tikvahethiopia | Unsorted

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1583422

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። መረጃ እና መልዕክት ፦ 0998999899 ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም 0979333111 @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Subscribe to a channel

TIKVAH-ETHIOPIA

#AddisAbabaRevenuesBureau

ማንም ልጅ በልቶ እንጂ ሳይበላ በባዶ ሆድ ትምህርት ቤት ገብቶ መማርም ሆነ መጫወት አይችልም የሚለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰው ተኮር የሆነው የተማሪዎች ምገባ ስንትና ስንት ደሀ እናቶችን እፎይ አሰኘ! ልጇ እየቦረቀ በማለዳ ወደትምህርት ቤት ሲሄድ መርቃ ከመሸኘት በቀር ጓዳዬ ባዶ ነው ምን እቋጥርለታለሁብሎ መጨነቅ ለከተማችን እናቶች ተረት ሆነኮ።የአዲስ አባ ከተማ አስተዳደር የልማት ስራዎች ሰው ተኮር ናቸው ለሚለው አንዱ መገለጫ የተማሪዎች ምገባ ነው።

(የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ)

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ምርጫ2018

ፓርቲዎች ለመጪው ምርጫ እጩዎቻቸውን እያስተዋወቁ ይገኛሉ።

ገዢው ብልፅግና ፓርቲም ለመጪው ምርጫ የሚወዳደሩ እጩዎችን እያስተዋወቀ ሲሆን ከነዚህም እጩዎች መካከል ጋዜጠኛ ፣ አርቲስት ፣ እንዲሁም አርሶ አደር የሆኑ ይገኙበታል።

በአዲስ አበባ ለምክር ቤት እጩ ሆነው ከቀረቡት መካከል አንደኛው በሙዚቃ አቀናባሪነት የሚታወቀው ካሙዙ ካሳ ነው።

ሙዚቀኛው ፥ ስራው አርቲስት ፣ የትምህርት ደረጃው መካከለኛ ደረጃ ትምህርት እንዲሁም የሚወዳደረው የካ ክፍለ ከተማ መሆኑ ተገልጾ ይፋ ተደርጓል።

ሌላኛዋ የቀድሞ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛዋ ወ/ሮ በሻቱ ቶሎማርያም እዛው የካ ክፍለ ከተማ እጩ ሆና ቀርባለች።

ከዚህ በተጨማሪ አቶ ሹሜ ግዛው የተባሉ አርሶ አደርም በእጩነት ቀርበዋል።

በዚህ ክፍለ ከተማ ሌሎች በፌዴራል ደረጃ፣ በከተማ፣ በክፍለ ከተማ አመራርነት ላይ የሚገኙ እጩዎችም ቀርበዋል።

ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከቀረቡ እጩዎች መካከል ደግሞ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ፣ ወ/ሮ አይሻ መሃመድ ፣ ዶ/ር ሌሊሴ ነሜ ይገኙበታል።

መረጃው የየካ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ልጅቷ ሜዳ ላይ ብቻዋን ነው የተገኘችው። የአባቷን ስም ስትጠየቅ 'አባ'፣ የእናቷን ስም ስትጠየቅ 'እማ' ነው የምትለው " - ነዋሪ

በኦሮሚያ ክልል፣ ሸገር ከተማ ልዩ ቦታው አሸዋ ሜዳ ጉጄ የሚባል ቦታ ቤተሰቦቿን የማታውቅ ህፃን ስለተገኘች ቤተሰቦቿ እንዲወስዷት ተጠየቀ።

ይህን መልዕክት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ያደረሰ የአካባቢው ግለሰብ፣ " ልጅቷን ሜዳ ላይ አግኝተው አንስተዋት። ወደ መስጅድ ሊያስገቧት " ሲሉ፣ እቤት አድራ በሚዲያ በኩል ቤተሰቦቿ እንዲፈለጉ ማሳሰቡን ገልጿል።

" ልጅቷ ሜዳ ላይ ብቻዋን ነው የተገኘችው። የአባቷን ስም ስትጠየቅ 'አባ'፣ የእናቷን ስም ስትጠየቅ 'እማ' ነው " የምትለው " ብሎ፣ ቤተሰቦቿን መናገር እንዳልቻለች ገልጿል።

" ከየት እንደመጣች ስትጠየቅም የምናገረው ነገር የለም። ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት አሸዋ ሜዳ አካባቢ ጉጄ ከሚባል ቦታ ነው የሆነች ሴት ያገኘቻት " ብሏል።

" ወደ መስጂድ ስትወስዳት፣ መስጊጅድ ከማን ጋር ታድራለች? ለብቻዋ ከምንትሆን አንቺ ውሳጃት በሚል ተስማምተው ከሴትዮዋ ቤት እንዳደረች" በመግለጽ፣ "እኔ" የሚሉ ቤተሰቦቿ እንዲወስዷት ጠይቋል።

ቤተሰቦቿን የምታውቁ በ 0912685024 ወድላችሁ አሳውቁ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ሩሲያ በግብርናው ዘርፍ የሚፈለገውን የአሞኒየም ናይትሬት ማዳበሪያ የውጭ ኤክስፖርት ለጊዜው ማገዷን አስታወቀች።

የሀገሪቱ የግብርና ሚኒስቴር እንደገለጸው ይህ የእገዳ ውሳኔ ከመጋቢት 12 እስከ ሚያዝያ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለአንድ ወር ይቆያል።

ዓላማው ለሀገር ውስጥ የግብርና ስራ በቂ የማዳበሪያ አቅርቦት መኖሩን ለማረጋገጥና የውስጥ ገበያውን ፍላጎት ለማርካት እንደሆነ ተጠቁሟል።

ሩሲያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛውን የአሞኒየም ናይትሬት ምርት የምታቀርብ ሀገር እንደመሆኗ ይህ ውሳኔ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየታየ ያለውን የማዳበሪያ አቅርቦት እጥረት ይበልጥ ሊያባብሰው እንደሚችል ተሰግቷል።

በተለይ በአሜሪካ/እስራኤል - ኢራን ጦርነት ምክንያት የሆርሙዝ ሰርጥ የንግድ መስመር መስተጓጎልና የዓለምን ሲሶ ያህል የማዳበሪያ ንግድ ማስተጓጎሉ በዘርፉ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ባለበት ወቅት የተላለፈ ውሳኔ መሆኑ የችግሩን አሳሳቢነት ይጨምረዋል።

ይሁን እንጂ በሀገራት መካከል በሚደረጉ ቀጥታ የመንግስት ስምምነቶች የሚላኩ ምርቶች ከዚህ እገዳ ውጭ መሆናቸው ተገልጿል።

መረጃው የብሉምበርግ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ፎቶ ፦ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል የነበሩት አቶ ርስቱ ይርዳው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሆነው ተሹመዋል።

#EthiopianFederalPolice

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

✨🎁 20% ቅናሽ በ20 ጥቅሎች!

ወደ ቴሌብር ሱፐርአፕ ጎራ ብለን ከተዘረዘሩት ጥቅሎች አንዳቸውን ስንገዛ እስከ 20% ተጨማሪ ጉርሻ አለን!

በልዩ ቅናሽ የቀረቡትን ጥቅሎች ይመልከቱ: https://bit.ly/20packages20discount

*127# ደውለን ወይም ቴሌብር ሱፐርአፕን https://bit.ly/telebirr_SuperApp ጭነን ስንመዘገብ እንዲህ ነን!

#ደንበኛ_ስንሆን_እንዲህ_ነን
#ስንመዘገብ_እንዲህ_ነን
#ስንጭን_እንዲህ_ነን
#ስናስጀምር_እንዲህ_ነንየሻሞ

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ማስታወሻ🔔

ዛሬ 11፡30 ይጠናቀቃል!

የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ዛሬ መጋቢት 15/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 ላይ ይጠናቀቃል።

በቀሩት ሰዓታት ይመዝገቡ!

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
➫ ከ9-11ኛ ክፍል የተማሩበት ውጤት
➫ አሁን ላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪ መሆን

በድጋሜ ተፈታኝ ከሆኑ https://register.eaes.et ላይ ከዚህ በፊት የተፈተኑበትን አድሚሽን ካርድ በማስገባትና 750 ብር ክፍያ በመፈጸም መመዝገብ ይችላሉ።

Via @tikvahuniversity

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የማህበራዊ ሚዲያ ኮንተንት ክሪኤተር ነዎት?

ከዩቲዩብ እና ከሌሎች ማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎች የሚላክልዎ የማረጋገጫ ደብዳቤ፣ የክፍያ ማስታወቂያ ወይም ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶች ለመቀበል አስበዋል ?

እንግዲያዉስ የኢትዮጵያ ፖስታ ዘመናዊ መፍትሄ የሆነዉን የ“Virtual P.O. Box” (ሳጥን አልባ የመልዕክት አገልግሎት) ይዞሎት መቷዋል፡፡

🔹 የተረጋገጠ እና ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት
🔹 መልዕክቶችዎን በማንኛውም ቦታ እና በማንኛውም ሰዓት ማግኘት የሚያስችልዎ
🔹 ፈጣን ማሳወቂያ እና ቀላል አስተዳደር

📱 ዛሬውኑ መተግበሪያውን ከአፕስቶር ወይም ከፕሌይ ስቶር "VIRTUAL POST" ብለው በማውረድ
አልያም 👉በ app.ethio.post በመግባት በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ይመዝገቡ። — አንድም አስፈላጊ መልዕክት እንዳይዘገይ!

ለበለጠ መረጃ በነጻ የስልክ መስመር 8536 ይደውሉልን ወይም በቴሌግራም @etpccsbot ያግኙን።

#Ethiopost #virtual po box
Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | ethiopostal">TikTok |

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ቪድዮ ፦ በኒውዮርክ ላጓርዲያ አውሮፕላን ማረፊያ የኤር ካናዳ ኤክስፕረስ የመንገደኞች አውሮፕላን እያረፈ ባለበት ወቅት በማረፊያ መንገዱ ላይ ከነበረ የእሳት አደጋ መኪና ጋር በመጋጨቱ የሁለት ሰዎች ሕይወት አልፏል።

ትላንት ሌሊት በተከሰተው በዚህ አደጋ በአጠቃላይ 41 ሰዎች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ዘጠኙ በከባድ ሁኔታ ሆስፒታል ይገኛሉ። በመኪናው ውስጥ የነበሩ ሁለት መኮንኖችም በሕክምና ላይ ናቸው።

አደጋው የደረሰው የእሳት አደጋ መኪናው ወደ ሌላ አስቸኳይ ጥሪ ለማምራት በበረራ መንገዱ ላይ እየተንቀሳቀሰ በነበረበት ወቅት ሲሆን አውሮፕላኑ በሰዓት 39 ኪሎ ሜትር ፍጥነት ላይ ነበር።

ቪድዮ ፦ ከሶሻል ሚዲያ

መጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

በኢራን እና አሜሪካ መካከል የድርድር ተስፋ አለ ?

" 10 ቢሊዮን ዶላር የወጣበትን ትልቁን የኤሌትሪክ ማመንጫ ፋብሪካቸውን ለማፈንዳት እየጠበቅን
ነበር " - ትራምፕ

➡ " የጊዜ ገደቡን ያራዘሙት የኢራን አጸፋዊ እርምጃ ስላስፈራቸው እንጂ በድርድር አይደለም " - የኢራን ዜና ወኪሎች

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን የኃይል መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ለመፈጸም አስቀምጠውት የነበረውን የ48 ሰዓታት የጊዜ ገደብ ወደ አምስት ቀናት ማራዘማቸውን አስታውቀዋል።

ፕሬዝዳንቱ ይህን የጊዜ ገደብ ያራዘሙት ከቴህራን ጋር በመካከለኛው ምስራቅ ስላለው ግጭት " በጣም ጥሩ እና ውጤታማ " ውይይቶችን ማድረጋቸውን ተከትሎ እንደሆነ ገልጸዋል።

ውይይቱ ዋነኛው አጀንዳ ስለ ኢራን የኒውኩሌር ፕሮግራም እንደሆነ አመልክተዋል።

" ለሰላም ሲባል የኒውክሌር ፕሮግራሟን ለመተው ልትስማማ ትችላለች " ብለዋል።

" ነገ ጠዋት፤ በእነርሱ የሆነ ሰዓት ላይ፣ ለመገንባት 10 ቢሊዮን ዶላር የወጣበትን ትልቁን የኤሌትሪክ ማመንጫ ፋብሪካቸውን ለማፈንዳት እየጠበቅን ነበር " ሲሉ ተናግረዋል።

" በጣም ጥሩ ነበር፤ የገንዘብ እጥረት አልነበረም፤ በአንድ ተኩስ ይወድማል፤ ይፈራርሳል። ለምን ይህን ይፈልጋሉ ? እነርሱ ናቸው የደወሉት፤ እኔ አልደወልኩም። እነርሱ ደወሉ። ስምምነት ላይ መድረስ ፈልገዋል " ብለዋል።

" እኛ ከስምምነት ላይ ለመድረስ በጣም ፈቃደኞች ነን። ጥሩ ስምምነት መኖር አለበት፤ እና ሌላ ጦርነት ሊኖር አይችልም፤ የኒውለክሌር ጦር መሣሪያ አይኖርም " ሲሉ ትራምፕ ገልጸዋል።

" ከእንግዲህ በኋላ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ አይኖራቸውም። በዚያ ይስማማሉ። ያለዚያ ግን ስምምነት አይኖርም " ብለዋል።

ስምምነት ላይ መድረስ ከተቻለ የነዳጅ ዋጋ በፍጥነት ሊቀንስ እንደሚችል ጠቁመው ነገር ግን አሁንም ለስምምነቱ ሙሉ ዋስትና እንዳልሌለና ሁኔታዎች ካልተሳኩ ጥቃቱ እንደሚቀጥል አስጠንቅቀዋል።

ትራምፕ ንግግር መጀመሩን ቢናገሩም የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የተለያዩ የሀገሪቱ የዜና ወኪሎች (ፋርስ እና ታስኒምን ጨምሮ) መረጃውን ሙሉ በሙሉ አስተባብለዋል።

ኢራን ከአሜሪካ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ምንም ዓይነት ንግግር አለማድረጓን ገልጻለች።

የሆርሙዝ ሰርጥ አሁንም " ጦርነት ለከፈቱብን ዝግ ነው " ያሉ ሲሆን " ትራምፕ የጊዜ ገደቡን ያራዘሙት የኢራን አጸፋዊ እርምጃ ስላስፈራቸው እንጂ በድርድር አይደለም " ሲሉ የዜና ምንጮቹ ገልጸዋል።

የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተጀመረ ንግግር እንዳለና አገራቸው ይህንን እንደምታውቀውና እንደምትደግፈው ገልጸዋል።

ስታርመር ማንኛውም ስምምነት በተለይ በኢራን የኒውክሌር ጉዳይ ላይ ጠንካራ ገደቦችን ሊያካትት እንደሚገባ አሳስበዋል።

መረጃው ከቢቢሲ፣ ታስኒም፣ ፋርስ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ነው የተሰበሰበው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት

ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Modern Accountancy) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን።

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 መሠረታዊ አካውንቲንግ እና ኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 ስልጠናው ከፒስቺሪ በተጨማሪ በExcel፣ Word እና ተግባራዊ ዶክመንቶች ታግዞ የሚሰጥ ነው።

የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
Tiktok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
Linkedin: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ነዳጅ

በአሜሪካ-እስራኤል እና በኢራን መካከል እየተባባሰ የመጣው ጦርነት የዓለምን የነዳጅ ገበያ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደከተተው ሲሆን ነገ ሰኞ የነዳጅ ዋጋ ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ ጭማሪ ሊያሳይ እንደሚችል ተገምቷል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሆርሙዝ ሰርጥ በ48 ሰዓታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ካልተከፈተ የኢራን የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን " እንደሚደበድቡ " መዛታቸውን ተከትሎ የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በበርሜል 112.19 ዶላር ደርሷል።

