#Tigray
" በአላማጣ ዙሪያ የነበረው ኃይል አከባቢውን ለቆ ወጥቷል " - የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ትላንትና ከምሸቱ 4:00 ባወጣው መግለጫ ፥ " በአላማጣ በቅሎ ማነቂያና ገርጃለ የነበረው #የተወስነ የትግራይ ተዋጊ ኃይል አከባቢውን ለቆ ወጥቷል " ብሏል።
የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነትን በማስመልከት በአዲስ አበባ በወጣው የአተገባበር ኦፕሬሽን ፕላን መሰረት በማድረግ ተዋጊ ኃይሉ አከባቢውን እንዲለቅ መደረጉን ገልጿል።
ለአላማጣ ህዝብ ደህንነት ተብሎ የተወሰነ ተዋጊ ኃይሉ ከቦታው ለቆ ቀድሞ ወደ ነበረበት ቦታ መመለሱን አመልክቷል።
የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንትም አቶ ጌታቸው ረዳም ይህኑን አረጋግጠዋል።
አቶ ጌታቸው ራዳ ፤ " የፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነት ትግበራ አካል ሆኖ የትግራይ ተፈናቃዮች በቀላሉ ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ ከፌዴራል መንግስት እና ከአማራ አስተዳደር ጋር ያለውን መግባባት ለማክበር በአላማጣ አቅራቢያ ከሚገኙት ገርጀለ እና በቅሎማናቂያ አካባቢዎች የትግራይ ሃይሎች እንዲወጡ ተወስኗል " ብለዋል።
ተጨማሪ የትግራይ ተፈናቃዮችን ለመመለስ ተመሳሳይ አይነት እርምጃ ለመውሰድ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
የጊዚያዊ አስተዳደሩ ም/ፕሬዝዳንት ሌ/ ጀነራል ታደሰ ወረደ ባለፈው እሁድ በሰጡት መግለጫ የትግራይ አስተዳደር ወደ አላማጣ እንደሚገባና በአከባቢው የሚገኘው የትግራይ ታጣቂ ኃይል ይወጣል በማለት ተናግረው ነበር።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
#SmartHomeFurniture
ቤትዎን በስማርት ፈርኒቸር ያስውቡ!!!
👉ቤት ውስጥ ስንሆን አብዛኛውን ጊዜ የአይናችን ማረፊያ ቦታ ቲቪያችን ጋር ነው።
👉 የቲሌቪዥንዎትን ደህንነት ያረጋግጡ
👉 አነስተኛ ቦታን ተጠቅመው ቤትዎን ያሳምሩ!
👉እጅግ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ
👉ብቃት ባላቸው ባለሙያዎቻችን ቤትዎን እናሳምርልዎታለን !!!
👉በነፃ ያሉበት አድርሰን እንገጥምሎታለን!!
👉ሌሎች አማራጮችን በቴሌግራም ቻናላችን ያገኛሉ
http://t.me//smartomeff
ለማዘዝ በ 📲 0911494931
0911494921 ይደውሉ!
የአሜሪካ ኤምባሲ ሁለት ቀን ተዘግቶ ይውላል።
በአዲስ አበባ የሚገኘው የኤሜሪካ ኤምባሲ ሰኞ እና ማክሰኞ ዝግ ሆኖ እንደሚውል አስታውቋል።
ኤምባሲው ፥ ሰኞ ግንቦት 19/2016 ' ሚሞሪያል ዴይ 'ን ወይም በግዳጅ ላይ የተሰዉ የአሜሪካ አርበኞች መታሰቢያ በዓልን ምክንያት በማድረግ እንደሚዘጋ አመልክቷል።
በነጋተው ማክሰኞ ግንቦት 20 የ #ደረግ_መንግሥት የወደቀበትን ቀን ምክንያት በማድረግ ሙሉ ቀን ተዘግቶ እንደሚውል ገልጿል።
ኤምባሲው ዳግም የሚከፈተው #ረቡዕ_ግንቦት_21 መሆኑን አሳውቋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ADHD
የስዊድን መንግሥት ፦
° ጥንቃቄ የጎደለው ትኩረት የማጣት፣
° ከፍተኛ የመቅበጥበጥ፣
° ብዙ የማውራት፣
° ግትርነት
° እራስን የመግዛት ቀውስ (ADHD -attention deficit hyperactivity disorder) ችግር በብዛት የሚታይባቸው ልጆች በሀገሪቱ ቁጥራቸው መጨመሩን ዛሬ አስታወቀ።
የሀገሪቱ የማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው ቃል የስዊድን የጤና እና ደህንነት ቦርድ መረጃ ADHD ተብሎ የሚገለጸው #የአእምሮ_ጤና_ችግር እ.ኤ.አ. ከ2022 ጀምሮ 10 በመቶ በሚሆኑ ወንዶች ልጆች ላይ እንዲሁም 6 በመቶ በሚሆኑት አዳጊ ሴት ልጆች ላይ በምርመራ መታየቱን ይፋ አድርጓል።
የችግሩ ተጋላጭ ልጆች ቁጥር ሊጨምርም ይችላል ተብሏል።
በመላው ዓለምም ከ5 እስከ 7 በመቶ የሚሆኑ ልጆች ለዚህ ችግር የተጋለጡ ናቸው።
ለዚህ ችግር የሚያጋልጡ ምክንያቶች ፦
- የተለያዩ እንደ ሊድ ወይም እርሳስ ባሉ ማዕድናት የተበከለ አካባቢ መኖር፣
- በእርግዝና ወቅት መድኃኒቶች፣ አልኮል ወይም ሲጋራ / ትንባሆ ማጨስ ማዘውተር ሊሆኑ እንደሚችሉ ይገመታል።
ከዚህም በተጨማሪ በደም አማካኝነት በዘር የአእምሮ ህመሞችም ሊተላለፉ እንደሚችሉ ነው የተገለጸው።
ይህ የአእምሮ ችግር (ADHD) ያለባቸው ልጆች ቁጥር ለምን እንደጨመረ መንስኤውን ለማወቅ ጥናቶች እየተካሄዱ ነው።
#DeutscheWelle
@tikvahethiopia
#Ethiotelecom
iPhone 15 Pro Max is now available, offering you the ultimate smartphone experience!
Prepare to be fully immersed in a realm of advanced technology and unparalleled convenience.
Choose from an amazing selection of packages to get everything you need.
📱 iPhone 15 Pro Max +
🔌 Charger Head
🌐 100/50 GB Mobile Data and
🎧 AirPods 3rd Generation
You can get the devices from our premium business centers, Churchill avenue next to Lycée Gebre Mariam School.
#iPhone15ProMax
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#INSA #ጥቆማ
የብሔራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ምዝገባ መካሄድ ጀምሯል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በ2014 ዓ/ም እና በ2015 ዓ/ም ለሁለት ተከታታይ አመታት በሳይበር ደህንነት እና ተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ታዳጊ ወጣቶች በክረምት ፕሮግራም (Summer Program) አሰልጥኖ ማስመረቁን ገልጿል።
ተመራቂዎችንም ፦
° #እንደየችሎታቸው እና #እንደስራዎቻቸው ከተለያዩ ባለሀብቶች ጋር የማስተሳሰር፤
° ኢመደአን (INSA) ጨምሮ በተለያዩ ተቋማት #ተቀጥረው መስራት የሚችሉበት ሁኔታ እንዳመቻቸ አመልክቷል።
ባለፉት ሁለት አመታት የተከናወኑ የሳይበር ታለንት ልማት ፕሮግራሞችን መነሻ በማድረግ በ2016 በጀት አመት “ብሄራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ” ፕሮግራም መዘጋጀቱ ተገልጿል።
የዚህ ቻሌንጅ ዋና ዓላማ በሳይበር ደህንነት እና ተያያዥ መስኮች ልዩ ተሰጥዖ ያላቸዉን ሰዎች በመመልመል በዘርፉ ላይ ተጨባጭ ተጽዕኖ መፍጠር የሚችል ብሄራዊ የሳይበር ሰራዊት (National Cyber Army) መገንባት ነው ተብሏል።
በሳይበር ደህንነት እና ተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላቸው እና እድሜያቸው ከ11 አመት ጀምሮ ያሉ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በዚህ ቻሌንጅ ላይ መሳተፍ ይችላሉ ተብሏል።
መመዝገቢያ ጊዜ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ነው።
መመዝገቢያ አድራሻው https://talent.insa.gov.et ነው።
@tikvahethiopia
" ሲጀመር ‘የኮቴ’ ክፍያ አገር ውስጥ መጠየቅ አግባብ አይደለም " - ጣና የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች ማኀበር
የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች ፣ ሞጆ መግቢያ ‘ #የኮቴ ’ በሚል ታጣቂዎች አስቁመው 2,000 ብር እያስከፈሏቸው መሆኑን እየገለጹ ይገኛሉ።
ካሁን ቀደም ገንዘቡን ሲጠየቋቸው የነበረው አንዳንድ ጊዜ በቀን እንደነበር ፣ ከሰሞኑን ግን ቀንም ሌሊትም እየጠየቋቸው ከመሆኑም ባሻገር ድብደባና እንግልት እያደረሱባቸው መሆኑን አስረድተዋል።
ሰሞኑን አንዱን ሹሬር ሞጆ መግቢያ ከሌሊቱ 6 ሰዓት አስቁመው ገንዘብ እንደጠየቁት፣ ‘የለኝም’ ሲላቸው እንዳንገላቱት ገልጸዋል።
ሌላኛው ሹፌር ክፉኛ መመታቱን አመልክተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለ “ ኮቴ ” ክፍያው ምንነት ያውቅ እንደሆን የጣና የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች ማኀበርን ጠይቋል።
ማኀበሩ ፤ " አሁን #ጂቡቲ ስንደርስ የሌላ አገር መሬት ስለምንረግጥ ‘ የኮቴ ’ እንከፍላለን። የተለመደ ነው። እዚህ ግን ‘የኮቴ’ እያሉ 2,000 ነው የሚጠይቁት። ይሄ ደግሞ ተገቢም አይደለም " ብሏል።
" ሞጆ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ድርጊቱ አለ " ያለው ማኀበሩ ፣ አንድ ጊዜም ቢሆን መከፈሉ ከህግ አግባብ ውጪ ሆኖ ሳለ በድጋሚ ሌላ ቦታ ላይ እንደሚያስከፍሏቸው አስረድቷል።
ማኀበሩ ፤ " ሲጀመር ‘ የኮቴ ’ ክፍያ በአገር ውስጥ መጠየቅ አግባብ አይደለም " ብሎ፣ ከክፍያው ባሻገር አሽከርካሪዎቹ ገንዘቡን በሚጠይቁ መሳሪያ የታጠቁ ታጣቂዎች ድብደባ እንደሚፈጸምባቸው፣ የክልሉ አካላት ድርጊቱን ቢያውቁም መፍትሄ እንዳልሰጡ ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ቅሬታውን በተመለከተ ምላሽ ለማግኘት ወደ ክልሉ ባለስልጣናት ያደረገው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም።
Video Credit - ኪያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Tecno #Camon30Pro5G
ቴክኖ ሞባይል በአይነቱ የተራቀቀውን አዲሱን Tecno Camon 30 pro 5G ምርጫዎ ያድርጉ ሲል ይጋብዛል!
