tikvahethiopia | Unsorted

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1519094

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Subscribe to a channel

TIKVAH-ETHIOPIA

#EthiopianInvestmentHoldings

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕን ጨምሮ 8 ተቋማት ከአሁን በኃላ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እንደሚተዳደሩ ተነገር።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ 8 ተጨማሪ የመንግስት ድርጅቶችን በስሩ በማካተት ፖርትፎሊዮውን ማስፋቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (ኢኢሆ) በስሩ ከሚገኘትና ከሚያስተዳድራቸው የመንግስት የልማት ድርጅቶች በተጨማሪ 8 አዳዲስ ቁልፍ ተቋማትን በስሩ በማካተት የድርጅቶቹን ቁጥር ጨምሯል።

8ቱ ተቋማት እነማን ናቸው ?

- ኢትዮ ፖስት፣
- ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፐ
- የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት፣
- የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣
- የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን፣
- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣
- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን እና ለኢትዮ ፋርማ ግሩT ተጠሪ የሆኑት ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥቢታ ተቋምና ሺልድ ቫክስ ናቸው።

እነዚህ ቀደም ሲል ለመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታ እና አስተዳደር ተጠሪ የነበሩት የልማት ድርጅቶች ከአሁን ጀምሮ በባለቤትነት የሚተዳደሩትና የሚመሩት በኢኢሆ ስር ሆኗል።

(ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Namibia

በናሚቢያ ምርጫ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት አሸንፈዋል፡፡

የገዢው ስዋፖ ፓርቲ (SWAPO) እጩ የሆኑት ኔቱምቦ ናንዲ-ንዳይትዋህ ከ57 በመቶ በላይ ድምጽ በማግኘት ማሸነፋቸውን የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን አሳውቋል፡፡

ተቀናቃኛቸው ፓንዱሌኒ ኢቱላ ደግሞ 26 በመቶ ድምጽ አጊኝተዋል፡፡

የሎጂስቲክ ችግር እና በተወሰኑ አካባቢዎች የነበረን እስከ ሦስት ቀናት የዘለቀ የድምጽ አሰጣጥ መዘግየትን ተከትሎ የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበሉት ተቃዋሚው ኢቱላ አሳውቀዋል፡፡

በዚህም በመዲናዋ ዊንድሆክ ትናንት ማምሻውን ውጤቱ ይፋ ሲደረግ በርካታ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች አልተገኙም ነበር፡፡

የውጤቱን ይፋ መሆን ተከትሎ " የናሚቢያ ህዝብ ሰላም እና መረጋጋትን መርጧል " ሲሉ ተመረጯ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል፡፡

SWAPO ፓርቲ አገሪቱ ከቅኝ ግዛት ነጻ ከወጣችበት እንደ አውሮፓውያኑ 1990 ጀምሮ በስልጣን ላይ ይገኛል፡፡

ተመረጯ ፕሬዝዳንት በቅርቡ የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑ ሲሆን በተለያዩ የመንግስት ኃላፊነተች ላለፉት 25 ዓመታት አገልግለዋል፡፡

ተመረጯ ፕሬዝዳንት ከታንዛኒያዋ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሀሰን በመቀጠል በአፍሪካ ሁለተኛዋ ሴት ፕሬዝዳንት ይሆናሉ፡፡

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ኢየሱስ ይወዳችኋል ! " - ማርክ ጉዬ

➡️ የእስልምና እምነት ተከታዩ ሳም ሞርሲም የግብረሰዶማውያንን ምልክት ሳያደርግ ወደ ሜዳ ገብቶ ጨዋታውን አድርጓል !

ማርክ ጉዬ የተባለው እግር ኳስ ተጫዋች በድጋሚ ክንድ ላይ በሚጠለቀው የግብረሰዶማውያን ምልክት ላይ " ኢየሱስ ይወዳችኋል ! " የሚል ፅሁፍ በመፃፍ ወደ ሜዳ በመግባት ጨዋታውን አድርጓል።

ክሪስታል ፓላስ ለተባለው ክለብ የሚጫወተውና የቡድኑ አምበል የሆነው ጉዬ ከቀናት በፊት ኒውካስል ዩናይትድ ከተባለው ቡድን ጋር ሲጫወት ክንዱ ላይ ባጠለቀው የግብረሰዶማውያን ምልክት ላይ " ኢየሱስን እወደዋለሁ " ብሎ ፅፎ በመግባቱ የሊጉን አስተዳዳሪዎች አስቆጥቶ ነበር።

ይኸው ተጫዋች ትላንት ምሽት ቡድኑ ኢፒስዊች ታውን ከተባለው ቡድን ጋር ሲጫወት ክንዱ ላይ ባለው የግብረሰዶማውያን ምልክት ላይ በድጋሚ " ኢየሱስ ይወዳችኋል ! " ብሎ በመፃፍ በመግባት ጨዋታውን አድርጓል።

ባለፈው ቅዳሜ ከፃፈው " ኢየሱስን እወደዋለሁ ! " ከሚለው ፅሁፍ በኃላ ፉትቦል አሶሲዬሽን የተባለው የሊጉ አስተዳዳሪ " ኃይማኖታዊ ምልክቶች የእግር ኳስ ማሊያ እና ሌሎች ቁሳቁሶች ላይ መፃፍ ክልክል ነው " ሲል ለክለቡ እና ለአምበሉ ማስጠንቀቂያ ቢልክም ማስጠንቀቂያው ወዲያ በሉት ብሎ ትላንት ምሽት በድጋሚ " ኢየሱስ ይወዳችኋል ! " ሲል በመፃፍ ገብቶ ተጫውቷል።

የሊጉ አስተዳዳሪ ቅጣት ሊጥልበት ይችላል እየተባለ ነው።

በሌላ በኩል የእስልምና እምነት ተከታይ የሆነው ሳም ሞርሲ የተባለው የኢፒስዊች ታውን ተጫዋች ትላንትም የግብረሰዶማውያንን ምልክት ያለበትን የአምበልነት መለያ ሳያደርግ ነው የገባው።

ተጫዋቹ " ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም " በማለት ባለፈው ቅዳሜም ይህንን የግብረሰዶሞች ምልክት ሳያደርግ መግባቱ የሚዘነጋ አይደለም።

' እኩልነት እና ብዝሃነት ' በሚል ሰብሰብ በዓለም ላይ የግብረሰዶማውያንን እንቅስቃሴ ለማስተዋወቅ እና ሰዎች ጋር ለማድረስ የግብረሰዶማውያን ደጋፊዎች ብዙ አይነት መንገድ ይከተላሉ።

አንዱ ግብረሰዶማውያንን ለማስተዋወቅ የሚጠቀሙት በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ በተለይም ወጣት ተመልካቾች ያሉትን የእግር ኳስ ፍልሚያ ነው።

ከነዚህ የእግር ኳስ ፍልሚያዎች አንዱ ደግሞ በኢትዮጵያ / አፍሪካ ሆነ በዓለም ላይ ብዙ ተመልካች ያለውን እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ነው።

በዚሁ ሊግ የሊጉ አስተዳዳሪ አካላት በ ' እኩልነት እና ብዝሃነት ' ሰበብ የክለብ አምበሎች ክንዳቸው ላይ የግብረሰዶማውያንን ምልክት እንዲያጠልቁ አድርገው ለግብረሰዶማውያን ማስታወቂያ እንዲሰሩ ያደርጋሉ።

ይህንን የሚያደርጉት ደግሞ የሊጉ ፍልሚያ በሚጋጋልበት ወቅት ነው።

ግብረሰዶማውያን እና የነሱ ደጋፊዎች እጅግ በጣም ተወዳጁን የእግር ኳስ ፍልሚያን ተጠቅመው ግብረሰዶምን የሚያስተዋውቁት በልጆች ፣ ታዳጊዎች ፣ ወጣቶች ዘንድ ድርጊቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለማድረግና እነሱን ለማነሳሳት ነው።

#TikvahEthiopia
#Guehi #Christian  #PremierLeague
#SamMorsy #Muslim

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#TecnoAI

የስራዎች መደራረብ ህይወቶን ፕሮግራም አልባ አድርጎታል? በላቁ ቴክኖሎጂዎች የተዋቀረው አዲሱ ቴክኖ ኤ አይ ፕሮፌሽናል አጋዥ በመሆን ህይወቶን ለማቅለል እየመጣ ነው፡፡

ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመከተል የቴክኖ ቲክቶክ ገጽ Bio ላይ ያለውን ሊንክ ተጭነው በመመዝገብ ታህሳስ 10 በስካይላይት ሆቴል በሚካሄደው የሀገራችን ትልቁ በሆነው የኤ አይ ሁነት ላይ ይሳተፉ፡፡

tecnoet">tecnoet" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@tecnoet

@tecno_et @tecno_et

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

" ጊዜያዊ አስታዳደሩ የወሰደው እርምጃ ህዝቡን ወደአላስፈላጊ ቁጣና ግርግር የሚያስገባ ነው " - የመቐለ ከተማ ምክር ቤት አስተባባሪ ቋሚ ኮሚቴ 

የመቐለ ከተማ ም/ቤት አስተባባሪ ቋሚ ኮሚቴ የትግራይ ጊዚያዊ  አስተዳደር ከህዳር 23/2017 ዓ.ም ጀምሮ የሰጠው የመቐለ ከንቲባ ሹመት ከመቃወም አልፎ " ህገ-መንግስት የጣሰ ተግባር " ብሎታል። 

የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ህዳር 24/ 2017 ዓ.ም ከሰአት በኋላ ባወጣው የአቋም መግለጫ ፥ ህዳር 23/2017 ዓ.ም በመቐለ ከተማ አስተዳደር በምክር ቤት አብላጫ ድምፅ የተሾሙ ከንቲባ በስራ ላይ እያሉ የምክር ቤት እና የህዝብ ሉአላውነት በመጣስ ፓሊስ ስራቸው እንዳይሰሩ አግዷል ብሏል።

" በዚያው ቀን ከሰዓት በኋላ ህጋዊ ያልሆኑ ከንቲባ በአስተዳደሩ አንድ አዳራሽ መግለጫ እንዲሰጡ ተደርገዋል " ሲልም ገልጿል።

" በምክር ቤት በስርዓት የተሾሙ ከንቲባ ወደ ቢሯቸው እንዳይገቡ የመቐለ ፓሊስ ከህግ አገባብ ውጪ ፅህፈት ቤታቸው በማሸግ ህዝብ አገልግሎት እንዳይገኝ አስተጓጉለዋል " ሲል ከሷል።

" የፓሊስ ኢ-ህጋዊ ተግባር  አገልግሎት ያጣ ህዝብ ወዳልተፈለገ ሽብርና ቀውስ እንዲገባ አድርገዋል " ብሏል።

በተጨማሪ የቋም ኮሚቴው በመግለጫ ምን አለ ?

👉 " በህገ-መንግስት የተሰጠ ስልጣን በመቀማት አምባገነን ስርዓት ለመትከል የተፈፀመ ተግባር ነው ይህንን እንኮንናለን። የተፈፀመው አግባብነት የጎደለው ተግባር በአስቸኳይ እንዲታረም ጥሪ እናቀርባለን። "

👉 " የመቐለ ፓሊስ አመራር በህገ-መንግስት የተሰጠው ተግባርና ሃላፊነት ወደ ጎን በመተው የፈፀመው ህገ-ወጥ ተግባር በማስተካከል በምክር ቤት የተሾሙ ከንቲባ ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) ሳይውል ሳያድር  ስራቸው እንዲሰሩ እና አገልግሎት እንዲሰጡ እንዲያደርግ እንጠይቃለን "

👉 " የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች የተፈፀመው የህግ ጥሰት በመገንዘብ ህግ እንዲያከብሩ ጥሪ እናቀርባለን "

👉 " የመቐለ ከተማ ህዝብ ህገ-ወጥ ተግባሩ በመቃወም ከምክር ቤቱ ጎን እንዲሰለፍ ጥሪ እናቀርባለን "

👉 " የትግራይ ጊዚያዊ  አስተዳደር የምክር ቤቶች ሉአላዊ ስልጣን በመጣስ የወሰደው እርምጃ ህዝቡ ወደ አላስፈላጊ ቁጣና ግርግር የሚያስገባ መሆኑ በመገንዘብ በዚሁ በህገ-መንግስት ጥሰት የተሳተፉት አካላት በህግ እንዲጠይቃቸው ጥሪ እናቀርባለን "

... ብሏል።



በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የተሸሙት አዲሱ ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስ መደበኛ ህዝባዊ አገልግሎት መስጠት አንደሚጀምሩ ታማኝ ምንጮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መረጃ ሰጥተውታል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም !! "

" ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም ! " ያለው የእግር ኳስ ተጫዋች ግብረሰዶማውያን ለመደገፍ ሲባል ክንድ ላይ የሚጠለቀውን ምልክት ሳያደርግ ቀርቷል።

በዓለም ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ የእግር ኳስ ፍልሚያ አፍቃሪያን እንዳሉ ይታወቃል።

ከየትኛውም ሀገራት በላይ ደግሞ የአውሮፓ ሀገራት ውስጥ የሚካሄዱት ፍልሚያዎች እጅግ ብዙ ተመልካች ያላቸውና ከፍተኛ ተወዳጅነትን ከፉክክር ጋር ያጣመሩ ናቸው።

በተለይም የእንግሊዝ ፕሪሜየርሊግ በሀገራችን ኢትዮጵያ ሳይቀር እጅግ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያለውና ብዙ ተመልካች ያለው ነው።

ከህጻን እስከ አዋቂ፣ አዛውንቶች ሳይቀሩ ነው ፍልሚያውን የሚከታተሉት።

ነገር ግን በየዓመቱ ይህ የእግር ኳስ ፍልሚያ የሚደራበት ወር በተለይም ሃይማኖተኛ የሆኑ የእግር ኳስ ተመልካቾችን የሚያስቀይም ነው።

ምክንያት ? ሊጉ ውስጥ ግብረሰዶማውያንን ለመደገፍ ሲባል ዘመቻ ስለሚካሄድበት ነው።

ሰዎቹ " እኩልነትን ለማምጣት " ይበሉት እንጂ በበርካታ ሃይማኖተኛ እግር ኳስ ተመልካቾች እና ተጫዋቾች ዘንድ የሚወገዝ ተግባር ነው የሚፈጽሙት።

የፕሪሚዬር ሊግ ክለቦች ለግበረሰዶማውያን ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት አምበሎቻቸው የግብረሰዶማውያኑን መለያ ምልክት ክንዳቸው ላይ እንዲያጠልቁ ያደርጋሉ።

ይህን ዘመቻ የሚያደርጉትም እኤአ ከኅዳር 29 እስከ ታኅሣሥ 5 ነው።

ከቀናት በፊት በነበረ አንድ ጨዋታ ላይ ግን የአንድ ክለብ አምበል " እኔ ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም " በማለት ምልክቱን ሳያድረግ ቀርቷል።

የተጨዋቹ ስም ሳም ሞርሲ ይባላል ፤ ኢፕስዊች ታውን የተባለው ክለብ አምበል ነው።

በእምነቱም የእስላም እምነት ተከታይ ሲሆን የግብፅ ዜጋ ነው።

ይኸው ተጫዋች ነው ቡድኑ ኖቲንግሃም ፎረስት ከተባለው ቡድን ጋር በተጫወተበት ወቅት ክንዱ ላይ ምልክቱን " አላጠልቅም " ብሎ ጨዋታውን ያካሄደው።

ክለቡ ባወጣው መግለጫ ምልክቱን ያላደረገው " በሃይማኖቱ ምክንያት ነው ፤ ውሳኔውን እናከብራለን " ብሏል።

ክለቡ አክሎም ፤ የግብረሰዶማውያኑን ምልክት የሚያሳየውን የአምበሎች መለያ በኩራት እንደሚደግፍ ፤ ከግብረሰዶማውያን ማኅበረሰብ ጋር አብሮ እንደሚቆም ፤ እኩልነት እና ተቀባይነት እንዲንሰራፋ እንደሚሰራ ገልጿል።

ከሳም ሞርሲ በስተቀር ሌሎች የፕሪሚዬር ሊጉ አምበሎች የግብረሰዶማውያንን ባንዲራ አጥልቀው ሲጫወቱ ነበር።

#SamMorsy #PremierLeague #Muslim

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Ethiotelecom

የድኅረ ክፍያ የሞባይል ጥቅል ለድርጅትዎ በተመጣጣኝ ዋጋ!

💁‍♂️ በወር ከ270 ብር ጀምሮ በብዙ አማራጭ ቀርበዋል፤ የ2 ዓመት ውል በመግባት እስከ 45% የሚደርስ ተጨማሪ ስጦታ ያግኙ።

📍 በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የድርጅት አገልግሎት ማዕከል ጎራ ይበሉ!

ለተጨማሪ መረጃ https://bit.ly/3Zect70 ይጎብኙ!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #SmartAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#AddisAbaba

በተለያዩ ቀናት ከሦስት ድርጅቶች ስልክና ላፕቶፕ ሲሰርቅ በካሜራ ዕይታ የገባው ግለሰብ በፖሊስ እየተፈለገ ነው።

በአዲስ አበባ ከተማ በቂርቆስ እና በቦሌ ክፍለ ከተማ በቀናት ልዩነት በ 3 ድርጅቶች የላፕቶፕ እና የሞባይል ስልኮች ስርቆት በተመሳሳይ ግለሰብ መፈጸሙን ዝርፊያው የተፈጸመባቸው የንብረቱ ባለቤቶች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል ።

ግለሰቡ የስርቆት ድርጊቱን ፈጸመ የተባለው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት እና ሦስት እንዲሁም በቦሌ ክፍለ ከተማ ቦሌ መድኃኒአለም አቢሲኒያ ህንጻ አካባቢ ነው።

ለቲክቫህ ቃላቸውን የሰጡ ስርቆቱ የተፈጸመባቸው ግለሰብ "ህዳር ዘጠኝ ስምንት ሰዓት ላይ ወሎ ሰፈር አካባቢ የሚገኝ ህንጻ ስድስተኛ ፎቅ ወደሚገኝ ቢሮአችን ነጭ ቲሸርት እና ጅንስ ሱሪ አድርጎ የገባ ግለሰብ ሪሰፕሽን ላይ ሰው አለመኖሩን በማረጋገጥ ላፕቶፕ ይዞ ተሰውሯል" ብለዋል።

ግለሰቡ የስርቆት ድርጊቱን ሲፈጽም በድርጅቱ በተገጠመ የደህንነት ካሜራ የተቀረጸ ሲሆን ላፕቶፑን በቲሸርቱ ውስጥ በመደበቅ ይዞ ሲወጣ ይታያል።

ስርቆቱ የተፈጸመባቸው ግለሰብ ግለሰቡን የሚያውቀው ሰው ካለ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በደህንነት ካሜራ የተቀረጸውን ቪዲዮ ማጋራታቸውን ተናግረዋል።

መረጃውን በማህበራዊ ሚዲያ ካጋሩት በኋላ በቀናት ልዩነት እኛም በተመሳሳይ ሰው ተዘርፈናል የሚሉ ግለሰቦች እንዳነጋገሯቸው ገልጸውልናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ስርቆቱ የተፈጸመባቸው ሌላኛውን በዳይ በማነጋገር ዝርፊያው መፈጸሙን አረጋግጧል።

ግለሰቡ ቦሌ መድኃኒአለም አካባቢ ወደሚገኝ ህንጻ በመግባት ስርቆቱን የፈጸመው ህዳር 9 ሰኞ የስርቆት ድርጊቱን ከፈጸመ ከአምስት ቀናት በኋላ ማለትም ህዳር 14 ቅዳሜ ቀን ሲሆን በዕለቱ ጥቁር ቲሸርት እና ጅንስ ሱሪ በመልበስ ስልኮቹን ሲያነሳ በተመሳሳይ በደህንነት ካሜራ እይታ ውስጥ ገብቷል።

በቀናት ልዩነት አንድ ላፕቶፕ እና ሁለት ስልኮችን ከሁለት የተለያዩ ድርጅቶች ሰርቆ የተሰወረው ይህ ግለሰብ ጻጉሜ 4/2016 ዓም ቂርቆስ ክፍለ ወረዳ ሁለት ፍላሚንጎ አካባቢ በተመሳሳይ ሰው የስርቆት ድርጊት ተፈጽሞብኛል ያሉ ግለሰብም ቃላቸው ለቲክቫህ ሰጥተዋል።

"ፍላሚንጎ ሰንሻይን ኮንስትራክሽን አካባቢ ወደሚገኝ ቢሮአችን በመግባት ላፕቶፕ በመስረቅ ተሰውሯል ለፖሊስ ብናመለክትም ስሙንም ሆነ አድራሻውን ማወቅ አልተቻለም" ሲሉ ነግረውናል።


ሶስቱም ግለሰቦች በተመሳሳይ ሰው መሰረቃቸውን ያወቁት ወሎ ሰፈር ከሚገኝ ቢሮአቸው ላፕቶፕ የተሰረቁት ግለሰብ ተንቀሳቃሽ ምስሉን በማህበራዊ ሚዲያ ማጋራታቸውን ተከትሎ ነው።

የስርቆቱ ድርጊቱ የተፈጸመባቸው ግለሰቦች ውስጥ ሁለቱ የደህንነት ካሜራውን ምስሎች እና አስፈላጊውን መረጃዎች በመያዝ ለፖሊስ ቢያመለክቱም ግለሰቡ እስካሁን በቁጥጥር ስር አልዋለም።

ፖሊስ ምን አለ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን በመያዝ ጉዳዩን እየተከታተለ የሚገኘውን በአዲስ አበባ ፖሊስ የመስቀል ፍላወር አከባቢ ፖሊስ ጣቢያ አነጋግሯል።

ፖሊስ "በእኛ በኩል ሰውዬውን ለመያዝ በክትትል ላይ ነው የምንገኘው እስካሁን ገና አልተያዘም ቦሌ እና ቂርቆስ ላይ ወንጀሉን ፈጽሟል በክትትል ላይ ነው ያለነው " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

ግለሰቡን ያያቹ ወይም ያለበትን የምታውቁ ከታች በተቀመጡት ስልኮች በመጠቆም ትብብር እንድታደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

ለጥቆማ፡ 0114621442, 0911115656

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

" ውሳኔው በሌሎች ሴቶች ላይ ጥቃት ለመፈጸም የሚያስቡ ቆመም ብለው እንዲያስቡ የሚያስተምርና የሚያደርግ ነው " - አባት

በግፍ የተገደለችው የዓድዋዋ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ የፍርድ ሂደት ገዳዮች ላይ የሞት እና የእድሜ ልክ ፅኑ እስራት በማስተላልፈ እልባት አግኝቷል።

የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት ዛሬ ህዳር 23/2017 ዓ.ም ባዋለው ችሎት በተማሪ ማህሌት ግድያ የተጠረጠሩት ሁለት ግለሰቦች ወንጀለኝታቸውን አረጋግጦ ፍርድ ሰጥቷል።

አንደኛው ወንጀለኛ በሞት ሁለተኛው ደግሞ በፅኑ የዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በትግራይ ማእከላዊ ዞን ዓድዋ ከተማ ታግታ ከወራት መሰወር በኋላ ተገድላ ተቀብራ ስለተገኘችው ወጣት ማህሌት ተኽላይ ጉዳይ ካለፈው ዓመት 2016 ዓ.ም ጀምሮ ተከታታይ መረጃዎች ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወሳል።

ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ከሰጠ በኋላም የሟች አባት አቶ ተኽላይ አጭር አስተያየት ተቀብሏል።

የሟች አባት አቶ ተኽላይ " የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ እንደ ቤተሰብ ትክክል እና የሚሳምን ፤ በሌሎች ሴቶች ጥቃት ለመፈጸም የሚያስቡ ቆመም ብለው እንዲያስቡት የሚያስተምርና የሚያደርግ ነው " ብለውታል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የተሾሙት የመቐለ ከተማ  ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስ ስራቸውን በይፋ ጀመሩ።

ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ወደ ቢሮ ሲገቡ በከተማው አመራሮች ሰራተኞች አቀባበል እንደተደረገላቸው ተሰምቷል። 

ከንቲባው ዛሬ ዝግ ሰብሰባ የሚያደርጉ ሲሆን አብረዋቸው ከሚሰሩ አካላት ጋር ስለ ቀጣይ እቅዳቸው ይወያያሉ። 

አዲሱ የመቐለ ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስ በቀጣይ ስለ እቅዶቻቸው እና ስራዎቻቸውን ለሚድያ ይፋዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከአቀባበሉ ስነ-ሰርዓት አዘጋጆች ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Mekelle

በመቐለም ሁለት ከንቲባ መሾሙ ተሰማ።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ለመቐለ ከተማ አዲስ ከንቲባ ሾመ።

ከተማዋ በቅርቡ በም/ቤት ከንቲባ ተሹሞላት እንደነበር አይዘነጋም።

በጊዚያዊ አስተዳደሩ አዲስ የተሾሙት ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስ ህወሓት ለሁለት ሳይሰነጠቅ የፓለቲካ ፓርቲው የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩ ናቸው።

በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ይፋዊ ደብዳቤ የተሾሙት ብርሃነ ገ/የሱስ ከጦርነቱ በፊት የከተማዋ ምክትል ከንቲባ በመሆን ያገለገሉ ናቸው።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ባገኘው መረጃ አዲሱ ከንቲባ ከዛሬ ጀምሮ የከንቲባ ስልጣናቸው የሚፀና ይሆናል።

ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እሁድ 22/2017 ዓ.ም ከትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ወጣቶች ባደረጉት ውይይት ፤ " ሁለት ከንቲባ የሚባል አይሰራም ፤ አንድ ከንቲባ ነው ያለው ያውም መንግስት የመደበው ብቻ ነው። በምክር ቤት ስም የሚካሄድ ከንቲባ የመቀየር ሂደት ተቀባይነት የለውም ፤ ህገ-ወጥ አካሄዱ መልክ እንዲይዝ ይሰራል " ብለዋል።

ባለፈው ጥቅምት 2017 ዓ.ም በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) የከተማዋ ከንቲባ በማድረግ የሾመ ሲሆን የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሹመቱ ውድቅ ማድረጉ መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል።

ከቀናት በፊት ዒግራይ ላይ የአቶ ጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ዐለም አረጋዊን ከንቲባ አድርጎ ሲሾም በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ደግሞ ረዳኢ ገ/እግዚአብሔርን ከንቲባ አድርጎ መሾሙ ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia            

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

🛑 ውድ የምናከብራችሁ የቤተሰባች አባላት በሀሰተኛ ገጾች ተታላችሁ ጊዜያችሁን እንዳታባክኑ ገንዘባችሁንም እንዳትበሉ አደራ እንላለን።

በቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ መድረክ ስም በርካታ ሀሰተኛ ገጾች ተከፍተው በማስታወቂያ ስም ገንዘብ እንደሚሰበስቡ ከዚህ ቀደም አሳውቀናል።

እኚህ አጭበርባሪዎች አሁን በዚሁ ተግባራቸው ቀጥለዋል።

ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ስለሌላቸው ጥንቃቄ ታደርጉ ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን።

ከሰዎች ገንዘብ ለመሰብሰብ የሚያንቀሳቅሷቸው ገጾች እና ስልክ ቁጥሮች ከላይ ተያይዟል። ለሚመለከታቸው አካላትም ይድረስ !

የቲክቫህ ኢትዮጵያ መድረኮችን ሁሉ እናተው እስከ ገነባችሁት ድረስ ድምጻችሁን ማሰማት፣ ጥያቄያችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ።

ከዚህ ባለፈ ከትልልቅ ድርጅቶች በስተቀር ወጣት ስራ ፈጣሪዎች፣ ጀማሪዎች የሆናችሁ የቲክቫህ አባላት ለማስታወቂያ ምንም ክፍያ አይጠበቅባችሁም በነጻ መገልገል ትችላላችሁ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከመነሻው አንስቶ በየትኛውም አካል / ድርጅት / ተቋም የማይደገፍ ፣ ድጋፍም የማይጠይቅ ፣ ጠይቆም የማያውቅ መድረክ ነው።

መድረኩ በቀናና ሚዛናዊ አመለካከት ቅድሚያ ሰውነትን ባስቀደሙ ነገሮችን በማመዛዘን የሚመለከቱ ፣ ከጥላቻ እና ጎጂ አመለካከት የነጹ ዜጎችን በማሰባሰብ እርስ በእርስ መረጃ ለመለዋወጥ ፣ ለመተጋገዝ ፣ የአባላቱን ድምጽ ለማሰማት የሚንቀሳቀስ ብቻ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ ውድ ቤተሰቦቻችን በትክክለኛው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስም የሚንቀሳቀስ ፦

❌ ምንም አይነት አክቲቭ የYoutube ገጽ የለም።

❌ ምንም አይነት የTikTok (ቲክቶክ) ገጽ የለም።

❌ ምንም አይነት የFacebook ገጽ የለም።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ጉምሩክ

" ከስተም (ጉምሩክ) ውስጥ ተደራድሮ ገንዘብ የሚቀበል ሌባ ሰራተኛ (ሰነድ ምርመራ፣ ፍተሻ ...) እንዳለው ሁሉ ሀቀኛ ሰራተኛም አለ " - የጉምሩክ ኮሚሽን የሕግ ተገዢነት ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ባዘዘው ጫኔ

🚨" ሀቀኛ አስመጪዎች እንዳሉት ሁሉ ኔትዎርክ ፈጥረው ሃገሪቱን የሚመነትፉ አሉ !  "

👉 " በአክሰሰሩና ዋጋውን በሚተምነው እጅ ላይ ነው ያለነው ፤ እሱ ደስ ካለው ከተመቸነው ዝቅ ያደርጋል ካልተመቸነው ከፍ ያደርጋል ! " - አስመጪ

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ ከአስመጪዎች እና አምራቾች ጋር በነበረው የውይይት መድረክ በተሳታፊዎች በኩል ጉምሩክ ውስጥ ስላሉ ችግሮች ተነስቶ ነበር።

የጉምሩክ ኮሚሽን የሕግ ተገዢነት ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ባዘዘው ጫኔ በተገኙበት መድረክ ነው ከስተም (ጉምሩክ) ውስጥ ስላለው ችግር የተነሳው።

አንድ የመድረኩ ተሳታፊ ፤ " ከስተም ያሉ ሰዎች ለአንድ እቃ ብዙ አይነት ዋጋ ነው የሚሰጡት " ብለዋል።

" እኔ ከምን የመነጨ እንደሆነ አይገባኝም። አንዳንዴ የምትናደዱበት ሁኔታ ይፈጠራል። ምናለ ሞጆ ሄጄ ባስቀረጥኩ፣ ምናለ ቃሊቲ ባስቀረጥኩ እያላችሁ የምትናደዱበት ሁኔታ ይፈጠራል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ይሄ ከቅርንጫፍ ቅርንጫፍ ልዩነት አለው የቀረጡ ዋጋ ፤ እኔ በቅርብ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ያወጣሁት እቃ ስላለ ነው እንደዚህ ጨከን ብዬ የምናገረው " ብለዋል።

" ከቅርንጫፎች ባለፈ ደግሞ ያለው የክፍተት መጠን እንዲህ ነው ብሎ መናገር ይከብዳል  ፤ 6 / 7 አይነት ዋጋ አለ በቃ በአክሰሰሩና ዋጋውን በሚተምነው እጅ ላይ ነው ያለነው ፤ እሱ ደስ ካለው ከተመቸነው ዝቅ ያደርግልናል ችግር የለውም ካልተመቸነው ከፍ ያደርግብናል " ሲሉ ያለው ችግር አስረድተዋል።

የጉምሩክ ኮሚሽን የሕግ ተገዢነት ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ባዘዘው ጫኔ በጉዳዩ ላይ ምላሽ ሰጥተዋል።

በዚህ ባለፈው የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 10.4 ሚሊዮን ላይን አይተምን ዋጋ ፕሌት መደረጉን ጠቁመዋል።

ከቅርንጫፍ ቅርንጫፍ ዋጋ ይለያያል በሚለው ጉዳይ " በመሰረቱ ዋጋ በማዕከል ነው የሚደራጀው " ሲሉ መልሰዋል።

አቶ ባዘዘው ፥ " እናተ ጋር እንዳለው ሁሉ እኛም ጋር ከፍተኛ የስነምግባር ችግር አለ " ያሉ ሲሆን " ከስተምስ (ጉምሩክ) ውስጥ ሌባ አለ ተደራድሮ ገንዘብ የሚቀበል ፣ ፈታሽ ፣ ሰነድ ምርመራ አለ ስለምንጠይቃቸው፤ የምንጠይቀው አስመጪ አለ የምንጠይቀው ትራንዚተር አለ ፤ ስለ ትራንዚስተር ስላላወራችሁ ነው መሃል የሚደልል መአት አለ " ብለዋል።

በከስተም (ጉምሩክ) ውስጥ ሌባ ሰራተኞች እንዳሉ ሁሉ ስራቸውን በአግባቡ የሚሰሩ ሀቀኛ ሰራተኞችም አሉ ሲሉ ተናግረዋል።

ሀቀኛ አስመጪዎች እንዳሉት ሁሉ ኔትዎርክ ፈጥረው ሃገሪቱን የሚመነትፉ እንዳሉ በግልጽ አሳውቀዋል።

" እዚህ ቦታ ብፃአን አይደለም ያለው ሁሉም ቦታ ያለ ችግር አለ እሱን ለማስተካከል በጋር መስራት ይጠይቃል ፤ እንዲህ አይነት ጉራማይሌዎችን እያስተካከልን እንሄዳለን " ሲሉ ቃል ገብተዋል።

#TikvahEthiopiaFamily
#ጉምሩክ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#SavetheChildren #MoH

የህፃናት አድን ደርጅት (Save the children) በኢትዮጵያ በ3 ክልሎችበ16 ወረዳዎች የክትባት ተደራሽነትን ለማስፋፋት የሚረዳ “ቡስት” የተሰኘ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።

ድርጅቱ ፕሮጀክቱን ይፋ ያደደረገው ከጂኤስኬ ተገኘ በተባለ የገንዘብ ድጋፍ ፣ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ነው።

ፕሮጀክቱ በአማራ፣ ኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች በሚገኙ 16 ወረዳዎች ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።

ክትባት በሚስጥበት ወቅት ገጠራማ በሆኑ ቦታዎች ለትራንስፓርት አገልግሎት የሚረዱ 50 ታብሌቶች የተገጠሙላቸው 52 ሞተር ሳይክሎችን ድርጅቱ አበርክቷል።

ድርጅቱ ፥ “ በዚህ ፕሮጀክት ከ200 ሺሕ በላይ ልጆች እንዲከተቡ ይደረጋል ” ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ቲክቫህ ለህጻናቱ የሚሰጡት ክትባት የምን በሽታ መከላከያ ነው ? ሲል ላቀገበው ጥያቄ “ በጤና ሚኒስቴር የተቀመጡትን 13ቱንም ክትባቶች ሳፓርት እናደርጋለን ” የሚል መልስ ከድርጅቱ ተሰጥቷል።

ክትባቱ ፦
- ሚዝልስ፣
- ፓሊዮ፣
- ዲያሪያ፣
- ኒሞኒያና ከመሳሰሉ ህመሞች የሚከላከል ነው ተብሏል።

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴዔታ ዶ/ር ደረጄ ድጉማ “ በኢትዮጵያ ውስጥ ክትባት በአግባቡ ያልወሰዱና ጭራሽም ያልወሰዱ በርከት ያሉ ህፃናት አሉ ” ሲሉ ጠቁመዋል።

እኚህም ከ1 ሚሊዮን በላይ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።

እነዚህም ራቅ ያሉ ቦታዎች ላይ የሚገኙ ናቸው።

ምንም ክትባት ያላገኙና ጀምረው ያቋረጡ ህፃናት በአብዛኛው በአማራ፣ ኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች እንደሚገኙ በጥናት መረጋገጡን ገልጸዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-12-01

 #TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ምን አሉ ?

🔵 " ሕገ-መንግሥቱ ለውጥረት መንስዔ ከመሆኑም ባሻገር ሀገር ግንባታን የሚያስፋፋ አይደለም " - የኤርትራው ፕሬዝዳንት

የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትላንት ምሽት በመንግሥታቸው የቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው ስለወቅታዊ ጉዳዮች ቃለ-ምልልስ ሰጥተዋል።

ፕሬዝደንቱ ሶማሊያ፣ ግብፅ እና ሀገራቸው ኤርትራ ስለገቡት ስምምነት፣ በኢትዮጵያ በተለይ በትግራይ ክልል ስላለው ሁኔታ ተናግረዋል።

ምን አሉ ?

➡️ አሁን በኢትዮጵያ ያለው ግጭት እና ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላት አለመስማማት የመነጨው በአውሮፓውያኑ 1994 ተግባራዊ በሆነው ሕገ-መንግሥት ነው (ብሔር ተኮር አሰራር የዘረጋ)። ሕገ-መንግሥቱ ለውጥረት መንስዔ ከመሆኑም ባሻገር ሀገር ግንባታን የሚያስፋፋ አይደለም።

➡️ ኢትዮጵያ ከራሷ ጋር ሰላም ካልፈጠረች ቀጣናው ለሚያስፈልገው መረጋጋት፣ ትብብር እና መቻቻል አዎንታዊ አስተዋፅዖ አይኖራትም።

➡️ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት እንዲሁም ለ20 ዓመታት ያክል በባድመ ምክንያት በሁለቱ ሀገራት መካከል ሰፍኖ የቆየው ውጥረት የዚህ ፖሊሲ ውጤት ነው።

➡️ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ለነበረው የድንበር ግጭት የውጭ ኃይሎች ተጠያቂ ናቸው። በኢትዮጵያ አዲስ አስተዳደር [የዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት] ከመጣ በኋላ የተቀሰቀሰውም ጦርነት በዚህ አግባብ ሊታይ ይገባል።

(ፕሬዝደንቱ በቀጣናው እንዲሁም በመላው የአፍሪካ ቀንድ ግጭት እያስፋፉ ነው ያሏቸው የውጭ ኃይሎችን ማንነት በስም አልጠቀሱም)

➡️ ህወሓት በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ ' አልቀበልም ' ብሎ ጦርነት ውስጥ በመግባት ኤርትራ ውስጥ ከ70 በላይ ዒላማዎችን በረዥም ርቀት ሮኬት መትቷል።  የኤርትራ መንግሥት ህወሓት ከዚህ ድርጊቱ እንዲቆጠብ ያቀረበው ጥሪ ሰሚ አላገኘም።

➡️ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኋላ በአማራ ክልል ግጭት ተከስቷል። ከዚህ ጋር በተያያዘ በመንግሥታችን ላይ የሚነሳውን ወቀሳ አንቀበልም። ደም አፋሳሽ ጦርነት ውስጥ ከመግባት ሁሌም እንደሚቆጠቡ ነው የምናሳስበው።

➡️ ዓላማችን በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን ነው። የውጭ ኃይሎች ጣልቃ እንዲገቡ ክፍተት ላለመፈጠር እንሰራለን።

🔴 በትግራይ ክልል በተካሄደው ጦርነት የኤርትራ ሠራዊት መሳተፉ ይታወሳል። በዛም እጅግ በርካታ ግፍ እና የጦር ወንጀል በመፈጸም ይከሰሳል። ጦርነቱን ካስቆመው የፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ ግን የኤርትራ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ግንኙነት መቀዛቀዝ ተስተውሎበታል።

ከግብፅ እና ሶማሊያ ጋር ስላደረጉት ስምምነት ምን አሉ ?

ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የባሕር በር የማግኘት የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራረመች በኋላ ከሶማሊያ ጋር አለመግባባት ውስጥ እንደገባች ይወቃል።

ግብፅም በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ምክንያት ከኢትዮጵያ ጋር አለመግባባት ውስጥ እንዳለች ይታወቃል።

ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ መተላለፊ እንዲሁም ሚና እንዲኖራት ያላትን ፍላጎት ይፋ ካደረገች በኋላ በቀጥታም ባይሆን ኤርትራ ደስተኛ አለመሆኗን ስታሳይ ነበር።

በዚህም የሶማሊያው ፕሬዝዳንት አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በኤርትራ ከሦስት ጊዜ በላይ ጉብኝት አድርገዋል።

በተጨማሪም ሶማሊያ ከግብፅ ጋር የወታደራዊ ስምምነት መፈራረሟን ተከትሎ አሥመራ ላይ የተፈረመው የጋራ ስምምነት ከኢትዮጵያ አንጻር መሆኑ በተደጋጋሚ ሲነገር ቆይቷል።

ነገር ግን የኤርትራው ፕሬዝዳንት ይህንን አስተባብለዋል።

ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ፦

👉 የውጭ ኃይሎች እና አቀንቃኞች በመገናኛ ብዙኃን እና በማኅበራዊ ሚዲያ የሚያሠራጩት የተዛባ መረጃ እና ዘመቻ በቀጣናው ግጭት ያባብሳል።

👉 ይህ በመገናኛ ብዙኃን ላይ የሚሠራጨው የመነጨው ከልብ ለኢትየጵያ ከማሰብ አይደለም።

👉 በሦስቱ ሀገራት መካከል የተደረሰው ስምምነት ዋና ዓላማው በቀጣናዊ መረጋጋትን ማስፈን ነው።

👉 የኤርትራ ዋና ፍላጎት በመላው የአፍሪካ ቀንድ፣ በአባይ ተፋሰስ እና በቀይ ባሕር አጎራባች ሀገራት መረጋጋት እና ትብብር እንዲኖር ነው።

👉 ኤርትራ በፍፁም ኢትዮጵያ ያለመረጋጋት ውስጥ ገብታ የማየት ፍላጎት የላትም። በቀጣናው ሀገራት መካከል የሚደረሱ ስምምነቶች ያለመተማመንን ይቀርፋሉ፤ ፍሬያማም ናቸው።

... ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ነው የወሰደው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

“ ችግራችን ብዙ ነው። ዘርፈ ብዙ የሆነ ምላሽ ያስፈልገናል ” - ማኀበሩ

የአካል ጉዳተኞችን ዘርፈ ብዙ ችግሮች መንግስትን ጭምሮ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሁሉ ትኩረት እንዲሰጡ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ አካል ጉዳተኞች ማኀበር በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል በአጽንኦት አሳሰበ።

የማኀበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሴ ጥላሁን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ብዙ ጉዳዮች ላይ ሕጎች የሉም። እንደሚባለው አይደለም። በቂና ተፈጻሚ ሕጎች አሉ ማለት አይቻልም” ብለዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ በዝርዝር ምን አሉ?

“ለምሳሌ ዓይነ ስውራንን በተመለከተ በተለይ ገጠር አካባቢ ያሉት ህፃናት ብሬል/የሚፅፉበት ማተሪያል ያስፈልጋቸዋል።

የኮሚፒዩተር አቅርቦት እንኳ ቢኖር ለመጠቀም የሚያስችል ስክሪን/ማንበቢያ ሶፍትዌር ያስፈፍጋል። ያ የለም።

በዘርፉ የሰለጠኑ ብሬል ማስተማር የሚችሉ መምህራን የሉም ለዓይነ ስውራን። መስማት የተሳናቸው ወገኖች ውስጥ የምልክት ቋንቋ የሚችል የለም ማለት ይቻላል።

በከፊል መስማት የተሳናቸው የመስሚያ መርጃ መሳሪያ ቢያገኙ ከማህበረሰቡ ጋር መቀላቀልና መማር ይችላሉ። በተለይ በገጠር አካባቢ ያሉ ያሉ አካል ጉዳተኞች በባትሪ የሚሰሩ ጠንካራ ዌልቸሮችን ተደራሽ ማድረግ ያስፈልጋል።

ችግራችን ብዙ ነው። ዘርፈ ብዙ የሆነ ምላሽ ይፈልጋል። አመለካከትን፣ ተጠያቂነትን ከማስፈን አኳያ ብዙ የሚቀሩ ሥራዎች አሉ።

➡️ የትምህርት መብት፣
➡️ የመስራት መብት፣
➡️ የተደራሽነት መብት፣
➡️ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት፣
➡️ የመኖሪያ ቤት መብት፣
➡️ ከቀረጥ ነጻ የአካል ጉዳተኞች መገልገያ እቃዎች አገር ወደ ውስጥ እንዲገቡ ከማድረግ የሚያስችል ሁኔታ፣
➡️ የአካል ጉዳተኞችን ሁኔታ በበላይነት የሚመራ ራሱን የቻለ ተቋም ከማቋቋም አኳያ፣
➡️ ሕጉን የሚጥሱ አካላት ላይ ተጠያቂ ማድረግን የሚያስችሉ ሁሉን አቀፍ አሰራሮች ያስፈፍጋሉ።

አንድ ጊዜ ሕግ ማውጣት ብቻም በቂ ላይሆን ይቻላል። ለምሳሌ የአካል ጉዳተኞች የሥራ ስምሪት ዐዋጅ የሚባል አለ። ከወጣ 17 ዓመታት ሆነው። 

ነገር ግን በቂ በቂ መመሪያ እንኳ በየጊዜው እየተሻሻለለት አይደለም። ለማሻሻልም ምንም አይነት እንቅስቃሴ ተደርጎ አያውቅም”
ሲሉ ተናግረዋል።

ከ20 ሚሊዮን በላይ የአካል ጉዳተኞች ከ90 በመቶ በላይ ህፃናት የትምህርት እድል እንደሌላቸው፣ 95 በመቶ ከድኀነት ወለል በታች እንደሚኖሩ፣ 98 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ምንም አይነት የገቢ ምንጭ የሌላቸው ወይም ተቀጥረው የማይሰሩ መሆናቸው ተነግሯል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#MPESASafaricom

🎁 ስድስት ወር ሙሉ ዳታ እንደልብ! በየትኘውም ሰአት ያልተገደበ ፍጥነት እና ደስታ!  ለረጅም ጊዜ የሚቆዩትን ሜጋ የኢንተርኔት ጥቅሎች በM-PESA በመግዛት እስከ 1,000 ብር የሚደርስ ቅናሽ አግኝተን ፏ እንበል! 🌐🤳 ከሳፋሪኮም አስተማማኝ ኔትወርክ ጋር ወደፊት!⚡


🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle


#SafaricomEthiopia #1Wedefit
#Furtheraheadtogether

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በምክር ቤት የተሾሙትን አመራር በግርግር ነው ከፅህፈት ቤቱ ያወጣው " - በድብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ትላንት ምሽት መግለጫ አውጥቷል።

ደርጅቱ በመግለጫው ለአቶ ጌታቸው ረዳ ሰጥቷቸው የነበረው የፕሬዜዳንት ውክልና አንስቶ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት እንዴት እና በማን እንዲሚተኩ ከፌደራል መንግስት እየተወያየበት እንደሚገኝ አስታውሷል።

' ቡድን ' ሲል የገለፀው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራውን የጊዚያዊ አስተዳደር በመምራት ላይ የሚገኘውን ህወሓት " የህዝብ ውክልና የያዙ ምክር ቤቶች እውቅና በመንሳት እና ውሳኔዎቻቸው በመጣስ በማን አለበኝነት ምስለኔዎች በመሾም አስተዳደራዊ እና ህዝባዊ ስራዎች እያደናቀፍ ይገኛል " ሲል ከሷል።

የአቶ ጌታቸው ረዳ ቡድን ህገ-መንግስት ላይ የተቀመጠውን የህዝብ እና የመንግስት ከፍተኛ መገለጫ የሆነው የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በመጣስ በህዝብ ላይ አምባገነንነት ለመጫን በሙሉ አቅሙ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል ብሏል።

" ህዳር 23/2017 ዓ.ም በመቐለ ምክር ቤት የተሾሙትን አመራር በግርግር ከፅህፈት ቤቱ በማውጣት በራሱ ምስሌኔ የአስተዳደሩ ፅህፈት ቤት ለመቆጣጠር መክሮዋል " ሲል አክሏል።

" ህገ-ወጥ ሙከራው ከግለሰባዊ አምባገነንነት የሚነሳ ነው " ያለው በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ፤ አባላቱ ትግላቸው አጠናክረው እንዲቀጥሉ በማስታውስ ፣ የፀጥታ እና የፍትህ አካላት ህጋዊ ተጠያቂነት ፣ ህግ እና ስርዓት እንዲያስከብሩ በማለት ጥሪ አቅርቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia   

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ልመና አልነበረም ማለት አይደለም ፤ አሁን ግን እየተባባሰ ሄዷል ! ... የኑሮ ውድነቱን መቋቋም አቅቶት ህብረተሰቡ መድረሻ እያጣ ነው " - አቶ አበረ አዳሙ

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ 8ኛ መደበኛ ሰብሰባው አድርጎ ነበር።

በዚህም ወቅት ከም/ቤት አባላት ለንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።

ሚኒስትሩም ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል የሆኑ አቶ አበረ አዳሙ ምን ጠየቁ ?

" 1. በዓለም አቀፍ ተጨባጭ ሁኔታዎች ምክንያት ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦች ዋጋ የኑሮ ውድነቱን እያናረው ከመሆኑንም በላይ በተለይ በሀገር ውስጥ ምርቶች ላይ የሚደረገው ምክንያት የለሽ ጭማሪ የህዝቡን ኑሮ እንዲመሰቃቀል አድርጎታል።

ለምሳሌ ፦
- ጤፍ
- ስንዴ
- ምስር ... ሆነ ሌሎች የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶች በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ቢሆኑም በጥራት እና በብዛት ገበያ ላይ አይገኙም ፤ ቢገኙም ዋጋቸው እጅግ የተጋነነ በመሆኑ በቀላሉ የሚቀመስ አይደለም።

የችግሩ ምንጭ ደግሞ ሰው ሰራሽ መሆኑ አይካድም።

ህጋዊ ነጋዴው በኮንትሮባንድ ነጋዴዎች እና ለደላላ እየተጠለፈ መስራት ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል።

በዚህ የተነሳ ' ልጆቼን የማበላቸው አጣሁ ' የሚሉ አዛውንቶች፣ ' ጋሽዬ ቁራሽ የዳቦ መግዣ ስጠኝ ራበኝ ' የሚሉ አንጀት የሚበሉ በርካታ ህጻናትን ማየት በከተማችን እየተለመደ መጥቷል።

ልመና አልነበረም ማለት አይደለም አሁን ግን እጅግ እየተባባሰ ሄዷል።

ደላላው ዋጋ ይተምናል ፤ ደላላው ዋጋ ይሰቅላል ቢፈልግም ያወርዳል ለዚህም አንድ ወቅት የሱዙኪ መኪና ዋጋን ሰማይ አድርሶ መሬት አስልሶት የነበረበትን አጋጣሚ ማስታወስ ይቻላል።

በአጭር አነጋገር ደላላ የንግዱን ስርዓት /ሲስተም እንደ ተባይ ወሮታል። በዚህም የኑሮ ውድነቱን መቋቋም አቅቶት ህብረተሰቡ መድረሻ እያጣ ነው።

ጥቅሙን የሚያገኘው  በጋ ከክረምት ደም ታፍቶ ያመረተው አርሶ አደሩ ቢሆን መልካም ነበር።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶ ህገወጥ ነጋዴዎች እና ደላላዎችን ስርዓት ሊያሲዝ የሚችል ዘላቂነት ያለው ስራ ከመስራት ይልቅ አልፎ አልፎ ወይም የሆነ አጋጣሚ ሲፈጠር ' ይሄን ያህል የንግድ ድርጅቶችን አሽኩ / ልናሽግ ነው ' እያሉ በመገናኛ ብዙሃን ማስታወቂያዎችን ከማስተጋባት የዘለለ ፦
° የንግድ ተቋማቱ በምን ምክንያት እንደታሸጉ
° ምን አይነት ህጋዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው
° የማሸጉ እርምጃ ምን ውጤት እንዳስገኘ
° የንግድ ድርጅቶቹ ከታሸጉ በኃላ የመጣንው ለውጥ ለህዝቡ ሲያሳውቅ አይታይም።

በኑሮ ላይ ጠብ የሚል ለውጥ አይስተዋልም።

ታዲያ የሀገራችንን ገበያ እየመራ ያለው ንግድ ሚኒስቴር ነው ወይስ ደላላና ህገወጥ ነጋዴ ?

2. ለንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተጠሪ የሆነው የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ከሚቆጣጠራቸው ተቋማት አንዱ መብራት ኃይል ነው። (በየጊዜው የመዋቅር መቀያየር ለውጥ ካለ ይቅርታ ጠይቃለሁ!)

ይሁን እንጂ የመብራት ተደራሽነት እና አግልግሎት አሰጣጥ በእጅጉ የተበላሸ ነው።

👉 ተደራሽነቱ ፍትሃዊነት የጎደለውና ለማዳረስ የተሞከረው ለረጅም አመታት የተተከሉ ፖሎች ሳይቀር ያለ አገልግሎት የቆሙበት፤

👉 ተዳረሰ የተባለውም በኃይል መቆራረጥ ችግር ተጠቃሚውን የሚያሰቃይ፤

👉 አገልግሎቱን ለማግኘት ያለ እፍረት በእጅ መንሻ / ጉባ ካልሆነ በቀር የማይሰራ ሰራተኛ የበዛበት ነው።

የሚያሳዝነው ደግሞ ጉቦ ወንጀል መሆኑ ቀርቶ መብት እስኪመስል ድረስ ዋጋ ተምነው ' ይህን ያህል አምጣ ' የሚሉ ሰራተኞች መብዛታቸው ነው።

በዚህ ከቀጠለ ምናልባትም ፓርላማውን ' የምቀበለው ጉቦ አንሶኛል እና ህግ አውጡልኝ ' ማለት የቀራቸው ይመስላል።

ይህ የእርሶን ተቋም ብቻ የሚመለከት አይደለም በርካታ ተቋማትን የሚያካትት ነው።

ክቡር ሚኒስትር ለመሆኑ ለእርሶ ተጠሪ የሆነው ባለስልጣን መ/ቤት ህዝቡን እያስለቀሰ የሚቀጥለው እስከመቼ ነው ? ይህንን ተቋም መቆጣጠርና ስርዓቱን ማስያዝ ያልተቻለው ለምንድነው ?

3. የኑሮ ውድነቱን ከሚያባብሱ ምክንያቶች አንዱ ነዳጅ ነው።

የዋጋው ማሻቀብ ምክንያቱ የሚታወቅ ቢሆንም ከዋጋው በላይ ሰልፉ ህዝቡን እያማረረ ይገኛል።

ከእጥረቱም በላይ ነዳጅ ለመቅዳት በሚደረግ ረጃጅም ሰልፍ ምክንያት የስራ ሰዓት ያለ አግባብ እየባከነ፣ የትራፊክ ፍሰቱን እያስተጓጎለ፣ እንዲያውም ሲል በህገወጥ መንገድ ነዳጅ ከሀገር እንዲወጣ ሰፊ በር እየከፈተ መሆኑን እማኝ መጥቀስ የሚያስፈልግ አይመስለኝም።

ክቡር ሚኒስትር ይህንን የተበላሸ አሰራር ስርዓት ማስያዝ የማን ኃላፊነት ይመስሎታል ? እባክዎ ለዚህ የተከበረ ም/ቤት እና ለብዙሃኑ የሀገራችን ህዝብ ተገቢውን መልስ ይስጡ። "

ሚኒስትሩ ምን ምላሽ ሰጡ ? ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-12-03

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" እኔ ኢየሱስ ክርስቶስን እወደዋለሁ !! "

በሀገራችን ኢትዮጵያ ጨምሮ በመላው ዓለም ላይ በቢሊዮኖች ተመልካች ያለው የእንግሊዝ ፕሪሜየርሊግ ግብረሰዶማውያንን ለመደገፍ በሚል በየአመቱ ዘመቻ ያደርጋል።

ይህንን ዘመቻ የሚያደርገውም በእያንዳንዱ ክለብ አምበል ክንዶች ላይ ግብረሰዶማውያንን የሚገልጸውን ባዲራ / እንዲያደርጉ በማድረግ ነው።

ይህን የሊጉን ተግባር እጅግ በርካታ ሃይማኖተኛ ደጋፊዎች እና ተጫዋቾች ነው የሚያወግዙት።

በዘንድሮው ዓመት የሊጉ ፍልሚያ ኢፒስዊች ታውን የተባለው ክለብ አምበል እና የእስልምና እምነት ተከታዩ ሳም ሞርሲ " እኔ ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም " በማለት የግብረሰዶማውያንን ምልክት ሳያደርግ ቀርቷል።

ከዚህ ባለፈ ግን አንድ የሌላ ክለብ ተጫዋችና አምበል የክርስትና እምነት ተከታይ ክንዱ ላይ ምልክቱን ቢያደርግም ከላይ " እኔ ኢየሱስ ክርስቶስን እወደዋለሁ !! " የሚል ፅሁፍ ፅፎ በመግባቱ የሊጉን አስተዳደሮች እንዳስቆጣ በዚህም ቅጣት ሊጣልበት እንደሚችል ተሰምቷል።

ተጫዋቹ ማርክ ጉሂ ይባላል ፤ እድሜው 24 ሲሆን የአይቮሪኮስት ዝርያ ያለበት የእንግሊዝ ዜጋ ነው።

የሚጫወትለት ክለብ ክርስታል ፓላስ የሚባል ነው።

ይኸው ተጫዋች ነው ባለፈው ቅዳሜ ኒውካስትል ከተባለው ሌላኛው የሊጉ ክለብ ጋር ጨዋታቸውን ሲያደርጉ ግብረሰዶማውያንን የሚደግፈውን ምልክት ክንዱ ላይ ቢያጠልቅም ከላዩ " እኔ ኢየሱስ ክርስቶስን እወደዋለሁ ! " የሚል ፅሁፍ ፅፎበት በመግባት ጨዋታውን አድርጓል።

በዚህም የሊጉን አስታዳዳሪዎች አስቆጥቶ ቅጣት ሊጥሉበት እንደሆነ ተነግሯል።

የእንግሊዝ ፕሪሜየርሊግ ግብረሰዶማውያንን ለመደገፍ በየዓመቱ አምበሎች የግብረሰዶማውያን ምልክት የሆነውን የተለያየ ቀለም ያለው ምልክት በክንዳቸው አጥልቀው እንዲጫወቱ ያደርጋል።

#Guehi #Christian #PremierLeague

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ሹመት

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከሰሞኑን 6 አዳዲስ ሹመቶች ሰጥተዋል።

ከስድስቱ ሽመቶች ሁለቱ በደብረፅዮን ገ / ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የተሾሙትን በማንሳት የተሰጠ ነው።

በዚሁ መሰረት ፕሬዜዳንቱ ከህዳር 20/2017 ዓ.ም  ጀምሮ የሚፀና በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የመቐለ ከንቲባ በመሆኑ የተሾሙት ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) በመሻር በብርሃነ ገ/ዮሱስ ተክተዋል።

የትግራይ ትምህርት ቢሮ ምክትል የስራ ሃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተው ከህዳር 17/2017 ዓ.ም ጀምሮ በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የዓዲግራት ከንቲባ በመሆን የተሾሙት ረዳኢ ገ/ሄር ምትክ ኪ/ማርያም ወ/ሚካኤል ምክትል የቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

ፕሬዜዳንቱ በጡሮታ በተገለሉት ሓዱሽ ካሱ ምትክ ዶ/ር ገብሩ ካሕሳይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ምክትል ፅሕፈት ቤት ሃላፊ አድርገዋቸዋል።

ኮማንደር ተስፋይ ገ/ማርያም በምክትል ኮሚሽነር መዓርግ የወንጀል ማጣራት ሃላፊ ፤ ኮማንደር ጌታቸው ኪሮስን በምክትል ኮሚሽነር መዓርግ የወንጀል መከላከል ሃላፊ እንዲሁም አቶ ሃይላይ ኣብራሃ በምክትል ኮሚሽነር መዓርግ የሰው ሃይል ልማት ዘርፍ ሃላፊ አደርገው ሹመዋል።

በቅርቡ የግድያ ሙከራ እንደተደረገባቸው በተናገሩት የትግራይ ማእከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰለሞን መዓሾ ምትክ ጉዕሽ ግደይ ሓድጉ የትግራይ ማእከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ደብዳቤ መሾማቸው ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia 

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የቀድሞ / ነባር ነኝ አይደለሁም የሚለውን ከፓሊስ እንነጋገርበታለን ፤ ያኔ ግልፅ ይሆንላቸዋል !! " - አቶ ጌታቸው ረዳ

ባለፈው ሳምንት ህዳር 17/2017 ዓ.ም በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በሚመራው ህወሓት ቡድን ምክትል ሊቀ መንበር የሆኑት አቶ አማኒኤል አሰፋ በሰጡት መግለጫ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን " የቀድሞ ፕሬዜዳንት " ሲሉ ጠርተዋቸው ነበር።

ህዳር 22/2017 ዓ/ም በመቐለ ከተማና ዙሪያዋ ከሚገኘው ደቡባዊ ምስራቃዊ ዞን ከተውጣጡ ወጣቶች ጋር የተወያዩት ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በመድረኩ ለአቶ አማኒኤል ንግግር በስሜትና ኃይለ ቃል በመጠቀም " እሳቸው ለሚገኙበት ቡድን " ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?   

" ባለፈው ጊዜ አንድ ሃላፊ ነኝ ባይ በመንግስት ሚድያ ' ነባር / የቀድሞ ፕሬዜዳንት ' ሲል ሰምታቹሃል ? ተልካሻ ነው። የቀድሞ / ነባር ነኝ አይደለሁም የሚለውን ከፓሊስ እንነጋገርበታለን ፤ ያኔ ግልፅ ይሆንላቸዋል።

እነዚህ አንድ ቀን ቁምነገር ሰርተው አያውቁም። መዋቅራቸው ስርቆት ላይ የተሰማራ ነው። አሁን የልዩነት ነጥቡ ፓለቲካ መሆኑ ቀርቷል። 

የኔ ሳምንት ይሁን ወር በዚህ ወንበር መቆየት ያን ያህል አያሳስበኝም ፤ ይህን አደገኛ ቡድን ግን የወንጅል ትስስር (Crime network ) ነው የሚመራው።

በሰሜን ምዕራብ ማእከላዊ ዞኖች ወርቅ ፣ መዳብ እና ሌላ ማዕድናት ያካተተ ዘረፋ የሚያካሄደው ይህን በወንጀል የተሳሰረ ቡድን ነው ፤ ስለሆነም ዞኖቹን ከሱ ቁጥጥር ውጪ እንዲወጡ ፍላጎት የለውም።

ቡድኑ ይህን የዘረፋ ባህሪ አሁን ያመጣው አዲስ ነገር አይደለም ፤ የቆየበት ነው ፤ ሃሜት አይደለም እየነገርኳችሁ ያለሁት ተደራጅቶ እየዘረፈ ነው ያለው።

በስንፍናችን ይሁን ድንገት ወደ ስርቆት ኔትወርክ ያልገባን ሰዎች አለን። ስለሆነም እነዚህን ያለ የሌለ ውሸት ፈጥሮ ስማችን በማጥፋትና በማጠልሸት ' ከጨዋታ ውጪ ማድረግ አለብን ' ብለው ነው በኛ ላይ የዘመቱት።

ስለዚህ ይህንን የቡድኑን ተግባር እንደ ፓለቲካ ሳይሆን እንደ ሌብነት ነው መቆጠር ያለበት፤ ስለሆነም ቡድኑ አንድ እሱን የመሰለ ሌባ አቀፎ ለመያዝ የመጣበት አከባቢ ሳይለይ አባሉ ያደርገዋል " ብለዋል። 


#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#SafaricomEthiopia

የምስራች! 🥳 💫 ፈጣኑን 4G ኔትወርካችንን የኩምሳ ሞረዳ መቀመጫ ወደ ነበረችው: በቡና እና በቂቤ የምትታወቀውና ለምለም ወደ ሆነችው ነቀምቴ ይዘን መጥተናል::

ፈጣኑን ኔትወርክ ዛሬውኑ እንቀላቀል!🙌🏼


#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit
#Furtheraheadtogether

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ተሾሙ።

የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ከሕዳር 23/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳዳር ሆነው መሾማቸውን ገልጿል።

ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ መሐመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ይታወሳል። #ENA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ፍሬዘርበቀለ👏

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሴኪዩሪቲ ክፍል ባልደረባ የሆኑት አቶ ፍሬዘር በቀለ ህዳር 16 ቀን 2024 ዓ.ም ከመንገደኛ ወድቆ ያገኙትን 50,000 የአሜሪካ ዶላር በታማኝንት ለመንገደኛው ማስረከባቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገልጿል።

አየር መንገዱ " ባልደረባችን በኢትዮጵያዊ ጨዋነትና ሲቀጠሩ በገቡት ቃል መሰረት አየር መንገዱ የሚመራበትን መርህና ሥነ ምገባር እንዲሁም ሙያዊ ታማኝነታቸውን በብቃት በመወጣት አስመስክረዋል " ብሏል።

" አየር መንገዳችን ዓለም-አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እና ስነ-ምግባር የተላበሰ የደንበኞች አገልግሎት ምንግዜም ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋል " ሲል አክሏል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Sidama

🔴 " በብልፅግና ፓርቲ መዋጮ ምክንያት አባላትና አመራሮች እየታሰሩብኝ ነው " -የሲዳማ ህዝብ አንድነት ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ሲህአዲድ)

🔵 " በፓለቲካ አቋሙና አመለካከቱ የታሰረ የፖለቲካ ፓርቲ አባልና አመራር የለም " - የሲዳማ ክልል ፖለቲካ ፖርቲ የጋራ ምክር ቤት

🚨" የታሰርነዉ ለሁለት ፖርቲዎች መዋጮ አናዋጣም ስላልን ነው " - የሲህአዲድ አባላትና አመራሮች


የሲዳማ ህዝብ አንድነት ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ሊቀመንበር እና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል አቶ ሠለሞን ቡሮዳ የፓርቲያቸው አባላትና አመራሮች " ለብልፅግና  ፖርቲ መዋጮ አናዋጣም " በማለታቸዉ እየታሰሩና በሐሰት እየተወነጀሉ ሲሉ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቀረቡ።

በክልሉ ከጥቅምት ወር መገባደጃ ጀምሮ በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች አባላትና አመራሮቻቸው ሰበብ እየተፈለገ ሲታሰሩና ሲፈቱ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

አሁን ላይ ደግሞ በአባላቶቻቸው ላይ ሐሰተኛ ክስ እየተፈበረከባቸዉ መሆኑን ጠቁመዋል።

በአንዳንድ ወረዳዎች ማሸማቀቅ ተበራክቷል ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

ለአብነትም ፦
- ወንሾ፣
- ጠጥቻ፣
- ጎርቼ፣
- ቦና ዙሪያ፣
- ቡርሳ፣
- ጫቤ ጋምቤልቱ፣
- ሸበዲኖ፣
- ጭሬና በንሳ ወረዳዎች አባላትና አመራሮቻቸው " የብልፅግና ፓርቲ መዋጮ ለምን አታዋጡም " በሚል ለእስር ተዳርገዉ እንደነበር አንስተዋል።

አቶ ሠለሞን ፤ " አሸናፊዉ ፓርቲ ብልፅግና ነዉ፤ ሁሉም ለብልፅግና ፓርቲ የህንፃ ግንባታ  መዋጮ የማዋጣት ግዴታ አለበት " የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ በአንዳንድ ወረዳዎች በግልፅ እየተስተዋለ ነው ብለዋል።

" በዚህ ሁኔታ የሚደረጉ ኢ-ሕገ መንግስታዊና የሁሉም ፖለቲካ ፓርቲዎች የቃል ኪዳን ሰነድ በሚፃረርር መልኩ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በአስቸኳይ ሊቆሙ ይገባል " ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ የሲዳማ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢና የኢሶዴፖ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የደቡባዊ ቀጠና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ በለጠ ሲጄቦ አነጋግሯል።

ቅሬታ መቅረቡን አልሸሸጉም።

ቅሬታውን ተከትሎ ምክር ቤቱ የታሰሩ ሰዎች እንዲፈቱ በማድረግ ኮሚቴ ተሰይሞ የማጣራት ሥራ መስራቱን ገልጸዋል።

በዚህም የታሰሩት ግለሰቦች በደረቅ ወንጀል የተጠረጠሩ አንጂ በፖለቲካ አቋማቸዉና አመለካከታቸዉ ምክንያት እንዳልሆነ መረጋገጡን አሳውቀዋል።

ከ2013 ዓ/ም ጀምሮ የፓርቲው የወረዳ አባል መሆናቸውን የሚገልጹት የጠጥቻ ወረዳ ነዋሪ አቶ አስራት ወርሶ ግን " ለሁለት ፓርቲ መዋጮ አላዋጣም በማለቴ ታስሬ ነበር " ሲሉ ስለእስራቸው ምክንያት ይገልጻሉ።

ከአንድ ቀን እስር በኋላም የፓርቲው አመራሮች ባቀረቧቸዉ መረጃዎች ምክንያት ከእስር መለለቃቸዉን አስረድተዋል።

የሲዳማ ህዝብ አንድነት ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የሁላ ወረዳ ስራ አስፈፃሚ መ/ር ሀንሳሶ በበኩላቸው " እኔም አባላቶቻችን ለምን ታሰሩ " በሚል ልንጠይቃቸዉ በሄድንበት ከሁለት አባላት ጋር ታስረን ነበር ሲሉ " ተጨማሪ ምስክርነት ሰጥተዋል።

አክለውም " ለብልፅግና ፓርቲ የሕንፃ መሰሪያ መዋጮ ካላዋጣችሁ በሚል በአባላትና አመራሮቻቸዉ ላይ በበርካታ ወረዳዎች እየደረሰ ያለዉ ጫና ስጋት ዉስጥ ከቶናል " ሲሉ ገልጸዋል።

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ እና የገዢዉ ብልፅግና ፓርቲ ሃሳብ ለማካተት ያደረግነዉ ሙከራ ያልተሳካ ሲሆን ኃሳባቸውን እንዳገኘን የምናካትት ይሆናል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ብርሃን_ባንክ
#ይቀበሉ_ይመንዝሩ_ተጨማሪ_ያግኙ

ከውጪ ሃገራት የሚላክልዎትን ገንዘብ ከብርሃን ጋር ከሚሰሩ አለምአቀፍ የገንዘብ አስተላላፊዎች #ሪያ #ዳሃብሽል #ዌስተርን_ዩኒየን #መኒግራም #ትራንስ_ፋስትና #ወርልድ_ረሚት ሲቀበሉ ወይም በእጅዎ ያለውን የውጭ ሃገር ገንዘብ በባንካችን ሲመነዝሩ ተጨማሪ ያገኛሉ!
#moneytransfer #Stressfreebanking #berhanbank #bank #finance #bankinethiopia

ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ!
➡️ Facebook
➡️ Telegram
➡️ Instagram
➡️ Twitter
➡️ LinkedIn
➡️ YouTube

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#መቄዶንያ❤️

🔵 “ የጎዳና ኑሮ ከባድ ነው፣ የ85 ዓመት እናቶች ተደፍረው የመጡበት አጋጣሚዎች አሉ። ጎዳና ላይ ሰዎች በብርድ ምክንያት ይሞታሉ” - የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ

🔴 “ ኢትዮጵያዊያን እባካችሁ ወደ ቀልባችን እንመለስ። ሰውን በመግደል፣ በማፈናቀል የምናገኘው ጥቅም የለም። ሰውን በመርዳት ግን ጥቅም ይገኛል ” - ቀሲስ ታጋይ ታደለ

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ከመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማኀበር ጋር በመተባበር ለመጀመሪያ ጊዜ በመቄዶንያን ቅጥር ግቢ ውስጥ አረጋዊያን በተገኙበት ዛሬ የጸሎት መርሀ ግብር አዘጋጅቶ ነበር።

ጸሎቱን የሰባቱም የሃይማኖት ተቋማት አባቶች ሁሉም በዬእምነታቸው መርሀ ግብሩን በጸሎት አስጀምረው፣ የጸሎት መርሀ ግብሩ ተከናውኗል።

የጸሎት ፕሮግራሙ ዓላማ አረጋዊያንን ጋር ተኩኖ ቢጸለይ ፈጣሪ ሰላሙን፣ ፍቅሩን እንደሚሰጥ በማሰብ እንዲሁም የካቲት 1 ቀን 2017 ዓ/ም በሚደረገው ለመቄዶንያ ርዳታ የማሰባሰብ መርሃ ግብር ሁሉም ኢትዮጵያውያን ርብርብ ያደርጉ ጥሪ ለማቅረብ ነው።

የመቄዶንያ መስራች የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ ምን አሉ?

“ እንደሚታወቀው መቄዶኒያ የዘር፣ የሃይማኖት፣ የጾታ ልዩነት ሳያደርግ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ነው የሚረዳው።

ሁሉም የእምነት ተከታዮች በመቄዶንያ አሉ። መቄዶንያ ውስጥ ፕሮቴስታንቶች፣ ሙስሊሞች፣ ኦሮቶዶክሶች፣ ካቶሊኮች አሉ።

እንዲያውም የሚጠበቅብን ምግብ፣ ልብስ መጠለያ ማሟላት ነው። ነገር ግን ከሚጠበቅበት በላይ ድርጅቱ መንፈሳዊ ፍላጎቶችንም ጭምር እያሟላ ይገኛል።

ዛሬ ስለመጣችሁ በጣም ደስ ብሎናል ምክንያቱም ሁሉም የሃይማኖት ተከታዮች እዚህ ስላሉ እናንተን ሲያዩ በጣም ደስ ይላቸዋል። ወደፊትም በሚመቻችሁ ጊዜ እንደዚሁ እየመጣችሁ ብትጎበኙን በጣም ደስ ይለናል።
 
በአሁኑ ወቅት በጣም በርካታ ሰዎች እየረዳን እንገኛለን። 5 ወለል ያለው ህንጻ እየገነባን እንገኛለን። በክልሎችም እንደዚሁ በተለያዩ ቦታዎች ግንባታዎች እየተፋጠኑ ይገኛሉ።

ደሴ፣ ድሬዳዋ፣ ጋምቤላ፣ ኮንሶ፣ ሞያሌ፣ ያቤሎ፣ ጅማ፣ አምቦ፣ ዓዲግራት፣ ዓድዋና ሌሎችም ቦታዎች መቄዶንያ አለ። በተለይ ደግሞ እኛ የምንረዳቸው የአልጋ ቁራኛ፣ የጎዳና ነዋሪ የሆኑ ሰዎችን ነው። 

የጎዳና ኑሮ በጣም ከባድ ነው፣ የሚገርማችሁ የ85 ዓመት እናቶች ተደፍረው እዚህ የመጡበት አጋጣሚዎች አሉ። ጎዳና ላይ ሰዎች በብርድ ምክንያት ይሞታሉ። ብርድ የመታቸው ሰዎች ወደ ህክምና የሚወስዳቸው የለም ”
ብለዋል።

በመሆኑም የካቲት 1 ቀን 2017 ዓ/ም በሚደረገው ዓለም አቀፍ ገቢ የማሰባሰብ መርሀ ግብር፣ ሁሉም አካላት ከወዲሁ ዝግጅት እንዲያደርጉ በ8,000 አረጋዊያን ስም ጥሪ አቅርበዋል።

በመርሀ ግብሩ የተገኙት የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የበላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በበኩላቸው፣ መርሀ ግብሩ የተዘጋጀው ከአረጋዊያኑ ጋር ቢጸለይ ፈጣሪ ጸሎት ይሰማን ተብሎ ታስቦ መሆኑን አስረድተዋል።

ቀሲስ ታጋይ ምን አሉ ?

“ ዛሬ በመቄዶንያ የተገኘነው ሁለት ጉዳዮችን መሠረት አድርገን ነው። አንደኛው ጸሎት ለማድረግ ነው። 

በአገር ሰላም ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የድርሻቸውን እንዲወጡ በማሰብ ጸሎት ማድረግና የሰላም ጥሪ የቀረበላቸው ወገኖች ወደ ሰላም እንዲመለሱ አስቸኳይ ሁኔታ ለመፍጠር የተደረገ ነው።

ሁለተኛው በመቄዶንያ የተገኘንበት ምክንያት በመቄዶንያ ከ8,000 የሚልቁ ለችግር የተጋለጡ፣ ጎዳና ላይ የወደቁ ኢትዮጵያዊያን ምዕመናን፣ ሙስሊሞች ክርስቲያኖች በኀብረት አሉ።

ስለዚህ ከእነርሱ ጋር ሆነን ብንጸልይ፣ ወደ ፈጣሪ ብናነባ ፈጣሪ ምህረት፣ ቸርነት ያደርግልናል በሚል እሳቤና መቄዶንያም መደገፍ ስላለበት ድጋፍ እንዲደረግለት በዚሁ አጋጣሚ ጥሪ ለማቅረብ ነው።

ስለዚህ ኢትዮጵያዊያን እባካችሁ ወደ ቀልባችን እንመለስ። ሰውን በመግደል፣ በማፈናቀል የምናገኘው ጥቅም የለም። ሰውን በመርዳት ግን ጥቅም ይገኛል። ሰላምን በማረጋገጥ ግን ጥቅም ይገኛል ”
ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ፍራንኮቫሉታ

የጉሙሩክ ኮሚሽን በፍራንኮ ቫሉታ ግዢ የተፈፀመባቸው ሽቀጦች ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ዉስጥ ወደ ሃገር እንዲገቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

በፍራንኮ ቫሉታ ከውጭ የሚገቡ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች በመደበኛ የንግድ ባንኮች የመተማመኛ ሰነድ /LC/ አማካኝነት እንዲገቡ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስትር ማስታወቁ ይታወሳል።

የጉምሩክ ኮሚሽን ህዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም. በፃፈዉ ደብዳቤ በፍራንኮ ቫሉታ ግዢ የተፈፀመባቸው ሸቀጦች በአንድ ወራት ባነሰ ጊዜ ዉስጥ ብቻ ወደ ሃገር ዉስጥ መግባት እንዳለባቸው አሳስቧል።

ኮሚሽኑ ይህን ያስተላለፈው የገንዘብ ሚኒስቴርን ዉሳኔ ተከትሎ መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን ለሁሉም ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች እንዲያዉቁት አድርጓል።

መንግስት በመሰረታዊ የንግድ ሸቀጦች ላይ የምርት እጥረት እንዳይከሰት በማሰብ ለግል ባለሀብቶች ፍራንኮ ቫሉታ መፍቀዱ ይታወሳል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት ፍራንኮ ቫሉታ መሰረታዊ ሸቀጦችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት የምርት እጥረት እንዳይከሰት የተወሰነ እገዛ አድርጓል፡፡

ይሁን እንጂ የፍራንኮ ቫሉታ ባልተገባ መንገድ ለጥቁር ገበያ በመጋለጡ በውጭ ምንዛሬ ላይ ጫና በማሳደር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ አመዝኗል ሲሉም ሚኒስትሩ ተናግረዋል ።

መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦችን በፍራንኮ ቫሉታ ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት ውሳኔ ሙሉ በሙሉ እንዲቆም መደረጉንም የገለፁት አቶ አህመድ ሽዴ " በሂደት ላይ ያሉ ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦች በሁለት ሳምንታት ውስጥ እንዲገቡ እንደሚደረግም " ተናግረው ነበር።

የጉምሩክ ኮሚሽን ከ ከጥቅም 28 ቀን 2017 ዓ.ም. በፊት የንግድ ሸቀጦች በፍራንኮቫሉታ ግዢ የተፈፀመባቸውን ሰነዶች በቅርንጫፍ ጽ/ቤት ያስመዘገቡ እና በዋና መስሪያቤት በኩል የተረጋገጡ አስመጪዎች በአንድ ወር ዉስጥ የንግድ ሸቀጣቸዉን አጠቃለዉ ወደ አገር ዉስጥ እንዲያስገቡ ነዉ ማሳሰቢያ የሰጠዉ።

መረጃው የካፒታል ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#DStvEthiopia

⚽️አዲስ ነገር ለኳስ አፍቃሪያን...

ሁሉንም ታላላቅ ሊጎች፣ ሁሉንም የቡድን ወኔ እንደ ምርጫችን በዲኤስቲቪ!

ℹ️ ሁሉንም የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎችን፣ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ፣ ሎችም ዋና ዋና እግር ኳስ እና ምርጥ ምርጥ መዝናኛዎችን ያካተቱ ከ125 በላይ ቻናሎችን በወር በ1699 ብር ብቻ!

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et
ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#DStvEthiopia  #ሁሉምያለውእኛጋርነው

Читать полностью…
Subscribe to a channel