tikvahethiopia | Unsorted

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1519086

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Subscribe to a channel

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update : ጅቡቲ የሚገኙት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞትዎስ (ዶ/ር) ከጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦመር ጊሌ ጋር ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል።

የውይይቱ ዓላማ የትውውቅ እና በሁለቱ ወንድማማች ሀገሮች መካከል ያለውን የቆየ ወዳጅነት ለማጠናከር ነው የተባለ ሲሆን በውይይታቸው የሁለትዮሽና አህጉራዊ ጉዳዮችን አንስተው መምክራቸውን በጅቡቲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Tigray

በወርቅ ማዕድን ቁፋሮ እና ዝውውር ዙሪያ መረጃዎች በማሰባሰብ ላይ የነበሩ የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች በታጣቂዎች መታገታቸውን ተቋሙ አስታወቀ።

የታገቱት ጋዜጠኞች ብዛት 3 እንደሆነ የገለፀው የሚድያ ተቋሙ ሞባይላቸው ከአገልግሎት ውጪ መደረጉን ጨምሮ ገልጿል። 

ትግራይ ቴሌቪዥን " በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ከህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ፍለጋ እና ዝውውር ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጉዳይ ለማጥራት የተሰማሩ ጋዜጠኞች ናቸው በታጣቂዎች የታገቱት " ሲል አሳውቋል።

ሦስት አባላት የያዘ የጋዜጠኞች ቡድን ዛሬ ታህሳስ 20/ 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 3:00 ጀምሮ በአስገዳ ወረዳ ' ሜይሊ ' ተብሎ ከሚጠራ ልዩ ቦታ በምትገኘው መንደር ነው የታገቱት ተብሏል።

ጋዜጠኞቹ በአከባቢው ስላለው ህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ቁፋሮና ዝውውር በማስመልከት በአካል ቦታው ድረስ በመሄድ የአከባቢውን ነዋሪዎች ፣ አርሶ አደሮችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ሲያነጋግሩ እንደሰነበቱ የገለፀው የትግራይ ቴሌቪዥን " የጋዜጠኞች ቡድኑ በስራ እያለ በታጣቂዎች ሊታገት እና ሊታሰር ችሏል " ሲል አመልክቷል።

የታገቱት የጋዜጠኞች ቡድን ከረፋዱ 4:00 ጀምሮ ሞባይላቸው ከአገልግሎት ውጪ በመደረጉ ምክንያት ያሉበት ሁኔታ እና ድህንነታቸው ማረጋገጥ እንዳልተቻለ አመልክቷል።

ጋዜጠኞቹን የሚመለከት መረጃ ለመጠይቅ በአከባቢው ለሚገኙ የመንግስት አመራሮች ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ቢያደርግም እንዳልተሳከለት የትግራይ ቴሌቪዥን አሳውቋል።

እገታውን ስለፈጸሙ ታጣቂዎች ማንነት በዝርዝር የተባለ ነገር የለም።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የትግራይ ቴሌቪዥን ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Earthquake አዋሽ አካባቢ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ መቀጠሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እየገለጹ ናቸው።

ትላንት ምሽት እንዲሁም ዛሬ ጥዋት አካባቢ ጠንከር ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበር ጠቁመዋል።

እንደ ' አሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ ድረገጽ ' መረጃ  ዛሬ እሁድ ከአዋሽ 33 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሬክተር ስኬል 4.8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ከ30 በላይ የመኖሪያ ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል " - አቶ አብዱ ዓሊ

በአፋር ክልል ጋቢ ረሱ ዞን በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ከ30 በላይ የመኖሪያ ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸው ነዋሪዎች ሌላ አማራጭ እንዲፈልጉ ማስገደዱ ተነግሯል።

በአዋሽ 7 ከተማ አሥተዳደር፣ በአዋሽ ፈንታሌ እና አሚባራ ወረዳዎች በሚገኙ የተወሰኑ ቀበሌዎች የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ መሆኑን የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ አብዱ ዓሊ ገልጸዋል፡፡

በዚህም እስከ አሁን በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ሳቡሬ እና ዶኾ ቀበሌዎች ከ30 በላይ የመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱን አረጋግጠዋል፡፡

ጉዳት በደረሰባቸውና ሌሎችም ሥጋት ባለባቸው መኖሪያ ቤቶች ያሉ ወገኖችን ከአካባቢያቸው ሳይርቁ ቀለል ባለ ባህላዊ ቤት እንዲኖሩ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

በሰው ላይ የተመዘገበ ጉዳት ባይኖርም በሰብል የተሸፈኑ ማሳዎች እና የመኪና መንገዶች ላይ የከፋም ባይሆን የመሰነጣጠቅ አደጋ መድረሱን ገልጸዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኤፍ ኤም ሲ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Architecture

በፍልስጤም ሀገር ለሚገነባ ትምህርት ቤት በተዘጋጀ ዓለም አቀፍ የአርክቴክቸራል ዲዛይን ውድድር ላይ ኢትዮጵያውያኑ ፦
➡️ አርክቴትክት ዳንኤል ዋጁ
➡️ አርክቴርክት ቢንያም በውቀቱ
➡️ አርክቴክት ፍሬዘር አብርሃ ከ231 ተወዳዳሪ አርክቴክቶች መካከል " የጣልያንን ተወዳዳሪዎች " በመከተል የ2ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል።

አርክቴክቶቹ " Mobile school as an emergency Response in Palestine " በተሰኘ ርዕስ በተዘጋጀው በዚህ ውድድር ከአፍሪካ ብቸኛ የደረጃ ተወዳዳሪ መሆን እንደቻሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት ለተከታታይ 5 የተለያዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ለ3 አመት ያክል የሞከሩ ሲሆን በነሱም የተለያዩ ውጤቶችን አስመዝበው እንደነበር ከ3 አመት በኋሏ ግን በአምላክ እርዳታ ለዚህ ከፍተኛ ስኬት መብቃታቸውን ገልጸዋል።

ወጣቶቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት " በሃገራችን ኢትዮጵያም ብሎም በአፍሪካ ብዙ እምቅ ችሎታ ያለቸው ወጣቶች አንዳሉም በጥቂቱ ማሳየት በመቻላችን እጅግ ደስተኞች ነን " ብለዋል።

በውድድሩ ላይ በአርክቴክቸር ሙያ የታወቁ ሎሬቶች እና ባለሙያዎች በዳኝነት ተሳትፈዋል።

ከዚህ ዓለማቀፍ ውድድር 2ኛ በመሆን በማጠናቀቃቸው የ2000 ዩሮ እና የእውቅና ሰርተፍኬት ተሸላሚ በመሆን የሃገራቸውን ስም አስጠርተዋል።

(ያሸነፉበትን ስራ ከላይ ይመልከቱ)

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

“ ከተማሪዎች ጋር የመጣላት ፍላጎት የለንም። ተማሪዎቹ  መነሻ አይደሉም ለብጥብጡ መነሻው  ራሱ ዩኒቨርሲቲው ነው ” - የክፍለ ከተማው ጸጥታ ጽ/ቤት

ከአዲሱ የምግብ ሜኑ ትግበራ ጋር በተያያዘ ቅሬታ ያቀረቡ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ 27 ተማሪዎች ታስረው እንደነበር፣ በኋላም ከእስር እንደተፈቱ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኀብረት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሳል።

ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብት ኢትዮጵያ የተሰኘው ድርጅትም፣ ተማሪዎች ከተወካዮቻቸው በሚገናኙበት ቴሌግራም ላይ በሜኑው ዙሪያ ተቃውሟቸውን አሰሙ በተባሉ 2 ተማሪዎች አማካኝነት በተነሳው ተቃውሞ “14 ተማሪዎች ታስረዋል” ሲል መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።

ነገር ግን አሁንም እስር ላይ ናቸው ያላቸውን ተማሪዎችን ስም፣ ዲፓርትመንት እና ስንተኛ ዓመት እንደሆኑ በይፋ በዝርዝር የሰጠው መረጃ የለም።

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ኅብረት ምንም ተማሪ ሳይቀር መፈታቱን አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ታሰሩ የተባሉት ተማሪዎች ሁሉም ተፈቱ ? ሲል የኣዲ ሓቂ ክፍለ ከተማ ጸጥታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ክብረዓብ ሰለሞንን ምላሽ ጠይቋል።

የጸጥታ ኃላፊው ምን መለሱ ?

