1532594
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
#Tigray
የትግራይ ኃይል አባላት ለአምስተኛ ቀን ያካሄዱት የመኪና መንገድ መዝጋት ያካተተ ሰልፍ ተከትሎ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር የሰራዊት አባላት ተጠቃሚ የሚያረጋግጥ ደንብ ማጸደቁ አስታውቋል።
እሁድ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም የጀመረው የትግራይ ኃይል ሰልፍና ተቃውሞ ዛሬ ቀጥሎ ከእንዳስላሰ-ሽረ ፣ አክሱም ፣ ዓድዋና ተምቤንና ሌሎች አከባቢዎች ወደ መቐለ የሚያስገባ መንገድ ተዘግቶ ውሏል።
ይህንን ተከትሎ ዛሬ ጥቅምት 7/2018 ዓ.ም ከሰዓት በኃላ የፅሁፍ መግለጫ ያወጣው የጊዚያዊ እስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ካቢኔ ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ያወጣው የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ረቂቅ ደንብ ዛሬ ማፅደቁን አመልክተዋል።
ካቢኔው በዛሬው አስቸኳይ ስብሰባው የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ደንብ በዝርዝር ተወያይቶ ተግባራዊ እንዲሆን በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።
የፀደቀው ደንብ ፦
- መሰረታዊ ፍላጎቶች
- የህክምና አገልግሎት
- የቤት መስሪያ መሬት
- በመንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የሚሰጥ የክብር አገልግሎት
- ትምህርት ስልጠናና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ያካተተ ነው ብሏል ከፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት የተሰጠው የፅሁፍ መግለጫ።
" የፀደቀው የትግራይ ፀጥታ ኃይሎች ተጠቃሚነት ደንብ ለረጅም ጊዜ ጥናት የተደረገበት ከፀጥታ አመራሮች ውይይት ሲካሄድበት የቆየ ነው " ሲል ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
#Update
ወደ መቐለ የሚያመሩ መንገዶች ዛሬም ለሁለተኛ ቀን በሁለት አቅጣጫ በትግራይ ኃይል ሰልፈኞች ተዘግተዋል።
የተዘጉት መንገዶች በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ከመቐለ በ35 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው የኣጉላዕ ከተማ ፤ በደቡባዊ ዞን ከመቐለ 100 ኪሎ ሜትር አከባቢ በምትርቀው የመኾኒ ከተማ መሆኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መረጃ ደርሶታል።
በተጨማሪ በሰሜን ምዕራብ ዞን ወደ እንዳስላሰ-ሽረ ከተማ የሚወስደው መንገድ ከከተማዋ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት በሚገኘው እንዳባጉና ከተማ በሰልፈኞች ተዘግቷል።
ሰልፈኞቹ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም ከመቐለ ከተማ ወደ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ የሚወስደው ዋና መንገድ ዘግተው ውለው በዚያው ቀን ምሸት ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) ተወያይተው " ጥያቄያችሁ ልክ ነው ፤ በየደረጃው ይመለሳል " ተብለው ነበር።
ጉዳዩን ተከታትለን መረጃውን የምንልክ ይሆናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ መንግስት ለአካል ጉዳተኞች ጤና-ነክ መልሶ ማቋቋም እና ፆታን ታሳቢ ያደረጉ አገልግሎቶች ተደራሽ መሆናቸውን ለማረጋገጥ አግባብነት ያላቸውን እርምጃዎች በሙሉ ለመውሰድ በአለምአቀፉ የአካል ጉዳተኞች ስምምነት አንቀጽ 25 መሰረት ግዴታዎችን ተቀብሏል! በተለይም የአካል ጉዳተኞች የስነተዋልዶ እና የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት መብቶች እውን እንዲሆኑ፤ አካል ጉዳተኞች ጾታዊ ግንኙነት፣ የስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎትን እንዲሁም ስነ ህዝብን መሠረት ያደረገ የህዝብ ጤና ፕሮግራሞችን በሚመለከት ከአድልዎ በጸዳ ሑኔታ እና ከሌሎች ሰዎች ጋር እኩል በሆነ መልኩ አገልግሎቶቹን የማግኘት መብት አላቸው! አካል ጉዳተኞች እነዚህን አገልግሎቶችን በሚያገኙበት ወቅት ለሌሎች ሰዎች እንደሚሰጠው ባለ ተመሳሳይ አይነት፣፣ ጥራትና ደረጃ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል! የስነተዋልዶ እና የቤተሰብ አገልግሎቶች በነፃ ወይም የአካል ጉዳተኞችን የመክፈል አቅምን ያገናዘቡ መሆን አለባቸው!
አካል ጉዳተኞች በአካል ጉዳታቸው ምክንያት አድልዎ ሳይደረግባቸው ሊደረስበት ለሚቻለው ከፍተኛው የጤና ደረጃ ባለቤትነት መብት እንሰራለን!
አካል ጉዳተኞችን ያካተተ የስነተዋልዶ እና የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ስርአት፤ለጤናማ ማህበረሰብ የእድገት እና የጥንካሬ ጉልላት።
የኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ አካል ጉዳተኞች ማህበር
Tel: 9110/ +251115581164
Website:
Facebook,
Twitter:
LinkedIn
#Tigray
በመቐለና ዙሪያዋ የሚገኙ የትግራይ ኃይል አባላት ትናንት ሰኞ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም የጀመሩት የመኪና መንገድ በመዝጋት የተደገፈ የተቃውሞ ሰልፍ ዛሬም በሌሎች አቅጣጫዎች ሲካሄድ ውሏል።
ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 4/2018 ዓ.ም ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ወደ መቐለ ከተማ የሚያስገባው ዋና አስፋልት ከጥዋት ጀምሮ ተዘግቶ ነበር።።
ሰልፈኞቹ ኣጉላዕና ጉርመዶ በሚባሉ ሁለት ቦታዎች መንገድ በመዝጋታቸው ምክንያት መኪኖች ቆመው ተጓዦች መስተጓጎላቸው የታወቀ ሲሆን ማምሻውን መንገዶች ተከፍተዋል ብለዋል ተጓዦች።
መንገድ በመዘጋቱ ምክንያት ከፍተኛ እንግልት እንደደረሰባቸውና ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ተቋውሟቸውን ከመንገድ መዝጋት ውጪ ቢያደርጉት የሚል ምክረ ሃሳብ ሰጥቷል።
ዛሬ ጥቅምት 4/2018 ዓ.ም ከሰዓት በኃላ መግለጫ ያወጣው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት " የሰራዊት አባላት ሰልፈኞቹ ጥያቄ ልክ ነው " ብሏል።
የሰላማዊ ሰልፈኞቹ ጥያቄዎች ኑሮን ማሻሻልና የደመወዝ ጭማሪ መሆናቸው ያስታወቀውና የተቀበለው የጊዚያዊ አስተዳዳሩ ጥያቄዎቹ እንዲፈቱ ከሚመለከታቸው አካላት በመቀናጀት እሰራለሁ ብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
ብሔራዊ ባንክ ዛሬ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አካሂዷል።
ባንኩ መሰል ጨረታ ሲያወጣ ለ10ኛው ዙር ሲሆን በዚህ ዙር 150 ሚሊዮን ዶላር ነበር ያቀረበው።
በጨረታው የአንድ የአሜሪካን ዶላር አማካይ የምንዛሪ ተመን 148.1007 ብር ሆኖ ተመዝግቧል። / 1 ዶላር በ148.1007 ተሽጧል /
ይህ አዲስ አማካኝ ዋጋ ከሁለት ወራት በፊት በ9ኛው ዙር ጨረታ ከተመዘገበው 138.2 ብር አማካይ ዋጋ ጋር ሲነጻጸር፣ የ9 ብር ከ90 ሳንቲም ወይም የ 7.16 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
ዛሬ በተካሄደው የውጭ ምንዛሪ ድልድል 31 ባንኮች የውጭ ምንዛሪ በማግኘት ተሳክቶላቸዋል።
ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ገበያው በሚፈቅደው ጊዜ ጨረታዎቹን ማካሄዱን እንደሚቀጥል አስታውቋል። #ካፒታል
@tikvahethiopia
#Update
የትግራይ ኃይል አባላት ሰልፍ ዛሬም በሌላ አቅጣጫ ሰልፍ ማድረግ ቀጥለዋል።
በመቐለና ዙሪያዋ የሚገኙ የትግራይ ኃይል አባላይ ትናንት ሰኞ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:30 እስከ ምሽት ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደው ነበር።
በዚያው ቀን ምሸት የሰላማዊ ሰልፈኞቹ ተወካዮች የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) ከሚገኙባቸው የህወሓትና የሰራዊት አዛዦች ቢነጋገሩም ፤ ስለተደረሰው ስምምነት በይፋ ለህዝብ የተሰጠ መረጃ የለም።
ሆኖም ከሰብሰባው አዳራሽ ተቆርጦ የወጣው ቪድዮ እንደሚያመለክተው ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የደመወዝ ፣ የጥቅማጥቅምና ለቤተሰቦቻቸው መኖሪያ የሚውል የመስሪያ ቦታ ጥያቄ አንስተዋል።
የትናንትናው ውይይት ውጤት ለህዝብ ሳይነገር ታድያ ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 4/2018 ዓ.ም ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ወደ መቐለ ከተማ የሚያስገባው ዋና አስፋልት ከጥዋት ጀምሮ ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ሰዓትና ደቂቃ በሁለት ቦታ ተዘግተዋል።
የትግራይ ኃይል አባላት ሰላማዊ ሰልፈኞች ኣጉላዕና ጉርመዶ በሚባሉ ሁለት ቦታዎች መንገድ በመዝጋታቸው ምክንያት መኪኖች ቆመዋል ተጓዦች ተስተጓጉለዋል።
ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ጥያቄያቸው ከትናንትናው ሰልፍ ተመሳሳይ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ቦታው ድረስ ደውሎ አረጋግጠዋል።
በዚህ ዙሪያ የሚኖሩ አዳዲስ መረጃዎች ተከታትለን እናቀርባለን።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
ወረቀት የለም! ጊዜ ማባከን የለም!
ቀላልና ፈጣን የባንክ አገልግሎት ብቻ!
የጣት አሻራንና የፊት ገጽን እንደ መለያ የሚጠቀመው አዲሱ የአቢሲንያ ባንክ ወረቀት አልባ አገልግሎት ደንበኞች በጊዜና ቦታ ሳይገደቡ ያለማንም እርዳታ በራስ-አገዝ (Self-Service) ወይም በሠራተኞች በመታገዝ (Assisted Service) ደህንነቱ በተጠበቀና ፈጣን በሆነ መልኩ የሚፈልጉትን የባንክ አገልግሎት መጠቀም ይችላሉ፡፡ #ወረቀትአልባየባንክአገልግሎት #Paperlessbranchmodel #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
የአዕምሮ ህሙማን ቁጥር በዓመት ውስጥ እስከ 15 ሺሕ ጨምሯል።
አማኑኤል የአዕምሮ ህሙማን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በሆስፒታሉ የሚስተናገዱ የአዕምሮ ህሙማን ቁጥር በዓመት ውስጥ እስከ 15 ሺሕ መጨመሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ፡፡
ይህን ያሉን፣ የአዕምሮ ህሙማን ቁጥር እየጨመረ ወይስ እየቀነሰ ነው ? ግጭትና ጦርነት የህሙማኑን ቁጥር ለመጨመር ገፊ መንስኤ አልሆነም ? ስንል የጠየቅናቸው የአዕምሮ ሐኪምና የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ክብሮም ኃይሌ ናቸው።
ዳይሬክተሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በዝርዝር ምን አሉ ?
" የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ግጭት፣ ድርቅ፣ ጦርነትና መፈናቀሎች በተደጋጋሚ አጋጥመዋል። እነዚህ ክስተቶች የአዕምሮ ጤና ችግርን እንደሚጨምሩ የሚያሻማ አይደለም።
ካለፈው ዓመት መጠነኛ ጭማሪ አለው፡፡ የ2017 እስከ ሰኔ ያለው ከ130 ሺሕ ትንሽ ከፍ ይላል፤ በዚያኛው ዓመት ካየነው 10 ሺሕ፣ 15 ሺሕ ጭማሪ አለው።
ስለዚህ የመጨመር ሁኔታዎች አሉ፤ እንደሚጨምርም ይታወቃል፡፡ ግን ሁሉም (ታማሚ) አይመጣም፡፡ ስለዚህ የሆስፒታሉ ዳታ ማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን ሁኔታ ላያሳይ ይችላል። ስለዚህ እኛ ጋር ያለው የታካሚ ቁጥር መጨመር አለመጨመሩ የችግሩን መኖር አለመኖሩን (ሙሉ በሙሉ) አያሳይም።
የአማኑኤል ሆስፒታል የህሙማን ፍሰትን የሚያግዱ የተለያዩ ምክንያቶች አሉ። ለአብነትም በገንዘብ አቅም ማነስ፣ በሚያግዝ ሰው አለመኖር ህሙማን ላይመጡ ይችላሉ።
የመፍትሄ ሀሳብ ምን ሰጡ ?
" እኛ ነን ችግሩ ወዳጋጠመበት ቦታ መሄድ ያለብን፡፡ በአንድ ቦታ ግጭት ሲያጋጥም 'ወገኖቼ ይሞታሉ' በሚል መሸበር ይኖራል፡፡ በተለይ በዚያ ወቅት ስነ ልቦናዊ ድጋፍ ካልተገኘ ችግሩ ይብሳል።
ስለዚህ አዕምሮ ጤናም ጉዳይ ሌሎች እርዳታዎች ጋር አብሮ መሄድ አለበት፡፡ በግንዛቤ እጥረት በትራንስፖርትና በሌሎች ምክንያቶች ሰዎች ወደ ህክምና ላይመጡ ይችላሉ፡፡ ስነልቦናዊና ማኀበራዊ ድጋፉን በዚያው ማቅረብ ያስፈልጋል፣ የታመሙ ከሆኑም እኛ መሄድ አለብን።
በሌላ በኩል፣ ሰዎች ድባቴ ውስጥ በሚገቡበት ወቅት ከሚያወቋቸው ሰዎች ጋር ጊዜ ቢያሳልፉ፣ ችግራቸውን ቢወያዩ ለአዕምሮ ህመም የመጋለጥ ሁኔታው ይቀንሳል።
የሆስፒታሉ ተመላላሽ ህክምና ክፍል ኃላፊስ ምን አሉ ?
የሆስፒታሉ የተመላላሽ ህክምና ክፍል ኃላፊ ሳሙኤል ቶለሳ፣ የዘንድሮው የአዕምሮ ጤና ቀን " በድንገተኛ አደጋዎችና ሰብዓዊ ቀውስ ወቅት የአዕምሮ ጤና አገልግሎት ተደራሽነት ምን ይመስላል ? " የሚለው ላይ እንዳተኮረ ገልጸዋል።
" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የእርስበርስ ግጭቶች አሉ፣ ያን ተከትሎ የሚመጡ ማኅበራዊ ቀውሶች አሉ " ያሉት ኃላፊው፣ በዚህም የተደራሽነት ውስነት መኖሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡
" በተለያዩ ክልሎች ያለው ቀውስ ራሱን የቻለ ተፅዕኖ አለው፣ ተማሪዎች እንዳይማሩ የማድረግ ሂደቶች አሉ " ብለው፣ ሰዎች ቀጥተኛ የጦርነቱ ተጠቂ ሲሆኑና የሚያስጨንቁ ነገሮች ሲፈጠሩ ለአዕምሮ ህመም ተጋላጭነታቸው እያደገ እንደሚመጣ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ደሴ
“ ህይወቷ በማለፉ አዝነናል ነገር ግን ተማሪዋ የደሴ ካምፓስ ተማሪ አይደለችም ” - ወሎ ዩኒቨርሲቲ
➡️ “ የምርመራ ኬዝ ስለሆነ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል ” - ጉዳዩን የሚከታተሉት ኢንስፔተክር
ተማሪ ሊዛ ደሳለ የተባለች ወጣት ሰሞኑን በደሴ ከተማ “ የአስገድዶ መድፈርና ግድያ ጥቃት ተፈጽሞባት ” መገኘቷ ተሰምቷል፡፡
መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ወጣቷ መስከረም 27 ቀን 2018 ዓ/ም ስልኳን ለማሰራት በደሴ ከተማ ወደ ፒያሳ በወጣችበት አልተመለሰችም፡፡
ይህን ተከትሎ ፍለጋ ሲደረግ ግን “ተደፍራና ተገድላ ተገኝታለች” የተባለ ሲሆን፣ “ፍትህ ለተማሪ ሊዛ” የሚል ጥያቄዎች ኢንተርኔቱን አጨናንቀውታል።
ወጣቷ “ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ናት ” የሚሉ መረጃዎች መሰራጨታቸውን ተከትሎ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ የጠየቃቸው አንድ የዩኒቨርሲቲው አካል ጉዳዩን አጣርተው በሰጡት ምላሽ፣ “ የተማሪዎች አገልግሎት ጋር ደውየ ነበር፤ 'እንዲህ አይነት ነገር እኛ አልተከሰተም፡፡ ተከሰተ የሚባለውም ከወይዘሮ ስህን ኮሌጅ ነው' ” እንዳሏቸው ገልጸዋል፡፡
እኝሁ የዩኒቨርሲቲው አካል፣ “የደሴ ካምፓስ ተማሪ አይደለችም፡፡ የወይዘሮ ስህን ኮሌጅ ተማሪ ናት፡፡ የኛ ተማሪ አለመሆኗን አሁን ከተማሪ አገልግሎት ደውዬ አጣርቻለሁ ” ሲሉም አክለዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በማህበራዊ ሚዲያ ስሙ በሀሰት መነሳቱን ገልጾ ይህን ባደረጉት ላይ ተጠያቂነት እንደሚከተል ገልጿል።
በሊዛ ደሳለ ሞት ማዘኑንም ገልጾ ለወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን ተመኝቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የተማሪዋን ቤተሰቦች ለማግኘት ያደረገው ጥረት ባይሳከለትም፣ ከቆቦ ከተማ ነዋሪዎች ባደረገው ማጣራት ግን ተማሪ ሊዛ ደሳለ በሰሜን ወሎ ዞን የራያ ቆቦ ወረዳ ቆቦ ከተማ ታዲጊ መሆኗን ለማወቅ ችሏል፡፡
የወይዘሮ ስህን ኮሌጅ ኃላፊዎችን ፣ የደሴ ከተማ ፓሊስን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም።
የደሴ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ነስረዲን ኃይሌ፣ " መድረክ እየመራሁ ነው " በማለታቸው ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም። ኃላፊው ቆየተው በላኩት የፅሑፍ መልዕክት ዝርዝር መረጃ ይሰጧችኋል ሲሉ ኮማንደር ሰይድ የሚባሉ አካል ጠቁመዋል።
" ጉዳዩን ተከታትለውታል " የተባሉት ኮማንደር ሰይድ አሊ ምላሽ ብንጠይቃቸውም፣ “ እኔ አልሰጥም፤ ፖሊስ ነው መግለጫ የሚሰጠው፤ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊው ናቸው የሚሰጡት ” ብለዋል።
“ የምርመራ ኬዝ ስለሆነ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል ” ያሉት እኝሁ አካል፣ የምርመራውን ሂደት ሳይሆን የግድያውንና ሁነት እንዲያስረዱ ስንጠይቃቸው ማብራሪያ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthioiaFamilyAA
@tikvahethiopia
በአፍሪካዊቷ ሀገር #ማዳጋስካር 🇲🇬 የሆነው ምንድነው ?
(በአጭሩ)
- ከ15 ቀን ገደማ በፊት የማዳጋስካር ወጣቶች የመሩት ተቃውሞ ይቀሰቀሳል። ይኸው ተቃውሞው በዋና ከተማዋ አንታናናሪቮ ካለ የኃይል መቆራረጥ እና የውሃ እጥረት ጋር የሚያያዝ ነበር። የወጣቶቹ ተቃውሞ ' Gen Z Madagascar ' የሚል ስያሜ ነበረው።
- በኃላ የወጣቶቹ ተቃውሞ ቁጣ የታከለበትና መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን፣ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ፣ ሙስና እንዲያበቃ ፣ የዜጎች ህይወት እንዲሻሻል ወደመጠየቅ ተሸጋገረ።
- የመንግሥት ምላሽ የነበረው ሰልፈኞችን በአስለቃሽ ጭስ መበተን፣ የሰዓት እላፊ መጣል፣ ሰልፈኞች ላይ መተኮስ ሆነ። በተቃውሞ 22 ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች በርካቶች ተጎድተዋል።
- የሀገሪቱ ፕሬዚደንት አንድሪ ራጆኤሊና መንግስታቸውን በትነው ወታደራዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ሾሙ፣ ጄነራል ሩፊን ፎርቱናት የሚባሉ። ግን አለመረጋጋቱ ለሚቆም አልቻለም።
- አንድ የማዳጋስካር የጦር ክንፍ ተቃዋሚዎችን ተቀላቀቀለ። ከፕሬዜዳንቱ ትእዛዝ ማቀበል አቆመ። ይኸው ኃይል ወደ ተቃዋሚዎች ምንም እንዳይተኮስ አዘዘ። ፕሬዚዳንቱም ሁኔታውን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እንደሆነ ገለጹ።
- ፕሬዝዳንቱ አሁን ላይ የት እንዳሉ ባይታወቅም ፤ አንዳንድ ሪፖርቶች ግን በፈረንሳይ ወታደራዊ አውሮፕላን በሞሪሺየስ አድርገው ወደ ዱባይ ሄደዋል ብለዋል።
- ዛሬ ምሽት 1:00 ላይ ማብራሪያ እንደሚሰጡ የፕሬዜዳንት ፅ/ቤታቸው ቢያሳውቅም የታጠቁ ወታደሮች የሀገሪቱን ሚዲያ ዋና መስሪያ ቤት ለመቆጣጠር መዛታቸውን ተከትሎ ፕሬዝዳንቱ የሚሰጡት ማብራሪያ እንዲራዘም ሆኗል።
መረጃው ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የተሰባሰበ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia
ስድስተኛው ዙር የበሽ ሽልማት ስነ-ስርዓት በደሴ ከተማ የተከናወነ ሲሆን የ1,000,000 ብር አሸናፊ ሽልማታቸዉን ተቀብለዋል። እንኳን ደስ አላችሁ!
ዛሬ ነገ ሳይሉ እድልዎን ይሞክሩ! ቀጣይ ዕድለኛ እርስዎ ይሆኑ ይሆናል!
📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ። https://onelink.to/ewsb22
ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ!
#besh
#HappyNewYear
#furtheraheadtogether
ቪድዮ ፦ እስራኤል እና ሃማስ ባደረጉት የተኩስ አቁም ስምምነት እስራኤል የፍልስጤም እስረኞችን ከእስር እየፈታች ትገኛለች።
ከእስር የተፈቱትን ፍልሴጤማውያንን በርካቶች ተሰብስበው በደስታ እያቀፉ እየተቀበሏቸው ነው።
ሃማስ በተመሳሳይ በህይወት የተረፉ 20 ታጋቾችን ለቋል። እስራኤልም ታጋቾች ስለመለቀቃቸው ማረጋገጫ ሰጥታለች።
#Peace🕊
Video Credit - Al Jazeera
@tikvahethiopia
#Peace🕊
" በጋዛ ጦርነቱ አክትሟል " - ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ
ከ2 ዓመት በፊት መስከረም 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ሐማስ በምዕራብ እስራኤል ድንገተኛ ጥቃት ፈጽሞ 1,200 ሰዎችን ከገደለ እና 251 አግቶ ከወሰደ በኋላ እስራኤል በጋዛ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ አካሄዳለች።
በዚህ ወታደራዊ ዘመቻም 67,000 ፍልስጤማውያን ሲገደሉ ከእነዚህ መካከልም 18,000 ያህሉ ሕጻናት መሆናቸውን በሐማስ የሚመራው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
አስከፊው ጦርነት እንዲቆም ብዙ ጥረት ቢደረግም ፍሬ ሳያፈራ ቆይቷል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡ በኃላ ከሌሎች ሀገራት ጋር ሆነው ብዙ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተው እስራኤል እና ሐማስ ከቀናት በፊት የተኩስ አቁም ስምምነት አድርገዋል ፤ ጋዛም እፎይ ብላለች።
በመጀመሪያው ስምምነት መሰረት ሀማስ ያገታቸውን እስራኤላውያን ይለቃል እስራኤልም አጉራ ያሰረቻቸውን ፍልስጤማውያንን ትለቃለች።
ዛሬ እስራኤላውያን ታጋቾች በሀማስ ተለቀው ለቀይ መስቀል ተሰጥተዋል።
ቀጣዩ ፈተና ምን ይሁን ?
ቀጣይ የሰላም ዕቅዱ ላይ ድርድር የሚደረግባቸው ፦
➡️ ጋዛ ማን ያስተዳድር ?
➡️ የእስራኤል ወታደሮች አካባቢውን ለቅው ይውጡ፤
➡️ የሐማስ ትጥቅ መፍታት የሚሉት ከስምምነት ለመድረስ አስቸጋሪ ነጥቦች ይሆናሉ ተብሎ ይጠበዋል።
በሌላ በኩል ፤ ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል ገብተዋል። ቴላቪቭ ሲደርሱ የእስራኤል ጠ/ሚ ቤኒያሚን ኔታንያሁ ተቀብለዋቸዋል።
ትራምፕ እስራኤል ለመሄድ ወደ ኤርፎርስ ዋን አውሮፕላን እየተሳፈሩ እያለ የተኩስ አቁሙ እንደሚፀና እና በጋዛ በፍጥነት " የሰላም ቦርድ " እንደሚቋቋም ተናግረዋል።
ለአሁኑ ስምምነት ኳታርም ላደረገችው አስተዋፅኦ አመስገነዋል።
" በጋዛ ጦርነቱ አክትሟል " ሲሉም ተደምጠዋል።
ትራምፕ ጋዛን ይጎበኙ እንደሆነ ሲጠየቁ፣ ቢያደርጉት ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
" ቢያንስ እግሬ ቢረግጥ ደስ ይለኛል " ብለዋል። በሚቀጥሉት አስርት ዓመታት ውስጥ ጋዛ " ተአምር " ትሆናለች ብለው እንደሚያስቡ ተናግረዋል።
መረጃው የቢቢሲ ነው።
@tikvahethiopia
#እንድታውቁት
ከነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በከፊል ዝግ ሆነው የቆዩት የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከሰኞ ጥቅምት 3/2018 ዓ/ም ጀምሮ መደበኛ አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ።
የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች የሚሰጡት የዳኝነት አገልግሎት ክብደትና ዉስብስብነትን ግምት ውስጥ በማስገባት በቂ እረፍት እንደሚያስፈልጋቸው ታምኖበት በየዓመቱ መጨረሻ ለተከታታይ ለሁለት ወራት ማለትም ከነሐሴ 01 እስከ መስከረም 30 በከፊል ዝግ እንደሚሆኑ ይታወቃል።
ፍርድ ቤቶቹ በከፊል ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው የሁለት ወራት ጊዜ በባህሪያቸዉ አስቸኳይ የሆኑና ጊዜ የማይሰጡ እንዲሁም ለዉሳኔ የደረሱ መዛግብትን መርምረው ውሣኔ የመስጠት አገልግሎቶች ቀጥለው ቆይተዋል።
በከፊል ዝግ ሆነው የቆዩት ፍርድ ቤቶች ከሰኞ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓም ጀምሮ መደበኛ አገልግሎታቸውን መስጠት እንደሚጀምሩ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አሳውቋል።
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አድራሻም ቀድሞ ከነበረበት አድራሻ በመቀየር ከአብረሆት ቤተ መጸሕፍት 100 ሜትር ዝቅ ብሎ ፍርድ ቤቱ አዲስ እያስገነባ ባለው ህንጻ ውስጥ የሚጀምር መሆኑን ገልጿል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Tigray
ጥቅምት 1/2018 ዓ.ም የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት በትግራክ 6 የመኖሪያ ቤቶች አፈረሰ።
የመሬት ንዝረቱ ዛሬም ተከስቷል።
በትግራይ ክልል ከምስራቃዊ ኣፅቢ ወምበርታ ወረዳ 26 ኪ/ሜ ርቀት ላይ የተከሰተው በሬክተር ስኬል 5.6 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ በቃል ኣሚን ቀበሌ ገበሬ ማህበር ቡሐለ መንደር 6 ቤቶች በከፊል እንደፈረሱ ወረዳው አሳውቋል።
እንደ ትናንትናው ከበድ ባይሆንም ዛሬ ጥቅምት 2/2018 ዓ.ም የመሬት ንዝረቱ በተወሰነ መልኩ መቀጠሉ የገለፀው የወረዳው አስተዳደር በሰው ፣ በእንስሳትና በንብረት ያስከተለው አደጋ እንደሌለ ገልጿል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
" የ12 ዓመት ህጻን ልጅ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል የፈፀመው የ65 ዓመት አዛዉንት የ23 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል " - የይርጋለም ከተማ ፖሊስ
➡️ " ግለሰቡ የኤችአይቪ/ኤድስ ታማሚና የመድሐኒት ተጠቃሚ ነበር "
በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን የይርጋለም ከተማ አስተዳደር የ12 ዓመት ህጻን ልጅ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል የፈጸመው የ65 ዓመት ግለሰብ የ23 ዓመት እስራት ተፈርዶበታል።
የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ደግነት ደስታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ፥ የከተማው ነዋሪ የሆነ አቶ ናስር ኑር የተባለ የ65 ዓመት ግለሰብ ነሐሴ 6/12/2017 ዓ.ም በከተማው 06 ቀበሌ የ12 አመት ታዳጊ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት መፈጸሙን የሚገለፅ መረጃ ለፖሊስ ይመጣል።
ፖሊስም ጉዳዩን ከፍትህ መዋቅር ጋር በመመርመር በሰውና በህክምና ማስረጃ በማጣራት ለከተማው ዐቃቤ ህግ አስተላልፏል።
በምርመራና መረጃ በማሰባሰብ ሂደትም ግለሰቡ ይህን አስነዋሪ ድርጊት ከመፈፀሙ ባሻገር የኤችአይቪ /ኤድስ (HIV/AIDS) ታማሚና እንደሆነና እራሱን አውቆ የመድሐኒት ተጠቃሚ እንደነበር ማወቅ መቻሉን አዛዡ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ጉዳዩን የያዘዉ የይርጋለም ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ህግ በተከሳሹ ላይ ያቀረበውን የክስ መዝገብ ሲያጣራ የቆየው የከተማ አስተዳደር መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተከሳሹን " ጥፋተኛ ነህ " በማለት ተከሳሹ እንዲከላከል ቢጠይቅም መከላከል አልቻለም።
እንዲሁም የኤችአይቪ/ኤድስ ታማሚ መሆኑን እያወቀ በታዳጊዋ ላይ በፈፀመው አስነዋሪ ድርጊት ጥፋቱን በማክበድ በቀን 4/2/2018 በዋለው ወንጀል ችሎት ተከሳሹን በ23 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
#Kenya
የኬንያው ጉምቱ ፖለቲከኛ ራይላ ኦዲንጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ህንድ ሀገር በህክምና ሲረዱ ቆይተው በ80 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ራይላ ኦዲንጋ ለኬንያ ፕሬዚዳንትነት 5 ጊዜ ዕጩ ሆነው ቢቀርቡም አልተሳካላቸውም።
በተጨማሪ በቅርቡ ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት ቦታ ቢወዳደሩም ማሸነፍ ሳይችሉ ቀርተዋል።
ለረጅም አመታት በፖለቲካ ውስጥ የቆዩት ኦዲንጋ በኬንያ የበዛ ድጋፍ ያላቸው ሲሆን የኦሬንጅ ዴሞክራቲክ ሙቭመንት መሪ ነበሩ።
ለዴሞክራሲ፣ ለመድብለ ፓርቲ ስርዓት፣ ከህገመንግስት ሪፎርም በመታገል ይታወቃል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በራይላ ኦዲንጋ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ገልጸዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Haile
“ በየቦታው የሰራናቸውን ሆቴሎች አይነት አንዷን ድሬዳዋ እናስቀምጣለን ብለን አቅደናል” - ሻለቃ ኃይሌ
➡️ “ደብረ ብርሃን ሆቴል የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ነው፤ በቀጣዮቹ ሦስት፣ አራት ወራት ወደ ሥራ ይገባል” - አቶ ጋዲሳ ግርማ
አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ በሆቴልና ሪዞርት ግንባታ ረገድ ወደ ድሬዳዋ ከተማ እየገቡ መሆኑን፣ የከተማዋን ከንቲባና ካቢኔውን አግኝተውም ቃል እንደተገባላቸው ዛሬ ገልጸዋል፡፡
የኃይሌ ሆቴሎች ሪዞርቶች ግሩፕ ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ጋዲሳ ግርማ በበኩላቸው፣ ድሬዳዋ ላይ የሆቴልና ሪዞት ግንባታ በቅርቡ እንደሚጀመር ዛሬ ምሽት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል፡፡
ሻለቃ ኃይሌ፣ በድሬ ከተማ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፣ “ኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በየከተማዎቹ እየገነባን ነን፡፡ እስካሁን በአስር ከተሞች ተከፍተዋል፡፡ ሌላ ሦስት ደግሞ በግንባታ ላይ ናቸው፡፡ አሁን ደግሞ የድሬው 14ኛው ይሆናል” ብለዋል፡፡
“መምጣት ካለብን በጣም የዘገየንበት ቦታ ነው፡፡ ግን አሁን ድሬዳዋ እየገባን ነው፤ ክቡር ከንቲባውንም ካቢኔውንም አግኝተን በጣም ጥሩ ቃል ገብተውልናል” ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ሥራው ቶሎ እንደሚጀመር ጠቁመው፣ “በየቦታው የሰራናቸውን ሆቴሎች አይነት አንዷን ድሬዳዋ እናስቀምጣለን ብለን አቅደናል፡፡ መጀመሪያ ስናጠና ቢዝነሱ እንዴት ነው ? የሚለውን ነው፤ ድሬዳዋም ከኢትዮጵያ ቀደምት ከተሞች አንዷ ነች፤ በቢዝነሱም” ነው ያሉት፡፡
ስለድሬዳዋው ሆቴል ግንባታ ተጨማሪ ማብራሪያ የጠየቅናቸው የኃይሌ ሆቴሎች ሪዞርቶች ግሩፕ ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ጋዲሳ ግርማ፣ “የቦታ ልየታና ገበያውን ለማየት ሂደን ነበር ዛሬ፡፡ ኢንቨስትመንት ላይ የሚሰሩ የመንግስት አካላት ቦታዎችን አሳይተውናል፤ ወደ ቀጣዩ ሂደት እንቀጥላለን” ብለዋል፡፡
ግንባታውን በቅርቡ የመጀመር እቅድ እንዳላቸው፣ በዚህ ቀን ይጀመራል የሚል ቀን ገና እንዳላስቀመጡ ገልጸው፣ “የመሬት ርክክብ ባለቀ በማግስቱ ግንባታ እንጀምራለን” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡
የጎንደርና ደብረ ብርሃን ፕሮጀክቶችን እያጠናቀቁ በመሆኑ ቀጣዩ አቅጣጫ ወደ ድሬ እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ጋዲሳ፣ “ደብረ ብርሃን ሆቴል የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ነው ያለው፤ በቀጣዮቹ ሦስት አራት ወራት ውስጥ ወደ ሥራ ይገባል፡፡ የጎንደር ደግሞ ከሰባት ውራት እስከ አንድ አመት ይወስዳል” ብለዋል፡፡
በጎንደሩ ፕሮጀክት የጸጥታው ሁኔታ ምን አይነት እንቅፋት እንዳፈጠረባቸው ማብራሪያ ሲጠየቁም፣ በዚህ ረገድ አስተያየት አለመስጠትን መርጠዋል፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#MoE
" ውጤት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል " - ትምህርት ሚኒስቴር
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሲሰጥ የነበረው የ2018 የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና መጠናቀቁን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
ፈተናው ለመውሰድ ከተመዘገቡ 29 ሺ491 አመልካቾች መካከል 96 በመቶ ፈተናውን እንደወሰዱ አመልክቷል።
በ2017 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ይሰጥ የነበረው የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና በተለያዩ ምክንያቶች ተራዝሞ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. በ53 የፈተና ማዕከላት ነው የተሰጠው።
የፈተናው ውጤትም በቅርቡ ለተማሪዎች ይፋ እንደሚደረግ ሚኒስቴሩ አመልክቷል።
የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና (NGAT) ከሌሎች አገር አቀፍ ፈተናዎች የተለየና የ2ኛ እና የ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን መቀጠል የሚፈልጉ አመልካቾች ለትምህርቱ ምን ያክል ዝግጁ ናቸው የሚለውን ለማረጋገጥ ደረጃውን ጠብቆ የሚሰጥ ምዘና ነው።
#DrEbaMijena
መረጃው የትምህርት ሚኒስቴር ነው።
@tikvahethiopia
ደንበኛዎትን በቀላሉ ካሉበት ለመድረስ የሚያስችልዎትን የዲጂታል ሱቅ በዘመን ገበያ ላይ አሁኑኑ ይክፈቱ፣ ተደራሽነትዎን ያስፉ።
የበለጠ መረጃ ለማግኘት 3131 ላይ ይደውሉ!
ዘመን ገበያ የዲጂታል ኢትዮጵያ የግብይት መዳረሻ!
#ZemenGEBEYA
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#ETHIOPIA🇪🇹
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባዉ የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ማቋቋሚያ ደንብን መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጸደቀ።
ይህ ደንብ በነጋሪት ጋዜጣ በይፋ ታትሞ ከወጣ በኋላ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን፣ ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ልማት የመጠቀም ጥረቷን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግር ይጠበቃል።
ኮሚሽኑ በዓለም አቀፍ ማዕቀፎች መሰረት የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ዓላማዎች የመጠቀም ሀገራዊ ጥረትን የመምራትና የማስተባበር ዋነኛ ኃላፊነት ይኖረዋል ተብሏል።
ትኩረት አድርጎ የሚሠራባቸው ቁልፍ ዘርፎችም የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት፣ የኢንዱስትሪ ልማት፣ የምግብ ዋስትና፣ የጤና አገልግሎት እንዲሁም ሳይንስና ምርምር መሆናቸው ተመላክቷል።
በሌላ በኩል ፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ አቶ ሳንዶካን ደበበ የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርገው ሾመዋል።
@tikvahethiopia
📣 𝐉𝐢𝐦𝐦𝐚 𝐔𝐧𝐢𝐯𝐞𝐫𝐬𝐢𝐭𝐲 𝐢𝐬 𝐍𝐨𝐰 𝐢𝐧 𝐭𝐡𝐞 𝐂𝐢𝐭𝐲!
Registration is officially 𝐎𝐏𝐄𝐍 for our selected undergraduate programs at the JU-ABH Campus in Addis Ababa. Your opportunity to earn a prestigious degree has arrived!
𝐎𝐮𝐫 𝐏𝐫𝐨𝐠𝐫𝐚𝐦𝐬
1. BA degree in Accounting & Finance 💰
2. BA degree in Management 💼
3. BSc degree in Computer Science 💻
4. Bachelor of Laws (LLB) ⚖️
𝐑𝐞𝐚𝐝𝐲 𝐭𝐨 𝐀𝐩𝐩𝐥𝐲?
Visit www.allianceacademy.edu.et/degree-program
𝐐𝐮𝐞𝐬𝐭𝐢𝐨𝐧𝐬? We are ready to assist!
📞 +251978464748 / +251979464748
𝐂𝐨𝐧𝐧𝐞𝐜𝐭 𝐰𝐢𝐭𝐡 𝐮𝐬
LinkedIn|Telegram |Facebook |Twitter/X |Instagram |abhpartners?_t=ZM-8v20SoqXLSZ&_r=1">TikTok ABHPartnersOfficial">|YouTube |abhpartnersofficial">Threads
#ኢትዮጵያ🇪🇹
" አያሰማን ፍጹም ያንቺን ክፉ
ኢትዮጵያ
ጠባቂሽ ነው ህዝብሽ እልፍ አእላፉ
ላንቺ ክብር
ላንቺ ክብር ሞትን የማይፈሩ
ኢትዮጵያ
ልጆች አሉሽ ዛሬም የሚያኮሩ
🇪🇹
አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ሰንደቅሽ
አልብሽን አንድ ላይ ልጆቼ ብለሽ፤
አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ሰንደቅሽ
ሰላም ፣ ልምላሜ ፣ ጸጋ ያልብስሽ። "
#ኢትዮጵያ #ETHIOPIA
@tikvahethiopia
" ዘንድሮ ኮሪደር ብለን እንደ አዲስ የምንጀምረው አይኖርም፤ ...ትልቁ ትኩረት የቤት ግንባታ እና የውሃ አቅርቦት ነው " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በዘንድሮው ዓመት 2018 በአዲስ አበባ ከተማ " የኮሪደር ስራ " ተብሎ እንደ አዲስ የሚጀመር ስራ እንደማይኖር ፤ የዘንድሮ ትኩረት ቤቶችን መገንባት እና የውሃ አቅርቦትን ማሻሻል እንደሆነ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ይህን ያሉት ለአዲስ አበባ ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ነው።
በማብራሪያቸው እስካሁን በኮሪደር ስራ የተገኙ ውጤቶች ከከተማው ስፋት አንጻር ገና እንደሆነ ገልጸዋል።
ስራዎቹ የተሰሩት ታቅዶባቸው፣ የበጀት ዝግጅት ተደርጎ፣ ቤቶች ተዘጋጅተው ፣ የበጀት ቅደም ተከተል ተስተካክሎ መሆኑን አንስተዋል ፤ ስራው ሰፊ ዝግጅት የሚፈልግ እንደሆነም አመልክተዋል።
በዚህም በዘንድሮ ዓመት 2018 በከተማው ' የኮሪደር ስራ ' ተብሎ እንደ አዲስ የሚጀመር ነገር እንደማይኖር አሳውቀዋል።
" የ2018 ትልቁ ትኩረት የቤት ግንባታና የውሃ አቅርቦት ነው ብለን አፀድቀናል ምክር ቤቱን " ያሉት ከንቲባ አዳነች " ዘንድሮ ዋናውና ትልቁ ትኩረታችን የመኖሪ ቤት ግንባታ ይሆናል ብለዋል።
ይህም ቢሆን ግን ስታንዳርዳቸውን መጠበቅ ያለባቸው የከተማው መንገዶች እንደሚሰሩ ፣ እንደሚታደሱ አመልክተዋል።
እነዚህ መንገዶች የትራፊክ ፍሰቱን የሚያስተካክሉ፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸው፣ ህዝብ የጠየቃቸው መንገዶች እንደሆኑ ተናግረዋል።
የመንገዶቹ ስራ ሲሰራም የኮሪደር ልማት ስታንዳርድን እንደሚከተሉ ገልጸዋል።
- የተሽከርካሪ መንገዶች ስራና እድሳት
- የተሽከርካሪ መንገዶች ማስፋት ስራ
- የእግረኛ መንገዶች ስራ
- የሳይክል መንገዶች ስራ እንደሚኖር ጠቁመዋል።
" ሁሉንም በአንዴ መጀመር አንችልም። አሁን ላይ አጥንተን የጨረስነው ከዑራኤል - ቦሌ ብራስ VIP የሚገናኘው ነው እሱ እየተሰራ ነው። በፍጥነት ካልሰራነው ቢዝነስ ላይ ተፅእኖ ያሳድራል ፣ በአካባቢው ላይ የትራፊክ ፍሰቱ ላይ ጫና ያሳድራል ለዛም የጀመርነውን በፍጥነት እየጨረስን ነው ሌላ የምንጀምረው " ብለዋል።
" በዚህ አመት ኮሪደር ብለን እንደ አዲስ የምንጀምረው አይኖርም፤ ጥናት እናደርጋለን ቤቶችን እንገነባለን፣ ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል በተባሉት ላይ ከህዝብ ጋር ውይይት እናደርጋለን ፣ ተግባቦት እንፈጥራለን " ሲሉ አስረድተዋል።
የመንገድ ግንባታዎች ግን ፦
- ቀድሞ የተጠየቁ፣
- የተጀመሩ ፣
- ከልማት ተነሺዎች ጋር ችግሮች ገጥመዋቸው የነበሩ በራስ ኃይል መሰራታቸውን እንደሚቀጥሉ አሳውቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Update
" ሰላምን እንሻለን ! " - የትግራይ ኃይል አባላት
➡️ " የኛን ጥያቄ መመለስ ከማይችል አመራር የሌላው ህዝብ ጥያቄ ሊመልስ አይችልም ! "
የትግራይ ኃይል አባላት ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:30 ጀምረው የመብት ጥያቄ አንስተው በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።
ሰልፈኛቹ ቁጣን ባዘለ ድምፅ ፦
- " የደመወዝና ጥቅማጥቅም ጥያቄያችን ይመለስ ! "
- " የሰራዊት ጥያቄ የማይመልስ አመራር የሌላው ህዝብ ጥያቄ መመለስ አይችልም ! "
- " የሰራዊት ድምፅ ይሰማ ! "
- " ሰላምን እንሻለን ! "
- " ክብር ለሰራዊትና ለተሰው ቤተሰብ አባላት ! "
የሚሉና ሌሎች መፈክሮች አሰምተዋል።
ሰላማዊ ሰልፈኞቹ መፈክራቸው እያሰሙ ወደ ትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የፕሬዜዳንት ፅህፈት ቢያመሩም ፕሬዜዳንቱ ማግኘት አልቻሉም።
ጥያቄያቸው ስምቶ መልስ የሚሰጥ ሃላፊ በማጣታቸው የተቆጡት ሰልፈኛቹ ከቀኑ 7:00 እስከ 11:00 ከመቐለ ወደ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ የሚወስደው ዋናው የመኪና መንገድ በድንጋይና በአካል ዘግተውት ውለዋል።
ይህንን መረጃ ከተዘጋጀበት ጥቂት ደቂቃዎች በፊት የሰላማዊ ሰልፈኞቹ ተወካዮቹ ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ለውይይት መቀመጣቸው ተከትሎ የተዘጋው መንገድ መከፈቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አረጋግጧል።
በተጀመረው ውይይት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) መገኘታቸውና አለመገኘታቸው ማረጋገጥ አልቻልንም።
የውይይቱን ውጤት ተከታትለን እናቀርባለን።
#Update - በአሁኑ ሰዓት የሰላማዊ ሰልፈኞቹ ተወካዮች የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) ከሚገኙባቸው ከፍተኛ ወታደራዊና የስቪል አመራሮች በመነጋገር ላይ ይገኛሉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
የዓቃቢያን ሕግ የደመወዝ ማስተካከያ ለየክልሎቹ ዛሬ መላኩን የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) አሳውቀዋል።
@tikvahethiopia
#Tigray
በጦርነት ላይ ተሳታፊ የነበሩ የትግራይ ኃይል አባላት በዛሬው ቀንና በአሁኑ ሰዓት በመቐለ ዋና ዋና መንገዶች የመብት ጥያቄ አንስተው ሰላማዊ ሰልፍ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።
አባላቱ ከሚያሰሙት መፈክር የደመወዝ ጭማሪ እና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎልቶ ተደምጧል።
ሰላማዊ ሰልፈኞቹ በአሁኑ ሰዓት ወደ ትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የፕሬዜዳንት ፅ/ቤት በማምራት ላይ ይገኛሉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ጉዳዩን ተከታትሎ ተጨማሪ መረጃ ያደርሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
ቪድዮ ፦ አብርሃ ገብረአረጋዊ
@tikvahethiopia
#ሓሸንገ_ሃይቅ
🕯ዩኒቨርሲቲ ሊገባ የመግቢያ ቀኑን እየተጠባበቀ የነበረው ተማሪ ለሽርሽር በወጣበት ሓሸንገ ሃይቅ ላይ ህይወቱ አለፈ።
በኦፍላ ሓሸንገ ሃይቅ ምንድነው ያጋጠመው?
ተማሪ ልኡል ገ/ኪዳን በትግራይ ደቡባዊ ዞን ኮረም ከተማ አሉ ከሚባሉ ብርቱ ተማሪዎች አንዱ ነው።
በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ከፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈትኖ 430 ነጥብ በማምጣት ጅማ ዩኒቨርሲቲ ደርሶት ለመግባት ቅድመ ዝግጅቱ አጠናቆ በመጠባበቅ ላይ ነበር።
ጅማ ዩኒቨርስቲ የሚገባበት ቀነ ቀጠሮ ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ.ም መሆኑን የተገነዘቡት ጓደኞቹ የመሸኛ ሽርሽር ዛሬ እሁድ ጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በሓሸንገ ሃይቅ አዘጋጁለት።
ሆኖም ዝግጅቱ ተጨናገፈ ፤ ባለራዕዩ ተማሪ ልኡል ገ/ኪዳን ሓሸንገ ሀይቅ ላይ ህይወቱ አለፈ።
የተማሪ ልኡል ገ/ኪዳን አስከሬን ከብዙ ፍለጋ በኃላ ዛሬ ከቀኑ 11:30 ተገኝቷል።
የተማሪ ልኡል ገ/ኪዳን የቀብር ስነ-ስርዓት ነገ ሰኞ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም በኮረም ከተማ ይፈፀማል።
መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
" አደጋው ከባድ በመሆኑ የተጎጂዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል " - ፖሊስ
በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በአርጡማ ፋርሲ ወረዳ በጃራ ቀበሌ በተከሰተ በትራፊክ አደጋ እስካሁን ባለው 11 ሰዎዥ ህይወታቸው አልፏል።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዛዥ እንስፔክተር ኡመር መሀመድ አደጋው የደረሰው በጨፋ ሮቢት ከተማ ልዩ ስሙ ' ጃራ ' ድልድይ አከባቢ መሆኑን ገልጸዋል።
ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኢት 73290 የሆነ ታታ አውቶቡስ እና ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኢት 41157 ተሳቢ መኪና ተጋጭተው አደጋው መድረሱን ገልጸዋል።
እስካሁን ባለው መረጃ 8 ወንድ 3 ሴት ባጠቃላይ 11 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 23 ሰዎች ደግሞ ከባድ እና ቀላል ጉዳት እንደረሰባቸው ተናግረዋል።
አደጋው ከባድ በመሆኑ የተጎጂዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ብለዋል።
@tikvahethiopia
#Afar
በአፋር ክልል ሰሜናዊ ዞን በባራሕሌ ወረዳ ትናንት ምሽት በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ እድሜው 12 ዓመት የሆነ ልጅ ህይወት ሲያልፍ 6 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።
የሰሜናዊ ዞን አስተዳደር የመሬት መንቀጥቀጡ በዞኑ ባራሕሌ፣ ኮናባ እና ዳሎል ወረዳዎች መከሰቱን አሳውቋል።
በዚህም የ12 ዓመት ልጅ ህይወቱ ሲያልፍ 6 ሰዎች ተጎድተዋል።
በቡሬ እና ዓስጉቢ ቀበሌዎች በርካታ ቤቶች ፈርሰዋል።
በመሬት መንቀጥቀጡ 43 ሺህ 456 የሚሆኑ ሰዎች ቤታቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙንና ያለመጠለያ ቀርተዋል።
ለተጎጂዎች ድጋፍ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ዞኑ ለኤፍ ኤም ሲ ገልጿል። #ኤፍኤምሲ
@tikvahethiopia