ኢራን ጥቃት የሚፈጸምባት ከሆነ በምላሹ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙና ከአሜሪካ ጋር ግንኙነት ያላቸውን የኃይል እና የውሃ ማጣሪያ ተቋማት ላይ ጥቃት እንደምትሰነዝር አስጠንቅቃለች። ይህም በቀጠናው የሚገኙ እንደ ሳዑዲ ዓረቢያ እና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ያሉ አገራት የውሃ እና የኃይል አቅርቦት ላይ ከፍተኛ አደጋ ሊደቅን እንደሚችል ተመላክቷል።

ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ የትራምፕ ማስጠንቀቂያ በገበያው ላይ ከፍተኛ አለመረጋጋትን ፈጥሯል።

እስካሁን በዘለቀው የ22 ቀናት ጦርነት የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት 440 ሚሊዮን በርሜል የሚጠጋ የነዳጅ አቅርቦት ከዓለም ገበያ እንዲጠፋ ያደረገ ሲሆን የዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ (IEA) አቅርቦቱን ወደ ነበረበት ለመመለስ እስከ 6 ወራት ሊፈጅ እንደሚችል አስታውቋል።

መረጃው የሮይተርስ ዜና ወኪል ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ቪድዮ ⬆️

በጀርመንና በኦስትሪያ እንዲሁም በሌሎች የአውሮፓ ሀገራት የሚተገበረው " Rettungsgasse ወይም የድንገተኛ ጊዜ መንገድ " አሰራር በትራፊክ መጨናነቅ ወቅት አምቡላንሶችና የእሳት አደጋ መኪኖች በፍጥነት እንዲያልፉ የሚያስችል የነፍስ አድን ዘዴ ነው።

ህጉ ማንኛውም አሽከርካሪ በትራፊክ ምክንያት ፍጥነቱን መቀነስ ሲጀምር አምቡላንስ እስኪመጣ ሳይጠብቅ ወዲያውኑ ወደ ግራ ወይም ወደ ቀኝ በመጠጋት በመሃል ክፍት መንገድ እንዲፈጥር ያስገድዳል።

ይህ ቀላል የሚመስል አሰራር የነፍስ አድን ሰራተኞች ከቦታ ቦታ የሚደርሱበትን ጊዜ በ40% በመቀነስ የአደጋ ተጎጂዎች የመትረፍ ዕድላቸውን እስከ 80% ያሳድገዋል።

ህጉን አለማክበር ደግሞ በነዚህ ሀገራት እስከ መንጃ ፈቃድ እገዳ የሚያደርስ ከባድ ቅጣት ያስከትላል።

ቪድዮ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#MPESAEthiopia

የ2018 የሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪ.ሜ ሩጫ በታላቅ ድምቀት ተካሄደ 🇪🇹🏁

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አበቤ ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ ክቡር ሻለቃ ሀይሌገ/ስላሴ ፣ በተለያዩ የሙያ መስኮች የተሰማሩ ተምሳሌት ሴቶች፣ ሴት አምባሳደሮች፣ ሴት አትሌቶች እና የክብር እንግዶች በተገኙበት የ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. የሩጫ ውድድር ተካሂዷል።

በዛሬው ዕለት በቦሌ ጎዳናዎች ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች ተገኝተው የአንድነት እና የጥንካሬ ተምሳሌትነታቸውን አሳይተዋል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከM-PESA ኢትዮጵያ ጋር በመሆን የሴቶችን አቅም ለማሳደግ እና ለማበረታታት የሚያደርገውን ጉዞ በዚህ ዝግጅት ላይ አሳይትዋል።

ለተሳተፋችሁ እና ለዚህ ታላቅ ቀን አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ በሙሉ ምስጋናችን የላቀ ነው።

#MPESAEthiopia #GreatEthiopianRun
#WomenFirst5km

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

20 ግዙፍ አየር መንገዶች በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ምክንያት እስካሁን ወደ 53 ቢሊዮን ዶላር ማጣታቸው ተሰማ።

በአሜሪካ-እስራኤል እና ኢራን ጦርነት ሳቢያ በዓለም ላይ የሚገኙ ሃያ (20) ግዙፍ አየር መንገዶች ጦርነቱ ከተጀመረበት የካቲት ወር ጀምሮ 53 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የገበያ ዋጋቸውን ማጣታቸውን ፋይናንሻል ታይምስ ዘግቧል።

ዘገባው የአየር መንገዶቹን ስም በዝርዝር ከማስቀመጥ ተቆጥቧል።

አየር መንገዶቹ ይህን ያህል ከፍተኛ ሀብት ሊያጡ የቻሉት ፦
- የነዳጅ ዋጋ በመናሩ፣
- የጸጥታ ስጋት ባለባቸው ቀጠናዎች በረራዎች በመሰረዛቸው፣
- የበረራ መስመሮች በመቀየራቸው ምክንያት መሆኑ ተመልክቷል።

ይህም በዓለም አቀፉ የአቪዬሽን ዘርፍ እና በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ መናጋት መፍጠሩ ተነግሯል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መጋቢት 12 ቀን 2018

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Iran
#StraitofHormuz

ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን ሙሉ በሙሉ እንዳልዘጋችው እየገለጸች ትገኛለች። ይሁን እንጂ መተላለፊያውን ለመጠቀም ጥብቅ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጣለች።

እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች ምንድናቸው ?


በዋነኝነት ኢራን የሚፈጸምባትን ጥቃት የማይደግፉ እና ከጥቃት ፈጻሚዎቹ ጋር ግንኙነት የሌላቸው ሀገራት መርከቦች ማለፍ እንደሚችሉ ገልጻለች።

ማንኛውም አይነት መርከብ ሆርሙዝን ከመሻገሩ በፊት ከኢራን የሚመለከታቸው አካላት በተለይ ከእስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ኃይል/IRGC ጋር አስቀድሞ መገናኘትና ፈቃድ ማግኘት ይኖርበታል።

የጭነት መርከቦች በኢራን የቁጥጥር ቀጠና ውስጥ በሚያልፉበት ወቅት ለማንነት ማረጋገጫና ለጭነት ምርመራ ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው ኢራን ገልጻለች።

"ጠላት" የተባሉ ሀገራት ዕጣ ፈንታ ምንድነው ?

ኢራን " በጠላትነት " የፈረጀቻቸው ሀገራት በተለይም አሜሪካና እስራኤል እንዲሁም የእነርሱ አጋር የሆኑ ሀገራት መርከቦች በሰርጡ እንዳያልፉ ጥብቅ እገዳ ጥላባቸዋለች።

የሀገሪቱ ወታደራዊ አዛዦች " ጥቃት ከቀጠለ ሙሉ በሙሉ እንዘጋዋለን " የሚል ማስጠንቀቂያ ደጋግመው እየሰጡ ይገኛሉ።

መርከቦች ሲያልፉ ለኢራን ይከፍላሉ ?

አንዳንድ መርከቦች ለደህንነቱ የተጠበቀ መተላለፊያ እስከ 2 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍሉ እየተጠየቁ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ሀገሪቱ ግን በይፋ ወጥታ ያለችው ነገር የለም ፤ በህንድ ያለው የኢራን ኤምባሲም " 2 ሚሊዮን ዶላር ይከፈላል " የሚባለውን መረጃ ምንም መሰረት የሌለ እንደሆነ በመግለፅ አጣጥሎታል።

እንደ ህንድ ፣ ቻይና ፣ ፓኪስታን እና ጃፓን ያሉ ሀገራት መርከቦች ከቴህራን ጋር በሚያደርጉት ቀጥታ ግንኙነት መተላለፍ መቻላቸው ተዘግቧል። ለምሳሌ በቅርቡ ሁለት የህንድ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች በተለየ ሁኔታ ማለፍ እንደቻሉ ተነግሯል።

የሰርጡ አለመረጋጋት የዓለምን የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያሻቅብና የመርከብ መድን ዋጋ ከ4 እስከ 6 እጥፍ እንዲጨምር አድርጓል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የብሉምበርግ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መጋቢት 16 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" አሁን ላይ እጅግ በጣም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው። አንደኛ ትምህርቱን ጀምረናል፣ ብዙ ሄደናል፤ ግን ጨርሰን ለመመለስ ደግሞ የበጀት እጥረት አጋጥሞናል " - የፒኤችዲ ተማሪዎች

