tikvahethiopia | Unsorted

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1519094

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Subscribe to a channel

TIKVAH-ETHIOPIA

" የሞባይል ስልክ እና ላፕቶፕ ጠፍቶብኛል የሚል ማስረጃ በማቅረብ ንብረቱን መረከብ ይችላል " - ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ በቴክኖሎጂ በመደገፍ ባደረገው ክትትል ግምቱ 150 ሺህ ብር የሚያወጣን ሞባይል ስልክን ከሌባ ላይ የገዛችን ግለሰብን በቁጥጥር ስር አውሎ ንብረቱን ማስመለሱን አስታወቀ፡፡

ግለሰቧ ከወንጀለኞች በተለያየ ጊዜ የገዛቻቸው ልዩ ልዩ ሞባይል ስልኮችን ፣ ላፕቶፖችንና ታብሌት ይዞ ምርመራው መቀጠሉን አዲስ አበባ ፖሊስ ገልፆል፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው ...
    
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው " አለምነሽ ፕላዛ " አካባቢ አንድ ግለሰብ  ግምቱ 150 ሺህ ብር የሚያወጣ አይነቱ አይፎን ፕሮ ማክስ ሞባይል ስልክ ይቀማሉ።

ይህን ተከትሎ አደይ አበባ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ያመለክታሉ።

የግለሰቡን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ፖሊስ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ሌሎች መንግስታዊ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በቴክኖሎጂ በመደገፍ ባደረገው ክትትል የተሰረቀው ስልክ አራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ አካባቢ ከሚገኝ አንድ የሞባይል መሸጫ ሱቅ መኖሩ ይረጋገጣል፡፡

ፖሊስ የህግ አግባብን በመከተል ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትእዛዝ በማውጣት ባደረገው ብርበራ ከግለሰቡ ላይ የተቀማውን ስልክ ጨምሮ በልዩ ልዩ ጊዜያት ከተለያዩ ቦታዎች የተሰረቁ ፦

➡️ 85 ስማርት ሞባይል ስልኮችን  ፣

➡️ 4 ለፕቶፖችን ፣

➡️ 1 ታብሌትና የላፕቶፕ ቦርሳዎችን በኤግዚቢትነት ይዟል።

የቅሚያ ወንጀል የፈፀመውን ተጠርጣሪ ለመያዝ ክትትሉ መቀጠሉን ፖሊስ አመልክቷል።

የሞባይል ስልክ እና ላፕቶፕ ጠፍቶብኛል የሚል ማንኛውም ግለሰብ አደይ አበባ ስቴዲዮም አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በአካል በመቅረብ ሞባይል ስልኩን በመለየትና  ትክክለኛ ማስረጃ በማቅረብ ንብረቱን መረከብ  እንደሚችል አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

#AddisAbabapolice

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Amahra

በአማራ ክልል ፤ በምዕራብ ጎንደር ዞን ' ታጣቂዎች ' ባደረሱት ጥቃት አንዲት ሱዳናዊ ስደተኛን ጨምሮ 3 ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል።

በጥቃቱ በሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል።

የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት የጥቃቱ ባለፈው እሁድ ሰኔ 9/2016 መፈጸሙን አረጋግጧል።

ጥቃት የተፈጸመው ከገንደ ዉሃ ወደ ነጋዴ ባህር ሲጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ " ደረቅ አባይ " በተባለ ስፍራ እንደሆነ ተጠቁሟል።

የዞኑ ኮሚኒኬሽን ጥቃቱ ከቀኑ 10 ሰዓት መድረሱን አሳውቋል።

የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት ፥ በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ ታጣቂዎች ተኩስ ከከፈቱ በኃላ አንድ ውስጥ የነበረ የመንግስት የጸጥታ አባል ወርዶ የታጣቂዎቹ ጥቃት ለመከላከል ባደረገው የተኩስ ልውውጥ ከመኪናው ውስጥ የነበረች አንዲት ሱዳናዊ ስደተኛና ሌሎች ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን አስረድቷል።

" የጥቃቱን መድረስ ተከትሎ የመንግስት ጸጥታ ኃይል በአፋጣኝ ባይደርሱ ኖሩ ከአሁኑ የበለጠ የከፋ ጉዳት ሊከሰት ይችል ነበር " ሲልም ገልጿል።

የተፈጸመው ጥቃት በዘፈቀደ እንጂ በስደተኛዋ ላይ ያነጣጠረ እንዳልነበር አክሏል።

ስደተኛዋ በወቅቱ ፤ መድሃኒት ገዝታ ወደ መጠለያዋ እየተመለሰች ነበር ተብሏል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ስደተኞች ከመጠለያ ጣቢያቸው እንዳይወጡ በተደጋጋሚ ቢነገራቸውም አንዳንዶቹ ተግባራዊ ማድረግ ባለመቻላቸው  ለአደጋ እየተጋለጡ ሲል ገልጿል።

የመረጃው የዶቼቨለ ሬድዮ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update #Adwa

ከ3 ወር በላይ ታግታ አድራሻዋ ጠፍቶ ዛሬ በግፍ መገደለዋ የተረጋገጠው ተማሪ ማህሌት ተኽላይ አጋቾችዋ ገድለው እንደቀበሯት ማመናቸውን ፓሊስ አስታወቀ።

የትግራይ ማእከላይ ዞን ፓሊስ የወንጀል ምርመራ ሃላፊ ኮማንደር ፀጋይ ኣስፍሃ ዛሬ ለ104.4 የመቐለ ኤፍኤም በስልክ በሰጡት ቃል ፥ በእገታው እና ግድያው የተጠረጠሩ መያዛቸውን ገልጸዋል።

ግለሰቦቹም ለፓሊስ በሰጡት ቃል ተማሪ ማህሌትን ገድለው በዓድዋ የፓንአፍሪካ ዩኒቨርስቲ ሊገነባበት የመሰረተ ደንጋይ የተጣለበት ቦታ መቅበራቸውን ቦታው ድረስ በመምራት አሳይተዋል ፤ አምነዋል ብለዋል። 

ተጠርጣሪዎቹ  ማህሌትን እንዴት እንዳገቷት ፣ አግተው ወዴት እንደወሰዱዋት ፣ እንዴት ገድለው እንደቀበርዋትና አስከሬንዋ የተቀበረበት ቦታ ጭምር በዝርዝር ለፓሊስ ማሰየታቸውን ኮማንደሩ በሰጡት መረጃ አረጋግጠዋል።

የተማሪ ማህሌት ተኽላይ አስከሬን ከተቀበረበት ጉድጓድ የማውጣት ስነ-ሰርዓት በመከናወን ላይ መሆኑ የገለፁት ኮማንደር ፀጋይ ፤ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ ተጨማሪ ምርመራ ይደረግበታል ብለዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
@TikvahEthiopiaTigrigna

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ተገድላ ተገኘች።

ለ91 ቀናት ታግታ የተሰወረችው ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ተገድላ ተገኝታለች።

ለወላጆችዋ ዛሬ መርዶ ተነግሯቸዋል።

የአስከሬን የአሸኛነት ስነ-ሰርዓት ዛሬ በአቡነ አረጋዊ ቤተክርስትያን ዓድዋ እንደሚፈፀም ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በተማሪ ማህሌት ተኽላይ ግድያ ዙሪያ ፓሊስ የሚሰጠው መረጃ ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።

በተማሪ ማህሌት ተኽላይ እገታና ስወራ ጉደይ የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ለወራት ተከታታይ መረጃ ሲያቀርብ እንደነበር አይዘነጋም።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Amahra

በአማራ ክልል ፤ ምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢጠህናን ወረዳ ፤ ጅጋ ከተማ እሁድ እለት ከቀኑ 11:30 ገደማ ሲቪል ሰዎች ላይ ግድያ ተፈጽሟል ሲሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የአካባቢዎች ነዋሪዎች በርካታ ሰዎች በመንግስት የጸጥታ ኃይል መገደላቸውን ከሟቾቹ ውስጥ ከባንክ ሰራተኞች እንዳሉበት ጠቁመዋል።

እንደ ነዋሪዎቹ ቃል ፥ አንድ ባለ አንድ ጋቢና መኪና የመንግስት የጸጥታ ኃይሎችን ጭኖ ከደምበጫ ወደ ፍኖተሰላም ሲጓዝ ጅጋ ፀደይ ባንክ አካባቢ በ ' ፋኖ ' ታጣቂዎች የደፈጣ ጥቃት ተፈጽሞበታል።

ታጣቂዎቹ ጥቃቱን አድርሰው ወደጫካ ካፈገፈጉ በኃላ ከጥቃቱ በኃላ የደረዱ ሌሎች የጸጥታ ኃይሎች የሲቪል ሰዎች ግድያ መፈጸቸውን ነዋሪዎች አመልክተዋል።

አንድ ነዋሪ ፥ " ድንገት ምንም ሳናስበው ነው አካባቢው በተኩስ የተናወጠው ፤ ከጫካ የመጡ የፋኖ ኃይሎች ናቸው፤ አንደኛውን ፓትሮል ላይ ጥቃት ፈጸሙ ከኋላ የሚከተል ፓትሮል ነበር ' ጎህ ' የሚባል መናፈሻ ነገር አለ እዛ ተኩስ ነበር። ብዙ ሰው ተገደለ። አንድ የአቢሲንያ ማናጀር፣ አንድ የአዋሽ ባንክ አካውንታት ፤ አንድ ምንም የማትናገር ዝናሽ የምትባል ሴት አጠቃላይ 13 ሰዎች መጠጥ የሚጠጣ፣ በቦታው የነበረ ተመቷል የመዝናኛ / የእረፍት ቀን ነበር። የሞቱት ከጫካው ኃይል ወይም ከተማው ውስጥ ካለው የጸጥታ ኃይል ገለልተኛ የስራ ሰው ነው " ብለዋል።

ሌላ ነዋሪ ፥ " የተኩስ ልውውጥ ነበር። መጀመሪያ ' ፋኖ ' ነበር የተኮሰው ፤ አጋጣሚ ሆኖ በፓትሮሉ ላይ ከነበሩት የሰራዊት አባላት አንድ ስናይፐር ተኳሽ አንድ ጥቁር ክላሽ የያዘ ልጅ ከመኪናው ፈጥነው ዘለው እነሱ ብቻ ነው የቀሩት ፤ ከዛ ከኃላ ሲመጣ የነበረ ሌላ የጸጥታ ኃይል ' ጎህ ' የሚባል የመዝናኛ አካባቢ የመንግሥት ሰራተኞች፣ የባንክ ሰራተኞች ፣ መምህራን የነበሩበት እዛ ያገኙትን በአሰቃቂ ሁኔታ በብሬን ገድለዋል። የሟቾች ቁጥር ከ20 ይበልጣል ነው እንደሰማነው። የአብዛኞቹ በየአካባቢያቸው ስርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል " ሲሉ ተናግረዋል።

የጅጋ ከተማን እና የአካባቢውን ህዝብ ወክለው የተመረጡት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ አበባው ደሳለው ፥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተጠናቋል በተባለበት በሲቪል ሰዎች ላይ ግድያ መፈጸሙ የሚያሳዝን ነው ብለዋል።

ከዚህ ቀደምም በሌሎችም ከተማዎች በሲቪል ሰዎች ላይ ስለሚደረስ ግድያ በተለያዩ መድረኮች መናገራቸውን አስታውሰው " ግን ሃሳባችን ሳይሰማ ቀርቶ ይሄ ሆኗል " ብለዋል።

" በጣም የሚያሳዝነው አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተጠናቋል የሽግግር ፍትህ ይኖራል ምክክር ኮሚሽን ስራውን ይሰራል ከታጣቂዎች ጋር ድርድር እና ውይይት ይደረጋል በተባለበት ሰዓት ይህ መፈጠሩ ያሳዝናል " ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ አበባ በዕለቱ ተገድለዋል ያሏቸውን የ13 ሰዎች ስም ዝርዝር በእጃቸው እንዳለ ይህን ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ መላካቸውን አሳውቀዋል።

የም/ቤት አባሉ ፥ " በክልሉ በመንግስት የጸጥታ ኃይል እና በፋኖ መካከል የሚደረገው ውጊያ ህዝብ ላይ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ ሁለቱም ኃይሎች ወደ ድርድር ሊመጡ ይገባል " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ሁኔታው እየተጣራ ነው ብሏል።

የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ስለ ጉዳዩ አስተያየታቸውን ለማድመጥ በተደጋጋሚ ስልክ ቢደወለም አላነሱም።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

Announcement of Professional Training Programs

1. Python Programming + Data Analytics and Visualization (4 Months)
2. Python Programming + Artificial Intelligence (2 Months)

By: Addis Ababa University,
Addis Ababa Institute of Technology (AAiT),
School of Electrical & Computer Engineering

Registration Deadline: June 27, 2024
Training Starts on: July 1, 2024
Registration: Addis Ababa University,
Addis Ababa Institute of Technology (AAiT),
School of Electrical and Computer Engineering, Main Building 1st Floor, Office Number: 124

Online Registration Link: https://forms.gle/VwkHzvE8cVEdvV6P8

Telephone: +251-940-182870 / +251-913-574525

Email: sece.training@aait.edu.et / menore.tekeba@aait.edu.et

For more information: Read instructions here ==> https://forms.gle/VwkHzvE8cVEdvV6P8

Telegram Channel: /channel/TrainingAAiT

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Mekelle

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የመቐለ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገልጿል።

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ዛሬ ነው።

በዚህም በጊዜያዊነት የጀመራቸው አገልግሎቶች ፦
☑️ ፓስፖርት ማደስ፣
☑️ የጠፋ ፓስፖርት መተካት፣
☑ የተበላሸ ወይ እርማት የመስጠት አገልግሎቶች እንደሆነም ተገልጿል።

የመቐለ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ፅህፈት ቤት ተወካይ ክንፈሚካኤል ረዳሀኝ ዛሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ከጦርነቱ በፊት በፅህፈት ቤቱ በርካታ አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር አመልክተዋል።

በጦርነቱ ሁሉም አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር አስታውሰዋል።

ከፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነት በኃላ ቢዘገይም የፓስፓርት እድሳት አገልግሎት አሁም መሰጠት እንደተጀመረ ገልጸው ፤ " በመላ ትግራይ የሚገኙ የፓስፓርት እድሳት ፈላጊዎች በአካል መምጣት ሳይስፈልጋቸው ባሉበት ሆኖው በኦንላይን መገለግል ይችላሉ " ብለዋል።

ተገልጋዮች ወደ (መቐለ) ፅ/ቤቱ መምጣት ያለባቸው ሁሉም ነገር ጨርሰው ማህተም ለማስመታት ብቻ እንደሆነ ጠቁመዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
            

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ኦዲት #ኢትዮጵያ

(ከ2015 የበጀት ዓመት የፋይናንስ ሕጋዊነት ኦዲት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት)

➡️ የበጀት አጠቃቀም ፦

ኦዲት በተደረጉ መስሪያ ቤቶች የተፈቀደላቸውን በጀት በስራ ላይ ያዋሉት ሂሳብ ሲነጻጸር ከበጀት በላይ ወጪ የተደረገበት ፣ በርካታ ያልተሰራበት በጀት ተገኝቷል።

በ20 መ/ቤቶች በልዩ ልዩ የሂሳብ መደቦች በደንቡ መሰረት #ሳያስፈቅዱ ለእያንዳንዱ የበጀት ኮድ ከተደለደለው በላይ ወጪ የሆነ ሂሳብ ከመደበኛው በጀት ብር 524. 7 ሚሊዮን ፣ ከውስጥ ገቢ 288.9 ሚሊዮን ፣ ከካፒታል በጀት 489.4 ሚሊዮን በድምሩ 1.3 ቢሊዮን ብር ተገኝቷል።

በኮድ ከተደለደለው በጀት በላይ ውጭ ያደረጉ ዋና ዋና መ/ቤቶች ፦
🟠 ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ 322.5 ሚሊዮን
🟠 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ተጠሪ ተቋማቱ 267.9 ሚሊዮን
🟠 ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ 173.2 ሚሊዮን
🟠 ወለጋ ዩኒቨርሲቲ 125.1 ሚሊዮን
🟠 የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት 109.5 ሚሊዮን
🟠 ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ 91.3 ሚሊዮን
🟠 አምቦ ዩኒቨርሲቲ 83.3 ሚሊዮን
🟠 አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 75.1 ሚሊዮን

ሁለት መስሪያ ቤቶች ደግሞ 9.7 ሚሊዮን ብር በጀት ስለመኖሩ ሳይረጋገጥ / ሳይፈቀድ ክፍያ ተፈጽሞ ተገኘቷል።

➡️ ከደንብ እና መመሪያ ውጭ የተከፈለ ፦

በ30 መ/ቤቶች ብር 16 ሚሊዮን 470 ሺህ ከደንብና መመሪያ ውጭ አላግባብ ተከፍሏል።

ዋና ዋናዎቹ መ/ቤቶች ፦
🔴 ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር 3 ሚሊዮን
🔴 የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት 2 ሚሊዮን 889 ሺህ
🔴 ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ 2 ሚሊዮን 42 ሺህ
🔴 መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ 1 ሚሊዮን 156 ሺህ

➡️ በመስሪያ ቤት ለሌሉና ከስራ ገበታ ለተሰናበቱ ሰራተኞች የተከፈለ ደመወዝ ፦

በ16 መስሪያ ቤቶች በመስሪያ ቤት ለሌሉ እና ከስራ ለተሰናበቱ ሰራተኞች ብር 485 ሺህ 183 ከ56 ሳንቲም ደመወዝ ተከፍሎ ተገኝቷል።

➡️ በበልጫ አላግባብ የተከፈለ ወጪ ፦

በ32 መ/ቤቶች እና በ9 ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በተለያዩ የግንባታና ግዥዎች 4.9 ሚሊዮንና ለውሎ አበልና ሌሎች ክፍያዎች 57.6 ሚሊዮን በድምር 62.6 በብልጫ ተከፍሎ ተገኝቷል።

➡️ የግዥ አዋጅ ደንብና መመሪያ ያልተከተሉ ግዥዎች ፦

በ73 መ/ቤቶች እና በ15 ቅ/ጽቤቶች ብር 2 ቢሊዮን 199 ሚሊዮን የመንግስት ግዥ አዋጅ ደንብ እና መመሪያን ሳይከተል ግዥ ተፈጽሟል።

° በጨረታ መግዛት ሲገባው ያለጨረታ በቀጥታ የተፈጸመ ግዥ 1.8 ቢሊዮን ብር
° መስፈርት ሳይሟላ በውስን ጨረታ የተገዛ 104.3 ሚሊዮን ብር
° ግልጽ ጨረታ መውጣት ሲገባው በዋጋ ማወዳደሪያ የተፈጸመ 96.1 ሚሊዮን ብር
° የዋጋ ማወዳደሪያ ሳይሰበሰብ በቀጥታ የተፈጸመ ግዥ 13.8 ሚሊዮን ብር
° ሌሎች የግዥ ሂደት ያልተከተሉ 134.6 ሚሊዮን ዋና ዋና ናቸው።

ዋና ዋና መስሪያ ቤቶች (ደንብና መመሪያ ሳይከተሉ ግዥ የፈጸሙ)፦
⚫ ገቢዎች ሚኒስቴር በዋናው መ/ቤትና በቅርንጫፍ ፅ/ቤት 1.4 ቢሊዮን
⚫ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት 91 ሚሊዮን
⚫ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር 65.5 ሚሊዮን
⚫ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን 62.9 ሚሊዮን
⚫ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ 57.1 ሚሊዮን
⚫ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ 37.4 ሚሊዮን
⚫ የጉምሩክ ኮሚሽን ዋና መ/ቤት እና በድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት 34 ሚሊዮን

➡️ በአማካሪ መሃንዲሳ ሳይረጋገጥ የተከፈለ ክፍያ ፦

የግንባታ ክፍያ #በአማካሪ_መሃንዲስ ተረጋግጠው መከፈላቸውን ለማረጋገጥ በተደረገ ኦዲት በ2 መ/ቤቶች 170 ሚሊዮን  394 ሺህ በአማካሪ መሃንዲስ የክፍያ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሳይቀርብ ክፍያ ተፈጽሞ ተገኝቷል።

👉 ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር 169.7 ሚሊዮን ብር ከፍሎ ተገኝቷል።

➡️ የተከፋይ ሂሳብ ፦

በ14 መ/ቤቶች 1.7 ቢሊዮን ብር በተከፋይ ሂሳብ ተይዞ ተገኝቷል። ለማን እንደሚከፈል እንኳን ተለይቶ አይታወቅም።

የተከፋይ ሂሳብ ለባለመብት መለየት ካልቻሉ መስሪያ ቤቶች ፦
🔵 የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር 1.5 ቢሊዮን
🔵 የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር 131.8 ሚሊዮን
🔵 ማዕድን ሚኒስቴር 29.9 ሚሊዮን ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ኦዲት

የተሰበሰበው ገቢ #ትክክለኛነቱን ለማረጋገጥ ሂሳብ ኦዲት ሲደረግ በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት #በዶላር የተሰበሰበ 1.3 ሚሊዮን ገቢ ትክክለኝነቱን ማረጋገጥ #አልተቻለም።

የፌዴራል ዋና ኦዲተር ማንኛውም ገቢ ተገቢ ማስረጃ ሳይሟላ በገቢ መመዝገብ ፍጹም ትክክል እንዳልሆነ አስገንብዝቦ የገቢ ማስረጃዎች በትክክል ተደራጅቶ እንዲያዝ ተገቢው ማስተካከያም እንዲደረግና እርምጃ እንዲወሰድ አሳስቧል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ኢትዮጵያ #ኦዲት

የ2015 በጀት ዓመት የፌዴራል የመንግስት መስሪያ ቤቶች የኦዲት ክንውን ላይ ማብራሪያ እየተሰጠ ነው።

ሂሳብ አቅራቢ የነበሩት 173 የፌዴራል መንግስት ባለ በጀት መስሪያ ቤቶች ሲሆኑ የ162 መ/ቤቶች እና 58 ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በፌዴራል ኦዲተር መ/ቤት 11 ደግሞ በሂሳብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን ኦዲት ሊደረጉ ታቅዶ ነበር።

10 መስሪያ ቤቶች 4 ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በጸጥታ ምክንያት ኦዲት ተጀምሮ ተቋርጧል። 1 መ/ቤት ቢሮ አላቀረበም።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በጥሬ ገንዘብ ሂሳብ ላይ ታገቢው ቁጥጥር ይደረግ እንደሆነ ለማረጋገጥ ክትትል ሲደረግ ፥ በሁለት መስሪያ ቤቶች ብቻ ብር 383 ሺህ 238 ከ48 ሳንቲም ጉድለት ተገኝቷል።

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ሴጅ_ማሰልጠኛ

ADVANCED STANDARDS AND PRACTICES OF ACCOUNTING ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን።
👉 IFRS + Peachtree + Asset Valuation + IFRS Conversion + IPSAS + Quick Book በአንድ ላይ
👉 ስልጠናው ሙሉ በሙሉ በተግባር የተደገፈና ፒስትሪ (Peachtree Software) ላይ የሚሰጥ ነው።

ስልክ ፦ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
Tiktok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
Linkedin: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ኢትዮጵያ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ፤ " ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ስለማስመለስ " ምን ይላል ?

➡️ #ማንኛውም_ሰው በቀጥታ ሆነ #በተዘዋዋሪ ያለው ንብረት ወይም የኑሮ ደረጃው አሁን ላይ ባለበት ወይም አስቀድሞ በነበረበት ስራ ወይም በሌላ መንገድ ከሚያገኘው ወይም ሲያገኝ ከነበረው ህጋዊ ገቢ የማይመጣጠን እንደሆነ እና የንብረቱን ወይም የኑሮ ደረጃውን ምንጭ በተመለከተ ምክንያታዊ የሆነ የወንጀል ጥርጣሬ በኖረ ጊዜ የዚህ አይነቱ የኑሮ ደረጃ ወይም ያለው ንብረት እንዴት ሊኖረው እንደቻለ ለፍርድ ቤት ካላስረዳ በስተቀር ንብረቱ #ይወረሳል።

➡️ ህጋዊ ገቢ እንዳለው የሚያስረዳ የተመዘገበበት ስርዓት የሌለው ወይም ገቢው እነስተኛ በመሆኑ #ከግብር_ነጻ የሆነ ሰው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያለው ንብረት ወይም የኑሮ ደረጃው ከሚያገኘው ወይም ሲያገኝ ከነበረው ህጋዊ ገቢ የማይመጣጠን እንደሆነ የዚህ አይነቱ የኑሮ ደረጃ ወይም ያለው ንብረት እንዴት ሊኖረው እንደቻለ ለፍርድ ቤት ካላስረዳ በስተቀር ንብረቱ ይወረሳል፡፡

➡️ " በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ያፈራው ንብረት " ማለት ፦

° በራሱ ስም የሚገኝ ንብረት፣

° በራሱ ስም ባይሆንም ለራሱ ጥቅም ሲያዝበት ወይም ሲቆጣጠረው የነበረው ንብረት ፣

° የተጠቀመው ወይም ደግሞ ያስወገደው ንብረት፣

° በሽያጭ ፣ በስጦታ ወይም በማንኛውም ሁኔታ #ያስተላለፈውን ንብረት ይጨምራል፡፡

➡️ ዐቃቤ ሕግ " #ምንጩ_ያልታወቀ_ነው " ብሎ የጠረጠረውን ማንኛውንም ንብረት ዝርዝር እና የተገኘበትን አግባብ የሚያሳይ መግለጫ እንዲያቀርብ በፅሁፍ ጥያቄ የቀረበለት ማንኛውም ሰው ጥያቄው በደረሰው በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ለዐቃቤ ህግ ዝርዝር ማስረጃዎችን በማያያዝ በፅሁፍ ማቅረብ ይኖርበታል።

➡️ የንብረቱን ምንጭ እንዲያስረዳ የተጠየቀው ሰው የንብረቱን ምንጭ ለማስረዳት የሚያቀርበው ማስረጃ ሀጋዊ መሆን አለበት።

ተጨማሪ ....

☑️ አንድ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ አውጥቶ የሚሰራ ነጋዴ ወይም ድርጅት ሕጋዊ ገቢው ተብሎ የሚገመተው ለተገቢው ባለስልጣን በወሩ ወይም በአመቱ ከንግዱ ያገኘሁት ብሎ ያሳወቀው የገቢ መጠን ሲሆን ወይም ተገቢው ታክስ የተከፈለባቸው ገቢዎች ሆነው ሲገኙና የታክስ ደረሰኝ ሲቀርብ ሲሆን ከዚህ ውጪ ህጋዊ ታክስ ያልተከፈለባቸው ገቢዎች ከህጋዊ ገቢ ውጪ ያፈራው ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ተብሎ ሊወሰን ይችላል።

☑️ ምንጩን ሲያስረዳ " ከውጪ የተላከለኝ ገንዘብ ነው " የሚል ማንኛውም ግለሰብ ገንዘቡ በሕጋዊ መንገድ #በባንክ_ሥርዓት ውስጥ ያለፉ ግብይቶች ወይም ክፍያዎች ስለመሆናቸው በተገቢው የባንክ ደረሰኝ አስደግፎ ማቅረብ የሚገባው ሲሆን ከዚህ ውጪ ያለው ግን እንደ ምንጩ ያልታወቀ ገቢ ተደርጎ ይቆጠራል።

በረቂቅ አዋጁ ላይ #ምንጩ_ያልታወቀ_ንብረት ክስ የሚቀርብበት ጊዜ እና የገንዘብ መጠን ተደንግጓል፡፡

በዚህም አዋጁ ወደኋላ 10 ዓመታት ተመልሶ የሚሠራ ሲሆን ይህንንም ለመክሰስ የ5 ሚሊዮን የገንዘብ ገደብ ተቀምጧል፡፡

ይህ የገንዘብ ገደብ የተቀመጠበት ዋነኛው ምክንያት በአሁኑ ወቅት ላይ በሀገሪቱ ያለውን የሰው ሃይል ፣ የመክሰስ አቅም እና የፋይናንስ አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት አነስተኛ የሃብት መጠን ያላቸውን ግለሰቦች በመተው ከፍተኛ ንብረት ያላቸውን ተጠያቂ ለማድረግ እንደሆነ ተብራርቷል።

ከዚህ በተጨማሪ ሕጉ ወደኋላ (10 ዓመታት) ተመልሶ እንደመስራቱ በሀገሪቱ #ኢኮኖሚ ፣ #ማሕበራዊ እና #የፋይናንስ_ሥርዓት ላይ ከፍተኛ የሆነ ተጽዕኖ ያደርሳሉ ተብሎ የሚገመቱትን ግለሰቦችና ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶችን ተጠያቂ ማድረግ የተሻለ አማራጭ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ ተብራርቷል።

አዋጁ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ተጠያቂነት ያለምንም የገንዘብ መጠን ተፈጻሚ ይደረጋል።

ስለ ረቂቅ አዋጁ አጭር ማብራሪያ ⬇️
/channel/tikvahethiopia/88313

ረቂቅ አዋጁ⬇️
/channel/tikvahethiopia/88314

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ያንብቡ ⬆️ የንብረት ማስመለስ አዋጅ አጭር ማብራሪያ።

#ኢትዮጵያ
#የሕዝብተወካዮችምክርቤት
#ንብረትማስመለስ
#ረቂቅአዋጅ

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Tigray
 
የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ፤ ከነገ ማክሰኞ ሰኔ 11/2016 ዓ.ም ጀምሮ የ8 ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እንደሚሰጥ ገልጿል።

ከ120 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ አመልክቷል።

እንደ ቢሮው መረጃ ፈተናው ሰኔ 13/2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

የቢሮው ሃላፊ ዶክተር ኪሮስ ጉዕሽ ለሁሉም ተፈታኞች መልካም ምኞታቸው ገልጸው ተረጋግተው ፈተናቸው እንዲሰሩ አደራ ብለዋል።

@tikvahethiopia            

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#AddisAbaba

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

በዚህም በአዲስ አበባ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን መዝግበው የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች 1332 የማስተማር ፈቃድ የተሰጣቸው መሆኑን ገልጿል።

43 ት/ቤቶች በራሳቸው ጊዜ መቀጠል ስላልቻሉ ፈቃዳቸው መሰረዙን አመልክቷል።

150 ት/ቤቶች ጉዳያቸው በሂደት ላይ ያለ በመሆኑ ወደፊት ይገለጻል ተብሏል።

41 ትምህርት ቤቶች ደግሞ የትምህርት ፖሊሲውን ባለመጠበቅና ስታንዳርዱን ባለማሟላታቸው ፍቃዳቸው የተሰረዘ መሆኑ ተመላክቷል።

የትምህርት ቤቶቹ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ExitExam

ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከአርብ ሰኔ 14/2016 ዓ.ም ጀምሮ ይሰጣል።

በኦንላይን ለሦስተኛ ጊዜ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተናው፤ በድጋሜ ፈተናውን ለሚወስዱ ተፈታኞችም ይሰጣል፡፡

Via @tikvahuniversity

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#DStvEthiopia

ክረምቱን ልጆችዎ በዲኤስቲቪ እየተዝናኑ ይማራሉ፣ ዓለምን እየጎበኙ ይመራመራሉ! 👩🏽‍🚀

በየትኛውም ዕድሜ ላሉ ልጆችዎ እንደ ኒክ ጁኒየር፥ ማይንድሴት፥ ኒኮሎዲየን እና ጂምጃም ያሉ ቻናሎችን በወር ከ350 ብር ጀምሮ በዲኤስቲቪ።

ክረምቱን ልጆችዎ በዲኤስቲቪ እየተዝናኑ ይማሩ!

የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ!
👇👇👇
https://bit.ly/3yBcOHc

#DStvEthiopia #ሁሉምያለውእኛጋርነው

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ማህሌት ተኽላይ !

መጋቢት 10 ቀን 2016 ዓ.ም በዓድዋ ከተማ  " ዓዲ ማሕለኻ " ከሚባል ስፍራ ነው ታግታ የተሰወረችው።

የታገተችው ቋንቋ ወደምትማርበት ትምህርት ቤት ስትሄድ ነው።

ባጃጅ ይዘው በመጡ ሰዎች ነበር የታገተችው።

ማህሌት ተኽላይ ታግታ ከተወሰደች በኃላ አጋቾች ለማስለቀቂያ 3 ሚሊዮን ብር እንደጠየቁ ወላጅ አባቷ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረው ነበር።

የዓድዋ ከተማ ፓሊስም ፥ ከሳምንታት በኃላ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች እንዳሉ ገልጾ ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ አድዋ ድረስ ተጉዞ የማህሌት ወላጅ አባት ተኽላይ ግርማይን አነጋግሮ በነበረበት ወቅት ቤተሰቦች ምን ያህል የከፋ ሀዘን እና ጭንቀት ላይ እንደወደቁ መመልከት ችሎ ነበር።

አባት ተኽላይና መላ ቤተሰብ ላለፉት ወራት እንቅልፍ ሚባል አላዩም።

የወለደ ሰው የልጅ ፍቅር በወላጅ የሚያሳደረው ነገር ያውቀዋልና 3 ወር ያህል እንቅልፍ ሳያገኙ ነው የቆዩት።

አቶ ተኽላይ ግርማይ እና መላው ቤተሰቦች ከዛሬ ነገ የልጃቸውን በህይወት ቤት መምጣት ሲጠብቁ ዛሬ ጥዋት ግን ልጃቸው በህይወት እንደሌለች መርዶ ተነግሯቸዋል።

#ዓድዋ

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ከዳሰነች ወረዳ ታማሚ አሳፍሮ ለተሻለ ሕክምና ወደ ጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ሲጓዝ የነበረ አምቡላንስ ተገልብጦ የ3 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ 4 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው፡፡

አደጋው የደረሰው በደቡብ ኦሞ ዞን በና ፀማይ ወረዳ አርጎ ቀበሌ " አርጎ ቁልቁለት " አካባቢ ነው።

ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች በጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታ የሕክምና ዕርዳታ እያገኙ ይገኛሉ።

የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

መረጃው የዳሰነች ወረዳ ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ሴጅ_ማሰልጠኛ

ብቁ የኮምፒውተር ጥገና እና ኔትዎርኪንግ ባለሙያ መሆን ይፈልጋሉ ? Computer Maintenance and Networking ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን።
👉 ንድፈ ሀሳብን ከተግባር ጋር በማዛመድ የሚሰጥ ስልጠና
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

ስልክ ፦ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
Tiktok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
Linkedin: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ኦዲት

ያልተሰራበት በጀት !

ገንዘብ ሚኒስቴር እና ጤና ሚኒስቴር የተመደበላቸውን በቢሊዮን የሚቆጠር በጀት ስራ ላይ ካላዋሉ ተቋማት ዋነኞቹ መሆናቸው ተሰምቷል።

በ2015 በጀት መስሪያ ቤቶች የተፈቀደላቸውን በጀት በአግባቡ ስራ ላይ ማዋላቸውንና መጠቀማቸውን ለማጣራት ኦዲት ሲደረግ በሂሳብ ኮዶች ከተደለደለው በጀት ከ10% በላይ #ያልተጠቀሙበትን ብቻ ተወስዶ 101 መስሪያ ቤቶች ፦
° መደበኛ በጀት 5.3 ቢሊዮን
° ከውስጥ ገቢ 207.6 ሚሊዮን
° ከካፒታል ብር 13.7 ቢሊዮን
በድምሩ 19.2 ቢሊዮን ብር #ያልተሰራበት_በጀት ተገኝቷል።

የተደለደለው በጀት ስራ ላይ እንዲውል #ካላደረጉት መስሪያ ቤቶች መካከል ፦

🔴 የገንዘብ ሚኒስቴር 8 ቢሊዮን ብር

🔴 ጤና ሚኒስቴር 1.9 ቢሊዮን ብር

🔴 የግብርና ሚኒስቴር 1.2 ቢሊዮን ብር

🔴 የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን 818.4 ሚሊዮን

🔴 ወለጋ ዩኒቨርሲቲ 727 ሚሊዮን ብር

🔴 ትምህርት ሚኒስቴር 724.2 ሚሊዮን ብር

🔴 የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር 613.6 ሚሊዮን ብር ... ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

#በጀት_ተፈቅዶ እያለ አለመጠቀም የታሰቡ ስራዎች እንዳይሰሩ ፤ መስሪያ ቤቱ አላማውን እንዳያሳካ ሊያደርግ ስለሚችል በበጀት ዝግጅት እና አጠቃቀም ላይ ጥንቃቄ እንዲደረግ ሲል የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት አሳስቧል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ኢትዮ_ቴሌኮም

ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ኃይል መጠባበቂያ በ 39% ቅናሽ!

እስከ 12 ወራት ድረስ በተራዘመ የክፍያ አማራጭ እጅግ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ኃይል መጠባበቂያ ለማግኘት ወደ ድርጅት አገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን ጎራ ይበሉ!

ለበለጠ መረጃ፡ https://bit.ly/48btdOJ ይጎብኙ!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ኢትዮጵያ #ኦዲት

በ11 መስሪያ ቤቶች 43.5 ሚሊዮን ብር #ምንም ማስረጃ ሳይኖር ወጪ ተደርጓል።

በ2015 የበጀት ዓመት መ/ቤቶች የተፈቀደላቸውን በጀት በአግባቡ ወጪ ማድረጋቸውን / በአግባቡ መጠቀማቸውን ፣ ተገቢ ማስረጃ መቅረቡንና ሂሳቡ በትክክል መመዝገቡን ለማጣራት ኦዲት ተደርጓል።

በዚህም ፥ ምንም አይነት ማስረጃ ሳይቀርብ በወጪ የተመዘገበ ክፍያ / ሂሳብ ተገኝቷል።

በ11 መ/ቤቶች 43.5 ሚሊዮን ማስረጃ ሳይኖረው በወጪ ሂሳብ የተመዘገበ ሲሆን ማስረጃም ባለመቅረቡ ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ አልተቻለም።

➡ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን 17.4 ሚሊዮን
➡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ባለስልጣን 8.7 ሚሊዮን
➡ የመንገድ ደህንነትና መድህን ፈንድ አገልግሎት 8.7 ሚሊዮን
➡ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ 4.4 ሚሊዮን
➡ የኢትዮጵያ አካል ድጋፍ አገልግሎት 3.3 ሚሊዮን ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

ከዚህ ባለፈ ፤ በወጪ ለተመዘገቡ ክፍያዎች የተሟላ ማስረጃ መቅረቡን ለማረጋገጥ በተደረገው ኦዲት በ 48 መ/ቤቶች የተሟላ ማስረጃ ሳይቀርብ 44 ሚሊዮን 440 ሺህ በወጪ ተመዝግቦ ተገኝቷል።

የተሟላ ማስረጃ ሳይዙ ወጪ ከመዘገቡት መካከል ፦
🔴 ማዕድን ሚኒስቴር 5 ሚሊዮን 719 ሺህ
🔴 ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ 5 ሚሊዮን 716 ሺህ
🔴 የጤና ሚኒስቴር 4 ሚሊዮን 677 ሺህ
🔴 ገንዘብ ሚኒስቴር 3 ሚሊዮን 34 ሺህ
🔴 በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ገዋኔ የግብርና የቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ 2 ሚሊዮን 450 ሺህ
🔴 የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት 2 ሚሊዮን 185 ሺህ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

የፌዴራል ኦዲተር መስሪያ ቤት ፤ ማስረጃ ካልቀረበ የሂሳቡን #ትክክለኝነት_ማረጋገጥ_እንደማይቻል ፤ የወጪ ማስረጃ ላልቀረበላቸው ክፍያዎች የወጪ ማስረጃ እንዲቀርብላቸው የማይቀርብላቸው ከሆነ #ገንዘቡ_ተመላሽ እንዲደረግ አሳስቧል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ኦዲት #ኢትዮጵያ

ጤና ሚኒስቴር እና ትምህርት ሚኒስቴር  ከፍተኛ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ ከተገኘባቸው ተቋማት መካከል መሆናቸው ተሰምቷል።

ለውሎ አበል እና ለመጓጓዣ እንዲሁም ለግዥ የተሰጠ ክፍያ ሰራተኛው ስራውን አጠናቆ ከተመልሱ በኃላ በ7 ቀናት መወራረድ እንዳለበት መመሪያ አለ።

ነገር ግን በ124 መስሪያ ቤቶች በጠቅላላው ብር 14.1 ቢሊዮን በወቅቱ ያልተወራረደ ወይም ያልተሰበሰበ ተሰብሳቢ ሂሳብ መኖሩ በኦዲት ታውቋል።

ጊዜው ሲታይም ከ1 ወር በላይ እስከ 1 ዓመት 1 ቢሊዮን 193 ሚሊዮን ብር ፤ ከ1 ዓመት በላይ እስከ 5 ዓመት 10.9 ቢሊዮን ብር ፤ ከ5 ዓመት በላይ እስከ 10 ዓመት 1.7 ቢሊዮን ብር ፤ ከ10 ዓመት በላይ 139 ሚሊዮን ነው።

ቀሪው ሂሳብ በቆይታው ጊዜ ያልተተነተነ ነው።

ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ ከተገኘባቸው ተቋማት #ከፍተኛውን ድርሻ የያዙት እነማን ናቸው ?

➡ #ጤና_ሚኒስቴር 6 ቢሊዮን
➡ የመስኖ ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር 1.1 ቢሊዮን
➡ የትምህርት ሚኒስቴር 1 ቢሊዮን 12 ሚሊዮን
➡ በፌዴራል መንግስት የህንጻዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት 970.9 ሚሊዮን
➡ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚኒሊየም የህክምና ኮሌጅ 756.3 ሚሊዮን
➡ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ 433.5 ሚሊዮን
➡ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት 286.8 ሚሊዮን
➡ የአደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን 272.4 ሚሊዮን
➡ የመንግስት ግዥ አገልግሎት 265.2 ሚሊዮን
➡ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን 250.7 ሚሊዮን
➡ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር 218.3 ሚሊዮን ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

በተጨማሪ የፕሮጀክት ሂሳብ በታየባቸው 4 መስሪያ ቤቶች 514.5 ሚሊዮን በወቅቱ ያልተወራረዳ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ ተገኝቷል።

እንደ የፌዴራል መ/ቤቶች የሂሳብ አያያዝ መመሪያ መሰረት የተሰብሳቢ ሂሳብ በቂ ማስረጃ ሲቀርብበት ብቻ  ነው በተሰብሳቢ ሂሳብነት የሚመዘገበው። የተሰብሳቢ ሂሳብ ክምችት እንዳይኖር ቁጥጥር መደረግ አለበትም ይላል።

ነገር ግን በ15 መስሪያ ቤቶች በጠቅላላው 363.1 ሚሊዮን ማስረጃ ባለመቅረቡ የሂሳቡን ትክክለኝነት ማረጋገጥ አልተቻለም።

የተሰብሰቢ ሂሳቡን ትክክለኝነት ማረጋገጥ ካልተቻለባቸው መስሪያ ቤቶች መካከል ፦

🔴 የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር 253.3 ሚሊዮን
🔴 የመንግስት ግዥ አገልግሎት 39.1 ሚሊዮን
🔴 ጤና ሚኒስቴር 28 ሚሊዮን ከፍተኛውን ድርሻ ይዘዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ኢትዮጵያ #ኦዲት

የፌዴራል ዋና ኦዲተር የ2015 የፌዴራል መንግሥት መ/ቤቶች የፋይናንስና ሕጋዊነት ኦዲት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ለምክር ቤት እያቀረበ ይገኛል።

በዚህም ወቅት ተከታዩን ሰምተናል ፦

በ2014 የበጀት ዓመት እና ከዚያ በፊት በፌዴራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች በተከናወነው የኦዲት ሪፖርት መሰረት እርምጃ የተወሰደ እንደሆነ ማጣራት ተደርጎ ነበር።

በ92 መስሪያ ቤቶች ተመላሽ እንዲደረግ ተብሎ አስተያየት ከተሰጠበት 443 ሚሊዮን ብር እና በዶላር 23,230 ከ43 ውስጥ ተመላሽ የተደረገው 48.2 ሚሊዮን ብቻ እንደሆነ ታውቋል፤ ይህም ተመላሽ ሊደረግ ከሚገባው ጋር ሲነጻጸር 11 በመቶ ብቻ ነው።

ቀሪው 394.8 ሚሊዮን እና 23,230 ከ43 ተገቢው እርምጃ ያልተወሰደበት እና ተመላሽ አልተደረገም።

በተጨማሪ በ2014 #የተሟላ_የማስረጃ_ሰነድ ካልቀረበበት 5 ቢሊዮን 61 ሚሊዮን ማስረጃ የቀረበበት 508. 1 ሚሊዮን ብቻ ሲሆን በመቶኛ 10% ብቻ ማስረጃው ቀርቦ ትክክለኝነቱ ተረጋግጧል።

የተመለሰው ትንሽ ቢሆንም አሰተያየት ተቀብለው ተመላሽ ካደረጉት ተቋማት ውስጥ ፦
➡ የኢንፎርሜሽን ደህንነት መረብ አስተዳደር 5.9 ሚሊዮን ተመላሽ እንዲያደርግ ተብሎ 5.8 መልሷል።
➡ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 4.1 ሚሊዮን ተመላሽ እንዲያደርግ ተብሎ 3.5 ሚሊዮን መልሷል።
➡ የስፔስ እና ጂኦስፔሻል ስልጠና ኢንስቲትዩት ተመላሽ እንዲያደርግ ከተባለው 5.6 ሚሊዮን ውስጥ 4.4 ሚሊዮን መልሷል።

የሰነድ ማስረጃ አቅርቡ ከተባሉት ውስጥ ፦
☑ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 124.25 ሚሊዮን ውስጥ ሁሉንም መልሷል።
☑ የአደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን 150.2 ሚሊዮን ውስጥ ሁሉንም መልሷል።
☑ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ከ3.9 ሚሊዮን 2.2 ሚሊዮን መልሷል።

ሰነዶቹም ትክክለኛ መሆናቸው ተረጋግጧል።

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#አቢሲንያ_ባንክ

በቅርቡ በቴሌግራም ቻናላችን በየሳምንቱ የአንድ አመት የቴሌግራም ፕሪምየም የሚያስገኝ ውድድር የምንጀምር ሲሆን የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል እና የምንጠይቃቸውን ቀላል ጥያቄዎች በመመለስ ይሳተፉ፤ ይሸለሙ፡፡ በየሳምንቱ አስር አሸናፊዎች ይሸለማሉ!
ዛሬውኑ የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ይሸለሙ!

የቴሌግራም ሊንክ፡ /channel/BoAEth

#telegram #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ያንብቡ ⬆️ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ።

#ኢትዮጵያ
#የሕዝብተወካዮችምክርቤት
#ንብረትማስመለስ
#ረቂቅአዋጅ

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Amahra

በአማራ ክልል አዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ጓጉሳ እሽኩዳዶ ወረዳ፣ “ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ንጹሐንን ገድለዋል ” ሲሉ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ፤ በአካባቢው ከ16 በላይ ንጹሐን መገደላቸው እና ከ37 በላይ ወጣቶች ታፍነው መወሰዳቸውን አመልክተው " ይንን ያደረጉት የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ናቸው " ብለዋል።

ግድያው የተፈጸመው አሽፋ ማርያም፣ አሽፋ አዲስ ዓለም እና ወንጀላ በሚባሉት ቦታዎች ከሰኔ 2 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እንደሆነ ጠቁመዋል።

አሽፋ ቀበሌ 8 ሰዎች መገደላቸውን ከ8ቱ 2ቱ ቄሶች እንደሆኑ አንዲት እመጫትም ከእነ ልጇ እንደተገደለች ቀሪዎቹ ደግሞ ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሆኑ አስረድተዋል።

ነዋሪዎቹ ፥ በወረዳው ' ፋኖዎች ' እንደነበሩ ከዛ በፊት መከላከያ እንዳልገባ ፤ ያለፈው እሁድ ግን ሌሊት 9 ሰዓት አካባቢ ከገባ በኋላ እዛ የነበሩ ፋኖዎች ምንም ሳይታኮሱ ነው ቦታውን ለቀው እንደሄዱና ከዛ በኋላ ንጹሐን እንደተገደሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም የነዋሪዎቹን ቃል ይዞ የዞኑን የጸጥታ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቢሻውን አነጋግሯል።

" ነዋሪዎች ከ16 በላይ ንጹሐን ተገድለዋል፣ ከ37 በላይ ወጣቶች ታፍነው ተወስደዋል " ብለዋል ይህ ለምን ተደረገ ? በማለት ጠይቀናቸዋል።

አቶ ጌታቸው ፤ " እኔ የጸጥታ ኃላፊ ሆኘ የምመራው አካባቢ ላይ የደረሰ ማንኛውም አይነት ጥቃት የለም። ኦፕሬሽን የተሰራበት አሽፋ ቀበሌ ነው። በስነ ስርዓት የጽንፈኛ ካምፕ ነው የወደመው " ብለዋል።

" ሐሙስ በነበረው ኦፕሬሽን ላይ በተመሳሳይ ከዛ የተረፈው የታጠቀ ኃይል እንጂ መንግስት የቆመው ለንጹሐን ህዝብ ነው " ሲሉ አክለዋል።

ታዲያ ሳይገደሉባቸው ማልቀስን ከየት አመጡት ? በማለት ለቀረበላቸው ጥያቄ " ንጹሐን ሰዎች አልተጎዱም " ብለው ፤ " የጸጥታ ኃይል ላይ ብረት ያነሳ፣ የተኮሰ ኃይል ሰላማዊ ኃይል ነው ብለን አናምንም " ሲሉ መልሰዋል።

እንደ ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊነትዎ የሞቱ ንጹሐን እንዳሉ ያውቃሉ ? ወጣቶቹስ የት ገቡ ? ለሚለው ጥያቄ ፥ " የሞቱ ሰዎች ፅንፈኞች ናቸው በእኛ እውቅና። ነገም እንዲህ አይነት እርምጃ እንወስዳለን " ብለዋል።

አክለው፣ " ሐሙስ በነበረ ኦፕሬሽን ላይ 3 ሰዎች በውጊያ መካከል ተይዘዋል። ሰላማዊ ሰዎች ናቸው፤ አሉ በሕይወት። ሕጋዊ የማጣራት ሥራ ይሰራባቸዋል። 37 ሰዎች አይደሉም " ነው ያሉት።

" ከዚያ ውጪ አሽፋ ላይ ደግሞ የተያዘ ሰው የለም። በውጊያ መካከል እርምጃ የተወሰደበት ሰው ሊኖር ይችላል " ያሉት ኃላፊው፣ " ውጊያ መካከል ንጹሐን ላይ ጉዳት አይደርስም ማለት አይደለም " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የእቁብ የቁጠባ ሒሳብ
ሕብረት ባንክ የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካት የእቁብ የቁጠባ ሂሳብ አዘጋጅቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ እርስዎ ስለገንዘብ አሰባበሰቡ አይጨነቁ ሰራተኞቻችን ባሉበት ቦታ መጥተው የእቁብ ገንዘቡን ይሰበስባሉ፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡ አዳዲስ መረጃ እንዲርሶ የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጫኑ፡፡
ቴሌግራም- /channel/HibretBanket
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/hibretbank/
ዌብሳይት- https://www.hibretbank.com.et/
#Hibretbank

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ኦሮሚያ #ኖኖ #ስልክአምባ

በኦሮሚያ ክልል ፤ በምዕራብ ሸዋ ዞን ፤ ኖኖ ወረዳ ሰርገኞችን ዒላማ ባደረገ ጥቃት ከ20 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ኮማንድ ፖስት እና ነዋሪዎች ገለጹ።

የኖኖ ወረዳ ኮማንድ ፖስት ኃላፊ አቶ ተሾመ ሰቦቃ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ በሰጡት ቃል ፥ ጥቃቱ ቅዳሜ ሰኔ 8 ንጋት ላይ ነው የተፈጸመው።

ጥቃት አድራሾቹ " ጽንፈኛ የአማራ ታጣቂዎች  ናቸው " ብለዋል።

ኃላፊው " ሰርገኞቹ ቤት ውስጥ እያሉ በር ዘግተውባቸው ቦምብ ወረወሩባቸው። ቤት ውስጥ ከነበሩት አንድም በሕይወት የወጣ የለም። እዚያው ተቃጥለው አልቀዋል "  ሲሉ ሁኔታውን አስረድተዋል።

አንድ የአካባቢው ነዋሪ ታጣቂዎቹ ሰርግ ቤቱ ላይ ከአንድ በላይ ቦምብ ወርውረው ሙሽሮቹን እና አብረዋቸው የነበሩ ሰዎችን መግደላቸውን ተናግረዋል።

የኮማንድ ፖስት ኃላፊን ጨምሮ የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት ቃል ፥ በሰርግ ቤት ላይ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት የመጡ የአካባቢው ነዋሪዎች በታጣቂዎቹ የተኩስ እሩምታ ተከፍቶባቸው በርካታ ሰዎች ተገድለዋል።

የአካባቢው ነዋሪ የሟቾች ቁጥር ከ30 እስከ 50 ሊደርስ እንደሚችል ተናግረዋል።

በጥቃቱ ሙሽሪት እና ሙሽራውን ጨምሮ የሰርጉ ታዳሚዎች የሆኑ ሰዎች በሙሉ ሕይወታቸው ማለፉን ነዋሪው ተናግረዋል።

የወረዳው የኮማንድ ፖስት ኃላፊ አቶ ተሾመ ሰቦቃ ፥ " በእሳት ተቃጥለው የሞቱ ሰዎችን ቁጥር መለየት አስቸጋሪ በመሆኑ ትክክለኛውን የሟቾች ቁጥር መለየት አልተቻለም " ሲሉ ለቢቢሲ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ባለፈው ሚያዚያ ወር ላይ በዚህ ወረዳ በ5 ቀበሌዎች በተፈጸመ ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸውን ፤ ቤቶች መቃጠላቸውን ፣ ከብቶችም እየተነዱ መወሰዳቸውን ነዋሪዎች መግለጻቸው ይታወሳል።

ኢሰመኮም መረጃውን የማጣራት ስራ እየሰራ እንደነበር መግለጹ አይዘነጋም።

ከሟቾች አብዛኛዎቹ የአማራ ብሔር ተወላጆች እንደነበሩ ፤ ጥቃት ፈጻሚዎችም የ " ሸኔ (የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት) ታጣቂዎች " እንደሆኑ ነዋሪዎች መናገራቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…
Subscribe to a channel