tikvahethiopia | Unsorted

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1532594

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Subscribe to a channel

TIKVAH-ETHIOPIA

እንጀራ እና ዳቦ በሸቀጣ ሸቀጦች ሱቅ መሸጥ መከልከሉ ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣንን የተለያዩ ሸቀጣሸቀጦች በሚሸጡባቸው ሱቆች ውስጥ እንጀራ እና ዳቦ መሸጥ መከልከሉን አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘግቧል።

ባለስልጣን መ/ቤቱ የተለያዩ መርዛማ ነገሮች ፦
- ሳሙና
- በረኪና
- ፍሊት
- የአይጥ መርዝ
- የፅዳት ኬሚካሎች እና ሌሎችም ለጤና ጠንቅ የሆኑ ሸቀጦች በሚሸጡባቸው ሱቆች በቀጥታ ለምግብነት የሚውሉትን እንጀራ እና ዳቦን መሸጥ ልክ እንዳልሆነ በመግለፅ ይህ ክልከላ መወሰኑን ገልጿል።

ክልከላው የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ ሲባል የተወሰነ እንደሆነ አመልክቷል።

እንጀራ እና ዳቦ መሸጥ ያለባቸው በምግብ ቤቶች፣ በዳቦ ቤተች እና በባልትና ወይም ለዚሁ መሻጫነት በተፈቀደ ቦታ ብቻ መሆኑን አሳውቋል።

እንጀራ እና ዳቦ ያልተፈቀደላቸው ነጋዴዎች ሲሸጡ ከተገኙ አስፈላጊው የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ማስጠንቀቂያ ተላልፏል።

ህብረተሰቡ ለጤናው ሲል ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል። #ኤኤምኤን

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#SafaricomEthiopia

በሽ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች እየደረሰ ነው!

የ1,000,000 እና የ100,000 ብር ሽልማት በመቀሌ፤ ቢሾፍቱ፤ ጅማ፤ ባህርዳር፤ ጎንደር፤ ዓዲ ሽሙድሕን፤ ድሬዳዋ፤ ጅጅጋ፤ ሻሸመኔ፤ ጎዴ፤ ሸዋሮቢት፤ ሃዋሳ፤ አምቦ፤ ደሴ፤ አሰላ፤ ወልድያ፤ አዲስ አበባ፤ መሆኒ፤ ነቀምቴ፤ ለገጣፎ፤ ሐረር፤ ሆሳዕና፤ መቀሌ፤ አዳማ እና በሌሎችም ቦታዎች ደርሱዋል!

አሁን ተራዉ የእርስዎ ነው! በሽ እየገዛን በሸ እንሸለም! 🥳🎉🎉

ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ!

📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፡
https://onelink.to/ewsb22

የቴሌግራም ቦታችን👉🏽 /channel/official_safaricomet_bot

#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
#Besh

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የኢትዮጵያን ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት #Marburg_virus

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የበሽታውን ምልክት አሳይተው የነበሩ 6 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ ነገር ግን በላብራቶሪ ማረጋገጥ የተቻለው የሦስቱን ብቻ ነው " - ጤና ሚኒስቴር

የጤና ሚኒስቴር በደቡበ ኢትዮጵያ ክልል በጅንካ ከተማ የተከሰተው የሄሞራጅከ ፊቨር (Viral Hemorragic Fever) በሽታ መንስኤ ማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus) መሆኑን መግለጹ ይታወቃል።

ይህን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መግለጫ እየሰጠ ይገኛል።

በዚህ መግለጫ ላይ የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ እስካሁን በበሽታው 17 ሰዎች ተጠርጥረው ምርመራ እንደተደረገላቸው ተናግረዋል።

በዚህም 3ቱ በላብራቶሪ ምርመራ በበሽታው መያዛቸው መረጋገጡን ገልጸዋል።

የበሽታውን ምልክት አሳይተው የነበሩ 6 ሰዎች ህይወት ማለፉን የገለጹት ሚኒስትሯ፥ ነገር ግን በላብራቶሪ ማረጋገጥ የተቻለው የሦስቱን ብቻ መሆኑን ነው የገለጹት።

ምርመራ ከተደረገላቸው 17 ሳምፕሎች በሽታው በላብራቶሪ ማረጋገጥ የተቻለው በሦስቱ እንደሆነም ነው የጠቆሙት።

ምርመራውም በሀገር አቅም መደረጉን ነው የጠቆሙት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#MoE

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለ1 ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ በ2019 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

ለመምህራን የሚቀርበው ጥቅማጥቅምና ደመወዝ በቂ አለመሆን ለመምህራን እጥራት ምክንያት እንደሆነ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለምክር ቤት አባላት ተናግረዋል። ይህም አዲስ መምህራንን በበቂ ሁኔታ ለማፍራት አስቸጋሪ እንዳረገው ገልፀዋል።

የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ግለሰቦች የአንድ ዓመት የማስተማር ዘዴ (Pedagogy) ኮርስ በመውሰድ ለመምህርነት ብቁ መሆን እንደሚችሉ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በዚህም የመምህራንን ቁጥር ለማሳደግ ይቻላል ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ሲሰጡ፣ የበለጠ የመምህነነት ሙያ ፍቅር ሊያጎለብቱ እንደሚችሉም ገልፀዋል።

ባለፈው ዓመት ከቅድመ-መዋዕለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል በሀገሪቱ አጠቃላይ የመምህራን ቁጥር 625,000 የነበረ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ቁጥሩን ወደ 700,000 ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የፎርቹን ጋዜጣ ነው።

Via @tikvahuniversity

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Tecno_Spark_40_Pro+

ቤቶት ቁጭ ብለው ቴሌቪዥን እየተመለከቱ ሪሞቶትን ቢያጡት እንዳይበሳጩ! አዲሱ Tecno Spark 40 Pro+ እንደ ሪሞትም ሆኖ ያገለግሎታል፡፡ ስልኮትን ለየትኛውም ብራንድ እንደሪሞት መጠቀም የሚያስችሎትን ዘርፈ ብዙ የሆነው አዲሱ የTecno Spark Pro+ ይለያል!

#Spark40Pro+ #SlimeverStrongForever #TecnoAI #TecnoSpark40Series

@tecno_et

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" አሁን ላይ በየሆቴሉ የሚሰሩ ሴት አስተናጋጆች ምሽት ሲሆን በማናጀራቸው አማካኝነት ሰውነታቸውን የሚያሳይ ወይም አጫጭር ልብስ እንዲለብሱ እየተደረጉ ነው፣ በየቀኑ ብዙ ስልክ እየተደወለልኝ ነው " - የኢትዮጵያ መስተንግዶ ባለሙያዎች ማህበር

የኢትዮጵያ መስተንግዶ ባለሙያዎች ማህበር በባለፈው አመት የአዲስ አበባ ከተማ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ በሆቴልና መሰል ተቋማት ለሚሰሩ አስተናጋጆች ያዘጋጀው የአለባበስ ደንብ በአግባቡ ተፈጻሚ እየሆነ አለመሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የማህበሩ መስራችና ፕሬዝዳንት አቶ ያሬድ ደገፉ " ደንቡ ተግባራዊ ቢደረግም አሁን ላይ በየሆቴሉ የሚሰሩ ሴት አስተናጋጆች ምሽት ሲሆን በማናጀራቸው አማካኝነት ሰውነታቸውን የሚያሳይ ወይም አጫጭር ልብስ እንዲለብሱ እየተደረጉ ነው፣ በየቀኑ ብዙ ስልክ እየተደወለልኝ ነው " ብለዋል።

አቶ ያሬድ ደገፉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በዝርዝር ምን አሉ ?

" ማህበሩ ከተቋቋመ ሶስት አመት ሆኖታል፣ 480 የሚሆኑ አባላቶችም አሉን፣ ሁሉም የመስተንግዶ ባለሙያዎች ናቸው።

በባለፈው አመት በሆቴል እና መሰል አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ለሚሰሩ አስተናጋጆች የአለባበስ ደንብ ወጥቶ ነበር።

ይህንን ደንብ ለማስፈጸም ከፀጥታ ተቋማት፣ ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን፣ ከፍትህ ሚኒስቴር እና ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ጋር በመሆን የአፈጻጸም ደንብ አዘጋጅተን ጸድቆ ተግባራዊ ተደርጓል። ይህን በሃላፊነት ሊሰራ የሚችለው ተቋም ቱሪዝም ኮሚሽን ነው።

እስካሁን ድረስ በወረዳ እና በክፍለ ከተማ ላይ ደንቡን የሚያስፈጽሙ አካላቶች ነበሩ ፣ አሁን ላይ ግን ይህ የለም፣ ቁጥጥር የሚያደርግም የለም። ቱሪዝም ኮሚሽን እየተቋቋመ ያለው በከተማ ደረጃ ነው። ይህ ደግሞ ለሰራተኞችም፣ ለማህበራችንም አስጊ ነው።

በአንዳንድ ሆቴሎች ላይ በሴት አባላቶቻችን ላይ እየተደረገ ያለው ምሽት 12 ስአት ሲሆን ' እየመሸ ስለሆነ ምን ችግር አለው አጭር ቀሚስ ልበሱ ' እያሏቸው ነው የሆቴል ማናጀሮች፣ ይህ ደግሞ መብታቸውን ይጋፋል። አስተናጋጆችም መብታችንን ለማስጠበቅ የወጣው ደንብ በአግባቡ ተግባራዊ ይደረግልን እያሉ ለማህበራችን ጥያቄ እያቀረቡልን ነው " ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር ሁንዴ ከበደ በጉዳዩ ላይ ምን አሉ ?

" የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር አንዱ ከሰራቸው ትልቅ ስራዎች የሆቴል ሰራተኞች ወይም አስተናጋጆች የአለባበስ ኮድ አዋጅ ማዘጋጀት ነው። ይህ አዋጅ በጣም ጥሩ ነው፣ በተለይም የሀገራችንን ባህል እና አገልግሎታችንን ከማስጠበቅ አንፃር ትልቅ ሚና አለው። አዋጁ ተፈጻሚነት እንዲኖረው እስከታች ድረስ ወርዷል።

ከዚህ በፊት በየወረዳው የኛ ቡድን ነበረ፣ አሁን ላይ ደግሞ በወረዳ ደረጃ ያለው መዋቅር ስለታጠፈ ከአለባበስ ጋር ያሉ ጉዳዮችን መቆጣጠር አልቻልንም። ነገር ግን በየወረዳው ካሉ ደንብ ማስከበር ጋር በአለባበስ ዙሪያ ውይይት አድርገናል። ችግሮች አልፈው አልፈው ይኖራሉ፣ እንደዚህ ያሉ ጉዳዮችን ለመቅረፍ ከሌሎች አካላቶች ጋር በመሆን በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል። ህጉን የሚጥስ አካልም በህግ ይጠየቃል።

ከዚህ በሗላ ህግ ወጥቶለታል፣ አሰራርም አለው፣ ህጉን ለማስከበር ደግሞ ከከተማ ደንቦች ጋር እየተነጋገርን ነው። ስራውንም ለእነሱ አሳልፈን የምንስጥበት እና እየተከታተሉ የሚያስፈጽሙበት ሁኔታ ይኖራል። በተለይ አሁን ላይ መዋቅሩን ስንሰራ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ላይ ሰፊ እና አድካሚ ስራ ተሰርቷል፣ ከላይ ያሉ ባለሙያዎች እስከታች ድረስ ወርደው እየተነሱ ያሉ ችግሮችን እንዲያዩ እየተደረገ ነው። " ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ በባለፈው አመት ያወጣው ደንብ በውስጡ የሰራተኛ አለባበስ የማያስተካክሉ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ላይ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ ከ1 እስከ 50ሺህ ብር የሚያስቀጣ እና የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድን እስከማገድ የሚደርስ ቅጣት እንደተካተተበት መገለፁ ይታወሳል።


ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

‎" በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ አምስት ኢትዮጵያዊያን ተገድለዋል" - ኢትዮጵያዊያን ከደቡብ አፍሪካ

‎ከሰሞኑ ሁለት ጓደኛሞችን ጨምሮ አምስት ኢትዮጵያዊያን በደቡብ አፍሪካ የተለያዩ ከተሞች በተሰነዘረባቸው ጥቃት ሕይወታቸዉ ማለፉን በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

‎ነዋሪዎቹ እንደሚሉት በተለያዩ ጊዜያት ኢትዮጵያውያንን ያነጣጠረ ጥቃት በታጠቁ ሰዎች ተደጋጋሚ እንደሚፈፀም ተናግረዉ ይህም የበርካታ ኢትዮጵያዊን ሕይወት መቅጠፉን ገልፀዋል።

‎ለደህንነታቸዉ ሲሉ ማንነታቸዉን እንዲገለፅ ያልፈለጉ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ከሁለት ቀናት በፊት በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ 2 ኢትዮጵያዊያን ጓደኛማቾች ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸዉን ተናግረዋል።

በተመሳሳይ መልኩ የጆሀንስበርግ ከተማ ነዋሪ የሆነ የሶስት ልጆች አባት ከስራ ወደቤቱ በሚመለስበት ወቅት በታጠቁ ሰዎች በበርካታ ጥይት ተደብድቦ መገደሉን አስረድተዋል።

‎በሌላ መልኩ አንድን ወጣትና ሌላ ታዳጊ በዚሁ በጁሀንስበርግ ከተማ አቅራቢያ በስራ ቦታ ሱቅ ዉስጥ እያሉ በጠራራ ፀሐይ በታጠቁ ሰዎች በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል ሲሉ ገልጸዋል።

‎በሀገሪቱ በኢትዮጵያዊያን ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት የሚፈፀም ቢሆንም በፈረንጆች አዲስ ዓመት ዋዜማ ጎልቶ ይስተዋላል ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገራቸው  በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አመራሮች መከካል የሆኑ አንድ ስማቸው እንዳይገለፅ ያልፈለሁ የመረጃ ምንጭ በተለያዩ ጊዜያት በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈፀመው ጥቃት የበርካቶችን ሕይወት እየቀጠፈ መቆየቱን ተናግረዉ ከላይ በሟቾች ቁጥር ጉዳይ ግን መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#UK🇬🇧

በዩናይትድ ኪንግደም (UK) የጥገኝነት ጥያቄያቸው ተቀባይነት ያገኘ ስደተኞች በአገሪቱ በቋሚነት እንዳይቆዩ እንደሚደረግ ተገለጸ።

ይህ ጉልህ የፖሊሲ ለውጥ የፊታችን ሰኞ በአገር ውስጥ ሚኒስቴሯ ሻባና መሕሙድ በኩል በምክር ቤት ይፋ እንደሚደረግ ቢቢሲ ዘግቧል።

በፖሊሲው መሠረት፤ ጥገኝነት ያገኙ ስደተኞች በዩኬ ለተወሰነ ጊዜ ብቻ የሚቆዩ ይሆናል።

ዩኬ ጥገኝነት ጠያቂዎችን በዘላቂነት የምታኖርበት አሠራር ሊለወጥ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፤ የፖሊሲ ለውጥ የተደረገው በጀልባ የሚገቡ ስደተኞችን ቁጥር ለመቀነስ ነው ተብሏል።

የጥገኝነት ጥያቄያቸው ተቀባይነት ያገኘ ሰዎች " አገራቸው መመለስ አስጊ አይደለም " ተብሎ በሚታመንበት ወቅት ላይ ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ ይደረጋል።

አሁን ላይ ዩኬ ለጥገኝነት ጠያቂዎች የአምስት ዓመት የቆይታ ጊዜ ትፈቅዳለች። ከዚያም ስደተኞች በዩኬ በዘላቂነት ለመቀጠል ማመልከት ይችላሉ።

ፖሊሲው የተወሰደው ከዴንማርክ እንደሆነ ተነግሯል።

የዴንማርክ ግራ ዘመም ሶሻል ዴሞክራት መንግሥት በአውሮፓ ጠንካራውን የስደተኞች ፖሊሲ በመተግበር ይታወቃል።

ጥገኝነት ጠያቂዎች የሁለት ዓመት የመኖሪያ ፈቃድ ከተሰጣቸው በኋላ በድጋሚ ማመልከት አለባቸው። ዜግነት ለማግኘት ያለው ሒደት ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ፈታኝ እየሆነ መጥቷል።

የዴንማርክን አሠራር ያደነቁት የዩኬ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር፤ " በምርጫ ወቅት የተሻለ የሕዝብ ድምጽ ያስገኘ አካሄድ ነው " ሲሉ አሞካሽተውታል።

የዩኬ ሌበር ፓርቲ ጠንካራ እርምጃ ካልወሰደ " የጨለማ ኃይሎች ይወርሱናል " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ዴንማርክ ስደተኞች ቤተሰቦቻቸውን የሚወስዱበትን ሒደት በማራዘም የምትታወቅ ሲሆን፤ ይህ አሠራርም በአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሯ ተወድሷል።

ዩኬ ለስደተኞች ያላት መልካም አቀባበል በጀልባ ወደ አገሪቱ የሚገቡ ጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር እንዲጨምር ማድረጉን ገልጸዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Afar

ዛሬ 10ኛ የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም የመክፈቻ መርሃ ግብር በአፋር ክልል ሠመራ ሎጊያ ከተማ ዛሬ እየተካሄደ ይገኛል። 

በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ወቅት ፦
- የአፋር ክልል ፕሬዚዳንት ሐጂ አወል አርባ፣
- የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ፣
- የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል፣
- የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዜዳንት አቶ አደም ፋራህ፣
- የሠመራ ሎጊያ ከተማ ከንቲባ አቶ አብዱ ሙሳ፣
- የአፋር እና ጅቡቲ ባህል ቡድን ማዕከል እንዲሁም ሌሎች ባለስልጣናትና እንግዶችና በርካታ ነዋሪዎች ተገኝተው ነበር።

የሠመራ ሎጊያ ከተማ ከንቲባ አቶ አብዱ ሙሳ፤ በከተማዋ በርካታ የልማት ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነና ስራው በዚህ አመትም እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

" ሠመራ ከተማ በ10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ራሷን ለማሰለፍ አምራና ተውባ ለገበያ ወጥታለች " ሲሉ ለአልሚ ባለሃብቶች መልዕክት አስተላልፈዋል።

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቲ ሳኒ፣ ከተሞችን የማስፋፋት ስራ እየተሰራ መሆኑን አንስተው፣ " ዛሬ እዚህ የተገኘነው ከተሞችን ለመገንባትና የከተሞችን የወደፊት እጣ ፋንታ ለመወሰን ነው " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም የከተሞች የእርስ በእርስ ቅርርብ የሚደረግበት መሆኑን አስረድተው፣ " ከተሞችን የብልጽግና ማዕከላት ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ይገኛል " ሲሉም ተደምጠዋል።

ነዋሪውን የቤት ባለቤት ለማድረግ፣ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሆኑ ከተሞችን ለማስፋፋት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዜዳንት አቶ አደም ፋራህ በበኩላቸው፣ " ከደረጃ በታች ያሉ ቤቶችን ማሻሻል ያስፈልጋል " ሲሉ ተደምጠዋል።

የአፋር ክልል ፕሬዜዳንት ሐጂ አወል አርባ በበኩላቸው፣ " የኛ ጥያቄ የሕዝባችን የልማት ጥያቄ ነው " በማለት ተናግረዋል። በዚህም " ሰፋፊ የልማት ሥራዎችን መስራት ተችሏል " ብለዋል። 

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አፋር
ሠመራ
#TikvahEthiopiaFamilyAA


@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ዳሸን ባንክ !

