" ቤተሰብ መበታተን አልፈልግም ፤ ቤተሰቦች የማይለያዩበት ብቸኛው መንገድ ሁሉንም አንድ ላይ ከአገር ማባረር ነው " - ትራምፕ
ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከNBC ጋር ቆይታ አድርገው ነበር።
በዚህም ቆይታቸው ከስድተኞች ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን አንስተዋል።
ምን አሉ ?
ትራምፕ ወላጆቻቸው በውጭ አገራት ቢወለዱም በአሜሪካ የተወለዱ ልጆቻቸው ዜግነት የሚያገኙበትን መብት እሽራለሁ ብለዋል።
ወላጆቻቸው ሌላ ቦታ ቢወለዱም በአሜሪካ የሚወልዷቸው ልጆች የአሜሪካ ፓስፖርት የማግኘት መብት የሚሰጠውን በመወለድ የሚገኝ የዜግነት መብት ለማስቆም ፕሬዚዳንታዊ ትዕዛዝ እንደሚያስተላልፉ አሳውቀዋል።
በተለያዩ ምክንያቶች ተሰደው ወደ አሜሪካ የሄዱ ሰዎች የመኖሪያም ሆነ የዜግነት መብት ባያገኙም አሜሪካ ውስጥ የወለዷቸው ልጆች ዜግነትን ማግኘት ይችላሉ ታዲያ ትራምፕ ስራ ሲጀምሩ ይህንን ነው የሚሽሩት።
ሆኖም በልጅነታቸው ወደ አሜሪካ የመጡ ሰነድ የሌላቸው ስደተኞች ለመርዳት ከዴሞክራቶች ጋር እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
🇺🇸 በመወለድ የሚገኝ የዜግነት መብት የአሜሪካ ህገ መንግሥት አንቀጽ 14ን መሰረት ያደረገ ነው። '' ማንኛውም አሜሪካ ውስጥ የተወለደ ወይም ተገቢውን ግዴታዎች የተወጣ ሰው የአሜሪካ ዜጋ የመሆን ሙሉ መብት አለው '' ይላል።
በሌላ በኩል ፤ ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው የቤተሰብ አባላት ያላቸውን ጨምሮ ህጋዊ ሰነዶች ያላሟሉ ስደተኞችን ከአገር ለማባረር የገቡትን ቃል ተግባራዊ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።
" ቤተሰብ መበተታተን አልፈልግም " ያሉት ትራምፕ " ስለዚህ ቤተሰቦች የማይለያዩበት ብቸኛው መንገድ ሁሉንም አንድ ላይ ከአገር ማባረር ነው " ብለዋል።
ትራምፕ በአንድ ወቅት ለመሰረዝ ሞክረው የነበረውን ወደ አሜሪካ ብቻቸውን ለሚመጡ ህጻናት ከለላ የሰጠውን የኦባማ 'ዲፈርድ አክሽን ፎር ቻይልድ ሁድ አራይቫልስ' በተሰኘው ፕሮግራም የታቀፉትን በተመለከተ ከምክር ቤቱ ጋር አብሬ እሰራለሁ ብለዋል።
" ከዴሞክራቶች ጋር በአንድ ዕቅድ ላይ እሰራለሁ " ያሉት ትራምፕ ከነዚህ ስደተኞች መካከል ጥቂቶች ጥሩ ስራ የያዙ በንግድ ላይ የተሰማሩም አሉ ሲሉ አክለዋል።
መረጃውን ኤንቢሲን ዋቢ በማድረግ ያጋራው ቢቢሲ ነው።
#USA #MASSDEPORTATION
@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ
በብርሃን ቅፅበት ካርድዎን በእጅዎ ያስገቡ!
#ልዩ_የኤቲኤም_ካርድ #liyuatmcard #atmcard #berhanbank #bank #finance
#Stressfreebanking #bankinethiopia
ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ!
➡️ Facebook
➡️ Telegram
➡️ Instagram
➡️ Twitter
➡️ LinkedIn
➡️ YouTube
#Update
አሳድ ሞስኮ ነው ያሉት።
ላለፉት 24 ዓመታት ሶሪያን ሲገዙ የነበሩት በሽር አላሳድ በታጠቁ ተቃዋሚዎች ከመንበራቸው ከተገረሰሱ በኃላ ሀገሪቱን ጥለው መጥፋታቸው መነገሩ ይታወሳል።
አሁን ላይ ሩስያ ዜና ምንጭ ' ታስ ' እንደዘገበው በሽር አላሳድ ከነቤተሰባቸው ሩስያ፣ ሞስኮ ነው የሚገኙት።
ሩስያ ለአላሳድ እና ለቤተሰባቸው በ ' ሰብዓዊነት ምክንያት ' ጥገኝነት እንደሰጠች ተነግሯል።
የአባታቸው መሞትን ተከትሎ ስልጣን የያዙት አሳድ ለ24 ዓመታት ሶሪያን ሲገዙ ቆይተዋል።
በተለይ ከ2011 በኃላ ሀገሪቱ የለየለት እልቂት ውስጥ ገብታ ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች ሞተዋል፣ ሚሊዮኖች ሀገራቸውን ጥለት ተበትነዋል።
ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የታጠቁት ኃይሎች በከፈቱት ዘመቻ ከመንበራቸው ተነስተዋል እሳቸውና ቤተሰባቸው በሰላም ምንም ሳይሆኑ ሩስያ ገብተዋል።
ሩስያ የበሽር አላሳድ መንግሥት ዋነኛዋ ደጋፊ እንደሆነች ይታወቃል።
በሌላ በኩል ፤ የደማስቆ ነዋሪዎች ወንዶች ፣ ሴቶችና ህጻናት ሳይቀሩ የአሳድ ቅንጡ ቤተመንግስታቸው ውስጥ ገብተው እየተዟዟሩ ቤቱን ሲመለከቱ፣ ወዲያ ወዲህ ሲሉ ነው የዋሉት።
ከቤተመንግስቱ ብዙ እቃዎች ተዘርፈው መወሰዳቸውም ተሰምቷል።
ከዚህ ባለፈ ታጣቂ ተቃዋሚዎቹ እጅግ ዘመናዊ እና ቅንጡ መኪናዎች የተከማቹበትን የአላሳድ ጋራጅ እንዳገኙም ተነገሯል። (ቪድዮው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
" በኢትዮጵያ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ዕዉቅና ያላቸዉ 76 ብሔር፣ ብሔረሰቦች ተወካዮች ብቻ ናቸዉ "- የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
19ኛዉ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዛሬዉ ዕለት በአርባምንጭ ከተማ ተከብሯል።
የተሳታፊ ብሔር፣ ብሔረሰቦች ቁጥር በተመለከተ በትናትናዉ ዕለት በሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን የተሰራጨዉን መረጃ መነሻ በማድረግ ልዩ ልዩ ሃሳቦች ሲሰነዘሩ ቆይተዋል።
ይህን ጉዳይ ለማጥራት ቲክቫህ ኢትዮጵያ የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነትን ጠይቋል።
የፌዴሬሽን ምክር-ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ተረፈ በዳዳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ ለኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሐረሰቦች ሕጋዊ ዕዉቅና የመስጠት ሥልጣን ያለው የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት መሆኑን አንስተዋል።
በ19ኛዉ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በዓል ላይም በዚህ ምክር ቤት ዕዉቅና ያላቸው 76ቱ ብሔረሰቦች ተሳታፊ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች ቁጥር በተመከተ " 86 በላይ ናቸዉ " እየተባለ የሚገለፀው በተለምዶ ነዉ ያሉት አቶ ተረፈ " ሕጋዊ ዉክልና ያላቸዉ ቋንቋና ባህላቸዉ የተመዘገበላቸዉ 76 ብሔር፣ ብሔረሰቦች ብቻ ናቸዉ " ብለዋል።
" ምናልባት በቀጣይ የማንነት ጥያቄ ያላቸዉ ይኖራሉ፤ ጥያቄያቸው ተጠንቶ፣ መስፈርቱን የሚያሟሉ ከሆነ ጥያቄያቸው ታይቶ ምክርቤቱ ምላሽ ይሰጣቸዋል " ሲሉ ገልጸዋል።
ሕገ መንግስቱ የፀደቀበትን ዕለት ምክንያት ማድረግ በየዓመቱ ህዳር 29 የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን የሚከበር ሲሆን 19ኛዉን ዙር በዓል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባምንጭ ከተማ በዛሬው ዕለት ተከብሯል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች ቀን በዓል እንደሚያስተናግድም ተነግሯል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
🔈 #የዜጎችድምጽ
" ወረዳው ከነእቃዬ ሜዳ ላይ ጥሎኝ የኔን ጉዳይ ይዞ የነበረውን ዳኛ ከቤቴ አስገባው " - እንባ የሚተናነቃት ወጣት
በአዲስ አበባ አስተዳደር የካ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ቀበሌ 9/10 የምትገኝ ወጣት ከአሳዳጊ አክስቷ ጋር ትኖርበት ከነበረው የቀበሌ ቤት አሳዳጊዋ ስትሞት ከቤቱ እንድትወጣ ተደርጋ ጎዳና እንደወጣች በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል እሮሮ አሰምታለች።
" ወረዳው ከነእቃዬን ሜዳ ጥሎ የኔን ጉዳይ ይዞ የነበረውን ዳኛ ከቤቴ አስገባው " ብላለች።
ወርቅነሽ አለሙ የምትባለው ይህች ወጣት የአባቷ ታላቅ እህት ከ3 ዓመቷ ጀምሮ ከባህር ዳር ወደ አ/አ አምጥታት ነው ያሳደገቻት።
እዚሁ ቤት እስከ 2016 ዓ/ም ማለቂያ ድረስ ነበሩ።
በ2016 ዓ/ም አሳዳጊ አክስቷ ከሞትች ከ40 ቀናት በኃላ ወረዳው " ወራሽ ልጅ ስላልሆሽ ልቀቂ " ይላታል።
ጉዳዩን ይዛ ፍርድ ቤት ሄደች። ፍርድ ቤትም ሄዳ መፍትሄ አልተሰጣትም።
" ወረዳ እኔን ጠዋት በግብረ ኃይል ከነእቃዬ አውጥቶ ጥሎኝ ከሰዓት በኋላ ራሱ የኔን ጉዳይ ይዞ የነበረውን ዳኛ ቤቴ ውስጥ አስገባው " ስትል ቅሬታ አሰምታለች።
ከዚህ አለፍ ሲል ቤቱ ሁለት ክፍል ሆኖ ሳለ ወደ አራት ክፍል አስፋፍቶ ሰርቶት ዞር ብሎ የጠየቀው አካል የለም ብላለች።
ወረዳው ምን ምላሽ ሰጠ ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታውን ይዞ የወረዳ 6 ጽ/ቤት አስተዳደር ኃላፊ አቶ ምስጋናው ሂጂቱን አነጋግሯል።
ቅሬታዋ አቅራቢዋ ልጅ ከሆነች የመውረስ መብት እንዳላት አምነውበታል።
ኃላፊው ፤ " ባለመብት ናት የቀበሌ ቤት መውረስ የሚችለው ልጅ ነውና ልጅ ከሆነች መውረስ መብቷ ነው " ብለዋል።
" በሕጉ መሠረት የቀበሌ ቤት ፣ ልጅ ከሆነች የመውረስ መብቷ የተጠበቀ ነው ፤ በዚያ ደረጃ ሆኖ ከነበረ እኔ ጋ ይምጡ እናስተካክላለን ይሄ የተነሳው ጉዳይ ትክክል ከሆነ " ሲሉ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ ጉዳይ ተጨማሪ ማብራሪያ እና ግልጽነት ስለሚፈልግ የሕግ ባለሙያ አነጋግሯል።
የሕግ ባለሙያ የሆኑት አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ምን አሉ ?
- ኑዛዜውን ማጽደቅ ትችላለች። ግን የቀበሌ ቤት ላይ ተወላጆች ካልሆኑ በስተቀር ከሕግ አንጻር በባዮሎጂካል ተወላጅ ያልሆነ ልጅ የጉጂፈቻ ማስረጃ ቀደም ሲል ሊኖር ይገባል።
- ለቀበሌ ቤት የጉዲፈቻ ማስረጃ ስሌላት ውርስ ተቀባዩዋን ከሞራልና ከአስተዳደራዊ አንጻር ካልሆነ በስተቀር ከሕግ አንጻር የወረዳው አስተደዳደር ሊያስተናግዳት አይችልም።
- ከሞራል አንጻር አሳዳጊዋ ስላረፉ፣ ልጅቷ ደግሞ ተተኪ ልጅ ናት፤ በሥነ ልቦና እናትና ልጅ ሆነው አብረው ኖረዋል። የቀበሌ ቤት የሚባለው ደግሞ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች የሚኖበት ነው። ስለዚህ ከሕግ አንጻር የኑዛዜ ተቀባይ መሆን ባትችልም አንዱ ወጥቶ ሌላው የሚገባበት፣ ለዜጎች የተሰራ ቤት በመሆኑ ልትኖርበት ይገባ ነበር ከሞራል አንጻር።
- ከሕግ አንጻር በቀበሌ ቤት ላይ ኑዛዜ ማድረግ አይቻልም።
- ለምሳሌ የፌደራል ኪራይ ቤቶችን አንድ ሰው ተከራይቶ ቢኖር ሲሞት ሊናዘዝበት አይችልም። ምክንያቱም የንብረቱ ባለቤት መንግስት ነው። በመሳሳይ ሁኔታ የቀበሌ ቤቶች ውስጥ የሚኖር ሰው ሲሞት ኑዛዜ ሊያደርግ አይችልም። ኑዛዜ ማድረጉ በሕግ ውጤት አያመጣም።
- በዜጎች ንብረትና ሕይወት ላይ ውሳኔ የሚሰጡ ሰዎች (ዳኞች) ከወረዳ ጋር በመመሳጠር ክርክር በተነሳበት የመንግስት ቤት ውስጥ መግባት የሕግ ጥሰት ነው። ሕግን ያልተከተለ አካሄድ ነው። በተወሰነ ደረጃ ሙስና ተብሎ ጉዳዩን ወደ ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ብታመለክትበት ዳኛው ከኃላፊነቱ የሚነሳበት ቀጥተኛ ማስረጃ ነው የሚሆነው።
- ክርክር በተነሳበት ጉዳይ ላይ የጥቅም ግንኙነት በመፍጠር እንዲህ ማድረግ ትልቅ የዲሲፒሊን ጥፋት ነው።
- ልጅቷ ቅጹ ላይ አለች፣ ደባል ናት፣ የቤተሰብ አባል ናት ቀጥተኛ ልጅ ባትሆንም፣ የቀበሌ ቤቶች ደግሞ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ሰዎቸ ነው የተዘጋጁት፣ ሜዳ ላይ መጣል የለባትም ብሎ የወረዳው አስተዳደር ወስኖ ወይ በዚያው ቤት ሊያስቀጥላት ይገባል የቀበሌ ቤቱ የሚፈርስ ከሆነም ምትክ የመንግስት ቤት እንድታገኝ ሁኔታዎችን ማመቻቸት አለበት።
- በህሊና ፍርድ ወይ አስተዳደራዊ በሆነ መንገድ የወረዳው አስተዳደር መፍትሄ ሊሰጣት ይገባል።
ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-12-08
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" አሳድ የሩስያን ድጋፍ በማጣታቸው ሶሪያን ለቀው ሸሽተዋል " - ትራምፕ
ተመራጩ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ የሶሪያው ፕሬዜዳንት በሽር አላሳድ የሩስያን ድጋፍ በማጣታቸው ሀገራቸውን ጥለው መሸሻቸውን ገለጹ።
ይህን ያሉት ' ትሩዝ ' በሚሰኘው ማህበራዊ ሚዲያቸው ላይ ነው።
" አሳድ ሄዷል " ያሉት ትራምፕ " ጠባቂው በቭላድሚር ፑቲን የሚመራው ሩስያ፣ ሩስያ፣ ሩስያ ! ከዚህ በላይ እሱን (አሳድን) ለመጠበቅ ፍላጎት አልነበረውም " ሲሉ ገልጸዋል።
የትራምፕ ሀገር አሜሪካ በርካቶች ባለቁበት የባለፉት 13 ዓመታት የሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት ሶሪያ ውስጥ ናት።
ሀገሪቱ ዋና አላማ ብላ የገባችው ' ISIS 'ን ለማፅዳት ቢሆንም በቀድሞ ፕሬዜዳንት ኦባማ ሰዓት " አሳድ መሄድ አለበት / ከአገዛዙ መወገድ አለበት " የሚል አቋም በይፋ ይንፀባረቅ ነበር።
እኤአ በ2013 ኦባማ እስራኤልን ሲጎበኙ ከቤኒያሚን ኔታንያሁ ጋር ሆነው " አሳድ መሄድ አለበት አገዛዙ ማብቃት አለበት " ሲሉ ተናግረዋል።
ከዚህም ባለፈ ፤ የአሳድን ተቃዋሚዎች በቁሳቁስ እና በስልጠና ድጋፍ ታደርግላቸው ነበር።
የፑቱን ሀገር ሩስያ የአላሳድን መንግሥት የምትደግፍ ሲሆን የአገዛዙ ጠላቶች ላይ እርምጃዎችን ስትወስድ ነበር።
#Syria
@tikvahethiopia
#SYRIA : የ24 ዓመታት የአልአሳድ አገዛዝ እንዴት ተገረሰሰ ?
በፕሬዜዳንት በሽር አላሳድ አገዛዝ ላይ እ.ኤ.አ. በ2011 / ከዛሬ 13 ዓመት በፊት ነው ህዝባዊ አመጽ የተነሳው።
ከዛ ጊዜ አንስቶ ሀገሪቱ መረጋጋት አልቻለችም።
ታጣቂዎች በየቦታው ተነሱ ሀገሪቱ የከፋ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ገባች።
ይኸው 13 ዓመታት በሆነው የማያባራ እልቂት በርካታ ህጻናት፣ እናቶች፣ ወጣቶች ፣ አዛውንቶች ተቀጥፈዋል።
ሀገሪቱ እንዳልነበር ሆና ወድማለች።
ሶሪያ ዳግም ከወደቀችበት አዘቅት ለመውጣት ዘመናት የሚያስፈልጋት ሆናለች።
በዚህ 13 ዓመታትን በቆየው የእርስ በርስ ጦርነት የውጭ ሀይሎች እነ ሩስያ፣ ኢራን፣ አሜሪካ ፣ ቱርክ ... እጃቸው አለበት።
የውጭ ኃይሎቹ እንደግፈዋለን የሚሉትን ኃይል በማገዝ እልቂቱን እንዳያባራ አድርገዋል።
ምንም እንኳን በሀገሪቱ ያሉ የታጠቁ ተቃዋሚዎች የአላሳድን አገዛዝ ለመገርሰስ ሲዋጉ ፣ የተለያዩ ቦታዎችን ሲይዙ ለዓመታት ቢቆዩም የሰሞኑን ከፍተኛ ፍጥነት የታየበት ድንገታዊ ጥቃት ግን " ድራማዊ " ተብሎለታል።
ካለፈው ሳምንት አንስቶ ተጣቂዎቹ በተለያየ የሀገሪቱ አቅጣጫ በከፈቱት መጠነ ሰፊ ጥቃት የሶሪያ ጦር ፈራርሷል።
ወታደሮች ሀገር ጥለው ሸሽተዋል ፤ የአላሳድ መቀመጫ ደማስቆን ጨምሮ ትልልቅ እና ቁልፍ የሚባሉ ከተሞች በፍጥነት በታጠቁት ተቃዋሚዎች እጅ ወድቀዋል።
የአላሳድ ደጋፊ ከሆኑ ሀገራት አንዷ ሩስያ በጦር አውሮፕላኖች ታግዛ ጭምር ለአላሳድ ድጋፍ ብታደርግም ፤ ኢራንም አለሁ " አግዛለሁ " ብትልም አገዛዙን ከውድቀት አልታደጉም።
ተንታኞች የአሳድ ጦር ኃይሎች በዝቅተኛ ደሞዝ እና በመኮንኖች መካከል በተንሰራፋው ሙስና የተነሳ የውግያ ሞራላቸው ተንኮታኩቷል ብለዋል።
ምንም እንኳን በቅርቡ ለሰራዊቱ የ50 በመቶ የደመወዝ ጭማሪ ቢደረግም ይህ ነው የሚባል ለውጥ ሊፈጠር ባለመቻሉ አገዛዙ ፈርሷል።
በአላሳድ ስር ሲዋጉ የነበሩ ወታደሮች ልብሳቸውን እያወለቁ ሲቪል መስለው ሲሸሹ ታይተዋል።
አላሳድም ሀገር ጥለው ጥፍተዋል። የት እንዳሉ አይታወቅም።
ቀጣዩ የሶሪያ ዕጣፋንታ ምንድነው ? ጁላኒ ማናቸው ?
አሁን ወደፊት ወጥተው የሚታዩት የቀድሞ ' አል-ኑስራ ' መሪ አሁን ደግሞ ሃያት ታህሪር አል-ሻም (ኤችቲኤስ) የተባለው የታጠቀ ኃይል መሪ አቡ መሀመድ አል ጁላኒ ናቸው።
በበላይነት የታጣቂዎቹን እንቅስቃሴ እያስትባበሩ ያሉት እሳቸው እንደሆኑ ተነግሯል።
ኑስራን ከመመስረታቸው በፊት ኢራቅ ውስጥ ለ #አልቃይዳ ተዋግተዋል። ወደዛ የሄዱት የአሜሪካን ወራር ተከትሎ ነው።
እኚህ ሰው ለ5 ዓመታት በአሜሪካ እስር ቤት አሳልፈዋል።
የአላሳድን አገዛዝ ለመጣል እንቅስቃሴ ሲጀመር በአልቃይዳው መሪ አቡ ባከር አል ባግዳዲ አማካኝነት የአልቃይዳ ህዋስ እንዲኖር ለማድረግ ታስበው ወደ ሶሪያ ተልከዋል። (IS በኢራቅ በኃላ ISIS የሆነው)
አሜሪካ በ2013 አል-ጁላኒን በአሸባሪነት ፈርጃቸዋለች።
እ.ኤ.አ. 2016 ላይ ከአልቃይዳ መፋታታቸው ከተነገር በኃላ ሃያት ታህሪር አል-ሻም የተሰኘውን ቡድን ይዘው መጥተዋል።
ከአልቃይዳም ሆነ ከሌላ ቡድን መፋታታቸው ተነገረ በኃላ የሶሪያ ኢስላሚክ ሪፐብሊክን የመመስረት ዓላማ አንግበው አላሳድን ሲዋጉ ቆይተዋል።
ይኸው የጁላኒ ቡድን አሁን የአላሳድን አገዛዝ በመጣል ትልቁን ድርሻ እንደያዘ ነው የተነገረው።
አቡ መሀመድ አል ጁላኒ ከአላሳድ መገርሰስ በኃላ በሰጡት ቃል ፤ ሁሉም የመንግስት ተቋማት በይፋ ተላልፈው እስኪሰጡ / ርክክብ እስኪደረግ ድረስ በአላሳድ ጠቅላይ ሚኒስትር ቁጥጥር ስር እንደሚቆዩ ይፋ አድርገዋል።
ጠ/ሚኒስትር መሀመድ ጋዚ አል ጃላሊ በሰጡት መግለጫ ፥ በደማስቆ ቤታቸው እንደሚቆዩ እና የህዝብ ተቋማት ስራቸውን እንዲቀጥሉ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በሽር አላሳድ ማን ናቸው ?
° እድሜያቸው 59 ነው። የተወለዱት ደማስቆ።
° ከህክምና ትምህርት ቤት ተመርቀዋል። ለንደን ውስጥ በኦፕታሞሎጂ ስፔሻላይዝድ አድርገዋል።
° የወንድማቸውን በመኪና አደጋ መሞት ተከትሎ ወደ ሶሪያ መጥተዋል።
° እኤአ 2000 ላይ ነው የአባታቸውን ሃፊዝ አላሳድን መሞት ተከትሎ ወደ አገዛዝ የመጡት። አባታቸው ከ1971 አንስቶ ሀገሪቱን ሲመሩ ነበር።
° ወንድማቸው ባሴል አላሳድ የአባታቸውን ስልጣን ይረከባሉ ተብሎ ቢጠበቅም በመኪና አደጋ በመሞታቸው በሽር አላሳድ ስልጣኑን መያዝ ችለዋል።
° የስልጣን ዘመናቸው ከ2011 በኃላ በጦርነት ተሞላ ነው።
አሁን ከሀገር ፍረጥጠዋል የተባሉት አላሳድ በበርካታ የየሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ ኬሚካል ጦር መሳሪያ በመጠቀም፣ እና በሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ይከሰሳሉ።
🚨በሶሪያ የ13 ዓመታት የእርስ በርስ ጦርነት ከ350 ሺህ በላይ ሰዎች እንደሞቱ ሪፖርቶች ያሳያሉ። ሚሊዮኖች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ተሰደዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃዎቹን ከሮይተርስ ፣ አልጀዚራ ፣ ዋሽንግተን ፖስት ፣ከፍራንስ 24 ነው አሰባስቦ ያዘጋጀው።
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#MPESASafaricom
አሜሪካ ያሉ ወዳጅ ዘመዶቻችን በRemitly በኩል ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ ሲልኩ እኛ በM-PESA ተቀብለን በተጨማሪ 5% የገንዘብ ሽልማት እና 1ጊ.ባ ነጻ የኢንተርኔት ዳታ እንበሸበሻለን!
የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉/channel/Safaricom_Ethiopia_PLC
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#FurtherAheadTogether
#BREAKING🚨
የበሽር አላሳድ አገዛዝ ተገረሰሰ።
የሶሪያው ፕሬዜዳንት በሽር አላሳድ አገዛዝ ወደቀ። እሳቸውም ሀገር ለቀው ጠፍተዋል።
የታጠቁ የሶሪያ ተዋጊዎች የፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድን የ24 ዓመት አገዛዝ ለመደምሰስ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄዱ ነበር።
በተለይም በሰሜናዊ ክፍል የሚገኙ የታጣቁ ተቃዋሚዎች ከረዥም ዓመታት በኋላ የአገሪቱ ጦር ላይ ድንገታዊ ጥቃት ከከፈቱ በኃላ ብዙ ቦታዎችን በፍጥነት ይዘዋል።
ከሳምንት በፊት ነው አሌፖን ዘልቀው የገቡት።
ከዛ በኃላ በመላ ሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የመንግስት መከላከያዎች በአስደናቂ ፍጥነት ፈራርሰዋል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች የአማጽያኑን ምት መቋቋም ከብዷቸው ድንበር አቋርጠው ኢራቅ ለመግባትና ጥገኝነት ለመጠየቅ ተገደዋል።
ተቃዋሚዎቹ በቀናት ውስጥ እጅግ በርካታ ቁልፍ ከተሞችን እና ቦታዎችን ከአላሳድ አገዛዝ ነጻ ያደረጉ ሲሆን ለሊቱን የአሳድ መቀመጫ ወደ ሆናችው ደማስቆ መግባታቸው ታውቋል።
አላሳድ ከደማስኮ ወጥተው ሄደዋል ተብሏል።
የፕሬዜዳንቱን ከደማስቆ መልቀቅ ሁለት ከፍተኛ የጦር አመራሮች ለሮይተርስ አረጋግጠዋል።
አሁን ላይ አሳድ የት እንደገቡ የሚታወቅ ነገር የለም።
የታጠቁት ተቃዋሚዎች ባወጡት መግለጫ ፤ " ጨቋኙ በሽር አላሳድ ከደማስቆ ለቀው ሄደዋል " ብለዋል።
" ደማስቆን ከጨቋኙ በሽር አላሳድ ነጻ አውጥተናል " ሲሉም ገልጸዋል።
በሽር አላሳድ ሀገሪቱን ለቀው መጥፋታቸውንም አሳውቀዋል።
ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያውንም ተቆጣጥረውታል።
አንዳንድ ቪድዮዎች እንዲሁም ሮይተርስ የአይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው በደማስቆ ጎዳናዎች ሶርያውያን ወጥተው ' ነጻነት ! ነጻነት ! ' እያሉ መፈክር ሲያሰሙ ደስታቸውን ሲገልጹ ታይተዋል።
እነ ሩስያ ፣ ኢራን ፣ አሜሪካ እና ቱርክ ?
የአገዛዙ ዋነኛ አጋር የሆኑት ሩሲያ እንዲሁም ኢራን ለአሳድ ቀጣይነት ያለውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ሲያሳውቁ ቢሰነብቱም አገዛዙን ከመፍረስ አልታደጉም።
ሩስያ በዩክሬን በሚያደርገው ጦርነት የተጠመደች ሲሆን፣ ኢራን ደግሞ እስራኤል በሊባኖስ ሔዝቦላህ ላይ በከፈተችው ዘመቻ ምክንያት ተዳክማለች።
ጦርነቱ ሲባባስ ሞስኮ የሩሲያ ዜጎች አገሪቱን ለቅቀው እንዲወጡ ጥሪ ስታቀርብ ነበር።
በሶሪያ የረጅም አመታት የእርስ በርስ ጦርነት ዋና ተዋናይቷ አሜሪካም ብትሆን ሁኔታውን አይታ ዜጎቿን " በደማስቆ በረራዎች እስካሉ ድረስ " ሶሪያን ለቅቀው እንዲወጡ ስትጮህ ነበር።
ቱርክ በሶሪያ ያሉ አንዳንድ የታጠቁ ተቃዋሚ ቡድኖችን ትደግፋለች።
የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ለወራት አሳድን ከተቃዋሚዎች ጋር ፖለቲካዊ መፍትሄ ላይ አንዲደርሱ ግፊት ሲያደርጉ ነበር።
ፕሬዜዳንቱ የተቃዋሚዎችን የቅርብ ጊዜ ግስጋሴ እንደሚደግፉ ተናግረው " አሳድ ጥሪዬን ቢቀበል ኖሮ ይህ አይከሰትም ነበር " ብለዋል።
#ሶሪያ : እ.ኤ.አ. ከ2011 ጀምሮ በተቃውሞ ስትናጥ ከቆየች በኃላ በከፋ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ የምትገኝ ሲሆን በዚህም እጅግ በርካታ ሰዎች አልቀዋል። ሀገሪቱ እንዳልነበረ ሆናለች። ለሀገሪቱ እንዲህ መሆን የውጭ ኃይሎች አገዛዙን እና አማጽያንን በመደገፍ ረገድ ትልቅ ድርሻ አላቸው።
መረጃው ከአልጀዚራ፣ ሮይተርስ እንዲሁም ቢቢሲ የተሰባሰበ ነው።
@tikvahethiopia
" እስካሁን ከ50 በመቶ በላይ በሚሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ኃይል መመለሱን " - የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል
በመላው ሀገሪቱ ከተቋረጠው ኃይል ከግማሽ በላይ የሚሆነው ወደነበረበት እየተመለሰ መሆኑን የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታወቀ።
ማዕከሉ እንዳስታወቀው ፦
- በአዲስ አበባ 85 በመቶ በሚሆነው በአብዛኛዎቹ አካባቢ ፣
- በአዳማ፣
- በሀዋሳ፣
- በጅማ፣
- በአርባምንጭ፣
- በወላይታ ሶዶ፣
- በሻሸመኔ፣
- በወልቂጤ፣
- በመቐለ፣
- በዓድዋ፣
- በአላማጣ፣
- በዲላ፣
- በቦንጋ፣
- በሚዛን እና ሀገረማርያም ኃይል ተመልሶ ተገናኝቷል።
እስካሁን ከ50 በመቶ በላይ በሚሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ኃይል መመለሱን የገለፀው ማዕከሉ በቀሪዎቹ አካባቢዎች መልሶ ለማገናኘት ርብርቡ መቀጠሉን ገልጿል።
የተፈጠረው ችግር ሙሉ በሙሉ አለመፈታቱ የተገለጸ ሲሆን ችግሩ እስኪቀረፍ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቋል።
#EEP
@tikvahethiopia
" የወንጀሉ ተጠርጣሪ እራሷ አሰሪዋ ሆና ነው የተገኘችው " - ፖሊስ
የግድያ ወንጀል እንደፈፀመች አምና በፖሊስ ቁጥጥር ሥር በነበረች የቤት ሰራተኛ ላይ በተደረገው እውነትን የማፈላለግ የምርመራ ሥራ የወንጀሉ ተጠርጣሪ አሰሪዋ ሆና እንደተገኘች የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
ህፃን ሰላማዊት አስፋው የ12 ዓመት ታዳጊ ስትሆን ነዋሪነቷም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሐድያ ዞን ነው ።
በሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም የአጎቷ ልጅ የሆነችው ወ/ሮ ዓለምፀሐይ ስላሴ ለህፃኗ ወላጆቿ እያስተማረች ልታሳድጋት ቃል በመግባት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው አለም ባንክ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መኖሪያ ቤቷ ይዛት በመምጣት መኖር ትጀምራለች፡፡
መስከረም 3ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5 ሰአት ሲሆን ለግዜው የፀቡ መነሻ ባልታወቀ ምክንያት ህፃን ሰላማዊት አስፋው ህይወቷ ያልፋል፡፡
ህፃኗን እያስተማረች ልታሳድጋት ያመጣቻች ተጠርጣሪ ታዳጊዋን የተለያየ የሰውነት ክፍሏን በእንጨት በመደብደብ ከ20 ቦታ በላይ ጉዳት በማድረስ እና አንገቷን በማነቅ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓን የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል፡፡
በህፃኗ ህልፈተ-ህይወት ተጠያቂ ላለመሆን ያሰቡት ተጠርጣሪዋ ግለሰብ ከባለቤቷ ጋር በመነጋገር በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ በመስራት ላይ የምትገኝ የ17 ዓመት ዕድሜ ያላት ተስፋነሽ ጀባኔን ህፃኗን በድንገት እንደገደለቻት ለፖሊስ ቃል እንድትሰጥና ለውለታዋም ደሞዟን በእጥፍ እንደሚጨምሩላት በተለያዩ መደለያዎች ያሳምናሉ።
በወንጀሉም ጉዳይ ጠበቃ እንደሚቀጥሩላት ካሳመኗት በኋላ ለፖሊስ የሰጠችው ቃል የወንጀል ድርጊቱን እንደፈፀመች የሚገልፅ ነበር፡፡
ሆኖም ፖሊስ የተስፋነሽ ጀባኔን ቃል መነሻ በማድረግ የምርመራ ስራውን በማስፋት ሂደት ለጊዜው ተጠርጣሪ የሆነችው የቤት ሰራተኛ " እኔ ነኝ የገደልኳት " ብትልም አንዳንድ አጠራጣሪ ነገሮች መኖራቸውን የደረሰበት ፖሊስ ባደረገው ጥልቅ እውነትን የማፈላለግ የምርመራ ሥራ የወንጀል ድርጊቱን የቤት ሰራተኛዋ እንዳልፈፀመች እና ልታሳድግ እና ልታስተምራት ባመጣቻት ግለሰብ በደረሰባት ድብደባ ህፃን ሰላማዊት አሰፋ ህይወቷ እንዳለፈ ይደርስበታል።
የምርመራ ሂደቱ ቀጥሎ ተጠርጣሪዋ ግለሰብም የወንጀል ድርጊቱን መፈፀሟን አምና በመኖሪያ ቤቷ ድርጊቱን እንዴት እንደፈፀመች መርታ ማሳየቷን የአዲስ አበባ ፓሊስ አስታውቋል።
ተጠርጣሪ ግለሰቧና ባለቤቷ ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ፍ/ቤት እንዳዘዘ ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል፡፡
ወንጀል ፈጽሞ ከህግ ተጠያቂነት የሚያመልጥ እንደማይኖር ያስታወቀው ፖሊስ ንዴትን በመቆጣጠርና በትዕግስት የወንጀል ድርጊትን መከላከል እንደሚቻል አስታውቆ ከቅድመ መከላከሉ ባሻገር ወንጀል ሲፈፀም በፍጥነት ለፖሊስ ማሳወቅ እንደሚገባም አስታውቋል፡፡
(የአዲስ አበባ ፖሊስ)
@tikvahethiopia
" የኮሚሽነር ትዕዛዝ ለሌሎችም ከተሞች ምሳሌ ነው ! " - ነዋሪዎች
ከጫኝ እና አውራጆች ጋር በተያያዘ የድሬዳዋ ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ለከተማው ፀጥታ አመራሮች የሰጡት ትዕዛዝ እጅግ እንዳስደሰታቸው ፤ ይህ ትልቅ ተሞክሮ በሌሎች ከተሞችም ተፈጻሚ ሊሆን የሚገባው እንደሆነ የተለያዩ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
የኮሚሽነሩን መረጃ ተመልክተው ቃላቸውን ከሰጡን ነዋሪዎችና የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት መካከል የአዲስ አበባ፣ ሸገር ሲቲ ፣ ሀዋሳ፣ አዳማ ፣ ጅማ ... የሌሎችም ይገኙበታል።
ነዋሪዎቹ " የገዛ እቃችንን ለማውጣት እና ለማስገባት የሰፈር ጫኝ እና አውራጆች ፍቃድ ማግኘት አለብን ይህ ምን አይነት ነገር ነው ? " ሲሉ ጠይቀዋል።
የድሬዳዋ ተሞክሮ ወደ ሌላም ቦታ መሄድ እንዳለበት ገልጸዋል።
" የገዛ እቃችንን ማስገባት እና ማስወጣት ፈተና ነው ፤ ለትንሽ እቃ እንኳን የሚጠይቁት ክፍያ ደግሞ የሚያስደነግጥ ነው ፤ አንዳንዴ እኮ ከእቃውም በላይ ይጠራሉ " ብለዋል።
" ሲፈልጉ ' ያለኛ እቃው አይገባም ' ብለው ያስፈራራሉ ሲያሻቸው ለፀብ ይጋበዛሉ ያለነሱ ሰው ያለ አይመስልም " ሲሉ ተናግረዋል።
ሰው በገዛ እቃው ስንት ሰዓት ሙሉ ተከራክሮ ትንሽ ይቀነስለትና ብሩን ይሰጣል። ይህ " ክፍያ ሳይሆን ዝርፊያ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
አንዳንዴ ህግ እንኳን እነሱ ላይ የሚሰራ አይመስልም እንደልባቸው ገንዘብ ይጠይቃሉ ኧረ የህግ ያለህ ብለን የሚመለከታቸውን ስንጠይቅ " ተስማሙ " ይሉናል ብለዋል።
" ሰዎች ከፍራቻ የተነሳ ለሊት እቃ ለማስገባት ይገደዳሉ ሰዎቹ አንዳንዴ ለሊት ሁሉ ተጠራርተው ይመጣሉ ፤ አንደንዴ ደግሞ ለሊት እቃ ማስገባት አይቻልም ይባላል " ሲሉ ችግሩን አስረድተዋል።
" ዛሬ ሰዎቹን እንቢ ብንላቸው ነገር መውጫና መግቢያ ስለሚያሳጡን ትንሽ ብርም ቢሆን አስቀንሰን እቃውን እናስገባለን " ሲሉ አክለዋል።
ይህ ቀላል ነገር አይደለም ስቃዩን እና እንግልቱን ያየ ብቻ ነው የሚያውቀው ብለዋል።
" ማንኛውም ሰው የገዛ እቃውን ቢፈልግ በራሱ ሰው ካስፈለገ እና ከፈቀደ አቅሙ በሚፈቅደው ተደራድሮ በጫኝ እና አውራጅ ማስወረድ መቻል አለበት " ሲሉ አክለዋል።
" የገዛ እቃችንን ለማስገባት የሰፈር ጎረምሳ ፍቃድ አያስፍልገንም ይህንን ማስከበር ያለበት የፀጥታው አካል ነው " ብለዋል።
ድሬዳዋ ለዚህ የዜጎች የሁል ጊዜ ስቃይ እና ሮሮ የሰጠችው መፍትሄ እጅግ ትልቅ ነው ሲሉ አወድሰዋል።
የድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ከፀጥታ ኃይል አመራሮች ጋር በነበራቸው ምክክር ፤ ህዝቡ በጫኝ እና አውራጅ የሚያየው ስቃይ ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዋል።
" ሰፈር ላይ አንድም ጫኝ እና አውራጅ የሚባል አደረጃጀት የለም ፤ ከአሁን በኃላ ሰፈር ላይ ቁጭ ብሎ ሰው ቤት ሲቀይር ጫኝ አውራጅ ብሎ የሚከተል ጎረምሳ እንዳይኖር " ሲሉ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።
" እኔ ማህበር ነኝ እኔ እንደዚህ ነኝ " የሚሉ ማን እንካን እንዳደራጃቸው የማይታወቁ ናቸው ብለዋል።
ሰው በፍርሃት እየኖረ እንዳለ በመሆኑም አንድም ጫኝ እና አውራጅ የሚባል ነገር እንዳይኖር ሰው ከፈለገ በራሱ ካልፈለገ ሰው ጠርቶ ተደራድሮ በሚችለው ማስወረድ እንደሚችል ገልጸዋል።
ገና ለገና ቤት ሲቀየር ሰው እዛ ጋር መጥቶ የሚያወርደውን ነገር ታሳቢ ተደርጎ ሰው የሚደራጅበት ስራ ትክክል እንዳልሆነ አስገንዝበዋል።
ጫኝና አውራጅ ጣጣው በጣም ብዙ እንደሆነም ተናግረዋል።
#TikvahEthiopiaFamily
@tikvahethiopia
#TecnoAI
ውስብስብ ስራዎችን በቀላል እና በአጭር ትዕዛዝ ጥንቅቅ አድርጎ መከወን፣ ብዙ ክህሎቶችን በአንድ ቦታ በቀላሉ ማግኘት፣ አጅግ የፈጠነ ምላሽ ላዘዙት እና ለጠየቁት ስራ ወይንም ጥያቄ በሰክንዶች ፍጥነት ማግኘት፡፡ እነዚህ የአዲሱ ቴክኖ ኤ አይ መገለጫዎች ናቸው።
ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመከተል የቴክኖ ቲክቶክ ገጽ ፎሎው በማድረግ እና Bio ላይ ያለውን ሊንክ ተጭነው በመመዝገብ ታህሳስ 10 በስካይላይት ሆቴል በሚካሄደው የሀገራችን ትልቁ የኤ አይ ሁነት ላይ ይሳተፉ፡፡
tecnoet" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@tecnoet
@tecno_et @tecno_et
#ድሬዳዋ
" አንድም ጫኝ እና አውራጅ የሚባል ነገር እንዳይኖር። ነግሬያችኃለሁ !! " - ኮሚሽነር ዓለሙ
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ዓለሙ መግራ ድሬ ውስጥ ሰዎች ቤት ሲቀይሩ " ጫኝ አውራጅ ነን እያሉ የሚከተሉ ጎረምሶች እንዳይኖሩ " ሲሉ ትዕዛዝ አስተላለፉ።
ይህን እጅግ ጠንካራ ትዕዛዝ የሰጡት ከከተማውን የፀጥታ አመራሮች ጋር በመከሩበት ወቅት ነው።
በህዝብ ላይ እንግልትና ዘረፋ በሚፈፅሙ ጫኝና አውራጆች ላይ የተጠናከረ እርምጃ ይወሰዳል ተብሏል።
ኮሚሽነር ምን አሉ ?
" ሰፈር ላይ ቁጭ ብሎ ሰው ቤት ሲቀይር ጫኝ አውራጅ ብሎ የሚከተል ጎረምሳ እንዳይኖር።
በየቀጠናችን ያለው የጫኝ አውራጅ ስቃይ ህዝቡን ብታዩ አንድም ጫኝ እና አውራጅ የሚባል አደረጃጀት የለም።
ይሄን ያደራጀ ሰው ካለ ኃላፊነቱን አናውቀውም።
አንድም ጫኝ እና አውራጅ በየትኛውም ቀጠና የውሃ ፋብሪካ ምናም ካልሆነ በስተቀር ሰፈር ላይ ቁጭ ብሎ ሰው ቤት ሲቀይር ጫኝ አውራጅ ብሎ የሚከተል ጎረምሳ እንዳይኖር።
ይሄ ከተገኘ እወቁ ! አንድም ቦታ ሰውዬው ሲፈልግ ተሸክሞ ያውርድ ሲፈልግ ይስበረው።
በቀደም አንዱ መጥቶ ነገረኝ ትንሽ እቃ ነው በዳማስ ሄዶ ቀስ ቀስ እያለ አወረደ ... ከዛ ሮጠው መጡና አንኳኩ ' ክፈቱ ' አሉ ግር ብለው ገቡ ፤ እቃው ወርዷል ከዛ ' ስጡን (ብር) ' አሉ ለምን ? ' የደንቡን ' የምን ደንብ ? እኛ አውርደናል እቃችንን አላቸው ' ሊሰጠን ይገባል አታውቅም እንዴ ይሄ የሰፈሩ ደንብ ነው ' አሉ። ሰውዬው ወደ ፖሊስ ሲደውል ከግቢ ወጥተው በር ላይ ቁጭ አሉ። ትንሽ ሲቆይ አንድም ሁለትም እየሆኑ ሄዱ።
እኚህ ወጣቶች ሌላ ቀን ወንጀል ከመስራት ወደኃላ አይሉም። ለዚህ ነው ሰግቶ የነገረኝ።
ሰው በፍርሃት ነው ያለው።
አይቻልም አንድም ጫኝ እና አውራጅ የሚባል !! ነግሬያችኃለሁ።
ቤት ሲቀየር ገና ሰው እዛ ጋር መጥቶ የሚያወርደውን ነገር ታሳቢ ተደርጎ ነው ሰው የሚደራጀው ስራ ?
አይቻልም !
ብሎኬት ማውረድ ከፈለገ ሰውየው ቤት ሲሰራ እዛው ጋር የሚሰሩትን ሰዎች ማስወረድ ይችላል ፤ ሌላ ሰው ጠርቶ ዋጋ ተደራድሮ እሱ ባለው ዋጋ ማስወረድ ይችላል አለቀ።
' እኔ ማህበር ነኝ ፤ እኔ እንደዚህ ነኝ ' ማን እንዳደራጃቸው የማይታወቁ።
አንድም እንዳይኖር ይሄን ሰፈራችሁ ላይ አወያዩ ፤ ማህበረሰቡ ይሄን ይወቅ ለናተ መረጃ ይስጣችሁ። ሰፈር መድረስ ማለት ይሄ ነው።
ጫኝ እና አውራጅ ጣጣው በጣም ብዙ ነው " ብለዋል።
ይሄ የጫኝ እና አውራጅ ስቃይ የድሬዳዋ ብቻ አይደለም። በአዲስ አበባ በየሰፈሩና በክልል ከተሞች ተመሳሳይ ነው።
ገና ሰው እቃ ይዞ ሲመጣ " እኛ ካላወረድን ማንም ማውረድ አይችልም " በሚል አምባጓሮ የሚፈጡ አሉ።
አውርዱ ሲባሉ ደረታቸውን ነፍተው የሚጠሩት ብር ደግሞ አስደንጋጭ ነው። ሰው በስንት ድካም ገንዘቡን እንደሚያገኝም አይረዱም።
ሰው ከፍራቻ የተነሳ በስንት መከራና ጭቅጭቅ ከፍተኛ ዋጋ ከፍሎ እቃውን ያስወርዳል። " ነገ የት እኖራለሁ " ብሎ በመፍራት።
እራሱና ቤተሰቦቹ፣ ጓደኞቹ በጋራ የገዛ እቃቸውን እንዳያወርዱ ዛቻ ሁሉ ሊፈጸምባቸው ይችላል።
ይህንን ስርዓት አልበኝነትና ድንፋታ እንዲያስቆሙ የሚጠሩ አንዳንድ የፀጥታ አባላት ነገሩን ለማስተካከል እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ የሚሉት ' ከነሱ ጋር ተስማሙ ' ነው።
ሰው ከፍራቻ የተነሳ ለሊት እቃውን ይዞ ይገባል። በገዛ ሀገሩ በገዛ ከተማው በገዛ እቃው ተሳቆ ነው የሚኖረው። ስቃዩ ብዙ ነው !
#TikvahEthiopiaFamily
#DirePolice #ድሬ
@tikvahethiopia
🔈#የተማሪዎችድምጽ
🔴 " ስኮላርሺፕ እና የውጭ ስራ እድሎች ኦርጅናል ዲግሪ ባለመስጠታቸው ምክንያት እያመለጠን ነው " - ተመራቂ ተማሪዎች
🔵 " ዲግሪያቸውን መስጠት ያልተቻለው ዩኒቨርሲቲው ላይ ባለ የበጀት እጥረት ምክንያት ነው " - የዩኒቨርሲቲው አመራር
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ከተመሰረተበት 1999 ዓ/ም ጀምሮ ላለፉት አመታት ላስመረቃቸውን ተማሪዎች ኦርጂናል ዲግሪ ባለመስጠቱ በርካታ ተመራቂ ተማሪዎች የስኮላርሺፕ እና የውጭ የስራ እድሎች እያመለጧቸው መሆኑን ቅሬታቸውን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሰምተዋል።
ተመራቂ ተማሪዎቹ ሲመረቁ የወሰዱት ጊዜያዊ (Temporary) ዲግሪ ሲሆን አስፈላጊውን የኮስት ሼሪንግ ክፍያ እና የአገልግሎት ጊዜያቸውን በመፈጸም ኦርጅናል ዲግሪያቸውን ከዩኒቨርሲቲው ቢጠይቁም በየጊዜው " ይሰጣችኋል " ከማለት ውጪ ምንም ምላሽ አላገኘንም ብለዋል።
" ኦርጅናል ዶክመንት አሳትሙልን ስንል ' ይታተማል ' ይባላል ግን መቼ የሚለው አይመለስም " ሲሉ ነው የገለጹት።
አክለውም " በቅርብ የተመሰረቱ ዩኒቨርሲቲዎች እየሰጡ ነው ለሚዛን ቴፒ ከባድ ያደረገው ምንድነው?በቂ የሚሉት ምክንያት የላቸውም ምክንያታቸው ለእኛም ግራ አጋብቶናል " ብለዋል።
ተመራቂ ተማሪዎች የቴሌግራም ግሩፕ በመክፈት እና ፊርማ በማሰባሰብ ዩንቨርስቲውን በተደራጀ መልኩ ጥያቄያቸውን ለማቅረብ እያሰቡ መሆኑን ነግረውናል።
የዩንቨርስቲው ምን ምላሽ ሰጠ ?
ኦርጅናል ዲግሪያቸውን ለተመራቂዎች አሳትሞ መስጠት ያልተቻለው በዩኒቨርሲቲው ከባድ የሚባል የበጀት እጥረት በመኖሩ መሆኑን ስሜ አይጠቀስ ያሉ የዩኒቨርሲቲው አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ነገር ግን ዩኒቨርሲቲው በዚህ ዓመት እስከ 2002 የተመረቁ ተመራቂዎችን ዲግሪ ለመስጠት ማቀዱን እና በ2018 በጀት አመት ደግሞ የቀሪ ተማሪዎችን ለመስጠት በእቅድ መያዙን ገልጸዋል።
ወደማተሚያ ቤት የተላከው እስከ 2002 ከተመረቁት መካከል የግማሹ ተመራቂዎች ብቻ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
" ከሁለት ወይም ሦስት ወር በኋላ እስከ 2002 ያሉ የመደበኛ፣የማታ እና የክረምት (Summer) ተመራቂዎች ይወስዳሉ ብዬ አስባለሁ እስካሁን ያልተሰጣቸው ዩኒቨርስቲው ላይ ባለ የበጀት እጥረት ምክንያት ነው አሁን ለማተሚያ ቤት ከ175 ሺ ብር በላይ ቅድመ ክፍያ ከፍለን እንዲታተምላቸው ተልኳል " ብለዋል።
ቀሪ ተማሪዎች በምን ያህል ጊዜ ይወስዳሉ ? ስንል ላነሳንላቸው ጥያቄም " አለን በምንለው በጀት አጣበን የሚቀሩትን እንሰጣለን ብዬ አስባለሁ የሚከብደን አይመስልኝም " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ሃላፊው ዩኒቨርስቲው ኦርጂናል ዲግሪ ያልሰጣቸው አጠቃላይ ተመራቂ ተማሪዎች ቁጥር ምን ያህል መሆኑን ከመናገር ተቆጥበዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#TecnoAI
የፈለጉትን ቢጠይቁት የሚመልስ እንደ እርሶ ሆኖ ስራዎትን የሚከውን የቀዱትን ድምፅ በፅሁፍ ቀይሮ የሚሰጥ፣ አስተርጓሚ ሆኖ ስራዎትን የሚያቀል፣ የሂሳብ ስራዎን በራሱ የሚከውን አባ መላ የተባለለት ቴክኖ ኤ አይ እየመጣ ነው፡፡
ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመከተል የቴክኖ ቲክቶክ ገጽ ፎሎው በማድረግ እና Bio ላይ ያለውን ሊንክ ተጭነው በመመዝገብ ታህሳስ 10 በስካይላይት ሆቴል በሚካሄደው የሀገራችን ትልቁ የኤ አይ ሁነት ላይ ይሳተፉ፡፡
tecnoet" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@tecnoet
@tecno_et @tecno_et
#የጋራመኖሪያቤቶች
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በተለያዩ ጊዜያት በእጣ እና በጨረታ ተላልፈው ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች የቤት ባለቤቶቹ እንዲገቡባቸው የሰጠው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ነገ ህዳር 30/2017 ዓ/ም ያበቃል።
ኮርፖሬሽኑ በሰጠው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የቤት ባለቤቶቹ ወደ ቤታቸው የማይገቡ ከሆነ በህግ አግባብ ውል የሚቋረጥ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል።
ቀደም ብሎ የተሰጠው ገደብ ጥምቅት 30 የነበረ ቢሆንም ቤታቸውን አድሰው ለመግባት የጊዜ እጥረት ላጋጠማቸው የቤት ባለቤቶች ተብሎ እስከ ህዳር 30 ተራዝሞ ነበር።
ይህ ለመጨረሻ ጊዜ የተሰጠ የጊዜ ገደብ መሆኑን ኮርፖሬሽኑ ገልጾ ነበር።
ቀኑ ነገ ሰኞ ያበቃል።
በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማይገቡ ነዋሪዎች የሽያጭ ውላቸው የሚቋረጥ እና በቤታቸው ውስጥ ለሚፈጸም ማንኛውም ህገወጥ ድርጊት ተጠያቂ እንደሚሆኑ መግለጹ ይታወሳል።
ከዘህ ቀደም ኮርፖሬሽኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥቶት በነበረው ማብራሪያ ምን ነበር ያለው ?
- ማስታወቂያው የወጣበት ዋናው ምክንያት ሰዎች ‘ ተቸገርን፣ ክፍት በሆኑ ቤቶች ወንጀል እየተሰራ ነው፣ እየተዘረፍን ነው፣ ሴቶች እየተደፈሩብን ነው፣ የጸጥታ ስጋትም እየሆኑብን ’ ብለው ቅሬታ ስላቀረቡ እንደሆነ፤
- ቤቶቹ ቼክ ሲደረጉ እጣ የወጣባቸው ፤ ውል የተፈጸመባቸው፣ በጨረታ የተላለፉ ነገር ግን ሰው ያልገባባቸው እንደሆኑ፤
- ነዋሪው በከፍተኛ ሁኔታ እየተቸገረ ፤ የጸጥታ ኃይሉም ጥያቄ እያነሳ እንደሆነ ፤
- " የቤት ባለቤቶች ቤታችሁን አድሳችሁ ግቡ " የተባለውም የግድ እራሳቸውን እንዳይደለ ፤ ቢፈልጉ አድሶ ማከራየት መብታቸው እንደሆነ፤
- የራሳቸው ቤት እስከሆነ ድረስ አድሰው ማከራት ከፈለጉ ደግሞ እራሳቸው መግባት መብታቸው እንደሆነ ዞሮ ዞሮ ሰው በቤቱ ሊኖርበት እንደሚገባ ማብራራቱ ይታወሳል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" እድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበታል ! "
የአንድ ልጅ እናት የሆነችውን ቅድስት ነጋሲን በግፍ የገደለው ወንጀለኛ ግለሰብ የእድሜ ልክ አስራት ተፈረደበት።
ገዳይ ወንጀለኛው ሓየሎም ተኽለማርያም ይባላል።
ነዋሪነቱ በትግራይ ማእከላዊ ዞን ዓዴት ወረዳ ነው።
ግለሰቡ በወረዳው በሚገኘው ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪ በሆነችው እንስት ቅድስት ነጋሲ ላይ አስገድዶ መድፈር የፈፀመ ቢሆንም ጉዳዩ በሽምግልና እና እርቅ ታይቶ በትዳር እንዲቀጥሉ ይደረጋሉ።
በዚህም የአብራካቸው ክፋይ የሆነ አንድ ልጅ ይወለዳል።
ይሁን እንጂ ግለሰቡ በተደጋጋሚ በሚያሳየው የበጥባጭነት ባህሪ ትዳሩ መቀጠል አልቻለም።
ስለሆነም ግለሰቡ በዚሁ ቂምና ቅናት ቋጥሮ ጨለማን ተገን አድርጎ በአሳቻ መንገድ በመጠበቅ የቅድስት አባትን " ልጅህ መክረህ አፋታኸኝ " በማለት በድንጋይ ቀጥቅጦ ከባድ የአካል ጉዳት አድርሶባቸዋል።
ይህ አልበቃ ብሎት የ12ኛ ክፍል ትምህርትዋ አጠናቅቃ ለቀጣይ ትምህርት እንዳስላሰ -ሽረ ከተማ ወደ ሚገኘው የእርሻ ኮሌጅ ያመራቸውን ቅድስት ነጋሲን ይከታተላት ይጀምራል።
ተከታትለዋት በመሄድ የተከራየችበት ቤት ውሎዋን ያጠናል።
ገዳይ ወንጀለኛው መጋቢት 20/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 1:30 በሌላው ሰው ሞባይል አሰድውሎ በቤት መኖርዋን ካረጋገጠ በኋላ የተከራየችበት ቤት ድረስ በመሄድ " እኔን ፈትተሽ ሌላ ልታገቢ ነው ? ከኔ ጋር ለምን አልቀጥለሽም " በማለት በፍፁም ጭካኔ እና አረመኔያዊ በሆነ ሁኔታ ደጋግሞ በቢላዋ በመውጋት ገድሏታል።
ገዳይ ወንጀለኛው አስነዋሪ ተግባሩ ፈፅሞ ሊሰወር ሲል በህዝብ እና የፀጥታ ሃይሎች ትብብር ወድያውኑ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።
ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ማእከላዊ ፍርድ ቤት በእንዳስላሰ-ሽረ ከተማ ህዳር 27/2017 ዓ.ም ባዋለው ችሎት ግለሰቡ ሆን ብሎ ተዘጋጅቶ አቅዶ በፈፀመው የግድያ ተግባር ወንጀለኛ ሆነ በመገኘቱ በእድሜ ልክ እስራት ቀጥጦታል።
በችሎቱ የተገኙ የሟች ቤተሰቦች ገዳይ ወንጀለኛው በሞት መቀጣት ነበረት ቢሆንም ውሳኔው ለሌሎች አስተማሪ ነው ብለዋል።
መረጃውን የመቐለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ድምጺ ወያነን ዋቢ በማድረግ ነው ያደረሰን።
@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን ዛሬ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፣ አርባ ምንጭ ከተማ ተከብሮ ውሏል።
ካለፉት ጥቂት ዓመታት በተሻለ ድምቀት በዓሉ መከበሩን አርባ ምንጭ የሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ገልጿል።
በዘንድሮው በዓል ላይ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የክልል ርዕሰ መስተዳደሮች ፣ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት የተገኙበት ነበር።
በአዲሱ ክልል የተሰናዳው በዓሉ ለአርባ ምንጭ ከተማ ከፍተኛ መነቃቃትን የፈጠረ እንደሆነ ቀጣይ አመት በዓል ደግሞ በሌላኛው አዲስ ክልል ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አስተናጋጅነት እንደሚካሄድ ተነግሯል።
#ArbaMinchLandofPeace
@tikvahethiopia
#TecnoAI
ዘናጭ ቴክኖሎጂ እየመጣ ነው! ያሰቡትን ያለገደብ ሚከውኑበት ቴክኖ ኤ አይን በቅርቡ ይጠብቁ!!!
ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመከተል የቴክኖ ቲክቶክ ገጽ ፎሎው በማድረግ እና Bio ላይ ያለውን ሊንክ ተጭነው በመመዝገብ ታህሳስ 10 በስካይላይት ሆቴል በሚካሄደው የሀገራችን ትልቁ የኤ አይ ሁነት ላይ ይሳተፉ፡፡
tecnoet" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@tecnoet
@tecno_et @tecno_et
" ትውልድን በማበላሸትና ለተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች መንስኤ እየሆኑ ባሉ ጉዳዮች ላይ እምርጃ መውሰድ እንቀጥላለን " - ድሬ ፖሊስ
የድሬዳዋ ፖሊስ ፤ " ወረዳ 2 ስር በሚገኙ በተለያዩ አካባቢዎች ኦፕሬሽን አድርጌ በርካታ የሺሻ ማጨሻ እቃዎች እና 54 ተጠርጣሪ ግለሰቦችን ይዣለሁ " አለ።
የሳቢያን ፖሊስ ጣቢያ ተወካይ አዛዥ ኢ/ር አበባ አሼቦ ከማህበረሰቡ በደረሰ ጥቆማ በቀጠናው ላይ በሚገኙ በ10 ቤቶች ላይ ብርበራ መደረጉን ገልጸዋል።
በዚህም ከ80 በላይ የሺሻ ማጨሻ ጠርሙስ ፤ ከመቶ በላይ ፓኬት ሺሻ፤ ከመቶ ሰላሳ ፍሬ በላይ ቡሪ፤ ሰላሳ ካርቶን ቀስቲር፤ ሌሎችም ... ቀሶች እንደተያዙ አመልክተዋል።
54 ተጠርጣሪዎችም የተያዙ ሲሆን 18ቱ በዋናነት 36ቱ በተባባሪነት የተያዙ ናቸው።
የድሬ ፖሊስ " ትውልድን በማበላሸት እንዲሁም ለተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች መንስኤ እየሆኑ ባሉ ጉዳዮች ላይ እምርጃ መውሰድ እንቀጥላለን " ያለ ሲሆን በዚህ ላይ ህብረተሰቡ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።
#DirePolice
@tikvahethiopia
#DStvEthiopia
ደማቁ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ወደ ሜዳ ተመልሰዋል💥
👉እነዚህን ድንቅ ፍልሚያዎች ጨምሮ ሌሎች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይመልከቱ።
ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh
ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et
#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው
#Syria : የ24 ዓመታት የፕሬዜዳንት በሽር አልአሳድን አገዛዝ ያስወገዱት የታጠቁት ተቃዋሚዎች አልአሳድ ሀገር ጥለው መጥፋታቸውን ገልጸዋል።
የሶሪያ ተዋጊዎች በደማስቆ የሚገኘውን የአውሮፕላን ማረፊያን ከመቆጣጠራቸው ጥቂት ጊዜ በፊት በሶሪያ አየር ክልል ውስጥ የአንድ አውሮፕላን እንቅስቃሴ ተመዝግቧል።
የIL76 አውሮፕላን የበረራ ቁጥሩ ' የሶሪያ አየር 9218 ' ከደማስቆ የተነሳ የመጨረሻ በረራ ነበር።
ይኸው አውሮፕላን መጀመሪያ ላይ ወደ ምሥራቅ በረረ፣ ከዚያም ወደ ሰሜን ዞሮ ሲበር ነበር።
ለደቂቃዎች ሆምስን ከዞረ በኃላ ከራዳር እይታ ውጭ ሆኗል። አውሮፕላኑ የት ይገባ የት ምንም አልታወቀም።
በሽር አልአሳድ ከሀገር መውጣታቸው ይነገር እንጂ የት እንዳሉ እስካሁን አይታወቅም።
@tikvahethiopia
#Update
ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ ተከስቶ የነበረው የኃይል መቋረጥ ወደነበረበት መመለሱን የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታውቋል። #EEP
@tikvahethiopia
#Update
" የተቋረጠው ኃይል ወደነበረበት እየተመለሰ ነው " - የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል
" ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ኃይል ወደነበረበት እየተመለሰ ነው " ሲል የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታወቀ።
ማዕከሉ እንዳስታወቀው የሲስተሙን ቮልቴጅ በማረጋጋት የተቋረጠውን ኃይል ደረጃ በደረጃ ለመመለስ የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ ነው።
በአዲስ አበባ በአንዳንድ አካባቢዎች እንዲሁም በክልል ከተሞች የተቋረጠው ኃይል ወደነበረበት መመለሰ መጀመሩን ገልጿል።
የተፈጠረው ችግር ሙሉ በሙሉ አልተፈታም።
ችግሩ ሙሉ በሙሉ እስኪፈታ ድረስ በትዕግስት ተጠባበቁ ተብሏል።
@tikvahethiopia
" በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።
ችግሩን በመፍታት የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል።
የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቆ፤ ያሉትን መረጃዎች በፍጥነት የሚያሳውቅ መሆኑንም ገልጿል።
#EEP
@tikvahethiopia
በፍቅር ከተማዋ ድሬ በፍቅር የተጠጣው ፔፕሲ ሽልማት ይዞ ገባ!!!!!
የቀኑን ግለት ሊያቀዘቅዝ ቀዝቃዛ ፔፕሲ ያዘዘው አቶ በላይ ሞላሮ ደስታው እንጂ ኤሌትሪኩ የማይነዝር ቢዋይዲ የኤሌክትሪክ መኪና አሸናፊ ሆኖዋል።
ሕዳር 28 ቀን 2017ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ በተዘጋጀ ልዩ የሽልማት ፕሮግራም ባለዕድለኛው አቶ በላይ ሞላሮ ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር ፣ ለደንበኞቹ ካዘጋጃቸው በርካታ ሽልማቶች ውስጥ 2ኛዋን የቢዋይዲ የኤሌክትሪክ መኪና ዕጣ ተረክበዋል።
ድሬዎች እንኳን ደስ ያላችሁ!
አሁንም በርካታ በርካታ ሽልማቶች ተረኛ ዕድለኞችን እየጠበቁ ነው፡፡ የሞሐን ምርቶች እያጣጣምን ዕድላችንን እንሞክር - እናሸንፍ!
ፔፕሲ፣ ሚሪንዳ እና ሰቨን አፕ ያሸልማሉ!
#ንጉስማልት ደስስስስ ደስስስስ የሚል ጥምረት ከንጉስ ማልት ጋር!
ዛሬ ንጉስ ማልት ከየትኛው ምግብ ጋር ለመሞከር አስበዋል? ስክሪን ሾት ያድርጉ፣ ከዛም ያገኛችሁትን ደስ ደስ የሚል ጥምረት በፌስቡክ ወይም በቴሌግራም ቻናሎቻችን ያጋሩን! https://fb.watch/wiDa1wrfDa/ /channel/Negus_Malt
#nonalcoholic #ንጉስ #DesDesWithNegus #ደስደስበንጉስ #የጣዕምልኬት_የደስታስሜት
#Tigray
በመቐለ ማንኛውም ሰላማዊ ስልፍ እንዳይካሄደ ተከለከለ ፤ ክልከካው አስከ መቼ እንደሚቀጥል የተገለፀ ነገር የለም።
በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት በመቐለ ከተማ ተደረግብኝ ላለው የከንቲባ መፈንቅለ ስልጣን " ሰላማዊ ስልፍ እንዳካሂድ ይፈቀድልኝ " ሲል በመቐለ የህወሓት ፅህፈት ቤት በኩል ህዳር 25/2017 ዓ.ም ለመቐለ ከተማ አስተዳደር በፃፈው ደብዳቤ ጥያቄ አቅርቧል።
ሰልፉን እሁድ ህዳር 29/2017 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:30 እስከ ቀኑ 6:30 ለማድረግ ነበር የጠየቀው።
ድርጅቱ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያካሂድ በጠየቀበት ደብዳቤው ፤ " ህዳር 23/2017 ዓ.ም የተፈፀመው በመሳሪያ የተደገፈ የመቐለ ከተማ መደበኛ አስተዳደር መፈንቅለ ስልጣን ለማውገዝ " ነው ብሏል።
በተጨማሪም ፥ " ለዘመናት በከፈልነው መስዋእት ያፀናነው መብታችን እና የመሰረትነው ምክር ቤት በአዲስ ገዢ ግለሰቦች አምባገነንነት ሲፈርስ አንታገስም " ሲል ገልጿል።
ደንረጽዮን (ዶ/ር) የሚመሩት ቡድን " ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እንድናካሂድ በተደጋጋሚ ከአባሎቻችን በቀረበልን ጥያቄ መሰረት ፤ እሁድ ህዳር 29/2017 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:30 አስከ ቀኑ 6:30 ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እንድናካሂድ ቅድመ ዝግጅት ስላጠናቀቅን ፍቃድ እንዲሰጠን እና የፀጥታ ጥበቃ እንዲደረግልን እንጠይቃለን " ሲል ነው በደብዳቤው የገለጸው።
ለመቐለ ህወሓት ፅህፈት ቤት ደብዳቤ ዛሬ አርብ ህዳር 27 /2017 ዓ.ም ምላሽ የሰጠው የመቐለ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ የከተማው ጥምር ኮሚቴ በሰጠው መምሪያ መሰረት በመቐለ ከተማ ማንኛውም ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይካሄድ #ተከልክለዋል ብሏል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
#Ethiotelecom
⏰ የአክሲዮን ሽያጩ ሊጠናቀቅ እየተቃረበ ነው!
❇️ የኢትዮ ቴሌኮም 10% አክሲዮን ሽያጭ ብስራትን ተከትሎ 100 ሚሊዮን መደበኛ አክሲዮኖች እየተሸጡ ይገኛሉ!
የአንድ ሼር ዋጋ 300 ብር፣ ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 9,900 ብር (33 አክሲዮኖች)፣ ከፍተኛው 999,900 ብር (3,333 አክሲዮኖች) ነው፡፡
💁♂️ የአክሲዮን ሽያጩ በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr ይከናወናል፤ እርሶም የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል፡፡
🗓 ለገበያ የቀረቡት አክሲዮኖች ቀድሞው ተሸጠው ካልተጠናቀቁ እስከ ታኅሣሥ 25/2017 ዓ.ም ይቆያል፡፡
ለተጨማሪ: https://bit.ly/3Y9JUae ይመልከቱ!
📖 የደንበኛ ሳቢ መግለጫውን https://teleshares.ethiotelecom.et/ ያንብቡ፡፡
#telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia