🔈#መምህራን
በወላይታ ዞን መምህራን በፖሊስ እየታሠሩ መሆኑን የታሳሪ ቤተሰቦች ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ገልጸዋል።
እስሩ የተፈፀመ ያለድ መምህራኑ ከደሞዝ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ፊርማ በማሰባሰብ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አቤቱታቸውን ለማስገባት መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል።
ፖሊስ መምህራኑን የሚያስረው " አመፅ ለመቀስቀስ ተንቀሳቅሰዋል፤ የዞኑን ገጽታ አጥፍተዋል " በሚል መሆኑን የታሳሪ ቤተሰቦች ተናግረዋል።
መምህር ዳንኤል ፋልታሞ በዳሞት ወይዴ ወረዳ በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በእንግሊኛ ቋንቋ መምህርነት በማገልገል ላይ ይገኛሉ።
መምህሩ በዞኑ ፖሊስ አባላት እስከታሠሩበት እስካለፈው ሰኞ ድረስ የመምህራን ደሞዝ እንዲከፈል ለመጠየቅ ፊርማ በማሰባሰብ ላይ እንደነበሩ የሚያውቋቸው የስራ ባልደረቦቻቸው ገልጸዋል።
መምህሩን ሌሊት ፖሊሶች ከቤት ይዘዋቸው እንደሄዱ ነው የ3 ልጆች እናት የሆኑት ባለቤታቸው ለሬድዮ ጣቢያው የጠቆሙት።
ፖሊሶች ሌሊት 9 ሰዓት ላይ ወደ ቤት እንደመጡ የጠቀሱት የመምህሩ ባለቤት " በወቅቱ ምንም የተፈጠረ ነገር አልነበረም። ቤተሰቡ በሙሉ በእንቅልፍ ላይ ነበር። ቤቱን አስከፍተው ከገቡ በኋላ አልጋ እና ፍራሽ ሳይቀር ፈትሸው ምንም ሊያገኙ አልቻሉም። በመጨረሻም ግን ባለቤቴን ይዘውት ሄዱ " ብለዋል።
ለደህንነታችን ሲባል ስማችን አይጠቀስ ያሉ ሌላ ሁለት የዚሁ ወረዳ ነዋሪዎች ባሎቻቸው ደሞዝ ይሰጠን ብለው የዳቦ ጥያቄ በማንሳታቸው ብቻ ታሰረውብናል ብለዋል።
" ፖሊሶች ወደ ቤት ሲመጡ ምንም አይነት የፍርድ ቤት መያዣ ወረቀት አላሳዩም " ያሉት የመምህራኑ ቤተሰቦች " የተሳሳተ መረጃ አሰራጭታችኋል " በሚል መያዛቸውን ከአንድ ፖሊስ አባል መስማታቸውን ተናግረዋል።
" የመምህራን ደሞዝ ይከፈል " በሚል የፊርማ ማሰባሰብ ስራ ሲያከናውኑ ከነበሩት መካከል 3 በቅርብ የሚያውቋቸው መምህራን መታሰራቸው የተናገሩ አንድ የዳሞት ወይዴ ወረዳ መምህር አስተባባሪዎቹ ከመታሠራቸው በፊት " እረፉ " የሚል መልዕክት ከወረዳው አመራሮች ተልኮባቸው እንደነበር ጠቁመዋል።
የወረዳው እና የዞን ኃላፊዎች ለቀረበው ክስ ምላሽ አልሰጡም።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት ሰብሳቢ አቶ አማኑኤል ጳውሎስ ለሬድዮ ጣቢያው ፤ " መምህራን ደሞዝ የመጠየቅ መብት መንግሥትም የመክፈል ግዴታ አለበት። የደሞዝ ጥያቄ በማቅረባቸው እሥርና ማስፈራሪያ ደርሶባቸዋል የሚል መረጃ እስከአሁን እኛ አልደረሰንም። ነገር ግን ድርጊቱ ተፈጽሞ ከሆነ ትክክል አይደለም። እኛም የምንታገለው ይሆናል " ብለዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።
@tikvahethiopia
#ኢትዮቴሌኮም
ጂ.ኤስ.ኤም.ኤ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በአጋርነት የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን ያዘጋጀውን በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የኢትዮጵያ ዲጂታላይዜሽን ሪፖርት ትላንት በአዲስ አበባ ይፋ አድርጓል።
ሪፖርቱ የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጥረት በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ በፈጠራ በማጎልበት እና ዘላቂ ልማትን በማምጣት ረገድ እያስመዘገበ ያለውን ውጤት እንዲሁም የሀገሪቱን ዲጂታል ስነ-ምህዳር ከማሳደግ አንጻር እየተደረገ ያለውን ጥረት ዳስሷል።
የጂ.ኤስ.ኤም.ኤ ዘገባ እንደሚያመለክተው የቴሌኮም ዘርፍ በኢትዮጵያ ቁልፍ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ሆኖ በመቀጠል እ.ኤ.አ በ2023 በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ ያበረከተው ተጨምሮ ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) 8% ደርሷል።
በሪፖርቱ የተዳሰሱ ግኝቶች ኢትዮጵያ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እያከናወነቻቸው ለሚገኙ ተግባራት ዓለም አቀፋዊ ዕውቅናን የሚፈጥርላት ሲሆን በተለይም ለዜጎች አካታች ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት ያላትን ቁርጠኝነት እንደሚያጎለብት ይታመናል፡፡
ኢንጅነር ባልቻ ሬባ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጂ.ኤስ.ኤም.ኤ እና ኢትዮ ቴሌኮም የዘርፉ ባለድርሻ አካላትን ያሰባሰበውን መርሃ ግብር በማዘጋጀታቸው ያላቸውን አድናቆት በመግለጽ ለቴሌኮም ኦፕሬተሮች የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያን ቀጣይ የዲጂታል ጉዞ ለማፋጠን ጠቃሚ ግብዓት ለሚሆነው የ ጂ.ኤስ.ኤም.ኤ አድናቆታችንን ለመግለጽ እንወዳለን።
ሪፖርቱን ያንብቡ፡ https://bit.ly/3NCN7Kx
(ኢትዮ ቴሌኮም)
#ነዳጅ
ዛሬ በአዲስ አበባ የምትንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ነዳጅ ያለባቸውን ማደያዎች ከያዙት የነዳጅ መጠን ጨምሮ ከላይ በምስሉ መመልከት ትችላላችሁ።
#AddisAbabaTradeBureau
@tikvahethiopia
ጁመዓ ሙባረክ!
ሕብረት ባንክ ሕብር ሀቅ በተሰኘው ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱ ስር የሚገኙትን በርካታ አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይጋብዝዎታል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!
📞 ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡
🤳 በቀላሉ አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ የቴሌግራም ገፃችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፡፡ /channel/HibretBanket
🌐 ሌሎች የማህበራዊ ገፆቻችንን እና ድህረ ገፃችንን linktr.ee/Hibret.Bank ይጎብኙ፡፡
#HibirHaq #IslamicBanking #ShariaCompliant #HibretBank
#BRICS+
በሩስያ፣ ካዛን ሲካሄድ የቆየው የBRICS+ አባል ሀገራት መሪዎች ጉባኤ ዛሬ ተጠናቋል።
ስብስቡ 13 ሀገራትን በአጋር (ፓርትነር) አድርጎ ተቀብሏል።
ሀገራቱን የBRICS አጋር (ፓርትነር) አድርጎ የተቀበለው በ2024 ምንም አይነት አዲስ ሙሉ አባል ሀገር ላለመቀበል በመወሰኑ ነው።
13ቱ ሀገራት ወደፊት የስብሰቡ ሙሉ አባል ሀገር ለመሆን እንደሚሰሩ ነው የተነገረው።
የBRICS+ ሙሉ አባል ሀገራት እነማን ናቸው ?
🇧🇷 ብራዚል
🇷🇺 ሩስያ
🇮🇳 ሕንድ
🇨🇳 ቻይና
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ
🇪🇹 ኢትዮጵያ
🇦🇪 የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ
🇮🇷 ኢራን
🇪🇬 ግብፅ ናቸው።
አሁን BRICS+ን በአጋርነት (ፓርትነር) ሆነው የተቀላቀሉት እነማን ናቸው ?
🇩🇿 አልጄሪያ
🇧🇾 ቤላሩስ
🇧🇴 ቦሊቪያ
🇨🇺 ኩባ
🇮🇩 ኢንዶኔዥያ
🇰🇿 ካዛኪስታን
🇲🇾 ማሌዢያ
🇳🇬 ናይጄሪያ
🇹🇭 ታይላንድ
🇹🇷 ቱርክ
🇺🇬 ዩጋንዳ
🇺🇿 ኡዝቤኪስታን
🇻🇳 ቬዬትናም ናቸው።
በካዛኑ የBRICS+ የመሪዎች ጉባኤ የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ፣ የቬንዝዌላው ፕሬዜዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ተገኝተው ነበር።
የሳዑዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም ካዛን ተገኝተው ነበር። ሳዑዲ ምንም እንኳን በይፋ የBRICS ስብስብን ባትቀላቀልም በተጋባዥ ሀገርነት ትሳተፋለች።
የሌሎች ሀገራት መሪዎችና ተወካዮችም በካዛን ተገኝተው ነበር።
#BRICSSummit #Russia
@tikvahethiopia
ኢትዮ 130 እንደተለመደው በ4ኛውም ዙር 100 ሺህ ብርን ጨምሮ ሌሎች አጓጊ ሽልማቶች ለዕድለኞች አበርክቷል!!
ዕድለኞች እንኳን ደስ አላችሁ!! 🎉🎉
🔥 ሽልማቶቹ ገና አልተነኩም 6ቱን ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢሎችን ጨምሮ በርካታ ሽልማቶች አሁንም እርስዎን ይጠብቃሉ!
💡ጥቅልና የአየርሰዓት በመግዛት፣ የአገልግሎት ክፍያዎችን በቴሌብር በመፈጸም እንዲሁም ገንዘብ በመላክና በመቀበል ተጨማሪ የጨዋታ ዕድሎችን ያግኙ!
🚘 6 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖች
🛺 9 ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች
💰በየቀኑ የ20 ሺህ ፤ በየሳምንቱ የ50 ሺህ እና 100 ሺህ ብር ገንዘብ ሽልማቶች በቴሌብር
📱 ዘመናዊ ስማርት ስልኮች እንዲሁም
🎁 በርካታ የሞባይል ጥቅሎች!
✅ እነዚህን አጓጊ ሽልማቶች የግልዎ ለማድረግ በቴሌብር ሱፐርአፕ ኢትዮ130 መተግበሪያ ወይም ለኢትዮ ፕሮሞ 1 ቁጥርን ወደ 130 በመላክ ለኢትዮ130 ላኪ ስሎት 131 ላይ Ok ብለው በመላክ ይመዝገቡ!
ለተጨማሪ መረጃ፡ https://bit.ly/3Y0pGzs ይጎብኙ!
#130_ዓመታትን_በጽናት_ታላቅ_አገርና_ሕዝብ_በማገልገል_ላይ
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#MoE
የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ።
በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።
ተማሪዎች ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።
በድረ-ገፅ 👇
https://placement.ethernet.edu.et
በቴሌግራም 👇
/channel/moestudentbot
የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።
@tikvahethiopia @tikvahuniversity
#ExchangeRate
የዶላር ምንዛሬ ዋጋ ጭማሪ አሳየ።
ባለፉት ቀናት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ113 ብር ከ1308 ሳንቲም እየተገዛ በ115 ብር 3934 ሳንቲም ሲሸጥ ነበር።
ዛሬ ይፋ በተደረገው የምንዛሬ ዋጋ ተመን አንድ ዶላር መግዣው ከ3 ብር በላይ ጨምሮ 116 ብር ከ6699 ሳንቲም የገባ ሲሆን መሸጫው ከ3 ብር በላይ ጨምሮ 119 ብር ከ0033 ሳንቲም ገብቷል።
በተመሳሳይ በሌሎችም የውጭ ሀገር የገንዘብ ምዛሬ ላይ ጭማሪ ታይቷል።
@tikvahethiopia
#ካዛን ፦ ከ16ኛው የ #BRICS+ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን የሀገራት መሪዎች የተናጠል ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
በተጨማሪም ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ፦
° ከተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) ፕሬዜዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን ፣
° ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዜዳንት ሲሪል ራማፎሳ
° ከኢራን ፕሬዝዳንት መስዑድ ፔዥሺካን ... ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
ቪድዮ ፦ አርቲ
@tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ከተማ ፓሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለኤ ኤም ኤን በሰጡት ቃል ፥ ከሰሜን ሆቴል ወደ አዲሱ ገበያ ይሄድ የነበረ ኮድ 3 43994 ሸገር ባስ ላይ ነው አደጋው የደረሰው።
እስካሁን የ1 ሰው ህይወት አልፏል። እድሜው ከ36 እስከ 40 የሚገመት ነው።
የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ ህክምና ተቋም ተልከዋል።
@tikvahethiopia
" ንፁኃንን ያለ አበሳቸው የማይገባቸውን ሰቆቃና ፍዳ እየከፈሉ ነው ! "
በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ምን ጠየቀ ?
ከተጀመረ ከአንድ ዓመት በላይ ባስቆጠረውና በአማራ ክልል በሁለት ተፋላሚ ኃይሎች መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት እየደረሰ ያለውን የከፋ የመብት ጥሰት፣ አገር በቀልና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች ምርመራ እንዲያደርጉበት በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ጠይቋል።
ከሰሞኑን ፎረሙ በጦርነት እየታመሰ ባለው የአማራ ክልል የጤና ተቋማትና አገልግሎት ላይ እየደረሰ ነው ላለው ቀውስ ምላሽ መስጫ ስትራቴጂ ይፋ አድርጓል፡፡
ይፋ በተደረገው ባለ 45 ገጽ ስትራቴጂ በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ዩኒሴፍ፣ የአለም ጤና ድርጅት፣ የተመድ የሥነ ሕዝብ ድርጅት፣ የአማራ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተሳትፈውበታል፡፡
ፎረሙ በስትራቴጂክ ሰነዱ ምን አለ ?
➡️ የጤናው ዘርፍ ከፍተኛ የሆነ አደጋ ተደቅኖበታል።
➡️ በጦርነት ምክንያት በርካታ የጤና ተቋማት ሥራ አቁመዋል።
➡️ ከ1,100 በላይ ሠራተኞች ተፈናቅለዋል ፤ ተገድለዋል።
➡️ ከ5,000 በላይ ሰዎች ለፆታዊ ጥቃት ተጋልጠዋል። ይህ ቁጥር የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑት ውስጥ ወደ ጤና ተቋም የመጡትና የተመዘገቡትን ብቻ የሚይዝ ነው።
➡️ በቀጠለው የደኅንነትና የፀጥታ ሥጋት የተነሳ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦትና የልማት አጋሮች በክልሉ የሚያደርጉት እንቅስቃሴና ድጋፍ በጊዜያዊነት ለማቆም እየተገደዱ ነው።
➡️ በጦርነቱ በመንገድ መዘጋት ምክንያት ወደ ክልሉ የሚላኩ መድኃኒቶችና የሕክምና መሣሪያዎች እንዳይገቡ ከመገደቡ ባሻገር፣ ከክልሉ ዋና ከተማ ባህር ዳር ወደ ዞንና ወረዳዎች ለመላክ አስቸጋሪ ሆኗል።
➡️ በርካታ የጤና ተቋማት በክልሉ ዝቅተኛውን የጤና አገልግሎት እንኳ ለህዝቡ ማቅረብ ተስኗቸዋል።
➡️ በሱዳን የሚካሄደውን ጦርነት ፈርተው ወደ አማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር መተማ የገቡ ሱዳናውያን ቁጥር ከ140 ሺሕ በላይ ደርሷል። የስደተኞች ቁጥር የጤና አገልግሎት ችግሩን አባብሶታል።
➡️ የኮሌራ በሽታ በክልሉ በ12 ዞኖችና በአራት የከተማ አስተዳደሮች ተከስቷል። የኮሌራን በሽታ ለመቆጣጠር አልተቻለም።
➡️ የአማራ ክልል ከሰሜኑ የኢትዮጵያ ጦርነት ውድመት ካለማገገሙ ባሻገር የሱዳን ጦርነት አማራ ክልል የቀጠለው ጦርነት፣ ድርቅ፣ ወባና ኩፍኝ ክልሉን አደጋ ውስጥ ጥለውታል።
➡️ መሠረታዊ የጤና አገልግሎቶችን ጨምሮ ሁሉም የሰብዓዊ ድጋፎች ያለምንም መስተጓጎልና ክልከላ ለሕዝቡ ተደራሽ እንዲሆን በጦርነት ውስጥ ያሉ ሁሉ ወገኖች ተባባሪ ሊሆኑ ይገባል።
የፎረሙ ዋና ጸሀፊ ታፈረ መላኩ (ዶ/ር) ለሪፖርተር በሰጡት ቃል ፥ " ንፁኃንን ያለ አበሳቸው የማይገባቸውን ሰቆቃና ፍዳ እየከፈሉ በመሆኑ፣ ሁለቱም ውጊያ ላይ ያሉ ወገኖች ያለምንም መስተጓጎል የጤና እና ሌሎች የሰብዓዊ አገልግሎትና አቅርቦቶችን ለሁሉም የክልሉ አካባቢዎች እንዲደርሱ መፍቀድ አለባቸው " ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ፤ ሰነዱ በውጊያ ላይ ያሉ ሃይሎች ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ሕጎችን እያከበሩ ባለመሆኑ ይህን እንዲያከብሩ የሚጠይቅ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡
አክለውም " የሴቶች መደፈር ትልቅ የሆነ ልብ የሚሰብር የመብት ጥሰት በመሆኑ ይህን ጉዳይ የመብት ተቆርቋሪዎች ሊመረምሩት ይገባል " ብለዋል፡፡
" የጤና ባለሙያዎች ደኅንነታቸው ሊከበር ይገባል ፤ የጤና ተቋማት በጦርነቱ ምክንያት በገጠማቸው የግብዓት አቅርቦት የደኅንነት ችግር የትራንስፖርት ችግርና የሰው ኃይል ችግር የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት እንዳይሰጡ አድርጓቸዋል " ሲሉ ገልጸዋል።
" የጤና ተቋማት አምቡላንስ በጣም በሚያሳዝን መንገድ ከተፈለገው ዓላማ ውጭ እየዋለ በመሆኑ ይህ ሊታረም ይገባል " ብለዋል፡፡
" በሰነዱ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ተብሎ የቀረበው ሰነድ በጤና ተቋማት የመጣውን ብቻ የያዘ ስለመሆኑ የሚገልጽ ነው። የሰብዓዊ ቀውሱን ሙሉ መረጃ የማያሳይ ቁንጽል መረጃ በመሆኑ የሰብዓዊ ተሟጋች ድርጅቶች የመብት ጥሰቱን እንዲመረምሩ ጥሪ እናቀርባለን " ሲሉ ተናግረዋል።
ስትራቴጂክ ሰነዱ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ችግሩን ተረድቶ ጫና እንዲያደርግና ሕጎች እንዲከበሩ በሚል ታስቦ የተዘጋጀ ነው። #ሪፖርተር
@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia
🌍✨በሳፋሪኮም ሮሚንግ ጥቅሎች የውጭ ሃገር ቆይታችንን ያለስጋት እናሳልፍ! በአፍሪካ ፣ በአውሮፓ ፣ በእስያ እና በሰሜን አሜሪካ ወዳሉ የተመረጡ ሃገራት ስንጓዝ ሳፋሪኮም አብሮን ነው! ከዳር እስከ ዳር አለምን ከአስተማማኙ ኔትወርክ ጋር እንቃኝ!
የቴሌግራም ቦታችንን /channel/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#1Wedefit #Furtheraheadtogether
#Infinix_TV
አለም አቀፉ የቲቪ እና የሞባይል ስልኮች ሲስተም አምራች ከሆነው ጎግል አንድሮይድ ጋር ይፋዊ ስምምነት ያለው የኢንፊኒክስ X5 ስማርት ቲቪ ከሌሎች ስማርት ቲቪዎች በተለየ መልኩ ተጨማሪ አፕሊኬሽኖች እና ተያያዥ አገልግሎቶችን በተለየ መልኩ ማግኘት እና ማስጠቀም ያስችላል፡፡
@Infinix_Et | infinixet?_t=8qe2yVJoUeU&_r=1">@Infinixet
#InfinixTVX5 #Infinix #ElevateYourSpace #Poweredbyandriod11 #tvx5
“ አንድ እንጀራ 30 ብር በገባበት ወቅት 450 ብር ለምን ይጠቅማል ? ለቤት ኪራይ፣ ወይስ ለቀለብ ነው የሚሆነው? ” - የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር።
የመምህራን የስልጠና ክፍያ እጅግ አነስተኛ መሆን ከኑሮ ውደነት ጋር ተያይዞ ፣ ዩኒቨርሲቲዎች ሲሰጡት የነበረውን የሙያ ስልጠና አለመስጠታቸው የትምህርት ጥራት ቀውስ ውስጥ እንዲገባ እያደረገ በመሆኑ ትኩረት እንዲሰጠው የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ጠየቀ።
ከማኀበሩ የተሰነዘሩ ቅሬታዎች ምንድን ናቸው ?
“ ከትምህርት ሥርዓት አንጻር በአሁኑ ሰዓት የትምህርት ጥራት ችግር ብቻ ልንለው አንችልም። የትምህርት ቀውስ ነው። ቀውስ ውስጥ ገብተናል። ወደ መምህራን ችግሩን የመግፋት ነገር ይታያል። ይሄ ትክክል አይደለም።
ሲጀመር የመምህርት ስልጠና ዋጋ አልተሰጠውም። ለምላሌ ፦ የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት እጩ መምህራን ከተወሰኑ ኮሌጆች ውጪ 450 ብር ተሰጥቷቸው ውጪ ሆነው እንዲማሩ የሚደረጉት።
አንድ እንጀራ 30 ብር በገባበት ወቅት 450 ብር ለምን ይጠቅማል ? ለቤት ኪራይ ወይስ ለቀለብ ነው የሚሆነው ? ችግሩ እዚያ ጋ ነው የሚጀምረው።
እጩ መምህራን ወደ ኮሌጅ ውስጥ ሲገቡ 450 ብር ይከፈላቸዋል። ፍላጎታቸውን ስለማይሟላ ትምህርት ላይ ትኩረት ሳያደርጉ ፍላጎታቸውን ለሟሟላት ይንቀሳቀሳሉ። ይሄ የመምህርነትን ሙያ ጥራቱን ቀንሶታል። ስለዚህ ጉዳዩ ሊታረብበት ይገባል።
የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር ጥናት አጥንቷል። በዚያ መልኩ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል።
በሌላ በኩል ፥ ወደ መምህርነት ሙያ ሴንተር ኦፍ ኤክሰለንሲ ተብለው እነዚህ የመቐለ ፣ ባሕር ዳር፣ የአዲስ አበባ፣ ጅማና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራንን የሚያሰለጥኑ ነበሩ ለ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች።
ነገር ግን ላለፉት ሦስትና አራት ዓመታት ምንም አይነት ተማሪ ወደ መምህርነት ሙያ እንዲገባ እያሰለጠኑ አይደለም።
ይሄ ደግሞ በቀጣይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቻችንን በድጎማ መምህር ልናስይዝ አይደለም ወይ ! ይሄ ወዴት እየሄደ ነው ?
በተያያዘ፣ የመፅሐፍት ስርጭት ችግሮች አሉ። ችግር መኖር ብቻ ሳንሆን አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ላይ በአንድ ላይ ኮምባይን የሆኑ ትምህርት ቤቶች አሉ።
ለምላሌ ፦ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስና ባይሎጂ አንድ ላይ ናቸው። በአንድ መምህር ነው የሚሰጡት። ይህም መምህራን ኬሚስትሪውን ፓርት ያስተምሩና ፊዚክስና ባይሎጂው የተመረቁበት ስለማይሆን ለማስተማር እየተቸገሩ ነው።
በሌሎች የትምህርት አይነቶችም ተመሳሳይ ችግር አለ። መምህር ያልተዘጋጀባቸው ሥርዓተ ትምህርቶች አሉ። የትምህርት ጥራቱን እየጎዳው ያለው አንዱ ችግር ይሄ ነው። አጠቃላይ ትምህርቱ ሴክተሩ በቂ ትኩረት አላገኘም። በቂ ፋይናንስ እየተመደበለት አይደለምና ሊመደብለት ይገባል።
መምህራንም የተለያዬ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ሲፈጠሩ መብታቸውን ለማስከበር ወደ ሕግ ተቋማት ስለሚሄዱ የትምህርት ጊዜ ይዘጋል። ይሄ ደግሞ የትምህርት ጥራት ላይ ችግር አምጥቷል። ”
እነዚህ ቅሬታዎች የትምህርት ሚኒስቴር በተገኘበት መድረክ እንደቀረቡ ማኀበርሩ ገልጾልናል።
የሚመለከታቸው አካላት ለጉዳዩ በቂ ትኩረት እንዲሰጡ ያሳሰበው ማኀበሩ፣ ትምህርት ሚኒስቴር በተነሱት ቅሬታዎች ዙሪያ መፍትሄ ለማምጣት አሳይመንት ይዞ እንደሄደ አመላክቷል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ኦርቶዶክስተዋሕዶ
" ...አለመግባባት በዝቷል፤ ማኵረፍና መቀያየም ሰፍቷል ፤ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባና የተመሰቃቀለ ሆኖ ይታያል፡፡ ችግሩ ከሕዝብ አልፎ የአምልኮ ስፍራዎችንና የአምልኮው ፈጻሚዎችን ዒላማ ያደረገ እግዚአብሔርን መዳፈር እየተለመደ መጥቷል " - ቅዱስነታቸው
የጥቅምት 2017 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ተጀመረ።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወሕዶ ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ አገልግሎትና የስራ አፈጻጸም ላይ ለመምከርና ለመወሰን ኃላፊነት ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ መደበኛና ዓመታዊ ጉባኤውን ጀምሯል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የጉባኤውን መጀመረ አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከመልዕክታቸው ፦
" የሰው ልጆች በዚህ ዓለም ሲኖሩ የተሟላ ሰላምና ጣዕመ ሕይወት ሊኖራቸው የሚችለው በመንፈሳዊ ኑሮአቸው የተሻለ ነገር ስላገኙ ብቻ አይደለም፡፡
ሰዎች ከሥጋዊ ክዋኔም ጭምር የተፈጠሩ እንጂ እንደመላእክት ሥጋ የሌላቸው መንፈስ ስላይደሉ ለኑሮአቸውና ለሥጋዊ ክዋኔአቸው የሚሆን ነገር ያስፈልጋቸዋል፡፡
በዚህም ዓለማዊው አስተዳደር የተመቻቸ መደላድል ሊፈጥርላቸው ግድ ነው፤ ዓለማዊው አስተዳደርም የመለኮትን ተልእኮ ለመፈጸም የተሾመ ሹመኛ እንደመሆኑ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በትክክል መምራት ይጠበቅበታል፡፡
ምንም ቢሆን የተቀበለው ኃላፊነት የእግዚአብሔር ነውና በሚሰራው ሁሉ በሿሚው አምላክ ከመጠየቅ አያመልጥም፡፡
እኛም በዚህ ዓለም የእግዚአብሔር ወኪሎች ስለሆንን ቢሰሙንም ባይሰሙንም ዓለማውያን ሹማምንትን የማስተማርና የመምከር ኃላፊነት አለብን፡፡
ይህ የሁለታችን ኃላፊነት እንደ እግዚብሔር ፈቃድ ስንፈጽም የሕዝብ ሰላምና በረከት፣ ፍቅርና አንድነት፣ ዕድገትና ልማት በአስተማማኝ ሁኔታ ይረጋገጣል፡፡
ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በሀገራችንም ሆነ በአካባቢያችን እየሆነ ያለው ይህ አይደለም፤ አለመግባባት በዝቶአል፣ ማኵረፍና መቀያየም ሰፍቶአል፤ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባና የተመሰቃቀለ ሆኖ ይታያል፡፡
ችግሩ ከሕዝብ አልፎ የአምልኮ ስፍራዎችንና የአምልኮው ፈጻሚዎችን ዒላማ ያደረገ እግዚአብሔርን መዳፈር እየተለመደ መጥቶአል፤ ይህ ለአንድ ሀገር ወይም ሕዝብ የውድቀት ምክንያት ከሚሆን በቀር ከቶውኑም የዕድገት ምልክት ሊሆን አይችልም፡፡
ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ደግሞ ይህ ክፉ ድርጊት እየተፈጸመ ያለው በእኛው ልጆች በኢትዮጵያውያን መሆኑ ነው፤ ስለሆነም በከተማም፣ በጫካም፣ በገጠርም በየትኛውም ስፍራ የምትገኙ ልጆቻችን ምንም ይሁን ምን ሀገርንና ሕዝብን ከመጉዳት ተቆጠቡ፡፡
በተለይም ከቤተ ክርስቲያንና ከሀገር እንደዚሁም ሕዝቡን ከሚያገለግሉ ካህናትና ሲቪል ሰራተኞች እባካችሁ እጃችሁን አንሡ፤ ቤተ ክርስቲያን እኮ የእናንተና የሕዝቡ ሁሉ እናት ናት፤ በእናታችሁ ላይ መጨከንን እንዴት ተለማመዳችሁት ? አሁንም ንስሐ ግቡ ያለፈው ይበቃል፡፡
ልብ በሉ ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት አይበጅም፤ ሰውን መጉዳትና እግዚአብሔርን መዳፈር አቁሙ፤ የእግዚአብሔር ገንዘብ የሆነውን ሥርዓተ አምልኮም ያለቦታው አታውሉ፤ ጥያቄአችሁን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ዕድል ስጡ፡፡
በእግዚአብሔር ስም ለመላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንና ልጆቻችን የምናስተላፈው ወቅታዊ መልእክታችን ይህ ነው፡፡ "
(የቅዱስነታቸው ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
አንጋፋው የቀድሞ ተጫዋችና አሰልጣኝ አሥራት ኃይሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ በተጫዋችነትና በአሰልጣንነት ግዙፍ አሻራቸውን ያሳረፉት አንጋፋው የእግር ኳስ ሰው አሥራት ኃይሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
በተጫዋችነት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ ጥጥ ማህበር እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ውስጥ ተጫውተዋል።
በአሰልጣኝነት በተለያዩ ጊዜያት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን እና የሀገራችንን ክለቦች በመምራት፤ የሴካፋ ድልን ጨምሮ የተለያዩ ስኬቶች በማስመዝገብ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ ቆይተዋል።
አሰልጣኝ አሥራት ኃይሌ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
#EFF
@tikvahethiopia
" ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ምዘና ከ100% የሚሰጠው ከማዕከል ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር
ትምህርት ሚኒስቴር በአቅም ማካካሻ (Remedial) ፕሮግራም ውጤት አያያዝ ላይ ማሻሻያ አደረገ፡፡
ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ከ50 በመቶ በታች ውጤት ካገኙ የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች መካከል የተሻለ ውጤት ያላቸውን በመምረጥ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማካካሻ (Remedial) ፕሮግራም ተመድበው የማካካሻ ትምህርት እንዲከታተሉ መደረጉ ይታወቃል።
በዚህ መሠረት ተማሪዎቹ 70% በማዕከል እና 30% በተቋማት የሚዘጋጁ ምዘናዎችን ተፈትነው ሲያልፉ የፍሬሽማን ፕሮግራም ተማሪዎች ሆነው እንዲቀጥሉ እየተደረገ ይገኛል።
ይሁን እንጂ ከ30% በተቋማት የሚሰጠው ውጤት አሰጣጥ ላይ ወጥነት የሌለ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፉት ሰርኩላር ገልፀዋል፡፡
በዚህም ዘንድሮ / ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ምዘና ፈተና ከ100% የሚሰጠው ከማዕከል እንዲሆን ተወስኗል፡፡
Via @tikvahuniversity
#ጤናባለሙያዎች
" ቀን ፣ ምሽት ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓል ወቅት ጭምር እየገባን ሰርተን ክፈሉን ስንል የሚሰጠን ምላሽ ማስፈራሪያ ነው " - ጤና ባለሙያዎች
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የዲዩቲ ክፍያ አልተከፈለንም ያሉ ከ 80 በላይ የጤና ባለሞያዎች ስራ ማቆማቸው ተሰምቷል።
በከምባታ ጠምባሮ ዞን ፤ አንጋጫ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች የ6 ወር የዲዩቲ (የትርፍ ሰዓት ስራ ክፍያ) ስላልተከፈላቸው ከማክሰኞ 12/02/17 ዓ/ም ጀምሮ ስራ ማቆማቸው ተሰምቷል።
በአመት ከ120 ሺ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የህክምና አገልግሎት የሚሰጠው የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ የሚሰሩ በቁጥር ከ80 በላይ ይሆናሉ የተባሉት የጤና ባለሞያዎች ከማክሰኞ ጀምሮ ስራ ያቆሙ ሲሆን የሆስፒታሉ አስተዳደር በበኩሉ እስከ ትላንት ድረስ ወደ ስራቸው ካልተመለሱ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወስድባቸው በደብዳቤ አሳውቋቸዋል።
ይሁን እንጂ እስከ ዛሬ ወደስራ ገበታው የተመለሰ ባለሞያ አለመኖሩን ሰምተናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው በሆስፒታሉ የሚሰሩ ባለሞያዎች " ከዚህ በፊትም በስራ ላይ ሆናችሁ ጥያቄያችሁን አቅርቡ ተብለን ተስማምተን ጀምረን ተታለናል ሳይከፈለን የመጀመር ፍላጎት የለንም " ሲሉ ገልጸዋል።
ክፍያው ያልተከፈለው የ2015 ዓ/ም የግንቦት ወር የ2016 ዓም የመስከረም፣ ጥቅምት፣ ጥር እና የነሀሴ ወር የ2017 ዓ/ም የመስከረም ወር በአጠቃላይ የ6 ወር የዲዩቲ ክፍያ ነው።
" ከዚህ በፊት የ4 ወር ክፍያ ባልተከፈለን ወቅት በወረቀት በዞን እና በክልል ደረጃ ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቀን ነበር ነገር ግን ችግራችን አልተፈታም ከዚህ በላይ በትዕግስት መጠበቅ አልቻልንም ለተለያዩ ማህበራዊ ቀውሶች እየተዳረግን ነው " ብለዋል።
አክለው " ቀን ፣ምሽት ፣ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓል ወቅት ጭምር እየገባን ሰርተን ክፈሉን ስንል የሚሰጠን ምላሽ ማስፈራሪያ በመሆኑ እና ' እየሰራችሁ ጠይቁ እንጂ ሥራ ማቆም አትችሉም ' በማለት እንዲሁም የሚያስተባብሩትን አካላት ' በህግ እንጠይቃለን ' የሚል ማስፈራሪያ ከወረዳ አስተዳዳሪዎች እየደረሰን ነው " ብለዋል።
ባለሙያዎቹ " አምና ጥር ወር ላይ በተመሳሳይ ስራ አቁመን የነበረ ሲሆን የክልሉ ጤና ቢሮ እና የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ጭምር አመልክተው ' እናንተ በስራ ላይ ተገኙ እንጂ እንዲከፈል እንነግራለን ' በማለታቸእ ወደ ስራ ተመልሰን ነበር ፤ ምንም ምላሽ ሳይሰጠን ቆይቶ በኋላ የአንድ ወር እንዲከፈለን ተደርጓል ፤ ከዚያ በኋላ ግን በተለመደው መቆራረጥ ነው የቀጠለው " ሲሉ ገልጸዋል።
ክፍያው እየተቆራረጠ ነው የሚገባው ወደ ኋላ ተመልሶ ያልተከፈለንን ክፍያ የመክፈል ምንም ፍላጎት የለም ነው ያሉት።
" የፊቱን እንከፍላለን ወደ ኋላ ተመልሶ ለመክፈል ግን ዞኑ በጀት የሌለው በመሆኑ በጀት ሲለቀቅልን ነው የምንከፍለው " የሚል ምላሽ እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል።
ሆስፒታሉ ዝግ ሆኖ በቆየባቸው ቀናት ሁለት ነብሰ ጡር እናቶች ምጥ ይዟቸው ወደ ሆስፒታል መጥተው የነበረ ሲሆን ባለሞያ በሆስፒታሉ ባለመኖሩ ወደሌላ ሆስፒታል በግል ትራንስፖርት በሚጓዙበት ወቅት የህፃናቱ ህይወት እንዳለፈ አክለዋል።
ሀኪሞች ሥራ በማቆማቸው ታካሚዎችም ከሆስፒታል በር እየተመለሱ መሆኑም ተነግሯል።
ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ በተመሳሳይ የስራ ማቆም አድማ ባደረጉበት ወቅት ሆስፒታሉ የወሰደው እርምጃ ያለምንም የቅጥር ማስታወቂያ 17 ሰዎችን መቅጠሩን የተናገሩት ጤና ባለሙያዎቹ " አሁንም ችግራችንን ከመፍታት ይልቅ ከሌሎች ቦታዎች ባለሞያ አምጥተን እንቀጥራለን በሚል እያስፈራሩ ነው " ብለዋል።
" ' ባለሞያ እንቀጥራለን እንደለቀቃቹ ቁጠሩት መጥታቹ ቁልፍ አስረክቡ ንብረት ላይ ቆልፋቹሃል ' በሚል ከፖሊስ ማዘዣ በማውጣት ማስፈራሪያ እየተደረገ ነው ፤ እኛ ሥራ እንለቃለን እላልንም እንሰራለን ግን ክፈሉን ነው ያልነው ተርበናል፣ ገንዘብ አጥተናል፣ ልጆቻችንን ማስተማር አልቻልንም የወተት እና የቤት ኪራይ መክፈል ከአቅማችን በላይ እየሆነ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
ቲክቫህ የባለሞያዎቹን ቅሬታ ይዞ የሆስፒታሉን ሥራ አስኪያጅ አቶ ተሰማ አበራን ትላንት ቢያነጋግርም ስብሰባ ላይ መሆናቸውን በመግለጽ ለጊዜው ምላሽ አልሰጡም።
ምላሻቸውን እንዳገኘን የምናካትት ይሆናል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
“ የመምህራን ደመወዝ በዘመቻ በሚባል መልኩ ይቆረጣል ” - ማኀበሩ
“ በተለይ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ጋምቤላ፣ ቤንሻንጉል ክልሎች የመምህራን ደመወዝ በዘመቻ በሚባል መልኩ ይቆረጣል ” ሲል የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ማኅበሩ 37ኛ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባ በአዳማ ከተማ ከጥቅምት 7 እስከ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ/ም አካሂዶ የነበረ ሲሆን፣ የመምህራን ቅሬታዎች ትምህርት ሚኒስቴር በተገኘት መቅረባቸውን ገልጿል።
መምህራን እየገጠሟቸው ያሉ በርካታ ችግሮች መኖራቸውን የገለጹት የማኀበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አበበ ችግሩ በወቅቱ እንዲፈታ አሳስበዋል።
ማኀበሩ በዝርዝር ምን አለ ?
“ ክልሎችና ዩኒቨርሲቲዎች በተገኙበት የተለያዩ አጀንዳዎች ተነስተዋል። የተነሱት አጀንዳዎችም እንደ ክልል የመልካም አስተዳደር ችግሮች አሉ የሚሉ ናቸው።
በየክልሎች የተለያዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች አሉ፡፡ ከመልካም አስተዳደር ችግር ደግሞ የጸዱ አካባቢዎች አሉ፡፡ በተለይ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሀረር አካባቢ የከፋ የመልካም አስተዳደር ችግር የለም።
ጦርነቱ በአማራ ክልል መምህራን ተረጋግተው እንዲሰሩ፣ ተማሪዎቹም ተረጋግተው እንዲማሩ እያደረገ አይደለም፡፡ ወደ 3,000 የሚሆኑ ት/ቤቶች ከሥራ ውጪ ናቸው፡፡
በዛው ልክ ደግሞ በእነዚህ ት/ቤቶች ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎችና መምህራን ከሥራ ውጪ እንደሆኑ ተገጿል።
እንደ ኦሮሚያ ክልልም ብዙ ቃል የተገቡ ነገሮች ነበሩ ነገር ግን አልተተገበሩም (በተለይም ከመኖሪያ ቤት አንጻር)፤ ይሄ መስተካከል አለበት፡፡ የተሻለ ነበረ ኦሮሚያ አፈጻጸሙ ግን በዚህ ዓመት ብዙ ርቀት አልሄደም።
ከእነዚህ ክልሎች ውጪ ያሉት ደግሞ በተለይ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ጋምቤላ፣ ቤንሻንጉል ክልሎች የመምህራን ደመወዝ በዘመቻ በሚባል መልኩ ይቆረጣል።
ይሄ በጣም የከፋ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ ነው የተነሳው።
በአፋር ክልልም ለረዥም ጊዜ የደረጃ እድገት፣ የትምህርት ማሻሻያ ያልተከፈለበት ሁኔታ አለ።
በትግራይ ክልል የ17 ወራት የመምህራን ደመወዝ አልተከፈለም። የአምስት ወሩን ክልሉ እከፍላለሁ ብሎ ነበር እስካሁን አልከፈለም።
የክልሉ መምህራን ማኀበር ጠበቃ ቀጥሮ ክስ መስርቷል። በሕግ ሂደት ላይ ነው ” የሚሉ ቅሬታዎች ተነስተው መፍትሄ እንዲሰጥ መጠየቁን ገልጿል።
ከትምህርት ሚኒስቴር ባለድርሻ አካላት ባሉበት ለተነሳው ቅሬታ ታዲያ ምን የመፍትሄ አቅጣጫ ተቀመጠ ? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ፣ የትምህርት ሚኒስቴር ጉዳዩን እንዳዳመጠ፣ በቀጣይ ለመፍትሄ እንደሚሰራ መጠቆሙን ማኅበሩ አስረድቷል።
ማኀበሩ በመጨረሻም የተነሱት ቅሬታዎች ምላሽ እንዲያገኙ በአንክሮ ጠይቋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Tigray
" በፓለቲካ አመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነት ወደ ፀጥታ ሃይሉ እንዲጋባ የሚያደርግ ቅስቀሳና ነጭ ውሸት አልታገስም " - የትግራይ ክልል የፀጥታ እና የሰላም ቢሮ
የትግራይ ክልል ፀጥታ እና ሰላም ቢሮ ባወጣው መግለጫ ፤ " የህዝብ እና የሰራዊት አንድነት በማላላት የአርስ በርስ ግጭት እንዲከሰት የሚሰሩት ግለሰቦች እና አካላት አንታገስም " ብሏል።
እንዲህ ያለው ተግባር ላይ ስለተሰማሩት ግለሰቦችና አካላት በግልጽ ስም ጠቅሶ ያለው ነገር የለም።
ቢሮው ፥ " በአገር ውስጥ እና በውጭ በመሆን በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች በመጠቀም በሬ ወለደ ውሸት በመንዛት በክልሉ የፀጥታ ሃይልና ህዝብ መካከል ያለው አንድነት እንዲላላ እየተሰራ እያየን በትእግስት ለማለፍ መርጠናል " ብሏል።
" ከአሁን በኋላ ህግ እንዲከበር በጥብቅ ይሰራል " ሲል አስታውቀዋል ።
" በፀጥታ ሃይሉ ጉድለት አለ የሚል አካል ተጨባጭ አሳማኝ መረጃ በማቅረብ ህጋዊ በሆነ መልኩ ጥያቄ ማቅረብ ይቻላል " ያለው ቢሮው " ይሁን እንጂ ፓለቲካ አስታኮ የሚነዛ የማህበራዊ ሚዲያ ገፅ ውሸት በግለሰብም ሆነ በየትኛውም አካል አያሰጠይቅም ማለት እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል " ሲል አስጠንቅቀዋል።
" በፓለቲካ አመራሮች መካከል የተፈጠረውም ልዩነት ወደ ፀጥታ ሃይሉ እንዲጋባ የሚያደርግ ቅስቀሳና ነጭ ውሸት አልታገስም " ሲልም ገልጿል።
ቢሮው ፤ " የፀጥታ ሃይል የማንም የፓለቲካ ቡድን መሳሪያ አይደለም " ሲልም አክሏል።
የፀጥታ ኃይሉ በክልሉ ባለው የፓለቲካ መከፋፈል መካከል ገብቶ የአንዱ ደጋፊ የሌላው ተቃዋሚ እንዲሆን ታልሞ የማህበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴ መሆኑን የገለጸው ቢሮው " ይህ አይሳካም ፍፁም ተቀባይነት የለውም፤ ይህንን ተላልፎ የሚገኝ ግለስብና አካል በህግ እንዲጠየቅ በማድረግ የህግ ልእልና እንዲከበርና የህዝቡ ሰላምና ፀጥታ እንዲከበር እንሰራለን " ብሏል።
#TikvahEthiopiaMekelleFamily
@tikvahethiopia
#DStvEthiopia
ዛሬ ምሽት ማን ዩናይትድ ከቀድሞ አሰልጣኛችው ሞሪኒዮ ጋር ይገናኛሉ!
ወደ ቱርክ ተጉዞ ከፌነርባቼ ጋር ይጫወታል! ይህንን ደማቅ ፍልሚያ በቀጥታ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት በቀጥታ በSS Football በ ቻናል 225 በጎጆ ፓኬጅ ይከታተሉ።
ዩናይትድ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ይችላል?
👉 ዛሬውኑ ፓኬጅዎን ያሳድጉ ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሜዳ ፕላስ ፓኬጅ ይከታተሉ!
ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ 👇
www.dstv.com/en-et
ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh
#ነዳጅ ፦ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የነዳጅ ማደያዎች እለታዊ የነዳጅ አቅርቦት መጠንን ከትላንት ጀምሮ ይፋ ማድረግ ጀምሯል።
አሁን ላይ በከተማዋ 123 ማደያዎች ግልጋሎት እየሰጡ ነው ተብሏል።
ቢሮው ፤ " በየዕለቱ የነዋጅ ማደያዎችን እለታዊ የነዳጅ አቅርቦት መጠን ይፋ ማድረግ የተጀመረው በአገልግሎቱ ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲሁም የተገልጋች እንግልት ለመቀነስ ነው " ብሏል።
ነዳጅ ማደያዎች የት ቦታ እንደሚገኙ እና በእለቱ የተራገፈው ነዳጅ መጠን እንዲሁም የጥቆማ ስርዓቱ ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia
#ትግራይ
" ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኋላ ብቻ ባልመከኑ ተተኳሾች ከ51 በላይ ወገኖች ሲቀጠፉ ፤ ከ286 በላይ ሰዎች የአካል ጉዳት ሰለባ ሆኗል " - በትግራይ ማእከላይ ዞን የየጭላ አበርገለ ወረዳ የፀጥታ ፅ/ቤት
በትግራይ በነበረው አውዳሚ እና አሰቃቂ ጦርነት ወቅት ተቀብረው እና ተጥለው ያልመከኑ ተተኳሾች የንፁሃን ዜጎችን ህይወት መቅጠፍና አካል ማጉደል ቀጥለዋል።
በየጭላ አሸርገለ ወረዳ የእምባ ሩፋኤል ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነዋሪ አርሶ አደር ባልመከነ ተተኳሽ 2 ልጆቻቸው ሲያጡ አንዱ ቆስሎ ተርፎላቸዋል።
ሌላዋ እናት ቁርስ አብልተው ለእንጨት ለቀማ የላኩዋቸው ልጆቻቸው አንዱ በተጣለ ተተኳሽ ሲሞት ሌላኛው የአካል ጉዳተኛ ሆኗል።
በጦርነቱ ወቅት በአከባቢው በነበረው የጦር መሳሪያ ዲፓ የቀሩ የተጣሉና የተቀበሩ በርካታ ያልመከኑ ተተካሾች መኖራቸው የጦቆሙት የጥቃቱ ሰለባዎች ፤ በሰው እና በእንስሳ ከፍተኛ አደጋ በማድረስ የሚገኘው ተተኳሽ እንዲወገድላቸው ጠይቀዋል።
የክልሉ እንዲሁም የፌደራሉ መንግስት የአደጋው አስከፊነት በመረዳት አከባቢያቸው ከተተካሾች እንዲታደጉላቸውም ተማፅነዋል።
የወረዳው የፀጥታ ፅ/ቤት የአርሶ አደሮቹ አስተያየት በመጋራት ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ ከ51 በላይ ወገኖች ባልመከኑ ተተኳሾች ህይወታቸው ሲቀጠፍ ፤ ከ286 በላይ ደግሞ ለአካል ጉዳት እንደተጋለጡ ገልጸዋል።
" ጉዳዩ እጅግ አሳሳቢ ነው " ያለው ፅ/ቤቱ ህዝቡ ከስጋት ድኖ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ መንግስትና ለጋሽ ደርጅቶች አከባቢውን ከተተኳሾች ለማፅዳት የበኩላቸው እንዲተባበሩ ጠይቋል።
" ዘላቂው መፍትሄ በአከባቢው ላይ ያለውን ተተኳሽ ማፅዳት ነው ፤ የጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት የወዳደቁና የተቀበሩ ተተኳሾችን በማስወገዱ በኩል አከባቢያችን ትኩረት ያሻዋል " ሲል ፅ/ቤቱ አስገንዝቧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከድምፂ ወያነ ነው ያገኘው።
@tikvahethiopia
#AAiT
Announcement of Professional Training Programs
1. Python Programming + Data Analytics and Visualization
2. Python Programming + Artificial Intelligence
By: Addis Ababa University,
Addis Ababa Institute of Technology (AAiT), School of Electrical & Computer Engineering
Registration Deadline: October 25, 2024
Training Starts on: October 28, 2024
Online Registration Link: https://forms.gle/E54L9aVkHQ1pCs8v5
Telephone: 0940182870 / 0913574525
Email: sece.training@aait.edu.et
For more information: https://forms.gle/E54L9aVkHQ1pCs8v5
Telegram : /channel/TrainingAAiT
" አደጋው በሸገር የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ ነው የደረሰው ፤ እስካሁን የአንድ ሰው ህይወት አልፏል " - ፖሊስ
በአዲስ አበባ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ' አዲሱ ገበያ ' አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ እስካሁ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።
አደጋው በሸገር የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ መድረሱን ፖሊስ ጠቁሟል።
በአደጋው የተጎዱ ሰዎችን ህይወት ለመታደግ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ እንደሆነ ገልጿል።
" እስካሁን በአደጋው የ1 ሰው ህይወት አልፏል " ያለው ፖሊስ " የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ ነው " ብሏል።
ፖሊስ ከአደጋው ጋር የተያያዙ ዝርዝር መረጃዎችን በቀጣይ ለህዝብ እንደሚገልጽም ለብሔራዊ ቴሌቪዥን በሰጠው ቃል አሳውቋል።
@tikvahethiopia
“ ጡረታ፣ ህክምና ይከበርልን። እኛ ወድቀናል፤ ከስረናል፤ ከሽፈናል። ቢያንስ እንደ ዜጋ እንታከም ” - የሶማሌ ክልል ቀድሞ ሰራዊት አባላት
ሰሞኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሶማሌ ክልል ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር የአጀንዳ ማሰባሰብ የውይይት መድረክ አድርጎ ነበር።
በዚህ መድረክ ከተሳተፉት ባለድርሻ አካላት መካከል አንዱ የሶማሌ ክልል የቀድሞ ሰራዊት አባላት ነው።
ኮሚሽኑ ስለቀድሞ ሰራዊት ጉዳይ ምን ማተኮር እንዳለበት፣ ስለታጠቁ ኃይሎችና የመንግስት አካሄድ የተመለከቱ ጥያቄዎች ያቀረብንላቸው የክልሉ የቀድሞ ሰራዊት አባላት ሊቀመንበር ሻለቃ ሴባ ቶንጃ ምላሽ ሰጥተዋል።
ምን አሉ ?
“ ሥርዓት ሲወድቅ የሚወድቅ ሥርዓት ሲነሳ የሚነሳ ሰራዊት ካለ ሀገርና ሕዝብ ዋስትና የለውም። ማንም እንደገባ ከዚያም ከዚህም ያዋክበዋል፤ ህዝብ ጉዳት ያደርስበታል።
ቀጣዩ ትውልድ እንዴት ይኑር? ለምን በባንዲራ እንጨቃጨቃለን? ከጥንት ጀምሮ ቅድመ አያቶቻችን ያወረሱን ነው እዚህ ላይ ያለው ስህተት ምንድን ነው? ለምን በአድዋ ድል እንጨቃጨለን? ስህተት ካለ ተመካክረን እናስተካክል እንጂ ለምን እንጋደላለን ?... በሚል ለሀገር የሚጠቅም አጀንዳ እየቀረጽን ነው።
ጡረታ ያልተከበረልን ነን፤ ጡረታ ይከበርልን፤ እንደዜጋ ለሀገር አገልግለናል፤ ሜዳ ላይ መውደቅ የለብንም። አሁንም እየተጠራን እየተሳተፍን ነው።
እኛ ለሀገር አሁንም ዝግጁ ነን፤ አላኮረፍንም፡፡ ሁሉም በእኩልነት ይታይ፡፡ የተወሰኑትን ብቻ መዞ ይዞ የተወሰነው ጭራሽ እስከነመፈጠሩም ይረሳል፡፡
ጡረታ ይከበርልን፤ ህክምና ይከበርልን፤ እኛ ሁሉን ትተን ለሀገር ብለን ስለንዘምት የነበረ ተማሪ አሁን ዶክተር ፕሮፌሰር ነው። እኛ ወድቀናል፤ ከስረናል፤ ከሽፈናል። ቢያንስ እንደ ዜጋ እንታከም። እኛ ስንዋጋ ተምረው ዶክተር የሆኑ ያክሙን።
መንግስት የሕክምና፣ የጡረታ ዋስትና ይስጠን። ከራሳችን ገንዘብ ተቆርጦ ገቢ ሲሆን የነበረውን ተከልክለናል። ይህ ይስተካከል።
እንደዜጋ በክብር እንኑር። በመስሪያ ቤቶች ተቀጥረን ጥበቃ ለመስራት እንኳ የታገደበት ሁኔታ ነበር፤ ‘እንዳይቀጠሩ’ የሚል። ዜጋ ነን፣ ይሄ ያሳምጻል ነገር ግን አላመጽም በሀገራችን አናምጽም፤ ህዝብ ይበጠበጣል ብለን።
ችግራችንን አምቀን ይዘን አሁንም ለህዝባችን ደኀንነት እየታገልን ነው።
ሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ግጭቶች በአያያዝ ስህተት የተፈጠሩ እንደሆኑ እናምናለን። በአጠቃላይ የእርስ በእርስ ግጭት የወንድማማቾች እልቂት አንደግፍም።
እገሌ እገሌ የሚል ስያሜ መንግስት ይስጠው እኛ የወንደማማቾች ግጭት አንደግፍም፡፡ ግን መጥተው ህዝቡን እንዲጨፈጭፉና ተቋም እንዲያወድሙም አንፈልግም፡፡
ይልቁንም ወደ መድረክ እንዲመጡ እንፈልጋለን፡፡ ለዚያ ደግሞ መንግስት በሆደ ሰፊነት ቀረብ ብሎ መሳብ ያስፈልጋል። ግጭት እስከወዲያኛው ይቁም።
አሁን የተፈጠረው ግጭት በአያያዝ ስህተትነው የተፈጠረው አይፈጠርም ነበር፡፡ ለምሳሌ ጊዜውን መጠበቅ ሲገባ ያልበሰለ አጀንዳ ወደ ህዝብ ይለቀቃል፡፡
በሚስጥር ተይዞ ቆይቶ በኋላ ሁኔታው ሲፈቅድ መልቀቅ ነው እንጂ ጊዜውን ያልጠበቀ አጀንዳ ከለተለቀቀ ግጭት ይፈጥራል፡፡ ጊዜውን ያልጠበቀ አጀንዳ መዓት ነገር ነው፡፡
ለምሳሌ ፦ ለመጥቀስ የፋኖም ራሱ ጊዜውን ያልጠበቀ አጀንዳ ሆኖ በግድ ስለተኬደበት እንጂ አይዋጉም ነበር፡፡ ትላንትና ራቁቱን የተባረረውን መካላከያ ሰራዊትን ያዳኑ እነርሱ አይደሉምን ?
አሁን የተፈጠረውን ብቻ ኮንነን መንግስት ይውደደን ብዬ አልናገርም፡፡ ሚዛናዊ ህሊና አለኝ፡፡ አሁን የሚሰሩት ሥራ ጥሩ ነው እያልኩ ሳይሆን ወደ መጥፎ ተገፋፍተው በእልህ የተገፉት ነገር ጥሩ ስላልሆነ ነው፡፡
በእርግጥ አሁን መንግስት ጥረት እያደረገ ነው በዚሁ ይቀጥል፡፡ ወደ ሰላም ቢያመጣቸው ጥሩ ነው፡፡
መጪው ትውልድ በሰላም እንዲኖር ከእንግዲህ በአገራችን የወንድማማቾች ጦርነት እንድናይ፣ እኛ ያየነው ችግር በእነርሱ ላይ እንዲደርስ አንፈልግም፡፡
ሁሉም የበኩል ድርሻ ተቀብሎ መንግስትም ያለውን ስህተት አርሞ ብለድርሻ አካላት በሙሉ ለሰላም አስተቃጽኦ አድርገው ከተንቀሳቀሱ ሰላም ይመጣል፡፡ ይህ ካልሆነ ከዚህ በባሰ እንጠፋፋለን፡፡ አሁን በዚህ ውይይት መፈታት አለበት ከዚህ ካለፈ አካሄዱ አያምርም፡፡
ከተሞክሯችን ተነስተን ነው መልዕከት የምናስተላልፈው፡፡ እሳት የጎረሰ መሳሪያ ይዘን ውሃ ጠምቶን ለምነን እየጠጣን ነበር፡፡
ከደረሰብን ጉዳት አንጸር እኛ ለመሸፈት ነበርን ቅርብ፡፡ አሁንም ቢሆን አኩርፈን ለመሄድ እኛ ነን ቅርብ፡፡ ጸጉራችንን ተላጭተን እድሜያችንን የጨረስነው በርሃ ውስጥ ነው፡፡
በውጊያ አውድ ያሉ አካላት እርግጥ ምክንያት ኖሯቸው ትግል ቢጀምሩም የትኛውም ግጭት ሂዶ ሂዶ በስምምነት መጠቃለሉ አይቀርም፡፡ ዞሮ ዞሮ ሰላም ይመጣል፤ በእድሜያችን እያየን ያለነው ይሄው ስለሆነ፡፡ ከብዙ መተላለቅ ይልቅ ለስምምነቱ፣ ለእርቁ፣ ለውይይቱ እድል ቢሰጡ ጥሩ ነው" ብለዋል።
ምን ያክል ቀድሞ ሰራዊት አባላት አሉ ለሚለው የቲክቫህ ጥያቄ በምላሻቸው “ ባለንበት አካባቢ በርካታ የቀድሞ ሰራዊት አባላት አሉ፡፡ ወደ 5 ሺሕ የሚሆኑ አሉ ” ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ
መደበኛ ባልሆነ ማቆያ ቦታ፣ ያሉበት ሳይገለጽ እንዲቆዩ የተደረጉ እና አስገድዶ መሰወር ሁኔታን ሊያቋቁም በሚችል ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ተጎጂዎች እና የተጎጂዎች ቤተሰቦችን በተመለከተ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ እና ፍትሕ ሊሰጣቸው እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አሳስቧል።
ኮሚሽኑ ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ ሪፖርት ልኮልናል።
ከሪፖርቱ ውስጥ የተገኘ ማሳያ ፦
(የአስገድዶ መሰወር ሁኔታን ሊያቋቁም በሚችል ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ተጎጂዎች)
🔴 አቶ መንበረ ቸኮል ምስጋናው፣ የግንባታ ባለሙያ፣ የ7 እና የ4 ዓመት ዕድሜ ያላቸው 2 ሕፃናት ልጆች አባት ሲሆኑ፣ ግንቦት 9 ቀን 2016 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ “ሰፈራ” ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በጸጥታ አካላት ሰሌዳ በሌለው ተሽከርካሪ የተወሰዱ ሲሆን፣ ያሉበት ቦታ እና ሁኔታ የማይታወቅ በመሆኑ ቤተሰቦቻቸው ለከፍተኛ ጭንቀትና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ተጋልጠው ይገኛሉ።
🔴 አቶ ዘላለም ግሩም ፍላቴ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባልና አሽከርካሪ ሲሆኑ፣ ኅዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ፣ ልዩ ስሙ “ዲቦራ ትምህርት ቤት” ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በጸጥታ አካላት ሰሌዳ ቁጥሩ ባልታወቀ ተሽከርካሪ ከተወሰዱ ጀምሮ፣ ያሉበት ቦታ እና ሁኔታ የማይታወቅ በመሆኑ ቤተሰቦቻቸው በከፍተኛ ጭንቀትና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ውስጥ ይገኛሉ።
(በተለያየ መደበኛ ባልሆኑ ቦታዎች ወይም ያሉበት ሳይታወቅ በተራዘመ እስር ሁኔታ ቆይተው የተለቀቁ)
➡ አቶ አማረ ግዳፍ፣ ባለ3 እግር ተሽከርካሪ በተለምዶ “ባጃጅ” በማሽከርከር ሥራ ላይ የተሰማሩ ሲሆኑ መጋቢት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ በአዲስ አበባ ከተማ፣ የካ ክፍለ ከተማ፣ በተለምዶ “ወሰን መስቀለኛ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ 6 የሲቪል ልብስ እና 1 የመከላከያ ሰራዊት የደንብ ልብስ በለበሱ ሰዎች እና ሰሌዳ በሌለው ተሽከርካሪ ተወስደው፣ ላለፉት 6 ወራት ያሉበት ቦታ ሳይታወቅ ቆይተው በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም. ተለቀዋል።
➡ አቶ ዓለማየሁ ከፈለ ተሰማ የተባሉ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ነሐሴ 20 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 1 በተለምዶ “ፍላሚንጎ” በሚባለው አካባቢ ሲቪል ልብስ ለብሰው መታወቂያ በያዙ 6 የፌዴራል ፖሊስ አባላት ተወስደው፣ በሚያዝያ ወር 2016 ዓ.ም. ተለቀዋል።
➡ አቶ መቼምጌታ አንዱዓለም፣ ባለትዳርና የ2 ሕፃናት ልጆች አባት፣ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ ነሐሴ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 11፡00 ሰዓት አካባቢ “ብስራተ ገብርኤል” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የታክሲ አገልግሎት ከሚሰጡበት አካባቢ ከነተሽከርካሪያቸው የሲቪል ልብስ በለበሱ የጸጥታ አካላት ተወስደው፣ በተለምዶ “ራሺያ ካምፕ” ተብሎ በሚጠራው የመከላከያ ሰራዊት አባላት መኖሪያ ለ7 ወራት ከቆዩ በኋላ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ተለቀዋል።
➡ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የቤተሰብ አስተዳዳሪ እና የልጆች አባት የሆኑ ተጎጂ፣ ነሐሴ 15 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ገደማ ከግል የሥራ ቦታቸው ሲቪል እና የደንብ ልብስ ለብሰው ቀይ ቦኔት ባደረጉ የጸጥታ አባላት ተይዘው፣ ሰሌዳ በሌለው ተሽከርካሪ ጦር ኃይሎች አካባቢ በተለምዶ “ራሺያ ካምፕ” ተብሎ በሚጠራው የመከላከያ ሰራዊት አባላት መኖሪያ እንደቆዩ አስረድተዋል። ከዚያ ቀን ጀምሮ ቤተሰቦቻቸው በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ በርካታ የአዲስ አበባ ከተማ እና የፌዴራል ፖሊስ ጣቢያዎች ቢያፈላልጓቸውም በምን ምክንያት እንደተያዙ ለማወቅ ሳይቻል፣ ለ2 ወራት ከቆዩ በኋላ ጥቅምት 18 ቀን 2016 ዓ.ም. ተለቀዋል።
➡ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ሌላው ተጎጂ ነሐሴ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ከሚሠሩበት አካባቢ ሲቪል እና የደንብ ልብስ ለብሰው ቀይ ቦኔት ባደረጉ የጸጥታ አካላት በተለምዶ “ፓትሮል” በሚባል ተሽከርካሪ በግዳጅ ተወስደው ባልታወቀ ቦታ ከቆዩ በኋላ፣ መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ተለቀዋል።
➡ ሌላ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ተጎጂ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ እና ባለትዳር ሲሆኑ፣ ታኅሣሥ 24 ቀን 2016 ዓ.ም. እኩለ ቀን ላይ በተለምዶ “ስታዲየም” በሚባለው አካባቢ ከሚሠሩበት ቦታ ሲቪል በለበሱና ሽጉጥ በታጠቁ፣ እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊት የደንብ ልብስ በለበሱና ቀይ ቦኔት ባደረጉ የጸጥታ አካላት ሰሌዳ ቁጥር በሌላቸው ዳለቻ ቀለም እንደሆኑ በተገለጸና በተለምዶ “ሎንግቤዝ” እና “ፓትሮል” ተብለው በሚጠሩ መኪናዎች ተጭነው ተወስደው፣ ከ6 ወራት እስር በኋላ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. ተለቀዋል።
➡ በተመሳሳይ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ተጎጂ ከግል የሥራ ቦታቸው የተወሰኑት ሲቪል እና ሌሎች የደንብ ልብስ በለበሱና በታጠቁ የጸጥታ አካላት መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ከተያዙ በኋላ፣ ዐይናቸውን በጨርቅ ተሸፍነው ተወስደው ያሉበት ሳይታወቅ እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቆዩ በኋላ፣ በድጋሚ ዐይናቸውን በጨርቅ ተሸፍነው አዲስ አበባ ከተማ፣ “ኃይሌ ጋርመንት” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እንዲወርዱ መደረጋቸውን አስረድተዋል።
(ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
#AAiT
Announcement of Professional Training Programs
1. Python Programming + Data Analytics and Visualization
2. Python Programming + Artificial Intelligence
By: Addis Ababa University,
Addis Ababa Institute of Technology (AAiT), School of Electrical & Computer Engineering
Registration Deadline: October 25, 2024
Training Starts on: October 28, 2024
Online Registration Link: https://forms.gle/E54L9aVkHQ1pCs8v5
Telephone: 0940182870 / 0913574525
Email: sece.training@aait.edu.et
For more information: https://forms.gle/E54L9aVkHQ1pCs8v5
Telegram : /channel/TrainingAAiT
ትላንትና መርካቶ ሸማ ተራ እሳት አደጋ ሲከሰት እጅግ በሚያሳፍር ሁኔታ አንዳንድ ህሊና የሌላቸው ሰዎች ዝርፊያ ላይ ተሰማርተው ነበር።
በዛ ጭንቅ ሰዓት፣ ሁሉም እሳቱን ለማጥፋ ሲረባረብ እነሱ ግን የራሳቸው ሃቅ ያልሆነን የሰው ንብረት ሲዘርፉ ነበር።
ከአሳዛኙ የእሳት አደጋ በተጨማሪ ይህ የዝርፊያ ተግባር የአካባቢው ነሪዎችን አሳዝኗል።
ዛሬ የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ ባደረገው መረጃ ፥ አደጋውን እንደ ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 33 ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ ይገኛል።
በሌላ በኩል ከአደጋው ጋር በተያያዘ በ7 ሰዎች ቀላል በ2 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን አሳውቋል።
የአደጋውን መንስኤ የለማጣራት ከፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራ ቡድን ጋር በመቀናጀት ምርመራ መጀመሩን አመልክቷል።
Photo Credit - Yeraguel Baria
@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ ' መርካቶ ሸማ ተራ ' ከትላንት ምሽቱ ከባድ የእሳት አደጋ በኃላ ዛሬ ከላይ በፎቶው የምትመለከቱትን ይመስላል።
ከቆርቆሮ እና ከኮነቴነር ቤቶች አቅራቢያ ወዳለው ' ነባር የገበያ ማዕከል (ህንጻ) ' የተዛመተው እሳት የህንጻውን አንደኛውን ክፍል ክፉኛ አውድሞታል።
እስካሁን ሰው ላይ ስለደረሰ ጉዳት ሪፖርት አልተደረገም።
በትላንት ምሽቱ የእሳት አደጋ ምንም እንኳን ይፋዊ የጉዳት መጠን ባይገለጽም የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ነው።
በርካቶች ብዙ የደከሙበት ንብረታቸው በአንድ ምሽት ወደ አመድነት ተቀይሯል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፥ " በአደጋው የደረሰውን የጉዳት መጠኑን የተመለከተ ዝርዝር ጥናት ተደርጎ ከባለሃብቶች እና ከህብረተሰቡም ጋር በመሆን በፍጥነት መልሶ የማቋቋም ስራ ይሰራል ፤ ቦታውንም ወደ ቀደመው የንግድ ተግባር እንዲመለስ የማድረግ ስራ እንሰራለን " ብሏል።
@tikvahethiopia