ዳሸን ባንክ እስከ 30 ሚሊዮን ብር ሽልማት ያለውን የ"ዳሸን ዕድል" ጨዋታ ይፋ አደረገ

ዳሸን ባንክ በዳሸን ሱፐር አፕ ላይ ብቻ የሚገኝ አዲስ የዲጂታል ሽልማት እና የጨዋታ ተሞክሮ የሆነውን ዳሸን እድልን በይፋ መጀመሩን አሳወቀ።

ይህበአይነቱ ልዩ የሆነው የሱፐር አፕ እድል እስከ 30 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ጠቅላላ የሽልማት ገንዘብ ያለው ሲሆን፣ ይህም የዳሸን ሱፐር አፕ ተጠቃሚዎች የባንኩን ዘመናዊ ዲጂታል አገልግሎቶች በመጠቀም አስደሳች ሽልማቶችን የማግኘት ልዩ እድል የሚሰጣቸው ነው።

የዳሸን ዕድል ሎተሪ ደንበኞች እንዲሳተፉ እና እንዲያሸንፉ በአርኪ መንገድ የቀረበ ጨዋታ ነው፡፡ የዳሸን ሱፐር አፕ ተጠቃሚዎች በዕለት ተዕለት በሚያደርጓቸው ዲጂታል ግብይቶች፣ (ማለትም የገንዘብ ዝውውሮችን በማድረግ፣ ሱፐር አፕን በማውረድ እና በመጠቀም፣ ከሌሎች ባንኮች ገንዘብ በመቀበል፣ የንግድ ክፍያዎችን በመፈፀም፣ የአየር ሰዓት በመሙላት እንዲሁም ሌሎች በመተግበሪያው ውስጥ የሚገኙትን የቻት ባንኪንግና የበጀት አገልግሎቶችን) እና ሌሎች አገልግሎቶችን በመጠቀም በቀላሉ "ሳንቲሞችን" መሰብሰብ ይችላሉ፡፡

ደንበኞች ከዚያም የሰበሰቡትን ሳንቲሞች በመጠቀም ስልኮቻቸውን "በማወዛወዝ" እና ከሞባይል ዳታ ፓኬጆች አንስቶ ከ100 ብር እስከ 100,000 ብር የሚደርሱ የኤሌክትሮኒክስ የገንዘብ (e-money) ሽልማቶችን፣ ሳምሰንግ ጋላክሲ ኤስ 23 እና ኤ 54፣  አይፎን 16 ሞዴል ስልኮችን እንዲሁም አዲስ የቢዋይዲ መኪና ሽልማቶችን ማሸነፍ ይችላሉ።

ከጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዳሸን ባንክ በዳሸን ዕድል የማስተዋወቅ ዘመቻው በሺዎች የሚቆጠሩ ሽልማቶችን ለአሸናፊዎች መስጠት ጀምሯል። ይህ የማስተዋወቅ ዘመቻ የዳሸንን ደንበኞች ለመሸለም ብቻ የቀረበ ሳይሆን ደንበኞች በዳሸን ሱፐር መተግበሪያ ላይ የቀረቡትን በርካታ የአገልግሎት አይነቶች እንዲጠቀሙ ለማነሳሳት የተነደፈ ነው።

ዛሬውኑ ይህን አስደሳች ጨዋታ ይቀላቀሉ!

የዳሸን ሱፐር መተግበሪያን ያውርዱ፣ ሳንቲሞችን ማግኘት ይጀምሩ፣ እና በዳሸን ባንክ የዲጂታል ባንክ ሕይወትን የሚቀይሩ ሽልማቶችን ለማሸነፍ እድልዎን ይጠቀሙ።

የዳሸን ባንክ ሱፐር አፕ መተግበሪያ ያውርዱ 👇  https://www.dashensuperapp.com/download

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#MoE

በዛሬው እለት የህዝብ ተወካዮች የሰው ሃብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የትምህርት ዘርፉን የ1ኛ ሩብ ዓመት ሥራ አፈፃፀም ተመልክቶ ነበር።

በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በከፍተኛ ትምህር ተቋማት የክብር ዶክትሬት አሰጣጥን በተመለከተ ችግር የነበረበት በመሆኑ ወጥ አሰራር መከተል በማስፈለጉ የክብር ዶክትሬት አሰጣጥን ሀገራዊ መመሪያ ተዘጋጅቶ ለትግበራ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።

ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በመመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ማድረግ ያለባቸው ሲሆን የክብር ዶክትሬት ማዕረግ የሚያገኙ ሰዎች ዶክተር ወይንም የክብር ዶክተር በሚል መጠሪያነት መጠቀም እንደማይቻል አሳስበዋል።

የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ለመስጠት ሀገራዊ እና አለም አቀፍ መስፈርቶችን ማሟላት እንዳለባቸው በመመሪያ መመላከቱን አንስተዋል።

በሙያው የተለየ ስራ ያበረከተ ኢትዮጵያዊም ሆነ ሌላ ዜጋ በመመሪያው የተዘረዘረውን መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ የክብር ዶክትሬት ማዓረግ ማግኘት እንደሚችል ጠቅሰዋል። ይሁን እንጂ የተሠጠውን የክብር ዶክትሬት ለመጠሪያነት መጠቀም እንደማይቻል አብራርተዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር የክብር ዶክትሬት መስጠት የሚችሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በተመለከተ እንዲሁም የክብር ዶክትሬት የተሰጠው ግለሰብ ዶክተር፣ የክብር ዶክተር እና መሰል መጠሪያዎችን በየትኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት መጠቀም እንደማይችል መመሪያ አዘጋጅቶ ለሚመለከታቸው መላኩ ይታወቃል።

#MoE

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

በታጣቂዎች የሚገደሉት በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ደግሞ ታፍሰው የሚታሰሩበት አሳሳባቢው የአማራ ክልል  የጤና ባለሙያዎች ጉዳይ ! 

የአማራ ክልል የጤና ባለሙያዎች ማህበር ፀሀፊ አቶ ተስፋ መኮነን በክልሉ ባሉ የጤና ባለሙያዎች ላይ በመንግስትም በታጣቂዎችም እየደረሰ ያለው ግድያ፣ እስር አስመልክተው ሰፋ ያለ ማብራሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።

አቶ ተስፋ ምን ምን አሉ ?

" በያዝነው ሳምንት ብቻ 2 የጤና ባለሙያዎች ተገድለዋል።

አንዷ ቤተልሄም አዲስ የምትባል በምዕራብ ጎጃም ዞን በደንበጫ ጤና ጣቢያ በስራ ላይ እያለች ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም በታጣቂዎች ተገድላለች። 

ባለፈው ጥቅምት 19/2018ዓ.ም በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንደ ውሃ ሆስፒታል የሚሰራ ዶ/ር ዳንኤል ነጋ የተባለ የአይን ስፔሻሊስት በታጣቂዎች ታግቶ ገንዘብ እንደተጠየቀበት ሰምተን ነበር ህዳር 1/2018ዓ.ም መገደሉን ሰምተናል።

ይህ የአንድ ሳምንት አሳዛኝ ክስተት ነው።

ሌላው በምስራቅ ጎጃም ዞን ስናን ወረዳ አርብ ገበያ በተባለ ከተማ ውድነህ አንዳርጋቸው የተባለ ነርስ ባለፈው መስከረም ወር 2018 ዓ.ም በታጣቂዎች መገደሉን መረጃ ደርሶኛል።

ሌላው ደግሞ፥ ከጥቅምት 23 እስከ 27 ድረስ 5 የጤና ባለሙያዎች በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ተይዘው 8ተኛ ፖሊስ ጣቢያ ይገኛሉ።

የዋስትና መብት ተሰጥቷቸው ከእስር እንዲለቀቁ ቤተሰቦቻቸው ቢጠይቁም የሰማቸው አልነበረም። ከሳምንት በኃላም የዋስ መብታቸው ተጠብቆ እላንት ህዳር 3/2018ዓ.ም 4ቱ ዶክተሮች ሲለቀቁ አንዱ ነርስ ግን እስካሁን አልተፈታም።

ታስረው የነበሩ የጤና ባለሙያዎች ስም፦

1. ዶ/ር መኩ ዳምጤ የአዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅና እውቅ የቀዶ ህክምና ባለሙያ
2. ዶ/ር ስመኘው ዘላለም የጠቅላላ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት
3. ዶ/ር ዳምጤ ዘውዴ የጥበበ ግዮን የነርቭ እና የጭንቅላት ቀዶ ህክምና ስፐሻሊስት
4. ዶ/ስመኘው  ተስፋ ከአሜን ሆስፒታል የቀዶህክምና ባለሙያ
5, ታደሰ ዳቤ ነርስ ከአሜን ሆስፒታል አሁን ያልተፈታ

እነዚህ በቅርቡ የተከሰቱ ግድያዎችና አፈሳዎች ናቸው።

እኔም በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ተይዤ ታስሬ ነበር። ባለቤቴ ደግሞ ለዘረፋ በተደራጁ ታጣቂዎች ተይዛ ገንዘብ ከፍለን ነው ያስለቀቅናት።

ነገሩ እንዲህ ነበር ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ሆምላንድ በተባለ ሆቴል ከ5 ባለደረቦቼ ጋር  ስብሰባ አምሽተን ስንወጣ ፖሊሶች መጥተው ያዙን ከዚያም 4ተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወስደው አሰሩን። ምን አደረግን ? ብለን ጠየቅናቸው ' ስልጣናችሁን ያለ አግባብ ተጠቅማችኃል ' አሉን የቱን  ስልጣን ? እኛኮ የጤና  ባለሙያዎች ነን የምንሰራውም በማህበሩ ውስጥና ጤና ቢሮ ነው አልናቸው ሁለት ቀን በእስር ካቆዩን በኃላ የወሰዱን ፖሊሶች በመጥፋታቸው ይቅርታ ብለው  ሌሎች ለቀቁን።

እንደገና ሰኔ 25/2017 ዓ.ም ባለቤቴን  ጨምሮ 3 ነርሶች ከፈለገ ህይወት ስፒሻላይዝድ ሆስፒታል አምሽተው በሰርቪስ ወደ ቤታቸው ሲሂዱ ከምሽቱ 2:00 ላይ ታጣቂዎች ከመኪና አስወርደው አግተው ወሰዷቸው። በብዙ ድርድር ብር ከፍለን ነው ያስለቀቅናቸው።

ይህ ጥቃት የሆነው በክልሉ ርዕሰ መዲና ባህር ዳር ነው በወረዳና በዞኖች ላይ ደግሞ በጣም የከፋ እንደሆነ መረጃ ይደርሰናል ግን ለማን አቤት እንደሚባል ግራ ገብቶናል " ብለዋል።

በአማራ ክልል በጤና ባለሙያዎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ግድያና አፈና ምን አስከትሏል ?


አቶ ተስፋ መኮነን እንደሚሉት ባለፈው አመት የጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ህክምና ክፍል ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር አንዱአለም ዳኜ  በክልሉ ርዕሰ መዲና ባህር ዳር ጥር 24/2017 ዓ.ም ከስራ አምሽተው ወደ ቤታቸው  በመጏዝ ላይ እያሉ  በዘራፌዎች  ከተገደሉ በኃላ ከ30 እስከ 40 የሚሆኑ እውቅ የጤና ባለሙያዎች ክልሉን ለቀው ወደ መሀል ከተማ ሂደዋል።

ሰሞኑን በተከሰተው ግድያና እስራትም ብዙ የጤና ባለሙያዎች ክልሉን ለመልቀቅ አኮብኩበዋል።

በዚህም በህክምና እጥረት ህዝቡ እየተሰቃየ ነው። ሆስፒታሎችም የባለሙያ ያለህ እያሉ ነው።

" ሀኪሙስ የትም ቦታ ተዘዋውሮ ሰላም ያለበት ሀገር ሄዶ ተቀጥሮ ይሰራል ህዝቡ የት ይሄዳል ? " ሲሉም ይጠይቃሉ።

" በተለይ በአሁኑ ሰዓት እየተሰቃየ ያለው የገጠሩ ማህበረሰብ ነው ከተሜውስ በአውሮፕላን ተሳፍሮ ሄዶ ታክሞ እየመጣ ነው " ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ጥቃት አድራሾቹ እነማን ናቸው ?

" እስርን በተመለከተ የመንግሰት የጸጥታ ኃይሎች ናቸው፤ ምክንያታቸው ደግሞ ' ታጣቂዎችን ታክማላችሁ ' በሚል ነው።

ታጣቂዎቹ ደግሞ 'ለብልፅግና ታግዛላችሁ' ነው የሚሉት እንደሚታወቀው ህክምና ሰብዓዊ አገልግሎት የሚሰጥበት ነው ሀኪም ዘርን፤ ቀለምን፤ ሀይማኖትን እንዲሁም ብሄርን ሳይለይ አገልግሎት እዲሰጥ ነው ቃል የገባው ይህንን መንግስትም ታጣቂዎችም መረዳት አለባቸው።

ከሁለቱ ውጭ ያለው ደግሞ የታጠቀ ዘራፈ ቡድን ነው እነዚህን ለህዝብ ቁመናል የሚሉ ሁለቱ ኃይሎች ተባብረው ማጥፋት አለባቸው። "
ማህበሩ ምን እያደረገ ነው ?

" የአማራ የጤና ባለሙያዎች ማህበር ከአማራ የግል ጤና ድርጅቶች ማህበር ጋር በመሆን በጤና ባለሙያው ላይ እየደረሰ ያለው አፈናና ግድያ ይቁም! ህግ ይከበር! ቤተሰቦቻችን የህክምና አገልግሎት ያግኙ ! የሚል ደብዳቤ በመያዘ፦
-ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ፅ/ቤት
-ለአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን
- ለአማራ ክልል አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ አስገብተናል።

ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትንም ለማነጋገር እየጣርን ነው። በቀጣይም ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ድምፃችን እናሰማለን " ብለዋል።

ሰሞኑን እንደገና ባገረሸው የሙያ አጋሮቻቸው ግድያና እስር ምን ይላሉ ?

በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳውሃ ከተማ የገንዳዋ አጠቃላይ ሆስፒታል ሀኪም የሆነውና ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀን አንድ የጤና ባለሙያ ስራውን እና ከተማውን ለመልቀቅ በዝግጅት ላይ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ይህው የመረጃ ምንጫችን በገንዳዋ አጠቃላይ ሆስፒታል ይሰራ የነበረው እና ሰሞኑን በታጣቂዎች ታግቶ ተወስዶ የቤዛ ገንዘብ የተጠየቀበትና ኃላም ተገሎ ተጥሎ ስለተገኘው ዶ/ር ዳንኤል ነጋ እንዲህ ሲል ተናግሯል።

" ዶ/ር ዳንኤልን የማውቀው ከ2015ዓ.ም ጀምሮ ነው በጣም ስነ ምግባር ያለውና ሙያውን የሚወድ ህመምተኞችን አክባሪ ነው።

ዶክተር ባለትዳርና የአንዲት ሴት ልጅ አባትም ነበር።

ባለፈው ጥቅምት 19/2018ዓ.ም በሆስፒታሉ አቅራቢያ ባለ አንድ ምግብ ቤት እራት እየበላ እያለ ነው ከብዙ ሰዎች መካከል ታጣቂዎች እሱን መርጠው አስነስተው ይዘውት የሄዱት ከዚያም 5 ሚልየን ብር እንዲከፈላቸው ጠየቁ።

ብሩን ማሰባሰብ ተጀምሮ ነበር ቤተሰቦቹ 600 ሺህ ብር ለአጋቾቹ እንደከፈሉ ሰማን ግን ብሩን ከመክፈላቸው በፊት ነው ልጁን ገድለው የጣሉት አስከሬኑ ሲገኝ ያመላከተውም ይህንን ነው። "

ከዶክተሩ እገታ ጋር በተያያዘ እርሱን ጨምሮ 6 የጤና ባለሙያዎች ከጥቅምት 21 እስከ 27 /2018 ዓ.ም ማለትም ለ6 ቀናት ታስረው እንደነበር ይህው የመረጃ ምንጫችን ነግሮናል።

ከሀኪሞች በተጨማሪም 7 በምግብ ቤቱ  አቅራቢያ የሚኖሩ ሰዎች ታስረዋል ብሏል።

የመረጃ ምንጫችን በመተማ ሆስፒታል ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ 5 የጤና ባለሙያዎች ታግተው የተገደሉ ሲሆን 4 የጤና ባለሙያውች ደግሞ ብር ተዋጥቶ ተከፍሎላቸው መለቀቃቸውን ተናግሯል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ፍርድ⚖️

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የግድያና የከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት የአባተ አበበን ገዳይ ተስፋዬ ሆርዶፋ ላይ የ20 ዓመት ፅኑ እስራት ፍርድ አስተላልፏል።

አባተ አበበ ታህሳስ 7 ቀን 2016 ዓ/ም ምሽት አዲስ አበባ ቦሌ ኤድና ሞል ወረድ ብሎ በሚገኝ አንድ የመዝናኛ ስፍራ አካባቢቢ በጥይት ተመቶ መገደሉ ይታወሳል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" 753 ሺሕ 000 ብር ወዴት ገባ ? " - የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዳር ፓሊ ካምፓስ ተማሪዎች

➡️ " አንዳንድ ተማሪዎች የመረጃ እጥረት ስለነበረባቸው ካፌ እየገቡ ልነበረም። ለዚህ ግቢው ተጠያቂ አይደለም" - የካምፓሱ ተማሪዎች ኀብረት


የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፓሊ ካምፓስ ተማሪዎች ከኪሳቸው አውጥተው ከግቢው ካፌ ውጭ የተመገቡበት የአምስት ቀናት ገንዘብ በትክክል እንዳልተከፈላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

‎ከጥቅምት 7 እስከ 11 2018 ዓ/ም ድረስ የካፌ አገልግሎት እንደተቋረጠ በማስታወቂያ እንደተነገራቸው ያስረዳው አንድ የግቢ ተማሪ፣ "ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ/ም ከሰዓት የካፌ አገልግሎት አልተቋረጠም ተባለ። እኛ ግን ለ5 ቀናት የካፌ አገልግሎት እንደተቋረጠ ነው የምናውቀው። አንድ ተማሪ ለ5 ቀን ካፌ አልገባም ማለት በቀን 100 ብር ሲታሰብ በአምስተኛው ቀን 500 ብር ይጠብቃል" ብሏል።

ሌሎች ተማሪዎች በበኩላቸው ይህንኑ ሀሳብ ተጋርተው፣‎ አጠቃላይ የነን ካፌ ተማሪዎች ቁጥር "1,506" እንደሆነ፣ በዚህም አንድ ተማሪ 500 ብር ሲደመደብ፣ ድምሩ 753 ሺሕ ብር እንደሚሆን በመግለጽ፣‎ "ይሄ 753 ሺሕ ብር ወዴት ገባ?" ሲሉ ጠይቀዋል።

የፓሊ ካምፓስ ተማሪዎች ኀብረት ፕሬዚዳንት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን መለሰ ?

