tikvahethiopia | Unsorted

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1519094

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Subscribe to a channel

TIKVAH-ETHIOPIA

#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ ፤ ' መስቀል አደባባይ ' ከሚደረግ የመንግስት የድጋፍ ሰልፍ ጋር በተያያዘ ተዘግተው የነበሩ መገዶች ተከፍተዋል።

ሰልፉ #መጠናቀቁን ተከትሎ ተዘግተው የነበሩት መንገዶች ለተሽከርካሪ ክፍት ሆነዋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ፊቼጨምባላላ

የፊቼ ጨምበላላ በዓል እየተከበረ ይገኛል።

የበዓሉ ዋነኛ መለያው ሰላም ፤ አንድነትና ፍቅር ሲሆን በዚህ በዓል ተጣሉ ሰዎች ይታረቃሉ ፤ ሃዘን ላይ የነበሩ ሰዎችም የሃዘን ልብሳቸውን ይቀይራሉ።

ከቀዬው ርቆ የነበረ ሰው ለፊቼ ጨምበላላ ወደቀዬው ይመለሳል። ለዚህ በዓል ተብሎ እርድ አይፈጸምም ፤ ስጋም አይበላም። ክብቶችን መምታትም ክልክል ነው። ላሞች ሳር የበዛበት መስክ ላይም እንዲሰማሩ ይደረጋል።

በሲዳማ ሕዝብ ዘንድ በፊቼ ጨምበላላ በዓል ወቅት ማረስ ነውር ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ የፊቼ ጨምበላላ በዓል የሲዳማ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮም ነው ተብሎ ስለሚታመን ነው።

በዓሉ የሲዳማ ሕዝብ ማንነቱን ከተረዳበት ጊዜ አንስቶ ሲከበር ቆይቷል። እንደ ሲዳማ የአገር ሽማግሌዎች " ፊቼ ጫምባላላ " መከበር ከጀመረ ከ1800 ዓመታት በላይ አስቆጥሯል።

መልካም በዓል !

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ከተጠቀሱት የባንክ አማራጮች ወደ M-PESA ገንዘብ በመላክ እስከ 50 ብር ስጦታ እናግኝ!

M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ!

🔗የM-PESAን ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉/channel/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom  #FurtherAheadTogether

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#መቐለ

ዛሬ በመቐለ #ሰላማዊ_ሰልፍ የወጡ የመቐለ ዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች በፖሊስ ድብደባና እስራት እንደተፈፀመባቸው ዶቼ ቨለ ሬድዮ ተማሪዎቹን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

ተማሪዎቹ ተራዝሟል ያሉትን የመመረቂያ ግዜን በመቃወም ሰልፍ የወጡ ሲሆን የትግራይ ክልል የፀጥታ ኃይሎች ከፍተኛ ድብደባ እና እንግልት እንደፈፀሙባቸው ተናግረዋል።

10 ተማሪዎች መታሰራቸውም ተገልጿል።

ተማሪዎቹ ዛሬ ረፋድ 4 ሰዓት ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ አሪድ ግቢ ተነስተው ያሏቸውን ቅሬታዎች ለማሰማት ወደ መቐለ ከተማ ጎዳናዎች ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉበት ወቅት ነው ድብደባና እስቱ የገጠማቸው።

ተማሪዎቹ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ለምን #ተገደዱ ?

በተለያዩ ችግሮች #ለዓመታት ትምህርታቸው ሲስተጓገል ቆይቶ ዘንድሮ 2016 ለመመረቅ እየተጠባበቁ የነበረ ቢሆንም ፤ ዩኒቨርሲቲው ሌላ ተጨማሪ ዓመት መማር እንደሚጠበቅባቸው ከገለፀላቸው በኃላ ነው ሰልፍ የወጡት።

ከሰላማዊ ሰልፉ በፊት ግን ለዩኒቨርሲቲው በተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ማቅረባቸውን እና ከዩኒቨርሲቲው ምላሽ አለማግኘታቸውን ለሬድዮ ጣቢያው ገልጸዋል።

@tikvahethiopua

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#እንድታውቁት

ነገ በአዲስ አበባ መንገዶች ይዘጋሉ።

በአዲስ አበባ ' መስቀል አደባባይ ' ነገ #ቅዳሜ ከሚደረግ የድጋፍ ሰልፍ ጋር በተያያዘ መንገዶች እንደሚዘጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ከንጋቱ 11፡00 ሰአት ጀምሮ ሰልፉ እስኪጠናቀቅ ድረስ ፦

- ከቴዎድሮስ አደባባይ በብሄራዊ ቴአትር ወደ ወደ መስቀል አደባባይ ሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ

- ከኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ ላይ

- ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ እና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ

- ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ

- ከጎተራ ማሳለጫ ወደ መስቀል አደባባይ አጎና ሲኒማ

- ከቅ/ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን በአዲሱ መንገድ  ወደ መስቀል አደባባይ ለሚሄዱ ለገሀር መብራት

- ከሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ቴሌ   ለሚጓዙ ለገሀር መብራት

- ከጌጃ ሰፈር አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ሰንጋተራ ትራፊክ መብራት ላይ

- ከሃራምቤ መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ  መብራት ላይ

- ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ

- ከካዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሼል አጠገብ

- ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA ሚወሰደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ ለተሽከርካሪ #ዝግ ይሆናሉ ተብሏል።

አሽከርካሪዎች መንገዶቹ እንደሚዘጉ አውቀው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

ከዚህ ባለፈ በተጠቀሱት መንገዶች ከዋዜማው ምሽት 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሰልፉ ፍፃሜ ድረስ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ወይም ማሳደር ተከልክሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የነገው የመስቀል አደባባይ ሰልፍ #መንግሥትን የሚደግፍ ሰልፍ መሆኑን ለማወቅ ችሏል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የጥሪ ማሳመሪያ አገልግሎት በተጨማሪ የምዝገባ አማራጮች (Micro Packages) ቀረቡ!

ከ2ብር ጀምሮ የሳምታዊ ፣ የአስራ አምስት ቀናት እና ወርሃዊ የጥሪ ማሳመሪያ ጥቅል ለመመዝገብ ወደ 822 ወይም *822# በመደወል አልያም በ www.crbt.et ለአገልግሎቱ ተመዝግበው ሙዚቃዎችን ወይም መንፈሳዊ ዜማዎች ይግዙ!

#CRBT #Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#AddisAbaba

“ በለበሰው ሹራብ የኮፍያ ገመድ አንቀው ነው የገደሉት። ተሽከርካሪውን ይዘው ተሰውረዋል ” - የሟች ቤተሰብ

“ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ ነው ” - የአዲስ አበባ ፓሊስ

ወጣት ሶፎኒያስ አስራት የሚባል ሹሬር ማክሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ/ም ከሌሊቱ 8 ሰዓት ገደማ ሰዎችን አሳፍሮ እንደወጣ አለሙለሱን፣ በመጨረሻም ሹፌሩን ገድለው ፣ ተሽከርካሪውን ይዘው እንደተሰወሩ፣ ገዳዮቹ አስካሁን #እንዳልተያዙ፣ በዚህም መሉ ቤተሰቡ መራራ ሀዘን ውስጥ መሆናቸውን የሟች ቤተሰብ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የሟች ቤተሰብ በሰጡት ቃል፣ “ ከላፍቶ ነበር መነሻውን ያደረገው (ልዩ ስሙ መስቀልኛ የሚባለው አካባቢ ናሆም ሆቴል የሚባል አለ)። ከዚያ ነበር ሦስቱንም ተሳፋሪዎች ማክሰኞ ከሌሊቱ 8 ሰዓት አካባቢ ያሳፈራቸው። መዳረሻቸውን ‘ቦሌ ሚካኤል’ ብለው ነበር መሳፈር የፈለጉት ” ብለዋል።

“ ትንሽ ወረድ እንዳለ/እንደተጓዘ ከእኔ ጋር ተገናኝተናል። አብረን የምንሰራበት ቦታ ነው። ሦስት ሰዎች እንዳሳፈረ አይቻለሁ” ያሉት የሟች ቤተሰብና የዓይን እማኝ፣ “ሶፊ ወዴት ነህ ስለው ‘መጣሁ። ቦሌ ሚካኤል አድሻቸው ልምጣ’ አለኝ። በቃ ደርሰህ ና ስራ የለም እንገናኛለን ተባባልን። በዛው እንደወጣ አልተመለሰም ” ሲሉ ሁነቱን አስረድተዋል።

አክለውም፣ ጠዋት ላይ ላፍቶ ፓሊስ ጣቢያ ሲያመለክቱ የቃሊቲ ፓሊስ ጣቢያ እንዲጠይቁ እንደነገሯቸው፣ ቃሊቲ ፓሊስ ጣቢያ ሲጠይቁ ፓሊስ ስለተፈላጊው ሰው ሙሉ መለያ መረጃ ከጠየቃቸው በኋላ “ እንግዲህ ጠንከር በሉ። ኤቲኤሙን አግኝተናል። አሁን ያለው ጳውሎስ ሆስፒታል ነው። አዲስ አበባ ፓሊስ ሂዳችሁ ቃል ሰጥታችሁ ትወስዳላችሁ ” ብለው #መገደሉን እንዳረዷቸውም ተናግረዋል።

“ ማሰልጠኛ ተሻግሮ ወደ አቦ ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ዳር ላይ ነው ሞቶ የተገኘው። ፓሊሶች አስከሬኑን ያነሱት ጠዋት 12 ሰዓት ላይ ነው። ከጥበቃ ሥራ የሚመለሱ አንድ አባት ናቸው በወደቀበት አግኝተውት ጥቆማ አድርገው ፓሊስ የሄደው ” ነው ያሉት።

“ በለበሰው ሹራብ የኮፍያ ገመድ አንቀው ነው የገደሉት። ተሽከርካሪውን ይዘው ተሰውረዋል ” ያሉት የሟች ቤተሰብ፣ ማንም ጋ ፀብ እንዳልነበር ገልጸው፣ ሙሉ ቤተሰቡ ሀዘን ላይ እንደሆነ፣ ቢያንስ ገዳዮቹ እንዲያዙ ፓሊስ ርብርብ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

ስለጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ፣ ስለሟች ሁኔታ ጠይቀው ጉዳዩን እንዲያጣሩ ፋታ እንዲሰጣቸው ከጠየቁ በኋላ በሰጡት ቃል ፣ “ አረጋግጫለሁ። ፓሊስ ሥራ ላይ ነው ያለው። የተለያዩ ዝርዝር መረጃዎችን ለመግለጽ የሚያስፈልግ የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ ነው ተጠርጣሪዎቹን ለመያዝ ” ብለዋል።

“ መረጃ እየተሰበሰበ ነው ያለው ” ያሉት ኮማንደር ማርቆስ፣ “ አንተ ማክሰኞ ሌሊት 8 ሰዓት አልከኝ እንጂ፣ ስጠይቅ ረቡዕ ለሐሙስ አጥቢያ 8 ሰዓት ላይ ነው ወንጀሉ የተፈጸመው የሚል መረጃ ነው ያለው። ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ ነው ያሉት ” የሚል ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ ወንጀሉ የተፈጸመው ማክሰኞ ሌሊት 8 ነው ያሉት የሟች ቤተሰብ በስህተት እንዳይሆን በሚል በድጋሚ የጠየቀ ሲሆን፣ ማክሰኞ ለረቡዕ ሌሊት 8 ሰዓት እንደሆነ፣ ረቡዕ ማታ ጣቢያ አስክሬን እንዳገኙ አስረድተዋል።

መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ትኩዬ የተዘጋጀ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#forfreemarket

እነዚህን👆የቤት ዕቃዎች በሱቃችን በቅናሽ ዋጋ እየተሸጡ ነው። የነዚህንና ሌሎች በርካታ ዕቃዎቻችንን ዋጋ ይሄንን ተጭነው ማየት ይችላሉ። 👉  /channel/forfreemarket
       
አድራሻ፦ ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ጊቢ ውስጥ ቢሮ ቁ04 ፣ መገናኛ መተባበር ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ316 ፣ ሳር ቤት ካናዳ ኤምባሲ ፊትለፊት ሸዋ ሱፐርማርኬት ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ11

ለማዘዝ እነዚን ቁጥሮች ይጠቀሙ ፦ 0911100302 / 0911887579
በቴሌግራም ለማዘዝ ➡️ @Akdat

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

" የቀን ህልም ነው ... ምንም የማይረባ ፤ እኛን አያሳስበንም " - ሶማሌላንድ

" የሶማሊያ መንግሥት አንዳች ስልጣን የለውም " - ፑንትላንድ

#ፑንትላንድ እና #ሶማሌላንድ የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥትን ማስጠንቀቂያ ውድቅ አደረጉ።

የሶማሊያ መንግሥት ፤ #ኢትዮጵያ ከሶማሌላድ ጋር ያደረገችውን የመግባቢያ ስምምነት ምክንያት በማድረግ ሞቃዲሹ ያሉት የኢትዮጵያ አምባሳደር በ72 ሰዓት ከሀገሪቱ ለቀው እንዲወጡ አዟል።

ከዚህ ባለፈ ግን በሶማሌላድ ፣ #ሀርጌሳ እና በፑንትላንድ፣ #ጋሮዌ የሚገኙት የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤቶች በ7 ቀን እንዲዘጉ አስጠንቅቋል። ካልሆነ ወደሌላ እርምጃ ገባለሁ ብሏል።

ለዚህ ማስጠንቀቂያ ፑንትላንድ እና ሶማሌላንድ ምላሽ ሰጥተዋል። የሶማሊያ ፌዴራል መንግስትን ማስጠንቀቂያም ውድቅ አድርገዋል።

ዛሬ ምሽት ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ሶማሊኛ ክፍል አጭር ቃላቸውን የሰጡት የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚንስትር አምባሳደር ሮዳ ኤሊ ፥ " የቀን ህልም ነው፤ ...ምንም የማይረባ ፤ እኛን አያሳስበንም " ሲሉ ማስጠንቀቂያውን አጣጥለዋል።

የሶማሊያ መንግሥት ስልጣኑ በቪላ ሱማሊያ እና በሙቃዲሾ ዘሌን ቤዝ የተወሰነ መሆኑን በመግለጽ " በውስጥ ጉዳዩ ላይ ቢያተኩር ነው የሚሻለው ... ከአቅሙ በላይ በሆነ ጉዳይ ጊዜ ማባከኑን ማቆም አለበት " ብለዋል።

የፑንትላንድ የማስታወቂያ ሚኒስትር ማህሙድ አይዲድ ድሪር  በበኩላቸው " የሶማሊያ ፌደራል መንግስት በጋሮዌ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት የመዝጋት አንዳችም ስልጣን የለውም " ብለዋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በቦምብ ጥቃቱ 31 ተማሪዎች ተጎድተዋል " - ፖሊስ

ዛሬ በፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ዳሞት  መሰናዶ ቁጥር 1 ት/ቤት ላይ በተፈፀመ የቦምብ ጥቃት በ31 ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የፍኖተ ሰላም ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ገለጸ።

በት/ቤቱ በተፈፀመው የቦምብ ጥቃት 6 ተማሪዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል ብሏል።

የቦምብ ጥቃቱ (ቦምቡ የተጣለው) ጥዋት 2፡30 ሰዓት ተማሪዎች በፈተና ላይ እንዳሉ መፈፀሙን የገለጸው ፖሊስ ፤ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው 6ቱ ተማሪዎች ለከፍተኛ ህክምና ሪፈር ተፅፎላቸዋል ህክምና ላይ ናቸው ብሏል።

15 ተማሪዎች ደግሞ በፍኖተ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል ህክምና እያገኙ ሲሆን 10 ተማሪዎች ላይ ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው አመልክቷል።

አደጋውን ተከትሎ አንድ ተጠርጣሪ #ተማሪ መያዙን ፤ እጁና እግሩ ላይም መቁሰሉን ያሳወቀው ፖሊስ ሌሎች በድርጊቱ የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሰራ እንደሆነ ገልጿል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ኢትዮጵያ

መንግስት ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች/startups እንዲያብቡ በርካታ የፖሊሲ ለውጦችን ለማድረግ መወሰኑ ተሰማ።

ከነዚህም መካከል ፦
- ከስራ ፈቃድ፣
- ከግብር፣
- ከቢሮ ኪራይ፣
- ከፋይናንስ አቅርቦት፣
- ከጉምሩክ አሰራር ጋር በተያያዘ ወሳኝ ለውጥ የሚደረግባቸው ይሆናሉ ተብሏል።

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በተገኙበት ዛሬ ይፋ የተደረጉ ለውጦች በተለይ ስራ ፈጣሪዎች ከውጭ ለሚኖራቸው ግዥ የቀጥታ ክፍያ መፈፀም እንዲችሉ እንዲሁም ያገኙትን የውጭ ምንዛሪ ሙሉ ለሙሉ መጠቀም እንዲችሉ የሚፈቅድ መሆኑን " ካፒታል ጋዜጣ " አስነብቧል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

MAMA'S kids ማማስ ኪድስ

▶️ ኦርጅናል እና ጥራታቸውን የጠበቁ የልጆች እቃዎች ለማግኘት ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👉/channel/mamaskids
አድራሻችን ፦ መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 2 ተኛ ፎቅ የሱቅ ቁጥር 225
👉 ውድ ደምበኞቻችን ሱቃችን  225 ቁጥር  መሆኑን እና የራሳችን ሎጎ መኖሩን ያረጋግጡ እናመሰግናለን።
ለበለጠ መረጃ ፦ በ0965809005 / በ0938309171 ይደውሉልን።

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Somalia

° " ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል " - የሶማሊያ ባለልስጣናት

° " ስለዚህ ጉዳይ መረጃው የለኝም " - አቶ ነብዩ ተድላ

ሶማሊያ ፥ በሶማሊያ #የኢትዮጵያን_አምባሳደር የሆኑትን ሙክታር ሞሃመድ ዋሬን ወደ ሀገራቸው #እንዲመለሱ ማድረጓን ሁለት ከፍተኛ የሶማሊያ ባለስልጣናትን ዋቢ በማድረግ ሮይተርስ ዘግቧል።

ሶማሊያ የኢትዮጵያን አምባሳደር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ያደረገችበት ምክንያት ከሶማሊላንድ ጋር የገባቸው የወደብ መግባቢያ ስምምነት እንደሆነ ተነግሯል።

ከዚህ ባለፈ ሶማሊያ በፑንትላንድ እና ሶማሊላንድ ያሉ የኢትዮጵያን ቆንስላ ጽህፈት ቤቶችን ዘግቻለሁ ብላለች።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ በጉዳዩ ዙሪያ ምንም አይነት መረጃ እንደሌላቸው እንደነገሩት ሮይተርስ አስነብቧል።

የፑንትላንድ እና ሶማሊላንድ ነገር ?

ፑንትላንድ ከሕገ-መንግስት ማሻሻያ ጋር በተያያዘ ለሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ዕውቅና መስጠት ማቆሟን ከቀናት በፊት ይፋ ማድረጓ ይታወሳል።

ከአሁን በኃላም ማንኛውም ፍላጎቷን ለማስጠበቅ ከማዕከላዊ የሶማሊያ መንግሥት እውቅና ውጪ በራሷ የውጭ ግንኙነትም እንደምታደርግ ገልጻለች።

ሶማሌላንድም ምንም እንኳን እስካሁን ሶማሊያ ' የራሴ ግዛት ነሽ ' ብትላትም ራሷን እንደ ነጻ ሀገር መቁጠር ከጀመረች አመታት አልፈዋል። የውጭ ግኝኑነቶችንም ታደርጋለች።

የሰሞኑን የፑንትላንድ ነገር ለሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት " በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ " ሆኖበታል።

ከፊል ራስ ገዟ ፑንትላንድ ሰሞኑን ፥ " ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጋር ተቆራጠናል ፤ እውቅናም አልሰጥም " ካለች በኃላ ከፍተኛ ባለስልጣናቷ ኢትዮጵያ / አዲስ አበባ ለውይይት መግባታቸው መነጋገሪያ ሆኗል።

እዚህ አዲስ አበባ የመጣው በገንዘብ ሚኒስትሯ ሞሃመድ ፋራህ ሞሀመድ የተመራ ልዑክ ነው።

ልዑኩ ከኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ጋር መክሯል።

በዚህም ኢትዮጵያ ከፑንትላንድ ጋር ያላትን ዘርፍ ብዙ ትብብሮች ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗ ተገልጿል።

የፑንትላንድ ልዑክም ፥ ኢትዮጵያ በፑንትላንድ በጸጥታና በትምህርት ዘርፍ ድጋፍ እያደረገች መሆኑን ገልጾ የፑንትላንድ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት የማሳደግ ፍላጎት እንዳለው አረጋግጧል።

በዚህ ወቅት የፑንትላንድ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ መምጣታቸው ግጥምጥሞች ወይስ ከወቅታዊ ሁኔታው ጋር የተያያዘ ነው ?

" ጉብኝቱ የቆየ ቀጠሮ ነው " - አቶ ነብዩ ተድላ

ዛሬ በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብዩ ተድላ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ወቅት ፑንትላንድ በገንዘብ ሚንስትሯ መሀመድ ፋራህ የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ አ/አ ጉብኝት ማድረጉን ገልጸዋል።

ይህ ጉብኝት ከሰሞነኛው የፑንትላንድ ወቅታዊ ጉዳይ ጋር #የማይገናኝ እንደሆነ እና የጉብኝት ፕሮግራሙም የቆየ ቀጠሮ መሆኑን አስረድተዋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ኢንተርን

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኢንተር ሀኪሞች ከስራ ሰዓትና ክፍያ ጋር በተያያዘ ቅሬታ እንዳላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ኢንተርን ሀኪሞቹ ምን አሉ ?

“ ከጥቂት ዓመታት በፊት የሆስፒታሉ የኢንተርን ሀኪሞች የሥራ ሰዓት ወደ 24 ሰዓታት ዝቅ እንዲል ተደርጎ ነበር።

ነገር ግን የኮሌጁ ግለሰብ / #ዳይሬክተር ሲቀየር በራሱ ውሳኔ የራሱን መላምት በመፍጠር መልሶ ወደ 36 ሰዓታት ከፍ አድርጎታል።

ይህን ውሳኔ ተከትሎ የሥራ ሰዓት ከዚህ በፊት ሴኔቱ በወሰነው መሠረት ይሁንልን ብለን ጠየቅን። ይህንንም በመጠየቃችን የተበሳጨው የዲፓርትመንት አስተባባሪ ፦
• ከቀዶ ጥገና፣
• ከህፃናት፣
• ከማህፀንና የፅንስ ዲፓርትመንት ጋር መከረ። እነዚህ ዲፓርትመንቶች አስገድደውን ሥራ ጀመርን።

የሥራ ሰዓታችን እንዲስተካከል በተደጋጋሚ ጠየቅን።

በዲፓርትመንት ደረጃ እየተሰበሰቡ ' ከዚህ በኋላ ይህን ጥያቄ የሚያየሳ ሀኪም እስከ ዲሲሚሳል ድረስ እንቀጣቸዋለን ' አሉ። ከዚህ በተጨማሪ የቀን ሥራ ሰዓታትን በአንድ ሰዓት ከፍ እንዲል ከነበረው ሕግ ውጪ ሆነብን።

ያንን ሁሉ ችለን ደመወዝ ይከፈለናል ብለን ብንጠብቅም ሳይከፈለን መጋቢት 14/2016 ዓ/ም 10ኛ ሳምንታት ጨርሰናል። ” የሚል ቅሬታ አቅርበዋል።

ለተነሳው ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጡን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህክምና ሳይንስ ኮሌጅና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቺፍ ኤክሴኩይቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር አይንሸት አዳነን ጠይቀናል።

ምን አሉ ?

ዶ/ር አይንሸት ፥ “ የሰዓት ጭማሪ ለሚለው እኔ ባለኝ መረጃ መሠረት የተጨመረ ነገር የለም። ከድሮው የተቀየረ አሰራር የለም። እኔ ባለኝ መረጃ መሠረት እነርሱን #ያስፈራራቸው_ሰው_የለም ” ብለዋል።

Q. ቲክቫህ ኢትዮጵያ የኢንተርን ሀኪሞች የሥራ ሰዓት ስንት ተብሎ ነው የተወሰነው ? ሲል ጥያቄ አቅርቧል።

ዶ/ር አይንሸት አዳነ ፦

“ በክሬዲት ደረጃ ይህን ያህል የትርፍ  ፤ ይህን ያህል የመደበኛ ተብሎ የተቀመጠ ነገር የለም።

ለበርካታ አመታት ሲሰራበት ከነበረው መንገድ የተለየ እነርሱ ጋ የተጨመረ ነገር የለም። ”

Q. ዩኒቨርሲቲው 36 ሰዓታት የነበረውን የሥራ ሰዓት ወደ 24 ሰዓታት ዝቅ እንዳደረገ መረጃዎች ያሳያሉ ፣ ሀኪሞቹም ወደ 24 ሰዓት ዝቅ ተደርጎ የነበረ ወደ 36 ሰዓት ከፍ እንዳለባቸው ገልጸዋል ፣ እርስዎ ደግሞ የተወሰነ ሰዓት እንደሌለ እየገለጹ ነው ለዚህስ ያለዎት ማብራሪያ ምንድን ነው ? ስንል ጠይቀናል።

ዶ/ር አይንሸት አዳነ ፦

“ የሆነ ጊዜ ጫናው ስለበዛ በኢንተርን ሀኪሞች ጥያቄ ተነሳና ዲፓርትመንቶች ራሳቸው ከኢንተርን ሀኪሞች ጋር ውይይት አድርገው (የተወሰኑ ዲፓርትመንቶች እንዲያውም ሙሉ አይደለም) አምነውበት ወደ ተግባር ተገባ። አሳማኝ ስለሆነ የሥራ ጫናው።

ይሁን እንጂ ለተወሰነ ወራት ተግባራዊ ከተደረገ በኋላ አድረው በሚወጡትና ተተኪ ሆነው በሚገቡት ኢንተርን ሀኪሞች መካከል የርክክብ ክፍተት መፈጠሩ የጤና አገልግሎት ላይ ተፅዕኖ ስላመጣ፣ የኢንተርን ሀኪሞች ተመርቀው ሲወጡ የተሟላ እውቀት እንዳይቀስሙ ያደርጋል በሚል ወደ ነበረበት ይመለስ ተብሎ ተመልሷል። ”

Q. ‘ደመወዝ አልተከፈለንም’ ሚለው የሀኪሞቹን ቅሬታስ?

ዶ/ር አይንሸት አዳነ ፦

“ ሀኪሞቹ አጠያየቃቸው ልክ አልነበረም።

ኦረንቴሽን እንዲሰጣቸው በደብዳቤ ጭምር ቢጠሩም መገኘት አልቻሉ።

‘ይህ ካልተደረገልን (ቅሬታው ምላሽ ካላገኘ) ሥራ አንገባም’ በማለታቸውና ሳምንቱን ሙሉ ከሥራና ት/ት ገበታ ባለመገኘታቸው የሕክምና ትምህርት ቤቱ ባሳለፈው ውሳኔ፣ የ3 ወራት ደመወዝ ነው የተቀጡት። ያለ ደመወዝ እንዲሰሩ ነው የህክምና ት/ቤቱ የወሰነው። ”

#ቲክቫህኢትዮጵያ
@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#forfreemarket

እነዚህን👆የቤት ዕቃዎች በሱቃችን በቅናሽ ዋጋ እየተሸጡ ነው። የነዚህንና ሌሎች በርካታ ዕቃዎቻችንን ዋጋ ይሄንን ተጭነው ማየት ይችላሉ። 👉  /channel/forfreemarket
       
አድራሻ፦ ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ጊቢ ውስጥ ቢሮ ቁ04 ፣ መገናኛ መተባበር ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ316 ፣ ሳር ቤት ካናዳ ኤምባሲ ፊትለፊት ሸዋ ሱፐርማርኬት ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ11

ለማዘዝ እነዚን ቁጥሮች ይጠቀሙ ፦ 0911100302 / 0911887579
በቴሌግራም ለማዘዝ ➡️ @Akdat

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#እንድታውቁት

የደብር ብርሃን - ደሴ ዋና የፌዴራል መንገድ ከዛሬ መጋቢት 28/2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለመንገደኞች ክፍት እንደሚሆን የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ገልጿል።

ከፀጥታ ጋር በተያያዘ ከየካቲት 16 /2016 ዓ.ም አንስቶ ተቋርጦ የቆየው ይኸው መንገድ ከዛሬ አንስቶ ለህዝብ ትራንስፖርት ክፍት ይደረጋል ተብሏል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#BK_COMPUTERS

ማንኛውንም አይነት አዳዲስ ላፕቶፖች ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች ዴስክ ቶፖችን ጨምሮ ከብዛት እና ከታላቅ ቅናሽ ጋር ያዘንላቹ መተናል። ቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለግሪፊክስ ዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች እንዲሁም ለጨረታ የሚሆኑ በጥራት እና በ ብዛት ከ1 አመት ዋስትና ጋር እኛ ያገኛሉ

ለተጨማሪ መረጃ እና የላፕቶፕ አማራጮችን ለማየት የቴሌግራም ፔጃችንን Join ያድርጉ።
👉 /channel/BKComputers
Inbox @bkcomputer27

አድራሻ ፦ አዲስ አበባ መገናኛ ሲቲ ሞል ከመሰረት ደፋር ህንፃ አጠገብ 1 ፎቅ ላይ እንገኛለን። 0911448148/ 0955413433 we make IT easy!

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#መቐለ

" ዲግሪ ለመያዝ 8 ዓመታትን መማር #ፍትሃዊ አይደለም " - ተማሪዎች

ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አደባባይ የወጡ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በፖሊስ በኃይል እንዲበተኑ ተደርገዋል።

ተማሪዎቹ ምንድነው ጥያቄያቸው ?

" አንድ ዲግሪ ለመያዝ 8 (#ስምንት) ዓመታትን መማር  #ፍትሃዊ አይደለም " ያሉት ተማሪዎቹ " ከሌሎች ዩኒቨርስቲዎች የምንለይበት ምክንያት የለም ፤ የመውጫ ፈተና መፈተን አለብን " ብለዋል።

" ተመርቀን ወጥተን ስራ መስራት ፤ ህይወትን ማሸነፍ ባለብን በዚህ እድሜያችን የመጀመሪያ ዲግሪ ለማግኘት 8 ዓመታት መጠበቅ የለብንም ፣ የወጣትነት እድሜያችን ያሳስበናል ፤ ብንጮህ ብንጮህ ሰሚ አላገኘንም " ሲሉ ገልጸዋል።

" በዚህ ዓመት መመረቅ ሲገባን ሌላ ተጨማሪ ጊዜ ትማራላችሁ እያሉን ነው ይሄ በፍፁም የማንቀበለው ነው " ብለዋል።

ዛሬ ተማሪዎቹ ከመቐለ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ በመነሳት የተለያዩ መፈክሮች በመያዝ ወደ ከተማ ለማምራት ሲሞክሩ በፓሊስ እንግልትና ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል።

የትራፊክ ፖሊስ አባላት ሰልፉን ለማደናቀፍ መንገድ ሲዘጉ ፤ ታጣቂዎች ሰልፈኛ ተማሪዎች ሲደበድቡ ታይተዋል።

ጥያቄ  ካነሱ ሰላማዊ ሰልፈኞች መካከል ሶስት ሴት ተማሪዎች በፓሊስ #ሲደበደቡ መመልከቱን ህሉፍ በርሀ የተባለ የአይን እማኝ ገልጿል።

ከዛሬው ሰልፍ ጋር በተያያዘም አንድ የፖሊስ አባል አንዲት #ሴትን እያንገላታ #ገፍትሮ መሬት ላይ ሲጥላት የሚያሳይ ቪድዮ ብዙዎችን አስቆጥቷል።

የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሰላማዊ ስልፍ በማስመልከት የዩቨርስቲው አስተዳደር እና የትምህርት ሚንስቴር እንዲሁም የከተማው ፖሊስ እስከ አሁን ያሉት ነገር የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተቋማቱ የሚሉት ካለ ተከታትሎ ያቀርባል።

መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

" የወሰዱትን ገንዘብ እስካሁን ድረስ አልመለሱም " ልያላቸው ግለሰቦችን #ፎቶግራፍ በተለያዩ ሚዲያዎች ማውጣት የቀጠለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ደግሞ  ከ64 ሺህ እስከ 71 ሺህ ብር " ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ አልመለሱም " ያላቸውን ገለሰቦች ፎቶግራፍ አሰራጭቷል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#እንድታውቁት

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል።

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ መጋቢት ወር ሲሸጥ በነበረበት ዋጋ የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ስንት ነው ?

- ቤንዚን በሊትር 77 ብር ከ65 ሳንቲም
- ነጭ ናፍጣ በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
- ኬሮሲን በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 62 ብር ከ36 ሳንቲም
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 61 ብር ከ16 ሳንቲም ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#አቢሲንያ_ባንክ
ወደ አፖሎ አካውንት አንድ ሰው ባስመዘገቡ ቁጥር የ50 ብር ጉርሻ!

ባንካችን አቢሲንያ በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ ተማሪዎችን የአፖሎ የተማሪ አምባሳደር በማድረግ፣ አፖሎን ለደንበኞች በማስተዋወቅ እና በምዝገባ ባሳኩት መጠን የኮሚሽን ክፍያ መክፈል ጀምሯል፡፡ ስለሆነም የአፖሎ አምባሳደር ለመሆን ፍላጎት ያላቸውን የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት ተማሪዎች አወዳድሮ እየወሰደ ነው፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት ማለትም
1. ዩኒቨርሲቲ
2. ኮሌጅ
3. ቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ናቸው

የዚህ እድል ተሳታፊ ለመሆን በቀላሉ ከታች ያለውን መስፈንጠሪያ በመጠቀም ይመዝግቡ፡፡
https://apolsup.bankofabyssinia.com/studentAgent

የ50 ብር ኮሚሽን አግኙ!
ከአፖሎ ጋር ተፍ ተፍ በሉ፡፡
ከስራ በፊት ስራ ጀምሩ፡፡

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ትግራይ

የኤርትራ ሰራዊት ከሶስት የኢትዮጵያ የትግራይ ምስራቃዊ ዞን ወረዳዎች ' 93 ወጣቶች ' አግቶ መሰወሩን የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ገልጹ።

እገታው የተፈፀመው ኢትዮጵያ በትግራይ በኩል ከኤርትራ ከምትዋሰንባቸው የዛላንበሳ ከተማ የጉሎመኻዳ እና የኢሮብ ወረዳዎች ላይ ነው ተብሏል።

ይህን የተገለፀው የከተማ እና የወረዳዎቹ አስተዳዳሪዎች ከኤርትራ ድንበር በ35 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው የዓዲግራት ከተማ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ከአፍሪካ ህብረት ወታደራዊ ታዛቢዎች (AU military attaches) ባካሄዱት ውይይት ነው። 

የዛላአንበሳ ከንቲባ መምህር ብርሀነ በርሀና ፣ የጉሎመኻዳ ዋና አስተዳዳሪ ሃፍቶም ባራኺ በጋራ ከአፍሪካ ህብረት ወታደራዊ ታዛቢዎች በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኃላ :- 

➡ በአከባቢያቸው የተለወጠ የፀጥታ ሁኔታ አለመኖሩ ፤

➡ ጦርነቱ ተከትሎ የተፈጠረው ችግር እንዳልተፈታ፤

➡ የኤርትራ ሰራዊት የዛላአንበሳ ከተማ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ፤

➡ ከዛላኣንበሳ ከተማ መግብያ በቅርብ ርቀት ዝባን ሑፃ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ኬላ አቋቁሞ ፍተሻ እንደሚያካሂድ ፤

➡ የኤርትራ ሰራዊት ከዛላኣንበሳ ከተማ 15 ፣ በቁጥጥሩ ስር ከሚገኙ የጉሎመኻዳና የኢሮብ ወረዳዎች የተለያዩ ቀበሌዎች 78 ባጠቃላይ 93 ወጣቶች አግቶ የወሰዳቸው ወጣቶች ያሉበት ሁኔታ እንደማይታወቅ  አብራርተዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በኤርትራ ሰራዊት ቁጥጥር ስር በሚገኙ የጉሎመኻዳ እና የኢሮብ ወረዳዎች 10 ቀበሌዎች የሚኖር ህዝብ እርዳታ ጨምሮ የጤና የትምህርት እንዲሁም ሌሎች የመንግስት አገልግሎቶች እንደማያገኝ አስተዳዳሪዎቹ ለአፍሪካ ህብረት ወታደራዊ ታዛቢዎች በዝርዝር አስረድተዋል።

በስብሰባው ወቅት የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ተወካዮች መሳተፋቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያገኘው መረጃ ያሳያል።

የሀገር መከላከያ ሚንስትሩ ዶክተር አብራሃም በላይ በየካቲት 2016 ዓ.ም የመጨረሻው ሳምንት ላይ በትግርኛ ቋንቋ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃለመጠይቅ ፥ "  የሻብዕያ ሰራዊት " ብለው የገለፁት የኤርትራ ጦር ከኢትዮጵያ መሬት ስለመውጣት ጉዳይ ፤

"  ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በፊት በበርካታ የትግራይ አከባቢዎች የሻዕብያ ሃይል ገብቶ ነበር ፣ ከስምምነቱ በኋላ እንዲወጣ ተደርጓል ፣ አሁንም የተቀሩ ቦታዎች ካሉ ቦታዎቹ እና ቀበሌዎች ከፌደራልና ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የተውጣጣ ቡድን በዝርዝር አጥንቶ እንዲያቀርብና መፍትሄ እንዲሰጠው እየሰራን ነው ሁሉም ልክና መስመር ይይዛል " ማለታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው የተዘጋጀው።
                                                
@tikvahethiopia            

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#BK_COMPUTERS

ማንኛውንም አይነት አዳዲስ ላፕቶፖች ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች ዴስክ ቶፖችን ጨምሮ ከብዛት እና ከታላቅ ቅናሽ ጋር ያዘንላቹ መተናል። ቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለግሪፊክስ ዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች እንዲሁም ለጨረታ የሚሆኑ በጥራት እና በ ብዛት ከ1 አመት ዋስትና ጋር እኛ ያገኛሉ

ለተጨማሪ መረጃ እና የላፕቶፕ አማራጮችን ለማየት የቴሌግራም ፔጃችንን Join ያድርጉ።
👉 /channel/BKComputers
Inbox @bkcomputer27

አድራሻ ፦ አዲስ አበባ መገናኛ ሲቲ ሞል ከመሰረት ደፋር ህንፃ አጠገብ 1 ፎቅ ላይ እንገኛለን። 0911448148/ 0955413433 we make IT easy!

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 6 / 2016 ዓ/ም ለሊት ችግር በገጠመው ጊዜ " የህዝብን ገንዘብ ያለአግባብ  ወስደው እስካሁን #አልመለሱልኝም " ያላቸው ግለሰቦች በተለያዩ ሚዲያዎች ፎቷቸውን እያሰራጨ ይገኛል።

ከሚዲያዎች በተጨማሪ በየባንኩ ቅርንጫፎች እንዲሁም በከፍተኛ ትምህርት ተቋም በር ላይ ለህዝብ በሚታይ መልኩ " ገንዘቡን አልመለሱም " ያላቸውን ግለሰቦች ፎቶግራፍ በትልልቅ ባነር በማሰራት ለጥፏል።

ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ " ብር ተመላሽ አድርገን እስካሁን ፎቷችን በሚዲያዎች እንዲሰራጭ እየሆነ ነው " ያሉ ቅሬታ አቅራቢዎች ባንኩ ገንዘብ የመለሱትንም በፎቶግራፍ ማውጣት እንዳለበት ገልጸዋል።

" የወሰድነውን ብር ተመላሽ አድርገን ሳለ ባንኩ ብር ካልመለሱት ጋር አደባልቆ ፎቶፍራፋችንን ማሰራጨቱ ተገቢ አይደለም በመሆኑንም ህዝብ በሚያውቀው መንገድ መመለሳችንን ሊያሳውቅ ይገባል " ብለዋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ፎቶ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 6 ከባንኩ ገንዘብ " ያለአግባብ ወስደው አልመለሱልኝም " ያላቸውን ግለሰቦች ፎቶ ማሰራጨት ቀጥሏል።

ዛሬ ከ80 ሺ እስከ 70 ሺ ብር ወስደው ያልመለሱ ግለሰቦችን ፎቶግራፍ አሰራጭቷል።

ባንኩ ባለፉት ቀናት ለ3 ዙር ያህል ፎቶግራፍ ማሰራጨቱ ይታወሳል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

የሶማሊያ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት #ለማቋረጥ በመወሰን በአገሪቱ የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደር እና ዲፕሎማቶች ለቀው እንዲወጡ ማዘዟ ተሰምቷል።

አዲስ አበባ ያሉትን አምባሳደሯንም ጠርታለች።

የሶማሊያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስቴር ይፋ እዳደረገው በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ሞሐመድ ዋሬ በ72 ሰዓታት ውስጥ ሞቃዲሾን ለቀው እንዲወጡ አዛለች።

በተጨማሪም ከሶማሊያ ነጻ አገርነቷን ባወጀችው ሶማሊላንድ እና በከፊል ራስ ገዟ ፑንትላንድ ውስጥ የሚገኙት ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች በ7 ቀናት ውስጥ እንዲዘጉ መወሰኑን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

በተመሳሳይም ሶማሊያ በአዲስ አበባ የሚገኙትን አምባሳደሯን “ ለአጠቃላይ ምክክር ” ከኢትዮጵያ ለቀው እንዲወጡ መታዘዛቸው ተገልጿል።

የሶማሊያ እርምጃ ኢትዮጵያ #ሶማሌለንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ማድረጓን ተከትሎ " በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ ገብታለች " በሚል ምክንያት ነው።

ሮይተርስ ከሰዓት በፊት የሶማሊያ ባለሥልጣናትን ዋቢ በማድረግ ባሰራጨው መረጃ የኢትዮጵያ አምባሳደር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል ብሎ የነበረ ሲሆን አሁን የሶማሊያ መንግሥት በይፋ አምባሳደሩ በ72 ሰዓታት ለቀው እንዲወጡ ማዘዙን አሳውቋል።

የሶማሊያን መንግሥትን ውሳኔን በተመለከተ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ነብዩ ተድላ በዚህ ጉዳይ መረጃ እንደሌላቸው ገልጸው ነበር።

መረጃው የቢቢሲ እና ሮይተርስ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#AddisAbaba

ምንም አይነት የጤና ችግር የሌለበት ጓደኛቸውን ሁለቱም ኩላሊቶቹ ከጥቅም ውጪ የሆኑ በማስመሰል በህክምና ሰበብ ገንዘብ ሲያሰባስቡ የነበሩ 10 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለጸ።

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ቦታው " አዲስ ሰፈር " አካባቢ መሆኑን አሳውቋል።

ግለሰቦቹ የሰሌዳ ቁጥር " ኮድ 3- B21705 አ.አ " የሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪን በመጠቀም ገንዘቡን ሲሰበስቡ የቆዩት " የኩላሊት ታማሚ ነው " ያሉትን ጓደኛቸውን መኪና ውስጥ በማስተኛት ነው።

በተያዙበት ወቅት ከ5 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ እጃቸው ላይ መገኘቱን ፖሊስ ገልጿል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ በከተማው በተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ የድጋፍ ጥያቄዎች ሲቀርቡ የሚስተዋል መሆኑን ገልጾ ነገር ግን ህብረተሰቡ እንዲህ አይነት #የማታለል ተግባርም የሚፈፅሙ ሰዎች መኖራቸውን ተገንዝቦ ድጋፍ ሲያደርግ ከህክምናው ጋር የተያያዙ አግባብነት ያላቸውን #ሰነዶች በማየትና ትክክለኛነቱን በማረጋገጥ ሊሆን ይገባል ሲል አሳስቧል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" 480 ስደተኞች #በሊቢያ የባህር ጠረፍ ላይ ተይዘዋል " - IOM

ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 480 ስደተኞች በሊቢያ የባህር ጠረፍ ላይ መያዛቸው ተነግሯል።

የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት/IOM ሰኞ'ለት ባወጣው መግለጫ 480 ስደተኞች በባህር ላይ ጠባቂዎች መያዛቸውን አስታውቋል።

ድርጅቱ "ከመጋቢት 24 እስከ 30,2024 ውስጥ 480 ስደተኞች ተይዘው ወደ ሊቢያ ተመልሰዋል " ነው ያለው።

ከተያዙት ስደተኞች ውስጥ 26 ሴቶች እንዲሁም 5 ህፃናት እንደሚገኙበትም ተነግሯል።

የስደተኞች 2 #አስክሬንም ተገኝቷል።

በዚህ ዓመት በጠቅላላ 3,791 ስደተኞች የተያዙ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 120ዎቹ #ሲሞቱ ፣ ሌሎች 250 የሚሆኑት #ጠፍተዋል መባሉን MDN ዘግቧል።

ፎቶ ፦ ፋይል

Via t.me/+LM-bJ8NzZMcxMjA8

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ደመወዝ #የትርፍሰዓትክፍያ

➡ “ ከ9 ወር በላይ ለሚሆን ጊዜ የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈለንም ”- ከ200 በላይ የጤና ባለሙያዎች

➡ “ የትርፍ ሰዓት በየወሩ እየተከፈለ አይደለም እሱ ትክክል ነው። የከተማ አስተዳደሩ ለመክፈል ቃል ገብቷል ” - የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፤ ጋሞ ዞን ፤ በሰላምበር ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚያገለግሉ የጤና ባለሙያዎች ከ9 ወራት በላይ ለሚሆን ጊዜ የትርፍ ጊዜ ሰዓት ክፍያ እንዳልተከፈላቸው ፣ ደመወዝም የሚገባላቸው እየተቆራረጠ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የጤና ባለሙያዎችን ወክለው ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ አንድ የጤና ባለሙያ ተከታዩን ብለዋል።

- “ ከ9 ወራት በላይ ለሚሆን ጊዜ የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈለንም። ሳይከፈለን 10ኛ ወር እየሰራን ነው ያለነው። ”

- “ በሌላ በኩል ደግሞ ዋና ደመወዝ ሁሌም እየተቆራረጠ ነው የሚገባው። ግማሹ ብቻ ያስገቡና ግማሹ ደግሞ ሳይገባ ወሩ ያልቃል። ”

- “ የደመወዝ ሆነ የትርፍ ሰዓት ክፍያ በተመለከተ ቅሬታ ያለን 113 ጤና ባለሙያዎች (የትርፍ ሰዓት ያልተከፈላቸው) ፣ 103 ድጋፍ ሰጭ ባለሙያዎች (የትርፍ ሰዓት ክፍያ የማይመለከታቸው) ናቸው። ”

- “ ያልተከፈለው የክፍያ መጠን እንደ ጤና ባለሙያው ፤ አሁን ለምሳሌ የእኔ 5,000 ነው በወር የሚሆነው። 15 ሺሕ የሚከፈለው አለ። 30 ሺሕ የሚከፈለው አለ እንደ ስፔሻሊቲ ከሆነ። ”

በጉዳዩ ላይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦
* የሰላምበር የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የCOA ተወካይ አቶ ደካሶ ዲቻ፣
* የሰላምበር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዘነበ ወንተ
* የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንደሻው ሽብሩን አግኝቶ ምላሽ እንዲሰጡ ቢሞክርም ፈቃደኛ አልሆኑም።

የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ግን ለተነሳው ቅሬታ ምላሽ ሰጥቷል። የዞኑ ጤና መምሪያ ቢሮ አቶ ሰይፉ ዋናካ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሠጥተዋል።

አቶ ሰይፉ ዋናካ ምን አሉ ?

° “ ቅሬታ ሲቀርብ ወርደን እናወያያለን። ከሁለት ወራት በፊት ወርደን አወያይተን፣ አግባብተን የትርፍ ሰዓት በየወሩ እየተከፈለ አይደለም እሱ ትክክል ነው። ግን ያው የተወዘፈም እየተከፈለ ነው ያለው። ”

° “ ችግሩ ካለ ወርደን እናስከፍላለን። የደመወዝ፣ የትርፍ ሰዓት ጉዳይ ከእኛ አቅም በላይ አይደለም። ”

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩ ካቅማችሁ በላይ ካልሆነ ከ9 ወራት በላይ ለምን ዘገዬ ? ሲል ጠይቋል።

ምላሽ ፦

° “ የከተማ አስተዳደሩ ችግርም ፣ አገራዊ ችግሮችም አለ። ሁሉ ወጥ አይሆንም። የከተማ አስተዳደሩ ለመክፈል ቃል ገብቷል። ስለዚህ የ10 ወራቱም ቢሆን ይከፈላል። ”

ጤና ባለሙያዎቹ በበኩላቸው፣ ከወራት በፊት ፒቲሽን ሰብስበው የትርፍ ሰዓት ሥራ እንደማይሰሩ አቋማቸውን ሲገልጹ ኃላፊዎች ቢያወያዩአቸውም ክፍያው እንዳልተሰጣቸው አስረድተዋል።

መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#DStv: ቀላል እና ፈጣን መላ ለዲኤስቲቪ ደንበኞች በሙሉ!

ወደ ዲኤስቲቪ የጥሪ ማዕከል ሳይደውሉ በማንኛውም ሰዓት በሞባይልዎ *9299# በመደወል እና My DStv App ስምዎንና የስማርት ካርድ ቁጥርዎን አስገብተው የዲኤስቲቪ ክፍያ መጠንዎንና ቀኑን በቀላሉ ለማወቅ ፓኬጅ ለመቀየር ብሎም በቴሌብር ፣ በሲቢኢ ብር እና በአዋሽ ብር መክፈል ይችላሉ።

የMyDStv
- የቴሌግራም
- የፕሌይ ስቶር
- የአፕ ስቶር ሊንክ ይጫኑ!

በተጨማሪም ስለ አገልግሎታችን ጥራት በሚደርስዎት የፅሁፍ መልዕክት ላይ ሊንኩን በመጫን መጠይቁን እንዲሞሉ በትህትና እንጠይቃለን።

ይሞክሩትና የማይጠገብ የመዝናኛ አማራጭ ያለማቋረጥ ያጣጥሙ ፤ የእርስዎንም አስተያየት ያጋሩ!

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET'

Читать полностью…
Subscribe to a channel