በዘንድሮው አመት መንግስት ለሰራተኞቹ የደመወዝ ማሻሻያ ሲያደርግ ለሁለተኛ ዲግሪ እና ለፒኤችዲ ተማሪዎች የምርምር እና የኪስ ገንዘብ ባለመሻሻሉ በምርምር ስራቸው ላይ ጫና እያሳደረባቸው መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጹ።

ማንነታቸው እንዲገለጥ ያልፈለጉ አንድ የባህርዳር ዩኒቨርስቲ የማህበራዊ ሳይንስ የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪ አሁን ላይ በመንግስት ለምርምር ስራ የሚመደበው በጀት እና በየወሩ የሚሰጣቸው የኪስ ገንዘብ አነስተኛ በመሆኑ የምርምር ስራቸውን ለማቆም እየተገደዱ መሆኑን ተናግረዋል።

አሁን ላይ የሚሰጣቸው የምርምር እና የኪስ ገንዘብ በቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ  ስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት በወጣ ተመን መሆኑን ገልፀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው የፒኤችዲ እና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ምን አሉ ?

" እኔ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነኝ። ለምዝገባም ሆነ ለእያንዳንዱ ጉዳይ የምንቀሳቀሰው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው። በዚህም ለትራንስፖርት የማወጣው ወጪ ከደሞዜ በላይ ነው። ለምርምር የተሰጠኝ ብር ካለቀ ቆይቷል።

አሁን ላይ የምርምር ስራዬን መስራት አልቻልኩኝም። ምክንያቱም ቤተሰብ አስተዳድራለሁ፣ ልጅ አስተምራለሁ፤ በዚህ ላይ ለምርምር ስንቀሳቀስ የተሰጠኝ ብር አይበቃም። ​በዚህ ምክንያት ትምህርቱን ለማቆም የምንገደድበት ሁኔታ ላይ ደርሰናል።

ለፒኤችዲ እና ለሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች በበጎ ፈቃደኝነት የገንዘብ ድጎማ ያደርጋሉ። ግን ይሄ ወጥ የሆነ መመሪያ በዩኒቨርሲቲዎች ስለሌለ እንደ ዩኒቨርሲቲዎቹ ማኔጅመንት በጎ ፈቃድ ነው የሚወሰነው። አፍ አውጥተህ መጠየቅ አትችልም፣ ምክንያቱም መመሪያ የለም።

በዘንድሮው አመት መንግስት እንደሀገር የደሞዝ ማሻሻያ ሲያደርግ ትምህርት ሚኒስቴር የፒኤችድ ተማሪዎች እንዲማሩ ከፈለገ እነዚህ ነገሮች አብረው እንድሻሻሉ ማድረግ ነበረበት። ለምርምር የሚመደበው በጀት ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪ 45,000 ብር ነው፣ ይህ የትም አያደርስም።

በየወሩ የሚሰጠን የኪስ ገንዘብ ወይም የቤት ኪራይ 1300 ነው። ይህ ከምንም የማይሆን ስለሆነ አሁን ላይ እጅግ በጣም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው። አንደኛ ትምህርቱን ጀምረናል፣ ብዙ ሄደናል፤ ግን የምርምር ስራችንን ጨርሰን ለመመለስ ደግሞ የበጀት እጥረት አጋጥሞናል።

አሁን ላይ ፒኤችዲ የሚማር ሰው የለም ይባላል፤ ግን ወዶ አይደለም። ቤተሰብ እያስተዳደርክ መማር ስለማትችል መተው ነው አማራጭ የምታደርገው። ነገ ላይ ደግሞ በየዘርፉ አነስም በዛም የተማረ የሰው ሀይል ለሀገሪቷ ያስፈልጋታል።

ይህን የሚመለከተው ትምህርት ሚኒስቴር ስለሆነ ከምን አግባብ እንዳዩት፣ የደሞዝ ማሻሻያ ሲደረግ የምርምር በጀት እንዴት እንዳልታየ ጠይቁልን " ብለዋል።

ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገው የጅማ ዩኒቨርሲቲ የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪ ለመንግስት ሰራተኞች ወቅቱን ያማከለ የደመወዝ ጭማሪ ቢደረግም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሁለተኛ እና የሶስተኛ ዲግሪ ለምንማር ተማሪዎች የምርምር ገንዘብ ጭማሪ አለመደረጉ የኑሮ ውድነቱን ታሳቢ ያደረገ አይደለም ሲል ተናግሯል።

" አሁን ላይ ለሦስተኛ ዲግሪ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ለምርምር የሚሰጠን ገንዘብ 60 ሺህ ብር ብቻ ነው። ​ይሄ ብር ድሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ወቅት የወጣለት ተመን ነው። ከዚያ ወዲህ የተጨመረ ነገር የለም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ይህ ገንዘብ በስአቱ በነበረው የዋጋ ግሽበት (inflation) ታስቦ የተሰራ ነው። በወቅቱ ለፒኤችዲ ተማሪዎች 30 ሺህ ብር የነበረውን አሻሽለው ወደ 60 ሺህ ብር ከፍ አድርገውት ነበር። አሁን የሚሰጠን የኪስ ገንዘብም በዚሁ ወቅት የወጣ ተመን ነው። እነዚህ ነገሮች መንግስት ደመወዝ ሲሻሻል አብሮ ማሻሻል ነበረበት " ብለዋል።

" አሁን ላይ ባለው የኑሮ ሁኔታ ትምህርታቸውን የማይጨርሱ የፒኤችዲ ተማሪዎች አሉ፣ በ4 አመት ሊጨርሱ የሚገባቸውን 8 እና 10 አመት ይፈጅባቸዋል። በኑሮ ውድነት ተገፍተው ወደ ሌላ የቀን ስራ የሚገቡ ሰዎችም አሉ። እኔም ቤተሰቦቼን ለማስተዳደር ስል ሌላ ተጨማሪ ስራ እየሰራሁ ነበር። ነገር ግን ሃሳቤ በየቦታው በመበተኑ በአንዱም እንኳ ውጤታማ ለመሆን ተቸግሬያለሁ " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ ከትምህርት ሚኒስቴር ምላሽ ለማግኘት ይጥራል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Turkey : የቱርኪዬ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶጋን ተባብሶ የቀጠለው የኢራን ጦርነት ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እያስከተለ መሆኑን ገልጸው ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆም እየቀረቡ ያሉ ጥሪዎችን እንደሚደግፉ አስታወቁ።

ኤርዶጋን " ጦርነቱ ከፍተኛ የኢኮኖሚ መዘዝ እያስከተለ ነው ፤ ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆም የቀረቡ ጥሪዎችን እንደግፋለን " ብለዋል።

መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት በ2018 ዓ.ም የሚካሄደውን 7ኛ ዙር አገራዊ ምርጫ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ በአገሪቱ በተለይም በአማራ፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች ያለው የጸጥታ ችግር ለምርጫ አስቻይ አለመሆኑን ገልጿል።

መንግሥት ጦርነቶችን በሰላማዊ ድርድር እንዲፈታ፣ የፖለቲካ እስረኞችን እንዲፈታና ለዕጩዎች የደህንነት ዋስትና እንዲሰጥ ቀደም ብሎ ጥሪ ቢያቀርብም፣ በተግባር ግን ግጭቶች በመቀጠላቸውና በዕጩዎች ላይ የሕይወት አደጋ እየደረሰ በመሆኑ ከፍተኛ ስጋት እንደገባው አመልክቷል።

በመሆኑም በጠቀሳቸው አካባቢዎች ያለው የጸጥታ ሁኔታ በአስቸኳይ ተፈትቶ ለዕጩዎችና ለአስተባባሪዎች አስተማማኝ ዋስትና እስካልተገኘ ድረስ ፓርቲው በእነዚህ አካባቢዎች ከሚያደርጋቸው ይፋዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች እንደሚቆጠብና በቀጣይ ተለዋጭ ውሳኔ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