በዩኒቨርሲቲው የፓሊ ካምፓስ ተማሪዎች ፕሬዚዳንት ቃለዓብ ሰሙንጉስ፣ " እውነት ለመናገር በቀን 7 የተለጠፈ ማስታወቂያ ነበር። በማግስቱ ግን ተማሪዎች 'ብራችን እየገባ አይደለም ካፌ መግባት አለብን' አሉ። የግቢው ኃላፊዎች ተነጋግረው አስገቧቸው " ብሏል።

" ከዚያን ቀን ጀምሮ እንደገና መግባት ትችላላችሁ ተብሎ ማስታወቂያ ተለጠፈ፥ ግን ተማሪው መረጃ እጥረት ነበረበት ሁለተኛ የተለጠፈውን አላዩትም፥ ያዩት ግን ገብተው ካፌ ሲመገቡ ነበር፤ አንዳንድ ተማሪዎች የመረጃ እጥረት ስለነበረባቸው ካፌ እየገቡ አልነበረም። ለዚህ ደግሞ ግቢው ተጠያቂ አይደለም " ሲል አክሏል።

ሲጀመር ለምን ብሩ በወቅቱ አልተላከላቸውም ? ገብተው የተመገቡትስ በቀን ስንት ነው ? የመረጃ እጥረት ካለስ ማሳወቅ የእናንተ ፋንታ አይደለም ወይ ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄም፥ " ብሩ ዘግይቶ ነው የሚገባው፤ ፋይናንስ ላይ ችግር ስለሚፈጠር በጣም ቀስ ብለው ነው የሚሰሩት። ከቀን 8 ጀምሮ ገብተው እየተመገቡ ነበር፤ ግቢው እንዳሳወቀ መረጃው አለኝ " ሲል መልሷል።

" ተማሪው እየተመገበ ነበር ስለዚህ ግቢው ያወጣውን ወጭ ሊከፍል አይችልም " ብሏል።

ስለዚህ ተማሪዎች ከቀን 8 እስከ 11/2018 ዓ/ም የግቢው ካፌ ገብተው እየተመገቡ ነበር ባይ ነህ ? ለሚለው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄም፣ " በደንብ ነው እየተመገቡ የነበረው " ሲል ምላሽ ሰጥቷታ።

ፕሬዚዳንቱ ቀጠል አድርጎም " ነገር ግን የመረጃ እጥረት የነበረባቸው ተማሪዎች ነበሩ፤ ያልተመገቡ ተማሪዎች እንዳሉ መረጃው አለኝ " ሲል በራሱ መስክሯራ።

ነንካፌ ተጠቃሚ ተማሪዎች 1506 እንደሆኑ፣ የ5 ቀናት ገንዘብ ሙሉው እንዳልተከፈላቸው፣ ከቀን 12 በኋላ ቢሆን ለእያንዳንዱ ተማሪ መከፈል ከነበረበት 3,000 ብር የተፈላቸው 1,800 ብር እንደሆነ በመግለጽ፣ " 753 ሺሕ ብር የት ገባ?" የሚል ጥያቄ አላቸው። ለዚህ ያላችሁ ምላሽ ምንድን ነው ? የሚል ጥያቄም ለፕሬዚዳንቱ አቅርበናል።

በምላሹም " እንደ ተማሪ ህብረት ለመጠየቅ ሞክረናል፤ የተማሪ ተወካዮችን ሰብስበን ያለውን ነገር አሳውቀናል። መረጃ ባለማግኘታቸው የተጎዱ ተማሪዎች አሉ። ግቢውም ብሩን ማጣት አይገባውም። ብሩ አልጠፋም በነገራችን ላይ። ስለዚህ ያለን አማራጭ ተማሪውም ግቢው በጣም በማይጎዱበት መልኩ ባላንስ ማድረግ ነበር ከ12 ጀምሮ እንዲከፈላቸው አድርገናል " ብሏል።

አንድ የግቢው ተማሪ ግን፣ "በጣም የሚያሳፍር ስራ ነው እየተሰራ ያለው። በ5 ቀናት ክፍተት የትኛውም ነንካፌ ተማሪ ካፌ አልገባም። ውጭ ነበር ሲጠቀም የነበረው በብድርም በምንም እያደረገ" ሲሉ ከሰዋል።


ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" እስካሁን ሌላ ቦታ (ከጂንካ ውጭ) የተገኘ ኬዝ የለም " - ጤና ሚኒስቴር

➡️ " ምልክት በታየበት አካባቢ ንክኪ የነበራቸው 129 ሰዎች እራሳቸውን ለይተው እንዲያስቀምጡ መልዕክት ተነግሯቸዋል "

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እስካሁን ተጠርጥሮ በለይቶ ማቆያ ያለ ታካሚ አለመኖሩን ተናግረዋል።

ዶ/ር መቅደስ በማርበርግ ቫይረስ በሽታ ተጠርጥረው የላብራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 17 ሰዎች 14ቱ ሰዎች ኔጌቲቭ (ነጻ) መሆናቸውን ገልጸዋል።

" ምልክት በታየበት አካባቢ ንክኪ የነበራቸው 129 ሰዎች እራሳቸውን ለይተው እንዲያስቀምጡ መልዕክት ተነግሯቸዋል " ያሉት ሚኒስትሯ " ያ ግን በጣም በሩመር ያለውንም ጨምረን ነው፣ ቀጥታ ንኪኪ ያላቸው ተብሎም የሚመዘገብ አይደለም፣ ይህንንም እያጣራን ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

በዚህ በሽታ ከጂንካ ውጪ ምልክት የታየበት አከባቢ አለ ?

የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ፤ የማርበርግ ቫይረስ ከተገኘበት ከጂንካ የወጡ ከቫይረሱ ጋር ንክኪ አላቸው የተባሉ ሰዎች እንደነበሩ አንስተዋል።

" ከእነሱ ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎችን የመለየት ስራ እየሰራን ነው። እስካሁን ሌላ ቦታ የተገኘ ኬዝ የለም " ብለዋል።

" ምልክት አለባቸው ብለን የምንጠረጥራቸውን በሙሉ ምርመራ አድርገናል። ሁሌም እንደዚህ አይነት ቫይረሶች ሲከሰቱ የምንቆጥረው ኬዙ ከተገኘበት ከክልሉ ነው ፤ ያለበለዚያ የማደናገጥ ሥራ ይሆናል " ሲሉ በሌላ አከባቢ ኬዙ አለመገኘቱን ገልጸዋል።

" ከክልሉ (ደቡብ ኢትዮጵያ) ውጪ ሌላ ፖዘቲቭ ኬዝ አላየንም። ወረርሽኙን በአጭር ጊዜ መቆጣጠር ነው ዋናው አላማችን ነው " ያሉት።

" በሽታው በንክኪ የሚተላለፍ ነው፣ የበሽታው ምልክት ካለባቸው ሰዎች ጋር መነካካት አያስፈልግም። ሁል ጊዜም ካላስፈላጊ ንክኪ መቆጠብ አለብን " ሲሉ አሳስበዋል።

ለዚህ በሽታ መድሀኒቱ ምንድን ነው ?

" ለዚህ በሽታ የመጀመሪያ መድሃኒቱ መከላከል ነው " ያሉት ሚኒስትሯ፥ " የበሽታው ምልክት በሚኖርበት ጊዜ በተለይ ፦
- ትውከት፣
- ማስቀመጥ፣ 
- ትኩሳት እና እንደዚህ አይነት ነገሮች በሚኖሩበት ጊዜ Supportive የምንላቸውን ህክምናዎች ይሰጣሉ " ብለዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለዚህ ቫይረስ  ይሄ ነው መድሀኒቱ ተብሎ የተቀመጠ ነገር አለመኖሩን ጠቅሰው፥ " ነገር ግን ሌሎች ሀገሮች የሞከሯቸውን እንዲሁም በሙከራ ላይ ያሉ መድሃኒቶችን ወደ እኛም ሀገር ማምጣት የሚቻልበትን ሁኔታ ጀምረናል " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ቦርዱ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚሳተፉ ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አቀረበ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዘንድሮ በሚካሄው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን ቦርዱ ባበለጸገው ሲስተም በኩል እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አቅርቧል።

ቦርዱ ባቀረበው ጥሪ መሰረት ሁሉም ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን ከዛሬ ህዳር 8 እስከ ህዳር 23/2018 ዓ/ም ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።

የምርጫ ቦርድ ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት:-

• በ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ የተወዳደሩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ለውድድር የተጠቀሙባቸው መወዳደሪያ ምልክቶችን ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመጠቀም ቀዳሚ መብት አላቸው፡፡

• ፖለቲካ ፓርቲዎች የሕጉን መሥፈርት የተከተለ የራሳቸውን የመወዳደሪያ ምልክት ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን፤ በአማራጭም ቦርዱ ጋር በአካል በመቅረብ ቦርዱ ከሚያቀርበው የመወዳደሪያ ምልክት ዝርዝር ውስጥ መምረጥ ይችላሉ፡፡

• የግል ዕጩዎች ምዝገባ ቦርዱ በለጸገው መተግበሪያ የሚከናወን ሲሆን፤የሚጀመርበትን ጊዜ በተመለከተ ቦርዱ በቀጣይ ይፋ የሚያደርግ ይሆናል።

የመመዝገቢያ ቅጾቹን በተከታዩ ማስፈንጠሪያ አማካኝነት :https://nebe.org.et/en/node/725 ማግኘት እንደሚቻል ቦርዱ አሳውቋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update
#MoH

በሽታው ወደ ሀገራችን ሲመጣ እንዴት መጣ፤ በየት በኩል ገባ የሚለውን ጥናት ለማድረግ በአከባቢው ካሉ ባለሞያዎች በተጨማሪ ከፍተኛ የተመራማሪዎች ቡድን ወደ ተከሰተበት አከባቢ መንቀሳቀሱን ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

በተለይ የሽታው አስተላላፊ እንደሆነች የሚታመንባት የሌሊት ወፍ በአከባቢው መኖር አለመኖሯን ፤ የማጥመድና የላብራቶሪ ምርመራዎችን የማድረግ ሥራ እንደሚሰራ አመልክቷል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Ethiopia

በነዳጅ ምርቶች ላይ የተጣለዉ አጠቃላይ የ30% ግብር በቀጣይ ወር ተግባራዊ ይሆናል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ለረጅም ጊዜ የዘለቀውን የነዳጅ ድጎማ ቀስ በቀስ ለማስወገድ ከሚወስዳቸው ሰፋፊ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች አንዱ የሆነው አዲስ የግብር አወቃቀር ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።

ይህ አዲስ እርምጃ በነዳጅ ምርቶች ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና 15% ኤክሳይዝ ቀረጥን ያካተተ አጠቃላይ 30% ታክስ መጣል ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከአንድ ወር በኋላ ታክሱን መሰብሰብ ይጀምራል።

በአዲሱ መመሪያ መሠረት፣ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅቱ የተሰበሰበውን ግብር በሙሉ ለገቢዎች ሚኒስቴር ማስገባት ግዴታው ሲሆን፣ መንግሥት በዚህም እስከ ታኅሣሥ 2018 ዓ.ም. ድረስ ለቤንዚንና ናፍጣ መሸጫ ዋጋዎች ሁሉንም ህጋዊ የግብር መጠን ጨምሮ ሙሉ ወጪን የመሸፈን ግብ ላይ ለመድረስ አቅዷል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ከአዲሱ በጀት ዓመት ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች ላይ አጠቃላይ 30 በመቶ ግብር ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሊያደርግ ማቀዱ መነገሩ ይታወሳል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ መስከረም 2018 ዓ.ም. አጋማሽ ላይ ባቀረቡት አጠቃላይ የዜጎች በጀት ዉስጥ፣ በተያዘው በጀት ዓመት ተግባራዊ የሚደረጉ የግብር አይነቶችን በዝርዝር አስቀምጠው ነበር።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የካፒታል ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#AAiT

Full Stack Software Developer Training Program

Registration: Sept 29 – Nov 28, 2025,
Class Start Date: Nov 29, 2025

Recognized & Accepted Training and Certificates in the USA, Canada, & Europe!

🎓 Earn 4 Professional Certificates:
✔️ Front-End Development
✔️ Back-End Development
✔️ Database Development
✔️ DevSecOps

💼 Career Support & Job Opportunities: Full-time, part-time & freelance opportunities in Ethiopia & worldwide. Portfolio Development and Resume & Interview Preparation

📞 Contact Us: 0902-340070 / 0945-039478 / 0935-602563 Office:011-1-260194

🔗 For more details, check our channel: @AAU_DEVELOPER

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus) ምንድነው ነው ?

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተከሰተው እና ምንነቱ ለማረጋገጥ የዘረመል ምርመራ ሲካሄድበት የቆየው ሄሞራጂክ ፊቨር በሽታ መንስኤ ማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus) መሆኑን መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጋራ በሰጡት መግለጫ ማሳወቃቸው ይታወቃል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለ ማርበርግ ቫይረስ ምሁራዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት እና የተላላፊ በሽታዎች ፌሎ የሆኑትን ዶ/ር ሰላም ቦጋለን አነጋግሯል።

የማርበርግ ቫይረስ መንስኤ ምንድነው ?

" ማርበርግ ቫይረስ 'ማርበርግ' ተብሎ በሚጠራ አር ኤን ኤ  ቫይረስ ምክንያት ይከሰታል። "

በምን አይነት መንገድ ይተላለፋል?

" በመጀመርያ ከለሊት ወፍ ወደ ሰው ይተላለፋል።

በመቀጠል በበሽታው ከተያዘ ሰው (በህይወት ካለም ይሁን ከሞተ ሰው) ጋር በሚኖር የደም ወይም ማንኛውም ፈሳሽ ንክኪ ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል።

በበሽታው የታመመ ሰው ፈሳሽ ያለበት ማንኛውም ነገር ለምሳሌ ልብሶች፣ ፎጣ፣ አልጋ ወዘተ መንካት በሽታውን ያስተላልፋል።

ማርበርግ እንደኮሮና በትንፋሽ አይተላለፍም። "

በበሽታው የተያዘ ሰው ምልክቶቹን በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ያሳያል ?

" ምልክቶች ከተጋለጡ በኋላ 2–21 ቀን ውስጥ ይታያሉ። "

የበሽታው ምልክቶች ምን ምን ናቸው?

" ህመሙ ሲጀምር እንደሌሎች ትኩሳት አምጪ ተላላፊ ህመሞች ፦
•  ትኩሳት
•  ከባድ ራስ ምታት
•  ጡንቻ  ህመም
• ብርድ ብርድ ማለት
•  ድካም
•  የጉሮሮ ህመም
• ትውከት እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ  ያስከትላሉ።

በቀጣይ ህመሙ ቀስ በቀስ ከበድ ማለት ሲጀምር ደግሞ:-

• ማቅለሽለሽ
• ማስቀመጥ
• የሆድ ህመም
• ደም መፍሰስ(ከአፍ ፣ከአፍንጫ ከተለያዩ ሰውነት ክፍሎች)
• የቆዳ ሽፍታ
• ትንፋሽ ማጠር ራስ መሳት
• የሰውነት ክፍሎች (ኦርጋኖች) ለምሳሌ ሳንባ፣ ኩላሊት፣ ጉበት ስራቸው መዳከም ወይም ማቆም

• ደም ግፊት መውረድና ሌሎችም የሰውነት አካሎች ጉዳትና ሞት ሊያስከትሉ ይችላሉ። "

መከላከያ መንገዶቹ ምንድን ናቸው?

" • ከታመመ ሰው፣ በዚህ ህመም ከሞተ ሰው፣ እና ይህ ህመም ያለበት ሰው የተጠቀመበትን ማንኛውም ነገር አለመንካት ።

• እጅን አዘውትሮ መታጠብ ( በሳሙና ወይም አልኮል)

• ለጤና ባለሞያዎች ህክምና ሲሰጡ እንደ ኮቪድ ከላይ እስከ ታች የሚለበስ መከላከያ(PPE) ማድረግ

• በበሽታው ህይወቱ ካለፈ ሰው ቀብር ላይ ጥንቃቄ በማድረግ መከላከል ይቻላል። "

በበሽታው መያዛችንን እንዴት ይረጋገጣል?

" ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች ከተከሰቱ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ የህመሙን ትክክለኛ መንስኤው በደም ወይም ሰውነት ፈሳሽ ናሙና ምርመራ ማረጋገጥ ይቻላል። "

በበሽታው መያዛችን ከተረጋገጠ ምን አይነት ህክምና ይደረጋል?

" እንዳስፈላጊነቱ ግሉኮስ ፣ደም መስጠት፣የደም ፕሮዳክቶችን መስጠት፣ ህመም ማስታገስ፣ ኦክስጅን እንዲሁም መተንፈሻና የኩላሊት ህክምና እንደየ ክብደቱና አይነቱ ይደረጋሉ። "

ዶ/ር ሰላም " የተወሰኑ በሙከራ ላይ ያሉ እና በተወሰነ መልኩ ውጤታማ የሆኑ የህክምና አይነቶች እንዳሉ የቅርብ ጊዜ ጥናቶች ያሳያሉ " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሱጡት ቃል አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

2 የእጣ ቁጥር በM-PESA!
ሚሊየነር የመሆን ዕድላችንን በእጥፍ ለማሳደግ የሳፋሪኮምን የበሽ ጥቅል በM-PESA እንግዛ።

መተግበሪያውን ለማውረድ ይህንን ይጫኑ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

ለተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ያግኙን፥
/channel/MPesaETCustomerCare

#MPESASafaricom #MPESAEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Tecno_Spark_40_Pro+

ቻርጀር ሳልይዝ ስልኬ ሊዘጋ ነው! የሚል ስጋት በአዲሱ Tecno Spark 40 Pro+ ታሪክ ነው፡፡ ምክንያቱም 30W Wireless ወይንም ገመድ አልባ የቻርጅ ቴክኖሎጂ ስላለው ያለምንም ሃሳብ ስልኮን በትንሽ ደቂቃ ቻርጅ አድረገው ወደ ስራዎት መመለስ ያስችሎታል፡፡ Tecno Spark Pro+ በልዩነት የሚገዙት ስልክ ነው፡፡

#Spark40Pro+ #SlimeverStrongForever #TecnoAI #TecnoSpark40Series

@tecno_et

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የፊት ገፃቸው እንዳለ ክርር ብሎ ስለነበር ወንድሞቻችንን ለመለየት አልተቸገርንም ብለዋል " -የተጎጂ ቤተሰብ

ከ20 ወራት በፊት በደላንታ ወረዳ በማዕድን ቆፋሮ ላይ እንዳሉ " ናዳ ተደርምሶባቸው " የሞቱ ሰዎች  አስከሬናቸው ወጥቶ መቀበሩን የወርቅ ዋሻ የማዕድን አምራቾች ማህበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የማኅበሩ ሊቀመንበር ተስፋዬ አጋዥ ፤ የካቲት 1 ቀን 2016 ዓ.ም በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን፣ ደላንታ ወረዳ  " ቆቃ ውሃ " ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ማዕድን ለማውጣት መሬት ሲቆፍሩ የነበሩ 8 ሰዎች ነበሩ ናዳ የተደረመሰባቸው ሲሉ አስታውሰዋል።

አቶ ተስፋዬ  ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት እነዚህ 8 የማህበሩ አባላት የነበሩትን ተጎጂዎችን በወቅቱ ለማውጣት የአካባቢው ማህበረሰብ፤  የተጎጂ ቤተሰቦች እንዲሁም የአካበቢዉ የመንግስት ባለስልጣናት ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም የቦታው አቀማመጥ ለማሽንም ለሰው ጉልበትም የተመቸ እንዳልነበር ገልጸዋል።

እስከ 70 ሜትር ርዝመት ውስጥ ለውስጥ ቁፋሮ ተደርጎ የነበረ ቢሆንም ከዚህ በላይ ቢቆፈር መሬቱ ተደርምሶ ተጨማሪ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል በሚል ስጋት የነፍስ አድን ጥረቱ ሳይሳካ እንደቀረም መለስ ብለው አስታውሰዋል።

ላለፉት 20 ወራት ማለትም አንድ አመት ከ10 ወር ተዳፍኖ የቆየው የተጎጂዎች አስከሬን የማህበሩ አባላት  በሌላ አቅጣጫ ማዕድን ለማውጣት ሲቆፍሩ የሟቾችን አስከሬን ህዳር 4/2018 ዓ.ም በማየታቸው እና ይህንኑ መረጃም ለማህበሩ አመራሮች በመናገራቸው የተጎጂ ቤተሰቦች እና የአካባቢው ማህበረሰብ በተገኙበት የ8ቱም አስከሬን ወጥቶ በወገል ጤና ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ከቀኑ 6:00 ላይ ስርዓተ ቀብራቸው እንደተፈጸመ ተናግረዋል።

" የሟቾችን አስከሬን ቤተሰቦቻቸው ተገኝተው በለበሱት ልብስና ይዘውት በነበረው ተንቀሳቃሽ ስልክ እንዲሁ በመታወቂያቸው ለይተው አስከሬናቸውን ለይተው ተረክበዋል " ሲሉም አክለዋል።

የ25 አመት ወጣት ባለ ትዳርና የአንድ ልጅ አባት የሆነው መራጃው አበበ የተባለውን የእህታቸው ልጅ በዚህ የመሬት ናዳ ያጡት አቶ ተስፋየ የተባሉ የአካባቢው ነዋሪ ከአንድ አመት ከ10 ወር በኃላ የእህታቸውን ልጅ አስከሬን አግኝተው አፈር ማልበሳቸው የመንፈስ እረፍት እንደሰጣቸው ይናገራሉ።

የመሬት ናዳው በተከሰተበት ወቅት ቤተሰብ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ እና መንግስት ርብርብ አድርጎ እንደነበር የገለፁት አቶ ተስፋየ እግዜር ባለው ቀን ጏደኞቻቸው በሌላ አቅጣጫ ሲቆፍሩ አስከሬናቸውን አይተው እንደተናገሩ ገልጸዋል።

" እኛም አስከሬናቸው ሲወጣ ተገኝተን እንደተመለከትነው የፊት ገፃቸው እንዳለ ክርር ብሎ ስለነበር ወንድሞቻችንን ለመለየት አልተቸገርንም " ብለዋል።

" ከቤተዘመድ ጋር በወገል ጤና ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን አፈር አልብሸዋለሁ " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#SafaricomEthiopia

2 ቀን ብቻ ቀረው!  ቀጣይ ሚሊየነር ማን ይሆን ?🏆💚 ዛሬዉኑ የበሽ ጥቅልን ይግዙ፤ ሚሊየነር የመሆን እድሎን ያስፉ!

📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፡
https://onelink.to/ewsb22

የቴሌግራም ቦታችን: /channel/official_safaricomet_bot

ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ!

#SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
#Besh

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

‎" ተጠርጣሪው ጭካኔ በተሞላበት መልኩ ሕፃኑን በመግደል ተከራይቶ ይኖርበት በነበረው የሟች ታዳጊ አያት ግቢ በሚገኝ መፀዳጃ ቤት መጣሉን ከተያዘ በኋላ በሰጠው መረጃ አስክሬኑ ተገኝቷል " - ፖሊስ

➡️ " የአርባምንጭ ነዋሪዎችን ያስቆጣ ድርጊት የፈፀመዉ ግለሰብ በጭር ጊዜ ውስጥ ተገቢዉን ፍርድ ያገኛል "


በአርባ ምንጭ ከተማ ‎በቀን 3/3/18 ዓ/ም ናትናኤል ማይክል የተባለ በግምት የ10 ዓመት ታዳጊ ከቤት መጥፋቱን ቤተሰቦች ለፖሊስ ያሳውቃሉ።

ይህን ተከትሎ ፖሊስ ፍለጋ ይጀምራል።

ፖሊስ ከሁሉም የፀጥታ መዋቅሮች ጋር በመሆን ክትትልና አፕሬሽን ሲያደርግ ቆይቶ ዛሬ አንድ ተጠሪጣሪ ለማምለጥ ሲሞክር በቁጥጥር ስር መዋሉን ‎የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ክበበው አዳል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

‎ተጠርጣሪው ወርቁ አሰፋ ይባላል።

ግለሰቡ በአርባ ምንጭ ከተማ ሴቻ ቀበሌ ዶሳ ቀጠና ፖሪቲ ስፕሪንግ ሆቴል ጀርባ ተከራይቶ በሚኖርበት ግቢ ውስጥ የነበረን ታዳጊ አፍኖ በመውሰድ ከወላጆቹ ገንዘብ መጠየቁንና የሕፃኑ ወላጅ እናት የተጠየቀችውን 50 ሺህ ብር በባንክ ማስተላለፏን መረጃ ማግኘታቸውን ኮማንደር ክበበው ገልፀዋል።

‎ግለሰቡ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተምሮ የተመረቀ እንደሆነ በሚገልፅ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ምክንያት በቅርቡ ከሚሰራበት ትምህርት ቤት መባረሩን መረጃዎች እንደሚያመላክቱ ኮማንደር ክበበው ተናግረዋል።

ይኸው ግለሰብ ኢ-ሰብዓዊ በሆነ ጭካኔ በተሞላበት መልኩ ሕፃኑን በመግደል ተከራይቶ ይኖርበት በነበረው የሟች ታዳጊ አያት ግቢ በሚገኝ መፀዳጃ ቤት ውስጥ መጣሉን ከተያዘ በኋላ በሰጠው መረጃ አስክሬኑ መገኘቱንም አስረድተዋል።

‎ግለሰቡ ይህን ሕዝብን ያስቆጣ ዘግናኝ ድርጊት ከፈፀመ በኋላ በሚኒባስ ተሳፍሮ ከከተማ ለመውጣት ሲሞክር የፀጥታ ኃይሉ ከመረጃና ደህንነት ተቋም ጋር በመሆን ባደረገው ክትትል በጋሞ ዞን ምዕራብ አባያ ወረዳ ፉራ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቀዋል።

‎ፖሊስ አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሕዝቡን ያስቆጣ ዘግናኝ ድርጊት የፈፀመውን ግለሰብ ለሕግ በማቅረብ ፈጣንና ተገቢውን ፍርድ እንደሚያሰጥም ገልፀዋል።

‎ሕብረተሰቡ በትዕግስት እና በመፅናናት የምርመራና የፍርድ ውሳኔዉን እንዲጠባበቅ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ማህበረሰቡ ፦
- መኖሪያ ቤቶችን በሚያከራይበት ወቅት፣
- የአልጋ ቤት አገልግሎት በሚሰጥበት ወቅት፣
- በቅጥርና ውሎች ወቅት ግለሰቦችን ህጋዊ የቀበሌ ነዋሪነት ወይም ፋይዳ የዲጂታል መታወቂያ መያዛቸውንና ትክክለኛ አድራሻቸውንና የመጡበት ምክንያት ፣ የሚሰሩበት ተቋም ወይም ድርጅትን በማጣራት እንዲሁም ህጋዊ ተያዥ መኖሩን በማረጋገጥ ማከራየትና አገልግሎት መስጠት እንደሚያስፈልግ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawssa

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የበሽታዉ መንስኤ ማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus) መሆኑን መለየት ተችሏል " - ጤና ሚኒስቴር

የጤና ሚኒስቴር በደቡበ ኢትዮጵያ ክልል በጅንካ ከተማ የሄሞራጅከ ፊቨር (Viral Hemorragic Fever) በሽታ መከሰቱን እና የበሽታዉን ምንነት በማረጋገጥ ላይ መሆኑን መግለጹ ይታወቃል፡፡

ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ የበሽታዉ መንስኤ ማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus) መሆኑን መለየት ተችሏል ብሏል።

የዘረመል ምርመራው የተከናወነው በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ብሄራዊ ሪፈረንስ ላብራቶሪ ነው።

መግለጫው "በዚህም የዘረመል ምርመራ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ የተገኘዉ ቫይረስ ሌሎች ምስራቅ አፍሪካ ሃገራት ላይ ከዚህ በፊት ከተከሰቱት ጋር ተመሳሳይ ዝርያ ያለዉ መሆኑ ታዉቋል" ነው ያለው።

በተጨማሪም በዛሬው እለትም አዲስ የበሽታውን ምልክት ያሳየ ወይም በቫይረሱ የተጠረጠረ ሰው ያልተገኘ መሆኑን ሚኒስትሩ ያሳወቀ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የተለያዩ የሙያ ስብጥር ያካተተ ከፍተኛ ፈጣን ምላሽ ሰጭ ቡድን ወደ ከልሉ በመላከ በሽታዉን የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብሏል።

ከነዚህም ውስጥ :-

° የማህበረሰብ አቀፍ የቅኝት ስራዎች፣

° በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ለይቶ ማከም፣

° የማህበረሰብ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እና ከተጠረጠሩ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸዉን ሰዎች የመለየት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተገልጿል።

በሃገር አቀፍ እንዲሁም በክልል ደረጃ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች የክስተት አስተዳደር ስርዓት (Incident Management System) ተቋሞ የፈጣን ምላሽ ስራዎችን በማስተባበር ላይ ይገኛል ተብሏል።

ጤና ሚኒስቴር:-

➢ ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚተላለፉ መረጃዎችንና የጥንቃቄ መልዕክቶችን መከታተልና መተግበር፣

➢ የበሽታው ምልከት የሆኑትን በአፍ፣አፍንጫ እና ሌሎች የሰውነት ክፍሎች የመድማት፣ትኩሳት፣ማስቀመጥ እና ማስመለስ ምልከት ሲኖር ወደ ህክምና ተቋማት መሄድና በወቅቱ የላቦራቶሪ ምርመራ ማድረግ፣

➢ ምልክት ከታየበት ማንኛዉም ሰዉ ጋር ንክኪ በሚኖርበት ግዜ ራስን የመከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም፣

➢ ሁልጊዜ እጅን በውሃና ሳሙና መታጠብ ወይም በሳኒታይዘር ማጽዳት እንደሚያስፈልግ አሳስቧል።

ማንኛውም ጤና ተቋም ለታካሚዎች ልየታ ልዩ ትኩርት በመስጠት የማርበርግ በሽታ (Marburg viral disease) መሰል በሸታ መለየት፣ ማከም እና በአፋጣኝ ሪፖርት ማድረግ እንደሚያስፈልግም በመግለጫው ጠቁሟል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Tecno_Spark_40_Pro+

Tecno Spark 40 Pro+ 16 GB RAM እንዲሁም 256 GB የሚሞሪ ስፔስን አካቶ ስለመጣ አግጅ ማራኪ እና ፈጣን ስልክ ከበቂ ስፔስ ጋር በአንድ ላይ ሰጥቶታል፡፡ ታዲያ ምን ይጠብቃሉ የTecno Spark 40 Pro+ ስልኮችን ዛሬ ነገ ሳይሉ በእጆት ያስገቡ!!

#Spark40Pro+ #SlimeverStrongForever #TecnoAI #TecnoSpark40Series

@tecno_et

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

'' ማህበራዊ ሚድያ የልጆቻችንን ጊዜ ፣ ልጅነታቸውን እና ደህንነታቸውን እየሰረቀ ነው " - ካርሎን ስቴጅ ኦልሰን 

ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች የማህበራዊ ሚድያ እንዳይጠቀሙ እገዳ ለመጣል መወሰኑን የዴንማርክ መንግስት አሳወቀ።

የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜት ፍሬድሪክሰን በባለፈው ወር ለፓርላማ መክፈቻ ባደረጉት ንግግር የህፃናት የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ እገዳ እንዲጣል ጥሪ አቅርበው ነበር። ይህንን ተከትሎ በዴንማርክ ፓርላማ ውስጥ ያሉ አብዛኛዎቹ ፓርቲዎች ዕቅዱን እንደሚደግፉ ተናግረዋል፡፡

'' ማህበራዊ ሚድያ የልጆቻችንን ጊዜ ፣ ልጅነታቸውን እና ደህንነታቸውን በመስረቅ ላይ ሲሆን እኛም ይህንን በማስቆም ላይ ነን ፤ ይህም የሚደረገው በዲጂታል ዓለም ውስጥ ህፃናትን እና ወጣትቶችን ለመጠበቅ ነው '' ሲሉ የዲጂታል ጉዳዮች ሚኒስትር ካርሎን ስቴጅ ኦልሰን ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሯ የትኞቹ የማህበራዊ ሚዲያ ላይ እገዳ እንደሚጣል እና እንዴት እንደሚተገበር በግልፅ አላሳወቁም ፤ ነገር ግን ወላጆች ከ13 ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ያሉ ልጆች የተወሰኑ መተግበሪያዎች ለመጠቀም እንዲችሉ ይፈቀድላቸዋል ብለዋል፡፡

ዴንማርክ በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ከመጀመሪያዎቹ ሀገራት አንዷ እንደመሆኗ መጠን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የዕድሜ ገደቦችን ለማስተዋወቅ አንድ ትልቅ እርምጃ እንደምተወስድ ተገልጿል።

#SocialMedia #Denmark

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#እንድታውቁት

ስለ ዓይን ጤና የሚነገሩ የተሳሳቱ እምነቶች / አመለካከቶች ምን ምን ናቸው ?

ብዙ ሰዎች በማህበረሰብ ውስጥ ስለ ዓይን ጤና የሚነገሩ ነገሮችን እውነት እንደሆኑ ያምናሉ። ነገር ግን እነዚህ ብዙ እምነቶች የተሳሳቱ እና ከሳይንስ ውጪ ናቸው።

በእነዚህ አንዳንድ እምነቶች ወይም አመለካከቶች ምክንያት ዓይናችንን በተገቢው መንገድ መንከባከብ ወይም መጠበቅ እንዳንችልና የዓይን ክትትል እንዳይኖረን ያደርጋል።

ማህበረሰብ ውስጥ በስፋት  ከተሰራጩ የተሳሳቱ አመለካከቶች ፦

1. " መነጽር ማድረግ ዓይንን ያበላሻል ወይም አንዴ መነፅር ማድረግ ከተጀመረ በዛው ይለምዳል "

ይህ የተሳሳተ አመለካከት ነው።

መነጽር እይታን አያበላሽም፣ በትክክል እንዲታየን ይረዳናል። ለምሳሌ፦ ለቅርብ ዕይታ ችግር ፣ ለርቀት ዕይታ ችግር ፣ ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ ለሆኑ አዋቂዎች ማንበቢያ ወዘተ... ጥራት ያለው ዕይታ ያስገኛል።

የዕይታችን ጥራት በተፈጥሮ ወይም በሌላ በሽታ ይቀየራል ይህ ደግሞ መነፅር ከማድረግ ጋር ሚያገናኘው ነገር የለም።

ጥንቃቄ ፦ በዓይን ሀኪም ብቻ የታዘዘ መነፅር ይጠቀሙ።

2. " ካሮት መብላት የእይታ ችግርን ይፈውሳል "

ካሮት ቫይታሚን A እናገኝበታለን ይህም ለዓይንም ሆነ ለሌሎች ሰውነታችን ክፍል በጣም አስፈላጊ ነው ነገር ግን በራሱ በሽታን አይፈውስም።

3. " የእይታ ችግር እድሜያቸው የገፋ ሰዎች ላይ ብቻ ነው የማከሰተው "

ይህ ፍጹም ስህተት ነው።

የእይታ ችግር በህፃናትና በወጣቶችም ላይም በሰፊው ይስተዋላል። ለዓይን ጤና እንክብካቤ ካልተደረገ ችግሩ በየትኛውም እድሜ ሊከሰት ይችላል።

በእድሜ ምክኒያት ብቻ የሚመጡ የዓይን ህመሞች ግን አሉ።

4. " የዓይን ምርመራ ሚያስፈልገው የዓይን ህመም ሲኖር ብቻ ነው "

ይህም የተሳሳተ አመለካከት ነው።

መደበኛ የዓይን ምርመራ ማድረግ ቀደም ብሎ የዓይን ችግር እንዲታወቅ ይረዳል።

በርካታ የዓይን ችግሮች በጊዜው ከታወቁ አመርቂ ህክምና አላቸው። ምሳሌ ፦ amblyopia (የዓይን መስነፍ) amblyopia በጊዜ ታውቆ ካልታከመ የህክምናው ውጤት እምብዛም ነው።

5. " የፀሐይ መነጽር ለማጌጥ ብቻ ነው "

ይህ የተሳሳተ አመለካከት ነው።

ትክክለኛ የፀሐይ መነጽር ማድረግ ከፀሀይ የሚመጣ የUV ጨርን ከዓይን ይጠብቃል፣ ስለዚህ የዓይን ጤና መንከባከብያም ጭምር ነው።

💬 በእውነታዊ መረጃዎች የዓይናችንን ጤና  እንከባከብ፣ መደበኛ ምርመራ እናድርግ። የተሳሳቱ አስተሳሰቦች የዓይን ጤና ይጎዳሉ።

ምንጮች፦
- World Health Organization (WHO), Eye Care Guidelines 2023
- American Academy of Ophthalmology (AAO), Common Eye Myths and Facts
- Centers for Disease Control and Prevention (CDC), Vision Health Initiative

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ

@tikvahethiopia

Читать полностью…
Subscribe to a channel