#ፋይዳ #ዲጂታል_መታወቂያ
በፋይዳ ይታወቁ ፣ በፋይዳ ይገልገሉ ፣ በፋይዳ ይዘምኑ!!!
ፋይዳ ለኢትዮዺያ!
Addis Ababa CRRSA - Civil Registration and Residency Service Agency Ethio telecom
#ፋይዳ #መታወቅ #DigitalID #fayda
የፖለቲከኛ ጃል በቴ ኡርጌሳ ግድያ ምርመራ ምን ደረሰ ?
🔴 “ መረጃ የማሰባብ ሥራችን እንደቀጠለ ነው ” - ኢሰመኮ
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ አመራር ፓለቲከኛ ጃል በቴ ኡርጌሳ በትውልድ ቦታቸው መቂ ከተማ በግፍ መገደላቸው የሚታወቅ ሲሆን፣ ባለቤቱም ሰሞኑን ልጆቻቸውን ይዘው ወደ አሜሪካ መሄዳቸው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በወቅቱ ስለግድያው ምርመራ ጀምሮ የነበረ ሲሆን፣ በኦሮሚያ ክልል በኩል በደረሰበት ጫና ምርመራውን ማቆሙን ለክልሉ በደብዳቤ ማሳወቁ በኋላ ደግሞ እንደገና ምርመራው እንደተጀመረ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሳል።
ምርመራው ቁሞ የነበረው፣ “ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ተሳትፎ መኖሩን የሚያመለክት ምስክሮችን ማሰባሰብ ከጀመረ ከሦስት ቀናት በኋላ የምርመራው ቡድን ምርመራውን እንዲያቋርጥ በመገደዱ ” መሆኑ በወቅቱ በኢሰመኮ ደብዳቤ መጠቀሱ ተነግሮ ነበር።
የፓለቲከኛውን ግድያ ከተፈጸመ ከስድስት ወራት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን፣ የግድያው ምክንያት እውቅና ግን የተነገረ ውጤት የለም።
ስለምርመራው አሁንስ ምን አዲስ ነገር አለ ?
እንዲያው የፓለቲከኛ ጃል በቴ ኡሬጌሳ ግድያን በተመለከተ የተጀመረው ምርመራ ከምን ደረሰ ? ያለው ሂደትስ ምንድን ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)ን ጠይቋል።
ኮሚሽኑም ምርመራው እንደቀጠለ ገልጿል።
“ ሥራችንን ስናጠናቅቅ ውጤቱን ይፋ የምናደርግ ይሆናል። አሁን ግን መረጃ የማሰባብ ሥራችን እንደቀጠለ ነው ” ብሏል።
ሂደቱን በተመለከተ “ ከክልሉ የሚመለከታቸው ባለስልጣናት ጋርም እየተነጋገርን ነው ” ሲል ገልጿል።
ስለግድያ የሚያደርገውን ምርመራ በተመለከተ ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ክልል አካላት ጋር መንገራገጭ ገጥሞት እንደነበር ይታወሳል፤ ለመሆኑ አሁን በምን ደረጃ ላይ ነው ? ችግሩ ተፈታ ወይስ አልተፈታም ? ሲልም ቲክቫህ ለኮሚሽኑ ጥያቄ አቅርቧል።
ኮሚሽኑም፣ “ ከክልሉ ጋር ያለው ግንኙኘት በተመለከተ አሁን መረጀ መስጠት አልችልም ” ከማለት ውጪ ስለግንኙነታቸው አሁናዊ ሁኔታ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥቧል።
አክሎ ደግሞ፣ “ ግን ሥራ እየሰራን ነው። አልተውንነውም ጉዳዩን ” ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ጃል በቴ ኡርጌሳ መቂ ላይ በግፍ በተገደሉበት ወቅት በሚዲያ ቀርቦ ግድያው ' ባልታወቁ ሰዎች መፈጸሙን ' ገልጾ መርምሬ ለህዝብ ውጤቱን ይፋ አደርጋለሁ ማለቱ ይታወሳል። ይህን ካለ ወራት ቢያልፉም እስካሁን ለህዝብ የተሰጠ ግልጽ እና ተጨባጭ መረጃም ሆነ ማብራሪያ የለም።
ሁነቱን እስከመጨረሻ በመከታተል መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ
#በባንካችን ሲቀበሉ እና ሲመነዝሩ ጭማሪዎን ያገኛሉ!
ከውጪ ሃገራት የሚላክልዎትን ገንዘብ በባንኩ የስዊፍት ኮድ (BERHETAA) እና ከብርሃን ጋር በሚሰሩ አለምአቀፍ የገንዘብ አስተላላፊዎች #ሪያ #ዳሃብሽል #ዌስተርን_ዩኒየን #መኒግራም #ትራንስ_ፋስትና #ወርልድ_ረሚት በኩል በቀላሉ ይቀበሉ!
#moneytransfer #Stressfreebanking #berhanbank #bank #finance #bankinethiopia
ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ!
➡️ Facebook
➡️ Telegram
➡️ Instagram
➡️ Twitter
➡️ LinkedIn
➡️ YouTube
#ትግራይ
" የፌደራል መንግስት ውስጣዊ ችግራችን በውይይት መፍታት ካልቻልን ትግራይን የማስተዳደር ስልጣኑን ብልፅግና በብቸኝነት እንደሚይዘው በግልፅ ነግሮናል " - አቶ ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ወደ ሁለት በተከፈሉ የህወሓት አመራሮች እየታመሰ የሚገኘው የክልሉ የፓለቲካ ሁኔታ ከመሻሻል ይልቅ ተባብሶ መቀጠሉ ተናግረዋል።
" በምንገኝበት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ የፓለቲካ የአሰላለፍ ለውጥ እየተፈጠረ ነው ፤ የትግራይ ሁኔታም ከሚታየው ለውጥ ተያይዞ ያሉት ዕድሎች እና ፈተናዎች መተንተን ያስፈልጋል " ብለዋል።
" የትግራይ ፓለቲካ ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ መገንዘብ ትቶ በአመራሮቹ እየታመሰ ነው " ሲሉም ገልጸዋል።
" የፌደራል መንግስት ውስጣዊ ችግራችንን እንድንፈታ እየገለፀ ነው ካልተቻለ ግን የማስተዳደር ስልጣኑን ብልፅግና በብቸኝነት እንደሚይዘው ግልፅ አድርጓል " ሲሉም አክለዋል።
በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው መከፋፈል ተባብሶ መቀጠሉን የገለጹት አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ በቅርቡ በአፍሪካ ህብረት ለሚካሄደው በፕሪቶሪያ የሰላም አፈፃፀም የሚመለከት የግምገማ መድረክ ከወዲሁ " እኔ ነው መሳተፍ ያለብኝ " ወደ ሚል መሳሳብ ተገብቷል ሲሉ በምሬት ተናግረዋል።
" የህወሓት አመራር ሉአላዊ የትግራይ ግዛት ከፌደራል የሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጭ ያሉ ታጣቂዎች ነጻ ሆኖ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው የመመለስ ዋና አጀንዳ ዘንግቶ የጊዚያዊ አስተዳደሩ የእለት ተእለት ስራዎች በማድናቀፍ ተጠምዷል " ሲሉም ከሰዋል።
" ከፕሬዜዳንት ስልጣን ወርደዋል ፤ ወደ ውጭ አገር ሊወጡ እያመቻቹ ነው ፤ ውጭ ሀገር ወጥተው እንዲቀሩ መንግሥት እያመቻቸላቸው ነው " ተብሎ ሲወራባቸው ስለ መሰንበቱ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው ረዳ " ለስራ በምወጣበት ጊዜ ከሁለቱ ምክትሎች አንዱ መወከል የተለመደ አሰራር ነው መወከሌም እቀጥላሎህ ፤ ' ከሀገር ሊወጣ ነው ' ተብሎ የተነዛው ወሬም ከሃቅ የራቀ መሰረተ ቢስ የውሸት ወሬ ነው " ሲሉ መልሰዋል።
' ለስልጣን መቆራቆስ ትተን በጦርነት እና ጦርነት ወለድ ችግሮች የተጎሳቆለው ህዝባችን መካስ ማስቀደም አለብን " ያሉት አቶ ጌታቸው ረዳ በእሳቸው የሚመሩ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ከሚመራው የህወሓት ከፍተኛ አመራር ጋር የሃይማኖት አባቶች በጀመሩት የእርቅ ጥረት ችግሮቻቸው ለመፍታት ቁርጠኛ እንደሆኑ አረጋግጠዋል።
#TikvahEthiopiaMekelle
@tikvahethiopia
#ነጋዴዎች #ደረሰኝ #መርካቶ
" ደረሰኝ መቆረጥ አለበት በዚህ ላይ ምንም አይነት ድርድር የለውም " - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
ከሰሞኑን በአዲስ አበባ በተለይ በግዙፉ የገበያ ማዕከል ' መርካቶ ' በንግድ ስርዓቱ ጋር በተያያዘ ቅሬታ አለን ያሉ ነጋዴዎች ሱቅ የመዝጋትና ስራ የማቆም እንቅስቃሴ ማድረጋቸው ይታወሳል።
ሰሞነኛውን የመርካቶ ገበያ ሁኔታ በተመለከተም ነጋዴዎቹ ከከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተቀምጠው ነበር።
በውይይቱ በነጋዴዎቹ በኩል በርካታ ጥያቄዎችና ሃሳቦች ተነስተው ነበር። ለተነሱት ጥያቄዎች የመንግሥት አካላት ምላሽ ሰጥተዋል።
ነጋዴዎች ሃሳባቸው ፣ ጥያቄያቸው፣ ቅሬታቸው ምንድነው ?
➡️ ደረሰኝ መቁረጥ ፣ ግብር መክፈል ለሀገር ወሳኝ ፤ ለራስም ይጠቅማል። ግን አከፋፈሉ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው።
➡️ እኛ ስንገበያይ ደረሰኝ እናገኛለን ወይ ? አንዳንድ ምርት የሚነሳው ከገበሬ ነው። ከገበሬ ነጋዴ ይሰበስባል ይከፍላል፣ ተረካቢው ይረከባል ይከፍላል፣ ተጭኖ ይመጣል እኛ እንረከባለን ይሄ ሁሉ ይከፍላል ብዙ ነገር ነው ያለው። የቆረጠው ይቆርጥልናል የሌለውን ንግድ ፍቃድ እናያይዛለን። እንዲህ ስንሰራ ነው የቆየነው።
➡️ ሁሉም እየመጣ ባለድርሻ ነኝ ይላል። መርካቶ እንደምንታመስ ያውቃል ሌባው ይገባና " ሄደህ 100 ሺህ ብር ከምትቀጣ ለኔ ይሄን ስጠኝ " ይላል።
➡️ እቃው በደላላ ነው የሚመጣው ፤ ድሮ አስመጪ በእያንዳንዱ ሱቅ ሄዶ እቃ ይበትን ነበር አሁን ግን አስመጪው ለደላላ፣ ለቤተሰብ ፣ ለዘመዱ ፣ ለጎረቤት፣ ለጓደኛ ነው የሚሰጠው። እቃው ይመጣና በተለያየ መጋዘን ይቅመጣል ከዛ በስልክ ነው ልውውጥ የሚደረገው ነጋዴው ደላላውን ' ደረሰኝ ስጠኝ ' ካለው ነገ እቃ አይሰጥም።
➡️ ቁጥጥር እየተባሉ የሚመደቡ ሰዎች ባጅ የላቸው፣ ምናቸውም አይታውቅ፣ ሱቅ የሚገቡት እንደ ሌባ 3 እና 2 እየሆኑ ነው ስለዚህ ህጋዊ ይሁኑ ህገወጥ ምናቸው ይለያል ?
➡️ ባልተማከለ ሲስተም ውስጥ ነው ያለነው። ደረሰኝ አልቆረጣችሁም በሚል መቶ ብር አትርፈን 100 ሺህ ብር ነው የምንጠየቀው።
➡️ እስቲ ኢንዱስትሪውን ተቆጣጠሩ ደረሰኝ ቼክ ይደረግ የሚወጣው አንደርኢንቮይስ ከሆነ በምን አግባብ ነው ነጋዴው የሚጠየቀው ?
➡️ " ደረሰኝ ቁረጡ ደረሰኝ ቁረጡ " ሲባል ሌላ ነገር ነው የሚመስለው ደረሰኝ ይዞት የሚመጣው ገንዘብ ነው። መጀመሪያ የንግድ ስርዓቱ መስተካከል አለበት።
➡️ ለ100 ሺህ ብር ቅጣት በዚህ ፍጥነት ከተሰራ ነጋዴውን ለማገዝ በገንዘብ ሚኒስቴር የሚሰጠቱን ዕድሎች ተፈጻሚ ለማድረግ ለምን አልተቻለም ?
➡️ አሰራሩ እኮ ብዙ ነው። አልታየም። እንደ ከተማ አንድም አስመጪ የለም። አስመጪዎቹ ' መርካቶ መጥተን አንሸጥም ጅግጅጋ መጥታችሁ ግዙ ' ይሉናል። በደረሰኝ ስንት ስቃይ ነው ያለው። እዛ ተኪዶ ነው ሚገዛው ? እሺ እዚህ ስናመጣ ገቢዎች ላይ ብዙ ነገር አለ ፤ ደረሠኝ ይጥላሉ፣ ' አንቀበልም ' ይላሉ የት እንሂድ ?
➡️ አሰራሩ ላይ ትልቅ ችግር አለ።
➡️ አምራቾች፣ አከፋፋዮች፣ አስመጪዎች ደረሰኝ ይሰጣሉ ወይ ? የሚለው ትልቁ ጥያቄ ነው።
ለነጋዴዎች ጥያቄ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ምን መለሱ ?
🔴 የገቢዎች የቁጥጥር ሰራተኞችን በተመለከተ መታወቂያ አላቸው፣ 3 እና 4 ሆነው ነው የሚገቡት። መታወቂያ የሌለው ካለ ህገወጥ አጭበርባሪ ነው ተከላከሉት።
🔴 " የገቢዎች ሰራተኛ ነን " ብለው ሲያጭበረብሩ የተያዙ ሰዎች አሉ።
🔴 ለገቢዎች ሰራተኞች መታወቂያ ተሰጥቷል። መታወቂያ ማሳየት አለባቸው። እናተም ጠይቋቸው።
🔴 ደረሰን ላለመቁረጥ የሚሰጡትን ምክንያቶች በጋር እየተነጋገርን እንፈታለን እንጂ ደረሰኝ መቁረጥ እንዲቆምላችሁ የምትጠይቁትን ጥያቄ መንግስት መመለስ አይችልም። ይሄን በግልጽ እየወቁት።
🔴 በገቢዎች ውስጥ ያሉ ችግሮች ይታወቃሉ መፈታት አለባቸው። ከብልሹ አሰራር፣ ከሌብነት ጋር በተያያዘ የተነሱ ችግሮች ይታረማሉ።
🔴 ቫትን በተመለከተ በአዲሱ አሰራር 7 ሺህ ብር ነው የቀን ግምቱ የተቀመጠው። ቀደም ሲል ቫት የነበረ ወደ ታች ሊወርድ አይችልም። በቀን 7 ሺህ ብር የሚሸጥ ሰው ምን ያክል ነው የሚለውን እናተው ታውቃላችሁ። ቅድሚያ እየተሰጠ ያለው ቫት ውስጥ መግባት እያለበት ቫት ውስጥ ያልገባው ነጋዴ በተለይ መርካቶ እሱ ባለመግባቱ በሚሸጠው እቃ ላይ የዋጋ ልዩነት እየመጣ ስለሆነ ቫት ውስጥ መግባት ያለበትን ቫት ውስጥ እያስገባን ነው።
🔴 ቫት ውስጥ የነበረ ነጋዴ ልወርድ ይገባል ብሎ ተጨባጭ ማስረጃ ካቀረበ ይታያል። አሁን ባለው የዋጋ ምረት እታች ያለው ወደላይ ይወጣል እንጂ እላይ የነበረው ወደ ታች አይወርድም።
🔴 የቁጥጥር ስርዓቱ እየጠበቀ ነው የሚሄደው።
🔴 እኛ ስለትላንቱ አለነሳንም አሁን ግን መርካቶ የሚደርገው ግብይት በደረሰኝ እና በደረሰኝ ብቻ መሆን አለበት። ይህን የሚያደርገውን ነጋዴ እንደግፋለን።
🔴 ነጋዴው በህጋዊ መንገድ ይጠቀም አልን እንጂ ነጋዴውን የሚያስቀይም ፣ የሚያሳድድ እርምጃ ለመውሰድ የሚፈልግ አካል የለም።
🔴 መርካቶ የሚደረገው እንቅስቃሴ በክልል ጥያቄ ያስነሳል። መረካቶ ደረሰኝ ስለማይቆረጥ የንግዱ ማህበረሰብ ክልል ሄዶ ሲነግድ ደረሰኝ አቅርቡ ሲባል " ያለ ደረሰኝ ነው የገዛነው እዛ ደረሰኝ አልተቆረጠም " የሚሉ አሉ።
🔴 የዚህ አመት እቅዳችን ግዙፍ የሆነ ገቢ ለመሰብሰብ አቅደናል። ይህን የምናደርገው የታክስ ቤዛችንን በማስፋት፣ ኢመደበኛውን ንግድ ወደ መደበኛ በመቀየር ነው።
🔴 ኢ-መደበኛ እናሳድዳለን አላልንም ግን ወደ መደበኛ ይግባ እያልን ነው።
🔴 ብዙዎቻችሁ (ነጋዴዎች) ያነሳችሁት ጥያቄ ደረሰኝ እንዳይቆረጥ የሚጠይቅ ዝንባሌ አለው። " ደረሰኝ አያስፈልግም " አትሉም ግን ጅምላውን፣ አከፋፋዩን ፣ አምራቹን ቅድሚያ ስጡ ነው የምትሉት። ጅምላውም ላይ፣ አከፋፋዩም ላይ ፣ አምራቹም ላይ እንሰራለን ቸርቻሪም ላይ እንደዛው ይሰራል። ሁሉም ደረሰኝ መቁረጥ አለበት።
🔴 ደረሰኝ ለመቁረጥ የማይስችል ሁኔታ ካለ ማስረዳት ነው እንጂ " ደረሰኝ አንቆርጥ " የሚል እሳቤ ተቀባይነት የለውም።
🔴 በደረሰኝ መቆረጥ አለበት ምንም አይነት ድርድር የለውም በዚህ ጉዳይ። እኛ ኢመደበኛውን ንግድ ወደ መደበኛ እናስገባለን።
🔴 አቤቱታ ካላችሁ በማንኛውም ጊዜ አቅርቡ። ገቢዎች አካባቢ ያለውን ነገርም እንፈትሻለን።
#AddisAbaba #Merkato
@tikvahethiopia
#ሴጅ_ማሰልጠኛ
የግራፊክ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኢዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና በፒያሣ እና መገናኛ ካምፓስ ሰኞ ህዳር 23/2017 ዓ.ም ይጀምራል።
👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 Advanced Graphics + Video Editing + Motion Graphics + Digital Marketing በአንድ ላይ
👉 ከ50 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት
ስልክ ፦ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
Tiktok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
Linkedin: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#ትግራይ
" ' ተቀምተናል ' የሚሉትን ስልጣን ለማስመለስ ስም ከማጥፋት ባለፈ እስከ ፕሬዜዳንት መቀየር ያለመ አደገኛ እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው " - ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ
ዛሬ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ የፀጥታ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተው ነበር።
በዚህም ወቅት አቶ ጌታቸው ፥ " የህዝብ ጥቅም ማእከል አድርጎ በሚንቀሳቀስ የፓለቲካ ፓርቲ ውስጥ ለግሉ ጥቅም ብቻ የሚያስብ አመራር ከተፈጠረ ረጅም ጊዜ ሆኗል " ብለዋል።
" ' ስልጣን ለኛ ነው የሚገባው ' የሚሉ የህዝብ አጀንዳ በማፈን ፍላጎታቸው ለማሳካት የግጭትና የግርግር መልእክቶች በማስተላለፍ ላይ ይገኛሉ " ሲሉም ገልጸዋል።
እነዚህን አካላት በስም አልጠቀሷቸውም።
ፕሬዜዳንቱ በስም ያልገለፁዋቸው አካላት " ተቀምተናል " የሚሉት ስልጣን ለማስመለስ ስም ከማጥፋት ባለፈ እስከ ፕሬዜዳንት መቀየር ያለመ አደገኛ እንቅስቃሴ እያካሄዱ እንደሆነ አመላክተዋል።
" ትኩረታችን የትግራይ ህዝብ መሆን ይገባ ነበር " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " ለወንበር ሲባል የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራዎች የማደናቅፍ ስራዎች ተባብሰው ቀጥለዋል " ሲሉ ገልፀዋል።
" ' ሰራዊት ከኛ ጎን ነው ' በማለት የግለሰቦችን ስልጣን ለማርካት ታስቦ የፀጥታ ሃይል ለመከፋፈል አልሞ እየተሰራ ነው " ሲሉም አክለዋል።
አቶ ጌታቸው ፥ " በትግራይ ሁሉንም ነገር በብቸኝነት ተቆጣጥሮ የቆየ ሃይል አሁንም የፀጥታ ሃይል ፤ ሚድያ ተቆጣጥሮ በለመደው መንገድ በመሄድ የግል ጥቅሙን ለማረጋገጥ ጠላት ከሚለው እየተደራደረ ይገኛል " ብለዋብ።
" ጠላት " ያሉትን ሃይል በስም አልገለፁም።
የም/ ቤት አባላት በማንሳት የአስተዳዳሪዎች ስልጣን እንዲለወጥ መስራት መፈንቅለ መንግስት ነው ያሉት አቶ ጌታቸው " መንግስትን ለማፍረስ የሚደረጉ መድረኮች በመንግስት በጀት ነው የሚካሄዱት " ሲሉ ተግባሩን ኮንነዋል።
" ' የፀጥታ ሃይል ከኛ ነው ' የሚለው አነጋገር የፀጥታ ሃይሉን በመጠቀም ' ከስልጣን እናስወግዳችኋለን ' የሚል መልእክት ለማስተላለፍ ተፈልጎ የሚሰራ ነው " ሲሉም ተናግረዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
ፎቶ፦ DW
@tikvahethiopia
#ማይናማር🚨
🔴 “ አምልጠን እንኳ ብንወጣ ያመለጠውን ኢትዮጵያዊ ለሚይዙ 500 ዶላር ይከፈላቸዋል። ” -ኢትዮጵያዊያን በማይናማር
🔵 “ ደብድበውት ራሱን አያውቅም ወጣቶች ተሸክመው ሆስፒታል ሲወስዱት የውጪ ዜጋ አናክምም ብለው መለሱት ” - በእንባ የታጀቡ እናት
ሰርተን እንለወጣለን፣ ቤተሰብም እንለውጣለን ብለው ከአገር የወጡ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በማይናማር በስቃይ ውስጥ መሆናቸው ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ መገለጻችን አይዘነጋም።
ኢትዮጵያዊያኑ ከሀገር ሲወጡ የተነገራቸውና አሁን ያሉበት ሁኔታ የማይገናኝ ነው።
ጉልበታቸው እየተበዘበዘ ከሆኑም ባሻገር የሚፈጸምባቸው ድብደባና የአካል ጉዳት አሰቃቂ መሆኑን የገፈቱ ቀማሾች ከዚህ ቀደም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው ነበር።
የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ፣ ኢትዮጵያዊያኑን ወደ አገራቸው ለመመለስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተየጋገረ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሳል።
የኢትዮጵያዊያኖቹ ጉዳይ አሁንስ ከምን ደረሰ ?
በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ፣ ያገቷቸው አካላት ካሉበት አገር መንግስት ጋር ያላቸውን ግንኙት…በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ የጠየቃቸው በማይናማር የሚገኙት ኢትዮጵያዊያን፣ በጣም በከፋ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን በሀዘን ስሜት ገልጸው፣ የመንግስትን እርዳታ ጠይቀዋል።
በዝርዝር ምን አሉ ?
“ የኢትዮጵያ መንግስት ሙሉ ኃላፊነት ወስዶ ከረዳን ብቻ ነው መውጣት የሚቻለው። የሌሎች አገራት እንዳደረጉት። ነገር ግን የተባልነው ነገር የለም እስካሁን በስቃይ ላይ ነን።
ያለንበት አገር ብዙም የተጠናከረ መንግስት የለውም። እንደሚታወቀው ወታደራዊ መንግስት ነውና። መንግስት ከመንግስት ጋር ተነጋግሮ ሊያስወጣን ከቻለ ብቻ ነው እንጂ።
እንወጣለን በሚል ተስፋ እያደረግን፣ እያለምን ነው እንጂ እስካሁን ምንም የተባልነው ነገር የለም። የኢትዮጵያ መንግስት ጫና ካላደረገ በስተቀር የያዙን ሽፍታዎችና የአገሪቱ መንግስት በጥቅም የተሳሰሩ ናቸውና መውጣት ይከብዳል።
አምልጠን እንኳ ብንወጣ ያመለጠውን ኢትዮጵያዊ ለሚይዙ 500 ዶላር ይከፈላቸዋል። ስለዚህ ተሳክቶልን ብናመልጥ እንኳ የአካባቢው ማህበረሰብ ይዞ አሳልፎ ይሰጠናል።
ሽፍቶቹ በቁጥር ብዙ ባይሆኑም መመሪያ የተሰጣቸው ናቸው። በዬቦታው ተሰራጭተው ነው የሚጠብቁት። ከእገታ ቦታው ወጣ ብለው በእስናይፐር የሚጠብቀ አሉ። በቁጥር ትንሽ ቢሆኑም የተጠናከረ ጥበቃ ላይ ያሉ ሽፍቶች ናቸው የያዙን።
የሚያሰሩን ቻይያዎች ናቸው። ያለነው ማይናማር ነው። ዜጎቹ ግን የቻይና ናቸው። ከአገሪቱ መንግስት ጋር በጥቅም የተሳሰሩ ናቸው። ለዚሁ መንግስት ግብር ይከፍላሁና ነገሩን ከባድ ያደረገው ከመንግስት ጋር የተያያዙ መሆናቸው ነው።
ወታደራዊ መንግስት ነው ያለው። ስለዚህ ከእኛ ከሚሰበሰው ገቢ ውስጥ ለመንግስት ይከፈላል። ለዛም ነው ሽፍቶቹ ደኀንነታቸው ተጠብቆ ሙሉ ድፍረት አግኝተው የሚሰሩት። የሕግ ከለላም አላቸው ነገሩ የተሳሰረ ነው። አጠቃላይ የአገራቱ መንግስት ሁኔታውን ሁሉ ያውቃል።
በስልክ እየደወልን ቤተሰብን ከመጠየቅ በስተቀር የኢትዮጵያ መንግስት ስለመውጣታችን እንዲህ ነው ያለን የሰማነው ነገር የለም። እባካችሁ በሕይወት ድረሱልን ” ሲሉ ተማጽነዋል።
ልጆቻቸው፣ የትዳር አጋሮቻቸው፣ እህትና ወንድሞቻቸው በማይናማር በከፋ ሁኔታ የሚገኙ ቤተሰቦች በበኩላቸው፣ ለወራት በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እንደሆኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ልጃቸው የታገተባቸው አንዲት እናት እያለቀሱ በሰጡን ቃል፣ “ እኛም በጭንቀት ተሰቃዬን እንዴት አድርጌ እንደምገልጽ አላውቅም ” ሲሉ ጭንቀታቸውን አጋርተዋል።
እኝሁ እናት አክለው ፦
“ ደብድበውት ራሱን አያውቅም ወጣቶች ተሸክመው ሆስፒታል ቢወስዱት 'የውጪ አገር ዜጋ አናክምም ' ብለው መለሱት።
እንደ ዜጋ መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባት ሲገባው ‘የራሳቸው ጉዳይ’ የተባለ ነው የሚመስለው። በጣም ያሳዝናል ለመናገር በጣም ነው የሚቸግረኝ።
እንደ ወላድ ይጨንቃል። ተቸግረን አሳድገን እንዲህ ሲሆኑ። እንደ ሀገር እኛ ከኡጋንዳ ሀገር በታች ነው እንዴ የኛ ሀገር መንግስት ! እንዲያው ጆሮ ዳባ ብለውን ነው እንጂ።
ስቲል ይሄዳሉ ልጆች ወደ ውጪ አገር። አምባሳደሩን ገብተን የውጪ ጉዳይ ቆንጽላ ጽህፈት ቤት ተሰባስበን አነጋግረን ነበር ከ15 ቀናት በፊት።
ልጆቻችን አካለ ጎደሎ እየሆኑ፣ በሥነ ልቦና እየተሰቃዩ፣ እየተጎዱ ነው ዳግም ሌላ ወጣት እንዳይሄድ ስንል ‘የመንቀሳቀስ መብትን መንፈግ ነው የሚሆነው እኛ እንዴት ብለን እናሳግዳለን ?’ ነው ያሉን ” ሲሉ ገልጸዋል።
ገና የ8 ወር ልጅ ይዘው የቀሩ የትዳር አጋራቸው በማይናማር እንደታገተባቸው የገለጹ ሌላኛዋ እናት በበኩላቸው፣ ባለቤታቸው በከፋ ሁኔታ እንደሚገኝ፣ ልጅ አዝለው ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ድረስ ቢሄዱም አጥጋቢ ምላሽ እንዳላገኙ ተናግረዋል።
በዝርዝር ምን አሉ ?
“ ባለቤቴ ማይናማር በስቃይ ውሰጥ ነው። ከሄደ 5 ወራት አስቆጥሯል። ‘የሥራ እድል አለ’ ተብሎ በደላሎች አማካኝነት ነበር ወደ ታይላንድ የሄደው። በሙያው ሐኪም ነው። ከሄደ በኋላ ግን ታይላንድ አይደለም የቀረው ወደ ማይናማር ነው የወሰዱት።
ያለበት ሁኔታ በጣም ከባድ ነው። የጨለማ ክፍል የሚባል አለ፤ ድብደባ አለ። በነገረኝ መሠረት አሰቃቂ ሁኔታ ነው። እኔም መፍትሄ ፍለጋ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ልጅ አዝዬ ጭምር ብዙ ጊዜ ተመላልሻለሁ።
የሚሰጠኝ ምላሽ በራሳቸው ፍላጎት እንደሄዱ፣ በሕገወጥ መንገድ እንደሄዱ ነው። ከሦስት ቀናት በፊትም ሂጀ ነበርና ከታች ያሉት የቀረበውን ቅሬታ ካሳወቁ ከ10 ወራት በላይ እንዳስቆጠረ፣ ግን መፍትሄ እንዳልተገኘለት ነው የነገሩኝ።
‘ ከላይ ያሉት አካላት ናቸው መስራት ያለባቸው ’ ነው ያሉኝ። ጥሩ መልስ የሰጠን የኤምባሲ አካል ግን አላገኘንም። ቤተሰቡ በጭንቀት ውስጥ ነው ያለው። ባለቤቴ ከሄደ በኋላ ኑሮው ከብዶኛል።
ስለእርሱ መጨነቁ፣ የኑሮ ውድነቱ ተደራረቡብኝ። የባለቤቴ ደመወዝ ተቋርጧል። አዲስ አበባ ከተማ ላይ ብቻዬን ልጅ እያሳደኩ ስቃይ ላይ ነኝ።
የኢትዮጵያ መንግስት በደንብ ትኩረት ሰጥቶ ቢሰራበት የማይናማር መንግስት ሊለቃቸው እንደሚችል ባለቤቴ ነገሮኛል። ባለቤቴ ጋር የነበሩ የህንድ አገር ዜጎች ወጥተዋል። መንግስት መፍትሄ ይስጠን ” ሲሉ ተማጽነዋል።
ማይናማር ውስጥ የሚገኙ የታጋች ኢትዮጵያዊያኑ ወላጅች ያቋቋሙት ኮሚቴ በበኩሉ፣ መፍትሄ እየጠየቀ መሆኑን የገለጸ ሲሆን፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ምን እየሰራ እንሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሰጠው ምላሽ ጋር በቀጣይ ይቀርባል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia
ለማይቋረጥ የኢንተርኔት ጌም ወሳኙ የማይቋረጥ ኢንተርኔት ነው ፤ አሁኑኑ የሳፋሪኮምን የ4G ዋይ ፋይ ጥቅል ከM-PESA ሳፋሪኮም mini app በመግዛት በጌማችን እንፍታታ!
#MPESASafaricom #FurtherAheadTogether
" አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል የተሰጠ ውክልና የለም " - ሚኒስቴሩ
" ካናዳን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ለሥራ ዜጎችን እንልካለን፡፡ ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ፍቃድ አግኝተናል " በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ህገ-ወጥ ማስታወቂያዎች እየተላለፉ እንደሆነ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አሳውቋል።
እየተለለፉ ባሉት ህገ-ወጥ ማስታወቂያዎች ህብረተሰቡ ላላስፈላጊ ወጪና እንግልት እየተዳረገ መሆኑን አመልክቷል።
በመሆኑ " መሰል የማጭበርበር ተግባር እየፈፀሙ የሚገኙ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራሁ ነው " ብሏል።
በውጭ ሀገር ስራ ስምሪቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል የሰጠው ውክልና የሌለ መሆኑን አሳውቋል።
ሚኒስቴሩ ፥ " ዜጎች በስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ካላስፈላጊ ወጪ፣ እንግልትና ሌሎች አስከፊ አደጋዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ በጥብቅ እናሳስባለን " ብሏል።
የሁለትየሽ ስምምነት የተፈረመባቸው መዳረሻ ሀገራት በ lmis.gov.et ላይ መመልከት እንደሚቻል ገልጿል።
@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia
በነፋሻማ ተፈጥሮ ተከባችሁ ፊልም ለመኮምኮም ዝግጁ ናችሁ? ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የAddis Open Air Cinemaን ስፖንሰር አድርጎ ይዞላችሁ መጥቷል! እንደ ባንድ ሙዚቃ እና ካሪኦኬ ያሉ ሌሎች መዝናኛዎችም በሽ ናቸው! ህዳር 15 በጊዮን ግሮቭ ጋርደን ዎክ አይቀርም!
ቲኬቱን በM-PESA Safaricom app ላይ ያገኙታል
#MPESASafaricom #1Wedefit #Furtheraheadtogether
🔈 #የመምህራንድምጽ
#Update
“ የተደበደቡ ስድስት መምህራን ህክምና ተከልክለዋል። ከታሰሩት አንድም የተፈታ የለም ” - የዞኑ መምህራን ማኀበር
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን በሳርማሌ ወረዳ የሚገኙ ከ60 በላይ መምህራን ከደመወዛቸው ያለፈቃዳቸው የተቆረጠ ገንዘብ እንዲመለስላቸው በመጠየቃቸው መታሰራቸውን የዞኑ መምህራን ማኀበር ትላንት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሳል።
ዛሬ ደግሞ፣ መምህራኑ ከእስር እንዳልተፈቱ፣ እየታሰሩ በነበረበት ወቅት ድብደባ የተፈጸመባቸው መምህራን እንዳይታከሙ መከልከላቸውን ማኀበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።
የማኀበሩ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ጭበጮ ለበሰጡት ቃል፣ “ በሚያስሩበት ወቅት የተደበደቡ ስድስት መምህራን ህክምና ተከልክለዋል። ከታሰሩት ውስጥ አንድም የተፈታ የለም ” ብለዋል።
ተጎጂዎቹን እንዲያዩ የማኀበሩን ሰዎች ወደ እስራት ቦታው ልኮ እንደነበር የገለጹት አቶ ተስፋዬ፣ “ አሁን ባለው ሂደት ብዙዎቹ እንደተገጎዱ ናቸው። እንዲያውም የአንዱ በጆሮው ሁሉ መግል እየወጣ ነው ህክምና ተከልክለዋል ” ብለው፣ ለማሳከም ቢጠይቁም እንደከላከሏቸው ተናግረዋል።
መምህራኑ ከታሰሩ ስንት ቀናት አስቆጠሩ ? የተቆረጠባቸው ምን ያህል ገንዘብ ነው ? ለሚለው ቲክቫህ ጥያቄ የሰጡት ምላሽ ደግሞ፣ “ ረቡዕ ነው እስራቱ የተጀመረው ፤ ዛሬ አራተኛ ቀናቸው ነው። 25 በመቶ ነው የተቆረጠባቸው ” የሚል ነው።
የዞኑ ትምህርት መምሪያ፣ መምህራኑ ደመወዛቸው የተቆረጠው በፈቃዳቸው እንደሆነ፣ የታሰሩትም ገንዘብ እንዲመለስላቸው በመጠየቃቸው ሳይሆን፣ “ ድንጋይ ወርውረው ሌሎችን በመበጥበጣቸው ” መሆኑን ነው የገለጸው፣ እውነትም እንደዛ ነው የሆነው ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።
ምን አሉ?
“ ይሄ ትልቅ ውሸት ነው። ቢነጋገሩ፣ ተስማምተው ቢሆን ኖሮ መምህራኑ ቅሬታ አያቀርቡም ነበር።
መምህራኑ ለትምህርት መምሪያው በፅሑፍ ያቀረቡት ‘አልተስማማንበትም፤ ባልተስማማንበት ጉዳይ የተቆረጠብን ገንዘብ ይመለስልን’ የሚል ነው።
‘ያልተስማማንበት ስለሆነ ገንዘቡ ይመለስ’ ብሎ እያንዳንዱ መምህር ትምህርት መምሪያውን ጠይቋል። መምሪያው ይሄን ሁሉ ክዶ ነው ለመሸፈን የሚሞክረው። ባወጣው መግለጫም እርምት ቢደረግ መልካም ነው።
ትምህርት መምሪያው መምህራኑ ‘ድንጋይ ወርውረዋል’ ማለቱ ውሸት ነው። አንድም የወረወረ የለም። አንድ መምህር ለስህተት ድንጋይ የሚባል ነገር አላነሳም። ይህን ወርዶ ማረጋገጥ ይቻላል ” ብለዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር ፕሬዜዳንት አቶ አማኑኤል ጳውሎስ በበኩላቸው፣ “ ‘አንድ መፅሐፍ ለአንድ ተማሪ’ በሚል ነው መምህራኑን ሳያወያዩ ‘በዞን ደረጃ ተወስኗል’ በሚል ከደመወዛቸው እየቆረጡ ያሉት ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
“ ደመወዝ ያለስምምነት መቆረጥ እንደሌለበት አቅጣጫ ቢቀመጥም ይሄን የሚያደርጉ አካላት ምንም ሲያደርጉ አይታዩም ” ሲሉም ተችተዋል።
“ ከዚህ በፊት ሌላ ዞንና ወረዳ ላይ እንደዚህ አይነት ነገር ሲያደርጉ የነበሩ ሰዎች ተመልሰው የተሻለ ሹመት እንዲያገኙ ነው የሚደረገው እንጂ ‘ይሄን አጥፍተሃል’ ተብሎ የማጠየቅ አካል የለም ” ነው ያሉት።
ስለቅሬታው ምላሽ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ታምራት፣ ለጊዜው የማይመች ቦታ እንደሆኑ ገልጸው፣ ቀጠሮ ሰጥተው የነበረ ሲሆን፣ በቀጠሩት ሰዓት በተደጋጋሚ ቢደወልም ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።
የዞኑ ትምህርት መምሪያ ትላንት በሰጠን ማብራሪያ፣ የመምህራኑ ደመወዝ የተቆረጠው በስምምነታቸው መሠረት እንደሆነ፣ የታሰሩትም፣ ድንጋይ ስለወረወሩ እንደሆነ፣ ቅሬታው እንዲፈታ እየሰራ ስለመሆኑ ገልጾ ነበር።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ሴጅ_ማሰልጠኛ
በቅዳሜ ጠዋት የልጆች የኮምፒውተር ኮዲንግ እና ግራፊክ ዲዛይን ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን።
👉ስልጠናው ዕድሜያቸው ከ 8-18 ዓመት ላሉ ልጆች የሚሰጥ
👉 ልጆች ፕሮጀክቶች እየሰሩ የሚሰለጥኑበት
👉ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
Tiktok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
Linkedin: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#ኢትዮጵያ
" ' ወደ ውጪ እንልካችኋለን ' በሚል ምክንያት ' ተጭበርብረናል ፣ ተዘርፈናል ' እያሉ ቅሬታ የሚያቀርቡ ሰዎች ተበራክተዋል " - የአ/አ ፍትህ ቢሮ
አሁን አሁን በኢትዮጵያ በርካታ ሰዎች በተለይም ወጣቶች ወደ ውጭ ሀገራት የመሄድ ፍላጎታቸው እየተበራከተ መጥቷል።
እኚህ ወጣቶች ከሀገር ለመውጣት የተለያዩ ሙከራዎችንም ሲያደርጉ ይታያል።
የውጭ ጉዞ ለማድረግ ከሚሞክሩባቸው አንዱ መንገድ ደግሞ በደላሎች ፣ በጉዞ ወኪሎች እና በሌሎችም አማካኝነት ነው።
ወጣቶች በትምህርት ፣ በስራ እንዲሁም በጉብኝነት አማካኝነት ነው ከሀገር ለመውጣት የሚጥሩት።
የራሳቸውንና የቤተሰባቸውን ህይወት ለመቀየር ፣ አፍላ የሆነ የወጣትነት እድሜያቸው ሳያልፍ አንዳች ነገር አፍርተው ቤተሰብ መስርተው ጥሩ ኑሮ ለመኖር ፤ ከድህነት ለመላቀቅ ሲሉ በሚሞክሯቸው የውጭ ሀገር እድሎች ግን ምንም ርህራሄ በሌላቸው አጨበርባሪዎች ሲታለሉም ይታያል።
የወጣቶቹን ፍላጎት እያየ ገንዘባቸውን የሚበላቸው ፣ አውሮፓና አሜሪካ ብሎ ሌላ የወንጀልና ደህንነት የሌለው ቀጠና የሚልካቸው ደላላ፣ ወኪል እየበዛ መጥቷል።
በመዲናችን አዲስ አበባ ህገወጥ ስራን የሚሰሩ የጉዞ ወኪሎች መበራከት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ተብሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፍትህ ቢሮ ለአሃዱ በሰጠው ቃል ፤ በየጊዜው የውጪ ሀገር የጉዞ ወኪልና አማካሪ ድርጅቶች እንዲሁም ደላሎች " ወደ ውጪ እንልካችኋለን " በሚል ምክንያት ' ተጭበርብረናል፣ ተዘርፈናል ' እያሉ ቅሬታ የሚያቀርቡ ሰዎች መበራከታቸውን አስታውቋል፡፡
እነዚህ ቅሬታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መምጣታቸው ተመላክቷል።
" እነዚህን ቅሬታዎች ተሰምተዉ ዝም የሚባልበት አግባብ የለም " ያለው ቢሮ በቀጥታ ለአዲስ አበባ እና ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በመላክ ተጠያቂነት እንዲሰፍን እየሰራሁ ነው ብሏል።
" በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም ወደ አውሮፓ የሚሄዱ ሰዎች ፍላጎት መበራከቱን ተከትሎ፤ ዜጎች ከሕግ ውጪ በሚሰሩ ድርጅቶችና ደላሎች አማካኝነት ረብጣ ገንዘባቸውን መጭበርበራቸው እየተባባሰ ይገኛል " ነው ያለው።
በብዙዎች ጥቆማና ቅሬታ መሰረት፤ ከዚህ ቀደም ከ40 በላይ ሕገ-ወጥ ሥራን በመስራት የተሰማሩ የውጪ ሀገር የጉዞ ወኪሎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ቢሮው አመልክቷል።
ፍትህ ቢሮ ፤ " ህብረተሰቡ በተለያየ መንገድ ወደ ውጪ ለመውጣት ሲፈልግ፤ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሕጋዊ የሆኑ ወኪሎችን ለይቶ ስላሰራጨ፤ በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎች ላይ ማግኘት ይችላል " ብሏል።
አልያም በአካል ቀርቦ መረጃ እንዲያገኝ ለአሃዱ በሰጠው ቃል አሳስቧል።
#ኢትዮጵያ #የውጭሀገራትጉዞ #ወጣቶች
@tikvahethiopia
🔴 "... አጭበርባሪዎቹ ከቦታው ዘወር ሲሉ በአካውንቱ ላይ ምንም ገንዘብ አይገኝምና እንደ አገር ታንቀው የሞቱ ወገኖች ጭምር እንዳሉ እናውቃለን " - የተወካዮች ምክር ቤት አባል
🔵 " ከማጭበርበር ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ሥራ እየደሰራን ነው " - ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ
የተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በታሪክ ለመጀመሪያ በመስሪያ ቤቱ በአካል በመገኘት የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን የሥራ አፈጻጸምን ገምግሟል።
ኮሚቴው እስከዛሬ ድረስ ድርጅቶችን ሲገመግም የነበረው በሚላክለት ሪፖርት ብቻ የነበረ ከመሆኑ አንጻር የአሁኑ ግምገማ በአካል በመገኘት መሆኑ ግምገማውን ለየት ያለ አድርጎታል።
ድርጅቱ በግምገማው ወቅት፣ የሳፋሪኮም ደንበኞች ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ተጠቃሚዎች በሚደውሉበት ወቅት ተጨማሪ ክፍያ እየከፈሉ መሆኑን ጠቅሶ፣ ይኼው ክፍያ እንዲቀርላቸው፣ የታወር ማስፋፊያ ፈቃድ በቅድመ ሁኔታ እንዲሰጥ ኮሚቴው ለመንግስት እንዲያሳስብለት ጠይቋል፡፡
ኮሚቴው በበኩላቸው፣ በቀረበው ጥያቄ ላይ ተወያይቶ ለተጠየቀው የድጋፍም ሆነ የፈቃድ ጥያቄ ምላሽ እንደሚሰጡ ቃል ገብቷል።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፣ በሦስት አመታት ውስጥ ከ6 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን እንዳፈራ፣ ከ12 ባንኮች ጋር እየሰራ መሆኑን፣ በዘጠኝ የክልል ከተሞች የኔቶርክ አገልግሎት ተደራሽ ማድረጉን የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዊም ቫንሄልፑት ገልጸዋል፡፡
በግምገማው የተገኙት የምክር ቤት አባላት ስለሳፋሪኮም የሥራ ሁኔታ የቀረበላቸውን ገለጻ ካዳመጡ በኋላ በአጭር አመት ውስጥ ድርጅቱ ያሳየው ውጤት ከፍተኛ መሆኑን በአንክሮ ገልጸው፣ በአንጻሩ ደግሞ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንሸራሽረዋል፡፡
የምክር ቤት አባላት ያነሷቸው ጥያቄዎች ምንድን ናቸው ?
➡️ ወ/ሮ ሙሉነሽ የተባሉ የም/ቤት አባል፣ “ ድጅታል ካሽ ፓይመንት ከፋይናንሻል ሰርቪስ አንፃር ለከስተመሩ ምን ያህል ሴኩይር ነው ?
ለምሳሌ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ማጭበርበሮች ይከናወናሉ፤ አንዳንድ የንግድ / የሽያጨ ተቋማት ኦንላይን ላይ ሽያጭ ተሽጧል ይባልና ገንዘቡ በአካውንት እንደተላከ የሚያሳይ ጊዜያዊ መልዕክት ይገባል ፤ ከዚያ በኋላ አጭበርባሪዎቹ ከቦታው ዘወር ሲሉ በአካውንቱ ላይ ምን ገንዘብ የማይገኝበት ሁኔታ በመኖሩ እንደ አገር ታንቀው የሞቱ ወገኖች ጭምር እንዳሉ እናውቃለን፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ የተጭበረበሩ እንዳሉም እናያለንና ይህን ጉዳይ ምን ያህል አስተማማኝ ነው ?
ድርጅቱ የሚሰራው ከ12 ባንኮች ብቻ ጋር እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ለምን ከቀሪ ባንኮች ጋር አብሮ አልሰራም ? ከሌሎች ባንኮችም ጋር በመስራት ሰርቪሱ ሰፋ እንዳይል ያደረገው ቻሌንጅ ምንድን ነው ? ” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
➡️ አቶ ከድር የተባሉ የምክት ቤት አባል ደግሞ ፥ " ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የምትሰሯቸው ሥራዎች ውጤታማ ናቸው ውይ ? ድርጅቱ ከመንግስት ጋር በገባው ውል አንጻር ተጽዕኖ አለበት ወይ ? ድርጅቱስ በውሉ መሠረት እየሰራ ነው " ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
➡️ ሌላኛው የምክር ቤት አባል ፥ " የድርጅቱ ዓላማ ኢትዮ ቴሌኮም ተደራሽ ባላደረጋቸው አካባቢዎች አገልግሎቱን ተደራሻ ማድረግ ከመሆኑ አንጻር፣ የመሠረተ ልማት ተደራሽነት በሌለባቸው አካባቢዎች በቂና የተለዬ ቴክኖሎጅ ከመጠቀም አንጻር ምን አድርገችኋል?
የኔቶርክ ጥራቱ ከኢትዮ ቴሌኮም የተሻለ ተብሎ ነው የቀረበቀው ነገር ግን አዲስ አበባ ራሱ የኔቶርክ ጥራት አለ ወይ ? " ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
የሳፋሪኮም በበኩሉ፣ " ከማጭበርበር ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ሥራ እየደሰራን ነው " ሲል የኮሚቴ አባል ላነሱት ጥያቄ ምላሽ ሰጥቷል፡፡
'ተጭበረበርን' የሚሉ ሰዎች ሪፖርት እንዳደረጉ ገንዘቡ ሆልድ እንዲሆን እንደሚያደርግ፣ ከዚያ ጉዳዩ በሕግ ታይቶ እርምጃ እንዲወሰድ እንደሚያደርግ ድርጅቱ አስረድቷል፡፡
ከ12 ባንኮች ባለፈ ከሌሎች ባንኮች ጋር ለምን እንዳልተሰራ ለቀረበው ጥያቄ ፥ የባንኮቹ ዝግጅትና የድርጅቱ ዝግጅት የተጣጣመ አለመሆኑን በምክንያት ጠቅሶ፣ ይህ ሲስተካከል ከሁሉም ባንኮች ጋር አብሮ መስራቱ የማይቀር እንደሆነ ጠቁሟል፡፡
ቴሌ ተደራሽ ባላደረጋቸው፣ የመሰረተ ልማት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች አገልግሎቱን ተደራሽ ከማድረግ አንጻር ምን እየሰራ እንደሆነ መጠይቅ የቀረበለት ድርጅቱ፣ የተቻለውን ያክል እየሰራ እንደሆነ፣ የጸጥታ ችግር ግን ፈተና እንደሆነበት ተናግሯል።
ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ያለው ሥራና ውድድር ከባድ ቻሌንጅ እንዳለው የገለጸው ድርጅቱ ከውል ጋር በተያያዘ ለቀረበለት ጥያቄ በእርግጥ በውሉ መሠረት እየሰራ እንደሆነ ገልጿል።
የኔቶርክ ጥራት በተመለከተ ለቀረበለት ጥያቄም፣ የኔቶርክ ጥራቱ የተሻለ እንደሆነ በመጥቀስ ምላሽ ሰጥቷል፡፡
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ነዳጅ #ረቂቅአዋጅ
🔴" ዋናው ነገር ኮንትሮባንድ ንግድ መስራታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ከባንኮች ብድር መውሰጃ እንደሆነ አረጋግጠናል " - የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት
🔵 " ለኮንትሮባንድ ንግድና ብድር ማግኛ ብሎ የገባው ኩባንያ ስርዓት ይይዛል " - ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር
በህገወጥ የነዳጅ ግብይት የታየዘ ግለሰብ ነዳጁ ተወርሶ ከ3 ዓመት በማይበልጥ እስራትና እስከ 100 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጣ የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ።
ረቂቁ ምን ይላል ?
- አዲስ የነዳጅ ምርት አከፋፋዮች ስራ ለመጀመር ቢያንስ 500 ሺህ ሊትር የነዳጅ ውጤቶች መያዝ የሚችል ማከማቻ / ዴፖ እና 4 ማደያዎችን ማዘጋጀት እንዳለባቸው ያስገድዳል።
- በስራ ላይ ያሉ ማደያዎች ደግሞ አዋጁ ከሚጸድቅበት ጊዜ ጀምሮ ለአዲስ አከፋፋዮች የተጣሉትን ግዴታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- አዲስ ጀማሪ ሆኑ ነባሮቹ በ3 ዓመታት ውስጥ ተጨማሪ 6 ማደያዎችን የመገንባት ግዴታ አለባቸው።
- የነዳጅ ውጤቶችን ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ያከማቸ፣ ሊሸጥ ከሚገባው ሰው ቦታና የግብይት ስርዓት ውጭ ሲሸጥ የተገኘ ወይም አደጋ ያስከትላሉ በተባሉ መያዣዎች ሲሸጥ የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ የተያዘው የነዳጅ ውጤት ተወርሶ ከ3 ዓመት በማይበልጥ እስርና ከብር 50 ሺህ እስከ ብር 100 ሺህ የሚደርስ ቅጣት ይፈጸምበታል።
- መንግሥት ከሚያወጣው የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ተመን ውጪ በተደጋጋሚ የመገበያየት ወንጀል እንዲሁም የነዳጅ ምርቶችን ከባዕድ ነገሮች ጋር መቀላቀል እስከ 3 ዓመት እስርና እስከ 300 ሺህ ብር ቅጣት ያስጥላል።
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ እስመለአለም ምህረቱ ምን አሉ ?
አሁን አሁን ወደነዳጅ አቅራቢነት ስራ ለመሰማራት ከፍተኛ ፍላጎት እየታየ ነው ብለዋል።
በድርጅቱ በተደረገው ጥናት ይህ ፍላጎት የኮንትሮባንድ ንግድ እና ከባንክ ብድር ለመወሰድ ተብሎ የሚደረግ እንደሆነ ተደርሶበታል ሲሉ ገልጸዋል።
ዋና ስራ አስፈጻሚው ፥ በዚህ 9 እና 10 ዓመት ውስጥ ከነበሩት 8 ወይም 9 ካምፓኒዎች አሁን 59 መድረሳቸውን ጠቁመዋል።
3ቱ የመንግሥት ገንዘብ አባክነው በፍርድ ቤት ክርክር ላይ ናቸው።
56ቱ ካምፓኒዎችን በማርኬትሼር በመደልደል ነዳጅ እየተሰጠ መሆኑን የገለጹ ሲሆን " ይህ ሁኔታ እራሱ እስካሁን ስምምነት የሌለበት ሁልጊዜ ጭቅጭቅ ያለበት ድርጊት ነው " ብለዋል።
ወደ ነዳጅ ግብይት አዲስ የሚገቡ ካምፓኒዎችን በተመለከተ ምንድነው አላማቸው ? ለምንድነው እንዲህ እያደገ የመጣው የሚለው መጠናቱን ገልጸዋል።
በጥናቱ ውጤትም " ዋናው ነገር ኮንትሮባንድ መስራታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ከባንኮች ብድር መውሰጃ እንደሆነ ነው የተረጋገጠው " ብለዋል።
እነዚህ የነዳጅ ካምፓኒዎች ባንኮች ጋር ሄደው ብድር በሚጠይቁበት ጊዜ ባንኮቹ " ከናተ ጋር ያላቸው የሥራ አፈጻጸም ይጻፍልን " እየተባለ ደብዳቤ እንደሚጻፍ ገልጸዋል።
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ምን አሉ ?
° አዋጁ አላማ መንግሥት በየዓመቱ በሚሊዮን ዶላሮች የሚያወጣበትን ለነዳጅ ምርት በአግባቡ ለማስተዳደር ነው።
° በመንግሥት በኩል የነዳጅ አቅርቦትን የማበራከት አላማ የለም።
° አዋጁ በእያንዳዱ የግብይት ሰንሰለት ውስጥ ባሉት ተዋናዮች ላይ የህግ ሪስትሪክሽኖችን ይጥላል። የአቅራቢ፣ የማደያ ... ግዴታዎች አሉ።
° ግብይታችን ችግር አለበት። የአቅርቦት ችግር ሳይኖር ስርጭት ላይ ትልቅ ችግር አለ። የታሰበላቸው ቦታ ያለመድረስን በተመለከተ በክልሎች የሚቀርበው ቅሬታ ገሚሱ ትክክል ነው።
° ነዳጅ አለ !! ሳምንት ሁለት ሳምንት ገበያ ማስራብ ፣ በነዳጅ ማደያዎች ውስጥ ነዳጅ ይዞ ' ቤንዚን የለም ፤ ናፍጣ የለም ' ብሎ መለጠፍ ይሄ ደግሞ ተጠያቂነት የማያስከትልበት ሴክተራል ባህሪው እንዲቀየር ይታሰባል፤ ይፈለጋል በመንግሥት በኩል ለዛም ነው ይሄ አዋጅ የሚወጣው።
° ከዚህ በኃላ ንግድን አንከለክልም እናሰፋዋለን ፤ ግብይቱ እንዲሳለጥ እንፈልጋለን ነገር ግን ለኮንትሮባንድ ንግድና ብድር ማግኛ ብሎ የገባው ኩባንያ ስርዓት ይይዛል።
° የነዳጅ ኮታ እና ስርጭት ላይ ፍትሃዊ ስርዓት ለመፍጠር ይሰራል።
° ከአቅርቦት እና ስርጭት ይልቅ ማስተዳደሩ ከባድ ነው።
° ነዳጅ እያላቸው ዘግተው የሚቀመጡ ማደያዎች በስፋት አሉ። የቅጣት መጠኑ ላይ ጠንካራ ስራ ይሰራል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከሪፖርተር እንዲሁም ከህ/ተ/ም/ቤት የቀጥታ ስርጭት ማግኘቱን ይገልጻል።
#ኢትዮጵያ #ነዳጅ #ረቂቅአዋጅ
@tikvahethiopia
#Update
🔴 " የቤንዚን አቅርቦት ባለባቸው ማደያዎች የፀጥታ መዋቅር እየተቆጣጠረ ተገቢዉ ስርጭት እየተካሄደ ነዉ " - ግብረ ኃይሉ
🔵 " ምንም እንኳን ማደያዎች አካባቢ ያለው ግብግብ ቢሻሻልም አሁንም ተሰልፎ መዋል ነው " - ነዋሪዎች
በሲዳማ ክልል፣ በሀዋሳ ከተማ የነበረዉን ሕገወጥ የቤንዚን ንግድ በተመለከተ ተደጋጋሚ መረጃዎችን መለዋወጣችን ይታወሳል።
ከሰሞኑን የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሆነ መገለጹም የሚዘነጋ አይደለም።
ምንም እንኳን የመፍትሄ አቅጣጫዎች ቢቀመጡም እርምጃዎችም እየተወሰዱ እንደሆነ ቢነገርም አሁንም ያልተቀረፉ ችግሮች መኖራቸውን መታዘቡን የሀዋሳ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ከስፍራው ያለውን ሁኔታ አድርሶናል።
በክልሉ የነዳጅ ሥርጭቱን ለመቆጣጠር ግብረ-ኃይል መቋቋሙን ተከትሎ የከተማዉ ንግድ ኃላፊ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ፤ ሁለት ከፍተኛ ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን፤ ሦስት ማደያዎች ላይ እርምጃ መወሰዱንና በአጠቃላይ ከ8 ሺህ ሊትር በላይ በሕገወጥ መንገድ የተከማቸ ቤንዚን መያዙ ተገልጿል።
ሆኖም ግን ግብረ-ኃይሉ ከቀናት በፊት ባካሄደው ውይይት ላይ " ከዚህ ቀደም ተሽከሪካሪ ተለይቶ ይደለደል የነበረዉ አሰራር ከአሁን ጀምሮ አይኖርም " ተብሎ ቢገለጽም ይህ የተሽከሪካሪ ምደባ አሁንም መቀጠሉን ታዝበናል።
ይህ ለምን ሆነ ? ብለን ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ መምሪያ ኃላፊ ጥያቄ ያቀረብን ሲሆን " ምደባዉን ማስቆማችን አይቀርም አሁን ላይ ባለዉ እጥረት ለቁጥጥር ስለሚያስቸግር ነዉ ያላቆምነዉ። ከአራት በላይ ማደያዎች አቅርቦት ሲኖር ምደባዉን እናስቆማለን " የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።
በቀጣይም በባለሙያዎች እና ማደያዎች ላይ የተጀመረው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል የተባለ ሲሆን የተረጋጋ የቤንዚን ስርጭት እስኪፈጠር ግብረሃይሉ በትኩረት ይሰራል ተብሏል።
በተጨማሪም ግብረኃይሉ፦
- የቤንዚን አቅርቦት ባለባቸው ማደያዎች የፀጥታ መዋቅር እየተቆጣጠረ ተገቢዉ ስርጭት እየተካሄደ ነዉ።
- በሕገወጥ ግብይትና ተባባሪነት የተጠረጠሩ 34 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዉለዋል።
- ለጥቁር ገበያዉ አመላላሽ የነበሩ ከ20 በላይ ተሽከርካሪዎች ተይዘዋል።
- የፀጥታ ሃይሎችና በእንግድነት ወደ ከተማዋ የሚገቡ ሰዎች እየተጣሩ ያለ ሰልፍ እንዲቀዱ ይደረጋል ... ብሏል።
ማደያዎች ምን አሉ ? ማደያዎች ግብረኃይሉ በሚመራው አካሄድ ስርጭት እየተካሄደ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
አሽከርካሪዎች እና ነዋሪዎች ምን ይላሉ ?
ያነጋገርናቸው አሽከርካሪዎች በማደያዎች አከባቢ ይስተዋሉ የነበሩ ግብግቦች መቀነሳቸውንና አሁን ላይ እየተቀዳ ያለዉ በተራ ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።
ሆኖም ግን የባጃጅ አሽከርካሪዎች " ከሰልፉ ብዛት የተነሳ አሁንም ተሰልፎ ዉሎ አለመቅዳት ስላለ፥ አይደለም የምንሰራበት ተሰልፈን ዉለን 12:ዐዐ ሲዘጋ ወደቤት መመለሻ እያጣን ነዉ " ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
አሁንም ቢሆን የቤንዚን ሰልፉ በጣም ረጃጅም መሆኑን የገለጹት አሽከርካሪዎች " የታክሲ አገልግሎት ሰጥተን ቤተሰቦቻችንን የምንመራ ሰዎች ለከፍተኛ ችግር ተዳርገናል " ሲሉ ሁኔታውን ገልጸዋል።
ቁጥጥሩ ወቅታዊ እንዳይሆን ስጋት ያላቸው አሽከርካሪዎቹ የዕለቱ የቤንዚን ስርጭት ከተዘጋ በኋላ በአንዳንድ ማደያዎች ያለ ተራ የመቅዳት ተግባራት እንደሚስተዋሉ ጠቁመዋል።
የሞተር ባለንበረቶችም እንደልብ ነዳጅ ማግኘትና መንቀሳቀስ አሁንም እንዳልተቻለ ፤ እርምጃዎች ተወሰዱ ከተባለ በኃላ በተጨባጭ የታየ ለውጥ መመልከት እንዳልሻሉ ጠቁመዋል።
ቃላቸውን ለቲክቫህ የሰጡ ሌሎች የከተማው ነዋሪዎች " በማደያዎች አከባቢ መሻሻሎች ቢኖሩም ችግሩ አልተቀረፈም የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ መቀዛቀዞች ይስተዋላሉ " ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
#USA
ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጾታቸውን የቀየሩ የሀገሪቱ ጦር አባላት ወታደሮችን እንደሚያግዱ ተነገረ።
ትራምፕ ሰዎች ተፈጥሯዊ ጾታዎችን መቀየር የለባቸውም ብለው ያምናሉ።
ይህን ተከትሎም ጾታቸውን የቀየሩ እና የሀገሪቱ ጦር አባላት የሆኑ ወታደሮችን ከስራ እንደሚያግዱ ዘ ታየምስ ዘግቧል።
እንደዘገባው ከሆነ 15 ሺህ ጾታቸውን የቀየሩ ወታደሮችን የማባረር እቅድ አላቸው።
ከዚህ በተጨማሪም ተፈጥሯዊ ጾታቸውን የቀየሩ አሜሪካዊያን የሀገሪቱን ጦር መቀላቀል እንዳይችሉ እገዳ እንደሚጥሉም ተገልጿል።
ዶኔልድ ትራምፕ በከ2016-2020 ድረስ በስልጣን ላይ በነበሩባቸው ዓመታት ውስጥ ተፈጥሯዊ ጾታቸውን የቀየሩ ዜጎች የአሜሪካ ጦርን እንዳይቀላቀሉ እገዳ ጥለው የነበረ ቢሆንም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ይህንን እገዳ አንስተውታል።
ይህን መረጃ ዘ ታይምስን ዋቢ በማድረግ ያጋራው አል አይን ኒውስ ነው።
@tikvahethiopia
#ExchangeRate
ከሰሞኑን የዶላር ምንዛሬ ዋጋ ጭማሪ እያሳየ ነው።
ባለፉት በርካታ ቀናት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር መግዣው 119 ብር ከ2044 ሳንቲም ፤ መሸጫው ደግሞ 121 ብር ከ5885 ሳንቲም ነበር።
ካለፈው ቅዳሜ አንስቶ ግን የምንዛሬ ዋጋው ጨምሯል።
ባንኩ በመግዣ ዋጋው ላይ ከ3 ብር በላይ ጭማሪ በማድረግ 122 ብር ከ5986 ሳንቲም አስገብቶታል።
መሸጫውም በተመሳሳይ ከ3 ብር በላይ ጨምሮ 125 ብር ከ0506 ሳንቲም ገብቷል።
ከግል ባንኮች በአቢሲንያ ባንክ ዶላር 123 ብር ከ0001 ሳንቲም እየተገዛ በ125 ብር ከ4601 ሳንቲም እየተሸጠ ነው።
በሕብረት ባንክ ደግሞ መግዣው 121 ብር ሲሆን መሸጫው 123 ብር ከ4200 ሳንቲም ነው።
(ከዶላር ውጭ የሌሎች ሀገራት ገንዘብ ምንዛሬ ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia
💫ከዳር እስከ ዳር አስተማማኙን ኔትወርካችንን እያሰፋን ወደ እናንተ እየቀረብን ነው!🙌👏ከአስተማማኙ ኔትወርካችን ጋር አሁንም በአብሮነት ወደፊት!
አስተማማኙን ኔትወርክ ዛሬውኑ እንቀላቀል!
የቴሌግራም ቦታችንን /channel/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!
#MPESASafaricom #1Wedefit
#Furtheraheadtogether
#ማይናማር🚨
🔴 “ ልጆቻችን በስቃይ ውስጥ ነው ያሉት። መንግስት አንድ መፍትሄ ይፍጠርልን ” - የወላጆች ኮሚቴ
🔵 “ ከአገራቱ ጋር የስራ ሥምሪት ስምምነት ባለመኖሩ፣ ሰዎቹም ያቀኑት በህገ ወጥ መንገድ በመሆኑ ያሉበት ቦታና ቁጥራቸውን በትክክል ለማወቅ አስቸጋሪ ሆኗል ” - ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር
ማይናማር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወላጆች ኮሚቴ አዋቅረው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ልጆቻቸው ካሉበት አስከፊ ሁኔታ እንዲያወጣላቸው እየጠየቁ ቢሆንም እስካሁን ልጆቻቸው ወደ አገር ባለመመለሳቸው ጥልቅ ጭንቀት ላይ መሆናቸውን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ተናግረዋል።
መንግስት ለጉዳዩ ይበልጥ ትኩረት እንዲሰጥም በአጽንኦት ጠይቀዋል።
የኮሚቴው በዝርዝር ምን አለ ?
“ ልጆቻችን አሁንም እየተገረፉ፤ እየተደበደቡ ነው። 18 ሰዓት እያሰሯቸው ነው። ጭራሽ ገንዘብ ካልገባና አጨበርብረው ብር ካላመጡ 24 ሰዓት ሙሉ ኮምፑዩተር ላይ ቁጭ ስለሚያደርጓቸው ፌንት እየነቀሉ የሚወድቁበት ሁኔታ አለ።
ልጆቻችን በስቃይ ውስጥ ነው ያሉት። መንግስት አንድ መፍትሄ ይፍጠርልን። በአካባቢው ያሉ ዲፕሎማቶች እንዲሰሩ የሚያሳስብ ነው የኛ ማመልከቻ።
ታግተው ካሉት ውስጥ 2 ሴት ወጣቶች መለቀቃቸውን ብቻ ነው የማውቀው። እኛ ወደ 153 ወጣቶችን ዝርዝር ነው ይዘን ወደ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እየሄድን ያለው።
ከእነዛ ውስጥ ወደ 2 ሴቶች ብቻ ናቸው የወጡት። በመንግስት በኩል ወደ 31 ወጣቶች ወጥተዋል የሚል ዜና ነው ያየነው። በተጨባጭ የወጡትን ልጆች አላየናቸውም።
ይሄው 11ኛ ወራችን ነው በማመልከቻ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መመላለስ ከጀመርን እካሁን ጠብ ያለ መፍትሄ የለም። ከ3,000 በላይ ኢትዮጵያን ናቸው እዛ እየተሰቃዩ ያሉት።
በስቃይ ላይ የሚገኙት ቢያንስ ከመጀመሪያ ድግሪ በላይ የትምህርት ደረጃ ያላቸው ልጆች ናቸው። ይሄ ለቤተሰብ ብቻ ሳይሆን ለአገርም ኪሳራ ነው። ለኛም ትልቅ ጭንቀት ነው ሆኖብን ያለው ” ብሏል።
የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትርን እየተመላለሳችሁ እየጠየቃችሁ ከሆነ ምን ምላሽ ሰጣችሁ? የሚል ጥያቄ ያቀሰብንለት ኮሚቴው፣ “ ‘ለተወካዮች እናሳውቃለን በዛ በኩል ነው መታዬት ያለበት፤ ቶኪዮ ያለው ነው ማይናማርን የሚመለከተው’ የሚል መልስ የሚሰጡን ” ብሏል።
በማይናማር ስለሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ቤተሰቦቻቸው ዜጎቹ በስቃይ ውስጥ እንደሆኑ፣ ለዚህም መንግስት መፍትሄ እንዲሰጣቸው እየተማጸኑ እንደሆነ በመግለጽ፣ ምን እየሰራ ነው ? ጉዳዩ ተስፋ አለው ? ስንል የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠይቀናል።
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በበኩላቸው ተከታዩን አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።
አምባደር ነብያት ጌታቸው ፦
“ ባለፈው ሳምንት መግለጫ ሰጥተን ነበር። በዛ ላይ እስከ ባለፈው ሳምነት መጨረሻ ያሉ ደቨሎፕመንቶችን ነው ያቀረብነው።
ከዚያ ወዲህ የክትትል ሥራ ነው የተሰራው ቶኪዮ ያለው ኤምባሲያችን ከማይናማር መንግስት አካላት ጋር በዚህ ሳምነት ውስጥ ክትትል እንደተደረገ ተገልጾልናል። እስካሁን ያለው ሂደት እዚህ ላይ ነው ያለው።
እስካሁን በተደረገ ጥረት 31 ዜጎቻችን ከነበሩበት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ወጥተው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረግ ተችሏል።
ከአገራቱ ጋር የስራ ሥምሪት ስምምነት ባለመኖሩ እና ሰዎቹም ያቀኑት በህገ ወጥ መንገድ በመሆኑ ያሉበት ቦታ እና ቁጥራቸውን በትክክል ለማወቅ አስቸጋሪ ሆኗል።
መንግሥት ለዜጋ ተኮር ቅድሚያ ትኩረት ስለሚሰጥ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል።
አሁንም ህብረተሰባችን ከህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችና ህገ ወጥ ጉዞ ራሱንና ልጆቹን መጠበቅ አለበት።
መገናኛ ብዙኃንም ይህን ጉዳይ ልዩ ትኩረት ሰጥተው መስራት ይገባል። ዜጎቻችን የህገ ወጥ ሰዎች አዘዋዋሪዎች ሰለባ መሆን የለባቸውም ” ብለዋል።
ቤተሰቦቻቸው በጣም ተጨንቀው እያለቀሱ ነው። ታጋቾቹም አብረዋቸው የነበሩ የሌሎች አገራት እየተለቀቁ ስለሆነ የኢትዮጵያ መንግስትም ጫና ቢያደርግ የመውጣት እድል እንዳላቸው እየገለጹ ነው፤ እንዲያው ሚኒስቴር መስሪያ ቤትዎ ምን ያህል ጥረት አድርጓል ? ስንል ለአምባሳደሩ ጥያቄ አቅርበናል።
አምባሳደር ነብያት ፤ “ ከአገራቱ ጋር የሥራ ስምሪት ስምምነት ያለበት ቦታ አይደለም። ሰዎቹም የሄዱት ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ነው። ያሉበትን ቦታና ቁጥራቸውን ራሱ በትክክል ለማወቅ እጅግ አዳጋች ነው ” ብለዋል።
“ የማይናማር መንግስት ከሚቆጣጠረው አካባቢም ያሉ አይደሉም ለዛነው ችግሩ እጅግ አስቸጋሪ የሆነው ” ሲሉ አክለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#DStvEthiopia
⚽️አዲስ ነገር ለኳስ አፍቃሪያን...
👉ከሕዳር 16 ጀምሮ ፈጥነው ወደ ሜዳ ስፖርት ፓኬጅ ከፍ ይበሉ! ሁሉንም የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎችን፣ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ፣ ሎችም ዋና ዋና እግር ኳስ እና ምርጥ ምርጥ መዝናኛዎችን ያካተቱ ከ129 በላይ ቻናሎችን በወር በ1699 ብር ብቻ!
ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et
ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/48oVhj8
#ሁሉምያለውእኛጋርነው #MedaSport
#Update
" ተገደን እንጂ ወደን የገባነው ጦርነት የለም ፤ በDDR አሰራር ወደ ህዝባችን ለመቀላቀል ፍቃደኞች ነን ሁሌም ምርጫችን ሰላም ነው " - ተመላሽ ታጣቂዎች
የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የዲሞብላይዜሽን እና መልሶ ማቋቋምያ ስነ-ሰርዓት በትግራይ መቐለ በይፋ ተጀምሯል።
ቅዳሜ ህዳር 14/2017 ዓ.ም በይፋ በተከናወነው የዲሞብላይዜሽን እና መልሶ ማቋቋምያ የማስጀመሪያ ስነ-ስርዓተ የክልሉ እና የፌደራል ከፍተኛ የስራ ኋላፊዎች ተገኝተው ነበር።
የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በDDR የሚታቀፉ የትግራይን ጨምሮ በስድስት የሀገሪቱ ክልሎች የሚገኙ ከ600 ሺህ በላይ ታጣቂዎች በሁለት ዓመት ውስጥ ዴሞብላይዝ በማድረግ ወደ ህዝቡ እንዲቀላቀሉ አቅዶ እየሰራ እንደሆነ በማስጀመሪያ ስነ-ስርዓቱ ተገልጿል።
የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን ምን አሉ ?
ትጥቅ መፍታትና ዴሞብላይዜሽን (DDR) ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነቶች ዋነኛ እና ጎልቶ የሚጠቀስ ነጥብ ቢሆንም በሃብት እጦት ምክንያት መዘግየቱ ተናግረዋል።
በትግራይ ጦርነት የተሳተፉ 274,800 ታጣቂዎች በDDR ዴሞብላይዝ ሆነው በሁለት ዓመት ውስጥ ወደ ህዝብ ይቀላቀላሉ ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ፦
👉 በአንድኛ ዙር 75 ሺህ
👉 በሁለተኛ 100 ሺህ
👉 በሦስታና ዙር 53 ሺህ 800
👉 በአራተኛ ዙር 46 ሺህ እንደሆነ አብራርተዋል።
በተካሄደው እጅግ አሰቃቂ ደም አፋሳሽ ጦርነት " በርካታ ህይወት ተቀጥፈዋል ፣ አካል ጎድሏል የሀገር እና የህዝብ ሃብት ወድመዋል " ያሉት አቶ ተመስገን ይህ እንዳይደገም እንደ ሀገር እና ህዝብ በቁርጠኝነት መስራት አለብን ሲሉ በአፅንኦት ተናግረዋል።
የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳን ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?
DDR ቀድሞ መደረግ የነበረበት ቢሆንም፤ ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ የሚሆን ሃብት ለማሰባሰብ ነው የዘገየው ፤ የዘገየም ቢሆን ዛሬ መጀመሩ ለሰላም ያለው ትርጉም ትልቅ ነው ብለዋል።
ተፈናቃዮች ባልተለመለሱበት፣ የትግራይ ሉኣላዊ ግዛቶች ከፌደራል የሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጭ ባሉ የሀገር ውስጥና የውጭ ታጣቂዎች ተይዞ ባለበት ወቅት DDR መጀመሩ ከስጋት ወጪ ሆኖ እየተፈፀመ ባይሆንም ሁኔታዎች እየተስተካከሉ ይሄዳሉ ከሚል ተስፋ ድጋፋችን መስጠት እንቀጥላለን ሲሉ ገልጸዋል።
የDDR መተግበር የትግራይ ሰላም መቀጠል ከሀገር ሰላም መፅናት ተያይዞ መታየትና መፈፀም እንዳለበት የፌደራል መንግስት እና ለጋሾች ትኩረት አደርገው ደጋፋቸው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅብረዋል።
የተሰናባች ታጣቂዎች ተወካይ ነጋሽ ገ/ዮሃንሰ ምን አሉ ?
" ተገደን እንጂ ወደን የገባነው ጦርነት የለም ፤ ስለሆነም የነበረው ችግር በጠረጴዛ ውይይት መፍታት ከተቻለ ትጥቅ አንግበን የምንኖርበት ፍላጎት ስለሌለን በDDR አሰራር ወደ ህዝባችን ለመቀላቀል ፍቃደኞች ነን " ብለዋል።
ታጣቂዎች " የመጀመሪያ እና የመጨረሻ ምርጫችን ሰላም ነው የተሟላ ሰላም እንዲሰፍን አሁንም ከፌደራል የሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጪ በትግራይ መሬት ያሉ ታጣቂዎች ለቀው እንዲወጡ ለፌደራል መንግስት እና ለአደራዳሪዎች እንጠይቃለን " ሲሉ ተናግረዋል።
" ለቀድሞ ታጣቂዎች ለማቋቋምያ የተመደበው በቂ ስላልሆነ ቀጣይ የሆነ ድጋፍ እንሻለን " በማለትም ተናግረዋል።
በመርሃ ግብሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ፣ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል አመራሮች ተገኝተው ነበር።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
Photo Credit - DW
@tikvahethiopia
🔈#የሠራተኞችድምፅ
🔴 " ደመወዛችን ተቆርጦ 15 ,000 ብር የሚከፈላቸው 5 ,000 ብር ነው የገባላቸው፡፡ ለ6 ወራት ደመወዛችን በስርዓት እየተከፈለን አይደለም " - ሠራተኞች
🔵 " ጥሩ ቅሬታ ነው። ድርጅቱ ደመወዝ የሚከፍለው ብር ሲኖር ነው " - የናሁ ቴሌቪዥን አስተዳደር
የናሁ ቴሌቪዥን ሠራተኞች የወር መወዛቸው በወቅቱ እንደማይፈጸም፣ ጊዜው ካፈ በኋላ ራሱ ከደመወዛቸው ከግማሽ በላይ ተቆርጦ እንደሚደርሳቸው፣ ደመወዛቸው ባለመከፈሉ ብድር ጭምር እንደገቡ፣ ድርጅቱ አጥጋቢ ምላሽ በመስጠት ፋንታ እያንጓጠጣቸው መሆኑን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ስሞታ አሰምተዋል፡፡
ሠራተኞቹ ያቀረቡት ዝርዝር እሮሮ ምንድን ነው?
" ደመወዛችን ተቆርጦ 15 ሺሕ ብር የሚከፈላቸው 5 ሺሕ ብር ነው የገባላቸው። ላለፉት ስድስት ወራት የሰራንበት ደመወዝ በትክክል እየተከፈለን አይደለም፡፡ አሁን ለምሳሌ የጥቅምት ወር ደመወዝ ዛሬ ነው የገባልን።
ወቅቱን ተላልፎ እንኳ 13 ሺሕ ብር የሚከፈለን ሰዎች ተቆርጦ 6,500 ብር ነው የገባልን፡፡ ወሩን ሥራ ገብተናል፡፡ ግን ‘ፊርማ አልፈረማችሁም’ ተብሎ ነው የተቆረጠው፡፡ ለዜናም፣ ለጥቆማም ልናናግር ወጥተን ያረፈድነው ሰዓት አይቆጠርልንም፡፡
የሐምሌን ደመወዝ ራሱ ‘ከባንክ ተበደሩና ውሰዱ እኛ እንከፍላን’ ነበር ያሉን፡፡ የሐምሌ ደመወዛችን ባለመፈጸሙ አቢሲኒያ ብድር ገብተናል፡ ግን እስካሁን እለተከፈለንም፡፡
የነሐሴ ወር ደመወዝ ደግሞ 20 ፐርሰንት ተቀንሶ ነው የገባው፡፡ ቀሪውን ራሱ እስካሁን አልሰጡንም፡፡ የመስከረም ደግሞ ጥቅምት 20 ነው የተከፈለን፡፡ ይህ ባለበት ሁኔታ አሁን ደግሞ ደመወዛችን ከግማሽ በታች ተቆርጦ ነው የገባው፡፡
ከ10 ሺሕ ብር እስከ 3,000 ብር ነው የተቆረጠብን፡፡ ይህ ሲደረግ ምንም አይነት ማስጠንቀቂያ አናውቅም፡፡ ብቻ ደመወዛችን ሲገባ ግን ተቆርጧል፡፡ ስንናገርም ‘ከፈለጋችሁ ውጡ ከፈለጋችሁ ተቀመጡ’ ነው የምንባለው።
ድርጊቱ ከአቅማችን በላይ ሆኗል። እስከ ሰባት ዓመት የሰሩ ጓደኞቻችንን ‘እንዳትመጡ’ ብለዋቸዋል። አንዷ ወር ሙሉ የሠራችበት ተቆርጦ 1,000 ሺሕ ብር ነው የገባላት ከ10 ሺሕ ብር ደመወዟ። ‘ምን ታመጣላችሁ ብትፈልጉ ውጡ’ ነው የሚሉት።
ሰው ለመቀነስ ፈልገው ከሆነ እንኳ በአግባቡ ምክንያቱ ተጠቅሶ፣ ደብዳቤ ተፅፎ፣ ለሠራተኛው የሚገባው ሁሉ ተሰጥቶ ነው የሚሆነው። ከዚህ ግን ማናጀሩ ‘ኑ’ ብሎ ‘ካሁን ወዲያ እንዳትመጡ’ ነው የሚለው " ብለዋል።
የሌሎች ደመወዝ በትክክል እየተፈጸመ ከሆነ የእናንተ ለብቻው ለምን በወቅቱና ሳይቆረጥ አልተፈጸመም? ምን የተለዬ ምክንያት ኖሮ ነው የእናንተ ብቻ እንዲህ የተደረገው? በሚል ላቀረብነው ጥያቄ ምላሻቸው፣ " እነርሱ የሚሉት ‘አቴንዳንስ በትክክል አልፈረማችሁም’ ነው፡፡ ግን ሰዓት አልፎም ቢሆን ፈርመናል " የሚል ነው።
“ ደመወዝ ሊቆረጥ የሚችለው በተሸረረፈው ሰዓት ነው፡፡ ሦስት ቀን ያልፈረመ የአንድ ቀን ይቆረጣል ነው የሚለው ሕጉ” ሲሉ አክለው፣ " እኛ ግን ለምሳሌ 4 ሰዓት ገብተን ቢሮ ውለን የሙሉ ቀን ደመዝ ነው የሚቆረጥብን " ብለዋል።
ቅሬታው ያላቸው 14 ሰዎች እንደሆኑ፣ ከድርጅቱ ደመወዝ ያልተቆረጠባቸው አራት ወይም አምስት ሰዎች እንደሆኑ አስረድተው፣ ድርጅቱ በአግባቡ እንዲያስተዳድራቸው ጠይቀዋል።
ሠራተኞቹ ያቀረቡትን ቅሬታ በመንገር እውነት ነው ? ከሆነ ለምን እንደህ ተደረገ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቃቸው የናሁ ቴሌቪዥን አስተዳደር አቶ ኢዶሳ ቀጀላ፣ " ጥሩ ቅሬታ ነው። ድርጅቱ ደመወዝ የሚከፍለው ብር ሲኖር ነው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
የድርጅቱ አስተዳደር አክለው ምን አሉ ?
" ብዙ ነገሮች ኪሳራ ላይ ስለጣሉን ብዙ ክፍያ ውጪ ላይ ስለሚያዝብንና ከከስተመሮቻችን ጋር ያሉትን ሴልሶች ቶሎ ኮሌክት ለማድረግ ስለማንችል/ ስለምንቸገር ደመወዝ ቆይተን ልንከፍል እንችላለን።
አንደኛ ደመወዝ ይቆያል። ሁለተኛ ደግሞ በአግባቡ ሥራ ያልገቡ ሰዎችን አቴንዳንሳቸው ኮሌክት ተደርጎ ይገባና ስንት ቀን ሥራ ገብተዋል? ተብሎ ነው ደመወዝ የሚከፈለው።
አሁን ‘ደመወዝ በአግባቡ አልተከፈለንም፣ ተቆረጠ’ የሚሉ ሠራተኞች በወር ውስጥ ስንት ቀን ገብተው እንደፈረሙ አቴንዳንሳቸው ታይቶ ነው ደመወዝ የተከፈላቸው እንጂ ሠራተኞች ስለሆኑ ብቻ 30 ቀናት ታስቦ አይሰጥም።
ስለዚህ የተቆረጠባቸው ሰዎች አሉ። እነርሱም በአግባቡ ያልገቡና አቴንዳንስ ያልፈረሙ ለድርጅቱ ሥራ ያልሰሩ ሰዎች ናቸው " ሲሉ ተናግረዋል።
ደመወዝ ሊቆረጥባቸው የሚገባው በሸራረፉት ሰዓት ሆኖ እያለ ሰዓት አሳልፈው ቢሮ ቢገቡም የሙሉ ቀን መቆረጡ ቅር እንዳሰኛቸው ሠራተኞቹ ገልጸዋል፤ ይህን ማድረጉ አግባብ ነው? ስንል ላቀረበው ጥያቄም ምላሽ ሰጥተዋል።
ምን አሉ ?
"አንድ ሠራተኛ ድርጅቱ በሚያውቀው መልክ ነው ገብቶ የሚወጣው እንጂ ሥራ ስለሌለ 4 ሰዓት መግባት የለም።
የቢሮ መግቢያ ሰዓት ከ2፡30 ይጀምራል። እስከ 3፡30 እኛ እዚያ እንቆያለን አቴንዳንስ ከዚያ በኋላ ይነሳል” ያሉት የድርጅቱ አሰሰተዳዳሪ፣ “እስከ 4 ሰዓት ያልገባ ሠራተኛ ገብቶ እንዲሰራ አንፈልግም፤ አንፈቅድም።
አጋጣሚ ሆኖ ችግር ካጋጠመ ደውሎ ማሳወቅ፣ ማስፈቀድ ይኖርበታል። እንደዚህ የሚያደርጉ ሠራተኞች በጥሩ ትራት ይደረጋሉ።
እንደፈለጉ ለሚገቡና ለሚወጡ ሠራተኞች ደመወዛቸውንም አንከፍልም፤ እሱም ብቻ ሳይሆን አስተዳደራዊ እርምጃም እንወስድባቸዋለን። ይህን ሕጉም ስርዓቱም ይፈቅዳል” በማለት ነው የመለሱት።
ድርጅቱ ሠራተኛ ለመቀነስ ፈልጎም ከሆነ በደብዳቤ እንጅ ‘ውጡ’ ተብሎ “ተጥላልተን” መሆን የለበትም የሚል ቅሬታ ሠራተኞቹ አላቸው፤ ይህን ማድረግስ ለምን አስፈለገ? በሚል ቲክቫህ ላቀረበው ጥየያቄ፣ “ይህን አላደረግነውም” የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንድስትሪ አ.ማ. ለደንበኞቹ ካዘጋጃቸው ሽልማቶች ውስጥ ሁለተኛው ቮልስ ዋገንአይዲ4 (VW ID4) የኤሌክትሪክ መኪና ዕጣ፣ በመዲናችን አዲስ አበባ ለዕድለኛ ወጥቷል፡፡
ዕድለኛዋ አሸናፊ ወ/ሮ መቅደስ አስናቀ፣ ሽልማታቸውን ኅዳር 14 ቀን 2017ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ በተከናወነ ልዩ የሽልማት ፕሮግራም ተረክበዋል፡፡
ከዚህ በፊት በሐዋሳ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ኤርሚያስ፣ የመጀመሪያውን ቮልስ ዋገን አይዲ4 (VWID4) የኤሌክትሪክ መኪና ዕጣ ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡
አሁንም በርካታ ሽልማቶች ተረኛ ዕድለኛቸውን እየጠበቁ ነው፡፡ የፔፕሲን ምርቶች እያጣጣምን ዕድላችን እንሞክር - እናሸንፍ! ፔፕሲ፣ ሚሪንዳ እና ሰቨን አፕ ይጥማሉ - ያስሸልማሉ!
ሞሐ !
#Bata
ፒላርሰ ትሬዲንግ ዓለም አቀፍ ብራንድ ከሆነው ' ባታ ጫማ ' ጋር ስምምነት በመፈረም ብቸኛ አከፋፋይ በመሆን ወደ ኢትዮጵያ ገቢያ በማሰገባት ለሺያጭ ለማቅረብ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ ላይ እንደሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
እ.ኤ.አ በ1894 ዓ/ም የተመሰረተው ባታ ጫማ በ5 አህጉር ከ70 በላይ ሀገሮች ላይ 5300 የጫማ መደብሮች ያለው ሲሆን በ21 ሀገሮች ላይም የጫማ ማምረቻ አሉት።
በችርቻሮ መደብሮቹም ለድንበኞቹ በሁሉም የእድሜ ክልል ላሉ ወንድና ሴቶች እንዲሁም ህፃናት የተለያዪ አይነት የጫማ አማራጮች ያቀርባል።
ፒላርሰ ትሬዲንግ በአጭር ጊዜ እቅድ ምርቶችን በማስመጣት ለገበያ ለማቅረብ ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል።
በቀጣይ 5 አመታት ውስጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ 100 ያህል የመሸጫ ሱቆችን የመክፈት እቅድ ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሆነ አመልክቷል።
የመጀመሪያው ሱቅ ቦሌ ማተሚያ ፊት ለፊት የሺ ህንፃ ግራውንድ ላይ በቅርቡ ከፍቶ ስራውን እንደሚጀምር ገልጿል።
ተጨማሪ መረጃ ፥ በ +251 966 96 56 76 (ዳግማዊ መስፍን) / +251913 03 77 24 (ትህትና ፀጋዬ) ላይ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
@tikvahethiopia
#ንጉስማልት ምግብ ያለ ንጉስ በጭራሽ አይታሰብም! የንጉስ ጠርሙስን ያሽከርክሩ ከዛም ከደረስዎ ምግብ ጋር ንጉስን ይሞክሩት::
#nonalcoholic #ንጉስ #DesDesWithNegus #ደስደስበንጉስ #የጣዕምልኬት_የደስታስሜት
#Mekelle
ዛሬ በመቐለ ከተማ በሚገኝ በአንድ የመንግስት ትምህርት ቤት በራፍ በጠራራ ፀሐይ ነዋሪዎችን ያስደነገጠ ድርጊት ተፈጽሟል።
አንድ መምህር በተማሪው በስለት ብዙ ቦታ ተውግቶ በህክምና እርዳታ ህይወቱ ተርፏል።
ተማሪው በምሳ ሰአት መውጪያ ላይ የደበቀውን ስል ቢላዋ በማውጣት መምህሩን 2 ጊዜ ደረቱ ላይ፣ 1 ጊዜ በሆዱ ላይ ፣ 1 ጊዜ በጀርባው ላይ ፣ 1 ጊዜ ጉኑ ላይ በአጠቃላይ 5 ቦታ ላይ ወግቶታል።
መምህሩን ወድያውኑ ወደ ዓይደር ሆስፒታል ማድረስ በመቻሉ በከባድ የቆዶ ህክምና ህይወቱ መታደግ ተችሏል።
ይህንን መረጃ ያጋሩት የዓይደር ኮምፕረሄንሲቭ ሆስፒታል ሃኪም የሆኑት ዶ/ር ፋሲካ ዓምደስላሴ " ብዙ ተማሪዎች ስለት ይዘው እንደሚንቀሳቀሱ እየሰማን ነው እንደ ማህበረሰብ አንድ ነገር ማድረግ አለብን " ብለዋል።
ድርጊቱን በተመለከተ ከፖሊስ በኩል የተባለ ነገር የለም።
ሆኖም ወላጆች እባካችሁ የልጆቻችሁን ውሎ ተከታተሉ። ካልተገባ ተግባርም እንዲርቁ ምከሩ ፤ ቸል አትበሏቸዋል እንላለን።
በሌላ በኩል ፤ በዛው መቐለ 6 ቀናት ያስቆጠረ ህፃን እናቱ ከቤት ትታው ወደ መፀዳጃ ቤት ታመራለች ፤ ዳናዋን ተከትሎ ህፃኑ ወደ ተኛበት ክፍል የገባ የቤታቸው ውሻ የህፃኑ መራብያ አካል ላይ ጉዳት አድርሷል።
እናቲቱ ወድያውኑ ደርሳ ልጇን ወደ ዓይደር ኮምፕረሄንሲቭ ሆስፒታል ይዛው እንደመጣች ዶ/ር ፋሲካ ዓምደስላሴ አጋርተዋል።
በእነዲህም አለና ወላጆች ልጨቅላ ልጆቻቹ የምታደረጉት ጥንቃቄ አይለያችሁ።
የተከሰቱት ድርጊቶች ምንም እንኳን ለመስማት የሚከብዱ ቢሆኑም ለወላጆች ጥንቃቄ ሲባል ያጋራናቸው ናቸው።
#Mekelle #AyderHospital
@tikvahethiopia
🔈 #የመምህራንድምጽ
🔴 “ ‘ለምን ደመወዛችን ተቆረጠ’ ብለው የጠየቁ 66 መምህን ታስረዋል” - የኮሬ ዞን መምህራን ማኀበር
🔵 “የታሰሩት በመምህራን ላይ ድንጋይ በመወርወር ሌሎቹን በመበጥበጣቸው ነው” - የዞኑ ትምህርት መምሪያ
🟢 “ምቹ ሁኔታ ላይ አይደለሁም። ሥራ ላይ ነኝ ስንት ሰዓት እንደምጨርስ አላውቅም” - የዞኑ ሰላምና ጽጥታ ቢሮ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ የሚገኙ መምህራን ደመወዛቸው ያለፈቃዳቸው በመቆረጡ እንዲመለስላቸው በመጠየቃቸው መታሰራቸውን የዞኑና የክልሉ መምህራን ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የዞኑ መምህራን ማኀበር ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ጭበጮ ለቲክቫህ በሰጡት ቃል፣ “‘ደመወዛችን ለምን ተቆረጠ’ ብለው የጠየቁ 66 መምህራን ታስረዋል” ብለዋል።
“‘የተቆረጠው ደመወዝ ከኛ ፈቃድና ስምምነት ውጪ ስለሆነ ይመለስልን’ የሚል ጥያቄ አቅርበው ነው የታሰሩት። ያለፈቃዳቸው ደመወዛቸው መቆረጡ፤ መታሰራቸው አግባብ አይደለም። አግባብ አለመሆኑን ለሚመለከተው አካል አሳውቀናል” ነው ያሉት።
“ከዞኑ መምህራን ማኀበር የታሰሩትን ለማነጋገር ሂደው የወረዳ አመራሮች የታሰሩት እንዳይጠየቁ ጭምር ከልክለዋል” ያሉት ሰብሳቢው፣ “ጥያቄያቸውን በውይይት መመለስ ሲገባችሁ ማሰር፣ መደብደብ፣ ማንገላታቱ ስህተት ነው” በሚል እየሞገቱ መሆኑን አስረድተዋል።
ስለጉዳየለ ማብራሪያ የጠየቅነው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማኀበር በበኩሉ፣ የመምህራኑ መታሰር ከዞኑ መምህራን ማኀበር ሪፓርት እንደተደረገለት በመግለጽ፣ “ያለአግባብ ማንም ተነስቶ ደመወዝ ቆርጦ መውሰድ ሕገወጥነት ነው” ሲል ወንጅሏል።
ከላይ ላሉት ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቃችኋል? በማለት የጠየቅናቸው የማኀበር ፕሬዚዳንት አቶ አማኑኤል ጳውሎስ፣ የመምህራኑን መታሰር አረጋግጠው፣ “ትላንት ነው ከዞኑ ሪፖርት የተደረገልን። ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቀናል” ብለዋል።
ያለፈቃዳቸው ደመወዝ መቁረጥና ለምን? ብለው የጠይቁ መምህራኑን ማሰር አግባብ ነው? የሚል ጥያቄ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ የቀረበላቸው የኮሬ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰረበ አሻግሬ፣ “ደመወዛቸው የተቆረጠው በፈቃዳቸው” ነው ሲሉ አስተባብለዋል።
ማኀበሩ ለእናንተም እንዳሳወቀ፤ ያለፍቃዳቸው እንደተቆረጠ፣ መምህራኑ እንደታሰሩ ነው የገለጸው፣ ፤ ይሄ ለምን ሆነ? በሚል ላቀረበሰነው ጥያቄ፣ “የሰርማሌ ወረዳ መምህን ጋር ተገናኝቻለሁ። ደመወዛቸው የተቆረጠው አሁን አይደለም፤ ፈቅደውም ነው” ብለዋል።
የኃላፊው ዝርዝር ምላሽ ምንድን ነው?
“ አንድ መፅሐፍ ለአንድ ተማሪ የሚል በሁሉም አካባቢ ወላጅም፣ ሠራተኞችም፣ ተማሪም እንዲተባበር የሚል አገር አቀፍ ጉዳይ አለ። የዞኑ አመራሮች ተስማምተው ነው ወደ ታች የወረደው።
የትምህርት ቤቱ መምህራን ባለሉበት ውይይት ተካሂዷል። ተስማምተው ደመወዛቸው ከተቆረጠ ቆይቷል። ሐምሌና ነሐሴ አካባቢ ነው የተቆረጠው። በተቆረጠ ጊዜ ነበር መቆረጡ ልክ አይደለም ብለው ማመልከት የነበረባቸው።
ተስማምተው ከተቆረጠ በኋላ የሳርማሌ ወረዳ ብቻ ይህንን ተግባሪዊ ሲያደርግ የከተማ አስተዳደርና ጎርካ አላደረገም። ግን ዞን ማዕከሉም ተግባራዊ አድርጓል 25 ፐርሰንቱን።
በመምህራኑ ‘እንዴት ሌሎች አካበቢ ያሉ መምህራን ሳይቆርጡ የኛ ብቻ ተቆረጠ? ስለዚህ ገንዘባችን ይመለስ’ የሚል ጥያቄ ነው የተነሳው መጀመሪያ። ገንዘብ ይመለስ የሚለው ነገር በጋራ እንነጋገራለን።
መምህራን በሁለት ነው የተከፈሉት። ግማሹ ‘እያስተማርን እንጠይቅ’፤ ግማሹ ‘ሙሉ ለሙሉ ትምህርት እናቁም’ የሚል ነው። የተወሰኑት ለማስተማር ክፍል ሲገቡ የተወሰኑት ደግሞ ድንጋይ ይዞ የሚሄድ፤ ተማሪ ይውጣ የሚል አለ።
በመምህራን መካከል ግጭት ተፈጠረ። የተቆረጠው ገንዘብ ይመለስ በመባሉ ሳይሆን በመምህራኑ መካከል በተፈጠረው ግጭት ነው የታሰሩት። ችግር የፈጠሩ ሰባት መምህራን ነበሩ ትላንት የታሰሩት።
መምህራኑ የታሰሩት ችግር ፈጥረው ነው ሳይፈጥሩ? የሚለውን እንዲያረጋግጡ ለአራት ዞኑን መምህራን ማኀበር ወደ ታች እንዲወርዱ አሳይመንት ሰጥቻሁ። ትላንት ነበር አሳይመንት የሰጠሁት እነርሱ ግን የወረዱት ዛሬ ነው።
‘እንደገና ደግሞ ሌሎች መምህራን ታስረዋል’ ሲባል በምን ምክንያት ? ስል በፊት የታሰሩት መምህራን ለምን ታሰሩ ? ብለው ሊረብሹ መጥተው ነው የሚል መረጃ አለ።
አሁን የዞኑን መምህራን ማህበር፣ ትምህርት ጽሕፈት ቤትንም አግኝታለሁ ውይይት ላይ ናቸው።
የታሰሩት በመምህራን ላይ ድንጋይ በመወርወር ሌሎቹን በመበጥበጣቸው ነው እንጂ ያ በውይይት የሚፈታ ነው። በዚህ ተስማምተናል። ” ብለዋል።
መምህራኑ ለምን ታሰሩ ? በሚለው ጉዳይ ማብራሪያ የጠየቅናቸው የኮሬ ዞን ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈራ ቦንደሮ፣ “ ምቹ ሁኔታ ላይ አይደለሁም። ሥራ ላይ ነኝ ስንት ሰዓት እንደምጨርስ አላውቅም ” በማለት ለማብራሪያ ቀጠሮ ከመስጠትም ተቆጥበዋል።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ለጉዳዩ ምላሽ ለመስጠት ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን፣ ምላሽ ሲሰጥ፣ ጉዳዩንም እስከመጨረሻው በመከታተል ተጨማሪ መረጃ የምናቀርብ ይሆናል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia