tikvahethiopia | Unsorted

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1532594

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Subscribe to a channel

TIKVAH-ETHIOPIA

#ሂጅራባንክ

ሂጅራ ባንክ በ2024/25 የበጀት አመት ከ1.8 ቢሊዮን ብር በላይ ጠቅላላ ገቢ አስመዘገበ።

ሂጅራ ባንክ ሦስተኛ ዓመት የእድገት ስትራቴጂ (Growth Strategy) በመተግበር ላይ የሚገኝ ሲሆን 2024/25 በጀት ዓመት "ስኬታማ ውጤት በማግኘት አዲስ ምዕራፍ የከፈተበት" ነው ሲል ገልጿል።

ባንኩ በበጀት ዓመቱ ከ1.8 ቢሊዮን ብር በላይ ጠቅላላ ገቢ (Total Income) ማስመዝገቡን ሲገልጽ፥ ከባለፈው ዓመት ጠቅላላ ገቢ ጋር ሲነጻጸር የ 148.85% በመቶ እድገት አሳይቷል።

ከ840 ሚሊየን ብር በላይ ትርፍ ማግኘቱን የገለጸው ሂጅራ ባንክ ይህም ውጤት ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር 740% ጭማሪ ማስመዝገቡንና በዚሁ መሰረትም የባንኩ ጠቅላላ ROE 40% መድረስ መቻሉን ገልጿል።

የባንኩ ጠቅላላ ሀብትም በከፍተኛ ደረጃ በማደግ በ2024/25 የበጀት አመት ከ15 ቢሊዮን ብር አልፏል፤ ይህም ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር 95.37% ጭማሪ አሳይቷል።

እንዲሁም የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ወደ 12 ቢሊዮን ብር በማሳደግ 91.4%በመቶ ስኬታማ የእድገት ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልጿል።

ሂጅራ ባንክ በበጀት ዓመቱ 40 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቱን ሲገልጽ፥ ይህም ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር 304.5% በመቶ ጭማሪ ማስመዝገብ ችሏል።

ባንኩ የማክሮ ኢኮኖሚ ነባራዊ ሁኔታዎችን ተቋቁሞ ተደራሽነቱን በማስፋት 135 ቅርንጫፎችን መክፈቱን የገለጸ ሲሆን በ2024/25 የበጀት አመት 35 አዳዲስ ቅርንጫፎችን ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉን አስታውቋል።

የደንበኞችን ብዛት በተመለከተ አዳዲስ ደንበኞችን በማፍራት ጠቅላላ የደንበኞቹን ቁጥር ወደ 931,148 ሲያሳድግ፥ ይህም ካለፈው ዓመት የደንበኞች ብዛት አንጻር 69.4%በመቶ የደንበኞች ጭማሪን ማሳየት ችሏል ብሏል።

ከዲጂታል አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ የኦምኒ ፕላስ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ተጠቃሚዎች ከ350 ሺህ በላይ መሆናቸውንና ይህም ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር 141.86% እድገት ማሳየቱን ነው የገለጸው።

ባለፉት 6 ወራት ብቻ የሀላል ፔይ ዋሌት ተጠቃሚዎች ከ811 ሺህ በላይ የደረሱ ሲሆን ባንኩ ከመሰረታዊ የባንክ አገልግሎቶች በተጨማሪ ያለ ማስያዣ የፋይናንስ አገልግሎት መጠቀም የሚያስችል ኢ-ሙራበሃ የፋይናንስ አገልግሎትን በዋሌት በማስጀመር ስኬታማ ዓመት ማሳለፉን አስታውቋል።

ከ20.9 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ በዲጂታል በኩል ተንቀሳቅሷል ያለው ባንኩ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር 198.60% ዕድገት ማስመዝገቡን አስታውቋል።

አጠቃላይ ከተደረገው የገንዘብ ዝውውር 34.52% በዲጂታል መንገድ ሲሆን ይህም ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር 10.68% እድገት አሳይቷል።

ሂጅራ ባንክ በ2024/25 የበጀት ዓመት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማስቀደም በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል፤ ከእነዚህም ውስጥ ማህበረሰቡን ከባንክ ተጠቃሚነት ወደ ባንክ ባለቤትነት ለማሸጋገር ሰፊ የአክሲዮን ሽያጭ ማከናወኑ ተጠቅሷል።

እንዲሁም "ሀላል ፋይናንሺያል ሊትረሲ ፕሮግራም" በሚል ስያሜ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ስለ ሀላል ፋይናንስ በማስተማርና ግንዛቤ በማስጨበጥ ላይ ሰፊ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል።

ባንኩ ስራ ፈጣሪዎችን እና ታታሪ ወጣቶችን ለማበረታታት በማሰብ "ሲራራ አዋርድ" የተሰኘ የውድድር መድረክ በማዘጋጀት እና ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት አኳያ፣ ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ተቋማት እና ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ ሲያደርግም ቆይቷል።

ባንኩ፥ "ይህ ስኬታማ ውጤት የሂጅራ ባንክን ስትራቴጂክ አቅጣጫ፣ የደንበኞቻችን፣ የባለአክሲዮኖቻችን፣ የቦርድ ዳይሬክተሮቻችን፣ የሸሪዓ አማካሪዎቻችን፣ የማኔጅመንት አባላት እና የሰራተኞቻችን ዉጤት ነው።" ሲል ነው የገለጸው።

ካለፉት አመታት ካስመዘገበው ውጤት እጅጉን የጎላ ነው ሲል በገለጸው በዚህ ስኬት "በሀገሪቱ ከወለድ ነጻ ባንኪንግ ዘርፍ ያለውን ሰፊ ​​እምቅ አቅም እና ዘላቂነት ዳግም ያረጋገጥንበት ዓመት ነው" ሲል አስታውቋል።

#HijraBank

/channel/HijraBank

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Ethiopia🇪🇹

የ1 ቢሊየን ዶላር የፋይናንስ ስምምነት በኢትዮጵያ እና ዓለም ባንክ መካከል ተፈርሟል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ይህ የድጋፍ ስምምነት የኢትዮጵያን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና አካታች የኢኮኖሚ እድገትን ለማገዝ ይውላል ብሏል።

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ እና የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ማሪያም ሳሊም ነው የተፈራረሙት።

Via Ministry of Finance

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Ethiopia🇪🇹

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ እንደሚሻሻል ተገልጿል።

ዛሬ 48ኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ተካሂዶ የአዋጁ መሻሻል ላይ ውሳኔ አሳልፏል።

ምክር ቤቱ " ቀደም ሲል ሲሰራበት የነበረው የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ አሁን ከምንገኝበት ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ አንጻር ሲታይ በርካታ ክፍተቶች ያሉበት ነው " ብሏል።

" የአዋጁን ድንጋጌዎች በማሻሻል የታክስ ስርአቱ መሠረታዊ የታክስ መርሆዎችን ለማሳካት በሚያስችል መልኩ እንዲቀረጽ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የማሻሻያ አዋጁ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል " ሲል ገልጿል።

ምክር ቤቱ በማሻሻያ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ በሙሉ ድምጽ አጽድቆ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ መወሰኑን አሳውቋል።

ከሳምንታት በፊት የገንዘብ ሚኒስቴር ከሠራተኛ የሚቀነስ ግብርን ጨምሮ ሌሎች የገቢ ጉዳዮችን የሚመለከተውን የገቢ ግብር አዋጅ ለማሻሻል ባስደረገው ጥናት በየወሩ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ከግብር ነፃ የሚሆነው የትኛው የደሞዝ መጠን ላይ ነው ለሚለው ሦስት አማራጮችን አቅርቦ እንደነበር ፤ እነዚህም 1,200፣ 1,600፣ ወይስ 2,000 ብር ከሚከፈላቸው ላይ ይሁን የሚል እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማሕበራት ኮንፌደሬሽን በበኩሉ ዝቅተኛው ከግብር ነፃ መሆን ያለበት የደሞዝ መጠን 8,300 ብር ነው መሆን ያለበት በሚል ሲከራከር እንደነበር አይዘነጋም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የትምህርት ቤት ክፍያዎን በቀላሉ በፀሐይ ባንክ በኩል ይክፈሉ!

እጅግ ዘመናዊ የሆነው የፀሐይ ኢ-ስኩል ሲስተም የሚሰጣቸው ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ተጠቃሚ ይሁኑ!

ወቅቱ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ምዝገባ የሚያደርጉበት ነው፡፡ ፀሐይ ባንክ የትምህርት ቤቶችን ምዝገባ እና ሌሎች ሥራዎችን የሚያቀላጥፍ ምርጥ መላ ይዞ መጥቷል፡፡

አሁኑኑ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ የፀሐይ ባንክ ቅርንጫፍ በመሔድ የፀሐይ ኢ-ስኩል ሲስተም ተጠቃሚ ይሁኑ!

ሥራዎትን ያቀላጥፉ! ከባንካችን ጋር በመስራት የሚያገኙትን ጥቅም ያሳድጉ!

ፀሐይ ባንክ
ለሁሉ!


Telegram: /channel/tsehaybanksc

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#NationalExam🇪🇹

ፆታዊ ትንኮሳ የፈፀሙ ሦስት ተማሪዎች ከሀገር አቀፍ ፈተና ታገዱ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ ባለው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመፈተን ወደ መቱ ዩንቨርስቲ ከገቡት ተማሪዎች ውስጥ ሦስት ተማሪዎች በሴት ተማሪዎች ላይ ዕፆታዊ ትንኮሳ በመፈፀማቸው ከፈተናው መታገዳቸውን የመቱ ዩንቨርስቲ አስታወቀ።

ዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት አለሙ ድሳሳ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ " በርካታ ተማሪዎች ወደ ግቢ ከገቡ በኃላ ወጣ ያለ ፀባይ እያሳዩ ነበር " ብለዋል።

ዩኒቨርስቲውም ለፈተናው ከተቋቋመ ኮማንድፖስት ጋር በመሆን የመቆጣጠር ሥራ ሲሰራ እንደነበር በማንሳት፤ ሦስቱ ተማሪዎች በሴት ተማሪዎች ላይ ሰኔ 22 ቀን 2017 ዓ.ም አደባባይ ላይ ትንኮሳ መፈፀማቸውን ተበድለናል ብለው በመጡ ሴቶች ቅሬታ እና ዩንቨርስቲውም ባደረገው ማጣራትብ ድርጊቱን መፈፀማቸውን አረጋግጧል።

" ትንኮሳ አድራጊዎቹ በአደባባይ ሴቶችን በግድ መሳም፤ ልብሳቸውን መገለብ እና መንካት የማይፈቀድ የአካላቸውን ክፍል በመንካታቸው ሴቶቹ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል " ብለዋል።

በዚህ የተነሳ የትንኮሳ ወንጀል በፈፀሙ ወንዶች ላይ ከዘንድሮው አመት ፈተና እንዲታገዱ መደረጉን ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ አንዱ ከኢሉ አባቦር ዞን በቾ ወረዳ ሁለቱ ደግሞ ከምስራቅ ወለጋ የመጡ መሆናቸውን ፕረዝዳንቱ አክለዋል።

እርምጃ ከተወሰደ በኃላ በግቢው ሲስተዋል የነበረው የተማሪዎች ሥነ ምግባር መሻሻሉንም ተናግረዋል።

ወደፊትን ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይፈጠር ትምህርት ቤቶች የፈተና ሥነ ምግባር ላይ ለተማሪዎች ግንዛቤ መስጠት እንዳለባቸው የገለፁት አለሙ ድሳሳ (ዶ/ር) ሴት ተማሪዎችም ራሳቸውን እንዲጠብቁና ለትንኮሳ ራሳቸውን እንዳይጋብዙም ጠይቀዋል።

የመቱ ዩንቨርስቲ በዘንድሮው ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከ14,000 በላይ ተማሪዎችን ለመፈተን መቀበሉንም ዩንቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር አለሙ ድሳሳ አክለው ገልፀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነቀምቴ
#TikvahEthiopiaFamliyNekemte

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ጦርነት ከተጀመረ ከዚህ በፊት እንደምናቀው አይደለም ነገር ይበላሻል !! " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ዛሬ በነበረው የህ/ተ/ም/ቤት ጉባኤን አንድ አባል " በትግራይ ክልል ዳግም ጦርንት እንዳይነሳ ስጋት አለ " በማለት በክልሉ ስላለው አሁናዊ የፖለቲካ እና የጸጥታ ሁኔታ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማብራርያ እና ምላሽ ጠይቀዋል።

" ህወሓት ለዳግም ግጭት ቅስቀሳ እያደረገ ነው "  በማለት " ከሰላም ወዳዱ የትግራይ ህዝብ፤ ምሁራን እና ወጣቶች ምን ይጠበቃል ? " ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምን መለሱ ?

" የሁሉም እምነት አባቶች እዚህ ተወካይዎች አላችሁ፣ ሌላ ምንም ስራ የላችሁም በፍጥነት ትግራይ ወደ ግጭት፣ ወደ ጦርነት እንዳይገባ ስራችሁን አሁን ጀምሩ፣ ከተጀመረ ወዲያ ብትናገሩ ዋጋ የለውም።

ባለሃብቶች፣ ምሁራን፣ ኤምባሲዎች ውጊያ እንዳይጀመር አሁን ሚናችሁን ተወጡ ምክንያቱም ከተጀመረ ከዚህ በፊት እንደምናቀው አይደለም ይበላሻል ነገር።

በእኛ በኩል በትግራይ ምድር እንድ ጥይት የመተኮስ ፍላጎት የለንም፣ ከቻልን ማልማት ነው የምንፈልገው።

ትግራይ ላሉ ሃይሎች ለትግራይ ህዝብም፣ ለኢትዮጵያ ህዝብም መታወቅ ያለበት ጦርነት አያስፈልገንም በሰላም እና በውይይት ጉዳያችንን መፍታት ይቻላል " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የፌዴራል መንግሥት በጀት 1.93 ትሪሊዮን ብር ሆኖ ፀደቀ።

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛው ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 42ኛ መደበኛ ጉባኤ የ2018 ዓ/ም የፌዴራል መንግስት በጀት 1.93 ትሪሊዮን ብር አድርጎ አፅድቋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#HoPR🇪🇹

" 3.5 ቢሊየን ዶላር ከዚህ ቀደም የነበሩ መንግስታት የተበደሩትን ገንዘብ ያለፉትን ሶስት እና አራት አመታት ተደራድረን የእዳ ሽግሽግ እንዲኖር አድርገናል የገንዘብ ሚንስቴር በትላንትናው እለት በፈረንሳይ ተፈራርሟል" - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።

የበጀት አመቱን አፈጻጸም በየዘርፉ አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግብርና ፣ በኢንዱስትሪ ፣በፋይናንስ እና በቱሪዝም ዘርፍ ተመዘገቡ ያሏቸውን ለውጦች ተናግረዋል።

በዚህም መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባነፈው አመት የ8.1 በመቶ እድገት ኢትዮጵያ ማስመዝገቧን በመግለጽ ዘንድሮ 8.4 በመቶ እድገት ለማስመዝገብ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ በየዘርፉ አስመዘገብናቸው ስሏሏቸው ለውጦች ምን አሉ ?

ግብርና

- በግብርና ዘርፍ 6.1 በመቶ እድገት እንዲያመጣ ታቅዶ ነው እየተሰራ ያለው።

- ባለፈው አመት 26 ሚሊየን ሄክታር መሬት ማረስ ችለን ነበር ዘንድሮ 31.8 ሚሊየን ሄክታር መሬት ማረስ ተችሏል።

- ባለፈው አመት በሁሉም አይነት የእርሻ ምርቶች 1.2 ቢሊየን ኩንታል ምርት ነበር የሰበሰብነው ዘንድሮ 1.5 ቢሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰብ ችለናል ይህም 24.7 በመቶ ጭማሪ አለው።

- ከ100 በላይ አነሰተኛ እና መካከለኛ ግድቦች ይሰራሉ።

- 50 ሺ ሄክታር አሲዳማ መሬት ታክሞ ወደ እርሻ ገብቷል።

ኢንዱስትሪ

° 12.8 በመቶ እድገት እንደሚያመጣ ታስቦ እየተሰራ ነው።

° የኢንዱስትሪው ሴክተር የኢነርጂ ፍላጎት 40 በመቶ ጨምሯል።

° የሲሚንቶ ምርት 6 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

° የብረት ውጤቶች 18 በመቶ አድጓል።

° የመስታወት ፋብሪካ በቂ አልነበረም በአመት 600 ሺ ቶን የሚያመርት የመስታወት ፋብሪካ እየተሰራ ይገኛል ጥሬ እቃውንም ከሃገር ውስጥ ይጠቀማል ታህሳስ ወይም ጥር ላይ ያልቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ማእድን

- ባለፈው አመት 4 ቶን ወርቅ ኤክስፖርት አድርገናል ዘንድሮ 37 ቶን ወርቅ ኤክስፖርት አድርገናል።

- አምና በወርቅ ኤክስፖርት 300 ሚሊየን ዶላር ዘንድሮ 3.5 ቢሊየን ዶላር አግኝተናል።

- ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚቀጥለው አመት የመጀመሪያውን የጋዝ ምርት ለገበያ ታቀርባለች።

- ምክር ቤቱ ከእረፍት ሳይመለስ ኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ መስራት ትጀምራለች ከ 40 ወራት በኋላም ግንባታው ይጠናቀቃል።

- የማዕድን ዘርፍ በጋዝ ፣በወርቅ እና በማዳበሪያ የተለያዩ እድገቶችን እያመጣ ነው።

ቱሪዝም

° 1.3 ሚሊየን የውጭ ቱሪስት ኢትዮጵያን ጎብኝቷል።

° ዩኒቲ ፣ፍሬንድ ሺፕ ፣ ፓላሱን እና ሳይንስ ሙዚየምን ብቻ ከ 1.5 ሚሊየን ህዝብ በላይ ጎብኝቶታል ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ገቢ አግኝተንበታል።

° አየር መንገድ በሃገር ውስጥ እና በውጭ 19 ሚሊየን ህዝብ አጓጉዟል።

ፋይናንስ

- ብድር ከአምና 75 በመቶ ጨምሯል የግሉ ሴክተር 80 በመቶ ድርሻ አላቸው።

- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 900 ቢሊየን ብር እዳ የነበረበት ተቋም ነበር እዳው ከባንኩ ወደ መንግሥት በመዘዋወሩ እና ለባንኩም 700 ሚሊየን ዶላር ድጎማ በመሰጠቱ ተቋሙንም ሆነ ሴክተሩም ማዳን ተችሏል።

- የሞባይል መኒ ተጠቃሚ 55 ሚሊየን ደንበኛ ደርሷል።

- ወደ 11 ሚሊየን ደንበኞች 24.5 ሚሊየን ብር ብድር በሞባይል መኒ አግኝተዋል።

ኤክስፖርት

° 5.1 ቢሊየን ዶላር ከኤክስፖርት ገቢ እናገኛለን ብለን አቅደን 8.2 ቢሊየን ዶላር አግኝተናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በዚህ ዓመት ብቻ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ አግኝተናል !! "

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፦

" ዩኒቲ ፓርክ ፣ ፍሬንድሺፕ ፣ ሳይንስ ሙዝየም ፣ ናሽናል ፓላስ ብቻ በዚህ ዓመት 1.5 ሚሊዮን ሰው ጎብኝቷል። ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አግኝተንበታል።

አስቡት ' ዩኒቲ ፣ ፍሬንድሺፕ ለምን ይሰራል ? ' ሲባል የነበረበትን ዘመን። በአንድ አመት 1.5 ሚሊዮን ሰው መሄጃ አዘጋጀንለት ማለት ነው። ያ አንድ ሚሊዮን ሰው ዩኒቲ ባይኖር ፣ ፍሬንድሺፕ ባይኖር ወይ ጫት ላይ ነው ወይ ድራፍት ላይ ነው።

ባለፉት ጥቂት አመታት በነዚህ ቦታዎች 13. 5 ሚሊዮን ሰው ጎብኝቷል። ሳይንስ ሙዝየም፣ ፍሬድሺፕ እና ዩኒቲ። ይሄ የተመዘገበና ብር የሚከፍል ነው። የሚታወቅ ቁጥር ነው።

አዲስ አበባ ላይ ባለው ዳታ በዚህ ዓመት ያለው የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቱሪስት እድገት በጣም ከፍተኛ ነው። "

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#HoPR🇪🇹

" በዝቋላ አቦና በተለያዩ ገዳማት ምንም መሳሪያ ያልታጠቁ መናኞች እና የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን ከሞት እና ከድብደባ ለመታደግ አግባብ ያለው የጸጥታ ሃይል የማይመድበው ለምንድነው ? " - የምክር ቤት አባሉ አበባው ደሳለው (ዶ/ር)

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉና አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባሉ አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ምን ጠየቁ ?

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ፦

" የመንግሥት ሰራተኞች እና ዝቅተኛው የማህበረሰብ ክፍል በተደጋጋሚ በአሁን ሰዓት ያለውን የኑሮ ውድነት መቋቋም እንዳቃታቸው ይገልጻሉ።

እንደመገለጫም ፦
- እራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን አብልቶ ማሳደር
- የቤት ኪራይ መክፈል
- የልብስ እና የትምህርት ወጪዎችን መሸፈን ዳገት እንደሆነባቸው ይዘረዝራሉ።

ከዚህ ጋር በተገናኘ የህክምና ባለሙያዎች የስራ ማቆም አድማ በማድረግ መሰረታዊ የዳቦ ጥያቄያቸው እንዲፈታ ጠይቀዋል። ሆኖም ግን መንግሥት ይህንን መሰረታዊ ጥያቄ የፖለቲካ ስም በመስጠት ጥያቄያቸው ሳይፈታ ተዳፍኖ ቀርቷል።

ለመሆኑ መንግሥት ' ድሃ ተኮር ኢኮኖሚ ሪፎርም አራማጅ ነኝ ' እያለ የመንግሥት ሰራተኛውን እና ዝቅተኛውን የማህበረሰብ ክፍሎችን ኑሮ ለማሻሻል ስራ የሚጀምረው መቼ ነው ?

ከዚህ ጋር በተገናኘ አጠቃላይ የኢኮኖሚው አካሄድ ላይ ጥያቄ ይነሳበታል። የኢኮኖሚክ ባላንሱ ችግር እንዳለበት ይነሳል። የተለያየ ጥረት እየተደረገ ነው inflation (የዋጋ ግሽበት) ለመቀነስ ግን IMF እኛን የሚደግፍ ኢኮኖሚክ ሪፎርሙን፣ ዓለም ባንክ ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን  ሳይቀር በጣም ፈተናዎች እንዳሉ ከኢኮኖሚክ ሪፎርሙ ጋር በተያያዘ ይገልጻሉ። ለምሳሌ ፦
° ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እንዳለ፣
° ገበያ ተኮር ምንዛሬ በመጠቀማችን ምክንያት የብር ዶላር ልዩነት ከፍተኛ መሆኑ፣
° በህዝብ ስም የተበደርነው ዕዳ እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ፣
° ከፍተኛ ስራ አጥነት እንዳለ በአሁን ሰዓት በየአመቱ 2 ሚሊዮን ስራ አጦች እንደሚቀላቀሉ ይገለጻልና ይሄንን ችግር እንዴት ነው የምንፈታው በተለመደው አዙሪት ውስጥ ነው ወይ የምንቀጥለው ? ከኢኮኖሚ ችግሩ ለመውጣት ምን የታሰበ ነገር አለ ?

ሁለተኛ በዝቋላ አቦና በተለያዩ ገዳማት ምንም ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ የሰማይ ቤትን ታሳቢ ያደረጉ መናኞች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት እየተፈጸመ ለሞት፣ ለድብደባ እና እንግልት ሲዳረጉ ይታያል። ለመሆኑ መንግሥት እንደዚህ ያለ ተደጋጋሚ የንጹሃን የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን ከሞት ፣ ከድብደባና እንግልት ለመታደግ አግባብ ያለው የጸጥታ ኃይል የማይመድበው ለምንድነው ?

ሶስተኛ መንግሥት ከፋኖ ፣ ከሸኔና ሌሎች የታጠቁ ኃይሎች ጋር ያለው የጸጥታ ችግር በድርድር እንዲፈታ ፣ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ (ከፖለቲካ እስረኞች ጋር ለተገናኘ በተደጋጋሚ ያቀረብነው ጥያቄ ነው) ጅምላ ጭፍጨፋ የመሩ የህወሓት ባለስልጣናት በቶሎ ነበር የተፈቱት ነገር ግን እንደዚህ አይነት ተሳትፎ (involvement) የሌላቸው የአማራ ፖለቲከኞች ፣ አንቂዎች፣ ጋዜጠኞች ከታሰሩ 2 ዓመት ሞልቷቸዋል።

የፍትህ ስርዓቱ በጣም ዘገምተኛ ነው፤ ቶሎ እየተፈታ አይደለም ፤ ምንም ምስክርም እየተሰማባቸው አይደለም በጄኖሳይድ ወይም በጦርነቱ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንደሆኑ የሚያመለክት ነገር የለም ግን በእስር ቤት እየተሰቃዩ ይገኛሉ። አማራ ክልል ብቻ አይደለም ኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከተለያዩ የምክር ቤት አባላት ጋር ባደረግነው ንግግር እንደዚህ አይነት ተመሳሳይ ችግር አለ። ቶሎ ፍትህ የማግኘት ችግርን በኢትዮጵያ መቼ ነው የምንቀርፈው ? የረፈደ ፍትህ እንደተነፈገ ይቆጠራልነውና።

ሌላው ድሮንን ጨምሮ በሌሎች ከባድ መሳሪያዎች ጭምር ንጹሃን እንዳይጠፉ የምክር ቤት አባላት፣ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ፣ኃያላን መንግሥታት አሜሪካን ጨምሮ ስንወተውት ቆይተናል። የተለያዩ መግለጫዎች ኃያላን መንግሥታት ጭምር ሲያወጡ ይታያል። ሆኖም ግን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ የመሳሰሉ ክልሎች ላይ የጸጥታ ችግሩ እስካሁን አልተቀረፈም።

ከዚህ ጋር በተገናኘ ' አግዙን ' ባሉን መሰረትም ሰላሙን ለማምጣት ወደ እርሶ ቢሮ መልዕክተኛ ብንልክም አልተሳካልንም። እንጂ እኛ ፖለቲከኞች፣ ተቃዋሚዎች ችግር መፍጠር ሳይሆን ችግሩ እንዲፈታ ቀረብ ብለን መነጋገር እንፈልጋለን ነገር ግን ያን መድረክ ልናገኝ አልቻልንም። ከዚህ ጋር በተገናኘ ምን የሚሉን ነገር አለ ሰላሙን ለማምጣት።

አራተኛ በተለያዩ አዲስ አበባ አካባቢዎች በሌሎች ትላልቅ የክልል ከተሞች ላይም ይሄ ችግር አለ ከ1998 ዓ/ም ጀምሮ መኖሪያ ቤት ሰርተው ፣ ውሃና መብራት አስገብተው፣ በርካታ የልማት ስራዎችን የሰሩ፣ መንግሥትዎን በድጋፍ ያገለገሉ ዜጎችን ያለምንም ምትክ ቤት ፣ መሬትና የገንዘብ ካሳ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው አቤቱታቸውን ይዘው የተለያዩ ቢሮዎች ቢሄዱም ጥያቄያቸው ውድቅ ሆኗል።

እነዚህ ሰዎች የሚያመለክተት ' ነገር ከ1998 ጀምሮ ነው ህገወጥ ከሆንን እናፍርስና በኮንዶሚኒየም እንደራጅ ' ስንል አይ ' እናተ ሰነድ አልባ ናችሁ እንጂ ህገወጥ አይደላችሁም በቅርቡ ህጋዊ እናደርጋችኃለን ' ተብለው እንደነበር ነው የሚያስታውሱት። በቅርቡ ያወጣነው አዋጅ አለ ከከተማ መሬት ጋር በተገናኘ ከ2004 ዓ/ም በፊት የተሰሩ ህገወጥ ቤቶች ህጋዊ እንደሚሆኑ የሚያመለክትና እነዚህን ሰዎች ለምድንነው በአግባቡ የማይስተናገዱት። የተለያዩ ቢሮዎች ሄደዋል አልተሳካላቸውም። በመጨረሻም እርሶን እንድጠይቅላቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ከሁለት ቀበሌ የተፈናቀሉ ከሰነድ ጋር ነው ያቀረቡልኝ። አመሰግናለሁ። "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በጸጥታ ምክንያት የባሕርና ትራንስፓርት ሎጂስቲክ ደረቅ ጭነት እንዳይጓጓዝ ያቋረጠባቸው ቦታዎች አሉ። ለምሳሌ ወረታ ደረቅ ወደብ " - ጠያቂዎች ስለባሕር ዳር ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

የባሕርና ትራንስፓርት ሎጂስቲክ አገልግሎት ድርጅት በጸጥታው ምክንያት ወደ ወረታ ወደብ ደረቅ ጭነት እንዳይጓጓዝ በማቋረጡ በባሕር ዳር ጉምሩክ ቅ/ጽሕፈት ቤት ቅሬታ መኖሩን የሚመለከት ጥያቄ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ቀረበበት።

ጥያቄው የቀረበው ከሰሞኑን ኮሚሽኑ፣ የ11 ወራት ሪፓርቱን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ነው።

በዚህም አንድ ጠያቂ፣ " በጸጥታ ምክንያት የባሕርና ትራንስፓርት ሎጂስቲክ ደረቅ ጭነት እንዳይጓጓዝ ያቋረጠባቸው ቦታዎች አሉ። ለምሳሌ 'በወረታ ደረቅ ወደብ አካባቢ እንዳይሄዱ በመደረጉ በገቢያችን ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አመጡብን' የሚል ቅሬታ አለ በቅ/ጽ/ቤቱ። ኮሚሽኑ በዚህ ዙሪያ ምን እየሰራ ነው ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

ሌላኛው ጠያቂም፣ ከወረታ ደረቅ ወደብ ጋር በተያያዘ የቅ/ጽሕፈት ቤቱ ቅሬታ ሲያስረዱ፣ "'ዩኒሞዳሉ (ግለሰቡ) ያስገባል፣ መልቲሞዳሉ (የመንግስቱ) ግን አቋርጧል። በተደጋጋሚ ብንጽፍም አድማጭ አልተገኘም። ይሄ በመሆኑ ገቢያችን ቀንሷል፤ አፈጻጻማችን ዝቅተኛ እንዲሆን አድርጎታል' የሚል ቅሬታ ስላለ የኮሚሽኑ ምላሽ ምንድን ነው?" ሲሉ ጠይቀዋል።

ጉምሩክ ኮሚሽን፣ "በመስክ ጉብኝታችሁ ካያችኋቸው መካከል ባሕር ዳር ጉምሩክ ቅ/ጽሕፈት ቤት በመልቲ ሞዳል የሚገቡ የእቃ ፍሰት መቀነስ ጋር የተነሳው እውነት ነው። የመልቲሞዳል ኦፕሬተሩ የመንግስት የባሕር የትራንስፓርትና ሎጂስቲክ አገልግሎት ድርጅት ነው" ሲል መልሷል።

"እቃ አገባብን በተመለከተ በክልሉ/በመስመሩ ያሉ የጸጥታ ችግሮች አልፎ፣ አልፎ የሚፈጸሙ ቢሆንም በሱ ስጋት መነሻ የመልቲሞዳል ሞደሉ እቃዎችን በፈለገው ደረጃ ቀደም ብሎ እንደነበረው ስሙዝሊ ለማማጓጓዝ ፍላጎት የለውም" ሲል አክሏል።

"በወደቡ የሚገባው የእቃ ፍሰት ከጸጥታ መነሻ በማድረግ የመልቲሞዳል ኦፕሬተሩ እቃ እያጓጓዘ አይደለም። ፍሰቱ የሚሻሻልበት ሁኔታ ይኖራል" ነው ያለው ኮሚሽኑ።

በሌላ በኩል ኮሚሽኑ፣ "የግብዓትና ሎጂስቱክስ ጉዳይ ቀለል ተደርጓል። ኤግሶስት አድርገናል ካገዛችሁን። 100 መኪና ይገዛልን ብለን ከጠየቅን ሁለት ዓመት አልፎታል። እስካሁን አልተገዛም። ዋጋ እየተከፈለ ሰው እየሞተ ነው፤ የጸጥታ ተቋማት ሰዎችም መዓት ነው የሚሞተው" ሲል ሪፓርት ባቀረበበት ወቅት ገልጿል።

ቋሚ ኮሚቴው በበኩሉ፣ ኮንትሮባንዲስቶችን ከመያዝ አኳያ በተደረገ ግምገማ፣ "መንግስት ያለው መኪና በጣም ደካማ፣ ችግር ያለበት፤ ኮንትሮባንዲስቶቹ የሚይዙት ደግሞ ዘመናዊ እንደሆነ በየጊዜው ሲነሳ ነበር" ብሎ፣ "ከመኪና ጋር ተያይዞ ሁልጊዜ አቅማችሁን እየተፈታተነ ያለ ነገር ስለሆነ ችግራችሁን በደንብ ብታስረዱን የኛ ቋሚ ኮሚቴም ለማገዝ ዝግጁ ነው" ብሏል።

"በዚህ ዘርፍ በሰው ሕይወት ጉዳት እየደረሰ እንዳለም እናውቃለን። እናንተም ራሳቸውን መስዋት ያደረጉ ሰዎችን ቤተሰቦች እየደገፋችሁ እንደሆነ ይታወቃል። ተቋሙ ስራውን እየሰራ ባለበት የጠየቀው የመኪና ግዥ ምላሽ የማይሰጥበት ችግሩ ምንድን ነው?" ሲልም ኮሚሽኑን ጠይቋል።

ኮሚሽኑም፣ "ግዢ ሂደት ላይም ደርሰው አሸናፊ ከተለየ በኋላ ክረምት ላይ በተደረገ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የውጪ ምንዛሬ ፍሎቴሽኑ ላይ ትልቅ ኢምፓክት ስለነበረው አቅራቢዎቹ የማቅረብ ፍላጎት አልነበራቸውም" የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት

የሁለት ወር የልጆች የክረምት ስልጠና ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።

👉ስልጠናው ዕድሜያቸው ከ 5-18  ዓመት ላሉ ልጆች የሚሰጥ ነው።
👉 ልጆች ፕሮጀክቶች እየሰሩ የሚሰለጥኑበት
የስልጠናዎቹ ዓይነት:
👉 Computer Programming and Website Development
👉 AI and Robotics
👉 Graphic Design, Video Editing and Animation
👉 Art (Film Acting, Writing and Modeling)
👉 Painting, Drawing and Sculpture
👉 Language and Basic Computer

☎️  0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram
sage_training_institute">Tiktok
Linkedin

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የውሃ ማሞቂያ ፈንድቶ ነው የሁለት ሰዎች ሕይወት ያልፈው " - የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ

➡️ " በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ከአደጋው ጋር ተያይዞ የሚዘዋወሩት መረጃዎች የተሳሳቱ ናቸው !! "


የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ስራ አስኪያጅ አቶ ማቴዎስ አሸናፊ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ትናንት ጠዋት በፓርኩ ሼድ 40 የውሃ ማሞቂያ (ቦይሌር) ባለሙያ ሰራተኞች መደበኛ ስራቸውን እያከናወኑ ባሉበት ፈንድቶ የ62 እና 45 ዕድሜ ውስጥ ያሉ ሁለት ባለሙያዎች ሕይወታቸዉ ማለፉንና በሁሉት ሰራተኞች ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።

ሕይወታቸዉ ያለፈዉ ሁለቱም ባለሙያዎች ወንዶች ሲሆኑ ለረጅም ዓመታት በዘርፉ የሰሩና ልምድ ያላቸዉ መሆናቸውን የገለፁት አቶ ማቴዎስ ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት ሰራተኞችም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቪ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሕክምና ላይ መሆናቸዉን ገልጸዋል።

የአደጋውን ትክክለኛ መንስኤ እንዲያጣራ መርማሪ ቡድን መዋቀሩን የገለፁት የፓርኩ ስራ አስኪያጅ ከአደጋው ጋር ተያይዞ በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች " ክስተቱ የእሳት አደጋ እንደሆነና መንስኤዉም ባለሙያዎች የልምድ ማነስ " ተደርጎ የሚሰራጩ መረጃዎች ፍፁም የተሳሳቱና ባለሙያዎችም የረጅም ዓመታት ማለትም ከ6 ዓመታት በላይ በዘርፉ ልምድ ያላቸው ስለመሆናቸው ተነግረዋል።

በዚህ ልክ በሰዉና በንብረት ላይ ጉዳት የሚያደርስ የእሳት አደጋ ከዚህ ቀደም በፓርኩ ዉስጥ ተከስቶ እንደማያዉቅም አቶ ማቴዎስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#HoPR🇪🇹

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነገ ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስታቸውን የ2017 የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡም ይጠበቃል።

በተጨማሪም የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፌዴራል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን እንደሚያፀድቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ጉባኤው ከጥዋት 2:30 ጀምሮ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን በቀጥታ ይሰራጫል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በተፈጠረው እሳት አደጋ ሁለት ሰዎች ሞተዋል፤ አንዱ ሆስፒታል ገብቷል " - የሲዳማ ክልል ጸጥታ ቢሮ

በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተፈጠረ በተባለ የፍንዳታ አደጋ በሰዎች ላይ ሞትና የአካል ጉዳት መድረሱን የሲዳማ ክልል ጸጥታ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የክልሉ ጸጥታ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ አህመድ በሰጡን ቃል፣ "ትላንት ሁለት ሰዓት አካባቢ በተፈጠረው እሳት አደጋ ሁለት ሰዎች ሞተዋል፤ አንዱ ሆስፒታል ገብቷል" ብለዋል።

የችግሩን መንስኤ ሲያስረዱም አቶ ሀሚድ፣ "የችግሩ መንስኤ ማሽኑ ላይ በተነሳው እሳት ምክንያት ነው፤ ማሽኑ ላይ እሳት/ ቃጠሎ ተነስቶ በዚያ የሚሰሩ ሰራተኞች ናቸው የተጎዱት" ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አደጋው መድረሱን ትላንት በሰሙበት ወቅት ሦስት ሰዎች ተጎድተው እንደነበር፣ አንዱ ሆስፒታል እንደገባ፣ ሁለቱ እንደሞቱ ነው የገለጹት።

የሀዋሳ ከተማ ጸጥታ መምሪያ በበኩሉ፣ ችግሩ ተፈጥሯል መባሉ ትክክል መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጾ፣ ተጨማሪ መረጃ ከፓሊስ እንዲጠየቅ ጠቁሟል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#GERD🇪🇹💪

የግብፅ ምሁራን፣ ባለስልጣናትና ሚዲያዎች የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ስራ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ስለ ግድቡ ተነግረው የማያልቁ እጅግ በርካታ መጥፎና አሉታዊ ነገሮችን ሲያስወሩ ቆይተዋል።

ይኸው አሁንም በዚሁ እኩይ በሆነው ድርጊታቸው ቀጥለዋል።

በየጊዜው አዳዲስ ሀሰተኛ ወሬዎችን እየፈበረኩ ያሰራጫሉ።

በቅርቡ ከግድቡ ብዙ ኪሎሜትር ርቀት ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እያለ የግብፅ ሰዎችና ሚዲያዎቻቸው " ግድቡ በመሬት መንቀጥቀጡ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ገብቷል ፤ የከፋ አደጋ ሊደርስበት ነው ፤ የመሬት መንቀጥቀጡ ግድቡን ያፈርሰው ነው ፤ ሊያወድመው ነው " የሚሉ ፍጹም የፈጠራ ወሬዎችን ለዓለም ህዝብ ሲያሰራጩ ከርመዋል።

ግን አንዳችም የተፈጠረ ነገር የለም ፤ በብዙ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥም ቆመ።

አሁን ደግሞ " የግድቡ ተርባይን ተበላሽቷል ፤ ሱዳን ካርቱም በግድቡ ምክንያት በጎርፍ ልትጥለቀለቅ ነው " የሚል የፈጠራ ወሬ ይዘው መጥተዋል።

ይህንን ወሬያቸውንም በሚዲያ እያሰራጩት ይገኛሉ።

ሀገሪቱ ግብፅ የግድቡ ስራ ገና ከመጀመሩ አንስቶ እንዲስተጓጎል ፣ እንዲደናቀፍ ያልፈነቀለችው ድንጋይ ፤ ያሞከረችው ሙከራ፣ ያልጠናችበት ደጅ አልነበረም። ያም ሆኖ ግን ምንም አልተሳካላትም።

የኢትዮጵያውያን የህይወት ፣ የደም እና የላብ ዋጋ የተከፈለበት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ወደ መጠናቀቁ ደርሶ በመጪው መስከረም ወር 2018 ይመረቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ሃይል እያቋረጥን ስራ ስንሰራ የነበረ በመሆኑ በምንፈልገው ደረጃ የሃይል መቆራረጡን እንዳንቀንስ የራሱን አስተዋጽኦ አድርጓል "- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

የኢትዮጵያ አሌክትሪክ አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ሦስት ወራት ለክረምት ዝግጅት ሲያከናውን የቆያቸውን ስራዎች በሚመለከት በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥቷል።

አገልግሎቱ በከተማዋ ለሚያጋጥም የሃይል መቆራረጥ ምክንያት ናቸው ብሎ የለያቸውን የመስመሮች ከዛፍ ጋር የሚፈጥሩት ንክኪ እና የረገቡ መስመሮች ላይ የተለያዩ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን አሳውቋል።

ተቋሙ ባለፉት ሦስት ወራት ብቻም ከ 25 ሺ በላይ ለሃይል መቆራረጥ ምክንያት የሆኑ አነስተኛ እና ከፍተኛ ግኝቶች አግኝተናል ነው ያለው።

ለሃይል መቆራረጥ ምክንያት ናቸው ካላቸው ግኝቶች ውስጥም ተቋሙ መፍታት የቻለው 56 በመቶዎቹን ብቻ ነው።

የአገልግሎቱ የኔትወርክ ኢንፍራስትራክቸር እና ኮርፖሬሽን ኤክሰለንስ ዳይሬክተር አቶ ፈሪድ አብዱሰላም ምን አሉ ?

" በስታንዳርዱ መሰረት ሽቦዎች እርስ በእርስ ሊኖራቸው የሚገባው ርቀት ከ 40-60 CM ፣ ከግራ እና ከቀኝ ካሉ ህንጻዎች እና ዛፎች 3 ሜትር እንዲሁም ከመሬት ያለው ከፍታ 5.5 ሜትር ከፍ ማለት የሚጠበቅባቸው ቢሆንም ይህ ሳይሆን በመቅረቱ ብልሽት እና አልፎ አልፎም አደጋ እያጋጠመ ነው።

ባለፉት ሦስት ወራት ብቻም ከ 25 ሺ 973 በላይ ለሃይል መቆራረጥ ምክንያት የሆኑ አነስተኛ እና ከፍተኛ ግኝቶች አግኝተናል።

ከተገኘው ግኝት አብዛኛው ወይም 30 በመቶ የሚሆነው የ ሃይል መቆራረጥ ምክንያት ዛፎች ናቸው።

በመዲናዋ 7,277 የሚሆኑ መስመር ውስጥ የገቡ እና ከ ኤሌክትሪክ መስመር 3 ሜትር መራቅ ያለባቸው ዛፎች የተገኙ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 5 ሺ 585 የሚሆኑትን የማጽዳት ስራ ተሰርቷል።

ያረጁ እና መቀየር የሚያስፈልጋቸው የኤሌክትሪክ ገመድ ተሸካሚ ፖሎች ቁጥር ከ 6 ሺ 367 በላይ ናቸው እዚህም ላይ ስራዎች ተሰርተዋል ይህም ለ ሃይል መቆራረጥ 25 በመቶ ምክንያት ነው።

በተጨማሪም 2 ሺ 425 ከግንባታዎችና እርስ በእርስ የተቀራረቡ መሥመሮች፣ 6 ሺ 298 የረገቡ እና የተለያዩ የመስመር ችግር ያለባቸው ሆነው ተገኝተዋል።

ከ 25 ሺ ግኝቶች ውስጥ 56 በመቶ የሚሆነውን ችግር ፈተናል።

በከተማዋ 10 ሺ 498 ትራንስፎርመሮች ላይ በተደረገ ምርምራ መጠነኛ ችግርች አግኝተንባቸዋል ለዚህም መፍትሄ በመስጠት ላይ እንገኛለን።

ሃይል እያቋረጥን ስራ ስንሰራ የነበረ በመሆኑ በምንፈልገው ደረጃ የሃይል መቆራረጡን እንዳንቀንስ የራሱን አስተዋጽኦ አድርጓል።

የሃይል መቆራረጥ መንስኤዎች ለስራ በሚል የሚቋረጡ ፣በብልሽት እና በሃይል አቅራቢው በኩል የሚያጋጥሙ ችግሮች ተጨማሪ ምክንያት ናቸው " ብለዋል።

ተቋሙ 20 ሚሊየን ብር በመመደብ ከነገ ጀምሮ 100 ሺ ችግኞችን ለመትከል ማቀዱን በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#መቃ

ሰሞኑን " መቃ " ላይ ታጣቂዎች በሹፌሮች  ንፁሃን ዜጎችና የጸጥታ ኃይሎች ላይ አሰቃቂ ነው የተባለ ግድያ መፈጸማቸው ይታወሳል።

ከዛ በኋላ ምን ተፈጠረ ?

- ከታጣቂዎቹ ግድያ በኋላ በመንግሥት ጸጥታ ኃይል በተወሰደ እርምጃ ከ17 በላይ የአካባቢው አርሶ አደሮች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

- በጫካ የሚገኘው የቅማንት ሀይል ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ " በእጀባ ላይ የነበሩ ሹፌሮች፤ ተሳፋሪዎችን እና የመንግስት ጸጥታ ኃይል ላይ ጥቃት ያደረሱት በውንብድና ተግባር የተሰማሩ ሽፍቶች ናቸው " ብሏል። " ሰኔ 16/2017 ዓ.ም የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የመንግስት ታጣቂዎች በአካባቢው ያሉ በመጀመሪያው በሁለተኛው ቀናቶች ወደ ከ17 በላይ ንፁሃን የአካባቢው ተወላጅ አርሶ አደሮችን ገድለዋል " ሲል ከሷል።

- የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ለጥቃቱ " ፅንፈኛው ቅማንት " ሲል የጠራውን ታጣቂ ኃይል ተጠያቂ ማድረጉ ይታወሳል።

- የብሄረሰቡ ተወላጅ የሆኑና በአካባቢው የሚኖሩ ስሜ አይጠቀስ ያሉ ግለሰብ " ጥቃቱን ተከትሎ የመንግስት ታጣቂዎች በወሰዱት እርምጃ ከ17 በላይ የአካባቢው ተወላጅ አርሶ አደሮች ተገድለዋል። ከተገደሉት መካከል ወንድሜ ይገኝበታል " ብለዋል።

- አንድ ሌላ ነዋሪ " የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ታጣቂው የወሰደባቸውን የቡድን መሳሪያ ለማስመለስ ወደ መቃ ከተማ ተኩሰዋል፤ በርካታ ንፁሃን ተገድለዋል ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ የተገደሉትን ጨምሮ ከ17 በላይ ንፁሃን አርሶ አደሮች ተገለዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

- በአሁኑ ሰዓት ቆስሎ ሆስፒታል የሚገኝ የዐይን እማኝ " ግጭቱ ከ10:30-11:00 ነበር የተካሄደው ታጣቂዎች አሽክርካሪዎችንና ተሳፋሪዎችን ተዟዙረው ገድለው ከጨረሱ በኃላ ተመልሰው ጫካ እስኪሄዱ ድረስ ከሞቱት ሰዎች ኪስ ግንዘብና ሞባይል እያወጡ ሲወስዱ በሞተ ሰው አስከሬን ተከልየ አይቻለሁ " ሲል ገልጿል። " ታጣቂዎቹ ወደ ጫካ ከሄዱ በኃላ መከላከያ መጥቶ አካባቢውን እስኪቆጣጠር እስከ ምሽቱ 2:30 ድረስ አስከሬን ሊያነሳ የመጣ ወጣት አላየሁም " ብሏል። የቆሰሉትን ሆነ የሞቱትን ሰዎች የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ናቸው ከወደቁበት ያነሱት።

(ተጨማሪ ዝርዝሩ ከላይ ያንብቡ)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
#TikvahEthiopiaFamilyBahirdar

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

አፍሪካ ከአፍሪካውያን አልፎ ለዓለም የሚተርፍ የመልማት ፀጋ የተጎናፀፈች የወጣቶች አህጉር ናት!

