#ATTENTION🚨
“ የካንሰር ሕመም እየጨመረ ነው ” - ዶክተር አስቻለው ወርቁ
በኢትዮጵያ የካንሰር ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን፣ በተለይም ማኀበረሰቡ ትንቦሆ፣ አልኮል ነክ ነገሮችን ከመጠቀም እንዲታቀብ ጥሪ ቀረበ።
ለካንሰር ሕሙማን የሕክምና አገልግሎት እየተሰጠ ቢሆንም በተለይ በኢትዮጵያ በኩል የፋይናንስ እጥረት ችግር እንደፈተነው ማቲዎስ ወንዱ ካንሰር ሶሳይቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ተቋሙ የ20ኛ ዓመት ምስረታውን በማስመልከት መግለጫ ሰጥቶ ነበር።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ካንሰር #በኢትዮጵያ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ? በበሽታው የተጠቂ ሰዎች ቁጥር ቀነሰ ወይስ ጨመረ ? ሲል ጥያቄ አቅርቧል።
የተቋሙ የቦርድ አባልና የውስጥ ደዌ ባለሙያው ዶክተር አስቻለው ወርቁ ምን አሉ ?
“ በጣም እየጨመረ ነው ያለው። ለመጨመሩ የተለያዩ ምክንያቶች ይኖራሉ። በአጠቃላይ ተላላፊ ያልሆኑ በሽዎች እየጨመሩ ነው። የካንሰር ህመምም እየጨመረ ነው።
ለምሳሌ፦ የሳንባ ካንሰርን ብናዬው ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ነው ያለው። የምንመረምረው ጥቂት ሰዎችን ስለሆነ በዚያችው ዳታ ተመርኩዘን ነው የምንገልጸው። ማኀበረሰቡን ያማከለ የዳሰሳ ጥናት ካልሰራን ቁጥሩን በትክክል መግለጽ ከባድ ነው።
10 ሰዎችን መርምሮ 5 ሕሙማን ቢገኝ 50 በመቶ ማለት አይቻልም። ምክንያቱም ያልተመረመሩ ብዙ ስለሚኖሩ። እንደ አጠቃላይ ካየነው ግን ፦
- የሳንባ፣
- የአንጀት፣
- የጉበት፣
- የማህፀን፣
- የደም ሴል ካንሰር ታማሚሞች ቁጥራቸው እጅግ ባጣም እየጨመረ ነው ያለው። ” ብለዋል።
ካንሰር ዋነኛ የሞት እና የስቃይ ምክንያት እየሆነ መምጣቱን ቁጥሮች እንደሚያመላክቱ ተገልጿል።
ለአብነት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከሞቱ ሰዎች ካንሰር የመገኘት እድሉ ከፍ ብሏል። ምክንያቱም የሳንባ ካንሰር ካሉት የካንሰር ዝርዝሮች ወደ 6ኛ ደረጃ ላይ ነው ያለው ተብሏል።
የማቲዎስ ወንዱ ካንሰር ሶሳይቲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንዱ በቀለ ምን አሉ ?
“ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትንባሆ መሸጥም መግዛትም እንዳይችል የሚነገርበት ጊዜ መቼ ነው ?
ትንባሆ ነክ ነገሮች፣ አልኮል በሽታውን እያስፋፉት ነው።
ከ3,000 በላይ የካንሰር ሕሙማንና ቤተሰባቸውን እረድተናል። በአሁኑ ወቅት 175 ለካንሰር ሕሙማንና ለቤተሰባቦቸው፦
° ከአገራቸው የሚመጡበት ሙሉ የትራንስፖርት፣
° ከውጪ የሚገዙ መድኃኒቶች፣
° በሆስፒታል ውጪ በግል ተቋማት ለሚሰሩ የላብራቶሪ ምርመራ፣
° ሆስፒታል ለተኙት ሕሙማን ለአንዳንድ ነገር መሸፈኛ በወር 1,000 ብር፣
° እየታከሙ ለሚማሩ ተማሪዎች በወር 1,000 ብር፣
° 24 አልጋ ባለው የካንሰር ሕክምና ማዕከል በየዕለቱ ለቁርስ፣ ምሳ፣ በክሰስና እራት ወጪዎችን እየሸፈንን ነው። ”
NB. ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ የአቶ ወንዱ በቀለ የ4 ዓመት ጨቅላ ልጃቸው በካንሰር በሽታ ሕይወቱ ማለፉን ተከትሎ ቤተሰቦቹ የደረሰባቸውን መሪር ሀዘን “ ማቲዎስ ቢሞትም ብዙ ማቲዎሶችን ማዳን እንችላለን ” በሚል መልካም አስተሳሰብ በመቀየር በ15 መስራች አባሎች ሚያዚያ 9 ቀን 1996 ዓ/ም የተመሠረተ ለካንሰር ሕሙማን የሕክምና አገልግሎት የሚሰጥ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ነው።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Ethiopia #Attention🚨
የትራፊክ አደጋ የበርካቶች ህይወት እየቀጠፈ ይገኛል።
በዚህ ወር ብቻ ፦
- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 2 ሰዎች ሲሞቱ 5 ሰዎች ተጎድተዋል።
- በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ወረዳ ከኔጌሌ ወደ ዶዶላ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ መኪና 'አላንቱ' ላይ ከ " ሲኖትራክ " የጭነት መኪና ጋር ተጋጭቶ የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል። ሌሎችም ተጎድተዋል።
- በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በካፋ ዞን ጨና ወረዳ ፤ ከዋቻ ወደ ቦንጋ ሲጓዝ የነበረ ዶልፊን ተሸከርካሪ እና ከሚዛን ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ #ሲኖ_ትራክ ተሸከርካሪ በጨና ወረዳ ቦባ በላ ቀበሌ ተጋጭተው 5 ሰዎች ሲሞቱ 13 ሰዎች ተጎድተዋል።
- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ ወርት በተባለች ቀበሌ እንጨት ጭኖ ሲጓዝ የነበረ #ሲኖ_ትራክ የጭነት ተሽከርካሪ በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ የ6 ወጣቶች ህይወት ወዲያዉ ሲያልፍ በ10 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሷል። አደጋዉን የከፋ ያደረገው ሲኖ ትራኩ ወጣቶችን እንጨት ላይ አሳፍሮ እየተጓዘ ባለበት ወቅት አደጋው በመድረሱ ነው።
ከላይ በተጠቀሰው እና በይፋ በታወቀው ብቻ 28 ዜጎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል። በርካቶች የአካል ጉዳተኛ ሆነው።
እባካችሁ ጥንቃቄ አይለያችሁ !
@tikvahethiopia
"ጥበብ እንደ መፈወሻ መንገድ/ Art as a path to healing" ኦላይን የስዕል ኤግዚቢሽን
በትግራይ መቐለ ከተማ ከወርሃ የካቲት እስከ ሚያዝያ 2016 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየውና ከ387 ተመዝጋቢዎች የተመረጡ 61 ታዳጊና ወጣት ሰአልያን የተሳተፉበት የቡድን የስእል ውድድር አሸናፊዎችን በመለየት ተጠናቋል።
በውድድሩ ወጣቶቹ በ10 ቡድን በመከፋፈል 10 ስዕሎችን ያቀረቡ ሲሆን፤ ስዕሎቹም ጦርነትን፣ ዘረኝነትን፣ የእርስ በርስ ግጭትና ጠባብነት በማውገዝ ሰላም አንድነት ስር እንዲሰድ የሚሰብኩ ነበሩ።
እነዚህን ስዕሎች ኦላይን በተዘጋጀው ኤግዚቢሽን እንድትመለከቷለቸው እንጋብዛለን።
ወደ ኤግዚቢሽኑ ጎራ ለማለት ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ https://redeem.tikvahethiopia.net/paintings
#USAID #RTG #TikvahEthiopia
“ ለፍጻሜው ምክንያት እንሁን ”
የመጠናቀቂያ ጊዜ ላለፈው የቅድስት ሥላሴ ካቴደራል እድሳት 85 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በማድረግ “ ለፍጻሜው ምክንያት እንሁን ” ስትል ቤተክርስቲያኗ ጥሪ አቀረበች።
የካቴደራሉ እድሳት በውሉ መሠረት ሥራው የሚጠናቀቅበት የጊዜ መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ/ም የነበረ ቢሆንም፣ የውጪ ምንዛሬ ተጠይቆ ባለመገኘቱ ለመጠናቀቅ ተጨማሪ የ3 ወራት የጊዜ ለኮንትራክተር እንደተጨመረ ቤተክርስቲያኗ ገልጻለች።
ሥራው የሚጠናቀቅበት የጊዜ ገደብ ያለፈው ከውጪ አገር የሚገቡ ፦
- የዶም ኮፐር ቀለም፣
- የውጫዊ ግድግዳ ቀለም፣
- ሞዛይኮች፣
- ጀነሬተር እንዲሁም መብራቶችን ለማስገባት በውጪ ምንዛሪ የሚገዙ በመሆናቸው ምንዛሪው ቢጠየቅም ባለመገኘቱ ነው ተብሏል።
የቅድስት ሥላሴ ካቴደራል ኃላፊዎች ይህን ያሉት ዛሬ (ሐሙስ ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ/ም) በካቴደራሉ ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።
በዚህም የካቴደራሉ ህንጻ ጥገና ሥራ 75 በመቶ እንደደረሰ፣ ለማጠናቀቅ 85 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ፣ እስካሁን 90 ሚሊዮን ብር ማሰባሰብ እንደተቻለ፣ ለእድሳት በ172 ሚሊዮን ብር ውል እንደተገባ አስረድተዋል።
አብዛኛው ማህበረሰብ ካቴደራሉ ከፍተኛ የገንዘብ አቅም እንዳለውና እርዳታ የማይፈልግ እንደሆነ ያለተጨባጭ መረጃ የተሳሳተ ግንዛቤ በማሳደሩ ለእድሳቱ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ እጥረት በማጋጠሙ ሁሉም ሰው በሁሉም ባንኮች በአጭር ቁጥር 7829 ማስገባት ርብርብ እንዲያደርግ ተጠይቋል።
ካቴደራሉን ለማደስ 18 ወራት ያህል ጥናት እንደተደረገ፣ በዚህም ህንጻውን ከሚያድሰው ቫርኔሮ ከተባለ ድርጅት ጋር በመዋዋለ የውስጥና የውጪ እድሳት እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
Photo Credit - ንቁ
@tikvahethiopia
ንጹሕ_ምንጭ _ኢትዮጵያ
ለልጆችዎ ቦታ አለን
በልዩነት ቅዳሜ ልዩ የህፃናት ዝግጅት
" ' በኃይል ይዣለሁ ፣ ይዣለሁ ማለቱ ፍጹም ሰላም አያመጣም " - ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት የሆኑት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ ፥ " በወረራ " ተይዘዋል ያሏቸውን የትግራይ ክልል ግዛቶችን በሰላም ስምምነቱ መሰረት ነጻ እንዲወጡ እና የአካባቢዎቹ ሰላምና ደህንነት ተረጋግጦ ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቄያቸው እንዲመለሱ የማድረግ ኃላፊነት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ ወስደው እንዲሰሩ ከፌዴራል መንግሥት ጋር መግባባት ላይ መድረሱን ተናግረዋል።
ከዚህ ውጭ የክልሉ ጸጥታ ኃይል ምንም አይነት የኃይል እርምጃ ለመውሰድ እንዳልተንቀሳቀሱ ከሰላም ስምምነቱ ጋር የሚጣረስ አንድም ነገር ላለመፈጸም በከፍተኛ ጥንቃቄ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ጄነራሉ የፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነቱን ለመገምገም በአፍሪካ ህብረት በተመራው የስትራቴጂክ ግምገማ ወቅት እስካሁን ድረስ ስላልተሰሩ ጉዳዮች ተነስቶ እንደነበር እና እንዲሰራባቸው አቅጣጫ መቀመጡን አስታውሰዋል።
ከስትራቴጂክ ግምገማው በኃላም ለውጦች መታየታቸውን አመልክተዋል።
መሰረታዊ ከሚባሉት የስምምነቱ ክፍሎች እና ካልተፈጸሙት አንዱ ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው መመለስ ነው ያሉት ጄነራሉ " ተፈናቃዮች እንዲመለሱ የትግራይ ግዛት መከበር አለበት ብለዋል።
" በዚህ ላይ ' እንደ ራያና ጸለምቲ ቀላል ነው ፤ ምዕራብ ትግራይ ነው ከባዱ ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሁሉም ቀላል ነው ሁሉም ከባድ ነው ' እየተባለ ምክንያት ይቀርባል። አንዳንዴ ደግሞ ' አከራካሪ ቦታዎች ' እያሉ ይገልጹታል ሆኖም በህገ መንግሥቱ መሰረት ትግራይ ትግራይ ነው አከራካሪ የሚባል ነገር የለም ጥያቄ ካለ እንኳን በህግ አግባብ ነው መተግበር ያለበት " ሲሉ ተናግረዋል።
" ' በኃይል ይዣለሁ ፣ ይዣለሁ ማለቱ ፍጹም ሰላም አያመጣም " ሲሉ አክለዋል።
ጄነራሉ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ችግሮች ዘላቂ ሰላም በሚያመጣ መልኩ እንዲፈቱ እንደሚፈልግ ገልጸው " ለዚህም የመከላከያ ሰራዊት እና ፌዴራል ፖሊስ ኃላፊነት ወስደው እንዲሰሩ እየተደረገ ያለው " ብለዋል።
" በወረራ ተይዟል " ባሉት የትግራይ ክፍል ሁሉም ነገር ያለ አግባብ መቀየሩን አስታውሰው " ሁሉም ፈርሶ ወደነበረበት የትግራይ ቅርጽ እንዲመለስ ፌዴራል መንግሥት በትኩረት እየሰራ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
የትግራይ የጸጥታ ኃይል ስምምነቱን የሚያፈርሱ ተግባራት ላለመፈጸም ከፍተኛ ጥንቃቄ እያደረገ ነው ብለዋል።
" በማህበራዊ ሚዲያ እና በሌሎችም ፦
- በራያ አላማጣ፣
- በኦፍላና ፣
- በኮረም ላይ ትኩረት አድርገው የሚናፈሱት ወሬዎች ከእውነት የራቁ ናቸው። እነሱ እንደሚሉት በኃይል መያዝ የምንፈልገው አካባቢ የለም። በስምምነቱ መሰረት በፌዴራል መንግሥት ጥረት ነጻ እንዲሆንልን ነው የምንፈልገው " ሲሉ ገልጸዋል።
" ዘላቂ ሰላም የሚያረጋግጥና ዳግም ደም አፋሳሽ ጦርነትን የማይቀሰቅስ ተግባር እንዲፈጸም ነው የምንፈልገው በእርግጥ ችግሩን በሰላም ለመፍታት በነበረው ሂደት አለመግባባትና ፍጥጫ ነበር ይህ ለራሳቸው ሆነ ለሀገራችን ስለማይጠቅም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና የሰላም ተባባሪ እንዲሆኑ እንጥራለን " ብለዋል።
ዛሬ የአማራ ክልል መንግሥት በሰጠው ይፋዊ መግለጫ፤ " ከትናንት ታሪካዊ ስህተቱ መማር የተሳነው ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሓት) የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመጣስ ለአራተኛ ዙር ሕዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል " ሲል ከሷል።
እስካሁን ድረስ በጉዳዩ ላይ የፌዴራል መንግሥት የሰጠው አስተያየት የለም።
@tikvahethiopia
#Update
የአማራ ክልል መንግሥት ምን አለ ?
ዛሬ የአማራ ክልል መንግሥት ይፋዊ መግለጫ ሰጠ።
የክልሉ መንግሥት ፥ " ከትናንት ታሪካዊ ስህተቱ መማር የተሳነው ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሓት) የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመጣስ ለአራተኛ ዙር ሕዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል " ሲል ከሷል።
" ህወሓት የአማራ ክልል ተማሪዎችን መማሪያ መጽሐፍ እንደ ሰበብ ተጠቅሞ በይፋ ጦርነት ማወጁና መቀስቀሱ ይታወቃል " ሲል አስታውሷል።
የአማራ ክልል መንግሥት ህወሓትን " የመላ ኢትዮጵያ ጠላትና የደኅንነት ስጋት " እንደሆነ ገልጾ " ባለፉት 3 ዙሮች ከተደረገው ደም አፋሳሽ ጦርነት ትምህርት ሊወስድ ይችል ይሆናል በሚል ጭላንጭል ተስፋ የፌዴራል መንግሥት እጅግ እልህ አስጨራሽ ትዕግስት ተላብሶ ውይይቶች እንዲካሄዱ ተደጋጋሚ ጥረት ሲያደረግ ቆይቷል " ብሏል።
" የአማራ ክልል መንግሥትም በተደጋጋሚ ከትግራይ ጊዜያዊ አሥተዳደር ጋር በፌዴራል መንግሥት አማካኝነት ውይይት ለማድረግ በርካታ ሙከራዎች የተደረጉ ቢሆንም ህወሓት ይህን የሰላም አማራጭ ወደ ጎን በመተው የማንነት ጥያቄ ያለባቸውን የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረምና ዛታ አካባቢዎች ላይ ወረራ ፈፅሟል " ሲል ገልጿል።
" ህወሓት ወረራ የፈፀመባቸው ፦
- የራያ አላማጣ፣
- ራያ ባላ፣
- ኦፍላ፣
- ኮረምና ዛታ እንዲሁም የወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት አካባቢዎች የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት ከመፅደቁ በፊት በነበሩ አሥተዳደራዊ መዋቅርና አደረጃጀት በኀይል ጠቅልሎ ከመውሰድ ጀምሮ የዘር ማጥፋት ወንጀል እስከመፈፀም ድረስ አሰቃቂ ጥፋት የፈፀመባቸው አካባቢዎች ናቸው " ብሏል።
" ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ህወሓት በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የከፈተውን አሰቃቂ ጥቃት ተከትሎ ከተቀሰቀሰው ጦርነት በኃላ አካባቢዎቹ በጉልበት ተገፎባቸው የነበረውን ራሳቸውን የማሥተዳደር ነጻነት መቀዳጀት እንደቻሉ " የአማራ ክልል መንግሥት ገልጿል።
በኃላም የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መፈረሙን ፤ ህወሓት ግን ስምምነቱን በማክበር በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የድርሻውን ከመወጣት ይልቅ ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ በመጣስ የተለያዩ ጥፋቶችን ሲፈጽም እንደቆየ አመላክቷል።
" አሁንም እየፈጸመ ይገኛል " ብሏል።
የአማራ ክልል መንግሥት ፥ ህወሓት ደም አፋሳሽ የሆነ ጦርነት ለማድረግ ከመሞከር እንዲታቀብ እና የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲያከብር አሳስቧል።
" በአጭር ጊዜ በወረራ የያዛቸውን አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ " ሲል ጠይቋል።
" ይህ የማይሆን ከሆነ የአማራ ክልል መንግሥት እና ሕዝብ ከሌሎቹ ወንድምና እህት ኢትዮጵያዊያን ጋር በጋራ በመሆን ሀገርን ከማፍረስ መታደግና ሕዝባችንንም ከጥቃት ለመከላከል እንገደዳለን " ሲል አስጠንቅቋል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
#NEVACOMPUTER
በጣም በተመጣጣኝ ዋጋ ዘመናዊ የሆኑ 2023 እና 2024 ቢዝነስ ላኘቶፓች፣ እጅግ ፈጣን የሆኑ የኤዲቲንግ ላፕቶፓች እንዲሁም ለተማሪዎች ቅናሽ የሆኑ ኢሮፕ ስታዳርድ እና ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች አሉን። ከበቂ መስተንግዶ መረጃ እና ከአንድ አመት ዋስትና ጋር እንጠብቆታለን።
ነቫ ኮምፒዉተር ቴሌግራማችንን ይቀላቀሉ👇
/channel/nevacomputer
ስልክ፦ 0920153333
አድራሻ - መገናኛ ማራቶን ህንፃ ግራውንድ ፍሎር - NEVA COMPUTER
www.nevacomputer.com
#Update
“ ከታገቱ ሚያዚያ 19/2016 ዓ/ም ሰባት ወራት ይሆናቸዋል። እንደቀላል ነገር በወጡበት ቀሩ ” - የታጋች ባለቤት
ከ6 ወራት በፊት ወደ ባቱ (ዝዋይ) ለስራ ጉዳይ እየተጓዙ በታጣቂዎች ታገቱ ከተባሉ 6 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኞች መካከል 3ቱ ቢለቀቁም 3ቱ ግን እንዳልተለቀቁ ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልም የሚችለውን ሁሉ እንደሞከረ ከ2 ሳምንታት በፊት ገልጾልን ነበር።
በወቅቱ #እንባ እየተናነቃቸው ቃላቸውን የሰጡን የአንዱ ታጋች እህት ፣ “ በስልክ እንኳን ‘አለሁ በሕይወት’ እንዲለን ድምጹን ያሰሙን። 2.8 ሚሊዮን ብር ተከፍሎ 3ቱ ሠራተኞች ግን ከእገታ አልተለቀቁም ” ማለታቸው ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ “ ሠራተኞቹ የአገር ልማት ሥራ ላይ ሲደክሙ ነው ይሄ ችግር የደረሰባቸው። ግለሰቦቹን በማገት የሚመጣ ለውጥ የለም። በሰላም እንዲለቋቸው የሚል ጥሪ ማስተላለፍ እፈልጋለሁ ” ነበር ያለው።
አሁንስ ምን አዲስ ነገር አለ ?
ከ3ቱ ታጋቾች መካከል የሁለት ልጆቻቸው አባት የታገተባቸው ወ/ሮ ቤተልሄም ገዛኸኝ ፥ ታጋቾቹ አሁንም እንዳልተለቀቁ ገልጸዋል።
ከባለቤታቸው በተጨማሪ አንድ የሁለት ልጃቸው እናት የሞቱባቸው አባትና አንድ ሁለት ቤተሰቦቹን የሚያስተምር ሠራተኞች እንደሚገኙበትና ከታገቱ ከ6 ወራት በላይ ቢያስቆጥሩም ፣ አሁንም ያሉበት እንደማይታወቅ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
በንግግራቸው መሀል #የሚያለቅሱት ወይዘሮ ቤተልሄም በሰጡት ቃል ፣ “ በሕይወቱ ስለመኖሩም እየተጠራጠርኩ ነው። ሁለቱ ልጆቹ በትምህርታቸው ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ ደርሶባቸዋል። አንዷ ተመራቂ፣ አንዱ ማትሪክ ተፈታኝ ናቸው። እኔም የስኳርና የደም ግፊት ሕመምተኛ ነኝ ” ብለዋል።
ለመንግሥት ጭምር ባስተላለፉት መልዕክትም፣ “ ሞቷልም፣ አለም ቢባል እኮ አንድ ነገር ነው። እንዲህ አድርጉ የሚሉን ነገር ካለም ቢጠቁሙን መፍትሄ ነው” ብለው፣ “እንደ ቀላል ነገር በሀገራቸው ላይ ታግተው በወጡበት ቅርት ሲሉ ዝም ማለት በጣም ይከብዳልና ሁሉም ርብርብ ያድርጉልን ” ሲሉ ጠይቀዋል።
“ ከታገቱ ሚያዚያ 19 ቀን 2016 ዓ/ም 7 ወራት ይሆናቸዋል። እንደቀላል ነገር በወጡበት ቀሩ። እቃ እንኳን ሲጠፋ ዝም አይባልም እንኳን ሰው። እንደ ሰው ትኩረት ይሰጣቸው ” ሲሉም አክለው አሳስበዋል።
“ እንዲያው በእግዚአብሔር፣ በሁሉም ልጆች ባሏቸው አባቶች፣ እህት፣ ወንድም ባላቸው ሰዎች ሁሉ ስም ሁሉም ሰዎች እንደራሳቸው አይተው የሚችሉትን ነገር ሁሉ ይተባበሩን። ያጣሩ። ከእግዚአብሔር በታች ሰዎችን ነው የምለምነው ” ነው ያሉት።
#ThikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Ethiopia
የመጋቢት ወር ሀገር አቀፍ የዋጋ ግሽበት 26.2 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አሳወቀ።
በወሩ ከተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ፦
➡️ ምግብ ነክ ዕቃዎች (food items) 29 በመቶ ድርሻ ይዘዋል።
➡️ ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች (Non-food Items) 22 በመቶ በመሆን ተመዝግቧል።
በአጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱ #በየካቲት_ወር ከነበረበት 28.2 በመቶ ወደ 26.2 በመቶ በመሆን መጠነኛ ቅናሽ ማሳየቱን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አመላክቷል።
@tikvahethiopia
#ትግራይ
ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ምን አሉ ?
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች በክልሉ ለሚገኙ ሚድያዎች መግለጫ ሰጥተው ነበር።
በዚህም ወቅት ፥ " በፕሪቶሪያ ውል ያልተፈፀሙት እንዲተገበሩ እየሰራን እንቀጥላለን " ብለዋል።
" የፕሪቶሪያ ውል የፈረምነው የተለያዩ የትግራይ ቦታዎች ከክልሉ አስተዳደር ውጭ በነበሩበት በርካታ ወገኖች ከቄያቸው በተፈናቅሉበት ጊዜ ነበር " ያሉት ጄነራሉ " የውሉ ተዋዋዮች በህገ-መንግስት መሰረት የትግራይ ግዛታዊ አንድነት እንዲረጋገጥ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ ተስማምተዋል " ብለዋል።
" የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ውልን በጥንቃቄ መተግበር ይገባል " ሲሉ ገልጸዋል።
" አሁን በመታየት ያለው ውጤት የጦርነቱ ውጤት እንጂ የጦርነቱ መነሻ አይደለም " ሲሉ ገልጸዋል።
" የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ትግራይ በሃይል የተያዘባት መሬት ሙሉ በሙሉ መልሳ የተማላ ቁመናዋ መያዝ ፤ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለስ እንዲተገበሩ ያስገድዳል ይህ እንዲሆን ደግሞ በሃይል በተያዙ ቦታዎች ያሉ ታጣቂዎች መውጣትና ህጋዊ ያልሆነው አስተዳደር መፍረስ አለባቸው " ብለዋል።
" ህጋዊ ያልሆኑ አስተዳደሮች ማፍረስና ታጣቂዎች ትጥቃቻውን ማስፈታት የፕሪቶሪያ ውል የመጀመሪያ ምዕራፍ ሲሆን ቀጥሎ የሚደረገው ሁሉ #ሰላም ከተረጋገጠ በኋላ የሚሆን ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
" ተፈናቃዮች ሲመለሱ ክብራቸው ተጠብቆ ፣ የሚያስፈልጋቸው መሰረተ ልማት ሁሉ ተሟልቶ ሰብአዊ ድጋፍ ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎች በማድረግ መሆን አለበት " ያሉት ጀነራሉ " አስተዳደርን በሚመለከት ቀበሌዎችና ወረዳዎችን የሚያስተዳድሩ ጊዚያዊ አስተዳደሮች ራሱ ህዝቡ ይመርጣል " ብለዋል።
ዘላቂ መፍትሄ በሚመለከት ምን አሉ ?
" የፌደራል መንግስት ' አከባቢዎቹ በፌዴራል ስር ቆይተው #ሪፈረንደም ይካሄድ ' የሚል አቋም ያለው ሲሆን በእኛ በኩል ደግሞ በአከባቢው ጊዚያዊ አስተዳደር ተቋቁሞ ወደ ትግራይ ይመለሱ የሚል አቋም ነው ያለው፤ ይህ የአቋም ልዩነት እስካሁን አልተፈታም እንዲፈታ ደግሞ ቀጣይ ሰላማዊ ትግል እናደርጋለን " ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
Photo Credit - Tigrai & DW TV
@tikvahethiopia
#Update
“ ለአጋቾቹ 700 ሺሕ ከከፈልኩ በኋላ እንደገና 400 ሺሕ ጠየቁኝ ” - በሊቢያ ልጃቸው የታገተባቸው አባት
በአዲስ አበባ ከተማ በካሜራ ማን የሥራ ዘርፍ ተሰማርቶ ይሰራ የነበረው አብርሃም አማረ የተባለ ወጣት ሕይወቱን ለመለወጥ ወደ ውጭ እየተሰደደ በነበረበት ወቅት በሊቢያ በደላሎች እንደታገተባቸው፣ አጋቾቹ ልጁን ለመልቀቅ 950 ሺሕ ብር እንደጠየቋቸው የታጋች አባት አቶ አማረ ዓለም መግለጻቸውን ከሁለት ሳምንታት በፊት ዝርዝር መረጃ አድርሰናችሁ ነበር።
የታጋቹ አባት በወቅቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ አጋቾቹ እያሰቃዩት ነው። ዱብ እዳ ወረደብኝ። ወደ 950 ሺሕ ጠይቀዋል። ልጄ ‘በአንድ መጋዘን ወደ 200 ሰዎች ታጎርን’ ነው የሚለው ” ማለታቸው አይዘነጋም።
አሁንስ የታጋቹ ጉዳይ ከምን እንደደረሰ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ አቶ አማረ ዓለምን ጠይቋል እሳቸውም ፥ “ ለአጋቾቹ ከ700 ሺሕ ከከፈልኩ በኋላ እንደገና 400 ሺሕ ጠየቁኝ ” ብለዋል።
“ ባለፈው ጎረቤቶች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ በጎ አድራጊዎች ተባብረው ገንዘብ ተሰባሰበልኝ። እግዚአብሔር ይመስገን ብዬ ከታሰረበት ወጣልኝ። አሁን እንደገና ወደዚህ (ወደ ኢትዮጵያ) መመለስ አይችልም ተብሎ እንደገና 400 ሺሕ ብር ደግሞ ተጠይቀናል ” ሲሉ አክለዋል።
ከዚህ በፊትም በተገለጸው መሠረት አጋቾቹ ታጋቹን ለመልቀቅ እንዲላክላቸው ጠይቀው የነበረው 950 ሺሕ ነበር ቀንሰውላችሁ ነው 700 ሺሕ የላካችሁት ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ፥ ቀንሰውልላቸው እንደነበር ገልጸው፣ አሁን ከተጠየቁት 400 ሺሕ ብር ሲደመር ግን በአጠቃላይ ደላሎች የጠየቋቸው የገንዘብ መጠን ከ1 ሚሊዮን በላይ እንደሆነ አስረድተዋል።
አሁን 400 ሺሕ ብሩን ላኩ የተባሉት ለምን እንደሆነ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ፣ ' ልጁ ወደ ጣሊያን እንዲሻገር 'በሚል ሊቢያ እና ጣሊያን ያሉ ደላሎች ገንዘቡን እንደጠየቋቸው፣ ልጃቸው አሁን ትሪፓሊ ከተማ ውስጥ እንደሚገኝ ፣ ገንዘቡ ካልገባ አደጋ ሊገጥመው እንደሚችል ልጃቸው ጭምር እንደነገራቸው ነው ያስረዱት።
ድጋሚ የተጠየቀውን 400 ሺህ ብር አሟልቶ ለመላክ 150 ሺሕ ብር እንደጎደላቸውም የታጋቹ አባት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የአቶ አማረን ልጅ ጨምሮ በሊቢያ ታግቶ 1.7 ሚሊዮን ብር የተጠየቆበት፣ 800 ሺሕ ብር ለአጋቾቹ በመላኩ ይለቀቃል ተብሎ እየተጠበቀ ያለውን የሀዋሳውን ታጋች የጌድዮ ሳሙኤልን ጉዳይ ከጊዜ በኋላ በዝርዝር መረጃ የምናቀርብላችሁ ይሆናል።
#TikvahEthiopiaFamhlyAA
@tikvahethiopia
#Update #Raya
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ " በደቡብ ትግራይ እና በሌሎች በኃይል በተያዙ የትግራይ ግዛቶች የተፈጠረው ክስተት በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ወይም በሕወሃት (TPLF) አልያም በትግራይ እና በአማራ ክልል አስተዳደሮች መካከል የተፈጠረ ግጭት አይደለም " ብለዋል።
" ይህ ሁለቱ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ፈራሚ ወገኖች ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ እያደረጉት ያለውን አወንታዊ ግንኙነት ለማደናቀፍ የፈለጉ የስምምነቱ ጠላት የሆኑ ኃይሎች የፈጠሩት ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
@tikvahethiopia
አዲሱን የአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግ በመጠቀም ደንበኞች እንዴት ወደ አዋጭ አካውንት ገንዘብ ማስተላለፍ ይችላሉ?
ሊንኩን በመጠቀም መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ!
ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.boaMobileBanking&hl=en&gl=US
ለአፕል ስልኮች https://apps.apple.com/us/app/boamobile/id6463218765
ለሁዋዌ ስልኮች https://appgallery.huawei.com/app/C110106115
#BankofAbyssina #mobilebanking #boamobile #bankinginethiopia #banksinethiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#Genocide
የዘር ፍጅት (ጄኖሳይድ) እንዳይፈጸም በመከላከል እና ሲፈጸምም በማስቆም ላይ የሚሰራው ተቋም " የጄኖሳይድ ዎች " ባደረገው ምርምር የሰው ልጆች ልባቸው ሲደድር የሚጠናወታቸው የዘር ጭፍጨፋ አባዜ 8 ደረጃዎች አሉት።
እነዚህም #በተደራጀ እና #ተቋማዊ በሆነ መንገድ የሚፈጸሙት ናቸው።
ደረጃዎቹ :-
1ኛ. መከፋፈል (Classification) - እኛና እነርሱ ብሎ በመከፋፈል ለየት ይላሉ ተብለው ሚታሰቡትን የኅብረተሰብ ክፍሎች #በቀልድም_ጭምር በማንቋሸሽ በሰዎች መካከል ያለውን ልዩነት አለማክበር።
2ኛ. የሚታይ መገለጫ መስጠት (Symbolization) - ይህ የጥላቻ ግልጽ መገለጫ ሲሆን ይሁዲዎች በናዚ ጀርመን ቢጫ ኮከብ ያለበት ልብስ እንዲለብሱ እንደተደረገው ነው፡፡
3ኛ. ከሰው ክብር ዝቅ ማድረግ (Dehumanization) - ይህ ተግባር ከራስ የተለዩትን ሰብዓዊ ክብርም ሆነ መብት በመንፈግ ይፈጸማል፡፡ በሩዋንዳ አክራሪ ሁቱዎች የቱትሲ ዘውግ ተወላጆችን " #በረሮ ፣ #እባብ " ይሏቸው እንደነበረው መሆኑ ነው፡፡ ይህ ሂደት ገዳዮቹ ' እየገደልን ያለነው ሰው አይደለም፤ ታዲያ ድርጊታችን ምኑ ላይ ነው ጥፋትነቱ ? ' እንዲሉ መንገዱን ይጠርግላቸዋል፡፡
4ኛ. ማደራጀት (Organization) - በጥላቻ ላይ የተመሠረቱ መንግሥታት አንድን ሕዝብ የሚያጠፋላቸውን ኃይል #ያሰለጥናሉ፡፡
5ኛ. በተቃራኒ ጎራዎች ማሰለፍ (Polarization) - ሕዝቡ በዘውጉ ከጨፍጫፊው እና ከተጨፍጫፊው ወገን ሚናውን እንዲለይ ይደረጋል፡፡ በብዛት ይህ የሚሆነው በጥላቻ ቡድኖች ውትወታ በመገናኛ ብዙሃን የጥላቻውን መርዝ በመርጨት ነው፡፡ አንዱን ዘውግ ከሌላው ለይቶ በማውጣት " ጠላት ነው " ብሎ ማወጅ ፤ ይህ የገዳዩን ዘውግ አባላት በቀላሉ ለማሳመንና ለህሊናው እንዲቀለው ለማድረግ ጥቅም ላይ የሚውል ነው።
6ኛ. ዝግጅት (Preparation) - ሰለባዎቹ በልዩነቶቻቸው ተለይተው ይፈረጃሉ፡፡ የጭፍጨፋው ንድፍ አውጭዎች ሰዎችን በመኖሪያ አድራሻቸውና በሌሎችም መለያዎች ይፈርጁና ለፍጅት ያዘጋጇቸዋል፡፡
7ኛ. ፍጅት (Extermination) - በታቀደና ሆነ ተብሎ በተመቻቸ ዘመቻ የጥላቻ ቡድኖቹ ሰለባዎቻቸውን ይጨፈጭፋሉ፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በዘር ፍጅት ማንነታቸውን መለየት እስኪከብድ ድረስ ተጨፍጭፈዋል፡፡
8ኛ. ክህደት (Denial) - ግድያውን የፈጸሙትም ሆኑ ቀጣይ ትውልዶች ምንም ዓይነት ጥፋት ያልተፈጸመ በማስመሰል ክህደት ይፈጽማሉ፡፡
ከዚህ የጭፍጨፋ ሂደት እንደምንረዳው የዘር ፍጅት በአንድ ሌሊት ያለምንም ዝግጅት ስለማይፈጸም ራሳችንን ከላይ ከተጠቀሱት በሌላው ላይ ጉዳት ከሚያደርሱ ከስተቶች ፈጽሞ ማራቅና የዕለት ከዕለት ድርጊቶቻችንን መገምገምም ያሰፈልገናል።
እነዚህን የዘር ፍጅት አመላካች ሂደቶች በማናቸውም ደረጃ በእንጭጩ መቅጨት ከተቻለ የከፋ እልቂትን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት ይችላል።
ሁቱትሲ
ኢማኪዩሌ ኢሊባጊዛና ስቲቭ ኤርዊን
በመዘምር ግርማ
#Rwanda2024 #Kwibuka #Remembering
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
2016 ዓ/ም
@tikvahethiopia
" የሟች ኪስ ውስጥ #ማንነቱን የሚገልጽ መረጃ ስላላገኘን ፎቶውን ለማሰራጨት ተገደናል " - የዓዲግራት ከተማ ፓሊስ
በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ዓዲግራት ከተማ ቀበሌ 03 በተባለ መጠጥ ቤቶች በብዛት በሚገኙበት ቦታ ሚያዝያ 9/2016 ዓ.ም ሌሊት አሰቃቂ ግድያ ተፈፅሟል።
አስቃቂ ግድያው በመፈፀም የተጠረጠሩ 3 ግለሰቦች በህዝብ ጥቆማ የሟቹ አስከሬን በወደቀበት አከባቢ በሚገኝ መጠጥ ቤት በቁጥጥር ስር ውለው የሟች አስከሬን ወደ ዒድግራት ሆስፒታል ተወስደዋል።
የዓዲግራት ከተማ ፓሊስ ምርመራው ጨርሶ ለቀብር የሟቹ ቤተሰብ ቢያፈላልግም ዜናው እስከ ተጠናቀረበት ቀን ሰዓትና ደቂቃ የሟች ቤተሰብ አልተገኙም።
በሟቹ ኪስ ማንነቱ የሚጠቅስ መረጃ እንዳላገኘ የገለፀው የዓዲግራት ፓሊስ ፤ የሟቹ ፎቶ በሚድያና በማህበራዊ የትስስር ገፅ ለማስራጨት መገደዱን ገልጿል።
ሟቹን የሚያውቅ ካለ ወደ ዓዲግራት ከተማ ፓሊስ ፅህፈት ቤት ደውሎ እንዲያሳውቅ ፖሊስ ትብብር ጠይቋል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
ፍቶ፦ የዓዲግራት ከተማ ፓሊስ ፅህፈት ቤት
@tikvahethiopia
የረቂቅ መንገድ
እራሳችንን እንደመስታወት የምናይበት…ሌሎችን እንደ መፅሐፍ የምናነብበት! የጠፋብን ያልተገለጠልን ነገር ካለ ያለጥርጥር የረቂቅ መንገድ ላይ እናገኘዋለን።
በቅርብ ቀን በአቦል ቲቪ 465!
የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ1,999 ብር ከ1 ወር ነፃ የሜዳ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ።
የዲኤስቲቪ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/2WDuBLk
#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #YerekikMenged #የረቂቅመንገድ
" ጥናቱ ሙሉ በሙሉ ቆሟል " - የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኙ የመንግሥት ተቋማት አገልግሎት የሚሰጡበትን ሰዓት ከስምንት ወደ 16 ሰዓት ለማራዘም የተጀመረው ጥናት መቆሙን የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል።
ጥናቱ የተጀመረው በከተማ አስተዳደሩ ሥር በሚገኙ የመንግሥት ተቋማት የሚሠሩ ሠራተኞች የግል ገቢ እንዲኖራቸው፣ እንዲሁም የከተማዋን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማነቃቃት ታስቦ መሆኑን ቢሮው ማስታወቁ ይታወሳል።
አሁን ላይ ግን የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሥራ ሰዓት ለማራዘም የተጀመረው ጥናት ሙሉ ለሙሉ ቆሟል፡፡
የከተማው የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጣሰው ገብሬ (ዶ/ር) ፥ " የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን የሥራ ሰዓት ለማራዘም መነሻ ጥናት ተደርጎ ነበር ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ የለም " ሲሉ ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናግረዋል።
ኃላፊው በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ መስጠት እንደማይፈልጉ ተናግረዋል።
ወደፊት የታሰበው አሠራር ተግባራዊ ይደረጋል አይደረግም የሚለውን እንደማያውቁ ገልጸዋል።
ጥናቱ የተጀመረው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኙ መሥሪያ ቤቶችን የሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 አስቀድሞ ለማስጀመርና ከ11፡30 በኋላ እስከ ምሽት ለማስቀጠል ታቅዶ ነበር፡፡
ዕቅዱ ይፋ የተደረገው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የከተማዋ መ/ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥን አስመልክቶ መሆኑን ቢሮው ግንቦት 3 ቀን 2015 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው ውይይት መግለጹን ሪፖርተር ጋዜጣ በዘገባው አስታውሷል።
@tikvahethiopia
#NEVACOMPUTER
በጣም በተመጣጣኝ ዋጋ ዘመናዊ የሆኑ 2023 እና 2024 ቢዝነስ ላኘቶፓች፣ እጅግ ፈጣን የሆኑ የኤዲቲንግ ላፕቶፓች እንዲሁም ለተማሪዎች ቅናሽ የሆኑ ኢሮፕ ስታዳርድ እና ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች አሉን። ከበቂ መስተንግዶ መረጃ እና ከአንድ አመት ዋስትና ጋር እንጠብቆታለን።
ነቫ ኮምፒዉተር ቴሌግራማችንን ይቀላቀሉ👇
/channel/nevacomputer
ስልክ፦ 0920153333
አድራሻ - መገናኛ ማራቶን ህንፃ ግራውንድ ፍሎር - NEVA COMPUTER
www.nevacomputer.com
" ቲክቶክ ላይት " ጥያቄ ቀረበበት።
አዲሱ መተግበሪያው ' ቲክቶክ ላይት ' በፈረንሳይ እና ስፔይን አገልግሎት የጀመረው ቲክቶክ በህጻናት እና ተጠቃሚዎች የአዕምሮ ጤንነት ላይ ሊያስከትል ስለሚችለው አደጋ ያለውን ግምገማ በ24 ሰዓት ውስጥ እንዲያቀርብ ዛሬ የአውሮፓ ኮሚሽን ጠየቀ።
ከዋናው ቲክቶክ መተግበሪያ አነስ ብሎ የወጣው የቲክቶክ መተገበሪያ ተጠቃሚዎች #ተከፍሏቸው የቪዲዮ ምስሎችን እንዲመለከቱ በማድረግ በሚያስቆጥሯቸው ነጥቦች የመግዛት አቅምና ዋጋ ያላቸውን የስጦታ ካርዶችን የሚሽልም ነው፡፡
በመተግበሪያው ተሳታፊ ለመሆን ተጠቃሚዎች ቢያንስ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
ሽልማቱን ለማግኘት በቀን እስከ 1.06 ዶላር የሚደርስ ሽልማት ለማግኘት በየቀኑ አንድ ሰዐት ድረስ ቪዲዮውን መመልከት ይችላሉ፡፡
የአውሮፓ ኮሚሽን የቻይናው ቲክቶክ ባለቤት ባይትዳንስ (ByteDance) መተግበሪያውን ከመልቀቁ በፊት ሊያስከትል ስለሚችለው አደጋ ቁጥጥርና ጥንቃቄ ግምገማ ማድረግ ነበረበት ብሏል።
ጥያቄው የቀረበው ቲክቶክ ያወጣው አዲሱ " Task and Reward Lite " የተባለው መተግበሪያ፣ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ሕፃናትን ደህንነት እንዲሁም በተጠቃሚዎች የአእምሮ ጤና ላይ ፣ በተለይ ሱስ አስያዥ ባህሪን ከማነሳሳት ጋር ተያይዞ ሊያመጣ የሚችለውን ተፅእኖ መሰረት በማድረግ ነው ” ሲል የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
መተግበሪያው ሊያስከትለው ስለሚችለው አደጋ ቁጥጥር እንዲሁም ጥንቃቄ ያለውን ግምገማ እንዲያቀርብ ከተሰጠው የ24-ሰዐት የጊዜ ገደብ ባሻገር፣ ቲክቶክ የተጠየቀውን ተጨማሪ መረጃ እ ኤ አ እስከ ሚያዝያ 26 ድረስ መስጠት አለበት ሲል ኮሚሽኑ አሳስቧል።
የቲክቶክ ቃል አቀባይ ፥ " አዲሱን መተግበሪያ በተመለከተ ከኮሚሽኑ ጋር በቀጥታ ተገናኝተናል፣ ለቀረበልን ጥያቄም ተገቢ ምላሽ እንሰጣለን " ማለታቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።
መረጃውን ቪኦኤ ፤ አዣንስ ፍራንስ ፕሬስን ዋቢ በማድረግ ነው ያስነበበው።
@tikvahethiopia
#NewsAlert
ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ አካሂዶ በሁለት ጉዳዮች ውሳኔ አሳልፏል።
ውሳኔ ከተላለፈበት አንዱ ጉዳይ የሽግግር ፍትሕ ረቂቅ ፖሊሲ ነው።
ምክር ቤቱ ፥ " በሀገሪቱ በተለያዩ ዘመናት የተከሰቱ እና የቀጠሉ ተደራራቢ እና ሰፊ የተጎጂና የአጥፊ ወሰን ያላቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ የእርስ በእርስ ግጭቶች፣ ያልጠሩ ትርከቶች እና በደሎችን ለመፍታት የተለያዩ ሙከራዎች ተደርገዋል " ብሏል።
" ሆኖም እነዚህ አሰራሮች ፦
- በእውኀት፣
- በዕርቅ፣
- በምህረት እና በፍትሕ ላይ የተዋቀረ እና በግልፅ ፖሊሲ የሚመራ ሁለንተናዊ የሽግግር ፍትሕ ስልትን አካታች፣ ሰብአዊ መብት ተኮር በሆነ እና በተሰናሰለ መንገድ ባለመተግበራቸው የሚፈለገውን ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት አልቻሉም " ሲል ገልጿል።
በመሆኑንም የሽግግር ፍትሕ ሂደቱን በተደራጀ፣ በተቀናጀ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመምራትና ለመተግበር እንዲቻል ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቀረቡን አስረድቷል።
ምክር ቤቱም በረቂቅ ፖሊሲው ላይ ከተወያያ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ #በስራ_ላይ_እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
@tikvahethiopia
" 400 ሺህ ብር ክፈል ይሉኛል። እኔ ይሄን ያህል ገንዘብ ከየትም ላመጣ አልችልም። ... ልመና ወጥታችለሁ። " - አባት
ኤርትራዊው ስደተኛ ባልታወቁ ሰዎች ተወስዶ ለማስለቀቂያ 400 ሺህ ብር እንደተጠየቀበት ተነገረ።
አባት ገንዘቡን ለማግኘት ልመና ወጥተዋል።
በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ በጭላ ቀበሌ በተቋቋመው የዓለምዋጭ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚኖሩት ኤርትራዊው ስደተኛ አቶ መሀመድ ኡስማን ባለፈው መጋቢት 26 ቀን 2016 ልጃቸው አማን መሀመድ መታገቱን ገልጸዋል።
ልጃቸው በአቅራቢያ ካለው የዳባት ትምህርት ቤት ቀን 10:00 እየተመለሰ እያለ ባልታወቁ ሰዎች መታገቱን አመልክተዋል።
አጋቾቹ በየሁለት ቀን በመደወል የማስለቀቂያ ገንዘብ እየጠየቋቸው እንደሆነ ጠቁመዋል።
አባት አቶ መሀመድ ፥ " እየደወሉ 400 ሺህ ብር ክፈል ብለውኛል። እኔ ይሄን ያህል ገንዘብ ከየትም ላመጣ አልችልም። እስከዚህች እለት ድረስ ይኸው በየአብያተክርስቲያናቱ እና በየመስጂዱ ለልጄ ማስለቀቂያ የሚሆን ገንዘብ ለማሰባሰብ ልመና ላይ ነኝ። ሌሎች ስደተኞችም በልመና ይተባበሩኛል እስካሁን የተገኘ ገንዘብ የለም " ብለዋል።
አጋቾቹ በየደወሉ ቁጥር ልጃቸው እያለቀሰ ድምፁን እንደሚያሰሟቸውም ገልጸዋል።
ልጃቸው በተለምዶ " ባጃጅ " በሚባለው ባለ3 እግር ተሽከርካሪ ታግቶ መወሰዱን ገልጸው የሰሌዳ ቁጥሩን ለፖሊስ ቢያመለክቱም እስካሁን ውጤት የለም።
የኢትዮጵያ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት ፥ " አንድ ልጅ የጠፋ አለ እገታ ሳይሆን አይቀርም የሚል መረጃ ስለመጣ እንደተቋም ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የማጣራት ስራ እየሰራን ነው " ብሏል።
የጭላ ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ምናለ ግንብነህ በበኩላቸው ፥ ከህፃኑ ጋር ሌላ የአስተማሪ ልጅም መወሰዱን ጠቁመዋል።
" እንዴት ሄደ ? ወደየት ሄደ ? የሚለውን ፖሊስ እየሰራበት ነው " ያሉት አስታዳዳሪው " አንድ የታሰረ ልጅ አለ መረጃ ስጥ እየተባለ ነው ያለው " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው የቪኦኤ አማርኛ አገልግሎት መሆኑን ይገልጻል።
@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia
🎁 ልዩ ልዩ የኢንተርኔት ጥቅሎችን ከ M-PESA በመግዛት 50% ተጨማሪ ዳታ አግኝተን በነጻ ከሳፋሪኮም ወደ ሳፋሪኮም እንደዋወል! 🤳
ዳታ እንግዛ! በነጻ እንደዋወል!
🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#Furtheraheadtogether
#Rwanda #UK
ዩናይትድ ኪንግደም (UK) ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ #ሩዋንዳ ለማዛወር የያዘችው እና ከፍ ያለ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር የታመነው ዕቅድ የሃገሪቱ ሕግ ሊሆን እንደተቃረበ ቪኦኤ ዘግቧል።
የዕቅዱ ተቃዋሚዎች ደግሞ ስደተኞቹን #በኃይል ከአገር የማስወጣቱን ውጥን ማገድ የሚችል አዲስ የሕግ መቋቋሚያ ለማበጀት እየሰሩ እንደሆነ ተነግሯል።
የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን እገዳ ተጽዕኖ ለማስቀረት እና በላይኛው ምክር የቀረበውን ተቃውሞ ለመቋቋም የታለመው ይህ ሕግ በዚህ ሳምንት በሃገሪቱ ፓርላማ ይድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
‘ የሩዋንዳ ዕቅድ ’ የሚል ቅጽል የተሰጠው ይህ ውጥን ጠቅላይ ሚንስትር ሪሺ ሱናክ ‘ሕገ ወጥ ስደተኞችን ወደዚያች አገር የሚያጓጉዙ ጀልባዎች እንቅስቃሴ’ ለማስቆም ለገቡት ቃል ‘ወሳኝ እርምጃ ነው’ ተብሏል።
የሱናክ ቃል አቀባይ ዴቭ ፓሬስ ምን አሉ ?
" የእንግሊዝ ፓርላማ በያዝነው ሳምንት በሕገ ወጥ አስተላላፊዎች ከፍተኛ እንግልት እና ብዝበዛ የሚፈጽምባቸውን ሰዎች ህይወት የሚታደግ ህግ የማጽደቅ እድል ያገኛል።
አሁን ባለው አካሄድ መቀጠል እንደማንችል ግልፅ ነው። በመሆኑም ይህ ሁኔታ የሚለወጥበት ጊዜው አሁን ነው። " ብለዋል።
በአነስተኛ ጀልባዎች ተጓጉዘው የእንግሊዝ ቻናልን በማቋረጥ ከዚያ የሚደርሱትን ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ሩዋንዳ ለማዛወር እና በቋሚነትም ኑሯቸውን በዚያ እንዲያደርጉ በማቀድ ሁለቱ አገሮች የተፈራረሙት ስምምነት 2 ዓመታት አስቆጥሯል።
በፍርድ ቤት የታገደው ዕቅድ እንግሊዝን በትንሹ 470 ሚሊዮን ዶላር ሊያስወጣት እንደሚችል ቪኦኤ በዘገባው አስፍሯል። #VOA
@tikvahethiopia
ቴሌብር ኢንጌጅ ምንድነው ?
(ኢትዮ ቴሌኮም)
ኩባንያችን የዲጂታል ሕይወትን በማቅለል እልፍ ጉዳይ በአንድ መተግበሪያ መከወን በሚያስችለው " ቴሌብር ሱፐርአፕ " ደንበኞች ከመገበያየት እና ገንዘብ ከማስተላለፍ ባሻገር መረጃን በነጻ በመለዋወጥ ማህበራዊ ግንኙነታቸውን እና ቢዝነሳቸውን የሚያጠናክሩበት ቴሌብር ኢንጌጅ የተሰኘ አገልግሎት አስጀመረ፡፡
አዲሱ ቴሌብር ኢንጌጅ የቢዝነስ እና ግለሰብ ደንበኞች #ያለምንም_ተጨማሪ_የኢንተርኔት_ክፍያ ለተናጠል ወይም ለጋራ ፦
- የጽሁፍ፣
- የፎቶ፣
- ድምጽ፣
- ቪዲዮ እና ፋይሎችን ለማጋራት የሚያስችል ሲሆን ከዚህም ባሻገር ለበዓል ወይም ለተለያዩ ማህበራዊ ሁነቶች የተናጠል ወይም የቡድን መልካም ምኞት መልእክት ከገንዘብ ስጦታ ጋር መላክ የሚያስችላቸውን አዲስ ገጽታ አካቷል፡፡
በተጨማሪም በጭውውቶች ወቅት ገንዘብ ለመጠየቅ፣ ለመላክ እና ለመቀበል፣ ቢል ለማጋራት እንዲሁም ጥቅል ወይም የአየር ሰዓት መግዛትን ጨምሮ በርካታ የዲጂታል አገልግሎቶችን በአንድ መተግበሪያ እንዲያከናውኑ ያስችላል፡፡
ኩባንያችን ለክቡራን ደንበኞቹ አዳዲስ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አማራጮችን በማስተዋወቅ የቢዝነስ ተሞክሮአቸው እና የዕለት ተዕለት ኑሮአቸው ላይ ተጨማሪ ምቾት እና ቅልጥፍና በመጨመር ለዲጂታል ኢትዮጵያ እውን መሆን ሁሉን አቀፍ ጥረት ማድረጉን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
ለተጨማሪ ማስፈንጠሪያውን https://bit.ly/3W3291x ይጠቀሙ፡፡
#telebirrEngage
#Ethiotelecom
#Update
አላማጣ ከተማ በመከላከያ ሠራዊትና በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆኗን ከንቲባው አቶ ኃይሉ አበራ ለቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት በሰጡት ቃል ተናግረዋል።
የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው መገደላቸውን እና ሌሎች የወረዳው እና የከተማዋ ኃላፊዎች አካባቢውን ለቅቀው ወደ ሌሎች የራያ ወረዳዎች መሄዳቸውንም ገልፀዋል።
አቶ ኃይሉ አበራ ምን አሉ ?
- " ከትላንት ሰኞ ጀምሮ ከተማው በመከላከያ ሠራዊት እና ፌዴራይል ፖሊስ ስር ይገኛል። "
- " አላማጣ ከተማው መከላከያ እና ፌደራል ፖሊስ ነው ያለው። ዙሪያው የተያዘው ግን በትግራይ ታጣቂዎች ነው። "
- " የራያ አላማጣ ወረዳ እና የአላማጣ ከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ከሰኞ ጀምሮ አካባቢውን ለቅቀው ወጥተዋል። በአሁኑ ሰዓት ቆቦ ነው የሚገኙት። "
- " አሁን እኛ እዚያ እየሠራን አይደለም። "
አቶ ኃይሉ አበራ ፥ የራያ አላማጣ አካባቢዎች በአማራ ክልል ስር ከሆነ በኋላ በተመሠረው የመንግሥት መዋቅር ውስጥ የነበሩት ኃላፊዎች በአሁኑ ሰዓት ከተማውን እያስተዳደሩ አይደለም ብለዋል።
በሌላ በኩል ፥ የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ሞላ ደርበው እና ለሌችም ሰዎች በትናንትናው ዕለት መገደላቸውን አቶ ኃይሉ አበራ ተናግረዋል።
" አቶ ሞላ ሕይወታቸው ያለፈው ከህወሓት ጋር በተያያዘ አይደለም። ሕግ የያዘው ነገር ስለሆነ ተጣርቶ የሆነ ነገር እስከሚባል ድረስ ዝርዝሩን አልገልፅም " ብለዋል።
ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ በርካታ የአላማጣ ነዋሪዎች ወረዳውን እና ከተማውን ለቀው በመውጣት ወደ አጎራባች አካባቢዎች መሸሻቸውን ተነግሯል።
ነዋሪዎች ሸሽተውባቸዋል ከተባሉ አጎራባች አካባቢዎች አንዱ ቆቦ ከተማ ሲሆን አንድ የቆቦ ከተማ ኃላፊ ከትናትን ጀምሮ በርካታ ወደ ከተማዋ እየገቡ መሆኑን ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በትግራይ በኩል ያሉ ነዋሪዎችን ያነጋገረ ሲሆን " በተለይም የአለማጣ ከተማ ከትላንት ጀምሮ ከማንም ታጣቂ ነፃ ናት " ብለዋል።
" የአማራ ይሁን የትግራይ ታጣቂዎች በቦታው አለመኖራቸውን " ገልጸው ስጋት ያደረበት ነዋሪው ወደ አጎራባች አካባቢ መሄዱን አስረድተዋል።
እስካሁን በራያ ጉዳይ በአማራ እና በትግራይ ክልል ደረጃ እንዲሁም በፌዴራሉ መንግሥት በኩል የተሰጠ ማብራሪያም ሆነ አስተያየት የለም።
@tikvahethiopia
#Update
በአዲስ አበባ ከተሞ ቦሌ ሚሊኒዬም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ከቀናት በፊት መገደላቸው የተነገረው የፋኖ አባላት ወላጆች የልጆቻቸው አስከሬን እንዲሰጣቸው ያቀረቡት ጥያቄ ምላሽ አለማግኘቱን ተናግረዋል።
ይህ የተናገሩት ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ክፍል በሰጡት ቃል ነው።
ባለፈው ሳምንት አርብ ዕለት የተገደሉት ናሁሰናይ አንዳርጌ እና አቤኔዘር ጋሻው ከሞቱ አራተኛ ቀናቸውን ቢያስቆጥሩም አስከሬናቸውን እስካሁን ማግኘት እንዳልቻሉ እናቶቻቸው ገልጸዋል።
እናቶቹ የልጃቸውን አስከሬን ለማግኘት እታች ላይ እያሉ እንደሆኑ አመልክተዋል።
እናቶቻቸው ምን አሉ ?
ወ/ሮ ሐረገወይን አዱኛ (የናሁሰናይ አንዳርጌ እናት) ፦
" ሰኞ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አምርቼ ነበር። ጉዳዩን የሚያየው የፌደራል ፖሊስ ነው የሚል ምላሽ ነው የተሰጠኝ።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም አስከሬን እንዲሰኝ የማመልከቻ ደብዳቤ ያስገባሁ ሲሆን ይህ ነው የሚል ቁርጥ ያለ ምላሽ አልተሰጠኝም።
' ይሄንን ጉዳይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ነበር እኮ መመለስ የነበረበት፤ ለምንስ እዚህ ድረስ መጣችሁ ? ' ነው የተባልኩት።
ዛሬ ደግሞ እንደገና ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ሄጄ የሚሉኝን እሰማለሁ።
ከባድ ነው ለእናት፤ በጣም ከባድ ከሚገባው በላይ። አስከሬን ነው የጠየቅኩት፤ ግድ ስለሆነ ምላሹን ለማግኘት ያው በተስፋ እየጠበቅኩ ነው። ምላሹንም ከመልካም ነገር ጋር እጠብቃለሁ። "
ወ/ሮ ኤልሳ ሰለሞንም (የአቤነዘር አባተ እናት) ፦
" ልጄ በተገደለ ማግስት ነው ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ የመጣሁት አስከሬን ለማግኘት ውጣ ውረድ ገጥሞኛል።
ያሳዝናል ፤ ህጻን ነው ደግሞ። አንድ ልጄን ምን ላድርግህ ? ከባድ ነው።
ሰኞ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አቅንቼ ኃላፈውን እና ኮሚሽነሩን አግኝቼ ማናገር ባልችልም በዚያው የሚሠሩ ሠራተኞች ይህ ጉዳይ የሚመለከተው የፌደራል ፖሊስን ነው የሚል ምላሽ ነው የሰጡኝ።
የፌደራል ፖሊስ ትላንት ምላሽ አልሰጠኝም ዛሬ ተመልሼ እሞክራለሁ።
ጳውሎስ ሆስፒታል አምርቼ የልጄ ስም ዝርዝሩ ውስጥ እንዳለ ከተነገረኝ በኋላ ከፖሊስ ትዕዛዝ ማምጣት እንዳለብኝ ተገልጾልኛል። "
ፖሊስ ምን ምላሽ ሰጠ ?
ወላጆቻቸው የልጆቻቸውን #አስክሬን እስካሁን አለመቀበላቸውን በተመለከተ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ተጠይቀው ፥ በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃው እንደሌላቸው እና ይሄን የሚመለከተው የፀጥታ እና ደኅንነት ግብረ ኃይል ወይም የፌደራል ፖሊስን እንደሆነ ተናግረዋል።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ጄላን አብዲ ደግሞ ፥ " ይህ ጉዳይ የሚመለከተው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንደሆነ " ገልጸዋል።
የፋኖ አመራር ነው የተባለው ናሁሰናይ አንዳርጌ እንዲሁም እንዲሁም አቤነዘር ጋሻው ባለፈው ሳምንት ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ መገደላቸውን ሌላኛው የፋኖ አባል ሀብታሙ አንዳርጌ ምንም ሳይሆን በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ መግለጹ ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት መሆኑን ይገልጻል።
@tikvahethiopia
#4WCOMPUTERS
አዲስና በብዙ አማራጭ የአሜሪካ የአውሮፓ የዱባይ ላፕቶፖችን በተመጣጣኝ እና ከገበያዉ በተሻለ ዋጋ ከመልካም መስተንግዶ ከተሟሉ ሶፍትዌሮች ጋር ይዘን እንጠብቆታለን። በተጨማሪ የ1 ዓመት ዋስትና እንዲዉም የ30 ቀን የመሞከሪያ ግዜ እንሰጣለን። የተለያዩ ዓይነት ላፕቶፓች ለማየት ና ለመምረጥ ሊንኩን ይጠቀሙ 👉 t.me/computers4w
ስልክ፦ 0911867992
አድራሻ - መገናኛ ማራቶን ህንፃ 1ኛ ፎቅ -ፎርደብሊ ኮምፒውተር
#ራያ
“ ሕወሓት /TPLF ወረራ ፈጽሟል። የፕሪቶሪያውን ስምምነት ጥሷል ” - አቶ ሀይሉ አበራ
የትግራይ እና አማራ ክልሎች የወሰን ይገባኛል ጥያቄዎች በሚያነሱባቸው የራያ አላማጣ አካቢዎች ሰሞኑን በተለይ ዛሬ የተኩስ ልውውጥ መደረጉን የአላማጣና አካባቢው ባለስልጣናትና የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የአላማጣ ከተማ እና ዙሪያው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ የትግራይ ታጣቂዎች በስናይፐርና ሌሎች መሳሪያዎች የታገዘ ተኩስ ተከፍቶብናል ” ብለዋል።
አክለውም፣ “ ባለፈው ጦርነት በደረሰብን ሀዘን እንባችን አልደረቀም። መንግሥት ግን እስከመቼ ድረስ ነው የዚህን አካባቢ ችግር የማይቀርፈው ? ነው ወይስ ሕዝቡ እርስ በእርሱ እንዲተላለቅ ነው የፈለገው ? ” ሲሉ ጠይቀዋል።
“ ወያኔ የኔ ናቸው የሚላቸው የአላማጣና አጠገቡ አካባቢዎች በሙሉ የአማራ እንጂ የትግራይ መሬት ሆነው አያውቁም። ደማችን ይፍሰስ እንጂ መሬታችንን አንለቅም። መንግሥት የትግራይ አመራሮችን ይዳኝልን ” ብለው፣ በንጹሐንና በንብረት ላይ ጉዳት ሳይደርስ እንዳልቀረ፣ አሁን ግን ትክክለኛውን ቁጥር ለመግለጽ ለጊዜው እንደሚያስቸግር አስረድተዋል።
ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው አንድ የአላማጣና አካባቢው አመራር በሰጡት ቃል፣ “ ወያኔ ሰሞኑን በሰላማዊ ሰልፍ ሽፋን ተቆጣጥሯቸው ከነበሩ ቦታዎች በተጨማሪ ተቆጣጥሯል። አርሚ 24 ነው ተኩስ የከፈተብን ” የሚል አጭር ቃሎ ሰጥተው ሁነቱን በሂደት እንደሚገልጹ ጠቁመዋል።
በተጨማሪ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለግጭቱ ሁኔታ፣ የደረሰው ጉዳት ምን እንደሚመስል አላማጣ ከተማን በከንቲባነት እያስተዳደሩ ለሉትና የወሎ ራያ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ ለሆኑት አቶ ሀይሉ አዱኛ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን ፥ “ ሕወሓት ወረራ ፈጽሟል። የፕሪቶሪያውን ስምምነት ጥሷል። ፍላጎታቸውን በኃይል ለመፈጸም እየሞከሩ ነው። ሂደቱ በዋነኝነት ይህን ነወሰ የሚመስለው። ዝርዝር ገለጻ ነገ እሰጣለሁ ” ብለዋል።
ዝርዝር ምላሻቸው ነገ ይቀርባል።
🔵 በትግራይ በኩል ምን ተባለ ?
የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለው አባል ፥ በትግራይ በኩል ነዋሪዎችን እና የመንግስት ሰዎችን ስለ ሁኔታው ጠይቋል።
ዛሬ ከሰዓት ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ፥ " የራያ ጨርጨር ፣ የራያ አላማጣ ፣ ኮረም ኦፍላና ዛታ አከባቢ ያሉ ቀበሌዎች ከታጣቂዎች ነፃ ሆነዋል " ብለዋል።
አጠቃላይ በርካታ ስፍራዎች ቦታውን ይዘው ከነበሩ ታጣቂዎች ነጻ ሆኗል ሲሉ ገልጸዋል።
በከፍተኛ የፀጥታ ስጋት ምክንያት ከአካባቢው የወጡ ነዋሪዎችም አሉ ሲሉ ገልጸዋል።
አሁንም ቢሆን የፕሪቶሪያው ስምምነት ተከብሮ የአማራ ታጣቂዎች ከአካባቢው ሊወጡ የተፈናቀለው ህዝብም ወደ ቦታው ሊመለስ ይገባል ብለዋል።
ትናንትና ወደ ራያ ጨርጨር አስተዳዳሪ አቶ ካልኣዩ ግደይ ደውለን የነበረ ሲሆን መጠነኛ ግጭት እንደነበረ ተናግረዋል።
ዛሬ በሰጡት ቃል ደግሞ ፥ " በወረዳው በአማራ ታጣቂዎች ሰር የነበሩት ሁለት ቀበሌዎች ነፃ ወጥቷል " ብለዋል።
ሌሎች የክልሉን ኃላፊዎች ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።
የትግራይና አማራ ክልሎች ይገባኛል በሚያነሱበት በራያ አካባቢ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የግጭት ሁኔታዎች ይታዩ እንደነበር በሁለቱም በኩል ያሉ የመንግስት አካላትን በማነጋገር መረጃ ማድረሳችን ይታወሳል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
#Kwibuka
" ክፍፍል እና ፅንፈኝነት ካልተገታ በማናቸውም ቦታ ወደ ዘር ማጥፋት ሊያመራ ይችላል " - ፖል ካጋሜ
ከ30 ዓመታት በፊት በሩዋንዳ በ100 ቀናት ብቻ እስከ 1,000,000 ሚደርሱ ሰዎች የተጨፈጨፉበት የሩዋንዳ ዘር ፍጅት እየታሰበ ይገኛል።
የዘር ፍጅቱ የተፈፀመበትን 100 ቀናት ታሳቢ በማድረግ ከሚያዚያ 7 (እ.ኤ.አ) አንስቶ ለ100 ቀናት የዘር ጭፍጨፋው ሰለባዎች ይታሰባሉ ፤ ይህም ኪውቡካ /Kwibuka/ ይባለል።
ከሳምንት በፊት በኪጋሊ በነበረ ስነስርዓት ላይ ፕሬዜዳንት ፖል ካጋሜ ፤ ከዘር ፍጅቱ በህይወት የተረፉ ዜጎች ለብሄራዊ አንድነት ሲሉ ስላደረጉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።
" እጅግ የሚከብደውን የእርቀ ሰላም ሸክም እናተ እንድትሸከሙ ጠየቅናችሁ እንሆ ለሀገራችን ስትሉ ይሄንን በየቀኑ ማድረጋችሁን ቀጥላችኃል ስለዚህ እናመሰግናችኃለን " ነው ያሉት።
ፖል ካጋሜ ፥ አሁንም ድረስ በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት #የጎሳ_ፖለቲካ እየተባባሰ መሄዱን እና የብሄረሰብ ማጽዳት አደጋ መደቀኑን በማንሳት አስጠንቅቀዋል።
" ሩዋንዳ ውስጥ የደረሰው መከራ ማስጠንቀቂያ ሊሆን ይገባል። ክፍፍል እና ፅንፈኝነት ካልተገታ በማናቸውም ቦታ ወደ ዘር ማጥፋት ሊያመራ ይችላል " ብለዋል።
ሩዋንዳ መከራ ውስጥ በገባችበት ጊዜ በርካታ ሀገራት የሰላም አስከባሪ ልጆቻቸውን ሩዋንዳ መላካቸውን እና እነዛም ወታደሮች ለሩዋንዳ እንደደረሱላት ገልጸዋል።
" ነገር ግን #በጥላቻም ይሁን #በፍራቻ ያልደረሰልን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
በሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ በወቅቱ በነበረው የሁቱ መንግሥት መሪነትና የሁቱ ብሄረሰብ አባላት በሆኑ ጽንፈኛ አክራሪዎች እንዲሁም በመንግሥት በሚደገፈው የ " ኢንተርሀምዌ ' ሚሊሻ አማካኝነት እስከ 1,000,000 ቱትሲዎች ፣ ለዘብተኛ ሁቱዎችና ትዋዎች ተጨፍጭፈዋል።
Rwandan genocide
Apr 7, 1994 – Jul 15, 1994
AP / VOA
#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ
@tikvahethiopia