቶ አባል ሀገራት በወቅቱ ስምምነቱን ተቃውመዋል።
የዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜቴ ፍሬድሪክሰን በበኩላቸው ትራምፕ እና ሩቴ በስዊዘርላንድ ዳቮስ ለፈፀሙት ስምምነት እውቅና እንደሌላቸው ገልጸው በወቅቱ "ስምምነቱ እኛን አይመለከትም" ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሯ ኔቶ ዴንማርክን ወክሎ በግዛቷ ዙሪያ ከአሜሪካ ጋር ስምምነት ላይ የመድረስ ስልጣን እንደሌለው ተናግረዋል። #euronews
@EyobTikuye @ThiqahETH
ቤርባዶስ ሀገራዊ ምርጫ እያካሄደች ትገኛለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ ባሳለፍነው ጥር ወር ላይ ፓርላማውን በመበተን ምርጫው በአስቸኳይ እንዲካሄድ አድርገዋል ተብሏል።
ሞተሊ የሚመሩት የቤርባዶስ ሰራተኛ ፓርቲ (BLP) የማሸነፍ ቅድመ ግምት ተሰጥቶታል።
የተፎካካሪ ፓርቲዎች መዋቅር ደካማ መሆን የጠቅላይ ሚኒስትሯ ፖርቲ ከፈረንጆቹ 2018 ጀምሮ የሀገሪቱን ፖለቲካ እንዲቆጣጠር እድል ሰጥቶታል ነው የተባለው። #rli
@EyobTikuye @ThiqahETH
"ወይ ከስምምነት ላይ እንደርሳለን፤ ካልሆነ ግን የሆነ እጅግ ብርቱ ነገር ይኖረናል" - ትራምፕ
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፍላጎቶች ካልተሟሉ ኢራን የከፋ ነገር ይገጥማታል በማለት መዛታቸው ተዘግቧል።
“ወይ ከስምምነት ላይ እንደርሳለን፤ ካልሆነ ግን የሆነ እጅግ ብርቱ ነገር ይኖረናል" ብለዋል።
ይህን ማለታቸው የተሰማው የኢራን የደህንነት ኃላፊ አሊ ላሪጃኒ ከዖማኑ ሱክጣን ቢን ታሪቅ አል-ሰይድ ጋር በድርድሩ ውጤት ላይ እየተመካከሩ ባሉበት ሰዓት ነው።
ኢራን እና አሜሪካ ወደ ድርድር መድረክ ከ8 ወራት በኋላ ቢመለሱም ትራምፕ ወታደራዊ እርምጃን ግምት ውስጥ እያስገቡ መሆኑ እየተነገረ ነው።
ከኑክሌር ማብላላት እስከ ሚሳኤል መርሃ ግብር ድረስ ቴህራን የዋሽንግተንን ፍላጎት እንድታሟላ የሪፐብሊካኑ ፍላጎታቸው መሆኑ ተገልጿል።
አያቶላውያኑ ደግሞ ከብሄራዊ ጥቅማችን በተወሰነ መጠንም ቢሆን ዝንፍ አንልም በሚል እየሞገቱ ተስተውዋል።
ስምምነት ላይ ካልተደረሰ አደገኛ እርምጃ በኢራን ላይ እንደሚወሰድ ትራምፕ ይግለጹ እንጂ በኢራን በኩል ያለው ወታደራዊ ዝግጅትም ስጋት ሆኖባቸዋል።
#Nbc #Aljazeera #channal24
@EyobTikuye @ThiqahETH
"የአውሮፓ ህብረት ከአሜሪካ እና ከቻይና ጋር መፎካከር አለበት" - ቮንደርሊን
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽነር ኦርሱላ ቮንደርሊን የአውሮፓ ኢኮኖሚ ማደግ እንዳለበት አሳሰቡ።
ቮንደርሊን በአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ላይ ባደረጉት ንግግር እንዲጀመር የጠየቁት "የአውሮፓን ይግዙ" ንቅናቄ መጀመር ለአህጉሩ ምጣኔ ሀብት ለውጥ እንደሚያመጣ ገልጸዋል።
"የዓለም ኢኮኖሚ ማዕከል ከመሆን የሚያግደንን እንቅፋት እናስወግዳለን" ያሉት ኮሚሽነሯ፣ "የአውሮፓ ህብረት ከአሜሪካ እና ከቻይና ጋር መፎካከር አለበት" ሲሉም ተናግረዋል።
"ካምፓኒዎቻችን አሁን ላይ ካፒታል ያስፈልጋቸዋል" ያሉት ቮንደርሊን "ይህን በዚህ አመት ማሳካት ይገባል" ነው ያሉት።
የአውሮፓ ኢኮኖሚ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በተፈጠረው የጂዖ ፖለቲካ ውጥረት ጫና ውስጥ ገብቷል። #trtworld
@EyobTikuye @ThiqahETH
አሜሪካ 200 ወታደሮችን ወደ ናይጄሪያ ላከች።
ወታደሮቹ በናይጄሪያ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት እንደተላኩ ተገልጿል።
አሜሪካ በሶኮቶ ግዛት በሚገኘው የቦኮሃራም አሸባሪ ቡድን ላይ ጥቃት ከፈጸመች ከሳምንት በኋላ ነው 200 ወታደሮችን መላኳ የተሰማው።
አሜሪካ የናይጄሪያ ወታደሮችን እንድታሰለጥን ፕሬዚዳንት ቦላ ቲኒቡ ያቀረቡትን ጥያቄ ዶናልድ ትራምፕ ተቀብለው አጽድቀውታል። #peoplesgazette
@EyobTikuye @ThiqahEth
የኢቤኤስ ቴሌቭዥን ዋና ስራ አስፈጻሚ እና መስራች አቶ አማን ፍስሃጽዮን አረፉ።
አቶ አማን ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ የካቲት 4/2018 ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል ሲል ድርጅቱ አስታውቋል።
"ለኢትዮጵያ ሚዲያ ዕድገትና ለጣቢያችን ኢቢኤስ ስኬት የማይተካ ሚና የተጫወቱት፣ የታላቅ ራዕይ ባለቤት የሆኑት ብርቱ ሰው ዛሬ እንደ ቤተሰብም እንደ ጣቢያ ብናጣም የአቶ አማን ፍስሃጽዮን ራዕይ ይቀጥላል" ሲል ገልጿል። #EBS
@EyobTikuye @ThiqahETH
ደቡብ አፍሪካ የዩክሬንን ጦርነት ለማቆም ጥረት እንደምታደርግ አስታወቀች።
ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ ከሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ ተወያይተዋል።
ራማፎዛ ሀገራቸው የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እንዲቋጭ ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል።
መሪዎቹ በቡድን 20 እና ብሪክስ ጉዳይ መምከራቸውም ተገልጿል።
ፕሬዚዳንት ፑቲን በዩክሬን በኩል ከቅጥረኛ ተዋጊዎች ጋር የተሰለፉ 17 የደቡብ አፍሪካ ዜጎች ወደሀገራቸው እንዲመለሱ ራማፎዛን ጠይቀዋል።#thestraightstimes
@EyobTikuye @ThiqahETH
ኢንዶኔዥያ 8000 ወታደሮችን ለጋዛ ዘመቻ አዘጋጀች።
ፕሬዚዳንት ፕራቦዎ ሱቢያንቶ የዶናልድ ትራምፕን የሰላም እቅድ በመቀበል ሰላም አስከባሪ ሀይል ለመላክ መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።
በዚህም 800ዐ ወታደሮች ለጋዛ ዘመቻ መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።
ሱቢያኔቶ ስለ ሰላም ቦርድ ለመወያየት እና ከአሜሪካ ጋር የንግድ ስምምነት ለመፈጸም ፌብርዋሪ 19/2026 ወደ ዋሽንግተን ያቀናሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የኢንዶኔዥያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ያቋቋሙት የሰላም ቦርድ (Board of peace) ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና ካልሰጠ ሀገሪቱ ከስብስቡ ራሷን ልታገል እንደምትችል ከሳምንት በፊት አሳውቆ ነበር። #cna
@EyobTikuye @ThiqahETH
የእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛግ ሄርዞግ በአውስትራሊያ ተቃውሞ ገጠማቸው።
በአውስትራሊያ የአራት ቀናት የስራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ሄርዞግ ከፍልስጤም ደጋፊዎች ብርቱ ትችት ገጥሟቸዋል።
በብዙ የአውስትራሊያ ከተሞች ለተቃውሞ የወጡት ዜጎች ሀገራቸው አውስትራሊያ "ወንጀለኛ" ያሏቸውን የእስራኤል ባለስልጣናት መቀበላቸውን አውግዘዋል።
ተቃዋሚዎቹ "ሄርዞግ የጦር ወንጀለኛ፣ ፍልስጤማውያን በየቀኑ እየተቀበሩ ነው" የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።
በተጨማሪም "ውሃ ወደ ወንዝ፣ ሄርዞግ ወደ አለማቀፍ ፍርድቤት" በማለት ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።
በዚህ ተቃዋሞ ከ3000 በላይ ዜጎች አደባባይ የወጡ ሲሆን፣ ፖሊስ ሰልፉን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ ተጠቅሟል ተብሏል። #middleeastmonitor
@EyobTikuye @ThiqahETH
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 4.4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አገኘሁ አለ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህን ገቢ ያገኘው በ2018 ዓ/ም በ6 ወራት ብቻ መሆኑን የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።
ይህን ያሉት ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል በሰጡት መግለጫ ሲሆን፣ አየር መንገዱ በተጠቀሱት ወራት ከ10 ሚሊዮን በላይ መንገደኞችንና 451 ሺሕ ቶን ጭነት ማጓጓዙን ገልጸዋል።
አየር መንገዱ በግማሽ አመቱ 7 አውሮፕላኖችን መረከቡን፣ ይህም የዘንደሮውን ገቢ ከአምናው የ14 በመቶ ብልጫ እንዲኖረው አስተዋጽዕ ማድረጉን አስረድተዋል።
አየር መንገዱ አሁንም የአውሮፕላን እጥረት እንዳለበት አቶ መስፍን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የአውሮፕላኖቿ ብዛት 147 ደርሷል።
@EyobTikuye @ThiqahETH