ባለፉት ሁለት ዓመታት አፍሪካ ያላትን እምቅ አቅም ወደ ተጨባጭ ሀይል ለመቀየር፣ የሥራ አጥነት ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀነስ፣ ፍትሃዊ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትንና አህጉራዊ ትስስርን ከፍ ለማድረግ በማለም የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፎረም ተካሂዷል፡፡

ዘንድሮም ለ 3ኛ ጊዜ ሦስተኛው የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፎረም ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 2/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

የፎረሙ ዋና አላማ በስራ ዕድል ፈጠራ መስክ የግብርና እሴት ሰንሰለት፣ ዲጂታላይዜሽንና የፋይናንስ አካታችነትን በማረጋገጥ ምቹና አስተማማኝ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትስስርን ማላቅ ነው፡፡

በዚህ ታላቅ የፓን አፍሪካን ፎረም መሪዎች፣ የፈጠራ ባለሙያዎች፣ ሥራ ፈጣሪዎች እና የዘርፉ ምሁራን በአፍሪካ የመጪው ዘመን ሥራ እና የጋራ ተጠቃሚነት ላይ ይመክራሉ፡፡

ከምክክሩ ጎን ለጎን አንድ መቶ የሚሆኑ ኢንተርፕራይዞች ምርትና አግልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁበትና የገበያ ትስስር የሚፈጥሩበት ኢግዚቢሽንና ባዛር ይካሄዳል፡፡

በመሆኑም በአድዋ ድል መታሰቢያ በመገኘት ባዛሩን እንድትጎበኙና ሥራ ፈጣሪዎችን እንድታበረታቱ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል፡፡

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" እነዚህ ሀገራት እንኳንስ እናተን እራሳቸውንም ማገዝ አይችሉም ! " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በትግራይ ጉዳይ ያነሷቸው ነጥቦች ምንድናቸው ?

- ፕሪቶሪያ ለትግራይ ህዝብ እፎይታ አምጥቷል።

- ትግራይ ቴሌኮሚኒኬሽን ፣ መብራት ፣ ባንክ ፣ የአየር ትራንስፖርት፣ ምርት  አልነበረም ፣ ፋብሪካዎችም ስራ አቁመው ነበር ይሄ ሁሉ ጀምሯል።

- ትግራይ ክልል መንግሥት አልነበረም መንግሥት ተቋቁሟል።

- የተፈናቀሉ ሰዎች ራያ ፣ ፀለምት ተመልሰዋል።

- ወልቃይት የተፈናቀሉ አልተመለሱም DDR አልተፈጸመም።

- የወልቃይት ተፈናቃዮች መመለስ አለባቸው መንግሥት የፀና አቋም አለው። DDR መፈጸም አለበት። በነዚህ ጉዳዮች የፌዴራል ችግር አስመስሎ ለመሳል ይሞከራል ስህተት ነው። የፌዴራል መንግሥት በትግራይ ያለውን ጉዳይ በሰላም የመፍታት ከፍተኛ ፍላጎት አለው።

- ለአንዳንዶች ውጊያ ጨዋታ ሊሆን ይችላል ለህዝባችን ፃረሞት ነው።

- ለአንዳንዶች ስለውጊያ እያነሱ መናገር ምንም ላይመስል ይችላል ስለማይሞቱ ለወጣት ግን ጉዳት ነው።

- የትግራይ ህዝብ 100% ጦርነት አይደልግም አይቶታል ትርፍ የለውም።

- ዓለም ትግራይ እና ምናምን ቢዋጉ ደንታው አይደለም ብዙ ውግያ እያስተናገደ ስለሆነ፤ ጆሮም የለውም ጊዜም የለውም። ዓለም ጊዜ ቢኖረው ኖሮ ሱዳንን ያዳምጥ ነበር።

- የዘመኑን የውጊያ ስልት መገንዘብ ይገባል ፤ አሁን እንደ ድሮ ተራራ መያዝ ተራራ መልቀቅ ብቻ ማሰብ ትክክል አይደለም። ኢራንን እና እስራኤልን ያዋጋው ተራራ አይደለም። ዘመን ተቀይሯል።

- አንዳንዶች " መንግሥት ተወጥሯል በፋኖ ፣ በሸኔ ወታደሩ ተበታትኗል አሁን ነው ጊዜው " የሚሉ ሰዎች አሉ እነዚህ ሰዎች ታሪክን መለስ ብለው ማየት አለባቸው። ሶማሊያ ኢትዮጵያን ስትወር ኢትዮጵያ ወታደር አልነበራትም ፤ ጣልያን ኢትዮጵያን ስትወር ወታደር አልነበራትም። ስለዚህ ኢትዮጵያ ራሷን ለመከላከል የግድ ሰልፍ የያዘ ወታደር አያስፈልጋትም።

- " የሚያግዙን ሰዎች አሉ ፤ የሚያግዙን ሀገራት አሉ " ብሎ ማሰብ በጣም የሚያሳዝነው ሌላው ጉዳይ ነው። እነዚህ ሀገራት እንኳንስ እናተን እራሳቸውንም ማገዝ አይችሉም። ሞራል ቲፎዞነትና ማገዝ ለየብቻ ነው። በትላልቅ ውጊያ እንኳን መደጋገፍ ችግር ሆኗል፤ እንኳንስ በሰፈር ውጊያ። የዓለም ኢኮኖሚ ከራስ ተርፎ ሰው ለማገዝ የሚያስችል ነገር ብዙ የለም ካለም ጥቂት ብቻ ነው።

- ትግራይ የሚያስፈልገው ሰላም ነው በንግግርና ውይይት ችግር መፍታት ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በዝቋላ አንድ አባት ተገድለዋል ማን እንደገደላቸው እየተጣራ ነው ያለው ተጣርቶ ምላሽ እንደሚያገኝ ተስፋ አደርጋለሁ "- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ባለው ደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም “የሸኔ ታጣቃዎች” ባህታውያን አባቶች በሚኖሩባቸው ዋሻዎች ተኩስ መክፈታቸውን ገዳሙ ማሳወቁ ይታወሳል።

ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ አንድ አባት መገደላቸውን እና ሟቹ አባት ባህታዊ አባ ኃይለሚካኤል እንደሚባሉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከገዳሙ ባገኘው መረጃ መዘገቡ ይታወሳል።

በተደጋጋሚ በገዳሙ እያጋጠመው ስላለው የመነኮሳት ግድያ መንግስት ለምን ማስቆም ተሳነው ሲሉ በዛሬው እለት የምክር ቤት አባሉ አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ አቅርበዋል።

የአብን አባሉ አቶ አበባው " በዝቋላ ምንም መሳሪያ ያልታጠቁ መናኞች እና የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን ከሞት እና ከድብደባ ለመታደግ አግባብ ያለው የጸጥታ ሃይል የማይመድበው ለምንድነው " ሲሉ ጥያቄያቸውን አንስተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ በዝቋላ አንድ መናኝ መገደላቸውን አረጋግጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዝርዝር በሰጡት ምላሽ ምን አሉ ?

" ' መሻቴን ፍላጎቴን በሃይል ማስፈጸም እችላለሁ ' የሚሉ ሃይል በብቸኝነት የመጠቀም ስልጣን የመንግስት ብቻ መሆኑን የማይቀበሉ ሰዎች ናቸዉ።

እንዳሉት በዝቋላ አንድ አባት ተገድለዋል ማን እንደገደላቸው እየተጣራ ነው ያለው  ተጣርቶ ምላሽ እንደሚያገኝ ተስፋ አደርጋለሁ።

የሃይማኖት ተቋማት የታጠቁ ሽፍቶች መሸሸጊያ ከሆኑ እንደዚህ አይነት አደጋ ሊፈጠር ይችላል የሃይማኖት ቦታ የሃይማኖት ብቻ መሆን አለበት ሲሸሹ የሚደበቁበት ከሆነ ሲከፋቸው ገድለው ሊሄዱ ስለሚችሉ።

የዝቋላው ምን ይገርማል 12 አመት ተምሮ ፈተና ሊፈተን የሚሄድ ሰው ላይ የሚተኩሱ ሰዎች ዝቋላ ላይ አንድ አባት ላይ ቢገድሉ ምን ይገርማል።

የግድያው እሳቤ ነው ችግር ያለው ፈተና አትፈተን፣ ማዳበሪያ አትውሰድ ፣ትምህርት አትማር ብሎ የሚገድል ሰዉ ኢትዮጵያ ውስጥ ካለ የትም ሞት አለ ማለት ነው።

'ልብ ሲያቅ ገንፎ ያንቅ ይባላል'  ልባችን ያውቀዋል እነማን እንደሆኑ፤ ድብብቆሽ አይደለም። እነማን ገዳይ እንደሆኑ ግልጽ ነው። 'ልብ ሲያቅ ገንፎ ያንቅ' የመባለው እያወቅነው የምናግበሰብሰው ጉዳይ ሲሆን ነው።

ግድያ ሽንፈት ብቻ ነው የሚያመጣው በመግደል አይሳካልኝም ብሎ ማመን ያስፈልጋል። ... በሃይል ፍላጎትን ማስፈጸም ማለቂያ የለውም መቆም አለበት። " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Ethiopia 🇪🇹
#GERD 🇪🇹

" መስከረም ላይ ዝናብ ጋብ ሲል ህዳሴን እናስመርቃለን !!! "

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በሚመለከት ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምን አሉ ?

" ህዳሴ አልቋል። ህዳሴን እናስመርቃለን። ህዳሴ ከመመረቁ በፊት ' ብንረብሽ ' ብለው የሚያስቡ ሰዎች አሉ ፤ እናስመርቃለን።

ህዳሴን እንዳይመረቅ ለማድረግ የሚያስችል ነገር አሁን የለም። የሚመረቀውም አሁን ነው ነገ ክረምቱ ሲያልቅ።

ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ያለኝ መልዕክት ህዳሴ ለሱዳን ህዳሴ ለግብፅ በረከት ነው። በፍጹም ጉዳት አያመጣባቸውም። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ልማት ልማታቸው ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ኢነርጂ ለሁሉም ጎረቤቶች የሚዳረስ ነው።

የኛ ግድብ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራትን የሚጎዳ ቢሆን ኖሮ ቱርካና አጀንዳ አይሆንም ነበር። ታስታውሳላችሁ ግቤ 3 ሲሰራ 'ቱርካና ይደርቃል የሚል ከፍተኛ ችግር ነበር። እንኳን ሊደርው ከግድቡ በኋላ ይኸው ሞልቶ እያስቸገረ ነው ያለው።

አሁንም ግብፅ ብትሄዱ የግብፅ አስዋን ግድብ አንድ ሊትር ውሃ አልቀነሰም። ወደፊትም ኢትዮጵያ እስከበለጸገች ድረስ እስካለች ድረስ የግብፅ ወንድሞቻችንን ጉዳት እኛ አናይም ተባብረን ከወንድሞቻች ጋር ማደግ እንፈልጋለን።

ግብፅ እንድትጎዳ ፣ ሱዳን እንድትጎዳ አንፈልግም። ኢነርጂውን በጋራ እንጠቀማለን ውሃውን በጋራ እንጠቀማለን ልማት በጋራ ይመጣል። ንግግር ካስፈለገ እንነጋገራለን ችግር የለም።

እኛ ለረጅም ጊዜ ስናነሳ የነበረው ' አትስሩ ' አትበሉን ነው ያልነው እንጂ በኛ ገንዘብ በኛ ምድር የሚሰራውም ስራ አታግዱ ነው ያልነው እንጂ ያን እስካልከለከሉ ድረስ አሁንም ከግብፆች ጋር ለመነጋገር፣ ለመደራደር ፣ ለመስራት ኢትዮጵያ ዝግጁ ናት፤ምንም ችግር የለብንም።

በእርግጠኝነት የምናገረው ህዳሴ ለግብፅም ለሱዳንም ጉዳት አያመጣም።

በዚሁ አጋጣሚ በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቁ የስልጣን ባለቤት ይህ የተከበረው ምክር ቤት ስለሆነ ለግብፅ መንግሥት ፣ ለሱዳን መንግሥት እንዲሁም ለተፋሰሱ ሀገራት መንግሥታት በሙሉ መስከረም ዝናብ ጋብ ሲል ህዳሴን ስናስመርቅ የደስታችን ተካፋይ እንዲሆኑ ግብዣ አቀርብላቸዋለሁ።

የጋራ ሃብታችን ነው ፤ በጋራ እናስመርቀዋለን በጋራ እናየዋለን፣ የሚታዩ ጉዳዮች ካሉ በጋራ እናያለን።

ከድርቅ ጋር ተያይዞ ግብፅ የሚነሳው ነገር ' ድርቅ በሚሆንበት ሰዓት ግብፅ ትጎዳለች ' ነው ፤ ድርቅ የሚባለው ኢትዮጵያ ነው ኢትዮጵያ ከደረቀች ውሃዋ የለም  ማለት ነው እዛ አይደለም ድርቅ የሚባለው፤ ኢትዮጵያ ደግሞ እንዳትደርቅ Green Legacy (አረንጓዴ አሻራ) እየሰራን ነው እኛ አንደርቅም ማለት ነው እኛ ዝናብ ካገኘን እኛም ግብፅም ሱዳንም ሌሎቹም ይጠቀማሉ። በቅንነት አይተን በጋራ ለልማት እንድንሰራ አደራ እላለሁ። "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#EthiopianAirlines🇪🇹

የአፍሪካ ግዙፉ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ ዓመት ተጨማሪ 13 አውሮፕላኖችን መግዛቱን ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

አሁን ላይ አየር መንገዱ ያሉት አውሮፕላኖች ብዛት 180 መድረሱን ጠቁመዋል።

በተመሳሳይ በዚህ ዓመት ብቻ 6 አዳዲስ መዳረሻዎችን በመጨመር አጠቃላይ መዳረሻውን ወደ 136 ከፍ ማድረጉን ገልጸዋል።

አየር መንገዱ በዚህ ዓመት በሀገር ውስጥ እና በውጭ ከ19 ሚሊዮን ሰው በላይ ማጓጓዙን አመልክተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ኢትዮጵያ🇪🇹

" የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ በቅርቡ ይጀመራል፤ ከ40 ወራት በኋላም ተጠናቅቆ ስራ ይጀምራል " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምን አሉ ?

" ኢትዮጵያ ከፍተኛ የማዕድን አቅም ያላት ሀገር ናት፤ በአፍሪካ ውስጥ ትላልቅ የማዕድን አቅም ካላቸው ሀገራት አንዷ ናት ፤ እስካሁን የትክረት የአመራር፣ የዕይታ ማነስ ስለነበረ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ማገዝ ይችል ነበር። አሁን እያነቃቃነው ነው።

ወርቅ ባለፈው ዓመት በዚህ ዓመት 37 ቶን ወርቅ ኤክስፖርት አድርገነዋል። 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ኤክስፖርት ዓመት ያገኘነውም ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተን ስለሰራን ነው። ይህ በየትኛውም ዘመን ያልነበረ ስኬተ ነው። ሌላው ጋዝ ነው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በጋዝ ላይ የሚሰማሩ ኩባንያወች ፈቃድ አውጥተው ወደ ተጨባጭ ስራ አይገቡም ነበር።

ኢትዮጵያ የጋዝ ምርት በቅርቡ ለገበያ ማቅረብ ትጀምራለች። በዚህም ሰርቶ አዳሪ እንጂ አውርቶ አዳሪ አለመሆናችንንም በተከታታይ እያሳየን እንቀጥላለን። የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ በቅርቡ ይጀመራል፤ ከ40 ወራት በኋላም ተጠናቅቆ ስራ ይጀምራል። "

Credit : PMO Ethiopia

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#HoPR🇪🇹

" የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበት ከፍተኛ ጫና እያሳደረባቸው ካሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የመንግሥት ሰራተኛው ግንባር ቀደም ነው ! " - የምክር ቤት አባል

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተዋል።

የምክር ቤቱ አባላትም ጥያቄያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እያቀረቡ ይገኛሉ።

እስካሁን ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል ከኑሮ ውድነት፣ ከመንግሥት ሰራተኞች ፣ ጤና ባለሙያዎች እና መምህራን የደመወዝ ጭማሪ ጋር የተያያዘ ጥያቄ ይገኝበታል።

ጥያቄው የቀረበው በምክር ቤት አባሉ አቶ ግዛቸው አየለ ነው።

ምን አሉ ?

" የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበት ከፍተኛ ጫና እያሳደረባቸው ካሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የመንግሥት ሰራተኛው በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል።

በዚህ ምክንያት የጤና ባለሙያዎችን እና መምህራንን ጨምሮ የተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ የመንግሥት ሰራተኞች የደመወዝ ማሻሻያ እንዲደረግ ጥያቄ እያነሱ ይገኛሉ።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የመንግሥት ሰራተኛን የኑሮ ደረጃ ከማሻሻል አኳያ በመንግሥት ምላሽ ዙሪያ ማብራሪያ ቢሰጥበት።

በተጨማሪ መንግሥት የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ እንዳለ ይታወቃል ይሁን እንጂ ካለው የቤት ፈላጊ ቁጥር ጋር ተነጻጽሮ ሲታይ ገና ብዙ ስራ ይጠይቃል። መንግሥት በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ በከተሞች የሚታየውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት ምን እየሰራ ይገኛል ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

የምክር ቤቱ ስብሰባ በብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀጥታ እየተላለፈ ይገኛል።

በተጨማሪ በምክር ቤቱ የዩትዩብ ገጽ መከታተል ይቻላል ፦ https://www.youtube.com/live/yLIns-2_vZM?feature=shared

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ለምሳሌ የካ ክፍለ ከተማ ወደ 100 የሚሆኑ ሰዎች መታሰራቸውን በማስረጃዎች አረጋግጠናል፤ ወደ ቦሌ ወደ 200 የሚሆኑ አሉ " - ድርጅቱ

" ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች ኢትዮጵያ " የመብት ተሟጋች የተሰኘው ድርጅት፣ " የትግራይ ተወላጆች በአዲስ አበባ በዘፈቀደ እየታሰሩ ነው " ሲል ለቲካቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ፡፡

ስለእስሩ በተጨባጭ ያላችሁ መረጃ ምንድን ነው ? ብለን የጠየቅናቸው የድርጅቱ ምክትል ዳይሬክተር አቶ መብሪሂ ብርሃነ፣ " በባለፉት ሁለት፣ ሦስት ሳምንታት ያለየፍርድ ቤት ትዕዛዝ፣ ያለበቂ ጥርጣሬ ሰዎች በማንነታቸው ብቻ እየታሰሩ ስለሆነ ይህን መሠረት አድረገን ክትትል ስናደርግ ቆይተናል " ብለዋል።

" ከክትትል ባለፈ ደግሞ ተጨባጭ ማስረጃ ካገኘን በኋላ እና ታስረው የወጡት፣ የታሳሪ ቤተሰቦችና ጓደኞችን ከጠየቅን በኋላ ሪፖርት አውጥተናል " ብለው፣ " ሰዎች ከሕግ ውጪ ሲታሰሩ ብቻ ሳይሆን ያለበቂ ጥርጣሬ ታስረው ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ሲቀር ይሄ የዘፈቀደ እስር ነው " ሲሉ ወንጅለዋል።

" ሰዎች ሊታሰሩ ይችላሉ። ግን ሕግ ቢተላለፉ እንኳ ወደ ፍርድ ቤት ነው እንጂ የሚቀርቡት ከ48 ሰዓታት በላይ ፓሊስ አስሮ ማቆየት አይችልም በወንጀል እንኳ የተጠረጠረውን። እነዚህ ግን የወንጀል ጥርጣሬም የላቸውም፣ ለምን እንደታሰሩም አይነገራቸውም " ነው ያሉት።

እስራቱ ከምን ጋር የተያያዘ እንደሆነ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ " እስሮች በየጊዜው ይፈጸማሉ አሁን በትግራይ ተወላጆች ትኩረቱን አደረገ እንጂ፤ ከዚህ በፊትም ማንነት ተኮር እስሮች አሉ። ምክንያቱን አሳሪዎቹ ናቸው የሚያውቁት " ብለዋል።

" አንድ ሰው ከታሰረ ፍርድ ቤት መቅረብ አለበት እንጂ አንድ ቦታ አጎሮ ሳምንት፣ ሁለት ሳምንት ማቆየት ሕገ ወጥ ድርጊት ነው በወንጀልም ያስጠይቃል። በቁጥጥር ሥር የሚያውሏቸው ሰዎች 'እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ ከላይ የመጣ ትዕዛዝ ነው' ነው የሚሉት " ብለዋል።

" ሰዎች በሕገ መግስቱ አንቀጽ 25 መሠረት በእኩልነት ነው መስተናገድ ያለባቸው " ያሉት ም/ዳይክተሩ፣ " የታሰሩ አንዳንድ ሰዎች ገንዘብ ከፍለው የወጡበት ሁኔታ አለ። ስለዚህ የሙስና ተግባራትም አለ ለማለት ያስችላል " ብለዋል።

በተጨባጭ ድርጅቱ ባለው መረጃ መሠረት ምን ያክል ሰዎች ታስረዋል ? የት ክፍለ ከተማስ ነው የታሰሩት ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረላቸው ጥያቄ፣ " በተጨባጭ በእያንዳንዱ ከተማ ምን ያህል ሰው እንደታሰረ መቁጠር ያስፈልጋል። ግን ለምሳሌ የካ ክፍለ ከተማ ወደ 100 ሰዎች መታሰራቸውን በማስረጃዎች አረጋግጠናል፤ ወደ ቦሌ ወደ 200 የሚሆኑ አሉ " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

" በመቶዎች ወይም እስከ 1000 ሊሆን ይችላል ብለን እንገምታለን አጠቃላይ በቁጥጥር ሥር ውለው የተፈቱትና አሁንም በእስር ላይ ያሉት" ያሉት አቶ መብሪሂ፣ "ሰዎቹ የታሰሩት ቦሌ፣ ሲኤምሲ፣ ሾላ፣ ልደታ እና ሌሎች ቦታዎች ላይ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ሰዎች ወንጀል ከሰሩ በሕግ አግባብ አይጠየቁ አንልም ነገር ግን በጅምላ እየተወሰዱ፣ አንዳንዴም ገንዘብ እየጠየቁ እየሆነ ያለ ተግባር ስለሆነ በማንም ተወላጅ ላይ ሊደረግ አይገባም። መንግስት አስቸኳይ መፍትሄ ይስጥበት " ሲሉም አሳስበዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ የጠየቀው አንድ ተቋም፣ ጉዳዩን እየተከታተለው መሆኑን የጠቆመ ሲሆን፣ ምላሽ ከሰጠ የምናቀርብ ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#DStvEthiopia
#ሁሉምያለውእኛጋርነው

📣 ከእሁድ እስከ እሁድ አለንላችሁ!

❗️❗️ለአጭር ጊዜ የሚቆይ! ደንበኝነትዎን ከሰኔ 8 ጀምሮ ሲያራዝሙ ከፍ ወዳለው ፓኬጅ ከተጨማሪ ቻናሎች ጋር በስጦታ ያገኛሉ!!

አዲሱን እና የተሻሻለውን MyDStv መተግበሪያ ያውርዱ።
⬇️ https://mydstv.onelink.me/vGln/xepsjmo7

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው!

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#NationalExam🇪🇹

ከሰኔ 23 እስከ 25/2017 ዓ/ም በበይነ መረብና በወረቀት ሲሰጥ የነበረው የአንደኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል፡፡

ፈተናውን በወረቀት 231,761 በበይነ መረብ 43,367 በድምሩ 275,128 ተፈታኞች ወስደዋል፡፡

የመጀመሪያ ቀን የመጀመሪያ ክፍለ ጊዜ ላይ ፈተናውን በበይነ መረብ ሲወስዱ በተወሰኑ የፈተና ማዕከላት ላይ በተለያየ ምክንያት የእንግሊዘኛ ፈተና ያልወሰዱ ተፈታኞች አብዛኞቹ ነገ ሐሙስ ጥዋት ከሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ጋር ያልወሰዱት ፈተና የሚሰጣቸው እንደሆነ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

በሁለተኛ ዙር ለመውሰድ ያልቻሉ ተፈታኞች ከሶስተኛውና ከአራተኛው ዙር ተፈታኞች ጋር እንደሚወስዱ አመልክቷል።

" ፈተናውን በተለያዩ ዙሮች መስጠት መቻላችን በተለያዩ ችግሮች ምክንያት በተመደቡበት ዙር መፈተን ያልቻሉ ተፈታኞች በሌሎቹ ዙሮች ከሚፈተኑ ተፈታኞች ጋር መፈተን እንዲችሉ ዕድል ፈጥሯል " ሲል አገልግሎቱ ገልጿል።

#EAES

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በእስራኤል እና በኢራን መካከል የተካሄደውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ ወደ ሶስቱም ከተሞች ያቋረጥናቸውን በረራዎች በድጋሚ አስጀምረናል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

በዛሬው ምሽት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፖርቶ ወደ ተሰኘች የፖርቹጋል ከተማ አዲስ በረራ ይጀምራል።

አየር መንገዱ የፖርቹጋል ሁለተኛ ትልቋ ከተማ ወደ ሆነችው ፖርቶ የሚያደርገው በረራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአውሮፓ ያሉትን የበረራ መዳረሻዎች ቁጥር 22 እንደሚያደርሰው ይፋ በማድረጊያ ስነስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አውሮፓ ከሚያደርጋቸው ጉዞዎች በሀገር ደረጃ ፖርቹጋል 17 ተኛዋ ሃገር ስትሆን ይህ በረራ ወደ ፖርቹጋል የተደረገ የመጀመሪያው በረራ መሆኑን ተነግሯል።

የአየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው " የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪው አንድ ወር ጊዜ ወደ ወደ ዱባይ እና ቬትናም  ተጨማሪ ሁለት መዳረሻዎችን ይፋ የሚያደርግ ይሆናል " ብለዋል።

በእስራኤል እና በኢራን መካከል ተቀስቅሶ የቆየውን ግጭት ተከትሎ አየር መንገዱ ወደ ቀጠናው የሚያደርገው ጉዞ ማቋረጡ ይታወሳል።

ተቋርጠው የቆዩት በረራዎች በድጋሚ መጀመራቸውን አቶ መስፍን ጣሰው አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ በዝርዝር ምን አሉ ?

" መካከለኛው ምስራቅ እና ገልፍ አካባቢ ያሉ ሃገሮች ላይ ግጭት መኖሩን ተከትሎ የተወሰኑ ከተሞች በረራ አቋርጠን ነበር።

እስራኤል ውስጥ ወደ ቴልአቪቭ፣ ሊባኖስ ውስጥ ወደ ቤሩት እንዲሁም ዮርዳኖስ ውስጥ ወደ ኦማን ከተሞች ስናደርግ የነበረውን በረራዎች በጊዜያዊነት አቋርጠን ቆይተናል።

በእስራኤል እና በኢራን መካከል የተካሄደውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ ወደ ሶስቱም ከተሞች ያቋረጥናቸውን በረራዎች በድጋሚ አስጀምረናል።

ተቋርጦ በቆየበት ወቅት መንገደኞች ወደዛ አካባቢ መጓጓዝ ያቆማሉ ስለዚህ መጠነኛ የተጓዦች መቀነስ ይታያል በረራ ላይ ሲታይ ግን ትልቅ ለውጥ የነበረው አይደለም " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ከሲስተማችን ጋር በተያያዘ መጠነኛ ችግር፣ የሲስተም መዘግየት በወረዳ ጽ/ቤቶቻችን ላይ እየገጠመን ይገኛል " - CRRSA

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ፣ ከሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ከሲስተም ጋር በተያያዘ መጠነኛ ችግር፣ የሲስተም መዘግየት በወረዳ ጽ/ቤቶች እንደገጠመው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

አገልግሎቱ የገጠመው ችግር ፦
- ቀድሞ የዲጂታል ምዝገባ ያደረጉ፣
- እድሚያቸው ከ12 በታች የሆኑ ህፃናትን፣
- በውክልና የሚስተናገዱ ተገልጋዮችን የማያካትት መሆኑን ገልጾ፣ ነዋሪዎች ሌሎች አገልግሎቶችን ማግኘት እንደሚችሉ አሳውቋል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ፣ የሲስተም መቅራረጡ ያጋጠማችሁ 119ኙ ወረዳዎች ሙሉ ለሙሉ ሳይሆን ህዝብ የሚበዛባቸው በማንዋል አገልግሎት ሲሰጡ በነበሩ ብዙ የዲጂታል ተመዝጋቢ ባለባቸው ክፍለ ከተሞች መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" ከዚህ በፊት ዲጂታል ያልነበረባቸውና ባለፈው ሰኔ የጀመርንባቸው የካ፣ ንፋስ ስልክ እና አቃቂ ክፍለ ከተሞች በጣም መጨናነቅ ያለባቸው ቦታዎች ናቸው" ያሉን አቶ ዮናስ፣ "በሌሎቹ ክፍለ ከተሞች ግን ሰላም ነው፤ ቀድመው ኢንሮል ስላደረጉ ነዋሪዎቹ ሰርቪስ ሲጠይቁ ጀነሬት ይደረጋል እንጂ እንደ አዲስ አሻራ፣ ፎቶ አንቀበልም " ሲሉ ተናግረዋል።

" አንዴ ዲጂታል የተመዘገበ ሰው ብዙም ችግር የለበትም፤ ያገኛል። ሲስተሙ ውስጥ ያልገባ የአዲስ ሰው ምዝገባ ላይ ነው ጫና የፈጠረብን። ነገ እስከ ከሰዓት እንፈታዋለን። ይህን ለማካካስም እሁድም ሥራ እንገባለን" ብለዋል።

" ከማንዋል ወደ ሲስተም እየገቡ ያሉ ሰዎች አገልግሎት ነው እየተዘገየ ያለው " ሲሉም አስረድተዋል።

ኤጀንሲው፣ ችግሩን ለመፍታት እየሰራን መሆኑን ጠቁሞ፤ " ለገጠመው የአገልግሎት መስተጓጎል ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን " ሲል ከወዲሁ አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…
Subscribe to a channel