#MPESASafaricom
💫ከዳር እስከ ዳር አስተማማኙን ኔትወርካችንን እያሰፋን ወደ እናንተ እየቀረብን ነው!🙌👏ከአስተማማኙ ኔትወርካችን ጋር አሁንም በአብሮነት ወደፊት!
አስተማማኙን ኔትወርክ ዛሬውኑ እንቀላቀል!
የቴሌግራም ቦታችንን /channel/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!
#SafaricomEthiopia #1Wedefit
#Furtheraheadtogether
#ዓለምአቀፍ
የሄይቲው ጠቅላይ ሚኒስትር በ6 ወራቸው ከስልጣናቸው ተባበሩ።
የሄይቲ ጠ/ሚ ጌሪ ኮኒል በ6 ወራቸው ከሥልጣን መባረራቸውን ሀገሪቱን የሚያስተዳድረው ም/ቤት አስታውቋል።
የምክር ቤቱ ዘጠኝ አባላት የፈረሙት ትዕዛዝ እንደሚያሳየው ከሥልጣን በተባረሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ምትክ ነጋዴ የሆኑትና የቀድሞ የሄይቲ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል የነበሩት አሊክስ ዲዲዬን ሾሟል።
የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ባልደረባ የነበሩት ኮኒል ወደ ሥልጣን የመጡት ሀገሪቱን ከታጠቁ ወሮበሎች እንዲታደጉ ነበር።
ሰውዬው በሄይቲ ምርጫ እስኪደረግ ድረስ ሥልጣን ላይ ይቆያሉ ተብሎ ቢጠበቅም በግማሽ ዓመት ከመንበራቸው ተባረዋል።
ሄይቲ ከአውሮፓውያኑ 2016 በኋላ ምርጫ አካሂዳ አታውቅም።
ሄይቲ በአሁኑ ወቅት ፕሬዝደንትም ሆነ ፓርላማ የላትም።
በሀገሪቱ ሕገ-መንግሥት መሠረት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከሥልጣን ማንሳት የሚችለው የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ብቻ ነው።
ኮኒል ሥልጣን የያዙት ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር መጨረሻ ነበር።
እንደ ተመድ መረጃ ፤ በሄይቲ ካለፈው ጥር ጀምሮ በወሮበሎች አመፅ ምክንያት 3600 ሰዎች ሲገደሉ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑት መኖሪያቸውን ጥለው ተሰደዋል።
በታጠቁ ወሮበሎች እየታመሰች ያለችው ሄይቲ በዓለማችን እጅግ ደሀ ከሚባሉ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን እንደ ተመድ መረጃ ሁለት ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ከሀገሪቱ ሕዝብ ግማሽ ያክሉ በቂ ምግብ የለውም።
መረጃው የቢቢሲ ነው።
@tikvahethiopia
ነጻ ትምህርት ☑️
#LG_KOICA_Hope_TVET_College
LG-KOICA Hope የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቲቪቲ መግቢያ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ተማሪዎች በICT እና Electronics የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን #በነጻ ማስተማር ይፈልጋል።
ኮሌጁ በዚህ ዙር እስከ 150 ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የተዘጋጀ ሲሆን የሀገር ዉስጥና የዉጭ ሀገር የሥራ ዕድል አማራጮችም አካቷል።
ከዚህ በተጨማሪ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸውና መስፈርቱን ለሚያማሉ የተመረጡ ተማሪዎች የምግብ፣ የትራንስፖርት እና ሌሎች ወጪዎችን የሚሸፍን ይሆናል።
የማመልከቻ ጊዜና ቦታ : ከጥቅምት 11 - ህዳር 13 2017 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 - 11፡00 ሰዓት ሰሚት ኮንዶሚኒየም 3ኛ በር
ለተጨማሪ መረጃ - 011-6-67-75-64 011-6-66-18-29
#ትግራይ
" ቡድኑ ለስልጣን ሲል ማንኛውም ዓይነት ጥፋት ከመፈፀም ወደ ኋላ እንደማይል በተደጋጋሚ እየታየ ነው " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር
የትግራይ ጊዚያዊ አስተደደር ዛሬ ህዳር 1/2017 ዓ.ም የፅሁፍ መግለጫ አውጥቷል።
በዚህም " በአንደኛው ገፅ ልዩነቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተካረሩ ሄደዋል በሌላኛው ገፅ ደግሞ የጊዚያዊ አስተዳደሩ እቅዶች የማደናቀፍ እና የማዳከም የተቀናጀ ዘመቻ ሲደረግ ቆይቷል አሁንም ቀጥሏል " ሲል ገልጿል።
በተለይም ከነሀሴ 2016 ዓ/ም ጀምሮ በህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እና በግልፅ የታየው ልዪነት መሰረታዊ የህዝብ ጥያቄያዎች በተቀናጀ መልኩ እንዳይፈቱ ከባድ እንቅፋት ፈጥረዋል ብሏል።
የጊዚያዊ አስተዳደሩን እቅዶች በተቀናጀ መልኩ የሚያደናቅፈው ህጋዊ ያልሆነ ጉባኤ ያካሄደው ቡድን ከፍተኛ አመራር ነው ያለው ጊዜያዊ አስተዳደሩ " ደርጊቱ ህዝቡ ተስፋ እንዲቆርጥ ሆነ ተብሎ የሚደረግ ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው " ሲል አውግዞታል።
" የቡድኑ ተግባር የጊዚያዊ አስተዳደሩ እቅዶች ከማደናቀፍ በዘለለ ይፋዊ ወደ ሆነ የመንግስት ግልበጣ እና ስርዓት አልበኝነት ማስስፋፋት ከፍ ብሏል " ሲል ከሷል።
ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ በመቐለ ከተማ ፣ በሰሜናዊ እና ማእከላዊ ዞኖች የታዩት የመንግስት ግልበጣና ስርዓት አልበኝነት ምልክቶች የቡድኑ ህግ አልበኝነት ማሳያ ናቸው ሲል አስረድቷል።
" ቡድኑ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ የመንግስት የአመራር እርከን ከላይ እስከ ታች ለመቆጣጠር ጨርሰናል " የሚል የማደናገሪያ እቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ገልጿል።
" የቡድኑ ማደናገሪያ በአጉል ተስፋ ራስን ከማታለል የዘለለ ቅንጣት ሀቅ እንደሌለው መታወቅ አለበት " ያለው አስተዳደሩ " ቡድኑ ለስልጣን ሲል ማንኛውም ዓይነት ጥፋት ከመፈፀም ወደ ኋላ እንደማይል በተደጋጋሚ እየታየ መጥቷል " ሲል ገልጿል።
" ' ከሰራዊት አመራሮች ተግባብተናል ' በሚል እየነዛው ያለው ማደናገሪያ ለጠባብ የስልጣን ፍላጎቱ ማሟያ ነው " ብሏል።
" በትግራይ ህልውና የቆመው ሃይል ከመጠቀም እንደማይመለስም ማሳያ ነው " ሲል አክሏል።
" ቡድን " ሲል የገለፀው አካል በሃይማኖት አባቶች የተጀመረው ነገሮች በውይይት የመፍታት ሂደት እንደማይቀበል በአደባባይ ገልፀዋልም ሲል ጊዜያዊ አስተዳደሩ ገልጿል።
የጊዚያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮቼ አሁንም ነገሮች በሰከነ አኳሃን በሰላም እና በውይይት ለመፍታት ዝግጁ ናቸው ብሏል።
የጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራሮች የጀመሩት የሰላምና የውይይት ጥረት እንዲሳካ ሁሉም ከጎኑ እንዲሰለፍ ጥሪ አቅርቧል።
በቅርቡ የትግራይ ሃይማኖት አባቶች የህወሓት አመራሮች በመካከላቸው ያለውን ልዩነት በንግግር እንዲፈቱ ለማድረግ ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል እና አቶ ጌታቸው ረዳ እና አመራሮቻቸውን በአካል አገናኝተው ነበር።
ከዚህ መድረክ በኃላ በወጡ የተለያዩ ፎቶዎች በርካቶች " ችግሩ በንግግር ሊፈታ ነው " በሚል ብዙ ተስፋ አድርገው ነበር።
በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ትናንት በትግራይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት አባቶች አማካኝነት ሁለቱ የህወሓት ቡድኖች ያደረጉት የፊት ለፊት ግንኙነት ከብፁአን የሃይማኖት አባቶች ተግሳፅና ምክር የዘለለ ውጤት እንደሌለው ተናገረ።
የደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት ዛሬ ምሽት አጭር መግለጫ አውጥቷል።
አንዳንድ ሚዲያዎች ደግሞ " ለእርቅና ሽምግልና ተስማምተዋል " የሚል መረጃ እስከማሰራጨትም ደርሰው ነበር።
በኃላ በዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ፥ " በብፁአን አበው የተዘጋጀው ፊት ለፊት የማገናኘት መርሃ ግብር ልዩነቶች በህግ ፣ ተቋማዊ ስርዓት ማእከል በማድረግ ህዝብን ከአደጋ መታደግ በሚችል የሰለጠነ ሰላማዊ መንገድ ችግሮቻችን እንድንፈታ ያለመ የምክርና የተግሳፅ መድረክ ነበር " ሲል አሳውዋል።
" ብፁአን አበው ላቀረቡልን ምክርና ተግሳፅ ያለንን ክብርና ድጋፍ ገልፀናል ፤ ከዚህ በዘለለ የተለያዩ አካላትና ሚዲያዎች ' ለእርቅ እና ሽምግልና ተስማምተዋል ' በማለት የሚያሰራጩት መረጃ ከእውነት የራቀ ነው " ሲል ነበር የገለጸው።
በቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ።
#TikvahEthiopiaFamilyAA #Tigray #Mekelle
@tikvahethiopia
#PremierLeagueallonDStv
🔥ከባድ ትንቅንቅ የማያጣው የለንደን ደርቢ
ቼልሲ ከ አርሰናል ጋር! ቼልሲ በሜዳው የለንደኑን ጎረቤት አርሰናልን ዛሬ ከምሽቱ 1፡30 ይገናኛሉ!
ጥሩ አቋም ላይ ያልው ቼልሲ በጉዳት ምክንያት ውጤት ያጣውን አርሰናልን ነጥብ ማስጣል ይችላል?
🏆 ማን ይሆን 3 ነጥብ ማሸነፍ የሚችለው!
ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et
ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh
#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
#AddisAbaba
" አሁንም አንዳንድ የቤት ባለቤቶች ወደ ቤታቸው ለመግባት ምንም እንቅስቃሴ እያደረጉ አይደለም ፤ ይህ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ነው " - ኮርፖሬሽኑ
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በተለያዩ ጊዜያት በእጣ እና በጨረታ ተላልፈው ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች አስመልክቶ እስከ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ድረስ የቤት ባለቤቶቹ ወደ ቤታቸው የማይገቡ ከሆነ በህግ አግባብ ውል የሚቋረጥ መሆኑን ማስጠንቀቁ ይታወሳል፡፡
በዚህም በርካታ የቤት ባለቤቶች ወደ ቤታቸው የገቡ ወይም ለመግባት ዕድሳት ላይ ስለመሆናቸው አደረኩት ባለው የአካል ምልከታ የተገነዘበ መሆኑን ገልጿል።
አሁንም ግን አንዳንድ የቤት ባለቤቶች ወደ ቤታቸው ለመግባት ምንም እንቅስቃሴ ያላደረጉ ፤ ነዋሪ ያልገባባቸው ቤቶች እንዳሉ መለየቱን አመክክቷል።
በኮርፖሬሽኑ የቀረበውን ጥሪ ተቀብለው ቤታቸውን አድሰው ለመግባት የጊዜ እጥረት ላጋጠማቸው አንዳንድ የቤት ባለቤቶች የተሰጠውን የጊዜ ገደብ አራዝሟል።
እስካሁን ድረስ ወደቤታቸው ለመግባት ምንም ይነት እንቅስቃሴ ያላደረጉ እንዲሁም ቤት ለማደስ የጊዜ እጥረት ያጋጠማቸው የቤት ባለቤቶች እስከ ህዳር 30 2017 ዓ.ም ወደ ቤታቸውን እንዲገቡ ለመጨራሻ ጊዜ አስጠንቅቋል።
በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማይገቡ ነዋሪዎች የሽያጭ ውላቸው የሚቋረጥ እና በቤታቸው ውስጥ ለሚፈጸም ማንኛውም ህገወጥ ድርጊት ተጠያቂ የሚሆኑ መሆኑን ኮርፖሬሽኑ አሳስቧል።
ከዘህ ቀደም ኮርፖሬሽኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥቶት በነበረው ማብራሪያ ፥ ማስታወቂያው የወጣበት ዋናው ምክንያት ሰዎች ‘ ተቸገርን፣ ክፍት በሆኑ ቤቶች ወንጀል እየተሰራ ነው፣ እየተዘረፍን ነው፣ ሴቶች እየተደፈሩብን ነው፣ የጸጥታ ስጋትም እየሆኑብን ’ ብለው ቅሬታ ስላቀረቡ እንደሆነ መግለጹ ይታወሳል።
ቤቶቹ ቼክ ሲደረጉ ደግሞ እጣ ወጥቶባቸዋል፤ ውል ተፈጽሞባቸዋል፣ ግን ሰው አልገባባቸውም፡፡
" ስለዚህ ነዋሪው ተቸግሯል፡፡ የጸጥታ ኃይሉም ጥያቄ እያነሳ ነው " ብሎም ነበር።
" የቤት ባለቤቶች ቤታችሁን አድሳችሁ ግቡ " የተባለውም የግድ እራሳቸውን እንዳይሰለ አስረድቶ ነበር።
" ቢፈልጉ አድሶ ማከራየት መብት ነው፡፡ የራሳቸው ቤት እስከሆነ ድረስ፡፡ ግን ዞሮ ዞሮ ሰው በቤቱ ይኑርበት ነው የኛ ጥያቄ፡፡ አካራይ አታከራይ የኛ መልዕክት ሊሆን አይገባም፡፡ ግን ቤቱን ኦውን ያድረጉ " ነው የሚል ማብራሪያ ነበር ኮርፖሬሽኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጠው።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Amhara
🔴 “ ስለፓለቲካ ምንም የማያውቁ፣ ሮጠው የማያመልጡና ሰርተው የማይበሉ አረጋዊያን ላይ መድፍ መወርወር ሊወገዝ ይገባል ” - ነዋሪዎች
🔵 “ ፈቃደኝነት እንዲኖራቸው የሚፈለጉ ኃይሎች ቢያንስ ድርድር እንደሚፈልጉ በመግለጫ የተደገፈ ሀሳብ ቢሰጡ ህዝቡ ከስቃይ እፎይ ይል ነበር ” - ካውንስሉ
ከአንድ ዓመት በላይ ባስቆጠረውና ልጓም ባጣው በአማራ ክልል በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ መካከል በሚደረገው የተኩስ ልውውጥ ሳቢያ የንጹሐ ስቃይ ተባብሶ መቀጠሉን አሁንም የገፈቱ ቀማሾችና የዓይን እማኞች ገልጸውልናል።
ንጻሃን ዜጎች እየተጎዱ ያሉት በምድር በሚደረግ የተኩስ ልውውጥ ከዚህም አለፍ ሲል በአየር ላይ በሚካሄድ ጥቃትም ጭምር ነው።
ሰሞኑን በክልሉ በከባድ መሳሪያ ጨምር የታገዘ የተኩስ ልውውጥ ከተካሄደባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ በሆነው አዊ ዞን በንጹሐን ላይ ከባድ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመት መድረሱ ታውቋል፡፡
በዞኑ ጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ቲሊሊ ከተማ ዙሪያ በ ‘ፋኖ’ እና መከላከያ መካከል የሚደረገው የተኩስ ልውውጥ በንጹሐን ላይ የከፋ ጉዳት እየደረሰ በመሆኑ ዓለም አቀፍ ተቋማት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ የተጎጂ ቤተሰቦችና ነዋሪዎች በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ተማጽነዋል።
ከቀናት በፊት ከእንጅባራ አቅጣጫ ተተኩሶ ቲሊሊ ከተማ ወጣ ብሎ ከአንድ የገጠር ቤት ላይ ያረፈ መድፍ በቤተሰብ አባላት ላይ ከባድ የአካል ጉዳት፣ በንብረት ላይም የከፋ ውድመት ማድረሱን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
“ ሰሞኑን ወደ ቲሊሊ መድፍ ተወርውሮ በንጹሐን ቤት ላይ አርፏል። አንዲት ሴት እግሯ ተቆርጧል። ህጻን ልጅም ተጎድታለች። ስድስት ከብቶች ተገድለዋል። ቤቱ ሙሉ ለሙሉ ወድሟል ” ሲሉ አንድ የዓይን እማኝ ገልጸዋል።
ሌላኛው የተጎጂ ቤተሰብ፣ “ ከቲሊሊ ከተማ ወጣ ብሎ ነው የተወረወረው መድፍ ጉዳት ያደረሰው ” ሲሉ ተናግረዋል።
“ በወቅቱ በመከላከያና በፋኖ መካከል የተኩስ ልውውጥ ተደርጎ ነበር። መድፉ የተተኮሰው ግን ከእንጅባራ አቅጣጫ ነው። እሳቱ አልበርድ ብሎ የሰፈር ሰው በልቅሶ፣ በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ ነው ያለው ” ብለዋል።
“ የሞተ የለም። ከሁለቱ ሰዎች ውጪ ሌላ የተጎዳም የለም። ከብቶች ግን ሁሉም አልቀዋል ” ነው ያሉት።
ስለፓለቲካ ምንም የማያውቁ፣ ሮጠው የማያመልጡና ሰርተው የማይበሉ አረጋዊያን ላይ መድፍ መወርወር ሊወገዝ ይገባል ሲሉም ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ድርጊቱ የተፈጸመው ማክሰኞ ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 7: 30 ገደማ መሆኑን አስረድተዋል።
በአካባቢው ባለው ሁኔታ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ንጹሐንን ይደበድባሉ ሲሉም ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
" ያለው ድባብም የሚመች አይደለም " ሲሉም ገልጸዋል።
በምዕራብና ሰሜን ጎጃም፣ በጎንደር፣ በሰሜን ወሎ የተለያዩ አከባቢዎች ሰሞኑን ተፈጸመ በተባለ በድሮንና ከባድ መሳሪያ ጭምር የታገዘ የተኩስ ልውውጥ ቁጥራቸው ገና በውል የማይታወቅ ንጹሐን ሰዎች ግድያና የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ነዋሪዎች በሀዘን ስሜት አስረድተዋል።
የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ‘ የፋኖ ኃይሎችን ትደግፋላችሁ ’ በማለት ንጹሃን ላይ ከሚያደርሱት ግድያና ድብደባ በተጨማሪ ፥ ታጣቂዎችም ‘ መንግስትን ትደፋላችሁ ’ በሚል በንጹሐን ላይ ግድያ መፈጸማቸው ከተጎጂ ቤተሰቦች የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በክልሉ ባለው የጸጥታ ችግር የንጹሐን ግድያ ፣ የአካል ጉዳት ፣ እገታ ፣ የትምህርትና የግብርና ሥራ መስተጓጎል እንዳስከተለ ይታወቃል ፤ እየደረሰ ያለው ዘርፈ ብዙ ጉዳትም ሊቀለበስ አልቻለም። ሁለቱንም ተዋጊ ኃይሎች ለድርድር እንዲቀራረቡ ከማድረግ አንፃር ተስፋ ይኖር ይሆን ? ሲል የአማራ ክልል የሰላም ካውንስልን ጠይቋል።
ካውንስሉ ምን ምላሽ ሰጠ ?
" በሁለቱም ወገኖች በኩል ድርድርና ምክክር መደረግ አለበት ብለን ነው የተነሳበውና ይሄንኑ ወደ ተግባር ለማሸጋገር በመንግስት በኩል ፈቃደኝነት እንዳለ ገልጸናል፡፡
ፈቃደኝነት እንዲኖራቸው የሚፈለጉ ኃይሎች ቢያንስ ድርድር እንደሚፈልጉ በመግለጫ የተደገፈ ሀሳብ ቢሰጡ ህዝቡ ከስቃይ እፎይ ይል ነበር፡፡
' የገበያ ግርግር ለሌባ ያመቻል ' እንዲሉ በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት ሌሎች አክተሮችም ስላሉ ግድያው፣ ሌብነቱ፣ እገታው ከዚሁ የመነጨ ነው፡፡
የእርስ በእርስ ጦርነት ከባድ ችግር ነው የሚያስከትከለው፡፡ ወደፊትም እንዲህ አይነቱ ነገር እጅግ በጣም ዘግናኝ የሆነ መጥፎ ነገር ሁሉ ያመጣል።
ይሄ እንዳይመጣ ወደ ድርድር እንዲመጡ ነው ለሁሉም አካላት ጥሪ ያደረግነው፡፡ የሆነው ሆነና እንደ ጠቅላላ ጉባዔ የምንለው ነገር አለና ያኔ ለሁሉም ጥያቄዎች ዝርዝር ማብራሪያ እንሰጣለን፡፡
ይህንኑ ጉዳይ በሚመለከት ሰሞኑን ስብሰብ እንደርጋለን፡፡ የሰላም ካውንስሉ የራሱን ጠቅላላ ጉባዔ ጠርቷል፡፡ ከእሁድ በኋላ ጠቅላላ መግለጫ የምንሰጥ ነው የሚሆነው በዚያን ጊዜ ጠቅላላ ህዝቡ እንዲያውቀው የምናደርገው ጉዳይ አለ " ብሏል።
(የካውንስሉን የጉባዔ ውጤትና ለሚቀርቡት እሮሮዎች የተሻለ የሚለውን ጉዳይ በተመለከተ በቀጣይ መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል)
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#MPESASafaricom
ይህን የመሰለ ቅናሽ ሲገኝ የምን አይን ማሸት፤ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ግቢ ጉዞ የሃገር ዉስጥ በረራ ትኬታችንን በM-PESA ስንቆርጥ 5% ተመላሽ በልዩ ሁኔታ ተዘጋጅቶ ይጠብቀናል ፤ እየሄዱ ማፈስ ነው እንግዲህ!
የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉/channel/Safaricom_Ethiopia_PLC
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#FurtherAheadTogether
#ጥቆማ #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በTRAINEE CABIN CREW ፣ በSENIOR ACCOUNTANT I እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ማስታወቂያ አውጥቷል።
ለTRAINEE CABIN CREW በኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ቢያንስ (ዝቅተኛው) 200 ነጥብ ያስመዘገበ ለማመልከት ብቁ ነው።
የዕድሜ ገደቡ ከ19 እስከ 30 ዓመት ነው።
ቁመት ቢያንስ 1.58 ሜትር እና 212 ሴ.ሜ የሆነ ክንድ ለሴት እንዲሁም ለወንድ ቢያንስ 1.70 ሜትር ቁመት መሆን አለበት።
የምዝገባ ጊዜው ከህዳር 08/2017 ዓ/ም እስከ ህዳር 12/2017 ዓ/ም ነው።
ምዝገባው ፦
- በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (አዳማ)
- አዲስ አበባ (በኦንላይን ልክ ማመልከቻው ሲከፈት ይፋ ይደረጋል)
- አምቦ ዩኒቨርሲቲ (አምቦ)
- አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ (አርባ ምንጭ)
- አሶሳ ዩኒቨርሲቲ (አሶሳ)
- ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (ባህር ዳር)
- ወሎ ዩኒቨርሲቲ (ደሴ)
- ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ (ድሬዳዋ)
- ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ( ጋምቤላ)
- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ (ጎንደር)
- ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ (ሀዋሳ)
- ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ (ጅግጅጋ)
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ (ጅማ)
- መቐለ ዩኒቨርሲቲ (መቐለ)
- ወለጋ ዩኒቨርሲቲ (ነቀምቴ)
- መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ (ሮቤ)
- ሰመራ ዩኒቨርሲቲ (ሰመራ)
- ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ (ወልቂጤ) ይከናወናል።
ተጨማሪ መረጃዎች፣ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፣ ዝርዝር ጉዳዮች እንዲሁም ሌሎችም የወጡ ማስታወቂያዎች በዚህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ድረገጽ ላይ ሰፍሮ ይገኛል ይመልከቱ 👇
https://corporate.ethiopianairlines.com/AboutEthiopian/careers/vacancies
@tikvahethiopia
#መቐለ
መቐለ ውስጥ ባለፉት 3 ወራት ብቻ 1,088 ወንጀሎች መፈፀማቸው የመቐለ ከተማ ፓሊስ አስታውቋል።
ከተፈፀሙት ወንጀሎች መካከል ፦
➡️ 16 የግድያ
➡️ 47 የግድያ ሙከራ
➡️ 16 የሴቶች አስገድዶ መድፈር ይገኙበታል።
በሩብ አመቱ የተመዘገበው የወንጀል ተግባር አሳሳቢና ህዝብ ያሳተፈ የመከላከል ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመላካች ነው ብሏል።
ፖሊስ የወንጀል ተግባራቱ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ 3 ወራት ሲነፃፃር የቀነሰ ቢሆንም አሁንም ቢሆን ህዝቡ ከወንጀልና የወንጀል ስጋት ነፃ እንዳልሆነ አመላካች ነው ሲል አሳውቋል።
@tikvahethiopia
#Update
" ጥያቄያችን ፖለቲካዊ ይዘት እንዲኖረው ተደርጓል " - ቅሬታ አቅራቢ የጤና ባለሙያዎች
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ የሚሰሩ ከ80 በላይ የጤና ባለሞያዎች ለ6 ወራት የሰሩበት የተጠራቀመ የዲዩቲ ክፍያ ስላልተከፈላቸው ከ12/02/17 ዓ/ም ጀምሮ ስራ ማቆማቸውን መግለጻችን ይታወሳል።
የሆስፒታሉ ሰራተኞች ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ለስድስት ቀናት ማለትም 12/02/17 እስከ 18/02/17 ድረስ ስራ ሳይገቡ ቆይተው ማክሰኞ በ19/02/2017 ዓ.ም ከአካባቢው ሽማግሌዎች ጋር የወረዳው ባለሥልጣናት በተገኙበት በተደረገ ውይይት ሽማግሌዎች ከወረዳው ሃላፊዎች ጋር ለማደራደር በመስማማታቸው ወደ ስራ ገበታቸው ተመልሰዋል።
ይሁን እንጂ ከስብሰባው ማብቃት በኋላ " አድማውን አስተባብራቹሃል " በሚል 14 የሚሆኑ ባለሞያዎች ለእስር ተዳርገዋል።
በተለያየ ቀናት ለእስር የተዳረጉት እነዚህ ባለሞያዎች ከ 2 እስከ 6 ቀናት ለሚሆን ጊዜ ታስረው በዋስ ከእስር ተፈተው ወደ ስራ ገበታቸው ተመልሰዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለእስር ከተዳረጉት ባለሞያዎች መካከል የተወሰኑትን አነጋግሯል።
ባለሙያዎቹ " ጥያቄያችን ፓለቲካዊ ይዘት እንዲኖረው ተደርጓል " ብለውናል።
" የጠየቅነው የሰራንበትን ክፍያ ሆኖ ሳለ ፍርድ ቤት ስንቀርብ ' ህዝብ በመንግስት ላይ እንዲነሳ አድርጋቹሃል፣ ሰዎችን ወደ ሥራ እንዳይጋቡ አስፈራርታቹሃል ' የሚል ክስ ተነቦልናል " ነው ያሉት።
በተጨማሪም ባለሞያዎች ወደ ሆስፒታል ሲመለሱ ከአሁን በኋላ ተመሳሳይ የሆነ የስራ ማቆም አድማ ውስጥ ቢገቡ አስፈላጊውን አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው የሚገልጽ ደብዳቤ ላይ እንዲፈርሙ ተደርጓል ብከዋክ።
ሰራተኞቹ ከተመለሱ በኋላ BPR የተሰኘ በየስምንት ሰዓቱ በሺፍት የሚቀያየሩበት አሰራር እንዲዘረጋ መደረጉን ተናግረዋል።
በአዲሱ አሰራር መሰረት ጠዋት 12 ሰዓት ወደ ስራ የገባ ሰራተኛ 8 ሰዓት ከስራ የሚወጣ ሲሆን 8 ሰዓት የገባው ምሽት 4 ሰዓት ከስራ ይወጣል።
ይሁን እንጂ ይህ አሰራር " ሆስፒታሉ ለሰራተኞች ሰርቪስ የሌለው በመሆኑ እና በምሽት ሺፍት ከስራ ስንወጣ እና ስንገባ ለጅብ እየተጋለጥን ነው " በሚል ቅሬታ አቅርበዋል።
" ይህ አይነቱ አሰራር የተዘረጋው የወረዳው አስተዳደር ለመቀጣጫ እንዲሆን በሚል ነው " ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ " የትርፍ ሰዓት ሥራ ለማስቀረት የተደረገ ነው " ብለዋል።
ቲክቫህ ጉዳዩ በዋናነት የሚመለከታቸውን የአንጋጫ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና የሆስፒታሉ ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑትን አቶ ማርቆስ ማሞን ቅሬታውን ከተቀበለበት ቀን ጀምሮ ለማናገር ተደጋጋሚ የሆነ የስልክ ሙከራ ቢያደርግም ስልካቸውን ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።
የሆስፒታሉ አስተዳዳሪ አቶ ተሰማ አበራ አዲሱ አሰራር ለአደጋ አጋልጦናል የሚለውን የሆስፒታሉን ባለሞያዎች ቅሬታ አይቀበሉም።
" የትርፍ ሰዓት ስራ ሲሰሩ ያልነበረ ጅብ ዛሬ ከየት መጣ " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ይህ አይነቱ አሰራር ያልነበረና አዲስ ተደርጎ መወሰድ የለበትም ብለዋል።
አክለውም " ይህን ጭቅጭቅ የሚያመጣው ወረዳው የመክፈል አቅም የሌለው በመሆኑ ነው በቀጣይም መጋጨት የለብንም " በማለት አሰራሩ በገንዘብ እጥረት ምክንያት የተዘረጋ መሆኑን ጠቁመዋል።
ባለሞያዎቹ የሰሩበት ገንዘባቸው ሳይከፈላቸው ወደ ስራ እንዲመለሱ ተደርጓል መቼ ክፍያቸው ይፈጸማል ስንል በድጋሚ ላነሳንላቸው ጥያቄም "አሁንም እየተነጋገርን ነው ከወረዳ መንግሥት ጋር የገንዘብ ክፍተት ስላጋጠመ እንጂ መከፈል እንዳለበት ተግባብተናል" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
የኢትዮ130 6ኛ ዙር ዕድለኞች እንኳን ደስ አላችሁ! 🎉🎉
💡 ሽልማቱ እንደቀጠለ ነው፤ ጥቅልና የአየርሰዓት በመግዛት፣ የአገልግሎት ክፍያዎችን በቴሌብር በመፈጸም እንዲሁም ገንዘብ በመላክና በመቀበል ተጨማሪ የጨዋታ ዕድሎችን ያግኙ!
🚘 6 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖች
🛺 7 ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች
💰 በየቀኑ የ20 ሺህ ፤ በየሳምንቱ የ50 ሺህ እና 100 ሺህ ብር ገንዘብ ሽልማቶች በቴሌብር
📱 ዘመናዊ ስማርት ስልኮች እንዲሁም
🎁 በርካታ የሞባይል ጥቅሎች!
✅ በቴሌብር ሱፐርአፕ ኢትዮ130 መተግበሪያ ወይም ለኢትዮ ፕሮሞ *130# ለኢትዮ ላኪ ስሎት *131# በመደወል ይመዝገቡ!
ለተጨማሪ መረጃ፡ https://bit.ly/3Y0pGzs ይጎብኙ!
#130_ዓመታትን_በጽናት_ታላቅ_አገርና_ሕዝብ_በማገልገል_ላይ
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#መልዕክት❤️
የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ባልደረባ ዶ/ር ዳዊት እሸቱ ከልብ ህመም ጋር በተያያዘ ለወላጆች መልዕክት አስተላልፈዋል።
" በተለይም አራስ ህፃናት ሲጠቡ የሚያልባቸው ፣ የሚደክማቸው ፣ በአጣዳፊ የሚተነፍሱ ፣ ኪሎ አልጨምር የሚሉ ፣ ጉንፋን በቶሎ ቶሎ የሚይዛቸው ፣ እድገታቸው የሚዘገይ ከሆነ በአፋጣኝ ወደ ህክምና መሄድ ይገባል በዚህም ከበሽታው መታደግ ይቻላል " ብለዋል።
@tikvahethiopia
“ በልብ ክፍተት የምትሰቃይ ልጄን አድኑልኝ። ለህክምና 685 ሺሕ ብር ተጠይቄአለሁ ” - አባት
ሁለት ዓመት ያልሞላት ጨቅላ ልጃቸው በልብ ክፍተት ህመም በጠና የታመመችባቸው አቶ ሺበሺ ፀጋዬ የተባሉ ኢትዮጵያዊ በውስጥም በውጪም ያሉ ኢትዮጵያውያን እርዳታ እንዲያደርጉላቸው በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ተማጽነዋል።
አቶ ሺበሺ በገለጹት መሠረት፣ ልጃቸው በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ በልብ ህሙማን መርጃ ማዕከል ክትትል ስታደርግ ቆይታ በመጨረሻ ወደ ውጪ አገር ሂዳ መታከም እንዳለባት ተነግሯቸው ነበር።
በኋላ ላይ ደግሞ በአገር ውስጥ የሚገኘው ታዝማ የውስጥ ደዌና ቀዶ ሕክምና ልዩ ማዕከል ህክምናውን ሊያደርግላት እንደሚችል እንደገለጸላቸው አስረድተዋል።
ማዕከሉ ህክምናውን ለመስጠት 685 ሺሕ ብር እንደጠየቃቸው ገልጸው ይህን ብር ማግኘት ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ እርዳታ እንዲደረግላቸው ተማጽነዋል።
አባት፣ " በልብ ክፍተት የምትሰቃይ ሌጄን አድኑልኝ። ለህክምና 685 ሺሕ ብር ተጠይቄአለሁ " ነው ያሉት።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው ደብዳቤም፤ ልጃቸው የአብስራ ሺበሺ ህክምናውን ለማድረግ 685 ሺሕ ብር እንደሚያስፈልጋት የሚገልጽ ነው።
መርዳት ለምትሹ 1000213009568 የአቶ ሺበሺ ፀጋዬ ፈዬ የንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር ነው። ደውሎ ለመጠየቅ ደግሞ 0928232593 ስልክ ቁጥራቸው ነው።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
በEBS ሔለን ሾው የተዘጋጀው ኢምፓወር አዲስ ዝግጅት ህዳር 7 እና 8 ቀን 2017 በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል፡፡
በዝግጅቱ በፋይናንስ፣ በቢዝነስ፣ በስራ ፈጠራ፣ በንግድ ክህሎት፣ በጤና ጉዳዮች፣ በፋሽን፣ በውበት አጠባበቅና ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይቶችና ዝግጅቶች ይኖራሉ:: እንዲሁም እስከ 600,000 ብር የሚያስሽልም አዲስ የሥራ ሐሳብ ውድድርም ይኖራል፡፡
የጤና ምርመራ አገልግሎትና የምግብ ዝግጅት ከሼፎች ጋር የሚደረግ ሲሆን ደራሲያንን የማግኘትና የማስፈረም፣ ሠዓሊያንን ሌሎች ባለሙያዎችን የማግኘትና ጥያቄ የመጠየቅ እድል ይኖራል፡፡ በተጨማሪም የመገበያያ መድረክ፣ የሙዚቃና የመዝናኛ ዝግጅቶች ይኖራሉ።
የኢምፓወር አዲስ ዝግጅት ትኬት ክፍያ የሚፈፀመው በቴሌብር ነው፡፡ ዋጋ በቅድሚያ ከገዙ 300 ብር ብቻ! በዕለቱ ከገዙ 500 ብር::
እንዳያመልጣችሁ!!!
አዘጋጆቹ !
#AddisAbaba
የሆቴል ባለሙያዎችን አለባበስ እና የመዋቢያ ጌጣጌጥ አጠቃቀም ሥርዓት የሚወስን ደንብ መውጣቱን የአዲስ አበባ ከተማ የፍትህ ቢሮ አሳውቋል።
ይህ ደንብ ቁጥር 178/2017 ሆኖ የወጣ ነው።
ደንቡ " በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ ባለሙያዎች ወጥ የሆነ የአለባበስ፤ የጌጣጌጥ እና የመዋቢያ አጠቃቀም ሥርዓት በመዘርጋት የሀገር ባህልና እሴት እንዲጠበቅ ለማድረግ የወጣ ደንብ ነው " ብሏል።
ከደንቡ የአለባበስ ስርአት ውስጥ ለአብነት ፦
➡ ደረት ክፍልን ያልሸፈነ ወይም ከአንገት በታች ያለውን የሰውነት ክፍል የሚሸፍን ሸሚዝ ያለበሰ፤
➡ የሴቶች ጉርድ ቀሚስ ቁመቱና ቅዱ ከጉልበት በላይ ከሆነ፤
➡ ከጋብቻ ቀለበት ውጪ ጌጣጌጦችን በሚታዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ከተደረገ እንደሚያስቀጣ ያስቀምጣል፡፡
ቢሮው " ደንብ ቁጥር 178/2017 በዘርፉ ተሰማርተው የሚሰሩ ሙያተኞች ሊደርስባቸው ከሚችለው አካላዊ፤ ሥነ-ልቦናዊ ጫና እና አላስፈላጊ ጥቃቶችን ለመከላከል ብሎም በከተማው የሚሰጠው የሆቴል አገልግሎት ዓለም አቀፍ መስፈርትን የሚያሟላ እንዲሆን ማድረግ ነው " ብሏል።
ይህ ደንብ በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተሰማራ ባለሙያ በደንቡ በተደነገገው መሰረት አክብሮ እየሰራ ስለመሆኑ ወቅቱን የጠበቀ ክትትል ይደረጋል ተብሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን እና የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ጋር በቅንጅት በመስራት ደንቡ ተፈጻሚ እንዲሆን ይደረጋል ነው የተባለው።
መረጃው ከየአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ የተገኘ ነው።
@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ
የብርሃን ባንክ #ልዩ_የኤቲኤም_ካርድ
👉 የካርድ አዘጋጁልኝ ጥያቄውን ባቀረቡበት ቅፅበት ማግኘት የሚችሉት
👉 ደንበኞች ለረዥም ጊዜያት ኤቲኤም ካርድ ለማግኘት የሚያባክኑትን ጊዜ ያስቀረ
👉 የሚስጥር ቁጥሩ ከወረቀት ነጻ ሆኖ በእጅ ስልክዎ ብቻ የሚደርስዎት
👉 የሚስጥር ቁጥርዎ ለሌላ ሰው እንዳይጋለጥ በማድረግ ደህንነቱ የተረጋገጠ
ወደ ቅርንጫፎቻችን ጎራ ይበሉ ፈጣኑን #ልዩ_የኤቲኤም_ካርድ ይውሰዱ!
#liyuatmcard #atmcard #berhanbank #bank #finance #Stressfreebanking #bankinethiopia
ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ!
➡️ Facebook ➡️ Telegram
➡️ Instagram ➡️ Twitter
➡️ LinkedIn ➡️ YouTube
አንጋፋው ጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
አንጋፋው ጋዜጠኛ ዜናነህ ፥ በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቭዥን እንዲሁም በዴቼ ቬለ ሬድዮ ለረዥም ዓመታት አገልግሏል።
ጋዜጠኛ ዜናነህ ለረዥም ጊዜያት ባደረበት ህመም ህክምናውን ሲከታተል ከነበረበት እስራኤል ቴል አቪቭ ዛሬ ጠዋት ኣፏል።
በስልሳ ስምንት ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው አንጋፋው ጋዜጠኛ ዜናነህ አዘዞ ጎንደር ነው የተወለደው።
ከ1970ዎቹ እስከ ሰማኒያዎቹ አጋማሽ ድረስ በኢትዮጵያ ራዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት በተለይ በዜና አንባቢነት አገልግሏል።
በ1980ዎቹ አጋማሽ ወደ እስራኤል ያቀናው ዜናነህ በህመም ተዳክሞ ከሥራው እስኪርቅ ድረስ በኢየሩሳሌም የዶቼ ቬለ ራዲዮ ዘጋቢ በመሆን ሲያገለግል ቆይቷል።
" ይህ ዶቼ ቨለ ነው !! " ከሚለው የዲቼቬለ ሬድዮ ጣቢያ መለያ አንስቶ የተለያዩ ዝግጅቶች መክፈቻም የአንጋፋው ጋዜጠኛ ድምፅ ነው።
የዶቼ ቬለ አድማጮች ዜናነህን ከመካከለኛው ምስራቅ በእስራኤል አረብ ግጭት እና ጦርነቶች ብሎም በቀጣናው በሚነሱ ፖለቲካዊ ዘገባዎች ያውቁታል።
የዜናነህ መኮንን የቀብር ሰነ ስረዓት ቴል አቪቭ ውስጥ በሚገኝ ፓርክ ያኮም መካነ መቃብር እንደሚፈጸም ልጁ ቢታንያ ዜናነህ ገልጻለች።
ዜናነህ ባለትዳር እና የሶስት ሴቶች ልጆች አባት ነበር።
#ዶቼቨለ
@tikvahethiopia
#PAUL_PHOTO_VELO_AND_MAKEUP
🩸Premium package 27.500ብር ብቻ
👉Laminate album 30x90 -10(20) page,Board photo 50x80-1,Signboard,Thankyou card 200,Wallet album 2,Save the date 4 photo,Slideshow,የሰርግ አልባሳት.2 ቬሎ የመስክ (በመረጡት አይነት),2 ቬሎ የስቱዲዮ (በመረጡት አይነት)Color Velo ጨምሮ,ካባ ( በመረጡት አይነት),2 ሱፍ (በመረጡት አይነት ),የሀበሻ ልብስ፣የእራት ቀሚስ፣የአፍሪካ ልብስ ሜካፕ:,ጥፍር እና ፀጉር ጨምሮ,የወንዶች የውበት ሳሎን (ጸጉር፣ ጺም፣ የፊት ስቲም፣ ስክራፕ፣ እጥበት)
☎️ 0943946144/ 0777630083
🏓22 ከ አክሱም ሆቴል ወረድ ብሎ ትጋት ግራውንድ ላይ ቢሮ ቁጥር G-24
#USA #MASS_DEPORTATION
ትራምፕ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶክመንት የሌላቸው ሰዎችን ከአሜሪካ ለማስወጣት ምን ያህል በጀት ያስፈልጋቸው ይሆን ?
ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልክ በፕሬዜዳንትነት ስራ ሲጀምሩ የመጀመሪያ ስራቸው ይሆናል የተባለው በአሜሪካ ታሪክ ከፍተኛ የተባለ ዶክመንት የሌላቸው ሰዎችን ከሀገር ማስወጣት / የዲፖርቴሽን ስራ ነው።
ይህ ግዙፍ የተባለ ዲፖርቴሽን በቢሊዮን ዶላሮችን ሊጠይቅ ይችላል።
እሳቸው ግን ይህ የዲፖርቴሽን ጉዳይ " ምንም ዋጋ የሚወጣለት / ዋጋ የሚለጠፍለት አይደለም " ብለዋል።
ከአሁን በኃላ የአሜሪካ ድንበሮች እጅግ ጠንካራ ደህንነት ያለባቸው ኃይለኛ ድንበሮች እንደሚሆኑ ጠቁመዋል።
" እውነት ለመናገር ምንም ምርጫ የለንም " ያሉት ትራምፕ ፤ በሀገሪቱ ሰዎች እየተገደሉ እና የአደንዛዥ እጽ አዘዋዋሪ ጌቶች ሀገሪቱን እያወደሙ የሚኖሩበት ምንም ምክንያት የለም ብለዋል።
" አሁን እነዚህ ሰዎች እዚህ አይቆዩም ፤ እንዲቆዩም አይደረግም ወደነዛ ሀገራት ይመለሳሉ " ሲሉ ገልጸዋል።
ለዚህ ደግሞ ምንም ዋጋ የሚለጠፍለት እንዳልሆነ ጠቁመዋል።
ትራምፕ በምርጫ ዘመቻ ዶክመንት የሌላቸው ሰዎችን ለማስወጣት የገቡትን ቃል እንደሚተገብሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።
" በቀላል መመሪያ ነው የማስተዳድረው " ያሉት ትራምፕ " የገባሁትን ቃልኪዳን አክብራለሁ አስፈጽማለሁ " ብለዋል።
እንዴት ባለ መንገድ እንደሚያስፈጽሙት ባይታወቅም ትራምፕ ከ11 ሚሊዮን እስከ 21 ሚሊዮን ሰዎችን ከአሜሪካ ሊያስወጡ እንደሚችሉ ተነግሯል።
ትክክለኛ ዶክመንት የሌላቸው ሰዎች ምን ያህል እንደሆኑ አይታወቅም። ምናልባትም አሁን ከሚባለው 21 ሚሊዮን ሊያንስ እንደሚችል ነው የሚነገረው።
' ፒው ሪሰርች ሴንተር ' 2021 ላይ ይፋ ባደረገው ዳታ 10.5 ሚሊዮን ዶክመንት የሌላቸው ሰዎች አሜሪካ ውስጥ አሉ።
#USA #NBC #TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#ደመወዝ
" በእኛ መስሪያ ቤት በኩል የተስተካከለው የጥቅምት ወር ደመወዝ ተከፍሏል " - መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር)
የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) ፥ የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያን በተመለከተ ባሰራጩት ፅሁፍ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የተጨማሪ ክፍያ በጀቱን ለሚመለከታቸው ተቋማት ፈቅዷል። በእኛ መስሪያ ቤትም በኩል የተስተካከለውን የጥቅምት ወር ደመወዝ ተከፍሏል " ብለዋል።
" ሌሎችም እንደዚሁ የከፈሉ አሉ። የቀሩት ደግሞ የማጥራት ሥራ እየሰሩ ሊሆን ይችላል። " ሲሉ ገልጸዋል።
" እነዚያም ዝግጅታቸውን ሲያጠናቅቁ የተስተካከለው የጥቅምት ወር ክፍያ ታሳቢ በማድረግ የሚከፍሉ ይሆናል " ሲሉ አስረድተዋል።
" የተፈቀደው የመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ ክፍያ ዘግይቷል፥ ቀርቷል የሚሉ ሃሳቦች እየተራመዱ ነው " ያሉት ኮሚሽነሩ " በሲቪል ሰርቪስ በኩል የሚለቀቁ መረጃዎች ኦፊሴላዊና የሚተገበሩ መሆኑን መተማመን ጥሩ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
" ከሠራተኞች ደመወዝ ስኬል ጋር በተገናኘ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ አሳሳች ወሬዎችን እንዳታምኗቸው መልዕክት አስተላልፌ ነበር " ሲሉም አክለዋል።
ከሰሞኑን ከሠራተኞች ደመወዝ ጋር በተገናኘ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች መረጃዎችን ተዘዋውረዋል።
ከነዚህም አንዱ ጭማሪው እንዳልተከፈለ የሚገልጽ ነው።
ነገር ግን በአንዳንድ መ/ቤቶች ጭማሪው መከፈሉ ታውቋል። ጭማሪው ያልተከፈለባቸውም መ/ቤቶችም ግን አሉ ፤ እነዚህ ናቸው ' እያጣሩ ናቸው " የተባሉት።
" ተጨምሯል የተባለው ገንዘብ ያን ያህል አይደለም " - ሠራተኞች
" የደመወዝ ጭማሪ ይደረጋል " የሚለውን መረጃ የሰሙ ሠራተኞች ከፍተኛ ጭማሪ ጠብቀው እንደነበር ነገር ግን እጃቸው ላይ የደረሰው እዚህ ግባ የማይባል እንደሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አንድ ቃላቸውን የሰጡ ሠራተኛ ፥ " ምንኑን ከምኑን ልናደርገው ይሄ ብቻ እንደተጨመረ አልገባኝም " ብለዋል።
ጭማሪው አነስተኛ እንደሆነ የገለጹ አንዲት ሠራተኛ በበኩላቸው " ከሚጨመረው ብር በላይ ወሬው በዝቶ ይበልጥ ኑሮውን እንዳያስወድደው " ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
" አይደለም ደመወዝ ተጨመረ ተብሎ ሳይባል እንኳን ነጋዴው ሁሉን ነገር አምጥቶ የሚጭነው እኛው ድሃው ዜጎች ላይ ነው አሁን ተጨምሯል የተባለው ገንዘብ ከኑሮው ውድነቱ አንጻር ያን ያህል አይደለም፤ ጭራሽ ነጋዴዎቹ ዋጋ ጨምረው አሁንም አልገፋ ያለውን ኑሮን እንዳያከብዱብን " ብለዋል።
ያነጋገርናቸው ሌሎችም ሠራተኞች " ደመወዝ ተጨመረ " የተባለው አነስተኛ እንደሆነ፣ የቁጥጥር ስራ እንዲሰራ ፣ ሌሎች የሠራተኞችን ህይወት የሚያቀሉ መፍትሄዎች እንዲፈለጉ ጥሪ አቅርበዋል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#PAUL_PHOTO_VELO_AND_MAKEUP
🩸Premium package 27.500ብር ብቻ
👉Laminate album 30x90 -10(20) page,Board photo 50x80-1,Signboard,Thankyou card 200,Wallet album 2,Save the date 4 photo,Slideshow,የሰርግ አልባሳት.2 ቬሎ የመስክ (በመረጡት አይነት),2 ቬሎ የስቱዲዮ (በመረጡት አይነት)Color Velo ጨምሮ,ካባ ( በመረጡት አይነት),2 ሱፍ (በመረጡት አይነት ),የሀበሻ ልብስ፣የእራት ቀሚስ፣የአፍሪካ ልብስ ሜካፕ:,ጥፍር እና ፀጉር ጨምሮ,የወንዶች የውበት ሳሎን (ጸጉር፣ ጺም፣ የፊት ስቲም፣ ስክራፕ፣ እጥበት)
☎️ 0943946144/ 0777630083
🏓22 ከ አክሱም ሆቴል ወረድ ብሎ ትጋት ግራውንድ ላይ ቢሮ ቁጥር G-24
#Infinix_HOT50_Pro+
አዲሱ የኢንፊኒክስ HOT 50 Pro+ ስልክ 7 ነጥብ 8 ሚሊሜትር ያህል ቀጭን ዲዛይን ይዞ የመጣ ሲሆን ይህም ስልኩን ለአያያዝ ምቹ ከማድረጉም በላይ እጅዎት ላይ እጅግ ያምራል፡፡
@Infinix_Et|infinixet">@Infinixet
#Infinix #InfinixHOT50Pro+ #WOOOWNewHOT #InfinixHOT50Series
#ሲሚንቶ
" ከዛሬ ጀምሮ በሚኒስትር መ/ቤቱ በኩል ይደረግ የነበረዉ የሲሚንቶ ግብይት ትስስር ሥራ ቀርቷል " - ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ ከሲሚንቶ አምራቾች ጋር መወያየታቸው ተሰምቷል።
በዚህም ወቅት " ከዚህ ቀደም በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በኩል ይደረግ የነበረዉ የሲሚንቶ ግብይት ትስስር ሥራ ከዛሬ ጀምሮ ቀርቷል " ብለዋል።
አምራቾች በራሳቸዉ ኃላፊነት በሚመርጧቸዉ አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎች በኩል ለተጠቃሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያቀርቡ አሳስበዋል፡፡
የሲሚንቶ ገበያዉን ለማረጋጋት ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል ይደረጋል ያሉ ሲሆን የአፈጻጸም ሪፖርት ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በማያቀርቡ በማናቸዉም የሲሚንቶ አምራች ላይ " የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ሚኒስትሩ " አዲሱን ዉሳኔና አቅጣጫ ተከትሎ በግብይት ሰንሰለቱ የደላላ ጣልቃ ገብነት የከሰመ፣ ለመንግስት ፕሮጀክቶችና ለተጠቃሚዉ ህብረተሰብ አስተማማኝ የሲሚንቶ አቅርቦት የተረጋገጠ፣ አምራቾችም ተገቢዉን ትርፍ እያገኙ የከምፓኒዎቻቸዉን ዘላቂ ዕድገት የሚያስቀጥሉበት እንዲሆን " ብለዋል።
የግብይት ሥርዓቱ ሙሉ በሙሉ ከካሽ ክፍያ ነጻ ሆኖ በዲጂታል ክፍያ ሥርዓት እንዲፈጸም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በውይይት መድረኩ ወቅት አምራቾች የምርት አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ተብሏል።
ሲሚንቶ አምራቾች አዲሱን ውሳኔ በማክበር እንደሚተገብሩ ተናግረው ነገር ግን የማምረቻ ግብዓት ፣ የኃይል አቅርቦትና ተያያዥ ችግሮች እንዲፈቱላቸዉ ጠይቀዋል፡፡
@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ
የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና ለጉምሩክ ኮሚሽን በፃፈው ደብዳቤ ፍራንኮ ቫሉታ ከዛሬ ጀምሮ መከልከሉን አሳውቋል።
የብር የመግዛት አቅም በገበያው እንዲወሰን ከተደረገ በኋላ ለተወሰነ ጊዜ የነዳጅ ተሽከርካሪዎችን እና የፀጥታ ተቋማት መሳሪያዎችን ሳይጨምር ሌሎች ምርቶችን በፍራንኮ ቫሉታ ወደ ሀገር ማስገባት ተፈቅዶ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ይሁንና ከሳምንት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በፓርላማ ተገኝተው ማብራሪያ ሲሰጡ የተፈቀደው ፍራንኮ ቫሉታ ሀብት ከሀገር እንዲሸሽ ምክንያት እየሆነ በመሆኑ ሊታገድ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተው እንደነበር ይታወሳል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር ዛሬ በፃፈው ደብዳቤም ከዚህ ቀደም በፍራንኮ ቫሉታ ሸቀጦችን ከውጪ ያዘዙ ካሉ ከዛሬ ጀምሮ በ2 ሳምንት ጊዜ ውስጥ ግዢ የተፈፀመባቸው ህጋዊ ሰነዶችን ለጉምሩክ ኮሚሽን በማቅረብ ተቀባይነት አቅርበው የንግድ ሸቀጦቹ ወደ ሀገር እንዲገቡ ይደረጋል ብሏል።
የፍራንኮ ቫሉታ ፍቃድ ከጥቅምት 28/2017 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የማይደረግ መሆኑ ተመላክቷል።
የመረጃው ባለቤት ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ነው።
@tikvahethiopia
#ጋምቤላ
አዲስ አመራር ከመጣ በኃላ በጋምቤላ መሻሻል ታይቷል ?
በጋምቤላ ክልል ካለፈው ነሐሴ 2016 ዓ/ም ወዲህ የአመራር ለውጥ ከተደረገ ወዲህ በክልሉ የነበረው የሠላም ሁኔታ እየተሻሻለ መምጣቱን አዲሱ አስተዳደር፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እንዲሁም ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ባለፈው ዓመት በጋምቤላ ክልል በተለያዩ አካባቢዎችና ጊዜዎች ግጭቶች እየተከሰቱ በሰው ህይዎት ላይ ጉዳት ሲደርስ ቆይቷል።
ከሰብዓዊ ጉዳቱ ባሻገር በክልሉ ነዋሪዎች መካክል የነበሩ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በአንዳንድ ቦታዎች እስከመገደብ ደርሰውም ነበር።
የክልሉ ልማትና ሰላምም በእጅጉ ተጎደቶ ነበር።
በተለይ ቀደም ባሉት ጊዜዎች የአኙዋክ ተውላጆች ወደ ኑዌር ሰፈር አይሄዱም፣ ኑዌሮችም በተመሳሳይ ወደ አኙዋክ ሰፈር ይሻገሩ አልነበረም።
አሁን ላይ ግን ሁኔታዎች እየተሻሻሉ መምጣታቸውን የጋምቤላ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ጋትሏክ ሮን ምን አሉ ?
- ችግሮችን ለማስተካክልና በክልሉ ሠላም ለማስፈንና ህዝቡን ወደልማት ለማምጣት በክልሉ ከነሐሴ 2016 ዓ/ም መጀመሪያ ሳምንት ላይ የአመራር ለውጥ በመደረጉ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ሠላም ሰፍኗል።
- በክልሉ በነበረው የሠላም እጦት ምክንያት የጋምቤላ ከተማ የአኙዋክና የኑዌር በሚል ተከፍሎ አኙዋኮች ወደ ኑዌር ሰፈር፣ ኑዌሮችም ወደ አኙዋክ መንደር ለመሻገር ችግሮች ነበሩ። አሁን ያ ሁሉ ቀርቶ አዲሱ አመራር ወደ ሥራ ከገባና ህዝባዊ ውይይቶች ከተደረጉ በኋላ ሁሉም በሠላም በሁሉም ሥፍራ ይንቀሳቀሳል።
🔵 ማሉት ዴቪድ የተባሉ የጋምቤላ ከተማ ነዋሪ የምክትል ርዕሰ መስተዳድሩን ሀሳብ ይጋሩታል፣ አሁን አንዱ ወደ ሌላው ያለስጋት እንደሚንቀሳቀስ ነው ያረጋገጡት። ከተማውም ሠላም እንደሆን አመልክተዋል።
- አዳዲስ ሹመቶችና ምደባዎች ተሰጥተዋል። ይህም የትምህርት ዝግጅትንና የሥራ ልምድን መሠረት ያደረገ ነው።
- ለውጥ ያመጣሉ ተብሎ የታመነባቸው ቀደም ሲል ስልጣን ላይ የነበሩና ህዝባዊ አመለካከት ያላቸው በርከት ያሉ አመራሮችም በአዲሱ ሹመትና ምደባ እንደገና ተካተዋል።
- " ሠላም ወርዶ ህዝቡ በልማት መካስ አለበት " በሚል እሳቤ እውቀት፣ ልምድና የተሻል አመለካክትና እይታ ያላችው ሠዎች ወደ አመራሩ ተካተዋል።
- በኮታ መታሰር ቀርቷል። ቀደም ሲል በነበረው አሰራር ወንጀል ያልሰሩ ሰዎች በኮታ ጭምር ይታሰሩ ነበር። አሁን ግን በወንጀል የተጠረጠሩትን ብቻ ተጠያቂ የሚያደርግ አሰራር ተዘርግቷል።
- በፊት አንድ ኑዌር ቢያጠፋና ቢታሰር ሌላ አኙዋክ አብሮ እንዲታሰር ይደረግ ነበር፣ ሌላ አኙዋክ አጥፍቶ ቢታሰር የኑዌር ተወላጅ ተደርቦ እንዲታሰር ይደረግ ነበር ፤ አሁን ግን ጠፋተኛው ከየትኛውም ወገን ይሁን ጠፋተኛ ከሆን ተጠርጣሪው ብቻ ተለይቶ ተጠያቂ ይሆናል። የኮታ እስር ቀርቷል።
" ከአዲሱ አመራር ጋር ለመስራት ዝግጁ ነኝ " - ጋብዴን
የጋምቤላ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ጋብዴን) ሊቀመንበር አቶ ኡባንግ ኡሞድ ቀደም ሲል የነበረው አመራር ህዝቡን መምራት እንዳልቻለና ለውጥ እንዲመጣ ሲታግሉ እንደንበር ገልጠዋል።
ችግሩ የአመራሩ ሆኖ ሳለ ህዝቡን በከፍተኛ የሠላም እጦት ውስጥ ከትቶት ነበር ነው ያሉት።
በክልሉ የነበረውን ችግር እስከ የተፎካካሪ ፓርቲ የጋራ ምክር ቤት በማድረስ የነበረው የሠላም እጦት እንዲታወቅ መደረጉንና ለውጥ እንዲደረግ በግልም በጋራም ትግል ሲደረግ እንደነበር አስረድተዋል።
አዲሶቹ አመራሮች በሕዝቡ ተቀባይነት ማግኘታቸውንና ፓርቲያቸውም በአዲሱ አመራር ደስተኛ መሆኑን አቶ ኡባንግ ተናግረዋል።
ከአዲሱ አመራር ጋርም በጋራ ለመስራት ዝግጁ እንደሆኑም ነው የገለጡት።
የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ነሐሴ 9/2016 ዓ ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ወ/ሮ ዓለሚቱ ኡመድን የመጀመሪያዋ የክልል ሴት ርዕሰ መስተዳድር፣ ዶ/ር ጋትሏክ ሮንን ደግሞ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ መሾሙ ይታወሳል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።
@tikvahethiopia
ሕብር ሼባ ማይል ካርድ
በሕብር ሼባ ማይል ካርድ ግብይትዎን በመፈፀም ለጉዞ የሚያስፈልግዎትን ተጨማሪ ማይል ጉርሻ ያግኙ፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!
📞 ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡
🤳 በቀላሉ አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ የቴሌግራም ገፃችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፡፡ /channel/HibretBanket
🌐 ሌሎች የማህበራዊ ገፆቻችንን እና ድህረ ገፃችንን linktr.ee/Hibret.Bank ይጎብኙ፡፡
#shebamiles #Rewardyourself #Hibretbank
" የአላቂ እቃዎች እጥረት በጣም ትልቅ ፈተና ሆኖብናል " - የልብ ሕሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል
የአላቂ እቃዎች እጥረት የህፃናት ታካሚዎችን ወረፋ እየጨመረው መሆኑን፣ አሁንም ድረስ በአቬሬጅ አራት ዓመት ለሚሆን ጊዜ ወረፋ እየጠበቁ ያሉ ወደ 8,000 የሚጠጉ ህፃናት እንዳሉ የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል ለቲክህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የማዕከሉ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ባልደረባ ዶ/ር ዳዊት እሸቱ በሰጡን ቃል፣ " የአላቂ እቃዎች እጥረት በጣም ትልቅ ፈተና ሆኖብናል" ብለዋል።
በማዕከሉ አጣዳፊ ትኩረት የሚሻው ፈታኝ ጉዳይ ምንድን ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ አቅርቧል።
ዶ/ር ዳዊት ፥ " እያጋጠመን ያለው አንዱና ትልቁ ፈተና የአላቂ እቃዎች ነው። የምንሰጣቸው አገልግሎቶች በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ አገልግሎት ላይ ለሚውሉ እቃዎች በተለያዩ ምክንያቶች እጥረት አለ " ብለዋል።
" የአላቂ እቃዎች እንደልብ አለመገኘት የታካሚ የወረፋ ጊዜን እየጨመረው ይገኛል። አሁንም ወደ 8,000 የሚጠጉ ህፃናት ወረፋ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ " ሲሉ ገልጸዋል።
" አቬሬጅ የወረፋ ጊዜ አራት ዓመት እየደረሰ ነው ። በዋናነኝነት ከምንጠቀማቸው እቃዎች በተጨማሪ በዬቀኑ አክቲቪቲው ላይ የሚውሉ ለኦፕሬሽንና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውሉ መድኃኒቶች/የአላቂ እቃዎች እጥረት በጣም ትልቅ ፈተና ሆኖብናል " ብለዋል።
በአቬሬጅ ለአራት ዓመት ወረፋ እየጠበቁ ያሉ ህፃናት ቢያንስ በምን ያክል ጊዜ ነበር ህክምና ማግኘት የነበረባቸው ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ " በዓመት እስከ 500 ታካሚዎችን እናስተናግዳለን። በሙሉ አቅማችን ግን ብንሰራ እስከ 1500 ህፃናትን መድረስ እንችላለን " ሲሉ መልሰዋል።
" ችግሩ ግን በዓመት 1,300 ያህል አዳዲስ ታካሚዎች ይኖራሉ። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገራት ከ20 ሺሕ በላይ ህፃናት በተፈጥሮ ከሚመጣ የልብ ችግር ጋር ይወለዳሉ ይባላል በዓመት። ስለዚህ ይሄ ችግር ውጪ አገር ቶሎ ነው መፍትሄ የሚሰጠው አገልግሎቱ አቬሌብል ስለሆነ። ወዲያው ቢሆን ይመረጣል " ነው ያሉት።
እጥረት እየተስተዋለባቸው ያሉ የእቃ አይነቶች ምንድን ናቸው ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ ዶ/ር ዳዊት እሸቱ ፦
" ለልብ ህክምና የሚያስፈልጉ መድኃኒቶች አሉ። እንደ የደም ማቅጠኛ አይነት መድኃኒቶች ናቸው። ሁለት አይነት አገልግሎቶችን ነው የምንሰጠው በኛ ማዕከል።
አንደኛው ደረት ተከፍቶ የሚሰራው ቀዶ ህክምና ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ በደም ስር ውስጥ ተኪዶ የልብ ጥገናው የሚካሄድበት አገልግሎቶች ናቸው። እያንዳንዳቸውም የሚጠቀሟቸው ማተሪያሎች አሉ።
በቀዶ ህክምናው ኦክስጂኔተር የሚባል አለ። የልብና የሳንባውን ሥራ ተክቶ የሚሰራው ማሽን ላይ የሚገጠም ነው። እሱ ማተሪያል ለአንድ ጊዜ ነው አገልግሎት ላይ የሚውለው። ለአንድ ታካሚ ለአንዴ ነው የሚሆነው።
ካትላብ ላይ ደግሞ በደም ስር ውስጥ ዋየሮች የተለያዬ የዋጋ ሬንጅ አላቸው። እነርሱን እኛ ጋ አጥበን እስከ 4፣ 5 ጊዜ ደጋግመን እንጠቀማቸዋለን።
ስለዚህ በዋነኝነት እነዚህ ማተሪያሎች፣ ከዚያ ደግሞ የተለያዩ ኬሚካሎች ሁሉ አላቂ ከምንላቸው እቃዎች ውስጥ ይካተታሉ " ሲሉ መልሰዋል።
የልብ ሕሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል ላለፉት 35 ዓመታት አገልግሎቱን በመስጠት ላይ ይገኛል።
በመጀመሪያዎቹ 20 ዓመታት ህክምና ሲሰጥ የነበረው ወደ ውጪ በመላክ ነበር። በዚህም ወደ 2,600 ገደማ ህፃናት ውጪ ሂደው እንደታከሙ፣ ላለፉት 15 ዓመታት ደግሞ አሁን ባለው ማዕከል አገልግሎት እየሰጠ ነው።
በአጠቃይ እስካሁን 9,000 ህፃናት የልብ ቀዶ ጥገና እንደተደረገላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቷል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
🔈#ለጥንቃቄ
ከአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ፦
" በቅርብ ጊዚያት ውስጥ በቦሌ ቡልብላ የጨለማ ዝርፊያ በብዛት እየሰማን ነው።
ከሳምንት በፊት ሊናጋጋ ሲል 11:30 አከባቢ የቅርብ ወዳጄ የአምልኮ ተግባሩን አከናውኖ ሲመለስ ነበር ቪትዝ መኪና በርቀት በማቆም ከጀርባ መጥተው በማነቅ እና እራሱን ስቶ እንዲወድቅ በማድረግ በኪሱ የነበረውን እስከ 60 ሺህ የሚገመት ሞባይል ወሰዱበት።
ተመሳሳይ ወንጀል በተለያየ ሰዓት በአከባቢው ሲከሰት በ15 ቀን ውስጥ ለ4ተኛ ጊዜ እንደሆነ ከተለያዩ ነዋሪዎች ጋር በነበረን ውይይት መገንዘብ ችየለሁ።
በተለይ በምሽት ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ አስጠንቅቁልን። "
ከዚህ ቀደም መሰል ድርጊቶች በአዲስ አበባ ከተማ ሲፈጸሙ እንደነበር ይታወሳል።
አሁን አሁንማ መኪና በመጠቀም የሚፈጸም ዝርፊያ እየተለመደ ነው።
ከወራት በፊት መካኒሳ አካባቢ አንድ ግለሰብ ለስራ ሲወጣ እዛው ሰፈሩ ላይ በቪትዝ መኪና የመጡ ሰዎች አንገቱን ይዘው መሬት ላይ ከጣሉት በኃላ ዘርፊያ ፈጽመው እንደሄዱ መግለጻችን ይታወሳል።
እንዲሁም ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ በነጭ የቤት መኪና ታርጋ ባለው ዲኤክስ መኪና የመጡ በቁጥር 5 የሚሆኑ ስለት ያያዙ ጎረምሶች ምሽር ላይ አንድ ሰው አስቁመው ንብረት ዘርፈው መሰወራቸውንም ነግረናችሁ ነበር።
መኪና በመያዝ የሚፈጸም ዝርፊያ ስላለ የጸጥታ አካላት ልዩ ክትትል ቢያደርጉ መልካም ነው።
ውድ ቤተሰቦቻችን ሆይ እናተም በመንገዳችሁ ላይ ጥንቃቄ አድርጉ። ሁሌም ቢሆን ዙሪያ ገባችሁን ቃኙ። መኪና ይዞ የሚንቀሳቀስ ሁሉ ሃብታም ነው ማለት አይደለም። ስትንቀሳቀሱ በአትኩሮት ይሁን።
በተቻለ አቅምም የምትጠራጠሩትን ማንኛውም እንቅስቃሴ መኪና ታርጋ በቃል ለመያዝም መሞከሩ አይከፋም።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Infinix_HOT50_Pro+
አጅግ ዘመናዊ ሆኖ በተሰራው አዲሱ የኢንፊኒክስ HOT 50 Pro+ ህይወቶን ያዘምኑ ይዞ በመጣቸው አዳዲስ ቴክኖሊጂዎች ትምህርቶን፣ ስራዎን እና የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎትን ያቅሉ፡፡
@Infinix_Et|infinixet">@Infinixet
#Infinix #InfinixHOT50Pro+ #WOOOWNewHOT #InfinixHOT50Series