ዲቪ 2025 ዛሬ ምሽት ይፋ ሆኗል።
የአሜሪካ ዲቪ (Diversity Visa) ሎተሪ 2025 ዛሬ ምሽት ይፋ መደረጉን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት አሳውቋል።
መ/ቤቱ፥ አመልካቾች መመረጥ አለመመረጣቸውን / ደርሷቸው እንደሆነ እና እንዳልሆነ ማየት የሚችሉት በ dvprogram.state.gov/ESC/ ላይ የማረጋገጫ ቁጥራቸውን በማስገባት #ብቻ መሆኑን አሳስቧል።
ከዚህ ውጭ የዲቪ ውጤት የሚታይበት ምንም አይነት መንገድ የለም።
N.B. ዲቪ የሚደርሳቸው ሰዎች የሚስጥር ቁጥሩን እስከ ቀጣይ አመት መስከረም መጨረሻ ቀናት መያዝ አለባቸው።
ምናልባትም " ዲቪ ደርሷችኃል ከአሜሪካ ኤምባሲ ነው የምንደውለው፣ ኢሜል / ቴክስት መልዕክት የሚንልከው " የሚሉ አጭበርባሪ ስለሚኖሩ ጥንቃቄ አድርጉ ተብሏል።
እንደ አሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ፥ የዲቪ ተመራጭ መሆን ለቪዛ ወይም ለቃለመጠይቅ ዋስትና አይሆንም።
የዲቪ ሎተሪ ተመራጭ መሆን የቪዛ ጥያቄ ለማቅረብ የመጀመሪያው መስፈርት ሲሆን በቀጥታ ለቪዛ ወይም ለቃለመጠይቅ ዋስትና አይሰጥም።
@tikvahethiopia
“ ... ተገምግመው ተነሱ እንጅ አመልክተው አልተነሱም ” - አየለ አናውጤ (ዶ/ር)
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባሉ አቶ ጣሂር መሐመድ " በግል ምክንያት" ከአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊነት መልቀቃቸውን፤ በእሳቸው ምትክ ሌላኛው የፓርቲው አባል አቶ መልካሙ ፀጋዬ መሾማቸውን መረጃ አድርሰናችሁ ነበር።
አቶ ጣሂር ለቢቢሲ አማርኛው ክፍል በሰጡት ቃል፣ " ከባለፉት ሶስት፣ አራት ወራት ወዲህ አንስቶ ከኃላፊነት የመልቀቅ ጉዳይ ላይ ከክልሉ አመራሮች ጋር በዝርዝር ንግግር አድርጌያለሁ። የክልሉ መንግሥት ጥያቄውን ተቀብሏል " ነበር ያሉት።
ይሁን እንጂ አቶ ጣሂር ከኃላፊነት የተነሱት “ በግል ምክንያት ” እንደሆነ ቃላቸውን ከሰጡ በኋላ፣ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ም/ ኃላፊ ዶክተር አየለ አናውጤ በፌስቡክ ገጻቸው ባሰራጩት መልዕክት፣ “ ተገምግመው ተነሱ እንጂ አመልክተው አልተነሱም ” ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ፣ የተነሱት በምን ምክንያት እንደሆነ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡ ለአየለ አናውጤ (ዶ/ር) ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ “ በፌስቡክ ገፄ በዝርዝር ፅፌዋለሁ። ለጊዜው ከዚህ የተለየ ነገር የለኝም ” ብለው ለዘገባ ያንኑ ፅሑፍ መጠቀም እንደሚቻል ገልጸዋል።
በፌስቡክ ገጻቸው ባሰራጩት ፅሑፍ “ ላለፈው አንድ አመት ተቋሙ በአንድ በኩል በአግባቡ እየተሰራ ባለመሆኑ፣ በሌላ በኩል ከፍተኛ የሀብት ብክነት አለ ብለን በማመናችን ተደጋጋሚ ግምገማዎች አድርገናል ” ብለዋል።
“ ለ2 ዓመት ከ8 ወራት አዲስ አበባ ተቀምጠው በ3 ወር አንዴ እየመጡ፣ ለዛውም ተደብቀው ገብተው ሕገ ወጥ ድርጊት ፈጽመው ይሄዳሉ ” ሲሉም ገልጸዋል።
“ በመሆኑም በቢሮው ማኔጅመንት ፣ በዘርፉ ማኔጅመንት ፣ በክልል ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴ፣ በከተማ ክላስተር ደረጃ በርካታ ግምገማዎች አድርገናል ” ያሉት ዶ/ር አየለ “ በመጨረሻ ከኃላፊነት እንደተነሱ ከተገለጸልን ቆይቷል፤ ደብዳቤው በእርሳቸው ጥያቄ ቢዘገይም ” ብለዋል።
“ ይህ ብቻ ሳይሆን ከወር በፊት የክልሉ መንግስት ልዩ የኦዲት ምርመራ አድርጎ እርምጃ እንዲወስድ ለርዕሰ መስተዳደሩ በደብዳቤ አሳውቄአለሁ ” የሚለውንና ሌሎች ማብራሪያዎች ሰጥተው፣ “ ተገምግመው ተነሱ እንጂ በግል ምክንያት በእሳቸው ጠያቂነት አልተነሱም ” ነው ያሉት። (ሙሉ ፅሑፋቸው ከላይ ተያይዟል)
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ለጥንቃቄ
በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ በተለያየ ቦታ እየተንቀሳቀሱ የመኪና ስፖኪዮ በመስረቅ ወንጀል የተጠረጠሩ 4 ግለሰቦች (ልጆች) በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።
ተጠርጣሪዎቹ ሚያዚያ 23 እና 24 ቀን 2016 ዓ.ም ወረዳ 2 ጋዜቦ አደባባይ እና ወረዳ 9 አካባቢ ነው የተያዙት ተብሏል።
ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ የትራፊክ መብራቶች እና ተሽከርካሪ በሚቆምባቸው ሌሎች ቦታዎች ላይ በመንቀሳቀስ ስፖኪዮ ሲሰርቁ እንደነበር አመልክቷል።
በዚህ የወንጀል ድርጊት ተሳትፈው የተገኙ ህፃናቶች መሆናቸውም ተመላክቷል።
ይህ መነሻ በማድረግ በተደረገ ምርመራ ለህፃናቱ ስምሪት የሚሰጡ የተደራጁ ወንጀለኞች መኖራቸውን ፖሊስ ማረጋገጡን ገልጿል።
አንዳንድ ህፃናት መኪና የሚጠብቁ እንዲሁም እርዳታ የሚፈልጉ መስለው በመቅረብ ወንጀል እንደሚፈፅሙ አሽከርካሪዎች ተገንዝበው በትራፊክ መብራቶችም ሆነ የትራፊክ ፍሰት በሚበዛባቸው ሌሎች ቦታዎች ላይ ሲቆሙና በዝግታ ሲያሽከረክሩ ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ተብሏል።
#AddisAbabaPolice
@tikvahethiopia
#DV2025
የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ (Diversity Visa) 2025 አሸናፊዎች ነገ ይፋ ይደረጋሉ።
ለዲቪ (Diversity Visa) 2025 ማመልከቻ የሞሉ በ dvprogram.state.gov/ESC/ ብቻ የማረጋገጫ ቁጥራቸውን በማስገባት ውጤቱን ወይም ማሸነፍ አለማሸነፋቸውን መመልከት ይችላሉ።
NB. የማረጋገጫ ቁጥር ማመልከቻው ሲሞላ የተሰጠ ነው። ይህ ቁጥር የጠፋበት Forgot Confirmation Number በማለት አስፈለጊ መረጃ በመሙላት በኢሜል አዲስ ቁጥር ማግኘት ይቻላል።
ውጤቱ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽት 1 ሰዓት ጀምሮ ይፋ ይሆናል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር " የዲቪ (DV) ሎተሪ አሸንፋችኋል ፣ ከአሜሪካ ኤምባሲ ነው ምንደውለው / ይህን ኢሜል / ቴክስት የምንልከው " በማለት #የሚያጭበረብሩ_አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች እንዲጠነቀቁ አሳስቧል።
አንድ አመልካች ዲቪ 2025 ደርሶት እንደሆነ እና እንዳልሆነ ማወቅ የሚችልበት ብቸኛው መንገድ ከላይ የተጠቀሰው ድረገጽ መሆኑን አስገንዝቧል።
አሜሪካ በየዓመቱ ከአፍሪካ (ኢትዮጵያ ጨምሮ) ፣ እስያ ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አውስትራሊያ 55 ሺህ ሰዎችን በዲቪ (DV) ሎተሪ ወደ ሀገሯ ታስገባለች።
@tikvahethiopia
#እንድታውቁት
በበዓሉ ወቅት ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች ምንድናቸው ?
- በምግብ ማብሰያ ወይም በማዕድቤት አካባቢ የኤሌክትሪክ ፣ የቡታጋዝ ፣ የከሰል ምድጃዎችን በአግባቡ እና በጥንቃቄ ይጠቀሙ።
- በገበያ ማዕከላት የገበያተኛውን ቀልብ ለመሳብ የሚጠቀሙባቸው የኤሌክትሮኒክስ ዲኮሬሸኖች ቃጠሎ እንዳያስነሱ ይጠንቀቁ።
- ሻማ እና ጧፍ ሲጠቀሙ ከተቀጣጣይ ነገር ያርቁት።
- ካምፋዬር ሚያዘጋጁ ከሆነ ከአካባቢው ከመራቅዎ በፊት በደንብ መጥፋቱን ያረጋግጡ።
- በፍጹም ጠጥተው አያሸከርክሩ።
ለማናቸውም የእሳት እና የድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም የአምቡላንስ አገልግሎት የሚከተሉትን የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ስልክ ቁጥሮች መዝግበው ይያዙ።
24 ሰዓት መደወል ይችላሉ።
1. ማዕከል - 0111555300/ 0111568601
2. አራዳ - 0111567004/ 0111560249
3. ቂርቆስ - 0114663420/21
4. አዲስ ከተማ - 0112769145/46
5. ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 0114425563/64
6. አቃቂ ቃሊቲ - 0114340096 / 0114343063
7. ቦሌ - 0116630373/74
8. ኮልፌ ቀራንዮ- 0113696085/ 0113696104
9. ጉለሌ - 0112730731/ 0112730653
10. ቦሌ ሰሚት - 0116680846/ 0116680760
11. ልደታ - 0115589043/ 0115589533
(በእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የቀረበ)
እንኳን አደረሳችሁ !
@tikvahethiopia
ከዘመናዊ የATM ማሽኖቻችን ብር ለማውጣት ካርድዎን ወደ ማሽኑ በማስጠጋት እና የሚስጥር ቁጥርዎን በማስገባት መገልገል ይችላሉ።
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
#BoAATM #ATM #bankinginethiopia #banksinethiopia #ITM #bankofabyssinia #contactless #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
" የመኪና እቃ የተሰረቀባችሁ በአካል ቀርባችሁ ንብረታችሁን ምረጡ " - ፖሊስ
የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ በከተማይቱ የመኪና እቃ ስርቆት ወንጀል ስጋትን ለመቀነስ ሕግን መሰረት ያደረገ ኦፕሬሽን በልደታ ፤በአራዳ እና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አዋሳኝ ወረዳዎች ላይ መስራቱን አሳውቋል።
ፖሊስ በተለምዶ ሱማሌ ተራ በሚባለው አካባቢ ባካሄደው ኦፕሬሽን ፦
➡ 528 ልዩ ልዩ ፍሬቻዎችን ፣
➡ 187 ስፖኪዮችን ፣
➡ 113 የመኪና መብራቶች ፣
➡ 172 የዝናብ መጥረጊያ በአጠቃላይ 33 ልዩ ልዩ በድምሩ 1 ሺ 269 አይነት የመኪና እቃዎችን መያዙን አስታውቋል፡፡
የተሰረቁ የመኪና እቃዎችን ሚገዙና የሚያሻሽጡ 89 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ መቀጠሉን ገልጿል።
በተለያየ ጊዜ የመኪና እቃ የተሰረቀባቸው ግለሰቦች ፦
° በልደታ ፣
° በአራዳ
° በአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎች በመቅረብ ንብረታቸውን መምረጥ እንደሚችሉም ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ፥ በከተማው ለመኪና እቃ ስርቆት መስፋፋት ልዩ ልዩ ምክንያቶች ቢኖሩም በተለይ ወንጀለኞችን በማደራጀትና በማሰማራት የመኪና እቃ የሚያሰርቁ እና የተሰረቁ እቃዎችን የሚገዙ ህገ-ወጦች ለወንጀሉ መስፋፋት ዋና ምክንያት ናቸው ብሏል።
#AddisAbabaPolice
@tikvahethiopia
#Urgent
ዶ/ር ቤቴል ገርማሞ ትባላለች።
ገና የመመረቋን ደስታ ሳታጣጥም እንደቀልድ ለ " ቶንሲል ህመም " በሚል ምርመራ ስትደረግ ያልጠበቀችውን መጥፎ ዜና ተረድታለች።
ዶክተሯ የደም ካንሰር በአይነቱ ደግሞ " acute lymphoblaatic leukemia " የሚባል እንዳለባት በፓቶሎጂ ምርመራ ተረጋገጠባት።
የጥቁር አንበሳ ሜዲካል ቦርድም አፋጣኝ የሆነ የመቅኒ ንቅለ ተከላ እንዲደረግላት መወሰኑን ከቤተሰቦቿ መረዳት ተችሏል።
የደም ካንሰር ምንም እንኳን እጅግ አጣዳፊ እና አስደንጋጭ ቢሆንም በጊዜ ከታከመ እና የመቅኒ ንቅለ ተከላ በማድረግ የመዳን እድል ያለው በሽታ ነው።
መላው ኢትዮጲያዊያ የዚህችን ምስኪን እና ወደፊት ህዝቧን በሞያዋ የምታገለግል ሀኪም ህይወት እንዲታደግ ጥሪ ቀርቧል።
ዶ/ር ቤቴል በወላይታ ዞን በዴሳ በምትባል ከተማ ተወልዳ ያደገች እና በቤተሰቦቿ እና በአከባቢው ማህበረሰብ እንደምሳሌ ምትጠቀስ ብርቱ ሴት ናት።
እንደአብዛኛው ኢትዮጲያዊ ቤተሰብ አቅማቸው እሷን ለማሳከም የሚበቃ አይደለም። ስለሆነም አቅም ያላችሁ ሁሉ ድጋፋችሁ ታደርጉ ዘንድ ቤተሰቦቿ ተማፅነዋል።
በስልክ ደውሎ ለማነጋገር በ0913922441 ላይ መደወል ይቻለል።
Dr Bethel Germamo Ganebo
➡️ የባንክ አካውንት CBE 1000105102384
@tikvahethiopia
በአዲስ አበባ ከተማ የወጣው የመሬት ሊዝ ጨረታ ተራዘመ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክፍለ ከተማ ፤ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ በሌሎችም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል።
በዚህም ከሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 24/2016 ዓ/ም ድረስ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ ሲከናወን ቆይቷል።
ነገር ግን የጨረታ ሰነድ ሽያጩ ከ28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 09/09/2016 ዓ/ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት መራዘሙ ተነግሯል።
ተጫራቾች ፦
- የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ፣
- ሲፒኦ፣
- የግንባታ አቅም ማሳያ ማስረጃ፣
- ሰነዱን ለመግዛት በቴሌ ብር የከፈሉበት ስሊፕ
- ሌሎች መያያዝ ያለባቸዉ እና በተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጹትን በመጨመር የጨረታ ሰነዶችን በኤንቨሎፕ በማሸግ ግንቦት 09/2016 ዓ/ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አከባቢ ኤም ኤ (MA) ህንፃ ላይ በሚገኘው የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ተብሏል።
ጨረታው ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 12/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ ለተከታታይ 9 የስራ ቀናት በቦሌ ክ/ከተማ አስተደዳር አዳራሽ እንደሚከፈት ተገልጿል።
የጨረታው ዝርዝር👇
/channel/tikvahethiopia/87112
@tikvahethiopia
" ' እኔ ሰርቂያለሁ ስሜን ግን ለጥፏል ' የሚል ይምጣና ይክሰሰኝ ካሳውን እንከፍላለን " - አቶ አቤ ሳኖ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ ከዋልታ ቴሌቪዥን ቆይታ አድርገው ነበር።
በዚህም ወቅት ፥ መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ/ም በሲስተም ችግር ምክንያት በተፈጠረው እክል ተዘርፎ የተወሰደውን ባንኩ ገንዘብ እያስመለሰ መሆኑንና ከ801 ሚሊዮን ብር የቀረው 25 ሚሊዮን ብር መሆኑን ገልጸዋል።
በዕለቱ 30 የባንኩ ሰራተኞች በግብይት ላይ መሳተፋቸውን ተከትሎ አሁን ላይ ከስራ ታግደው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ፥ ባንኩ በምን የሕግ አግባብ ነው ሰዎች ነጻ ሆኖ የመገመት መብታቸው ተጥሶ ፎቷቸው የተሰራጨው ? የሰዎችን ምስል ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዴት አሰራጨ በሚል ተጠይቀዋል።
አቶ አቤ ፤ " እኛ ዛሬም ድረስ ወንጀለኛ ናቸው የሚል ቃል አልወጣንም። ይሄን ገንዘባችንን ወስደዋል መልሱ ነው ያልነው መውሰዳቸውን 101% እናውቃለን " ሲሉ ገልጸዋል።
" ዛሬ ያለንበት ሁኔታ እና መጀመሪያ ላይ የነበረው ይለያያል። እሁድ የነበረው ታሪክ ' ባንኩ ማን ብር እንደወሰደበት አያውቅም ' የሚል ነው በተለይ ሶሻል ሚዲያ ላይ ሲቀለድ ነበር እኛ ግን ' እናውቃለን መልሱ ስንል ' ነበር ምላሹ ' አያውቅም ' የሚል ነበር በኃላ 1 ሳምንት ሰጠን በተደጋጋሚ አስጠነቀቅም እንዲመልሱ ከዛ ስም እና ፎቷቸው እዲወጣ ወደማድረጉ ገባን " ብለዋል።
" ምስል አታሰራጭ የሚል በህገ-መንግስቱ አልተገለጸም። ሲቀጥል 15 ሺህ ሰው በኮንቬንሽናል ህግ ሊፈታ የሚችል ችግር አይደለም " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " naming and shaming የሚል ህግ አለ ገንዘብ የወሰደውን ሰው ስሙን አውጥቶ ያያችሁት ንገሩትና ይመልስ ነው ያልነው " ብለዋል።
" ነጻ ሆኖ የመገመት መብቴ ተነክቷል " የሚል ካለ ይክሰሱንና ካሳ ይጠይቁ ሲሉ ገልጸዋል።
አቶ አቤ " ' እኔ ሰርቂያለሁ ስሜን ግን ለጥፏል ' የሚል ይምጣና ይክሰሰኝ ካሳውን እንከፍላለን " ሲሉ ተናግረዋል።
" ያደረግነው ነገር በተወሰነ ደረጃ ወቀሳ ሊቀርብበት የሚችል ነገር ነው። ለችግሩ መፍትሄ ግን ያደረግነው ብቻ ነበር። ነገሩ ከህግም ከፖሊስም አቅም በላይ ነው ይሄን ሁሉ ሰው ማሰር አይችሉም፤ ፍርድ ቤት ይሄን ሁሉ ሊዳኝ አይችልም። የህግ ጥያቄ ቢነሳም ትክክለኛው መፍትሄ ያደረግነው ብቻ ነበር እሱንም አማራጭ ስላልነበረን ነው ያደረግነው ያን ማድረጋችን ህዝቡ እንዲያውቀው ሆኖ የወሰደው ሁሉ ተሰልፎ መጥቶ መለሰ " ብለዋል።
" ገንዘቡ የህዝብ ነው እያስመለስን የቀረው ከ801 ሚሊዮን ብር 25 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው ፤ የማሰባሰቡ ስራ 96.8 በመቶ ደርሷል " ሲሉ አሳውቀዋል።
" ምንም እንኳን ልጆች ቢያጠፉም ወላጆች መጥተው አርመዋልና የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም ጨዋ ነው ፤ አሁንም አዋቂ አለ ፣ የሚያስትምር አለ፣ ሽማግሌ አለ፣ ጨዋ ወላጅ አለ ማለት እፈልጋለሁ " ሲሉ ለቴሌቪዥን ጣቢያው ተናግረዋል።
@tikvahethiopia
እነ ቀሲስ በላይ ክስ እስኪመሰረትባቸው በእስር ይቆያሉ።
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በነ ቀሲስ በላይ መኮንንና ሌሎች 2 ተጠርጣሪዎች ላይ የክስ መመሥረቻ 15 ቀናት ፈቅዷል።
በሀሰተኛ ሰነድ ከአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ከ6 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ለማውጣት ሙከራ አድርገዋል ተብለው የተጠረጠሩትና በቁጥጥር ስር የዋሉት ቀሲስ በላይ መኮንንና 2 በወቅቱ አብረዋቸው የነበሩ ግለሰቦች ዛሬ ለ3ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።
በዚህም ፍርድ ቤት ለዐቃቤ ሕግ 15 ቀናት የክስ መመስረቻ ፈቅዷል።
ተጠርጣሪዎች ክሱ እስኪመሰረት ድረስ ባሉበት ማረፊያ ቤት እንዲቆዩ ፍርድ ቤት አዟል።
@tikvahethiopia
#ጸሎተ_ሐሙስ
ጸሎተ ሐሙስ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች ተከብሯል።
በአዲስ አበባ ፒያሳ ልደታ ማርያም ካቴድራል የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሀነኢየሱስ ሱራፌልን ጨምሮ ካህናት፣ ደናግላንና ምዕመናን በተገኙበት መሥዋዕተ ቅዳሴና የቅባ ቅዱስ ቡራኬ ተካሂዷል።
Photo Credit - FBC & Emdiber Catholic Secretariat
@tikvahethiopia
#ጸሎተ_ሐሙስ
የሕፅበተ እግር ስነ ሥርዓት ተከናወነ።
ዛሬ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክሃይማኖት መሪነት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የሕፅበተ እግር ስነ ሥርዓት ተከናወነ።
በስነ ሥርዓቱ ላይ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ ቆሞሳት ፣ ካህናትና በርካታ ምዕመናን ተገኝተው እንደነበር ከቤተክርስቲያኗ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
Photo Credit - TMC
@tikvahethiopia
የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፈተና መቼ ይሰጣል ?
እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ፤ የ2016 ዓ/ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ይሰጣል።
ፈተናው ለ15 ቀናት በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ ነው።
ከ70 በመቶ የሚዘጋጀው ፈተና በኦንላይንና በወረቀት ወይም በጥብቅ ቁጥጥር በወረቀት ይሰጣል ተብሏል።
ባለፈው ዓመት የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ የሪሚዲያል ፈተናውን በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች #ብቻ ለመስጠት ታቅዶ እየተሰራበት ነው።
ዘንድሮ 32,500 ተማሪዎች 50 በመቶ በላይ ውጤት በማምጣት በቀጥታ ዩኒቨርሲቲ ገብተው መደበኛ ትምህርት እየተከታተሉ ሲሆን ከ78 ሺህ በላይ ተማሪዎች ደግሞ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሪሚዲያል ትምህርት እየወሰዱ እንደሚገኙ ሚኒስቴሩ ለኢፕድ ከሰጠው መረጃ ተመልክተናል።
በሌላ በኩል ፤ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ የሬሜዲያ ተማሪዎች ከታህሳስ ወር ጀምሮ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ቢሆንም በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የተመደቡ ተማሪዎች እስካሁን ጥሪ አልተደረገላቸውም።
ተማሪዎቹ የትምህርት ጊዜያቸው እያለፈ እንደሆነና አስቸጋሪ ጊዜ እያሳለፉ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ቅሬታ አቅርበዋል።
70% ፈተናው በሰኔ ወር ይሰጣ መባሉ ደግሞ እንዳስጨነቃቸው ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦
- የነዚህ ልጆች ዕጣ ፋንታ ምንድነው ?
- ከዚህ በኃላ መቼ ተጠርተው ተምረው ለፈተና ይቀርባሉ ?
- ለምን ምቹ ሁኔታ ከሌለ ቀደም ብሎ ሌላ ግቢ አይመደቡም ነበር ?
- አሁን መፍትሄ ምንድነው ? የሚሉ ጥያቄዎችን ይዞ የዩኒቨርሲቲውን አመራሮች በተደጋጋሚ በድምጽ እና በፅሁፍ ለማናገር ጥረት ቢያደርግም #ቁርጥ ያለ ምላሽ ማግኘት አልቻለም።
በቀጣይም ጥረቱን ይቀጥላል።
ዩኒቨርሲቲውም ሆነ ከትምህርት ሚኒስቴር ምላሽ ካገኘ ያቀርባል።
Via @tikvahUniversity
@tikvahethiopia
#DStvEthiopia
🏆የዋንጫው ደረሰ🏆
በታላላቅ የዓለማችን እግር ኳስ ሊጎች ዋንጫ ለመሳም የሚደረጉትን ግስጋሴዎችን በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ቻናሎች በቀጥታ ይከታተሉ!
አንድም ደቂቃ እዳያመልጦ አሁኑኑ ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ወርሃዊ ካፍያዎን ይፈፅሙ!
💥 የአውሮፓ ምርጥ ተጫዋቾችን ፍልሚያ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ቻናሎች ይከታተሉ!
የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ1,999 ብር ከ1 ወር ነፃ የሜዳ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ።
የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/2WDuBLk
#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
#ለጥንቃቄ🚨
" በከፍተኛ ሁኔታ የሚንቀሳቀስ #የጅብ_መንጋ ተከስቷል ማህበረሰቡ ሊጠነቀቅ ይገባል " - የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሠላምና ጸጥታ ቢሮ
ከሰሞኑ በማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል በምሽት አንዳንዴም በቀን ጅቦች በሰው ላይ በተለይ በህጻናት እና ሴቶች እንዲሁም በአቅመደካሞች ላይ ጥቃት እያደረሱ ተነግሯል።
በደረሰን መረጃ በስልጤ ዞን 2 ሰዎች ሲሞቱ በሀዲያ ዞን እንዲሁም በሀላባ አካባቢ ሌሎች 2 የአካል ጉድለት ያደረሱ ጉዳቶች ተመዝግበዋል።
ከሟቾች አንዷ የ3 ዓመት ህጻን ናት። በስልጤ ዞን ላንፉሮ ወረዳ ነዋሪ የሆነችው ይህች ህጻን በእናቷ ጀርባ ላይ ታዝላ (እናትየው ከወፍጮ ቤት እህል አስፈጭታ ስትመለስ) በነበረበት ወቅት አድፍጦ ይጠብቅ በነበረ የተራበ ጅብ ተወስዳ ጉዳት ከደረሰባት በኃላ ህይወቷ አልፏል።
በአጠቃላይ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሰላምና ጸጥታ ጉዳይ ኃላፊ የሆኑትን አቶ ተመስገን ካሳን አነጋግሯቸዋል።
አቶ ተመስገን ፤ በዚህ አመት ከፍተኛ የጅብ መንጋ መፈጠሩን አመልከተዋል። መንጋው ሲበዛ ለረሀብ በመጋለጡ ወደ ሰዎች እንደሚሄድ ገልጸዋል።
እስካሁን በክልሉ የሁለት ሞትና በርካታ ለሞት ያላበቁ ጉዳቶች ሪፖርት እንደደረሳቸዉ ጠቅሰዉ ጉዳቱ በህጻናት ላይ የበረታ መሆኑን ተናግረዋል።
አሁን ላይ ባካሄዱት ግምገማ መንጋዉ ከፍተኛ ቁጥር ያለው እንደሆነ ገልጸዋል። ይህን ለማጥፋት ከሚመለከተዉ አካል ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ማህበረሰቡ ግን የራሱን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
" የኦንላይን ፈተናው በተመረጡ 25 ከተሞች ይሰጣል " - ትምህርት ሚኒስቴር
ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ 25 ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ገልጿል።
ተፈታኝ ተማሪዎች በኦንላይን ለሚሰጠው ፈተና እንዲዘጋጁ ማሳሰቢያ ተላልፏል።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከሁሉም ክልሎች በተመረጡ 25 ከተሞች በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።
በወረቀት ከሚሰጠው ፈተና ጎን ለጎን የሚሰጠው የኦንላይን ፈተና ተማሪዎች ከቦታ ቦታ ሳይጓጓዙ በየአካባቢያቸው #ቤተሰቦቻቸው_ጋር_እያደሩ ፈተናውን ይወስዳሉ ሲሉ አሳውቀዋል።
ወ/ሮ አየለች ፤ ተማሪዎች ለፈተናው እንዲዘጋጁ፣ ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ፣ ወላጆችንም ልጆቻቸውን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር እስካሁን ፈተናው በኦንላይን የሚሰጥባቸውን 25 ከተሞች በዝርዝር ይፋ አላደረገም።
የኦንላይን ተፈታኞች ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ደጋግመው እንዲለማመዱ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው ተብሏል።
@tikvahethiopia
#LionInternationalBank
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ መጪውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን የሚያስገኙ የጥያቄና መልስ ውድድር ይዞላችሁ መጥቷል፡፡
እርስዎም የሽልማቱ ተሳታፊ ለመሆን ከታች ያሉትን የባንኩን ይፋዊ የቴሌግራም እና የፌስቡክ ገፆች በመቀላቀል እና ጥያቄውን ቀድመው በመመለስ ሽልማቶችን የራስዎ ያድርጉl
ጥያቄው የሚካሄዳው እሁድ ሚያዚያ 27 ከቀኑ 5:00 ሰዓት ሲሆን ጥያቄውን ቀድመው ለመለሱ 3 ሰዎች ሊሸልም ዝግጅቱን ጨርሷል።
1ኛ ለሚወጣ ተሸላሚ የበግ ሽልማት
2ኛ ለሚወጣ የ5000 ብር ሽልማት
3ኛ ለሚወጣ የ3000 ብር ሽልማት ያበረክትላችኋል።
እርስዎም ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት የውድድሩ ተሳታፊ ይሁኑ!!
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!
[Telegram] [Facebook]
/channel/LionBankSC
#LIB #lioninternationalbank #anbesabank #keytosuccess
" በየቤቱ የቁም እንስሳት ማረድ / በየአካባቢው ቅርጫ አድርጎ መከፋፈል አልተከለከለም " - የአዲስ አበባ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ፥ ከትንሳዔ በዓል ጋር በተያያዘ " ህብረተሰቡ በየቤቱ የቁም እንስሳት እርድ በማካሄድ ወይም በየአካባቢው ቅርጫ በማድረግ የሚከፋፈልበት አሰራር ተከልክሏል " በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ #ሐሰተኛ ነው ሲል አሳወቀ።
ከዚህም ጋር በተያያዘ #ምንም_ዓይነት_ክልከላ ያልተደረገ መሆኑን አረጋግጧል።
ነገር ግን በየአካባቢው #በሕገወጥ_መንገድ እርድ በመፈፀም ለሆቴሎች እና ለስጋ ቤቶች በማከፋፈል ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላት የቁም እንስሳቱ ጤንነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ድርጊቱ በከተማው ነዋሪዎች ጤንነት ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል ብሏል።
የከተማዋ ነዋሪዎችም ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።
@tikvahethiopia
“ ... ለኩራዝ የሚጠቀሙበት ነዳጅ በግልጽ ሁኔታ በችርቻሮ፣ የአረቄ በርሜል በከፍተኛ መጠን የሚሸጥበት ቦታ ነው ” - አቶ ንጋቱ ማሞ
በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አቃቂ ገበያ ማዕከል ትላንት ከምሽቱ 3 ሰዓት ገደማ የእሳት አደጋ አጋጥሞ ነበር።
በሰዎች ላይ ጉዳት ያልደረሰ ሲሆን 6 ሙሉ ለሙሉ፣ 10 በከፊል፣ በድምሩ 16 ሱቆች እንደተቃጠሉ የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የአደጋው መንስኤ ታውቋል? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ፣ “ ፓሊስ ምርመራ እያደረገ ነው። በንብረት ላይ የደረሰን ጉዳትም ባለንብረቶቹን ፓሊስ አጣርቶ ምርመራ እያደረገ ነው ” ብለዋል።
ገበያ ማዕከሉ ለእሳት አደጋ ተጋላጭ ተብሎ የተለዬ እንደሆነ ፣ ለአደጋ የተጋለጠባቸውን ጉዳዮች ለሚመለከታቸው አካላት ቢያቀርብም የማስተካከያ እንዳልተደረገ ኮሚሽኑ ያስታወቀ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያም ተሰጥቶ የነበረው ማስጠንቀቂያ ምን እንደነበር ኮሚሽኑን ጠይቋል።
አቶ ንጋቱ በሰጡት ምላሽ፣ “ ለገበያ ማዕከሉ አክሲዮን ማኅበራት አደጋ ውስጥ ናችሁ። ገበያ ማዕከሉ በዘመናዊ መልክ ይገንባ ንብረታችሁ ለአደጋ ሰለባ እንዳይሆን የሚል ምክረ ሀሳብ አቅርበናል። በግልባጭ ደግሞ ለወረዳውም ” ብለዋል።
“ ቤቶቹ በቀላሉ ሊቀጣጠሉ ከሚችሉ ግብዓቶች (ቆርቆሮ በቆርቆሮ) የተገነቡ ናቸው። መፍትሄ ብለን ያቀረብነው ገበያ ማዕከሉ ዘመናዊ ሆኖ እንዲገነባ ነው። ዘመናዊ ስንል እሳትን ሊቋቋም ከሚችል እንደ ድንጋይ ከመሳሰሉ ግብዓቶች እንዲሰራ ነው ” ሲሉ አስረድተዋል።
አቶ ንጋቱ፣ “ ከገጠር የሚመጡ ሰዎች ለኩራዝ የሚጠቀሙበት ነዳጅ በግልጽ በችርቻሮ፣ የአረቄ በርሜል በከፍተኛ መጠን የሚሸጥበት ቦታ ነው” ብለዋል።
“ ንግዱ ዘርፍ፤ ዘርፍ ያስፈልገዋል። በጎን ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እየተሸጡ፣ በጎን ደግሞ የካቲካላ ንግድ በፍጹም ምንም አይነት ህብረት የላቸውም ” ነው ያሉት።
የገበያ ማዕከሉ በተደጋጋሚ አደጋ እንደደረሰበት አስታውሰው፣ አደጋ ቢያጋጥም እንኳ የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ ለማስገባት ምቹ ባለመሆኑ፣ በውስጡ የሚከናወኑ የንግድ ዘርፎች የተደበላለቁ በመሆናቸው የሚመለከታቸው አካላት አሁንም ትኩረት እንዲሰጡ አሳስበዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Update
የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉኅን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም እና የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ መ/ር ዋሲሁን በላይ ትላንት በመንግሥት የጸጥታ አካላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስደው ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደሚገኙ ተገልጾ ነበር።
ዛሬ ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን ማኅበረ ቅዱሳን አሳውቋል።
ምንም እንኳን አመራሮቹ በምን ምክንያት ተይዘው እነደነበር ያብራራው ነገር ባይኖርም ፥ " በሂደቱ ጉዳዩን በመረዳት #አፋጣኝ_ምላሽ የሰጡንን የመንግሥት የጸጥታ አካላት እናመሰግናለን " ብሏል።
@tikvahethiopia
#ስቅለት
በክርስትና አስተምሮ ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለ በደል ያለ ጥፋት ንጹሕ እና ጻድቅ የኾነውን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰቀሉበት ዕለት ነው።
ዕለቱ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ዂሉ መድኀኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልዕልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የሚታሰብበት ታላቅ ቀን ነው።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን #በስግደት እና #በጾም የሚታሰብ ሲሆን በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረትም በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች ታስቦ ይውላል፡፡
በተለይም ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከንጋታው ጀምሮ እስከ ማምሻው በዕለቱ የተፈጸሙትን ክስተቶች በሰዓት ከፍላ በልዩ መንፈሳዊ ሥርዓትና በስግደት ታከብረዋለች ፦
✝ ዓርብ ጠዋት
ዓርብ ጠዋት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ ፊት በፍርድ አደባባይ መቆሙ ይታሰባል። የካህናት አለቆችና ሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ሊገድሉት በኢየሱስ ላይ ተማከሩ ፤ አስረውም ወሰዱት ፥ ለገዢው ለጰንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት።
✝ በ3 ሰዓት
ጲላጦስ በወቅቱ በነበረው ሕዝብ ግፊት መሠረት ወንጀለኛውን በርባንን ከእስር አስፈትቶ በምትኩ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠበት ፤ አካሉ እስኪያልቅም 6,666 የገረፉት ከሊቶስጥራ - ቀራኒዮ እርጥብ መስቀል አሸክመው የወሰዱበት ነው።
✝ በ6 ሰዓት
ኢየሱስ ክርስቶስን እጆቹን እና እግሮቹን ቸንክረው በቀራንዮ ጎልጎታ ተራራ በ2 ወንበዴዎች መካከል የተሰቀለበት ነው።
✝ በ9 ሰዓት
በእምነቱ አስተምሮ ይህ ሰዓት ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ከሥጋው በባሕርይ ሥልጣኑ የለየበት ወደ ሲዖል ወርዶም የታሠሩትን ሁሉ ያስፈታበት ነው።
✝ 11 ሰዓት
ዮሴፍ እና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብር እና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር የቀበሩበት ነው።
(Tikvah Ethiopia Family)
@tikvahethiopia
ኢትዮ ቴሌኮም
ተናፋቂው የትንሳኤ በዓል ፋሲካ
እንደ ሁልጊዜው ደምቆ እንዲፈካ
በፍጥነት ግንኙነት የበዓል ድባቡን ለማቅለም
ልዩ የትንሳኤ ጥቅል ከ ኢትዮ ቴሌኮም
እስከ 25% ቅናሽ የተደረገባቸውን የትንሳኤ ጥቅል በተለያየ የጊዜ ገደብ አማራጮች ማቅረባችንን በደስታ እንገልጻለን!
ጥቅሎቹን በቴሌብር ሱፐርአፕ ከተጨማሪ 10% ስጦታ ጋር እንዲሁም በማይ ኢትዮቴል፣ አርዲ ቻትቦት ወይም በ*999# ይግዙ፤ ለሚወዷቸውም በስጦታ እያበረከቱ መልካም ምኞትዎን ይግለጹ!
መልካም የትንሳኤ በዓል !
ተጨማሪ መረጃ ፦
/channel/telebirr
/channel/ethio_telecom
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#Kenya
በጎረቤት ኬንያ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 188 ደርሷል።
ካለፈው መጋቢት ጀምሮ በደረሰው አውዳሚ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 188 መድረሱን የሀገር አስተዳደር ሚኒስቴር አሳውቋል።
እስካሁን ያልተገኙ በርካታ ሰዎች መኖራቸውም ተገልጿል።
በኬንያና ሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች በተከታታይ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ የብዙ ሰዎች ህይወት እየጠፋ ሲሆን የከፍታ ቦታዎች መናድም ነዋሪዎችን ካለመጠጊያ አስቀርቷል፡፡
መንገዶችን ድልድዮችን እና ሌላም የመሰረተ ልማት አውታሮችን ውድሟል። #VOA
@tikvahethiopia
" በየጊዜው ወጣቶች የምገብርበት የጦርነት ምዕራፍ መዘጋት አለበት " - አቶ ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በኩል ዛሬ መልዕክት አሰራጭተው ነበር።
በዚህም ፤ " የህዝባችን ሁለንተናዊ መብትና ጥቅም ከማረጋገጥና አስተማማኝ ከማድረግ የሚቀድም ሌላ አጀንዳ የለንም " ብለዋል።
" የህዝባችን ጥቅምና መብት የሚያረጋግጥ መንገድ ሁሉ እንጓዘዋለን " ያሉት አቶ ጌታቸው " ጉዞው እንዲሳካ የህዝቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነው " ሲሉ አክለዋል።
ፕሬዜዳንቱ ፤ " ከሚገባው በላይ ያበረከተ ህዝብ በቅንነትና ታማኝነት ማገለገል ይገባል " ሲሉም ገልጸዋል።
" ህዝቡ ከጦርነትና ጦርነት ወለድ ችግሮች በማላቀቅ ወደ አስተማማኝ ሰላም እንዲሸጋገር መስራት ይገባል " ሲሉም አስገንዝበዋል።
አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ " በየጊዜው ትኩስ ሃይል የሆኑትን ወጣቶች የምንገብርበት የጦርነት ምዕራፍ ተዘግቶ ፤ የልማትና የእድገት ፍላጎታችን እንዲሳካ መስራት አለብን " ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር
በዓሉን ምክንያት በማድረግ እስከ 25% ቅናሽ የተደረገባቸውን ማራኪና ውብ የመመገቢያ ጠረጴዛዎቻችንን በመግዛት ልዩ የአብሮነት ጊዜ ያሳልፉ!
የዘመናዊነት ተምሳሌት!
አድራሻችን፦
1. ዊንጌት አደባባዩን ተሻግሮ: +251 995 27 2727 / +251 911 51 6843
2. ፒያሳ እሪ በከንቱ : +251 957 86 8686
3. ሲ ኤም ሲ አደባባዩን አለፍ ብሎ: +251 993 82 8282
👉 Telegram: /channel/yonatanbt_furniture
👉 Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100087238034736
👉 TikTok: yonatanbtfurniture" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@yonatanbtfurniture
👉 Instagram: https://www.instagram.com/yonatanbtfurniture/
የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን ብርሃኑ ተክለ ያሬድ በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 12:00 በፌዴራል ፖሊስ " #ለጥያቄ_ይፈለጋሉ " በሚል ከቤታቸው ተወስደው መታሠራቸውን ቤተሰቦቻቸው መናገራቸውን ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ዘግቧል።
ቀደም ብሎ ፥ የሰንበት ት/ ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ የሆኑት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶክተር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ ከቤታቸው በጸጥታ ኃይል መወሰዳቸውና ቤታቸው ላክ ፍተሻ መደረጉን የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን መዝገቡ ይታወሳል።
@tikvahethiopia
#ማኅብረቅዱሳን
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ የሆኑት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ ዛሬ ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤታቸው በጸጥታ አካላት መወሰዳቸውን የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ዘግቧል።
የሁለቱም አገልጋዮች የመኖሪያ ቤት መፈተሹም ተገልጿል።
በአሁኑ ሰዓት ሜክሲኮ ፌዴራል ፓሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ይገኛሉ የተባለ ሲሆን የተያዙበት ምክንያት እንዳልታወቀ የቴሌቪዥን ጣቢያው ገልጿል።
@tikvahethiopia
#AddisAbaba
" የ4 ሰዎች አስክሬን ከተለያየ ቦታ አውጥተናል። ...‘13 ሰዎች በጎርፍ ተወሰዱ’ የሚለው ትክክለኛ መረጃ አይደለም " - አቶ ንጋቱ ማሞ
ከቀናት በፊት “ ሰዓሊተ ምህረት ጀርባ ያድሩ የነበሩ 13 የጎዳና ተዳዳሪ ልጆች በጎርፍ ተወስደው ሕይወታቸው እንዳለፈ አካባቢው ላይ ተነግሯል ” ሲሉ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
በስፍራው የእሳት አደጋ ሠራተኞች ፣ ዋናተኞች፣ የፌደራል ፓሊስ አባላት ተገኝተው አስክሬን ለማውጣት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደተመለከቱ የገለጹ ሲሆን ፤ ቲክቫህ ኢትዮጵያም ስለጉዳዩ የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ሥራ አመረራር ኮሚሽንን ጠይቋል።
የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ በሰጡት ምላሽ፤ “ ባለፈው እንደገለጽነው የ4 ሰዎች አስከሬን አውጥተናል። ‘13 ሰዎች በጎርፍ ተወሰዱ’ የሚለው ትክክለኛ መረጃ አይደለም። ጥቆማ ከሆነ ሊሆን ይችላል ” ብለዋል።
“ ምክንያቱም በየትኛውም ጉዳይ ሕይወቱ ያለፈ ሰው ቢኖር ወይ እሳት አደጋ ወይ ፓሊስ ነው የሚያነሳው፤ በግለሰብ ደረጃ አስከሬን አንስቶ ቀብር ያለ አይመስለኝም ” ነው ያሉት።
“ በቦታው ነበርን ግን ይሄ አሁን የተጠቀሰው ቁጥር (13) አስከሬን አልተገኘም። ያገኘነው 4 አስከሬን ነው ” ያሉት አቶ ንጋቱ ፣ 4ቱን አስክሬን ለፓሊስ አስረክበናል ሲሉ አስረድተዋል።
4 አስክሬን የት አካባቢ ነው የተገኘው ? ለሚለው ጥያቄ፣ “ ሰዓሊተ ምህረትም፤ ከተለያዩ ቦታም ነው የገኘነው። ጎዳና ተዳዳሪ ይሁኑ፣ እዛው አካባቢ ነዋሪ ይሁኑ እኛ መረጃ የለንም። ፓሊስ ነው የሚያረጋግጠው ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
“ አሁን የሚሉት ጥቆማ ትክክለኛነቱ የሚረጋገጥ ከሆነ ከፓሊስ ጋር ሆነን ፍለጋ እናካሂዳለን። አንዳንድ ጊዜ ጥቆማ ትክክል አይደለም የሚል መደምደሚያ ላይኖር ይችላል” ሲሉ ተናግረዋል።
ጎርፉ ተቋማትን ጨምሮ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን፣ በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለው ኑሯቸውንና እንቅስቃሴያቸውን ወንዝ አካባቢ ባደረጉ ሰዎች እንደሆነ፣ ማህበረሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ፣ አደጋ ከደረሰም በ #939 የኮሚሽኑ ስልክ በፍጥነት ደውለው እንዲያሳውቁ አስገንዝበዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
/channel/LionBankSC
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ መጪዎቹን የትንሳኤ እና ፋሲካ በዓላት ምክንያት በማድረግ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን የሚያስገኙ የጥያቄና መልስ ውድድር ይዞላችሁ መጥቷል፡፡
እርስዎም የሽልማቱ ተሳታፊ ለመሆን ከታች ያሉትን የባንኩን ይፋዊ የቴሌግራም እና የፌስቡክ ገፆች በመቀላቀል እና ጥያቄውን ቀድመው በመመለስ ሽልማቶችን የራስዎ ያድርጉl
ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት የውድድሩ ተሳታፊ ይሁኑ!!
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!
[Telegram] [Facebook]
#LIB #lioninternationalbank #anbesabank #keytosuccess