tikvahethiopia | Unsorted

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1519094

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Subscribe to a channel

TIKVAH-ETHIOPIA

#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራትም፣ በብራንድም፣ በባትሪ ቆይታም  አስተማማኝ የሆኑ የተለያዩ  ሞዴል ያላቸዉ  በፈለጉት ስክሪን መጠን ኮር እና ጀነሬሽን   አሉን።

ላፕቶፕ  ከመገዛቶ በፊት ማወቅ ያለባቹሁን ወሳኝ ነገሮች እናስረዳለን። ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች  ወ.ዘ.ተ ሁሉም አሉን ። በላፕፖቻችን ጥራት ላይ አንደራደርም!
!
የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።

@sww2844 0928442662 / 0940141114

https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የ5 ተማሪዎቻችን ህይወት አልፏል " - መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ

በቀን 22/01/2017 በግምት ከጥዋቱ 4:00 ገደማ የመቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ በነበረ በተለምዶ " አባዱላ " የሚባለው መኪና ላይ በደረሰ የመገልበጥ አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል።

እንደ አማራ ፖሊስ መረጃ ፤ አደጋው የደረሰው በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ 015 ቀበሌ ደቦት ልዩ ቦታው እቧዮች ኪዳነምህረት አካባቢ ነው። መኪናው ከባህር ዳር ወደ ወልድያ መስመር ወደ መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ሲጓዝ ነበር።

መኪናው በወቅቱ 21 ሰው ጭኖ ሲጓዝ እንደነበር ተነግሯል።

ከተሳፋሪዎቹ 7 ሰዎች ሲሞቱ 14 ሰዎች ላይ ጉዳት አጋጥሟል።

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ 5 ተማሪዎቹ በአደጋው እንደሞቱበትና በ13 ተማሪዎቹ ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት እንደደረሰ አሳውቋል።

ህይወታቸው ያለፈው ተማሪዎች ፥ አሜሪካ ሙሉ፣ ይርጋ ወርቁ፣ ሰናይታ ካሳ፣ አቤል ግደይ ፣ በላይነሽ ሽፈራው እንደሆነ ገልጿል።

ነፍስ ይማር !

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ደመወዝ ፦ ይህ ስለ መንግሥት ሰራተኞች ደመወዝ ጭማሪ የሚያትት ዶክመንት ባለፈው ዓመት ነሃሴ ወር ላይ ሲዘዋወር የነበር ነው።

ዶክመንቱ ከየትኛው አካል የወጣ እንደሆነ በግልጽ አይታወቅም።

በእርግጥም ከዚህ ወር ጀምሮ ወደ ትግበራ የሚገባው የመንግሥት ሰራተኞች ደመወዝ ጭማሪ ይኸው ይሁን ወይስ ሌላ ስለሚለው ጉዳይ ወይም ደግሞ ስለዚህ ዶክመንት ትክክለኝነት ወይም ትክክል አለመሆን በግልጽ ወጥቶ ምላሽ የሰጠ አንድም አካል የለም።

ይህ ዶክመንት ወጥቶ ከመሰራጨቱ በፊት አንድ ስለ ደመወዝ ጭማሪ የሚያትት ምስል ተሰራጭቶ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ' ሀሰት ' ነው ማለቱ አይዘነጋም።

ስለዚህ የደመወዝ ጭማሪ ዶክመንት ግን ወጥቶ ያስተባበለ ሆነ ማረጋገጫ የሰጠ አካል የለም።

ይህ ጉዳይ በቀጥታ ይመለከታቸዋል የተባሉ አካላትን በማነጋገር ምላሽ ለማግኘት ጥረት ብናደርግም አልተሳካም።

NB. ከላይ በፋይል የተያያዘው ስለ ደመወዝ ጭማሪ የሚያትተው ዶክመት በቀጥታ ጉዳዩ በሚመላከታቸው የትኛውም አካላት ያልተረጋገጠ ነገር ግን ደግሞ በይፋ ትክክል አይደለም ተብሎ ማስተባበያ ሆነ አስተያየት ያልተሰጠበት ነው።

#Ethiopia

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

“ለፒኤችዲ የሚመጡት ተማሪዎች የኑሮ ሁኔታ ዩኒቨርሲቲው ለብቻው ሶልቭ የሚያደርገው አይደለም፡፡ አጠቃላይ የአገሪቷ ችግር ነው ” - አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

በአንጋፋውና ራስ ገዙ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፒኤችዲ ትምህርታቸውን የሚማሩ ቤተሰብ ጭምር የሚያስተዳድሩ ተማሪዎች ኑሮው እጅግ ፈታኝ እንደሆነባቸው በምሬት ሲገልጹ ተስትውለዋል፡፡

ትምህርትቻውን የሚከታተሉት ለዛውም ሲያገኙ ሻይ በዳቦ እየተመገቡ፣ መቀየሪያ አጥተው ለበርካታ ጊዜ አንድ ልብስ ለብሰውና አንድ ጫማ ተጫምተው እንደሆነ ያነሳሉ።

በዚህም ሃፍረትና የዝቅተኝነት ስሜት አሸማቋቸው የሚያውቋቸውን ሰዎች ሲያዩ መንገድ ቀይሰው ለመሄድ፣ ቤተሰብ ላለመጠየቅ እንደተገደዱ በተሰበረ ድምጽ እሮሮ እያቀረቡ ነው፡፡ 

ይህንኑ ቅሬታ በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምን አስተያየት እንዳለው ተጠይቆ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ምን አለ ?

“ ችግሩ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ብቻ አይደለም፡፡ አጠቃላይ ችግር ነው፡፡

ነገር ግን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለይ ለድኀረ ምረቃ ፕሮግራም በተቻለ አቅም ለመፍታት ካደረጋቸው አንዱ ጥረት በአነስተኛ ኪራይ የመኖሪያ ክፍሎችን (ዶርሚተሪ) ማዘጋጀት ነው፡፡

በግል በከተማ ውስጥ እንከራይ ቢባል ክራይስ እንደሚያመጣ ማንም ሰው መገመት የሚያቅተው አይደለምና አንዱ የዩቨርሲቲው ኮንትሪቢሽን በቀላሉ የፒኤችዲ ተማሪዎች ዶርም እንዲይዙ ማድረግ ነው፡፡

በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በሚኖሩት የጥናትና ምርምር ሥራዎችም እንዲሳተፉ እያደረገም ነው ያደርጋልም፡፡

የፒኤችዲ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ፕሮግራም ውስጥ መማር ማስተማር በተወሰነ ደረጃ እስከ 3 ክሬዲት ሊሆን የሚችል ሎድ እንዲይዝ ነው የተደረገው፡፡ ይሄም ከመደገፍ አንጻር ሊታይ ይገባል፡፡

እንደ አጠቃላይ ለፒኤችዲ የሚመጡት ተማሪዎች የኑሮ ሁኔታ ዩኒቨርሲቲው ለብቻው ሶልቭ የሚያደርገው አይደለም፡፡ አጠቃላይ የአገሪቷ ችግር ነው፡፡

ከዛ ውጪ ዩኒቨርሲቲው ባለው አቅም ለመደገፍና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ፋላጎትና አቅም ኖሮት የያዘው አይደለም። ማድረግ የሚችለውን እያጣረ፣ መደገፍ የሚችለውን እያደገ ነው ያለው”
ብሏል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆነዋል።

ከኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ጋር በተያያዘ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል።

የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል መስከረም 25/ 2017 ዓ/ም በአዲስ አበባ ይከበራል ፤ ይህን ተከትሎ የሚከተሉት መንገዶች ይዘጋሉ።

- ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ላይ፤

- ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ፤

- ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ፤

- ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ አጠገብ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ (አራተኛ ክፍለ ጦር ላይ)፤

- ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለገሀር መብራት ላይ፤

- ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ፤

- ከራስ ሆቴል ወደ ስታድዮም ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ራስ ሆቴል ላይ፤

- ከሃራምቤ መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ፤

- ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ፤

- ከካዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ካዛንቺስ ሼል አጠገብ፤

- ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወስደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ፤


ከመስከረም 24/ 2017 ዓ/ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ ነው ተብሏል።

ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በ011-1-11-01-11 እንዲሁም በ991 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ መስጠት ይችላል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራትም፣ በብራንድም፣ በባትሪ ቆይታም  አስተማማኝ የሆኑ የተለያዩ  ሞዴል ያላቸዉ  በፈለጉት ስክሪን መጠን ኮር እና ጀነሬሽን   አሉን።

ላፕቶፕ  ከመገዛቶ በፊት ማወቅ ያለባቹሁን ወሳኝ ነገሮች እናስረዳለን። ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች  ወ.ዘ.ተ ሁሉም አሉን ። በላፕፖቻችን ጥራት ላይ አንደራደርም!
!
የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።

@sww2844 0928442662 / 0940141114

https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#DV2026

የ2026 የአሜሪካ ዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ማመልከቻ ከዛሬ ጀምሮ ክፍት ተደርጓል።

ለ2026 DV ለማመልከት https://dvprogram.state.gov/ ይጠቀሙ።

ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ አያስፈልግም።

ማመልከቻው እስከ ህዳር 5 /2024 ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል።

ከፍተኛ የመሙላት ፍላጎቶች ድረገጹ ላይ መዘግየቶችን ሊያስከትል ስለሚችል ለመሙላት እስከ የምዝገባው ጊዜ የመጨረሻ ሳምንት ድረስ ባይጠብቁ ይመከራል።

ዘግይተው የሚገቡ ማመልከቻዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

ህጉ ለአንድ ሰው አንድ ጊዜ ብቻ እንዲያመለክት ነው የሚፈቅደው። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የሚጠቀመው የተራቀቀ ቴክኖሎጂ ደጋግሞ የሚገቡ ማመልከቻዎችን የሚለይ ነው። ከአንድ ጊዜ በላይ አንድ ሰው ካመለከተ ሁሉንም የዛን ሰዎች ማመልከቻዎች ይሰርዛል።

ያልተሟላ ማመልከቻም ተቀባይነት የለውም።

ዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ከቪዛ አማካሪዎች ፣ ' እንሞላለን ' ከሚሉ ወኪሎችና ከሌሎች አካላት እገዛ ሳይጠይቁ ራስዎ እንዲሞሉ ይመከራል።

ማመልከቻውን እንዲሞላሎት የሰው እርዳታ ካስፈለገ ጥያቄዎችን በትክክል ለመመለስ በሚሞላበት ስፍራ መገኘት ያስፈልጋል። ከዚህ በተጨማሪም የ ' ልዩ ማረጋገጫ ቁጥሩ ' ን ለመያዝ በስፍራው መገኝት ያስፈልጋል።

አንዳንድ የሚሞሉ ሰዎች ይህን ቁጥር ይዘው በመቀየር ተጨማሪ ብር የሚጠይቁ ስላሉ እንዳይታለሉ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

የማረጋገጫ ቁጥሩ እጅግ ወሳኝ በመሆኑ በጥንቃቄ መያዝ አለበት።

ለ2026 የፊስካል ዓመት እስከ 55,000 የሚደርስ የዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ተዘጋጅቷል። ይህ ቁጥር ብቁ የሆኑ ሀገራት ሁሉ የሚጠቃልል ነው።

ኢትዮጵያውያንም ለማመልከት ብቁ ናቸው።

አሜሪካ በየዓመቱ ከኢትዮጵያ ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) አማካኝነት እንደምትቀበል ይታወቃል።

🇺🇸 ለአሜሪካ ዳይቨርሲቲ ቪዛ 2026 ለማመልከት ይህንን dvprogram.state.gov ሊንክ ይጠቀሙ !🇺🇸

(ተጨማሪ ማብራሪያ እና እንዴት መሙላት እንደሚቻል የሚገልጽ መመሪያ በቀጣይ እናያይዛለን)

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የጥገና ሥራው ከ20 ቀን ያላነሰ ጊዜ ሊወስድ ይችላል " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

ከቆቃ-ሁርሶ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ጥምር የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተፈፀመ ስርቆት ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል።

ኃይል የተቋረጠው በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ በንቲ ቀበሌ ልዩ ስሙ አዋሽ ፓርክ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ የኃይል ተሸካሚ ምሰሶ ላይ በተፈፀመ ስርቆት ምክንያት ነው።

የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ፦
- በምስራቅ የሃገሪቱ ክፍል ለሚገኙ ከተሞችና አካባቢዎች፣
- ለአዲስ አበባ- ጅቡቲ የባቡር መስመር
- ለጅቡቲ የኤሌክትሪክ ኃይል እያቀረበ ነበር።

በደረሰው ጉዳት ምክንያት በተጠቀሱት ቦታዎች የኃይል አቅርቦት መቋረጡ ተገልጿል።

በስርቆት ምክንያት ከወደቀው አንድ ምሰሶ በተጨማሪ ሰባት የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች በአስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

ጉዳት የደረሰበትን የኃይል ተሸካሚ ምሰሶ ለመቀየር የቴክኒክ ባለሙያዎች ቡድን ተዋቅሮ ወደ ሥራ መግባቱ ተገልጿል።

ስርቆት የተፈፀመበት የኃይል ተሸካሚ ምሰሶ ጥምር የኤሌክትሪክ መስመሮችን የያዘ በመሆኑ የጥገና ሥራው ከ20 ቀን ያላነሰ ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ተመላክቷል።

የጥገና ሥራው ሙሉ በሙሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስም ከመስመሩ ኃይል ሲያገኙ ለነበሩ ከተሞችና አካባቢዎች በፈረቃ ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ለማድረግ ጥረቶች ይደረጋሉ ተብሏል።

ህብረተሰቡ የተፈጠረውን ችግር ተረድቶ በትዕግስት እንዲጠብቅ ተቋሙ መልዕክት አስተላልፏል።

በሌላ በኩል ፥ ከመተሃራ - አዋሽ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የባቡር መስመር ላይ በሚገኙ 9 የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

የጥገና ሥራዎችን ለማከናወን ርብርብ እየተደረገ ነው ተብሏል።

በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ በኃይል ማስተላለፊያ ተሸካሚ ምሰሶ አካላት ላይ እየተፈፀሙ የሚገኙ የስርቆት ወንጀሎች መበራከታቸው የገለጸው ተቋሙ ፦
- የአካባቢው ማህበረሰብ፣
- የመስተዳድር
- የፀጥታ አካላት ለኃይል መሰረተ ልማቶቹ ተገቢውን ጥበቃና ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#AAU

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ተከትሎ ተማሪዎችን ለማስተማር በራሱ መስፈርት አወዳድሮ እንደሚቀበል የምልመላ ፖሊሲ መዘርጋቱን ከዚህ ቀደም መግለጹ ይታወሳል፡፡

ለማስተማር የተቀባላቸውን ተማሪዎች በተመለከተም ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚደንት ዩኒቨርሲቲ ጀይል ዑመር (ዶ/ር) ፣ “ ዩኒቨርሲቲው በቅድመ ምረቃም ሆነ በድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች የሚከታተሉትን ብቃትና አቅም ለመመልመል የሚያስችል የቅበላ ፖሊሲ በማዘጋጀት ምልመላውን አዘጋጂቷል ” ብለዋል፡፡

“ ለምልመላው ትልቁ መስፈርት በሀገራችን ለቅድመ መረቃ ፕሮግራሞች በአገሪቷ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባት የሚያስችል ውጤት ያላቸው ተማሪዎች እንዲወዳደሩ ነው የተደረገው ” ነው ያሉት፡፡

ለምልመላው በጥቅሉ፣ ዩኒቨርሲቲው የሰጠው የአድሚሽን ፈተና ከ50 ፐርሰንት፣ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ውጤት ከ50 ፐርሰንት መያዙ ተነግሯል፡፡

“ በዚህ ዓመት ለከፍተኛ ትምህርት ብቁ ናቸው ተብለው ትምህርት ሚኒስቴር ካረጋገጠላቸው መካካል 11 ሺሕ 939 ተማሪዎች ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመመረጥ ለፈተና ቀርበዋል፡፡ የቅበላ ፈተናው የሚለካው ተማሪዎቹ ወደ ዩኒቨርሲቲው ቢገቡ ያለ ምንም እንከን የቅድሞ ምረቃውን ፕሮግራም ዝግጁነት ኑሯቸው የሚችሉ መሆኑን የሚያረጋግጡ ናቸው ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የክሪቲካል ቲንኪንግ፣ የቋንቋ ዝግጁነትን፣ የስሌት ብቃቶችን ሊያረጋግጡ የሚችሉ ጉዳዮችን የቅበላ ፈተናው ማካተቱንም ገልጸዋል፡፡

“ ከ11 ሺሕ 939 ለፈተናው የተቀመጡትን ስናይ፣ በቅድመ ምረቃ ፕሮግራም የመጀመሪያው ነው፡፡ የፍሬሽማን ፕሮግራም ዘርፍ አለው፡፡ በተፈጥሮ ሳይንስና በማህበራዊ ሳይንስ ተብሎ ይከፈላል ” ነው ያሉት።

“ በተፈጥሮ ሳይንስ ያመለከቱትና ለፈተና የተቀመጡት 7,589 ሲሆኑ፣ በሶሻል ሳይንስ ደግሞ 4,350 ተማሪዎች ናቸው ” ነው የተባለው።

በዚህም በመንግስት ስኮላርሽፕ የሚማሩት 4,402፣ በራሳቸው ከፍለው የሚማሩት ደግሞ 7,537 ተማሪዎች ለፈተና እንደተቀመጡ ተገልጿል፡፡

በዬፕሮግራሞቹ የማስተናገድ አቅምም አንዱ ታሳቢ የሆነ መስፈርት እንደሆነ የገለጸው ዩኒቨርሲቲው፣ “ በዚህ ስሌት በመንግስት ስፖንሰርነት የተመለመሉት 2,660፣ በግል አመልካችነት (ከፍሎ ለመማር) 2,640፣ በአጠቃላይ ዩኒቨርሲቲው በቅድመ ምረቃ ፕሮግራም 5300 ተማሪዎችን ቅበላ አድርጓል ” ነው ያሉት፡፡

በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ተመዝግበው ትምህርትቸውን እንደሚቀጥሉም ተመላክቷል፡፡

በተለይ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ያሉ ተማሪዎች ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መጥተው ለመማር የሚፈልጉ ከመሆናቸው አንጻር ዩኒቨርሲቲው ምልመላውን በምን መልኩ እንደዳሰሰው ለቀረበለት ጥያቄ በሰጠው ምላሽ፣ “ ከየትኛውም የአገሪቷ ኮርነር ላሉት እድሉ ተሰጥቷል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በዚህ በኩል ነፍጓል የምንለው ነገር የለም ” ብሏል፡፡

ክፍያው ስንት እንደሆነ ከጋዜጠኞች ለቀረበው ጥያቄም፣ ክፍያው የተለያዬ እንደሆነ፣ መንግስት ስፖንሰር ያደረጋቸው የምግብ፣ የመኝታ፣ የትምህርታና ሌሎች ወጪዎው በመንግስት እንደሚሸፈኑ ዪኒቨርሲቲው ምላሽ ሰጥቶበታል፡፡

“ ከፍለው የሚማሩ ደግሞ ምግብም፣ መኝታ ቤትም ያስፈልገኛል ለሚል ኮስት ያደርጋል፡፡ የትምህርት ወጪ የምንለው ስሌቱ በኢሲቲኤስ ነው፡፡

እንደዬየፕሮግራሞቹ ይለያያል፡፡ ለምሳሌ ዝቅተኛ በአንድ ኢሲቲኤስ 600 ብር፣ በኢሲቲኤስ ከፍተኛው እስከ 2000 ብር የሚሄድ ነው ” ብሏል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Afar #Tigray

ትግራይ እና ዓፋር ክልሎች በፕሬዜዳንቶቻቸው በኩል ባደረጉት ይፋዊ ግንኙነት የሁለቱም ህዝቦች አብሮነት የሚጎዱ ወንጀለኞች ተላለፈው እንዲሰጣጡ ተሰማሙ።

በትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ የተመራ ልኡክ በዓፋር ክልል ሰመራ ከተማ ያደረገው የአንድ ቀን ምክክር አድርጓል።

ምክክሩ ውጤታማ እንደነበር ተገልጿል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ልኡክ አባል የዓፋር ክልል አጎራባች ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጸጋይ ገብረተኽለ ፥ " ውይይቱ የሁለቱ ክልል ህዝቦች ጉርብትና ሰላማዊ ሆኖ እንዲቀጥል የሚያግዝ ውጤታማ ውይይት ነው " ብሎውታል።

" በትግራይ እና ዓፋር ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዲጀመር ፣ የተዘጉ መንገዶች እንዲከፈቱ ፣  ነፃ የሆነ ግንኙነት እንዲኖር ፣ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ እና የቆየው የሰላም እና የልማት ግንኙነት እንዲቀጥል በውይይቱ ስምምነት ላይ ተደርሷል " ብለዋል።

" ሁለቱ ክልሎች በሚያዋስኑ አከባቢዎች ተደጋጋሚ ግጭቶች እንደሚከሰቱ " የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው " ግጭት ጠማቂዎችና ወንጀለኞች ተላልፈው እንዲሰጣጡ ፣ የጋራ የሰላም እና የፀጥታ እቅድ እንዲኖርና በየወሩ እየተገመገመ እንዲመራ ትግራይ እና ዓፋር ተስማምተዋል " ሲሉ አሳውቀዋል።

በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የተመራ ልኡክ በዓፋር ክልል የነበረው የአንድ ቀን ቆይታ አጠናቅቆ ወደ መቐለ መመለሱ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት በመጥቀስ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia  

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Afar #Tigray

የትግራይ እና ዓፋር ክልሎች በፕሬዜዳንቶቻቸው የተደገፈ ይፋዊ ምክክር አደረጉ።

ዛሬ በዓፋርዋ ሰመራ ከተማ የተሳለጠው ግንኙነት በትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ጌታቸው ረዳ እና በዓፋር ክልል ፕሬዜዳንት አወል አርባ የተመራ ነው። 

በአቶ ጌታቸው ረዳ የተመራ ልኡክ ሰመራ ከተማ አውሮፕላን ማረፍያ ሲደርስ ፕሬዜዳንት አወል አርባ እና ካቢኔያቸው አቀባበል አደርገውለታል።

የሁለቱ አጎራባች ክልሎች ይፋዊ ግንኙነት በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የሻከረው ግንኙነት ለማደስ ያለመ እንደሆነ ድምጺ ወያነ ዘግቧል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ኢትዮጵያ #ማክሮኢኮኖሚ

የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ዛሬ ጠዋት ተሰብስቦ ነበር።

በቅርብ የተደረገውን የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያዎች አፈፃፀም መገምገሙም ተሰምቷል።

ይህን ተከትሎ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፥ " ፖሊሲው ተፈፃሚ በሆነባቸው ሁለት ወራት የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ከባቢን መመልከት ችለናል " ሲሉ ገልጸዋል።

" በተመሳሳይ የገቢ ግባችን የተቀመጠለትን ግብ በመምታት በታለመለት መንገድ ላይ ይገኛል " ብለዋል።

" በአጠቃላይ ያለፉት ሁለት ወራት ፖሊሲው በስኬታማ አፈፃፀም ላይ መሆኑን አሳይተዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Djibouti

45 ስደተኞች ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ።

ከየመን 310 ስደተኞችን በመጫን በጉዞ ላይ የነበሩ ሁለት ጀልባዎች ሰጥመው እስካሁን ባለው 45 ሰዎች መሞታቸውን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታውቋል።

የጅቡቲ የባህር ጠረፍ ጠባቂ እንዳስታወቀው አደጋው በሰሜናዊ ምዕራብ ሖር አንጋር አካባቢ ካለው የባህር ዳርቻ 150 ሜትሮች ርቆ ነው የተከሰተው።

ከሰኞ ጀምሮ በተደረገው ፍለጋ በህይወት የተረፉ 115 ሰዎች ማዳን እንደተቻለ የጅቡቲ የባህር ጠረፍ ጥበቃ አሳውቋል።

እስካሁን በርካታ ስደተኞች የደረሱበት አልታወቀም።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#እናትፓርቲ

" አንዱን ሰቆቃ ማን ፣ እንዴት ፣ ለምን እንዳደረገው በበቂ ሳይጠናና ጠያቂም፣ ተጠያቂም ሳይኖር ለጥቂት ጊዜያት ዝም ያለና የቆመ ካስመሰለ በኋላ ያለፈውን በሚያስንቅ እልቂቱ ይቀጥላል " - እናት ፓርቲ

እናት ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ልኳል።

ፓርቲው " በሀገራችን ኢትዮጵያ ሥርዓታዊ የሆነ በእምነት ተቋማት፣ በሃይማኖት አባቶችና ምእመናን ላይ የሚደርስ ጥቃት አቻ በሌለው መልኩ ከዳር ዳር ሲያምሳት ማየትና ምንም እንዳልተፈጠረ በዝምታ ማለፍ የተለመደና በተዘዋዋሪ ይኹንታ የመስጠት የሚመስል ክስተት ከሆነ ዓመታት ተቆጥረዋል " ብሏል።

" የግፉ መጠን ከዕለት ዕለት እየቀነሰ ከመሄድ ይልቅ መልኩንና ቦታውን እየቀያየረ አሰቃቂነቱንም በየወቅቱ የከፋ እያደረገ ቀጥሏል " ሲል ገልጿል።

" አንዱን ሰቆቃ ማን፣ እንዴት፣ ለምን እንዳደረገው በበቂ ሳይጠናና ጠያቂም፣ ተጠያቂም ሳይኖር ለጥቂት ጊዜያት ዝም ያለና የቆመ ካስመሰለ በኋላ ያለፈውን በሚያስንቅ እልቂቱ ይቀጥላል። እንደማኅበረሰብም ጣት መቀሳሰርና አኹን አኹን ደግሞ እልቂትን በጥንቃቄ በመለማመድ ላይ ያለን ይመስላል " ብሏል።

" ባለፈው መስከረም 16/2017 ዓ/ም በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ሞጆ ወረዳ የቢቃ ደ/መ/ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህን የነበሩት ቀሲስ ወልደ ኢየሱስ አያሌው እና 4 ቤተሰባቸው በግፍ በአሰቃቂ ኹኔታ መገደል ተራ ግድያ ሳይሆን በእምነት ተቋማት ላይ ያነጣጠረ፣ ቤተሰብን በሙሉ በአንድ ላይ በመፍጀት ዘር እንዳይተርፍ ጭምር የተወሰደና ቀደም ሲል ከተፈጸሙ መሰል ግድያዎች የጥፋት ደረጃውን ከፍ አድርጎ ያሳየ ጭፍጨፋ ነው " ሲል ፓርቲው ገልጿል።

ፓርቲው " ይኽንና ቀደም ሲል በተለያዩ ጊዜያት የደረሱ ጥቃቶችና የጅምላ ፍጅቶች በአጋጣሚና በዘፈቀደ እየሆኑ ያሉ ሳይሆን በተጠና መልኩ ሀገርን አጽንተው ባቆሙ ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን ላይ ያነጣጠሩና ፈርጀ ብዙ አንድምታ ያላቸው በመጣህብኝ ሰበብ የተጠና ዘር ማጽዳትና ማሳሳት/systemic ethnic cleansing/፣ በቀል/revenge/፣ ማዋረድ/humiliation/፣ የአዲሱን ዓለም አስተሳሰብ/new world order/ ትግበራ አካል እንደሆነ በጽኑ እናምናለን " ብሏል።

" በዓለም ላይ የተፈጸሙ መሰል ድርጊቶች ያለመንግሥት መዋቅር ቀጥተኛም ይኹን ተዘዋዋሪ ተሳትፎ አልተፈጸሙም " የሚለው ፓርቲው " የእኛውም ከዚያ ሊለይበት የሚችል አመክንዮና ዕውናዊ ማሳያ ይኖራል ተብሎ አይታመንም " ሲል ገልጿል።

" እንዲህ ያሉ ድርጊቶች በጥንቃቄና አሻራ በማይተው መልኩ፣ ገፋ አድርጎ ቢሄድም በማዳፈን የሚፈጸሙ ናቸው። እርግጥ ነው የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር የዚኽም ሆነ የቀደሙ ጅምላ ጭፍጨፋዎች ተዋንያን ለፍርድ አደባባይ መቅረባቸው አይቀሬ ነው " ብሏል።

" የእኛን ፓርቲ ጨምሮ መሰል ተቋማትና ግለሰቦች በቀደሙት ጊዜያት በተደጋጋሚ ያሰማነው ዜጎችና ተጋላጭ የሆኑ የሃይማኖት ተቋማት /hotspot areas/ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ያስተላለፍነው ጥሪ ሰሚ በማጣቱ ወይም ሆነ ተብሎ በመታለፉ ዛሬም ጭፍጨፋውና ግድያው በከፋ መልኩ እንደቀጠለ ነው " ብሏል።

" ኢትዮጵያውያን አንዳችን የአንዳችንን ደህንነት እየጠበቅን የእምነት ተቋማቶቻችንን ከሥርዓታዊ ጥቃት ለመታደግ እጅ ለእጅ ተያይዘን እንድንቆምና ለተሻለ ጊዜ እንድንተጋ " ሲል እናት ፓርቲ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

Hibret Bank !

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ቅሬታ ወደ 995 የጥሪ ማዕከላችን በመደወል ፣ በኢሜል CRM@hibretbank.com.et በመላክ  ወይም በዋናው መ/ቤት 3ኛ ፎቅ በመቅረብ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡ አዳዲስ መረጃ እንዲደርሶ የሚከተሉትን የማህበራዊ ገፆቻችንን ይቀላቀሉ፡፡
    ቴሌግራም-    /channel/HibretBanket

                         linktr.ee/Hibret.Bank

#Hibretbank

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

🎉🎉 የኢትዮ 130 lucky slot አሸናፊዎች ሽልማታቸው እየወሰዱ ነው!!

🔥3ቱ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ አውቶሞቢሎች ገና አልተነኩም

በቴሌብር ሲገበያዩ፣ የአየር ሰዓት ወይም ጥቅል ሲሞሉ፣ ገንዘብ ገቢ ሲያደርጉ፣ ሲያወጡ ወይም ሲላላኩ፣ የአገልግሎት ክፍያ ሲፈጽሙ በሚሰበስቧቸው ሲልቨር/ጎልድ ሳንቲሞች በመጠቀም የዕድል ጨዋታ እና የማስታወስ ጨዋታ በመመለስ ሽልማቶችን ያግኙ!

🚘 3 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖች
🛺 3 ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች
💰 በየቀኑ የ20 ሺህ እና በየሳምንቱ የ50 ሺህ ኢ-የገንዘብ ሽልማቶች በቴሌብር
📱 70 ዘመናዊ ስማርት ስልኮች
🎁 130 ሺህ የሞባይል ጥቅሎች

💁‍♂️ ከእርስዎ የሚጠበቀው አገልግሎቶቻችን እየተጠቀሙ በ131 ጨዋታዎች እየተዝናኑ ዕድልዎን መሞከር ብቻ ነው!
✅ በቴሌብር ሱፐርአፕ ኢትዮ 130 ላኪ ስሎትን (Ethio 130 lucky slot) በመምረጥ ወይም ወደ 131 ok ብለው በመላክ ይመዝገቡ፡፡

ደንብና ሁኔታዎች ተፈጻሚነት አላቸው

ለበለጠ መረጃ፡ https://bit.ly/4dckxdb
🎉የአሸናፊዎችን ዝርዝር ለመመልከት 👇🏼

#130_ዓመታትን_በጽናት_ታላቅ_አገርና_ሕዝብ_በማገልገል_ላይ

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ደመወዝ

" የደመወዝ ጭማሪ ዝርዝሩ በቅርቡ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በኩል ይፋ ይደረጋል " - የገንዘብ ሚኒስቴር

የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ፤ ከመስከረም ወር 2017 ጀምሮ የሚጨመር ደመወዝ በካቢኔ መፅደቁን አሳውቀዋል።

ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ትኩረት ያደረገ የተወሰነ የደመወዝ ጭማሪ መደረጉን አመልክተዋል።

አቶ አህመድ " የተወሰነ የደመወዝ ጭማሪ ለኑሮ ድጎማ ጭምር እንዲሆን ታሳቢ ተደርጎ በካቢኔ ፀድቋል ከመስከረም ወር ጀምሮ ታሳቢ ይደረጋል። የደመወዝ ጭማሪው ከ91 እስከ 92 ቢሊዮን ብር መካከል ተጨማሪ በጀት የሚጠይቅ ይሆናል " ብለዋል።

በነባሩ በጀት የተወሰነ መግባቱን ፤ በተጨማሪ በጀትነትም የሚታወጅ መኖሩን ጠቁመዋል።

" ሲቪል ሰርቫንቱ አጠቃላይ የመንግሥት ሰራተኛው በሁሉም መስክ በፀጥታም በሌሎችም ዘርፍ ያሉትን የኑሮ ጫና ለመቋቋም የሚያስችለውን ድጋፍ ለማድረግ መንግሥት በከፍተኛ ቁርጠኝነት ተገባበት ነው " ሲሉ አቶ አህመድ ተናግረዋል።

" የባለፉት ሁለት ወራት የኢንፍሌሽን አፈጻጸም በሚታይበት ጊዜ እንደተሰጋው አይደለም። የተረጋጋ የዋጋ ሁኔታ ነው ያለው። የተወስነ ጭማሪ በአንዳንድ እቃዎች ላይ እንጂ በአብዛኛው የተረጋጋ ሁኔታ ነው ያለው። " ብለዋል።

" እንደዛም ሆኖ የደመወዝ ጭማሪው እጅግ አስፈላጊ ስለሆነ የሰራተኛውን ቋሚ ደመወዝተኛ ገቢ ያለውን ዝቅተኛውን ትኩረት አድርገን የዝቅተኛውን በጣም ከፍተኛ ጭማሪ አድርገናል የላይኛውን ዝቅተኛ ጭማሪ አድርገን ነው የተሰራው ዝርዝሩ በቅርቡ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በኩል ይፋ ይደረጋል " ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የሞቱት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው " - በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ

ሰሞኑን በጅቡቲ የባህር ዳርቻ በደረሰው የጀልባ መስጠም አደጋ በአደጋው የሞቱት ዜጎች በሙሉ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው መረጋጋገጡን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም ማምሻውን ከየመን ወደ ጅቡቲ 320 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞች ይዘው የተነሱት ሁለት የስደተኞች ጀልባዎች በጅቡቲ ባህር ዳርቻ አከባቢ ሲደርሱ በደረሰው አደጋ የበርካቶች ህይወት ማለፉ ይታወሳል።

አደጋውን ተከትሎ 48 ፍልሰተኞች ህይወታቸው ሲያልፍ፣ 197 ፍልሰተኞች ከአደጋው ተርፈው ኦቦክ የሚገኘው ዓለም አቀፉ የስደተኞች ካምፕ መድረሳቸው ተጠቅሷል።

የተቀሩት 75 ፍልሰተኞችን አካል የማፈላለጉ ስራ በነፍስ አድን ሠራተኞች መቀጠሉ ተጠቁሟል። 

እስከአሁን በስፍራው በተደረገው የዜጎች ማጣራት ሂደት ሁሉም ፍልሰተኞች ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ከሚመለከተው አካላት በተገኘው መረጃ ማወቅ መቻሉን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገልጿል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#DStvEthiopia

💥ማን ዩናይትድ ከ ቶተንሃም 0-3 ሸንፈት በኋካ ዛሬ ምሽት ወደ ፖርቹጋል ተጉዞ ከፖርቶ ጋር ይጫወታል!

ዩናይትድ ወደ አሸናፊነት መንገድ ይመለሳል?

👉 ዛሬውኑ ፓኬጅዎን ያሳድጉ ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሜዳ ፕላስ ፓኬጅ ይከታተሉ!

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#ChampionsLeagueAllonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvSelfServiceET

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ባይቶና

" በትግራይ ያጋጠመው ፓለቲካዊ ብልሽት የሚያጠራ ብሄራዊ እርቅ ያስፈልጋል " - ባይቶና ፓርቲ 

ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) የፓለቲካ ፓርቲ በክልሉ ወቅታዊ የፓለቲካ ሁኔታ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ " በትግራይ ያጋጠመው ፓለቲካዊ ብልሽት የሚፈታ ብሄራዊ የእርቅ ምክር ቤት ያስፈልጋል " ብሏል።

ብሄራዊ የዕርቅ ምክር ቤት በአስቸኳይ እንዲቋቋም የጠየቁት የባይቶና ፓርቲ ሊቀመንበር ክብሮም በርሀ ፥ ምክር ቤቱን የማቋቋም ሃላፊነት ለጊዚያዊ አስተዳደሩ ይሰጥ ብሏል። 

የትግራይ ጥቅም የሚያረጋግጥ ብሄራዊ ዕርቅ ማካሄድ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ የገለፁት ሊቀመንበሩ እርቅ ሲባል በልሂቃን መካከል የሚፈፀም እንደሆነ  አብራርተዋል። 

" የተፈጠረው መገፋፋት የትግራይ ብሄራዊ ጥቅም ወደ አደጋ እያስገባው ነው " ያሉት አቶ ክብሮም " ከመጠፋፋት ፓለቲካ ወጥተን የሰለጠነ ፓለቲካ ማራመድ አለብን " በማለት ተናግረዋል። 

" ጊዚያዊ አስተዳደሩ የአንድ ቡድን ሳይሆን የጀግኖች ደም ባረጋገጠው የፕሪቶሪያ ስምምነት እውቅና ያለው ነው " ያሉት አቶ ክብሮም " ጊዚያዊ አስተዳደሩ እንዳሻን የምንገነባውና የምናፈርሰው ሳይሆን ፀጋዎቹን አሟጠን በመጠቀም የህዝባችን ድህንነት ማረጋገጠረ አለብን ' ማለታቸው ቲክሻህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል። 

@tikvahethiopia 

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#MesiratEthiopia

📢 በሐዋሳ እና በድሬዳዋ ለምትገኙ ወጣቶች በሙሉ!

የመስራት የወጣቶች መማክርት ቡድን (M-YAG) አባል በመሆን ለለውጥ ድምጽ ሁኑ !

M-YAG ከቡድን በላይ ነው፤ በመስራት ፕሮግራም ውስጥ የወጣቶችን ድምጽ ለማሰማት የተዘጋጀ እንቅስቃሴ ነው።
ከ 15 እስከ 35 እድሜ የሆኑ ለመምራት፣ ለማነሳሳት እና በማህበረሰቦቻቸው ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ለማሳደር ዝግጁ የሆኑ ወጣቶችን እየፈለግን ነው። በM-YAG በኩል በዋጋ ሊተመን የማይችል የግል እና ሙያዊ ክህሎቶችን ታገኛላችሁ፣ ጠንካራ አመራር ላይ ቁርጠኛ የሆነ ቡድን አካል ትሆናላችሁ።

ተጽዕኖ ለማሳደር ዝግጁ ከሆናችሁ እዚህ ተመዝገቡ፥ https://forms.gle/pd3JLtHM1u1fDD4D6

#MYAG #መስራት #Hawassa #ሐዋሳ #DireDawa #ድሬዳዋ

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#DV2026

የ2026 የአሜሪካ ዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ማመልከቻ ከዛሬ ጀምሮ ክፍት ተደርጓል።

ለ2026 DV ለማመልከት https://dvprogram.state.gov/ ይጠቀሙ።

ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ አያስፈልግም።

ማመከቻው እስከ ህዳር 5 /2024 ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል።

ከፍተኛ የመሙላት ፍላጎቶች ድረገጹ ላይ መዘግየቶችን ሊያስከትል ስለሚችል እስከ የምዝገባው ጊዜ የመጨረሻ ሳምንት ድረስ ባይጠብቁ ይመከራል።

ዘግይተው የሚገቡ ማመልከቻዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

ህጉ ለአንድ ሰው አንድ ጊዜ ብቻ እንዲያመለክት ነው የሚፈቅደው። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የሚጠቀመው የተራቀቀ ቴክኖሎጂ ደጋግሞ የሚገቡ ማመልከቻዎችን የሚለይ ነው። ከአንድ ጊዜ በላይ አንድ ሰው ካመለከተ ሁሉንም የዛን ሰዎች ማመልከቻዎች ይሰርዛል።

ያልተሟላ ማመልከቻም ተቀባይነት የለውም።

ዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ከቪዛ አማካሪዎች ፣ ' እንሞላለን ' ከሚሉ ወኪሎችና ከሌሎች አካላት እገዛ ሳይጠይቁ ራስዎ እንዲሞሉ ይመከራል።

ማመልከቻውን እንዲሞላሎት የሰው እርዳታ ካስፈለገ ጥያቄዎችን በትክክል ለመመለስ በስፍራው መገኘት ያስፈልጋል። ከዚህ በተጨማሪ የልዩ ማረጋገጫ ቁጥሩን ለመያዝ በስፍራው መገኝት ያስፈልጋል።

አንዳንድ የሚሞሉ ሰዎች ይህን ቁጥር ይዘው በመቀየር ተጨማሪ ብር የሚጠይቁ ስላሉ እንዳይታለሉ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

የማረጋገጫ ቁጥሩ እጅግ ወሳኝ በመሆኑ በጥንቃቄ መያዝ አለበት።

ለ2026 የፊስካል ዓመት እስከ 55,000 የሚደርስ የዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ተዘጋጅቷል። ይህ ቁጥር ብቁ የሆኑ ሀገራትን ሁሉ የሚያጠቃልል ነው።

ኢትዮጵያውያንም ለማመልከት ብቁ ናቸው።

አሜሪካ በየዓመቱ ከኢትዮጵያ ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) አማካኝነት እንደምትቀበል ይታወቃል።

🇺🇸 ለአሜሪካ ዳይቨርሲቲ ቪዛ 2026 ለማመልከት ይህንን dvprogram.state.gov ሊንክ ይጠቀሙ !🇺🇸

(ተጨማሪ ማብራሪያ እና እንዴት መሙላት እንደሚቻል የሚገልጽ ዝርዝር መመሪያ በቀጣይ እናያይዛለን)

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Afar #Tigray

" የትግራይ ክልል ሰላም ለክልላችን ሰላም ወሳኝ ነው " - ሀጂ አወል አርባ

የአፋር ክልል ፕሬዜዳንት ሀጂ አወል አርባ ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ከፍተኛ አመራርን ላካተተዉ ሉዑካን ቡድን ምን አሉ ?

" የአፋርና ትግራይ ህዝቦች መካከል የሰላምና ፀጥታ ችግሮችን መፍታት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን ማጠናከር አስፈላጊ ነው።

በሁለቱ ክልሎች መካከል ዘላቂ ሰላምን ማስፈን አስፈላጊ ነው።

የትግራይ ክልል ሰላም ለክልላችን ሰላም ወሳኝ በመሆኑ በክልሉ መረጋጋትን ለመፍጠር የሁሉንም ተሳትፎ ይጠይቃል።

ለክልሉ ሰላምና መረጋገት የድርሻችንን እንወጣለን " ብለዋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#NBE : የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአምስት ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች የስራ ፈቃድ ሰጠ።

የስራ ፍቃድ የተሰጣቸው ፦

1. Dugda Fidelity Investment PLC
2. Ethio Independent Foreign Exchange Bureau
3. Global Independent Foreign Exchange Bureau
4. Robust Independent Foreign Exchange Bureau
5. Yoga Forex Bureau ናቸው።

" እነዚህ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች በሙሉ ተቀባይነት ያላቸው " ናቸው ያለው ብሔራዊ ባንክ " የውጭ ሀገር ጥሬ ገንዘቦችን በመግዛትና በመሸጥ እንዲሁም ከባንኮች ጋር በመቀናጀት ለወጪና ገቢ ንግድ የሚውል የውጭ ምንዛሪ በማመቻቸት የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ገበያ ለማስፋፋትና ለማዳበር የሚረዳ ሚና ይኖራቸዋል " ብሏል።

የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎቹ በዋናነት የሚያካሂዱት የውጭ ምንዛሪ ሽያጭም ሆነ ግዥ ወዲያውኑ የሚፈጸም (spot transaction) ብቻ ይሆናል ተብሏል።

የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ያለ ጉምሩክ ዴክላራሲዮን ከደንበኞች እስከ 10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር፣ የጉምሩክ ፈቃድ ከሚያቀርቡት ደግሞ ከዚያ በላይ የውጭ ምንዛሪ በጥሬ ገንዘብ መግዛት ይችላሉ፡፡

እንዲሁም ተፈላጊ የጉዞ መረጃ ላላቸው የግል ተጓዦች እስከ 5 ሺህ የአሜሪካን ዶላር፣ ለንግድ ሥራ ተጓዦች ደግሞ እስከ 10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በጥሬ ገንዘብ መሸጥ ይችላሉ፡፡

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#MPESASafaricom

💨 ⚡ቅመም MIFIን ገዝተን ፈጣን 4G ኢንተርኔት እንጠቀም! ለ30 ቀን ከሚቆይ ነጻ 100ጊባ ዳታ ጉርሻ ጋር 😋
ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት⚡
  
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#SafaricomEthiopia #1Wedefit #Furtheraheadtogether

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ኢትዮጵያ

ባንኮች በአገልግሎት ክፍያ ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ታሪፍ ጨምረዋል።

በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሕግ መሰረት ባንኮች በሚሰጧቸው አገልግሎቶች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲጣል ታውጇል፡፡

በዚህም የመንግሥት እና የግል ባንኮች ከመስከረም 21 ቀን 2017 ዓ. ም ጀምሮ በባንክ አገልግሎቶች ላይ በሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ታሪፍ ጨምረዋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#EZEMA

" የህዝባዊ በዓላት የፖለቲካ መድረክ ሊሆን አይገባም " ሲል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ ገለጸ።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለይ " ኢሬቻ " በዓልን በማክበር ሒደት በመንግሥት መዋቅሮች እና በመንግሥታዊ ኃላፊነት ቦታ ላይ የተቀመጡ ባለሥልጣናት ባሕሉ ካለው ሕዝባዊ እሴት ባፈነገጠ መልኩ ባሕሉን ከሕዝቡ ባለቤትነት ነጥቆ ፖለቲከኞቹ ዋነኛ አጋፋሪ ሆነው መጥተዋል ብሏል።

ይህ በሌሎች ዘንድ የመገለል እና የስጋት ስሜት ይፈጥራል ሲል አመልክቷል።

" ገዢው ፓርቲም በዚህ መልኩ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት በሚመስል መልኩ መንቀሳቀሱ ተገቢ አይደለም ብለን እናምናለን " ብሏል።

ፓርቲው ፤ በተለይ ለባሕሉ ተብሎ በተለያዩ አካባቢዎች ከተቋማት እና ከንግዱ ማኅበረሠብ በድጋፍ ስም በመንግስት መስሪያ ቤቶች ደብዳቤ የንግድ ማኅበረሠቡን በሚያስጨንቅ እና ከአቅም በላይ የሆነ ከፍተኛ አስገዳጅ የገንዘብ መዋጮ የመጠየቅ እንቅስቃሴ እንዳለ ጠቁሟል።

ይህ ተግባር " ማኅበረሠቡን ከፍተኛ ምሬት ውስጥ በመክተት ባሕሉን በስጋት  እንዲመለከተው እያደረገ ይገኛል " ብሏል።

" የባሕሉ ባለቤት የሆነው ሕዝብ ' ተቋማትን እና ግለሰቦችን አስጨንቃችሁ መዋጮ በመሰብሰብ በዓሉን አድምቁልኝ ' አይልም ፤ ይህንንም ሕገወጥ ተግባር የሚጠየፈው መሆኑን አንዳች ጥርጥር የለንም " ሲል ገልጿል።

" የየትኛውንም ማኅበረሠብ ባሕላዊም ሆነ ሃይማኖታዊ በዓል ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋል ባሕሉን መበረዝ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል " ያለው ፓርቲው " ይህን መሰል የአደባባይ ክብረ በዓላት ለየትኛውም አይነት የፖለቲካ አጀንዳ ማራመጃነት መጠቀምን ፍፁም እናወግዛለን " ብሏል።

በንግዱ ማኅበረሠብ ላይ እየተደረገ ያለውን ተጠያቂነት የሌለበት ሕገወጥ ጫናን ጨምሮ ሌሎች አስገዳጅ ድርጊቶችን መንግሥት በቶሎ እንዲያቆም አሳስቧል።

መንግሥት ባሕሎችን ጠንቅቆ ለሚያውቀው ማኅበረሠብ እንዲመልስ መሠረታዊ ኃላፊነቶቹን ብቻ በቅጡ እንዲወጣም ጠይቋል።

#Ethiopia

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#TPLF

" ህጋዊ እና ትክክለኛ 14ኛ ጉባኤ ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንገኛለን " - በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት  

" ህዝብ እና ህወሓት በማዳን የትግራይ ህዝብ ህልውና ማረጋገጥ " በሚል መሪ ቃል ሰብሰባ የተቀመጠው በምክትል ሊቀመንበር  አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት  ሰብሰባውን ቀጥሏል።

የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት እና ከፍተኛ ካድሬዎች " ህዝብ እና ህወሓት በማዳን የትግራይ ህልውና ማረጋገጥ " በሚል ርእስ በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ተወያይተዋል።   

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ህወሓት ህጋዊ እና ትክክለኛ የድርጅቱ 14ኛ ጉባኤ ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑ በውይይት መድረኩ ገልጿል።

" ድርጅቱ አሁን ለደረሰበት የመከፋፈል አደጋ ዋና መንስኤው በድርጅቱ ስር የሰደደው ፀረ ዴሞክራሲ አካሄድና ተጠያቂነት አለመኖር ነው " ብለዋል ተሳታፊዎቹ።

" የድርጅትና የመንግስት አሰራር መደባላለቅ ይቁም " በማለት አቋም የያዘው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ቡድን " በነበረው ይቀጥል " ከሚለው በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው ቡድን እንደ አንድ የመለያያ ነጥብ ሆኖ በመድረኩ ውይይት እንደተካሄደበት ታውቋል።

በዶ/ር ደብረፅዮን የተመራው 14ኛው ጉባኤ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቦለት ያልተቀበለው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው በዱን አሁን በተራው " ህጋዊና ትክክለኛ " በማለት ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት እያደረገለት በሚገኘው 14ኛው ጉባኤ ከዶ/ር ደብረፅዮን ጎን የወገኑት " ከያዙት የተሳሳተ መንገድ በመውጣት ጉባኤው ላይ እንዲሳተፉ " ከወዲሁ ጥሪ አቅርቧል። 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል መሪነት የተካሄደው ጉባኤ ቀደም ብሎ ጉባኤውም ሆነ ውሳኔዎቹ ቅቡልነት እንደሌለው ማሳወቁ መዘገባችን ይታወሳል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

#TikvahEthiopiaMekelleFamily

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራትም፣ በብራንድም፣ በባትሪ ቆይታም  አስተማማኝ የሆኑ የተለያዩ  ሞዴል ያላቸዉ  በፈለጉት ስክሪን መጠን ኮር እና ጀነሬሽን   አሉን።

ላፕቶፕ  ከመገዛቶ በፊት ማወቅ ያለባቹሁን ወሳኝ ነገሮች እናስረዳለን። ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች  ወ.ዘ.ተ ሁሉም አሉን ። በላፕፖቻችን ጥራት ላይ አንደራደርም!
!
የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።

@sww2844 0928442662 / 0940141114

https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#DV2026

የ2026 የአሜሪካ ዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ማመልከቻ ከነገ ጀምሮ ክፍት ይደረጋል።

ለ2026 የፊስካል ዓመት እስከ 55,000 የዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) አዘጋጅታለች።

ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ አያስፈልግም።

አሜሪካ በየዓመቱ ከኢትዮጵያ ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) አማካኝነት እንደምትቀበል ይታወቃል።

በነገው ዕለት ዝርዝር መረጃ የምንልክላችሁ ይሆናል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…
Subscribe to a channel