" ... ወንዶች በትምህርት ሰአት ሁሉ የቀን ስራ በመስራት ርሀባቸውን ለማስታገስ በጥረት ላይ ሲሆኑ ሴቶችም ላልተገባ ችግር ተጋልጠዉ መማር አልቻሉም " - የደቡብ ኢትዮጵያ መምህራን ማህበር
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር አደረኩት ባለው ማጣራት በክልሉ ውስጥ ባሉት የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች ለመማር የተመደቡ ዕጩ መምህራን ሁሉም በሚባል መልኩ ትምህርታቸውን በፋይናንስ እጥረት በአግባቡ እየተማሩ አይደለም።
ዕጩ መምህራን በ2015 ዓ/ም ወደ ኮሌጆች ሲገቡ ከመንግስት የሚሰጣቸዉ 450 ብር በቂ እንዳልሆነ እየታወቀ ቢጀመርም እስካሁን ሊስተካከልላቸው አልቻለም።
ይህን ችግር በተመለከተ ኮሌጆቹ በቦርድ ደረጃ ያመኑበት ከመሆኑ ባለፈ ማስተካከያ እንዲደረግ ለክልሉ መንግስት ጥያቄ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።
ይሁንና የክልሉ መንግስት ለጥያቄው ተገቢ ምላሽ ባለመስጠቱ በክልሉ በተለያዬ ደረጃ የመምህራንነት ስልጠና ለመዉሰድ ወደኮሌጆች ገብተዉ በትምህርት ላይ የሚገኙ በርካታ ዕጩ መምህራን በችግር እየተጠበሱና ትምህርታቸዉን ትተዉ ወደመጡበት እየተመለሱ መሆናቸዉን የክልሉ መምህራን ማህበር አውቂያለሁ ብሏል።
የመምህራን ማህበሩ ፕሬዝደንት አቶ አማኑኤል ጳዉሎስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ፤ " ከነዚህ ተማሪዎች መካከል አብዛኛዉ ወንዶች በትምህርት ሰአት ሁሉ የቀን ስራ በመስራት ርሀባቸውን ለማስታገስ በጥረት ላይ ሲሆኑ ሴቶችም ላልተገባ ችግር ተጋልጠዉ መማር አልቻሉም " ብለዋል።
" በመሆኑም ተማሪዎች በ450 ብር በልተዉና ጠጥተዉ እንዲሁም ሌሎች ወጭዎችን ሸፍነዉ መማር አይችሉምና የክልሉ መንግስት በተለይም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ባስቸኳይ ችግራቸዉን ይፈታላቸዉ ዘንድ ማህበሩ በደብዳቤ ሁሉ ጠይቋል " ሲሉ ተናግረዋል።
ጉዳዩን በተመለከተ ስለምን ተማሪዎቹ በዚህ ልክ እስኪሰቃዩ ድረስ መፍትሄ አልተፈለገም ? በማለት ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነዉ ጥረት አልተሳካም።
ምላሽ ሲሰጥ ምላሹን የምናካትት ይሆናል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
#DStvEthiopia
🔥 አርሰናሎች የ20 ዓመት የዋንጫ ጥማታቸውን ሊቆርጡ መድፋቸውን እያገላበጡ ወደ የፕሪሚየር ሊግ አፋፉ ተቃርበዋል።
አፋፉ ላይ ደግሞ ቀያዮቹ ቆመዋል!
⚽️ እሁድ ከምሽቱ 12፡30 ማንችስተር ዩናይትድ ከአርሰናል በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ብቻ!
ይህ ታሪካዊ ፉክክር እንዳያመልጥዎ…
👉 ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ። ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ይከታተሉ!
የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2
#PremierLeagueOnDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
#ብሔራዊፈተና
ከትግራይ ክልል ውጭ በሁሉም ክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች ላሉ ተፈታኞች በወረቀት እና በበይነ መረብ (ኦንላይን) የሚሰጠው የፈተና መርሃ ግብር ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia
#ምርጥ_ዕቃ
የእነዚህን እና ሌሎች ምርጥ የቤት ዕቃዎቻችንን ዋጋ እና መረጃ በቴሌግራምዎ ለማየት ይሄንን 👉 t.me/MerttEka ይጫኑት።
አድራሻችን ፦ አዲስ አበባ ፤መገናኛ ፤ዘፍመሽ ግራንድ ሞል፤ 3ተኛ ፎቅ፤ ከሊፍት ሲወርዱ ወደ ቀኝ ታጥፈው ቀጥታ ሱቅ ቁጥር 376
#Mekelle
በመቐለ ከተማ መምህራን ለመኖሪያ መስሪያ በእጣ መሬት ተሰጣቸው።
ለመኖሪያ በእጣ በተሰጠው መሬት በ19 ማህበራት የታቀፉ ከ400 በላይ የመቐለ መምህራን ተጠቃሚ እንደሆኑ ተነግሯል።
ዛሬ የተካሄደው የመምህራን የመኖሪያ መሬት በእጣ የማስተላለፍ ስነ-ሰርዓት ሂደት ከጦርነት በፊት የተጀመረውን ያሰቀጠለ ነው።
ከጦርነቱ በፊት የትግራይ ክልል መምህራን ለመኖሪያ መስሪያ የሚሆን በዕጣ የተሰጣቸው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በተለይ በመቐለ የዕድሉ ተጠቃሚ ሳይሆኑ የቆዩት በ19 ማህበራት የታቀፉ ከ400 በላይ መምህራን ዛሬ ተጠቃሚ ሆነዋል።
መምህራን ደመወዝ ጨምሮ ሌሎች የሚጠይቁዋቸው ጥያቄዎች በየደረጃው መመለስ እንዳለበት ይህም ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
የትግራይ መምህራን ፦
° በጦርነቱ ምክንያት ያልተሰጣቸው ውዙፍ 17 ወራት ደመወዝ እንዲከፈላቸው ፣
° የመኪና የሰርቪስ አገልግሎትም ጨምሮ ሌሎችም ጥያቄዎች ለጊዚያዊ አስተዳደሩ ደጋግመው ጠይቀው አጥጋቢ መልስ ማግኘት እንዳልቻሉ የሚመለከቱ ተከታታይ ዘገባዎች ስናቀርብ መቆያታችን ይታወሳል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
#Adigrat
በጦርነቱ ምክንያት ከ70 ከመቶ በላይ ውድመት የደረሰበት " የዓዲግራት አዲስ የመድሃኒት ፋብሪካ " አግግሞ እስከ 110 የሚደርሱ የተለያዩ በሽታዎች የሚፈውሱ መድሃኒቶች በማምረት ላይ እንደሚገኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የፋብሪካው ዋና ስራ አስፈፃሚ ሃይለ ገ/ሚካኤል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ የመድሃኒት ፋብሪካው ጦርነቱ በጀመረ ማግስት በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ውሎ ነበር።
በእነዚህ የኤርትራ ወታደሮችም 7 ሰራተኞቹ በሞት መነጠቁንና በርካቶችም መቁሰላቸውን አስታውሰዋል፡፡
የመድሃኒት ፋብሪካው ከህዳር እስከ የካቲት 2013 ዓ.ም ባሉት ሶስት ወራት የኤርትራ ወታደሮች እንደ #ካምፕ ሲገለገሉበት እንደነበር ገልጸዋል።
" ወታደሮቹ ማሽነሪዎች ጨምሮ የተለያዩ የፅህፈት ቤት እቃዎች ዘርፈው መውሰዳቸውንና መውሰድ ያልቻሉት ፈንጅ በማጥመድ አጋይቶውታል " ብለዋል፡፡
ፋብሪካው ሚያዝያ ወር 2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በተነፃፃሪ የጥበቃ ከለላ ስር የተወሰኑ የጥገና ስራዎች ጀምሮ ነበር ሲሉ ገልጸዋል።
ነገር ግን በውቅቱ በነበረው የተወሳሰበ ውግያና የፀጥታ መድፍረስ ሳይሳካለት ቀርቶ 1500 ቀዋሚና ጊዚያዊ ሰራተኞቹ ለመበተን መገደዱን አመልክተዋል።
ፋብሪካው ከጥቅምት 2015 የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ማግስት የጥገና ስራዎች በማካሄድ ከፌደራል የመድሃኒትና የምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን መልሶ ለማምረት የሚያስችለው የብቃት ማረጋገጫ ማግኘቱ አቶ ሃይለ ገልፀዋል፡፡
ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-05-11
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ መጪውን የዳግማ ትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን የሚያስገኝ የጥያቄና መልስ ውድድር ይዞላችሁ መጥቷል፡፡
እርስዎም የሽልማቱ ተሳታፊ ለመሆን ከታች ያሉትን የባንኩን ይፋዊ የቴሌግራም እና የፌስቡክ ገፆች በመቀላቀል እና ጥያቄውን ቀድመው በመመለስ ሽልማቶችን የራስዎ ያድርጉl
ጥያቄው የሚካሄዳው እሁድ ግንቦት 4 ቀን 2016 ከቀኑ 8:00 ሰዓት ሲሆን ፤ ጥያቄውን ለመለሱ 3 ተሳታፊዎች ሊሸልም ዝግጅቱን ጨርሷል።
ከአንድ እስከ ሦስት ለወጡ ተወዳዳሪዎች የብር ሽልማቶን አዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል። እርስዎም ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት የውድድሩ ተሳታፊ ይሁኑ!!
ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!
[Telegram] (/channel/LionBankSC) [Facebook] (https://www.facebook.com/LionBankSC)
#LIB #lioninternationalbank #anbesabank #keytosuccess
#AddisAbaba
በማህበራዊ ሚዲያ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ብቻ ከማህበረሰቡ መልካም ባህልና ወግ የተቃረኑ አፀያፊ የፈጠራ ታሪኮችን / ወሬዎችን እየፈበረኩ በማሰራጨት የህዝብን ደህንነት ስጋት ላይ የሚጥሉ #ዩቲዩበሮችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 " አማረ እና ቤተሰቦቹ " በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ ተከራይተው የተለያዩ የዩቲዩብ ገፆችን በመክፈት የማህበረሰቡን ሥነ ልቦና የሚጎዱ የፈጠራ ታሪክ በማሰራጨት የተጠረጠሩ 6 ግለሰቦች በህዝብ ጥቆማና በፖሊስ ክትትል ተይዘዋል።
አሁን ላይ የካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ምርመራ እየተጣራ ይገኛል፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል መቅደስ መብራት መኮንን የተባለችው ግለሰብ ፦
- ሮሄ፣
- ልዩነት፣
- ጣዕም፣
- አዲስ አለም፣
- ዘይቤ፣
- ህይወት፣
- እይታ፣ እና ዩኒት ህይወት የተባሉ የዩቲዩብ ገፆችን በመክፈት በስራ አስኪያጅነት ስትመራ የነበረች ናት ተብሏል፡፡
ብሩክ ወርቅነህ ጌታሰው የተባለ ግለሰብ ደግሞ ገፆቹን በምክትል ስራ አስኪያጅነት እና በአስተባባሪነት ሲመራ ነበር።
ናትናኤል አበራ በቀለ፣ እየሩሳሌም አስማረ ምህረት እና ምህረት ያሲን ቲጋ የተባሉት ግለሰቦች ደግሞ በፕሮግራም አቅራቢነት እንዲሁም ናትናኤል ዮሃንስ አሸነፊ በካሜራ ባለሙያነት ሲሰሩ የነበሩ ናቸው።
ከላይ ከተጠቀሱት 8 የዩቲዩብ ገፆች በተጨማሪ #ክህሎት እና #ሲንግል የተባሉ ሌሎች ሁለት የዩቲዩብ ገፆችም በዚያው ህንፃ ላይ የፈጠራ ወሬ ሲፈበርኩ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡
ፖሊስ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ እና ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ ተከራይተው በሚሰሩበት ህንፃ 8ኛ እና 13ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮአቸው ላይ በህግ አግባብ ባደረገው ብርበራ የፈጠራ ወሬ ለመቅረፅ እና ለማሰራጨት የሚጠቀሙባቸው የኤሌክትሮኒክ እቃዎች ተይዘዋል፡፡
ግለሰቦቹ መረጃውን ለማሰራጨት የሚያስችል ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የህጋዊነት ማረጋገጫ ሆነ ፈቃድ እንደሌላቸው በምርመራ ሂደት ተረጋግጧል።
እነዚህ ተጠርጣሪዎች ሃሰተኛና የፈጠራ ወሬዎቹን የሚሰራጩት ታሪኩን ለሚተውኑላቸው ግለሰቦች #ገንዘብ_በመክፈል ሲሆን በወቅቱ ጉዳዩን በጥልቀት ሳይረዱ እና መረጃው ሳይኖራቸው የማያውቁትን የፈጠራ ታሪክ ሊሰሩ ለቀረፃ ስራ የተጠሩ ሌሎች 3 ሰዎችን ፖሊስ አግኝቷል፡፡
መሰል የውሽት ታሪኮችን ቀልብ በሚስብ መልኩ እያቀናበሩ በማሰራጨት በህብረተሰቡ ላይ መደናገርን የሚፈጥሩ ሌሎች ግለሰቦችም ተለይተው የታወቁ እና በቁጥጥር ስር ለማዋል የክትትል ስራው ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡
#AddisAbabaPolice
@tikvahethiopia
“ መምህራን እየቆዘሙ፣ ቅሬታ ተሸክመው ክፍል ውስጥ ገብተው ትውልድን ለመቅረጽ ይቸገራሉ ” - ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር)
በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ለሚነሱ ደመወዝን መሠረት ያደረጉ ቅሬታዎች ትልቁ መንስኤ የመልካም አስተዳደር ችግር መሆኑን የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።
የማኅበሩ ፕሬዜዳንት ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
ምን አሉ ?
Q. በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ መምህራን የሚያነሷቸው ቅሬታዎች በዚህ ዓመት ብቻ የተስተዋሉ ሳይሆን ሰንበትበት ያሉ ቢሆኑም መፍትሄ ሳይሰጣቸው አሁንም እንደቀጠሉ ናቸው። ለምን ችግሩን መቅረፍ አልተቻለም ?
ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) ፦
“ ልክ ነው። የመልካም አስተዳደር ችግር ነው። ይሄ የመልካም አስተዳደር ችግር አገራዊ እየሆነ ነው። መምህራንም የዚህ ገፈጥ ቀማሽ ሆነዋል። የግምገማ ቼክ ሊስት መደረግ አለበት ብለን ከሚመለከተው ጋር እያወራን ነው።
በተለይ መምህራን ላይ የሚከሰተው ችግር ከትውልድ ጋር የተያያዘ ነው። መምህራን እየቆዘሙ፣ እያዘኑ፣ ቅሬታ ተሸክመው ክፍል ውስጥ ገብተው ትውልድን ለመቅረጽ ይቸገራሉ። ችግሩ በፍጥነት መታረም አለበት። ”
Q. “ የመልካም አስተዳደር ችግር ” ሲሉ ምን ለማለት ነው ? ግልጽ ቢያደርጉት ?
ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) ፦
“ አንዱ ክፍያ ነው። መቼም መምህራን የመንግስት ሠራተኞች ናቸው። የወር ደመወዝ በጊዜ ማግኘት መቻል አለባቸው።
ለልማት ሲባል መምህራንን #ሳያሳምኑ ደመወዝ የመቁረጥ አይነት ቅሬታዎች አልፈው አልፈው ይመጣሉ። ከአብዛኞዎቹ በጥቂቱ እነዚህ ናቸው።
እነዚህን ችግሮች በመሠረታዊነት መፈታት ቢቻል ሌሎቹ ደግሞ በሂደት ይፈታሉ። ”
Q. ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ተፈናቃይ መምህራንን በተመለከተ ተቋምዎ ያለው መረጃ ምንድን ነው ? ችግሩን ለመቅረፍስ ምን እየተሰራ ነው ? ስንት መምህራን እንደተፈናቀሉ ተቋምዎ ያውቃል ?
ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) ፦
“ በጦርነት ምክንያት የወደሙ ትምህርት ቤቶች አሉ። በዚህም የተፈናቀሉ ተማሪዎችና መምህራን ይኖራሉ።
በተቻለ መጠን ሰላም ወርዶ ወደ ቦታቸው ተመልሰው ስራቸውን እንዲሰሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እያደረግን ነው። ”
ፕሬዝዳንቱ ከጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ የሰጡትን ማብራሪያ ያንብቡ 👇 https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-05-10
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ምርጥ_ዕቃ
የእነዚህን እና ሌሎች ምርጥ የቤት ዕቃዎቻችንን ዋጋ እና መረጃ በቴሌግራምዎ ለማየት ይሄንን 👉 t.me/MerttEka ይጫኑት።
አድራሻችን ፦ አዲስ አበባ ፤መገናኛ ፤ዘፍመሽ ግራንድ ሞል፤ 3ተኛ ፎቅ፤ ከሊፍት ሲወርዱ ወደ ቀኝ ታጥፈው ቀጥታ ሱቅ ቁጥር 376
" የተሻለ ህይወት ፍለጋ አህጉሩን ጥለው የተሰደዱ አፍሪካውያን የጤና ባለሞያዎች ቁጥር የሚስደነግጥ ነው " - ካሉምቢ ሻንጉላ
አፍሪካ የጤና ባለሙያዎች እጥረት እንዳለባት የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።
ድርጅቱ በናሚቢያ ዋና ከተማ ፤ #ዊንድሆክ በዚህ ሳምንት እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ የጤና ባለሞያዎች ፎረም ላይ ነው ይህን ያሳወቀው።
ፎረሙ ላይ የናሚቢያ የጤናና የማህበራዊ አገልግሎት ሚኒስትር ካሉምቢ ሻንጉላ ፥ " #አፍሪካ ያጋጠማት የጤና ባለሙያዎች እጥረት አህጉሪቱ እ.አ.አ በ2030 ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ለማግኘት የያዘችውን እቅድ እንዳታሳካ እንቅፋት ይሆናል " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
" የተሻለ ህይወት ፍለጋ አህጉሩን ጥለው የተሰደዱ አፍሪካውያን ቁጥር #የሚስደነግጥ_ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
ይህን ጉዳይ የአፍሪካ መንግስታትም ሆኑ ታሪካዊ እና ወቅታዊ ሁኔታዎች ተለውጠው ማየት የሚሹ በሙሉ ቅድሚያ ሰጥተው ሊፈቱት የሚገባ ጉዳይ እንደሆነ አስረድተዋል።
የአፍሪካ በሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል ዳይሬክተር ጀነራል ጂን ካሳያ እንዳስታወቁት፣ እ.አ.አ በ2030 ለመድረስ የታቀደውን ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ለማሳካት አፍሪካ ተጨማሪ 1.8 ሚሊየን የጤና ሰራተኞች ያስፈልጓታል።
በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ 1.55 የጤና ባለሙያዎች ለአንድ ሺህ ሰዎች አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆን ፣ ይህም ለ1 ሺህ ሰዎች 4.55 የጤና ባለሙያዎች እንደሚያስፈልግ የዓለም ጤና ድርጅት ካስቀመጠው ገደብ በታች ነው።
እ.አ.አ በ2023 ብቻ አፍሪካ " 166 ወረርሽኞች "ን መመዝገቧን ያመለከቱት ካሳያ ፤ የአፍሪካ ህብረት አባል አገራት እ.አ.አ በ2030 ሁለት ሚሊየን የቋማዊ የማህበረሰብ የጤና ሠራተኞችን እንዲመለምሉ እንዲያሰለጥኑና ወደ ስራ እንዲያሰማሩ የተወሰነውን ውሳኔ ለማሳካት በጣም ወደኃላ መቅረታቸውንም አመልክተዋል። #ቪኦኤ
@tikvahethiopia
" 41 የጸጥታ አካላት ከኃላፊነታቸው #ተነስተዋል " - አቶ ሀሚድ አህመድ
ከሰሞኑን በሲዳማ ክልል ፤ የጸጥታ አካላት የግምገማ መድረክ ሲካሄድ መሰንበቱ ተነግሯል።
ይህን ተከትሎ " ለህዝብ ሳይሆን ለራሳቸዉ ቆመዋል " የተባሉ አመራሮች ከስልጣን መነሳታቸው ተገልጿል።
የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ አህመድ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " የተጣለባቸውን የስራ ኃላፊነት በአግባቡ ያልተወጡ በተለይ ህዝብን #ሲያማርሩ እና #ሲያሰቃዩ እንዲሁም የሀገርን ሀብት ሲዘርፉ የነበሩ 41 የፀጥታ አካላት ተነስተዋል " ብለዋል።
በቀጣይ ለፍርድ እንደሚቀርቡ ገልጸዋል።
#በታችኛው_እርከን ላይ ያሉ የጸጥታ አመራሮች ላይም አስተዳደራዊ እርምጃ ይቀጥላል ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ 291 ከፍተኛ አመራሮች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸዉ ገልጸዋል።
ለመሆኑ እነማን ናቸው ከኃላፊነት የተነሱት ? በማለት ጥያቄ ያቀረብንላቸዉ ዳይሬክተሩ ፤ " አሁን ላይ መግለጽ የምችለው ብዛታቸዉን ብቻ ነው። " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
" በቀጣይ ቀናት ማንነታቸውን እናሳውቃችኋለን " ሲሉ ገልጸዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
ለ Big 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ ይዘጋጁ! በሃገሪቱ ግንባታ ዘርፍ ትልቁ ዝግጅት፤ ከግንቦት 22 እስከ ግንቦት 24፣ 2016 በሚሊኒየም አዳራሽ ይዘጋጃል።
- ከ 150 በላይ ከሚሆኑ ተሳታፊዎች የሚቀርቡ አዳዲስ ምርቶችንና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ይጎብኙ!
- ከ 15 በላይ ሃገራት ከሚመጡ ተሳታፊዎች ጋር ይገናኙ!
- በግንባታው ዘርፍ ከበቁ 9000 ባለሙያዎች ጋር ትስስር ይፍጠሩ!
- ከ 20 በላይ በሚሆኑ፣ በዋጋ በማይተመኑ መረጃ ሰጪ መድረኮች ላይ የመሳተፍና የ Continuous professional development ነጥብዎን የማሳደግ ዕድሉን ያግኙ!
በሁነቱ ላይ ልናገኝዎ በጉጉት እንጠብቃልን!
በነጻ ለመጎብኘት አሁኑኑ ይመዝገቡ : https://bit.ly/3UsrL5I
'ቲክቶክ' ን ሙሉ በሙሉ / በከፊል ያገዱ ሀገራት የትኞቹ ናቸው ?
1ኛ. ህንድ
ቲክቶክን ያገደችው በ2020 ላይ ነው። በድንበር አካባቢ ከቻይና ጋር የተፈጠረው #ግጭትን ተከትሎ ነው ለደህንነት በሚል ቲክቶክን እና ሌሎች ከቻይና ጋር የተገናኙ መተገበሪያዎችን ያገደችው።
በወቅቱ በሀገሪቱ 200 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ነበሩ።
2. አፍጋኒስታን
ቲክቶክን በ2022 ያገደች ሲሆን ምክንያቷ ደግሞ ወጣቱ ትውልድ በተሳሳተ አቅጣጫ እንዳይሄድ ለመከላከል ነበር።
3. አውስትራሊያ
በፌዴራል መንግሥት ማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ ማሳሪያ ላይ እንዳይሰራ ተደርጓል። ከደህንነት ጋር በተያያዘ
4. ቤልጂየም
ከደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ ቲክቶክን በፌደራል የህዝብ አገልግሎት መሳሪያዎች ላይ እንዳይሰራ ጊዜያዊ እገዳ ጥላለች።
5. ካናዳ
ከደህንነት ጋር በተያያዘ የፌዴራል መንግሥት መሳሪያዎች ላይ ታግዷል።
6. ዴንማርክ
የሀገር መከላከያው ሚኒስቴር ማንኛውም ሰራተኛ በስራ ስልኩ ቲክቶክ እንዳይጠቀመ ያገደ ሲሆን ሁሉም ሰራተኛ ጭኖት የነበረውን መተግበሪያ እንዲያጠፋ አስደርጓል።
7. የአውሮፓ ህብረት
ሰራተኞች ሚጠቀሙበት መሳሪያ ላይ ታግዷል። የፓርላማው ህግ አውጭዎች እና ሰራተኞችም ከኤሌክትሮኒክ መሳሪያቸው ላይ እንዲያስወግዱ ተደርጓል።
8. ፈረንሳይ
ከደህንነት ጋር በተያያዘ ቲክቶክና ሌሎች እንደ X ፣ ኢንስታግራም ያሉ መተግበሪያዎችን የመንግስት ሰራተኞች ስልካቸው ላይ ለ 'መዝናኛ' በሚል እንዳይጠቀሙ ታግደዋል።
9. ላቲቪያ
ከደህንነት ጋር ተያይዞ በሁሉም የላቲቪያ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት ኤሌክትሮኒክስ እንዳይሰራ ታግዷል።
10. ኔዘርላንድስ
ማዕከላዊ መንግሥት ቲክቶክ ጨምሮ ሌሎችንም መተግበሪያዎች ከደህንነት ጋር በተያያዘ ከሰራተኞች ስልክ ላይ እንዲታገዱ አድርጓል።
11. ኔፓል
ማህበራዊ መስተጋብር በመሸርሸር፣ ወጣቶችን ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ በመውሰድ በሚል ሙሉ በሙሉ ነው ያገደችው።
12. ኒውዚለንድ
የፓርላማው ህግ አውጪዎችና ሰራተኞች በሙሉ ስልካቸው ላይ ቲክቶክ እንዳይኖር ታግደዋል፤ ይህ ከደህንነት ጋር በተያያዘ ነው።
13. ኖርዌይ
ከመላው የኖርዌይ ፓርላማ የስራ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ላይ እንዲታገድ ተደርጓል። የመንግስት ሰራተኞች ስልካቸው ላይ እንዳይጭኑ ታዟል።
14. ፓኪስታን
ከ2020 ጀምሮ ቢያንስ ለአራት ጊዜ በጊዜያዊነት አግዳለች ይህም ከስነ ምግባር ያፈነገጠ ይዘትን ያስተዋውቃል በሚል ነው።
15. ሶማሊያ
መንግሥት ቲክቶክ፣ ቴሌግራምና 1 የቁማር ድረገጽ እንዳይሰሩ እንዲያደርጉ አዟል። መተግበሪያዎቹ የጽንፈኝነት መፈንጫ ሆነዋል በሚል ነው።
16. ታይዋን
ከደህንነት ጋር ተያይዞ ከሁሉም መንግሥታዊ መሳሪያዎች ከስልክ ፣ ታብሌት ፣ ኮምፒዩተር ፣ እንዳይሰራ ተደርጓል።
17. ዩናይትድ ኪንግደም
የመንግስት ሚኒስትሮችና የመንግስት ሰራተኞች ከሚጠቀሙባቸው የሞባይል ስልኮች እንዳይሰራ ታግዷል። ፓርላማው ከኦፊሴላዊ መሳሪያዎችና ኔትዎትክ ላይ አግዷል። ይህ ከደህንነት ጥንቃቄ ጋር በተያያዘ ነው።
18. ኪርጊስታን
የልጆች አእምሯዊ፣ መንፈሳዊ እና ሥነምግባራዊ እድገትን ለመጠበቅ በህግ የተዘረዘሩ ህጋዊ መስፈርቶችን ማክበር አልቻለም በሚል ቲክቶክን በሙሉ አግዳለች።
19. አሜሪካ
ከደህንነት ጋር በተያያዘ ከፌደራል ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች እንዲታገድ ተድርጓል። ከ50 ግዛቶች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት መተግበሪያውን ከይፋዊ የመንግስት መሳሪያዎች ላይ አግደዋል።
አሁን ሙሉ በሙሉ ልታግድ ጫፍ ደርሳለች።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፤ መረጃውን ያሰባሰበው ከዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ነው።
@tikvahethiopia
#RosewoodFurniture
ጠበብ ላሉ መኝታ ክፍሎች ቆንጆ ቦታ አጠቃቀም ያለው አልጋ እና ቁምሳጥን።
✔️ በአርኪቴክት ባለሞያ ለክተን እና ዲዛይን አደርገን
✔️ካሉበት አድራሻ ዴሊቨር እናደርጋለን
ሮዝዉድ ፈርኒቸር ፦ 0905848586
አድራሻ፦ 📍4ኪሎ ኣምባሳደር ሞል 2ኛ ፎቅ
📍 እንቁላል ፋብሪካ ሩፋኤል
ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👇
/channel/R0seWood
#AddisAbaba
ከላይ ባለው ፎቶ የምትመለከቱት ትላንት ለሊት 6:50 በአዲስ አበባ የረር ጎሮ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል አጠገብ የተከሰተ የእሳት አደጋ ያደረሰው ከፍተኛ ውድመት ነው።
እሳቱ ከፍተኛ የነበረ ሲሆን የህዝብ ርብርብ ተደርጎ ፣ በ12 የእሳት አደጋ መኪኖች አገልግሎት እና በጸጥታ አካላት ተባባሪነት ከሌሊቱ 9:00 ላይ መቆጣጠር ተችሏል።
ርብርቡ እሳቱ ወደ ቤተክርስቲያን እንዳይዛመት አድርጓል።
በሌሊቱ አደጋ በቤተክርስቲያን ዙሪያ የነበሩ 13 የንግድ ሱቆችና ሙሉ በሙሉ ወድመዋል።
በጋራዡ ውስጥ የነበሩ 5 ተሽከርካሪዎች በተመሳሳይ ሙሉ ሙሉ ሲወድሙ በጋራዡ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።
በጋራዡ የነበሩ 15 የሆኑ ተሽከርካሪዎችን ማዳን ተችሏል።
በአደጋዉ ሰው ላይ ምንም ጉዳት አልደረሰም።
Photo Credit ፦ Media of Addis Ababa Diocese
@tikvahethiopia
#Tigray #Exam
የትግራይ ክልል በቀድሞ ስርዓተ ትምህርት የተማሩና በ2013 እና በ2014 የትምህርት ዘመን መፈተን የነበረባቸው ተፈታኞ በ2016 ትምህርት ዘመን በወረቀትና በበይነ መረብ የሚፈተኑበት መርሃ ግብር ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia
መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ያሥገነባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዛሬ ለባለ ዕድለኞች በዕጣ አስተላልፏል።
በዕጣ የተላለፉት አጠቃላይ 1,336 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፦
- ባለ 4 መኝታ
- ባለ 3 መኝታ
- ባለ 2 መኝታ
- ባለ 1 መኝታ ናቸው።
የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ለሠራዊት አባላት እና ቋሚ ለሆኑ ስቪል ሰራተኞች ነው የተላለፉት።
(የቤት ባለዕድለኞች ስም ዝርዝር ከላይ በPDF ተያይዟል)
#FDREDefenseForce
@tikvahethiopia
#AddisAbaba
“ ኖህ ሪልስቴስት እየሰራው ያለው ህንፃ ላይ የወደቀ ብረት ነው የገደለው ” - ኮማንደር ማርቆስ
ኢዩኤል ታዬወርቅ የተባለ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ቤተሰብን ለመጠየቅ በመጣበት ከህንፃ ላይ በወደቀ ብረት በድንገት ሕይወቱ ማለፉ በማኀበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ ተስተውሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞን ለአደጋው ምላሽ እንዲሰጡ የጠየቀ ሲሆን፣ “ እኛ አገልግሎት አልሰጠንም ” ብለዋል።
ሆኖም፣ ተመሳሳይ ጥያቄ የቀረበላቸው የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ምላሽ ሰጥተዋል።
ኮማንደር በሰጡት ምላሽ፣ “ ኖህ ሪልስቴስት እየሰራው ያለው ህንፃ ላይ የወደቀ ብረት ነው የገደለው። 4 ሰዓት ላይ ነው የሞተው በሚያዚያ 29 ቀን 2016 ዓ/ም ” ብለዋል።
“ ሟቹ ኢዩኤል የሚባል ልጅ ነው። እድሜው 23 ነው። የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረ እንደሆነ ነው የተነገረኝ” ያሉት ኮማንደር ማርቆስ፣ አደጋው የደረሰው “የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
የጎንደር ዩኒቨርስቲ በበኩሉ ሟቹ የኪነህንፃ (Architecture) #ተመራቂ ተማሪ እነደነበር ባሰራጨው የሀዘን መግለጫ አስታውቆ፣ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል።
“ ተማሪ ኢዩኤል ታዬወርቅ የፋሲካ በዓልን ከቤተሰቦቹ ጋር በአዲስ አበባ ለማክበር የሄደ ሲሆን፣ በማግስቱ ከታናሽ ወንድሙ ጋር እየተንቀሳቀሱ ባሉበት ኬንያ ኢምባሲ አካባቢ እየተሰራ ከሚገኝ ከፍተኛ ፎቅ በወደቀ ብረት በመጎዳቱ ሚያዚያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም በለጋ እድሜው ህይወቱ አልፏል ” ብሏል ዩኒቨርሲቲው።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ያስገነባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዛሬ ለባለ ዕድለኞች በእጣ ያስተላልፋል።
ፋውንዴሽኑ ከዚህ በፊት ተመዝግበውና ቆጥበው መመዘኛውን አሟልተው ለተገኙ የሠራዊት አባላትና ስቪል ሠራተኞች 1236 ቤቶችን በእጣ አስተለልፎ ነበር።
ዛሬ ደግሞ 1336 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በእጣ ያስተላልፋል ተብሏል።
#FDREDefenseForce
@tikvahethiopia
#RoseWood
የቤትዎን ኪችን ካቢኔት እና ቁምሳጥን በአጭር ጊዜ ገጥመን እናስረክባለን 🙌
ሮዝዉድ ፈርኒቸር 📲 0905848586
ኣድራሻ : 📍4ኪሎ ኣምባሳደር ሞል 2ኛ ፎቅ
📍 እንቁላል ፋብሪካ ሩፋኤል
Showroom Location 👇
https://goo.gl/maps/X6Q2exa7dfvjBPvWA
ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👇
/channel/R0seWood
ስለብፁዕነታቸው የሚሰራጨው መረጃ ፍጹም ሐሰተኛ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አሳወቀች።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም ወደ #ደቡብ_አፍሪካ ሊያደርጉ የነበረውን ጉዞ መሰረዛቸውን ተከትሎ #የሐሰት_ዜና በመሰራጨት ላይ እንደሚገኝ ቤተክርስቲያኗ አሳውቃለች።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፦
- በደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ጆሐንስበርግ መንበረ ጵጵስና ጽርሐ ጽዮን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተበት ፳፭ኛ ዓመት በዓል ላይ ለመገኘት፣
- ቅዳሴ ቤቱን ለማክበር
- በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን ለመባረክ
- ምዕመናንን ለማስተማር ዛሬ ከቅዱስነታቸው ጋር ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ መርሐ ግብር ይዘው ነበር።
ይሁን እንጂ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ካለባቸው ተደራራቢና አስቸኳይ ሥራዎች አንጻር ለ10 ቀናት ሙሉ ፦
° ከጽ/ቤታቸው ርቀው መቆየት በጠቅላይ ጽ/ቤቱ የዕለት ተዕለት ሥራዎች ላይ ክፍተት እንዳይፈጠር በመስጋታቸው
° ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊውና ምክትል ሥራ አስኪያጁ በሌሉበት ሁኔታ ለበርካታ ቀናት ከጠ/ጽሕፈቱ ርቀው ከተጓዙ ሥራዎች ስለሚበደሉ ቀደም ሲል ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊያደርጉት የነበረውን ሐዋርያዊ ጉዞ ከቅዱስነታቸው ጋር በጥሞና በመወያየት #ለመሰረዝ መገደዳቸው ተነግሯል።
እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ በአንዳንድ ማኅበራዊ ገጾች ፈጽሞ እውነትነት በሌለው መንገድ " ብፁዕነታቸው ወደ ኤርፖርት እንዳይሔዱ እንደተከለከሉ እንዲሁም ፓስፖርታቸው እንደተያዘ " በማስመሰል የሚሰራጨው ዜና ፍፁም መሰረተ ቢስና የሐሰት ዜና መሆኑን ቤተክርስቲያን አሳውቃለች።
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ከታቀደው ሐዋርያዊ ጉዞ ለመቅረት የተገደዱት በተደራራቢ ሥራ ምክንያት መሆኑን እና የብፁዕነታቸው ፓስፖርትም ለጉዞ ሲባል ቀደም ብሎ ከሚመለከተው አካል መጥቶ በልዩ ጽሕፈት ቤቱ ጉዳይ አስፈጻሚ እጅ የሚገኝ መሆኑን ገልጻለች።
ቅዱስ ፓትርያርኩ ከብፁዓን አባቶች ጋር ሆነው በዛሬው ዕለት ደቡብ አፍሪካ ፤ ጁሐንስበርግ ከተማ በሰላም የገቡ ሲሆን ምዕመናንም አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ደቡብ አፍሪካ ፦ https://telegra.ph/EOTC-05-10
@tikvahethiopia
በቴሌብር የአየር ሰዓት በመሙላት ተጨማሪ ያግኙ!
ከዚህ በፊት ከነበረው የ 15 ብር፣ የ100 ሜ.ባ እና 10% ስጦታ በተጨማሪ በቴሌብር የአየር ሰዓት በመሙላት እስከ 25% ተጨማሪ ያግኙ!
መተግበሪያውን ከ http://onelink.to/fpgu4m ይጫኑ፤ ኑሮዎን ያቅልሉ!
#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
#ጥቆማ
° በኢትዮጵያ 1.1 ሚሊዮን ህጻናት መደበኛ ክትባት ወስደው አያቁም።
° የአለም የህጻናት አድን ድርጅት ከክትባት ጋር የተያያዘ ችግሮችን የሚፈቱ የፈጠራ ስራዎችን እያወዳረ ነው።
አፍሪካ በዓለም ' ዜሮ ዶዝ ' ህፃናት ከሚገኙባቸው አህጉራት በቁጥር ከፍተኛውን ደረጃ ትይዛለች። ይህም ማለት መደበኛ ክትባት ወስደው የማያውቁ 8.7 ሚሊዮን ህፃናቶች አሉ ማለት ነው፡፡
ከእነዚህ ህፃናት ውስጥ ከአንድ ሦስተኛ በላይ የሚሆኑት የሚኖሩት በናይጄሪያ እና ኢትዮጵያ ውስጥ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ 1.1 ሚሊዮን ህጻናት መደበኛ ክትባት ወስደው አያቁም።
በተጨማሪም ወረርሽኝ ፣ ድህነት ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ፣ አለመረጋጋት፣ ግጭቶችናና ተያያዥ ምክንያቶች የክትባት መርሃግብሮችን እየተስተጓጎሉ ይገኛሉ።
የዓለም የህጻናት አድን ድርጅት (ሴቭ ዘ ችልድረን) እና ጂኤስኬ በመተባበር የክትባት አቅርቦትን እና አጠቃቀምን በተመለከተ ማንኛውንም አይነት ከክትባት ጋር የተያያዘ ችግሮችን የሚፈቱ የፈጠራ ስራዎችን በማወዳደር ላይ እንደሚገኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ጠቅሷል።
የተመረጡ ኃሳቦች / ሥራዎች በፕሮጀክት እስከ 100,000 ዶላር የሚደርስ የገንዝብ እንዲሁም የቴክኒክ ድጋፍ ይደረግላቸዋል ተብሏል።
ለማመልከት www.stc-accelerator.org ይጎብኙ።
የማመልከቻ ቀን እስከ #ግንቦት_16 ቀን 2016 ዓም ድረስ ነው።
ሁለተኛው የፈጠራ ጥሪ በ2017/2025 የሚካሄድ ይሆናል።
@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ
በቨርችዋል ባንካችን 24/7 ገንዘብ ማስገባት ይችላሉ።
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
#virtualbanking #bankinginethiopia #banksinethiopia #ITM #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#Axum
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰኔ 2016 ዓ/ም ወደ ትግራይ አክሱም ከተማ በረራ እንደሚጀመር መግለጹን ትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
የአክሱም ሃፀይ ዮውሃንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፍያ በትግራይ በነበረው ደም አፋሳሽ ጦርነት በደረሰበት ወድመት ምክንያት ከበረራ አገልግሎት ውጪ ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል።
በቅርቡ ግን አውሮፕላን ማረፊያው መልሶ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገልጿል።
የአየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ዋና ስራ አስፈፃሚ ለማየ ያደቻ ለትግራይ ቴሌቪዥን በስልክ በሰጡት መረጃ ፤ " በአውሮፕላን ማረፍያው ሲካሄድ የቆየው የጥገና ምዕራፍ ወደ መጨረሻ መደረሱን ተከትሎ በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ሳምንት መልሶ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል " ብለዋል።
ወደ ታሪካዊቷ አክሱም ሲከናወን የነበረው የአውሮፕላን በረራ በመቋረጡ ምክንያት ነዋሪዎች መቸገራቸው እንዲሁም በአከባቢው የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎች ላይ ከፍታኛ መቀዛቀዝ እንዲታይ ማድረጉ በተደጋጋሚ መዘጋቡ ይታወሳል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
#DStvEthiopia
አርሰናሎች የ20 ዓመት የዋንጫ ጥማታቸውን ሊቆርጡ መድፋቸውን እያገላበጡ ወደ የፕሪሚየር ሊግ አፋፉ ተቃርበዋል።
አፋፉ ላይ ደግሞ ቀያዮቹ ቆመዋል !
እሁድ ከምሽቱ 12፡30 ማንችስተር ዩናይትድ ከአርሰናል በዲኤስቲቪ #ሱፐርስፖርት ብቻ!
ይህ ታሪካዊ ፉክክር እንዳያመልጥዎ…
ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ። ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ይከታተሉ!
የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2
#ሁሉምያለውእኛጋርነው
➡️ " ውላችን ይቋረጥ ፣ ገንዘባችንም ይመለስ ብለው የፈረሙ 4,000 ቆጣቢዎች አሉ " - የቤት እጣ ቆጣቢዎች
➡️ " ከጤና ሚኒስቴርም ከዳሽን ባንክም ጋር የመግባቢያ ሰነድ ስላለን ተመካክረን መልስ እንሰጣለን " - ጎጆ ብሪጂ
ከ7,500 በላይ ለሚሆኑ ጤና ባለሙያዎች ቤት ገንብቶ ለማስረከብ ከጤና ሚኒስቴርና ከዳሽን ባንክ የሦስትዮሽ ውል የፈረመው ጎጆ ብሪጂ ሀውሲንግ፣ እጣውን በወቅቱ እያወጣ ባለመሆኑ፣ ለወጣላቸውም ግንባታ ባለመጀመሩ፣ 4,000 ቆጣቢዎች ገንዘባቸው እንዲመለስ ቢጠይቁም እንዳልተመለሰላቸው ገልጸዋል።
አሁንም ቢሆን እንዲመለስላቸው ጠይቀል።
የቆጣቢዎቹ ኮሚቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ " በየ 3 ወሩ ለማውጣት እጣው ሳይሰጥ 2 ዙር አልፏል። ለምን ? ተብለው ሲጠየቁ 'የመሬት አስተዳደር ችግር ስላለብን ነው' እያሉ እስካሁን ቆዩ" ብሏል።
" ውላችን ይቋረጥ፣ ገንዘባችን ይመለስ ብለው የፈረሙ 4,000 ቆጣቢዎች አሉ " ያለው ኮሚቴው፣ በደብዳቤ ጭምር ቢጠይቅም መፍትሄ እንዳልተሰጠው አስረድቷል።
ለተየሳው የእጣ መዘግየት ቅሬታ በጎጆ ብሪጅ ሃውሲንግ በኩል ምላሽ እንዲሰጡ የተጠየቁት አቶ አልማው ጋሪ በሰጡት ሞላሽ፣ " የገጠመን ችግር አደረጃጀት ላይ መዘግየቶች ስለነበሩ ነው " ብለዋል።
" የሚያደራጀው የአዲስ አበባ ህብረት ሥራ ኮሚሽን የሚባለው ነው " ያሉት አቶ አልማው፣ " በሌላ ሳይት ላይ በተፈጠረ ክስ ትንሽ ሥራው ስለቆመ እስኪ ውጤቱን እንየው የሚል ሀሳብ ተነስቶ ስለነበረ የመዘግየት ጉዳይ አጋጥሟል " ነው ያሉት።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጠየቁ ለምን ገንዘባቸውን አልመለሳችሁም ? በማለት ለጠየቀው ጥያቄ ፣ " ውሉ የሚያስቀምጣቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ይህን ደግሞ ለብቻችን ሳይሆን ከጤና ሚኒስቴርም ከዳሽን ባንክም ጋር የመግባቢያ ሰነድ ስላለን ተመካክረን መልስ እንሰጣለን " ብለዋል።
የመጀመሪያው እጣ ማውጣት ተደርሶ ወደ 300 ሰዎች እጣ የደረሳቸው አሉ። እነርሱን ለማደራጀት በሂደት ላይ ነው ያለነው” ያሉት አቶ አልማው፣ “አንዳንዶች ደግሞ ቅሬታ አላቸው እየመጡ ይጠይቃሉ” ሲሉ ተናግረዋል።
" የቅሬታ አቅራቢዎቹን ጉዳይም ባለፈው ሳምንት ጤና ሚኒስቴር የተቋማት ተወካዮች በተገኙበት ውይይት ተደርጎ አቀረቡ አቅጣጫ ተቀምጧል። ምናልባት በዚህ ሳምንት አንድ ደረጃ ላይ ይደርሳል " ብለዋል።
#TikvahEthinpiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" በ5ቱ ኮሪደር ልማት ስራ 16 ሺህ ሰዎች የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በአዲስ አበባ ከተማ ፦
° መንገዶችን የማስፋት ፣
° የመንገድ ዳሮችን የማሳመር ፣
° የእግረኛና የሳይክል ብስክሌት መሄጃዎችን መስራት
° የቴሌ፣ የመብራት ኬብሎችን ወደ መሬት መቅበር
° የውሃ ፍሳሽ መሄጃዎችን መስራት
° ፕላዛዎችን መስራት የሚያጠቃልለው የኮሪደር ልማት ስራ በ5 ኮሪደሮች በመሰራት ላይ ይገኛል።
48.7 ኪሎ ሜትር ይሸፍናል የተባለው የኮሪደር ስራ ፥
➡️ ከ4 ኪሎ - ፒያሳና የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ ፣
➡️ ከ4 ኪሎ አደባባይ በእንግሊዝ ኤምባሲ መገናኛ ፣
➡️ ከሜክሲኮ ሳር ቤት በጎተራ ወሎ ሰፈር አደባባይ፣
➡️ ከ4 ኪሎ መስቀል አደባባይ ቦሌ ድልድይ ፣
➡️ ከቦሌ ድልድይ በመገናኛ እስከ አፍሪካ ኮንፌሽንን ያካልላል።
ስራዎቹ በሳምንት ለ7 ቀናት በቀን ለ24 ሰዓት የሚሰሩ ሲሆን ብዙ ቦታ ላይ መሰረታዊ ስራዎች ተሰርተው መጠናቀቃቸው ታውቋል።
የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፤ በአምስቱ የኮሪደር ልማት ስራ " 16,000 ሰዎች ስራ እድል አግኝተዋል " ብለዋል።
ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-05-08-4
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ መጪውን የዳግመ ትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን የሚያስገኝ የጥያቄና መልስ ውድድር ይዞላችሁ ይቀርባል፡፡
እርስዎም የሽልማቱ ተሳታፊ ለመሆን ከታች ያሉትን የባንኩን ይፋዊ የቴሌግራም እና የፌስቡክ ገፆች በመቀላቀል እንዲሁም ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት ከወዲሁ ተዘጋጅተው ይጠብቁን !
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!
[Telegram] [Facebook]
/channel/LionBankSC
#LIB #lioninternationalbank #anbesabank #keytosuccess