tikvahethiopia | Unsorted

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1519086

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Subscribe to a channel

TIKVAH-ETHIOPIA

#አእላፋትዝማሬ #TheMelodyofMyriads

በአዲስ አበባ አእላፋት የተሳተፉበት " የአእላፋት ዝማሬ / The Melody of Myriads " መርሐግብር በቦሌ በድብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ተከናውኗል።

ይህ ዘንድሮ ለ2ኛ ጊዜ የተከናወነው መርሐግብር ከአምናውን የላቀ የምእመን ቁጥር የተገኘበት እንደሆነ በስፍራው በመገኘት ለመገንዘብ ችለናል።

መርሐግብሩ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እንዲሁም ብፁአን አባቶች ተገኝተው ነበር።

የዝማሬና የምስጋና መርሐግብሩ የልደት በዓልን በማይገባ ቦታ የሚያሳልፉ በእግዚአብሔር ቤት ሆነው እንዲያሳልፉ ለማድረግ ዓላማ ያነገበ ነው።

የፎቶ ባለቤት ፦ ሚኪ ፎቶግራፊ
የቪድዮ ባለቤት ፦ ጃንደረባው ሚዲያ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው በእግሩ ነው የመጣው ፤ ቀጥሎ በትራንስፓርት እየመጣ ያለ እንግዳ አለ " - የላሊበላ ከተማ አስተዳደር

የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በተለይ በላሊላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን በደማቁ ይከበራል።

ድንቁ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን የሚገኝበት አማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎችና በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች መካከል የተኩስ ቀጠና ከሆነ አንድ አመት ከወራት በላይ ቢያስቆጥርም፣ ህዝበ ክርስያቱ በዓሉን በቦታው ለማክበር ከመጓዝ እንዳልተገደበ ተሰምቷል።

የክልሉ ህዝብ ከአንድ አመት በላይ ለሆነ ጊዜ በጦርነት ቀጠና በመሆኑ ከቦታ ቦታ በሰላም በመንቀሳቀስ የነፍስና የሥጋ ስራውን ለማከናወን ከመቸገሩ ባሻገር ሞት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት እያስተናገደ ይገኛል።

ከዚህ ባሻገር በቡግና ወረዳ በድርቅና በምግብ እጥረት የሚላስ የሚቀመስ እንደ ሰማይ የራቃቸው ጨቅላ ህፃናት በከፋ ችግር ውስጥ ያሉበት ክልል ነው።

ይሁን እንጂ የክልሉን ህዝብ ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች ያሉ ኦርቶዶክሳዊያን ወደ ቦታው ለማቅናት የክልሉ ሁኔታ እምብዛም እንዳልገደባቸው ተነግሯል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የበዓሉ የዋዜማ ድባብ እና ዝግጅት ምን ይመስላል ? ሲል ለላሊበላ ከተማ አስተዳደር ጥያቄ አቅርቧል።

የላሊበላ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ወንድምነው ወዳጅ ምን አሉ ?

“ ቅዱስ ላሊበላ ከተማ የገና በዓልን ለማክበር በቂ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ እንግዶቿን እየተቀበለች ነው። እንግዶች ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ወደ ከተማዋ እየገቡ ይገኛሉ።

ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው በእግሩ ነው የሚመጣው። ከዛ ቀጥሎ በትራንስፓርት እየመጣ ያለ እንግዳ አለ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ፣ ከባሕር ዳር፣ ከጎንደር በዘረጋው በረራም እንግዶች ገብተዋል።

ቅዱስ ላሊበላ ከተማ እንግዷቿን በመቀበል የነበረ ግርማ ሞገሷን በመላበስ ተናገራለች። ወጣቶች ዝቅ ብለው እግር በማጠብ እንግዶችን የማስተናገድ ባህላቸውን አከናውነዋል ”
ሲሉ ገልጸዋል።

ክልሉ የጸጥታ ችግር ላይ መሆኑ ይታወቃል፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የጸጥታውን ጉዳይ በተመለከተ ምን እንደተሰራ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል።

አቶ ወንድምነው በሰጡት ምላሽም፣ “ ገናን ማክበር የጸጥታ ችግር ስጋት ሊሆን አይችልም ” ብለዋል።

“ ገና ሃይማኖታዊ በዓል ነው፤ ገና ህዝባዊ በዓል ነው፣ ገና እምነታዊ በዓል ነው። ገና የጸጥታ ችግር ሊሆን አይችልም። ገናን ማክበር የሚፈልግ ሰው ልቦናውን አዘጋጅቶ መገኘት ብቻ ቅድመ ሁኔታ ነው ” ሲሉ አክለዋል።

ምን ያህል እንግዶች እንደሚገኙ ሲጠየቁም፣ ከበዓሉ በኋላ እንጂ አሁን ለመገመት እንደሚያዳግት አቶ ወንድምነው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ ሰጥተዋል።

የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተልፈው ፣ “ ጥሪያችንን አክብራችሁ በላሊበላ ታድማችሁ ከተማችንን ወደነበረ ግርማ ሞገሷ እየመለሳችሁ ላላችሁ ላቅ ያለ ክብር አለን ” ሲሉ አመስግነዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

“ይሄ ፌሪያቲክ ኢራፕሽን ይባላል። ብዙ ጊዜ ቅልጥ አለቱ ወደ ላይ መጠጋቱን አንዱ ማመላከቻ ነው ” - ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር)

በአፋር ክልል የመሬት መንቀጥቀጥ ከተስተዋለባቸው አካባቢዎች ተጠቃሽ በሆነው ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ሰሞኑን “ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከሰተ ” መባሉ ይታወቃል።

በዚህም በነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ እየተሰራ መሆኑ ሰሞኑን ተገልጿል።

ተከሰተ የተባለውን የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ በተመለከተ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ስፔስ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም ዳይሬክተር ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዳይሬክተሩ ምን አሉ ?

“ እሳተ ገሞራ እስካሁን አልፈነዳም። እሳተ ገሞራ ፈነዳ የሚለው መታረም አለበት። እስካሁን የመጣውን ፌሪያቲክ ኢራፕሽን እንለዋለን። 

እንፋሎት እና የአለት ስብርባሪዎች ናቸው በከፍተኛ ግፊት ወደ ላይ ወደ መሬት እየተወረወሩ የሚወጡት። ይሄም የጋለ መሬት ውስጥ ያለ ውሃ አለ። ያም ከታች ማግማው እየተጠጋ ሲሄድ ይግላል። 

ውሃው በከባድ ፕሬዠር መሬት ውስጥ ታምቆ ስለሚቆይ ቅልጥ አለቱ ወደ ላይ እየተጠጋ ሲመጣና ውሃውን ያቀፈውን አለት ሲያበላው ውሃው በጣም ስለሚፈላ በጉልበት በየስንጥቁ ተመንጭቆ ነው የሚወጣው።

ከትላንትና በስቲያ የሆነው ይሄ ነው። እርግጥ የጭቃ፣ የድንጋይ ስብርባሪዎች ጠራርጎ ይዞ ወጥቷል። ይሄ ፌሪያቲክ ኢራፕሽን ይባላል። ብዙ ጊዜ ቅልጥ አለቱ ወደ ላይ መጠጋቱን አንዱ ማመላከቻ ነው።

ይሄ ማለት ግን ይፈነዳል ብቻ ማለትም አይደለም። ሊፈነዳ ይችላል፤ ላይፈነዳም ይችላል እንጂ።

ነገር ግን ከትላንትና በስቲያ በብዙ ቦታ ላይ ‘ተነፈሰ፣ ፈነዳ’ ሲባል ነበር። ይህ ትክክል አይደለም። እሳተ ገሞራ ሲፈነዳ እንዲህ ቀላል አይደለም።

ለማንኛውም ግን ይሄም ቢሆን ለጤና አደገኛ የሆኑ ጋዞች ይዞ ሊወጣ ስለሚችል ይህን ስብስቦ ከአካባቢው ማራቅ አስፈላጊ ነው። 

ብዙ ሰዎች አካባቢው ሲሯሯጡ አንዳንድ መረጃዎች ያሳዩ ነበር።

ስለዚህ እስካሁን ቅልጥ አለት ወደ መሬት ላይ አልመጣም። እሳተ ገሞራ ፍንዳታ አልነበረም። ይሄ መታረም ያለበት ነገር ነው ማስረዳትም ያስፈልጋል


አልፈነዳም። ቮልካኒክ ኢራፕሽን የለም። ነገር ግን ይሄ ፌሪያቲክ ኢራፕሽን ራሱ ጋዝ፣ ሽታ ሊፈጥር ይችላል።

የፈላው ውሃ ራሱ ሰዎችን ያቃጥላል፣ እንፋሎት ነውና። ተስፈንጥሮ የሚወጣው ጭቃ ራሱ የጋለ ጭቃ ነው። ያ፣ ያአደጋ ሊያደርስ ይችላል። ግን የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ እኛ እስካሁን አልሰማንም" ብለዋል።

#TikvahEthipiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ብርሃን_ባንክ
እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ!

በዚህ የበዓል ወቅት ከውጭ ሃገራት የሚላክልዎትን ገንዘብ በብርሃን ባንክ በኩል ሲቀበሉ ወይም በእጅዎ ያለውን የውጭ ሃገር ገንዘብ በባንካችን ሲመነዝሩ ከእለቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን በተጨማሪ 2% እና ልዩ የበዓል ስጦታ ያገኛሉ!
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ሥራችን!
#Christmas #moneytransfer #Stressfreebanking #berhanbank #bank #finance #bankinethiopia
➡️ Facebook
➡️ Telegram
➡️ Instagram
➡️ Twitter
➡️ LinkedIn
➡️ YouTube

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#MoE

የመውጫ ምዘና ከየካቲት 10 እስከ የካቲት 12
/2017 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ ተገለጸ።

በክረምት በመምህርነት ሙያ ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ድግሪ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና ሲከታተሉ ቆይ የመውጫ ምዘና ለሚጠባበቁ መምህራን የመውጫ ምዘና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ተደርጓል።

በዚህም የመውጫ ምዘናው ከየካቲት 10 እስከ የካቲት 12/2017 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን መምህራኑ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዳያድረጉ ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

ሚኒስቴሩ ምዘናው በየአቅራቢያ ባሉ ዩኒቨርስቲዎች የሚሰጥ መሆኑን ገልጾ " በቀጣይ ክልል / ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮዎች በኩል የምናሳውቃችሁ ይሆናል " ብሏል።

#MinistryofEducation

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#AtoBulchaDemeksa

ጉምቱው ፖለቲከኛ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ ስም የነበራቸው ጉምቱው ፖለቲከኛ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

" አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በማረፋቸው የተሰማኝን ኀዘን እገልጻለሁ " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " በሚችሉት ሁሉ ሀገራቸውንና አፍሪካን ያገለገሉ፣ በአቋማቸው ጽኑ፣ ሕዝቦችን ለማቀራረብ የተጉ፣ እውነት ነው ብለው ያመኑትን የትምና መቼም የሚናገሩ ነበሩ " ብለዋቸዋል።

" እንዲህ ዓይነት ብርቱ ሽማግሌዎችን ማጣት ጉዳቱ ለሀገር ነው። ፈጣሪ ነፍሳቸውን ይቀበላት " ሲሉም ገልጸዋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#DireDawa

" በወንጀል ተግባሩ ላይ የተሳተፉ የፖሊስ አመራር እና አባላት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው ወደ መጠናቀቁ ነው " - ድሬ ፖሊስ

ከሰሞኑን በድሬዳዋ ከተማ አንድ ወጣት በአሰቃቂ ሁኔታ በፖሊስ አባላት ድብደባ መገደሉ በርካቶችን አስቆጥቷል ፤ አሳዝኗል።

በተለይ ገንደቦዬ ዛሬም ድረስ ሀዘን ላይ ናት።

የ1 ልጅ አባት የሆነው ወጣት ሙራድ መሀመድ (አሳዶ) ከሰሞኑን በፖሊስ ድብደባ ለሞት መዳረጉ ተነግሯል።

የቅርብ ወዳጆቹ ፥ " ሙራዴ ከሰው ጋር ተግባቢ ፤ በሚኖርበት አካባቢ ገንደቦዬ ላይም የሚታወቅ ፤ የሚወደድ ወንድማችን የሰፈራችን ድምቀት ነበር። ህግ አለባት በምንልበት ከተማችን ያውም ደግሞ ህግ አስከባሪ ተብሎ ዩኒፎርም በለበሱ ፖሊስ አባላት በአሰቃቂ ሁኔታ ተደብድቦ ተገደለ መባሉ እጅግ በጣም አስደንግጦናል፣ አሳዝኖናል ፣ አስቆጥቶናል " ብለዋል።

" የተፈጸመው አሰቃቂ ወንጀል ሰዎች በፖሊስ እና የህግ የበላይነት ላይ ጥያቄ እንዲያነሱ የሚያደርግ ነው። ሙራድ ሰላማዊ ህይወቱን እየመራ ባለበት ነው ይህ ግፍ የተፈጸመው " ሲሉ አክለዋል።

" ፍትህ ሊሰጥ ፤ እውነት ሊወጣ ፣ ወንድማችንን ለሞት የዳረጉት የሚገባቸውን ቅጣት ሊያገኙ ይገባል " ሲሉ አክለዋል።

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ፥ " ወጣት ሙራድ መሀመድን በግል ቂም በቀል ተነሳስተው ኢሰብዓዊ በሆነ መልኩ በመደብደብ ፣ ለሞት በመዳረግ አስነዋሪ ተግባር የፈጸሙ አባላቶችን በቁጥጥር ስር አውለን ምርመራ በማጣራት ላይ ነን " ሲል መግለጫ አውጥቷል።

ድርጊቱ " ጥቂት " ሲል በጠራቸው የፖሊስ አባላት መፈጸሙን አመልክቷል።

ወጣት ሙራድ በፖሊስ አባላት ተደብድቦ ለሞት በመዳረጉ እጅግ ማዘኑን ገልጾ " ጠቅላይ መምሪያውን በፍጹም የማይወክል ነው " ብሏል። " አስነዋሪ " ሲል የጠራውን የወንጀል ተግባርም አውግዟል።

አሁን ላይ በወንጀል ተግባሩ ላይ የተሳተፉ የፖሊስ አመራር እና አባላት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው ወደ መጠናቀቁ እንደሆነ ገልጿል።

ወጣቱ ተደብድቦ ለሞት ከተዳረገ በኃላ ስርዓተ ቀብሩ በተፈጸመበት ወቅት የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ከድር ጁሀር ፤ " ግለሰባዊ የቂም በቀል ጥላቻ ነው የመንግሥትን ልብስ ሽፋን አድርጎ የተፈጸመው " ያሉ ሲሆን ድብደባውን ፈጽመው ሙራድን ለሞት የዳረጉት 3 የፖሊስ አባላት እንደሆኑ ገልጸዋል።

" ጣቢያ አላመጡትም ፤ ከዚራ አላመጡትም እኛም ምንም መረጃ አልነበረንም ፤ ወስደው በድብደባ ነው የሞተው። ማታ ጤና ጣቢያ መልካ ላይ ነው የተወሰደው ከዛ በኃላ ነው መረጃው የደረሰን " ብለዋል።

በሙራድ መሀመድ ህልፈት ሀዘናቸውን ገልጸው " ልጅ አለው፣ ሚስት አለው እናትም አለው ቤተሰቦቹን የማገዝ እና መርዳት ኃላፊነት አለብን " ሲሉ ተናግረዋል።

#Murad #DireDawa #Police

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ቪድዮ ፦ ነዳጅ ጭነው ያለአግባባ በየቦታው ቆመው የሚገኙ የነዳጅ ጭነት ተሸከርካሪዎች ከተደበቁበት እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አሳወቀ።

የአፋር ክልል ንግድ ቢሮን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በጠየቀው ትብብር መሠረት ከክልሉ የፀጥታ አካል ጋር በመሆን በሰጠው ምላሽ ነው ከተደበቁበት እንዲወጡ እየተደረገ ያለው።

አዲስ አበባን ጨምሮ ለተለያዩ ክልሎች የሚጓጓዝን ነዳጅ ይዘው በአፋር ክልል ልዩ ቦታው " ሰርዶ አድማስ " በሚባል ቦታ በየጥሻው የቆሙት ቦቴዎች የፀጥታ አካል ባደረገው አሰሳ ተደብቀው በቆሙበት መያዛቸውን ባለስልጣን መ/ቤቱ ገልጿል።

" በአሁን ሠዓት የክልሉ ንግድ ቢሮ ለተሸከርካሪዎቹ እጀባ በመስጠት ወደ የመዳረሻቸው እንዲንቀሳቀሱ ተደርጓል " ብሏክ።

" ' በወሩ መጨረሻ የነዳጅ ዋጋ ክለሳ ይሠራል ' በሚል ያልተጨበጠ ተስፋ ነዳጁን ይዘው የተሸሸጉት እነዚህ ተሸከርካሪዎች ያለአግባባ የሚያገኙትን ትርፍ ከማሰብ ውጪ የጫኑት ነዳጅ በባህሪው በትነት የሚባክን፣ አደጋን የማስከተል አቅም ያለው መሆኑን ለማሰብ አልፈቀዱም " ሲል ኮንኗል።

" ከዚህ ባለፈ በየክልል ከተሞች የነዳጅ ማደያዎችን በማድረቅ እጥረት በመፍጠር ህብረተሰቡን የማጉላላት ስራን መስራታቸውን ማመን አይፈልጉም " ሲል አክሏል።

በዚህም " የፈፀሙት ሕገወጥ ተግባር በተጨባጭ የተረጋገጠ በመሆኑ ይህን ተግባር የፈጸሙት ላይ መንግስት ለህብረተሰብ ተጠቃሚነት ሲል በድጎማ የከፈለበትን የነዳጅ ወጪ እንዲሸፍኑ የሚደረግ እንደሆነ እና ከምርት መሰውር ጋር በተያያዘ በሕግ ተጠያቂ የሚደረጉ ይሆናል " ብሏል።

" በነዳጅ ግብይት ሂደት ውስጥ የሚፈፀሙ ሕገ-ወጥ ተግባራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱ መጥተዋል " ያለው ባለስልጣን መ/ቤቱ " በግብይት የሚሳተፉ አካላት ጤናማ የንግድ ስርዓትን ተከትሎ ትርፍ ከማግኘት ይልቅ ለህብረተሰቡ ጥቅም ሲባል ድጎማ ተደርጎበት የሚቀርበውን ነዳጅ በኮንትሮባንድ እና በጥቁር ገበያ አሳልፈው ይሰጣሉ " ብሏል።

በዚህም " በየክልሉ ከሚፈጠሩት እጥረት ባሻገር በዚህ መልኩ ነዳጅ የጫኑ ተሸከርካሪዎች በየቦታው እንዲዘገዩ በማድረግ ተጨማሪ ትርፍ ለማግኘት ተስፋ በማድረግ ተጠቃሚውን ህብረተሰብ የማጉላላት ተግባር ይፈጽማሉ " ሲል ወቅሷል።

" ነዳጅ አቅርቦት ላይ ሰው ሰራሽ እጥረት በየጊዜው እንዲፈጠር የሚያደርጉ መሰል ተግባራት በግልጽ እየታዩ ባለበት አንዳንድ መረጃ ሰጪዎች ለመገናኛ ብዙኃን በሚሰጡት መረጃ ' የነዳጅ እጥረቱን የፈጠረው ለኛ የሚሰጠው የገበያ ድርሻ ማነስ ነው ' የሚል የማይገናኝ ምክንያት ሲያቀርቡ ይሰማሉ " ሲል ኮንኗል።

" የነዚህ ተሸከርካሪዎች እና የነዳጁ ባለቤቶች በዚህ ወቅት የፈፀሙት ተግባር ግን የችግሩን ዋነኛ ባለቤት አሳይቷል " ብሏል።

#PetroleumandEnergyAuthority

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Earthquake : ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር።

በተለይ ቤት ውስጥ የነበሩ ሰዎች ረዘም ላለ ሰከንድ ንዝረቱ ተሰምቷቸዋል።

የአሁኑ ንዝረት ከትላንት ምሽቱ አንፃር ጠንክሮ የተሰማ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

“ ከ29 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሌላ ቦታ ሸጠዋቸዋል። ቀሪዎቹም ከፍተኛ ስጋት አለባቸው ” - በማይናማር ያሉ ኢትዮጵያውያን ወላጆች ኮሚቴ

በማይናማር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ካሉበት አስቸጋሪ ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግስት እንዲያስወጣቸው በተደጋጋሚ እየተማጸኑ እንደሚገኙ ይታወቃል።

የወላጆች ኮሚቴ በበኩሉ፣ “ ግብረሰዶም ወደማፈጸምበትና ኩካሊት እያወጡ የሚሸጡ ሰዎች ወዳሉበት ካምቦዲያ ሊሸጧቸው እንደሆነ ሰምተናል ” ሲል ስጋቱን ገልጾልን ነበር።

ስለጉዳዩ ማብራሪያ የጠየቅነው ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ልጆቹ ያሉበት ቦታ አዳጋች እንደሆነ፣ ከአገራቱ ጋር የሥራ ስምሪት አለመኖሩ ሁኔታውን አስቸጋሪ እንዳደረገው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲገልጽ መቆየቱ አይዘነጋም።

ከቶኪዮ ኤምባሲ ጋር እየተነጋገረ መሆኑንም ገልጾ የነበረው ሚኒስቴሩ ከዚያ በኋላ ላቀረብለት ጥያቄ፣ “ አዲስ መረጃ ካለ አሳውቃለሁ ” ቢልም እስካሁን ያለው ነገር የለም።

አሁንስ የኢትዮጵያውያኑ ጉዳይ ከምን ደረሰ ?

የወላጆች ከሚቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ “ ከ29 በላይ የማሆኑ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሌላ አገር ሸጠዋቸዋል። ቀሪዎቹም ከፍተኛ ስጋት አለባቸው ” ብሏል።

በመሆኑም ልጆቹ ካሉበት ስቃይ እንዲወጡ በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ጫና እንዲያደርጉ ቢሯዎቻቸውን እያንኳኳ በደብዳቤ ጭምር እየተማጸነ መሆኑን ገልጾ፣ መንግስት አሁንም ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቋል።

ኮሚቴው በዝርዝር ምን አለ ?

“ ምንም መፍትሄ የለም። እንዲያውም የተወሰኑ ልጆችን ወደሌላ ቦታ ሸጠዋቸዋልና ያን የሰሙ ልጆች በጣም ተረብሸዋል።

ወደ ካምቦዲያ እየሸጧቸው ነው ስለተባለ ተጨናንቀዋል። በየቀኑ ‘ምን አዲስ ነገር አለ?’ ነው የሚሉን። እኛም ውጪ ጉዳይን አሳስበን መፍትሄ በመጥፋቱ አሁን የሃይማኖት ተቋማትን እየተማጸንን እንገኛለን።

ልጆቹን በማይናማር ከነበሩበት ቦታ አንስተው ወደ ሌላ ቦታ እየሸጧቸው ነው። ይሄ ነው ችግር የሆነው። በየጊዜው አዲስ ነገር ነው የሚሰማው በጣም ይጨንቃል።

ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርን በተደጋጋሚ ብንጠይቅም ምንም አዲስ ነገር የለም። አሁንም ተሰባስበን ልንሄድ ነው። የሃይማኖት ተቋማት ጫና እንዲያደርጉ እየተማጸንን ነው።

ዱኣ አድርጉ፤ ጾም ጸሎት ይታወጅ ብለን እየጠየቅን ነው።

ሀገራቱንም፣ ህዝብንም፣ ቤተሰብንም መጥቀም የሚችሉ የተማሩ ልጆቻችን ስቃዬ ላይ እያሉ ውጪ ጉዳይ ሰምቶ ዝም ከማለት ያስቸገረው ነገር ካለም ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት እንዲያቀርቡልን እንጠይቃለን።

ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤትም ሄደን ነበር ለቅሬታ ሰሚ ክፍል ጥያቄያችንን በኢሜይል እንድናስገባ ነው የነገሩን። ግን በኢሜይል ብቻ አስገብተን አንቀመጥም ደብዳቤም እንወስዳለን ”
ብሏል።

(ጉዳዩን እስከ መጨረሻው የምንከታተለው ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

ከጥቂት ከደቂቃዎች በፊት ተከስቶ የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 5.0 የተለካ እንደሆነ የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ አሳውቋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ ከአዋሽ 31 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተከሰተ ነው።


ዛሬ በተለያየ ሰዓት አምስት ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ ሲሆን የአሁኑ ለስድስተኛ ጊዜ የተከሰተው (በሬክተር ስኬል 5.0 የተለካው ) በመጠን ከፍተኛው ነው።

ንዝረቱ አዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች ላይ በደንብ ተሰምቷል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Earthquake

ትላንት ለሊት 9:52 ላይ በርካቶችን ከተኙበት የቀሰቀሰው በሬክተር ስኬል 5.8 ከተለካው የመሬት መንቀጥቀጥ በኃላ በሬክተር ስኬል 4.4 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል።

ዛሬ ደግሞ በሬክተር ስኬል ፦
➡️ 4.7
➡️ 4.6
➡️ በድጋሚ 4.7
➡️ በድጋሚ 4.6
➡️ 4.9 የተለኩ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ተመዝግበዋል።

ሁሉም አዋሽ እና አካባቢው ናቸው።

ባለፉት ሰዓታት ከተመዘገበው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ 4.9 ከፍተኛው ነው።

በሌላ በኩል አፋር ክልል ዱላሳ ወረዳ የሚገኘው የኢፌዴሪ ከሰም ስኳር ፋብሪካ በመሬት መንቀጥቀጡ ከፍተኛ ጉዳት አስተናግዷል።

በስኳር ፋብሪካው አስተዳደር ህንፃ፣ በኃይል ማስተላለፊያ ክፍል፣ የላብራቶሪ እና ኤሌክትሮ ሜካኒካል ክፍል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

አሁን ላይ መሬት መንቀጥቀጡ በከፍተኛ ሁኔታ በአከባቢው እየጨመረ በመምጣቱ ጉዳት በደረሰባቸው ህንፃዎች ውስጥ የሚገኙትን ሌሎች ንብረቶችን ለማዳን የመሬት መንቀጥቀጡ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል።

የፋብሪካው ሰራተኞች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ አስቀድሞ እንዲለቁ መደረጉ ተነግሯል።

ከ4 ሺህ በላይ ሰራተኞች ያለው የከሰም ስኳር ፋብሪካ በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ስራ ማቆሙን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

በተያያዘ መረጃ ፥ መንግሥት የርዕደ መሬቱ ማዕከል ከሆኑ አካባቢዎች ነዋሪዎችን የማራቅ ሥራ እያከናወነ መሆኑን አሳውቋል።

በተለይም ደግሞ የርዕደ መሬቱ ማዕከል የሆኑት አካባቢዎችን በመለየት በ12 ቀበሌዎች ላይ ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተውጣጡ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችን በቦታው በማሰማራት የጉዳቱን መጠን አሰሳ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በእነዚህ ቀበሌዎች ከሚኖሩ 80 ሺህ ዜጎች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን በመለየት ነዋሪዎችን ከአካባቢው በማራቅ ለማስፈር ርብርብ እየተደረገ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

#Ethiopia #Afar #Earthquake

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#መግለጫ : " የአእላፋት ዝማሬ/The Melody of Myriads " ሰኞ በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ በተመሳሳይ ሰዓት ይካሄዳል።

ይህንን አስመልክቶ የተሰጠው መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

የዘንድሮው የእላፋት ዝማሬ / The Melody of Myriads በአዲስ አበባ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል (ቦሌ መድኃኔዓለም) ፤ በድሬዳዋ ደግሞ ለገሀር አደባባይ ብቻ ነው የሚካሄደው።

(መግለጫውን ያንብቡ)

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

🚨#ጥንቃቄ

ውድ ቤተሰቦቻችን ሆይ ፤ የመሬት መንቀጥቀጥ ድንገተኛ ፣ ቅፅበታዊ መቼ እንደሚፈጠር መቼስ እንደሚቆም የማይታወቅ ክስተት ነው።

መሬት መንቀጥቀጥ ክስተትን መተንበይ የሚባል ነገር የለም ፤ የት አካባቢ እንደሆነ እንጂ መቼ ይከሰታል የሚባለውን ተመራማሪዎች መተንበይ አይችሉም።

ስለዚህ በየትኛውም ሰዓት፣ ጊዜ ሊከሰት ይችላል ፤ ሊመጣ ይችላል ብሎ ማሰብ የግድ ይላል።

" አሁንማ እኮ ተለመደ " ተብሎ መዘናጋት አይገባም።

" ፈጣሪ ክፉን ሁሉ ያርቅልን " እያልን መማፀኑ እንዳለ ሆኖ በዚህ ወቅት ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች በአግባቡ ማወቅ ያስፈልጋል።

የሰሞነኛው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት እንዳለ ሆኖ የትላንት ለሊቱ ከፍተኛ የሆነ የማንቂያ ደውል ነው።

ብዙዎች ተኝተው ከነበሩበት ቀስቅሷል ፣ ፎቅ ላይ የሚኖሩ ሰዎች ወዲያና ወዲህ ብለዋል፣ እቃዎች ከላይ ወደ ታች ወድቀዋል።

ሰዓቱ ለሊት የመኝታ ሰዓት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አንዳንዶች ያልሰሙት ይሆናል እንጂ ጥንካሬው ከእስከዛሬው ሁሉ የተለየ ፤ " ሰምተን እናውቅም " ያሉ ሰዎች ሁሉ የሰሙት ሆኗል።

አዲስ አበባ ብዙ ህንጻዎች ያሉባት በመሆኑ ልዩ ጥንቃቄ ማድረግ ያሻል።

በመሆኑም ውድ ቤተሰቦቻችን ፍጹም አትዘናጉ ! ፈጣሪያችንን ከክፉ ሁሉ ነገር እንዲጠብቀን እየተማፀንና ሳንደናገጥ ንቁ ሁነን የጥንቃቄ እርምጃዎችን ለመተግበር በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ መሆን ይገባናል።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ዋሪት !

ውድ ደንበኞቻችን  የገና በዓልን  ምክንያት በማድረግ በምርቶቻችን ላይ ላይ ከታህሳስ 9 - ጥር 23/2016  የሚቆይ እስከ 30% ልዪ ቅናሽ ማድረጋችንን  ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው እንዳያመልጥዎት ወደ ማሳያ ክፍሎቻችንን በመምጣት ይጎብኙን !
* 22- ዋሪት ህንፃ
* ጉርድ ሾላ- ሴንቸሪ ሞል
* ለቡ- ቫርኔሮ ፊት ለፊት
* ፒያሳ- ፍርዱ ኮሜርሻል
* ቡልቡላ- ልዑል ህንፃ ፊት ለፊት
* አዳማ- ሶረቲ ሞል
*ወሎ ሰፈር-  ከጋራ ሙለታ ህንጻ ጎን
📞0911210706 | 07

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ፎቶ ፦ በድሬዳዋ ከተማ አእላፋት የተሳተፉበት የአእላፋት ዝማሬ መርሐግብር በለገሀር አደባባይ ተከናውኗል።

ይህ የዝማሬና የምስጋና መርሐግብር የልደት በዓልን በማይገባ ቦታ የሚያሳልፉ በእግዚአብሔር ቤት ሆነው እንዲያሳልፉ ለማድረግ ዓላማ ያነገበ ነው።

ባለፈው ዓመት በአዲስ አበባ የጀመረው ይኸው የዝማሬና ምስጋና መርሐግብር ዘንድሮ ድሬዳዋን አካቶ ተካሂዷል።

የፎቶ ባለቤቶች ፦ መኮንን እንግዳው፣ ሀብታሙ አለሙ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

“ ቅልጥ አለቱ በመሬት ውስጥ የሚያደርገዉ እንቅስቃሴና ወደ ላይ የመውጣት ግፊቱ እንደቀጠለ ነው።  ግን ቀዝቅዞ እዛው ሊቀር፣ ከመሬት በላይ ሊፈነዳ ይችላል ” - ኤሊያስ ሌዊ (ዶ/ር)

በአዋሽ ፈንታሌና ዶፈን ቮልካኖዎች መካከል የሚከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ጠንከርና ከፍ እያለ መምጣቱ በተደጋጋሚ ተገልጿል። ሰሞኑንም በተደጋጋሚ እየተከሰተ ተስተውሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ለመሆኑ ምን መደረግ አለበት? ሲል ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ስፔስ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም ዳይሬክተር ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር) ጥያቄ አቅርቧል።

ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር) ምን መለሱ ?

“ ስምጥ ሸለቆ አካባቢ ነው ያለነው። ስምጥ ሸለቆ የሚፈጠርበት ተፈጥሯዊ ሂደት ነው። ተፈጥሯዊ ስል፤ ርዕደ መሬት እያስጨነቀው ላለ ማህበረሰብም ሆነ ለእኛ ባለመያዎቹ ሲንቀጠቀጥ ያስጨንቃል። 

ወዴትስ ያመራ ይሆን? የሚለው ያሳስባል። ግን መንስዔው ይታወቃል ተፈጥሮም የራሷን ሂደት እየሄደች ነው ያለችው ለማለት ነው። የስምጥ ሸለቆ አፈጣጠር አንዱ ሂደት ነው ለማለት ነው። 

እናም ከዚህ ቀደምም እንደገለጽነው ቅልጥ አለት መሬት ውስጥ እየተንቀሳበሰ ነው። በፈንታሌና በዶፈን ተራራዎች መካከል። የምናየው ርዕደ መሬት የዛ ውጤት ነው።

የሰሞኑ ክስተት እየነሆነ ያለው የዛ እንቅስቃሴ የፈጠረው መንቀጥቀጥ ሞገድ በመሬት ውስጥ ተጉዞ ነው አዲስ አበባ ድረስ የሚሰማን። 

መጠኑ ከፍ ሊል ይችላል ወይ? ለሚለው ጥያቄ፣ ሊልም ላይልም ይችላል። ማለትም ከዚህም በላይም ከፍ ሊል ይችላል።

ነገር ግን ይሄ በሚሆንበት ጊዜ እኛ ምን ማድረግ አለብን? የሚለው ነው መታወቅ ያለበት"
የሚል ማብራሪያ ሰጥተዋል።

መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ ኤልያስ (ዶ/ር) ምን ተናገሩ?

“እስካሁን ድረስ ከፍ ያለ የመሬት መንቀጥቀጥም አልመጣም። መደርግ ስለሚገባው ነገርም ሲጠቀስ አንዳንድ ሚዲያ ላይ ሰዎች መቀለጃ አድርገውታል። ‘ጠረንጴዛ ሊያድነን ነው ወይ?’ ይላሉ።

ግን ይሄ የዓለም አቀፍ ተሞክሮና ስታንዶርድ ነው። ብዙ ሰዎች በዚሁ መንገድ ከአደጋ ድነዋል። 

ስለዚህ ከኮለን አካባቢ ሥር መቆም፣ ከጠረንጴዛ ሥር በፍጥነት መግባት፣ አሳንሰር አለመጠቀም፣ ፎቅ ላይ ለመውረድ አለመሞከር ያስፈልጋል። 

እሳት ሊያቀጣጥሉ የሚችሉ እንደ ሻማ ያሉ ነገሮችን ማጥፋት የመሳሰሉት እርምጃዎች ቀላል ይመስላሉ ግን የብዙዎችን ሕይወት አትርፈዋል።

በጣም የአጭር ጊዜ ስለሆነ የሚሆነው ከቤት ለመውጣትም ጊዜ ላይሰጥም ይችላል። 

የጊዜ አለማግኘት ብቻም ሳይሆን ቁልፍ ቆልፈን ቁጭ ብለን እንኳ እጃችንን እየተንቀጠቀጠ ለመክፈት ያዳግታል። በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን ጥንቃቄዎች ማድረግ አለብን።

ማንም ሊያቆመው አይችልም ይሄንን ክስተት። ለኛ አሁን እዚህ ካለው የመሬት መንቀጥቀጥ በይበልጥ እያሰጋን ያለው ፈንታሌ አካባቢ ያለው ሁኔታ ነው። ጥፋት ካደረሰ ከኛ በበለጠ እዛ አካባቢ ነው ብዙ ጥፋት የሚያደርሰው።

እዛም ያለው የሰው ሕይወት ነው፤ እዚህም ያለው የሰው ሕይወት ነው። ሕይወት ነው የትም ቦታ ያለው። እዛ ላሉት ወገኖቻችንም እየተጨነቅን ነን ያለነው።

እዛ አካባቢ መሬት ውስጥ የሚጓዘው ቅልጥ አለት ወደ ላይ የመውጣትም እዛው የመቅረትም የሁለቱም ፓስቢሊቲ አለው። 

ከቀን ወደ ቀን የምናየው መረጃ እንደሚያሳየው ቅልጥ አለቱ ወደ ላይ ለመውጣት በሚያደርገው ግፊት መሬት እየተወጣጠረች ነው፡፡

ይህ ማለት ግን እርግጠኛ ሆነን ይፈነዳል ማለት አይደለም። ቀዝቅዞም እዛው ሊቀር፣ መጨረሻም እዛው ሊቆም ይችላል።

ቅልጥ አለቱ ወደ ላይ የሚመጣ ከሆነ ምን ማድረግ አለብን የሚለውን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት፣ የመንግስት አካላት፣ መስሪያ ቤቶች፣ የግል ድርጅቶች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በሕብረት እየተሰራ እንደሆነ አውቃለሁ።

እኛ የምርምር ማዕከል ነን ሥራችን መረጃ ማቅረብ ነው። እነርሱ ደግሞ ያንን መረጃ ወስደው በተግባር ላይ ያውሉታል የሚል ሙሉ እምነትና ግምት አለን። አንዳንድ ሥራዎችም እንደተጀመሩ መረጃ አለኝ። 

በኛ በኩል እንደ ምርምር ተቋም መንስኤው ምንድን ነው? መጠኑ ስንት ነው? ምን መደረግ አለበት? የሚለውን እያቀረብን ነው ያለነው። 

ከዚህ በተጨማሪ ያለው ነገር መጠነ ሰፊ ሥራዎችን ናቸው የሚጠይቁት። መጠነ ሰፊ መስሪያ ቤቶችንም መቀናጀት ያስፈልጋል። 

እኛ ብቻም ሳንሆን በዓለም አቀፍ በሙያው ዘርፍ ካሉት ባለሙያዎች ጋር እንደ ኢንስቲትዩት እየተገናኘና መረጃ እያቀናጀ ነው ያለው”
ነው ያሉት።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ፎቶ ፦  የ2017 ዓ/ም የአእላፋት ዝማሬ / The Melody of Myriads በአዲስ አበባና ድሬዳዋ እየተከናወነ ይገኛል።

በአዲስ አበባ መርሐግብር እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን ተገኝቶ የልደት በዓል ዋዜማን በዝማሬ እንዲሁም በምስጋና እያከበረ ይገኛል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#የአእላፋትዝማሬ #TheMelodyofMyriads

በዓልን በማይገባ ቦታ የሚያሳልፉ በእግዚአብሔር ቤት ሆነው እንዲያሳልፉ ለማድረግ ዓላማ ያለው የአእላፋት ዝማሬ / The Melody of Myriads መርሐግብር ዛሬ ሰኞ በገና ዋዜማ በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ይከናወናል።

ቦታው ፦
👉አዲስ አባባ ፦ ቦሌ በድብረ ሳሌም መድኃኔዓለም
👉 ድሬዳዋ ፦ ለገሀር አደባባይ


ከነዚህ ከተሞች ውጭ በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ / ኢጃት አማካኝነት  የተዘጋጀት የአእላፋት ዝማሬ መርሐግብር የሌለ ቢሆንም ሁሉም ምእመናን ፣ ኦርቶዶክሳዊያን ሁሉ በዓሉን ቤተክርስቲያን እንዲያሳልፉት ጥሪ ቀርቧል።

በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ምእመናን ከዝማሬው በፊት ልክ 10:00 ሰዓት ላይ ተገኝተው የአንድ ሰዓት ጸሎተ የምሕላና ጸሎተ ኪዳን ላይ እንዲሳተፉ አደራ ተብሏል።

የዘንድሮው የአእላፋት ዝማሬ ከአምናው በተለየ ጥራት ለማካሄድ በየትኛውም ቦታ የቆመ ሰው የሚሰማው ድምጽ ሆነ የሚያየው ምስል እኩል እንዲሆን ጥረት ተደርጓል።

ለነፍሰ ጡሮች  እና የአካል ጉዳተኞች ልዩ ስፍራ የተዘጋጀ ሲሆን ለአስተባባሪዎች በመንገር ቦታ ማግኘት ይቻላል።

የጤና እክል ለሚያጋጥማቸው ተንቀሳቃሽ ክሊኒኮች አሉ።

የመኪና ማቆሚያን በተመለከተ በቤተክርስቲያን ቅፅጽረ ግቢ ሆነ አስፋልት ዳር መኪና ማቆም ተከልክሏል። መኪና ማቆም የሚቻለው ከህንጻዎቹ ጀርባ ነው።

መኪና ያላችሁ መርሐግብሩ ሲጠናቀቅ ወደናተ አቅጣጫ የሚሄዱትን በመጫን የትራንስፖርት ሰርቪስ እንድትሰጡ አደራ ተብሏል።

ወደ መርሐግብሩ የምትመጡ ነጭ ልብስ አድርጋችሁ እንድትመጡ ያንን ማድረግ ያልቻላችሁ ያላችሁን ልብስ ንጹህ አድርጋችሁ እንድትመጡ ጥሪ ቀርቧል።

በቂ ከበሮ ስለተዘጋጀ ከበሮ ይዞ መምጣት አያስፈልግም።

ቦሌ መድኃኔዓለም በጊብሰን በኩል ያለው በር ለቅዱስ ፓትርያርኩና ለሊቃነ ጳጳሳት መግቢያ ስለሆነ ምእመናን ሌሎች በሮችን እንዲጠቀሙ ተብሏል።

ድሬዳዋ ምድር ባቡር አደባባይ የሚያስገቡትን 5 በሮች መጠቀም ይቻላል።

በመርሐግብሩ በቂ ጥበቃ የተመደበ ሲሆን ፍተሻም ይኖራል።

ምን ይዞ መገኘት / መግባት አይቻልም ?

➡ መሳሪያዎች
➡ ተቀጣጣይ ነገሮች
➡ የግል ካሜራ ፣ ድሮን
➡ ሽቶና ስፕሬይ
➡ ኮስሞቲክስ
➡ ክብሪት
➡ ስክሪብቶና የሾሉ ነገሮች
➡ የግል ከበሮ ይዞ መምጣት ክልክል ነው።


ወደ አእላፋት ዝማሬ የሚመጡ ምዕመናን እስከ 10 ጧፍ ይዘው እንዲመጡ ጥሪ ቀርቧል።

ሦስቱ ጧፎች የአእላፋት ዝማሬ / The Melody of Myriads / እስኪጠናቀቅ የሚበሩ ሲሆን የቀሩትን ለደብሩ በመባ መልክ ያስረክቡ። በደብሩ በኩልም ለገጠር አብያተ ክርስትያናት ድጋፍ ይደረጋል ተብሏል።

NB. የዕለቱን ሁነት የሚቀርጹ ፣ በቀጥታም የሚያስተላልፉ መገናኛ ብዙሃን ስላሉ ምእመናን በዝማሬና ምስጋና ላይ ብቻ ትኩረት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

' ልደቱን በባለ ልደቱ ቤት ! '
#TheMelodyofMyriads

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ትውስታ ...

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በምን ይታወሳሉ ?

በኢህአዴግ ጊዜ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሀገራቸውን በሚመሩበት ወቅት ፓርላማ የነበሩት ጉምቱው ፖለቲከኛ እና የኢኮኖሚ ምሁር አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ጠንከር ያሉ ምሁራዊ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በማንሳት ይታወቃሉ።

ንግግራቸው ለዛ የነበረው ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስን ጨምሮ መላ የፓርላማ አባላትን ሳቅ በሳቅ የሚያድረግ ፤ ድፍረትና እውቀት የተሞላበት ነበር።

በተለይ  ደግሞ በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ የዳበረ እውቀት ስለነበራቸው ሁሉም ሰው እሳቸው እድሉን አግኝተው እስኪናገሩ በጉጉት ነበር የሚጠብቀው።

በብዙዎች የሚታወሰው እና ሁሌም ተደጋግሞ የሚነሳው ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት ጋር በተያያዘ ያነሱት ጥያቄና ፓርላማውን ሳቅ በሳቅ ያደረጉበት ንግግራቸው ነው።

" ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ መንግስቱም ደጋግሞ ደጋግሞ ' ኢትዮጵያ በ110 ፣ በ111 አድጋለች ' ይላል ፤ እኔ ፣ እሳቸውም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚስቶችም ያውቃሉ በ111 ማደግ ማለት ተአምር ነው። ይሄን ተአምር የሰራችው ቻይና እንደውም አሁን እየሰራች አይደለም ፣ ታይዋን ፣ ደቡብ ኮሪያ ናቸው።

ኢትዮጵያ እንዴት አድርጋ ነው በ111 ያደገቸው ? አንጎላ አሁን በ112 እያደገ ነው ለምንድነው በአንድ ጊዜ ብዙ ዘይት አገኙ፣ ዘይት ያገኙ ሰዎች ወይም ሌላ ነገር ያገኙ በ110 ወይም በ111 ቢያድጉ አይገርምም። 111 አደግን ብለን ለዓለምስ እንዴት አድርገን ነው የምንገልጸው ?

የዓለም የገንዘብ ድርጅት ኢትዮጵያ እና ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገሮች ቢበዛ በ106 ያድጋሉ ብሏል እኛ ግን እንቢ ብለን ' አስራ አንድ ነው ! ' እንላለን ይሄ ተገቢ ነው ? "


ሌላ በእጅጉ ከሚታወሱበት ንግግራቸው መካከል ደግሞ መንግሥት ስለሚሳተፍባቸው የተለያዩ ሽያጮች ጉዳይ ነው።

" መንግሥት ለምንድነው ማዳበሪያን የሚሸጠው ብቻውን ? ፤ መንግሥት ለምንድነው ሆቴል ውስጥ ገብቶ የሚነግደው ? ፤ መንግሥት ለምንድነው ቱሪዝም ውስጥ ገብቶ የሚነግደው ?  ፤ መንግሥት ለምንድነው ሲሚንቶ የሚሸጠው ? ፤ አልፎ ፍራፍሬ ሽንኩርት የሚሸጠው ለምንድነው ? መንግሥት ሶሻሊት ኢኮኖሚ አይደለም የሚያራምደው ? "

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በምዕራብ ወለጋ የተወለዱ ሲሆን በትላልቅ ዩኒቨርሲቲዎች  የተማሩ የተዋጣላቸው የኢኮኖሚ ምሁር ነበሩ። የአዋሽ ባንክ እንዲሁም የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስን (ኦፌኮ) መስራችም ነበሩ።

#AtoBulchaDemeksa

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

“ ቀሪው አንድ ኩላሊቱ በዲያሌሲስ እንጅ ዝም ብሎ አይሰራም። ጫፍ ላይ ደርሶ ኢመርጀንሲ ዲያሌሲስ ነው ያለው ” - ኩላሊቱ እክል የገጠመው ታዳጊ ቤተሰብ

በተፈጥሮ አንድ ኩላሊት የሌለው፣ ቀሪ አንድ ኩላሊቱም “ የመጨረሻ ደረጃ ደርሷል ” የተባለው የ14 ዓመት ታዳጊ አገር ውጪ ካልታከመ በህይወት እንደማይቆይ ሀኪሞች በመግለጻቸው፣ ደጋግ ኢትዮጵያውያን ለህክምና ድጋፍ እንዲያደርጉ ቤተሰቦቹ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ተማጽነዋል።

የህፃን ጃቤዝ ሰለሞን አጎት በሰጡት ቃል፣ “ ከስድስት ወራት በፊት ነበር እግሩን አሞት ህክምና የወሰድነው። ቼክ ሲደረግ አንድ ኩላሊት በተፈጥሮ የለውም። አንደኛው ደግሞ የአንድ ዓመት ህፃን ኩላሊት ያህል ሆኗል ” ብለዋል።

“ ቢበዛ ለስድስት ወር ነበር ብቸኛ ኩላሊቱ አገልግሎት የሚሰጠው። አሁን እነቀነሰ ነው። ኢመርጀንሲ ዲያሌሲስ ጀመርንለት ” ሲሉም ያለበትን የከፋ ሁነት አስረድተዋል።

“ ጳውሎስ ሆስፒታል ህክምናውን ጨረስን። ከዛም ‘ውጪ አገር ሂዶ ይታከም። እዚህ አገር ህክምና የለምና ኩላሊት ፈልጉ’ ስለተባልን ሊሄድ ግድ ሆኖበታል ” ነው ያሉት።

“ ቀሪው አንድ ኩላሊት በዲያሌሲስ እንጅ ዝም ብሎ አይሰራም። ጫፍ ላይ ደርሶ ኢመርጀንሲ ዲያሌሲስ ነው ያለው” ያሉት ድጋፍ ጠያቂው፣ ሁሉም የቻለውን ያክል ድጋፍ እንዲያደርግ ተማጽነዋል።

ታዳጊ ጃቤዝ ህንድ አገር ሂዶ ታክሞ ህይወቱ እንዲተርፍ፣ “ ወደ 5 ሚሊዮን ብር ነው የተጠየቀው። ከነ ጉዞውና ህክምናው። ሦስት ወራት ነው የሚፈጀው ” ብለዋል።

ድጋፍ ለማድረግ 1000057164143 የአቶ ሰለሞን አለማየሁ ብሩ የንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር ነው። ደውሎ ዝርዝር ጉዳዮችን ለመጠየቅ 0911670476 ስልካቸው ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#NationalExam : የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ምዝገባቸውን ያላጠናቀቁ ተማሪዎች ከቀነ ገደቡ አስቀድመው እንዲያጠናቅቁ አገልግሎቱ አሳስቧል።

የፈተና ይዘትን በተመለከተ የሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና በአጠቃላይ ከ9-12ኛ ክፍሎች እንዲሁም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከ7-8ኛ ክፍሎች እንደሚሸፍን ተገልጿል።

ተማሪዎች በተማሩበት የክፍል ደረጀ የተማሪ መጽሐፍን መሠረት አድርገው እንዲዘጋጁ ተብሏል።

በሌላ በኩል ፥ ዘንድሮ በመደበኛው እና በግል 750,000 ተማሪዎች ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ  ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

እስካለፈው ሳምንት ባለው ዳታ ወደ 500 ሺህ  ተማሪዎች ተመዝግበል።

በመደበኛው ፕሮግራም 600 ሺህ ተማሪዎች ለመመዝገብ እቅድ የተያዘ ሲሆን እስካሁን ባለው 82 በመቶ የሚሆኑ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ አከናውነዋል ፤ በግል የሚፈተኑ 150 ሺህ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ ይጠበቃል።

ኢንተርኔት ማይሰራበት ቦታ ተማሪዎች በወረቀት ከተመዘገቡ በኋላ ኢንተርኔት የሚሠራበት አካባቢ በመሔድ መረጃቸውን ወደ ኦንላይን እየተጫነ ነው።

የመረጃ ባለቤቶች የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እንዲሁም ኤፍኤምሲ መሆናቸውን እንገልጸለን።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ፤ በሳቡሬ ቀበሌ የሚገኙ ሁለት ት/ቤቶች በመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ትምህርት ቤቶቹ ዑንጋይቱ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት እና ሳቡሬ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ናቸው።

የወረዳው ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት እንዳለው ፥ ዑንጋይቱ  የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ካሉት 12 የመማሪያ ክፍሎች ስድስቱ ፤ ሳቡሬ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ካሉት 16 ክፍሎች ስምንቱ መስኮታቸው ረግፏል ፤ ግድግዳቸው የመሰንጠቅና የመፍረስ አደጋ ደርሶበታል፣ ወለላቸውም ሰርጓል።

የዑንጋይቱ ት/ቤት ፤ በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት በመማሪያ ክፍሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰ በኋላ ተማሪዎችን በዛፍ ስር እና ድንኳን ውስጥ ሲያስተምር ነበር።

ማክሰኞ ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ/ም ጠዋት 2፡30 የመሬት መንቀጥቀጡ በባሰ ሁኔታ በመከሰቱ  ተማሪዎች እና መምህራን በድንጋጤ ት/ቤቱን ለቀው ወጥተዋል ተማሪዎች  ከዚያ በኋላ አልተመለሱም።

ትምህርት ቤቱ ወላጆቻቸውን ጠርቶ ካነጋገረ በኋላ ወልጆች " ልጆቻችን አብረውን ቢቆዩ ይሻለናል " ስላሉ የመማር ማስተማር ሂደቱ ተቋርጧል።

በወረዳው ከሚገኙት 6 ቀበሌዎች በአራቱ ላይ የመሬት መንቀጥቀጡ በተደጋጋሚ መከሰቱን ተከትሎ ነዋሪዎችን ወደተሻሉ አካባቢዎች የማስፈር ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል።

በሌላ በኩል ፥ በሃንሩካ ወረዳም በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት በትምህርት ቤት ላይ ጉዳት ደርሷል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እና የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#TPLF #Tigray

ለሁለት ቡድን የተከፈሉት የህወሓት አመራሮች አሸናፊ እና ተሸናፊ በሌለበት የፓለቲካ ችግሮቻቸውን ለመፍታት የተደረገው ተደጋጋሚ ድርድር አልተሳካም አለ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር።

ሁለቱ ቡድኖች ፓለቲካዊ ልዩነታቸው እንዲፈታ ከመጣር ይልቅ ፤ አንዱ ሌላውን ጠርጎ ለማጥፋት በሚል እሳቤ መጠመዳቸው ለድርድሩ አለማሳካት አንዱ እና ዋነኛ ምክንያት ነው ተብሏል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ዛሬ ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ምን አሉ ?

- የፓለቲካ ልዩነቱ ዋና መነሻ ከፍተኛ አመራሩ በመሆኑ ችግሩ በድርድር እንዲፈታ ጥረት የተደረገው በከፍተኛ አመራሩ ነው ብለዋል።

- የክልሉ የፀጥታ ሃይል ጨምሮ ሌሎች አካላት " ሁለቱ የህወሓት ቡድኖች ችግሮቻቸው ፓለቲካዊ ነው መፈታት ያለበትም በፓለቲካዊ መግባባት ነው " በሚል ለማደራደር በርካታ ጥረት ተደርጓል።

- በሁለቱ ቡድኖች መካከል የተፈጠረ የፓለቲካ ልዩነት አሁን የተፈጠረ ሳይሆን በወቅቱ ሳይፈታ ለዓመታት እየተከማቸ የመጣ መሆኑ ቡድኖቹ ለማቀራረብ አዳጋች አድርጎታል።

- በሁለቱን ቡድኖች ያለው ፓለቲካዊ መሳሳብ  አሁንም ፓለቲካዊ መፍትሄ ያሻዋል። የፀጥታ ሃይሉ  " የኛ ደጋፊ ነው " የሚል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚናገረው ተቀባይነት የለውም።

- የፀጥታ ሃይሉ የክልሉ እና የህዝቡ ፀጥታ እና ሰላም ከማስከበር ባለፈ አንዱን ቡድን በመደገፍ ሊቆም አይችልም። ህዝቡ ሁለቱ ቡድኖቹ ችግራቸው በጠረጴዛ ውይይት እንዲፈቱ ጫናውን ማሳደር ይጠበቅበታል።

- የፀጥታ ሃይሉ የአንዱ ደጋፊ ለማሰመሰል የሚደረግ ጥላሸት የመቀባት ተግባር ልክ አይደለም። ይህን መሰል በሬ ወለደ ውሸት የሚያራግቡ አካላትም ሆነ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እናሳስባቸዋለን።

መረጃውን የትግራይ የመገናኛ ብዙሃንን ጠቅሶ የላከው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ዮናታን_ቢቲ_ፈርኒቸር

በዓሉን አስመልክቶ የተደርገው ልዩ ቅናሽ ሳያመልጥዎ እነዚህን ውብ እቃዎች የግልዎ ያድርጉ።
🌐 የማህበራዊ ገጾቻችንን ይቀላለቀሉ
Telegram 👉 Telegram/yonatanbtfurniture
Facebook 👉 Facebook/yonatanbtfurniture
Instagram 👉 Instagram/yonatanbtfurniture
TikTok 👉 yonatanbtfurniture?is_from_webapp=1&sender_device=pc">TikTok/yonatanbtfurniture

📍አድራሻችን
1. ፒያሳ እሪ በከንቱ ቢቲ ታወር (ከኢቲዮ ሴራሚክ ዝቅ ብሎ)
2. ከዊንጌት አደባባይ አለፍ ብሎ ከአቢሲኒያ ባንክ ፊትለፊት
3. ከሲኤምሲ አደባባይ ወደ አያት መንገድ መሪ ሳይደርስ (ዘመን ባንክ አጠገብ)

☎️ +251957868686/ +251995272727/ +251993828282

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Earthquake : ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር።

ቤት ውስጥ ፣ አልጋ ላይ፣ ከቤት ውጭ የነበሩ ሰዎች ንዝረቱ ተሰምቷቸዋል።

ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ አሁንም በመቀጠሉ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳትዘናጉ።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#የአእላፋትዝማሬ #TheMelodyofMyriads

“ ኦርቶዶክሳዊያን ወጣቶች ልደትን በቤተ ክርስቲያን አሳልፉ ፤ በአዲስ አበባና በድሬዳዋ የምትገኙም በዝማሬው ላይ እንድትገኙ ” - የኢትዮጵያ ጃንደረባው ትውልድ (ኢጃት)

ታኅሳስ 29 ቀን 2017 ዓ/ም የሚከበረውን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያው ጃንደረባ ትውልድ ያዘጋጀው “ልደትን በባለ ልደቱ ቤት” የተሰኘውን የአእላፍ ዝማሬ በተመለከተ አዘጋጆቹ ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል መግለጫ ሰጥተዋል።

የዝማሬ ጉባዔው በአዲስ አበባ በድሬዳዋ እንደሚከናወን የገለጹት አዘጋጆች፣ “ ላለፉት ስምንት ወራት ለዚህ ታላቅ የዝማሬ ጉባዔ ከፍተኛ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል ” ብለዋል።

የጉባዔው ዋነኛ ዓላማ በአልባሌ ቦታ የሚውሉ ወገኖች በዓሉን በቤተክርስቲያን የመላክትን ዝማሬ በመዘመር እንዲያሳልፉ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተመልክቷል።

የኢትዮጵያው ጃንረባ ትውልድ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ቢንያም አሕመድ ፤  “ ኦርቶዶክሳዊያን ወጣቶች ልደትን በቤተ ክርስቲያን አሳልፉ ፤ በአዲስ አበባና በድሬዳዋ የምትገኙም በዝማሬው ላይ እንድትገኙ ” ብለዋል።

“ በሌሎች አካባቢዎች ላይ የተዘጋጁ ዝግጅቶች ካሉም በእዛው በመገኘት እንድታሳልፉ የኢትዮጵያ ጃንደረባው ትውልድ ጥሪ ያቀርባል ” ሲሉ አሳስበዋል።

በመርሃ ግብሩ በቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ ውስጥ ምንም አይነት ሽያጭ እንደማይከናውን አዘጋጆቹ አሳውቀዋል።

በሌላ በኩል፣ “ አእላፋት ዝማሬ ነጭ ልብስ ልበሱ ” ተብሏል በሚል ነጭ ልብስ በተጋነነ ዋጋ የሚቸበችቡ ሁነቱን የተከተሉ ነጋዴዎች ተስተውለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ነጭ ልብስ በውድ ወጋ እየተቸበቸበ ነው የሚል አስተያዬት እየተሰጠ ተስተውሏል፣ ለመርሀ ግብሩ ነጭ ልብስ ብቻ ለብሶ መምጣት ግዴታ ነው ? ሲል ለአዘጋጆቹ ጥያቄ አቅርቧል።

የኢትዮጵያው ጃንረባ ትውልድ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ብንያም አሕመድ በሰጡት ምላሽም፣ “ ነጭ ልብስ የሌለን ያለንን ልብስ ንጹህ አድርገን እንምጣ። ዓላማችን ልብሱ ለመቁረቢያ እንዲሆን ነው ” ብለዋል።

“ ኦርቶዶክሳዊ ኢኮኖሚ እንዲፈጠር ይፈለጋል ግልጽ ነው። በዚህ ምክንያት ወደ ስራ የሚገቡ፣ ሥራቸውን የሚያስፋፉ፣ የሚለወጡ ኦርቶዶክሳዊያን ቢኖሩ ይሄ የማኀበራችን አንዱ ዓላማ ነው ” ሲሉ ነው የተናገሩት።

“ ስለዚህ ይህን በቀና ዓይን ነው የምናየው ” ያሉት አቶ ብንያም፣ “ በእርግጥ በዚሁ ምክንያት ደግሞ አጋጣሚውን የሚጠቀሙ፣ Accidental Entrprenuers የምንላቸው መጥተው ባለሃብት ለመሆን የሚጥሩ ይኖራሉ ” ሲሉም አክለዋል።

“ ልደቱ የሰዎች የመላክት ዝማሬ ነው። ስለዚህ ይህንን በማሰብ ነጭ ለብሰን እንመጣለን ” ብለው፣ “ ዘወትር ወደ ቤተ ክርስቲያን ስንሄድ የምናደርገው ነው፣ የተለዬ ነገር የለውም ” ነው ያሉት።

ሆኖም ነጭ ልብስ የሌላቸው ያላቸውን ልብስ በአግባቡ ለብሰው በዝማሬ መርሀ ግብሩ መገኘታቸው እንዳይዘነጋ መልዕክት ተላልፏል። 

ዝማሬው ዘማሪያን እየዘመሩ ምዕመናን የሚቀበሉበት ሂደት ሳይሆን ልደቱን በሚያወሱ ዝማሬዎች ሁሉም በጋራ ምስጋና እንዲያቀርብ መሆኑ ተሰምሮበታል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የአስቸኳይ ጊዜ ግብረ-ኃይሎች ችግር ቢደርስ በአስቸኳይ ለመፍታት ከወዲሁ ሰፊ ዝግጅት ማድረግ  አለባቸው " - አታላይ አየለ (ፕሮፌሰር)

የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቱ መጠን ከፍ እያለ እየመጣ በመሆኑ ጉዳት እንዳይከሰት ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስ ስፔስ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አታላይ አየለ (ፕ/ር) አሳስበዋል።

ፕሮፌሰር ምን አሉ ?

" ትላንት ሌሊት 9:52 ሰዓት ላይ በአቦምሳ የተከሰተው በሬክተር ስኬል 5 ነጥብ 8 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ሰሞኑን በአፋር ክልል አካባቢዎች ሲከሰቱ ከነበሩ ከፍተኛው ነው።

በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት በአዲስ አበባ የተሰማው የመሬት ንዝረትም በመጠኑ ከፍ ያለ ነው።

የመሬት ንዝረቱ በሕንፃዎችም ሆነ በሌሎች ቤቶች ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ይሰማ ነበር።

ነገር ግን እስካሁን በንዝረቱ ምክንያት በአዲስ አበባ የተፈጠረውን ጉዳት ለማወቅ አይቻልም።

የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቱ መጠን ከፍ እያለ እየመጣ በመሆኑ ጉዳት እንዳይከሰት ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል።

መደረግ ካለባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች መካከል ፦

📣 ቁምሳጥን ላይ የሚቀመጡ ውድ እና ተሰባሪ እንዲሁም ተቀጣጣይ የሆኑ ዕቃዎችን መሬት ላይ ማስቀመጥ፣

📣 የመሬት ንዝረቱ ቅፅበት እስከሚያልፍ ማዕዘን አካባቢ መቆም እና ጠረጴዛ ስር እና ጭንቅላትን መከላከል በሚያስችሉ ቦታዎች መከለል ይጠቀሳሉ።

የአስቸኳይ ጊዜ ግብረ-ኃይሎችም ችግር ቢደርስ በአስቸኳይ ለመፍታት ከወዲሁ ሰፊ ዝግጅት ማድረግ  አለባቸው " ብለዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኤኤምኤን ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የመሬት መንቀጥቀጡ እየተከሰተ ባለበት አፋር ክልል አዋሽና አካባቢው ህዝቡ ለበርካታ ሳምንታት ቀን እና ለሊት ከአሁን አሁን ምን ሊፈጠር ነው እያለ በሰቀቀን እያሳለፈ ነው የሚገኘው።

ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፣ ሰዎች ቤታቸውን ጥለው ሄደዋል።

በርካቶች ቤት ውስጥ ማደር አቁመው ውጭ በረንዳ ላይ ለማደር ተገደዋል።

ከየትኛውም የሀገሪቱ አካባቢ በላይ ፤ የአፋር ነዋሪዎች ተደጋጋሚና ሊቆም ያልቻለው የመሬት መንቀጥቀጥ ተፅእኖ እያሳደረባቸው ይገኛል።

የትላንት ለሊቱን የመሬት መንቀጥቀጥ በተመለከተ ቃሉን የላከልን የቤተሰባችን አባል ፤ " በጣም አስፈሪ ነበር፣ ከተኛንበት ደንግጠን ተነሳንና መሬት ቁጭ አልን ፤ ያአላህ ምን ማድረግ እንዳለብን እንኳን ግራ ተጋባን ለረጅም ደቂቃዎች ሁላችንም በዝምታ ተውጠን ነበር " ሲል ገልጿል።

የትላንቱ ከሁሉም ይለይ እንደነበረ ጠቁሞ ፤ " ላለፉት በርካታ ሳምንታት እንዲህ ነው እያሳለፍን ያለነው አላህ መፍትሄውን ያምጣው " ብሏል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ደስደስበንጉስማልት
ከንጉስ ማልት ጋር ተጨማሪ ደስስስስስስስስስስታን ያጣጥሙ!

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ /channel/Negus_Malt
#ከአልኮልነፃ #ደስደስበንጉስ #የጣዕምልኬት_የደስታስሜት #ንጉስማልት

Читать полностью…
Subscribe to a channel