“ የተማሪዎች ኀብረት ማለት የተማሪዎች ተወካዮች ናቸው። ስለዚህ እነርሱ ከእኛ ጋር አብረው እየሰሩ ነው። ተደብቀን ዋሽተን የምንሰራው ሥራ የለም። 

ያደረሱት ጉዳት ትልቅ በመሆኑ ሊፈቱ ባይገባቸውም የጉዳዩ መነሻ እነርሱ ሳይሆኑ ዩኒቨርሲቲው ሊያቀርበው የሚገባውን ነገር ባለማቅረቡ የተነሳ ስለሆነ እንደዚህ አድርገዋል ብለን አናስርም በሚገባ አስተምሮ ሰጥተን አንድም ልጅ ሳይቀር ፈትተናቸዋል።

የታሰረ ተማሪ የለንም ለቀናቸዋል። አሁንም ድጋሚ የሚሰሩት ስራ አለ ግን እየተከላከልን ነው። 

አስረን የነበረው 13 ተማሪዎችን ነው። ከ13ቱ መካከል ዋና ዋና ለብጥብጡ ተዋናይ የነበሩ ተማሪዎችን ልንለቃቸው አልፈለግንም ነበር። 

የተማሪዎች ኀብረት ግን ‘እንደዚህ ከሚሆን እኛው ራሳችን እናስተካክለዋለን’ ስላሉን ለቀናቸው ችግሩ እንዲፈታ እየሰራን ነው ”
ብለዋል።

ከሌላና ከኣዲ ሓቂ ፓሊስ ጣቢያ ታስረው የነበሩ 27 ተማሪዎች (13ቱ ኣዲ ሓቂ) ከተፈቱ በኋላ በቴሌግራም ተቃውሞ አስነሱ የተባሉ 14 ተማሪዎች በክልሉ የጸጥታ አካላት ታስረዋል ተብሏል፤ እነርሱ ተፈቱ ወይ ? ስንል በድጋሚ ጥያቄ አቅርበናል።

ኃላፊው ምን አሉ ?

“ ከተማሪዎች ጋር የመጣላት ፍላጎትም የለንም። ተማሪዎቹ መነሻ አይደሉም ለብጥብጡ፣ ለብጥብጡ መነሻው ራሱ ዩኒቨርሲቲው ነው።

ዩኒቨርሲቲው ማቅረብ የነበረበት ጽዳቱና መጠኑ የተጠበቀ ምግብ እኛ ስናየው ተማሪዎቹን ምን ሆናችሁ ነው ከዚህ ደረጃ የሚያደርስ ነው እንዴ ? የሚያስብል ቢሆን ጥሩ ነበር።

ነገር ግን ራሳችን ሂደን ያረጋገጥነው ትልቅ ማስረጃ እያለ ተማሪዎቹ ጋር መበጣበጥ አልፈለግንም። 

ተማሪዎቹ ሀሳባቸውን ሊያቀርቡ ተሰብስበው፣ እኛም ሂደን ስናበቃ ‘የታሰሩት ካልተፈቱ አንረጋጋም’ አሉ። አታስቡ ከወገናቸው ጋር ነው ያሉት፤ ፓሊስ ማለት ወገናችሁ ነው ብለናቸዋል። 

ከተረዳዳን የታሰሩትን ሂደን እናመጣቸዋለን። የብጥብጡ መነሻ ደግሞ እነርሱ (ተማሪዎቹ) አይደሉም። መነሻው ‘በምግብ እየተቸገርን ነው’ ማለታችሁ ነው። ስለዚህ የታሰሩን እንለቃቸዋለን ብለን ለቀናቸዋል ” ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

🚨 #ትኩረት

ዝም አትበሉ !!

በሴቶች ፣ በተለይም ምንም በማያውቁ ፤ ክፉ ደጉን እንኳን በማይለዩ ትንንሽ ህጻናት ላይ የሚፈጸመው የግብረ ስጋ መድፍረት ተግባር እጅግ አሳሳቢ እጅግም እየከፋ እየሄደ ነው።

ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ፥ መቼም ሴት ልጆቻችን ፣ እህቶቻችን ላይ ስለሚፈጸም የአስገድዶ መድፈር / የግብረ ስጋ ድፍረትናከዛ ጋር ተያይዞ ስለሚሰጡ ፍርዶች ብዙ ጊዜ መልዕክት መለዋወጣችን ይታወሳል።

ብዙዎችሁ በምትሰሙት ፍርድ እንደምታዝኑም ህጉ ሊስተካከል እንደሚገባ ስትገልጹ ኖራችኋል።

አንዳንድ ጊዜ " እንደው የሚሰጠው ፍርድ ለጆሮ የሚቀፍ ፣ ሰው ለማስተማርና ለመቅጣት ሳይሆን ወንጀለኞችንና ግፈኞችን ለማበረታታ " እንደሚመስል በመግለጽ መሰል መረጃዎች ለብዙሃን እንዳይሰራጩ የጠየቃችሁ ሁላ አላችሁ።

በተለይ በተለይ ሴት ህጻናትን የሚደፍሩ ሰዎች ምንም በማያጠያይቅ ሁኔታ ' የሞት ቅጣት ' እንዲጣልባቸውም የሚገልጽ ሀሳብ ስትፅፉ ነበር።

ከሰሞኑን ደግሞ የተሰሙት ከህጻናት የግብረ ስጋት ድፍረት / መድፈር ጋር የተያያዙ ፍርዶች በርካታ የቲክቫህ አባላትን አስቆጥቷል፤ አሳዝኗል።

ለመረጃ ይሆናችሁ ዘንድ ...

1. ተከሳሽ ሙሉነህ ኡጋሞ የ37 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን የባለቤቱን እህት የሆነችውን የ12 ዓመት ህጻን ከ3 ዓመት በላይ በቆየ ጊዜ ውስጥ  " ለማንም ሰው ከተናገርሽ እገልሻለሁ ! " በማለት በማስፈራራት በተደጋጋሚ አስገድዶ የግብረ ስጋት ድፍረት እንደፈጸመ የክስ መዝገቡ እንደሚያስረዳ የሲዳማ ክልል ፍትህ ቢሮ ገልጿል።

ተከሳሹ ወንጀሉን የፈጸመው ባለቤቱ በወሊድ ምክንያት ታማ ለ2 ወር ሪፌራል ሆስፒታል ከተኛችበት ከቀን 11/04/2013 ዓ.ም. ወንጀሉ እስከታወቀበት 27/05/2016 ዓ.ም. ድረስ መሆኑ ነው የተገለጸው።

የቀረበውን ክስ ተቀብሎ ሲያከራክር የቆየው የሀዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰውና በሰነድ ማስረጃ በማስደገፍ በቀን 16/04/2017 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት
#በ14_ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

2. የገዛ የአብራኩን ክፋይ የ9 ዓመት ልጁን የደፈረ ወላጅ አባት 17 ዓመት እስር ተፈርዶበታል።

ተከሳሽ አዶኒያስ አቡታ 40 ዓመቱ ሲሆን የ9 ዓመት ህጻን ልጁን በቀን 07/07/2016 ዓ.ም.ከምሽቱ 3፡30 አካባቢ ከቤተሰቦቹ ጋር ተከራይቶ በሚኖርበት ቤት ውስጥ መድፈሩን የዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ ያስረዳል።

ተከሳሹ ድርጊቱን የተበዳይ እናት ቤተሰቧን ለማስተዳደር በከፈተችው የቁርሳ ቁርስ ቤት ውስጥ ለማደር በሄደችበት ዕለት የፈጸመ ሲሆን ተጎጂ ህጻን ተኝታ ካለችበት ቀስቅሶ አስገድዶ መድፈሩ ነው የተጠቀሰው።

የቀረበውን ክስ ተቀብሎ ሲያከራክር የቆየው የሀዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰውና በሰነድ ማስረጃ በማስደገፍ በቀን 16/04/2017 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት
#በ17_ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

3. የ31 ዓመቱ ከሳሽ ልደቱ አስፋ የ7 ዓመት ህጻን ከቀን 01/01/2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ አመት ያህል የተለያ ማባበያዎችን በመስጠት የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል ሲፈጽም መቆየቱን የአቃቤ ህግ የክስ መዝገብ ያስረዳል።

የቀረበውን ክስ ተቀብሎ ሲያከራክር የቆየው የሀዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰውና በሰነድ ማስረጃ በማስደገፍ በቀን 16/04/2017 ዓ.ም. በዋለው በህጻናት ችሎት ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት
#በ18_ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

4. የ5 ዓመት ህፃን ልጅ የደፈሩ 2 ግለሰቦች የ19 ዓመት እስር ተፈርዶባቸዋል።

በወናጎ ከተማ ቱቱፈላ ቀበሌ ኦዶላ ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ የ5 ዓመቷ ህፃን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ዳቦ ለመግዛት በሄደችበት የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል ተፈጸሞባታል።

ወንጀሉን የፈጸሙት አቶ ኤልያስ ኤቶ እና አቶ ታምሩ ንጋቱ የተባሉ የዳቦ መጋገሪያ ቤቱ ሰራተኞች ናቸው።

በግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ክስ የቀረበባቸው ወንጀለኞቹ ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በወናጎ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዋለ ችሎት ሁለቱም ተከሳሾች እያንዳንዳቸው
#በ19_ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ተወስኗል።

5. የ3 ዓመት ከ6 ወር ህጻን ላይ የመድፈር ሙከራ ያደረገው ግለሰብ በ10 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል።

ወጣት ኤርምያስ ፀጋዬ 3 ዓመት ከ 6 ወር በሆነችው ተበዳይ ህፃን ከምትጫወትበት ቦታ ወደ ኤት ኤል ትምህርት ቤት ይዞ በመሄድ የመድፈር ሙከራ ማድረጉን በምስክር ያረጋገጠው የወናጎ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ግለሰቡን
#በ10_ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

ተጨማሪ ፦ የ28 ዓመት እድሜ ያለው ክብሮም ኣብርሃ የተባለ በትግራይ እንዳስላሰ ከተማ የሚኖር ወጣት የ11 እና 12 ዕድሜ ህፃናትን እንዲቀርቡትና እንዲላመዱት በማድረግ በጨርቅ እና በማጣበቂያ ማስቲሽ እንዳይጮሁ አፍኖ የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል መፈጸሙ በመረጋገጡ
#የ16_ዓመት ጽኑ እስራት ተፈርዶበታል።

ውድ የቲክቫህ አባላት ሆይ ፥ እነዚህ ያጋራናችሁ ከሰሞኑን የተላለፉ የፍርድ ውሳኔዎች ናቸው።

ድርጊቶቹ እጅግ አሰቃቂና ለጆሮም የሚከብዱ አስደንጋጭ ናቸው።

በህጻናት ላይ የሚፈጸሙ የጭካኔ ተግባራት በየጊዜው ይሰማሉ።

እኛ አሁን እየሰማን ያለነው ወደ ፍ/ቤትና ሚዲያ እየቀረቡ ያሉትን ነው በየመንደሩ በየአካባቢው ምን ያህል ልጆቻችን ጥቃት እየደረሰባቸው ይሆን ?

የፍርድ ውሳኔዎች አስተማሪ ናቸው ?

ልጆቻችንን ከዚህ የከፋ እና አስፈሪ ጊዜ ለመጠበቅ ምን መደረግ አለበት ?

መፍትሄው ምን ይሆን ?

በዚህ ጉዳይ ላይ የህግ ባለሙያ አስተያየት በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል። እናተም የሚሰማችሁን በ @tikvahethiopiaBot ላይ ፃፉ።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Ethiopia #Djibouti

በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ ዛሬ ማምሻውን ጅቡቲ ገብቷል።

የልዑካን ቡድኑ አባላት ጅቡቲ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሃመድ አሊ የሱፍ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ልዑካኑ በጅቡቲ ቆይታቸው ከተለያዩ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

Via The Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ፎቶ ፦ የታኅሣሥ 19 የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በሰላም በድምቀት ተከብሮ ውሏል።

በበዓሉ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ተገኝተው ነበር።

በክብረ በዓሉ ላይ ቅዱስነታቸው ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ ሰጥተዋል።

በቁልቢ የቅዱስ ገብርኤል ንግሥ በዓል ላይ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምእመን ተገኝቶ ነበር።

ዓመታዊው የታሥሣ 19 የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በተለያዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አህጉረ ስብከቶችም ተከብሮ ውሏል።

የፎቶ ባለቤት ፦ የኢ/ኦ/ተ/ዋ/ቤተ ክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ


@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#አክሱም

🧕" እኛ የምንፈልገው ፍትህ ነው። ሂጃባችንን አድርገን ነው መማር የምንፈልገው። ያለ ሂጃብ ሸሪዓም አይፈቅድም አስቸኳይ እና ዘላቂ መፍትሄ ይሰጠን " - ተማሪዎች

➡️ " የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በአጠቃላይ ሁሉም የሉም ከትምህርት ገበታ ላይ ወጥተዋል " - የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት

👉 " ማንም ተማሪ በትምህርት ቤት ሃይማኖትን የሚያንጸባርቅ ነገር ማድረግ የለበትም " - የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

በትግራይ ፣ አክሱም ከተማ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ላለፉት 2 ሳምንታት የራስ መሸፈኛ ሂጃብ ለብሰው ወደ ትምህርት ቤት መግባት እንደተከለከሉና በዚህም ከትምህርት ገበታ መውጣታቸውን የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት አሳውቋል።

በዚህ ዓመት ከሂጃብ መልበስ ጋር በተያያዘ በአክሱም በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውዝግቡ የጀመረው ጥቅምት ወር ነው።

ተቋሙ ለክልል ትምህርት ቢሮ አሳውቆ አውንታዊ ምላሽ ቢሰጠውም በተግባር የተቀየረ ነገር ግን የለም።

የምክር ቤቱ ፀሀፊ ሓጂ መሓመድ ካሕሳይ ምን አሉ ?

" ፀጉራቸውን ሸፍነው ትምህር ቤት እንዲሄዱ ማየት ያልተፈቀደበት መታየት የለበትም ፀጉሯ የአንድ ሴት ይሄ ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው።

ሃይማኖት ውስጥ ፖለቲካ አይገባም፣ ፖለቲካ በሃይማኖት አይገባም እየተባለ በአንቀጽ ተቀምጦ እያለ አሁን ፖለቲካ በሃይማኖት እየገባ ነው።

ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ዩኒፎርም ጋር የሚመሳሰል የፀጉር መሸፈኛ ሂጃብ መጠቀም እንደሚችሉ በ2000 ዓ/ም የወጣ ሀገር አቀፍ መመሪያ አለ።

ስለዚህ ዝም ብለን የምናየው ነገር አይሆንም።

በአሁኑ ጊዜ በአራት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ወጥተዋል።

ዋናው ደግሞ 3 ወር ሲማሩ የነበሩ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለብሔራዊ ፈተና የኦንላይ ምዝገባ የሚደረግበት ወቅት ነው በዚህ ሳምንት ያልቃል የአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች እስካሁን አልተመዘገቡም።

የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በአጠቃላይ ሁሉም የሉም ትምህርት ገበታ ላይ ወጥተዋል፤ አልገቡም እስካሁን።

ችግሩ እንዲፈታ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ እና ከአክሱም ከተማ አስተዳደር ትምህርይ ፅ/ቤት ጋር ውይይት እየተደረገ ነው " ብለዋል።


ተማሪዎች ምን ይላሉ ?

" በጦርነት ምክንያት ለ2 ዓመታት ከሌሎች  ተማሪዎች ወደኃላ ቀርተናል አሁን ደግሞ በሂጃብ ምክንያት ፈተና ሊያመልጠን ነው።

ፎርሙ እያመለጠን ነው። ሌሎች ተማሪዎች በሂጀብ ፎርም እንደሞሉ ነው የምናውቀው። እኛ የምንፈልገው ፍትህ ነው። ሂጃባችንን አድርገን ነው መማር የምንፈልገው።

ያለ ሂጃብ ሸሪዓም አይፈቅድም ፤ መፍትሄው ደግሞ በጣም አስቸኳይ እና ዘላቂ መሆን አለበት። እስካሁን መብታችን እየተከበረ አይደለም " ብለዋል።

NB. የክልል ትምህርት ቢሮ እና የአክሱም ከተማ አስተዳደር ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆኑም።

የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምን አለ ?

ምክትል ርዕሰ መምህር ገ/መስቀል ገ/እግዚአብሔር ፦

" ' ትምህርት ቤቶች ከሃይማኖት እና ከፖለቲካ ነጻ መሆን አለባቸው ' ይላል የትግራይ ክልል የትምህርት ቤቶች አደረጃጀት መመሪያ ማንም ተማሪ በትምህርት ቤት ሃይማኖትን የሚያንጸባርቅ ነገር ማድረግ የለበትም።

ክርስቲያኑ መስቀል ወይም መጠምጠሚያ ፤ ሙስሊሙም ሂጀብ ወይም ኮፍያ ማድረግ አይፈቀድም። የትምህርት ቤቱ መለያ ዩኒፎርም ብቻ ነው መልበስ የሚገባው።

የተወሰኑ ተማሪዎች ሂጃባቸውን አናውልቅም ብለው ነበር አሁን ግን ተማሪዎች የትምህት ቤቱን መመሪያ ተከትለው እየገቡ ናቸው።

አሰራሩ ለዓመታት የቆየ ነው " ብለዋል።


አንድ በጉዳዩ ላይ ቃላቸው የሰጡ የክልል ትምህርት ቢሮ ሰራተኛ ፤ " በክልሉ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እየሆነ ያለው በ1995 የወጣ መመሪያ ነው በዚያ መመሪያ ትምህርት ቤቶች የራሳቸውን መተዳደሪያ ማውጣት እንደሚችሉ ይደነግጋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ትግርኛ አገልግሎት መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በአማራ ክልል አጀንዳ ልየታ እንደማንሳተፍ ለኮሚሽኑ በአክብሮት እንገልጻለን " - መኢአድ እና እናት ፓርቲ

መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና እናት ፓርቲ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል ባቀደው አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ በአጀንዳ ልየታ የሚሳተፉ የፓርቲ ተወካዮችን እንዲያሳውቁ በደብዳቤ ቢጠይቃቸውም ከወዲሁ እራሳቸውን ማግለላቸውን የሚገልጽ የጋራ መግለጫ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ልከዋል።

ፓርቲዎቹ ራሳቸውን ከምክክሩ እንዳገለሉ በገለጹበት በዚሁ መግለጫ ፤ የጦርነት ችግሮች ካልተፈቱ በምክክሩ ለመሳተፍ እንደሚቸገሩ ሲያሳስቡ መቆየታቸውን አስታውሰዋል ፤ የአማራ ክልል ህዝብ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በአየርና በምድር በከባድ መሳሪያ እንዲሁም በድሮን ጭምር የሚደርስበት ጥቃት አለመቆሙን ጠቅሰዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቢያበቃም አማራ ክልል በኮማንድ ፖስት እየተዳደረና ጦርነቱ እየተስፋፋ ያለበት፣ በርካታ ዜጎች በማንነታቸው እና በፖለቲካ አመላካከታቸው የታሰሩበት፣ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ አልፎ አልፎ ሙሉ በሙሉ የሚገደብበት ፣ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት የራቀበት ሁኔታ መኖሩን ገልጸዋል።

" በዚህ መልክ በተጠቀሰው የአጀንዳ ልየታ ለመሳተፍ መሞከር እውነተኛ ምክክር አድርጎ ለሀገር የሚበጅ መፍትሄ ለማምጣት ሳይሆን የተጠና ተውኔት አካል ከመሆንና ራስን ከማታለል የዘለለ የሚያመጣው መፍትሄ እንደሌለው በውል እንረዳለን " ብለዋል።

በህዝቡ የሚፈደርሰው ጉዳት አለመቆሙን ጠቅሰው፣ " በክልሉ የአጀንዳ ልየታ ሥራ ማሰብ ከፈረሱ ጋሪው የቀደመበትና ኮሚሽኑ እውነተኛ ምክክር የማድረግ እንቅስቃሴ ሳይሆን የስርዓት ዓላማ ማስፈጸሚያ መሣሪያ ወደ መሆን ገባ ወይ ? እንድንል አስገድዶናል " ብለዋል።

ፓርቲዎቹ፣ የሀገራዊ ምክክሩ አካሄድ ከዐዋጁ አጸዳደቅ ጀምሮ ከታዩበት የተለያዩ የጎሉ ችግሮች ላይ ተጠደምደው ከመቆዘም ይልቅ ምክክሩ ለአገር የሚያመጣውን ውጤት በመገንዘብ " ችግሮች እየተቀረፉ ይሄዳሉ " በሚል እሳቤ በመደገፍ እንደቆዩ አስታውሰዋል።

በምክክሩ ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ፣ የሰሜኑ ጦርነት በፕሪቶሪያው ስምምነት እንደተቋጨ ሁሉ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ጦርነቶች ተቋጭተው ወደ ምክክር መኬድ እንዳለበት፣ ይህ ካልሆነ የሀገሪቱ እጣ ፈንታ ሀገራዊ ምክክሩ ሳይሆን የጦርነቶቹ ሂደት ሊወስን እንደሚችል ምክረ ሀሳብ ሲያቀርቡ መቆየታቸውን ነው የገለጹት።

በመሆኑም፣ " ኮሚሽኑ በሰው ቁስል እንጨት ከመስደድ " ይልቅ ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ እና ከመንግስት ጋር ያለውን መልካም ግንኙነት ተጠቅሞና ጫና አድርጎ በገለልተኛ አካላት አሸማጋይነት እውነተኛ ሰላምን ሊያዋልድ የሚችል ድርድር እንዲደረግ አሳስበዋል።

(የትብብር ፓርቲዎቹ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)


@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ethiotelecom

ኢትዮ ቴሌኮም በ67 ከተሞች የ4ጂ ሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት ማስጀመሩን አሳውቋል።

የከተሞቹ ዝርዝር ከላይ በምስል ተያይዟል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ethiotelecom #telebirr

✨🏑 ሁላችንም የምንሳተፍበት የዘንድሮ የገና ጨዋታ የሚደረግበት ሜዳ ቴሌብር ሱፐርአፕ ነው!! 😁

💁‍♂️ መተግበሪያው https://onelink.to/uecbbr ከሌለዎት ያውርዱ፤ በሞቀው የገና ጨዋታ ተሳታፊ ይሁኑ!

🤩 ከ15 ሚሊየኑ የዕድልዎን ለመውሰድ ታኅሣሥ 23 ይጠብቁን!!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የተሠረቀባችሁን ዕቃ በአካል ቀርባቹ በመለየት መረከብ ትችላላችሁ " - ፖሊስ

በልደታ ክ/ከተማ በተደረገ የሌባ ጥናት የተለያዩ የተሠረቁ የመኪና ዕቃዎችን ከአንድ ተጠርጣሪ ጋር መያዙን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

" የሌባ ተቀባዬች ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰረቁ የመኪና ዕቃዎችን በማከማቸት ዕቃዎቹን ለማስመለስ ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠየቅባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ ተደጋግሞ ይገለፃል " ያለው ፖሊስ የተሰረቁ የተሽከርካሪ ዕቃዎችን በመኖሪያ ቤት ውስጥ በመደበቅና የተሽከርካሪዎቹ ባለቤቶች ሲመጡ የራሳቸውን ዕቃ በገንዘብ የሚሸጡ ግለሰቦች ላይ ጥናት ሲደረግ መቆየቱን አመልክቷል።

ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ/ም በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ቀጠና አራት አካባቢ በጥናት በተለዩ አራት የመኖሪያ ቤቶች ውስጥ ከሌቦች እየተቀበሉ በመደበቅ የሚሸጡ ግለሰቦችን ላይ በተደረገ ኦፕሬሽን ፦
👉 152 የተለያዩ ስፖኬዎች፣
👉 08 ዓርማዎች ( ማርክ )፣
👉 08 የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀር ክዳኖች፣
👉 01 የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀር፣
👉 15 የስፖኪዮ ማቀፊያ፣
👉 01 የሞተር ሳይክል ፍሬቻ ከአንድ ተጠርጣሪ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ገልጿል።

ፖሊስ አሁንም መሰል የወንጀል ድርጊት ውስጥ በመግባት የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ተገቢውን የፍርድ ቤት የመያዣና የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት ተጠርጣሪዎችን የመያዝና ብርበራዎችን የማድረግ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

" ተመሳሳይ ወንጀል ተፈጽሞብኛል " የሚል ካለ ጎማ ቁጠባ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በአካል በመቅረብ የተሠረቀበትን ዕቃ መለየትና መረከብ እንደሚችል ፖሊስ አስታውቋል።

በነገራችን ላይ ...

አዲስ አበባ ውስጥ የትም ቦታ የራሳችሁን የመኪና ዕቃ ብትሰረቁ ዕቃችሁን የት እንደሚገባ ይታወቃል።

የተሰረቁ ሰዎች ዕቃቸውን ፍለጋ ወደ እነዚህ ስፍራዎች ሲሄዱ ሌቦቹ እና ተቀባዮቹ ልክ እንደ ህጋዊ የራሳቸው እቃ ከፍተኛ ብር ይጠይቃሉ።

የራሳችሁ በሆነና በተሰረቃችሁት ዕቃ ላይ ይደራደራሉ " አያዋጣኝም ከቦታው አልመጣም " ይላሉ።

ከዛም በፈለጉት ዋጋ የራሳችሁን ዕቃ ሽጠውላችሁ ይሸኟችኃል።

ይህ ብቻ አይደለም የጠፋባችሁን የመኪና ዕቃ ፍለጋ ባሄዳችሁት " ቆዩ አንድ 40 ደቂቃ ጠብቁ " ትባሉና ተመሳሳዩ ይመጣላችኋል። ይህን የሚያደርጉት ሌቦችን አሰማርተው በማሰረቅ ነው።

ይህ ሁሉ የሚሆንባቸው የአዲስ አበባ ቦታዎች በግልጽ በይፋ ይታወቃሉ።

የተሰረቁ ሰዎች " ለፖሊስ አመልክተን እቃችንን የምናገኝበት እድል ጠባብ ነው ፤ የሚወስደው ጊዜም ብዙ ነው " በሚል የራሳቸውን እቃ በውድ ዋጋ ይገዛሉ።

የሚሰረቁ የመኪና እቃዎች የት እንደሚወስዱ እየታወቀ ፤ የሚሸጥባቸው እና ድርድር የሚደረግባቸው ቦታዎች በይፋ እየታወቀ ይህንን ተግባር ለምን በዘላቂነት ማስቆም እንዳልተቻለ የብዙ ሰዎች ጥያቄ ነው።

ማልባትም በዚህ ነገር እጃቸው የረዘመ እና የጥቅሙ ተካፋይ ፣ የሌቦችም ጠበቃ የሆኑ ብዙ ግለሰቦች ይኖራሉ።

በመኪና ስርቆት የተማረሩ በኃላም የራሳቸውን እቃ ሄደው በከፍተኛ ብር የገዙ ብዙ ሰዎች ይኖራሉ። እናተስ የምታውቁት ታሪክ ይኖር ይሆን ? አጋሩን
@tikvahethiopiaBot

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

🔈 #የጤናባለሞያዎችድምጽ

🔴 " ከደመወዝ ጋር ይከፈለናል ብለን በተስፋ ስንጠብቅ አሁንም ሳይከፈለን ቀርቷል " -ቅሬታ አቅራቢ የጤና ባለሞያዎች

🔵 " ምን ያህል ይታገሱ የሚለውን አላውቅም " -የወረዳው አስተዳዳሪ

በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ በ9 ጤና ጣቢያ ውስጥ የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች ከግንቦት 2016 ዓ/ም ጀምሮ የተጠራቀመ የትርፍ ሰዓት ስራ (ዲዩቲ) ክፍያቸው እንዳልተከፈላቸው በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ባለሞያዎቹ ያልተከፈላቸው የ2016 ዓ/ም የግንቦት እና የሰኔ ወር እንዲሁም በ2017 ዓ/ም የ3 ወር በጠቅላላው የ5 ወር የዱዩቲ (የትርፍ ሰዓት) የሰሩበት ክፍያ ነው።

መረጃውን ባጋራንበት ወቅት ባለሞያዎቹ ያልተከፈላቸው የ4 ወር የትርፍ ሰአት ክፍያ የነበረ ሲሆን በወቅቱ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቃሉ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑትን አቶ ሙህዲን አህመድን በጉዳዩ ላይ አነጋግሮ ነበር።

አስተዳዳሪው " ክፍያው የዘገየው በየጤና ጣቢያዎቹ የሚሰጠው አገልግሎት እና የሥራ ጫና የሚለያይ በመሆኑ የሚያድረው የጤና ባለሞያ ቁጥርም ይለያያል በዛ ምክንያት ደረጃ ይውጣለትና በሚሰጡት አገልግሎት እና ባለባቸው የስራ ጫና ልክ ይከፈላቸው ተብሎ ይህንን የሚያጣራ ኮሚቴ ተቋቁሞ በወረዳው በሚገኙ በዘጠኙም ጤና ጣቢያዎች እያጣራ ነው ሪፖርቱን እንዳቀረበ ይከፈላቸዋል " ማለታቸው ይታወሳል።

አስተዳዳሪው ይህንን ምላሽ ይስጡ እንጂ የባለሞያዎቹ የትርፍ ሰአት ክፍያ ሳይከፈል 5 ወር ማለፉን የጤና ባለሞያዎች በድጋሚ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

ባለሞያዎቹ " የሰራንበትን ክፍያ እንዲከፈለን ደጋግመን ብንጠይቅም የሚሰማ አመራር በማጣታችን አሁንም ለችግር ተጋልጠናል " ብለዋል።

" በህዳር ወር መጨረሻ ከደመወዝ ጋር ይከፈለናል ብለን በተስፋ ስንጠብቅ አሁንም ሳይከፈለን ቀርቷል ለምን ? ብለን ስንጠይቅ እንደገና በወረዳው ጤና ጥበቃ ኦፊሰሮች ኮሚቴ ተዋቅሮ 9ኙም ጤና ጣቢያዎች  ቼክ ይደረጉ ተብሎ ከወረዳ አስተዳደር አቅጣጫ ተቀምጧል በዚህ ወር የሰራችሁበት አይከፈላቹም " የሚል ምላሽ ተሰጥቶናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የወረዳውን አስተዳዳሪ የጤና ባለሞያዎቹ ምን ያህል ጊዜ ይታገሱ ሲል በድጋሚ ጠይቋል " ምን ያህል ይታገሱ የሚለውን አላውቅም በቴክኒክ ኮሚቴው ተጨማሪ ጥናት እየተደረገ ነው እሱ እንዳለቀ ይከፈላቸዋል " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ወረዳው ኮሚቴዎችን አዋቅሮ በዘጠኙም ጤና ጣቢያ ጀምሮት የነበረውን የማጣራት ስራ ካጠናቀቀ በኋላ በድጋሚ ጤና ጣቢያዎቹ በራሳቸው የማጣራት ስራ ጀምረዋል ይህ ለምን ሆነ ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ " ተቋማቱ (ጤና ጣቢያዎቹ) እኛም ቼክ እናድርግ አሉ እኛ ከሰራነው ጋር ያለውን mismatch (ልዩነት) እንየው ከቴክኒኩ ውጤት ጋር ይገጥማል ወይስ ልዩነት አለው የሚለውን ለማየት ፈልገው ስለሆነ እሱ እንዳለቀ ይከፈላል " ሲሉ መልሰዋል።

ሃላፊው በወረዳው ደረጃ የሰሩት የጥናት ውጤት ምን እንደሆነ ከመናገር የተቆጠቡ ሲሆን ተጨማሪ ምላሽ ለመስጠትም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ዳንኤል ጋሻው ምን ምላሽ ሰጡ ?

ሃላፊው " የጤና ጣቢያዎቹ አሰራራቸውን ማየት ስላለብን በድጋሚ ጀምረናል የሚሰጡት አገልግሎት እና የባለሞያው ቁጥር ትንሽ ይጣረሳል " ብለዋል።

ጥናቱም በዚህ ሳምንት እንደሚያልቅ እና በውጤቱም መሰረት እንደሚከፈላቸው ተናግረዋል።

" ነገሩን ማስተካከል ስለሚቻል በዚህ ሳምንት ጨርሰን ያለውን ነገር ችግሮቹን ለይተን የሚከፈለው ካለ ይከፈላል ያልሰራበትንም የወሰደ ካለ በምርመራው መሰረት ያሰራውም አካል የወሰደውም አካል ተጠያቂ ይሆናል " ነው ያሉት።

" ጥናት ማድረግ የተለየ ነገር አይደለም አሰራርን መፈተሽ ያለ ነው ለሰራተኛውም ይጠቅማል የሚሰራውን እና የማይሰራውን ለመለየትም ያግዛል " ሲሉ አክለዋል።

ጥናቱን ከጨረሳችሁ በኋላ የቀረውን ክፍያ በሙሉ ትከፍላላቹ ወይስ እየቀነሳቹ ? ስንል ላነሳንላቸው ጥያቄ " እሱን ከጥናቱ በኋላ ነው የምናየው ግን የሰሩበት ይከፈላል " ብለዋል።

በውጤቱ መሰረትም በጣም ኬዝ ሎድ ኖሮባቸው ዝቅተኛ የሚከፈለው ካለ ክፍያውን ሊሻሻል እንደሚችል እና ምንም ሳይሰራ እንደ መርሐ ግብር የሚከፈለው ካለም ክፍያውን ሊያጣ እንደሚችል ጠቁመዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

ማንነታቸው ባልታወቁ  ታጣቃዎች የታገቱት ሦስት የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን አስገደ ወረዳ ሜይሊ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በሚገኝ እስር ቤት እንደሚገኙ የትግራይ ቴሌቪዥን ማረጋገጡን አስታውቋል።

ጋዜጠኞቹ ከህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ፍለጋ እና ዝውውር ጋር ተያይዞ ስለሚነሳው ጉዳይ ለማጥራት በተሰማሩበት ነው በታጣቂዎች መታገታቸው የተበገረው።

አሁን ላይ ጋዜጠኞቹ እስር ቤት እንዳሉ ተነግሯል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ካናዳ

በካናዳ፣ ሀሊፋክስ ኤርፖርት ሲያርፍ የነበረ አንድ የመንገደኞች አውሮፕላን በእሳት መያያዙ ተሰምቷል።

73 መንገደኞችን እና የበረራ ሰራተኞችን የያዘው በፒኤኤል አየር መንገድ የሚሰራው የኤር ካናዳ በረራ ቁጥር 2259 አውሮፕላን በሚያስደነግጥ አኳኋን ሊቆም ችሏል።

በህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ተነግሯል።

ከሴንት ጆንስ ተነስቶ ሀሊፋክስ ኤርፖርት ሲያርፍ የነበረው አውሮፕላን የቴክኒክ ችግር እንዳጋጠመው ነው የተነገረው።

አውሮፕላኑ ሲያርፍ ከማረፊያው መንገድ ወጥቶ በእሳት ተያይዟል።

ለሲቢሲ ኒውስ ቃላቸውን የሰጡ አንድ መንገደኛ ፥ " አውሮፕላኑ በሚያርፍበት ወቅት አንዱ ጎማ በትክክል አልተዘረጋም ነበር ፤ በጣም የሚያስፈራ ድምጽም ነበር " ብለዋል።

አንዱ የአውሮፕላን ክፍል በእሳት መጋየቱን ነው የጠቆሙት።

የክስተቱ ምክንያቱ እየተመረመረ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

በደቡብ ኮሪያ ፣ ሙዋን በደረሰው አሰቃቂ የአውሮፕላን አደጋ አውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት 181 ሰዎች 177 ሰዎች መሞታቸው መረጋገጡን " ሮይተርስ " ዘግቧል።

የቀሩት ሁለት ሰዎች በህይወት ይገኛሉ የሚለው ተስፋ እየተሟጠጠ ነው ተብሏል።

ንብረትነቱ የ " ጄጁ አየር መንገድ " በሆነው Boeing 737-800 የአውሮፕላን አደጋ በህይወት የተረፉት ሁለት ሰዎች ሲሆኑ እነሱም የበረራ ሰራተኞች ናቸው። የደረሰባቸው ጉዳት ለህይወታቸው የሚያሰጋ አይደለም ተብሏል።

ምንም እንኳ የአደጋው መንስኤ እየተመረመረ ቢሆንም ባለስልጣናት ግን  " ከወፍ ተጋጭቶ ነው " ብለዋል። ከአደጋው ቀደም ብሎ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አውሮፕላኑን የወፎች ጥቃት ስጋት እንዳለ አሳውቀው ነበር ተብሏል።

ከአደጋው በህይወት ከተረፉ የበረራ አባላት መካከል እንደተሰማው ከአደጋው ቀደም ብሎ የወፎች ጥቃት እንደነበር መጠቆሙን " ዘጋርዲያን " ዘግቧል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ቪድዮ፦ በአስደንጋጩ አውሮፕላን አደጋ እስካሁን 151 ሰዎች ሞቱ።

በደቡብ ኮሪያ ውስጥ በማረፍ ላይ የነበረ አንድ አውሮፕላን ባጋጠመው አደጋ እስካሁን ድረስ 151 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል።

" ጄጁ " የተባለው አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን ከባንግኮክ መጥቶ በደቡብ ኮሪያው ሙዋን አየር ማረፊያ ሲያርፍ ነበር መንገዱን ስቶ የአውሮፕላኑ የፊተኛው ክፍል በእሣት ሲያያዝ የታየው።

ምንም እንኳ እስካሁን ድረስ የአደጋው መንስዔ ባይታወቅም የእሣት አደጋ አገልግሎት " ምናልባት ከወፍ ተጋጭቶ አሊያም ባለው ከባድ የአየር ፀባይ ምክንያት ሊሆን ይችላል " ብሏል።

አውሮፕላኑ 181 ሰዎች አሳፍሮ ነው ከታይላንድ የተነሳው።

አብዛኛዎቹ ደቡብ ኮሪያዊያን መሆናቸውን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

እስካሁን አንድ ተሳፋሪና አንድ የበረራ ሠራተኛ በሕይወት ሲተርፉ ሌሎች ከአደጋው የተረፉ ሰዎችን የማዳን ሥራው መቀጠሉን ቢቢሲ ኒውስ ፣ ቲአርቲ ወርልድና ሮይተርስ ዘግበዋል።

ቪድዮ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር !

በዓሉን ምክንያት በማድረግ በዕቃዎቻችን ላይ ልዩ ቅናሽ ማድረጋችንን ስናበስርዎ በታላቅ ደስታ ነው!
እነዚህን ረቂቅ የንድፍ ጥበብ የሚታይባቸውን ውብ ዕቃዎች ገዝተው የቤትዎን ድባብ ይቀይሩ!
የውበት፣ የጥራት እና የምቾት ዳር ድንበር ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር!

🌐 የማህበራዊ ገጾቻችንን ይቀላለቀሉ
Telegram 👉 Telegram/yonatanbtfurniture
Facebook 👉 Facebook/yonatanbtfurniture
Instagram👉Instagram/yonatanbtfurniture
TikTok      👉 yonatanbtfurniture?is_from_webapp=1&sender_device=pc">TikTok/yonatanbtfurniture

📍አድራሻችን፦
1. ፒያሳ እሪ በከንቱ ቢቲ ታወር (ከኢቲዮ ሴራሚክ ዝቅ ብሎ)
2. ከዊንጌት አደባባይ አለፍ ብሎ ከአቢሲኒያ ባንክ ፊትለፊት
3. ከሲኤምሲ አደባባይ ወደ አያት መንገድ መሪ ሳይደርስ (ዘመን ባንክ አጠገብ)

ስልክ ፦ +251957868686/ +251995272727/ +251993828282

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Earthquake : ዛሬ ቅዳሜ ምሽት ጨምሮ ቀን ላይ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበር የአፋር ቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ገልጸዋል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ድግግሞሹ እየጨመረ ነው ብለዋል።

አንድ የቤተሰባችን አባል፥ " አላህ መፍትሄውን ይስጠን ፤ ያረጋጋው እንጂ እጅግ በጣም ያስፈራል ፤ የዓለሙ ፈጣሪ አላህ መጨረሻችንን ያሳምረው " ሲል ገልጿል።

መሬት መንቀጥቀጡ እየፈጠረ ያለው ንዝረት በተለያዩ ከተሞችም መሰማቱን ለመረዳት ችለናል።

በፈንታሌ አካባቢ በተደጋጋሚ የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ የሚገኝ ሲሆን ትላንትና ከፍተኛ የሆነው በሬክተር ስኬል 5 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር።

#TikvahEthiopiaFamilyAfar

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Somalia #Djibouti

ከቀናት በፊት ኤርትራ አስመራ የነበሩት የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀመድ ዛሬ ጅቡቲ ገብተዋል።

ወደ ጅቡቲ ያቀኑት በፕሬዜዳንት ኢስማኤል ኡማር ጌሌህ ግብዣ እንደሆነ ተነግሯል።

ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ተገልጿል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

🚨 " የመብት ጥየቄ በማንሳታችን ከስራ ታግደናል " - የመስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጅነሪንግ ሰራተኞች

🔴 " ባልተገባ አመፅ ድርጅቱን በማክሰራቸው ምክንያት ለ30 ቀናት ከስራ እንዲታገዱ ተወሰኗል " - ድርጅቱ


በመቐለ ከተማ የሚገኘው የትእምት (EFORT) ድርጅቶች አህት ኩባንያ በሆነው መስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጅነሪንግ እና ሰራተኞቹ መካከል የተፈጠረው ሰጣ ገባ ከጀመረ ቆይቷል።

ሰራተኞች ያሉባቸው የመብት እና ጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎች እንዲፈቱላቸው በወርሃ ጥቅምት 2017 ዓ.ም ሰላማዊ ስልፈው አድርገው ነበር።

ያነሱዋቸው ጥያቄዎች ሳይመለሱ በመቅረታቸው ለሁለተኛ ጊዜ በያዝነው ወር ሁለተኛ ሳምንት መጀመሪያ ካለፈው የቀጠለ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።

ሰራተኞቹ ታህሳስ 11/2017 ዓ.ም ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ፦

- በድርጅቱ የሰራተኞች አስተዳደር መመሪያ መሰረት በውድድር የተሰጠን የእድገት እርከን የሚመጥን ደመወዝ እንዲሰጠን ብንጠይቅም ' በጀት የለም ' በሚል ጥየቄያችን ጀሮ ዳባ ልበስ ተብሏል።

- ለድካም እና ልፋታችን የሚመጥን ደመወዝ ስለማይከፈለን ኑሮሯችንን ለመምራት ተቸግረናል።

- አንድ የሙያ እና የጉልበት ሰራተኛ በቀን ከ50 አስከ 200 ብር ነው የሚከፈለው በዚህ አነስተኛ ክፍያ ቤተሰብ ይቅር እና ራስን ማስተዳደር አቅቶናል ስለሆነም አስፈላጊ የደመወዝ ጭማሪ ይደረግልን።

- ለ10 አመታት የቆየው ጥያቄያችን " ስትራክቸር እየተሰራ ነው " በሚል ሽፋን ምክንያት እየተንከባለለ ቆይቶ በአሁኑ ወቅት " የፈለገ ይስራ ፤ ያልፈለገ ይሂድ " ወደ ማለት ተገብቷል ይህ ልክ አይደለም።

- አቅማችን አሟጠን እየሰራን የልፋታችን እያገኘን አይደለምን ... ሲሉ ድምፃቸው አሰምተዋል። 

የድርጅቱ የገበያ ልማት እና የሰው ሃይል አስተዳደደር ታህሳስ 17/2017 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቅያ ፤ ሰራተኞቹ ከታህሳስ 11 እስከ 16/2017 ዓ.ም  የስራ ማቆም አድማ በማድረግ ድርጅቱን ላልተገባ ኪሳራ በመጣላቸእ ከታህሳስ 17/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ1 ወር ከስራ እንዲታገዱ መወሰኑን አስታውቋል።

ለአንድ ወር ከስራ የታገዱት ሰራተኞች ቁጥራቸው 250 መሆኑን ደርጅቱ ስማቸው ጠቅሶ ይፋ አድርጓል።

" የድርጅቱ ማኔጅመንት መብታችሁ እና የሚገባችሁ ለምን ትጠይቃላችሁ ? ለምን አጋላጥችሁን ? ስማችንን ጥላሸት ቀብታችሁታል ብሎ የወሰደው እርምጃ ተቀባይነት የለውም " ሲሉ ሰራተኞቹ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪነንግ በብረታ ብረትና ሞደፊክ ስራዎች የተሰማራ ከትእምት (EFORT) ግዙፍ ካምፓኒዎች አንዱ መሆኑ ይታወቃል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia 

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ፎቶ ፦ ዓመታዊው የታኅሣሥ 19 የሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል የንግሥ በዓል በሐዋሳ ከተማ ተከብሯል።

የንግሥ በዓሉ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኦርቶዶክሳውያን በተገኙበት ነው የተከበረው።

የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በዓሉ ያለ አንዳች ኮሽታ በሰላም በከፍተኛ ድምቀት ተከብሯል ብሏል።

የፎቶ ባለቤት ፦ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ዛሬ የተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 5 ነው ፤ ካለፈው አንጻር የዛሬው ጠንካራ ነው " -  አታላይ አየለ (ፕ/ር)

ዛሬ አመሻሽ ላይ በሬክተር ስኬል 5 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ።

አመሻሽ 12 ሠዓት ከ26 ላይ በፈንታሌ አካባቢ በሬክተር ስኬል 5 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል።

በዩኒቨርሲቲው የጂኦ ፊዚክስ ሕዋ ሣይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ሣይንስ መምህርና ተመራማሪ አታላይ አየለ (ፕ/ር) ምን አሉ ?

" የመሬት መንቀጥቀጡ በተደጋጋሚ እየተስተዋለ ነው።

ባሳለፍነው ቅዳሜ ዕለትም በዚሁ አካባቢ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 3 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመዝግቦ ነበር።

ካለፈው አንጻር የዛሬው ጠንከር ያለ ነው " ብለዋል። (ለኤፍ ኤም ሲ)

ከሰሞኑን በተደጋጋሚ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የሚሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ ሲሆን በሬክተር ስኬል የሚመዘገበው መጠንም ጨምሮ ታይቷል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

" የምግብ ጥራቱ ወርዷል ፤ መጠኑ ቀንሷል 22 ብር በነበረ ጊዜ ይሻላል ፤ የብሩ መጨመር ምንም ነገር ካላስተካከለ ትርፉ ከፍተኛ ኮስት ሸሪንግ / የወጪ መጋራት እዳ ነው " - ተማሪዎች

ከሰሞኑን በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ወጥነት ባለው መንገድ መተግበር የጀመረው የምግብ ሜኑ በተማሪዎች ዘንድ ቅሬታን የፈጠረ ሆኗል።

ምግቡ መጠኑ ቀንሷል፤ ጥራቱም 22 ብር የነበረ ጊዜ ይሻላል የሚል ቅሬታ ነው ተማሪዎች ዘንድ ያለው።

ከዚህ ባለፈ የብሩ መጨመር በተማሪዎች ኮስት ሼሪንግ / ወጪ መጋራት ላይ ከፍተኛ ጭማሪ አድርጎ ተማሪውን ባለዕዳ ከማድረግ ባለፈ አንድም የጥራት መሻሻል አይታይም ፤ ጭራሽ መጠንም ቀንሷል ብለዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስተዳደርና ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶ/ር ሰሎሞን አብርሃ  ስለ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ በጀት (100 ብር) ምን አሉ ?

" የምግብ በጀቱ 100 ብር ሆነ ማለት የግድ የተለየ ለውጥ ይመጣል ማለት አይደለም። የምግብ አይነቱም ሙሉ ለሙሉ አስደናቂ በሆነ መልኩ ይቀየራል ማለት አይደለም፣ ሊቀየርም አይችልም።

ድሮውንም ተማሪዎች በተመደበላቸው 22 ብር ብቻ ሲመገቡ አልቆዩም።

ከፌዴራል መንግሥት የሚመደበው 22 ብር አነስተኛ መሆኑ ስለሚታወቅ ዩኒቨርሲቲዎች በራሳቸው አካሄድ ሲያስተካክሉ ቆይተዋል።

ዩኒቨርስቲዎች ከሚመደብላቸው የተለያየ በጀት እያዟዟሩ በቀን ከ80 እስከ 150 ብር በማውጣት ተማሪዎችን ሲመግቡ ነበር።

የተማሪዎች የምግብ ሜኑ ከመሻሻሉ በፊት አንድ እንጀራን እስከ 24 ብር ድረስ የሚገዛ ዩኒቨርስቲ ነበር። ድሮ ይመደብ የነበረው በጀት አንድ እንጀራ እንኳን በቅጡ የማይገዛ ነበር።

በመሆኑም ይህ አካሄድ የዩኒቨርሲቲዎችን እንቅስቃሴ ስላስተጓጎለና የአሰራር ስርዓታቸው ላይም ችግር ስለፈጠረ፣ የምግብ ሜኑ ሲዘጋጅ ጥናት ተጠንቶ ሀገር አቀፍ የተማሪ ህብረት ተወካዮች ጭምር በአካል በተገኙበት የዩኒቨርሲቲዎች ምግብ ማሻሻያ ተደርጓል።

ተማሪዎች አሁን ካለው ሁኔታ አንፃር ማድረግ ያለባቸው የሚመደብላቸው በጀት በአግባቡ ለእነርሱ መድረሱን እና በቀን የመቶ ብሩ በጀት ተሰልቶ በሳምንት 700 ብር ወጪ መደረጉን፣ እንዲሁም ያንን ወጪ ታሳቢ ያደረገ ሜኑ መቅረብና አለመቅረቡን ማረጋገጥ ነው።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የተማሪዎች ህብረት አደረጃጀትም ኃላፊነት በመውሰድ በአግባቡ መከታተል አለበት " ብለዋል።


ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ የሰሎሞን አብርሃ (ዶ/ር) ንግግር የተወሰደው ለአሐዱ መሆኑን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ዝቅተኛ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ዩኒቨርሲቲዎች እኩል በጀት የሚመደብበት አሰራር አይኖርም " - ትምህርት ሚኒስቴር

ከዚህ በኃላ ዝቅተኛ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ዩኒቨርሲቲዎች እኩል በጀት የሚመደብበት አሰራር እንደሚቀር የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደብላቸው በጀት ባስመዘገቡት ውጤት ልክ እንደሚሆን ሚኒስትሩ ይፋ አድርገዋል።

ይህን ይፋ ያደረጉት ከሰሞኑን በትምህርት ዘርፉ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በተቀናጀ መልኩ ማሻሻል የሚያስችል ስምምነት ትምህርት ሚኒስቴር እና 47 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የቦርድ ሰብሳቢዎችና የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች በተፈራረሙበት ወቅት ነው።

ሚኒስትሩ ፤ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን በመሰረታዊነት ለመቀየር የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ ወሳኝ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የተጣለባቸውን ሃላፊነት በብቃትና በጥራት እንዲፈፅሙ በተለይ ሙስናን ማጥፋት ግዴታ መሆኑን ፕ/ር ብርሃኑ አሳስበዋል።

" ሙስና የትውልድ ጸር በመሆኑ ለትውልዱ አርዓያ የሚሆን ዩኒቨርሲቲ መፍጠር ይገባል " ብለዋል። #ኤፍኤምሲ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#እንድታውቁት

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በድጋሚ የሚፈተኑ ተፈታኞች በበየነ መረብ (ኦንላይን) መመዝገብ እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ተፈታኞች በራሳቸው የሚመዘገቡበት አድራሻ https://register.eaes.et/Online እንደሆነ ተገልጿል።

ይህ የበይነ መረብ (አንላይን) ምዝገባ መተግበሪያ ራስ አገዝ (self services ) ሲሆን ተመዝጋቢዎች የሚፈልጉትን ድጋፍ በመጠየቅ ከማዕከል ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።

(እንዴት መመዝገብ እንደሚቻል ከላይ ይመልከቱ)

(የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት)

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት እስከምሽቱ 4:00 እንዲሰጥ ተወስኗል " - የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ

በአዲስ አበባ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት እስከምሽቱ 4:00 የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ወስኗል።

በዚህ ውሳኔ መሠረት ማንኛውም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ፦
- አውቶቡሶች፣
- ሚዲ ባስ
- ሚኒ ባሶች በመደበኛ ቀን በሚትሰሩበት መስመር እና ቀን ላይ በሚከፈለው ህጋዊ ታሪፍ መሠረት እስከምሽቱ 4:00 አገልግሎት እንዲሰጡ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

ቢሮው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎች እስከምሽት 4:00 አገልግሎት እንዲያገኙና እና የትራንስፖርት ቁጥጥር ሠራተኞች እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ለተግባራዊነቱ ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ቢሮው አገልግሎት ሰጪዎች እስከ ምሽት 4:00 አገልግሎት ባይሰጡስ ምን እንደሚጠብቃቸው በዝርዝር ያለው ነገር የለም።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ሕብር የወጣቶች የቁጠባ ሒሳብ

ከመደበኛ የቁጠባ አይነት የተሻለ ወለድ የሚያስገኝ እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ ጥቅሞችን የያዘ ልዩ የወጣቶች የቁጠባ ሒሳብ ነው፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

📞  ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡
🤳 በቀላሉ አዳዲስ መረጃዎች  እንዲደርስዎ የቴሌግራም ገፃችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፡፡ /channel/HibretBanket
🌐 ሌሎች የማህበራዊ ገፆቻችንን እና ድህረ ገፃችንን linktr.ee/Hibret.Bank ይጎብኙ፡፡

#Youthsaving #hibirYouth #Startsaving

Читать полностью…
Subscribe to a channel