#Camon30Et #Camon30pro5GEt #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
#OnlineNationalExam
ለመጀመሪያ ጊዜ በኦንላይን የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና መንግሥት በሚያዘጋጃቸው ኮምፒውተሮች እንደሚከናወን የሀገር አቀፍ ትምህርት፣ ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለኢቢሲ ገልጿል።
አንዳንድ ወላጆች " በኦንላይን ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና የመፈተኛ ኮምፒውተር እንድናቀርብ ተጠይቀናል " ብለዋል።
አገልግሎቱ ግን ይህንን በሚመለከት ለትምህርት ቤቶች ያስተላለፈው መልዕክት እንደሌለ እና ወላጆች መጠየቃቸውም ተገቢ አለመሆኑን ገልጿል።
የኦንላይን ፈተናው መንግስት በሚያዘጋጀው አቅርቦት እንደሚከናወን አመልክቷል።
ተማሪዎች ለፈተና ሲመጡ የሚጠበቅባቸው አንብቦ እና በቂ ዝግጅት አድርጎ የተመዘገቡበትን መታወቂያ ይዞ መምጣት ብቻ ነው ብሏል።
ነገር ግን ትምህርት ቤቶችም ሆኑ ተማሪዎች የግል ኮምፒውተሮቻቸውን ለፈተናው መጠቀም ከፈለጉ #እንደማይከለከሉ አገልግሎቱ አሳውቋል።
ሁሉም ተማሪዎች በኦንላይ እንዳይፈተኑ የመሰረተ ልማት አለመሟላት እንቅፋት ሊሆን ስለሚችል ዘንድሮ #በተወሰኑ ተማሪዎች ብቻ እንደሚጀመር ገልጿል።
በሌላ በኩል ፥ በወረቀት ለሚሰጠው ፈተና የህትመት ስራው ወደ #መጠናቀቅ መቃረቡን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለኢቢሲ በሰጠው ቃል አመልክቷል።
ይህ እንዴት ይታያል ?
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በኦንላይን ለሚሰጠው ፈተና " ትምህርት ቤቶች ሆኑ ተማሪዎች #የግል_ኮምፒዩተራቸውን ለፈተና መጠቀም አይከለከሉም " ብሏል።
ተማሪዎች የራሳቸውን ኮፒዩተሮች ይዘው ሲገቡ በውስጡ ለፈተና ደህንነት የሚያሰጋ ወይም ፈተናውን እንዲሰሩ የሚያግዛቸው የተለያየ ዶክመት ተደብቆበት እንዳልሆነ የሚረጋገጥበት ምን አይነት መንገድ እንዳለ አልተብራራም።
ሌላው ተፈታኞች በፈተና ወቅት በኢንተርኔት ድረ ገጾችን በመጎብኘት ጥያቄ የሚሰሩበት መንገድ እንዳይኖር ስለሚወሰደው የጥንቃቄ እርምጃ የተብራራ ነገር የለም።
መሰልና ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች ችግር ይዘው እንዳይመጡ ከወዲሁ ማሰብና ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#እንድታውቁት #አዲስአበባ
' ሜክሲኮ ' በሚገኘው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ዋና መ/ቤት በነበረ ፕሮግራም ተዘግተው የነበሩ መንገዶች አሁን ላይ ክፍት ናቸው።
በምሽትና ለሊት የትራንስፖርት አገልግሎት የምትሰጡ የቤተሰብ አባላቶቻችን ይህ መረጃ ይጠቅማችሁ ይሆናል።
@tikvahethiopia
#WHO🚨
በግብረ ስጋ ግኝኑነት የሚተላለፉ ሽታዎች ወይም የአባላዘር በሽታዎች በዓለም ዙሪያ እጅግ አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ እየጨመሩ እንደሚገኙ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) አዲስ ሪፖርት አሳይቷል።
ሪፖርቱ ፥ በየዓመቱ በመላው ዓለም 2.5 ሚሊዮን ሰዎች በግብረ ስጋ ግኙነት በሚተላለፉ በሽታዎች ፣ በኤችአይቪ እንዲሁም ሄፓታይተስ እየሞቱ ናቸው ብሏል።
በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉት እና ሊታከሙ የሚችሉ በሽታዎች እጅግ በፍጥነት እየተስፋፉ ሲሆን ሁኔታው አሳሳቢ ስለመሆኑ በሪፖርቱ ላይ ሰፍሯል።
ሪፖርቱ ፦ https://www.who.int/news/item/21-05-2024-new-report-flags-major-increase-in-sexually-transmitted-infections---amidst-challenges-in-hiv-and-hepatitis
በዓለም ላይ በየዕለቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በግብረ ስጋ ግንኙነት በሚተላለፉ የተለያዩ የሽታ አይነቶች ይያዛሉ።
ዲኤንኤ ዊክሊ የተሰኘ የጤና ድረገጽ እንደሚለው ፤ ዛሬም ድረስ በግብረ ስጋ ግንኙነት ስለሚመጡ በሽታዎች መነጋገር ' እንደ ሚያሳፍር እና እንደ ተከለከለ ' አድርገው የሚቆጥሩ ብዙ ናቸው።
ከጤና ባለሞያዎች ጋር መመካከር ፣ ስለጉዳዩ ማወቅ ፣ ሲታመሙ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ የሚያፍሩ ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አይደለም።
ነገር ግን በበሽታዎቹ በየዕለቱ ሚሊዮኖች የሚያዙ ሲሆን በየአመቱም ሚሊዮኖች የሞታሉ።
በመሆኑ ስለ ጉዳዩ አሳስቢነት ሳያፍሩ መነጋገር ፣ የመተላለፊያ የመከላከያ መንገዶች ማወቅ ፣ የጤና ባለሞያዎችን ማማከር ምክራቸውንም መስማት ይገባል።
@tikvahethiopia
#AddisAbaba
ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ በግንባታ ላይ ከነበረ ህንጻ አጠገብ ያለ ቤት ውሃልክ እና አፈር ተደርምሶ የአንድ ወጣት ህይዎት አልፏል።
አደጋው የደረሰው ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 በተለምዶ " የረር ጉሊት " ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ነው።
በግንባታ ስራ ላይ የነበሩ ሰራተኞች ከአጠገቡ ዳገት ላይ የነበረ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ውሃ ልክ እና አፈር ተደርምሶ የ28 ዓመት ወጣት ህይወት አልፏል።
አደጋው መፈጠሩ ከተሰማ ጀምሮ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት ሰራተኞችን ህይዎት ለመታደግ ከፍተኛ ርብርብ ማድረጋቸው ተነግሯል።
በቅርቡ የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፤ ከተማዋ ውስጥ በአደጋ የሚከሰት ሞት ከባለፈው ዓመት ሲታይ ዘንድሮ መጨመሩን ፤ በብዛት የሞት አደጋ እየደረሰባቸው ያሉት ደግሞ የቀን ሠራተኞች መሆናቸውን ጠቁሞ እንደነበር አይዘነጋም።
@tikvahethiopia
#አበረታቷቸው🙏
" ከበርካታ ችግሮች ጋር እየታገልንም ቢሆን ከ90 በላይ ህጻናትን ቁርስ አብልተን ወደትምህርት ቤት እንልካለን " - ተዋናይትና ደራሲ ሀና ፍቃዱ
የበጎ ልቦች የእርዳታ ድርጅት በቅን አሳቢ ወጣት የሀዋሳ ልጆች የተመሰረተ ድርጅት ነው።
ድርጅቱ ሲመሰረት ጥቂት አረጋዉያንን በየቤቱ እየሄዱ ማገዝና አልፎ አልፎ ለህጻናት የትምህርት ቁሳቁስ የማገዝ አላማ አንግቦ ነበር።
አሁን ላይ ከ90 በላይ ህጻናትን ቁርስ አብልቶ ወደትምህርት ቤት የሚልክና ከ30 በላይ አረጋዉያንን እየተንቀሳቀሰ የሚረዳ ድርጅት ለመሆን በቅቷል።
በድርጅቱ ውስጥ በማስተባበርና ቅን ልብ ያላቸው ኢትዮጵያዊያን እየጠየቀች ገንዘብ በማሰባሰቡ በኩል የነቃ ተሳትፎ የምታደርገዉ ተዋናይትና ደራሲ ሀና ፈቃዱ ፥ " እቅዳችን በምግብ ችግር ትምህርት ቤት የሚያቋርጡ 30 ልጆችን መርጠን ቁርስ በማብላት ወደ ትምህርት ቤት መላክ ቢሆንም አሁን ላይ ከ90 በላይ ልጆችን እያስተናገድን ነው " ብላለች።
" ለዚህም ሀገር ውስጥና ውጭ ሀገር የሚኖሩ ልበ ቀናዎች እያገዙን ነው " የምትለው ሀና ፥ " እገዛዉ ከጠበኩት በላይ ሆኖ በኢትዮጵያዊነቴ እንድኮራ አድርጎኛል " በማለት በሶሻል ሚዲያና በአካል የሚያግዟቸውን አካላት አመሰግናለች።
ይሁንና አሁን ላይ ያለው የህጻናት ቁጥር በጣም በማሻቀቡ ከፍተኛ ድጋፍ ያሻናል በማለት ማህበረሰቡ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርባለች።
በድርጅቱ ውስጥ " የሰኞን የቁርስ ወጭ እኔ እሸፍናለሁ " ብሎ ህጻናቱ ጋር ያገኘነዉ የባህርዳር ከነማዉ ተጫዋች ፍሬዉ ሰለሞን ወይም ጣቁሩና ባለቤቱ በህጻናቱ ሁኔታ ልባቸዉ እንደተነካና ለወደፊቱም ቤተሰብ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።
" ሁላችንም ተባብረን ህጻናቱን ልንረዳ ይገባል " የሚለዉ ተጫዋቹ በሚቀጥለዉ ሲመጣ ጓደኞቹን ይዞ እንደሆነ ገልጾ " የበጎ ልቦችን ሁኔታ እየመጣችሁ ጎብኙ " በማለት ጥሪ አቅርቧል።
ተማሪዎቹን ቁርስ አብሎት ለመሸኘት በቀን ከ8 ሺህ እስከ 10 ሺህ ብር የሚጠይቅ ሲሆን ሀና ፍቃዱን ጨምሮ ሌሎችም የማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም በሚያደርጉት ጥረት ተማሪዎቹ የሚመገቡት።
አስተባባሪዎችን በስልክ ቁጥር 0911992312 ወይም 0926441657 ደውለው አግኟቸው።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
#Tecno #Camon30Pro5G
ፍጥነት እና ቅልጥፍና መገለጫው የሆነውን MediaTek Dimensity 8200 ፕሮሰሰር አካቶ Tecno Camon 30 pro 5G ቀርቦሎታል
#Camon30Et #Camon30proEt #Camon30 #Camon30Pro #TecnoEt
#ዓዲግራት
በንዋየ ቅዱሳን ሰርቆት ወንጀል የተጠረጠሩ 4 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ግለሰቦቹ የመቐለ ነዋሪ ናቸው።
5 የወርቅ መስቀሎችን ከመቐለ ወደ ዓዲግራት ወስደው ሊሸጡ ሲደራደሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዓዲግራት ፓሊስ ፅ/ቤት አስታውቀዋል።
የዓዲግራት ከተማ ፓሊስ ዋና አዛዥ የማነ ኪዳኑ ፥ " ቅዳሜ ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ/ም የግል ተበዳይ ከመቐለ ወደ ሽረ ከተማ የወርቅ መስቀሉን ጭኖ በመውሰድ ላይ ሳለ ነው ተጠርጣሪዎቹ ሰርቆቱን ፈጽመው የተሰወሩት " ብለዋል።
ግለሰቡም በመቐለ ከተማ ለቀዳማይ ወያነ ፓሊስ ፅህፈት ቤት ያመለከተውን መረጃ መነሻ በማድረግ በተካሄደው ክትትል ተጠርጣሪዎች በዓዲግራት ከተማ ውስጥ ሊያዙ እንደቻሉ ገልጸዋል።
ተጠርጣሪዎች የሰረቁትን አንዱ ብር 25 ሺህ የሚያወጣ መስቀል ፤ በ15 ሺህ ሊሸጡት ተሰማምተው በዋጋው ማነሰ የተጠራጠረ ገዢ በኩል መረጃው ወደ ፓሊስ በመድረሱ ግለሰቦች ከነእግዚብታቸው በፓሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ የፖሊስ አዛዡ ገልጸዋል።
ግለሰቦቹ 4 ሲሆኑ ነዋሪነታቸውም መቐለ ነው።
የዓዲግራት ፖሊስ ፤ እንዲገዛ ግብዣ የቀረበለት ግለሰብ ጊዚያዊ ጥቅም እና ትርፍ ሳያሸንፈው ለፓሊስ ያደረገው ትብብር ሌላው እጅግ አርአያ የሚሆነው ሲል አወድሷል።
መረጃው ይህ ሆኖ ሳለ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " የዓዲግራት ወጣቶች የሆኑ ከቤተክርስቲያን ቤተመቅደስ ውስጥ ንዋየ ቅዱሳን ዘረፉ " እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
#ሰከላ
➡ " ባለፈው ሳምንት ውስጥ ብቻ 47 ሰዎች ናቸው የተገደሉት " - ነዋሪዎች
➡ " በተጨባጭ የሞተ አንድም ሲቪል የለም። ይህ ነው ትክክለኛው እውነት " - የኮማንድ ፖስት ምክትል ሰብሰቢ
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ላይ ግንቦት 4 ቀን 2016 ዓ/ም በ " ፋኖ " እና በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች መካከል የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ፣ ከዚያ በኋላ ባሉት ቀናት " በጸጥታ ኃይሎች " ንጹሐን መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ቃላቸውም የሰጡ ነዋሪዎች ምን አሉ ?
° #ሰርገኞች ሳይቀሩ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ተገድለዋል። ሰርግ ላይ የነበሩ የሙሽራው ወንድም፣ አጃቢዎች ሰኞ ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ/ም መንገድ ላይ ተረሽነዋል።
° ሴቶች ተገድለዋል።
° 3 ካህናት ከቤተክርስቲያን እየተመለሱ በነበረበት ወቅት ተገድለዋል።
° ባለፈው ሳምንት ብቻ 47 ሰዎች ናቸው የተገደሉት።
° እውነት የተናገሩ ሰዎች ተጨፍጭፈዋል።
° ግንቦት 15/2016 ዓ/ም ከሰከላ 4 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ቦታ 6 ሰዓት የተጀመረ ተኩስ እስከ ምሽቱ 12 ቆይቷል።
° ተራው ህዝብ ወደ ገጠራማው አካባቢ፣ ባለሃብቶች ወደ ባሕር ዳር ከተማ ለመፈናቀል ተገደዋል።
አንድ አሽከርካሪ አባትም ልጃቸው ሱቅ ብሎ እንደወጣ እንደተገደለባቸው በሀዘን ስሜት ሆነው ቃላቸውን ሰጥተዋል።
ተኩስ ያለው ሰሞኑን ብቻ ነው ከዚህ በፊትም ነበር ? ተብሎ ጥያቄ የቀረበላቸው ነዋሪዎች ፣ የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ/ም ነበር። ከየካቲት 2016 ዓ/ም ጀምሮ በሰከላ ብቻ 107 ሰዎች ተገድለዋል " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ሰላም እንዲያሰፍንላቸው የጠየቁ ሲሆን " ሰላም ይውረድልን ግጭት በመጣ ቁጥር እየሞተ ያለው ንጹሃን እንጂ የታጠቀ ኃይል አይደለም " ብለዋል።
የምዕራብ ጎጃም ኮማንድ ፖስት ምክትል ሰብሳቢ እና የዞን ዋና አስተዳዳሪ እድሜአለም አንተነህ ከሰሞኑን ለ ' አሻም ቴሌቪዥን ' በሰጡት ቃል ፥ " አንድም ንጹሃን አልተገደለም " ብለዋል።
ዋና አስተዳዳሪው ምን አሉ ?
- ከሳምንት በፊት ሰከላ ላይ ሌሎች ቦታዎች አልፎ አልፎ እንደሚደረገው ግጭት ነበር። ግጭት የነበረው ከከተማው 18 ኪሎ ሜትር ቦታ ላይ ነበር። ግጭቱ የነበረው በታጠቁ ኃይሎች እና በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች መካከል ነው። ሁለቱም መሳሪያ የያዙ ናቸው።
- እዛ የነበረውን ክፍተት መነሻ አድርጎ ሌላው የታጠቀ ኃይል እኛ ' ፅንፈኛው ኃይል ' የምንለው ሾልኮ ገብቶ ባንኮችን እና የግለሰብ ድርጅቶች ላይ ከፍተኛ ዝርፊያ ነው የፈጸመው። በቦታው ላይ በሁኔታው ላይ የተሳተፈ በተጨባጭ የሞተ አንድም ሲቪል የለም።
- በተጨባጭ የሞተ አንድም ሲቪል የለም። ይህ ነው ትክክለኛው እውነት።
- ሲቪሊያን ሰዎች የሚኖሩበት አካባቢ ላይ ግጭት መተንኮስ አግባብ አይደለም። የተፈናቀለ ሰው የለም፣ የወጣ ሲቪልም የለም። በግጭቱ የተሳተፈ ሲቪል የለም። ከተማው ላይ ያችግር ሲፈጠር ሰዎች ቤታቸው ውስጥ ነበሩ።
- አሁን የገጠሩ ህዝብ ዘር እየዘራ ነው። የአካባቢው ኑሮም መደበኛው ነው። የተፈናቀለም የለም፤ እንደዛ የሚባል ስጋት የለም።
በሰከላ ተፈጸሟል የተባለውን ግድያ ሰምቶ እንደሆን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበለት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ፣ ሰሞኑን በአማራ ክልል ስላለው ጥቃት ሪፓርት ይፋ እንደሚያደርግ፣ የሰከላውም በዚሁ ሪፖርት ውስጥ ተካቶ ሊሆን እንደሚችል ገልጿል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Tecno #Camon30Pro5G
Tecno Camon 30 pro 5G እያንዳንዱ ፎቶ እና ቪድዮ ከፍተኛ ጥራት እንዲላበሱ የSony IMX890 ካሜራ ሴንሰር ገጥሞ ቀርቧል!
#Camon30Et #Camon30Pro5GEt #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
#Tigray
በትግራዩ ጦርነት ምክንያት በየቦታው የተቀበሩ እና የተጣሉ ተተኳሾች፣ ፈንጂዎች አሁንም በሰው ህይወት ላይ አደጋ ማድረሳቸው ቀጥሏል።
ዛሬ ዓርብ ግንቦት 16 / 2016 በተጣለ ተተኳሽ ባል እና ሚስት ህይወታቸው አልፏል።
አደጋው ያጋጠመው በትግራይ ክልል ፣ በማእከላዊ ዞን ቆላ ተምቤን ምረረ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ሲሆን በተተኳሹ ምክንያት የባል ህይወት ወድያው አልፏል።
የሟች ሚስት ወደ ሆስፒታል ብትወሰድም ህይወቷን ማዳን አልተቻለም።
የቆላ ተምቤን ወረዳ በአስከፊው እና በደም አፋሳሹ የትግራይ ጦርነት በርካታ ውግያ ያስተናገደ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በአከባቢው ላይ የተቀበሩና የተጣሉ ተተኳሾችና ፈንጂዎች የማፅዳ ጉዳይ ትኩረት ይሻል ብለዋል የአከባቢው ነዋሪዎች።
ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በኋላ በቆላ ተምቤን ወረዳ ብቻ በተጣሉ ተተኳሾችና ፈንጂዎች 103 ሰዎች ላይ የሞት የአካል መጉደል አደጋ መድረሱ በሚያዝያ ወር 2016 ዓ/ም የመጨረሻ ሳምንት ላይ መዘገባችን ይታወሳል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
#SmartHomeFurniture
ቤትዎን በስማርት ፈርኒቸር ያስውቡ !
ቤት ውስጥ ስንሆን አብዛኛውን ጊዜ የአይናችን ማረፊያ ቦታ ቲቪያችን ጋር ነው።
👉 የቲሌቪዥንዎትን ደህንነት ያረጋግጡ
👉 አነስተኛ ቦታን ተጠቅመውቤትዎን ያሳምሩ
👉እጅግ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ እና ብቃት ባላቸው ባለሙያዎቻችን ቤትዎን እናሳምርልዎታለን።
👉በነፃ ያሉበት አድርሰን እንገጥምሎታለን!!
👉ሌሎች አማራጮችን በቴሌግራም ቻናላችን ያገኛሉ http://t.me//smartomeff
ለማዘዝ በ 0911494931/21ይደውሉ!
አዲስ አበባ
#USA #kenya
የጎረቤታችን ሀገር ኬንያን ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶን ተቀብለው እያስተናገዱ ያሉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ኬንያን ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት መካከል የመጀመሪያዋ #የNATO_አባል_ያልሆነች (non-NATO) ዋና አጋር ሀገር እንደምታደርጋት ቃል መግባታቸው ተነግሯል።
@tikvahethiopia
#ጥቆማ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) የ " National Cyber Talent Challenge Program " ማዘጋጀቱን ገልጿል።
በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላቸው በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በሙሉ በዚህ ቻሌንጅ ላይ መሳተፍ ይችላሉ ተብሏል።
የታለንት መስኮች፦
- Cyber Security
- Cyber Development
- Embedded Systems
- Aerospace ናቸው።
ስልጠናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለአንድ ወር ይሰጣል።
አመልካቾች በዌብሳይት https://talent.Insa.gov.et በመግባት ከዛሬ ጀምሮ እስከ ግንቦት 30/ 2016 ዓ/ም መመዝገብ እንደሚችሉ ተገልጿል።
ለበለጠ መረጃ ደግሞ በ +251910974317 ወይም +251904311837 ላይ ስልክ መደወል ይቻላል።
@Tikvahethiopia
#Kenya #USA
የጎረቤት ኬንያ ፕሬዜዳንት በአሜሪካ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።
እ.ኤ.አ ከ2008 ወዲህ ወይም ከ16 ዓመት በኃላ ነው ዋይት ሃውስ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ መሪ በዚህ ደረጃ ተቀብሎ እያስተናገደ የሚገኘው።
አሜሪካን እየጎበኙ የሚገኙት ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ከፍ ያለ አቀባበል እና ከፍተኛ የቀድሞና የአሁን ባለስልጣናት በተገኙበት ልዩ እራት ግብዣ እንደተደረገላቸው ታውቋል።
ከፕሬዜዳንት ጆ ባይደንና ከሌሎች ባለልሰጣናት ጋር ተገናኝተው የሁለትዮሽ ውይይት ያደረጉም ሲሆን ሁነኛ ስምምነቶችም ከአሜሪካ መንግሥት ጋር መፈራረማቸው ተሰምቷል።
ሩቶ ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ባራክ ኦባማ ጋርም ተገናኝነትው መክረዋል።
በሌላ በኩል ፥ ኬንያ የሀገሪቱን የጸጥታ ስራዎች እና የሰላም ማስከበር ተልእኮዎቿን ለማሳደግ 16 በአሜሪካ የተሰሩ እጅግ ዘመናዊ ሄሊኮፕተሮች ልትቀበል እንደሆነ " ሲትዝን ቲቪ " ዘግቧል።
ይህ የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በዋሽንግተን ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ለኬንያ ካበረከቱት መልካም ነገሮች አንዱ ነው ተብሏል።
ሂሊኮፕተሮቹ እ.ኤ.አ ከ2024 እስከ 2025 መጨረሻ ናይሮቢ ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ዋይት ሀውስ አስታውቋል።
ከዚህ በተጨማሪ ኬንያ በመስከረም ወር 150 " M1117 " የታጠቁ እጅግ ዘመናዊ የደህንነት ተሽከርካሪዎችን ትቀበላለች።
More ➡️ @thiqahEth
@tikvahethiopia
#Abyssinia_Bank
ዕሴቶቻችሁንና የሸሪዓን መርሆች በማክበር የሚያገለግላችሁ አቢሲንያ አሚን ለእርሰዎ የሚስማሙ በርካታ አገልግሎቶችን ይዟል።
አቢሲንያ አሚን ዕሴትዎን ያከበረ!
#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia
#Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
" ሞቶ የመገኘቱ ጉዳይ እንቆቅልሽ ነው የሆነብን " - የጋዜጠኛው ጓደኞችና የስራ ባልደረቦች
የደቡብ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት የሆሳዕና ቅርንጫፍ ጋዜጠኛ የሆነው አብይ አበራ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ስርአተ ቀብሩም በትዉልድ መንደሩ በአንጋጫ ወረዳ ፉነሙራ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።
ወጣቱ ጋዜጠኛ አብይ ከ2010 ዓ/ም ጀምሮ በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ተቀጥሮ ሲሰራ በጠንካራ አቋሙና በታታሪነቱ የሚታወቅ ቢሆንም ከሰሞኑ በቤቱ ውስጥ ሞቶ መገኘቱን ተከትሎ በቤተሰቦቹ በጓደኞቹ እና በስራ ባልደረቦቹ ላይ ታላቅ ድንጋጤ የፈጠረ ጉዳይ ሆኗል።
በጋዜጠኝነት ስራ ላይ የሚያዉቁት ጓደኞቹ ስለታላላቅ ህልሞቹ የሚናገሩለት አብይ ትናንት ጠዋት ሞቶ የመገኘቱ ጉዳይ እንቆቅልሽ እንደሆነባቸዉ ገልጸዋል።
ለቲኪቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ የጋዜጠኛው ጓደኞች እና የስራ ባልደረቦች ፥ " አብይ ራስን የማጥፋት ተግባር ይፈጽማል ብለን ፈጽሞ አናስብም " ብለዋል።
ከጋዜጠኝነት ስራው ባለፈ ራሱን ለመደገፍ ማንኛዉንም ስራ በመስራቱ ለብዙዎች አርአያ መሆኑን የሚናገሩት ባልደረቦቹ በቅርቡ የራሱን ምግብ ቤት ከፍቶ በሰዎች ሲያሰራ እንደነበር አስታውሰዋል።
ላመነበት ጉዳይም ወደኋላ የማይል ጠንካራ አቋም ያለዉ ሰው መሆኑን ተከትሎ " የአሟሟቱ ጉዳይ እንቆቅልሽ ሆኖብናል " ብለዋል።
ይህን ጉዳይ ይዘን ያነጋገርናቸዉ የጸጥታ አካላት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ምላሽ ምንም ፤ ሁኔታዉን ለማጣራት አስከሬኑ በተገኘ ቅጽበት ወደ ወራቤ ሪፈራል ሆስፒታል ለምርመራ መላኩን ገልጸዋል።
ፖሊስ ፤ ጋዜጠኛው ተከራይቶ በሚኖርበት ቤት ሞቶ የተገኘ መሆኑን በመጥቀስ ከአስከሬን ምርመራዉ በተጨማሪም ሌሎች የማጣራት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንና የሚገኘዉን ውጤት እንደሚሳውቅ ተናግሯል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
#እንድታውቁት #አዲስአበባ
ዛሬ ከቀኑ 11:00 ጀምሮ ' ከፖሊስ ስራ ' ጋር በተያያዘ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ፕሮግራም አለ።
ይህ ተከትሎ መንገዶች ተዘግተዋል።
የተዘጉት መንገዶች ፦
- ከልደታ በላይኛው መንገድ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
- ከአፍሪካ ህብረት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
- ከጠማማ ፎቅ በንግድ ምክር ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
- ከገነት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
- ከሰንጋ ተራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
- ከዲአፍሪክ ሆቴል ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
- ከቡናና ሻይ በላይኛው መንገድ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ሲሆኑ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ ነው የአዲስ አበባ ፖሊስ ያሳወቀው።
በመሆኑም ፦
° በስራ ላይ ምትገኙ አገልግሎት የምትሰጡ አሽከርካሪዎች ፣
° ወደ ስራ እየገባችሁ ያላችሁ ሰራተኞች
° ከስራ ወጥታችሁ ወደ የቤታችሁ እየሄዳችሁ ያላችሁ ነዋሪዎች ይህን መረጃ ተመልክታችሁ አማራጭ መንገድ ተጠቀሙ።
#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba
@tikvahethiopia
#DStvEthiopia
🏆የዋንጫውን አሸናፊ ይገምቱ🏆
🔥 ማንቼስተሮቹ ለዚህ ዓመት ለመጨረሻ ጊዜ ለኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫ ፍፃሜ ይገናኛሉ!
🤔 የእናንተን ግምት ከታች አጋሩን!
👉 ጨዋታውን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ለመከታተል ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2
#PremierLeagueOnDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
#Update
የተማሪ ደራርቱ ገዳይ የ18 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈርዶበታል።
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችውን ደራርቱ ለሜሳን አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ በጩቤ ሶስት ቦታ በጀርባዋ ላይ በመውጋት የግድያ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ18 አመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ ፖሊስ አስታውቋል።
ረቡዕ ግንቦት 9 ቀን 2016 ዓ/ም በግምት ከጧቱ 2፡45 ሰዓት አከባቢ ተከሳሽ አቶ ዩሀንስ መርጋ ኢተቻ የተባለው ግለሰብ የሴት ጓደኛው የሆነችው ተማሪ ደራርቱ ለሜሳ ላይ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ የግድያ ወንጀል በመፈፀሙ ተከሳሽ በፈፀመው ሰው በመግደል ወንጀል ተከሷል።
መርማሪ ፖሊስና ዐቃቢ ህግ በጋራ ተጠርጣሪው ላይ ክስ መስርተው ምርመራ በማጣራት የወንጀል ድርጊቱን የሚያስረዱ የሰው ማስረጃና የህክምና ማስረጃ በማስደገፍ ለሚመለከተው ፍ/ቤት ልከዋል።
የክስ መዝገቡ የደረሰው የአሶሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት መዝገቡን ሲመርምር ከቆየ በኃላ ተከሳሹ በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ በመሆኑ በቀን 15/9/2016 ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት #በ18_ዓመት_ጽኑ_እስራት እንዲቀጣ ውስኗል።
መረጃው የአሶሳ ከተማ ወረዳ አንድ ፖሊስ ጽ/ቤት ነው።
#AssosaUniversity
@tikvahethiopia
#ወጋገን_ባንክ
ወጋገን ባንክ ባዘጋጀው የጥያቄ እና መልስ ውድድር ጠቀም ባሉ አጓጊ ሽልማቶች አሸናፊዎችን ማንበሻበሹን አሁንም ቀጥሏል !!
ታዲያ እርስዎስ ምን ይጠብቃሉ ?
አሁኑኑ ከስር የተቀመጡትን የወጋገን ባንክ ይፋዊ የቴሌግራም እና የፌስቡክ ገፅ ሊንኮች ተጭነው በመቀላቀል እና ሌሎችም እንዲቀላቀሉ በመጋበዝ ፣ ጥያቄዎችን አስቀድመው እየመለሱ አጓጊ ሽልማቶችን የራስዎ ያድርጉ !
በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጫኑ
| Facebook | Telegram
ደንብ እና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው
/channel/WegagenBanksc
#AmanuelMentalHospital
ወደ አማኑኤል ሆስፒታል የሚገቡ የአዕምሮ ህሙማን ቁጥር እየጨመረ ነው።
ሆስፒታሉ አዳዲስ ታካሚዎች እየጨመሩ መጥተዋል ብሏል።
አማኑኤል አዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ምን አለ ?
- ከሚመጡ ታካሚዎች ከሴቶች በበለጠ ወንዶች ትልቁን ቦታ ይይዛሉ።
- ከሆስፒታሉ ደህና ሆነው ወጥተው ከወጡም በኋላ ያለው ሁኔታ የተስተካከለ ስለማይሆንላቸው ተመልሶ የማገርሸት እና ተመልሶ የመምጣት ነገር እየጨመረ ይገኛል።
- አንድ ክፍተት እየፈጠረ ያለው የተጠኑ ጥናቶች ባለመኖራቸው መንግስትም ትኩረት እየሰጠው ባለመሆኑ ነው።
- ወደ ሆስፒታል የሚመጡ አብዛኞቹ ታካሚዎች ፦
° #ድባቴ ፣
° #ባይፖላር ፣
° #ከባድ_የአእምሮ_ህመም
° #በአደንዛዥ_እፅ_ሱስ ሳቢያ የሚመጣ የአዕምሮ ህመም የተጠቁ ናቸው።
- በሆስፒታሉ ከሚታከሙ ታካሚዎቸ ውስጥ በብዛት ከ20-40 አመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙት ቁጥራቸው ከፍ ይላል።
- የሆስፒታሉ ግንባታ በጣም የቆየና ደረጃውን የጠበቀ ባለመሆኑ በተደጋጋሚ የአልጋ እጥረቶች እየገጠሙ ነው።
- ለሚፈጠሩት ክፍተቶች እንደማስተንፈሻ እንዲሆን በጤና ሚኒስቴር አማካኝነት በሆስፒታሉ ግቢ ሌላ ህንፃ ለመገንባት መሰረተ ድንጋይ ተጥሏል። በአንድ አመት ግዜ ውስጥ ያልቃል ተብሎ እቅድ ተይዟል።
- የአእምሮ ህመም ታክሞ መዳን የሚችል በመሆኑ ህብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ ሊኖረው ይገባል።
የዚህ መረጃ ባለቤት ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ ነው።
@tikvahethiopia
ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር
Yonatan BT Furniture
የዘመናዊነት ተምሳሌት!
አድራሻችን፦
1. ዊንጌት አደባባዩን ተሻግሮ: +251 995 27 2727
2. ፒያሳ እሪ በከንቱ : +251 957 86 8686
3. ሲ ኤም ሲ አደባባዩን አለፍ ብሎ: +251 993 82 8282
👉 Telegram: /channel/yonatanbt_furniture
👉 Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100087238034736
👉 TikTok: yonatanbtfurniture" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@yonatanbtfurniture
👉 Instagram: https://www.instagram.com/yonatanbtfurniture/