ቲክቶክ ወደ ፍርድ ቤት አመራ።
ቲክቶክ የተሰኘው የቪድዮ ማጋሪያ የማህበራዊ ሚዲያ ለአሜሪካ ኩባንያ የማይሸጥ ከሆነ በመላ አሜሪካ ለመታገድ ተቃርቧል።
እግዱ ተግባራዊ እንዳይደረግ ወይም ውድቅ እንዲሆን ቲክቶክ ወደ አሜሪካ ፍርድ ቤት አምርቷል፤ ሙግትም ከፍቷል።
መተግበሪያው ለፍ/ቤት ባቀረበው የአቤቱታ መዝገብ " ከ9 ወር - 1 ዓመት ባለው ጊዜ ቲክቶክ ካልተሸጠ #ይታገድ " የሚለው ሕግ ኢ-ሕገመንግስታዊ ነው ብሎታል።
" ሕጉ የአሜሪካውያንን የመናገር ነጻነትን የሚያደናቅፍ እና ሕጋዊ መረጃን እንዳያገኙ የሚከለክል ነው " ሲል አክሏል።
አሜሪካ እርምጃውን ለመውሰድ " ግምታዊ ስጋቶችን " ብቻ እንዳቀረበች የገለጸው ቲክቶክ ፍርድ ቤት እግዱን እንዲያስቆምለት ጠይቋል።
ባይትዳንስ ኩባንያ 'ቲክቶክ'ን አሁን ባለው አልጎሪዝም ከመሸጥ አሜሪካ ውስጥ ሙሉ በሙሉ #መዘጋትን እንደሚመርጥ የኩባንያው ምንጮች መናገራቸው ይታወሳል።
አሜሪካም ከሀገር ደህንነት ጋር በተያያዘ " ካልተሸጠ ይታገድ " በሚለው ሕግ ላይ አቋሟ ፍጹም የጸና ነው ተብሏል።
በቀሩት ጥቂት ወራት ውስጥ #ካልተሸጠ በመላው አሜሪካ መታገዱ የማይቀርለት ቲክቶክ 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎቹን ያጣል።
@tikvahethiopia
የቤንዚን የችርቻሮ መሸጫ ላይ ጭማሪ ተደረገ።
የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ ከግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ/ም ለሊት 6፡00 ሰዓት ጀምሮ በስራ ላይ ያለው የነጭ ናፍጣ ፣ የኬሮሲን ፣ የአይሮፕላን ነዳጅ ፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣና የከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ #ባለበት_እንደሚቀጥል አሳውቋል።
በዚህ መሰረት ፦
- ነጭ ናፍጣ ➡ ብር 79.75 በሊትር
- ኬሮሲን ➡ ብር 79.75 በሊትር
- የአውሮፕላን ነዳጅ ➡ ብር 70.83 በሊትር
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ ➡ ብር 62.36 በሊትር
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ ➡ ብር 61.16 በሊትር ሆኖ ባለበት ይቀጥላል።
የቤንዚን ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደርጎ በሊትር 78 ብር 67 ሳንቲም ገብቷል።
@tikvahethiopia
#Ethiopia
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐ ግብር ሊጀምር ነው።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጪው #መስከረም_ወር ጀምሮ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐግብር እንደሚጀምር አስታውቋል።
ዩኒቨርሲቲው በቅደመ ምረቃና ድህረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞች ተመርቀው የስራ ዓለም ውስጥ ለሚገቡ ተመራቂዎች ራሱን የቻለ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ እንደሚሰጥ ገልጿል።
ፕሮግራሙ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና የገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ነው ያለው ዩኒቨርሲቲው " ይህ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጥ ነው " ብሏል።
" የፕሮግራሙ መጀመር በሥራ ገበያው ውስጥ ብቁ ሙያተኞችን ለማግኘትና የዩኒቨርሲቲውን አቅምና ብቃት ያለው ባለሙያ የማፍራት ተልዕኮ የሚያሳካ ነው " ሲል ገልጿል።
የሙያ ብቃት ማረጋገጫው #በሁሉም_ዘርፎች ላይ የሚሰጥ ሲሆን ይህ የሚመራበት አሰራር ይዘረጋል ተብሏል።
በትምህርት ስርዓት ውስጥ ያሉ #ተማሪዎችም ሆኑ በስራ ገበያ ያሉ ሰራተኞችና ምሁራን ለተማሩበት ሙያ የብቃት ማረጋገጫ ወይም #ፕሮፌሽናል_ሰርትፊኬት መውሰድ እንደሚችሉ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል። #ኢዜአ
@tikvahethiopia
#ሴጅ_ማሰልጠኛ_ኢንስቲትዩት
13ኛ ዙር የድህረ-ገፅ እና ሞባይል መተግበሪያ ማበልፀግ (Full-Stack Website and Mobile Application Development) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን።
👉 100 % በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 መሠረታዊ ኮምፒውተርና ፕሮግራሚንግ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 Front-end እና Back-end በአንድ ላይ እስከ Deployment ያካተተ
👉 በተግባር ድህረ ገጾችን እና ሞባይል መተግበሪያዎችን እያበለፀጉ የሚሰለጥኑበት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት
ስልክ ፦ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
Facebook Instagram Telegram
sage_training_institute">TikTok Linkedin
" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ #ጅቦቹ ሰው መተናኮስ ፤ በቀን መታየትና #ሰብሰብ ብሎ መሄድ ጀምረዋል " - ነዋሪዎች
" በኛ ቀበሌ ብቻ 3 ህጸናት በጅቦች ተበልተዋል። 2ቱ ሲሞቱ አንዷ ተርፋለች " - አቶ ማርቆስ ቡታ
ከሰሞኑን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የተራቡ ጅቦች እያደረሱ ስላለው ጥቃት የሚመለከቱ መረጃዎችን ማጋራታችን ይታወሳል።
በተለይ በስልጤ ዞን እና በሀላባ ዙሪያ በተፈጸሙ የጅብ ጥቃቶች ምክኒያት የሰው ህይወት መጥፋትና የአካል ጉዳት መድረሱን መግለጻችን አይዘነጋም።
በወቅቱ " የጅብ መንጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ተከስቷል " የሚለውን ዜና የሰሙ የሲዳማ ክልል፣ የሀዋሳ ከተማ ዙሪያ ነዋሪዎች " ችግሩ እኛም ጋር አለ እንዲያዉም ከህጻናት ባለፈ አዋቂዎችንም አሳስቦናል " በማለት መልዕክቶቻቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አድረሰዋል።
ጉዳዩን በተመለከተ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የሀዋሳ አባል በሀዋሳ ዙሪያ ቡሽሎ ፣ ፊንጭ ውሀና ገመጦ... ወዘተ ቀበሌዎች ያሉ ማህበረሰቦችና የጸጥታ አካላትን አነጋግሯል።
የአካባቢው ነዋሪዎች በጊዜ ወደ ቤታቸው መግባት መጀመራቸውን በመጥቀስ ህጻናት ልጆቸውም ፍርሀት እንዳደረባቸዉ ገልጸዋል።
በተለያየ ጊዜ በ5 ሰዎች ላይ የጅብ ጥቃት ደርሶ እንደነበር እና 2 ህጻናት እንደሞቱ 1 ህጻን እንዲሁም 4 አዋቂዎች ደግሞ እንደተጎዱ አስረድተዋል። የሚመለከተው አካል አንዳች መፍትሄ እንዲሰጣቸውም ጠይቀዋል።
በአካባቢው ለረዥም ጊዜያት ጅቦች እንደነበሩ የሚገልጹት ነዋሪዎቹ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሰው መተናኮስ ፤ በቀን መታየትና #ሰብሰብ ብሎ መሄድ መጀመራቸው እንዳስገረማቸው ገልጸዋል።
ጉዳዩን በተመለከተ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የቡሽሎ ቀበሌ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ማርቆስ ቡታ ፤ " በእኛ ቀበሌ ብቻ 3 ህጻናት በጅቦች ተበልተዋል " ሲሉ ተናግረዋል።
2ቱ መሞታቸውን ፤ አንዷ ህጻን በወቅቱ በተደረገ ርብርብ ተርፋ በተደረገላት ህክምና መዳኗን ገልጸዋል።
በአጎራባች ቀበሌያት ውስጥ በ2 አዋቂ ሰዎች ላይ አሰቃቂ አደጋ ቢደርስም ለመትረፍ እንደቻሉ የጠቀሱት አቶ ማርቆስ ችግሩ አሳሳቢ በመሆን የጸጥታ አካላት እየተነጋገረበት ነው ብለዋል።
ማህበረሰቡ በጊዜ በመግባት የሚሰጠዉን የጥንቃቄ መልእክት በአግባቡ እንዲተገብርም ጠይቀዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
የትንሳኤ ልዩ የሞባይል ጥቅል የቆይታ ጊዜ ነገ ያበቃል!
ልዩ የበዓል ጥቅሎቹን በቴሌብር ሱፐርአፕ ከተጨማሪ 10% ስጦታ ጋር እንዲሁም በማይ ኢትዮቴል፣ አርዲ ቻትቦት ወይም በ*999# ይግዙ፤ ለሚወዷቸውም በስጦታ በማበርከት እስከ 25% ቅናሽ ያግኙ!
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
" ፍጹም ሀሰተኛ ነው " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ከሰሞኑን የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይል /Rapid Support Forces - RSF/ በሚባል የሚጠራው " የህወሓት ታጣቂዎች ከሱዳን ወታደራዊ ሃይል /SUDANESE ARMED FORCES SAF/ ጋር በማበር እየወጉኝ ነው " በማለት ያወጣውን መግለጫ ፍጹም ሀሰተኛ እና መሰረተ ቢስ እንደሆነ ገለጸ።
ሱዳን በእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ከገባች በርከታ ወራት ያለፉ ሲሆን በዚህም የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሹ ኃይል ደም አፋሳሽ ግጭት እያደረጉ ናቸው።
ታዲያ ፈጥኖ ደራሹ ኃይል " ህወሓት (TPLF) ከሱዳን ጦር ጋር ሆኖ ወግቶኛል " ብሏል።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መግለጫ ለዘመናት የቆየውና በፅኑ መሰረት የቆመው የትግራይና የሱዳን ህዝቦች ወዳጅነት ከግምት ያላስገባ ነው ብሎታል።
" በሱዳን ያለው የአርስበርስ ግጭት ዓለምአቀፍ መልክ ለማስያዝና እርዳታ ለማግኘ ያለመ ነው " ሲልም ገልጿል።
ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በዚሁ የሺዎች ህይወት በመቅጠፍ ላይ ያለውን የአገሪቱ የእርስ በርስ ጦርነት ላክ የህወሓት ሃይሎች ተሳትፈዋል የሚል ክስ ማቅረቡ " ሃሳባዊና መሬት ላይ መረጋገጥ የማይችል የለየለት ፈጠራ " ሲል አጣጥሎታል።
" በመሰረቱ ህወሓት የፓለቲካ ድርጅት እንጂ የሚያዘውና የሚያስተዳድረው ታጣቂ ሃይል የለውም " ያለው የጊዚያዊ አስተዳደሩ መግለጫ " የትግራይ ህዝብ ከወንድም የሱዳን ህዝብ የረጅም ጊዜ መልካም ግንኙነትና ጉርብትና አለው " ብሏል።
" ከዚህ አኳያ ትግራይ በሱዳን የውስጥ ጉዳይ ነገሮች በማጋጋል የምትገባበት ምክንያትና የምታገኘው ጥቅም የለም " ሲል አሳውቋል።
ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፤ በሱዳን የተፈጠረው አውዳሚ የአርስ በርስ ጦርነት የሚያስከትለው አደጋ በመረዳት የውጭ ሃይሎች በአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠቡ አሳስቧል።
@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ
የባንክ አካውንት ባንክ ሳይሄዱ መክፈት ይቻላል? አዎ! በአቢሲንያ ቨርቹዋል ባንክ ከእሁድ እስከ እሁድ ለ24 ሰዓት ይቻላል።
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
#virtualbanking #bankinginethiopia #banksinethiopia #ITM #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#AddisAbaba
ታግታ 150 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የተጠየቀባት ህጻን ተገኘች።
የ2 ዓመት ከ8 ወር ዕድሜ ያላት አቢጊያ ዳንኤል የተባለች ህፃን ነዋሪነቷ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 " ሳርቤት ' አካባቢ ሲሆን ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስዳ ትታገታለች።
አጋቿ ቸርነት ጥላሁን የተባለው ግለሰብ ነው።
ግለሰቡ ከቤተሰቡ ጋር በነበረው ቅርበት ህፃን አቢጊያን በተለያዩ ቦታዎች እየወሰደ በማዝናናት እንደ ቤተሰቡ አባል ያጫውታት እንደነበረ እና ከ5 ወር በላይ ከቤተሰቡ ጋር በትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪነት የነበረው ቅርብ ወንጀሉን በቀላሉ ለመፈፀም ምቹ ሁኔታን እንደፈጠረለት የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።
ግለሰቡ ሚያዚያ 25 ቀን 2016 ዓ/ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ተኩል ገደማ ወደ ህፃኗ ወላጆች መኖሪያ ቤት በመሄድና "እናቷ አምጣት ብላኛለች "ብሎ ለቤት ሰራተኛዋ ከነገረ በሗላ ህፃን አቢጊያ ዳንኤልን ወስዶ በማገት ገንዘብ እንዲሰጠው ከወላጆቿ ጋር ሲደራደር ቆይቷል።
ተጠርጣሪው ግለሰብ 150 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እንዲሰጠው በመጠየቅ ገንዘቡን ማግኘት ካልቻለ ግን ህፃኗን በህይወት እንደማያገኟት ሲዝት ነበር።
የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ ህፃኗን ለማስመለስ እና ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።
በተደረገው ክትትልም ዛሬ ሚያዚያ 28/ 2016 ዓ/ም በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አለም ሰላም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተጠርጣሪው ተከራይቶ በሚኖርበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ለ3 ቀናት ያህል ታግታ የቆየችው ህፃን አቢጊያ ዳንኤል ልትገኝ መቻሏን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
ምንም እንኳን ፖሊስ ህጿን መገኘቷን ቢገልጽም አጋቹ በቁጥጥር ስር ስለመዋሉ ያብራራው ነገር የለም።
@tikvahethiopia
ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር
Yonatan BT Furniture
የዘመናዊነት ተምሳሌት!
አድራሻችን፦
1. ዊንጌት አደባባዩን ተሻግሮ: +251 995 27 2727
2. ፒያሳ እሪ በከንቱ : +251 957 86 8686
3. ሲ ኤም ሲ አደባባዩን አለፍ ብሎ: +251 993 82 8282
👉 Telegram: /channel/yonatanbt_furniture
👉 Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100087238034736
👉 TikTok: yonatanbtfurniture" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@yonatanbtfurniture
👉 Instagram: https://www.instagram.com/yonatanbtfurniture/
በደቡብ ወሎ ዞን፤ በደላንታ ወረዳ የመአድን ቁፋሮዉ ዳግም መጀመሩ ተነገረ።
በደላንታ ወረዳ አለኋት ቀበሌ " ቆቅ ውሀ " እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የኦፓል ማዕድን ለማውጣት ቁፋሮ ላይ የነበሩ ሰዎች ዋሻ ተደርምሶባቸው እንደነበር ይታወሳል።
የሰዎቹን ህይወት ለማዳን ሲደረግ የነበረው ጥረት በመቋረጡ የተጎጂ ቤተሰቦች ተስፋ በመቁረጥ ለቅሶ መቀመጣቸውም መነገሩ አይዘነጋም።
አሁን ላይ የአካባቢው ማሕበረሰብ ተስፋ በመቁረጥ እና እርሙን በማውጣት ወደ መደበኛው የኦፓል ማዕድን የማውጣት ስራ የተሰማራ መሆኑ ተሰምቷል።
የደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ የማዕድን ስራዎች ፈቃድ መስጠትና ማስተዳደር ቡድን መሪ አቶ በሪሁን ማህብረሰቡ ተስፋ ቆርጦና እርሙን አውጥቶ ወደ መደበኛው የኦፓል ማዕድን የማውጣት ስራ ገብቷል ብለዋል።
ከተፈጠረው አደጋ ለምን መማር አልተቻለም ? አሁን ላይስ ማዕድን ለማውጣት ከበፊቱ በተለየ ጥቅም ላይ የሚውል የተሻለ መሳሪያ አለ ወይ ? ተብለው የተጠየቁት ኃላፊው ፥ " የአካባቢው ማሕበረሰብ ኑሮውን የሚያስተዳድረው የኦፓል ማዕድን በማውጣት በመሆኑ ያለ ምንም መሳሪያ ቀደም ሲል በነበረው በባህላዊ መንገድ ስራውን እያከናወነ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
ይህ መረጃ #ባለቤትነቱ የአሐዱ ሬድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን ጣቢያ ነው።
@tikvahethiopia
#ታምራት_ፕሌት_እና_ጄቦልት_አቅራቢ
📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን
✂️ላሜራ መቁረጫ መብሻና ማጠፊያ ማሽኖች አሉን
🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ እናበጃለን እንዲሁም እናጥፋለን
📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን
📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን
አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
ቁ.2 መርካቶ
ቁ.3 ተክለሀይማኖት
0904040477
0911016833
Manager : Netsanet Tamene
#Update
በጎረቤት ሀገር #ኬንያ ለሳምንታት በዘለቀ ከባድ ዝናብ እና ጎርፍ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 228 መድረሱን የኬንያ የሀገሪር ውስጥ ሚኒስቴር አሳውቋል።
ደብዛቸው የጠፋ በርካታ ሰዎች እንዳሉም ተነግሯል።
@tikvahethiopia
" የ2 ሰዎችን አስክሬን እየፈለግን ነው " - የዞኑ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ
በሀላባ ዞን ንፋስ እና በረዶ ቀላቅሎ የጣለዉ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የሰዎች ህይወት ጠፍቷል።
ከሰው ህይወት መጥፋት ባለፈ በአዝእርትና በብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።
ይህ ሁሉ ጉዳት የደረሰው በአጭር ጊዜ ውስጥ ሲሆን ከዝናቡ ጋር በተያያዘ የተከሰተው የመሬት መሰንጠቅ በህብረተሰቡ ዘንድ ድንጋጤ መፍጠሩ ተነግሯል።
በጉዳዩ ላይ ቃላቸውን ለቲኪቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የሀላባ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ሀላፊው አቶ ሸምሰዲን ጉታጎ ፥ " ሁኔታዉ እጅግ አስደንጋጭ ነው " ብለዋል።
በጎርፍ አደጋው የ5 ሰዎች ህይወት ጠፍቷል ሲሉ ገልጸዋል።
" አሁንም በጎርፍ ተወስደዉ ከሞቱት 5 ወገኖች መካከል የሁለቱን አስክሬን ማግኘት አልቻልንም " ብለዋል።
የአስከሬን ፍለጋው ሻላ ሀይቅ ውስጥ እየተካሄደ መሆኑን እና የኦሮሚያ የጸጥታ ኃይሎች በተለይ ዋናተኞች እያገዟቸዉ መሆኑን አስረድተዋል።
በተጨማሪም አደጋው በርካታ የግለሰብ ቤቶችን እንዲሁም ዌራ ወረዳ ያለን ሆስፒታልን ሙሉ በሙሉ ከስራ ዉጭ እንዳደረገው ገልጸዋል።
በዞኑ በበርካታ ቦታዎች ላይ የተፈጠረው የመሬት መሰንጠቅም በህብረተሰቡ ዘንድ ድንጋጤ መፍጠሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
#ትንሣኤ
ለመላው #የክርስትና_እምነት_ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ !
" በዚህ የለም ፤ እርሱ እንደተናገረው ተነሥቶአል "
በማቴዎስ ወንጌል ፥ " እነሆ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ ወርዶአልና ፤ ቀርቦም በመቃብሩ አፍ ላይ ድንጋይዋን አንከባሎ በላይዋ ተቀመጠ፡፡
መልኩም እንደ መብረቅ ፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበር፡፡
እርሱንም ከመፍራት የተነሣ መቃብሩን የሚጠብቁ ታወኩ ፤ እንደ በድንም ሆኑ፡፡
መልአኩ መልሶ ሴቶቹን እንዲህ አላቸው፥ ' እናንተስ #አትፍሩ ፤ የተሰቀለውን #ኢየሱስን_እንደምትሹ አውቃለሁና፡፡ በዚህ የለም ፤ እርሱ እንደ ተናገረው ተነሥቶአል ' " ተብሎ እንደተጻፈው #መድኃኒዓለም ብርሃንን ተጎናጽፎ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን በክብር #ተነሥቶአል፡፡
መልካም የትንሣኤ በዓል !
በዓሉ የሰላምና የፍቅር ይሆን ዘንድ እንመኛለን !
#TikvahEthiopiaFamily❤️
@tikvahethiopia
#Ethiopia
ትላንትና ማክሰኞ #ከሀዋሳ ወደ #አዲስ_አበባ በመብረር ላይ እያለ የደኅንነት ችግር ሊያስከትል የሚችል ክስተት በገጠመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በረራ ቁጥር #ET154 ላይ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጥልቅ የሆነ የደኅንነት ምርመራ ሊያደርግ እንደሆነ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።
ትላንት ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ ከፍተኛ ጭስ መከሰቱን፣ ነገር ግን በመንገደኞች ላይም ሆነ በአውሮፕላኑ ላይ ምን ዓይነት እክል ሳይፈጠር ቦሌ ኤርፖርት በሰላም ማረፉ መገለጹ ይታወሳል።
አውሮፕላኑ ውስጥ ለጊዜው በምን ምክንያት እንደተነሳ ያልታወቀው ጭስ መንገደኞችን ከፍተኛ ድንጋጤና ፍርኃት ውስጥ አስገብቷቸው ነበር።
የአውሮፕላኑ ዋና አብራሪ ባስተላለፉት የደኅንነት ጥንቃቄ ዕርምጃ መሠረት ሁሉም ተሳፋሪዎች በአውሮፕላኑ ላይ የተገጠመውን የአየር መሳቢያ የፊት ጭምብል (oxygen mask) እስከማድረግ ደርሰው ነበር።
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን የበረራ ደኅንነት ክፍል እክል የገጠመው አውሮፕላን ቀጣይ በረራ እንዳያደርግ በማገድ በበረራ ወቅት ያጋጠመውን የደኅንነት ክስተት እንደሚያጣራ ሪፖርተር ጋዜጣ ስማቸው ያልተገለጹ የተቋሙን ምንጮች ዋቢ በማድረግ አስነብቧል።
እኚሁ ምንጮ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አየር መንገዱ በሚሰጠው የአገር ውስጥ የበረራ አገልግሎት ላይ የደኅንነት አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ክስተቶች ደጋግመው መከሰታቸውን አስታውሰው የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን አጠቃላይ የደኅንነት ፍተሻ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
ባለፈው ጥር ወር 2016 ዓ/ም ላይ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ሲበር የነበረ አንድ የመንገደኞች አውሮፕላን በመቐለ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ በሚሞክርበት ወቅት ከማረፊያው አስፋልት ውጪ የመውጣት እክል ገጥሞት እንደነበር ይታወሳል።
ሌላው የመንገደኞች አውሮፕላን በተመሳሳይ በአርባ ምንጭ አየር ማረፊያ ከማረፊያ መስመሩ (ራንዌይ) የመውጣት እክል ገጥሞት እንደነበር ተስምቷል።
በአጠቃላይ በአንድ ዓመት 4 የደኅንነት እክሎች የተመዘገቡ መሆኑን ጋዜጣው ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ ጠቁሟል።
ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ ከተማ ሲበር የነበረውን ጨምሮ እክል ያጋጠማቸው አውሮፕላኖች ' #Q400 ' በመባል የሚታወቁት አየር መንገዱ በአገር ውስጥ እና ወደ ጎረቤት አገሮች ለሚደረጉ በረራዎች የሚገለገልባቸው ናቸው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካሉት 178 አውሮፕላኖች መካከል 33 የሚሆኑት Q400 በመባል የሚታወቁት ለመካከለኛ ርቀት የሚጠቀምባቸው አውሮፕላኖች ናቸው። #ሪፖርተር
@tikvahethiopia
ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር
በዓሉን ምክንያት በማድረግ እስከ 25% ቅናሽ የተደረገባቸውን ማራኪና ውብ የመመገቢያ ጠረጴዛዎቻችንን በመግዛት ልዩ የአብሮነት ጊዜ ያሳልፉ!
የዘመናዊነት ተምሳሌት!
አድራሻችን፦
1. ዊንጌት አደባባዩን ተሻግሮ: +251 995 27 2727 / +251 911 51 6843
2. ፒያሳ እሪ በከንቱ : +251 957 86 8686
3. ሲ ኤም ሲ አደባባዩን አለፍ ብሎ: +251 993 82 8282
👉 Telegram: /channel/yonatanbt_furniture
👉 Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100087238034736
👉 TikTok: yonatanbtfurniture" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@yonatanbtfurniture
👉 Instagram: https://www.instagram.com/yonatanbtfurniture/
#Update
" በጎርፍ የተወሰዱ አስክሬኖች #አልተገኙም " - የሀላባ ዞን ሰላምና ጸጥታ ጉዳይ መምሪያ
ከሰሞኑን በሀላባ ዞን ንፋስ እና በረዶ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ በተከሰተ ከባድ የጎርፍ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉን መረጃ እንደሰጠናችሁ ይታወሳል።
በወቅቱ 5 ሰዎች መሞታቸዉንና ከነዚህ ዉስጥ የ2 ሰዎች አስከሬን አለመገኘቱ መግለጹ አይዘነጋም።
አስክሬን ፍለጋው ከምን ደረሰ ? ከአደጋው ጋር በተያያዘ ምን አዲስ ነገር አለ ? ስንል የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሀላፊን አቶ ሙደስር ጉታጎ ጠይቀናቸዋል።
ኃላፊው አስከሬኖቹ አሁን ድረስ አለመገኘታቸውን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ፤ አንድ አስክሬን በዞኑ መገኘቱን በተደረገው ማጣራት አስከሬኑ ከስልጤ ዞን በጎርፍ ምክንያት የመጣ እንደሆነ ጠቁመዋል።
የጎርፍ አደጋው እስካሁን መሬት ላይ የነበረዉን ሰብል ሙሉ በሙሉ እንዳወደመ ገልጸዋል።
በዞኑ ውስጥ ባለው የሀላባ ቁሊቶ ሆስፒታል ላይ ከ6 ሚሊየን 500 ሺህ ብር በላይ ጉዳት እንዳደረሰ ተናግረዋል። ነገር ግን ሆስፒታሉ አሁንም በስራ ላይ መሆኑን አመልክተዋል።
ከዚህ ቀደም የተገለጸው ዌራ ወረዳ ሆስፒታል ግን በአደጋው ምንም ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ስራ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በአጠቃላይ ጎርፉ ያስከተለዉ አደጋ በህዝብና ግለሰቦች ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ እና የንብረት ውድመት ያስከተለ ሲሆን ዞኑ አሁንም አስክሬን እና የጠፉ ሰዎችን የማፈላለጉ ስራ እንደቀጠለ መሆኑን ተናግረዋል።
አሁንም የአየር ትንበያ ዘገባዎች በደቡቡ ኢትዮጵያ ክፍል ከፍተኛ ዝናብ እንደሚኖር ስለሚጠቁሙ ማህበረሰቡ ሊከሰቱ ከሚችሉ አደጋዎች ራሱን እንዲጠብቅ መልዕክት ተላልፏል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
ለ Big 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ ይዘጋጁ! በሃገሪቱ ግንባታ ዘርፍ ትልቁ ዝግጅት፤ ከግንቦት 22 እስከ ግንቦት 24፣ 2016 በሚሊኒየም አዳራሽ ይዘጋጃል።
- ከ 150 በላይ ከሚሆኑ ተሳታፊዎች የሚቀርቡ አዳዲስ ምርቶችንና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ይጎብኙ!
- ከ 15 በላይ ሃገራት ከሚመጡ ተሳታፊዎች ጋር ይገናኙ!
- በግንባታው ዘርፍ ከበቁ 9000 ባለሙያዎች ጋር ትስስር ይፍጠሩ!
- ከ 20 በላይ በሚሆኑ፣ በዋጋ በማይተመኑ መረጃ ሰጪ መድረኮች ላይ የመሳተፍና የ Continuous professional development ነጥብዎን የማሳደግ ዕድሉን ያግኙ!
በሁነቱ ላይ ልናገኝዎ በጉጉት እንጠብቃልን!
በነጻ ለመጎብኘት አሁኑኑ ይመዝገቡ : https://bit.ly/3UsrL5I
#AddisAbaba
ሀሙስ ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ ለመምህራንና ለትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና ፈተና እንደሚሰጥ ተነግሯል።
ፈተናው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በጋራ በመሆን ነው የሚሰጡት ተብሏል።
ፈተናው በተመረጡ የመፈተኛ ጣቢያዎች በፈቃደኝነት ለተመዘገቡ 18 ሺህ 591 ለሚሆኑ መምህራንና የትምህርት አመራሮች እንደሚሰጥ ተገልጿል።
በፈተና ወቅት ተመዛኞች ስልክ ሆነ ማንኛውንም አይነት ኤሌክትሮኒክስ ግብአቶች ይዞ ፈተና ክፍል መግባት እንደማቻል ተገልጿል።
ተመዛኞች ፦
➡️ የታደሠ መታወቂያ ይዘው መገኘት እንደሚጠበቅባቸው ፣
➡️ ፈተናው ከመጀመሩ በፊት 1:00 ሠዓት ቀደም ብለው (1:30) ላይ የምዘና ፈተና መስጫ ቅጥር ግቢ ውስጥ መገኘት እንዳለባቸው እና አርፍዶ መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው ተብሏል።
ምንም እንኳን ፈተናው በፍቃደኝነት ለተመዘገቡ 18,491 መምህራን እና የትምህርት አመራሮች እንደሚሰጥ ቢገለጽም የምዘና ፈተና ለመውሰድ #ስላልተመዘገቡ ወይም ፍቃደኛ ስላልሆኑ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ምንም የተባለ ነገር የለም።
@tikvahethiopia
ዛሬ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET154 ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ ታይቷል።
ነገር ግን አውሮፕላኑ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ በተመደበለት የመንገደኞች ማስተናገጃ በር ያለ ምንም እክል መቆሙን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል።
መንገዶኞቹም ከአውሮፕላን ላይ ደህንነታቸው እንደተጠበቀ መወርዳቸውን ገልጿል።
" በአሁኑ ሰአት የክስተቱ መንስኤ በመጣራት ላይ ይገኛል " ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው ክስተት ደንበኞቹን ይቅርታ ይጠይቋል።
@tikvahethiopia
#ታምራት_ፕሌት_እና_ጄቦልት_አቅራቢ
📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን
✂️ላሜራ መቁረጫ መብሻና ማጠፊያ ማሽኖች አሉን
🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ እናበጃለን እንዲሁም እናጥፋለን
📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን እንሰራለን
📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን
አድራሻችን፦ ቁ.1 አዉቶብስ ተራ(መሳለሚያ)
ቁ.2 መርካቶ
ቁ.3 ተክለሀይማኖት
0904040477
0911016833
Manager : Netsanet Tamene
#Update
የታገቱ ሰዎች ጉዳይ ከምን ደረሰ ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ፦
➡️ ወደ ባቱ ሲጓዙ በታጣቂዎች ስለታገቱና እስካሁን ስላልተለቀቁ 3 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኞች ጉዳይ፤
➡️ ልጃቸው በሊቢያ ስለታገተባቸው የሀዋሳዋ እናት ፣
➡️ ልጃቸው በሊቢያ ስለታገተባቸው የአዲስ አበባው አባት ፤
➡️ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ስትጓዝ የመን ላይ ታግታ 300 ሺህ ብር ስለተጠየቀባት ወጣት መረጃዎችን ማድረሱ ይታወሳል።
ስለታጋቾች አሁንስ #ምን_አዲስ_ነገር_አለ ? በሚል ቤተሰቦቻቸውን ጠይቋል።
የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ታጋቾችን በተመለከተ አዲስ ነገር የጠየቅናቸው የአንዱ ታጋች እህት ወይዘሮ ራሄል ሶስቱም #እንዳልተለቀቁ ገልጸው ፤ “ ምንም አይነት ፍንጭ የሚሰጠንም አጣን። የት እንሂድ ? ምን እናድርግ ? ” ሲሉ በሀዘን ጠይቀዋል።
ልጃቸው በሊቢያ እንደታገተባቸው ገልጸው የነበሩት የሀዋሳዋ ወይዘሮ ገነት ጥላሁን ፥ “ አሁንማ ‘ ፓሊስ ከቧቸዋል ’ ተብሎ ስልክም ብንደውል አይነሳም። ስልካቸው ከጠፋ ከ15 ቀናት በላይ ሆኗል ” ሲሉ ገልጸዋል።
“ ትሪፓሊ ከተማ ከደረሱት ውስጥ መረጃ ስንጠይቅ ‘ፓሊስ መጥቶባቸው ነው ፤ ከበዋቸዋል አካባቢውን’ ” እንዳሏቸው ገልጸዋል።
“ ደላላውን 1 ጊዜ ብቻ አግኝቸው ‘ ፓሊስ ስለመጣብን ሌላ መጋዘን ወስደናቸዋል ’ አለኝ ” ሲሉ ተናግረዋል።
በተመሳሳይ ልጃቸው በሊቢያ ታግቶባቸው 700 ሺሕ ከከፈሉ በኋላ በድጋሚ 400 ሺሕ ብር ተጠይቀው የነበሩት የታጋች አባት አቶ አማረ አለም ፣ ለ2ኛ ጊዜ የተጠየቁትን ገንዘብ ካርታ አስይዘው ተበድረው ከላኩ በኋላ ልጃቸው #እንደተለቀቀ ባሕሩን ለመሻገር አስቦ ሞገድ ስለተነሳ ገና እየጠበቀ እንደሆነ ገልጸዋል።
ሳዑዲ ለመሄድ " ራጎ " ላይ ስትደርስ በደላሎች 300 ሺሕ ብር የተጠየቀባት ታጋች ቤተሰቦች በበኩላቸው፣ ገንዘቡ ስላልተሟላ ገና እንዳልተላከ፣ ደላሎቹን ጊዜ እንዲሰጧቸው እየጠየቁ መሆናቸውን አስረድተዋል።
ውድ ቤተሰቦቻችን ፤ እገዛችሁን ጠይቀው የነበሩት ሁሉም የታጋቾች ቤተሰቦች ለረዷቸው ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Ethiopia
ሳፋሪኮም ፥ በ1.5 ቢሊዮን ዶላር 5,000 የቴሌኮም ማማዎችን ሊገነባ መሆኑን ገለጸ።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ማማዎቹን የሚገነባው የኔትወርክ መሰረተ ልማትን በአገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች ለማስፋፋት መሆኑን አስታውቋል።
በዚህም በቀጣዮቹ 3 ዓመታት የኔትወርክ ማማዎችን ለመገንባት ማቀዱን የገለጸው ተቋሙ ፣ ለግንባታው 1,5 ቢሊዮን ዶላን ፈሰስ ለማድረግ እንደመደበ ገልጿል።
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዊም ቫንሄለፑት ባደረጉት ገለጻ፣ “ ኔትወርካችንን ለማስፋፋት እና ለመላው ኢትዮጵያዊያን የቴሌኮም ትስስርን ለማሻሻል ከፍተኛ ጥረት እያደረግን እንገኛለን ” ብለዋል።
በአጠቃላይ የኔትወርክ ማማዎችን ቁጥር ወደ 7,000 ለማድረስ እየሰሩ እንደሚገኙ አስረድተው፣ “ በአሁኑ ጊዜ አገልግሎት ከምንሰጥባቸው 2,500 የቴሌኮም ማማዎች ውስጥ 1,5000 እራሳችን የገነባናቸው ናቸው ” ሲሉ ተናግረዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
ትላንት በአዲስ አበባ ፣ በቦሌ ክ/ከተማ " ስካይ ላይት ሆቴል " አካባቢ #እግረኞች ላይ በደረሰ የትራራፊክ ግጭት 1 ሰው ሞቷል። አንድ ሰዉ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በተለምዶው " ቸራአሊያ " በሚባል አካባቢ #እግረኛ ላይ በደረሰ ግጭት ደግሞ አንድ ሰዉ ሞቷል።
ልደታ ክ/ከተማም በተመሳሳይ የአንድ ሰው በትራፊክ አደጋ ሞቷል።
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ደግሞ ቡና በመሸጥ ላይ የነበረችው ወጣት ወደ ኋላ እየሄደ በነበረ ኤፍኤሳር መኪና ተገጭታ ሞታለች።
የመረጃዎቹ ምንጮች የአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ ማኔጅመንት / የአዲስ አበባ ፖሊስ (ኢትዮ ኤፍ ኤም) ናቸው።
@tikvahethiopia
መምህራኑ ላለፉት 2 ወራት ደመወዝ አልተከፈለንም አሉ።
በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎጃም ዞን፣ ጎንጂ ቆለላ ወረዳ ፣ ላለፉት 2 ወራት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው የገለጹ መምህራን የከፋ ችግር ላይ እንደሚገኙ ገለጹ።
መምህራኑ በቁጥር ከ1 ሺሕ በላይ ይሆናሉ።
በወረዳው በሚገኙ 52 የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩት እኚህ መምህራን ፤ ኑሯቸውን የሚገፉት በወርሃዊ ደመወዛቸው ብቻ በመሆኑ ፣ ዩኒቨርሲቲ ለሚማሩ ልጆቻቸው የሚላክ ገንዘብን ጨምሮ ቤተሰቦቻቸውን ለመደገፍ እንደተሳናቸው ገልጸዋል፡፡
የቆንጂ ቆለላ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ጌታቸው ደገፋው ችግሩ መሆኑን አምነዋል።
በአካባቢው ባለው የጸጥታ ችግር የሒሳብ ሠራተኞች ወደ ቢሮ ገብተው ለመሥራት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የተፈጠረ እንደሆነ ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት፣ ከመምህራን ማኅበር ጋራ በመነጋገር አዲስ ሠራተኞች ተመድበው ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። #ቪኦኤ
@tikvahethiopia
እንኳን ለብርሃነ ትንሳዔው በሠላም አደረሳችሁ!
በዓሉ ከቤተሰብዎ እና ከወዳጅ ዘመድዎ ጋር በፍቅር እና በደስታ የሚያሳልፉት እንዲሆንልዎ እንመኛለን፡፡
መልካም በዓል!
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!
ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡ አዳዲስ መረጃ እንዲደርሶ የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጫኑ፡፡
ቴሌግራም- /channel/HibretBanket
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/hibretbank/
ዌብሳይት- https://www.hibretbank.com.et/
#HibretBank
#Hawassa
" እንደሚወራው አይደለም ፤ ከአንድ ቤት በላይ የከፋ ጉዳት አላደረሰም " - የሀዋሳ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ
በሀዋሳ ከተማ የተነሳ የእሳት አደጋ አንድ መዝናኛ ቤት አውድሞ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል።
ዛሬ ረፋድ 4 ሰዓት አካባቢ በከተማው በተለምዶ 05 በመባል በሚታውቀዉ ሰፈር (አደባባይ አለፍ ብሎ ወይም ከመድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት/አስፓልት ተሻግሮ) የተነሳው የእሳት አደጋ አንድ መዝናኛ ቤትን በከፋ ሁኔታ አውድሞ በቁጥጥር ስር ውሏል።
እሳት አደጋው የደረሰው በማህበር ተደራጅተዉ በምግብና መጠጥ ሽያጭ የሚተዳደሩ ወጣቶች ውስጥ በአንደኛው ቤት ነው።
የእሳት አደጋው መፈጠሩን ተከትሎ በአካባቢው ግርግር ቢፈጠርም ከሰአት በኋላ ሁሉም ተረጋግቶ ወደተለመደው እንቅስቃሴ ተመልሷል።
ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የከተማው ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ሀላፊ አቶ ወንድሙ ቶርባ ፤ " ችግሩ እንደተፈጠረ የሀዋሳ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እና የኢንዱስትሪው መንደር የእሳት ብርጌድ በፍጥነት ደርሶ ተቆጣጥሮታል " ብለዋል።
" ከፍተኛ አደጋ በደረሰበት መዝናኛ ቤት ውስጥ በነበረ የኤሌክትሪክ ገመድ ላይ በተፈጠረ እሳት ነው አደጋው የተፈጠረው " ሲሉ ገልጸዋል።
በአደጋው በመዝናኛ ቤቱ ላይ ውድመት መድረሱን ጠቁመዋል።
አደጋው በደረሰበት ወቅት በአካባቢው ወደነበሩ ቤቶች እሳቱ እንዳይስፋፋ ሌሎች ሰዎች እቃቸዉን ቢያወጡም ቆይተው ወደቤቶቻቸዉ ተመልሰዋል ብለዋል።
" ከሁኔታው ጋር በተያያዘ ግርግር ቢፈጠርም ሰዎች ተመልሰው ወደ ስራቸዉ ገብተዋል " ሲሉ አክለዋል።
" አደጋው እንደሚወራዉ #እጅግ የከፋ አይደለም " ያሉ ሲሆን ከአንድ ቤት በላይ የከፋ ጉዳት አላደረሰም ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
#ለጥንቃቄ🚨
“ በጀኔተር ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ የ1 ሰው ሕይወት አልፏል ” - አቶ ንጋቱ ማሞ
ትላንት ምሽት 3:03 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ማርያም ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በእሳት አደጋ የ1 ሰው ሕይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና ሥራ አመራር ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው አቶ ንጋቱ ማሞ በሰጡት ቃል፣ “ ኤሌክትሪክ በመቋረጡ ጀነሬተር ለማስነሳት ነዳጅ በመጨመር ላይ የነበረ የ26 ዓመት የሆቴል ሠራተኛ በጀነሬተሩ ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ ወዲያው ሕይወቱ አልፏል ” ብለዋል።
“ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በስፍራው ፈጥነው ቢደርሱም በጀነሬተሩ ላይ በተፈጠረው ከፍተኛ እሳት አስቀድሞ ሕይወቱ አልፏል ” ነው ያሉት።
አቶ ንጋቱ፣ “ በጄኔሬተር የነዳጅ ታንከር ውስጥ ነዳጅ ከተጨመረ በኋላ #ቫልቩ በአግባቡ መዘጋቱን ማረጋገጥ ፣ እንዲሁም ጄነሬተሩ አስቀድሞ አገልግሎት ሲሰጥ ከቆየና ግለት ካለ ነዳጅ ከመጨመር መቆጠብ ያስፈልጋል ” ሲሉ አስገንዝበዋል።
በሌላ በኩል ፥ የበዓል ስራዎች እንቅስቃሴዎች አሁንም ድረስ ያልጠተናቀቁ በመሆኑ ህብረተሰቡ ከኮሚሽን መስሪያ ቤቱ እየተላለፉ ያሉ የጥንቃቄ መልዕክቶች እንዲተገብር አሳስበዋል።
የእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ሲያጋጥሙ ፣ እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት ማህበረሰቡ በኮሚሽኑ ስልክ #በ939 ላይ ፈጥኖ ደውሎ እንዲያሳውቅ ጥሪ አቅርበዋል።
በተጨማሪ መረጃ ፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በስሊንደር ፍንዳታ ምክንያት የ1 ሰው ህይወት ማለፉን ገልጿል።
የድሮው ቄራ አካባቢ ትላንት ቀን 9:30 በአነስተኛ መጠጥ ቤት ውስጥ ድስት ተጥዶበት በነበረ ስሊንደር ላይ በተፈጠረው ፍንዳታ ዕድሜው 30 ዓመት የሚገመት 1 ሰው ህይወቱ ያለፈ ሲሆን በ3 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ህክምና ተወስደዋል።
ፖሊስ በበዓል ወቅት የምንጠቀማቸውን ምግቦች ስናበስል #ከሲልንደር_አጠቃቀም ጋር በተያያዘ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል።
#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba
@tikvahethiopia
#ትንሣኤሎተሪ
የ2016 የትንሳኤ ሎተሪ ዕጣ የወጣ ሲሆን 10 ሚሊዮን ብር ባለዕድለኛ የሚያደርገው የአንደኛ ዕጣ ቁጥር 1407747 ሆኖ ወጥቷል።
5 ሚሊዮን ብር የሚያስገኘው የሁለተኛው የዕጣ ቁጥር ደግሞ 0179265 ሆኖ ወጥቷል።
የ2.5 ሚሊዮን ብሩ የሶስተኛው ዕጣ ቁጥር 2160591 እንዲሁም የ1.5 ሚሊዮን ብር የ4ኛ ዕጣ ቁጥር 0165786 ሆኖ ወጥቷል።
(ተጨማሪ ዝርዝር የዕጣ ማውጫው ከላይ ተያይዟል)
#NationalLottery
@tikvahethiopia