በሞባይል እየደወለ" የከተማዋ ከንቲባ ነኝ " በማለት ያጭበረበረ ተጠርጣሪ ይዞ  በማጣራት ለህግ ማቅረቡን የወቕሮ ፓሊስ አስታወቀ።

የወንጀል ተግባሩ በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የውቕሮ ከተማ የተፈፀመ ሲሆን ተጠርጣሪው ተወልደ ኣለም ይባላል።

ግለሰቡ ቀደም ሲል የመከላከያ ሰራዊት አባል እንደነበረ በውቕሮና ዓዲግራት ከተሞች እየተመላለሰ እንደሚኖር ፓሊስ በምርመራው እንዳረጋገጠ ገልጿል።

የካቲት 6 ቀን 2018 ዓ.ም በውቕሮ ከተማ ነዋሪ ለሆኑ እንዲት እናት ሁኔታቸው አጥንቶ ሞባይል በመደወል የከተማዋ ከንቲባ እንደሆነ ራሱን አስተዋውቆ ዘይትና ስኳር ከቀበሌ እንዲወስዱ በመንገር 15 ሺህ ቅድመ ክፍያ ወደ የግል ባንክ አካውንቱ ገቢ እንዲያደርጉ በማግባባት  አታሏል።

የካቲት 15/2018 ዓ.ም ደግሞ በከተማዋ የመስኖ ስራ ወደ ተሰማሩ ግለሰብ በመደወል ለስራቸው የሚጠቀሙበት ጀነሬተር የሚሆን 146 ሊትር ነዳጅ እንዲወስዱ ነግሮ ከ23 ሺህ ብር በላይ ወደ ግል የባንክ አካውንቱ ገቢ በማስደረግ አጭበርብሯል።

እንዲሁም የካቲት 28/2018 ዓ.ም ወደ አንድ ግለሰብ ሞባይል በመደወል በትግራይ ደረጃ የከተማዋ አርአያ በመሆን መመረጡንና በሽልማት ለተበረከተችለት የአሜሪካ ዝርያ ያላት የወተት ላም ከመቐለ ወደ ውቕሮ ለማምጣት ከ12 ሺህ ብር በላይ ወደ የግል ባንክ አካውንቱ ገቢ እንዲያደርግ በማሳመን ማጭበርበሩ የፓሊስ የምርመራ ሰነድ አመልክቷል።

ህብረተሰቡ ከዚህ መሰል የማታለል ተግባራት ራሱ እንዲጠብቅ ያሳሰበው የውቕሮ ከተማ ፓሊስ ተጠርጣሪው ላይ ክስ መመስረቱ አስታውቋል ሲል ድምፂ ወያነ ሚድያ ዘግቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update
#MiddleEast

የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ተባብሶ ቀጥሏል፤ የመብረድ ምልክትም አላሳየም።

ባለፉት 24 ሰዓታት ምን ሆነ ?

➡ ኢራን በርካታ የሚሳኤል ማዕበሎችን ወደ እስራኤል አስወንጭፋለች። በቴል አቪቭ ሰሜናዊ ክፍል በሚገኝ አንድ መንደር ላይ ሚሳኤል ያረፈ ሲሆን በመኖሪያ ህንፃዎች እና ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። እስካሁን ባለው መረጃ ቢያንስ 6 ሰዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።   ከቴል አቪቭ በተጨማሪ ኤይላት እና ዲሞና የጥቃቱ ኢላማ ነበሩ።

➡ እስራኤል ከአሜሪካ ጋር በመቀናጀት በኢራን ውስጥ በሚገኙ ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ላይ ሰፊ የአየር ድብደባ ፈጽማለች። የሚሳኤል ማምረቻ ፋብሪካዎች፣ የደህንነት ተቋማት እና የኢራን አብዮታዊ ዘበ የጦር ሰፈሮች ኢላማ ነበሩ። ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ ከ200 በላይ የአየር ድብደባዎች ተፈጽመዋል።

➡ በኢራን መገናኛ ብዙኃን እየተሰራጨ ባለው ዘገባ መሠረት ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን የኃይል መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር አቅደውት የነበረውን እቅድ በ5 ቀን ማራዘማቸውን በገለጹ በጥቂት ሰዓታት ልዩነት ውስጥ በኢራን ሁለት የጋዝ ፋብሪካዎችና በአንድ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ላይ የአሜሪካ ጥቃት ተፈጽሟል።

➡ ባለፉት 24 ሰዓታት ኢራን የአሜሪካ አጋር ወደሆኑ የባህረሰላጤው ሀገራት ሚሳኤል እና ድሮን አዝንባለች። አብዛኛው በአየር መከላከያ የከሸፉ ናቸው።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ፦ 7 ባሊስቲክ ሚሳኤሎች እና 16 ድሮኖች ቢወረወርባትም የሀገሪቱ የአየር መከላከያ ሥርዓት አብዛኞቹን ጥቃቶች ማክሸፍ የቻለ ሲሆን እስካሁን የደረሰ ከፍተኛ ውድመት አልተመዘገበም።

ሳውዲ አረቢያ፦ በሀገሪቱ ላይ በርካታ ድሮኖች እና ሚሳኤሎች ቢዘንቡም የሳውዲ መከላከያ ኃይል ከአንድ ደርዘን በላይ ድሮኖችን በአየር ላይ መትቶ መጣሉን አስታውቋል።

ባህሬን፦ በአንድ ተቋም ላይ የእሳት አደጋ የተከሰተ ሲሆን፣ አደጋው ከኢራን ጥቃት ጋር ግንኙነት ሊኖረው እንደሚችል ተጠርጥሮ ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል።

በአጠቃላይ ኢራን ወደ አሜሪካ ወዳጅ በሆኑ ባህረሰላጤው ሀገራት ኢላማዎች የምትሰነዝረው ጥቃት ቀጥሏል።

ንግግር አለ ? የዲፕሎማሲ ጥረት እየተደረገ ነው ?

በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለው ግንኙነት እጅግ የተወሳሰበ እና እርስ በርሱ የሚጋጭ መረጃዎች የሚወጡበት ሆኗል።

ፕሬዝዳንት ዶላንድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረጉ ንግግሮች "ውጤታማ" መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን አንዳንድ መረጃዎች በፓኪስታን ወይም በኦማን ስብሰባዎች ሊካሄዱ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጥተዋል።

የኢራን መንግስት ግን ይህንን መረጃ " ሀሰተኛ ወሬ " ሲል ያስተባበለ ሲሆን ምንም ዓይነት ንግግር እየተካሄደ እንዳልሆነ በይፋ አስታውቋል።

መሬት ላይ ያለው እውነታ አንዳንድ ቀጥተኛ ያልሆኑ ንግግሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ቢጠቁም እስካሁን ድረስ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረሰ ምንም ዓይነት እውነተኛ ስምምነት የለም።

እጅግ በጣም አሳሳቢው የነዳጅ ዋጋ ምን ላይ ነው ?

በአሁኑ ወቅት በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ግጭት ሳቢያ የሆርሙዝ ሰርጥ የንግድ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ በመስተጓጎሉ የዓለም የነዳጅ ገበያ በከፋ ቀውስ ውስጥ ነው።

እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ ዛሬ ላይ የነዳጅ ዋጋ በበርሜል ከአንድ መቶ ዶላር በላይ ነው።

ባለሙያዎች ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ይህ ቀውስ እጅግ አስከፊ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

መረጃው ከተለያዩ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የተሰባሰበ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በደረሰው የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ በአርባምንጭ ከተማ ብቻ 70 ምሰሶዎች በጎርፍ ተወስደዋል " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን፣ በአርባ ምንጭ ሪጅን አጋጥሞ በነበረው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል።

እንደ አገልግሎቱ መግለጫ ከሆነ፣ በአደጋው ምክንያት የኃይል መቆራረጥ አጋጥሞባቸው ለነበሩ አካባቢዎች ጊዜያዊ መስመር በመዘርጋት መልሶ የማገናኘት ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።

በደረሰው ድንገተኛ አደጋ የደረሰውን ጉዳት ዝርዝር አገልግሎቱ የገለጸ ሲሆን አደጋው በከተማውና በዙሪያው በሚገኙ ወረዳዎች ላይ ባደረሰው ጉዳት፦

- በአርባ ምንጭ ከተማ 70 የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች፣ ከ4 ኪሎ ሜትር በላይ የሚረዝም የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ እና 4 የኤ.ኤም.አይ (AMI) ቆጣሪዎች በጎርፍ ተወስደዋል።

- በአካባቢው ወረዳዎች ማለትም በገረሴ፣ ከንባ፣ ጨንቻና ምዕራብ አባያ ወረዳዎች በድምሩ ከ150 በላይ ምሰሶዎችና የ10 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ መስመር ውድመት ደርሷል።

- በአርባ ምንጭ ከተማ ቁጥር አንድ ማዕከል ግምጃ ቤት አዳዲስ ደንበኞችን ተጠቃሚ ለማድረግ ተዘጋጅተው የነበሩ 155 ምሰሶዎች በጎርፍ ተወስደዋል።

የአርባ ምንጭ ሪጅን የአገልግሎት መስጫ ማዕከል የቴክኒክ ባለሙያዎችና የሪጅኑ ሰራተኞች በቅንጅት በመሆን የመልሶ ግንባታ ስራዎችን እያከናወኑ ይገኛሉ ተብሏል።

በዚህም በተከናወነው የጥገና ሥራ፣ የመኖሪያ ቤታቸው ሙሉ በሙሉ በጎርፍ ከተወሰደባቸው ደንበኞች ውጪ፣ በአርባ ምንጭ፣ ገረሴ፣ ከንባ፣ ጨንቻና ምዕራብ አባያ የሚገኙ ነዋሪዎች በሙሉ በሚባል ደረጃ የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘት መጀመራቸውን ተቋሙ አረጋግጧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

በቪዛ ካርድዎ በፊፋ ዓለም ዋንጫ አይረሴ ጊዜ ያሳልፉ !

አንድ ሺ ብርና ከዛ በላይ በቪዛ ካርድዎ ግብይት በመፈፀም የዕጣ ቁጥር ይቀበሉ!ዕድለኛ ከሆኑም በ2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫ ድንቅ ጊዜ ያሳልፋሉ ! ትኬቱን የማሸነፍ ዕድል በእጅዎ ነው ! ዕድሜ ለቪዛ ! !

ሊንኩን ይንኩ፤ ግብይትዎን ያሳድጉ፤ ወደ እኛ ይምጡ
https://mcnpkmnf81rz7s-0mxl8ql8p6yz8.pub.sfmc-content.com/hehzo3aayy2?src=telegram&cmp=fifa

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ምርጫ2018

የኢዜማ እጩዎችን በመሰረዝ " የብልጽግና አባላት " በመተካታቸው ለቦርዱ ቅሬታ መቅረቡ ታውቋል።

በቁጫ ወረዳ ምርጫ ክልል ኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) እጩዎችን በመሰረዝ " የብልጽግና ፓርቲ አባላት " ፣ " ለእጩነት " እንዲቀርቡ በመደረጉ ለምርጫ ቦርድ ቅሬታ ማስገባታቸውን በወረዳው የኢዜማ ጽህፈት ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ለምርጫ ቦርድ የተጻፈው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው ደብዳቤም፣ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በቁጫ ወረዳ ኢዜማን ወክለው በተመለመሉ አራት እጩዎች ፋንታ የፓርቲው አባል ያልሆኑ " የብልጽግና አባላት " እንዲተኩ መደረጉን ያስረዳል።

በወረዳው የኢዜማ ጽ/ቤት ዋና ሰብሳቢ ሻ/ባሻ ጋሳላ ጋኔቦ፣ እጩዎች ተመልምለው ወደ አዲስ አበባ የኢዜማ ጽሕፈት ቤት ማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲላክ መደረጉን ገልጸው፣ " እኛ የኢዜማ እጩዎችን በመሰረዝ አራት የብልጽግና አባሎችን " አስገብተዋል ሲሉ ከሰዋል።

ድርጊቱ የተፈጸመው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት ሲሆን፣ ለድርጊቱ ተጠያቂ ያደረጉትን የአዲስ አበባ ኢዜማ ጽህፈት ቤትን ጠይቀው መፍትሄ ባለማግኘታቸው ከቀናት በፊት ጉዳዩን ለምርጫ ቦርድ አሳውቀው ምላሽ እየጠበቁ መሆኑን ዋና ሰብሳቢው ገልጸዋል።

ቦርዱ ይህንኑ ጉዳይ በፍጥነት ካላስተካከለ ከ2013 ዓ/ም ጀምሮ በቁጫ " የተገነቡ " 2 ሺሕ 850 የኢዜማ አባል " ልንበትን ነው " ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" መፍትሄ ከተሰጠ ወደ ኢዜማ እንመለሳለን፤ ካልሆነ ድርጅቱን ለቀን እንወጣለን ብለን ቁጫ ላይ በጠቅላላ ጉባዔ ተወስኗል። 2 ሺሕ 850 አባል ለመበተን ተዘጋጅቷል " ሲሉ አክለዋል።

የተሰረዙበት የሚጠረጥሩት ጉዳይ ካለ ስንጠይቃቸው ደግሞ፣ " በ2013 ዓ/ም 'የቁጫ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁህዴፓ) ደግፋችኋል' በሚል የገንዘብ መቀጮ እና እስራት ሁሉ ተፈጽሞብን ያን ተቋጭቷል " ብለው፣ መሰል ስጋት አድሮበት እንዳይሆን ስጋታቸውን ገልጸዋል።

(የእጩዎችን ስም ዝርዝር የያዘው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" አውሮፕላኑ ለሁለት ወር ጊዜ ነው የሄደው የእነሱ አውሮፕላኖች እስከዛ ተጠግነው ይደርሱላቸዋል፤ ከዛ አውሮፕላኑ ተመልሶ ለእኛ ስራ ይመጣል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ (ለቲክቫህ ኢትዮጵያ)

የኡጋንዳ አየር መንገድ ተቋርጦ የነበረውን የረጅም ርቀት በረራ ለመቀጠል እንዲረዳው፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 787-8 ድሪምላይነር አውሮፕላንን በጊዜያዊነት መከራየቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

የአየር መንገዱ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል የኪራይ ውል ስምምነቱ ለሁለት ወር የሚቆይ ነው ብለዋል።

"የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለዚህ ስራው ከኡጋንዳ አየር መንገድ ተገቢውን ክፍያ ያገኛል" ያሉ ሲሆን በምን ያህል ወርሃዊ ክፍያ ኪራዩ እንደተከናወነ ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኡጋንዳ አየር መንገድ ጋር በጊዜያዊ ውል ስምምነት የአውሮፕላን ኪራዩን የፈጸመው የኡጋንዳ አየር መንገድ ያሏቸው ሁለት ኤርባስ A380 አውሮፕላኖች ባልታሰበ ምክንያት ከአገልግሎት ውጪ በመሆናቸው ምክንያት ወደ ለንደን የሚያከናውኑት በረራ እንዳይቋረጥ ለማድረግ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስምምነቱን በሚመለከት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ምን አሉ ?

" በኢንዱስትሪው ሁልጊዜም ሊሰመርበት የሚገባው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ አየር መንገድ ነው።

እኛ Pan-African Airline ነን ብለን ስንል ለማለት ብቻ አይደለም ተግባራችንን የምንናገረውን መምሰል አለብን።

ስለዚህ የዩጋንዳ አየር መንገድ ችግር ላይ ወድቋል፤ የማኔጅመንት ለውጥ አለ፣ አውሮፕላኖች ችግር ገጥሟቸዋል።

ይህ በሚሆንበት ጊዜ እንድንረዳቸው ጠየቁን ሲጠይቁን አንድ ሙሉ የበረራ ሰራተኞችን እና አንድ አውሮፕላን ሰጥተናቸዋል።

ይሄ በኢንዱስትሪው Wet Lease ይባላል ዌት ሊዝ ማለት ይዘው የሚበሩት የዩጋንዳ አየር መንገድን የበረራ ቁጥር ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ፍላግ (Flag) ነው የሚሰሩት።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ህግና ስርዓት ተከትሎ ነው የሚሰሩት ስለዚህ ከዚህ የኪራይ ስምምነት ነው ያደረግነው ማለት ነው።

ከነሙሉ ኩሩው (Crew)፣ ፓይለቶቹን፣ ሆስተሶችን፣ የጥገና ሰራተኞችን ሁሉም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ይይዝና እዛ ሆኖ (ዩጋንዳ) ስራውን ይሰራል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለዛ ስራው ተገቢውን ክፍያ ይጠይቃል።

አውሮፕላኑ ለሁለት ወር ጊዜ ነው የሄደው የእነሱ አውሮፕላኖች እስከዛ ተጠግነው ይደርሱላቸዋል፤ ከዛ አውሮፕላኑ ተመልሶ ለእኛ ስራ ይመጣል " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት ከቦስተን ፓርትነርስ( ኩሪፍቱ ሪዞርቶች) ጋር የስራ ስምምነት ተፈራረመ

ሁለቱ ተቋማት በስምምነቱ ከታች የተጠቀሱትን ዋና ዋና ስራዎች በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል

1ኛ እንደ እንጦጦ ፓርክ፣ አፍሪካ ቪሌጅ ፣ ኩሪፍቱ ቢሾፍቱ ሪዞርቶች ራይድ የኤሌክትሪክ መኪኖችን በመመደብ ከቦስተን ፓረተነርስ ጋር በጋራ ይሰራል፣

2ኛ በኩሪፍቱ ሪዞርቶች በሚካሄዱ ትልልቅ ስብሰባዎች፣የጋብቻ ስነ-ስርዓቶች እና ኮንሰርቶች በሚዘጋጁበት ወቅት ራይድ ትራንስፖርት በቂ እና አስተማማኝ ትራንስፖርት ያቀርባል

3ኛ የራይድ ትራንስፖርትንም ሆነ የቦስተን ፓርትነርስን አገልግሎቶችን መልካም ስም እና ዝና በጠበቀ መልኩ የጋራ የገበያ ትስስር፣ የማስተዋወቅ እና የብራንድ ፕሮሞሽን ስራዎችን በትብብር ይሰራሉ፡፡

4ኛ አዳዲስ የገበያ ተደራሽነትን የሚያሰፉ ፓኬጆችን በጋራ በማዘጋጀት ለተጠቃዎች ለማድረስ በጋራ እንስራለን ብለዋል

https://ride8294.com/ride-signs-with-kuriftu/

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ስፖርት : ማንችስተር ሲቲ የካራባኦ ዋንጫ ፍጻሜ አሸናፊ ሆነ።

ማንቺስተር ሲቲ ከቀደኛ ተቀናቃኙ #አርሴናል ጋር ያደረገውን የፍጻሜ ጨዋታ ፍልሚያ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ዋንጫውን በልቷል።

የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኦሬሊ 2x ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ቲክቫህ ስፖርት 👇
/channel/tikvahethsport/80106

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ሁሉም የስራ ማስኬጃዎች ለጊዜው ቆመው የየካቲት ወር ደመወዝ ይከፈል " - ታደሰ ወረደ (ሌ/ጄነራል)

የትግራይ ክልል የመንግስት ሰራተኞች የየካቲት ወር ደመወዝ ከውስጥ ገቢ እንዲከፈል መወሰኑ ተገለጸ።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር " ከፌደራል መንግስት በጀት አልተላከም " በሚል ምክንያት ከየካቲት ወር 2018 ዓ.ም ጀምሮ የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ መክፈል ማቆሙን በደብዳቤ ማሳወቁን ተከትሎ፣ በአሁኑ ወቅት የየካቲት ወር ደመወዝ ከክልሉ የውስጥ ገቢ አቅም እንዲከፈል መወሰኑ ታውቋል።

የክልሉ ፋይናንስና ሃብት ማሰባሰብ ቢሮ ባሳለፍነው የካቲት ወር መጨረሻ ሳምንት ላይ ባወጣው መግለጫ፥ ካለው የውስጥ የፋይናንስ አቅም አሰባስቦ ደመወዝ ለመክፈል ጥረት እንደሚያደርግ ገልጾ የነበረ ሲሆን በመጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ.ም በፕሬዝዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) ተፈርሞ ለሁሉም መስሪያ ቤቶች የተላከው ደብዳቤም ሁሉም የስራ ማስኬጃዎች ለጊዜው ቆመው የየካቲት ወር ደመወዝ እንዲከፈል አዟል።

በዚህም መሰረት የየካቲት ወር ደመወዝ መከፈል መጀመሩን የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል አረጋግጧል።

በሌላ በኩል፥ በክልሉ የበጀት አላላክና ደመወዝ ክፍያ መዘግየት ዙሪያ ከፌደራል መንግስት ጋር ለመወያየት ጥያቄ አቅርቦ እንደነበርና ውይይቱም መካሄዱን " ወለዶ ትግራይ " የተባለው ፓርቲ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

ፓርቲው በመግለጫው እንዳመለከተው፥ የፌደራል መንግስት ለትግራይ የሚልከው በጀት ከታለመለት የልማትና መልሶ ግንባታ ውጪ የማዋል አዝማሚያ አለ የሚል ስጋት በውይይቱ ወቅት ተነስቷል።

በተጨማሪም ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከመንግስት ሰራተኞች የግል ፍላጎት ውጪ ደመወዝ እንዲቆረጥ ያወጣው መመሪያ ጉዳይም መነሳቱንና መመሪያው እንዲሻር መጠየቁን ፓርቲው አመልክቷል።

ፓርቲው ፥ ለአፈጻጸም አስቸጋሪ ቢሆንም የፌደራል መንግስት ከክልሉ ፋይናንስ ቢሮ በሚቀርብለት ፔሮል መሰረት ደመወዙን በቀጥታ ወደ እያንዳንዱ ሰራተኛ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ የሚያደርግበት ሁኔታ እንዲመቻች ከፌደራል የስራ ኃላፊዎች ጋር መነጋገሩን ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በክልሉ የሚገኙ 137 ሺህ የመንግስት ሰራተኞችን የሚመለከተው ይህ ጉዳይ ላይ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ የሚሰጥ ምላሽ ካለ ተከታትሎ ያቀርባል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" አብዛኛው ሠራተኛ እኛን አይመርጥም፤ ስራ ቢቀጠርም እንኳ ረጅም ጊዜ አይቆይም " - ባለሃብቶች

በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ባለሀብቶች በተለይ ከፋይናንስ ተደራሽነት ከባንክ አገልግሎት ክፍያ መናርና ከመሠረተ ልማት እጥረት ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶች እያጋጠሟቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ይህን ያሉት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የፋይናንስ ተቋማት በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ለማጠናከር ካለሙ የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር ውይይት ባካሔደበት ወቅት ነው።

የውይይቱ ተሳታፊ ባለሀብቶች በዝርዝር ምን አሉ ?

" በድሬዳዋ በሚገኙ ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች የሚሰሩ ባንኮች ለዛ የሚመጥን አገልግሎት ለመስጠት በብቃት ራሳቸውን አደራጅተው አለመቅረባቸው ትልቅ ፈተና ሆኖብናል።

በተለይም ሀገራችን ውስጥ የውጭ ምንዛሬ አካውንት ከፍተን ስንጠቀም ከአገልግሎት ክፈያ በተጨማሪ ሌሎች ተደራራቢ ወጪዎች ተደምረው አላስፈላጊ ወጫችን እስከ 10% እና ከዚያ በላይ ደርሷል።

አምራቾችን፣ ባንኮችንና ገዢዎችን የሚያስተሳስር የሦስትዮሽ ስምምነት ተጠናክሮ ካልቀጠለ፣ የነፃ ንግድ ቀጠና በሚከፈትበት ወቅት የሀገር ውስጥ አምራቾች ህልውና ምን ሊሆን ነው ? ምክንያቱም ጥሬ ዕቃ በጣም ውድ ነው፤ ያለቀለት ዕቃ ደግሞ በጣም ርካሽ ነው። ይህም ህልውናችንን አደጋ ላይ ይጥለዋል።

ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች መግባት ለሚፈልጉ ባንኮች ብሔራዊ ባንክ ያወጣው መመሪያ ከ5 ወይም 7 ባንኮች ውጭ ሌሎቹን የሚያስተናግድ አይደለም። መመሪያው ለሚያስቀምጠው መስፈርት የሚመጥን ባንክ የለም።

​የኢንዱስትሪ ፓርኮች የተቋቋሙት ከከተማ ርቀው በመሆኑ አብዛኛው ሠራተኛ እኛን አይመርጥም ፤ ስራ ቢቀጠርም እንኳ ረጅም ጊዜ አይቆይም። ይህንን ችግር ለመፍታት ደመወዛቸውን ማሳደግ ወይም ሌሎች ጥቅማጥቅሞችን መስጠት እንዳለብን ብንረዳም ይህ ደግሞ በድርጅታችን ላይ ከፍተኛ የወጪ ጫና እየፈጠረብን ነው። ይህም ተወዳዳሪነታችንን እያዳከመው ይገኛል።

ከዚህም ባለፈ የውጭ ምንዛሬ ተመን በመለዋወጡ የብር ዋጋን ስለሚያለዋውጠው ጫና እየፈጠረብን ነው። ይህንን ችግር ለመፍታት ጥሬ ዕቃን ከሀገር ውስጥ ማግኘትና ምርትን ለሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች ማቅረብ ላይ ትኩረት ይደረግ።

​በአሁኑ ወቅት ባለው የነዳጅ አቅርቦት እጥረት ምክንያት አብዛኞቹ መኪኖቻችን መንገድ ላይ ተሰልፈው ነው የሚውሉትም የሚድሩትም። ይህም ስራችን ላይ ችግር ፈጥሮብናል ያሉ ሲሆን መንግሥት ለእነዚህ ችግሮች አስቸኳይ መፍትሔ ይሰጣቸው። " ብለዋል።

ለተነሱ ጥያቄዎች በብሔራዊ ባንክ የስታቲስቲክስ ዳይሬክተር አበባየው ዱፌራ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ምን አሉ ?

" በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ አንድ ባንክ ብቻ አገልግሎት ሲሰጥ ነበር። ብቻውን በመሆኑ የአገልግሎት መስተጓጎሎች ሲፈጠሩ ነበር። አሁን ላይ የወጣው መመሪያ ይህን ያስቀራል።

ከባንኮች ጋር በአገልግሎት ክፍያ ዙሪያ ተደራደሩ። የውጭ ባንኮች ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ ደግሞ ክፍያው በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል ብለን እንጠብቃለን።

በሀገር ውስጥ የውጭ ምንዛሬን እንዴት ማዘዋወር እንችላለን ለሚለው ጥያቄ ስራዎች ተጀምረዋል ነው መልሴ።

በአዲሱ መመሪያ ከአንዱ አካውንት ወደ ሌላ አካውንት በሀገር ውስጥ ማስተላለፍ ይቻላል። ይህ አሰራር ልክ እንደ ብር የክፍያ ስርዓት (RTGS) በቅርቡ ወደ ስራ ይገባል ብለን እናስባለን።

ባንኮች የራሳቸው የሆነ ነፃነት አላቸው። እኛ መመሪያ እናወጣለን እንጂ በነፃ ገበያ ስርዓት ውስጥ ስላለን ለዚህ ስጡ ለዚያ አትስጡ ብለን ጣልቃ መግባት አንችልም።

ወደ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚገቡ ባንኮች ላይ የምናስቀምጠው መስፈርት ጠጠር ያለ የሆነውም የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ነው። መጀመሪያ አቅም ያላቸው ይግቡ እና ከዛ ሌላውን በሒደት የማሻሻል ስራ ይሰራል " ብለዋል።

More Tikvah FB Page https://www.facebook.com/61588053582297/posts/122107187733268452/?app=fbl

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ምን ላይ ነው ?

ባለፉት ቀናት የአሜሪካ/እስራኤል እና የኢራን ጦርነት ወደ ሌላ ከባድ ምዕራፍ ተሸጋገረ ነው።

ከምንም በላይ የሚጠፋው የሰው ልጆች ህይወት እና መሰረተ ልማት እየጨመረ ነው። እስካሁን በተለያዩ ሀገራት በጦርነቱ ምክንያት ከ2000 እስከ 2500 ሰዎች ሞተዋል።

ሌላች ዋና ዋና ጉዳዮችን በአጭሩ እንመልከት።

1. የሆርሙዝ ሰርጥ ቀውስ ብሶበታል።

20 በመቶ የሚሆነው የዓለም የነዳጅ ምርት የሚያልፍበት የሆርሙዝ ሰርጥ በኢራን መገደቡ ለዓለም ስጋት ሆኖ ቀጥሏል።

አሜሪካ ለኢራን የ48 ሰዓታት ማስጠንቀቂያ የሰጠች ሲሆን፤ ሰርጡ የማይከፈት ከሆነ በኢራን የኃይል ማመንጫዎችና መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት እንደምትፈጽም አስታውቃለች።

2. የሚሳኤል ጥቃቶች ተስፋፍተዋል።

ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ቀናት ኢራን ወደ እስራኤልና ወደ ተለያዩ የባህረ ሰላጤው አገራት ኢላማዎች በርለታ የሚሳኤል ጥቃት ሰንዝራለች። አሁን ጦርነቱ በኢራንና በአሜሪካ/እስራኤል መካከል ብቻ ሳይሆን በመላው መካከለኛው ምስራቅ እየተስፋፋ ይገኛል።

3. በኃይልና በመሰረተ ልማት ላይ ስጋት ተደቅኗል።

አሁን ላይ ጦርነቱ ወታደራዊ ኢላማዎችን ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚያዊ ስርዓቶችን ማውደም ላይም በእጅጉ እያነጣጠረ ነው። አሜሪካ የኢራን የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫዎችን ለማውደም ስትዝት ፤ ኢራን በበኩሏ በባህረ ሰላጤው አገራት የሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮችንና የኃይል መሰረተ ልማቶችን እንደምትመታ አስጠንቅቃለች።

4. የዓለም ነዳጅና የኢኮኖሚ ቀውስ እየተባባሰ ነው።

የነዳጅ ዋጋ ባለፉት ዓመታት ታይቶ የማይታወቅ ጭማሪ አሳይቷል። በዓለም ዙሪያ የቤንዚን እና ናፍጣ ዋጋ እየናረ ሲሆን የአየር መንገዶችም በነዳጅ እጥረት ምክንያት በረራዎችን እየቀነሱ ነው። ይህ ሁኔታ በጥቂት ቀናት በአፍሪካ አገራት ከፍተኛ አሉታዊ ተፅእኖ ያመጣል።

5. ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ አደገኛ ሁኔታዎች ምንድናቸው ?

የነ አሜሪካ ቀጣዩ እርምጃ የኢራን የኃይል አቅርቦት መረብን መምታት ሊሆን ይችላል። ኢራንም መልሳ የአሜሪካ አጋሮች ላይ ተመሳሳይ ምላሽ ልትሰጥ ትችላለች። ይህም ቀጠናዊ ጦርነትን ሊያስነሳና የዓለም ኢኮኖሚን ወደ ከፍተኛ ቀውስ ሊከተው እንደሚችል ይጠበቃል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ወሳኙን የሆርሙዝ ሰርጥ በ48 ሰዓታት ውስጥ እንድትከፍት ካልሆነ ግን የኃይል ማመንጫዎቿ እንደሚመቱ አስጠንቅቀዋል።

ኢራን ዛቻውን አጣጥላ ጥቃት ከተፈጸመ ግን የከፋ አፀፋ ለመስጠት መዘጋጀቷን አሳውቃለች። ከጠላቶች መርከብ ውጭ ሌላው ማለፍ ይችላል ብላለች።

መረጃዎቹ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የተወሰዱ ናቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

Читать полностью…
Subscribe to a channel