#Update
4:18 ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.8 ተመዝግቧል።
የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ልክ 4:18 ላይ ከአዋሽ 16 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሬክተር ስኬል 4.8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አመላክቷል።
ይህ 4.8 ሆኖ የተለካው የመሬት መንቀጥቀጥ ትላንት ለሊት ከተመዘገበው ከፍተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ ጋር ተመሳሳይ ነው።
ትላንትና ሰኞ ከጥዋት አንስቶ የተለያየ መጠን ያላቸው በርካታ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ተመዝግበው የነበረ ሲሆን ከፍተኛው 4.8 ነበር።
ዛሬም አዋሽ እና አካባቢው ላይ 4.3 እና ከዚያ በላይ የተመዘገቡ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ነበሩ።
#TikvahEthiopiaFamilyAfar
@tikvahethiopia
#Earthquake : ዛሬ ምሽትም 4:17 ላይ ጠንከር ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን በአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የሚገኙ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።
የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ተሰምቷል።
በተለይም ደግሞ ቤት ውስጥ የነበሩ ሰዎች በደንብ ተሰምቷቸዋል። ጠንከር ያለ እንደነበረም ጠቁመዋል።
ከጋርመንት፣ ጀሞ፣ አራብሳ፣ አያት ፣ ጎተራ፣ አያት 49 ጣፎ ... ሌሎችም አካባቢዎች በተለይ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች መልዕክቶችን ተቀብለናል።
@tikvahethiopia
🚨#እንድታውቁት
" ከሌሊቱ 6:00 እስከ 6:15 ሰዓት ላይ ርችት ይተኮሳል " - ፖሊስ
የፈረንጆች አዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ርችት እንደሚተኮስ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የደህንነትና ልዩ ኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ማስታወቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።
ዋና መምሪያው ለአዲስ አበባ ፖሊስ በላከው ደብዳቤ እንዳስታወቀው ዛሬ ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ/ም የሚከበረውን የፈረንጆቹን የአዲስ ዓመት ዋዜማ በዓል ምክንያት በማድረግ ከሌሊቱ 6:00 እስከ 6:15 ሰዓት ላይ ርችት ይተኮሳል፡፡
በመሆኑም ህብረተሰቡ ተገቢው መረጃ እንዲኖረው ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
@tikvahethiopia
🌟 ቴሌብር ሐዋላ በሽልማት ያንበሸብሻል!!
መጪውን የገና በዓል አስመልክቶ ከባህርማዶ በቴሌብር ሬሚት እና በአጋሮቻችን በኩል የተላከልዎን ዓለም አቀፍ ሐዋላ በቴሌብር ሲቀበሉ 10% የገንዘብ ስጦታ ያገኛሉ፡፡
💁♂️ በተጨማሪም 6ሺህ ብር እና ከዛ በላይ ሲቀበሉ አጓጊ ለሆነው ልዩ የዕድል ጨዋታ ብቁ ይሆናሉ!
🛋 የቤት ዕቃዎች - 15 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው 100,000 ብር
🐏 የበግ ስጦታዎች - 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው 15,000 ብር
🛒 የበዓል አስቤዛ - 50 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው 10,000 ብር
💰 የኪስ ገንዘብ - 300 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው 5,000 ብር
🎁 እንዲሁም በርካታ የሞባይል ዳታ ጥቅሎች
የሚቀበሉት የገንዘብ መጠን ሲጨምር የጨዋታ ዕድልዎም ይጨምራል!
🗓 እስከ ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ብቻ!
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSupperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቅሬታ ምንድነው ?
የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በግቢያቸው የተፈጠረው አለመረጋጋትና ረብሻ አስመልክቶ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል የወጡት መረጃዎች " ሚዛናዊ አልነበሩም " ሲሉ ተቋውማቸው በፅሁፍ አቅርበዋል።
94 የሚሆኑ የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በትግርኛ ቋንቋ ቅሬታቸውን ፅፈው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስገብተዋል።
ምን አሉ ?
እኚህ ተማሪዎች " የነበረውን እና እየቀጠለ ያለው የተማሪዎች ጥያቄ የሚከተለው ነው " ብለዋል።
ችግሩ ከመስከረም 26/2017 ዓ.ም የጀመረ ሆኖ ፦
1ኛ. አሸዋ የተደባለቀበት መግብ አንበላም፤
2ኛ. የፌደራል መንግስት ያወጣውን ሜኑ ይተግበር
3ኛ. ኢንተርፕራይዝ የተባለ አስቤዛ አቅራቢ ድርጅት ከቅጥር ግቢያችን ይውጣ
4ኛ. ያለውን ስለማይወክለን ድምፃችን የምናሰማበት የተማሪዎች ህብረት ለመመረጥ እንድንችል እድል ይመቻችልን
የሚሉ ናቸው ... ሲሉ ገልጸዋል።
" እነዚህ ያነሳናቸው የመብት ጥያቄዎች ተከትሎ ጥቅምት 7 እና ታህሳስ 14/2017 ዓ.ም ፓሊስ ግቢያችን ድረስ ዘልቆ ከባድ ድብድባ አካሂዶብናል " ብለዋል።
" በተለይ ታህሳስ 14 በ47 ተማሪዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል። የሴቶች የምኝታ ክፍል ሳይቀር በመክፈት ፓሊስ በአስነዋሪ መልኩ በመደብደብ አስፋልት ላይ ጥሎዋቸዋል " ሲሉ አመልክተዋል።
" አንድ አካል ጉዳተኛ ደግሞ ደብድበው ወደ ጉድጓድ ጥለውታል " ሲሉ ጠቁመዋል።
" 14 ተማሪዎች ፣ አንዲት ጥበቃ ፣ አንድ ከዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ፣ አንድ መምህር በከባድ ግርፋት በአጠቃላይ 17 ሰዎች በዓዲ ሓቂ ግቢ ብቻ በፓሊስ ተቀጥቅጠዋል ታስረዋል " ብለዋል።
" የተደበደቡት ተማሪዎች ህክምና እንዳያገኙ ለሦስት ቀናት በፓሊስ ተከልክለው ከቁሳላቸው ጋር እንዲሰቃዩ ተደርገዋል " ያሉት ተማሪዎቹ " ማንኛውም ተማሪ ለሚድያ ቃሉ እንዳይሰጥ፤ ወደ ማህበራዊ የትስስር ገፅ እንዳይለጥፍ እና እንዳያሰራጭ የተማሪዎች ህብረት እና ፓሊስ አስፈራርተውታል " ብለዋል።
" ቢሆንም ተማሪው የደረሰውን ግፍ በፅሑፍ ፤ በድምፅ እና በቪድዮ ደምፁ ከማሰማት ወደ ኋላ አላለም " ሲሉ ገልጸዋል።
ተማሪዎቹ በወጡት መረጃዎች ላይ ህፀፆች ያሏቸው ምን ምን ጉዳዮች ናቸው ?
" ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ሁኔታን አስመልክቶ ባቀረባቸው ተከታታይ መረጃዎች የሚከተሉት ህፀፆች ነበሩት " ሲሉ ቃላቸውን ሰጥተዋል።
1ኛ. መጀመሪያ በወጣው መረጃ " ሜኑ ይተግበር " ብለን የመብት ጥያቄ ያነሳን ተማሪዎች የፌደራል ሜኑን የተቃወምን በሚመስል መልኩ ነው የቀረበው።
2ኛ. ከታህሳስ 14 /2017 ዓ.ም በፊት በተከታይ ስናቀርበው የነበረውን የመብት ጥያቄያችን አልተካከተልንም።
3ኛ. በፓሊስ የተደበደብን ፣ የታሰርን የተንገላታን እኛ እያለን ፤ ንብረት እንዳወደምን ፣ ሰራተኞች እንደደበደብን ፣ አድማ እንደምታን ተደርጎ የቀረበው መረጃ ፍፁም የተሳሳተ ነው።
4ኛ. የተማሪዎች ህብረት ያስፈታቸው የታሰሩ ተማሪዎች እንዳሉ ተደርጎ የቀረበው ስህተት ነው እየጠቆመ ተማሪዎች የሚያሳስር ማን ሆነና ነው ? ተማሪዎች እንዲፈቱ ያደረግነው ከኛ ተማሪዎች የተውጣጣ ኮሚቴ ነው።
5ኛ. ያነሳነው የመብት ጥያቄ ሆን ተብሎ ፓለቲካዊ መልክ እንዲይዝ ተደርገዋል፤ የእኛ ጥያቄ የፓለቲካ ሳይሆን የዳቦ ጥያቄ መሆኑ እንዲታወቅልን እንፈልጋለን።
6ኛ. ድምፃችን እንዲሰማ አዲስ የቴሌግራም ገፅ በከፈቱ ሁለት ተማሪዎች የተማሪዎች ህብረት እስከ አሁን እያስፈራራቸው እንደሚገኝ እንዲታወቅልን እንፈልጋለን።
7ኛ. የምግብ አቅርቦቱ እንደተሻሻለ ፣ የአንዱ ዳቦ ግራም 120 እንዲሆን እንደተደረገ ተደርጎ የቀረበው መረጃ ልክ አይደለም። እስከ ታህሳስ 21/2017 ዓ.ም የተሻሻለ የምግብ አቀራረብና የዳቦ ግራም የለም 50 ግራም የሚመዘን ዳቦ ነው እየቀረበልን ያለው።
8ኛ. በመልእክት መለዋወጫ ቴሌግራማችን የታፈነ ድምፅ ፣ እንዲጠፋ የተደረገ ድምፅ ፣ የተሰረዘ ተማሪ እንደሌለ ተደርጎ የቀረበውም ውሸት ነው። ጥያቄ ያነሱ በርካታ ተማሪዎች ከቴሌግራም ግሩፕ እንዲወገዱ ተደርገዋል።
9ኛ. በዓዲ ሓቂ ግቢ በፓሊሶች እንጂ በተማሪዎች የተሰበረ በር እና መስተዋት እንደሌለ እንዲታወቅልን እንፈልጋለን።
10ኛ. በአጠቃላይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላይ የወጡት መረጃዎች ወደ ዩኒቨርስቲ አስተዳደር ፣ የተማሪዎች ህብረት እና ፓሊስ ያደላ የጉዳዩ ባለቤት የሆነው ተማሪ ድምፅ ያፈነ አቀራረብ ነበር፤ በዚህም እስካሁን ከማስፈራሪያ ከድብደባ ፣ ከህክምና እጦት ፣ ስቃይ እና ረሃብ እንዳንላቀቅ ሆኗል ... ብለዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ እኛ የ42 የተማሪ ክፍሎች ፣ 14 በእስር የሰነበቱ፣ 38 በከባድ የቆሰሉ በድምር 94 የመቐለ ዩኒቨርስቲ ዓዲ ሓቂ ግቢ ተማሪዎች እንደሆኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ባስገቡት ደብዳቤ አመልክተዋል።
በተማሪዎች ጉዳይ ዩኒቨርሲቲው፣ ኅብረቱ፣ የፀጥታ ኃይሉ ምንድ ነበር ያሉት ?
ዩኒቨርሲቲው፦
👉 በሜኑው ላይ የሚስተካከሉ ነገሮች ካሉ ብሄራዊ ሜኑ በይዘትና በጀት ደረጃ እስካልተለየ ድረስ ጥያቄዎች በተማሪዎች ህብረት በኩል ቀርበው ማስተካከል እንደሚቻል
👉 በሃገር ደረጃ ተግባራዊ የሆነውን የምግብ ሜኑ ተቃውሞ የዩኒቨርሲቲውን መሰረተልማት ማጥፋትና የካፊተርያ እና የጥበቃ ሰራተኞች ላይ ጉዳት ማድረስ ተማሪዎችን እንዲሁም ማህበረሰቡን እና ሃገሪቱን የሚጎዳና ተግባር መሆኑን
👉 ተማሪዎች ቅሬታቸውን በሰላማዊ መንገድ መግለጽ እንደሚችሉ ነበር የገለጸው።
የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኅብረትና የመቐለ ተማሪዎች ኅብረት፦
➡ ‘አንድ ዳቦ፣ ሁለት ዳቦ፣ አሸዋ አለው’ በሚለው ጉዳይ ቅሬታ ተነስቶ ነበር። 120 ግራም ነበር አንድ ዳቦ የሚጋገረው አሁን 60፣ 60 ተደርጎ ወደ ሁለት ሆኗል። ግራሙ ላይ የተጨመረ፣ የቀነሰ ነገር የለም።
➡ የቅሬታ መነሻ አዲሱ የምግብ ሜኑ ትግበራ ነው።
➡ 27 የታሰሩ ተማሪዎችን በዲፓርትመንት እና በስማቸው ለይተን ነው ያስፈታናቸው። ግን ካስፈታናቸው በኃላ ሌሊት ላይ ‘ሲቀጠቀጡ ከነበሩ የመለቐ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል አንዱ ሞቷል’ ብለው ፓስት አደረጉ ሄደን ስናጣራ የሞተ ተማሪ የለም። ይህ ሀንድል ከተደረገ በኃላ ‘የታፈኑ ተማሪዎች’ አሉ ወደሚል መጡ፤ ዝርዝር የላቸው ምን የላቸው ይህም ትክክል አይደለም።
➡ ተማሪዎች ተደብድበዋል፣ንብረት ወድሟል፣ በኃላ የታሰሩ ተማሪዎች ተፈትተዋል፤ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ነው.. ያሉት።
የኣዲ ሓቂ ፀጥታ ኃላፊ፦
🔴 የተማሪዎች ኀብረት ማለት የተማሪዎች ተወካዮች ናቸው። እነርሱ ከእኛ ጋር አብረው እየሰሩ ነው።
🔴 ተማሪዎቹ ያደረሱት ጉዳት ትልቅ በመሆኑ ሊፈቱ ባይገባቸውም የጉዳዩ መነሻ እነርሱ ሳይሆኑ ዩኒቨርሲቲው ሊያቀርበው የሚገባውን ነገር ባለማቅረቡ የተነሳ ነው። አስተምሮት ሰጥተን አንድም ልጅ ሳይቀር ፈትተናቸዋል።
🔴 የታሰረ ተማሪ የለንም ለቀናል። አሁንም ድጋሚ የሚሰሩት ስራ አለ እየተከላከልን ነው።
🔴 ዋና ዋና ለብጥብጡ ተዋናይ የነበሩ ተማሪዎችን ልንለቃቸው አልፈለግንም ነበር። የተማሪዎች ኀብረት ግን ‘እንደዚህ ከሚሆን እኛው ራሳችን እናስተካክለዋለን’ ስላሉን ለቀናቸው ችግሩ እንዲፈታ እየሰራን ነው።
🔴 ከተማሪዎች ጋር የመጣላት ፍላጎትም የለንም። ተማሪዎቹ መነሻ አይደሉም ለብጥብጡ፣ ለብጥብጡ መነሻው ራሱ ዩኒቨርሲቲው ነው...ብሎ የነበረው።
NB. ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሁሉም ያዘጋጃቸው መረጃዎች ከተማሪዎች የመጡ ቅሬታዎችን መነሻ አድርጎ፤ የሚመለከታቸውን አካላት ምላሽ አካቶ የቀረበ ነው።
@tikvahethiopia
#Earthquake
ለሊት 7:13 ላይ በሬክተር ስኬል 4.8 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደተከሰተ የጀርመኑ ጂኦ ሳይንስ እና የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ ያመላክታል።
የመሬት መንቀጥቀጡ የተመዘገበው ከአቦምሳ 39 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ነው።
ይህ ባለፉት ሰዓታት ከተመዘገበው ከፍተኛው ሲሆን በሬክተር ስኬል 4.0 ፣ 4.5 ፣ 4.6 ፣ 4.7 ... የሆኑ የመሬት መንቀጥቀጦች ቀን፣ ምሽት እና ለሊቱን በተከታታይ ተመዝግበዋል።
የነዚህ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቶች አዲስ አበባ እና የተለያዩ የክልል ከተሞች ጠንክረው ተሰምተዋል።
በተለይ በህጻዎች ላይ ያሉ ሰዎች ጠንከር ያለ ንዝረት ተሰምቷቸዋል።
በሌላ በኩል ፤ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት በከሰም ቀበና ቤቶች እና ንብረት ላይ ወድመት መድረሱን ነዋሪዎች ጥቆማቸውን በፎቶ አስደግፈው ልከዋል።
@tikvahethiopia
#Earthquake
በድጋሚ የአዋሽና አካባቢው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት " አስፈሪ ነበር " ያሉት የመሬት መንቀጥቀጥ ከደቂቃዎች በፊት መከሰቱን ጠቁመዋል።
" የመሬት መንቀጥቀጥ ድግግሞሹ እየባሰበት ነው " ያሉ ሲሆን " አላህ ይዘንልን ምናደርገው ጠፋን " ሲሉ ገልጸዋል።
" ነገሩ አዲስ አበባ እና ሌሎችም ቦታዎች ካልተሰማ ትኩረት እያገኘ አይደለም። ድግግሞሹ እኮ ብዙ ነው በሚዲያ ከሚገለጸውም በላይ ነው። ቤታቸውን ጥለው የወጡም አሉ ፤ ብቻ በጣም ነው የፈራነው " ሲሉም ተናግረዋል።
አሁን ድጋሚ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ነበር።
በተለይም በአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች ጠንከር ብሎ ተሰምቷቸዋል።
በአርባሳ ፣ ጣፎ ፣ አባዶ ፣ አያት ፣ ጀሞ ፣ ጋርመንት ... ሌሎችም ቦታዎች ንዝረቱ በደንብ ይሰማ እንደነበር የቲክቫህ አባላት ጠቁመዋል።
ከአዲስ አበባ ውጭ በሌሎች ከተሞች ንዝረቱ በደንብ እየተሰማ ነው።
@tikvahethiopia
" የአእላፋት ዝማሬ/The Melody of Myriads " በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ በተመሳሳይ ሰዓት እንደሚካሄድ ተገለጸ።
ይህንን የገለጸው አዘጋጁ የኢትዮጵያ ጃንደረባ ትውልድ / ኢጃት ማኅበር ነው።
የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ልደት ምክንያት በማድረግ የሚዘጋጀው ይህ የዝማሬ መርሐግብር በበዓሉ ዋዜማ ታኅሣሥ 28/ 2017 ዓ/ም ይካሄዳል።
በአዲስ አበባ ከተማ የዝማሬ መርሐግብሩ አምና በተካሄደበት በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል (ቦሌ መድኃኔዓለም) እንደሚካሄድ ነው አዘጋጆቹ ያሳወቁት።
" የጌታችንን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ልደት በዝማሬ እናክብር " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች የልደት በዓልን ዋዜማ በቤተክርስቲያን ተገኝተው በዝማሬ እንዲያከብሩ ተብሏል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ አዘጋጆቹ በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ካዘጋጁት " የአእላፋት ዝማሬ / The Melody of Myriads " መርሐግብር ውጭ ሌላ እንዳላዘጋጁ እንዲሁም ለዚህ መርሐግብር ተብሎ የሚደረግ ምዝገባም እንደሌለና ምዕመኑ ከሀሰተኛ መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል።
ባለፈው ዓመት በአዲስ አበባ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል በተካሄደው " የአእላፋት ዝማሬ/The Melody of Myriads " እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኦርቶዶክሳዊ ወጣት የልደት ዋዜማን በዝማሬና በፀሎት ተቀብሎ ነበር።
መርሐግብሩ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖትና ብፁአን አባቶች ተገኝተው እንደነበር አይዘነጋም።
ከመርሐግብሩ ቀደም ብሎ ምዕመናን በተለይም ወጣቶች የተዘጋጁ መዝሙሮችን አጥንተው እንዲመጡ መዝሙሮቹ በኦንላይን ሲሰራጩ ነበር።
ዘንድሮም በተመሳሳይ ለመርሃግብሩ የተዘጋጁ መዝሙሮች በማኅበሩ የማህበራዊ ሚዲያዎች (Janderbaw Media Youtube) ተጭነው ምዕመኑ ጋር እንዲዳረሱ እየተደረገ ነው።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Tigray
የትግራይ የፀጥታና የሰላም ቢሮ " ትግራይ ቴሌቪዥን " ይቅርታ ይጠይቅ አለ።
ቢሮው ይህን ያለድ ለአንድ ቀን ያህል በእገታና አስር ቆይተው ተለቀቁ በተባሉት ሦስት የትግራይ ቴሌቪዥን ባለሙያዎች ዙሪያ ባወጣው መግለጫ ነው።
የቢሮው መግለጫ የሚድያ ባለሙያዎቹ እገታ እና እስር አስመልክቶ የተሰራጨውን መረጃ የሚቃወም እንድምታ አለው።
ተስፋዝጊ ዓስበይ ፣ ኢሳያስ በየነ እና ኣታኽልቲ የተባሉ የትግራይ ቴሌቪዥን የሚድያ ባለሙያዎች ታግተውበታል ወደ ተባለው ቦታ መሄዳቸው የወረዳ ፣ የቀበሌ እና የመንደር አመራሮች መረጃ አልነበራቸውም ብሏል።
ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ' ታግተናል ታስረናል ' ማለታቸው ልክ እንዳልሆነ አመላክቷል።
" ጋዜጠኞቹ ወደ ቦታው እንዲንቀሳቀሱ የቀበሌ እና የመንደር አመራሮች መረጃ እንዲኖራቸው የግድ ነው ወይ ? " የሚል ጥያቄን ግን የቢሮው መግለጫ አለመለሰም።
" ሊበሉዋት የፈለጓትን አሞራ ቆቅ ናት ይሉዋታል " ብሎ የተረተው የሰላምና የፀጥታ ቢሮ መግለጫ ፤ ተገቢ ማጣራት ሳይደረግ የሚድያ ባለሙያዎቹ ' ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ታግተዋል ፤ ታፍነዋል ' ተብሎ የተሰራጨው መረጃ መስተካከል እና የትግራይ ቴሌቪዥን ይቅርታ ሊጠየቅበት እንደሚገባ አስገንዝቧል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ጋዜጠኞች እና የሚድያ ባለሙያዎች የሙያ ነፃነታቸው ተከብሮ በማንኛውም ጊዜ በማንኛውም ቦታ ተዘዋውረው መረጃ በማሰባሰብ ለህዝብ የማድረስ መብት እንዳላቸው የገለጸው የትግራይ ጋዜጠኞች ማህበር ፤ በትግራይ ቴሌቪዥን የሚድያ ባለሙያዎች ላይ የተደረገው ወከባ አፈና ፣ እስር እና እንግልት በፅኑ ኮንነዋል።
ጋዜጠኞቹ ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወር ለህዝብ እና ለአገር መረጃ ለማቅረብ ሲንቀሳቀሱ ተገቢ የፀጥታ ጥብቃ ሊድረግላቸው እንደሚገባ ያሳሰበው የማህበሩ መግለጫ ፤ ህግ እና ስርዓት አክብረው ተገቢ የሙያ ተግባራቸው በሚከውኑ የሚድያ ባለሙያዎች ላይ የሚድረግ ማንኛውም ዓይነት አፈና ፣ በደል ፣ ክልከላ እና ወከባ በጥብቅ እንቃወማለን ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
የመሬት መንቀጥቀጡ የቦታ ለውጥ አድርጓል ?
" በአንድ አካባቢ ተደጋግሞ እየተከሰተ ነው ያለው እንጂ የቀረበ ነገር የለም " - ፕ/ር አታላይ አየለ
በትላንትናው ዕለት በቀን፣ በምሽትና በለሊቱ ክፍለ ጊዜ ተደጋጋሚ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጦች መከሰታቸው ዓለም አቀፍ ጁኦሎጂካል ተቋማት ዘግበዋል።
ትላንት ምሽት 2:10 የተከሰተው እና ንዝረቱ እስከ አዲስ አበባ ከተሰማው በሬክተር ስኬል 5.0 ሆኖ ከተመዘገበው መንቀጥቀጥ በተጨማሪ ለሊት 7:20 ላይ 5.1 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ አስታውቋል።
የመሬት መንቀጥቀጡ በተጠቀሰው መጠን መከሰቱን እና ዛሬ ጠዋት 2:11 ላይም ሌላ መንቀጥቀጥ በመታየቱ የመተንተን ስራ እየተሰራ መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስ ህዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም፤ የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ፕ/ር አታላይ አየለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።
ትላንት ለሊት 7:20 ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከደብረ ሲና 52 ኪሜ ርቀት ላይ ምሽት ላይ የተከሰተው ደግሞ ከአዋሽ 14 ኪሜ ርቀት ላይ የተከሰተ ነው መባሉ ከዚህ ቀደም ይከሰት ከነበረበት የአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የቦታ ለውጥ አለ ማለት አለመሆኑን አስረድተዋል።
ተመራማሪው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል በዝርዝር ምን አሉ ?
" ትላንትና ከሰዓት ጀምሮ በጣም የተደጋጋመ ከፍተኛ መጠን ያለው ከ4.6 ጀምሮ እስከ 5.0 የተመዘገበ መንቀጥቀጥ ተከስቷል ፤ ነገር ግን ደብረ ሲና ሲል ከፈንታሌ በወፍ በረር ሲለካ ነው ከተለያየ አቅጣጫ በማየት ነው እንጂ መነሻው ስለተቀየረ አይደለም።
አንድ አካባቢ ላይ መሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት በአቅራቢያው ያለው ከተማ የትኛው ነው ? የሚለው ይታያል ከዛ የተለያዩ ከተሞችን እንደ ሪፈረንስ ይጠቅስና ከዛ ከተማ ምን ያህል ነው የሚርቀው የሚለውን ሪፈር ያደርጋል፤ እንደዛ ሲሆን ሌላ ሰው መንቀጥቀጡ ለዛ ከተማ ቀርቧል ማለት ነው የሚል ስጋት ሊያድርበት ይችላል ነገር ግን እስካሁን የተቀየረ ነገር የለም፤ ፈንታሌ ዙሪያ ነው እንቅስቃሴው እየተታየ ያለው።
የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ እና የጀርመኑ የጂኦ ሳይንስ ተቋማት የሚጠቀሙት ዳታ አውቶማቲክ ነው ሲስተሙ ቶሎ አናላይዝ አድርጎ የተከሰተበትን መጠን እና አካባቢ ከርቀት ጋር ይናገራል ነገር ግን ይህ አይነቱን አዘጋገብ የሚከተሉት ለማህበረሰቡ በምን ያህል ርቀት ላይ ነው የተከሰተው የሚለውን ለማስረዳት ነው።
ለምሳሌ፦ አንድ ብቻ አይደለም የተለያዩ ቦታዎች ይጠቅሳሉ ከመተሃራ፣ከደብረሲና ፣ከደብረ ብርሃን እና ከአዲስ አበባስ ምን ያህል ርቀት ላይ ይገኛል ሊል ይችላል በአንድ አካባቢ ተደጋግሞ እየተከሰተ ነው ያለው እንጂ የቀረበ ነገር የለም።
አዲስ ነገር አይደለም ስንመዘግብ የኖርነው ነገር ነው ነገር ግን መሃንዲስም፣ ኢንቨስተርም ሆነ የሚመለከተው አካል ጆሮ ሰጥቶ ጥንቃቄ አድርጎ አያውቅም አሁን የሚከሰተውንም መአት እንደተከሰተ አድርጎ የሚያወራ አለ እንደዛ አይደለም በተለያየ ጊዜ ይመዘገባል።
በ1997 በአፋር ታይቶ የማይታወቅ የቅልጥ አለት እንቅስቃሴ ነበር ብዙ አለም አቀፍ ሳይንቲስቶች ሁሉ መጥተው አብረን የሰራናቸው ስራዎች አሉ፣ ፈንታሌም በፈረንጂዎቹ 1981 እንደ አሁኑ 3 እና 4 ወር የቆየ የቅልጥ አለት እንቅስቃሴ ነበር።
የመረጃ ውንዥብር እየተፈጠረ ነው ሳይንቲስት የምንለው ማነው ? ታማኝነቱስ ምን ያህል ነው ?የሚለው አስቸጋሪ ሆኗል ያልሆነውን ሆኗል እያሉ የሚያወናብደውም ብዝቷል ተማረ የምንለውም መሬት ላይ ያለውም ህብረተሰብ።
መሬት በራሷ ጉዞ እየሄደች የምታስተነፍሰው ሃይል ነው ምንም የሚያስደንቅ ነገር አይደለም ቦታውም፣ በምን ያህል ርቀት ላይ እንደሆነ ይታወቃል በተለይ አዲስ አበባ ያለ ሰው ምንም ሊደነግጥ አይገባም።
ከትላንት እኩለ ቀን ጀምሮ ጎላ ጎላ ያሉት መንቀጥቀጦች የመደጋገም ፍጥነታቸው ጨምሯል ቀጣይነትም ያለው ሊሆን ይችላል እየተከታተልን እየመዘገብን እንገኛለን " ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
#AAU
#ቲክቫህኢትዮጵያ
@tikvahethiopia
" ከ2 ሺሕ 500 በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል " - አቶ አደም ባሂ
በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ አከባቢ በሚከሰት ተደጋጋሚ ርዕደ መሬት ከ100 በላይ ቤቶች ጉዳት የደረሰባቸዉ ሲሆን 2 ሺሕ 560 ሰዎች መፈናቀላቸውን እና እንሰሳት መሞታቸውን የአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ አስተዳደር አቶ አደም ባሂ አሳውቀዋል።
ለአሐዱ በሰጡት ቃል ፤ " ይህ ክስተት በሚድያ እንደሚባለዉ በቀን ሦስቴ እና ሁለቴ የሚከሰት ሳይሆን ከዚያም በላይ አስጊ እየሆነ ይገኛል " ብለዋል።
በአካባቢዉ ያለዉ የከሰም ግድብን ጨምሮ ሌሎች መሰረተ ልማቶችስ ጉዳት ደርሶባቸዋል ወይ ? ለሚለው ጥያቄ " ግድቡን በተመለከተ ራሱን የቻለ አደረጃጀት ተደራጅቶ እየተጠበቀ ይገኛል " ሲሉ ተናግረዋል።
" እስካሁን በተፈጠረዉ ርዕደ መሬት ምክንያት ምንም ጉዳት ባይደርስበትም፤ በተደጋጋሚ በአቅራቢያው እየተከሰተ በመሆኑ በጥብቅ እየተከታተሉ ነው " ሲሉ አክለዋል።
በተጨማሪም በአካባቢዉ ያለዉ ተፈናቃይ ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ መሆኑን አንስተው ፤ መጠለያ፣ ምግብ እና መሰረታዊ ግብአቶች እንደሚያስፈልጉ ተናግረዋል።
የክልሉ የአደጋ ስጋት ድጋፍ እንዲያደርግም እንደጠየቁ ገልጸዋል።
በተደጋጋሚ ጊዜ በተከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጦች ምክንያት፤ እስከ አሁን በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ሳቡሬ እና ዶኾ ቀበሌዎች ከ30 በላይ የመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱም ተነግሯል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የአሐዱ ነው።
@tikvahethiopia
#Update
" በአደጋዉ ሙሽራዉን ጨምሮ የ71 ሰዎች ሕይወት አልፏል " - ማቴ መንገሻ (ዶ/ር)
🚨 " አደጋዉ ' ከቡና ሳይት በሚመለሱ ሰዎች ላይ የተከሰተ ነዉ ' ተብሎ የተገለፀት አግባብ ሙሽራዉን ጨምሮ አብዛኞቹ ሟቾች የቡና ሳይት የሚሰሩ በመሆናቸዉ ነው ! "
ዛሬ በሲዳማ ክልል፣ ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ቦና ወረዳ ልዩ ስሙ ጋላና ድልድይ ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ ሰርገኞችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ መኪና ተገልብጦ ሙሽራውን ጨምሮ የ71 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ ማቴ መንገሻ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" አይሱዙው 11 ሰዓት አካባቢ መነሻዉን ቦና ወረዳ ሚሪዴ ገጠር ቀበሌ አድርጎ ወራንቻ ወደተባለ አጎራበች ቀበሌ የወንድ ወገን የሆኑ ከ70 በላይ ሰርገኞችን ጭኖ ወደ ሴቷ ቤት ጉዞ ላይ ነበር " ብለዋል።
ገላና ድልድይ ላይ ሲደርስ ግን ድልድዩን ስቶ ወደ ወንዝ ዉስጥ በመግባቱ እስካሁን በተጣራዉ መረጃ አስክሬናቸው ቦና አጠቃላይ ሆስፒታል የደረሰ 66 እንዲሁም ከአደጋዉ ቦታ በቀጥታ ቤተሰቦቻቼዉ የወሰዷቸዉን ጨምሮ በአጠቃላይ ወንድ 68 ሴት 3 በድምሩ 71 ሰዎች ሕይወት ማለፉን አረጋግጠዋል።
በ4 ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱንና አንዲት ሴት ወደ ሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል መላኳንም ማቴ (ዶ/ር) ጨምረው ገልፀዋል
የአደጋው ትክክለኛ መንስኤ እየተጣራ ነዉ ያሉት ማቴ (ዶ/ር) ፤ " በገጠር አከባቢ በሰርግ እና ደስታ ወቅት በክፍት መኪኖች ላይ ከመጠን በላይ መጫንና አልፎ አልፎም መጠጥ የመቀማመስ ሁኔታዎች ስለሚኖሩ፤ ይህ ለአደጋው አንዱ መንስዔ ተደርጎ ይገመታል " ብለዋል።
" አደጋዉ ' ከቡና ሳይት በሚመለሱ ሰዎች ላይ የተከሰተ ነዉ ' ተብሎ የተገለፀት አግባብ ሙሽራዉን ጨምሮ አብዛኞቹ ሟቾች የቡና ሳይት የሚሰሩ በመሆናቸዉና ተሽከሪካሪዉም የቡና ሳይት በመሆኑ ነዉ " ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
የክልሉ ፖሊስ ቀደም ብሎ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል መኪናው ላይ የነበሩት ወገኖች የቡና ሳይት ስራ ላይ ቆይተው ሲመለሱ የነበሩ እንደሆኑ ገልጾ ነበር።
እንደ ዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ማብራሪያ ግን ምንም እንኳን መኪናው ላይ የነበሩት አብዛኛዎቹ ወገኖች (ሙሽራውን ጨምሮ) የቡና ሳይት ስራ ላይ ተሰማርተው የሚሰሩና መኪናውም የቡና ሳይት ቢሆንም በሰዓቱ ሲጓዙ የነበረውና አደጋው የደረሰው ለሰርግ ወደ ሴቷ ቤት ማለትም ሙሽራው ሙሽሪትን ለመውሰድ ሲሄዱ ነው።
በአደጋዉ ከአንድ ቤተሰብ እስከ 4 ሰዉ የሞተበት ሁኔታ ስለመኖሩ የገለጹት ማቴ ማንገሻ (ዶ/ር) የአደጋው ሰለባ የሆኑት ሁሉም ሟቾች ከ40 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች ስለመሆናቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
" የ71 ሰዎች ሕይወት አልፏል " - ፖሊስ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በቦና ዙሪያ ወረዳ ጋላና ወንዝ ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ 74 ሰዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ መኪና ድልድዩን ስቶ ወንዝ ዉስጥ በመግባቱ የ71 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታዉቋል።
የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ቶማስ አደጋዉን አስመልክቶ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት " በመኪናው ላይ የነበሩት የቡና ሳይት ስራ ላይ ቆይተዉ ወደ ከተማ ሲመለሱ የነበሩ ሰዎች ናቸዉ " ብለዋል።
የአደጋዉ መንስኤ የተጣራ ሲሆን 68 ወንዶችና 3 ሴት በድምሩ 71 ሰዎች ሕይወት ማለፉን አረጋግጠዋል።
የተረፉት 3 ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዉ በሕክምና እየተረዱ መሆኑን የገለፁት ኮሚሽነሩ ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝተዋል።
ነፍስ ይማር !
@tikvahethiopia
አል-ሲሲ ምን እያሉ ነው ?
ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ ከባህር በር ጋር በተያያዘ የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራረሙ ማግስት አንስቶ ከሶማሊያው መሪ ጋር እየተደዋወሉ እና እየተገናኙ ፦
" ° አይዟችሁ እኛ አለን ፤
° ከፈለጋችሁ ወታደርም እንልካለን ፣
° የጦር መሳሪያ ድጋፍም ይኸው፣
° በሰላም ማስከበርም እንሳተፋለን ፣
° እናተን ማንም እንዲነካ አንፈቅድም " እያሉ ሲለፍፉ የከረሙት የግብጹ መሪ አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ አሁን ደግሞ የአንካራውን ስምምነት " በቅርበት እየተከታተልን ነው ፤ መረጋጋትንም ሊያመጣ ይችላል " የሚል ዲስኩር ይዘው ብቅ ብለዋል።
ድሮውንም የኢትዮጵያ ነገር አይኗን የሚያቀላው ግብፅ ከመግባቢያ ስምምነቱ (MoU) በኃላ ስለ ኢትዮጵያ ብዙ አሉታዊ ነገር ስታወራ ፣ የማጠልሸት ስራ ስትሰራ ነበር የከረመችው።
ትላንት የግብፁ መሪ አል-ሲሲ በቅርብ ኢትዮጵያ መጥተው ከነበሩትና የኢትዮጵያ የባህር ባር ጥያቄን በይፋ ከደገፉት የፈረንሳዩ ፕሬዜዳንት ማክሮን ጋር የስልክ ውይይት አድርገው ነበር።
በዚህም ወቅት ፥ አል ሲሲ በቱርክ አሸማጋይነት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የፈረሙትን ስምምነት ጠቅሰው " በቅርብ እየተከታተልን ነው ፤ ስምምነቱ በአፍሪካ ቀንድ ፀጥታ እና መረጋጋት ሊያመጣ ይችላል " ሲሉ ተናግረዋል።
" ይህ ስምምነት በአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት እንደሚያመጣ ተስፋ አለኝ ዓለም አቀፍ ሕግን ተከትሎ ሊሆን ይችላል። በአፍሪካ ቀንድ ያለው መረጋጋት እና የግብፅ ብሔራዊ ጥቅምት የተሳሰሩ ናቸው " ሲሉ እንደገለጹም ተነግሯል።
አል-ሲሲ " ለሶማሊያ ድጋፍ ለማድረግ እንሰራለን ይህ ድጋፍ በሁለትዮሽ ግንኙነት አሊያም በአፍሪካ ሕብረት የሰላም አስከባሪ ሚሽን አማካይነት ነው " ብለዋል።
ግብፅ ፤ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ቁርሾ ውስጥ በከረሙበት ወራት ስታወጣ የነበረው መግለጫና ስታደርግ የነበረው እንቅስቃሴ ሀገራቱን ወደ መግባባትና ሰላም እንዲመጡ ለማድረግ ሳይሆን ነገሩን ለማጋጋል ፣ ለማባባስ ፣ የለየለት ቀውስና ጦርነት እንዲፈጠር ለማድረግ የታስበ እንደሆነ አመላካች እንደነበር ብዙዎች የሚገልጹት ነው።
#Ethiopia🇪🇹
@tikvahethiopia
" የሰላም ችግር ከሁሉም በፊት ቀድሞ መፍትሔ ማግኘት አለበት " - ፕ/ር መረራ ጉዲና
ባለፈው ሳምንት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ (ኦፌኮ) አዲሱን ዋና ፅ/ቤቱን በአዲስ አበባ አስመርቋል።
የቀድሞ ሜክሲኮ የሚገኘው ዋና ፅ/ቤቱ በኮሪደር ልማት ምክንያት በመፍረሱ አዲሱን ቢሮ ቀበና አደባባይ አከባቢ ከፍቶ ስራ አስጀምሯል።
በዚህ ወቅት የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ንግግር ያደረጉ ሲሆን " አሁንም ሀገራችን ትልቅ ችግር ውስጥ ናት " ብለዋል።
የሰላም ችግር ከሁሉም በፊት ቀድሞ መፍትሔ ማግኘት እንዳለበትም ገልጸዋል። ለዚህ ደግሞ ወደጦርነት የሚመሩትን የፖለቲካ ችግሮች በውይይት መፍታት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።
" የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎትም ሆነ የሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ፍላጎት ዘላቂ ሰላም ፣ ጠንካራ የዲሞክራሲ ስርዓት እና በኢኮኖሚ የበለፀገች ኢትዮጵያን ማየት ነው " ያሉ ሲሆን፤ " ይሄን ከግብ ለማድረስ ኦፌኮ'ን ጨምሮ ሌሎች የተቃዋሚ ፖርቲ ህብረቶች ትግላቸውን ማጠናከር አለባቸው " ሲሉ ተናግረዋል።
በወቅቱ ተገኝተው የነበሩ የተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች " ህዝቡ ላይ እየደረሰ ያላውን ችግር ለመፍታት ህብረታችንን በደንብ በማጠናከር እና ህዝቡን ከጎን በማሰለፍ አንድላይ መቀጠል ይኖርብናል " ብለዋል።
ኦፌኮ አዲሱን ዋና ፅ/ቤቱን ስራ ባስጀመረበት ወቅት " በአገሪቱ ውስጥ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ እና በቀጣዩ ትግል አቅጣጫ ላይ ዝርዝር ውይይት ተደርጓል " ያለ ሲሆን " በዚህ መሠረት በጦርነቱ ጉዳት፣ በኢኮኖሚ ውድቀት ምክንያት የማህበራዊ መቃወስና ወደ መፍረስ እየተኬደ ካለው መንገድ ኢትዮጵያን ለመታደግ ትኩረት ይሰጣል " ብሏል።
#OFC #AddisAbaba
@tikvahethiopia
#Update
ከመሬት መንቀጥቀጡ ጋር በተያያዘ አፋር፣ አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ልከዋል።
" ዛሬ በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ነበር። መጠናቸው ግን ዝቅ ያለ ነው። ከደቂቃዎች በፊት የነበረው ግን በጣም ያስፈራ ነበር። ሁኔታ አለመቆሙ እጅግ አስደንግጦናል ፤ የከፋ ነገር እንዳይፈጠር እያልን በሰቀቀን ውስጥ ነን " ብለዋል።
ከደቂቃዎች በፊት የነበረው መንቀጥቀጥ ንዝረት አዲስ አበባ ከተማ ብዙ ቦታዎች በደንብ ተሰምቷል።
እቃ አንቀሳቅሷል፣ አልጋ ላይ ያሉ ሰዎች ሲንቀሳቁም እንደነበር ጠቁመዋል። ከዚህ ቀደም ስሜቱን ያልሰሙ ቦታዎችም ንዝረቱ ተሰምቷል።
" ተሰምቶን አያቅም እኮ " የሚሉ ሰዎችም ዛሬ ምሽት ስሜቱን እያተውታል።
ቃላቸውን ለቲክቫህ የላኩ ቤተሰቦች " ከወትሮ የተለየ ነበር ድንጋጤን ፈጥሮብናል " ሲሉ ገልጸዋል።
አንድ የጋራ መኖሪያ ቤት ላይ የሚኖር ነዋሪ " የዛሬው ይለይ ነበር። በተኛሁበት ሲነቃነቅ ተሰምቶኛል ደንግጬ ወደ መሬት ወረድኩ " ብሏል።
ሌላ መልዕክቱን የላከ የቤተሰባችን አባል ፥ ነዋሪነቱ ጃክሮስ እንደሆነ ቪላ ቤት ውስጥ እንደሚኖሩ ስለ ንዝረቱን ከዚህ ቀደም በሚዲያ ከሚሰሙት ውጭ በተግሻር ተሰምቷቸው እንደማያውቅ ዛሬ ግን እንደተሰማቸው ገልጿል።
" በጣም ነው ፍራቻ የለቀቀብን " ሲል ሁኔታውን ገልጿል።
አንድ የቤተሰባችን አባል ፥ " ንዝረቱን በደንብ እንደሰሙ ቋቋ የሚል ድምጽም እንደተሰማቸው " ጠቁመዋል።
ሌላኛዋ የመልዕክት ላኪ ቤተሰባችን " የእቃ እንቅስቃሴ እንደነበር ፤ እሷም በተቀመጠችበት መንቀሳቀሷን ፤ በፊት ከነበረው ይለይ እንደነበር " ገልጻለች።
ቱሉዲምቱ ፣ አራብሳ ፣ ጃክሮስ ፣ ጋርመንት ፣ ለቡ፣ ጀሞ፣ አያት ፣ አያት 49 ፣ ጎሮ፣ አባዶ፣ ካራ፣ ጣፎ፣ ... ከሌሎችም ብዙ ቦታዎች ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባላቱን መልዕክት ተቀብሏል።
ውድ የአፋር እና የሌሎችም የክልል ከተሞች ቤተሰቦቻችን " ሁኔታው የተለመደ ነው " ብላችሁ እንዳትዘናጉ አደራ እያልን በዚህ ሊንክ👇 /channel/tikvahethiopia/93268 ያለውን የጥንቃቄ መንገዶች በማስተወሻችሁ ላይ አኑሩት።
ፎቶ ፦ ፋይል
@tikvahethiopia
" አደጋው የአንድ ቤተሰብና ዘመድ አዝማድ 33 ሰዎችን ከአንድ ቀበሌ የ52 ሰዎችን እንዲሁም ከአንድ ቤት የ4 ወንድማማቾችን ሕይወት የቀጠፈ ነበር " - ማቴ መንገሻ (ዶ/ር)
በቦና ወረዳ በመኪና አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ 71 ወገኖቻችን ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ።
ከትላንት በስቲያ አመሻሽ ሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ቦና ወረዳ የሙሽራዉ ወገን ሰርገኞችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ ክፍት መኪና የገላና ድልድይ ተብሎ በሚጠራዉ ቦታ መንገድ ስቶ ገደል ውስጥ በመግባቱ የ71 ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ማለፉ ይታወሳል።
በአደጋዉ ምክንያት ሕይወታቸዉን ያጡ 71 ወገኖች ስርዓተ ቀብር ዛሬ ተፈጽሟል።
በስርዓተ ቀብሩ ወቅት የክልሉ ርዕሰ መስተደድር አቶ ደስታ ሌዳሞና ከፍተኛ አመራሮች፤ ከሁሉም አከባቢዎች የተሰባሰቡ ወዳጅ ዘመዶች ተገኝተው ነበር።
ርዕሰ መስተዳድሩ ፤ " በአንድ ድንገተኛ አደጋ ይህን ሁሉ ሰዉ ማጣት መሪር ሀዘን ነዉ፤ ፈጣሪ መፅናናቱን ይስጠን " ብለዋል።
የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ ማቴ መንገሻ (ዶ/ር) ፥ " አደጋው የአንድ ቤተሰብና ዘመድ አዝማድ 33 ሰዎችን ከአንድ ቀበሌ የ52 ሰዎችን እንዲሁም ከአንድ ቤት የ4 ወንድማማቾችን ሕይወት የቀጠፈ ነበር " ብለዋል።
ከክልሉ መንግስት ጀምሮ መላዉ ሕብረተሰብ የጤናና ፀጥታ መዋቅሩ ላደረገዉ ርብርብ ምስጋና አቅርበዋል።
የሟቹችን ቤተሰቦች ለማፅናናት እና ለማገዝ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን ገልጸው በገንዘብና በዓይነት የተሰበሰቡና እየተሰበሰቡም ያሉ ድጋፎችን በቀጣይ ለተጓጂ ቤተሰቦች በአግባቡ የማዳረስ ስራ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከው በሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
@tikvahethiopia
#TPLF : ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) ጠቅላላ ጉባዔውን እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳስቧል።
ምርጫ ቦርድ ፤ ህወሓት በኢትዮጵያ የምርጫ የፖለቲካ ፖርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነምግባር አዋጅን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር መሠረት በልዩ ሁኔታ መመዝገቡን አስታውሷል።
ፖርቲው ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ባሉት ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የፓርቲውን ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ እንደሚጠበቅም አመልክቷል።
ምንም እንኳን ፓርቲው በስድስት ወር ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ የሚለውን ግዴታ ያለተጨማሪ ማሳሰቢያ መፈፀም እንዳለበት የሚታመን ቢሆንም ቦርዱ ለፓርቲው ነሀሴ 3 ፣ ነሀሴ 20 /2016 ዓ/ም እንዲሁም ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም በፃፋቸው ደብዳቤዎች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማከናዎን ጠቅላለ ጉባኤውን እንዲያደርግ ማስታወቁን አመልክቷል።
" ፓርቲው በልዩ ሁኔታ የተመዘገበው ነሀሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም በመሆኑ ጠቅላላ ጉባኤውን እስከ የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲያደርግ ይጠበቃል " ያለው ምርጫ ቦርድ " ለዚሁ የጠቅላላ ጉባኤ ዝግጅት የሚያስፈልገውን የቅድመ ጉባኤ ዝግጅት የተመለከቱ ስራዎችን ቦርዱ መከታተል እንዲችል ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤውን ከማድረጉ 21 ቀናት በፊት ጉባኤው የሚደረግበትን ቀን ለቦርድ እንዲያሳውቅ ይጠበቃል " ብሏል።
ይሁንና እስከ ዛሬ ድረስ ፓርቲው ከተመዘገበ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ ማድረግ የሚያስችለውን እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ቦርዱ እንደማያውቅ አመልክቷል።
ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ማድረግ የሚገባው ወቅት ሊገባደድ ከሁለት ወር ያነሰ ጊዜ የቀረው በመሆኑ ፖርቲው ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በቀረው አጭር ጊዜ የጠቅላለ ጉባኤውን እንዲያደርግ ቦርዱ በጥበቅ አሳስቧል።
ይህ በሕግ ፓርቲው ላይ የተጣለ ግዴታ በወቅቱ ሳይፈፀም ቢቀር ቦርዱ ሕጉን መሠረት በማድረግ ተገቢ ነው የሚለውን ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑን አሳውቋል።
ከዚህ ቀደም የህወሓት አመራሮችን ለሁለት የከፈለ ጉባኤ መደረጉ አይዘነጋም።
በወቅቱም ምርጫ ቦርድ ያልተገኘበትን እና ስርዓቱን ያልተከተለ ጠቅላላ ጉባኤ እውቅና እንደማይሰጥ ማስገንዘቡ ይታወሳል።
ምንም እንኳን ምርጫ ቦርድ እውቅና እንደማይሰጥ ቢያሳውቅም በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ቡድን ጉባኤ አድርጎ አመራሮቹን መርጧል።
አቶ ጌታቸው ረዳን እና ሌሎች ከእሳቸው ጋር የነበሩ ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮችን ከቦታቸውን አንስቷል።
በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ቡድንም ለጉባኤው እውቅና የነፈገ ሲሆን ትክክለኛ ቅቡልነት ያለው ጉባኤ እንዲደረግ እየሰራ መሆኑን ማሳወቁ አይዘነጋም።
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#Kesem_Dam
🚨 "በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ በከሰም ግድብ አከባቢ ያሉ ነዋሪዎች በብዛት እየለቀቁ ነው" - ነዋሪዎች
🔴 " ግድቡ ዲዛይኑ እስከ 7.0 ሬክተር ስኬል የመሬት መንቀጥቀጥ ይችላል ተብሎ ይገመታል " - ጽ/ቤቱ
በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ በተለያዩ ቦታዎች የመሬት መሰንጠቆች በመፈጠራቸውና በተፈጠሩ ስጋቶች ምክንያት ነዋሪዎች ካሉበት አከባቢ ወደ ሌላ አከባቢ እየሸሹ መሆኑን ሰምተናል።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ የአፋር ቤተሰብ በትላንትናው ዕለት በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ አርብሃራ ቀበሌ እና ዶኾ ቀበሌ በመገኘት በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት እቃቸውን ጭነው ሲጓዙ የነበሩ ነዋሪዎችን አግኝቶ አነጋግሯል።
ኃሳባቸውን የሰጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች የመሬት መንቀጥቀጡ እንዲሁም እሱን ተከትሎ የሚሰማው ድምጽ በተለይ ለልጆቻቸው ፍርኃት እንደፈጠረባቸው አስረድተዋል።
ከትላንት በስቲያ ከአርብሀራ ቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው መልካወረር ከተማ የመሬት መንቀጥቀጡ ከፍ በማለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች ለሶላት (ዱኣ ለማድረግ) ወደ መስጂድ እንደገቡ ነው የገለጹት።
በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት እቃቸውን በሦስት እግር ተሽከርካሪ ጭነው አከባቢውን ሲለቁ ያገኘናቸው ወጣቶች " ብዙ ሰው ለቋል፤ አረ ሁሉም ለቋል እዚያ ሰፈር ያለ ሁሉም እየለቀቀ ነው " በማለት ወደ አዋሽ አርባ እየተጓዙ መሆኑን ተናግረዋል።
የአስፋልት መሰንጠቅ በተከሰተበት ቦታ ያገኘነው አንድ ነዋሪ እንዳስረዳው በርካታ ሰዎች እየለቀቁ ያሉት በወረዳው ከሚገኘው የከሰም ግድብ አከባቢ ያሉ ነዋሪዎች መሆናቸውን ጠቅሷል።
" ከ7 ጀምሮ [በትላንትናው ዕለት] ያለውን ሁኔታ ብታየው በሚገርም ሁኔታ እቃ እየተጫነ ነው፤ በጣም ደግሞ በትናንሽ መኪኖች በባጃጅም ሁሉም እንደ አቅሙ እንደ ኑሮ ደረጃው እቃውን ጭኖ እየወጣ ነው። " ሲልም ነው ያስረዳው።
በተለይም " ግድቡ የመሰንጠቅ አደጋ ደርሶበታል " በሚል የፋብሪካው ሰራተኞች ጨምሮ ነዋሪው በሌሊት ጭምር እቃውን እየጫነ፤ ግመሎቹንና እንስሳቱን እየነዳ ከአከባቢው መሸሹን ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረዳት ችሏል።
ዛሬ ጠዋትም በከሰም ያሉ ነዋሪዎችን ያነጋገርን ሲሆን ትላንት ሌሊት በነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ በርካቶች ከቤታቸው ወጥተው አስፓልት ላይ ማደራቸውን ነግረውናል።
የመሬት መንቀጥቀጡ ንጋት ላይም በመቀጠሉ በርካቶች ንብረታቸውን ይዘው ወደ አዋሽ አርባ እየሸሹ መሆኑን ለመረዳት ችለናል። ነዋሪዎች በመንግሥት በኩል በቂ የማረጋጋትም ሆነ ድጋፍ የማድረግ ሥራ በአከባቢው እንዳልተሰራነው የገለጹት።
በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳዎች ለሚገኘው ከሰም ስኳር ፋብሪካ አገልግሎት የሚሰጠው የከሰም ግድብ 500 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የመያዝ አቅም ያለው ነው።
የግድቡ ባለሞያዎች ነዋሪዎች አከባቢውን ለቀው የሄዱት " ግድቡን ውሃ እየጣሰ ነው " በሚል ሀሰተኛ ወሬ መሆኑን መግለጻቸውን ከአዋሽ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የአዋሽ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አደን አብዶ ስለ ግድቡ አሁናዊ ሁኔታ ለቲክቫህ ምን ምላሽ ሰጡ ?
" የግድቡ አካባቢ ላይ ያለውን አሁናዊ ሁኔታ በቅርበት እየተከታተልን ስለሆነ ምንም አይነት ችግሮች የሉም በአሁን ሰዓት ሰላም ነው።
ከግድቡ 30 እና 40 ኪሜ ላይ ነው መንቀጥቀጡ ከበድ ያለው። ቦታው ላይ ካሉ አስተዳደሮች እስካሁን ድረስ ከግድቡ ጋር የተያያዘ የደረሰን መጥፎ መረጃ የለም።
ግድቡ ዲዛይኑ እስከ 7.0 ሬክተር ስኬል የመሬት መንቀጥቀጥ ይችላል ተብሎ ይገመታል እስካሁን እዚህ አልደረሰም ባለሞያዎች እየተከታተሉ ያለውን ስጋት ሪፖርት ያደርጋሉ እኛም ለሚመለከተው አካል እናስተላልፋለን።
በተፋሰስ ውስጥ ያለውን ህብረተሰብ የማንቃት እና ያለውን ሂደቶችን ኮሚቴ ተዋቅሮ መረጃ የሚለዋወጡበት ሂደት ከክልሉ መስኖና ቆላማ ቢሮ እስከ እስከ አደጋ መከላከል ድረስ የቅድመ መከላከል ስራዎች እየተሰሩ ነው " ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAfar
@tikvahethiopia
#BankOfAbysinia
ዘመናዊ ፖስ ማሽኖቻችን ባሉባቸው የግብይት ቦታዎች ሰልፍ አይታሰብም!
#POSMachine #contactless #DigitalPayments #CashlessTransactions
#BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#ለጥንቃቄ🚨
የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ምን ማድረግ አለብን ?
➡️ ከቤት ውጭ ከሆኑ ፦ ከዛፎች ፣ ከሕንፃዎች ፣ ከኤሌትሪክ ምሶሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እና ገላጣ ሜዳ አካባቢ መቆየት።
➡️ በቤት ውስጥ ከሆኑ ፦ በበር መቃኖች ፣ ኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ። ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች እንዲሁም ከመስኮት አካባቢ መራቅ። የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።
➡️ በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ ፦ ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር ፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።
➡️ መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ ፦ የኤሌትሪክ መተላለፊያ ምሶሶዎችን፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌትሪክ መስመር ምሶሶዎች እና ሽቦዎች ተሽርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም።
#Ethiopia
#የአአእሳትናአደጋስራአመራርኮሚሽን
@tikvahethiopia
#Earthquake
ዛሬ ምሽቱን ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ በደንብ የተሰማ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ተከስቷል።
በተለይ አዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ያሉ ነዋሪዎች ጠንከር ብሎ እንደተሰማቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠቁመዋል።
አያት፣ ጣፎ፣ አራብሳ ፣ ጀሞ ... ሌሎችም አካባቢዎች ምዝረቱ ተደጋጋሚ ጊዜ ተሰምቷል።
የአዋሽ ቲክቫህ አባላት ደግሞ የመሬት መንቀጥቀጡ በጣም እያስፈራቸው እንደመጣና ድግግሞሹ እየበዛ መሆኑን ጠቁመዋል።
" ባለፉት 48 ሰዓታት የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ብዙ ነበር። ድግግሞሹ ከመጨመሩ በኃላ መጠኑን ከመጨመሩ ጋር በተያያዘ አስፈሪ ሆኗል " ብለዋል።
@tikvahethiopia
ወደ ኖርዌይ ለልምድ ልውውጥ የሄዱ የሁለት የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ወደ ሀገር ሳይመለሱ ቀሩ።
የኢዜማ እና የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አባላት ለልምድ ልውውጥ ከሃገር በወጡበት አለመመለሳቸው ተሰምቷል።
የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦሮ) የሴቶች ጉዳይ ሃላፊ ወ/ሮ አበበች ደቻሳ እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የሴቶች ጉዳይ ተጠሪ የነበሩት ወ/ሮ ቅድስት ግርማ በመስከረም አጋማሽ ለልምድ ልውውጥ ወደ #ኖርዌይ ባቀኑበት ወቅት አለመመለሳቸው ተነግሯል።
ሁለቱ አባላት ወደ ኖርዌይ ያቀኑትና ያልተመለሱት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የልምምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ በተላኩበት ወቅት መሆኑን የም/ ቤቱ ጸሃፊ አቶ ደስታ ዲንቃ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አባላቱ በጋራ ምክር ቤቱ የሴቶች ክንፍ ሰብሳቢነት እና ስራ አስፈጻሚነት ሲያገለግሉ ነበር።
አቶ ደስታ ፥ " የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ ለማጠናከር በሃገር ደረጃ ከፓርላማ አባላት ጋር እና የሲቪክ ተቋማት ጋር እየተገናኙ ብዙ ስራዎችን ሲሰሩ ነበር " ብለዋል።
ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ የኢዜማ አባል ፤ አባሏ በስራ ገበታቸው ላይ አለመኖራቸው በማስረዳት " ለምን እንዳልተመለሱ የምናውቀው ነገር የለም " ብሏል።
የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በበኩሉ ከልጆቿና ከባለቤቷ ጋር በፖለቲካ ምክንያት ለእስር ተዳርገው እንደነበር የገለጸ ሲሆን ለመቅረቷም ምክንያት ይህ ሳይሆን እንዳልቀረ ገልጿል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#AwashBank
ሽልማትዎን ይውሰዱ!
=========
አዋሽ ባንክ ‘ባንክዎ በእጅዎ’ በሚል መሪ ቃል ለአንድ ወር የሚቆይ የዲጂታል ባንኪንግ ንቅናቄ እያካሄደ ይገኛል። በመሆኑም የአዋሽ ብር ፕሮ ሞባይል ባንኪንግ አገልግሎትን ሲጠቀሙ፡
- ለነጋዴዎች 52 ስማርት ስልክ ስጦታዎች
- ለድርጅት ገንዘብ ተቀባዮች በጋራ እስከ 15 ሺህ ብር የጉርሻ ስጦታ
- ለደንበኞች አዋሽ ብር ፕሮን ሲመዘገቡና መጠቀም ሲጀምሩ የ15 ብር የጉርሻ ስጦታ
- ከዚህ በፊት ተመዝግበው ነገር ግን ሳያንቀሳቅሱት ቆይተው አሁን መጠቀም ሲጀምሩ የ15 ብር የጉርሻ ስጦታ ይበረከትልዎታል!
ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ።
ለበለጠ መረጃ /channel/awash_bank_official ወይም www.awashbank.com ይጎብኙ!
አዋሽ ባንክ!
#NGAT
ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) አመልካቾች ምዝገባ ከታህሳስ 21 እስከ 25/2017 ዓ.ም ይከናወናል፡፡
ለመመዝገብ 👇
HTTPS://NGAT.ETHERNET.EDU.ET
ከምዝገባው ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ በሥራ ሰዓት በኢሜል አድራሻ ngat@ethernet.edu.et ወይም በስልክ ቁጥር 0920157474 (Enatnesh Gebeyehu) እና 0911335683 (Fasil Tsegaye) ማብራሪያ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን ተገልጿል።
የመፈተኛ ' USER NAME ' እና " PASSWORD ' በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል የሚላክ ሲሆን፤ የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 750 በቴሌብር በኩል ብቻ መፈጸም ይጠበቅባችኋል ተብሏል፡፡
ፈተናው የሚሰጥበትን ጊዜ በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
#MoE
Via @tikvahuniversity
#ብርሃን_ባንክ
#ይቀበሉ_ይመንዝሩ_ተጨማሪ_2%_ #እና_ልዩ_የበአል_ስጦታዎን_ይውሰዱ
ከውጪ ሃገራት የሚላክልዎትን ገንዘብ ከብርሃን ባንክ ጋር ከሚሰሩ አለምአቀፍ የገንዘብ አስተላላፊዎች #ሪያ #ዳሃብሽል #ዌስተርን_ዩኒየን #መኒግራም #ትራንስ_ፋስትና #ወርልድ_ረሚት በኩል ሲቀበሉ ወይም በእጅዎ ያለውን የውጭ ሃገር ገንዘብ በባንካችን ሲመነዝሩ ከእለቱ የምንዛሪ ተመን በተጨማሪ 2% እና ልዩ የበዓል ስጦታ ያገኛሉ!
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
#moneytransfer #Stressfreebanking #berhanbank #bank #finance #bankinethiopia
ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ!
➡️ Facebook
➡️ Telegram
➡️ Instagram
➡️ Twitter
➡️ LinkedIn
➡️ YouTube
#Earthquake አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ አሁንም ቀጥሏል።
ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ በሬክተር ስኬል 5 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ በድጋሚ ተከስቷል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ የጂኦፊዚክስ እና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር የሆኑት ኤሊያስ ሌዊ (ዶ/ር) ፤ ዛሬ ምሽት 2 ሰዓት ላይ በሬክተር ስኬል 5 ሆኖ የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ በአዲስ አበባ በተደጋጋሚ መሰማቱን ተናግረዋል።
" በአካባቢው ያለው የቅልጥ ዓለት ድንጋይ (ማግማ) እንቅስቃሴ አሁንም ቀጥሏል " ያሉት ኤልያስ (ዶ/ር) " የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ እንዲከሰት እያደረገ ያለውም ይኸው ነው " ሲሉ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል።
@tikvahethiopia
በሲዳማ ክልል በደረሰ አሰቃቂ የመኪና አደጋ ከ70 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አለፈ።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በቦና ዙሪያ ወረዳ ጋላና ወንዝ ተብሎ በሚጠራዉ ድልድይ ላይ ከ70 በላይ ሰርገኞችን ይዞ ወደ በንሳ ወረዳ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ ክፍት መኪና ድልድዩን ስቶ ወንዝ ዉስጥ መግባቱን የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉን የሲዳማ ክልል መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታዉቋል።
ቢሮው " እስካሁን ቁጥሩ ያልታወቀ ሰዉ ሕይወት አልፏል " ሲል ገልጿል።
የክልሉ ፖሊስ በሰጠን ቃል 71 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን አሳውቋል።
የአደጋ መንስኤ እየተጣራ ሲሆን አጠቃላይ የተጠቃለለ መረጃ ይገለጻል።
ነፍስ ይማር !
@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ገንዘብ እያሰባሰበች ነው ?
👉 " ምዕመናን ፤ ቅዱሳን ገንዘባችሁን እንዳትበሉ ተጠንቀቁ " - መጋቢ ለወየሁ ስንሻው
➡ " የሚታየው የባንክ አካውንት ሆነ መልዕክት እኛ የማናውቀው ነው " - አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ
" በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ያሉ የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ከፓስተር/መጋቢ ዮናታን አክሊሉ ጋር በመተባበር የገቢ ማሰባሰቢያ / ገንዘብ መሰብስበ ስራዎች እየሰሩ ነው " በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ እንደሆነ ተገልጸ።
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን በሰጠችው ይፋዊ መግለጫ ፥ የባንክ ቁጥር ጭምር በመግለጽ የተለያዩ ፖስተሮችንም በማሰራት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተደረገ ያለው የገንዘብ የማሰባሰብ እንቅስቃሴ ፍጹም የማታውቀው ስራ እንደሆነ ገልጻለች።
የቤተክርስቲያኗ ምክትል ፕሬዜዳንት መጋቢ ለወየሁ ስንሻው ፤ " ከወንድማችን ዮናታን አክሊሉ ጋር በዚህ ስራ ዙሪያ ንግግር አላደርግንም ይህንን መግለጽ እንፈልጋለን " ብለዋል።
የባንክ አካውንቶቹ በአንድ ግለሰብ ስም እንደተከፈቱ እንደተደረሰበትና ቤተክርስቲያኗ በሚመለከተው አካል በኩል ጉዳዩን እንደምትሄድበት ተገልጿል።
ጉዳዩ ቤተክርስቲያንን ያሳሰበና ያስደነገጠ እንደሆነ ተመላክቷል።
መጋቢ ለወየሁ ፤ " ምዕመናን ፣ ቅዱሳን የገንዘብ ማሰባሰቢያ ስራ የተባለው በፍጹም ማታለል እና ማጭበርበር የተሞላበት በመሆኑ በዚህ የማታለል ተግባር ገንዘባችሁን እንዳትበሉ፣ እንዳትሳተፉ " ሲሉ አሳስበዋል።
በተመሳሳይም አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ፥ ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በአዲስ አበባ ዙሪያ ካሉ የሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤተክርስቲያናት እና ከኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ጋር በመተባበር የገቢ ማሰባሰቢያ እያካሄዱ እንደሆነ የሚገልጹት መልዕክቶች ፍጹም ሀሰተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
" በስሜ የተከፈተ ለዚህ የሙሉ ወንጌል አገልግሎት የሚውል የባንክ አካውንት እንደሌለ አሳውቃለሁ " ብለዋል።
አካውንቱን ማነው የከፈተው (በማስታወቂያዎች ላይ ያለውን) ስለሚለው ጉዳይም ፤ ማን እንደከፈረው እንደተደረሰበትና የቤተክርስቲያኒቱ እና የእሳቸውም የህግ ክፍል ጉዳዩን እንደሚከታተለው ጠቁመዋል።
" በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚታየው የባንክ አካውንት ሆነ መልዕክት እኔን እና ቤተክርስቲያናችንን የአዲስ ካህናት ቤተክርስቲያን የማይመለከት የማናውቀው ነው " ብለዋል።
" እራሳችሁን ከዚህ የማታለል ስራ ጠብቁ ፤ ምንም ተሳትፎም እንዳታደርጉ " ሲሉ አሳስበዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Update
" ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቃዎች ታግተዋል " የተባሉት 3 የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ሜይሊ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በሚገኝ እስር ቤት እንደሚገኙ የትግራይ ቴሌቪዥን ከደቂቃዎች በፊት ማረጋገጡ ይታወሳል።
አሁን ከስፍራው በተገኘው መረጃ ሦስቱ ጋዜጠኞች ከእስር ተለቀዋል።
የጋዜጠኞቹ መፈታት በማስመልከት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ፥ ጋዜጠኞቹ መረጃ በማሰባሰብ ስራ እያሉ በአከባቢው በሚገኙ ፓሊስ እና ሚሊሻዎች ነው የተያዙት።
ጋዜጠኞቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ከወረዳው የፀጥታ እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት መካከል በተደረሰ መግባባት ከሰዓታት እስር ሊለቀቁ ችለዋል።
ጋዜጠኞቹ በአከባቢው ያለውን ህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ቁፋሮና ዝውውር የሚመለከት የምርመራ ዘገባ በመስራት ላይ እንደነበሩ ለወረዳው የፀጥታ እና አስተዳደር አካላት የተናገሩ ሲሆን የጋዜጠኞች እስር እና እንግልት በክልሉ ካለው የፓለቲካ ቀውስ ትስስር አለው ተብሏል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia