tikvahethiopia | Unsorted

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1519094

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Subscribe to a channel

TIKVAH-ETHIOPIA

#AddisAbaba

➡️ " የቀብር ስርዓቱ ተፈጽሟል " - የዶክተር በሀይሉ ቤተሰብ 

➡️ " ይቅርታ መረጃው የለኝም " - የአዲስ አበባ ፓሊስ

እውቁና እጅግ የተዋጣላቸው የቀዶ ጥገና ሐኪም ዶ/ር በኃይሉ ኃይሉ መገደላቸውን የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ዶ/ር በኃይሉ ከቀናት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ለጥዋት ሩጫ በሚል በወጡበት በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ነው የተገለጸው።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ አንድ የሟች ቅርብ ቤተሰብ፣ " ቤተሰብ ጠቅላላ ' ወጥቶ ሞተ ' ነው የምናውቀው። ሚዲያ ላይ ካለው ውጪ አዲስ የሰማነው ነገር የለም " ብለዋል።

ስርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል ? ቤታቸው የት አካባቢ ነው ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ " ቀብሩ ተፈጽሟል፣ ከትላንት ወዲያ ሰዓሊተ ምህረት " ብለው፣ ቤታቸውን በተመለከተም፣ " ቦሌ ሚካኤል ነው። ሞተ ያሉት ደግሞ ወደ ሳሪስ በሚወስደው ድልድይ ጠዋት ወክ ሲያደርግ ነው። ዞሮ ዞሮ አስከሬኑን ፓሊስ ነው ያነሳው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስን ለመጠየቅ ጥረት አድርጓል።

የኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ በሰጡት አጭር የፅሑፍ  ምላሽ፤  " ይቅርታ መረጃው የለኝም " ሲሉ ለጊዜው አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

በቀጣይም የአዲስ አበባ ፖሊስን ስለ ጉዳዩ የምጠይቅ ይሆናል።

በተጨማሪም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፣ የቀድ ጥገና ሀኪሙን ግድያ በተመለከተ የደረሰው መረጃ እንዳለ ለኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኀበር ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ አንድ የማኀበሩ ባለስልጣን በሰጡት ቃል፣ " እኔም በማኀበራዊ ድረገፅ ነው የሰማሁት በጣም ያሳዝናል " ብለዋል።

አክለውም፣ " ሦስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው ተመሳሳይ ነገር የተፈጸመው። ዶክተር እስራኤል ጥላሁን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገሏል። እየሆነ ያለዉ ነገር ልብ ይሰብራል። ሁኔታውን አጣርተን መግለጫ እናወጣለን። ለአሁኑ ግን በቂ መረጃ የለንም በጉዳዩ ዙርያ " ሲሉ አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ሕክምና ማኀበር በበኩሉ በዶክተር በሀይሉ ሀይሉ ሞት የተሰማውን ሀዘን በመግለጽ መግለጫ አውጥቷል።

ለዶክተሩ ቤተሰቦች፣ ወዳጆች፣ የስራ ባልደረቦች መፅናናትን ተመኝቷል።

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ኑ ቸርነትን እናድርግ "

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን " ኑ ቸርነትን  እናድርግ " በሚል መሪ ቃል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር መጋቢት 15 ቀን ከቀኑ 7:00 ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ ማዘጋጀቱን ገልጿል።

ማህበሩ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን አመልክቷል።

ገቢ ማሰባሰቢያው በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመው ማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ የተጎዱ ወገኖቻችንን፣ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶችን ለመደገፍ የሚውል እንደሆነ ገልጿል።

የማኅበሩ ሰብሳቢ ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም ፤ " በየጊዜው በሚከሰከቱ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት አስቸጋሪ ቢሆንም ወገን ለወገኑ መርዳት ስላለበት ሌሎች አገልግሎቶችን ለጊዜው በመግታት ኅብረተሰቡን በማስተባበር ትኩረት ተደርጎ እንዲሠራ ተወስኗል " ብለዋል።

በተለይም ገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶች ላይ በስፋት ድጋፍና እርዳታ እንደሚደረግ በዚህ የጾም ወቅት ደግሞ ምጽዋት ማድረግ አግባብም እንደሆነ ተናግረዋል።

አያይዘውም ፤ ሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች በዚህ ወቅት ፤ በአንድ ልብ እና ሀሳብ በመሆን ለተቸገሩት መድረስ እንደሚገባ ፤ ብፁዓን አባቶች በማስተማር ፤ ማኅበራት ፣ ሰንበት ት/ቤቶች ፣ አጠቃላይ የቤተክርስቲያን ልጅ የሆነ ሁሉ በገንዘብ በዓይነት ሊበላሹ የማይችሉ የታሸጉ ምግቦችን ጨምሮ ድጋፍ እንዲያደርጉ በማኅበሩ ስም ጥሪ አቅርበዋል።

በዕለቱ፦
- ብፁዓን አባቶች ቡራኬና ቃለ ምዕዳን ይሰጣሉ ፤
- በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን መምህራን ትምህርተ ወንጌል ፤
- የመዝሙር አገልግሎት፤
- ዶክመንተሪ ቪዲዮ የሚቀርብ ሲሆን በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ የገዳማትና አድባራት አባቶችን ጨምሮ የሚደረግ መርሐ ግብር ይሆናል ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከማህበሩ ባገኘው መረጃ ፤ የመግቢያ ትኬት መቶ ብር እየተሸጠ ሲሆን በዕለቱ እዛው በር ላይም ይሸጣል።

አሁን በተዘጋጀው የማኅበራዊ ድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ላይ መሳተፍ ለማይችሉ በተለያዩ በሚዘጋጁ የድጋፍ ማድረጊያዎች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።

የመርሐ ግብሩን የመግቢያ ትኬት :-
1.  በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ 4ኛ ወለል (ቤተ አብርሃም)
2.  በወረዳ ማዕከላት ጽ/ቤቶች  
3.  በማኅበረ ቅዱሳን ንዋያተ ቅድሳት መሸጫ ሱቆች
4.  በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ የዕለት ገንዘብ መሰብሰቢያዎች
5.  በአሐዱ ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች
6.  በሰ/ት/ቤት ጽ/ቤቶች ይገኛል ተብሏል።

ተጨማሪ መረጃ ለሚፈልጉ በ09 44 71 82 82 እና 09 42 40 76 60 መደወል ይችላሉ።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ገንዘቡን ካልመለሱ ማንነታቸውን ለፖሊስ እናሳውቃለን - ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ባንክ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ ከ " ቢቢሲ ኒውስ ዴይ " ጋር በነበራቸው ቆይታ ባንኩ የሲስተም ብልሽት ባጋጠመው ወቅት የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ ደንበኞች እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ድረስ ገንዘቡን ካልመለሱ ማንነታቸውን ለፖሊስ እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል።

" በዲጂታል ነው ዝውውር የፈጸሙት። ደንበኞቻችን ስለሆኑ እናውቃቸዋለን። " ያሉት የባንኩ ፕሬዜዳንት ፤ " የፈጸሙት ተግባር በሕግ ያስጠይቃቸዋል። ለፖሊስ ማንነታቸውን እናሳውቃለን " ብለዋል።

" አሶሼትድ ፕሬስ " ባንኩ አርብ መጋቢት 6 ለሊት የሲስተም ችግር በገጠመው ወቅት የተወሰደበት ገንዘብ 2.4 ቢሊዮን ብር (40 ሚሊዮን ዶላር) መሆኑን ዘግቧል።

ይህ ወጥቷል የተባለው ገንዘብ ትክክለኛ ነው ወይ ? ተብለው የተጠየቁት የባንኩ ፕሬዝዳንት ፤ " የኦዲት ምርመራው ባለመጠናቀቁ የተወሰደውን ገንዘብ መጠን አሁን ላይ አይታወቀም " ብለዋል።

" ገና ኦዲት እየተደረገ ነው። ዝውውሩ ውስብስብ ነው። ጤናማ የሆነ ዝውውር የፈጸሙ እንዳሉ ሁሉ፤ የሌላቸውን ገንዘብ ያወጡም አሉ። ስለዚህ ማጣራት ይጠይቃል። ይህ ደግሞ ጊዜ ይፈልጋል። ምናልባት በዚህ ሳምንት መጨረሻ እንጭርሳለን ብለን እንጠብቃለን "ብለዋል።

አቶ አቤ ፤ 10 ሺህ የሚሆኑ #ግለሰቦች የገንዘብ ዝውውር ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ሰኞ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አርብ ሌሊት ከ490 ሺህ በላይ " ጤናማ እና ጤናማ ያልሆኑ " የገንዘብ ዝውውሮች መከናወናቸውን መናገራቸው ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በቴክኒካል ብልሽት የዲጅታል አገልግሎት ተቋርጧል " - CRRSA

የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ፤ በዋና የከተማው መረጃ ማዕከል ላይ የቴክኒካል ብልሽት እንዳጋጠመው አሳውቋል።

በዚህም ምክንያት የዲጂታል አገልግሎቱ ከትላንት ጀምሮ እንደተቋረጠ ገልጿል።

ከከተማው የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እንዲሁም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ ጥገና በማድረግ ለመፍታት ጥረት እያደረገ እንደሆነም አስረድቶ ነዋሪዎች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

እንደልብ ለ 7 ቀናት !

በ350ብር ብቻ ያልተገደበ ሳምንታዊ የኢንተርኔት ጥቅል የM-PESA Appን በመጠቀም አሁኑኑ እንግዛ!

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#FurtherAheadTogether

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ለጥንቃቄ⚠️

እንዲህ ካሉ አጭበርባሪዎች ተጠንቀቁ።

ከላይ የምትሰሙት የድምፅ ቅጂ ከአንድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተላከ ነው።

አጭበርባሪው ደዋይ ግለሰብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ #ዋናው_ቢሮ እንደደወለ በማስመሰል በኦንላይን ዘረፋ ለመፈፀም ሞክሯል።

የደወለው #የባንክ_ሰራተኛ ጋር መሆኑን አላወቀም ነበር።

ሰራተኛው ግለሰቡ የሚለፈልፈውን ሁሉ እስከ መጨረሻ ድረስ አዳመጠው።

በኃላም የአንድ የባንኩን ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅ ስምን ይጠይቀዋል።

በዚህ ግዜ ከዋናው መ/ቤት ነኝ ያለው አጭበርባሪ ምን ይዋጠው ? መቀባጠር ይጀምራል።

በመጨረሻ ውርደቱን ተከናንቦ ስልኩን ዘግቷል።

እንዲህ ያሉ የማጭበርበር ስልቶች አንድ ሰሞን እንደጉድ ተበራክተው ነበር። አሁን ደግሞ ሰሞነኛውን የንግድ ባንክን ሁኔታ ተከትሎ እንደ አዲስ ተስፋፍተዋል።

ውድ ቤተሰቦቻችን ፦
* የማታውቋቸው የግል ስልኮችን ባለማንሳት ፣
* #የሚስጥር_ቁጥሮችን ባለመስጠት እራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች ጠብቁ። የሚመለከታቸው አካላትም ይህን ነገር እንደ ቀላል ከማየት የማጭበርበር ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች #በደወሉበት_ስልክ ክትትል በማድረግ ወደ ህግ ማቀረብ አለባቸው።

(የድምፅ ቅጂውን ለላከው የቤተሰባችን አባል ምስጋና እናቀርባለን)

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ScamAlert

በርካታ ሰዎች አሁንም በኦንላንይን #አጭበርባሪዎች ገንዘባቸውን የተጭበረበሩ ይገኛሉ።

ዛሬ እንዲሁም ትላንትና " #ተዘረፍን " ሲሉ መልዕክት የላኩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በዋስትስአፕ እና በቴሌግራም  ያነገሯቸው ሰዎች ፤ " ቀለል ያለ ስራ ስሩና ትርፋማ ሁኑ " በማለት ከ150,000 ብር በላይ እንዲልኩላቸው ካደረጉ በኃላ ሰዎቹ የውሃ ሽታ ሆነዋል።

" በእኛ የደረሰ በናተ እንዳይደርስ ለማንም የማታውቁት ሰው መልዕክት አትመልሱ ፤ እንዲሁ ቁጭ ተብሎ ምንም ሳይደክሙ ብቻ ትርፋማ መሆን አይቻልምና ገንዘባችሁ እንዳትበሉ " ብለዋል።

በድጋሚ ማኛውም የማታውቁት ሰው በቴሌግራም ፣ ዋትስአፕ፣ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም ላይ " ትርፋማ ስራ እናሰራችሁ " ወይም ሌላም መልዕክት ሲልክላችሁ አትመልሱ።

ሌላው የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እና ሌሎች የመገልገያ እቃዎችን " #በርካሽ እንሸጥላችኃለን ቅድሚያ የሂሳቡን ግማሽ ላኩ " ለሚሏችሁም ሰዎች መልስ አትስጧቸው / እቃውን ይላኩና ገንዘቡን ላኩላቸው።

አንድ የቤተሰባችን አባል " አዲሱን አይፎን 15 ስልክ ከአሜሪካ በርካሽ እንልክልሃለን ቅድሚያ ግን ግማሹን አስገባ " በማለት 50 ሺህ ብር ካስላኩት በኃላ አድራሻቸውን አጠፋፍተዋል።

ከዚህም ባለፈ ደግሞ ወደ ውጭ ሀገራት ለትምህርት ለስራ እንላካችሁ የሚሉም በዝተዋልና አድራሻሸውን ፣ ህጋዊናታቸውን አጣሩ። በቅድሚያ ምንም አይነት ክፍያ እንዳትከፍላቸው። " ቅድመ ክፍያ የለውም " ካሉም በኃላ በተለያየ መንገድ ጉዳይ መጨረሻ በሚል የሚበዘብዙ አሉና ተጠንቀቁ።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#አቢሲንያ_ባንክ

ለአሜሪካ የቪዛ ክፍያ የአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግ ካሉበት ሆነው ይጠቀሙ።

ሊንኩን በመጠቀም መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ!

ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.boaMobileBanking&hl=en&gl=US

ለአፕል ስልኮች https://apps.apple.com/us/app/boamobile/id6463218765

ለሁዋዌ ስልኮች https://appgallery.huawei.com/app/C110106115

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

" የትግራይ ጡረተኞች ክፍያው እንዲፈፀምላቸው ተወስኗል " - ዶ/ር እዮብ ተካልኝ

በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ምክንያት የጡረታ ገንዘብ ያልተከፈላቸው ጡረተኞች፤ በፖለቲካ ውሳኔ መሰረት ደሞዝ እንዲከፈላቸው መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታና የጡረታ ፈንድ የቦርድ አባል ዶክተር እዮብ ተካልኝ ማሳወቃቸውን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

ዶ/ር እዮብ ፤ የጡረታ መዋጮ ባልተሰበሰበበት ሁኔታ ጡረታ እንዲከፈል የሚፈቅድ አሰራር አለመኖሩን ጠቅሰው፤ ውሳኔው ፖለቲካዊ ስለመሆኑ ተናግረዋል።

በዚህም ከፕሪቶሪያው ስምምነት በፊት ክፍያ ተቋረጦባቸው የነበሩ ጡረተኞች፤ በሚቀጥሉት ሳምንታት ክፍያ ይፈፀምላቸዋል ብለዋል። አሰራሩ በመንግስት ተቋማት እና በግል ድርጅቶች ይሰሩ የነበሩ ጡረተኞችን እንደሚመለከት ጠቁመዋል።

ከትግራይ ጡረተኞች ክፍያ ጋር በተያያዘ ተደጋጋሚ ጥያቄ ሲነሳ እንደነበር ጠረተኞችም ሰላማዊ ሰልፍ እስከመውጣት መድረሳቸው ይታወሳል።

ከቀናት በፊት ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከትግራይ ክልል ከመጡ የህዝብ ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት፤ የጡረተኞች የደሞዝ ክፍያ አልተፈጸመም የሚል ቅሬታ ቀርቦ ነበር።

ጠ/ሚኒስትሩ ፤ " ከሚመለከታቸው የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተነጋግሬ በአጭር ጊዜ ምላሽ ይሰጣል " የሚል ምላሽ ሰጥተው እንደነበር ይታወሳል።

በተደረሰው ፖለቲካዊ ውሳኔ በጦርነቱ ምክንያት ያለተከፈለ የጡረተኞች ደሞዝ ተሰልቶ ይከፈላቸዋል ተብሏል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ስለ ትውልዱ ግድ ይለናል የምትሉ ኃላፊዎች መፍትሄ ስጡን " - ተማሪዎቹ

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፤ " መፍትሄ የሚሰጠን አጥተን ያለ ትምህርት ቤታችን ቁጭ ብለናል ፤ ጊዜያችንም እየተቃጠለ ነው " ሲሉ አማረዋል።

የባህር ዳር ዩንቨርሲቲ የ2016 ዓ/ም የ1ኛ ዓመት እና የሬሚድያል ተማሪዎች ወደ ግቢ እንዲገቡ ጥሪ ተደርጎላቸው በኃላም መራዘሙ ይታወሳል። ነገር ግን እስካሁን ምንም አይነት ጥሪ አልተደረገላቸውም ፤ ተማሪዎቹም የትምህርት ገበታቸው ላይ መገኘት አልቻሉም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የነዚህን ተማሪዎች ጉዳይ እየተከታተለ ተደጋጋጋሚ የመረጃ ልውውጥ ማድረጉ ይታወሳል።

አሁንም ተማሪዎቹ በሰጡት ቃል ፤ ሌላ ቦታ ያሉ እኩዮቻቸው ትምህርታቸውን እየተከታተሉ፣ እነሱ ያለ ትምህርት እድሜያቸው እየሄደ ፣ የራሳቸው መፍትሄ እንዳይወስዱም ጊዜው እየገፋ መሄዱን በመግለፅ ቁርጥ ያለ መፍትሄ እንዲሰጣቸው በድጋሚ ጠይቀዋል።

" የሚጠሩን ከሆነ ይጥሩን ፤ የማይጠሩን ከሆነም ይንገሩን ፤ አልያም ትምህርት ሚኒስቴር ወደ ሌሎች ተቋማት ይመድበን እየደረሰብን ያለው የስነልቦና ጫና ከባድ ነው " ብለዋል።

ስለ ትውልዱ ግድ ይለናል የሚሉ ኃላፊዎች መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ያነጋገራቸው አንድ የዩኒቨርሲቲው አካል ተቋሙ ተማሪዎችን ያልጠራበት ምክንያት በአካባቢው ካለው ደህንነት ጋር በተያያዘ መሆኑን መግለፃቸው ይታወቃል።

ተቋሙ ተማሪ አልጠራም ማለት እንደማይችል ፤ ከዛ ይልቅ አንፃራዊ ሰላም ሲኖር አስገብቶ በ45 ቀን 1 ሴሚስተር አስተምሮ ሊያካክሰው እንደሚችል (ልክ ከአሁን በፊት በኮሮናና ጦርነት እንደተደረገው) ተናግረው ነበር።

ከዚህ ቀደም " በአካባቢው ተማሪዎችን ለመጥራት አስቻይ ሁኔታ ከሌለ ለምን የልጆቹ ጊዜ ይቃጠላል አመቱም እያለቀ ስለሆነ ወደ ሌላ ተቋም አይመደቡም ? " የሚል ጥያቄ ለማቅረብ በተደጋጋሚ ትምህርት ሚኒስቴርን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#MerttEka

እነዚህ 👆 የቤት ዕቃዎች በሱቃችን በቅናሽ ዋጋ እየተሸጡ ነው። የሁሉንም ዕቃዎች ዋጋ  ይሄንን👉 t.me/MerttEka ተጭነው በቴሌግራም ማየት ይችላሉ።

አድራሻችን፦ አዲስ አበባ፤ መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 3ተኛ ፎቅ ሱቅ 376

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ፑቲን

አሜሪካ ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤቷ በኩል በሰጠችው መግለጫ ፤ የሩስያ ምርጫን " ኢ-ዲሞክራሲያዊ ነው " ስትል አጣጥላለች።

በከፍተኛ ልዩነት አሸንፈዋል የተባሉትን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንንም " እንኳን ደስ አልዎት " አንላቸውም ብላለች።

ሩስያን እስከ 2030 ለመምራት በበላይነት ፕሬዜዳንታዊ ምርጫውን ያሸነፉት ቭላድሚር ፑቲ ትላንት ድላቸውን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ የአሜሪካን ዴሞክራሲ ወርፈዋል።

ምን አሉ ?

ቭላድሚፕ ፑቲን ፦

" ያካሄድነው ምርጫ ከአሜሪካ በላይ ተዓማኒ እና ግልጽ የሆነ ዓላማ ያለው ነው።

በአሜሪካ በፖስታ አማካይነት ድምጽ እንደሚሰጡት አይደለም። እዛ (አሜሪካ) ድምጽ በ10 ዶላር መግዛት ይቻላል።

የምርጫ ስርዓታቸው ኢ-ዴሞክራሲያዊ ነው።

ዓለም ሁሉ እዚያ እየሆነ ባለው ነገር ይስቃል (በአሜሪካ ዴሞክራሲ) " ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ፑቲን ፕሬዜዳንታዊ ምርጫውን በከፍተኛ ብልጫ ማሸነፋቸው ተከትሎ ፦
- ቻይና
- ህንድ
- ኢራን
- ሰሜን ኮሪያ
- ቬንዙዌላ #የደስታ መልዕክት ሲያስተላልፉ እነ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ ዩክሬን፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ሌሎች አጋሮቻቸው ምርጫውን ኢ-ዴሞክራሲያዊ ሲሉ እያጣጣሉት ይገኛሉ።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ወጋገን_ባንክ

በአምስት የተለያዩ ቋንቋዎች የቀረበውን ደህንነቱ የተጠበቀ ፈጣን እና አስተማማኝ የወጋገን ሞባይል መተግበሪያ አሁኑኑ ከአፕስቶር ወይም ፕሌይስቶር በማውረድ ስልክዎ ላይ ይጫኑ፣ በቀልጣፋ አገልግሎታችን ህይወትዎን ያቅልሉ!

ስልክዎ ባንክዎ

ለተጨማሪ መረጃ በ866 ነፃ የስልክ መስመር ወደ ደንበኞች ግንኙነት ማዕከል ይደውሉ፣ ይስተናገዱ::

Download now:

Android:https://play.google.com/store/apps/details?id=com.act.wegagen&hl

IOS:https://apps.apple.com/in/app/wegagen-mobile/id6472656143

#WegagenBank #WegagenMobile #MobileBanking

Follow us and get more information...

https://linktr.ee/WegagenBank

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ገንዘቡን ተመላሽ ባደረጉ ተማሪዎች ላይ ባንኩ ምንም አይነት ክስ አይመሰርትም " - ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከቀናት በፊት ባንኩ ላይ አጋጥሞ ስለነበረው ችግር መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የባንኩ ፕሬዜዳንት አቶ አቤ ሳኖ ናቸው።

ምን አሉ ?

የባንኩ ፕሬዜዳንት አርብ ለሊት ባንኩ አጋጥሞት በነበረው ችግር የደንበኞች የግል አካውንት ላይ የደረሰ ምንም አይነት ጉዳት እንደሌለ ገልጸዋል።

ባንኩ የውስጥ አሰራሩን ለማዘመን (የሲስተም ማሻሻያ) ሲያደርግ በነበረው እንቅስቃሴ ምክንያት በተፈጠረ ስህተት የአርብ መጋቢት 6 ለሊቱ ክስተት መፈጠሩን እና ጉዳዩ ከሳይበር ጥቃት ጋር የሚያያዝ እንዳልሆነ ተናግረዋል።

" በተፈጠረ ስህተት ምክንያት ጤናማ ያልሆነ የገንዘብ እንቅስቃሴ ነበር " ብለዋል።

አርብ ለሊት ብቻ ከ490 ሺህ በላይ የገንዘብ ልውውጥ እንደነበር ገልጸዋል። ይህ የገንዘብ ልውውጥ ጤናማ የሆነውንም እንደሚጨምር ጠቁመዋል፡፡

" ገንዘብ በተለያየ መንገድ ጤናማ ባልሆነ መልኩ ከባንኩ በማውጣት ላይ በዋናነት የተሳተፉት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው " ሲሉ ገልጸዋል።

የድርጊቱ ተሳታፊ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በባንኩ በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት የወሰዱትን ገንዘብ እየመለሱ እነደሆነና ገንዘቡን ተመላሽ ባደረጉ ተማሪዎች ላይ ባንኩ ምንም አይነት ክስ እንደማይመሰርት አሳውቀዋል።

አሁንም ያልመለሱ ስም ዝርዝራቸው የወጣ ተማሪዎች የወሰዱትን ገንዘብ እንዲመልሱ አሳስበዋል።

ከዚህ ባለፈ ወደ ሌሎች ባንኮች የተደረጉ እና ጤናማ የማይመስሉ የገንዘብ ዝውውሮች ታግደው እንደሚገኙ አስረድተዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ በባንኩ ላይ ጉዳት መድረሱን ያልደበቁ ሲሆን ባንኩ አጠቃላይ ሀብት አንፃር ሲታይ በጣም አነስተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

የደንበኞች የግል አካውንት ላይ የደረሰ ምንም አይነት ጉዳት ባለመኖሩ የባንኩ ደንበኞች ምንም አይነት ስጋት እንዳይገባቸው ማለታቸውን የብሔራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#CBE

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰሞኑን " በሲስተም መበላሸት " ምክንያት አጋጥሞት ከነበረው ሁኔታ ጋር በተያያዘ ያሉ ጉዳዮች ላይ ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ በዋና መ/ቤቱ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልጿል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

• " በአማራ ክልል ውስጥ የተያዙት ልጆቻችን እንጀራ ፍለጋ የወጡ እንጅ ሌላ ተለእኮ እንደሌላቸዉ እኛ ምስክሮች ነን " - የጋርዱላ ዞን የሀይማኖት አባቶች

• " ወጣቶቹን መልምሎ የወሰደዉ የግል ድርጅት መሆኑ የወጣቶችን ለስራ መሰማራት ያሳያል " - የጋረዱላ ዞን አስተዳደር

ከሰሞኑ ለስራ ጉዳይ ወደታላቁ የህዳሴ ግድብ በመሄድ ላይ ሳሉ በፋኖ ተያዙ ስለተባሉ ወጣቶችን በተመለከተ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ ያደረጉት የጋርዱላ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሀኑ ኩናሎ ፤ ከዞናቸዉ ለስራ ሄደዉ የተያዙ ወጣቶች እጅግ አሳሳቢ እንደሆነባቸዉና ከሀገር ሽማግሌ እስከ ሀይማኖት አባትና የመንግስት አካላት ወጣቶቹን ለማስለቀቅ ከፍተኛ እርብርብ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ብርሀኑ ፤ ወጣቶቹ ከደራሼ አሌና አካባቢዉ በባለሀብት በኩል ተመዝግበዉ እንጀራ ፍለጋ መሄዳቸውን በመግለጽ " ይህ ደግሞ ንጽህናቸዉን ይገልጻል " ብለዋል።

አሁን ላይ ጉዳዩን ውጤታማ ለማድረግ  ከቀይ መስቀል ጋርም ስራ እየተሰራ ሲሆን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፣ የአማራ ክልልና የፌደራል መንግስቱም እየጣሩ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

በሌላ በኩል ፤ የጋርዱላ ዞን ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢ ቀሲስ መምሬ ተክሌ ደስይበለዉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ " እነዚህ ወጣቶች ምስኪን እነጀራ ፈላጊ እንጅ የፖለቲካ ተልእኮ የላቸዉም " ብለዋል።

" አሁን ላይ የታጋቾቹ ቤተሰቦች ከአማራ ክልል ጋር ተነጋግራችሁ ልጆቻችን አስመልሱ " በማለት እየጠየቁን ነው የሚሉት ቀሲስ መምሬ ተክሌ ፤ " የልጆቹን ንጽህና ተረድተዉ  የያዟቸዉ አካላት ይለቁልን ዘንድ  እንጠይቃለን " ብለዋል።

ወደ ህዳሴው ግድብ ለስራ ሲሄዱ ተያዙ ከተባሉ ወጣቶች ጋር በተያያዘ ከቀናት በፊት ለቪኦኤ ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡት የሰጡት ' የአማራ ፋኖ የጎጃም ቃል አቀባይ ነኝ ' ያሉት ፋኖ ማርሸት ፀሀዩ ፦ " ልጆቹ አውቀውም ይሁን ተጭበርብረው ጎጃም ውስጥ ወደሚገኘው የብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ሲወሰዱ እንዳገኟቸው፤ ሲመሯቸው የነበሩትም ወታደሮች እንደነበሩ ከራሳቸው ከተገኘው መታወቂያቸው ማረጋገጣቸውን ነገር ግን በቀጣይ ከ72 እስከ 100 ሰዓታት ውስጥ ለቀይ መስቀል ለማስረከብ እየተዘጋጁ እንደሆነ " አሳውቀው ነበር።

ምንም እንኳን ይህ ከተባለ ቀናት ቢያልፉም የወጣቶቹ ጉዳይ ከምን እንደደረሰ የሚታወቅ ነገር የለም።

መረጃው በሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

መተግበሪያዎን ሲቢኢ ብር ላይ ያስቀምጡ
በቀላሉ በርካታ ደንበኞች ዘንድ ይድረሱ!

#CBE #cbebirr #apps #digitalbanking
*************
የሲቢኢ ብር መተግበሪያ ማስፈንጠሪያ፡

• ለአንድሮይድ ስልኮች፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡ https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ትግራይ
 
የትግራይ የማህበረሰብ ተወካዮች ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በመከሩበት ወቅት የትግራይ የንግድ ማህበረሰብ አባላት ከጦርነት በፊት ለንግድና ኢንቨስትመንት ማስፋፍያ የወሰዱት የብድር ወለድ ፣ የወለድ ወለድና ቅጣት እንዲነሳ የሚል ጥያቄ ማንሳታቸው ይታወሳል።

ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ምን የተደረሰ ውሳኔ አለ ? ሲል የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ፤ የትግራይ የንግድ ማህበረሰብ ከፍተኛ አመራሮችን አነጋግሯል።

አመራሮቹ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ በሰጡት ትእዛዝ እና ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት ከጦርነቱ በፊት የተወሰደው የብድር ወለድ ፣ የወለድ ወለድና ቅጣት በሚመለከት አጥንቶ በ10 ቀናት ውስጥ የውሳኔ ሃሳብ የሚያቀርብ አገር አቀፍ ኮሚቴ ተቋቁሞዋል ብለዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በሰጡት ትእዛዝና ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት ፤ በጠቅላይ ሚንስትሩ የኢኮኖሚ አማካሪ አቶ ግርማ ብሩ የሚመራ ፦
- የመከላከያ ሚንስትሩ ዶክተር አብራሃም በላይ 
- የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ
- የብሄራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ
- የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ 
- የጠቅላይ ሚንስትሩ የኢኮኖሚ አማካሪ አቶ ተክልወለድ አጥናፉ 
- የትግራይ የማህበረሰብ ንግድ ከፍተኛ አመራሮች በአባልነት ያካተተ አገር አቀፍ ኮሚቴ ተቋቁሞ በመስራት ላይ ይገኛል ሲሉ ገልጸዋል።

አገር አቀፍ ኮሚቴው ፦
➡ ከጦርነቱ በፊት የተወሰደው በድር ምን ያህል እንደሆነ ?
➡ የብድሩ ወለድ የወለድ ወለድና ቅጣት ስንት እንደሆነ ? አጥንቶ ያቀርባል ያሉት የትግራይ የንግድ ማህበረሰብ ከፍተኛ አመራሮች ፤ በጦርነቱ የወደመ የንግድና የኢንቨስትመንት የገንዘብ መጠን ሳይጨምር የወለድ ፣ የወለድ ወለድና ቅጣት ብቻ እስከ 60 ቢሊዮን ብር እንዲሰረዝ በጥናት ያቀርባል ብለዋል።
 
ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ማግስት ለብሄራዊ ባንክና ገንዘብ ሚንስቴር ጨምሮ ጥያቄው ለሚመለከታቸው ከፍተኛ የፌደራል የሚንስቴር መ/ቤቶች በተደጋጋሚ መቅረቡም አስታውሰው ጠቅላይ ሚንስትሩ በሰጡት ትእዛዝና ባስቀመጡት አቅጣጫ ጥናቱ አስከ መጋቢት 20/2016 ዓ.ም ተጠናቅቆ ቀርቦ እንደ ጡረታው የመጨረሻ ውሳኔ ያገኛል ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።

መረጃው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
                        
@tikvahethiopia            

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ሴጅ_ማሰልጠኛ

ማክሰኞ መጋቢት 17 2016 ዓ.ም 9ኛ ዙር ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Modern Accountancy and Auditing) ስልጠና ይጀምራል።
👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 መሠረታዊ አካውንቲንግ እና ኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት
ስልክ ፦ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
Facebook: https://www.facebook.com/sagetraininginstitute
Instagram: https://www.instagram.com/sage_training_institute/

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ለጥንቃቄ⚠️

" ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት ነው " እየተባለ ወደ ተለያዩ የባንኩ ደንበኞች ስልክ እየተደወለ የግል መረጃ መውሰድና የኦንላይን ዝርፊያ እየተሞከረ ይገኛል።

ቀደም ብሎ አንድ #አጭበርባሪ ግለሰብ (ጾታ - ወንድ) ሳያውቀው ለባንክ ሰራተኛ ደውሎ ያጋጠመውን ክስተት አጋርተናል።

የዜጎችን ሀቅና ገንዘብ አታለው ለመዝረፍ ስልክ ከሚደውሉት መካከል #ሴቶችም ስለሚገኙበት ጥንቃቄ አድርጉ።

ከላይ ባለው የድምፅ ቅጂ የምትሰሟት አጭበርባሪ ግለሰብ (ጾታ-ሴት) ከንግድ ባንክ ዋና መ/ቤት እንደደወለች በማስመሰል ፦ ደንበኞች የሞባይል ባንኪንግ ሲጠቀሙ ኔትዎርኩ please try again ፣ connection problem ፣ error ፣ service not available " የሚል ችግር እየገጠማቸው እንደሆነ ትገልጸለች።

በዚህ ምክንያት ባንኩ ከብዙ ደንበኞቹ ቅሬታ በመምጣቱ ፤ " ችግሩን በዋናው የንግድ ባንክ መ/ ቤት #ሲስተም ላይ ለማስተከል ነው " በማለት የደንበኛውን የግል መረጃዎች በመቀበልና በማታለል ዝርፊያ ለመፈፀም ሞክራለች።

አሁን ላይ እንዲህ ያሉት አጭበርባሪዎች ተበራክተዋል ተጠንቀቁ።

ለማንኛውም #የማታውቁት ስልክ የባንክ መረጃችሁን እንዳትሰጡ።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ወንጂ

" ከመቆጨት ከማዘን፣ ከመቃጠል በስተቀር ምንም ማድረግ አይቻልም " - የሟች ቤተሰብ

ለስራ በወጡበት በታጣቂዎች ታግተው ከቆዩ በኃላ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው ስለተገኙት 5ቱ የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች ቤተሰቦቻቸው ምን አሉ ?

ለደህንነቴ ስለምሰጋ ስሜ አጠቀስ ያሉ የሟች ቤተሰብ አባል ፦

" 6 ሰዎች ነበሩ ፤ ለስራ በሄዱበት ነው የታገቱ። ምንድነው ሲባል ገንዘብ ነው የሚፈልጉት ፤ መጀመሪያ በሰው 600 ሺህ ብር አሉ ከዛ ደግሞ 300 ሺህ ብር አሉ።

የተጠየቀውን ገንዘብ መ/ቤቱ እንደ ህግ አይፈቅድም ብሎ ህዝብ፣ ሠራተኛው በሙሉ ማሰባሰብ መሯራጥ ጀመረ፤ እነሱን ለማትረፍ።

በዛ መሃል ከቤተሰብም ከምንም ገንዘቡ ተሰባስቦ ከእነሱ ጋር ግንኙነት አድርገን ገንዘብ ሰጥተን ለማስለቀቅ ሲባል ይሄ ወንጀል ነው ተብሎ የቤተሰብ አካል ሁሉ እንዲያዝ ተደርጎ ግንኙነቶቹም እንዲቆሙ ተደረገ።

ከዛ ፌዴራል እነሱን እናስለቅቃለን በሚል ገብቶ ግጥሚያ ገጥሞ ወንድሞቻችን በዚያ ምክንያት ህይወታችን አለፈ።

ምንም ማድረግ አይቻልም ከመቆጨት ከማዘን፣ ከመቃጠል በስተቀር። ስድስት ነበሩ አምስቱን ገደሏቸው። አንዱ አምልጧል ተብሏል አንዴ ሞቷል ይባለል ጭራሽ ሌላ ሰቀቀን ነው ለቤተሰብ ያ ሰውየ በህይወት ይኑር አይኑር አይታወቅም። "

ሌላ አንድ የቤተሰብ አባል ፦

" እስከ ማክሰኞ ዕለት የሚፈልጉትን ብሩን ሰብስበን ፤ በአንድ ሰው 300 ሺህ ብር ነው የተስማማነው  ፤ ለእሮብ ጥዋት ብሩን እንድንሰጥና ቤተሰቦቻችንን እንድንወስድ ተነጋገርን።

ከዛ ብሩ ተሰብሰቦ ከ1.1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን በካሽ እየቆጠርን እያለ መጡ ፖሊስ አባላት ከነብራችን ያዙን ከዛ " ብር መያዝ ብር መሰብሰብ እንደ ወንጀል እንደሚቆጠር አታውቁም ወይ ? " ብለው ፖሊስ ጣቢያ ወስደው አሰሩን።  የተገረፈም አለ፣ ከየቤቱ አንድም ሁለትም ሰው ታሰረ ብቻ በጅምላ ነገሮችን እንደዛ አደረጉ፤ ወንጀለኛን በመርዳት በመደገፍ በሚል።

አጋቾች ሀሙስ ይሄ ነገር እንደ ሰሙ ብሩም እንደተያዘና ከዚህ መረጃ ተነግሯቸዋል (ብሩ ቀጥታ ፖሊስ ጣቢያ ነው ቀጥታ ተይዞ የገባው ከቤተሰቦቻችን ጋር) ፤ አጋቾቹ ያገቷቸውን ቤተሰቦቻችንን ከተነጋገርንበት ቦታ አንስተው ወደ ሌላ ቦታ ወስደው ህይወት እንዳጠፉ ተነገረን።

5ቱ ሰዎች ናቸው የተገደሉት። እጅግ በጣም አዘንን በቀል የእግዚአብሔር ነው ብለን ሁሉንም ነገር ትተናል።

6 እና 7 ቀን ከ60 ኪ/ሜ በላይ በእግር አስጉዘዋቸዋል። በየጫካው አሳድረዋቸዋል። ይህን በየአካባቢ ያሉ ሰዎች ነግረውናል። በጣም አዝነናል፤ ሞት አንድ ነው ግን እንዴት እንደዚህ አንድ ሞትን ለምኖ እስኪሞት ድረስ የተለመኑትን ሞት እንኳን ሳይሰጧቸው ተሰቃይተው ነው ቤተሰቦቻችን የሞቱት፤ ባሉበት በስብሰው።

መሳሪያ ብቻ አይደለም ያገኛቸው #በስለትም እንደተቆረጡ ሆስፒታል ሄደን አይተናል። በጣም አዝነናል። "

➡ 6ቱ የስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች የካቲት 29 ነበር በአንድ ተሽከርካሪ ሆነው ለስራ ወደ ፋብሪካው የሸንኮራ ማሳ በማቅናት ላይ እያሉ  የታገቱ። ከፍተኛ ገቢ አላቸው ተብለው የተገመቱት ሲታገቱ ሌሎች ተለቀዋል። ከ6ቱ አምስቱ ተገድለዋል።

➡ 4ቱ ፋብሪካውን ለረጅም አመታት ያገለገሉ አንጋፋ ሰራተኞች ናቸው አንዱ ገና ወጣት ነው። ሁሉም ቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ነበሩ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሟች ቤተሰቦችን ቃል ያዳመጠው ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ  / ጋዜጠኛ ኬኔዲ አባተ ከሰጡት ቃለምልልስ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ይጋብዙ፤ ይሸለሙ!

ቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያ ላይ “ይጋብዙ ይሸለሙ” የሚለውን አማራጭ በመጠቀም በአጭር መልዕክት ወይም በማኅበራዊ ሚዲያ መተግበሪያውን ያጋሩ፤ ወዳጆችዎ ግብይት ሲጀምሩ እርስዎ የ10 ብር ስጦታ ያገኛሉ፡፡

የቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያ በስልክዎ ከሌለ ከ http://onelink.to/fpgu4m ያውርዱ

ቴሌብር - ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የዘረፋ ሙከራ እየተደረገ ነው ተጠንቀቁ " - ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞቹ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበ።

ባንኩ ፤ " አጭበርባሪዎች ሰሞኑን ከሲስተም ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን ችግር እንደ አጋጣሚ ለመጠቀም ሙከራ እያደረጉ ነው " ብሏል።

አጭበርባሪዎች በአብዛኛው ከባንክ የደወሉ በማስመሰል “ የተዘጋ ሂሳብችሁን እንክፈትላችሁ” ፤ “ሂሳባችሁ እንዳይዘጋ የምንልክላቹሁን ኮድ አስገቡ” የሚል የማጭበርበሪያ ዘዴ በመጠቀም የዘረፋ ሙከራ እያደረጉ ነው ሲል ገልጿል።

ባንኩ ስልክ ደውሎ ስለ ሂሳብ መረጃ የሚጠይቅበት፣ ሂሳብ የሚከፍትበትም ሆነ የሚዘጋበት አሰራር እንዲሁም ደንበኞች እንዲጠቀሙበት የሚልከው  ምንም አይነት ኮድ እንደሌለ አስገንዘቧል።

ማንኛውም የባንኩ ደንበኛ መሰል ሁኔታ ሲገጥመው ምንም አይነት እርምጃ ከመውሰድ እንዲቆጠብ አሳስቧል።

በሌላ በኩል ፤ ከሰሞኑን በነበረው ሁኔታ ምንም ባላወቅንበት አካውንታችን ታግዷል  በሚል በርካታ ሰዎች ቅሬታቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ።

ለአብነት ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ደንበኞች ፤ " በዕለቱ ምንም ዝውውር ባላደረግንበት፣ ገንዘብ ባላወጣንበት፣ ባላክንበት ሁኔታ አካውንታችን ታግዷል የሚል መልዕክት የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያችን ላይ እያየን ነው " ብለዋል።

ችግሩ ተጣርቶ በፍጥነት እንዲፈታም ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

የሳሞአው ስምምነት ከምን ደረሰ ?

ኢትዮጵያ ከ79 ሀገራት ጋር የፈረመችው የሳሞዓ ስምምነት እስካሁን ለፓርላማ አለመቅረቡን “ ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ትውልዱን ከግብረሰዶም እንታደግ ” ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

ኢትዮጵያን ጨምሮ አጠቃላይ 79 የአፍሪካ እና የካረቢያንና ፓስፊክ ሀገራት (48 ከአፍሪካ፣ 16 ከካረቢያን፣ 15 ከፓስፊክ) ሳሞአ ላይ አንድ ስምምነት መፈራረማቸው ከወራት በፊት ተዘግቦ ነበር።

የተፈረመው ስምምነት " የአፍሪካ፣ የካረቢያን እና የፓስፊክ ሀገራት ከአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ጋር የሚያደርጉት የንግድ እና ኢኮኖሚ ትብብር " መሆኑ፣ ምስምነቱ 22 ዓመታትን የዘለቀ " የኮቶኑ ስምምነት " ቀጣይ እንደሆነ በወቅቱ መብራራቱ አይዘነጋም።

ይህንኑ ስምምነት በበርካታ ሀገራት ጥያቄ አስነስቶ ነቀፌታ ሲያስተናግድ የተስተዋለ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ የሚገኙ የዘርፉ ተቋማት በበኩሉቸው ስምምነቱን " ትውልድ ገዳይ " ሲሉ አውግዘውታል።

“ ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ትውልዱን ከግብረሰዶም እንታደግ ” የተሰኘው ማኀበር፣ ኢትዮጵያ ከ79 አገራት መካከል አንዷ ሆና የሳሞዓ ስምምነትን እንደፈረመች፣  ስምምነቱ ግብረሰዶማዊነትን ማስፋፊያ ሃሳብ መያዙን በአንክሮ በማስረዳት፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ውድቅ እንዲደረግ (እንዳይጸድቅ) ጠይቆ ነበር።

ይህን ተከትሎም ጉዳዩ ከምን ደረሰ ? ፓርላማ ላይ ቀርቦ እንዳይጸድቅ ተደረገ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለማኀበሩ ፕሬዚዳንት ሊቀ ትጉሃን መምህር ደረጀ ነጋሽ (ዘወይንዬ) ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ “ አላቀረቡትም እነርሱም ቁጭ ብለዋል። ግን ብዙዎቹን አናግረናቸዋል፣ ብዙዎቹ አልወደዱትም። እነርሱም ፈርተው ነው እስካሁን ያላቀረቡት ” ብለዋል።

ያለውን ሂደት በተመለከተ ባስረዱበት አውድ ፥ “ በዚሁ ዙሪያ እኛም የግንዛቤ ማስጨበጫ እየሰጠን ነው ለተለያዩ መ/ቤቶች። ከሃይማኖት ተቋማት ጋር አወራን፣ ከሌሎቹም የሃይማኖት አባቶች አናገርን እነርሱም አላቀረቡትም ” ሲሉ አስረድተዋል።

መምህር ደረጀ ከዚህ በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ማብራሪያ፣ የስምምነቱን ከባድ ምስጢራዊነትና እንድምታ በGender፣ በጾታ ስርዓተ ትምህርትና በሌሎች ነጥቦች እያጣቀሱ ስምምነቱ በሰብዓዊ መብት ሽፋን ግብረ ሰዶማዊነትን ማስፋፊያ መንገድ መሆኑን፣ “ ፍጹም የሆነ ትውልዱን ለ20 ዓመታት ታሳሪ የሚያደርግ የሞት ውል ነው ” ብለውታል።

ማኀበራቸው በወቅቱ በሰጠው መግለጫም
፣ “ ዘመናዊ ቅኝ ግዛትና ድምጽ አልባው ትውልድ ገዳይ የግብረሰ ዶማዊያን ድርጊትን እንቃወማለን ” ነበር ያለው።

ከዚህ ማህበር በተጨማሪ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ስምምነቱን በመቃወም በህ/ተ/ም/ቤትም ስምምነቱን ባለማፅደቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርቦ ነበር። ይህ መግለጫ ከወጣ በኃላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዶቼ ቨለ በሰጠው ቃል ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚባለውን አይነት ስምምነት አፀድቃለሁ ብሎ እንዳልፈረመ ፤ የሃይማኖት ተቋማት የስራ ኃላፊዎችም ያላቸው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ምላሽ ሰጥቶ ነበር።

መረጀው የተዘጋጀው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ እና  በዕቃዎቻችን ጥራት ላይ  ደንበኞቻችን ምስክሮቻችን ናቸው። ዛሬም ብዛትንም ጥራትንም ሳንቀንስ እያስተናገድን እንገኛለን።

👉ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ

አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ የሚያገኙበትን ሱቃችንን ይጎብኙ። የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ ባሉበት ሆነው ይዘዙን እናደርሳለን።

የዕቃዎች ዋጋ  ፣ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech
ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።
@sww2844 0928442662 / 0940141114

https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ሲቢኢ #ዩኒቨርሲቲዎች #ኦዲት

" ባንኩ ላይ የሳይበር ጥቃት ደርሷል፤ ዝውውሩም አይታወቅም ብለው አስበው ነው ያደረጉት " - አቶ አቤ ሳኖ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዜዳንት አቶ አቤ ሳኖ በዩኒቨርሲቲዎች አካባቢ ስለነበረው የመጋቢት 6 ለሊት የገንዘብ ዝውውር እና አጠቃላይ ወጭ ስለተደረገው / አሁን ስለተመለሰው የገንዘብ መጠን ምን አሉ ?

አቶ አቤ ሳኖ ፦

" የተቋረጠውን አገልግሎት ካስጀመርን በኃላ ወደ ግብይቶች ምርመራ ነው የገባነው።

በዛ ያለ ግብይት ያደረጉትን ለይተናቸው የፍትሕ አካላት እንዲያውቁት አድርገናል። በብዛት በዛ ያለ ቁጥር ያለው እጅግ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ #በዩኒቨርሲቲዎች አካባቢ ነው።

ተማሪዎቹ (የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ) ያሰቡት ባንኩ ላይ የሳይበር ጥቃት ደርሷል ብለው ነው። ስለዚህ የሚደረገው ግብይት (ወጭ / ዝውውር) አይታወቅም ብለው ነው ያደረጉት።

አሁን ላይ ግን ግብይቱ እንደሚታወቅ ሲያውቁ የወሰዱትን ገንዘብ እየመለሱ ነው ያሉት። አሁንም እንዲመልሱ ነው የምንፈልገው።

የወሰዱትን ገንዘብ ከመለሱ ወደ ክስ አንሄድም። የማይመልሱ ከሆነ ግን የህግ እርምጃ እንወስዳለን።

ዝርዝር ጉዳዩ (ከገንዘብ ዝውውር/ወጭ የተደረገ/የተመለሰ) ኦዲት ተደርጎ ሲያልቅ ይቀርባል።

የኦዲት ሂደቱ ስላላለቀ በዚህ መካከል ሌሎች ነገሮችን ማንሳት ከፋይናንሻል ኦዲት አካሄድ ጋር የሚሄድ ስላልሆነ አንዳንድ የህጋዊ እርምጃዎችም ሊከተሉ ስለሚችሉ ጥንቃቄ ስለሚፈልግ ነው። "

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ነእፓ

በሀገሪቱ ያሉ የእርስ በርስ ግጭቶችን ለማስቆም “ ኢትዮጵያ በልጆቿ ትታረቅ ! ” በሚል የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ የእርቅ እና የሰላም ሀሳብ ይዞ መቅረቡን አሳውቋል።

ፓርቲው በላከልን መግለጫ ፤ ሀገራችን በታሪኳ በርካታ በእርስ በእርስ ግጭቶችን ማስተናጓን ገልጿን።

ለ2 አመታት በትግራይ፣ በአማራ እና አፋር ክልሎች የተካሄደው ጦርነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖቻችንን ህይወት መቅጠፉን አመልክቷል።

አሁንም በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች የቀጠለው የወንድማማቾች ጦርነት የወገኖቻችንን ህይወት እየቀጠፈ እንደሚገኝ ገልጿል።

በየአካባቢው በተለኮሱ ጦርነቶች ሳቢያ ፦

- በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ውድ ህይወታቸውን እንዳጡ፣ አካላቸው እንደጎደለ፤

- እድሜ ልካቸውን ያፈሩት ንብረት እና የሀገራችን ኢትዮጵያ አንጡራ ሀብትም እንደወደመና እየወደመም እንደሚገኝ ገልጿል።

በእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ህጻናት ያለ አሳዳጊ፣ አረጋውያን ያለ ጧሪ ፣ አያሌ ኢትዮጵያውያን ለርሀብ፣ ለእንግልት፣ ለስደት እና ለሞት መዳረጋቸውን ገልጿል።

በየአካባቢው የተከሰቱ ግጭቶች ማህበራዊ ግንኙነታች እንዲበጣጠስ፣ በዜጎች መካከል ጥርጣሬ እንዲነግስ፣ ማህበራዊ ትስስራችን እንዲላላ፣ ጥላቻ፣ እልህ፣ በቀል እንዲስፋፋ፣ ስጋት እና ጭንቀት በዜጎች ልቦና እንዲሰፍን ማድረጋቸውንም አመልክቷል።

ነእፓ፤ ጦርነት መቼም ቢሆን የፖለቲካ ልዩነቶችን ለመፍታት የተሻለ አማራጭ አይሆንም ፤ የእርስ በእርስ ጦርነት አሸናፊና ተሸናፊ የሌለው የመጨረሻ ውጤቱ ሞት፣ ስደት፣ ስቃይ፣ ሀዘን ፣ የሀገር ድቀትና መፍረስ ነው ብሏል።

ላለፉት ዓመታት ሰላም እንዲሰፍን በተለያዩ መንገዶች ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን የሚገልጸው ነእፓ ሀገራችንን ለክፉ ችግር፣ ህዝባችንን ማባሪያ ለሌለው ሰቆቃ የዳረጉ ጦርነቶች እንዲቆሙ “ #ኢትዮጵያ_በልጆቿ_ትታረቅ ” በሚል ስያሜ አዲስ የእርቅ እና የሰላም ሀሳብ መንደፉን ይፋ አድርጓል።

ዋናው ዓላማ በመንግስት እና ከመንግስት ጋር ነፍጥ አንግበው በሚፋለሙ ማናቸውም ኃይሎች መካከል በሀገር ሽማግሌዎች፣ በኃይማኖት አባቶች እና በሌሎች ታዋቂ ስብእናዎች አማካኝነት እርቅ ማውረድ እንደሆነ ገልጿል።

በቀጣይ ሂደቱን በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎች ይሰጣሉ ብሏል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#CBE

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ ምን አሉ ?

- " ችግሩ የተከሰተው አንድ ሂሳብ ማስታረቅ ቅልጥፍና እንዲያመጣ ታስቦ የተሰራ የሲስተም ማሻሻያ ሲተገበር ስህተት በመፈጠሩ ነው። የተፈጠረው ስህተት ለሌቦች ቀዳዳ ከፍቶ ነበር። "

- " የሲስተም ማሻሻያው የተተገበረው አርብ መጋቢት 6/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዓት አካባቢ ነበር። ከሌሊቱ 8 ሰዓት አካባቢ ችግር እንዳለ ሊለይ ችሏል። ይህን ተከትሎም አንዳንድ የተጠረጠሩ አገልግሎቶች እንዲቋረጡ ተደርጓል። ይህም ሆኖ ሙሉ በሙሉ ችግሩ ስላልቆመ ሁሉም የዲጂታል ባንክ ስርዓቶች እንዲቋረጡ ተደርጎ ነበር። "

- " ባንኩ ችግሩ በተከሰተበት ወቅት ከ490 ሺህ በላይ የገንዘብ ልውውጥ ተካሂዷን። ሌሊቱን ሙሉ ግብይት ሲፈጸምባቸው የነበረባቸው የባንክ ሂሳቦች በሙሉ እስኪጣራ ድረስ #እንዲታገድ ተደርጓል። "

- " በቀጣይ ከፍተኛ እና ያልተገባ ግብይት የፈጸሙ አካላትን እየለየን ለህግ የማቅረብ ስራ ይሰራል። "

- " የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በወንጀሉ ዋነኛ ተዋናይ መሆናቸው አሳዝኖናል። በየአካባቢው ያሉ የዲስትሪክት ኃፊዎች በየአካባው ከሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመቀናጀት ተማሪዎች የወሰዱትን ገንዘብ #እንዲመልሱ እየተደረገ ነው። "

- " ከተፈጠረው ችግር ጋር ተያይዞ አጠቃላይ የደረሰው ጉዳት ላይ ምርመራ እየተደረገ ነው። የችግሩ መሰረታዊ መንስዔ እና ያስከተለውን ጉዳትም ምርመራው ሲጠናቀቅ ይፋ ይደረጋል። "

- " ባንኩ ላይ የደረሰው ጉዳት ባንኩ ካለው ሀበት እና አቅም አንጻር የጎላ ተጽእኖ የለውም፤ ከደንበኞች ሂሳብ ጋርም አይገናኝም። " #አልአይን

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#NationalExam

" የ12ኛ ክፍል ፈተና ዝግጅት እየተገባደደ ነው ፤ ... በቀጣይ የፈተናው ሕትመት ይጀመራል " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

ለ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የፀጥታ ችግር በሌላባቸው አካባቢዎች ብቻ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች በስተቀር በአብዛኛው ሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የተማሪዎች ምዝገባ ተካሂዶ መጠናቀቁን የገለጸው መ/ቤቱ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለብሄራዊ ፈተናው ምዝገባ ማከናወናቸውን ጠቁሟል።

የፀጥታ ችግር ባለባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የሚገኙ ተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ በዚህ ሣምንት ይከናወናል ብሏል።

የፈተና ዝግጅት ሥራው የሀገሪቱን ሥርዓተ ትምህርት የተከተለ እና ተማሪዎቹን በአግባቡ መመዘን በሚያስችል መልኩ መዘጋጀቱን አገልግሎቱ ገልጿል።

የፈተናው ዝግጅት እየተገባደደ መሆኑን አመልክቶ በቀጣይ #የፈተናው_ሕትመት እንደሚጀመር አሳውቋል።

የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የመስጫው የጊዜ ሰሌዳ ወደፊት ይፋ እንደሚሆንም የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#EthiopianAirlines

" ተፈፅሟል የተባለውን ሙስና እና እንግልት የፈፀሙት የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ናቸው ፤ ሰራተኞቹም በቁጥጥር ስር ውለዋል " - አቶ መስፍን ጣሰው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰሞነኛና በአየር መንገዱ እንቅስቃሴ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ፤ " በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ለሚፈፀሙ ወንጀሎች አየር መንገዱን ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ማድረግ ተቀባይነት የለውም " ብለዋል።

በአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ከአየር መንገዱ በተጨማሪ፦
- ኢሚግሬሽን ፣
- የጉምሩክ ፣
- የብሄራዊ መረጃና ደህንነት እንዲሁም ፌደራል ፖሊስ የራሳቸው ድርሻ አላቸው ሲሉ ገልጸዋል።

በቅርቡ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በአንዲት መንገደኛ ላይ ተፈፅሟል የተባለውን ሙስናና እንግልት የፈፀሙት የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች እንጅ የአየር መንገዱ ሰራተኞች አይደሉም ብለዋል።

" ወርቅና ብር ይዘው መውጣት አይችሉም " ሲሉ የነበሩት አካላት የጉምሩክ ክፍል ሰራተኞች እንደሆኑ ጠቁመዋል።

አቶ መስፍን ፤ ወርቅና ብር ይዘው መውጣት አይችሉም የተባሉት ደንበኛ ጉዳይ ዋነኛው ቅሬታ እንደነበር አስታውሰው " ድርጊቱን የፈፀሙ የከስተም ወይም የጉምሩክ ክፍል ሰራተኞች ናቸው " ሲሉ ተናግረዋል።

ግለሰቦቹን በካሜራ እገዛ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን ተናግረዋል።

በቀጣይም አየር መንገዱ እንዲህ አይነት ድርጊቶችን የማይታገስ መሆኑንና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እርምጃ እንደሚወስድ አሳስቧል፡፡

በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ከ3 ሺህ በላይ የደህንነት ካሜራዎች እንዳሉም ተሰምቷል።

መረጃው የኢትዮ ኤፍ ኤም እና WMCC ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…
Subscribe to a channel