tikvahethiopia | Unsorted

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1519086

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Subscribe to a channel

TIKVAH-ETHIOPIA

#Somaliland

የአዲሱ የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዱረህማን መሀመድ አብዱላሂ (ኢሮ) በዓለ ሲመት በሀርጌሳ እየተከናወነ ይገኛል።

በበዓለ ሲመቱ ላይ የቀድሞ ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ፣ የቀድሞ ፕሬዜዳንት ዳሂር ሪያሌ ካሂን፣ የአሜሪካው አምባሳደር ሪቻርድ ሪሌይን ጨምሮ የሀገራት ዲፕሎማቶች ተወካዮች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ፕሬዜዳንት ሙስጠፋ ሙሁመድ በዚሁ የበዓለ ሲመት ስነ ስርዓት ላይ ለመገኘት ትላንት ልዑካቸውን ይዘው ሀርጌሳ መግባታቸው ይታወሳል።

ከሶማሊያ ተነጥላ ላለፉት በርካታ አመታት ራሷን የምታስተዳድረው ሶማሊላንድ በሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲሁም ደግሞ በዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ ምርጫ በግንባር ቀደምነት ትታወቃለች።

ቪድዮ፦ አዲሱ የሶማሊላንድ ፕሮዜዳንት እና የቀድሞው ፕሬዜዳንት በፈገግታ ተሞልተው ወደ አዳራሽ ሲገቡ።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ሶማሊያውያኑ ምን እያሉ ነው ?

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሶማሊያውያን በተለይም አክቲቪስቶች " ሀሰን ሼክ ሀገራችንን ሸጠብን ፤ በዲፕሎማሲ ተበልጦ አስበላን " ማለት ጀምረዋል።

ኢትዮጵያ የሶማሊያን ሉላዓዊነት፣ አንድነት እና የግዛት አንድነት ባከበረ ሁኔታ ዘላቂነት ያለው አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ የባህር በር ታገኛለች መባሉ የሶማሊያ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን አበሳጭቷቸዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ በተለይ በX ቪላ ሶማሊያ ገጽ ስር ፤ ከወራት በፊት ሲያሞጋግሷቸው የነበሩትን ፕሬዜዳንታቸውን ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ላይ ውግዘት ማዝነብ ጀምረዋል።

እኚህ አስተያየት ሰጪዎች ምን እያሉ ነው ?

➡️ " ሀሰን ሼክ ባህራችንን ሸጠብን። ካደን ፤ ከሀዲ ነው "

➡️ " እንዴት በድርድሩ ላይ ሆነ በስምምነቱ ላይ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር ያደረገችው የባህር በር ለማግኘት የፈረመችው የመግባቢያ ስምምነት / MoU አልተነሳም ፤ በግልጽ ቀርቷል ለምን አልተባለም "

➡️ " አዋረደን ! ለሶማሊያ ጨለማ ቀን ነው "

➡️ " ስለ ኢትዮጵያ የቀጣይ የሰላም ማስከበር ተሳትፎ (ሶማሊያ ውስጥ) ለምን አለተነሳም "

➡️ " ዘላቂነት እና አስተማማኝ የባህር በር ኢትዮጵያ ስታገኝ ሶማሊያ በምላሹ ምን ታገኛለች ? "

➡️ " ሁሉንም ኢትዮጵያ የፈለገችውን ነው የተቀበልነው፤ ኢትዮጵያ በመረጠችው መንገድ ሄዳ ፤ በዚህም በዚያ ብላ ባህር በር ስታገኝ እኛ ምን አገኘን ? " 

➡️ " ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲው እና ድርድሩ በልጣ ባህር በር አሳካች " ... የሚሉ አስተያየቶችን በመስጠት ፕሬዜዳንታቸው ላይ ውግዘት እና የስድብ ናዳ እያወረዱ ነው።

አንዳንዶቹ ከቦታው ይነሳልን ወደማለትም ገብተዋል።

120 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ የባህር በር ጉዳይ " በፍጹም የማልተወው የህልውዬ ጉዳይ ነው " ብላ በይፋና በድፍረት አደባባይ ከወጣች በኃላ ጉዳዩ ከፍተኛ አጀንዳ ሆኖ ዓለም አቀፍ መወያያ መሆን ችሏል።

ከሶማሌላንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ከተፈራረመች በኃላ ሶማሊያ አኩርፋ ብዙ ስትል ከርማለች ፤ ከኢትዮጵያ ጋርም ተጎረባብጣለች።

ፕሬዜዳንቷ እና አስተዳደራቸው በየጊዜው ወደ ሚዲያ እየወጡ ፦
- ከኢትዮጵያ ጋር በፍጹም አንነጋገርም፤
- የኢትዮጵያ ወታደሮች በሰላም ማስከበር ላይ አይሳተፉም፤
- እንድንነጋገር ከፈለገች MoU ቀዳ ጥላ በይፋ ይቅርታ ትጠይቅ ይህ ካልሆነ ኢትዮጵያን አንሰማትም፤
- በኢትዮጵያ ያሉ ታጣቂዎችን እንደግፋቸዋለን / እናስታጥቃለን፤
- ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ደሟን እንዳልገበረችላት የኢትዮጵያ እድገት እንቅልፍ ከሚነሳቸው አካላት ጋር እየሄደ ጥምረት ሲፈጥር
- ከኢትዮጵያ ለመነጋገር ቅድመ ሁኔታዎችን ሲደረድር ... ሲዝት ፣ ሲፎክር ከርሟል።

በመጨረሻ በቱርክ አሸማጋይነት አንካር ሄደው ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

በስምምነቱ ይፋዊ ሰነድ ላይ ሆነ በመሪዎች መግለጫ ምንም ቦታ ላይ ስለ ሶማሊለንዱ MoU አለመነሳቱ ፤ ማብራሪያ አለመሰጠቱ እንዲሁም በግልጽ ተሰርዟል አለመባሉን በማንሳት " ኢትዮጵያ የምትፈልገውን አገኘች " በማለት ሶማሊያውያን በፕሬዜዳንታቸው ላይ ተነስተዋል።

#TikvahEthiopia
#Ethiopia🇪🇹
#Seaaccess

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#TecnoAI

ዘምኖ የሚያዘምኖ፣ ህይወቶን የሚያቀል፣ ከበርካታ አርቴፊሻል ቴክኖሎጂ ካመጣቸው ከፍ ያሉ ቴክኖሎጂዎች ጋር የሚያስተዋውቆት በኪስዎት ውስጥ ይዘውት የሚዞሩት ፕሮፌሽናል አጋዥ ቴክኖ ኤ አይ ወደ እርሶ እየመጣ ነው፡፡

ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመከተል የቴክኖ ቲክቶክ ገጽ ፎሎው በማድረግ እና Bio ላይ ያለውን ሊንክ ተጭነው በመመዝገብ ታህሳስ 10 በስካይላይት ሆቴል በሚካሄደው የሀገራችን ትልቁ የኤ አይ ሁነት ላይ ይሳተፉ፡፡

tecnoet" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@tecnoet

@tecno_et @tecno_et

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Ethiopia #Somalia

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ስምምነት ላይ ደረሱ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አሸማጋይነት በቱርክ አንካራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

(ዝርዝር መረጃዎችን ይጠብቁ)

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Tigray

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ፤ በምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ የሚመራውን ህወሓት " በትግራይ ህዝብ ብሄራዊ ክህደት የፈፀመ ቡድን " ሲል ፈረጀ።

በምክትል ሊቀ-መንበር ጌታቸው ረዳ የሚመራውን ህወሓት " ብሄራዊ ክህደት ፈፅሟል " ሲል የፈረጀው ማእከላዊ ኮሚቴ " ቡድኑ ከአፍራሽ ተግባሩ እንዲቆጠብ " መላው የትግራይ ህዝብ እና አባላት እንዲታገሉት ሲል ጥሪ አቅርቧል።

ማእከላዊ ኮሚቴ ፤ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት " የትግራይ ህዝብ መብት እና ራስን በራስ የማስተዳደር መገለጫ የሆኑት ምክር ቤቶች እንዲፈርሱ ለፌደራል መንግስት ጠይቀዋል " ሲል ገልፀዋል።

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስተር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ካካሄደው ውይይት መልስ ባወጣው መግለጫው ነው ይህን ጠንከር ያለ ፍረጃ ያቀረበው።

በተጨማሪ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት የትግራይ ሉአላዊ ግዛት ሳይረጋገጥ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ሳይመለሱ የትግራይ ሰራዊት በዲሞብላይዜሽን (DDR) ምክንያት በችኮላ እንዲሰናበቱ እያደረገ ነው ብሏል።

በትግራይ በኩል የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ፈራሚን ጥያቄ ውስጥ በሚከት መልኩ ፤ " የፕሪቶሪያ ውል ፈራሚ ባለቤት ማን እንደሆነ የኢትዮጵያ መንግስት እንዲወስን " በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት ጠይቀዋል ሲልም አክሏል።

በክልሉ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እየተካሄደ ነው ከሚባለው ህገ ወጥ የወርቅ ማእድን ማውጣት እና ማዘዋወር ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያን በትግራይ ክልል ከኤርትራ በሚያዋስኑዋት አከባቢዎች የአገር መከላከያ ሰራዊት እንዲሰፍር በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት ለፌደራል መንግስት ጥያቄ እንዳቀረበም በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ገልጿል።

እስካሁን በእነ አቶ ጌታቸው ረዳ በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Jubaland #Somlaia

ከሶማሊያ ፌዴራል መንግስት ጋር ሁሉንም ግኑኝነቴን አቋርጫለሁ ፤ ተቆራርጫለሁ ያለው የጁባላንድ አስተዳደር እና የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ዛሬ ወደ ግጭት ገብተዋል።

ዛሬ ከቀትር ጀምሮ ራስኮምቦኒ ላይ ከፍተኛ ውጊያ መደረጉ ተነግሯል።

ሁለቱም ወገኖች ግጭት መነሳቱን ገልጸው ግጭቱን ማን አስጀመረ በሚለው ላይ እርስ በእርስ እየተወነጃጀሉ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#SafaricomEthiopia

🎉ለወራት የፈለግናቸውን ኳስ ጨዋታዎች ሁሉ ከዳር እስከ ዳር በሚገኘው በሳፋሪኮም ኔትወርክ ላይ በDSTV በቀጥታ እንከታተል! ⚽️

በM-PESA ላይ ስንገዛ የ6ወር 90ጊባ በ6,000 ብር ብቻ! 

🔗የM-PESAን ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቦታችንን /channel/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉/channel/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #1Wedefit
#Furtheraheadtogether

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Berbera

የሶማሌላንድ የገንዘብ እና ልማት ሚኒስቴር ዛሬ በሶማሌላንድ በርበራ ወደብ የኢትዮጵያ ትራንዚት ማሳለጫ ቢሮ ስራ መጀመሩን ገልጿል።

የሶማሌላንድ የንግድና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አብዲረሺድ ኢብራሂም ደግሞ " የሶማሌላንድ መንግሥት በበርበራ ወደብ የኢትዮጵያ ትራንዚት ማሳለጫ ቢሮ ስራ አስጀምሯል " ሲሉ ይፋ አድርገዋል።

" ይህ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ ምዕራፍ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ ውጥን ቀጠናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ለማጠናከር ሶማሌላንድ ያላትን ቁርጠኝንተ ያሳያል ሲሉ አክለዋል።

ቢሮው በወደቡ የሚራገፉ ጭነቶችን ወደ ኢትዮጵያ የተለያዩ መዳረሻዎች እንዲጓጓዙ የሚያሳልጥ ነው ተብሏል።

በሌላ በኩል ፥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን በይፋዊ ማስጀመሪያ ስርዓቱ ላይ ወደቡን የሚያስተዳድረው የተባበሩት አረብ ኤሜሬትሱ DP World በርበራ ዋና ስራ አስፈፃሚ ስፓቺ ዋታንቫራቺ ተገኝተው እንደነበር ገልጿል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው ፤ " ይህ ቢሮ ወደቡ ላይ የሚራገፉ የተለያዩ ጭነቶችን ወደ ኢትዮጵያ እንዲጓጓዙ የሚያሳልጥ ነው " ብለዋል።

የሶማሌላንድ የገንዘብ እና ልማት ሚኒስትሩ ሳድ (ዶ/ር) " ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ ግንኙነታቸው የተጠናከረ ነው ፤ 120 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ አማራጭ ወደቦችን መጠቀም ትችላለች " ማለታቸውን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

Photo Credit : #SomalilandFinanceDevelopment

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ሶሪያ በቀጣይ ወዴት ?

የ24 ዓመታት የበሽር አላሳድ አገዛዝ አክትሟል።

ቤተሰባቸውን ይዘውም ሩስያ ገብተዋል። ጥገኝነትም ተሰጥቷቸዋል።

አሁን ላይ የታጠቁ ተቃዋሚዎች መንበሩን ይዘዋል።

አላሳድን አንባገነን እንደሆኑ የሚገልጹ በርካቶች ክስተቱን ለሶሪያ ዘላቂ ሰላም እድል ያመጣል ይላሉ።

ከዚህ በተቃራኒ በሀገሪቱ ብዙ ታጣቂዎች ነፍጥ ስለያዙ  ለስልጣን ሲባል ወደ 2ኛው ዙር የእርስ በእርስ እልቂት ሊገባ ይችላል የሚሉ ቁጥራቸው ቀላል አይደለም።

ሶሪያ ከፊቷ ተስፋ እና ስጋት ተደቅኗል።

ሶሪያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱት እነማን ናቸው ?

እ.ኤ.አ 2011 ነው የሶሪያ እርስ በርስ እልቂት የጀመረው።

የተሳታፊው ብዛት በርካታ ነው። እነዚህ የየራሳቸው ተሳትፎ፣ አመለካከት፣ ዓላማ ያነገቡ ናቸው።

ጉዳዩ ወስብስብ ያለ ነው።

👉 የአሳድ መንግሥት ኃይሎች

የሶሪያ አረብ ጦር (SAA) እና የብሔራዊ መከላከያ ኃይል (NDF) እኚህ የአላሳድ የጀርባ አጥንት ናቸው። SAA ኦፊሴላዊ የሆነው የሶሪያ መከላከያ ነው። NDF በመንግሥት የሚደገፍ ሚሊሻ ነው። SAA በኢራን እና ሩስያ ይደገፋል። በቀጣዩ መንግሥት ምስረታ ዕጣ ፋንታቸው ምን ይሆን ? የሚለው ምናልባትም በነ ሩስያ እና ኢራን ተፅእኖ ስር የወደቀ ሊሆን ይችላል።

👉 ነጻ የሶሪያ ጦር (FSA)

ቡድኑ መጀመሪያ የተቋቋመው ከሶሪያ ጦር ከድተው በወጡ አካላት ነው። ከዛም ወደ ተለያዩ አንጃዎች እና ጥምረት ተለውጣል። ብዙ ጊዜ ከምዕራባውያን እና ከባህረ ሰላጤው ሀገራት ድጋፍ ያገኛል። በብዙ የሶሪያ ክፍሎች ይንቀሳቀሳል ነገር ግን በተለይ በሰሜን የአሳድን ጦር ሲዋጋ ነበር። በኃላም ISISን ሲዋጋ ነበር።

👉 ሀያት ታህሪር አል-ሻም (HTS)

ይህ በመጀመሪያ የሶሪያ የአልቃይዳ ክንፍ ነበር ፤ አልኑስራ በሚል ነበር ይንቀሳቀስ የነበረው። 2017 ላይ ግን በኢድሊብ እና ከፊል አሌፖ ፈርጠም ብሎ ወጥቷል። አላማው እስላማዊ መንግሥት መመስረት እንደሆነ ይነገርለታል። በቅርቡ አሳድን በመገርሰስ ጥቃት ላይ ቁልፍ ሚና ነበረው። በአዲሱ መንግሥት መመስረት ውስጥ የራሱን አላማ ለማስረጽ ግፊት ሊያደርግ ይችላል በዚህም ሴኩላር ከሚባሉት እና መሃከል ላይ ካሉት ጋር ሊጋጭ ይችላል። በኢድሊብ ከነበራቸው የመንግሥት አስተዳደር ጥብቅ የሸሪያ ህግ ለመተግበር ሊሰራ ይችላል።

👉 የሶሪያ ብሔራዊ ጦር (SNA)

እኚህ በቱርክ የሚደገፉ ናቸው። በዋነኝነት በሰሜናዊ ሶሪያ ነው የሚንቀሳቀሱት። የኩርዲሽ ኃይሎችን በመዋጋት የቱርክን ተፅእኖ ለማስረጽ ይንቀሳቀሳሉ ይባላሉ። በአዲሱ መንግሥት የቱርክን ፍላጎት የያዘ ሃሳብ ይዘው ሊቀርቡ ይችላሉ።

👉 የሶሪያ ዴሞክራቲክ ኃይል (SDF)

እኚህ በኩርዲሽ ዋይፒጂ ነው የሚመሩት። በአሜሪካ ድጋፍ ISISን በማሸነፉ ረገድ ትልቁን ሚና ተጫውተዋል። እኚህ ቡድኖች ሰሜናዊ ምስራቅ ሶሪያን ተቆጣጥረው የያዙ ናቸው። ራዕያቸው የፌዴራል፣ ያልተማከለ ሶሪያ እንድትኖር ነው። በማንኛውም አዲስ መንግስት ውስጥ፣ የኩርድ የራስ ገዝ አስተዳደር ወይም ፌደራሊዝም እንዲሰፍን ግፊት ሊያደርጉ ይችላሉ። ይህ ደግሞ እንደ SNA ካሉ ሌሎች ቡድኖች ጋር ሊያጋጫቸው ይችላል።

እንግዴ እኚህ ሁሉ አላማቸው የሚለያይ ነፍጥ ያነገቡ ቡድኖች ናቸው ሶሪያ ውስጥ ያሉት።

ከአሳድ አገዛዝ ወደ አዲስ መንግሥት ለሚደረገው ሽግግር ምናልባትም እጅግ ወሳኝና ጥልቅ ድርድር አልያም የእርስ በእርስ ግጭት በቡድኖቹ መካከል ሊፈጠር ይችላል።

🚨 SAA እና የአሳድ ደጋፊ ሚሊሻዎች ለውጡ ለነሱ ወይም አጋሮቻቸው ምቹ ሁኔታ ካልፈጠረ ሊቃወሙ ይችላሉ።
🚨 HTS ይበልጥ ሃይማኖታዊ የመንግሥት አስታዳደር ለመመስረት ሊንቀሳቀሱ ይችላሉ።
🚨 FSA እና ተመሳሳይ አቋም ያላቸው ቡድኖች ዴሞክራሲያዊ ሂደትን ይደግፋሉ ነገር ግን ጉልህ ተፅእኖ እንዲኖራቸው በአንድ የፖለቲካ ጥላ ስር መጠቃለል አለባቸው።
🚨 SDF ፌዴራሊዝም (ክልላዊ ራስን በራስ የማስተዳደር) እንዲተገበር ግፊት ሊያደርግ ይችላል። ይህን ሞዴል ሌሎች ከተቃወሙት ግጭት መቀጠሉ አይቀሬ ነው።
🚨 ቱርክ በSNA በኩል በምታደርገው ተፅእኖ ጠንካራ ፣ የተማከለ የኩርድ አካል እንዳይፈጠር ለመከላከል በመሆኑ ይህ ወደ ቀጣይ ውጥረት ሊያመራ ይችላል።


በአዲሱ የሶሪያ መንግሥት መስረታ የኃይል መመጣጠን ፣ በቡድኖቹ መካከል ያለው የአስተሳሰብ ልዩነት እና የውጭ ኃይሎች ተፅእኖ ትልቅ ፈታና ይሆናል። የእያንዳንዱ ቡድን ወታደራዊ ጥንካሬ በውጭ ኃይሎች ድጋፍ እና በውስጥ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የተቀረጸ በመሆኑ ሰላማዊ  ሽግግር ይኖር ይሆን ? የሚለው አሳሳቢ ነው።

አንዳንዶች ለውጡን በአግባቡ መያዝ ካልተቻለ ሀገሪቱ የመበታተን አደጋ እና ከበፊቱም የባሰ ሰቆቃ ውስጥ ልትገባ የምትችልበት ዕድል ሰፊ እንደሆነ እየገለጹ ነው።

እኚህ ሁሉ ነፍጥ ያነገቡ ቡድኖች ወደ አንድነት መጥተው ጠንካራ ሶሪያን ይመሰርቱ ይሆን ? ወይስ ሁለተኛው ዙር የሶሪያ እርስ በርስ እልቂት ይቀጥላል ? ሁሉንም ጊዜ ይፈታዋል !

🛑 ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን ፅሁፍ ለማዘጋጀት በመሰል ጉዳዮች ላይ የሚተነትኑትን ቻክ ፈረን ጨምሮ የተለያዩ ድረገጾችን ተጠቅሟል።

#TikvahEthiopia #ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

🪪 የዲጂታል መታወቂያ ካርድ ኅትመት በቀላሉ በቴሌብር ሱፐርአፕ ይዘዙ!!

💁‍♂️ ቴሌብር ሱፐርአፕ ላይ ‘’NID (Fayda) Printing’’ በሚለው ሚኒ መተግበሪያ ተጠቅመው የፋይዳ ቁጥርዎን በማስገባትና ክፍያዎን በመፈጸም እንደምርጫዎ በ6 የሥራ ሰዓታት፣ በ2 ቀናት ወይም በ7 ቀናት ውስጥ በመረጡት የመረከቢያ ቀንና ቦታ ይደርስዎታል፡፡

📍 በመዲናችን የሚገኙ የመረከቢያ ቦታዎችን ለመመልከት፡ https://bit.ly/3UT6rY3

🔗 ቴሌብር ሱፐርአፕን https://onelink.to/uecbbr ይጫኑ!

ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSupperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Alert🚨

ከመቐለ ወደ ዓዲግራት የሚወሰደው ዋና የመኪና መንገድ አጉላዕ በተባለ ቦታ መዘጋቱ ተጓዦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" መንገዱ ከዲሞብላይዜሽን (DDR) ጋር በተያያዘ ጥያቄ ባነሱ የቀድሞ የትግራይ ታዋጊ አባላት ነው የተዘጋው " ብለዋል።

ጥያቄው በዝርዝር ምን እንደሆነ የሚታወቅ ነገር የለም።

መንገዱ ከዛሬ ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም ጠዋት ጀምሮ ይህ መረጃ እስከወጣበት ከቀኑ 7:00 ድረስ ተዘግቷል።

መንገዱ በመዘጋቱ ምክንያት ከመቐለ የተነሱ መኪኖች 40 ኪሎ ሜትር ከተጓዙ በኋላ አጉላዕ ከተማ ደርሰው ወደ ውቕሮ ዓዲግራት እና ሌሎች ቦታዎች ማለፍ አይችሉም።

ከዓዲግራት ፣ ወቕሮ እና ሌሎች ከተሞች የመጡት ደግሞ አጉላዕ ደርሰው ወደ መቐለ ከተማ ማለፍ አይችሉም ብለዋል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ መንገደኞች።

ተጓዦች መንገዱ በመዘጋቱ ምክንያት ለከፍተኛ እንግልት መጋለጣቸው ገልፀው ፤ እስካሁን መንገዱን የዘጉትን የቀድሞ ተዋጊዎች አባላትን ጥያቄ ሰምቶ መልስ የሰጣቸው የለም ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ጉዳዩ ተከታትሎ ያለውን መረጃ እንደሚያቀርብ ከወዲሁ ይጠቁማል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ኤርትራ

🚨 " አምባገነኑ ኢሳያስ በህግ ለመተዳደር፣ ለህጋዊ ጉዳዮች፣ ለህገመንግስት ባዕድ ናቸው ! " - የፋና ቴሌቪዥን ዘገባ

🔴 " አምባገነንነትን አጥብቀው የሚወዱት ኢሳያስ ምርጫንም ሆነ የህግ የበላይነትን እምቢኝ እንዳሉ ወንበራቸው ላይ አርጅተዋል ! "


ፋና ቴሌቪዥን በኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ላይ " የአስመራው መንግሥት ነገር - የራሷ አሮባት " በሚል የሰራው ጠንከር ያለ ዘገባ መነጋገሪያ ሆኗል።

" የገዢውን ፓርቲ አቋም ያንጸባርቃል እንዲሁም የመንግሥት ልሳን ነው " እየተባለ የሚነገርለት ፋና ቴሌቪዥን ከዓመታት በፊት በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል የሰላም ስምምነት ከተፈረመ ወዲህ በዚህ ልክ ኢሳያስን እና አስተዳደራቸውን አምርሮ የሚተች ዘገባ አውጥቶ አያውቅም።

በትግራይ ጦርነት ወቅት እንኳን ስለ ኤርትራው ገዢ ኢሳያስ ብዙ ሲባል የነበረ ቢሆንም የሻዕቢያ ሰራዊት የሰራቸውን የግፍ ተግባራት በይፋ ተናግሮ አያውቅም ነበር።

በተለይ ከፕሪቶሪያው ስምምነት መፈረም እና ኢትዮጵያ የባህር በር ሊኖራት የግድ እንደሚገባ በግልጽ አቋሟን ይፋ ካደረገች በኃላ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል የነበረው ግንኙነት ሻክሯል በሚባልበት በዚህ ወቅት ጠንካራ እና ድፍረት የተሞላበት ዘገባ ሰርቶ ወጥቷል።

የዘገባው መነሻ ሰሞነኛው የኢሳያስ ቃለ ምልልስ ነው።

የፋና ዘገባ " በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ያለውን እጅግ የሻከረ ወቅታዊ ሁኔታ ያሳያል " ተብሏል።

ፋና በሰራው ዘገባ ስለ ፕሬዜዳንት ኢሳያስ ምን አለ ?

➡ በቡዙ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግር ውስጥ የተዘፈቀችውን የራሳቸውን ሀገር ረስተው ስለ ሌሎች ሀገራት እና ስለ ኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ሲፈተፍቱ ነበር።

➡ ኤርትራ በህገመንግስት መስተዳደር ብርቅ የሆናባት ሀገር ናት። ይህ ሆኖ እያለ ህገመንግስት ያላትን ኢትዮጵያን መተቸታቸው አስገራሚ ነው።

➡ ላለፉት 30 ዓመታት በላይ ያለ ምንም ተቀናቃኝ ኤርትራን የገዙት ኢሳያስ መንግሥታቸው ህገመንግስት ፣ ምርጫ ፣ ነጻና ገለልተኛ የዴሞክራሲ ተቋማት የሚባል ነገር አያውቅም ፤ ፍላጎትም የላቸውም። ደግሞ አፋቸውን ሞልተው ይህንኑ ይናገራሉ።

➡ ምርጫም ሆነ ተቀናቃኝ እንዳይኖር ለሶስት አስርት ዓመታት አፍነው እያስተዳደሩ ፣ በኢኮኖሚም ሆነ ፖለቲካም ከዓለም ስለራቀች ሀገራቸ ኤርትራ ለመናገር ነውር አስመስለውታል።

➡ ለቀጠናዊ ሰላም እና ትብብር ጆሮ የማይሰጡት ኢሳያስ በቀጠናው ሰላም መደፍረስ ጣታቸውን ኢትዮጵያ ላይ ቀስረዋል።

➡ የህገመንግስት አስተዳደር የሌላቸው ኢሳያስ የኢትዮጵያን ህገመንግስት ለመተቸት ደፍረዋል።

➡ ኤርትራ ህገመንግስት ካፀደቀች ሩብ ክፍለዘመን ቢሆናትም አምባገነንነትን አጥብቀው የሚወዱት ኢሳያስ ከመሳቢያቸው ስር ሽጉጠው ምርጫንም የህግ የበላይነትንም እምቢኝ እንዳሉ ወንበራቸው ላይ አርጅተዋል።

➡ ህገመንግስት የሌላቸው ሰው የኢትዮጵያ ህገመንግስት ላይ አስተያየት መስጠታቸው ስላቅ ይሆናል።

➡ አምባገነኑ ኢሳያስ በህግ ለመተዳደር፣ ለህጋዊ ጉዳዮች፣ ለህገመንግስት ባዕድ ናቸው።

➡ አምባገነኑ ኢሳያስ  የጎረቤቶቻቸው በህግ መመራት የራሳቸውን ድካም የሚያጋልጥባቸው ይመስላቸዋል።

➡ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የሚያደረጉ የጎረቤት ሀገራትን አይወዱም።

➡ ኢሳያስ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠን መንግስት ለማወክ ከጀርባ ታጣቂ አሰልጥነው የሚልኩ መሆናቸውን ቴሌቪዥን ላይ ሲቀርቡ ይረሱታል።

➡ እራሳቸውን የቀጠናው ጠበቃ የሀገራቱ ሰላም ወዳድ አድርገው የብልጣ ብልጥ ጨዋታ ይጫወታሉ።

➡ ኤርትራን እንደ ሲንጋፖር አደርጋለሁ የሚለው ቅዠት ወደ ተግባር መለወጥ ሲያቅታቸው የናቋት ጎረቤታቸው ኢትዮጵያ በየአመቱ 8% በላይ እድገት እያስመዘገበች በኢኮኖሚ የቀጠናው ቁንጮ መሆኗ ቅናት ውስጥ ከቷቸዋል።

➡ ኢትዮጵያ ዜጎቿን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ከማድረግ አልፋ ምስራቅ አፍሪካን በኃይል እያስተሳሰረች ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት የአፍሪካን ሁለተኛ ኢኮኖሚ ገንብታለች።

➡ ኢሳያስ ድፍን 30 ዓመታት የመሯት ሀገር ከ30 ዓመታት በፊት በተገነባ መሰረተ ልማት እየኖሩ ነው።

➡ በኤርትራ ኢንተርኔት እና ስልክ በቤተሰብ ኮታ ነው የሚሰጠው። ገንዘብ በATM ማውጣት ብርቅ የሆነባት ሀገር ናት። ዜጎች ሰርግ እንኳን ለመከወን የሚያወጡት ወጪ ኦዲት የሚደረግባት ሀገር ናት።

➡ ኤርትራውያን ነገን ያለ ተስፋ ኑሮን በጨለማ ለመግፋት ተገደዋል።

➡ ጉባ ላይ በተለኮሰው የብርሃን ችቦ (GERD) ዜጎቿን ከጨለማ ወደ ብርሃን ለማሻገር እየተጣደፈችን ያለችውን ጎረቤታቸውን (ኢትዮጵያን) ለመተቸት አንደበታቸውን ሲያላቅቁ ምንም የመሸማቀቅ ስሜት አይታይባቸውም።

➡ ኢሳያስ የሚመሩት መንግሥት የጀርባ እቅዱ ኢትዮጵያን አፈራርሶ ለመግዛት እንደነበር በተደጋጋሚ ከሚያሰሙት ንግግራቸው ተስተውሏል።

➡ ከግብፅ እና ሶማሊያ መሪዎች ጋር ' ቀጠናዊ ሰላም ለማምጣት ' በሚል የዳቦ ስም በሰጡት መርዛማ ቀጠናውን የማተራመስ ሃሳብ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ላይ ስጋት የደቀነ ስምምነት አስመራ ላይ ሲፈራረሙ ታይተዋል። ' ነገሩ ሆድ ሲያቅ .. ' መሆኑን ከ30 ዓመቷ ወጣት ሀገር መረዳት ይቻላል።

➡ አንድ አምስተኛውን ህዝባቸውን ስደተኛ ያደረጉ ኢሳያስ በሰው ሀገር ጉዳይ በመፈትፈት የሚስተካከላቸው አይገኝም።

➡ ኢሳያስ አምርረው የሚጠሉት ለኢትዮጵያውያን የሰንደቅ አላማ ፕሮጀክት የሆነው የህዳሴ ግድብ ሪቫን ሊቆረጥ መቅረቡ እረፍት ነስቷቸዋል።

ይህንን ዘገባ የተመለከቱ በርካቶች ዘገባው " ወቅታዊውን በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ያለውን ቁርሾ / ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት ያሳያል " የሚል ሃሳባቸውን ሰጥተውበታል።

https://youtu.be/UdzP3vtR4DI?feature=shared

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Democracy👏

" የህዝቤን ውሳኔ አከብራለሁ " - በምርጫ የተሸነፉት ባውሚያ

አፍሪካ ውስጥ የተረጋጋ ምርጫና የስልጣን ሽግግር ከሚደረግባቸው ሀገራት አንዷ ጋና ናት።

ሀገሪቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አካሂዳለች።

ለውድድር የቀረቡትም ተቃዋሚው የናሽናል ዴሞክራቲክ ኮንግረስ ፓርቲው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ እና የአሁን የገዢው ኒው ፓትርዮቲክ ፓርቲ ዕጩና የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት መሃሙዱ ባውሚያ ናቸው።

ውጤት ?

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆን ማሃማ የገዢውን ፓርቲና የአሁኑ ምክትል ፕሬዜዳንት ባውሚያን አሸንፈዋቸዋል።

በምርጫው የተሸነፉት የገዢው ፓርቲ ዕጩ ለተፎካካሪያቸው " እንኳን ደስ አልዎት ! " ብለዋቸዋል።

ምርጫውን የተሸነፉት የገዢው ዕጩ ባውሚያ ህዝባቸውን / ጋናውያንን ለለውጥ የሰጡትን ድምጽ እና ውሳኔ እንደሚያከብሩ ተናግረዋል።

" የጋና ፕሬዜዳንት ሆነው ለተመረጡት የተከበሩ ጆን ማሃማ ስልክ ደውዬ እንኳን ደስ አለህ ብዬዋለሁ " ሲሉም ገልጸዋል።

ተመራጩ ፕሬዜዳንት ምርጫውን በማሸነፋቸው ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸው በሀገሪቱ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።

ተመራጩ ፕሬዜዳንት ከዚህ ቀደም እ.ኤ አ. ከሃምሌ 2012 እስከ ጥር 2017 ሀገሪቱን መርተዋል።

የምርጫው ውጤት ለሁለት ስልጣን ዘመን የቆየው የፕሬዜዳንት ናና አኩፎ ኦዶ ገዢ ፓርቲ ማብቂያ ሆኗል።

ባለፉት የስልጣን ዘመናት ጋና አይታ የማይታውቀው የኢኮኖሚ ቀውስ እንዳጋጠማት ፣ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እንዲሁም ከፍተኛ ዕዳ ጉድለት እንደተመዘገበ ተገልጿል።

ህዝቡም በተለይ ለተሻለ የኢኮኖሚ ለውጥ ፤ ያለው የከፋ የኢኮኖሚ ቀውስ መፍትሄ እንዲያገኝ በማሰብ የገዢውን ፓርቲ ዕጩ በድምጹ በመቅጣት ተቀናቃኙን የቀድሞውን ፕሬዜዳንት ወደ ቢሮ ለመመለስ እንደወሰነ ተመላክቷል።

የሀገሪቱ ምርጫ ትልቁ ማጠንጠኛ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች እንደነበሩ ተሰምቷል።

አጠቃላይ የምርጫው ውጤት ግፋ ቢል ማክሰኞ ይፋ ይደረጋል።

ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ናና አኩፎ ኦዶ ለምን ምርጫ አልተወዳደሩም ?

በጋና የፕሬዜዳንቱ ስልጣን ገደብ አለው።

ሁለት የስልጣን ዘመን አሸንፎ ሀገር ከመራ ለሌላ የስልጣን ዘመን " ልወዳደር " ቢል አይፈቀድለትም።

በዚህም ሀገር ለመምራት የሚፈቀድላቸው የስልጣን ዘመን ገደቡ ላይ ስለደረሰና መወዳደር ስለማይችሉ ምክትል ፕሬዜዳንቱ ነው የተወዳደሩት።

ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ወንበሩን ለሌላ የሀገራቸው ልጅ ያስረክባሉ።

#Ghana
#Democracy #Election

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#SafaricomEthiopia

📽 😍 የምርጥ አስሩን ቆይታ እንከታተል!

የሳፋሪኮም #1Wedefit ዲጂታል የሙዚቃ ውድድር ኮከቦቻችን ያደረጉትን አስደሳች ቆይታ የመጀመሪያው ክፍል ቅዳሜ ምሽት 3 ሰአት በአርትስ ቲቪ እንዲሁም እሁድ ከሰአት 9፡00 ደግሞ በአባይ ቲቪ እንድትከታተሉ እንጋብዛችኋለን!

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#FurtherAheadTogether #DigitalMusicChallenge

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የምግብ ዋጋ ጣሪያ መንካት 💥

ዛሬ ላይ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የቀን የምግብ ወጪ የሚመደበው ገንዘብ እንዲጨምር ተደርጓል።

ይህ የሆነው ደግሞ የምግብ ዋጋ በመጨመሩ ነው።

በፊት ለአንድ ተማሪ ይመደብ የነበረው 22 ብር  ዛሬ ላይ ወደ 100 ብር ከፍ እንዲል ተደርጓል።

የተቋማት የምግብ ሜኑም ተመሳሳይ እንዲሆን ተወስኗል።

በፊት በፊት ምንም እንኳን ከግቢ ግቢ ጥራቱ ቢለያይም የዩኒቨርሲቲ ካፌዎች ከዓመት ዓመት በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን ያለ ሰቀቀን መግበው ያስመርቁ ነበር።

የጥራቱ ጉዳይ እንዳለ ሆኖ ካለው የተማሪዎች ቁጥር ብዛት አንጻር ተቋማት በየዕለቱ ያለ ችግር ተማሪዎችን የተለያየ አይነት ምግብ ነበር የሚመግቡት።

ዛሬ ላይ ያለው የምግብ ዋጋ መናር ግን ፈተና ሆኗል። ለዚህም የመስላል የቀን የተማሪዎች የምግብ ዋጋ ላይ ማስተካከያ የተደረገው።

ሌላው ግን በአጭር አመታት በሀገሪቱ የታየው የምግብ ዋጋ መጨመር ግርምትን የሚያጭር ፤ ልብን ቀጥ የሚያደርግ ነው።

ከዛሬ 4 እና 5 ዓመት በፊት በዩኒቨርሲቲዎች የነበሩ ተማሪዎች በተለይም ደግሞ ግቢ መመገብ የማይፈልጉ ምግብ በርካሽ ዋጋ ያገኙ ነበር።

500 ብር የማትሞላውን ወርሃዊ ኮስት ተቀብለው እዛ ላይ ከቤተሰብ የሚላከውን ጨምረው ወጣ ብለው የምግብ ኮንትራት ይዘው የሚበሉ በርካቶች ነበሩ።

ከኮቪድ በፊት እጅግ ጥሩና ፅድት ብሎ የተዘጋጀ በየአይነቱ በየዩኒቨርሲቲው ዙሪያ ባሉ መንደሮች በኮንትራት ከ12 ብር እስከ 17 ብር ድረስ ይገኝ ነበር።

የስጋ ነክ ምግቦችንም ከ23 ብር 35 ብር ድረስ ማግኘት ይቻል ነበር።

እንጅራው ወጡም ፍጹም ጤነኛ።

በግቢ ባሉ የተለያዩ የኢንተርፕራይዝ ካፌዎችም ምግብ በቅናሽ ማግኘት ቀላል ነበር።

ዛሬ ላይ የበፊቱ የበየአይነቱ ዋጋ ደረቅ እንጀራ ለመግዛት አይበቃም።

በበፊቱ የስጋ ነክ ምግቦች ዋጋ ዛሬ ላይ ወጥቼ ልብላ ማለት ቅንጦት ነው፤ አይታሰብም።

ይህ እንግዴ የዛሬ 4 ፣ 5 ፣ 6 ዓመት ታሪክ ነው የረጅም ጊዜ መስሎ የሚወራው።

በአጭር አመታት የታየው የምግብ ዋጋ መተኮስ የሚያስደንግጥ ነው።

ምንም እንኳን በኮስት ከተቋማት የሚገኘው ብር ትንሽ ቢሆንም እሱ ላይ የቤተሰብ ትንሽ ብር ከተጨመረበት ዘና ብሎ ያለሰቀቀን ወር ሙሉ ውጭ መመገብ ይቻል ነበር።

ዛሬ ላይ በሀገራችን ያልጨመረ ነገር ባይኖርም ለመኖር መሰረታዊ ያሆነው የምግብ ዋጋ ተተኩሶ የደረሰበት ደረጃ ብዙዎችን የሚያስጨንቅ ነው።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#JawarMohammed

" አልፀፀትም " / " HIN GAABBU "

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የገዘፈ ስም ካላቸው ፖለቲከኞች አንዱ የሆኑት የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ መፅሀፍ ይዘው እየመጡ እንደሆነ ገለጹ።

የኢህአዴግን ስርዓት በሰላማዊ መንገድ በመታገል ስርዓቱ ሳይወድ በግዱ እንዲቀየር በማድረጉ ረገድ ግንባር ቀደሙን ድርሻ እንደሚይዙ የሚነገርላቸው አቶ ጃዋር መሀመድ ከዚህ ቀደም ሰፋ ያለ መፅሀፍ እየጻፉ እንደነበር መግለፃቸው ይታወሳል።

በመጨረሻም መፅሀፋቸው መጠናቀቁን እና ለአንባቢያ ሊደርስ መሆኑን አሳውቀዋል።

በቀጣይ ሳምንት ኬንያ፣ ናይሮቢ ውስጥ በሚዘጋጅ ዝግጅት መፅሀፉ ለአንባቢያን ይቀርባል ተብሏል።

" አልፀፀትም " / " HIN GAABBU " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መፅሀፋቸው በርካታ እና ከዚህ ቀደም ይፋ ያላደረጓቸው ጉዳዮች የተዳሰሰበት እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመረዳት ችሏል።

አቶ ጃዋር መሀመድ ፦
° በኢትዮጵያ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የገዘፈ ስም ያላቸው ፤
° አሜሪካ ሆነው የኢህአዴግን ስርዓት በሰላማዊ ትግል በመጣሉ በኩል ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፤
° ' ለውጥ መጣ ' ተብሎ ወደ ሀገር ከገቡ በኃላ የሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ከቀብር ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ሁኔታ ታስረው ለበርካታ ወራት በእስር ቆየተው መፈታታቸው ይታወሳል።

ፖለቲከኛው ከእስር ቤት ቆይታ በኃላ ቀድሞ የሚታወቁባቸውን ኃይለኛ ንግግሮችን እና ፅሁፎችን በመተው ዝምታን መርጠው ብዙ ጊዜያቸውን በመፅሀፍ ዝግጅት ላይ እንዲሁም በሀገሪቱ ያሉ ግጭቶች እንዲቆሙ የድርሻቸውን የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርጉ መቆየታቸው ይነገራል።

ከእስር በኃላ ኢትዮጵያ እንዲሁም ኬንያ ናይሮቢ እየተመላለሱ የሚኖሩ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜያቸውን ግን ናይሮቢ ናቸው።

በኬንያ ፣ ናይሮቢ ገቢ የሚያገኙባቸውን ስራዎች ከመስራት ባለፈ እንደ ኢትዮጵያ ብዙ ሰዎች ሊያገኟቸው / ሊጠይቋቸው ስለማይመጡ በጥሞና ለማሰብ፣ ለማንበብ እና መፅሀፋቸውን ለማዘጋጀት ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው ለመረዳት ተችሏል።

" አልፀፀትም / HIN GAABBU " የተሰኘው መፅሀፋቸው ቀጣይ ሳምንት ሀሙስ ናይሮቢ ውስጥ ላውንች ይደረጋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Ethiopia🇪🇹

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በቱርክ አንካራ ፤ ከሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ጋር ያደረጉትን የፊት ለፊት ውይይትና ድርድር አጠናቀው ጥዋት አዲስ አበባ መግባታቸውን ከጠ/ሚ ፅ/ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ምን ተስማሙ ?

በቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አደራዳሪነት የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ስምምነቱ " የአንካራ ስምምነት " ተብሏል።

ይህ ተከትሎ በወጣው የስምምነት ሰነድ የተስማሙባቸው ጉዳዮች በዝርዝር ተቀምጠዋል።

ምንድናቸው ?

➡️ የሶማሊያ እና የኢትዮጵያ መሪዎች አንዳቸው ለሌላኛቸውን ሉዓላዊነት ፣ አንድነት ፣ነፃነት እና የግዛት አንድነት ለማክበር ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል።

➡️ በወዳጅነት እና በመከባበር መንፈስ ልዩነቶችን እና አከራካሪ ጉዳዮችን በመተው ፤ በመተጋገዝ ለጋራ ብልጽግና ለመስራት ተስማምተዋል።

➡️  ሶማሊያ በአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ውስጥ የኢትዮጵያ ወታደሮች ለከፈሉት መስዋዕትነት እውቅና ሰጥታለች።

➡️ ኢትዮጵያ የሶማሊያን የግዛት አንድነት ባከበረ ሁኔታ የባህር በር ተጠቃሚ መሆኗ / ወደ ባህር እና ' ከ ' ባህር / ሊያስገኝ የሚችለው ልዩ ልዩ ጥቅም ላይ ተማምነውበታል።

➡️ ሁለቱንም ተጠቃሚ ባደረገ ሁኔታ የንግድ ውል ይታሰራል።

➡️ ኢትዮጵያ አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀና እና ቀጣይነት ያለው / ዘላቂ የባህር በር መዳረሻ / አክሰስ እንዲኖራት ስምምነት ላይ ተደርሷል
ይህም በሶማሊያ መንግሥት ስልጣን ስር የሚተገበር ነው።

ለዚህም የሚሆን ፦
- የኮንትራንት
- የሊዝ ውልን ጨምሮ ሌሎች ሞዳሊቲዎች ላይ በቀጣይ በቅርበት አብሮ ለመስራትና ለማጠናቀቅ ተስማምተዋል።

ለነዚህ ዓላማዎች መሳካት በጥሩ እምነት ከየካቲት 2025 መጨረሻ በፊት የቴክኒካል ድርድር ለመጀመር ወስነዋል። ይህም በቱርክ አመቻችነት የሚሳለጥ ሲሆን በ4 ወራት ውስጥ ተጠናቆ ስምምነት ይፈረማል።

ለዚህም ቁርጠኝነትና ለቃል ኪዳኑ ተግባራዊ መደረግ የቱርክን እገዛ በደስታ ተቀብለዋል።

➡️ በአተገባበር ሆነ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ያሉ ልዩነቶችን በውይይት እና በሰላማዊ መንገድ ' እንደአስፈላጊነቱ ' በቱርክ ድጋፍ ለመፍታት ቃል ገብተዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Somaliland

አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ሶማሊለንድ ፤ ሀርጌሳ ገብተዋል።

አዲሱ የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት በሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ለተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አቶ አብዱረህማን መሀመድ አብዱላሂ በአቶ ሙስጠፋ የተመራውን ልዑክ በጽ/ቤታቸው ተቀብለዋቸዋል።

ልዑኩ በሀርጌሳ ቆይታው ተመራጩ አዲሱ የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አቶ አብዱረህማን መሀመድ አብዱላሂ በዓለ ሲመት ላይ ይሳተፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሶማሊ ክልል ቴሌቪዥን ዘግቧል።

#Ethiopia #Somaliland

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በመርሕ ደረጃ መጥፎ ሰላም ጥሩ ጦርነት ባይኖርም የስምምነቶች ግልጽነት ማጣት ውጤቱን የተገላቢጦሽ ሊያደርገው ይችላል ! " - የትብብሩ ፓርቲዎች

መኢአድ፣ ኢሕአፓ፣ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄና እናት ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግለጫ ልከዋል።

ፓርቲዎቹ ፤ " አገራችን በሰላም እጦት፣ ሕዝባችን ለዓመታት በዘለቀ ጦርነት ቁምስቅሉን እያየ እንዳለ ምሥክር መቁጠር አይሻም። " ብለዋል።

" በተለይ በብዙ ተስፋና ጉጉት ተጠብቆ የነበረው ' ለውጥ ' የኋልዮሽ መሄድ ከጀመረ ወዲህ ሰላም ማደር ብርቅ፣ ፍጅትና ትርምስ ጌጣችን ከኾነ ሰነበተ " ሲሉ ገልጸዋል።

" ከዚህ ቀደም ኤርትራ በረሃ ከኦነግ ጋር በክልል አመራሮች ደረጃ ግልጽነት የጎደለው ስምምነት ከተደረገ በኋላ ሕዝብ ደስታውን ሳያጣጥም የሰላም ተፈራራሚው ኃይል " ቃል የተገባልኝ አልተፈጸመም " በሚል ሰበብ ተመልሶ ጫካ ከገባ ወዲኽ እንደ አገር ባጠቃላይ በተለይም ደግሞ የኦሮሚያ ክልል ያየው ቁምስቅል ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም " ሲሉ ገልጸዋል።

ከሰሞኑ መንግሥት ' ኦነግ ሸኔ ' እያለ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የተወሰነ ቡድን ሰላም መፈረሙ በመንግሥት የመገናኛ ብዙሃን በስፋት መዘገቡን የገለጹት ፓርቲዎቹ " መጥፎ ሰላም የለም በሚል ጥቂቶች እንኳን የሰላም አካል መኾናቸውን በበጎ የምንመለከተው ነው " ብለውታል።

ከዚኹ ጋር ተያይዞ " የታጣቂ ቡድኑ መሪ ናቸው የተባሉ ግለሰብና የተወሰኑ ወጣቶች ከክልል አመራሮች ጋር ስምምነት ሲፈራረሙ ታይተዋል " ብለዋል።

" ከስምምነቱ ማግስትም አዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ለሦስት ቀናት በዘለቀ ተኩስ ስትናጥ ከርማለች " ያሉት ፓርቲዎቹ " በተኩሱ እስከ አኹን አንዲት እናት በጥይት ተመትተው ሕይወታቸው ማለፉን አረጋግጠናል " ብለዋል።

ይኸው ድርጊት በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች እንደተከሰተ ገልጸዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ሂደቱ ጥርጣሬን እንዳጫረባቸው ጥርጣሬያቸው የሚነሳውም ከስምምነቱ ግልጸኝነት ማጣት ብቻ ሳይሆን ከእንዲህ ዓይነት ክስተቶች ጭምር መሆኑን ገልጸዋል።

" ስምምነቱ መሣሪያ ማውረድን አይጨምርም ወይ ? " ያሉት ፓርቲዎቹ " የከተማ አስተዳደሩ ርችት እንኳን እንዳይተኮስ ሲከለክል እንዳልከረመ እንዴት ሙሉ ትጥቅ ተይዞ መግባትንና ለቀናት ጭምር የድልነሺነት ብሥራት በሚመስያመስል መልኩ ተኩስን ሊፈቅድ ቻለ ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

በተጨማሪ ፦

° ' ከተማ ውስጥ ኹከት ለመፍጠር የመጡ ' በሚል በመታወቂያ ማንነት በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን ተጉዘው የመጡ ነብሰ ጡሮችና አረጋውያን ጭምር ከአዲስ አበባ መግቢያ ክብረ ነክ በኾነ መንገድ ሲመልስ የነበረ ኃይል አኹን የት ሄዴ ?

° ከዚኹ መሐል ሲገድል ሲቀማ የነበረ በውል ተጣርቶ ተጠያቂነት አይኖርም ወይ ?

° መንግሥት የሰላም ስምምነት ፈጸመ ከተባለው ግለሰብና ቡድን ጋር ከዚኽ ቀደም የነበረው ግንኙነት ምን ነበር ?

° ታንዛኒያ ድረስ ኹለት ጊዜ አድካሚ ሙከራዎች ተደርገው ጫፍ እየደረሱ የተናፈቀው ሰላም ሲጨነግፍ በአቋራጭ አዲስ አበባ እውን የኾነበት ተዓምር ምን ቢኾን ነው ?

° የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ ሥነልቡናዊ ጫና እንዲደርስበት ታስቦ ተሠርቷል ወይ ? የሚሉ ጥያቄዎችን ፓርቲዎቹ አንስተዋል።

ፓርቲዎቹ ፤ የለአንድም ቀን እንኳን ሰላም መስፈን እጅጉን እንሻለን ብለዋል።

" የአንድም ሰው የሰላምን መንገድ መምረጥ ያስደስተናል " ሲሉ አክበላለዋል።

" በአንጻሩ ደግሞ በሂደቱ ዙሪያ የግልጽነት አለመኖርና የሰላሙ ዘላቂነት እጅግ ስለሚያሳስበን አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲኖሩ ማንሳት በጎ ይመስለናል " ብለዋል።

ፓርቲዎቹ፦

➡️ የሰላም መጥፎ የለውምና የተደረሰውን ስምምነት ከነገዘፉ ችግሮቹ በበጎ እናየዋለን ብለዋል።

➡️ መንግሥት የስምምነቱን ሂደትና ዝርዝር ነጥቦች የመከራው ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ ለሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ በአጽንኦት አሳስበዋል።

➡️ በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ለቀናት የዘለቀው ተኩስ፣ በሰላም ስምምነት የመጣ ሳይኾን ኾን ተብሎ የሕዝብን ሥነ ልቡና ለመስለብና ለማስፈራራት የተደረገ መኾኑን ሕዝባችን እንዲያውቀው እንሻለን ብለዋል።

➡️ በዚኹ የተኩስ እሩምታ ሰበብ መገናኛ አካባቢ ለተገደሉት እናት መንግሥት ሓላፊነት የሚወስድ ኾኖ ቢያንስ ቤተሰባቸውን ይፋዊ ይቅርታ እንዲጠይቅና ተገቢውን ካሳ እንዲከፍል እንጠይቃለን ብለዋል።

➡️ መንግሥት ከሽርፍራፊ ደስታና ማስመሰል ወጥቶ ዘላቂ ሰላምን በሰጥቶ መቀበል መርኅ በገለልተኛ ታዛቢዎች አማካይነት ድርድር ለማድረግ ፈቃደኝነቱን በመግለጽና ለዚህም ተግባራዊ እርምጃ በመውሰድ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ያሉ ደም አፋሳሽ ጦርነቶች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት እንዲያገኙ፣ በአፋጣኝም ተኩስ አቁም እንዲታወጅ በአጽንዖት አሳስበዋል።

#እናትፓርቲ
#መኢአድ
#ኢሕአፓ
#ዐማራግዮናዊንቅናቄ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Ethiopia #Somalia #Turkey

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ልዑካቸው አንካራ ቱርክ ይገኛሉ።

የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጽሕፈት ቤታቸው አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን ሁለቱ መሪዎች ከልዑካን ቡድናቸው ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

በሌላ በኩል ፤ የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሼክ መሐመድ አንካራ ይገኛሉ።

እሳቸውም ከኤርዶጋን ጋር ተነጋግረዋል።

መሪዎቹ አንካራ የሄዱበት ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ የገቡበትን ውጥረት ለማርገብ እንዲቻል ኤርዶጋን የንግግር መድረክ አመቻችተውላቸእ ነው።

መሪዎቹ ፊት ለፊት ይነጋገራሉ እየተባለ ይገኛል።

ሮይተርስ የሶማሊያ ዜና አገልግሎት ሶናን ጠቅሶ እንደዘገበው የሁለቱ መሪዎች የፊት ለፊት ንግግር እየተካረረ የሄደውን የሁለቱን ሃገራት ዲፕሎማሲያዊ ቀውስ ለማርገብ ያስችላል ብሏል።

እንደ ተባለው ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከሀሰን ሼክ መሀመድ ጋር ፊት ለፊት የሚገናኙ ከሆነ ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሌ ላንድ ጋር የወደብ ባለቤት የሚያደርጋትን ስምምነት ከተፈራረሙ ወዲህ ይህ የመጀመሪያዉ ይሆናል።

መረጃው ከጠ/ሚ ፅ/ቤት ፣ ዶቼ ቨለ ፣ ሮይተርስ የተሰባሰበ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#TecnoAI

በተለምዶ ረጅም ሰዓታትን አንድ ስራ ላይ ማባከን ታሪክ ሆነ ፤ ቀናት የሚወሰዱ ስራዎችን በሰዓታት ብቻ መፈፅም የአዲሱ ቴክኖ ኤ አይ ዋነኛ መገለጫ ነው፡፡

ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመከተል የቴክኖ ቲክቶክ ገጽ ፎሎው በማድረግ እና Bio ላይ ያለውን ሊንክ ተጭነው በመመዝገብ ታህሳስ 10 በስካይላይት ሆቴል በሚካሄደው የሀገራችን ትልቁ የኤ አይ ሁነት ላይ ይሳተፉ፡፡

tecnoet" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@tecnoet

@tecno_et @tecno_et

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ArbaMinch

🔴 የእሳት አደጋ መድረሱን ተከትሎ የድረሱልን ጥሪ ሲያሰሙ የነበሩ እናት ህይወት አለፈ።

በአርባ ምንጭ ከተማ ዛሬ ረፋድ 4 ሠዓት አከባቢ በተለምዶ ' ቡቡ ሜዳ ' ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ በሚገኘዉ አዲሱ ገበያ የእሳት አደጋ ተከስቶ በንብረት ላይ ዉድመት ማድረሱን የከተማው አስተዳደር ፖሊስ አስታውቋል።

በእሳት አደጋዉም የሰዉ ሕይወት መጥፋቱን የሚገልፁ መረጃዎች መውጣታቸውን ተከትሎ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ፖሊስን ማብራሪያ ጠይቋል።

የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ም/ኢንስፔክተር ጋፋሮ ቶማስ ፤ በአከባቢው በሚገኝ አንድ የኤሌክትሮንክስ ሱቅ ዉስጥ በኤሌክትሪክ ኮንታክት ምክንያት በተነሳ የእሳት አደጋ 12 ሱቆች መዉደማቸዉን ገልጸዋል።

በአደጋው ወቅት በገበያው ዉስጥ በተለምዶ መንገድ በጩኸት ይድረሱልን ጥሪ ሲያደርጉ ከነበሩ ሴቶች መካከል አንዲት እናት ባለባቸው የጤና እክል ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

እኚህ እናት የልብ ሕመም እንደነበራቸው የገለጹት ም/ኢንስፔክተር ጋፋሮ ፤ በጩኸት የድረሱልን ጥሪ ሲያሰሙ ሳለ በመድከማቸው ወደ ነጭ ሳር ሆስፒታል ቢወሰዱም ሕይወታቸው ማርተፍ አልተቻለም ነው ያሉት።

ሆኖም በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ሕይወቷ ያለፈዉ በእሳት አደጋዉ በደረሰ ጉዳት ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነዉ ብለዋል።

በገበያዉ ዉስጥ ያለዉ የሱቆች አሰራር እና አጠቃቀም ለእሳት አደጋ አጋላጭ ነዉ ያሉት አዛዡ ፤ ሕይወቷ ያለፈዉ ግለሰብ በገበያው ዉስጥ ሱቅ እንደነበራቸውና ሱቃቸዉም እሳት አደጋዉ እንዳልደረሰበት ገልፀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የእሳት አደጋዉ በተገለፀው አኳሃን መፈጠሩን በገበያው ውስጥ ካሉ ነጋዴዎች የሰማ ሲሆን ሕይወታቸዉ ያለፈዉ ግለሰብም በቀጥታ በእሳት አደጋው በደረሰ ጉዳት አለመሆኑን ነጋዴዎች ተናግረዋል።

" ሞች ወ/ሮ አበባየሁ መንገሻ እንደ እናት ያሳደጉኝ እናቴ ናቸዉ፤ የሞቱት በእሳት አደጋዉ አይደለም " ያሉት አቶ አማኑኤል ሰይፉ የተባሉ ነጋዴ አስቀድመው የልብ ሕመምና የሕክምና ክትትል እንደነበራቸው አስረድተዋል።

አክለው በእሳት አደጋዉ ወቅት መደንገጣቸዉና ከሌሎችም ሴቶች ጋር ሆነዉ ለይድረሱልን ብዙ መጮኻቸዉን ተከትሎ መዳከማቸዉንና ወደ ነጭ ሳር ሆስፒታል ቢወሰዱም ሕይወታቸው ማለፉን ነው የገለጹት።

#TikvahEthiopiaFamilyArbaMinch

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

የተዘጋው የመኪና መንገድ ከ10 ሰዓታት ቆይታ በኋላ ተከፍቷል።

ከውቕሮ ዓዲግራት በሚወስድ ከመቐለ በ40 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው አጉላዕ በምትባለው ከተማ መንገዱ የተዘጋበት ምክንያት ምንድን ነው ?

መንገዱ ከጥዋት እስከ 10:00 ከሰዓት በኋላ የዘጉት በይፋ በዲሞብላይዜሽን (DDR) ወደ ህብረተሰቡ ያልተቀላቀሉ የትግራይ የቀድሞ ተዋጊዎች ናቸው።

የቀድሞ ተዋጊዎቹ ከዲሞብላይዜሽን  (DDR) አጀማመር እና አፈፃፀም ጋር በተያያዘ ፦

1ኛ. የዴሞብላይዜሽን (DDR) አሰራርና መመሪያ ሴት ተዋጊዎች ፣ በጦርነቱ የተጎዱ ታጣቂዎች ቀጥሎ በሙሉ ጤንነት ያሉ እየለ በየደረጃው እንዲፈፀም የሚፈቅድና የሚያዝዝ እያለ በጦርነቱ የተጎዳን ትቶ ጤነኞቹ ለምን አስቀደመ ?

2ኛ. ዴሞብላይዜሽን (DDR) የማይመለከታቸው አንዳንድ ግለሰቦች በወጣው ዝርዝር ስማቸው ተካተዋል ለምን ? ... የሚሉ እና መሰል ጥያቄዎች አንስተዋል።  

ያነሱዋቸው ጥያቄዎች አስመልክተው ከሚመለከታቸው የፀጥታ እና የፓለቲካ አመራሮች ከተወያዩ በኋላ መንገዱ ሊከፈት እንደቻለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል አሳውቆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የሌሊትና የማለዳዉ ቅዝቃዜ ቀጣይነት ይኖረዋል " - የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት

በሚቀጥሉት አሥር ቀናት ከሳይቤሪያ ከፍተኛ የአየር ግፊት ላይ በመነሳት ወደ ሀገራችን የሚነፍሰው ደረቅ እና ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ በተለይም በመጀመሪያዎቹ ቀናቶች ላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ዋቢ በማድረግ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳውቋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛዎቹ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ይስተዋላል።

የሌሊትና የማለዳዉ ቅዝቃዜ በተለይም በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን፣ በምስራቅና በደቡብ ደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖረዋል ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ በጥቂት የምዕራብና የደቡብ ምዕራብ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ይሆናል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በምዕራብ፣ በደቡም ምዕራብ በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸዉ በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ አነስተኛ መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

"  ለፕሮጀክቱ ግንባታ ከኩፖን እና ከቶንቦላ ትኬት አጠቃላይ 23.7 ሚሊዮን ብር ቢሸጥም ባንክ አልገባም " - የፌደራል ዋና ኦዲተር

የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የወሎ ተሪሸሪ ኬር የህክምናና ማስተማሪያ ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከወሎ ዩኒቨርስቲ የሥራ ሀላፊዎች፣ ከፌደራል ኦዲተር መስሪያ ቤት እና ከተሪሸሪው የቦርድ አባላት ጋር በመሆን ከህብረተሰቡ የተሰበሰበውን ገንዘብ በማስመልከት በኦዲት ግኝት ዙሪያ ውይይት አድርጓል።

ቋሚ ኮሚቴው ምን አለ ?

⚫ ለወሎ ተርሸሪ ኬር የህክምናና  የማስተማሪያ ሆስፒታል ፕሮጀክት ግንባታ የሚውል በየክልሎች ፣በውጭ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች እና ቆንፅላ ጽ/ቤቶች በኩል ይሸጣል ተብሎ የተሰራጨው 9.3 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የኩፖን ትኬት ጠፍቷል። የሥራ አመራር ቦርዱ አጠቃላይ 17 ሚሊዮን የእዳ ሥረዛ ማድረጉ በኦዲት ሪፖርት ተረጋግጧል።

⚫ በህብረተሰቡ ተነሳሽነት የተሰበሰበው ገንዘብ ያለ አግባብ ሲባክንና ለፕሮጀክቱ ለታለመለት ዓላማ ሳይውል መቅረቱ ተገቢ አይደለም።

⚫ ሆስፒታሉ ሁሉም ኢትዮጵያዊና ለምስራቅ አፍሪካ ተስፋ ለነበረው ፕሮጀክት የሚሆን በኢምባሲዎች የተበታተነው የሎተሪ ዕጣዎችም የት እንደደረሱ አልታወቀም።

⚫ የኦዲት ግኝቱ መነሻ ህዝቡ ያነሳው ቅሬታ ስለሆነ ተጠያቂ መሆን ያለበት አካል መጠየቅ አለበት።

⚫ እስካሁን ባንክ ያልገባው ገንዘብ በማን እጅ እንዳለና ለምንስ ባንክ ገቢ እንዳልተደረገ እንዲሁም የተሸጡ ትኬቶችና ቦንዶች ባንክ ገቢ አልተደረጉም።

⚫ የሲቪል ማህበራት እንደገና ሲቋቋም ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ እንደገና መመዝገብ ቢኖርበትም አልተመዘገበም። ወሎ ዩኒቨርስቲ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባራት በቦርዱ የተወሰነውን ውሳኔዎችን መቀበል አለበት።

⚫ ቦርዱ ውሳኔ ከወሰነ በኋላ የህዝብ ገንዘብ ወጪ እያደረገ ነበር። ቦርዱ ስልጣን ሳይኖረው 17 ሚሊዮን ብር የእዳ ስረዛ አድርጓል። የተወሳሰቡ ችግርች ናቸው ያሉት።


የፌደራል ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ ምን አሉ ?

🔴 ለፕሮጀክቱ ግንባታ ከኩፖን እና ከቶንቦላ ትኬት አጠቃላይ 23.7 ሚሊዮን ብር ቢሸጥም ባንክ አልገባም። ቦርዱ የመሰረዝ ስልጣን ሳይኖረው 11.1 ሚሊዮን የሚጠጉ የኩፖን ትኬቶችን የጠፉ በሚል ሰርዟል።

🔴 ባንክ ያልገባው ገንዘብ ለማን እንደተሰጠ ስለሚታወቅ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ከሚፈልገው አካል ጋር በመሆን ገንዘቡን ለህዝቡ ይፋ ለማድረግ ወደ ባንክ መግባት አለበት።

🔴 ከ2010 ዓ.ም. እስከ 2016 ዓ.ም. የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከፕሮጀክቱ 9.1 ሚሊዮን ለተለያዩ የሥራ ማስኬጃዎች ተብሎ የወጣ ገንዘብ አለ ይህ መውጣት አልነበረበትም።

የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ሚናስ ህሩይ ምን አሉ ?

🟠 ለፕሮጀክቱ የታቀደው ገንዘብ 3.5 ቢሊዮን ብር ነበር። የተሰበሰበው ግን 50 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው።

🟠 በተለያዩ አካባቢዎች የተበተነው የተንቦላ ሎተሪ ገንዘብ በቸልተኝነት ተረስቷል። ቀጣይ አቅማችን በሚችለው መንገድ ለማስመለስ እንሰራለን።
#HoPR

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#TecnoAI

ቴክኖ ኢትዮጵያ ያዘጋጀው በሀገራችን ትልቁ የኤ አይ ሁነት ታህሳስ 10 በስካይላይት ሆቴል እጅግ በደማቅ ሁኔታ ይካሄዳል፡፡ ከፍ ያሉ የአርቴፊሻል ቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን ይዞ ብቅ ካለው ከቴክኖ ኤ አይ በተጨማሪ አጅግ የተራቀቁ አዳዲስ የቴክኖ የምርት ውጤቶች ለዕይታ ይፋ ይሆናሉ፡፡

ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመከተል የቴክኖ ቲክቶክ ገጽ ፎሎው በማድረግ እና Bio ላይ ያለውን ሊንክ ተጭነው በመመዝገብ ታህሳስ 10 በስካይላይት ሆቴል በሚካሄደው የሀገራችን ትልቁ የኤ አይ ሁነት ላይ ይሳተፉ፡፡

tecnoet" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@tecnoet

@tecno_et @tecno_et

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በመሳሪያ የሚደረገው ፍልሚያ ይጎዳል እንጂ ለአገሪቱ አይጠቅማትም " - የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

በኦሮሚያ ክልል አጀንዳ የማሰባሰብ መድረክ ከታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዛሬ በአዳማ ከተማ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

ማህበረሰቡ በአጀንዳ ልዬታ ወቅት የመረጣቸው ከ7 ሺሕ በላይ ተወካዮች እንደሚገኙ፣ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ በቀጣዩ ሳምንት እንደሚጠናቀቅ በቦታው የተገኙት ኮሚሽነር መሐመድ ድሪር ተናግረዋል።

ኮሚሽነር መሐመድ ድሪር ምን አሉ?

“ ኮሚሽኑ አሁን በአጠቃላይ በአገራቱ ያለውን ሁኔታ ወደ ተሻለ ሰላም ለማድረስ የጸና፣ ዴሞክራሲያዊ፣ የመመካከር ባህልን ያዳበረ ማህበረሰብ እንዲኖረን እየሰራ ይገኛል።

ላለፉት ሦስት ዓመታት በ10 ክሌሎች፣ ሁለት የከተማ አስተዳደሮችን ስራችንን ስንሰራ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ኦሮሚያም ክልልም እንዲሁም በአማራ ክልል ሥራው ተጀምሯል።

ኦሮሚያ ውስጥ ሆነን መናገር የምንችለው 7,000 የተለያዩ የኦሮሚያ የማህበረሰብ ክፍሎች ከዚህኛው በፊት በተሳታፊ ልዬታ ውስጥ ህዝቡ የመረጣቸው ተወካዮችን እናገኛለን። 

በቀጣዩ ሳምንት የምንሰራቸው ሥራዎች ለሰላም ከፍተኛ  አስተዋጽኦ አላቸው ብለን እናምናለን። በሂደቱ የሚሳተፉ በሙሉ በነቂስ ወጥተው እንዲሳተፉ ጥሪ አቀርባለሁ።

በትግራይ የተካሄደው የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በመሠረቱ እንዲጸና እና ክልሉ ደግሞ ኮሚሽኑ ሥራውን እንዲጀምር ፍላጎቱ እንደሆነ በዚሁ አጋጣሚ እንገልጻለን "
ብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል የሚካሄደውን አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት በተመለከተ ተጠይቀው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ምን አሉ ?

° ኮሚሽኑ ሰዎችን አይመርጥም።

° በማህበረሰብ፣ ክልል፣ አገር፣ ከተማ ያሉ ዜጎች የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች አሏቸው። የማህበረሰብ ክፍሎቹን በአሰራር ዜዬ ለይተናል። 

° አርሶ አደሮች፣ አርብቶ  አደሮች፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ የሚገፉ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ በግጮቶች ምክንያት ከቄያቸው የተፈናቀሉ፣ በሌላ አካባቢ ሰቆቃቸውን የሚያዩ ዜጎችም አሉ። እነርሱም እንዲሳፉ ነው የሚደረጉት።

° ሴቶች፣ ወጣቶች፣ ምሁራን፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች ሳይቀሩ። ከዚህ በፊት የፓለቲካ ፓርቲዎች ጥርጣሬዎች ነበሯቸው ከዚያ ጥርጣሬ የወጡ በርካታ የፓለቲካ ፓርቲዎች በሂደቱ ውስጥ እየተሳተፉ ነው። አሁንም ልዩነት ያላቸው እንዳሉ እናውቃለን። ለእነርሱም ጥሪያችንን እያቀረብን
እንገኛለን።

ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ያለውን ሁነት በተመለከተ ምን አሉ ?

" ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች (ለምሳሌ በምዕራብ ወለጋ የነበረውን ሁኔታ ሁላትንም የማንስተው ነው) ጅማ ላይ መጥተው ተወካዮቻቸውን መርጠው፣ በሰላም ወደ አካባቢያቸው ተመልሰዋል እነርሱ ናቸው የሚሳተፉት።

እየተሟላ ያለ ሂደት እየሰራን ነው። በኦሮሚያ ውስጥ አሁን ያለውን ሰላም ቸር አምላክ ያጽናልን። ሌሎች ብረት ያነሱ ከመንግስት ጋር ግጭት ያላቸው ወገኖችም ወንድሞቻቸው እንደተመለሱት ሁሉ ሰላምን ተቀብለው ችግሮችን በሰለጠነ መንገድ እንፍታ።

በመሳሪያ የሚደረገው ፍልሚያ ይጎዳል እንጂ ለአገሪቱ አይጠቅማትም ብለው የወሰኑ ወገኖች አሉ። ለሌሎችም ይሄንኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ፎቶ ፦ ትላንት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በቻይና ምድር የመጀመሪያዋን ደብር በመሰየም ሥርዓተ ቅዳሴ አከናውናለች።

ለሐዋርያዊ አገልግሎት ቻይና እንደሚገኙት ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ በቻይና ምድር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የመጀመርያዋን ቤተ ክርስቲያን ደብረ ምሕረት መድኃኔዓለም ብለው በመሰየም ሥርዓተ ቅዳሴ በመፈጸም ምዕምናንን አቁርበዋል።

በቻይና የመጀመሪያው አንድ ኢትዮጵያዊ ዲያቆንም ሾመዋል።

ከቻይና ክፍላተ ግዛቶች የተሰባሰቡ ምዕመናን ፣ ቻይናውያንና ትውልደ ቻይናውያን በሥርዓተ ቅዳሴው ተሳፍተዋል።

ደብረ ምሕረት መድኃኔዓለም !

Photo Credit - EOTC Far East Diocese & ETOC TV

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#MoE : በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ በጀት ማስተካከያ መደረጉንም ይፋ አድርጓል።

" ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን የምግብ ሜኑ ተቀራራቢ እንዲሆን እየሰሩ ነው " ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

ወቅታዊውን የምግብ ዋጋ መጨመር መነሻ በማድረግ ትምህርት ሚኒስቴር ጥናት ማድረጉን በጥናቱ ውጤት መነሻነትም የከፍትኛ ትምህርት ተቋማት / የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ በጀት በቀን ወደ 100 ብር ከፍ እንዲል መደረጉን አሳውቋል።

በተደረገው የበጀት ማሻሻያ መሰረት በተቋማቱ የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ይሰራል ተብሏል።

በአዲሱ የበጀት ተመን መሰረት ለዩኒቨርስቲዎቹ ባላቸው ተማሪ ቁጥር ልክ ገንዘቡ እንደሚለቀቅላቸው ተጠቁሟል።

ዩኒቨርሲቲዎች ከዚህ ቀደም በቀን አንድ ተማሪ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት ለመመገብ በመንግሥት የሚመድብላቸው 22 ብር በጀት ብቻ እንደነበር ይታወሳል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…
Subscribe to a channel