tikvahethiopia | Unsorted

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1519086

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Subscribe to a channel

TIKVAH-ETHIOPIA

#አክሱም

🧕" እኛ የምንፈልገው ፍትህ ነው። ሂጃባችንን አድርገን ነው መማር የምንፈልገው። ያለ ሂጃብ ሸሪዓም አይፈቅድም አስቸኳይ እና ዘላቂ መፍትሄ ይሰጠን " - ተማሪዎች

➡️ " የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በአጠቃላይ ሁሉም የሉም ከትምህርት ገበታ ላይ ወጥተዋል " - የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት

👉 " ማንም ተማሪ በትምህርት ቤት ሃይማኖትን የሚያንጸባርቅ ነገር ማድረግ የለበትም " - የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

በትግራይ ፣ አክሱም ከተማ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ላለፉት 2 ሳምንታት የራስ መሸፈኛ ሂጃብ ለብሰው ወደ ትምህርት ቤት መግባት እንደተከለከሉና በዚህም ከትምህርት ገበታ መውጣታቸውን የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት አሳውቋል።

በዚህ ዓመት ከሂጃብ መልበስ ጋር በተያያዘ በአክሱም በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውዝግቡ የጀመረው ጥቅምት ወር ነው።

ተቋሙ ለክልል ትምህርት ቢሮ አሳውቆ አውንታዊ ምላሽ ቢሰጠውም በተግባር የተቀየረ ነገር ግን የለም።

የምክር ቤቱ ፀሀፊ ሓጂ መሓመድ ካሕሳይ ምን አሉ ?

" ፀጉራቸውን ሸፍነው ትምህር ቤት እንዲሄዱ ማየት ያልተፈቀደበት መታየት የለበትም ፀጉሯ የአንድ ሴት ይሄ ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው።

ሃይማኖት ውስጥ ፖለቲካ አይገባም፣ ፖለቲካ በሃይማኖት አይገባም እየተባለ በአንቀጽ ተቀምጦ እያለ አሁን ፖለቲካ በሃይማኖት እየገባ ነው።

ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ዩኒፎርም ጋር የሚመሳሰል የፀጉር መሸፈኛ ሂጃብ መጠቀም እንደሚችሉ በ2000 ዓ/ም የወጣ ሀገር አቀፍ መመሪያ አለ።

ስለዚህ ዝም ብለን የምናየው ነገር አይሆንም።

በአሁኑ ጊዜ በአራት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ወጥተዋል።

ዋናው ደግሞ 3 ወር ሲማሩ የነበሩ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለብሔራዊ ፈተና የኦንላይ ምዝገባ የሚደረግበት ወቅት ነው በዚህ ሳምንት ያልቃል የአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች እስካሁን አልተመዘገቡም።

የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በአጠቃላይ ሁሉም የሉም ትምህርት ገበታ ላይ ወጥተዋል፤ አልገቡም እስካሁን።

ችግሩ እንዲፈታ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ እና ከአክሱም ከተማ አስተዳደር ትምህርይ ፅ/ቤት ጋር ውይይት እየተደረገ ነው " ብለዋል።


ተማሪዎች ምን ይላሉ ?

" በጦርነት ምክንያት ለ2 ዓመታት ከሌሎች  ተማሪዎች ወደኃላ ቀርተናል አሁን ደግሞ በሂጃብ ምክንያት ፈተና ሊያመልጠን ነው።

ፎርሙ እያመለጠን ነው። ሌሎች ተማሪዎች በሂጀብ ፎርም እንደሞሉ ነው የምናውቀው። እኛ የምንፈልገው ፍትህ ነው። ሂጃባችንን አድርገን ነው መማር የምንፈልገው።

ያለ ሂጃብ ሸሪዓም አይፈቅድም ፤ መፍትሄው ደግሞ በጣም አስቸኳይ እና ዘላቂ መሆን አለበት። እስካሁን መብታችን እየተከበረ አይደለም " ብለዋል።

NB. የክልል ትምህርት ቢሮ እና የአክሱም ከተማ አስተዳደር ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆኑም።

የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምን አለ ?

ምክትል ርዕሰ መምህር ገ/መስቀል ገ/እግዚአብሔር ፦

" ' ትምህርት ቤቶች ከሃይማኖት እና ከፖለቲካ ነጻ መሆን አለባቸው ' ይላል የትግራይ ክልል የትምህርት ቤቶች አደረጃጀት መመሪያ ማንም ተማሪ በትምህርት ቤት ሃይማኖትን የሚያንጸባርቅ ነገር ማድረግ የለበትም።

ክርስቲያኑ መስቀል ወይም መጠምጠሚያ ፤ ሙስሊሙም ሂጀብ ወይም ኮፍያ ማድረግ አይፈቀድም። የትምህርት ቤቱ መለያ ዩኒፎርም ብቻ ነው መልበስ የሚገባው።

የተወሰኑ ተማሪዎች ሂጃባቸውን አናውልቅም ብለው ነበር አሁን ግን ተማሪዎች የትምህት ቤቱን መመሪያ ተከትለው እየገቡ ናቸው።

አሰራሩ ለዓመታት የቆየ ነው " ብለዋል።


አንድ በጉዳዩ ላይ ቃላቸው የሰጡ የክልል ትምህርት ቢሮ ሰራተኛ ፤ " በክልሉ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እየሆነ ያለው በ1995 የወጣ መመሪያ ነው በዚያ መመሪያ ትምህርት ቤቶች የራሳቸውን መተዳደሪያ ማውጣት እንደሚችሉ ይደነግጋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ትግርኛ አገልግሎት መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በአማራ ክልል አጀንዳ ልየታ እንደማንሳተፍ ለኮሚሽኑ በአክብሮት እንገልጻለን " - መኢአድ እና እናት ፓርቲ

መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና እናት ፓርቲ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል ባቀደው አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ በአጀንዳ ልየታ የሚሳተፉ የፓርቲ ተወካዮችን እንዲያሳውቁ በደብዳቤ ቢጠይቃቸውም ከወዲሁ እራሳቸውን ማግለላቸውን የሚገልጽ የጋራ መግለጫ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ልከዋል።

ፓርቲዎቹ ራሳቸውን ከምክክሩ እንዳገለሉ በገለጹበት በዚሁ መግለጫ ፤ የጦርነት ችግሮች ካልተፈቱ በምክክሩ ለመሳተፍ እንደሚቸገሩ ሲያሳስቡ መቆየታቸውን አስታውሰዋል ፤ የአማራ ክልል ህዝብ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በአየርና በምድር በከባድ መሳሪያ እንዲሁም በድሮን ጭምር የሚደርስበት ጥቃት አለመቆሙን ጠቅሰዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቢያበቃም አማራ ክልል በኮማንድ ፖስት እየተዳደረና ጦርነቱ እየተስፋፋ ያለበት፣ በርካታ ዜጎች በማንነታቸው እና በፖለቲካ አመላካከታቸው የታሰሩበት፣ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ አልፎ አልፎ ሙሉ በሙሉ የሚገደብበት ፣ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት የራቀበት ሁኔታ መኖሩን ገልጸዋል።

" በዚህ መልክ በተጠቀሰው የአጀንዳ ልየታ ለመሳተፍ መሞከር እውነተኛ ምክክር አድርጎ ለሀገር የሚበጅ መፍትሄ ለማምጣት ሳይሆን የተጠና ተውኔት አካል ከመሆንና ራስን ከማታለል የዘለለ የሚያመጣው መፍትሄ እንደሌለው በውል እንረዳለን " ብለዋል።

በህዝቡ የሚፈደርሰው ጉዳት አለመቆሙን ጠቅሰው፣ " በክልሉ የአጀንዳ ልየታ ሥራ ማሰብ ከፈረሱ ጋሪው የቀደመበትና ኮሚሽኑ እውነተኛ ምክክር የማድረግ እንቅስቃሴ ሳይሆን የስርዓት ዓላማ ማስፈጸሚያ መሣሪያ ወደ መሆን ገባ ወይ ? እንድንል አስገድዶናል " ብለዋል።

ፓርቲዎቹ፣ የሀገራዊ ምክክሩ አካሄድ ከዐዋጁ አጸዳደቅ ጀምሮ ከታዩበት የተለያዩ የጎሉ ችግሮች ላይ ተጠደምደው ከመቆዘም ይልቅ ምክክሩ ለአገር የሚያመጣውን ውጤት በመገንዘብ " ችግሮች እየተቀረፉ ይሄዳሉ " በሚል እሳቤ በመደገፍ እንደቆዩ አስታውሰዋል።

በምክክሩ ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ፣ የሰሜኑ ጦርነት በፕሪቶሪያው ስምምነት እንደተቋጨ ሁሉ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ጦርነቶች ተቋጭተው ወደ ምክክር መኬድ እንዳለበት፣ ይህ ካልሆነ የሀገሪቱ እጣ ፈንታ ሀገራዊ ምክክሩ ሳይሆን የጦርነቶቹ ሂደት ሊወስን እንደሚችል ምክረ ሀሳብ ሲያቀርቡ መቆየታቸውን ነው የገለጹት።

በመሆኑም፣ " ኮሚሽኑ በሰው ቁስል እንጨት ከመስደድ " ይልቅ ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ እና ከመንግስት ጋር ያለውን መልካም ግንኙነት ተጠቅሞና ጫና አድርጎ በገለልተኛ አካላት አሸማጋይነት እውነተኛ ሰላምን ሊያዋልድ የሚችል ድርድር እንዲደረግ አሳስበዋል።

(የትብብር ፓርቲዎቹ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)


@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ethiotelecom

ኢትዮ ቴሌኮም በ67 ከተሞች የ4ጂ ሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት ማስጀመሩን አሳውቋል።

የከተሞቹ ዝርዝር ከላይ በምስል ተያይዟል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ethiotelecom #telebirr

✨🏑 ሁላችንም የምንሳተፍበት የዘንድሮ የገና ጨዋታ የሚደረግበት ሜዳ ቴሌብር ሱፐርአፕ ነው!! 😁

💁‍♂️ መተግበሪያው https://onelink.to/uecbbr ከሌለዎት ያውርዱ፤ በሞቀው የገና ጨዋታ ተሳታፊ ይሁኑ!

🤩 ከ15 ሚሊየኑ የዕድልዎን ለመውሰድ ታኅሣሥ 23 ይጠብቁን!!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የተሠረቀባችሁን ዕቃ በአካል ቀርባቹ በመለየት መረከብ ትችላላችሁ " - ፖሊስ

በልደታ ክ/ከተማ በተደረገ የሌባ ጥናት የተለያዩ የተሠረቁ የመኪና ዕቃዎችን ከአንድ ተጠርጣሪ ጋር መያዙን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

" የሌባ ተቀባዬች ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰረቁ የመኪና ዕቃዎችን በማከማቸት ዕቃዎቹን ለማስመለስ ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠየቅባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ ተደጋግሞ ይገለፃል " ያለው ፖሊስ የተሰረቁ የተሽከርካሪ ዕቃዎችን በመኖሪያ ቤት ውስጥ በመደበቅና የተሽከርካሪዎቹ ባለቤቶች ሲመጡ የራሳቸውን ዕቃ በገንዘብ የሚሸጡ ግለሰቦች ላይ ጥናት ሲደረግ መቆየቱን አመልክቷል።

ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ/ም በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ቀጠና አራት አካባቢ በጥናት በተለዩ አራት የመኖሪያ ቤቶች ውስጥ ከሌቦች እየተቀበሉ በመደበቅ የሚሸጡ ግለሰቦችን ላይ በተደረገ ኦፕሬሽን ፦
👉 152 የተለያዩ ስፖኬዎች፣
👉 08 ዓርማዎች ( ማርክ )፣
👉 08 የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀር ክዳኖች፣
👉 01 የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀር፣
👉 15 የስፖኪዮ ማቀፊያ፣
👉 01 የሞተር ሳይክል ፍሬቻ ከአንድ ተጠርጣሪ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ገልጿል።

ፖሊስ አሁንም መሰል የወንጀል ድርጊት ውስጥ በመግባት የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ተገቢውን የፍርድ ቤት የመያዣና የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት ተጠርጣሪዎችን የመያዝና ብርበራዎችን የማድረግ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

" ተመሳሳይ ወንጀል ተፈጽሞብኛል " የሚል ካለ ጎማ ቁጠባ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በአካል በመቅረብ የተሠረቀበትን ዕቃ መለየትና መረከብ እንደሚችል ፖሊስ አስታውቋል።

በነገራችን ላይ ...

አዲስ አበባ ውስጥ የትም ቦታ የራሳችሁን የመኪና ዕቃ ብትሰረቁ ዕቃችሁን የት እንደሚገባ ይታወቃል።

የተሰረቁ ሰዎች ዕቃቸውን ፍለጋ ወደ እነዚህ ስፍራዎች ሲሄዱ ሌቦቹ እና ተቀባዮቹ ልክ እንደ ህጋዊ የራሳቸው እቃ ከፍተኛ ብር ይጠይቃሉ።

የራሳችሁ በሆነና በተሰረቃችሁት ዕቃ ላይ ይደራደራሉ " አያዋጣኝም ከቦታው አልመጣም " ይላሉ።

ከዛም በፈለጉት ዋጋ የራሳችሁን ዕቃ ሽጠውላችሁ ይሸኟችኃል።

ይህ ብቻ አይደለም የጠፋባችሁን የመኪና ዕቃ ፍለጋ ባሄዳችሁት " ቆዩ አንድ 40 ደቂቃ ጠብቁ " ትባሉና ተመሳሳዩ ይመጣላችኋል። ይህን የሚያደርጉት ሌቦችን አሰማርተው በማሰረቅ ነው።

ይህ ሁሉ የሚሆንባቸው የአዲስ አበባ ቦታዎች በግልጽ በይፋ ይታወቃሉ።

የተሰረቁ ሰዎች " ለፖሊስ አመልክተን እቃችንን የምናገኝበት እድል ጠባብ ነው ፤ የሚወስደው ጊዜም ብዙ ነው " በሚል የራሳቸውን እቃ በውድ ዋጋ ይገዛሉ።

የሚሰረቁ የመኪና እቃዎች የት እንደሚወስዱ እየታወቀ ፤ የሚሸጥባቸው እና ድርድር የሚደረግባቸው ቦታዎች በይፋ እየታወቀ ይህንን ተግባር ለምን በዘላቂነት ማስቆም እንዳልተቻለ የብዙ ሰዎች ጥያቄ ነው።

ማልባትም በዚህ ነገር እጃቸው የረዘመ እና የጥቅሙ ተካፋይ ፣ የሌቦችም ጠበቃ የሆኑ ብዙ ግለሰቦች ይኖራሉ።

በመኪና ስርቆት የተማረሩ በኃላም የራሳቸውን እቃ ሄደው በከፍተኛ ብር የገዙ ብዙ ሰዎች ይኖራሉ። እናተስ የምታውቁት ታሪክ ይኖር ይሆን ? አጋሩን
@tikvahethiopiaBot

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

🔈 #የጤናባለሞያዎችድምጽ

🔴 " ከደመወዝ ጋር ይከፈለናል ብለን በተስፋ ስንጠብቅ አሁንም ሳይከፈለን ቀርቷል " -ቅሬታ አቅራቢ የጤና ባለሞያዎች

🔵 " ምን ያህል ይታገሱ የሚለውን አላውቅም " -የወረዳው አስተዳዳሪ

በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ በ9 ጤና ጣቢያ ውስጥ የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች ከግንቦት 2016 ዓ/ም ጀምሮ የተጠራቀመ የትርፍ ሰዓት ስራ (ዲዩቲ) ክፍያቸው እንዳልተከፈላቸው በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ባለሞያዎቹ ያልተከፈላቸው የ2016 ዓ/ም የግንቦት እና የሰኔ ወር እንዲሁም በ2017 ዓ/ም የ3 ወር በጠቅላላው የ5 ወር የዱዩቲ (የትርፍ ሰዓት) የሰሩበት ክፍያ ነው።

መረጃውን ባጋራንበት ወቅት ባለሞያዎቹ ያልተከፈላቸው የ4 ወር የትርፍ ሰአት ክፍያ የነበረ ሲሆን በወቅቱ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቃሉ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑትን አቶ ሙህዲን አህመድን በጉዳዩ ላይ አነጋግሮ ነበር።

አስተዳዳሪው " ክፍያው የዘገየው በየጤና ጣቢያዎቹ የሚሰጠው አገልግሎት እና የሥራ ጫና የሚለያይ በመሆኑ የሚያድረው የጤና ባለሞያ ቁጥርም ይለያያል በዛ ምክንያት ደረጃ ይውጣለትና በሚሰጡት አገልግሎት እና ባለባቸው የስራ ጫና ልክ ይከፈላቸው ተብሎ ይህንን የሚያጣራ ኮሚቴ ተቋቁሞ በወረዳው በሚገኙ በዘጠኙም ጤና ጣቢያዎች እያጣራ ነው ሪፖርቱን እንዳቀረበ ይከፈላቸዋል " ማለታቸው ይታወሳል።

አስተዳዳሪው ይህንን ምላሽ ይስጡ እንጂ የባለሞያዎቹ የትርፍ ሰአት ክፍያ ሳይከፈል 5 ወር ማለፉን የጤና ባለሞያዎች በድጋሚ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

ባለሞያዎቹ " የሰራንበትን ክፍያ እንዲከፈለን ደጋግመን ብንጠይቅም የሚሰማ አመራር በማጣታችን አሁንም ለችግር ተጋልጠናል " ብለዋል።

" በህዳር ወር መጨረሻ ከደመወዝ ጋር ይከፈለናል ብለን በተስፋ ስንጠብቅ አሁንም ሳይከፈለን ቀርቷል ለምን ? ብለን ስንጠይቅ እንደገና በወረዳው ጤና ጥበቃ ኦፊሰሮች ኮሚቴ ተዋቅሮ 9ኙም ጤና ጣቢያዎች  ቼክ ይደረጉ ተብሎ ከወረዳ አስተዳደር አቅጣጫ ተቀምጧል በዚህ ወር የሰራችሁበት አይከፈላቹም " የሚል ምላሽ ተሰጥቶናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የወረዳውን አስተዳዳሪ የጤና ባለሞያዎቹ ምን ያህል ጊዜ ይታገሱ ሲል በድጋሚ ጠይቋል " ምን ያህል ይታገሱ የሚለውን አላውቅም በቴክኒክ ኮሚቴው ተጨማሪ ጥናት እየተደረገ ነው እሱ እንዳለቀ ይከፈላቸዋል " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ወረዳው ኮሚቴዎችን አዋቅሮ በዘጠኙም ጤና ጣቢያ ጀምሮት የነበረውን የማጣራት ስራ ካጠናቀቀ በኋላ በድጋሚ ጤና ጣቢያዎቹ በራሳቸው የማጣራት ስራ ጀምረዋል ይህ ለምን ሆነ ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ " ተቋማቱ (ጤና ጣቢያዎቹ) እኛም ቼክ እናድርግ አሉ እኛ ከሰራነው ጋር ያለውን mismatch (ልዩነት) እንየው ከቴክኒኩ ውጤት ጋር ይገጥማል ወይስ ልዩነት አለው የሚለውን ለማየት ፈልገው ስለሆነ እሱ እንዳለቀ ይከፈላል " ሲሉ መልሰዋል።

ሃላፊው በወረዳው ደረጃ የሰሩት የጥናት ውጤት ምን እንደሆነ ከመናገር የተቆጠቡ ሲሆን ተጨማሪ ምላሽ ለመስጠትም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ዳንኤል ጋሻው ምን ምላሽ ሰጡ ?

ሃላፊው " የጤና ጣቢያዎቹ አሰራራቸውን ማየት ስላለብን በድጋሚ ጀምረናል የሚሰጡት አገልግሎት እና የባለሞያው ቁጥር ትንሽ ይጣረሳል " ብለዋል።

ጥናቱም በዚህ ሳምንት እንደሚያልቅ እና በውጤቱም መሰረት እንደሚከፈላቸው ተናግረዋል።

" ነገሩን ማስተካከል ስለሚቻል በዚህ ሳምንት ጨርሰን ያለውን ነገር ችግሮቹን ለይተን የሚከፈለው ካለ ይከፈላል ያልሰራበትንም የወሰደ ካለ በምርመራው መሰረት ያሰራውም አካል የወሰደውም አካል ተጠያቂ ይሆናል " ነው ያሉት።

" ጥናት ማድረግ የተለየ ነገር አይደለም አሰራርን መፈተሽ ያለ ነው ለሰራተኛውም ይጠቅማል የሚሰራውን እና የማይሰራውን ለመለየትም ያግዛል " ሲሉ አክለዋል።

ጥናቱን ከጨረሳችሁ በኋላ የቀረውን ክፍያ በሙሉ ትከፍላላቹ ወይስ እየቀነሳቹ ? ስንል ላነሳንላቸው ጥያቄ " እሱን ከጥናቱ በኋላ ነው የምናየው ግን የሰሩበት ይከፈላል " ብለዋል።

በውጤቱ መሰረትም በጣም ኬዝ ሎድ ኖሮባቸው ዝቅተኛ የሚከፈለው ካለ ክፍያውን ሊሻሻል እንደሚችል እና ምንም ሳይሰራ እንደ መርሐ ግብር የሚከፈለው ካለም ክፍያውን ሊያጣ እንደሚችል ጠቁመዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

🔴“ 14 ተማሪዎች ታስረዋል ”  - ድርጅቱ

🔵 “ ስማቸውን ካረጋገጡልኝ እኔ ነኝ የማስፈታቸው። ግን ስምና ዲፓርትመንት አምጡ ስንል ‘አናመጣም’ ነው የሚሉት ” - ኀብረቱ

🟢 “ የታሰሩት መፈታታቸውን እንጂ ያልተፈቱ እንዳሉ መረጃው የለኝም ” - መቐለ ዩኒቨርሲቲ

ከአዲሱ የዩኒቨርሲቲዎች የምግብ ሜኑ ትግበራ ጋር ተያይዞ ተማሪዎች ቅሬታ እያነሱ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን፣ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ከቀናት በፊት ከተግበራው ጋር በያያዘ ቅሬታ አድሮባቸው ግርግር ተፈጥሮ ነበር።

በግርግሩ ተማሪዎች ላይ ድብደባና እስር ፣ በንብረት ላይ ደግሞ ውድመት መድረሱን ፣ በኋላም 27 ተማሪዎች ከእስር እንደተፈቱ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኅብረት ትላንት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሳል። 

ዛሬስ ምን እየተባለ ነው ?

' ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብት ኢትዮጵያ ' የተሰኘው ሀገር በቀል የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅት “ 14 ተማሪዎች ታመታሰራዋል ” የሚል ሪፓርት አውጥቷል።

ተማሪዎቹ ከተማሪ ተወካዮቻቸው ጋር ሲገናኙበት በነበረው የቴሌግራም ገጽ አማካኝነት ከሜኑ ጋር በተያያዘ ተቃውሞ አሰምተው ከቴሌግራም ገጹ እንደታገዱ፣ በዚህም ልላ ከፈቱ የተባሉ ሁለት ተማሪዎች ታኀሳስ 15 ቀን 2017 ዓ/ም በክልሉ የጸጥታ ኃይሎች እንደታሰሩ ሪፓርቱ ያወሳል።

ይህን ተከትሎ በተነሳው ተቃው ደግሞ 14 ተማሪዎች መታሰራቸውን የድርጅቱ ሪፓርት ያመለከተ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያም ስለጉዳዩ መቐለ ዩኒቨርሲቲን ጠይቋል።

ዩኒቨርሲቲው ምን መለሰ ?

አሁንም ያልተፈቱ ተማሪዎች አሉ እንዴ ? ስንል የጠየቅናቸው አንድ የዩኒቨርቲው አካል፣ “ የታሰሩት መፈታታቸውን እንጂ ያልተፈቱ እንዳሉ መረጃው የለኝም ” ብለዋል።

እኝሁ የዩኒቨርሲቲው አካል፣ “ ምናልባት ቼክ እናድርገው ” በማለት ሁኔታውን አጣርተው ምላሽ እንደሚሰጡ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃል ገብተዋል።

ከዩኒቨርሲቲው በተጨማሪ ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ከተማሪ ተወካዮቻቸው ጋር በሚገናኙት የቴሌግራም ገጹ አማካኝነት ስለምግብ ሜኑው ተቃውሞ ያነሱ ተማሪዎች ታስረዋል ? ሲል ለኢትዮጵያ ተማሪዎች ኀብረት ጥያቄ አቀርቧል።

ኀብረቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ምን አለ ?

“ ‘አንድ ዳቦ፣ ሁለት ዳቦ፣ አሸዋ አለው’ በሚለው ጉዳይ ቅሬታ ተነስቶ ነበር። 120 ግራም ነበር አንድ ዳቦ የሚጋገረው አሁን 60፣ 60 ተደርጎ ወደ ሁለት ሆኗል። ግራሙ ላይ የተጨመረ፣ የቀነሰ ነገር የለም።

ሌላው ደግሞ ትላንት 5 ሰዓት ተኩል አካባቢ እኔ ራሴ አስወጥታቸው ታስረው የነበሩ 27 ተማሪዎችን ሌሊት ላይ ግን ‘ሲቀጠቀጡ ከነበሩ የመለቐ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል አንዱ ሞቷል’ ብለው ፓስት አደረጉ።

ሌሊት ሄደን አይደር ግቢ አረጋጋግጥን ምንም እንደሌለ ሪፓርት አደረግን። ከዛ ደግሞ 8 ሰዓት ፓስት ተደረገ። ግን በእነዚህ ሦስትና አራት ቀናት በአይደር ግቢ ውስጥ የሞተ ተማሪ የለም። 

ይሄ አሉባልታ ወሬ መሆኑ መታወቅ አለበት። እሱን ሀንድል ካደረግን በኋላ ደግሞ ተመልሰው ‘የታፈኑ ተማሪዎች’ አሉ ወደሚል መጡ። የታሰሩ እንኳ አላሉም። የታሰሩ ቢሉማ ወደ ህግ ነው። ‘ታፍነዋል’ ነው እየተባለ ያለው።

ይህም አይደለም። እርግጠኛ ከሆኑ የታፈኑ ተማሪዎችን እነማን ናቸው ? የት ዲፓርትመንት ናቸው ? መቼ ተወሰዱ ? ማንስ ወሰዳቸው። የሚለውን ማጣራት ግድ ነው።

ታስረው የነበሩ ተማሪዎችን ስማቸውንና ዲፓርትመንታቸውን ስላወቅን ነው ያስፈታናቸው። አሁን ግን ' ይባላል ' ነው እየተባለ ያለው። በይባላል ስለተባለ ይሆናል ማለት አይደለም። እስር ቤት ተኪዶ ቼክ የሚደረግ ነው።

የታፈኑትን ተማሪዎች ስም ዝርዝር ስጡን ስንልም ‘አንሰጥም’ በማለት ዝም ብለው ‘ታፍነዋል’ ይላሉ። ስም ለማስጠቆር የሚሄዱት ዘዴ ነው ሌላ ምንም የተደረገ ነገር የለም።

‘ተማሪዎች ተደብድበዋል፣ ንብረት ወድሟል፣ ተማሪዎች ተፈትተዋል። ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ነው ”
ብሏል ኅብረቱ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብት ኢትዮጵያ የተሰኘው ድርጅት ያወጣውን ሪፓርት አይታችሁት ነበር ? ሲል ለኅብረቱ ተጨማሪ ጥያቄ አቅርቧል።

ኅብረቱ በምላሹ፣ “ አይቸዋለሁ። ይሄ ዝም ብሎ የለቃቀመው ነው እንጂ ትክክል አይደለም ” ብሎ፣ “ መሬት ላይ የሌለ ነገር ሆነ የሚባል ከሆነ ለቀጣይ ትውልድ ምንድን ነው የምናስተላልፈው? ” ሲል ጠይቋል።

አክሎ፣ “ እነዚህ 14 ተማሪዎች ማን ማን ይባላሉ ? ምን ድፓርትመንት ናቸው ? የስንተኛ ዓመት ናቸው ? የሚመውን ይናጋገሩ ” ሲል ገልጿል።

“ ኣዲ ሓቂ ከተማ ፓሊስ ጣቢያ ታስረዋል ” ነው የተባለውና ቼክ አድርጋችሁ ነበር ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ፣ “ ኣዲ ሓቂ ታስረው የነበሩን አስፈትተናቸዋል ” የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

“ ስማቸውን ካረጋገጡልኝ (አሁን ታስረው ያሉ) እኔ ነኝ የማስፈታቸው። ግን ስምና ዲፓርትመንት አምጡ ስንል ‘አናመጣም’ ነው የሚሉት ” ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ከቴሌግራም ገጹ ተነስተዋል መባሉን በተመለከተ ማብራሪያ እንደሰጥ ስንጠይቀውም፣ ከስድስቱ ግቢዎት የተማሪዎች መገናኛ የቴሌግራም ገጽ ተነስተው ከሆነ እንዳላወቀ፣ ከዋናው ከተማሪዎች ኀብረት ግን የተቀነሰ ተማሪ እንደሌለ ገልጿል። (ጉዳዩን የምንከታተለው ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" አብዛኛዎቹ ከአፍሪካ ናቸው !! "

በመጠናቀቅ ላይ ባለው የፈረንጆች 2024 ባሕር አቋርጠው ወደ ስፔን ለመግባት የሞከሩ ቢያንስ 10 ሺሕ 457 ስደተኞች መሞታቸውን ' ካሚናንዶ ፍሮንቴራስ '  የተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም አስታውቋል።

ካለፈው ዓመት ጋራ ሲነጻጸር በ58 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየም ድርጅቱ ጠቁሟል።

በአሐዙ መሠረት በቀን 30 ፍልሰተኞች ወደ ስፔን ለመሻገር ሲሞክሩ ሕይወታቸውን ያጣሉ። ይህም ከ2023 ጋራ ሲነጻጸር በ18 ጨምሯል።

ከሟቾቹ ውስጥ 1 ሺሕ 538 ሕጻናትና 421 ሴቶች እንደሚገኙበት ተገልጿል።

ድርጅቱ መረጃ መሰብሰብ ከጀመረበት ከእ.አ.አ. አቆጣጠር 2007 ወዲህ ከፍተኛው የሟቾች ቁጥር የተመዘገበበት ዓመት መሆኑም ተነግሯል።

በወጉ ያልተሠሩ ጀልባዎች፣ አደገኛ የባሕር ላይ ሁኔታዎች እንዲሁም የነፍስ አድን አገልግሎት ሰጪዎች በቂ አቅም ስለሌላቸው ችግሩ ሊባባስ መቻሉንም ድርጅቱ ጠቁሟል።

ተጎጂዎቹ ከ28 ሀገራት ሲሆኑ በዋነኝነት ግን ከአፍሪካ ናቸው።

በዓመቱ 60 ሺሕ 216 ፍልሰተኞች ስፔን መግባታቸው መታወቁን ቪኦኤ ዘግቧል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#EHRC #EHRDC

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) እና የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ማዕከል በኢፌድሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ታግደዋል።

ስለ እግዱ ኢሰመጉ ምን አለ ?

ላለፉት 33 አመታት በሀገሪቱ የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ፥ ዲሞክራሲ እንዲስፍን እና የህግ የበላይነት እንዲከበር ከፍተኛ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየ አንጋፋ ድርጅት እንደሆነ ገልጿል።

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሠልጣን ታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም የተጻፈ ደብዳቤ በቀን ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓ/ም ድርጅቱ በደረሰው መሰረት እገዳ እንደተጣለበት አመልክቷል።

ምክንያት የተባለው ምንድነው ?

ለኢሰመጉ መታገድ ምክንያት የተባለው ፤
° ከተቋቋመለት አላማ ውጪ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ፤
° ገለልተኛ እንዳልሆነ፤
° በ2023 የበጀት አመት የአስተዳደር ወጭ ገደብ ጠብቆ ባለመስራቱና ኃላፊነት በጎደለው መልኩ እየተንቀሳቀሰ ነው በሚል ነው ድርጅቱን ከማንኛውም የስራ እንቅስቃሴ የታገደው።

ሆኖም ዕግዱን ተከትሎ ኢሰመጉ በጉዳዩ ላይ ለማንኛውም መገናኛ ብዙሃን የሰጠው መግለጫ የለም።

ኢሰመጉ ፤ ሁሌም ቢሆን ሕግና ስርዓትን ጠብቆ የሚንቀሳቀስ ነፃና ገለልተኛ የሰብዓዊ መብት ድርጅት መሆኑን ገልጾ በአሁኑ ሰዓት ዕግዱ በሚነሳበት ሁኔታ ላይ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር በመነጋገር ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

በዚህም ምንም አይነት መግለጫ የማውጣት ሃሳብ አልነበረውም።

ሆኖም ግን በማህበራዊ ድረገጽ ኢሰመጉ የፖለቲካ እንቅስቃሴ በማድረጉ እና በመሳሰሉት ምክንያቶች እንደታገደ የሚገልጹ ጽሁፎች እየተንሽራሽሩ በመሆናቸው መግለጫ ለማውጣት መገደዱን አመልክቷል።

ድርጅቱ በማሀበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተንሽራሸሩ የሚገኙት ሃሳቦች በባለስልጣኑ ስለዕግዱ ከተሰጡት ምክንያቶች ጋር ፈጽሞ የማይገናኙ የኢሰመጉን ዓላማና ተግበር የማይወክሉ እና መልካም ስራውን ለማጥፋት የሚደረጉ ሙከራዎች ናቸው ብሏቸዋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ምን አለ ?

ባለፉት አራት አመታት ድርጅቱ በርካታ ሥራዎችን ሲያከናውን የቆየ መሆኑን በዋነኝነት ለበርካታ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች የተለያዩ ሥልጠናዎችን በመስጠት እና የውትወታ (advocacy) ስራዎችን ሲያከናውን እንደቆየ ገልጿል።

ድርጅቱ የተቋቋመለትን አላማ ሊያሳካ በሚያስችል መልኩ የአገሪቱን ህጎች ባከበረና አለም አቀፍ መስፈርቶችን ባሟላ መልኩ እንደ አንድ የሰብአዊ መብት ድርጅት ሲንቀሳቀስ የቆየ መሆኑን ጠቁሟል።

ይሁንና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን መስሪያ ቤት በፃፈው ደብዳቤ ድርጅቱ ከማንኛውም እንቅስቃሴዎች እገዳ የተጣለበት መሆኑን ገልጿል።

ምክንያት ?

" ባለስልጣኑ በድርጅቱ ላይ ባደረገው የክትትልና ግምገማ ስራዎች ድርጅቱ ከተቋቋመበት አላማ ውጭ መንቀሳቀሱ፣ ገለልተኛ አለመሆኑ፣ ግልፅ የሆነ የአደረጃጀት መዋቅር የሌለው መሆኑ እና ሃላፊነት በጎደለው መልኩ የተንቀሳቀሰ መሆኑ በተደረገ ክትትልና ግምገማ ለማረጋገጥ መቻሉ ነው " ተብሏል።

ድርጅቱ ግን ከተመስረተበት ጊዜ አንስቶ ከተቋቋመበት አላማ ውጪ በየትኛውም ያልተገባ ወይም ከህግ የሚጻረር እንቅስቃሴ ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተሳትፎ የማያውቅ መሆኑን ገልጿል።

ድርጅቱ በማያውቀው መልኩና ሃሳቡም በህግ አግባብ ባልተጠየቀበት ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ክትትልና ግምገማ ያካሄደ መሆኑን ገልጾ የተጣለው እገዳ አግባብነት እንደሌለው እና ህግን የተከተለ እንዳልሆነ በመግለፅ  በእግዱ ላይ በቂ ማብራሪያ እንዲሰጠው የሚጠይቅ ደብዳቤ ዛሬ ለባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ያስገባ መሆኑን አሳውቋል።

ዝርዝር ማብራሪያ የመጠየቂያ ደብዳቤ አይቶ ውሳኔ እስኪሰጠን ድረስ ድርጅታችን ከየትኛውም ሥራዎቹ ታግዶና ጽ/ቤቱም ተዘግቶ የሚቆይ መሆኑን የአገልግሎቶቻችን ተጠቃሚ ለሆኑ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች፣ ለአጋር ድርጅቶች እና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሁሉ እናሳውቃለን፡፡

እገዳ የተጣለበት ድርጅቱ ፅ/ቤቱ ተዘግቶ እንደሚቆይ አመልክቷል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

🔴 “ በቡድንም ሆነው ቅሬታ እያቀረቡ ያሉ አሉ። ‘ፌደራል ጋር ስንሄድ እኔ ይህንን ጉዳይ አላወረድኩም ነው’ የሚለን ” - ተሽከርካሪ አስመጪዎች

🔵 “ ክልሎችን እንዲህ አድርጉ፣ እንዲህ አታድርጉ ብሎ ቀጥታ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እነርሱን የማዘዝ ስልጣን የለውም ” - ገቢዎች ሚኒስቴር

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ተሽከርከሪ አስመጪዎች፣ የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ባወረደው የደብዳቤ መመሪያ ከአቅም በላይ ግብር እየጠየቃቸው መሆኑን በተመለከተ ያደረባቸውን ቅሬታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል።

አስመጪዎቹ፣ “ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አዲስ መመሪያ አውርዶ ከአቅማችን በላይ ግብር እየጠየቀን ነው ” ነበር ያሉት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ በወቅቱ ምላሽ የጠየቃቸው የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ፣ መመሪያው የግብር ስወራን ለማስቀረት እንደወረደ፣ ይህን ማድረግም የቢሮው ማንዴት መሆኑን የሚመለከት ምላሽ ሰጥተውን ነበር።

“ ግብር ስወራው ተጨባጭ እንደሆነ በሸጡት መኪና ልክ ዋጋ እንደማይቆረጥ የተረጋገጠ ነው ” በማለት ኃላፊው የሰጡትን ዝርዝር ማብራሪያም ማቅረባችን ይታወቃል።

አስመጪዎቹ በበኩላቸው፣ “ በቡድንም ሆነው ይህን ቅሬታ እያቀረቡ ያሉ አሉ። ፌደራል ጋር ስንሄድ 'እኔ ይህንን ጉዳይ አላወረድኩም ነው' የሚለን” ብለው ስለጉዳዩ ገቢዎች ሚኒስቴር እንዲጠየቅ አሳስበዋል።

“ ለምሳሌ የአዲስ አበባ አስመጪና የክልል አስመጪ ተመሳሳይ መኪና አምጥተው ቢሸጡ። የአዲስ አበባው 45% ግብር እየከፈለ ያኛው በድሮው በ5% ይከፍላል። ይሄ ትልቅ ልዩነት ነው የሚያመጣው ” በማለት ያለውን ሰፊ ልዩነት ሚኒስቴሩ እንዲያጤንላቸው ጠይቀዋል።

አስመጪዎቹ ተመሳሳይ ተሽከርካሪ እያመጡ እያለ አዲሱ መመሪያ የሚጠየቁት ግብር ግን አዲስ አበባ ውጪ ካሉት አስመጪዎች ስለሚለያይ መመሪያውን ገቢዎች ሚኒስቴር ያውቀው እንደሆን እንዲጠየቅላቸው መጠየቃቸውን በመግለጽ፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሚኒስቴሩን ማብራሪያ ጠይቋል።

ተሽከርካሪ አስመጪዎቹ “ ተመሳሳይ ፕሮዳክት እየመጣ እንዴት የተለያዬ ክፍያ ይኖራል ? ” የሚል ጥያቄ አላቸው፤ ቢሮው በበኩሉ የታክስ ስወራ ለማስቀረት መመሪያውን እንዳወረደና ይህን የማድረግ ማንደቱ እንዳለው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል፣ ማንዴቱ ለቢሮው የተሰጠ ነው ? የሚል ጥያቄ አቅርበናል።

የተሰጠው ምላሽስ ምንድን ነው ?

ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስለጉዳዩ የጠየቅናቸው አንድ የኮሚዩኒኬሽን አካል ተከታዩን ቃል ሰጥተዋል።

“ የክልልን እና የሚኒስቴሩን ስልጣን ያስቀመጠው ህገ መንግስቱ ነው።  የሚሉትን መመሪያውንም አላወኩትም።

እነኛን መመሪያዎች ማዬት ይጠይቃል። ክልሎችን እንዲህ አድርጉ፣ እንዲህ አታድርጉ ብሎ ቀጥታ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እነርሱን የማዘዝ ስልጣን የለውም።

የጋራ መድረክ አለን። በእዛ የጋራ መድረክ ላይ አሰራራችሁ እንዴት ነው ? የማለት እንጂ በፌደራል ስርዓት የፌደራል መስሪያ ቤት የክልል መስሪያ ቤቶችን እንደዚህና እንደዛ አድርጉ ብሎ የማዘዝ ስልጣን የለውም።

የውይይት የጋራ መድረክ አለን። የክልል ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ጉዳዩን ከእነርሱ ጋር እንዲነጋርና ያሉት ጉዳይ ላይ ምንድን ነው ያለው ? አስተካክሉ የሚል የጋራ መድረክ ስላለን እዛም ላይ አንስቶ በግልም ሂዶ ሊነጋገርበት ይችላል።

መመሪያ ቁጥሩን ላኩልን። ከክልል ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ጋር እንንነጋገርበታለንና የአዲስ አበባዎች ጋር እንወያያለን። 

የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የራሳቸው ስለሆኑ፣ ግን ይሄ የተጣጣመ እንዲሆን ይሄ ቢሆን ብሎ መነጋገር ይቻላል። በዛ አግባብ ልንነጋገር እንችላን። በአዛዥና በታዛዥነት መንፈስ ሳይሆን ማለት ነው ”
ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ የቅሬታ ነጥቡ መመሪያው አዲስ አበባ ያሉ ስመጪዎችን የሚጠይቀው ግብር ከአዲስ አበባ ውጪ ካሉት ተመሳሳይ ተሽከርካሪ ከሚያመጡት ጋር ሲነጻጸር ጭማሪ ያለው መሆኑ ነው፤ ሚኒስቴሩ የሚጥለው የግብር መጠን አንድ መሆን የለበትም ወይ ? የአዲስ አበባ ከተማ ብቻ የተለዬ መሆን አለበት ? የሚል ጥያቄ አቅርቧል።

እኝሁ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አካል፣ “መመሪያውን ቢለኩልንና ከእነርሱ ጋር ብንነጋገርበት ይቻላል” የሚል ምላሽ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።

አስመጪዎቹ በደብዳቤ መልክ ወርዷል ያሉትን መመሪያ ከላክንላቸው በኋላ በሰጡን ምላሽ ደግሞ፣ “ መሄድ ያለብንን እንሄዳለን እንጂ ለህዝብ አሁን እንዲህ ነው እያልን ምላሽ አንሰጥም በዚህ ላይ። ለማንኛውም አየዋለሁ የሚሆነውን እናደርጋለን ” ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#DStvEthiopia

💥 የBoxing Day ፍልሚያዎች ዛሬ ይደረጋሉ!

የሊጉ መሪ ሊቨርፑል የነጥብ ልዩነቱን ያሰፋል ወይስ ቼልሲ፥ አርሰናልና ማን ሲቲ ልዩነቱን ያጠቡታል?

ያጓጓል!

👉እነዚህን ድንቅ ፍልሚያዎች ጨምሮ ሌሎች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይመልከቱ።

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et

#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የሐይማኖት ሐገር የሆነችውና በርካታ የችግር መፍቻ ባህልና ልምድ  ያላት ሀገር ላይ ዜጎች በሰላም እጦት ምክንያት መቸገር  የለባቸውም ! " - የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ

የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መሐመድ እድሪስ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮችና  የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ትውውቅ ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ሚኒስትሩ በሰላም ግንባታና በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከጠቅላይ  ምክር  ቤቱ ጋር ትብብራቸውን እንደሚያጠናክሩ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም  ቱፋ  ምን አሉ ?

-  መጅሊሱን ለመጎብኘት  ሚኒስትሩ  መምጣታቸው በራሳቸው እና በጠቅላይ  ምክር ቤቱ  ስም አመስግነዋል።

- የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሙስሊሙን አንድነትና የሐገራችንን ሰላም ለማጠናከር  የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ ጅምሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል  ተናግረዋል።

- ጠቅላይ ምክር ቤቱ በቀጣይ በሚያካሄደው የመጅሊስ ምርጫ መንግስት በተለይ የሰላም ሚኒስቴር አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።


የሰላም ሚኒስትር አቶ መሐመድ እድሪስ ምን አሉ ?

° በዓለም መድረክ ላይ የሃገራችንን ኢትዮጵያን  ስም ከፍ ለማድረግ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ እየሰሩ  ያሉትን ስራ አድንቀዋል።

- በአፋርና በሱማሌ ወንድም ሕዝቦች መካከል የነበረውን የቆየ አለመግባባትና ግጭት ለመፍታት ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለሰራው ስራ ምስጋና አቅርበዋል።   በቀጣይ ሁሉ አቀፍ የሰላምና የልማት ስራዎችን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

° የሐይማኖት ሐገር የሆነችውና በርካታ የችግር መፍቻ ባህልና ልምድ  ያላት ሀገር ላይ ዜጎች በሰላም እጦት ምክንያት መቸገር እንደሌለባቸው ተናግረዋል።

° ጠቅላይ ምክር ቤቱ አሁን ያለው ሰላም እንዲጎለብት ፣እየታዩ ያሉ የሰላም ፈተናዎች እንዲፈቱና ዘላቂ መፍትሄ እንዲመጣ ሀገራዊ የሰላም ጥሪና ዱዓ በጁምዓ ሰላት ላይ  የሰላም ጥሪ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

° መንግስት ግጭቶች በንግግር እንዲፈቱ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ያቀረበ እና ለዚህም ቁርጠኝነቱ ያለው መሆኑን ገልጸው የሰላም ሚኒስቴርም ከሁሉም የእምነት አባቶችና ተቋማት ጋር በትብብር እንደሚሰራ አመልክተዋል።

° መጭው የመጅሊስ ምርጫ በሰላማዊ ሁኔታ እንዲካሄድ መንግስት አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ አሳውቀዋል።

#MinistryofPeace

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ፓስፖርት

🚨 " በምሽት ጊዜ ለጾታዊ ጥቃት ጭምር የተዳረጉ ሴቶች እንዳሉ ሰምተናል " - የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም

🔴 " ሁኔታዎቹ ከመንገድ መዘጋጋት ጋር በተያያዘ የተፈጠሩ ናቸው " -ኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት

" በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚጠበቅብንን ክፍያዎችን እና መረጃዎች አሟልተን በቀጠሮአችን መሰረት በመገኘት ፓስፖርት እንዲሰጠን ለብዙ ጊዜ ብንመላለስም አገልግሎቱን ማግኘት አልቻልንም " ያሉ ተገልጋዮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አቀረቡ።

" ከምልልሱም በላይ ያለምንም ህጋዊ ምክንያት ከ2000 እስከ 5000 ብር ከፍለን ቀጠሮ አስይዘን በቀጠሮአችንም ተገኝተን እያለ የቀጠሮ ቀን ተቃጥሏል አዲስ ቀጠሮ መያዝ አለባችሁ በመባላችን ላልተገባ ወጭ እና እንግልት ተዳርገናል " ነው ያሉት።

ተገልጋዮቹ አስተዳደራዊ እና ተቋማዊ በደል ደርሶብናል ሲሉ አቤቱታቸውን ለኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አቅርበዋል።

የእንባ ጠባቂ ተቋምም በቁጥር 127 የሚሆኑት እነዚህ ቅሬታ አቅራቢ ተገልጋዮች ለተቋሙ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ጉዳያቸውን በመመልከት ምላሽ እንዲሰጡበት ለኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በደብዳቤ ጠይቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው " አመልካቾች የሚጠበቅባቸውን ክፍያ እንዲሁም መረጃዎችን አሟልተው በተገኙበት እና የቀጠሮ ቀናቸው በምን ህጋዊ ምክንያት እንደተቃጠለ የሚገልጽ መልስ እና ማስረጃ ይህ ደብዳቤ በደረሳችሁ በ05 (አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ እንድትልኩ እንጠይቃለን " ይላል፡፡

እንባ ጠባቂ ተቋሙ ደብዳቤውን የጻፈው 01/04/17 ዓ/ም ሲሆን በአምስት የስራ ቀናት ምላሽ እንዲሰጠው ጠይቆ ነበር።

ነገር ግን ከተቋሙ ምንም አይነት ምላሽ አለማግኘቱን በኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የመንግስት ተቋማት አስተዳደር በደል መርማሪ ባለሞያ የሆኑት አቶ እንዳየሁ ውቤ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

መርማሪው በዝርዝር ምን አሉ ?

" ቅሬታቸውን ይዘው ወደ ተቋማችን የመጡ ተገልጋዮች በመጀመሪያ 127 የነበሩ ቢሆንም በኋላ ቀስ በቀስ 205 በላይ ደርሰዋል።

በቦታው ተገኝተን ባደረግነው ምልከታ ተመሳሳይ የሆነ መጉላላት ያጋጠማቸው ዜጎች ግን ከ5 ሺ በላይ እንደሚገመቱ ታዝበናል።

ተገልጋዮቹ ከደሴ እና የተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ፓስፖርት ለማውጣት በቀጠሮአቸው መሰረት የመጡ ቢሆንም ነገር ግን አገልግሎቱን በጊዜ ባለማግኘታቸው እና እዛው ለማደር በመገደዳቸው ምክንያት በምሽት ጊዜ ለጾታዊ ጥቃት ጭምር የተዳረጉ ሴቶች እንዳሉ ሰምተናል።

አብዛኞቹ ከደሴ፣ ወሎ ፣ከጎንደር እና ሎሎችም ሩቅ አካባቢዎች ወደ ባህር ዳር መጥተው ለሶስት እና አራት ቀናት ለማደር እየተገደዱ ነው የሚበላው አጥቶ የሚለምንም አለ ተርበናል እያሉ የሚያለቅሱም አሉ " ብለዋል።

ከ6 ወር እስከ አንድ አመት ለሚጠጋ ጊዜ እየተጉላሉ ያሉት እኚህ ተገልጋዮች አብዛኞቹ ጉዳያቸው ከአሻራ ጋር የተገናኘ ነው።

መርማሪው ደብዳቤውን ለባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ ለአቶ አስማረ ጫኔ በአካል በመገኘት የሰጡ ሲሆን በወቅቱ ለሃላፊው ቀጠሮአችውን ሳያጠፉ ተቃጥሎባቸዋል ብላችሁ በአዲስ ተመዝገቡ ያላችኋቸው ለምንድነው ? የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውን ነግረውናል።

ሃላፊው በምላሻቸው ከታህሳስ 1 ጀምሮ አዲስ መመሪያ በመምጣቱ ቀጠሮ ያለፋቸው ተገልጋዮች እንደ አዲስ ተመዝግበው ብቻ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ነግረውናል ብለዋል።

ነገር ግን ቅሬታ አቅራቢ ተገልጋዮቹ በቀጠሮአቸው የተገኙ በመሆናቸው አዲስ የተባለው መመሪያ የማይመለከታቸው እና ከቅሬታ አቅራቢዎቹ ጋር የማይገናኝ በመሆኑ ምላሽ የሚሉትን ነገር በደብዳቤ እንዲያሳውቁ በመንገር እንደተመለሱ አስታውሰዋል።

ይሁን እንጂ እስካሁን ምንም አይነት ምላሽ ተቋሙ አለመስጠቱን ገልጸው በድጋሚ ደብዳቤ ለመጻፍ እየተዘጋጀን ነው ብለዋል።

ነገር ግን የአሁኑ ደብዳቤ ለሃላፊው በስሙ እንዲጻፍ የሚደረግ መሆኑን ጠቅሰው በድጋሚ ምላሽ የማይሰጡ ከሆነ ጉዳዩ ወደ ክስ እንደሚያመራ አቶ እንዳየሁ ተናግረዋል።

ቲክቫህ የቅሬታ አቅራቢዎቹን እና የዕንባ ጠባቂ ተቋምን ቅሬታ በመያዝ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑትን አቶ አስማረ ጫኔን  ምላሽ ጠይቋል።

ሃላፊው በምላሻቸው ምን አሉ ?

" ሁኔታዎቹ ከመንገድ መዘጋጋት ጋር በተያያዘ ምክንያት በቀጠሮ ስለማይመጡ የቀጠሮ መደራረብ ጋር የተያያዙ ችግሮች ናቸው።

ይህንን ችግር ለመቅረፍ ምሽትን ጨምሮ ቅዳሜ እና እሁድም ያለምንም ቅጣት አገልግሎት ስንሰጥ ቆይተናል " ብለዋል።


ስለ ዝርዝር ነገሮች ግን ምላሽ የሚሰጠው በዋና መስሪያ ቤት ደረጃ መሆኑን በመግለጽ ተጨማሪ ማብራሪያ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

🤙🏽ከሳፋሪኮም ወደ የቴሌ የሚያስደውሉ የድምፅ ጥቅሎች በመጠቀም ከ07 ➡️ 09 መስመር በሽ በሽ ብለን እንደዋወል! ከሳፋሪኮም ጋር በአብሮነት አንድ ወደፊት⚡️

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle


#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

“ አቶ ዮሐንስን ቧያለውን ለይተው ‘ዞን አምስት’ የሚባል ቦታ አስገብተውታል። ያ ቦታ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሰው ከባድ ጥፋት ሲያጠፋ መቅጫ ነው ” - ጉዳዩን የሚከታተሉ አካል

ለ1 ዓመት ከ5 ወር በእስራት ላይ የሚገኙት የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል አቶ ዮሐንስ ቧያለው አብረዋቸው ከነበሩት 41 እስረኞች ተለይተው “ ለሕይወታቸው አስጊ ወደሆነ ቦታ ” ለማዘወር ተገደዋል ይህ ደግሞ ጭንቀት ፈጥሮብናል ሲሉ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ አካል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ሰኞ ታኀሳስ 14 ቀን 2017 ዓ/ም 41 እስረኞች ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ወደ ቂሊንጦ እንደተዘዋወሩ ገልጸው፣ አቶ ዮሐንስን ለይተው “ በ‘ሸኔ ተጠርጥረው’ ካሉ ሰዎች " ጋር ወስደዋቸዋል ሲሉ ጠቁመዋል።

በመሆኑም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ያሉበትን ቦታ ጎብኝተው የአቶ ዮሐንስን ሕይወት ደህንነት እንዲያረጋግጡ ጠይቀዋል።

ስለአቶ ዮሐንስ ቧያለው በዝርዝር የተባለው ምንድን ነው ?

“ ትላንት እስረኞቹን ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ወደ ቂሊንጦ አዘዋውረዋል። 41 እስረኞችን ነው ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የወሰዱት። 

ከዚያ በኋላ አቶ ዮሐንስን ቧያለውን ለይተው አስቀርተው ‘ዞን አምስት’ የሚባል ቦታ አስገብተውታል። ያ ቦታ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሰው ከባድ ጥፋት ሲያጠፋ መቅጫ ነው።

እዛ ውስጥ ያሉት በ'ሸኔ' ተጠርጥረው ያሉ ሰዎች ናቸው።  ለይተው ከእነርሱ ጋር ነው  ያስቀመጡት። ‘ሸኔ ናችሁ’ ተብለው የታሰሩ፣ ‘ሸኔ’ የተባሉ ልጆች ናቸው እዛ ያሉት።

ይሄ ሁኔታውን ያከብደዋል። በዛ ላይ ደግሞ ኦፕራሲዮን ከተሰራ ሁለት ሳምንቱ ነው። አሁን ካስገቡት ቦታ አልጋ የሚባል ነገር የለም። ባዶ መሬት ላይ ነው እየተኛ ያለው።

አቶ ዮሐንስ አሁን የገባበት ቦታ በጣም የሚያሰጋ፣ እንኳን ኦፕራሲዮን የተደረገ ጤነኛ ሰውም የሚታመምበት ክፍል ነው። ቤቱ በጣም ቅዝቃዜ ስላለው እያነከሰ ነው። ”
ሲሉ ገልጸዋል።

አቶ ዮሐንስ ከ41 እስረኞች ተለይተው የተወሰዱት ምክንያት በግልጽ ሳይታወቅና ከአቶ ክርስቲያን ታደለ ጋር ኦፕራሲዮን ተሰርተው የነበረ ቢሆንም በቀጠሯቸው ቀን ሀኪም ቤት ሳይሄዱ በቀሩበት ሁኔታ መሆኑ ተገልጿል።

አሁንም የጤናቸው ጉዳይ አሳሳቢ እንደሆነ፣ ለአቶ ዮሐንስ ማስታገሻ መድኃኒት እንኳ ለመውሰድ ፈቃድ እንዳልተገኘ፣ ቁስላቸውን መመርመር ባለመቻላቸው በጠና እየታመሙ መሆናቸውን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ አካላት ጠቁመዋል።

አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና ክርስቲያን ታደለ በአዋሽ አርባ እስር ቤት በነበሩበት ወቅት በጠና ታመው በጊዜው ባለመታከማቸው ለአንጀት ድርቀት በሽታ ተጋልጠው ከቆዩ በኋላ ከሳምንታት በፊት ቀዶ ጥገና ቢደረግላቸውም በቀጠሯቸው ቀን ወደ ህክምና ለመሄድ መከልከላቸውን መነገሩ ይታወሳል።

(የአቶ ዮሐንስን የቦታ ለውጥ እንዲገመግሙ መልክዕት የተላለፈላቸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ድርጊቱን ገምግመው ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆኑ ማብራሪያቸው በቀጣይ ይቀርባል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ዛሬ የተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 5 ነው ፤ ካለፈው አንጻር የዛሬው ጠንካራ ነው " -  አታላይ አየለ (ፕ/ር)

ዛሬ አመሻሽ ላይ በሬክተር ስኬል 5 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ።

አመሻሽ 12 ሠዓት ከ26 ላይ በፈንታሌ አካባቢ በሬክተር ስኬል 5 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል።

በዩኒቨርሲቲው የጂኦ ፊዚክስ ሕዋ ሣይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ሣይንስ መምህርና ተመራማሪ አታላይ አየለ (ፕ/ር) ምን አሉ ?

" የመሬት መንቀጥቀጡ በተደጋጋሚ እየተስተዋለ ነው።

ባሳለፍነው ቅዳሜ ዕለትም በዚሁ አካባቢ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 3 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመዝግቦ ነበር።

ካለፈው አንጻር የዛሬው ጠንከር ያለ ነው " ብለዋል። (ለኤፍ ኤም ሲ)

ከሰሞኑን በተደጋጋሚ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የሚሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ ሲሆን በሬክተር ስኬል የሚመዘገበው መጠንም ጨምሮ ታይቷል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

" የምግብ ጥራቱ ወርዷል ፤ መጠኑ ቀንሷል 22 ብር በነበረ ጊዜ ይሻላል ፤ የብሩ መጨመር ምንም ነገር ካላስተካከለ ትርፉ ከፍተኛ ኮስት ሸሪንግ / የወጪ መጋራት እዳ ነው " - ተማሪዎች

ከሰሞኑን በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ወጥነት ባለው መንገድ መተግበር የጀመረው የምግብ ሜኑ በተማሪዎች ዘንድ ቅሬታን የፈጠረ ሆኗል።

ምግቡ መጠኑ ቀንሷል፤ ጥራቱም 22 ብር የነበረ ጊዜ ይሻላል የሚል ቅሬታ ነው ተማሪዎች ዘንድ ያለው።

ከዚህ ባለፈ የብሩ መጨመር በተማሪዎች ኮስት ሼሪንግ / ወጪ መጋራት ላይ ከፍተኛ ጭማሪ አድርጎ ተማሪውን ባለዕዳ ከማድረግ ባለፈ አንድም የጥራት መሻሻል አይታይም ፤ ጭራሽ መጠንም ቀንሷል ብለዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስተዳደርና ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶ/ር ሰሎሞን አብርሃ  ስለ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ በጀት (100 ብር) ምን አሉ ?

" የምግብ በጀቱ 100 ብር ሆነ ማለት የግድ የተለየ ለውጥ ይመጣል ማለት አይደለም። የምግብ አይነቱም ሙሉ ለሙሉ አስደናቂ በሆነ መልኩ ይቀየራል ማለት አይደለም፣ ሊቀየርም አይችልም።

ድሮውንም ተማሪዎች በተመደበላቸው 22 ብር ብቻ ሲመገቡ አልቆዩም።

ከፌዴራል መንግሥት የሚመደበው 22 ብር አነስተኛ መሆኑ ስለሚታወቅ ዩኒቨርሲቲዎች በራሳቸው አካሄድ ሲያስተካክሉ ቆይተዋል።

ዩኒቨርስቲዎች ከሚመደብላቸው የተለያየ በጀት እያዟዟሩ በቀን ከ80 እስከ 150 ብር በማውጣት ተማሪዎችን ሲመግቡ ነበር።

የተማሪዎች የምግብ ሜኑ ከመሻሻሉ በፊት አንድ እንጀራን እስከ 24 ብር ድረስ የሚገዛ ዩኒቨርስቲ ነበር። ድሮ ይመደብ የነበረው በጀት አንድ እንጀራ እንኳን በቅጡ የማይገዛ ነበር።

በመሆኑም ይህ አካሄድ የዩኒቨርሲቲዎችን እንቅስቃሴ ስላስተጓጎለና የአሰራር ስርዓታቸው ላይም ችግር ስለፈጠረ፣ የምግብ ሜኑ ሲዘጋጅ ጥናት ተጠንቶ ሀገር አቀፍ የተማሪ ህብረት ተወካዮች ጭምር በአካል በተገኙበት የዩኒቨርሲቲዎች ምግብ ማሻሻያ ተደርጓል።

ተማሪዎች አሁን ካለው ሁኔታ አንፃር ማድረግ ያለባቸው የሚመደብላቸው በጀት በአግባቡ ለእነርሱ መድረሱን እና በቀን የመቶ ብሩ በጀት ተሰልቶ በሳምንት 700 ብር ወጪ መደረጉን፣ እንዲሁም ያንን ወጪ ታሳቢ ያደረገ ሜኑ መቅረብና አለመቅረቡን ማረጋገጥ ነው።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የተማሪዎች ህብረት አደረጃጀትም ኃላፊነት በመውሰድ በአግባቡ መከታተል አለበት " ብለዋል።


ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ የሰሎሞን አብርሃ (ዶ/ር) ንግግር የተወሰደው ለአሐዱ መሆኑን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ዝቅተኛ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ዩኒቨርሲቲዎች እኩል በጀት የሚመደብበት አሰራር አይኖርም " - ትምህርት ሚኒስቴር

ከዚህ በኃላ ዝቅተኛ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ዩኒቨርሲቲዎች እኩል በጀት የሚመደብበት አሰራር እንደሚቀር የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደብላቸው በጀት ባስመዘገቡት ውጤት ልክ እንደሚሆን ሚኒስትሩ ይፋ አድርገዋል።

ይህን ይፋ ያደረጉት ከሰሞኑን በትምህርት ዘርፉ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በተቀናጀ መልኩ ማሻሻል የሚያስችል ስምምነት ትምህርት ሚኒስቴር እና 47 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የቦርድ ሰብሳቢዎችና የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች በተፈራረሙበት ወቅት ነው።

ሚኒስትሩ ፤ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን በመሰረታዊነት ለመቀየር የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ ወሳኝ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የተጣለባቸውን ሃላፊነት በብቃትና በጥራት እንዲፈፅሙ በተለይ ሙስናን ማጥፋት ግዴታ መሆኑን ፕ/ር ብርሃኑ አሳስበዋል።

" ሙስና የትውልድ ጸር በመሆኑ ለትውልዱ አርዓያ የሚሆን ዩኒቨርሲቲ መፍጠር ይገባል " ብለዋል። #ኤፍኤምሲ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#እንድታውቁት

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በድጋሚ የሚፈተኑ ተፈታኞች በበየነ መረብ (ኦንላይን) መመዝገብ እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ተፈታኞች በራሳቸው የሚመዘገቡበት አድራሻ https://register.eaes.et/Online እንደሆነ ተገልጿል።

ይህ የበይነ መረብ (አንላይን) ምዝገባ መተግበሪያ ራስ አገዝ (self services ) ሲሆን ተመዝጋቢዎች የሚፈልጉትን ድጋፍ በመጠየቅ ከማዕከል ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።

(እንዴት መመዝገብ እንደሚቻል ከላይ ይመልከቱ)

(የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት)

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት እስከምሽቱ 4:00 እንዲሰጥ ተወስኗል " - የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ

በአዲስ አበባ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት እስከምሽቱ 4:00 የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ወስኗል።

በዚህ ውሳኔ መሠረት ማንኛውም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ፦
- አውቶቡሶች፣
- ሚዲ ባስ
- ሚኒ ባሶች በመደበኛ ቀን በሚትሰሩበት መስመር እና ቀን ላይ በሚከፈለው ህጋዊ ታሪፍ መሠረት እስከምሽቱ 4:00 አገልግሎት እንዲሰጡ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

ቢሮው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎች እስከምሽት 4:00 አገልግሎት እንዲያገኙና እና የትራንስፖርት ቁጥጥር ሠራተኞች እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ለተግባራዊነቱ ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ቢሮው አገልግሎት ሰጪዎች እስከ ምሽት 4:00 አገልግሎት ባይሰጡስ ምን እንደሚጠብቃቸው በዝርዝር ያለው ነገር የለም።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ሕብር የወጣቶች የቁጠባ ሒሳብ

ከመደበኛ የቁጠባ አይነት የተሻለ ወለድ የሚያስገኝ እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ ጥቅሞችን የያዘ ልዩ የወጣቶች የቁጠባ ሒሳብ ነው፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

📞  ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡
🤳 በቀላሉ አዳዲስ መረጃዎች  እንዲደርስዎ የቴሌግራም ገፃችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፡፡ /channel/HibretBanket
🌐 ሌሎች የማህበራዊ ገፆቻችንን እና ድህረ ገፃችንን linktr.ee/Hibret.Bank ይጎብኙ፡፡

#Youthsaving #hibirYouth #Startsaving

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#አዲስአበባ #አሶሳ

➡️ " በስራ ዘመን ቆይታዬ ይህን ያህል ክብደት የሚመዝን ልጅ ሲወለድ የመጀመሪያው ነው " - ዶ/ር ረታ ትዕዛዙ (ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል

👉 " የ3 ቀን ጨቅላ ህፃን አንገቷ ላይ በአፈጣጠር ትልቅ እብጠት ይዛ የተወለደች ቢሆንም የተሳካ ቀዶ ህክምና ተደርጎላታል አሁን በተሻለ የጤና ሁኔታ ላይ ናት " - አሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል


በአዲስ አበባ ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ቤቴልሄም አመኑ የተባለች እናት 6 ኪሎ ግራም የሚመዝን ወንድ ልጅ በተደረገላት የቀዶ ህክምና በሰላም ተገላገለች።

የሆስፒታሉ የማህፀን ስፔሻሊስት እና የዲፓርትመንት ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ረታ ትዕዛዙ ለኢቢሲ በሰጡት ቃል " በስራ ዘመን ቆይታዬ ይህን ያህል ክብደት የሚመዝን ልጅ ሲወለድ የመጀመሪያው ነው " ብለዋል።

ልጆች ከ5 ኪሎ በላይ ሆነው ሲወለዱ የሚደረግላቸው ህክምና መኖሩን የገለጹት ዶ/ር " ለልጁ የህክምና ክትትል እየተደረገለት ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

በሌላ መረጃ በአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል የተሳካ ቀዶ ህክምና ተደርጓል።

የ3 ቀን ጨቅላ ህፃን አንገቷ ላይ በአፈጣጠር ትልቅ እብጠት (Bilateral huge cystic hygroma) ይዛ የተወለደች ስትሆን  በእብጠቱ ምክንያት ጡት መጥባትም ሆነ እንደ ልቧዋ መተንፈስ አትችልም ነበር።

በ13/4/17 ዓ/ም በሆስፒታሉ የተሳካ ቀዶ ህክምና ተደርጎላት አሁን በተሻለ የጤና ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ተገልጿል።

አሁን እንደልቧ መተንፈስ ጡት መጥባትም ጀምራለች ተብኳል።

በህክምናው ላይ የተሳተፉ ባለሞያዎች ፦
🙏 Surgeons ፦ ዶ/ር ሮቤራ ተሾመ እና ዶ/ር መብራቴ ወ/መድህን
🙏 Anaesthesiologist ፦ ዶ/ር ሲሳይ እብስቱ
🙏 Anesthesia team: ደመቀ ወ/ኪዳን፣ ተሰፋዬ አሰፋ እና ሰለሞን አዳሙ
🙏 Scrub Nurse ፦ሲ/ር ሳይሽልዋል ወርቁ (ቹቹ)
🙏 Circulator Nrs ፦ አልሃጅ ሀሰን እንደሆኑ ሆስፒታሉ አሳውቋል።


@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ለጥንቃቄ

በቴሌግራም መረጃዎች እየተመዘበሩ እንደሆነ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር / ኢንሳ አሳውቋል።

ኢንሳ በዛሬው ዕለት በቴሌግራም መረጃዎች እየተመዘበሩ በመሆኑ ተጠቃሚዎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲል አሳስቧል።

ኢንሳ ብዙ የቴሌግራም አካውንቶች በተለያዩ ማስገሪያ (ፊሺንግ ሊንክ) አማካኝነት መረጃዎች እየተመዘበሩ እንደሆነ ገልጷል።

በመሆኑንም ከማንኛውም የቴሌግራም ተጠቃሚ (ከሚያውቁትም ሆነ ከማያውቁት) ግለሰብ ሊንክ ቢላክ መክፈት ተገቢ እንዳልሆነ እና ወዲያውኑ ማጥፋት እንደሚገባ አሳስቧል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#YonatanBTFurniture

በዓሉን ምክንያት በማድረግ በዕቃዎቻችን ላይ ልዩ ቅናሽ ማድረጋችንን ስናበስርዎ በታላቅ ደስታ ነው!
እነዚህን ረቂቅ የንድፍ ጥበብ የሚታይባቸውን ውብ ዕቃዎች ገዝተው የቤትዎን ድባብ ይቀይሩ!
የውበት፣ የጥራት እና የምቾት ዳር ድንበር ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር!

🌐  የማህበራዊ ገጾቻችንን ይቀላለቀሉ
Telegram 👉 Telegram/yonatanbtfurniture
Facebook 👉 Facebook/yonatanbtfurniture
Instagram👉Instagram/yonatanbtfurniture
TikTok      👉 yonatanbtfurniture?is_from_webapp=1&sender_device=pc">TikTok/yonatanbtfurniture

📍አድራሻችን
1. ፒያሳ እሪ በከንቱ ቢቲ ታወር (ከኢቲዮ ሴራሚክ ዝቅ ብሎ)
2. ከዊንጌት አደባባይ አለፍ ብሎ ከአቢሲኒያ ባንክ ፊትለፊት
3. ከሲኤምሲ አደባባይ ወደ አያት መንገድ መሪ ሳይደርስ (ዘመን ባንክ አጠገብ)

☎️ +251957868686/ +251995272727/ +251993828282

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

“ ሰውኮ በየሰብሉ ውስጥ እየተገደለ እየተገኘ ነው። አንድ ሰው አስቀርተዋል። 10 ሰዎች ገንዘብ ከፍለው ተለቀዋል ” - የሽርካ ወረዳ ቤተ ክኀነት

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሽርካ ወረዳ ታኀሳስ 5 እና 6 ቀን 2017 ዓ/ም 20 ኦርቶዶክሰዊያን በታጣቂዎች እንደታገቱ፣ ከ80 በላይ ከብቶችም እየተነዱ እንደተወሰዱ ነዋሪዎችና የወረዳው ቤተ ክኀነት መግለጻቸው ይታወሳል።

ከእገታው በኋላ የወረዳ ቤተ ክኀነት ሥራ አስኪያጁን ጨምሮ 9 ሰዎች ገንዘብ ከፍለው ተለቀዋል ተብሎ ነበር።

ከወረዳው ቤተ ክኀነት ስማቸው እንዲነገር ያልፈለጉ አካል ከቀናት በፊት፣ “ አንድ ሰው መገደሉ ተረጋግጧል። 11 ሰዎች ያሉበት አይታወቅም ” ብለውን ነበር።

ያሉበት እንዳልታወቀ የተነገረላቸው ታጋቾች ተለቀቁ ?

ታጣቂዎቹ አንድ ሰው አስቀርተው አስሩን ታጋቾች ገንዘብ አስፍለው ከቀናት በፊት እንደለቀቋቸው የወረዳው ቤተ ክኀነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።

“ ሰውኮ በየሰብሉ እየተገደለ እየተገኘ ነው ያለው። አንድ ሰው አስቀርተዋል። 10 ሰዎች ገንዘብ ፍለው ተለቀዋል ” ብሎ፣ “ ሌላም ሴት አዝመራ/ሰብል ውስጥ ተገድላለች ” በማለት ከታገቱት ውጪም ያሉት ላይ ጥቃት እየተፈጸመ መሆኑን አስረድቷል።

“ ከታገቱት 20 ሰዎች መካከልም አንድ ሰው ገድለዋል። አንድ ሰው አስቀርተዋል። ሌላው አስፈላጊውን ገንዘብ ከፍሎ ተለቋል ” ሲልም  ገልጿል።

ችግሩ እየተደጋገመ የመጣ ነውና መፍትሄው ምንድነው ? ለሚለው ጥያቄ የወረዳው ቤተ ክኅነት ምላሽ፣ “ መልዕክት አስተላልፈን አስተላልፈን አቆቶናል ” የሚል ነው።

“ አሁንም መፍትሄ አልተገኘም። ዞሮ ዞሮ ጉዳዩ በጣም ስር የሰደደ ነው። መንግስትና የጸጥታ አካላት ይኖሩበታልና ያ ሁሉ ካልጠራ ችግሩ ሊጠፋ አይችልም ” ሲል የችግሩን ውስብስብነትና አሳሳቢነት አስረድቷል።

“ ሁሉም ትኩረት ሰጥቶ እዚሁ ላይ ቢሰራና ህዝቡም ራሱን የሚከላከልበት ሞራል የሚሰጠው አካል ቢያገኝ ነው ከዚህ ችግር መውጣት የሚቻለው ” ሲልም አክሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

🔴 “  100 ብር ከተበጀተ በኋላ ከቀረበልን ይልቅ የበፊቱ ምግብ ጥራት አለው ” - የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች

🔵 “ እንደ እውነቱ ከሆነ በ100 ብር በተሰጠው የምግብ ዝርዝር መሰረት ለማስተናገድ የማንችልበት ደረጃ ላይ ነው ያለነው ” - ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ

በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች ከአዲሱ የምግብ ሜኑ ጋር በተያያዘ የምግብ ጥራት ፣ የኮስት ሸሪንግ ጉዳይ ለይ ቅሬታ እንዳላቸው በመግለጽ፣ የሚመለከታቸው አካላት መመሪያውን በድጋሚ እንዲያጤኑት ጠይቀዋል።

በአዲሱ የምግብ ሜኑ መሰረት ከቀረላቸው ምግብ ይልቅ የድሮው ጥራት እንደነበረው አስረድተው፣ ማስተካከያ ካልተደረገበት ትርፉ ከፍተኛ ኮስት ሸሪንግ/ የወጪ መጋራት እዳ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኅብረት በበኩሉ፣ ከምግብ ሜኑው ትግበራ ጋር በተያያዘ ቅሬታ እያቀረቡ ያሉት ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች እንደሆኑ፣ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለዚህ ተጠቃሽ እንደሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጡ ከደባርቅ ዩኒቨርቲ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ አካልን ያነጋገረ ሲሆን፣ ተከታዩን ማብራሪያ ሰጠተዋል።

ዩኒቨርሲቲው በሰጠው ማብራሪያ ምን አለ ?

" መንግስት የተማሪ በጀት ከ22 ነበር ወደ 100 ብር ማሳደጉ ይታወቃል። 22 ብር እያለ ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውንም ሌላም በጀት አጣበው እየደጎሙ አገልግሎት ሲሰጡ ነበር።

ከሌላ በጀት እየተነሳ፣ እየተዘዋወረ አገልግሎት ከመስጠት ለራሱ ወጥ የሆነ የመንግስትንም ያገናዘበ የሀገሪቱን አቅም ያገናዘበ፣ በምግብ ጥራት ሊመጥን የሚችል (አሁን ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር እንዴት እንዳጠናው ባናውቅም) ብር መድቧል። 

በ100 ብር ምን መመገብ ይቻላል ? የምግብ ዓይነቱስ ምን ቢሆን ? ብሎ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ኮሚቴ ተዋቅሮ የአካባቢውን ግብዓት መሰረት ባደረገ አሰራር ዩኒቨርሲቲዎች አገልግሎት እንዲሰጡ ብሎ ለአንድ ተማሪ ምን ያክል ምስር፣ ክክ፣ እንጀራ፣ ዳቦ ያስፈልጋል ብሎ የምግብ ዝርዝር ቋሚ በሆነ መልኩ አቅርቦልናል።

ለኛ የተሰጠን ስራ ግራሙን መቀየር አይደለም። ዝርዝሮቹ 10 ቢሆኑ (ለምሳሌ አዲስ አበባ፣ ደባርቅ፣ መቐለ፣ ደብረ ብርሃን የሚገኝ ሌላም) አንድ ላይሆን ስለሚችል ያን መሰረት አድርገን አገልግሎት እንሰጣለን ”
ብሏል።

ስለተማሪዎቹ ቅሬታ ዩኒቨርሲቲው ምን አለ?

“ ተማሪዎች  ‘በዚህ አንስማማም የተሰጠው የምግብ ዝርዝር የጥራት ችግር ያመጣል’ የሚል ጥያቄ አንስተዋል። ነገር ግን ስራውን ከመጀመራችን ከ4 ቀን በፊት ከተማሪዎች ጋር ውይይት አድርገን መግባባት ላይ ደርሰን ነበር።

ተማሪዎቹ ጥያቄ ካላቸው በኀብረቶቻቸው አማካኝነት እንዲያቀርቡልን፣ እኛም ቀጥታ ከትምህርትና ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ የሚመለከታቸው አካላት ጋር ጥያቄ ካለን በሰላማዊ መልኩ አቅርበን የተሻለ አገልግሎት መስጠት አለብን በማለት ተስማምተን ነው ወደ ስራ የገባነው።

ተማሪዎቹ ‘ምግቡ ድሮ 22 ብር እያለ የተሻለ የሚመስል ነገር ነበረው። ስለዚህ በጀቱ ሲጨምር የምግብ ጥራቱም በዛው ልክ መጨመር አለበት’ የሚል አመለካከት አላቸው።

እኛ ደግሞ የምግብ ጥራቱን የማንጨምርበት ምክንያት መጀመሪያም አሁን ከተመደበው በጀት እኩል/ አንዳንዴም እንደ ወቅቱ የገበያና የፀጥታ ሁኔታ እላፊ ሊሆን ይችላል እንጂ በ22 ብር ብቻ አልነበረም ሲመገቡ የነበረው።

ለምሳሌ ፦ ተማሪዎቻችንን ስንመግብ የነበረው እንጀራ በ23 ብር እየገዛን ነበር። ስለዚህ 22 ብር ብቻ በቂ አልነበረም። በተዘዋዋሪ ተማሪዎቻችን ይህን ያውቁታል። እንዲያው አመፅ ለማስነሳት ምክንያት ፈልገው ካልሆነ በስተቀር።

ሌላው ጥያቄያቸው ‘አሁን የተመደበው 100 ብር ቀጥታ ኮስት ሸሪንግ ላይ ነው የሚያርፈው’ የሚል ሲሆን፣ ይህ ከእኛ አቅም በላይ ነው። ስለዚህ ጥያቄውን ይዘን ለሚመለከተው አካል እናቀርባለን።

ነገር ግን መንግስት ‘የምግብን ኮስት ሸሪንግ ተማሪው ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል’ ካለ አለ ነው። በተዘዋዋሪ 100ም ሆነ 1000 የተጠቀመውን ያክል ነው የሚከፍለው። 

የተማሪዎቹ ጥያቄ ‘ከመጣው ዝርዝር አንፃር የምግብ ጥራቱ በጣም ያንሳል’ የሚል ስለሆነ የምግብ ጥራቱ ይጨምር ከተባለም፣ በእኛ ዩኒቨርሲቲ analysis ሰርተናል። ከዝርዝሩ ውስጥ በርበሬና የሻይ ቅመም አልተካተተም።

የበርበሬና የሻይ ቅመም እንኳን ሳናስገባ ራሱ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅቶ በሰጠን መመሪያ ዋጋ ሽንኩርት ፣ ዳቦ፣ እንጀራ፣ ዘይት፣ ስኳር፣ ጨው የመሳሰሉትን ግብዓቶች ለአንድ ተማሪ የገዛንበትን ዋጋ ስንሰራው 115 ብር እስከ 120 ብር ይመጣል ስለዚህ ከተማሪው በላይ ለኛ ነው ጥያቄ የሆነብን።

አንደ እውነቱ ከሆነ በ100 ብር በተሰጠው የምግብ ዝርዝር መሰረት ለማስተናገድ የማንችልበት ደረጃ ላይ ነው ያለነው።

ይህ ዋጋ የተሰራው አሁን ባለንበት የገበያ ሁኔታ ሲሆን፣ ነገ ሊጨምርም ይችላል። እንኳን ኦቨር ጥራት ተማሪዎች እንደሚጠይቁት ልናደርግ በ100 ብር አጣጥመን ስናስበው ጨረታ በሰጠናቸው ውል በያዝንባቸው ከ100 ብር በላይ ነው የሚመጣው። ይህን በሰነድ ማረጋገጥ ይቻላል።

ስለዚህ በ100 ብሯ ግዴታ አብቃቅተን ማስተናገድ ይጠበቅብናል። ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ዊዝድሮውም፣ ሌላም መረጃ አለ ያንን መሰረት አድርገን ኦዲት እናደርጋለን። በዚህ መሰረት ብሩን ከፍ እናደርጋለን ቁጥጥራችን ከፍ ይላል። 

ለኛም አስጨናቂ ነው የሆነብን ተማሪው ‘አልፈልገውም’ ያለው የምግብ ዝርዝር ራሱ ከተሰጠን በጀት በላይ ነው። ስለዚህ የግንዛቤ ፈጠራዉ እንደ ሀገር አቀፍ አስተያየትም ስላልተሰጠበት ለኛ ፈተና የሆነብን ነገር ይሄ ነው።

ለጊዜው በድሮው የምግብ ዝርዝር ነው እየተጠቀምን ያለነው። እንደኛ ዩኒቨርስቲ ተጨባጭ ጥያቄ ‘አዲሱን አትጀምሩት በድሮው ይቀጥልልን’ የሚል ነው ከተማሪዎቹ የተነሳው።

ለዚህ ደግሞ የዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች ለስራ ጉዳይ አዲስ አበባ ነው  ያሉት ትምህርት ሚኒስቴር ጠርቷቸው። እናም ይህንን ጉዳይ ያነሱታል ብዬ አስባለሁ። 

ይህ ጉዳይ በብዙ አቅጣጫ ቢታይ ዝም ተብሎ አንድ ወገን ላይ ብቻ ጣት የሚቀሰርበት አይደለም። አሁን ላይ ተማሪው የምግብ ጥራት ይልና ኮስት ሸሪንግንም ያነሳል።

‘የምከፍል ከሆነ የምግብ ጥራቱ መጨመር አለበት ነው’ ነጥቡ። እኛ ደግሞ በ100  ብር አስተናግዱ ሲባል እንደ ምግብ ዝርዝሩ 100 ብሩ አያሰራንም አይበቃንም እያልን ነው ያለነው ” ብሏል።


መፍትሄውን በተመለከተ ዩኒቨርሲቲው ምን አለ ?

መንግስት የሰጠው ሜኑ አለ። ተማሪዎች ጥያቄ ካላቸው በሰላማዊ መልኩ ከዩኒቨርሲቲው ማኔጅመን፣ ከተማሪዎች ኀብረት ጋር በመሆን ጥያቄ አቅርቦ መግባባት ላይ መድረስ ነው። 

መግባባት ላይ ከተደረሰ ይህንንም ሊቀበሉ ይችላሉ። መንግስተም ኮንሲደር የሚያደርገው ነገር ሊኖር ይችላል። ስለዚህ የመንግስትን ሀሳብ በጉልበት ከመግፋት ተወያይቶ ጥያቄው ቢፈታ መልካም ነው።

ንብረት እያወደሙ፣ ትምህርት እያቋረጡ ሳይሆን በሰላማዊ መንገድ በተወካዮቻቸው አማካኝተት ጥያቄያቸዌን አቅርበው ውይይት ይደረግበት ”
ሲል አስገንዝቧል።

(የሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችን አስተያዬትና የትምህርት ሚኒስቴርን ምላሽ ለማካተት የተደረገው ጥረት ለጊዜው ያልተሳካ ሲሆን፣ ፈቃደኞች ከሆኑ በቀጣይ እናቀርባለን)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

“ መቐለ ብቻ አይደለም። ትላንት ደብረ ብርሃንም ፣ ደባርቅም ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ተነስቷል ቅሬታው ” - የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኀብረት

🚨 " የታሰሩ ተማሪዎች ተፈተዋል !! "

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን የምግብ በጀት ላይ ትምህርት ሚኒስቴር ማስተካከያ ማድረጉ ይታወቃል።

በዚህም ትምህርት ሚኒስቴር አጠናሁት ባለው ወቅታዊ የምግብ ዋጋ ጥናት መሠረት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን የምግብ በጀት ከታኀሳስ 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በቀን 100 ብር እንዲሆን መወሰኑ አይዘነጋም።

ውሳኔው ተግባራዊ መሆኑን ተከትሎ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአዲሱ የምግብ ሜኑ ቅሬታ እንዳላቸው እየገለጹ ይገኛሉ።

በመቐለ ፣ ደብረ ብርሃን፣ ደባርቅና ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች ትላንት ቅሬታቸውን በአደባባይ መግለጻቸውን የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኀብረት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

በመቐለ ዩኒቨርሲቲ በነበረው በዚሁ ሂደት በተማሪዎቹ ድብደባ እስራት እንደደረሰ፣ ንብረት እንወደመም ተመልክቷል።

በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ትላንት በተፈጠረው ግርግር የታሰሩ ተማሪዎች ተፈቱ ? ምን ያህል ተማሪዎች ናቸው የታሰሩት ? ስንል የጠየቅነው ኀብረቱ፣ “ 27 አካባቢ ተማሪዎች ነበሩ የታሰሩት ” ሲል መልሷል።

ኀብረቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣“ ታስረው የነበሩት ሁሉም የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተፈተትተዋል። አሁን እዛ እየወጣን ነው ” ሲል አረጋግጧል።

“ ሁሉም ነገር ተረጋግቷል። ተቋሙ የራሳቸው በመሆኑ ተማሪዎች መጠበቅ እንዳለባቸው፣ የወደመው ንብረትም በጋራ መስተካከል ያለበት እንዲስተካከል ማሰሰቢያ ተሰጥቶ ሁሉንም አስፈትተናቸዋል ” ነው ያለው።

“ ተማሪዎቹ ታስረው የነበረው ቀዳማዊ ወያኔ እና ኣደ ሓቂ ነበር። ግማሾቹ ከቁኑ ስምንት ሰዓት ገደማ፣ ቀሪዎቹ ደግሞ ከምሽቱ 12 ሰዓት ተኩል ነው የፈቱት ” ብሏል።

በተማሪዎች ላይ ድብደባ ደርሷል የተባለውን በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቀነው በሰጠን ምላሽ ደግሞ፣ “ ተማሪ ላይ ድብደባ ደርሷል። ጉዳትም ደርሷል ” ነው ያለው።

የአዲሱ የምግብ ሜኑ ውሳኔ ቅሬታ ያሳደረው በመቐለ ዩኒቨርሲቲ በሚገኙ ተማሪዎች ብቻ እንዳልሆነ ኅብረቱ ገልጿል።

ኅብረቱ “ መቐለ ብቻ አይደለም። ትላንት ደብረ ብርሃን፣ ደባርቅም በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ተነስቷል ” ሲል ነው ያስረዳው።

“ በይበልጥ የመቐለው ፓለቲሳይዝ ስለሆነ ነው እንጂ በሌሎችም እኮ አለ ሰላማዊ ሰልፍ የወጡበት በዚሁ በሜኑ ጉዳይ። ጉዳዩ አገራዊ ነው እየሆነ ያለው ” ሲልም አክሏል።

የሰላማዊ ሰልፉን ምክንያት በተመለከተ በሰጠን ማብራሪያ ኀብረቱ፣ “ አዲስ የወጣውን የምግብ ፓሊሲ እንቀበላለን አንቀበልም በሚል ነው ” ብሏል።

ቅሬታ የተነሳበትን የምግብ ሜኑውን በተመለከተ ከትምህር ሚኒስቴር ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ለመወያዬት ቀጠሮ እንደያዘም ኅብረቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

“ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲው፣ የመቐለው አሁን ተረጋግቷል። ኮንሰርኑ ግን የ100 ብሯ ጉዳይ  ነው ” ሲልም ገልጿል።

ቅሬታው በሌሎችም ዩኒቨርቲዎች መሆኑን ኀብረቱ በገለጸው መሠረት ቅሬታ አለበት የተባለውን ደባርቅ ዩኒቨርሲቲን የጠየቅን ሲሆን፣ የአዲሱ ሜኑ ጉዳይ ለእርሱም ጥያቄ  እንደሆነበት ገልጿል።

(አዱሱን የምግብ ሜኑ የተመለከተው የተማሪዎቹ ቅሬታና የደባርቅ ዩኒቨርሲቲዝርዝር ማብራሪያ በቀጣይ ይቀርባል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Somalia #Eritrea

የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ኤርትራ ናቸው።

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኤርትራ ፣ አስመራ መግባታቸው ተነግሯል።

አስመራ ሲደርሱ ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ነው ኤርፖርት ተገኝተው የተቀበሏቸው።

የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ ፣በቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ብለዋል።

ፕሬዜዳንቱ በቱርክ፣ አንካራ ከኢትዮጵያ ጋር ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በኢትዮጵያ የባህር በር ተጠቃሚነት ጉዳይ ላይ ስምምነት ከፈረሙ በኃላ ነው ኤርትራ የሄዱት።

አንደንድ ዘገባዎች የኤርትራው እና የሱማሊያው መሪ የአንካራውን ስምምነት አጀንዳቸው ሊያደርጉት እንደሚችሉ አሳይተዋል።

የሶማሊያው መሪ ከዚህ ቀደም ወደ ኤርትራ በመመላለስ የሚታወቁ ሲሆን በተለይ ግን ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ከፈረሙ በኃላ እንዲሁም ኢትዮጵያ ለህዝቦቼ የባህር በር ያስፈልጋቸዋል ይህ የህልውና ጉዳይ ጭምር ነው በማለት አቋማን ይፋ ካደረገችና ዓለም አቀፍ አጀንዳ ካደረገችው በኃላ ደጋግመው ኤርትራ ፣ አስመራ ኢሳያስ ጋር ተመላልሰዋል።

የኤርትራው መሪ በነዚህ ወቅቶች አንድም ጊዜ ሶማሊያ፣ ሙቃዲሾ ለጉብኝት ብለው ሄደው አያውቁም።

ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ የግብፅ፣ የኤርትራ እና የሶማሊያ መሪዎች በአስመራ የሶስትዮሽ ጉባኤ አካሂደው የሶማሊያ ተቋማት እና ጦር ድንበሯን ለመጠበቅ እና የግዛት አንድነቷን ለማስጠበቅ የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሳቸው የሚዘነጋ አይደለም።

#Somlaia #Eritrea

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ከከባዱ አደጋ አንዲትም ጭረት ሰውነታችንን ሳይነካን ነው የወጣነው። ይህን ማድረግ የሚችለው አላህ (ሱወ) ብቻና ብቻ ነው !! " - ሳቢር ይርጉ

ኡስታዝ ሀሺም ሽፋ እና ሳቢር ይርጉ አስከፊ ከሆነ የመኪና አደጋ አንድም ነገር ሳይሆኑ በህይወት ተረፉ።

ዛሬ ምሽት ከሱሉልታ አቅጣጫ አጣና ጭኖ ቁልቁለቱን ሲምዘገዘግ የነበረ ኤኔትሬ ከባድ መኪና ከነጭነቱ እነ ኡስታዝ ሲጓዙበት በነበረችው መኪና ላይ ከባዱ አደጋ አድርሷል።

ሳቢር ይርጉ ፤ " እንሆ የአላህን ኒዕማ አውጀናል። በአላህ ፈቃድ ሁለታችንም ከከባዱ አደጋ ምንም ሳንሆን ተርፈናል። ሁለታችንም አንዲትም ጭረት ሰውነታችን ላይ ሳይደርስ በሰላም ወጥተናል አልሀምዱሊላህ !! ወደ የቤታችንም ገብተናል " ሲሉ ገልጸዋል።

" በህይወት ስንተርፍ ሞትን አንዘንጋው። ይህን ማድረግ የሚችለው አላህ (ሱወ) ብቻና ብቻ ነው። አልሀምዱሊላህ ጀዛኩሙላሁ ኸይር ! " ሲሉ አክለዋል።

አደጋው የደረሰባቸው ዛሬ ምሽት ለጥቂት ቀናት የሊደርሺፕ ስልጠና ለመካፈል እየተጓዙ በነበረበት ወቅት ነው።

መኪናዋን ሲያሽከረክሩ የነበሩት ኡስታዝ ሀሺም ሽፋ ሲሆኑ ሁለቱም ከከባዱ አደጋ አንድም ጭረት ሰይነካቸው በህይወት ተርፈው ወደ ቤት ገብተዋል።

መረጃውን ያካፈሉን በ ' ድምጻችን ይሰማ ' የሰላማዊ እንቅስቃሴና ትግል ወቅት በእጅጉ የሚታወቁት ሳቢር ይርጉ ናቸው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ ተመን ወጪ 100 በሆነበት ማግስት አንድ ዳቦ ለቁርስ ማቅረብ ማሻሻል አይደለም " -የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች

በትላንትናው ዕለት በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ከተሻሻለው የምግብ ሜኑ ጋር በተያያዘ በዩኒቨርሲቲው የተፈጠረ ግርግር ለተማሪዎች መጎዳት እና ለንብረት ውድመት ምክንያት መሆኑ ተሰምቷል።

ለአለመግባባቱ መነሻ የሆነው በትምህርት ሚኒስቴር በተሻሻለው እና በሁሉም የዩኒቨርሲቲዎች ወጥነት ያለው የምግብ ሜኑ እንዲኖር የሚያዘውን መመሪያ ተከትሎ " ዩኒቨርሲቲው አግባብ ባልሆነ መንገድ ተግባራዊ እያደረገው ነው " በሚል ነው።

ዩኒቨርስቲው ከቅዳሜ 12/04/2017 ዓ/ም ጀምሮ አንድ ዳቦ ለቁርስ እየቀረበ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" ከዚህ በፊት ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ዕለታዊ ለቁርስ ይቀርብልን የነበረው ዳቦ ምንም እንኳን መጠኑ በጣም አነስተኛ ቢሆንም ሁለት ነበር አሁን ግን የተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ ተመን ወጪ 100 በሆነበት ማግስት አንድ ዳቦ ለቁርስ ማቅረብ ማሻሻል አይደለም " ሲሉ ወቅሰዋል።

በዚህ የምግብ አቅርቦት ደስተኛ ያልሆኑ የዋና ግቢ እና የዓዲ ሓቂ ግቢ ተማሪዎች ድርጊቱን በመቃወማቸው ለድብደባ እና ለእስር መዳረጋቸውን ገልጸዋል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ በመቐለ ዩኒቨርስቲ የአሪድ የተማሪዎች ምግብ ቤት ሰራተኛን አነጋግሯል።

እኚሁ ሰራተኛ ፤ " ግርግሩ በቁርስ ሰዓት ነበር የጀመረው ተማሪዎቹ በቁርስ ሰዓት ሲቅርብላቸው የነበረው ሁለት ዳቦ ግራሙ ጨምሯል በማለት አንድ ዳቦ እንዲሰጣቸው ተደረገ ተማሪዎቹ ዳቦው አንድ መሆኑን እና የተጨመረ ግራም እንደሌለ ተናግረው የዩኒቨርስቲው አመራሮች እንዲያነጋግሩዋቸው ጠየቁ " በማለት የጉዳዩን መነሻ አብራርተዋል።

" ይሁን እንጂ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት መልስ ባለመስጠታቸው የተቆጡ ተማሪዎች የምግብ ጠረጴዛዎችን ፣ የምግብ ቁሳቁሶችን ፣ መስታወቶችን እና ሌሎች ነገሮች ወደ መስበር ተሸጋግረዋል በምግብ ቤቱ ሰራተኞች ላይ ግን ያደረሱት ጉዳት የለም " ብለዋል።

በቁርስ ሰዓት በአሪድ ካምፓስ የጀመረው ግርግር ወደ ዓዲ ሓቂ ካምፓስ በመዝለቅ እስከ እራት ሰዓት ድረስ በዩኒቨርስቲ ንብረቶች ላይ ውድመት መድረሱን ተገልጿል።

የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን ወደ ካምፓሶቹ የፀጥታ አካላት መላኩ ተነግሯል።

በዚህም ሳቢያ በፓሊስ እና በተማሪዎቹ መካከል በተፈጠረ ግጭት ተማሪዎች የድብደባ ጥቃት እንደደረሰባቸው ተነግሯል።

በሁለቱ ካምፓሶች ግን ለጊዜው ግምቱ ያልተጣራ ንብረት መውደሙን ለመረዳት ተችሏል።

በመቐለ ዩኒቨርስቲ አሪድ እና ዓዲ ሓቂ ካምፓሶች  የተፈጠረው ግርግር በአሁኑ ሰዓት ሙሉ በሙሉ ቆሟል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የዩኒቨርስቲውን የኮሙኒኬሽን ኮርፓሬት ስለ ተፈጠረው ግርግር ማብራርያ እንዲስጥ ያቀረበው ጥያቄ " የጉዳዩ መነሻ እና መድረሻ የሚመለከት ይፋዊ መግለጫ በሚድያ እስከሚሰጥ ጠብቁ የሚል "  ምላሽ ተሰጥቶታል።

በኃላም ተቋሙ ማብራሪያ አውጥቷል።

በዚህም ፦

- በሃገር ደረጃ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሃገራዊ የምግብ ሜኑ በትምህርት ሚኒስቴር ጸድቆ ለትግበራ መላኩን ገልጿል።

- ዩኒቨርሲቲው ከተማሪዎች ህብረት ጋር በመነጋገር የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የምግብ ሜኑን አዘጋጅቶ ወደ ትግበራ መግባቱን አመልክቷል።

- በሜኑው ላይ የሚስተካከሉ ነገሮች ካሉ ብሄራዊ  ሜኑ በይዘት እና በጀት ደረጃ እስካልተለየ ድረስ ጥያቄዎች በተማሪዎች ህብረት በኩል ቀርበው ማስተካከል እንደሚቻል አመልክቷል።

- በሃገር ደረጃ ተግባራዊ የሆነውን የምግብ ሜኑ ተቃውሞ የዩኒቨርሲቲውን መሰረተልማት ማጥፋት እና የካፊተርያ እና የጥበቃ ሰራተኞች ላይ ጉዳት ማድረስ ተማሪዎችን እንዲሁም ማህበረሰቡን እና ሃገሪቱን የሚጎዳና  ተግባር እንደሆነ ገልጿል።

- ተማሪዎች ቅሬታቸውን በሰላማዊ መንገድ መግለጽ እንዳለባቸው አሳስቧል።


ጉዳዩን በተመለከተ የመቐለ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ህብረት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ትክክለኛ ስለመሆናቸው የሚገልጽ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የአቋም መግለጫ ከሚመለከታቸው የማኔጅመንት አካላት ጋር በተደረገ ውይይት ያለኣግባብ የታሰሩ ተማሪዎች እንዲፈቱ እና ያለ መረጃ በተማሪዎች ላይ እርምጃ እንዳይወሰድ መወያየታቸውን ይገልጻል።

በተጨማሪም አዲሱ ሜኑ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እስከሚሆን ድረስ በነባሩ ሜኑ እንዲቀጥል ከመግባባት ላይ መደረሱን ገልጿል።

ህብረቱ ለተማሪዎች ሰላማዊ ጥያቄ ከተማሪዎች ጎን እንደሚቆም ይሁን እንጂ በዋና ግቢ ካፍቴሪያ እና በኣዲ ሓቂ ተማሪዎች ላይ የደረሰው ጉዳት እና ስህተት ፈጽሞ መደገም የለበትም ብሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…
Subscribe to a channel