#ዶላር
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዶላር ዋጋ አሽቆለቆለ።
ባለፉት በርካታ ቀናት በንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ112 ብር ከ3957 ሳንቲም እየተገዛ በ123 ብር ከ6353 ሳንቲም ሲሸጥ ነበር።
ዛሬ ባንኩ ይፋ ባደረገው የዕለታዊ የምንዛሬ ተመን አንዱን የአሜሪካ ዶላር የሚገዛበትን ዋጋ ወደ 113 ብር ከ1308 ሳንቲም አሳድጎ መሸጫውን ወደ 115 ብር ከ3934 ሳንቲም አውርዶታል።
እንደ ዛሬው የምንዛሬ ተመን ባንኩ ዶላር መግዣውን በ1 ብር ከፍ ያደረገው ሲሆን መሸጫው ላይ ካለፉት ቀናት የ8 ብር ቅናሽ አድርጎበታል።
@tikvahethiopia
ዛሬና ነገ በኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም በአፍሪካ እጅግ ትልቁ የቴክኖሎጂ ውድድር ”A2SV - AI for Impact Hackathon Expo” ይከናወናል! ለሁለተኛ ጊዜ በአዲስ አበባ የሚካሄደው ይህ ውድድር የአፍሪካ ድንቅ ባለ ተሰጥኦ ወጣቶች አርተፊሻል አስተውሎትን በመጠቀም ችግር ፈቺ የሆኑ ፈጠራዎች የሚያሳዩበት ነው።
ሁላችሁም ይሄንን የቴክኖሎጂ ኤክስፓ መታችሁ እንድትጎበኙ እንጋብዛለን ። እንዲሁም ረቡዕ ጥቅምት 6 የሚካሄደውን ከ 7 የአፍሪካ ሀገራት የመጡትን ተወዳደሪዎች የመጨረሻ ለ 30,000 ዶላር ሽልማት የሚያደርጉትን ፍልምያ እንድትታደሙ ጋብዘኖታል ። በእለቱም የአዲስ ኣበባ ከንቲባ ክብርት አዳነች አቤቤ የመክፈቻ ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ።
የፕሮግራሙ መርሀግብር
- ኤክስፖ: ጥቅምት 5 - 6 2017 ከጠዋቱ 3 ሰአት እስከ ምሽት 12 ሰዓት
- መዝጊያ ፕሮግራም: ጥቅምት 6 2017 ከምሽት 12 ሰአት እስከ ምሽት 1 ሰዓት
- ቦታው: የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚያም
መግቢያ በነፃ !
(አዘጋጆቹ)
#AAiT
Announcement of Professional Training Programs
1. Python Programming + Data Analytics and Visualization
2. Python Programming + Artificial Intelligence
By: Addis Ababa University,
Addis Ababa Institute of Technology (AAiT),
School of Electrical & Computer Engineering
Registration Deadline: October 19, 2024
Training Starts on: October 28, 2024
Registration: Addis Ababa Institute of Technology (AAiT),
School of Electrical and Computer Engineering, Main Building 1st Floor, Office Number: 124
Online Registration Link: https://forms.gle/E54L9aVkHQ1pCs8v5
Telephone: +251-940-182870 / +251-913-574525
Email: sece.training@aait.edu.et
For more information: Read instructions here ==> https://forms.gle/E54L9aVkHQ1pCs8v5
Our Telegram Channel for updated information: /channel/TrainingAAiT
" አሻራ የሚቀመጠው ታሪክን በመደምሰስና በሕዝብ ሰቆቃ ላይ አይደለም ! " - አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች
አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ልከዋል።
ፓርቲዎቹ ፦
➡️ እናት
➡️ መኢአድ፣
➡️ ኢሕአፓ፣
➡️ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ ናቸው።
ፓርቲዎቹ ምን አሉ ?
" ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ በመጀመሪያ የወንዝ ዳር ልማትና የጫካ ፕሮጀክት በሚል ተጀምሮ አኹን ላይ የኮሪደር ልማት በሚል መጠኑንና አድማሱን አስፍቶ ሙሉ ከተማ ወደማፍረስ የተሸጋገረው ሥራ አሻራ በማሳረፍ ሰበብ የመቶ ሺህዎችን ሕይወት እያመሰቃቀለ እንደሚገኝ ባደረግነው ዳሰሳ ተረድተናል " ብለዋል።
" በድንገት ቤታቸው የፈረሰባቸውና የይፈርሳል መርዶው ሲነገር ለጠና ሕመም የተዳረጉ፣ ከለመዱት ማኅበራዊ መሠረት የተናጠቡ፣ ሥራቸው ሙሉ ለሙሉ የተቋረጠና ለከፋ ችግር የተዳረጉ፣ ቍጥሩ በውል ያልታወቀ በድንጋጤም የሞቱ እንዳሉ ለመረዳት ችለናል " ሲሉ ገልጸዋል።
" ከዋና ባለቤቶች/ባልይዞታዎች ባልትናነሰ ተከራዮች ከፍ ላለ ስቃይ እንደተዳረጉ፣ አካል ጉዳተኞችና አቅመ ደካሞች የከፋ ችግር ላይ መውደቃቸውን ታዝበናል " ሲሉም ጠቁመዋል።
ፓርቲዎቹ " ይዋል ይደር እንጂ ይህ የሕይወት መመሰቃቀል የማይነካው የከተማዋ ነዋሪ እንደማይኖር ለመገመት ነቢይ መሆን አይጠይቅም " ብለዋል።
" አዲስ አበባ በዓለም ሦስተኛዋ ድፕሎማቲክ ከተማ በመኾኗ ንፁሕ መሆን፣ የበለጠ ማማርና መዘመን እንዳለባት ኹሉም የሚቀበለው ሀቅ ነው " ያሉት ፓርቲዎቹ " ይህ ማለት ግን ከተማው ' ያረጀ ነው፤ የቤቶቹ ግድግዳ ጭቃና እንጨት ነው፤ ሸራ ነው፤ አብዛኛው የመንግሥት ቤቶች ናቸው፤ ...' በሚል ሰበብ በአንድ በኩል አዛኝ በመምሰል በግልባጩ ግን ከተማው ' የእኛ ' አሻራ የለበትም በሚል ከስሁት ትርክት በተወለደ ጥላቻ የማፍረሻ ምክንያት እየፈለጉ የከተማዋን ነዋሪ በማፈናቀልና በአንድ ጀምበር ኑሮውን ወደ ሲዖልነት መለወጥ ፍጹም ተቀባይነት የሌለውም " ብለዋል።
ከዚህ ባለፈው " ሀገር የምትተዳደርበትን ሕገ መንግሥት (አንቀጽ 40፣ 41፣ 89፣ 90፣ 91፣ 92) እና አዋጅ ቍ. 1161/2011 ዓ.ም በመሠረታዊነት የጣሰና ይጠብቀው ዘንድ ሓላፊነቱን በተቀበለ መንግሥት እየተፈጸመ የሚገኝ ከፍተኛ ወንጀል ነው ብለን እናምናለን " ሲሉ ገልጸዋል።
" ቤት ንብረታቸው በአንድ ጀምበር እንዲፈርስ የሚደረጉ ዜጎች በአብዛኛው ካሳም ሆነ ምትክ ቦታ እንዲሁም በቂ የመዘጋጃ ጊዜ ሳይሰጣቸው በማኅበረሰብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ጭምር ለመኖር እየተገደዱና ሌሎች ደግሞ ጊዜያዊ መጠለያ በቆርቆሮ ሠርተው እንዲገቡ መመሪያ የተሰጣቸው መሆኑን ከተረኛ የጉዳቱ ሰለባዎች ለመረዳት ችለናል " ብለዋል።
" ከእነዚህ ዜጎች ‘እድለኛ’ የሆኑ ጥቂቶቹ በማካካሻ መልክ የሚሰጣቸው ኮንዶሚኒዬም ቤት ብዙ 100 ሺዎች ለአሥርት ዓመታት ቆጥበው የተሠራና እጣው ባለመውጣቱ እንጂ ባለቤት ያለው ነበር " ሲሉ ገልጸዋል።
አራቱ ፓርቲዎች ፥
° " በአያገባህም " ስሜት የከተማ ልማት መሪ እቅድ ወደ ጎን ተወርውሮ በጥናትና ስሌት ሳይሆን በስሜት ብቻ ከላይ ወደታች በሚወርድ ውሳኔ፣
° ጥቅምና ጉዳታቸው በዘርፉ ባለሙያዎች ያልተመዘነ፣
° በፕሮግራም/strategy/ ያልተያዙና የአጭር ጊዜ ትርፍ ብቻ ያላቸው (project based) አካሄድ እንዲህ የኑሮ ውድነት፣ የቤት/የቦታ እጥረትና ዋጋ መናር፣ የመጓጓዣ፣ የውሐና መሰል መሠረተ ልማት ችግር ጠፍሮ ለያዛቸው ከተሞች የእግረኛ መንገድ፣ የሕንጻ ላይ መብራትና ቀለም፣ ሣርና ዘንባባ ተከላ እና መሰል የተብለጨለጩ ማሸብረቂያዎች የወረት ያህል ለጊዜው ከላይ ሲታይ ያማረ ቢመስልም የከተማውን ነዋሪ ማኅበረ ኢኮኖሚያዊ ችግር ቢያወሳስበው እንጂ እሴት ጨምሮ ችግራቸውን አይፈታውም፤ የሥርዓቱንም ስም አይገነባም ብለዋል።
" ከተማን የማሳመርና ማዘመን ሀሳብ ከየትኛውም ወገን ሊነሳ ቢችልም ከመሪዎች ፍላጎት /inspiration/ በላይ በዘርፉ ልምድና እውቀት ጠገብ በሆኑ ባለሙያዎች ኹለንተናዊ ምልከታና ሙግት ተደርጎበት ትርፍና ኪሳራው ተሰልቶ ሊሆን እንደሚገባ በጽኑ እናምናለን " ሲሉ ገልጸዋል።
" አሻራ ማኖር በራሱ የሚጠላ ባይሆንም ፖለቲካዊ ፍላጎት የተጫነው፣ ሕዝብን ያገለለ፣ ታሪክን የሚያፈርስ፣ የማኅበረሰብን በዘመናት የተገነባ ማኅበረ ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር የሚያናጋ፣ ነዋሪዎችን በአንድ ጀምበር ጥሪት አልባ የሚያደርግ፣ ብዙ መቶ ሺዎች የሚተዳደሩበትን የንግድ ሥራ ሙሉ በሙሉ የሚገድል፣ ግብታዊና ነዋሪው ‘በአብሬ አድጋለሁ’ ተስፋ ሳይሆን ‘በያፈናቅሉኛል’ ሥጋትና ኹል ጊዜ መጻተኛ ስሜት እንዲሰማው የሚያደርግ መሆን እንደሌለበት የሚታመን ቢሆንም በአዲስ አበባ ከተማ እየተተገበረ ያለው ይህ መራራ እውነት ነው " ብለዋል።
ፓርቲዎቹ ፤ " አኹን ላይ በአዲስ አበባ በ4ኪሎ፣ 5ኪሎ፣ ፒያሳ፣ ቤላ፣ አምባሳደር፣ ፈረንሳይ፣ ቦሌ፣ ካዛንችስ፣ ገርጂ እና በኹሉም ወንዝ አለባቸው በሚባሉ የከተማዋ አካባቢዎችና በሌሎችም አካባቢዎች በዋና ዋና መንገዶች ዳርቻ ከፍተኛ ፈረሳዎች እየተካሄዱ/እንደሚካሄዱ በይፋም ይፋዊ ባልሆነ መንገድም እያየንና እየሰማን ነው " ሲሉ ጠቁመዋል።
" በኑሮ ውድነትና ሰላም እጦት ወገቡ የጎበጠን ማኅበረሰብ አለፍ ሲልም ገሃድ የወጣ የከተማ ውስጥ ረሃብ ባለበት በተጣደፈ አኳኋን ዜጎችን ከድጡ ወደ ማጡ መውሰድ ለምን እንደተፈለገ አፍራሾቹ ብቻ የሚገባቸው እውነት ኾኖ ዋናው ግን ልማት ሳይሆን ፦
• ነባሩን ማኅበረሰብ ከማኅበራዊ መሠረቱ መነጠልና ማሳሳት፣
• የእምነት ቦታዎችን ያለሰው ማስቀረት፣
• ሰውን ከመሐል መግፋት ከዳር ማስጨነቅ፣
• መንግሥት የገጠመውን በጀት እጥረት ከሊዝ ሽያጭ መሰብሰብ፣
• ሥርዓቱን ተጠግተው ፍርፋሪ ለሚጠብቁ " የአየር ባየር ባለሀብቶች " ማበልጸጊያ እንደሆነ እሙን ነው " ብለዋል።
" በሌላ በኩል እንደሥርዓት በሀገር ደረጃ ያጣውን ቅቡልነትና ቁጥጥር በማዕከል አለሁ ለማለትና አዲስ የከተማ ትርክት/narration/ ከመፍጠር የመነጨ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
" ቢያንስ ቢያንስ ተነሽዎችን ከአልሚዎቹ/ባለሀብቶች ጋር በመስማማት ከሚሠራው ሕንፃ አንደአቅማቸው የድርሻቸውን አግኝተው እንዲኖሩ ማድረግ በተገባ ነበር " ያሉት ፓርቲዎቹ " እየተፈጸመ ያለው ነገር ኢ ሕገ መንግሥታዊ፣ አግላይ፣ የበላይና የበታች አካሄድ በመሆኑ በጽኑ እናወግዛለን " ብለዋል።
አራቱ ፓርቲዎች ፦
1ኛ. " መንግሥት በሕገ መንግሥቱ የተደነገገውን የዜጎች መብት እንዲያከብርና ማኅበረሰቡን መሠረታዊ በሆነ መልኩ ከሚያናጋ በልማት ሽፋን የሚተገበር ደባ እንዲያቆም " ብለዋል።
2ኛ. " የፈረሳው ሰለባ የሆነው የአዲስ አበባ ነዋሪ ባገኘው አጋጣሚ ኹሉ ድርጊቱን በሰላማዊ መንገድ በመቃወም ሕገ መንግሥታዊ መብቱን እንዲያስከብር " የሚል ጥሪ አቅርበዋል።
3ኛ. " ከቦታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች የነበሩበትን ቦታ ካርታና መሰል የነዋሪነት/ባለ ይዞታነት/ ማስረጃዎች በጥንቃቄ እንዲያስቀምጡ " አስገንዝበዋል።
4ኛ. " አዲስ በፈረሱ አካባቢዎች ላይ እየገነችሁ ያላችሁ ባለሀብቶች የተፈናቀለ ወገናችሁ አንድ ቀን ተመልሶ እንደሚመጣ አድርጋችሁ ማሰብም መሥራትም አለባችሁ " ሲሉ አሳስበዋል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia #1Wedefit
🥇የሳፋሪኮም #1ወደፊት ዲጂታል ሙዚቃ ውድድር ምርጥ አስሮቹ ታውቀዋል!
የ#1Wedefit ዲጂታል የሙዚቃ ውድድራችን ምርጥ 10 አሸናፊዎች እነዚህ ናቸው! እስቲ 💫 ክዋክብቶቻችንን አብረታቱልን! አሸናፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ!
#FurtherAheadTogether #DigitalMusicChallenge
“ መንግስት አልፈጽምም ቢል ለኢትዮጵያ ህዝብ የማሳወቅ ኃላፊነት ተሰጥቶታል” - ኮሚሽኑ
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ አጀንዳ የማሰባሰብ የምክክር መድረክ ምዕራፍ ዛሬ በይፋ መጀመሩን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መላኩ ወ/ማርያም አብስረዋል።
እስከ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ/ም ባሉት ቀናትም ከክልሉ 10 የማህበረሰብ መሰረቶችን የወከሉ ከ2,000 በላይ ተሳታፊዎች በጅግጅጋ፣ በጎዴ እና ዶሎ አዶ ማዕከላት ተከፋፍለው ከወከሉት ማህበረሰብ ባመጧቸው አጀንዳዎች ይመካከራሉ።
በአጠቃላይ የምክክሩን የመጨረሻ ውጤት መንግስት አልቀበልም ቢል የምክክሩ ውጤት ተፈጻሚነት የማግኘት እድል አይኖረመውም የሚሉ ስጋቶች ሲሰነዘሩ ይስተዋላል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም ኮሚሽኑ አስገዳጅ አንቀጽ አለው ወይ ? ሲል ለኮሚሽነር መላኩ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን እሳቸውም ምላሽ ሰጥተዋል።
“ አስገዳጅ አንቀጽ አለው። ቢቲውን ዘላይንስ ማንበብ አለብን። እንደገና ደግሞ ሕግን ስንተረጉም ብሮዴሊ ነው መተርጎም ያለብን። ለኮሚሽኑ የተሰጠው ስልጣን ሪሊይ ከፍተኛ ነው።
ምክንያቱም በሀገራዊ ምክክር ጉባዔው የተካሄዱ ምክክሮችና አውት ካሞች በስርዓት ተሰንደው፣ ከዚያ በኋላ የማፈጸሙበት የአተገባበር እቅዱ ወጥቷላቸው መሬት ላይ እስከሚወርዱ ድረስ የመከታተል ኃላፊነት የኮሚሽኑ ነው ይላል።
ዝም ብሎ የሀገራዊ ምክክር ጉባዔው በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል ብሎ አሳውቆ የሚገባ ብቻ ኮሚሽን አይደለም።
ውጤቶቹ መፈጸማቸውን እስከሚረጋገጥ ድረስ የሚሄድ ኮሚሽን ነው። መንግስት አልፈጽምም ቢል ለኢትዮጵያ ህዝብ የማሳወቅ ኃላፊነት ተሰጥቶታል።
የተመካከርክበት ጉዳይ ይሄ ነው፤ የወሰንከው ጉዳይ ይሄ ነው፣ ውሳኔህን አስተላልፈናል፤ ውሳኔህን ተፈጻሚ ለማድረግ ያልፈለገ ወገን አለ፤ ይሄ ወገን ደግሞ ይሄ ነው፤ ብለን ማሳወቅ ነው።
ለዚህም ነው ይሄ ምክክር የኢትዮጵያ ህዝብ መብቱን የሚያረጋግጥበት ሂደት፣ ባለቤትነቱን የሚያረጋግጥበት ሂደት መሆን ያለበት።
የተወሰኑ ሰዎች የሚወስኑበት አግባብ ከዚህ በኋላ ማቆም አለበት። መጨረሻም የጉዳዩ ባለቤት ወደሆነው ወደ ህዝብ ነው የምናመጣው። ህዝቡ ግፊት እንዲያደርግ፣ እንዲፈጸም እንዲጠይቅ ማለት ነው ” ብለዋል።
የታጠቁ ኃይሎች በምክክሩ እንዲሳተፉ ጥሪ ከተደረገላቸው ኮሚሽኑ ጋር ለመመካከር ፈቃደኞች ናቸው ? ሲል ቲክቫህ ላቀረበው ጥያቄ የኮሚሽነሩ በምላሻው፣ “ ጥረት እየተደረገ ነው ” ብለው ተጨማሪ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
ጦርነቱ፣ ግጭቱ፣ ግድያው፣ እገታው፣ መፈናቀሉ እንደቀጠለ ከመሆኑ አንጻር የኮሚሽኑ የምክክር ውሰኔ ውጤት ዘገዬ የሚል አስተያዬት ሲዘነዘር ይስተዋላልና ኮሚሽኑ ምላሹ ምንድን ነው ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄም ምላሽ ሰጥተዋል።
በዚህም፣ “ አልዘገዬም። ምክንያቱም ሀገር ነው የምንመሰክረው ” ነው ያሉት።
“ ኢትዮጵያ ትልቅ ናት የህዝብ ቁጥር ብዙ ነው። ሁሉም መሳተፍ አለበት እያልን ነው። እስከዛሬ ድረስ እንኳ ከ180 ሺሕ በላይ በቀጥታ ያገኘናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አሉ። ይሄ ትልቅ ቁጥር ነው ” ሲሉም አክለዋል።
የ3 ሺሕ ዘመናት ችግር በ3 ዓመታት ለመፍታት አሁን ዘገዬ መባል እንደሌሉበት አስረድተው፣ “ ችግሩ መፈታት አለበት በእርግጥም። እኛ ከተመደበልን ከተርማችን ማለው አንፈልግም። በዚያ ጊዜ ውስጥ አንድ ነገር ለመስራት አስበናል ” ነው ያሉት።
ኮሚሽኑ በሶማሌ ክልል እያደረገው ስላለው አጀንዳ የማሰባሰብ የምከክር መድረክ መረጃ የምናቀብላችሁ ይሆናል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ
ስለ ብርሃን ስኩልፔይ (school pay) በጥቂቱ፤
#ለወላጆች ወይም #ለተማሪዎች የትኛውም ቅርንጫፍ መሄድ ሳያስፈልግ የትምህርት ቤቱን መለያ ኮድ በመጠቀም የትምህርት ክፍያዎችን መክፈል፤ የክፍያ ማረጋገጫዎችን፤ የክፍያ ሪፖርቶችን እና ተያያዥ መረጃዎችን በእጅዎ ባለው ስልክዎ በቀላሉ ማግኘት ያስችልዎታል፡፡
#ለትምህርት_ቤቶች ደግሞ ክፍያ ሲፈጸም ደረሰኝ ይዞ መሄድ ሳያስፈልግ ት/ቤቱ ሁሉንም ክፍያዎች በስኩልፔይ ሲስተም ማየት እና በቀላሉ መቆጣጠር ከማስቻሉም በላይ ሙሉ የሆነ የተማሪዎችን መረጃ በመያዝ ምቹ አሰራርን ይፈጥራል፡፡
ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ!
➡️ Facebook
➡️ Telegram
➡️ Instagram
➡️ Twitter
➡️ LinkedIn
➡️ YouTube
#dereka #mastercardfoundation
ለ2015/2016 ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ!
ደረጃ ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ታላቅ ሀገር አቀፍ የስራ አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ጥቅምት 27-28, 2017 ዓ. ም አዘጋጅቷል።
በአውደ ርዕዩ ላይ ከ300 በላይ ቀጣሪ ድርጅቶች እንዲሁም ወደ 20,000 የሚጠጉ የ2015/2016 ተመራቂ ተማሪዎች ይሳተፋሉ።
የስራ አውደ ርዕዩ ላይ ለመሳተፍ ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠርያ በመጫን ተመዝግቦ ዲጂታል የመግቢያ ትኬት (coupon) ማግኘት እንዲሁም ለስራ አውደ ርዕዩ ተብሎ በተዘጋጀ ስልጠና ላይ መገኘት ይኖርቦታል፤ የስልጠናው ቦታና ሰዓት ከተመዘገቡ በኋላ ይገለፃል።
መስፈንጠርያ:- https://bit.ly/Dereja-MilkRun
ጥቅምት 27 እና 28 በሚሊኒየም አዳራሽ እንገናኝ!
" ለመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት የሆነው ቅልጥ አለት መሬት ውስጥ መምጣቱ ነው " - ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር)
ዛሬ ጠዋት 1 ሰዓት ከ37 ደቂቃ ከ50 ሴኮንድ ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።
ቦታው ባለፈው በተከሰተበት አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ሲሆን በሬክተር ስኬል 4.6 አካባቢ እነደሆነ ተገልጿል።
የዛሬው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት አዲስ አበባ ድረስ በደንብ ተሰምቷል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤሊያስ ሌዊ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ፥ " ሰሞኑን በተደጋጋሚ በአካባቢው የመሬት መንቀጥቀጥ እንቅስቃሴው አልቆመም " ብለዋል።
" ለመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት የሆነው ቅልጥ አለት መሬት ውስጥ መምጣቱ ነው " ያሉ ሲሆን ፤ " ይሄው እንቅስቃሴ ወደላይ አልወጣም " ሲሉ አብራርተዋል።
ላለፉት 19 ተከታታይ ቀናት ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን እና አሁንም ያለውን ሁኔታ ክትትል እየተደረገበት እነድሆነ ጠቁመዋል።
ቪድዮ ፦ በአዲስ አበባ የነበረው ንዝረት በደህንነት ካሜራ የተቀረጸ (ሙሉቀን - አዲስ አበባ ቲክቫህ ቤተሰብ)
@tikvahethiopia
" በሰው ሀገር ላይ ሆኜ እግሬ እስኪንቀጠቀጥ የሰራሁበት ገንዘቤ ነው ፤ ... በደሌን ስሙኝ ! ፍትሕን እሻለሁ ! "
(የቤት ገዢ ከአውስትራሊያ)
እህታችን ነዋሪነቷ በአውስትራሊያ ሀገር ነው።
እኤአ 2012 ላይ እዚህ ሀገር ውስጥ የቤት ግዢ ስምምነት ታደርጋለች።
ስምምነቱ ያደረገችው ከአክሰስ ሪልስቴትና ኤስኤንቢ ከተባለው አካል ጋር ነው። ቤቱን በ2 ዓመት ገንብቶ ለማጠናቀቅ ነበር ስምምነቱ የነበረው።
በኃላ አክሰስ ወጥቶ ኤስኤንቢ ብቻ ይዞታል መባሉን ትሰማለች።
ኮንትራቱን ፈርማ የላከችው ከአውስትራሊያ ሲሆን በወቅቱ 50% ክፍያ ፈጽማለች።
የቤቱ ዋጋ በሰዓቱ 1 ሚሊዮን ብር ነበር።
ከ50% ክፍያ በኃላ ግን ወደ 20% ክፍያ ከፍላለች። በአጠቃላይ 70% ክፍያ ማለት ነዉ የተከፈለዉ።
ክፍያ ከከፈለች በኃላ ግን ቤቱ እየተሰራ አልነበረም። አንዴ እቃ አልመጣም፣ አንዴ የሆነ ነገር ሲሉ አንጓተዋል።
እኤአ 2017 ላይ ወደ ሀገር ቤት መጣች።
ሙለር ሪልስቴት ቢሮ ሔዳም ቤቴ ከምን ደረሰ ? ብላ ስትጠይቅ ' ኤስኤንቢን ለኖህ ሪልስቴት ሸጠነዋል ፥ መሬቱንም አስረክበናቸዋል ' እዛ ሂጂ ይሏታል።
እሺ ብላም አቢሲኒያ ህንፃ የሚገኘው ቢሮአቸዉ ትሄዳለች።
ቢሮአቸዉ ስትሄድም አንድ ሴልስ አግኝቷት ወደ ሳይቱ ጭምር ወሰዶን ቤቷን እንዳየችና በወቅቱ ብሎኬት ተሰርቶለት እንደበር ታስታውሳለች።
70% ከፍላም ፣ ከ5 ዓመታት በኃላ ገና ብሎኬት ላይ ነበር።
በኃላ 2019 ላይ ወደ ኖህ ዋናው ቢሮ ትደውልና " ገና ቤቱ አልደረሰም ስትመጪ ይደርሳል " እንዳሏት ገልጻለች።
በኃላ ኮቪድ ገባ በዚህም ነገሮች ቆሙ እሷም ከአውስትራሊያ መውጣት ሳትችል ቀረች።
ከጊዜ በኃላ ግን " ቤቱ ለሌላ ሰው ተሽጧል " የሚል ፍጹም ያልተጠቀ ነገር ተነገራት።
" ለምን ኮንታክት አላደረጋችሁንም " የሚል ነበር የአልሚዎቹ ቃል። ማስጠንቀቂያም ልከልናችሁ ነበርም ብለዋል።
ገዥ እህታችን ግን አንድም ማስጠንቀቂያ የሚባል ነገር እንዳልደረሳት፣ አውስትራልያ ሆና በፈረመችበት አድራሻ የደረሳት ነገር እንደሌለ እዚህም ባሉ ቤተሰብ ወኪሏ በኩል የተባለችው ነገር እንደሌለ ገልጸለች።
እሺ ለሰው ከተሰጠ የሰው ቤት አንረብሽም በሚል ሌላ ቤት ስጡኝ ብልም ሰሚ አላገኘሁም ብላለች።
በኃላም ጉዳዩ ወደ ክስ አምርቷል።
ይህንን የቤት ሽያጭ ጉዳይ የተከታተለው ቻምበር ኦፍ ኮሜርስ እንደፈረደላት ግን እስካሁን ምንም መፍትሄ እንዳልተገኘላት ገልጸለች።
ሰው ሀገር ሆኜ እግሬ እስኪንቀጠቀጥ የሰራሁበት ገንዘቤ ነው ፤ እናተም ጉዳዬን ስሙና ፍረዱኝ ይኸው ቤቴን አጥቼ እየተሰቃየሁ ነው ብላለች።
ያንብቡ : tikvahethiopia/EaZgM8G36Oi" rel="nofollow">https://teletype.in/@tikvahethiopia/EaZgM8G36Oi
#PremierLeagueallonDStv
🔥ሁሉቱም ቡድኖች ምርጥ አቋም ላይ ናቸው! ማን ዩሆን 3 ነጥቡን የሚያሸንፈው?
👉 ይህንን ድንቅ ፍልሚያ ጨምሮ ሌሎች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይመልከቱ።
👉 ዛሬውኑ ፓኬጅዎን ያሳድጉ። ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት በቀጥታ ይከታተሉ!
ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et
የዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh
#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
#Update #ሲዳማክልል
“ ከሀዋሳ ወደ ሻምና ለመሄድ የመኪና መንገድ የለም። መንገድ ለመክፈት ደግሞ አርሶ አደሩ መሬት መስጠት አለበት። የግድ በእነርሱ መሬት ላይ ነው መንገዱ የሚወጣው ” - የሲዳማ ክልል ጸጥታ ቢሮ
በሲዳማ ክልል ሰሜን ሲዳማ ዞን ሲዳማ ዙሪያ ወረዳ ሻመና ሁሩፋ ቀበሌ ባለይዞታዎች፣ “ ፓሊሶች በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ጠመንጃ በመደቀን ቤተሰብ ላይ ድብደባ ፈጽመዋል ” ሲሉ ለቲክቫህ ላቀረቡት አቤቱታ የክልሉ ጸጥታ ቢሮ ምላሽ ሰጥቷል።
ለዛውም በፍርድ ሂደት ላይ ባለ ጉዳይ “ ጠመንጃ በመደቀን ድብደባ መፈጸም ” ተገቢ ነው ? ስንል የጠየቅናቸው የክልሉ ጸጥታ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳዬሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ አሀመድ፣ “ ህዝቡ ተደብድቧል የሚል ቅሬታ አልመጣም። ተደብድቦ ከሆነ የምናጣራ ይሆናል ” ብለዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ በገለጹት መሠረት ቅር ያሰኛቸው መንገድ መከፈቱ ሳይይሆን ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሂደት እያለ ደርጊቱ መፈጸሙ፣ በፓሊስ ደብደባ ስለተፈጸመባቸው፣ በንብረት ላይ ውድመት ስለደረሰባቸው፣ ካሳ ስላልተከፈላቸው በመሆኑ ነውና ለዚህስ ምላሽዎ ምንድን ነው ? ስንል ላቀረብው ጥያቄም ምላሽ ሰጥተዋል።
አቶ ሀሚድ አሀመድ ፦
“ አዎ በእርግጥ ፍርድ ቤት ያለ ኬዝ ነው። ከላይ ያለ አካል አቅጣጫ ሲያስቀምጥ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የማይጠበቅበት ሁኔታዎች ሊኖሩ ይችላሉ።
ከጠቅላይ ሚኒስቴር ትዕዛዝ ከመጣ እንደዚህ አይነት ጉዳዮች አንዳንድ ቅድመ ሁኔታዎች የሚጠቅባቸው አይነት ነገሮች ሳይመጡ ሲቀሩ ላይጠበቅ ይችላል።
የሚገመት አይነት ንብረት አይደለም። ፎቶውን ሳይ የተወሰነ አትክልት ነገር አለ ፤ ድንች ፣ ቀይ ሽንኩርት ነበረ። ካሰ የሚከፈል ከሆነ እንደ ካሳ ነው የሚነጋገሩት። ካልሆነ ደግሞ በሌላ ካሳ እንዲከፈላቸው ነበር ማድረግ የነበረባቸው።
‘ በጭራሽ መንገድ አይወጣም ’ ነው እነርሱ ሲሉ የነበሩት። ካሳ ተከፈለ አልተከፈለ የግድ ይላል ህዝቡ ያነሳው ጥያቄ መንገድ የለንም’ የሚል ነውና።
ከሀዋሳ ወደ ሻምና ለመሄድ የመኪና መንገድ የለም። መንገድ ለመክፈት ደግሞ አርሶ አደሩ መሬት መስጠት አለበት። የግድ በእነርሱ መሬት ላይ ነው መንገዱ የሚወጣው።
የፍርድ ቤት ኬዛቸውንም ይከታተሉ። ይሄ ደግሞ እንዳይከታተሉ የሚያደርጋቸው ነገር አይደለም። ተከታትለው ከጨረሱ በኋላ ፍርድ ቤቱ ካሳ ሊያስከፍልላቸው ይችላል።
እኔ ጉዳዩን አጣርቻለሁ። ባለፈው ፕሬዝደንቱ እዛ ሂደው ነበር። አጋጣሚ የፓሊስ ግንባታ ፕሮጀክት ሊያስመርቁ በሄዱበት ‘ እዛ መንገድ እንዲወጣ ነበር ’ ያሉት።
መንገድ በፊት ተከልክሎ ነበር እዚያ ቦታ እንዳይወጣና ፕሬዚደንቱ ካዩ በኋላ መንገዱ እንዲወጣ ነበር ያዘዙት። ባስቀመጡት አቅጣጫ መሠረት ነው መንገዱ እንዲወጣ የተደረገው።
የመንገድ ከፈታ የትም ያለ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሀዋሳ መጥተው በነበረበት ወቅት ማግስት ‘ምንድን ነው ችግራችሁ?’ ብለው ሲጠይቁ፣ ‘ሀዋሳ መውጫና መግቢያ መንገድ አጥተናል። ምንም መንገድ አልተከፈተልንም’ የሚል ቅሬታ ሲያነሱ ‘በሲዳማ ክልል ከተሞች የውስጥ መንገድ ሁሉም ቦታ እንዲከፈት ነበር አቅጣጫ አስቀምጠው የወጡት።
በክስ ያሉ ቦታዎች ነበሩ። መንገድ ከፈታ ላይ አንዳንድ ማህበረሰብ እንዲወጣላቸው ይፈልጋሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ እንዲወጣ አይፈልጉም።
አንዳንድ ንብረት ይነካል። ይሄ ደግሞ የምንደራደረው ጉዳይ አይደለም። የምንጓዘው፣ መድኃኒት የሚደርሰው፣ ችግር የሚፈታው በመንገድ ነው። ግን ‘መንገድ አይከፈት’ በማለት ሁከት እንዲነሳ የሚፈልጉ አካላት አሉ።
ወደ 6፣ 7፣ 8 ሰዎች ሆነው ነው እዛ ሲጨቃጨቁ የነበረው። ነገር ግን አብዛኛው መንገድ እንዲከፈትላቸው የሚፈልጉ አሉ። በዚህም ከፌደራል እስከ ክልል ድረስ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ነው እንዲከፈት የተደረገው። ”
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ሲዳማክልል
🛑 " በፍርድ ቤት ሂደት ባለ ጉዳይ ፖሊሶች ጠመንጃ በመደቀን ቤተሰብ ላይ ድብደባ ፈጽመዋል " - ስሞታ አቅራቢዎች
🔵 " ከ200 በላይ ሰዎች ‘ይሰራልን’ ብለው አምነው ሁለት ሰዎች ካመጹ ምን ይደረጋል ? " - ሰሜን ሲዳማ ዞን አስተዳደር
በሲዳማ ክልል፣ ሰሜን ሲዳማ ዞንዝ፣ ሲዳማ ዙሪያ ወረዳ ሻመና ሁሩፋ ቀበሌ " በፍርድ ቤት ሂደት ባለ ጉዳይ በጸጥታ አካላት የድብደባና ንብረት ጭፍጨፋ " እንደተፈጸመባቸው ባለይዞታዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ቅሬታቸው በዝርዝር ምንድን ነው ?
" በፍርድ ቤት በሂደት የነበረ የመንገድ ጉዳይ ነበር። የዛሬ ሁለት ወር አካባቢ ነበር ነገሩ የተቀሰቀሰው።
የተቀሰቀሰውም በግድ መንገድ ለማውጣት የቀበሌ አመራሮች ‘መንገድ ይወጣል’ ብለው ጀምረው ነበር የክሱ ሂደት የተጀመረው።
ቤተሰብ ተበትኖ፣ ንብረት ወድሞ እንዴት መኖር ይቻላል ? በሚል ክስ ተነስቶ ጠበቃ ቆሞ እየተካሰሰ ነው። ግን ትላንት የወረዳው ፓሊስ ሙሉ ፓትሮል መጥቶ በግድ ሙሉ ንብረት አውድመው ሂደዋል።
በፍርድ ቤት ሂደት ባለጉዳይ ፖሊሶች ጠመንጃ በመደቀን ቤተሰብ ላይ ድብደባ ፈጽመዋል።
ድብደባ ካደረሱ በኋላ ስድብ፣ ማሸማቀቅና የዛቻ ቃል ተናግረዋል። ‘ለአርሶአሮቹ የሚያስፈልገው ሂደት ተሟልቶ ነው መንገድ መውጣት የሚችለው’ ተብሎ ውሳኔ አግኝቶ ነበር።
እንዲህ የሚያደርጉት ምንም አይነት ወረቀት የላቸውም። ጉዳዩ ወረዳ ላይ በክስ ሂደት ያለ ነው። የሚያፈርሱት ቦታ እንሰት፣ መቃብር፣ ደን፣ ጎመን፣ ባሕር ዛፍ አለው።
ይዞታው የአቶ በቀለ በዶሬ እና አቶ አዲሴ አንጂሎ ሲሆን፣ ወደ 18 ሁለት የቤተሰብ አባላት የሚተዳደሩበት ነው " ብለዋል።
" መንገዱ ያስፈልጋል ከተባለ እንኳ የይገባኛል ጥያቄው ውሳኔውን ሳያገኝ፣ ካሳ ሳይታሰብ ማንም መጥቶ ነው እንዴ መንገድ የሚያወጣው ? " ሲሉ ጠይቀው፣ ባለድርሻ አካላት ለጉዳዩ በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።
በፍርድ ሂደት ላይ ባለጉዳይ ለምን እንዲህ አይነት ድርጊት ተመፈጸመ ? ስንል የጠየቅናቸው የሰሜን ሲዳማ አስተዳደር አቶ አዱሱ ቃሚሶ፣ " በፍርድ ቤት የታገደ እኛ ጋ የመጣ ነገር የለም። ውሳኔው እስኪጸድቅ ድረስ ይሄ ቦታ ታግዶ ይቆይ የሚል አልደረሰንም " ብለዋል።
" የንብረት ጭፍጨፋ የተደረገው ከፍርድ ቤት ሂደት በኋላ ይሁን በፊት በሚለው ዙሪያ ያጣራሁት ነገር የለም ለጊዜው " ያሉት አስተዳዳሪው፣ ድብደባውን በተመለከተ ማጣራት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
በሁሉም አካባቢዎች መንገድ የመክፈት ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፣ " በእግርጥ መንገዱ የሚነሳው ያለ ካሳ ነው። ንብረቱ ብዙም አይደለም ከግራም ከቀኝም 3፣ 3 ሜትር ብቻ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
" ከ200 በላይ ሰዎች ‘ይሰራልን’ ብለው አምነውበት ሁለት ሰዎች ካመጹ ምን ይደረጋል? የሌሎቹ ተከፍቶ የሌላው አይተው ልማት ነው " ብለዋል።
" ጉዳዩ የእነርሱ ብቻ አይደለም። እስከ ቀበሌ ድረስ መንገድ ከፈታ እንዲደረግ እቅድ ታቅዶ ነበር። ህብረተሰቡ በመንገድ ተጠቃሚ መሆን አለበት "ነው ያሉት።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ሴጅማሰልጠኛ
ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Principles and Practices of Accounting) የ5 ወር የቅዳሜ እና እሑድ ስልጠና በፒያሣ እና መገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።
👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 መሠረታዊ አካውንቲንግ እና ኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት
ስልክ ፦ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
Tiktok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
Linkedin: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#AddisAbaba
“በክፍት ቤቶች ባለቤቶቻቸው አድሰው የፈለጉትን አገልግሎት ሊያውሉት የሚችሉበት ሁኔታ እንዲፈጠር ነው ማስታወቂያው የወጣው” - ኮርፖሬሽኑ
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን " የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤቶች እስከ ጥቅምት 30/2017 ድረስ ወደ ቤታችሁ ግቡ " በሚል ባወጣው ማሳሰቢያ ዙሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጠው ዝርዝር ምላሽ ምንድን ነው ?
የኮርፖሬሽኑ ማብራሪያ ፦
“ ማስታወቂያው የወጣበት ዋናው ምክንያት ሰዎች ‘ተቸገርን፣ ክፍት በሆኑ ቤቶች ወንጀል እየተሰራ ነው፣ እየተዘረፍን ነው፣ ሴቶች እየተደፈሩብን ነው’ ብለው እኛ ጋ ስለመጡ ነው፡፡
ቤቶቹን ቼክ ስናደርጋቸው ደግሞ እጣ ወጥቶባቸዋል፤ ውል ተፈጽሞባቸዋል፣ ግን ሰው አልገባባቸውም፡፡
ስለዚህ ነዋሪው ተቸግሯል፡፡ በዚህ ምክንያት ተደጋጋሚ ወደኛ ቢሮ የሚመጡ የየሳይቱ የነዋሪዎች ማኀበራት አሉ፡፡
ስለዚህ እነዚህ አካባቢዎች ላይ ያሉ ቤቶች በአግባቡ ቤት የደረሳቸው ሰዎች አብዛኛዎቹ መሠረተ ልማቶቹም የተሟሉ፣ ሰው ገብቶ መኖር የጀመረባቸው በመሆናቸው ክፍት መሆን የለባቸውም፡፡ የቤት ባለቤቶች ቤታችሁን አድሳችሁ ግቡ፡፡
ቢፈልጉ አድሶ ማከራየት መብት ነው፡፡ የራሳቸው ቤት እስከሆነ ድረስ፡፡ ግን ዞሮ ዞሮ ሰው በቤቱ ይኑርበት ነው የኛ ጥያቄ፡፡ አካራይ አታከራይ የኔ መልዕክት ሊሆን አይገባም፡፡ ግን ቤቱን ኦውን ያድረጉ፡፡
ሰው ‘የጸጥታ ስጋት ብሎ ይጠይቀናል’፣ የጸጥታ መዋቅሩም እኛን ይጠይቀናል፣ በአንድ ወይም በሌላ መልኩ ደግሞ ቤት ደርሶት ያልገባበት ሰውም ጭምር በመኖሩ እጣ ያልወጣላቸውም ሰዎች ጭምር ቅሬታ ያቀርባሉ፡፡ ‘ይሄው ክፍት ቤት አለ ይላሉ፡፡’
ስለዚህ በክፍት ቤቶች ባለቤቶቻቸው አድሰው የፈለጉትን አገልግሎት ሊያውሉት የሚችሉበት ሁኔታ እንዲፈጠር ነው ማስታወቂያው የወጣው፡፡
የማኅበራዊ ሚዲያ በበዛበት ዘመን በተለያዬ መንገድ ኢንተርፕሬት ሊደረግ ይችላል፡፡
ዋናው የመንግስት ኢንቴንሽን ግን ይሄ ነው፡፡
ክፍት ቤቶች ያሉት አብዛኛው ሳይት ላይ ነው የቤቶቹ መጠን ይለያያል እንጅ (አንዳንድ ቦታ ላይ አምስት፣ አንድ ቦታ ላይ ደግሞ አስር ሊሆኑ ይችላሉ)፡፡
ከተነሳው ቅሬታ አንጻር መሠረተ ልማት ያልተሟላባቸው ደግሞ የተወሰኑ ሳይቶች አሉ (እየተሟላባቸው ያሉ ማለት ነው)፡፡
ለምሳሌ በተደጋጋሚ የሚነሳው አራብሳ ሳይት (ፓኬጅ ሦስት) ነው፡፡ ወደ መጨረሻ አካባቢ ከተገነቡት ቤቶች መካከል ነው። አራብሳ ሦስት አብዛኛው መሠረተ ልማት ተሟልቷል፡፡
ለምሳሌ መንገድ አክሰስ ነው፡፡ አክሰስ ተሰርቶለታል፡፡ ወደ ዘላቂ መንገድ ለማስገባት ለሁለት፣ ሦስት ዓመታት ኢኮስኮ የተባለው ኮንትራክተር ቦታውን ይዞት ነበር ከመንገዶች ተረክቦ ለመስራት፡፡
ነገር ግን ሳይሰራው ቆዬ፡፡ ይሄ ጥያቄ በተደጋጋሚ የማህበረሰቡ ጥያቄ ስለሆነ አቅርበን አሁን ተርሚኔት ተደርጎ መንገዶች ለመስራት ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡
ክረምቱን በሙሉ አክሰስ ወደ መስራት ዝግጅት ላይ ነው የነበሩት አሁን በተሟላ መልኩ ቋሚ መንገድ ሊሰራ ነው፡፡
የመጠጥ ውሃ ወደየ ሳይቱ፣ ወደዬ ብሎኩ ገብቷል፡፡
ፍሳሽን በተመለከተ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ሜጋ ፕሮጀክት እየተሰራ ነው፡፡ በውጭ ካምፓኒ ነው የሚሰራው፡፡ የበጀት እጥረት ገጥሟቸው ጋፕ ነበረ አሁን ግን በተሟላ መልኩ እየተሰራ ነው፡፡ በቅርብ ጊዜ ያልቃል፡፡
የአራብሳን አጠቃላይ ችግር ይህ ፕሮጀክት ነው የሚፈታው፡፡ ይህ እስኪሆን ድረስ ግን የኮሪደር ልማት ተነሽዎች እየገቡ ስለሆነ ሴፍቲ እስታንክ እየተቆፈረ ለጊዜው ፍሳሹ እንዲመጣ፣ ዘላቂው ሲሰራ ደግሞ በቋሚነት እንዲሆን እየሰራን ነው፡፡
አምስትና ስድስት ላይ በተመሳሳይ እየሞከርን ነው፡፡ የተወሰኑ ችግሮች አሉ ሰፈራ የሚባለው አካባቢ የወሰን ማስከበር ችግር አለው፡፡
ለምሳሌ ፍሳሽ፣ የመጠጥ ውሃ በዚያ በኩል ያልፋል ግን የወሰን ማስከበር ችግር አለ፡፡ መፈታት አለበት በሚል ከተማውም ይዞት ለመስራት ጥረት እያደረገ ነው፡፡
የመሠረተ ልማት ችግር ያለባቸውን ቦታዎች እናውቃቸዋለን፡፡ ችግሩ እንዲፈታም ጥረት እያደረግን ነው፡፡ እኛ እያልን ያለነው ይህን አይደለም፡፡
መሠረተ ልማት ተሟቶላቸው በአብዛኛው ነባር ሳይት የሚባሉ፣ ሕዝቡ ገብቶ እየኖረበት ያለ አካባቢ ክፍት ቤቶች አሉ፡፡ እነዚህን ጉዳዮች ነው ያነሳነው፡፡
ማስታቂያውን በተዛባ መልኩ ለማስተላለፍ የሚፈልጉ አካላት አሉ፡፡ ‘ቤት ሊነጠቅ ነው፣ ሊወሰድባችሁ ነው’ የሚል መልዕክት ላስተላለፍ የሞከሩ አሉ፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ነባርና አዳዲስ የቤት ፍላጎቶችን ለማሟላት የተለያዩ ሞዳሊቲዎችን አጥንቶ ወደ ተግባር በመግባት ላይ ነው ያለው እንኳን የነበረውን ወደዚህ ደረጃ ለማድረስ። ”
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#NBE
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ በሚገዙበት እና በሚሸጡበት ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት ከ2 በመቶ መብለጥ እንደሌለበት አሳስቧል።
ብሔራዊ ባንክ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ በሚገዙበት እና በሚሸጡበት መካከል ያለው ልዩነት በዓለም አቀፍ አሰራር መሰረት መሆን እንዳለበት አመልክቷል።
አሁንም ቢሆን ንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ መግዣ እና መሸጫ ዋጋቸውን ገበያ መር በሆነ መንገድ መተመናቸውን እና ይህንኑ ዋጋቸውን በተናጠል በየቀኑ ማሳወቃቸውን መቀጠል እንዳለባቸው ጠቁሟል።
ባንኩ እስካሁን በነበረው አሰራር ንግድ ባንኮች ከውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ጋር በተያያዘ የሚጠይቁትን ኮሚሽን ከምንዛሪ መሸጫ ጋር ደምረው ያስታውቁ እንደነበር ጠቅሶ፤ ወደፊት ግን ኮሚሽኑን ከምንዛሪ መሸጫ ጋር ሳይሆን በተናጠል ለደንበኞቻቸው እንዲያሳውቁ አስታውቋል።
#NBE
@tikvahethiopia
ሴጅ ማሰልጠኛ !
የግራፊክ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኢዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክስ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን።
👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 Advanced Graphics + Video Editing + Motion Graphics + Digital Marketing በአንድ ላይ
👉 ከ50 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት
ስልክ ፦ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram
sage_training_institute">Tiktok
Linkedin
#ኮሬ
🛑 “ አሁንም ግድያው እንደቀጠለ ነው። ዛሬም 3 ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል” - ኮሬ ዞን
🔵 “ ምንም መፍትሄ የሌለው ጉዳይ ነው የሆነው። ግድያና መፈናቀሉ ቀጥሏል” - በፌደራል ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የኮሬ ህዝብ ተወካይ
ዛሬ (ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ/ም) ሦስት ንጹሐን ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል ከምዕራብ ጉጂ በተነሱ ታጣቂዎች መገዳላቸውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኮሬ ዞን አስተዳደር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጿል።
“ ችግሩን ማስቆም የሚችል መንግሥት አካል አልተገኘም ” ያሉት አንድ ስማቸው እንዲነገር ያልፈለጉ በዞኑ ኃላፊነት ላይ የተቀመጡ አካል፣ በሁለተኛው ዙር የመኸር ወቅት ብቻ 11 ሰዎች ሲገደሉ አራት ደግሞ መቁሰላቸውን ገልጸዋል።
“ ጉዳቱ የደረሰባቸው ቀበሌዎች ዳኖ፣ ጎልቤ፣ ጋሙሌ፣ ኬረዳ፣ ሻሮ ናቸው። በአጠቃላይ ከ3.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት በታጣቂዎች ተዘርፏል ” ነው ያሉት።
በአካባቢው ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ የሚፈጸመው ግድያ ለምን ይሆን መቋጫ ያጣው ? ምን እየተሰራ ነው ? የሚል ጥያቄ ያቀረብንላቸው በፌደራል ተወካዮች ምክር ቤት የኮሬ የህዝብ ተወካይ አምዛዬ አወቀ (ዶ/ር) ምላሽ ተሰጥተዋል።
“ ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። ምንም መቋጫ አላገኘም። እኛም በተደጋጋሚ ለመንግስት አመልክተናል። ግን ምንም መፍትሄ የለም። በየቀኑ ግድያ እንሰማለን ” ብለዋል።
“ የሀገር ሽማግሌዎች፣ እኛም ሁሉም በዬቦታው እየጮኸ ነው ግን መፍትሄ የለም። ግራ የሚያጋባ ሁኔታ ነው ” ሲሉም አክለዋል።
የኮሬን ህዝብ የወከሉት በፌደራል ደረጃ እንደመሆንዎ ለመንግስት ቅርብ ነዎትና ጉዳዩን በግልጽ ለመንግስት አንስታችሁ ነበር? ከሆነስ የመንግስት ምላሽ ምንድን ነው? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄም ፦
“ በየጊዜው ነው የሚነሳው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርላማ በተገኙበት ጊዜ ኦፊሻሊ ጥያቄ ሁሉ አንስቼ ነበር በ2016 ዓ/ም። ‘ሁኔታውን ለማርገብ የተወሰነ የመከላከያ ኃይል ይላካልና ሁኔታው ይረጋጋል’ ብለው ነበር።
ከዚያ በኋላ የተወሰነ ኃይል ሂዶ ነበር። እሱም አሁን በአገሪቱ ባለው ሁኔታ ይመስለኛል ተቀነሰ። ከዚያ በኋላ ግን ሁኔታው እየተባባሰ ነው የሄደው።
ወር በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ወደ 10 ሰዎች ተገድለዋል። ህዝቡ በዬቀኑ ይዘረፋል። መንገድም የለም። የዲላ ህዝብ ጋር ነው የኮሬ ዞን የሚገናኘው ይሄ መንገድም ከተዘጋ ዘጠኝ ዓመት ሆኖታል።
ይሄን ሁሉ በማመልከታቸም አመልክተናል። ሽማግሌዎች ወጥተው ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት፣ ለሰላም ሚኒስቴር አመልክተዋል፤ ለክልሉ መንግስት በዬጊዜው የሚቀርብ ጉዳይ ነው።
ነገር ግን ምንም መፍትሄ የሌለው ጉዳይ ነው የሆነው። ግድያና መፈናቀሉ ቀጥሏል ” ሲሉ መልሰዋል።
ስለዚህ የመፍትሄው ጉዳይ ምንም እየተሰራበት አይደለም ማለት ነው ? ለሚለው የቲክቫህ ጥያቄ ምላሻቸው፣ “ ምንም መፍትሄ የለም ” የሚል ነው።
“ አንዳንድ ጊዜ ‘እርቅ ተደርጓል’ ይባላል፤ አምና እርቅም ለማድረግ ተሰብስበው የነበሩት የብልጽና ፓርቲ ኃላፊም ጭምር የተገደሉበት ሁኔታ አለ። መንግስት የራሱ ፓርቲ አባል ሲገደል እንኳ ገዳዮች እነማን ናቸው ብሎ ተከታትሎ ሊያቀርብ አልቻለም ” ሲሉም ተናግረዋል።
በመሆኑም መንግስት፣ ሚዲያዎችም የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ህዝቡን እንዲታደጉ በህዝቡ ስም ጥሪ አስተላልፈዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
በእነ ፍስሐ እሸቱ (ዶ/ር) ላይ የተመሰረተው ተደራራቢ ክስ ምንድነው ?
የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ የፐርTዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የቦርድ አባልና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍስሐ እሽቱን (ዶ/ር) ጨምሮ በ10 ግለሰቦች እና ሁለት ድርጅቶች ላይ ክስ መስርቷል።
ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
ተከሳሾቹ ፦
1ኛ የፐርTዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የቦርድ አባልና ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍስሐ እሽቱ (ዶ/ር)፣
2ኛ የተቋሙ ም/ስራ አስፈጻሚ ኤርሚያስ ብርሃኑ (ዶ/ር)፣
3ኛ የተቋሙ ቺፍ ኦፕሬሽን ኦፊሰር እና የቦርድ አባል ወ/ሮ ኤፍራታን ነጋሽን ጨምሮ በአጠቃላይ 10 ግለሰቦች እንዲሁም ፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ እና ኖትር ዲዛይን ሃ/የተ/የግ/ማህበር ናቸው፡፡
ተከሳሾቹ ፦
➡️ በአዲስ አበባ ከተማ መሃል ሜክሲኮ ላይ በ100 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ ባለ 3 መኝታ ቤት መኖሪያ ቤት በ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚሸጥ መሆኑን በሚዲያ በማስተዋወቅ ሰዎች ቤት ለመግዛት ሲሄዱ "መጀመሪያ ገንዘቡን አስገቡና ውሉን ትመለከታላችሁ " በማለት ከሌሎች ግብረዓበሮቻቸው ጋር በመሆን አሳሳች ቃላቶችን በመጠቀም፣
➡️ ሰዎች ገንዘቡን ካስገቡ በኋላ ደግሞ የአክሲዮን ግዢ ውል እንዲፈርሙ በማድረግ ምንም አይነት የግንባታ ቦታ ባልተረከቡበት ሁኔታ 2 ቢሊየን 234 ሚሊየን 200 ሺህ ብር በመሰብሰብ፣
➡️ ቤቱን ሰርተው ሳያስረክቡ በመቅረት
➡️ ግማሹን ገንዘብ ወደ ውጭ እንዲሸሽ በማድረግ፣
➡️ ኮሚሽን በመቀበልና በማታለል ወንጀል ተጠርጥረው በአዲስ አበባ ፖሊስ በኩል በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ የምርመራ ማጣሪያ ሥራ ሲከናወን ነበር።
በዚህ መልኩ ፖሊስ ሲያከናውነው የቆየው የምርመራ ማጣሪያ ሥራ መጠናቀቁን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ዐቃቤ ሕግ ተደራራቢ ዝርዝር ክሶችን በየደረጃቸው አቅርቦባቸዋል።
ከቀረቡ ክሶች መካከል በአንደኛው ክስ ላይ ከ1ኛ - 9ኛ ባሉ ተከሳሾች ላይ እንደተመላከተው በኢፌዲሪ የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1) (ሀ) እና (ለ) እንዲሁም የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 32 (2) ላይ የተመላከተውን ድንጋጌ መተላለፍ የሚል ክስ ይገኝበታል።
እንደ አጠቃላይ በቀረበው ተደራራቢ ክስ ዝርዝር ችሎት ለቀረቡ 4 ተከሳሾች ዝርዝሩ እንዲደርሳቸው የተደረገ ሲሆን የተከሳሾቹ ጠበቆች በደንበኞቻቸው ላይ የቀረበውን ክስ ዝርዝር ተመልክተው ዋስትና ላይ ክርክር ለማድረግ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡
ፍርድ ቤቱም ዋስትና ላይ የሚደረገውን የግራ ቀኝ ክርክር ለመከታተል ለፊታችን ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ተዋጭ ቀጠሮ በመስጠት ችሎት ያልቀረቡ ተከሳሾችን ፖሊስ በአድራሻቸው አፈላልጎ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ መስጠቱን #ኤፍቢሲ ዘግቧል።
ፍስሕ እሸቱ (ዶ/ር) ሀገር ጥለው አሜሪካ ሀገር መግባታቸው ይታወሳል።
@tikvahethiopia
#አማኑኤልየአዕምሮስፔሻላይዝድሆስፒታል
" በአብዛኛው ዋርድ ያሉት ህሙማን ወንዶች ናቸው። በሦስቱ ዋርዶች ሴቶች፣ በአስሩ ዋርድ ደግሞ ወንዶች የአዕምሮ ህሙማን ናቸው ያሉት " - ሆስፒታሉ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክፍለ ከተማ የሚገኘው አማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሆስፒታሉን የውስጥ ግንባታዎች እያከናወነ መሆኑ ከዚህ ቀደም መነገሩ ይታወሳል።
በዚህም ታካሚዎች የውስጥ ግንባታ መጠናቀቁና አለመጠናቀቁን ሲጠይቁ የተስተዋሉ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያም እድሳቱ ከምን ደረሰ ተጠናቀቀ ወይስ ገና ነው? ሲል ለሆስፒታሉ ጥያቄ አቅርቧል።
ሆስፒታሉ በሰጠን ቃል፣ " ውስጥ ላይ ያለ የተወሰነ የማስፋፊያ ግንባታ አለ። አሁን በቅርቡ ተመርቆ ወደ ሥራ ይገባል " ብሏል።
" ጥቅምት መጀመሪያ አካባቢ ይጠናቀቃል " ሲል አክሏል።
ህክምና የሚሰጠው ጠባብ በሆነ ቦታ መሆኑ በእጅጉ ፈታኝ እንደሆነበት አስረድቶ፣ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠውም አሳስቧል።
" እንደ ስትራቴጂ በእርግጥ ጤና ሚኒስቴር የያዘው ጉዳይ አለ። ሁሉም የጤና ተቋማት ባሉበት ቦታ የአዕምሮ ህክምና ልክ እንደ ማንኛውም ህመም መሰጠት አለበት የሚል አቅጣጫ ተይዟል " ሲልም ገልጿል።
" ይህ ጥሩ ነገር ነው። ምክንያቱም በሆስፒታሉ ያለውን ጫና ስለሚቀንስ " ብሎ፣ ' ሁሉም የሚሰጡ ከሆነ ከጫናው ባለፈም ማንኛውም ሰው ለትራንስፖርት ወጪ ሳይዳረግ፣ ጉልበቱ ሳይበዘበዝ፣ ማህበራዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ክስረት ሳይደርስበት በአካባቢው የሚታከምበት ሁኔታ እንዲፈጠር ይረዳል " ነው ያለው።
" ግን አሁን ያም ቢሆን በአጥጋቢ ሁኔታ እየተሰራ ነው ብሎ መውሰድ አይቻልም፣ ተጠናክሮ ሊሄድ ይገባዋል የሚል መልዕክት አለኝ " ሲል አሳስቧል።
በሆስፒታሉ የሚገኙት የአዕምሮ ህሙማን በብዛት ሴቶች ናቸው ወይስ ወንዶች ? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ሆስፒታሉ ተከታዩን ምላሽ ሰጥቷል።
" እንደኛ ሆስፒታል በአብዛኛው ዋርድ ያሉት ህሙማን ወንዶች ናቸው። ወደ 13 ዋርዶች አሉን።
ከእነዚህ ውስጥ በሦስቱ ዋርዶች ሴቶች፣ በአስሩ ዋርዶች ደግሞ ወንዶች የአዕምሮ ህሙማን ናቸው ያሉት።
ከአስሩ ዋርድ አንዱ የሱስ ታካሚዎች ያሉበት ነው። "
በሆስፒታሉ እንደ አጠቃላይ ምን ያክል በአስተኝቶ ታካሚዎች አሉ ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ፣ " በአንድ ዋርድ ላይ 25 ታካሚዎች ናቸው የሚኖሩት። ስለዚህ 13 በ25 ሲባዛ 325 ይሆናሉ " ነው ያለው።
ከዚህ ቀደም ሆስፒታሉ የአዕምሮ ህሙማን ቁጥር እንደጨመረ ህሙማኑ በአብዛኛው የአፍላ እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ መሆናቸው መገለጹ ይታወሳል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
ሴጅ ማሰልጠኛ !
የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 09/2017 ዓ.ም ADVANCED STANDARDS AND PRACTICES OF ACCOUNTING ስልጠና ይጀምራል።
👉 IFRS + Peachtree + Asset Valuation + IFRS Conversion + IPSAS + Quick Book በአንድ ላይ
👉 ስልጠናው ሙሉ በሙሉ በተግባር የተደገፈና ፒስትሪ (Peachtree Software) ላይ የሚሰጥ ነው።
ስልክ ፦ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
➡️ Telegram
➡️ sage_training_institute">Tiktok
➡️ Linkedin
#ተመስግናችኋል🙏
" የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍና ጸሎት ልጄን ከአስከፊው የልብ ህመም ታድጎልኛል " - የመቐለ የኒቨርሲቲ መምህር
የሁለት ዓመት ከ5 ወር ልጃቸው ታሞባቸው የነበሩ የመቐለ ዩኒቨርሲቲው መምህር አቶ ገ/መድህን መብርሃቱ ለህክምና የተጠየቁት ገንዘብ ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ ድጋፍ እንድታደርጉላቸው እናንተኑ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ተማጽነው ነበር።
" የልጅነት ልጄን አድኑልኝ። ሁለት የልብ ክፍተት ህመም አለበት፤ ለህክምና 665 ሺህ ብር ተጠይቄአለሁ " ነበር ያሉት።
የህፃኑ አባት ዛሬስ ምን አሉ ?
ልጃቸው ህክምናውን ማጠናቀቁን ገልጸው ልባዊ ምስጋና አቅርበውላችኋል።
" የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍና ጸሎት ልጄን ከአስከፊው የልብ ህመም ታድጎልኛል። አመሰግናለሁ " ነው ያሉት።
" ለሁሉም በዚህ የእርዳታ ጥሪ የተሳተፋቹ ወገኖቼ በሙሉ ከመሬት እጅጉን ከፍ ከሰማይ ደግሞ ዝቅ ያለው ምስጋናዬ ይድረሳቹ ፈጣሪ ጤናችሁን፣ ፀጋችሁን አብዝቶ ይባርክ " ሲሉ መርቀዋል።
ልጃቸው ህፃን ኢዮብ ገ/መድህን በሁለት የልብ ክፍተት (VSD+PDA) ሲሰቃይ ነበር።
@tikvahethiopia
" ኢትዮ ቴሌኮም የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ግብይት አገናኝነት (broker) ፈቃድ አግኝቷል " - ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)
ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ባለቤትነት የተያዘው ኢትዮ ቴሌኮም ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ለመሸጥ ያቀደውን 10 በመቶ ድርሻውን፣ የራሱን የቴሌብር መተግበሪያ በመጠቀም ራሱ እንዲያገበያይ እንደተፈቀደለት ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።
ከኢትዮ ቴሌኮም ጠቅላላ ሀብት ውስጥ አሥር በመቶ የሚሆነው በአክሲዮን ተከፋፍሎ በሚቀጥለው ሳምንት ከረቡዕ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለሽያጭ የሚያቀርብ ሲሆን፣ መንግሥት ቀደም ብሎ በወሰነው መሠረት የኩባንያው አክሲዮኖች ለአገር ውስጥ አክሲዮን ገዥዎች ይሸጣል።
የኢትዮጵያ ሙዓለ ነዋይ ገበያ የኢትዮ ቴሌኮምን አሥር በመቶ ድርሻ በማገበያየት አገልግሎቱን እንደሚጀምር ከዚህ ቀደም ተግልጾ የነበረ ቢሆንም፣ ይህ ዕቅድ ተቀይሮ ኢትዮ ቴሌኮም ራሱ ለሕዝብ የሚያቀርበውን ድርሻ በቴሌብር መተግበሪያው በመጠቀም እንዲያገበያይ እንደተፈቀደለት ለማወቅ ተችሏል።
ማክሰኞ መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም. በለንደን በተካሄደው የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ኮንፈረንስ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)፣ በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ሲያብራሩ የኢትዮ ቴሌኮም አሥር በመቶ ድርሻ በቀጣዩ ሳምንት ለገበያ እንደሚቀርብ አረጋግጠዋል።
በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ በቀጣዩ ወር በይፋ ሥራ እንደሚጀምር የተናገሩት ብሩክ (ዶ/ር)፣ ኢትዮ ቴሌኮም እንዲሸጥ የተፈቀደለትን 10 በመቶ ድርሻውን በኢትዮጵያ የሰነደ መዋዕለ ነዋዮች ገበያ አማካይነት ሳይሆን የራሱን የቴሌብር መተግበሪያ በመጠቀም ለሽያጭ እንደሚያቀርብና የግብይት ሒደቱም በኩባንያው እንደሚፈጸም አስታውቀዋል።
የመጀመሪያ ዙር የሕዝብ አክሲዮን ሽያጭ (Initial Public Offering) ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ይህ ሒደት ተዘሎ ኩባንያው ራሱ በቀጥታ አክሲዮኖቹን እንደሚሸጥ ገልጸዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ግብይት አገናኝነት (broker) ፈቃድ ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ያገኘ መሆኑን የጠቀሱት ብሩክ (ዶ/ር)፣ ይህም ኩባንያው የራሱን አሥር በመቶ ድርሻ በቀጥታ ለአገር ውስጥ ኢንቨስተሮች መሸጥ እንደሚያስችለው አስረድተዋል።
በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰነደ ሙዓለ ነዋዮችን ለማገበያየት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ፣ በሚቀጥለው ወር በይፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርም ተናግረዋል።
የተመሠረተበትን 130ኛ ዓመት ዘንድሮ የሚያከብረው ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት 93 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ያስታወቀ ሲሆን፣ ይህንን ገቢ በ2017 ዓ.ም. ወደ 163.7 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ዕቅድ ይዟል። #ሪፖርተርጋዜጣ
@tikvahethiopia
🔈 #የዜጎችድምጽ
" ስራ መስራት ... ቤተሰብ ማስተዳደር አልተቻለም ! " - አሽከርካሪዎች
በክልል ከተሞች የሚታየው ቤንዚን የማግኘት ፈተና አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል።
የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ዜጎች ስራ ሰርቶ መግባትና ቤተሰብ ማስተዳደር ፈተና ከሆነባቸው ቢቆይም አሁን ላይ ሁኔታው ይበልጥ እየከበዳቸው እንደሆነ ገልጸዋል።
" ቤንዚን እንደልብ ማግኘት ከቆም በርካታ ወራት አልፈዋል " የሚሉት መልዕክታቸውን የላኩ ዜጎች " ልጆቻችንን ለማስተዳደር፣ እኛም በልተን ለማደር ስንል አንድ ሊትር ቤንዚን ከ120 ብር በላይ ስንገዛ ከርመናል አሁን ጭራሽ ቤንዚን ጨመሯል ተብሎ እሱም ጠፍቷል ፤ ሲገኝ ደግሞ ብሩ ጨምሯል " ብለዋል።
ባሉበት አካባቢ ማደያዎች ቢኖሩም ቤንዚን እንዲሁ መቅዳት ቅንጦት ከሆነ መቆየቱን ተናግረዋል።
" 1 ቀን መስራት 1 ቀን ደግሞ ሰልፍ ተሰልፎ መዋል ነው ፤ እንዲህ እየሆንን እንዴት ነው ይህንን ከዕለት ወደ ዕለት እየናረ ያለውን ከፍተኛ የኑሮ ውድነት መቋቋም የምንችለው ? " ሲሉ ጠይቀዋል።
" ልጆቻችንን የምናሳድገው ፤ ከሰው እንዳያንሱ ጥሩ ትምህርት እንዲማሩ የምንለፋው መስእዋትነት የምንከፍለው በዚሁ ባለችን ስራ ነው ይሄን ለመስራት ፈተና ከሆነ ምን ተስፋ ይኖረናል ? እንደው ግራ ተጋብተናል " ብለዋል።
የሞተር አሽከርካሪዎችም የስራና የተለያዩ የግል ጉዳዮች ለሚፈጽሙበት የሞተር ሳይክል እንኳን የሚሆን ቤንዚን ለማግኘት በብዙ ይሰቃያሉ።
ቤንዚን በሰልፍ በሚኖርበት ወቅት ከጥበቃ እስከ ቀጂ ድረስ በመመሳጠር ሰው በፀሀይ ተንገላቶ ተሰልፎ እያለ ካለሰልፍ የሚያስቀዱት ብዙ ነው ፤ ከዚህ ሲያልፍም ለህገወጥ ሽያጭ የሚያውሉ ሰዎችን ደጋግመው እንዲቀዱ በማድረግ የችግሩ አካል ሲሆኑም ይታያል።
በክልል ከተሞች ቤንዚን እንደልብ አይገኝም ፤ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ማግኘቱ ቅጦት ወደመሆን ተሸጋግሯል።
በየከተማው እንደ አሸን የፈሉት ማደያዎች ሲጠየቁ " ቤንዚን የለም ፤ ካለም አገልግሎት የምንሰጠው በፈረቃ ነው " የሚል መልስ ነው የሚመልሱት።
ከጥዋት 2:30 በፊት አይከፈይም ፤ ከምሽት 12:00 በኃላ ደግሞ የቤንዚን ሽያጭ ጥርቅም ተደርጎ ይዘጋል።
ማደያዎች 24 ሰዓት መስራት ቢጠበቅባቸውም ፤ እንኳን 24 ሰዓት ሊሰሩ ቀኑን እንኳን " ቤንዚን የለም " የሚል ምንም ምክንያቱ የማይገለጽ ምላሽ በመስጠት ነው የሚውሉት።
ይህ ሁሉ ሆኖ ግን በህገወጥ መልኩ ቤንዚን በየቦታው በውሃ መያዣ ፕላስቲኮች ልክ እንደ ህጋዊ ነገር ከእጥፍ በላይ በሆነ ዋጋ ሲቸበቸብ ይታያል። ያውም በየቦታው በየስርቻው።
በአንዳንድ ቦታዎች ማደያዎች በጥቅም ለተሳሰሯቸው አካላት በምሽት በህገወጥ መንገድ ቤንዚን በበርሜል እንደሚሸጡ ይነገራል።
ማደያ ሲጠየቅ " የለም " የሚባለው ቤንዚን በጥቁር ገበያ በህገወጥ መንገድ በየመንደሩ እጅግ ከፍተኛ በሆነ ዋጋ ነው የሚሸጠው።
ከዋናዎቹ አካላት በአቅርቦት ጉዳይ ላይ ምንም ችግር እንደሌለ በተደጋጋሚ ይነሳል ፤ ነገር ግን ክልል ከተሞች ላይ ቤንዚን ማግኘት ፈተና እንደሆነ ይኸው አመታት አልፏል። ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ መዘዙ ብዙ ሊሆንም ይችላል።
° እንዴት ይሄን ሁሉ ጊዜ ዜጋው ሲቸገር ዝም ተብሎ ታየ ?
° እንዴት ይሄን ሁሉ ጊዜ መፍትሄ አይገኝም ?
° በክልል ከተሞች ያለው ህገወጥ የቤንዚን ሽያጭና ስርጭት ሰንሰለት የሚቆረጠው መቼ ነው ?
° በሀገር ደረጃ የሚገባ መጠን ላይ ችግር ከሌለ ለሚታየው ለዚህ ሁሉ ችግር ተጠያቂ ማን ነው ? የሚሉ ጥያቄዎች መልስ ይሻሉ።
ከክልል ከተሞች ውጭ አዲስ አበባ ከተማ ላይ ቤንዚን አንዳንድ ወቅቶች ላይ ካልሆነ በስተቀር በከተማው ባሉ ማደያዎች በቀንም በማታም ይገኛል።
የክልሎቹ ግን ልዩ ነው ማደያ ውስጥ የለም ፤ በየስርቻው በችርቻሮ እንደጉድ ይቸበቸባል።
በአሁን ሰዓት በማደያዎች የአንድ ሊትር ቤንዚን ዋጋ 91 ብር ከ14 ሳንቲም ነው።
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#AddisAbaba
በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ' የኢንቨስትመንትና ፓርትነርሺፕ ኤክስፖ ' ሊዘጋጅ ነው።
አዘጋጆቹ ኤክስፖው ጥቅምት 7 እና 8 / 2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ ገልጸዋል።
" ከ10 በላይ ግዙፍ የኬንያ ሪል እስቴት አልሚዎች፣ የህግ ባለሙያዎች እና ታዋቂ የንብረት አስተዳደር ኩባንያዎች ሁሉም በአንድ ጣሪያ የሚከትሙበት ዝግጅት ነው " ብለዋል።
" እነዚህ አልሚዎች ከተለያዩ የኢንቨስትመንት ፍላጎት ካላቸዉ ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁ ሆነዉ እንደሚጠብቁም " ገልጸዋል።
" የተባበሩት መንግስታት አንድ ሶስተኛ ሰራተኛ ከኒውዮርክ ወደ አፍሪካ እያዘዋወረባት በምትገኘው እና በከፍትኛ ፍጥነት እያደገ ባለው የኬንያ ገበያ ውስጥ ለመሳተፍ ጊዜው አሁን ነው " ያሉት አዘጋጆቹ ተሳታፊ መሆን የሚፈልጉ እንደሚዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል።
ለበለጠ መረጃ እና ለምዝገባ ፦ በ0991718664 ይደውሉ።
ጥቅምት 7 እና 8 ቀን 2017 በሸራተን አዲስ
' አሻም ' ስያሜውን እንዲቀይር በፍርድ ቤት ለምን ተወሰነ ?
“ ተከሳሽ ' አሻም ' ሚለውን የንግድ ምልክት መጠቀም ማቆም አለበት በማለት ተወስኗል ” - ፍርድ ቤት
አሻም ቴሌቪዝን ሲጠቀምበት የነበረውን አሻም የሚለውን ስያሜ መጠቀም አንዲያቆምና እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ/ም እንዲያሳውቅ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኅን ባለሥልጣን በኩል ማሳሰቢያ እንደተሰጠው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለሥልጣኑ ይፋ ካደረገው ደብዳቤ ተረድቷል።
ባለሥልጣኑ ተቋሙ የስም ቅያሬ እንዲያደርግ ያሳሰበው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍ/ብሔር ምድብ ችሎትና የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወሰኑት ውሳኔን መሠረት በማድረግ ነው፡፡
የስም ቅያሬ ማሳሰቢያው ምንን መሠረት ያደረገ ነው ?
የትዕዛዙ መሠረት አሻም ቴሌቪዥን በብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ሬድዮ ላይ በሚተላለፈው “ አሻም ” የተሰኘ ፕሮግራም ባቀረበበት የክስ መሠረት ነው።
ቲክቫህ ኢትየጵያ የተመለከታቸው ሰነዶች የስም ቅያሬ ጉዳዩ በይግባኝ እስከ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተኪዶበት ከሳሽ ያቀረቡትን ክስ አሸንፈው ፤ የካሳ ጉዳይ ተጣርቶ ወደፊት እንደሚወሰን ፤ ነገር ግን የቴሌቪዥን ጣቢያው ' አሻም ' የሚለውን ስም መጠቀም እንዲያቆም ውሳኔ የተሰጠበት መሆኑን ያስረዳሉ፡፡
በ2014 ዓ/ም የተጻፈው የፍርድ ቤት ሰነድ ከሳሽ ' አሻም ' የሚለውን ስያሜ በብስራት ኤፍኤም 101.1 እንደሚጠቀምበት፣ ለዚህም ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን የምስክር ወረቀት እንዳገኘበት፣ በንግድ ምልክቱ የመጠቀምና ሌሎች እንዳይጠቀሙ የመከልከል መብት በአዋጅ እንደተሰጠው መግለጹን ይተነትናል፡፡
“ ተከሳሽ የከሳሽን ፈቃድ ሳያገኝ እንዲሁም ፈቃድ ሳይጠቅይቅ ' አሻም ' በሚለው በከሻስ የተመዘገበ የንግድ ምልክት በመጠቀም የቴሌቪዥን ጣቢያ ከፍቶ ስርጭት ጅምሯል ” ይላል ሰነዱ።
ከሳሽ ተከሳሹን፣ “ ተከሳሽ የንግድ ምልክት መጠቀሙ ሆን ብሎ ያለአግባብ ለመበልጸግ የተደረገ ተግባር ነው ይህም ተግባር ያልተገባ የንግድ ውድድር ከመሆኑም ባሻገር በከሳሽ ንግድ ስራ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል ” ሲልም ከሶታል፡፡
በዚህም ' አሻም ' የሚለውን የከሳሽን የንግድ ምልክት በቴሌቪዝን ጣቢያ ስያሜነት መጠቀም እንዲያቆም ተከሽ የከሳሽን የንግድ ምልክት እየተጠቀመ በመቆየቱ ከሳሽ ላይ በደረሰው ጉዳት 1 ሚሊዮን ብር እንዲከፈል እንዲወሰን ሲጠይቅ ቆይቷል፡፡
ተከሳሽ (አሻም ቴሌቪዥን) በበኩሉ፣ ከ2009 ጀምሮ አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ በሚል ስያሜ በቴሌቪዥን ማሰራጨት ሥራ እየተጠቀመበት እንደሆነ፣ እውቅና እንዳገኘበት በመግለጽ፣ “ ከሳሽ እኔን ሊከሰኝ የሚያስችለው የህግና የማስረጃ ድጋፍ የለውም ” ሲል አጸፋ መስጠቱን ሰነዱ ያስረዳል፡፡
' አሻም ' የሚለውን ስያሜ ያወጣው “ በህጋዊ መንገድ ከንግድ ቢሮ ” ክፍያ በመፈጸም መሆኑን፣ ቢሮው የሚጠቀምበት ሌላ ሰው ያለመኖሩን አጣርቶ የንግድ ስያሜን እንዲጠቀምበት እንደፈቀደለት በመግለጽ ምላሽ መስጠቱና ሌሎች ጉዳዮች በሰነዱ ተብራርተዋል፡፡
ጉዳዩ በእንዲህ አይነት በርካታ ሂደቶች ከተደረጉ በኋላም ተከሳሽ አሻም የሚለውን ስያሜ እንዲያቆም፣ ንግድ ባንክ በፍርድ ባለእዳ ስም የተከፈተ ሂሳብ ቁጥር ካለ እስከ 292 ሺሕ 850 ብር እንዲያግድ ውሳኔ ትዕዛዝ መሰጠቱ ታውቋል፡፡
የፍርድ ቤት ውሳኔው የክርክር ሂደቱን በዝርዝር ካስረዳ በኋላ፣ “ ተከሳሽ አሻም የሚለውን የንግድ ምልክት መጠቀም ማቆም አለበት በማለት ወስኗል ” ይላል።
ይህንንም የፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲያስፈጽም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኅን ባለሥልጣን ታዟል።
(ይህ በከፊል የቀረበ መረጃ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ደርሶት የተመለከተው ሙሉ የፍርድ ቤት ሰነድ ከላይ ተያይዟል)
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ
ከሰሞኑን በኢትዮጵያ የዘር ፍሬ ልገሳ ማከናወንን የሚፈቅድ ድንጋጌ የያዘ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ።
ለተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ ሕግ " የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ " ይሰኛል።
አስራ ሁለት ክፍሎች ያሉት ረቂቅ አዋጁ ፦
- ስለ አጠቃላይ የጤና አገልግሎት፣
- ስለ ጤና አገልግሎት አሰጣጥ፣
- ስለ ልዩ የጤና አገልግሎቶች፤
- ስለ ጤና ዘርፍ የሰው ኃብት ልማት እና አስተዳደር፤
- ስለ ጤና እና ጤና ነክ ተቋማት እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች ቁጥጥርን የሚመለከቱ 60 አንቀጾች አሉት።
ስለ ልዩ የጤና አገልግሎቶች የሚያወሳው የአዋጁ አራተኛ ክፍል ከዘረዘራቸው የጤና አገልግሎቶች መካከል አንዱ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ ተዋልዶ ሕክምና አገልግሎት ነው።
በዚህ ንዑስ ክፍል ሥር የተካተተው አንቀጽ " ፈቃድ የተሰጠው የጤና ተቋም በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ ተዋልዶ የሕክምና አገልገሎት ሊሰጥ ይችላል " ሲል ሕክምናው በሕግ መፈቀዱን ይደነግጋል።
" የዘርፍ ፍሬ ልገሳ... ከዚህ ቀደም በሕግ የተፈቀደ ተግባር ያልነበረ” መሆኑን የጠቆመው የረቂቅ አዋጁ ማብራሪያ፤ በዚህኛው ረቂቅ አዋጅ “ልገሳውን ማከናወን እንደሚቻል የሚደነግግ እና የሚከናወንበትን ሥርዓት የያዘ ዝርዝር ድንጋጌ " መካታቱን አብራርቷል።
ከአስራ አንድ ዓመታት በፊት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣው " የምግብ፣ መድኃኒት እና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር " ደንብ፤ ፈቃድ ያገኙ ተቋማት የሰው ሰራሽ ሕክምና መስጠት እንደሚችሉ ደንግጓል። የአዋጁ ድንጋጌ " አግባብ ያለው አካል ፈቃድ በሚሰጠው የጤና ተቋም እና የጤና ባለሙያ ሰው ሰራሽ የተዋልዶ ሕክምና መስጠጥ ይቻላል " ይላል።
ደንቡ ዘር ፍሬ ልገሳ ላይ ክለከላን ባያስቀምጥም በግልጽ በሕግ ተፈቀደ መሆኑንም አይጠቅስም።
ለምክር ቤቱ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ በበኩሉ የዘር ፍሬ ልገሳ ማድረግ እንደሚቻል እና ሂደቱ ምን መሆን እንዳለበት አስፍሯል።
በረቂቁ መሠረት የዘር ፍሬ መሰብሰብ የሚቻለው ለዚሁ ዓላማ በጤና ሚኒስቴር የተለየ ተቋም ብቻ ነው። ማንኛውም ሰው በሚኒስቴሩ ለተለየው ተቋም የዘር ፍሬውን መለገስ እንደሚችል ረቂቅ ላይ ሰፍሯል።
ይህ የአዋጁ ድንጋጌ ቢኖርም ረቂቁ የዘር ፍሬ ከለጋሾች የሚወሰደው " ከፍተኛ ጉዳት የማያስከትልባቸው መሆኑ በሕክምና ሲረጋገጥ ብቻ " መሆኑን አስቀምጧል።
በረቂቅ አዋጁ ድንጋጌ ከተቀመጠው አግባብ ውጪ " የዘር ፍሬ መለገስ፣ መሰብሰብ ወይም መሸጥ " የተከለከለ መሆኑ ረቂቁ ላይ ሰፍሯል።
የዘር ፍሬ ለመሰብሰብ ከተፈቀደለት ተቋም በተገኘ የዘር ፍሬ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ-ተዋልዶ ሕክምና አገልግሎት ለሚያስፈልጋቸው ተገልጋዮች ሊሰጥ እንደሚችል ያትታል።
በዚህ የሕክምና አገልግሎት " ልጅ ያገኙ ባለትዳሮች የሚወለደው ልጅ ሕጋዊ ወላጆች ይሆናሉ " ይላል።
በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ ተዋልዶ ሕክምና አገልግሎት ሊሰጥ የሚችለው በአራት አስገዳጅ ሁኔታዎች ብቻ መሆኑን ያስቀምጣል።
በዚህ መሠረት ፦
➡️ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በሕጋዊ ጋብቻ የተጣመሩ እና ለዚህም ከሚመለከተው አካል ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።
➡️ " ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ልጅ መውለድ የማይችሉ መሆኑ በዘርፉ ባለሙያ ሲረጋገጥ " መሆኑ ሰፍሯል።
➡️ የሚሰጠው ሕክምና አወንታዊ ውጤት ሊኖረው እንደሚችል እና በተገልጋዩ ጤና ላይ ጉዳት የማያስከትል መሆኑ በሕክምና ባለሙያ መረጋገጥ አለበት።
➡️ የባለትዳሮቹን " አገልግሎቱን ለማግኘት በመረጃ ላይ የተመሠረተ የጽሁፍ ፈቃድ " የሚጠይቅ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ባለትዳሮቹ ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ልጅ መውለድ ቢችሉም፤ " መውለዳቸው በጤናቸው ላይ ከባድ እክል የሚያስከትል መሆኑ በባለሙያ ከተረጋገጠ " ሕክምናውን ማግኘት እንደሚችሉ ረቂቁ ላይ ሰፍሯል።
" የዘር ፍሬ ወይም ከማህፀን ውጪ የተዘጋጀ የዘር ፍሬ ውህድ ወደ ሴቷ ማህጸን ከመግባቱ በፊት በባለሙያ ውሳኔ ወይም በባለ ትዳሮቹ ፍላጎት በማንኛውም ጊዜ ሊወገድ ይችላል " የሚል ድንጋጌን አካትቷል።
ለምክር ቤቱ የቀረበው ረቂቅ እንዲወገድ የተወሰነው የዘር ፍሬ ወይም ዘርፍ ፍሬ ውሃ " ከተገልጋዮች ፍቃድ ከተገኘ ለምርምር ዓላማ ሊውል ይችላል " ይላል።
የረቂቅ አዋጁ ማብራሪያ " በዘር ፍሬ ልገሳ ሥርዓት የሚወለዱ ልጆች እና ወላጆችን በተመለከተ የፌደራል ቤተሰብ ሕግ ላይ ከተቀመጠው የተለየ በመሆኑ ይህንኑ ልዩነት ከቤተሰብ ሕጉ ጋር ባልተፋለሰ መልኩ እንዲቀመጥ ተደርጓል " ይላል።
ተፈጻሚነት የሌላቸውን ሕጎች የሚዘረዝረው የረቂቁ ክፍል በቤተሰብ ሕግ አዋጁ " ስለመወለድ የሚደነግጉት የአዋጁ ... ድንጋጌዎች በዘር ፍሬ ልገሳ በተገኙ ልጆች እና ወላጆቻቸው ላይ ተፈጻሚነት አይኖራቸውም " ሲል ይደነግጋል።
ተፈጻሚነት አይኖራቸውም የተባሉት ድንጋጌዎች አባትነትን እና እናትነትን ስለማወቅ፣ ልጅነትን ስለመቀበል፣ ስለ ልጅነት ማስረጃ እና ሌሎች ጉዳዮችን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች ናቸው።
መረጃው የቢቢሲ አማርኛ ነው።
@tikvahethiopia
#MPESASafaricom
ሁሉንም የሃገር ውስጥ በረራዎች ትኬት በM-PESA እንግዛ ፤ በ5% ተመላሽ ተደስተን እንጓዝ! መልካም ጉዞ 5% ቅናሿን ይዞ !
የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉/channel/Safaricom_Ethiopia_PLC
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#FurtherAheadTogether
ከንጉስ ማልት ጋር ተጨማሪ ደስስስስስስስስስስታን ያጣጥሙ!
ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ /channel/Negus_Malt
#ከአልኮልነፃ #ደስደስበንጉስ #የጣዕምልኬት_የደስታስሜት #ንጉስማልት
#AddisAbaba
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በእጣና በጨረታ ተላልፈው ነዋሪ ባልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ/ም ባለቤቶቹ እንዲገቡ ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡
ውሳኔው የተላለፈው ቤቶቹ “ሕገ ወጥ ተግባራት እየተፈጸመባቸው” መሆኑን በመጥቀስ ነው።
የቤቱ ባለቤቶች እስከ ተባለው ቀን ድረስ ካልገቡ ቤቶቹ በእጣና በሽያጭ ለሌላ ነዋሪ እንደሚተላለፉ ኮርፖሬሽኑ መግለጹ አይዘነጋም።
ይህን ውሳኔ ተከትሎም የቤት ባለቤቶች የተለያዩ ጥያቄዎችን ለሚዲያችን አቅርበዋል።
በተለይም በአራብሳ ሳይት የሚገኙ የቤቶቻቸው መሠረተ ልማት ያልተጠናቀቀላቸው ሰዎች ውሳኔው ብዥታ እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል።
የቤት ባለቤቶቹ መሠረተ ልማታቸው ሳይሟሉ እንዴት መግባት እንችላለን? ግዴታ መግባት ነው ወይስ ማከራየት ይቻላል? የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎችን አቅርበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣
₀መሠረተ ልማት ባልተሟላባቸው ቤቶች እንዴት መግባት ይቻላል?
₀የቤቱ ባለቤቶች ግዴታ መግባት ነው ያለባቸው ማከራየት ይችላሉ?
₀ክፍት በሆኑ ቤቶች የሚፈጸሙ ጥቃቶች ምንድን ናቸው?
₀እንዲህ አይነት ድርጊት የሚፈጸመው በተጨባጭ በየትኞቹ ሳይቶች ነው? ሲል ኮርፖሬሽኑን ጠይቋል፡፡
አንድ ስማቸው እንዲነገር ያልፈለጉ የኮርፖሬሽኑ አካል፣ ማስታወቂያው የወጣው መሠረተ ልማት ተሟልቶላቸው ላልገቡ የቤት ባለቤቶች እንጂ መሠረተ ልማታቸው ላልተሟላላቸው እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡
“ያልተሟላቸውን እማ እንዴት ተብሎ!? የማሟላት ግዴታ አለበት መንግስት መሠረተ ልማቱን” ነው ያሉት፡፡
የኮርፖሬሽኑ በዝርዝር ማብራሪያ በቀጣይ ይቀርባል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia