#OMEGA_COMPUTER_TRADING
ሁሉንም አይነት ላፕቶፖች ከእኛ ጋር ያገኛሉ።
ለድርጅቶች፣ ለቢሮ ሰራተኛዎችና ለተማሪዎች ከአስተማማኝ የ1 አመት ዋስትና እንዲሁም ከ በቂ መስተንግዶው ጋር ይዘን እንጠብቆታለን።
እኛ ጋር መሸጥም ሆነ መግዛት ይችላሉ !!
የቴሌግራም ቻናል ሊንክ
/channel/Omegacomputer2
አድራሻ : - መገናኛ ማራቶን የ ገበያ ማእከል በ ዋናው መግቢያ መሬት ላይ ወይንም ግራውንድ: ቁጥር 15 OMEGA COMPUTER
Inbox @teddyjo1 Call 0911539252 : 0913667240
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹
ከነገ ግንቦት 21 ጀምሮ ለ7 ቀናት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ የምክክር ምዕራፉን ይጀምራል። ከ2 ሺህ በላይ ሰዎችም ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃን።
የስብሰባው ሥርዓቶች ምንድናቸው ?
1. ማንኛውም ተሳታፊ #በነጻነት ሀሳቡን የመግለጽ መብት አለው። ሆኖም ተሳታፊዎች ከጥላቻ፣ ከአዋራጅ እና ከተንኳሽ ንግግሮችመቆጠብ፤
2. በምክክሩ ጊዜ መደማመጥን ከሚያውኩ፣ ሁከትን ከሚፈጥሩ እና መረጋጋትን ከሚነፍጉ ድርጊቶች እና ንግግሮች መቆጠብ፤
3. በጽሁፍ፣ ምልክት ወይም ድምጽ የጎንዮሽ ንግግር አለማድረግ እና ከተሳታፊዎች የሚቀርበውን ሃሳብ በአክብሮትና በጥሞና ማዳመጥ፤
4. እያንዳንዱ የምክክሩ ተሳታፊ የሚሰጠውን ሃሳብና የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ማክበር፣ በቅንነትና በታጋሽነት ማዳመጥ ፤
5. ሌላው ተሳታፊ ያቀረበውን ሃሳብ የመደገፍ ወይም የመቃወም ሁኔታ ሲኖር የሌሎች ተሳታፊዎችን መብት በሚያከብር መልኩ ማቅረብ፣
6. ተሳታፊው እድል ተሰጥቶት ሃሳቡን በመግለጽ ሂደት ላይ እያለ በማንኛውም ሁኔታ ያለማቋረጥ፤
7. የሰውን ክብር ከሚነኩ ነቀፌታዎች ፣ ዘለፋዎች ፣ ስብዕናን ከሚነኩ ንግግሮችና ድርጊቶች መቆጠብ፤
8. ሰዎች በሚያቀርቡት ሃሳብ እንዲሁም አስተሳሰብ ባይስማሙ እንኳ ሃሳባቸውን እና አስተሳሰባቸውን ማክበር፤
9. የሚሰጠውን ሀሳብ በቅን ልቦና ላይ የተመሠረተ ሆኖ ከውይይቱ አጀንዳ ጋር አግባብነት ያለው አጭር፣ ግልጽ ያልተደጋገመ እና የተፈቀደውን ጊዜ ባከበረ መልኩ መግለጽ፤
10. በሂደቱ ላይ ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ማብራሪያ እንዲሰጥ መጠየቅ ናቸው፡፡
#የኢትዮጵያ_ሀገራዊ_ምክክር_ኮሚሽን
#NationalDialogue
@tikvahethiopia
#Oromia
ኢሰመኮ ፦
- ታኀሣሥ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በግምት ከጠዋቱ 1፡30 ሰዓት አካባቢ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ጉዱሩ ወረዳ ውስጥ በተፈጸመ #የድሮን_ጥቃት ፦
° በየነ ጢቂ፣
° ጉደታ ፊጤ፣
° ሀብታሙ ንጋቱ፣
° ታዴ መንገሻ፣
° ዳመና ሊካሳ፣
° ዱጋሳ ዋኬኔ፣
° ሕፃን አብዲ ጥላሁን
° ሕፃን ኦብሳ ተሬሳ የተባሉ 8 ሰዎች ተገድለዋል።
በተጨማሪም፦
• ስንታየሁ ታከለ፣
• ሽቶ እምሩ፣
• ተሜ ኑጉሴ
• አለሚ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በአካባቢው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ #ኦነግ_ሸኔ ”) በሰፊው ይንቀሳቀስ የነበረ መሆኑን እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአካባቢው በሚደረጉ ውጊያዎች አልፎ አልፎ #በድሮን_ይጠቀም የነበረ መሆኑን ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
- ጥር 9/2016 ዓ/ም በሰሜን ሸዋ ዞን ፤ ደራ ወረዳ የሀገር መከላከያ ሰራዊት #ለሌላ_ግዳጅ አካባቢውን ለቅቆ ይወጣል። ይህን ተከትሎም የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነግ ሸኔ) ታጣቂዎች በማግስቱ አካባቢውን ከተቆጣጠሩ በኋላ “ ለመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ምግብ ስታቀርቡ ነበር ” በማለት 01 ቀበሌ የሚገኘው ሳላይሽ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ጥበቃ የነበሩት አቶ ስዩም ካሴን #በጥይት_በመምታት ገድሏል። አቶ ከበደ ዓለማየሁ የተባሉ ነዋሪን ከመኖሪያ ቤታቸው አስወጥተው ከወሰዷቸው በኋላ በአካባቢው ጫካ አስክሬናቸው ወድቆ ተገኝቷል።
- ጥር 13 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋት 2 ሰዓት ጀምሮ ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች በምዕራብ ጉጂ ዞን፣ ገላና አባያ ወረዳ ኤርገንሳ ቀበሌ ለሚኖሩ ነዋሪዎች የኩፍኝ በሽታ ክትባት ለመስጠት በመጓዝ ላይ በነበሩ ሠራተኞች ላይ በፈጸሙት ጥቃት የገላና አባያ ወረዳ አስተዳደር ጤና ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊን ጨምሮ ሁለት ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል። እንዲሁም 3 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
- ከየካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በአማራ ክልል ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ #የአማራ_ታጣቂ_ቡድኖች የኦሮሚያ ክልል ፤ በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ በሚገኙ አዋሳኝ ቀበሌዎች በሲቪል ሰዎች ላይ #በተከታታይ በፈጸሟቸው ጥቃቶች ፦
➡️ 25 ሲቪል ሰዎችን ገድለዋል ፤
➡️ 4 ሲቪል ሰዎች ላይ የአካል ጉዳትን አድርሰዋል
➡️ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሲቪል (ሰላማዊ) ሰዎችን #አግተው ወስደዋል። በታጣቂዎቹ በተፈጸመ ጥቃት በርካታ የመኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል።
- በሰሜን ሸዋ ዞን ፤ ደራ ወረዳ የሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶው “ ኦነግ ሸኔ ”) ታጣቂዎች ከኅዳር ወር 2016 ዓ/ም ጀምሮ በወረዳው በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች በሲቪል ሰዎች ላይ በፈጸሟቸው ጥቃቶች ፦
➡️ 15 ሲቪል (ሰላማዊ) ሰዎች #ተገድለዋል ፤
➡️ ቁጥራቸው ለጊዜው በትክክል ያልታወቀ በርካታ ነዋሪዎችን #አግተው_ወስደዋል ፤
➡️ በርካታ የቀንድ ከብቶችን ዘርፈዋል
➡️ መኖሪያ ቤቶችን አቃጥለዋል።
- መጋቢት 1/2016 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ስልካምባ ከተማ ላይ የኦሮሞ ነጸነት ሰራዊት (በተለምዶ “ #ኦነግ_ሸኔ ”) ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት የወረዳው አበዪ ሄቤን ቀበሌ ነዋሪ የነበሩ አቶ ሹመቴ ፋርስ እና ወ/ሮ ተቀባ አበጋዝ የተባሉ አረጋዊያን በመኖሪያ ቤቶቻቸው ፊት ለፊት ተገድለዋል።
- መጋቢት 16/2016 ዓ/ም ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 ባሉት ሰዓታት ማንነታቸው ያልታወቀ የታጠቁ ቡድኖች በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ 02 ቀበሌ ውስጥ 7 ሰዎችን ተኩሰው መግደላቸውን ለማወቅ ተችሏል። በዕለቱ በተፈጸመ ጥቃት የቀበሌው ነዋሪ የሆነ እና የምዕራብ አርሲ ሃገረ ስብከት የዶዶላ ደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆነ ግለሰብ ፣ ከባለቤቱ እና #ከ2_ልጆቹ ጋር በመኖሪያ ቤታቸው እያሉ እንዲሁም ሌላ አንድ ዲያቆን ከባለቤቱ እና ከእህቱ ጋር በመኖሪያ ቤታቸው መገደላቸውን ለማወቅ ተችሏል።
- መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም በዶዶላ ወረዳ በደነባ ቀበሌ በግምት ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ ላይ 4 የቀበሌው ነዋሪዎች ማንነታቸው ባልታወቀ የታጠቁ ሰዎች/ቡድኖች በጥይት ተመተው ሲገደሉ 5 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ለማወቅ ተችሏል።
- የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ( በተለምዶ “ #ኦነግ_ሸኔ ” ) በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን፣ አመያ ወረዳ ውስጥ “ የመንግሥት ሠራተኞች እና የመንግሥት ጸጥታ ኃይል አባላት ቤተሰቦች ናችሁ ” በሚል ወይም “ለመንግሥት አካላት ትብብር አድርጋችኋል” በሚል ምክንያት በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች በየካቲት እና ሚያዝያ ወራት በፈጸማቸው ተከታታይ ጥቃቶች በሲቪል ሰዎች ላይ ግድያ፣ አካል ጉዳት፣ እገታ፣ ንብረት ውድመት እና ዘረፋ ፈጽሟል።
ለምሳሌ ፦
👉 በወረዳው አቡዬ ጀብላል ቀበሌ የካቲት 7/ 2016 ዓ.ም. በፈጸመው ጥቃት 11 ሲቪል ሰዎችን ገድሏል፤ መኖሪያ ቤቶችንና ሞተር ብስክሌቶችን አቃጥሏል፤ የቀንድ ከብቶችን ዘርፏል።
👉 መጋቢት 27/2016 ዓ.ም. በወረዳው ቆታ ከተማ ላይ በፈጸመው ጥቃት 31 ሲቪል ሰዎችን ገድሏል፣ 3 ሲቪል ሰዎችን አቁስሏል፣ የቀንድ ከብቶችንና ሌሎች ንብረቶችን ዘርፏል እንዲሁም ንብረቶችን አቃጥሏል።
👉 ሚያዝያ 8/2016 ዓ/ም በደራ ቲርቲሪ ቀበሌ ላይ ታጣቂ ቡድኑ በፈጸመው ጥቃት 2 ሲቪል ሰዎችን ገድሏል ፣ ከ100 በላይ የተለያዩ የቀንድ ከብቶች ዘርፏል።
👉 በሚያዝያ 13/2016 ዓ/ም በጎምንቦሬ አሊይ ቀበሌ 36 የቀንድ ከብቶችንና 3 የሞቶር ብስክሌት ዘርፏል።
#Oromia #Ethiopia #EHRC
@tikvahethiopia
#ሪፖርት
በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በግጭት ዐውድ ውስጥና ውጭ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች አሳሳቢነትና ሥጋቶችን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሪፖርት አውጥቷል።
በሪፖርቱ ፦
- ከሕግ ውጭ ግድያ (በድሮን ጨምሮ) ፣ የሲቪል ሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመትና ዘረፋ፤
- የዘፈቀደ፣ ሕገወጥ፣ የጅምላና የተራዘመ እስራትና የተፋጠነ ፍትሕ እጦት፤
- እገታ
- አስገድዶ መሰወር እና ያሉበት ቦታ ሳይታወቅ አስሮ ማቆየት
- የሀገር ውስጥ መፈናቀል ... ተዳሰዋል።
° በጸጥታ መደፍረስ፣
° ከመንግሥት አካላት ተገቢውን ምላሽና ትብብር በወቅቱ ባለማግኘት
° በሌሎች ምክንያቶች ምርመራቸውና ክትትላቸው የዘገዩና የተጓተቱ በርካታ ጉዳዮችን መኖራቸው ተገልጿል።
እነዚህን ጉዳዮች በመርመርና ክትትል በማድረግ በተገቢው ጊዜ ይፋ የሚያደርግ ይሆናል ተብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከኮሚሽኑ የተላከለትን ዝርዝር ሪፖርት ከላይ አያይዟል፤ በጥሞና ያንብቡት።
ኢሰመኮ በግጭት ዐውድ ውስጥ እና ከዐውድ ውጭ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችንና ሥጋቶችን በአስቸኳይ ማቆም ይገባል ብሏል።
የአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎችን ጨምሮ ሁሉንም የትጥቅ ግጭቶች በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምና የሰብአዊ መብቶች መከበርን ማረጋገጥ እንደሚገባም አስገንዝቧል።
#EHRC
#Ethiopia #TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
(ኢትዮ ቴሌኮም)
እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!
ቴሌብር በዲጂታል ሥነ-ምህዳሩ ላይ በነበረው የላቀ አበርክቶ የስትራይድ አዋርድ 2024 ኢኮሲስተም ሻምፒዮን (Stride Award 2024 Ecosystem Champion) ተሸላሚ ሆነ!
የሽልማት መርሃግብሩን ያዘጋጀው የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሲሆን ኩባንያችን የዲጂታል ኢትዮጵያን ከመገንባት አንጻር በተለይም ለሀገራችን የዲጂታል ፋይናንስ መነቃቃት ላበረከተው የላቀ አስተዋጽዖ እውቅናው መበርከቱ ተገልጿል፡፡
ለዚህ ሽልማት ላበቃችሁን ለመላው የኩባንያችን ቤተሰቦች፣ ደንበኞቻችን፣ ባለድርሻ አካላት እና አጋሮቻችን ከልብ እናመሰግናለን!
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica #GSMA #ITU
#ETHIOPIA
' አልያንስ 2015 ' የተባለው 8 የአዉሮጳ የልማት ድርጅቶች ያቀፉት ተቋም ሀገራት ያሉበትን የረሃብ አደጋ ደረጃ የሚያመላክተውን የዓለም አቀፍ የረሃብ ኢንዴክስ (Global Hunger Index) ይፋ አድርጓል።
በዚህ የረሃብ መለኪያ ሪፖርት ከ125 ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ ከመጨረሻዎቹ 101ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
የሰቆጣ ቃልኪዳን የፕሮግራም አስተባባሪ ዶክተር ሲሳይ ሲናሞ ምን አሉ ?
- ሪፖርቱ ሲዘጋጅ ሀገራት ካሉበት ደረጃ አንጻር የተለያየ ደረጃ ይሰጣቸዋል።
- የረሃብ ደረጃው ባለፉት 20 ዓመታት በተሰሩት ስራዎች ከ53 በመቶ ወደ 26.1 በመቶ ዝቅ ብሏል። በጣም alarming ከነበረበት ወደ serious ደረጃ ነው የወረደው።
- አሁንም ብዙ ስራ ይቀራል።
- በሀገራችን ያለው የምግብ እና የስርዓተ ምግብ ሁኔታ ብዙ መሰራት አለበት።
- ሪፖርቱ በየዓመት ነው የሚወጣው። በቀጣይ ወጣቶችን ማዕከል ባደረጉ ስራዎች ትኩረት በማድረግ ለመስራት ያለው ሁኔታ ለማሻሻል ይረዳል።
- በአፍሪካ ያለው ከፍተኛ የወጣት ቁጥር በግብርናው ዘርፍ አሰማርቶ መጠቀም አለመቻል አፍሪካ በምግብ ራሷን እንዳትችል አድርጓል።
- ኢትዮጵያ ውስጥ 70 በመቶ የስራ እድል የሚመነጨው ከግብርና ሆኖ እያለ ያላደገው የግብርና ዘርፍ የሚፈለገውን ያህል የስራ እድል እንዳይፈጠር እንቅፋት ሆኗል።
እንደ ዓለም አቀፉ ሪፖርት በኢትዮጵያ እና በዓለም ዙሪያ ለታየው በምግብ እራስን ያለመቻል ችግር ፦
➡ የአየር ንብረት ለውጥ
➡ በየቦታው የሚደረጉት #ጦርነቶች
➡ የኢኮኖሚ መላሸቅ
➡ የኮሮና ወረርሽኝ ዋነኞቹ ናቸው።
በከፍተኛ የምግብ እጥረት እና በረሃብ አደጋ ውስጥ ላሉ ሀገራት መፍትሄ ተብሎ የተቀመጠው መንግሥታት ፦
° ትልቅ አቅም ያላቸው ወጣቶችን ወደ ስራ ገብተው ውጤት እንዲያመጡ ቦታ መስጠት፤
° ብድር ማመቻቸት፤
° ለስራ የሚሆኑ የተለያዩ ስልጠናዎች ማመቻቸት ይኖርባቸዋል የሚሉት ይገኙበታል።
በግብርናው ዘርፍ ለመዘናት የቆየው በበሬ ማረስ ተግባር ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በማዘመን በመጠንም በአይነትም ከፍ ያለ ምርት ማምረት ካልተቻለ ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት አሳስቢ ደረጃ ወደ መጨረሻው አስከፊ ደረጃ ልትደርስ ትችላለች ሲል ሪፖርቱ አስጠንቅቋል።
⚠️ ኢትዮጵያ በ2022 ሪፖርት ላይ 27.6 በመቶ በማስመዝገብ ከ121 ሀገራት 104ኛ ደረጃ ላይ ነበረች።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የዚህ መረጃ ምንጮች ፦ ሸገር ኤፍ ኤም ፣ የAlliance 2015 እና የGlobal Hunger Index ድረገጽ መሆናቸውን ያሳውቃል።
@tikvahethiopia
#OMEGA_COMPUTER_TRADING
ሁሉንም አይነት ላፕቶፖች ከእኛ ጋር ያገኛሉ።
ለድርጅቶች፣ ለቢሮ ሰራተኛዎችና ለተማሪዎች ከአስተማማኝ የ1 አመት ዋስትና እንዲሁም ከ በቂ መስተንግዶው ጋር ይዘን እንጠብቆታለን።
እኛ ጋር መሸጥም ሆነ መግዛት ይችላሉ !!
የቴሌግራም ቻናል ሊንክ
/channel/Omegacomputer2
አድራሻ : - መገናኛ ማራቶን የ ገበያ ማእከል በ ዋናው መግቢያ መሬት ላይ ወይንም ግራውንድ: ቁጥር 15 OMEGA COMPUTER
Inbox @teddyjo1 Call 0911539252 : 0913667240
#መቐለ
ከሳምንት በፊት " በአፈልጉን ማስታወቅያ " ስትፈለግ የሰነበተች ተማሪ በውሃ ጉድጓድ ውስጥ ሞታ ተገኘች።
ተማሪ ቤቴልሄም ገብረሚካኤል ነጋሽ ግንቦት 11 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ላይ ነው በመቐለ ከተማ ፤ ዓዲ ሓቂ ክፍለ ከተማ ዓዲ ሓውሲ ቀበሌ ከሚገኝ ቤትዋ እንደወጣች የቀረችው።
ዛሬ ግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ/ም ግን አስክሬኗ ደብሪ ቀበሌ ጨለዓንቋ ተብሎ በሚታወቅ ኩሬ ተጥሎ መገኘቱ ተገልጿል።
የ17 ዓመትዋ ተማሪ ቤቴልሄም በመቐለ የቀላሚኖ ልዩ ትምህርት ቤት የ10ኛ ክፍል ተማሪ የነበረች ስትሆን ከአንድ ሳምንት የአፋልጉን ጥሪ በኋላ በውሃ ጉድጓድ አስክሬኗ ተጥሎ መገኘቱ ብዙዎችን አስደንግጧል፤ አሳስዝኗል።
የተማሪዋ አስክሬን በፓሊስ ትእዛዝ ወደ ዓይደር ሪፈራል ኮምፕሬሄንሲቭ ሆስፒታል ተወስዶ ከተመረመረ በኋላ አመሻሽ በመቐለ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስትያን በክብር እንዲያርፍ ተደርጓል።
በቀብር ስነሰርዓቱ ላይ ቤተሰቦች፣ የቀላሚኖ ትምህርት ቤት ኮሙዩኒቲ ፣ ወዳጆች እና አብሮ አደጎችን ጨምሮ በርካታ ህዝብ በመገኘት የተሰማው ጥልቅ ሃዘን በእንባ በመታጀብ ገልጿል።
በቀብር ስርዓቱ ላይ የተገኘው ህዝብ ፍትህ ጠይቋል።
የአሟሟትዋ ጉዳይ እጅግ በጣም ያሳዘናቸው የተለያዩ የህብረተሰብ አካላት ወንጀሉ ተጣርቶ ወንጀለኞች ወደ ህግ እንደዲቀርቡ ጠይቀዋል።
ፖሊስ በጉዳዩ ላይ የሚሰጠው ዝርዝር ማብራሪያ ካለ ተከታትሎ እንደሚልክ የመቐለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ገልጿል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
#ግንቦት20
ነገ የደርግ መንግሥት የወደቀበት የግንቦት 20 በዓል ይከበራል።
በዓሉ በተለይ ኢህአዴግ ስልጣን ላይ በነበረበት ዓመታት በሀገር ደረጃ ስራ እና ትምህርት ተዘግቶ በድምቀት ሲከበር ቆይቷል።
ካለፉት 6 ዓመታት ወዲህ ግን በዓሉ የነበረውን ድምቀት አጥቶ ተቀዛቅዟል። ያም ቢሆን ግን የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በዕለቱ ዝግ ይሆናሉ።
የዘንድሮው የግንቦት 20 በዓልስ ?
በቅርቡ ይፋ የተደረገው እና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገና ያልጸደቀው " የሕዝብ በዓላት እና የበዓላት አከባበር ረቂቅ አዋጅ " ተከብረው በሚውሉ ብሔራዊ ባላት ውስጥ ግንቦት 20ን አላካተተም።
በእርግጥ አሁን ላይ ባለውም አዋጅ ሳይካተት እንደ ብሔራዊ በዓል ሲከበር ነው የቆየው።
በዓሉ በሕግ በዓልነቱ ታውቆ አከባበሩም ተዘርዝሮ ያልወጣ ቢሆንም እንደ ብሔራዊ በዓል ሲከበር ቆይቷል ፤ በዕለቱም ሰራተኞች የእረፍት ጊዜ ያገኛሉ።
ከዚህ በተያያዘ በርካቶች " ስለ ነገው በዓል ግልጽ ይሁንልን " ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ብሎ ያሰባቸውን አካላት " ነገ ግንቦት 20 ስራ ተዘግቶ ነው የሚውለው ? " ሲል ጠይቋል።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " አዲሱ የበዓላት ሕግ ገና አልጸደቀም፤ ስለዚህ ዝግ ነው " ሲሉ አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።
በተጨማሪም " ነገ በሚከበረው የግንቦት 20 በዓል መስሪያ ቤት ዝግ ነው ወይስ ክፍት ? " ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ደሲሳ ጥያቄ አቅርቦላቸዋል።
እሳቸውም ፤ " በካላንደር ላይ የተለወጠ ነገር ስለመኖሩ እርግጠኛ አይደለሁም። ካላንደር ይዘጋዋል " ብለዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው፣ " ካላንደር እንደሚዘጋው ነው የምናውቀው ለምን እንዳወዛገበ አይገባኝም " ሲሉ አክለዋል።
አንዳንድ መስሪያ ቤቶች ሠራተኞች ሥራ እንዲገቡ ጠርተዋል መጥራት ይችላሉ ? ለሚለው ጥያቄ በሰጡት ምላሽም ፣ " መስሪያ ቤቶች በራሳቸው ውሳኔ ሥራዎችን ሊያቅዱ ይችላሉ። ከሠራተኞቻቸው ጋር ተስማምተው " ብለዋል።
አክለው " መጥራት ይችላሉ ማን ይከለክላቸዋል። አብዛኞቻችን ሥራ የምንውልበት ጊዜ ይኖራል። ያ ማለት ግን ያንን አፍርሰው ሳይሆን መስሪያ ቤቶች፣ ሠራተኞች በፈቃዳቸው ነው " ሲሉ አስረድተዋል።
" እሁድም እኮ ሠራተኛ የምናስገባበት ወቅት አለ። እንጂ ከዚያ ያለፈ የተለዬ ነገር የለም " ነው ያሉት።
በሌላ በኩል ፥ የአሜሪካ ኤምባሲ ነገ የደርግ መንግሥት የወደቀበትን #የግንቦት_20 በዓል ምክንያት በማድረግ ሙሉ ቀን ስራ ዝግ ሆኖ እንደሚውል አሳውቋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba
@tikvahethiopia
#ቦይንግ
ቦይንግ የአፍሪካ ዋና መሥሪያ ቤቱን በአዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ እንደሚከፍት ማስታወቁ ተዘግቧል።
ውሳኔው ግዙፉ የኤሮስፔስ ኩባንያ ቦይንግ፤ በአፍሪካ ላቀደው የማስፋፊያ ስራ ኢትዮጵያ ከኬንያ እና ደቡብ አፍሪካ እንድትቀድም አድርጓታል።
ይህም ደግሞ ኬንያ ወይም ደቡብ አፍሪካ የቦይንግ የማስፋፊያ ቦታዎች ይሆናሉ የሚለውን ግምት ውድቅ አድርጓል።
እ.ኤ.አ. በ2023 ላይ ኢትዮጵያ እና ቦይንግ አንዳንድ የአውሮፕላን ክፍሎችን በኢትዮጵያ ለማምረት የጋራ ስምምነት አድርገዋል።
ቦይንግ በድረ-ገፁ ላይ እንዳሰፈረው " የአፍሪካ ዕምቅ የተፈጥሮ ሀብት እና እያደገ የመጣው ወጣት የሰው ሃይል በሚቀጥሉት ሁለት አስርተ ዓመታት ውስጥ በአየር ትራፊክ እና በአውሮፕላን ፍላጎት ላይ ከፍተኛ እድገት ያመጣል " ብሏል።
ቦይንግ ኩባንያ ፥ የአፍሪካውያን የመጓጓዣ አገልግሎት በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ከ1,000 በላይ አዳዲስ ጄት አውሮፕላኖችን እንደሚፈልጉ ገምቷል።
ከእነዚህ ውስጥ 80% ነባር አውሮፕላኖችን ለማስፋት ያለመ እንደሆነ DW Africa ዘግቧል።
@tikvahethiopia
የሕብረት ባንክ ማህበራዊ ገፆቻችንን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም: /channel/HibretBanket
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/HibretBank
ሊንክዲን: https://www.linkedin.com/company/hibretbank/
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/hibretbank/
ዩቲዩብ: hibretbanket" rel="nofollow">https://www.youtube.com/@hibretbanket
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ የምክክር ምዕራፉን ይጀምራል።
ለ7 ቀናት ያህል በሚቆየው የአዲስ አበባው ምክክር ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ2 ሺህ በላይ ሰዎች እንደሚሳተፉ ኮሚሽኑ ገልጿል።
በምክክሩ የውይይት የአጀንዳ ሀሳቦችን የሚያመጡ ለምክክሩ የሚቀርቡ ተሳታፊዎች ሲሆኑ ፤ እነዚሁ ተሳታፊዎች በተስማሙባቸው የጋራ አጀንዳዎች ላይ የመፍትሔ ሀሳቦችን እንደሚያቀርቡ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አመልክቷል። #DW
@tikvahethiopia
#ግሬስ_የቋንቋ_አካዳሚ
በዚህ ጊዜ ኢንግሊዘኛ ቋንቋ አለመቻል ከብዙ ነገር ወደኋላ ያስቀሮታል። ለእዚህም ግሬስ የቋንቋ አካዳሚ በ ይዘቱ ልዩ የሆነ የ 2 ወር ከ 15 ቀን የ ኦንላይን ኘሪምየም ስልጠና ይዞሎት ቀርቧል።
- ከ10 አመት በላይ ልምድ ባላቸው አስተማሪዎች
- በማንኛውም ቦታ ከስራ ሰዓት በኋላ የሚማሩት
ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ በ50% ቅናሽ ፈጥነው ይመዝገቡ። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮቻችን ይደውሉልን እንዲሁም ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
ስልክ ፦ 09-49-75-54-48 / 09-89-98-56-84
ቴሌግራም ቻናል
/channel/GraceEnglish_amh
" የሃይማኖት ጉዳዮች " ረቂቅ አዋጅ ምን ይዟል ?
በኢትዮጵያ አዲስ የተዘጋጀ " #የሃይማኖት_ጉዳዮች " ረቂቅ አዋጅ አለ። ይህ ረቂቅ አዋጅ በርካታ ጉዳዮችን ይዟል።
አንዱ የአምልኮና የመቃብር ቦታን የተመለከተ ሲሆን ፥ ረቂቅ አዋጁ ለሃይማኖት ተቋማት የመሬት አቅርቦት በመሬት አጠቃቀምና የሊዝ ሕጎች መሠረት ይወሰናል ይላል።
ለአምልኮ ወይም ለመቃብር ቦታ በተጠየቀበት አካባቢ ለሃይማኖት ተቋሙ ለተመሳሳይ ዓላማ የተሰጠ ቦታ አለመኖሩ ወይም ደግሞ #ተጨማሪ_ቦታ መስጠት አስፈላጊ መሆኑ መረጋገጥ እንዳለበትም ይገልጻል።
በተለያዩ ቤተ እምነቶች መካከል ላይ የሚኖረው ርቀት ቢያንስ 500 ሜትር መሆን አለበትም ይደነግጋል።
ትምህርትና የሃይማኖት ተግባራትን በተመለከተ ረቂቁ ፥ መደበኛ ትምህርት በሚሰጡ የመንግሥት / የግል ተቋማት የሚሰጠው ትምህርት ሃይማኖታዊ ይዘት የሌለው መሆን አለበት ይላል።
በትምህርት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውስጥ ሃይማኖታዊ ትምህርትን ማስተማር ወይም በቡድን ማምለክ ፈጽሞ የተከለከለ ስለመሆኑ ይገልጻል።
ሌላውረቂቁ ማንነትን ለመለየት ሚያስችሉ ሃይማኖታዊ አለባበሶችን ጥቅም ላይ ሊውሉ እንደማይገባ ይደነግጋል።
ከአለባበስን ጋር በተያያዘ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት " ሃይማኖታዊ ምልክቶችን እንደ ቤተ እምነቱ አስገዳጅ ሕግጋቶች #ልዩ_ሁኔታዎች እንደሚኖሩ መደንገግ ሲገባው፣ ሙሉ ለሙሉ ከትምህርትና ሥራ ገበታ የሚያስገድዱ ድንጋጌዎችን መያዙ አግባብ አይደለም " በማለት ለሰላም ሚኒስቴር አስተያየት ፣ ቅሬታ እና የመፍትሔ ሐሳብ ልኳል።
የመንግስት ስራ ኃላፊዎችን በተመለከተ መንግሥትን ወክለው በሃይማኖት በዓላት አከባበር ላይ መገኘት እንደማይችሉ ተቀምጧል።
በየት/ቤት ፣ በመኖሪያ ቤት እና በሕክምና ማዕከላት አካባቢ የሚደረግ አምልኮ በተመለከተም ፤ በአካባቢ ጥበቃ ሕግ የተቀመጠውን የድምፅ መጠን ያከበረ መሆን አለበት ይላል።
ካልተፈቀደ በስተቀር ማስተማርን ጨምሮ ሃይማኖታዊ ተግባራትን በሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች መፈጸም እንደማይቻልም ተቀምጧል።
የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ይህ በልዩ ሁኔታ በወንጌል አማኞች ላይ ጫና የሚፈጥርና ሕገ መንግሥታዊ የሆነ መሠረት የሌለው በመሆኑን መስተካከል ይኖርበታል በማለት ለሰላም ሚኒስቴር ደብዳቤ ልኳል።
#ሪፖርተርጋዜጣ
@tikvahethiopia
#የመውጫፈተና #ምረቃ
➡️ " ትምህርታችን በአግባቡ ብንጨርስም ለ8 ወራት ትዘገያላችሁ ተብለናል " - ተማሪዎች
➡️ " ይህ ውሳኔ የመጣዉ #ከትምህርት_ሚኒስቴር በመሆኑ ምንም ማድረግ አልቻልንም " - የኮሌጅ አመራሮች
➡️ " የመጀመሪያ ዲግሪ የሚማሩ ተማሪዎች የተቋም ቆይታቸው ቢያንስ 4 ዓመት ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር
ከሰሞኑን በርካታ #የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከምረቃ እና ከመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የቅሬታ መልዕክቶችን ልከዋል።
ቅሬታቸውን ከላኩት መካከል በአዲስ አበባ፣ በሀዋሳ ደሴ እና ሌሎች ከተማ የሚገኙ የኮሌጅ ተማሪዎች ይገኙበታል።
ተማሪዎቹ " በ4 አመታት ውስጥ ማጠናቀቅ ያለብንን ትምህርታችን በአግባቡ ጨርሰን ፤ ክሊራንስም ሆነ የመውጫ ፈተና ለመውሰድ ክፍያ ብንፈጽምም ድንገት ለ8 ወራት መቆየት አለባችሁ ተባልን " ሲሉ ገልጸዋል ።
ቅሬታ አቅራቢ ተማሪዎቹ ፦
° ከሌሎች ተመራቂ ተማሪዎች እኩል በሚባል ደረጃ ትምህርት እንደጀመሩ፤
° መወሰድ የሚጠበቅባቸው አስፈላጊውን ኮርስ ወስደው ማጠናቀቃቸውን፤
° የመዉጫ ፈተና የማዘጋጃ ቲቶሪያል መውሰዳቸውን ገልጸዋል።
ይሁንና " የመዉጫ ፈተናዉን ልንወስድ ጥቂት ቀናት ሲቀሩን የመመረቂያ ቀናችሁ ጊዜ በሚቀጥለዉ ዓመት ጥር ላይ ነው " በማለት የመውጫ ፈተናውን መውሰድ እንደማይጠቅመን እና የሀምሌ ወር ምረቃችን መሰረዙ ተነገረን ሲሉ ቅሬታቸዉን ገልጸዋል።
ተማሪዎቹ " ተመሳሳይ ባች ከሆኑ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች እኛ በምን ተለይተን ነው ይሄ የተደረገው ? ለምን ሌላው ሊፈተን ሲዘጋጅ እኛ ግን ' ብትፈተኑም ጥቅም የለውም ቀጣይ ዓመት ጠብቁ ' ተባልን ? ይህ በፍጹም አግባብነት የለውም ፤ መፍትሄ እንሻለን " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም ከደረሱት ብዛት ያላቸው ቅሬታዎች በመነሳት ኮሌጆችን ለማነጋገር ጥረት አድርጓል።
ከነዚህም ውስጥ አንዱ የሆነዉ የኢንፎ ሊንክ ኮሌጅ ፥ ተማሪዎቹ የሚጠበቅባቸዉን ኮርስና ሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮችን ማጠናቀቃቸዉን ልክ እንደሆነ ገልጿል።
ይሁንና የመመረቂያ ጊዜያቸዉ የተወሰነዉ ከትምህርት ሚኒስቴር በመጣ አቅጣጫ መሆኑን አስረድቷል።
ኮሌጁ ፤ ተማሪዎቹ #የተፈተኑበት_ጊዜ ምንም እንኳን 2012 ዓ/ም መሆኑን በወቅቱ ከትምህርት ሚኒስቴር በኩል ያገኙት 'የኦንላይን ዶክሜንት' ቢያሳይም በኋላ የመጣላቸዉ ኦሪጅናል ደግሞ 2013 ዓ/ም እንደሚል ገልጿል።
ይህም ደግሞ ተማሪዎቹን ወደኋላ እንደሚያቆያቸዉና ለሚቀጥሉት ወራት የተለያዩ ትሬኒጎችና የመዉጫ ፈተና መለማመጃዎች እየሰጡ ለማቆየት መታሰቡን አስረድቷል።
በሌላ በኩል ፤ ከትምህርት ሚኒስቴር ለተለያዩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከ አንድ ደብዳቤ ተመልክተዋል።
ደብዳቤው ፦
በ2013 ዓ/ም ሁለተኛ ሴሚስተር ትምህርት የጀመሩ ተማሪዎች ለሰኔ ወር 2016 ዓ/ም የመውጫ ፈተና እንዲወስዱ እንዲደረግላቸው የጠየቁ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዳሉ ያስረዳል።
ነገር ግን የትምህርት ሥልጠና ፓሊሲው የመጀመሪያ ዲግሪ የሚማሩ ተማሪዎች የተቋም ቆይታቸው ቢያንስ 4 ዓመት እንደሆነ እንደሚደነግግ ይገልጻል።
አንዳንድ ተቋማት ህጋዊ ባልሆነ አግባብ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና እንዲወስዱ መጠየቃቸውን በማንሳት ይህ የሚያስጠይቅ ነገር ስለሆነ ተቋማት ተማሪዎችን በአግባቡ በማብቃት የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥ እንዲሰሩ አስጠንቅቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተጨማሪ መረጃዎችን ከትምህርት ሚኒስቴር ጠይቆ ለማቅረብ ጥረት ያደርጋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahethiopia
#AddisAbaba
ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ መኪና ይዘው የነበሩ ሁለት ወጣቶች ከቤት እንደወጡ እስካሁን አልተመለሱም።
የመጀመሪያው ዳዊት አስናቀ ይባላል።
ተወልዶ ያደገዉ አዲስ አበባ ከተማ ነው። ከ4 ቀናት በፊት የጠፋ እሰካሁን ድረስ እንዳልተመለሰ ታውቋል።
ዳዊት ኮድ 2-B65248 ኮሮላ መኪና እያሽከረከረ ነበር።
ስልኩም አይሰራም ፤ በምን ሁኔታ ላይም እንዳለ አይታወቅም ብለዋል ቤተሰቦች።
ዳዊት ያለበትን የምታውቁ ወይም ደግሞ ያያችሁት ካላችሁ ቤተሠቦቹ ጭንቀት ላይ ናቸውና በስልክ ቁጥር 0918706526 / 0913412564 / 0911609294 በመደወል አሳውቋቸው።
ሌላኛው ፥ እዮብ አንዳርጌ ይባላል።
እዮብ በ14/9/2016 ከቤት እንደወጣ እስካሁን አልተመለሰም።
በወቅቱ ኮድ 1 አ/አ 30805 ታርጋ ያላት ቢጫ ያሪስ ይዞ ነበር።
ፈላጊ ቤተሰቦች እዮብን ያየ ወይም ያለበትን የሚያውቅ በስልክ ቁጥር 0913577424 / 0911116275 / 0910479302 / 0945576477 በመደወል እንዲያሳውቃቸው ተማጽነዋል።
@tikvahethiopia
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹
የመጅሊሱ ቅሬታ ምንድነው ?
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ህዝበ ሙስሊሙ ሀገራዊ ምክክሩን እጅግ እንደሚደግፈው ነገር ግን ከምክክሩ ተሳታፊዎች ጋር በተያያዘ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እንዳልተሰጠው በዚህም ምክንያት ቅሬታ እንዳደረበት ገልጿል።
ም/ቤቱ ያደረበት ቅሬታ " በምክክሩ ላይ የሙስሊሞች ውክልና አነስተኛ ነው ፤ ይህ ደግሞ በምክክር ውጤቱ ላይ ተጽእኖ እንዳያሳድር ስጋት አለኝ " የሚል ነው።
" #ከወረዳ እስከ #ክልል ድረስ የሚሳተፉት ተወካይ ሙስሊሞች ቁጥር እጅግ አነስተኛ ነው " የሚለው ም/ቤቱ ፥ " እንደ ሙስሊም በጋራ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ መግባባት ላይ ለመድረስ በቂ ተወካዮች አልተወከሉም " ብሏል።
የምክር ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ከማል ሀሩን ምን አሉ ? (ለሃሩን ሚዲያ)
- ሙስሊሙ ከምንም በላይ ምክክሩን ይፈልገዋል።
- ሙስሊሙ የቆዩ ችግሮች ስላሉበት ይሄን ምክክር እንዲሳካ በጣም ከሚደግፉት ማህበረሰብ ክፍሎች ዋነኛው ነው።
- ከሌሎች እምነቶች ሲነጻጸር ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለዚህ ምክክር ያለው ድጋፍ ፈጽሞ ሊወዳደር የሚችል አይደለም። ሙስሊሙ ይህንን ምክክር የሚፈልገው ያልተመለሱለት ጥያቄዎቹ እንዲመለሱለት ነው።
- ተወካዮች ከታች ሲመረጡ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ተሳታፊ እንዲሆን ያስፈልጋል። ኮሚሽኑም check and balance ማድረግ አለበት ፤ በትክክልም የዚህን ማህበረሰብ ጥያቄዎች የሚያነሱ ተወካዮች ተወክለዋል የሚለውን።
- የተሳታፊዎች ልየታ ከታች ጀምሮ ሲመጣ በትክክል ሁሉም ማህበረሰብ መወከሉን ማረጋገጥ ይገባል። ኮሚሽኑም ከሌሎች እምነቶች ጋር balance የማድረግ ስራ ይጠበቅበታል።
- ተሳትፎ ላይ ቁጥሩ የተዛባ ከሆነ፣ በጣም አነስተኛ ከሆነ ቅሬታ ስለሚያስከትል ጥንቃቄ ያስፈልጋል።
- ኮሚሽኑ አካሄድ የነበረው ሲቪል ማህበራት፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ መምህራን ፣ አርብቶ አደሮች፣ እድሮች፣ የፍትህ አካላት፣ የመንግሥት ሰራተኞች፣ ፖለቲከኞች የያዘ ነው በሃይማኖት መልክ ግን የቀረበ ነገር የለም። እነዚህ አደረጃጀቶች ምን ያህል ሙስሊሙ ተሳትፎ አለው ? የሚለው ያሳስበናል፤ ስጋትም አድሮብናል።
- የተነሱ ጥያቄዎችን እና ያሉትን ስጋቶች በተደጋጋሚ ለኮሚሽኑ ቀርበው የጋራ ኮሚቴ ጭምር እንዲቋቋም መረጃዎችም እንዲሰጡ ተጠይቆ በተለያየ ምክንያት ሊሳካ አልቻለም።
- ውይይቶች አድርገናል በተደጋጋሚ ፤ በውጤቱ ላይ የሙስሊሙን ተሳትፎ የሚያሳዩ መረጃዎች (ዳታ) ማግኘት አልተቻለንም።
- እንደ አጀንዳ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄዎች በ9 አጀንዳዎች ተካተው ፣ በ47 ጥያቄ ቀርቦ የካቲት 2 ላይ ለኮሚሽኑ ቀርቧል። መጨረሻ ላይ ኮሚሽኑ ያንን የማስፈጸም ኃላፊት አለበት።
- ታች ያለው የማህበረሰቡ ውክልና በተሻለ ሁኔታ ሁሉ የሃይማኖት ተቋማት ባገናዘበ፣ ሃይማኖት ተቋማትን balanced ባደረገ ሁኔታ መታየት አለበት ቁጥሩ። ለምሳሌ ፦ ከ12 ሺህ ምን ያህል ሙስሊም ተካቷል ፤ ከአዲስ አበባም ከ2500 ተሳታፊ ካለ ምን ያህል ሙስሊም ተሳታፊ ነው ? የሚለው ነው የማህበረሰቡ ጥያቄ።
- እኛ በቂ መረጃዎች የሉንም ለማህበረሰቡ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት አስቸጋሪ ነው። በአንዳንድ ሁኔታ ስናጣራ በጣም አነስተኛ ቁጥር ያለበት ስለሆነ የተሻለ ውጤት እንዲገኝ ጥያቄ በማያስነሳ መንገድ እንዲሄድ ማድረግ ይገባል።
- የሙስሊሙ ማህበረሰብ ተሳታፊ ቁጥር አነስተኛ ከሆነ የሚቀርበው አጀንዳ ይቀራል ፤ ያ ደግሞ እጅጉን ያሳስበናል።
- በእኛ በኩል አሁንም ምላሽ እየጠበቅን ነው።
#EthiopianMuslims
#HarunMedia
#NationalDialogue
@tikvahethiopia
#Amhara
ኢሰመኮ፦
- ከየካቲት 15 እስከ 28 ቀን 2016 ዓ/ም በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ደጋ ዳሞት ወረዳ (ዝቋላ ወገም፣ ፈረስ ቤት01፣ ገሳግስና ጉድባ ሰቀላ ቀበሌዎች) እና ሰከላ (አጉት፣ ጉንድልና አምቢሲ ቀበሌዎች እና ግሼ ዓባይ ከተማ) በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና በታጣቂዎች መካከል የተካሄዱ የትጥቅ ግጭቶችን ተከትሎ በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት፣ አካል ጉዳትና የንብረት ውድመት ደርሷል።
- የካቲት 20/2016 በሰሜን ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ ብራቃት ቀበሌ በሚገኘው የጋፊት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የአብነት ተማሪዎች የዕለቱን ትምህርትና ጉባኤ ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ አጠናቀው ወደ ማደሪያ ጎጇቸው ከገቡ በኋላ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች አባላት ከሌሊቱ 6፡30 ሰዓት ገደማ ላይ ወደ ቦታው ደርሰው ተማሪዎችን “ #ውጡ ” እያሉ ተኩስ በመክፈት ቀድመው በወጡ #በ11_ተማሪዎች ላይ ግድያ እንደፈጸሙ፤ ሌሎች 8 ተማሪዎችንም ደግሞ በቁጥጥር ሥር አውለው ካሳደሩ በኋላ በማግስቱ ምንም ጥፋት የለባችሁም ብለው እንደለቀቋቸው ኢሰመኮ ለመረዳት ችሏል። በወቅቱ በአቅራቢያው የሚንቀሳቀስ የታጠቀ ኃይል እንዳልነበር ምስክሮች አስረድተዋል።
- መጋቢት 2 ቀን 2016 ዓ/ም በኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን የተነሱ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር #በኤፍራታና_ግድም እና #ቀወት ወረዳዎች በሚገኙ የተወሰኑ ቀበሌዎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት በሲቪል ሰዎች ላይ ግድያ መፈጸሙን፣ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ ንብረት መውደሙን፣ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን እና የቀንድ ከብቶችና ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች መዘረፋቸውን ኢሰመኮ ተረድቷል።
- መጋቢት 6 ቀን 2016 በአማራ ክልል፣ በባሕር ዳር ከተማ ዘንዘልማ አካባቢ አቶ ብርሃኑ ሽባባው አካል ፣ አቶ በላይ አካል እና አቶ ተሾመ ይበልጣል የተባሉ ነዋሪዎች አንዱ በሚሠራበት ሱቅ እና ሁለቱ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ " ኑ ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ " በሚል በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ መጋቢት 7 ቀን 2016 በባሕር ዳር ቀበሌ 14 በተለምዶ ጉዶ ባሕር አካባቢ #የፊጥኝ_እንደታሰሩ በጥይት ተገድለው ተገኝተዋል።
- በባሕር ዳር ዳግማዊ ምኒልክ ክ/ከተማ ጋጃ መስክ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ መጋቢት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት በተፈጸመ ጥቃት ሶላት ስግደት አከናውነው ወደ ቤታቸው እየተመለሱ የነበሩ የእስልምና ተከታይ 5 ሰዎች (4ቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ) ተገድለዋል።
- ሚያዝያ 7/2016 ከጧቱ 3፡00 ሰዓት ላይ በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ አጎና ቀበሌ ላይ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከእስቴ ወረዳ ወደ ላይ ጋይንት ወረዳ በመጓዝ ላይ እያሉ በአካባቢው ላይ በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች (#ፋኖ ) ድንገተኛ የደፈጣ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ታጣቂዎቹ አካባቢውን ጥለው እንደሸሹ #የመንግሥት_የጸጥታ_ኃይሎች ወደ ቦታው በመግባት 7 (1 ሴትና 6 ወንዶች) ሲቪል ሰዎች ላይ ከሕግ ውጪ ግድያ ፈጽመዋል። ከ15 በላይ የሚሆኑ የቆርቆሮ ክዳን ያላቸው መኖሪያ ቤቶች እና 3 የገለባ ቤቶችና ንብረት መቃጠላቸውን እንዲሁም ከ100 በላይ የሚሆኑ የቀበሌው ነዋሪዎች ወደ ሌላ አካባቢ የተፈናቀሉ መሆኑን የቀበሌው ነዋሪዎች እና ተጎጂዎች ገልጸዋል።
- ግንቦት 4/2016 ዓ/ም ከቀኑ ከ7፡00 ሰዓት አካባቢ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ ተሬ ቀበሌ ውስጥ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በጉሎ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ግቢ ውስጥ 2 ሲቪል ሰዎች ሲገደሉ አንድ ሴት መምህርትን ጨምሮ ሌሎች 9 ሲቪል ሰዎች የቆሰሉ መሆኑን ኢሰመኮ ተረድቷል።
#Amhara #EHRC
@tikvahethiopia
#ሞደርን_ሾፒንግ_ሴንተር
ሞደርን ሾፒንግ እጅግ ዘመናዊ እና ጥራት ያላቸዉ አንዲሁም ኑሮን የሚያቀሉ የቤት ዉስጥና የኪችን እቃዎች የሚሸጡበት ገበያ ነዉ።
የሁሉንም እቃዎች ዋጋ እና ሌሎች ተጨማሪ እቃዎችን ለማየት የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ። ቴልግራም 👉 t.me/modernshoppingcenter
አድራሻ ፦ ቁጥር 1=ጉርድ ሾላ ሆሊ ሲቲ ሴንተር M06
ቁጥር 2= ጀሞ መስተዋት ፋብሪካ ፊትለፊት ራሐ ሞል ግራዉንድ ፍሎር
አዲስ አበባ ዉስጥ ያሉበት ድረስ በፈጣን ሞተረኞቻችን እንልክልዎታለን። ለክፍለሀገር ደንበኞቻችን ባሉበት ሐገር በመናሐሪያ እንልካለን።
#ተመስግናችኃል🙏
ከሳምንታት በፊት ' የልብ ክፍተት ' ችግር ስላለባት እና በአስቸኳይ መታከም ስላለባት የ9 ዓመቷ ብላቴና ሊያ የእገዛ መልዕክት ወደናተ ደርሶ ነበር።
በወቅቱም እናቷ ወ/ሮ መባ አላምረው ለህክምና 700 ሺ ብር መጠየቁን በመግለጽ አቅም ያለው ኢትዮጵያዊ ወገን ልጃቸውን ለመታደግ ትብብር እንዲያደርግላቸው ተማጽነው ነበር።
አሁን ላይ ጉዳዩ ከምን ደረሰ ? ስንል ጠይቀናል።
እናት ወ/ሮ መባ አላምረው ትላንትና ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ “ እናንተ ልበ ቀናዎች ባደረጋችሁት ድጋፍ ጭምር የልጄ ሰርጀሪ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል ” ሲል መልካም ዜና አሰምተዋል።
ወ/ሮ መባ በሰጡት ቃል ፦
“ አሁን በጥሩ ጤንነት ላይ ትገኛለች። ከ4 ቀናት ቆይታ በኋላ፣ እሁድ ግንቦት 18 ቀን 2016 ዓ/ም ወደ ቤቷ ገብታለች። ሰርጀሪዋ በጣም ውጤታማ እንደሆነ ዶክተሯ ነግሮኛል።
እናተን እንድገናኝ የረዳኝን ሀይሌ ከፍያለው ከፈረንሳይ እንዲሁም ዶክተር ፈቀደ አግዋር ፈጣሪ እድሜ ያድልልኝ።
#መላው_ኢትዮጵያውያን ፣ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ማመን በማልችለው ፍቅር እና በፈጣን ምላሽ በአጭር ቀን ውስጥ ልጄ ህክምና እንድታገኝ አግዛችሁኛል።
ቤተሰቦቼ ፣ ወዳጆቼ በሙሉ እርዳታችሁ ለዚህ ቀን ለማመስገን አድርሶኛል።
አሁንም ፀሎታችሁ አይለየኝ። አመሰግናለሁ ! ” ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ሪፖርት
የሀገራትን የረሃብ ደረጃ የሚለካው የረሀብ ኢንዴክስ (GHI) ሪፖርት ይፋ ተደርጓል።
በዚህም #ኢትዮጵያ 26.2 በመቶ በማስመዝገብ ከ125 ሀገራት ከመጨረሻዎቹ 101ኛ ደረጃን ይዛለች።
ኢትዮጵያ በ2022 ለይ ከ121 ሀገራት ውስጥ በ27.6 በመቶ በማስመዝገብ 104ኛ ደረጃም ይዛ ነበር።
በ2023 ሪፖርት የረሃብ ልኬቱ ቀንሶ 26.2 በመቶ ተሰጥቷታል።
ሪፖርቱ በየዓመቱ ይፋ የሚደረግ ነው።
በዚህ ጥናት ላይ የሀገራትን ደረጃ ለመስጠት ከሚዳሰሱ ዋና ዋና መሰረታዊ የሚባሉ ቁልፍ ጉዳዮች መካከል ፤ ከ5 ዓመት በታች ያሉ ሕፃናት የምግብ እጥረት ፣ ሞትና የምግብ አቅርቦት ዋነኞቹ ናቸው።
@tikvahethiopia
#Abyssinia_Bank
የሐጅ አካውንት በመክፈት ለታላቁ መንፈሳዊ ጉዞ ራስዎን በፋይናንስ ማዘጋጀት እንደሚችሉ ያውቃሉ? በአቢሲንያአሚን የሐጅ ኒያዎትን ያሳኩ!
አቢሲንያ አሚን ዕሴትዎን ያከበረ!
#የሐጅኒያ #የሐጅጉዞ #አቢሲኒያአሚን
#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia
#Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
" የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የተዘጋጀ ረቂቃ አዋጅ " ምን ይዟል ?
የሚከተሉት በዓላት በሀገርአቀፍ ደረጃ ተከብረው የሚውሉ ብሔራዊ በዓላት ናቸው ፡-
1. መስከረም አንድ ቀን የዘመን መለወጫ (እንቁጣጣሽ) በዓል
2. የካቲት ሃያ ሶስት ቀን የአድዋ ድል በዓል
3. ሚያዚያ ሃያ ሶስት ቀን የዓለም የሠራተኞች (የላብአደሮች) ቀን
4. ሚያዚያ ሃያ ሰባት ቀን የአርበኞች (የድል) ቀን በዓል
በተጠቀሱት ብሔራዊ በዓላት የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለሕዝብ አገልግሎት ዝግ ይሆናሉ፡፡
የሚከተሉት በዓላት በሀገርአቀፍ ደረጃ ታስበው የሚውሉ ብሔራዊ በዓላት ናቸው ፡-
1. የካቲት አስራ ሁለት ቀን የሰማዕታት ቀን
2. ሕዳር ሃያ ዘጠኝ ቀን የኢትዮጵያ ህብረ-ብሄራዊነት (የብሔር ብሔረሰቦች) ቀን
በተጠቀሱት ብሔራዊ በዓላት የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት ይሆናሉ፡፡
የሚከተሉት በዓላት በሀገርአቀፍ ደረጃ የሚከበሩ ኃይማኖታዊ በዓላት ናቸው ፡-
1. መስከረም አስራ ሰባት ቀን የመስቀል በዓል
2. በየአራት አመቱ የሚመጣው ልዩነት እንደተጠበቀ ሆኖ ታህሳስ ሃያ ዘጠኝ ቀን የሚውለው የገና ወይም የልደት በዓል
3. ጥር አስራ አንድ ቀን የጥምቀት በዓል
4. የስቅለት በዓል
5. የትንሳኤ (ፋሲካ) በዓል
6. የኢድ-አልአድሃ (አረፋ) በዓል
7. የመውሊድ በዓል
8. የኢድ አልፈጥር በዓል
በተጠቀሱት ኃይማኖታዊ በዓላት የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለሕዝብ አገልግሎት ዝግ ይሆናሉ።
⚠️ ይህ ገና ረቂቅ አዋጅ ሲሆን ገና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት #አልጸደቀም። ረቂቅ አዋጁ በም/ቤት ሲጸድቅና በነጋሪት ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ነው የጸና የሚሆነው።
ከላይ በተያያዘው ፋይል ሙሉውን ያንብቡ።
@tikvahethiopia
የግንቦት 2016 ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ #ረቡዕ ይከፈታል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዓመት ሁለት ጊዜያት ከሚካሔዱት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤያት አንዱ የግንቦት 2016 ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ነው፡፡
ይህ ጉባኤ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ርእሰ መንበርነት ረቡዕ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከጧቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በመንበረ ፓትርያርክ የቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሚከፈት ተገልጿል።
@tikvahethiopia
#Update
ከ 'አፍሪካ ህብረት' የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ በ6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር የምዝበራ ሙከራ የተከሰሱት እነ ቀሲስ በላይ የጠየቁት ዋስትና ውድቅ ተደርጎ ተደርጓል።
ጥያቄውን ውድቅ ያደረገው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
ከምዝበራ መኩራው ጋር በተያያዘ የተከሰሱት ፦
1ኛ. ቀሲስ በላይ መኮንን፣
2ኛ. በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማራው እያሱ እንዳለ ወ/መስቀል፣
3ኛ. በኮሚሽን ስራ ላይ የተሰማራው በረከት ሙላቱ ጃፋር፣
4ኛ. አለምገና ሳሙኤል ዲንሳ
5ኛ. የኒሞና ንግድ ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ አበራ መርጋ ተስፋዬ ናቸው።
ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያሉ ተከሳሾች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።
ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄም ውድቅ ተደርጎ በማረፊያ ቤት እንዲቆዩ ታይዟል።
ፍርድ ቤት ለግንቦት 29/2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
በዛሬ ችሎት ተጠርጣሪዎች የተከሰሱበት አዋጅ ከ10 ዓመት በላይ የሚያሳስርና ከባድ ፍርድ የሚያስከትል በመሆኑ ማረሚያ ወርደው ፍርዳቸውን ይከታተሉ ተብሏል።
ቀሲስ በላይ #የጤና_እክል እንዳለባቸው ጠቅሰዋል። በፌደራል ፖሊስ ጊዜያዊ ማቆያ ለመቆየት እንዲችሉ እንዲፈቀድላቸውም ጠይቀዋል።
ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የተወከለ መርማሪ የጊዜያዊ ማቆያው ቦታ ጥበት መኖሩን ጠቅሶ ወደ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ እንዲደረግ ጠይቋል።
ፍርድ ቤቱ እስከ ቀጣይ ቀጠሮ ግንቦት 29 ቀን ድረስ ባሉበት የፖሊስ ማረፊያ እንዲቆዩ ፈቅዷል።
4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾችን በሚመለከት የፌደራል ፖሊስ ተገቢ ጥረት አድርጎ አፈላልጎ እንዲያቀርባቸው ታዟል።
መረጃው ከኤፍቢሲና ዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ የተወሰደ ነው።
https://telegra.ph/fbc-05-27-2
@tikvahethiopia
#ትግራይ
በትግራይ፣ መቐለ የሚገኘው ፍሬምናጦስ የአረጋውያን ፣ የአእምሮ ህሙማንና የህፃናት እንክብካቤ ማእከል ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ሚገመት የገንዘብ የቁሳቁስ ድጋፍ ቃል ተገባለት።
ይህን የገንዘብና የአይነት ድጋፍ ቃል የተገባለት ትላንት " #አለሁ_ለፍሬምናጦስ " በሚል በመቐለ ከተማ በተካሄደ ዓለም አቀፍ የሆነ የገቢ ማሳባሰብያ የቴሌቶን ፕሮግራም ላይ ነው።
መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪንግ የተባለ የትእምት ኩባንያ በምግባረ ሰናይ ደርጅቱ ላክ በባለፈው ሚያዝያ ወር በተነሳ የእሳት ቃጠሎ የወደመውን አዳራሽ ሙሉ ለሙሉ መልሶ እንደሚገነባው ቃል ገብቷል።
ከዚህ በተጨማሪም የ20 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የጭነት መኪና፣ አምቡላንስ የምግባረ ሰናይ ድርጅቱ ለሚያሰገነባው ግዙፍ የእንክብካቤ ማእከል የሚውሉ ማሽነሪዎች በአገር ውስጥና በውጭ በጎ ለጋሾች ተበርክቷል።
የምግባረ ሰናይ ድርጅቱ መስራችና ስራ አስኪያጅ አባ ገብረ መድህን በርሀ ፥ " ጦርነት በፈጠረው ጉዳት ምክንያት #የአእምሮ_ህሙማን_ቁጥር በመጨመር ላይ በመሆኑ ድርጅቱ ለሚሰጠው የነፃ እንክብካቤ አገልግሎት የህዝቡ እገዛ ይሻል " ብለዋል።
ፍሬምናጦስ የአረጋውያን የአእምሮ ህሙማን የህፃናት እንክብካቤ ማእከል በአሁኑ ወቅት 29 አረጋውያን ፣ 206 የአእምሮ ህሙማን እና 40 አሳዳጊ የሌላቸውን ህፃናት ጨምሮ በአጠቃላይ #ከ275_በላይ ለሆኑ ወገኖች የተሟላ የመጠለያ አገልግሎት በመስጠትና በመንከባከብ ላይ ይገኛል።
በትግራይ በነበረው አስከፊ የሆነ ጦርነት ምክንያት ግን ወደ ማዕከሉ መግባት የሚፈልጉ ወገኖች ቁጥር በእጅጉ ጨምሯል።
ለማሳያ ባለፉት ወራት ብቻ 1500 የእእምሮ ህሙማን ወደ ማእከሉ ለመግባት መመዝገባቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከምግባረ ሰናይ ድርጅቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
#ሞደርን_ሾፒንግ_ሴንተር
ሞደርን ሾፒንግ እጅግ ዘመናዊ እና ጥራት ያላቸዉ አንዲሁም ኑሮን የሚያቀሉ የቤት ዉስጥና የኪችን እቃዎች የሚሸጡበት ገበያ ነዉ።
የሁሉንም እቃዎች ዋጋ እና ሌሎች ተጨማሪ እቃዎችን ለማየት የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ። ቴልግራም 👉 t.me/modernshoppingcenter
አድራሻ ፦ ቁጥር 1=ጉርድ ሾላ ሆሊ ሲቲ ሴንተር M06
ቁጥር 2= ጀሞ መስተዋት ፋብሪካ ፊትለፊት ራሐ ሞል ግራዉንድ ፍሎር
አዲስ አበባ ዉስጥ ያሉበት ድረስ በፈጣን ሞተረኞቻችን እንልክልዎታለን። ለክፍለሀገር ደንበኞቻችን ባሉበት ሐገር በመናሐሪያ እንልካለን።
#ኢትዮጵያ
በሀገሪቱ ውስጥ ያለ ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርቱን ለሰላም ሚኒስቴር ማቅረብ እንደሚኖርበት ፤ ከውጭ አገር የሚመጣ የገንዘብ ዕርዳታ በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ እንደሚኖርበት የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።
" የሃይማኖት ጉዳዮች አዋጅ " የተሰኘው ረቂቅ አዋጁ የሃይማኖት ተቋማቱ ተቀባይነት ያለው የሒሳብ አያያዝና የኦዲት ሥርዓት መዘርጋት እንደሚኖርባቸው፣ የኦዲት ሪፖርታቸውን ለሰላም ሚኒስቴር ማቀረብ እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡
ረቂቅ አዋጁ ምን ይዟል ?
- የሃይማኖት ተቋማት የሚጠቀሙት የሒሳብ አያያዝ ሥርዓት የገቢ፣ የወጪና አጠቃላይ የንብረት ዝርዝር የያዘ መሆን አለበት።
- የገቢ አሰባሰብና የወጪ አስተዳደር በሕጋዊ መንገድ ማከናወን አለባቸው።
- የሃይማኖት ተቋም በራሱ #የገቢ_ማስገኛ ሥራዎችን በሚያከናውንበት ጊዜ ለዚሁ ሥራ ሲባል የተለየ የባንክ ሒሳብ መክፈትና የተለየ መዝገብ መያዝ አለበት።
- ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ከውጭ የሚላክለትን የገንዘብ ዕርዳታ፣ ስጦታ ወይም ሌሎች የገንዘብ ድጋፎችን በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ አለበት። ሲያሳውቅም ፦
° የለጋሹን ድርጅት ወይም ግለሰብ ስም እና አድራሻ፣
° የተለገሰው የገንዘብ፣ ስጦታ ዓይነት እና መጠን ፣
° ስጦታው / ድጋፉ የተሰጠበት ልዩ ዓላማ መካተት አለበት።
- ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም የበጀት ዓመቱ ባለቀ በ3 ወር ውስጥ የፋይናንስ እንቅስቃሴውን በገለልተኛ ኦዲተር ማስመርመር አለበት። የኦዲተሩን አቋም እና የውሳኔ ሐሳብም መያዝ ይኖርበታል።
- የሰላም ሚኒስቴር የደረሰውን የኦዲት ሪፖርት አመቺ በሆነ መንገድ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ይኖርበታል።
#ሪፖርተርጋዜጣ
@tikvahethiopia
ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር
Yonatan BT Furniture
የዘመናዊነት ተምሳሌት!
አድራሻችን፦
1. ዊንጌት አደባባዩን ተሻግሮ: +251 995 27 2727
2. ፒያሳ እሪ በከንቱ : +251 957 86 8686
3. ሲ ኤም ሲ አደባባዩን አለፍ ብሎ: +251 993 82 8282
👉 Telegram: /channel/yonatanbt_furniture
👉 Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100087238034736
👉 TikTok: yonatanbtfurniture" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@yonatanbtfurniture
👉 Instagram: https://www.instagram.com/yonatanbtfurniture/
#ኢሰመጉ #ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ( #ኢሰመጉ ) ፤ መንግስት ከፍተኛ ጥቃትና ጫና እየፈጸመበት እንደሆነ ይህም አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን ትላንት ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።
ጉባኤው በተለያዩ ጊዜ ተፈጽመውብኛል ያላቸው ጥቃቶች እና ከፍተኛ ጫናዎች ምንድናቸው ?
- ኢሰመጉ አመራር ላይ በመንግስት የደህንነት ሰዎች የሚፈጸም ክትትል ፣ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ፤
- የሰብዓዊ መብት ክትትል ስራችሁን ካላቆማችሁ ፤ መንግሥትን በሰብዓዊ መብት ጥሰት መወንጀል ካላቆማችሁ ' ዋጋ ትከፍላላችሁ ' የሚል ዛቻ፤
- የሰብዓዊ መብት ጥሰት የምርመራ ስራ በሚሰሩ ሰራተኞች ላይ የመንግስት ጸጥታ አካላት አካላዊ ጥቃት ማድረስ ፣ መሳደብ፣ ማንገላታት፣ ከስራቸው እንዲቆጠቡ ማስፈራራት
- ምንም እንኳን ኢሰመጉ ላለፉት 32 ዓመታት በሀገሪቱ ህግ አግባብ ተመዝግቦ እየሰራ ቢሆንም በኦሮሚያ ክልል በጸጥታ ሰዎች " ፍቃድ የላችሁም " በማለት ማስፈራራትና የእስር ዛቻ መሰንዘር፤
- በአባላት ላይ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ህገወጥ እስር መፈጸም፤
- በአዲስ አበባ ተገቢ ያልሆኑ ክሶችን ለመመስረት እንቅስቃሴ ማድረግ ከፍተኛ ጫና ለማሳደር መሞከር ፤
- የኢሰመጉ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ከሀገር ውጭ ካሉ ስራዎችና ስብሰባዎች ወደሀገር ቤት ሲመለሱ ማንገላታት ፣ ማዋከብ ፣ክትትል ማድረግ ፤
.... የሚሉና ሌሎችም ይገኙበታል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በበጎ አድራጎትና ማኅበራት አዋጅ ቁጥር " 13/2011 " መሠረት ሐገር በቀል ድርጅት ሆኖ በ1984 ዓ.ም የተመሠረተ እና በምዝገባ ቁጥር " 1146 " ከ02/11/11 ዓ.ም ጀምሮ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዳግም ተመዝግቦ በሕጋዊነት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግሥታዊ ያልሆነ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት መሆኑን አስገንዝቧል።
(የኢሰመጉ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia