ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
#Hawassa
#ማሳሰቢያ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላለፈ።
ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል ቅዳሜ ይከበራል።
በዓሉን አስታኮ ግን አንዳንድ አገልግሎት ሰጪዎች ከፍ ያለ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ እንደሆነ በግልጽ ታይተዋል።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያም " ጥቂት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በዓሉን አስታከው በአንዳንድ አገልግሎቶችና በማረፊያ ቦታዎች ላይ ከወትሮው ውጭ የዋጋ ጭማሬ የሚመስሉ አዝማሚያዎችን እያደረጉ ስለመገኘታቸው ጥቆማዎች ቀርበውልኛል " ብሏል።
" የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በእነዚህ አብዛኛው አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን በማይወክሉ ላይ እርምጃ ከመውሰዱ በፊት ቀደም ብለው እንዲታረሙ በጥብቅ ያሳስባል " ሲል ገልጿል።
" ይህ አይነቱ ድርጊት በተለይም ሁላችንም የአይን ብሌን አድርገን የምናያትን ከተማችን የሀዋሳን ስም የሚያጠለሽ ሆኖ እንዳይገኝ ከወዲሁ በመሰል ድርጊት ላይ የተሰማሩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ማስገንዘብ እንወዳለን " ሲል መምሪያው አሳስቧል።
" በጥቆማው መሰረት በተጨባጭ መልኩ በዓሉን አስታከው ያልተገባ የዋጋ ጭማሬ በማንኛውም አገልግሎት ላይ በሚያደርጉ አካላት ላይ አስተዳደሩ የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል " ብሏል።
#TikvahEthiopiaFamliyHawassa
@tikvahethiopia
ስግብግብነትም ልክ አለው !
" የአንድ አልጋ ዋጋ 800 ብር ከነበረበት 2500 እና 3000 ብር ብለው አስደነገጡኝ ! "
(ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ታከለ)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ አመታዊው የቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግስ ከሚከበርባቸው ከተሞች መካከል የፍቅር ከተማዋ ሀዋሳ አንዷ ናት።
በርካቶች ከተለያዩ የአለም እና የሀገሪቱ አካባቢዎች ለዚህ መንፈሳዊ በዓል ወደ ከተማዋ በመምጣት በደመቀ መልኩ ያከብራሉ።
የእንግዶቹን መምጣት ተከትሎም የእንግዳ ማረፊያዎች ፣ ሆቴሎች እና ምግብ ቤቶች አለፍ ሲልም ከሊስትሮ እስከ ቡና መሸጫ ቦታዎች እንዲሁም ሌሎች በንግድ የሚተዳደሩ የከተማይቱ ግለሰቦች በዚህ በአል ተጠቃሚ በመሆን ገቢ ያገኛሉ።
ነገር ግን አንዳንድ ስግብግቦች በእጅጉ እንግዶችን የሚያሳቅቁ የዋጋ ጭማሪዎችን በማድረግ ከተማው ላይ ሰዎች ቆይታቸውን እንዳያራዝሙ በአጭሩም እንዲያጥር እያደረጉ ናቸው።
ትዝብቴ እዚህ ጋር ነው አንድ የቅርብ ወዳጄ ወደ ከተማይቱ ለመምጣት የአልጋ አገልግሎትን ፈልጎ እንዳመቻችለት ስለነገረኝ ወደ አንድ የእንግዳ ማረፊያ ሆቴል / በቅርበት ወደማውቀው ቦታ ሄድኩኝ።
ወደ ቦታው የሄድኩት የአልጋ ዋጋ በቅርብ እንኳን ስምንት መቶ ብር እንደሆነ ስለማውቅ ነው።
የአልጋ ዋጋ በዚሁ በዓል ምክንያት ብቻ ከእጥፍ በላይ በመጨመር ሁለት ሺህ አምስት መቶ እና ሦስት ሺህ ብር ነው ብለው በእጅጉ አስደንግጠውኛል።
ስለሆነም የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከተማዋ ከፍተኛ ገቢ ከምታገኝበት በዓል መካከል አንዱ የሆነውን የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በአልን አክብረው ከተማዋን ጎብኝተው እንግዶች ቀናቸውን አራዝመው ይቆዩ ዘንድ እንዲህ አይነት ራስ ወዳድ የሆኑ ስግብግብ የአልጋ ፣ የሆቴል ፣ የምግብ እና መሰል ነጋዴዎች ላይ በአፋጣኝ ክትትል በማድረግ እልባት ሊሰጠው ይገባል ስል በትዕትና እጠይቃለሁ። "
#TikvahEthiopiaFamliyHawassa
@tikvahethiopia
" ነጻ፤ ፍትሃዊ እና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያለ ሰላምና መረጋጋት ውጪ ሊታሰቡ አይችልም " - የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
የኢትዮጵያ ፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር " ሰላምን በማጽናት የፓለቲካ ፓርቲዎች ሚና " በሚል ጉዳይ ክልላዊና ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች ጋር ለሁለት ቀናት የሚቆይ የውይይት መድረክ ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል።
በዚህ መድረክ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አየለ ምክር ቤቱ በ2017 ዓ/ም አገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ ለማካሄድ እቅድ እንደነበረውና የዛሬው መድረክም ከባለድርሻ አካላት ጋር ይህንኑ እውን ያደደረገበት ነው ብለዋል።
" የሰላም ኮንፈረንሱ ዓላማ በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ያሉ ግጭቶች እንዲቆሙ ለማስቻል " ሲሉ ነው የገለጹት።
ሰብሳቢው በንግግራቸው መድረኩ ፦
- በመንግስትና በተፋላሚ ወገኖች መካከል ያለ የፓለቲካ ልዩነትን በዘላቂነት ለመፍታት ውይይት እንዲጀመር ጥሪ ለማስተላለፍ፤
- በቀጣይ ይካሄዳል ተብሎ ለሚጠበቀው ለ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ነጻ፣ ፍትሃዊና ሰላማዊ እንዲሆን አስዋጽኦ ለማበርከት ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል።
" ነጻ፤ ፍትሃዊ እና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያለ ከሰላምና መረጋጋት ውጪ ሊታሰቡ አይችልም " ያሉት አቶ ሰለሞን፣ ሀገረ መንግስትን ለመገንባት ሰላም ትልቅ ድርሻ እንዳለው በንግግራቸው አንስተዋል።
" ሀገራችን ባለፉት 6 ዓመታትም ከግጭትና ከጦርነት አልተላቀቀችም " ያሉት አቶ ሰለሞን፣ " በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ዛሬም ድረስ የቀጠለው ግጭት የአያሌ ኢትዮጵያዊያንን ሕይወት ቀጥፏል" ሲሉ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አየለ አክለውም " ኢትዮጵያ ከድህነት አዙሪት እንድትላቀቅ ቅድሚያ ሰላምን ማስፈን ይገባል” ብለዋል።
በመድረኩ የተገኙት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ምን አሉ ?
" ሰው ሰራሽና የተፈጠሮ አደጋዎች ሰላማችንን ሲነሱን ኖረዋል፤ ድርቅ ወረርሽኝ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ጎርፍ፣ ቸነፈር ህዝባችንን ሲያሰቃዩ ኖረዋል።
እነዚህ ጋብ ሲሉ ደግሞ፣ ግጭት ጦርነትና መፈናቀል መልሰው ሰላማዊ ህይወታችን ይበጠብጡታል፤ እስካሁን ድረስ ለሁለቱም የሚሆነውን ሁነኛ መፍትሄ አላበጀንም።
በዚህ የተነሳ ሁለቱም ተባብረው ለድህነትና ለኋላቀርነት አሳልፈው ሰጥተውናል " ብለዋል።
በወቅቱ ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስትር አቶ መሐመድ እንድሪስ፣ በቅርብ ጊዚያት ችግሮችን ለመፍታት በተሰራ ሥራ፣ " በአብዛኛው በሀገራችን ክፍሎች አንፃራዊ ሰላም ማረጋገጥ ተችሏል " ሲሉ ተደምጠዋል።
የመድረኩ የከሰዓት ውሎ ለሚዲያ ዝግ ሆኖ መካሄዱን በስፍራው የተገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል መመልከት ችሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) እና የፋይናነስና ሃብት ማስተባበርያ ሃላፊ ምሕረት በየነ (ዶ/ር) እስረኛ ሆነው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡልን እና የፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲያስፈፅሙ ትእዛዝ ይፃፍልን " - የትግራይ መምህራን ማህበር ጠበቃ
➡️ " የእስር ትእዛዝ ይፃፍልን ጥያቄው ተቀባይነት የለውም " - የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ማግስት በ2015 ዓ.ም የተጀመረው የ " 17 ወራት የመምህራን ውዙፍ ደመወዝ ይከፈለን " ጥያቄ ወደ ፍርድ ቤት ከተመራ ወራት ተቆጥረዋል።
ክርክሩ በመዳኘት ላይ የሚገኘው የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሀምሌ 15/2017 ዓ.ም ባዋለው ችሎት የመምህራን ክስ የያዘው የህግ ጠበቃ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር የሚገኘው የፌደራል የገንዘብ ሚንስቴርና የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ገንዘብ እንዲታገድ ወስኗል።
የፍርድ ቤት የእግድ ትእዛዝ የተጣለበት ብር ግማሽ ቢሊየን እና 17 ሚሊዮን ሲሆን ግማሽ ቢሊዮኑ የክልሉ ፋይናንስና ሃብት ማሰባሰብ ቢሮ ቀሪው 17 ሚሊዮን ብር ደግሞ የፌደራል የገንዘብ ሚንስቴር እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
አቃቤ ህግ የገንዘቡ እግድ በማስመልከት ባቀረበው ክርክር በተጠቀሰው የባንክ ሂሳብ ቁጥር የሚገኘው ግማሽ ቢሊዮን ብር ቢሮው በሃላፊነት ያስቀመጠው የክልሉ መንግስታዊ መ/ቤቶች ያልተጠቀሙበት በአደራ የተቀመጠ ነው ብሏል።
" የይታገድ " ውሳኔ የተላለፈበት የፌደራል የገንዘብ ሚንስቴር 17 ሚሊዮን ብር አስመልክቶ የተባለ ነገር የለም።
የከሳሽ ጠበቃ የመምህራን የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዝ እንዳይከፈል እያስተጓጎሉ ናቸው ያላቸው የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) እና የፋይናነስና ሃብት ማስተባበርያ ሃላፊ ምሕረት በየነ (ዶ/ር) በእስር ወደ ፍርድ ቤት ሸርበው እንዲሰረዱ ትእዛዝ ይፃፍልኝ ሲል ያመለከተ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል።
ፍርድ ቤቱ የቀረበው ክስ አፈፃፀም ለመመልከት ለሀምሌ 22/2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
" የአውሮፕላን የውስጥ ክፍሎች የሚጠገኑበትን ባለ አራት ወለል ማእከል ብቻ ለመገንባት ከስልሳ ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ ተደርጓል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአይነቱ የመጀመሪያ ነው ያለውን የአውሮፕላን አካላት የጥገና ክፍል (Aircraft Component maintenance Shop) ፣ ሴንትራል ዌርሃውስ እና ሁለት ጋራዦችን (Hangars) ትላንት አስመርቋል።
በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰውን ፣ የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ ሌተናንት ጀነራል ይልማ መርዳሳ እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ነበር።
በአጠቃላይ ከ 150 ሚሊየን ዶላር በላይ እንደወጣባቸው የተገለጹት ሦስቱ ግንባታዎችን ለማጠናቀቅ በአማካይ ከ3 እስከ 5 አመት መፍጀቱን በአየር መንገዱ የሜንቴናንስ፣ ሪፔር እና ኦፈርሃውል ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዳንኤል ደመቀ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የተመረቁት ሁለት የአውሮፕላን ጋራጆች አየር መንገዱ ከዚህ ቀደም ከነበሩት አራት የዋይድ ቦዲ እና የስሞል ቦዲ ጋራጆች በአጠቃላይ የስድስት ጋራጆችን ቁጥር ወደ ስምንት ከፍ ያደርገዋል።
የአውሮፕላን የውስጥ ክፍሎች የሚጠገኑበትን ባለ አራት ወለል ማእከል ብቻ ለመገንባት ከስልሳ ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ መደረጉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአየር መንገዱ ሰምቷል።
የአየር መንገዱ የአውሮፕላን ክፍሎች መለዋወጫ ጥገና ማዕከል በግንባታ ላይ በነበረበት ወቅት ለውስጥ ሰራተኞች በሃገር ውስጥ እና በውጭ ሥልጠና ሲሰጥ ቆይቷል ተብሏል።
በጥገና ማዕከሉ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል አንዱ በሆነው የአውሮፕላን የፊት እና የዋና የጎማ ክፍሎች የጥገና ማዕከል ውስጥ በአሁኑ ሰአት Bombardier Q400 እና Boing 737 ለተሰኙ አውሮፕላኖች የጎማዎች ጥገና ይከናወናል።
አየር መንገዱ አየተጠቀመባቸው የሚገኙትን ለትሪፕል ሰቨን (ቦይንግ 777 ) አውሮፕላኖች የጥገና ሰአት ሲደርስም በውስጥ አቅም ለማከናወን የሚቻልበትን አቅም መፈጠሩን ተገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከክፍሉ ሰራተኞች እንዳረጋገጠው የQ400 የፊት የጎማ ክፍል (nose landing gear) ለመጠገን ለአንዱ እስከ 100 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ይጠየቃል።
የዋናው ጎማዎች ጥገና (main landing gear) ጥገና ለማከናወንም ከሁለት እስከ ሦስት መቶ ሺህ ዶላር ይጠየቃል።
ከሌሎች ሃገራት የደንበኞች የጥገና ጥያቄ ከመጣም ከዚህ ቀደም ለ Q400 Bombardia አውሮፕላን የፊት የጎማ ክፍሎችን ጥገና ሰርተናል አሁንም ከመጣ አቅሙ አለን ተብሏል።
የአውሮፕላን የተለያዩ የጥገና ዲፓርትመንቶች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ሲሰሩ በአይነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነ በምረቃ ስነስርአቱ ወቅት ተገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamliyAA
ፎቶ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ + ቲክቫህ ኢትዮጵያ
@tikvahethiopia
#MinistryOfHealth
የብቃት ምዘና ፈተና የሚወስዱ የጤና ባለሙያዎች የኦንላይን ምዝገባ ከሐምሌ 15 እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ/ም እንደሚከናወን ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።
አመልካቾች በኦንላይን ሲስተሙ ለመመዝገብ ኮምፒውተር መጠቀም እንደሚኖርባቸው ተመላክቷል። በሞባይል ስልክ ለመመዝገብ መሞከር ምዝገባውን ያልተሟላ ሊያደርገው ይችላል ተብሏል።
ተመዛኞች መደበኛ የEmail አድራሻም ሊኖራችሁ እንደሚገባ ተገልጿል።
ተመዛኞች የብቃት ምዘና ፈተናውን መውሰድ የሚፈልጉበትን የፈተና ጣቢያ ከተዘረዘሩት አማራጮች ውስጥ መምረጥ እንዳለባቸው ፤ እያንዳንዱ የፈተና ጣቢያ ማስተናገድ በሚችለው ከፍተኛ የተመዛኝ ቁጥር ልክ ገደብ ስለተቀመጠለት ተመዛኞች ምዝገባውን ቀድሞ በማጠናቀቅ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ።
ከፍተኛው የተመዛኝ ቁጥር በደረሰበት የፈተና ጣቢያ ላይ ተጨማሪ ምዝገባ ማከናወን የማይቻል መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
ተመዛኞች ምዝገባቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ሲስተሙ የሚሰጣቸውን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration ID) ፕሪንት አድርገር መያዝ አለባቸው።
ምዝገባቸውን ጀምረው ሳይጨርሱ ያቋረጡ አመልካቾች ዋናው ገጽ ላይ System Login የሚለውን ሊንክ በመጫን Email እና Password አስገብተው ምዝገባቸውን ማጠናቀቅ ይኖርባችኋል ተብሏል።
http://hple.moh.gov.et/hple ላይ በመግባትና Registration የሚለውን በመጫን ዝርዝር የፈተናውን መመሪያ ይመልከቱ/ከላይ ያንብቡ።
ይመዝገቡ : http://hple.moh.gov.et/hple
Via @tikvahuniversity
#ጥቆማ
#ለሚመለከታችሁ_አካላት
አዲስ አበባ አስኮ አዲስ ሰፈር ወደ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን መንገድ ላይ የእንጨት ኤሌክትሪክ ፖል ተንጋዶ ለመውደቅ እጅጉን መቃረቡን የአካባቢው ነዋሪዎች ጠቁመዋል።
" ሰፈሩ የነዋሪዎች መግቢያ መውጫ፣ ህጻናትም ያሉበት ፣ መኪኖች የሚመላለሱበት ስለሆነ ወድቆ አደጋ ከመድረሱ በፊት መፍትሄ ይሰጠው " ብለዋል።
ወቅቱ ክረምት በመሆኑ ከፍተኛ ዝናብና ንፋስ ስላለ ፈጣን መፍትሄ እንዲሰጥ ተጠይቋል።
#TikvahEthiopiaFamliyAA
@tikvahethiopi
#SafaricomEthiopia
የSMS ጥቅሎች እየገዛን ከምንወዳቸው ጋር እንደልብ መልዕክት እንለዋወጥ! 💬
#1wedefit
#Furtheraheadtogether
ፎቶ ፦ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ የአፋር፣ አፍዴራ አካባቢ ተከታታይ የተፈጥሮ አደጋዎች እየተፈራረቀበት እንደሆነ አመልክቷል።
ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ጠዋት 4:00 ሰዓት አካባቢ አፍዴራ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር ጠቁሟል። በዚህም አፍዴራ አቅራቢያ የመሬት መሰንጠቆች እንዲሁም ጉድጓዶች መፈጠራቸው ገልጿል።
ይኸው ክስተት ባለፈው ሳምንት የተከሰተውን የኤርታሌ እሳተ ገሞራ ፍንዳታን ተከትሎ የመጣ እንደሆነ አመልክቷል።
ዩኒቨርሲቲው አሁንም ስጋቶች እንዳሉ ጠቁሟል።
ሰሞኑን ከተማዋን የመታው ከባድ ንፋስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን በማውደም በርካታ ነዋሪዎች ቤት አልባ እንዲሆኑ ማድረጉን አስታውሷል።
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ የጂኦሳይንሳዊ ባለሙያዎች ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ ለመገምገም እንዲሁም ለመከላከል የሚያስችሉ ጥረቶችን ለመደገፍ በአስቸኳይ በመስክ ምርምርና ክትትል ላይ እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርቧል።
#SamaraUniversity
@tikvahethiopia
" ከሰዓት በኋላ 10 ሰዓት አካባቢ ከማረሚያ ቤት ወጥቷል " - የዶክተር ዳንኤል ቤተሰብ
የጤና ባለሙያዎች የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን በማንሳት እያደረጉት ባለው እንቅስቃሴ ሳቢያ ባለፈው ወር ታስሮ የነበረው በባሕር ዳር ፈለገ ግዮን ሆስፒታል የማህጸን ፅንስና ስፔሻሊቲ ዶክተር ዳንኤል ፈንታነህ ከእስር መፈታቱን ቤተሰቦቹና ጤና ባለሙያዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።
ቤተሰቦቹና ጤና ባለሙያዎች በሰጡን ማረጣገጫ፣ ዶክተር ዳንኤል " በ15 ሺሕ ብር ዋስ ዛሬ ተፈቷል " ብለዋል።
አንድ የቅርብ ቤተሰቡ ፣ " ዋስትና ነው የተፈቀደው፤ ጠዋት ዋስትና ፍርድ ቤት ወስኖ ስለነበር ከሰዓት በኋላ 10 ሰዓት አካባቢ ከማረሚያ ቤት ወጥቷል " ሲሉ ገልጸውልናል።
ጤና ባለሙያዎችና የታሳሪው የሥራ ባልደረቦችም ዶክተር ዳንኤል ከእስር መፈታቱን ገልጸው፣ ከእንቅስቃሴው ጋር በተያያዘ የታሰሩ " ሁሉም ጤና ባለሙያዎች በሚባል ደረጃ " ከእስር እንደተፈቱ፣ ከመንግስት በኩል " እየሰራችሁ ጠይቁ " በተባሉት መሠረት እየሰሩ የጥያቄያቸውን ምላሽ እስከ መስከረም እየጠበቁ እንደሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ከእንቅስቃሴው ጋር በተያያዘ ታስረው ከነበሩ ባለሙያዎች መካከል፣ ዶክተር ዳንኤል " ህዝብ አሳምፃችኋል " በሚል በደኅንነቶች ተይዞ ታሰረ መባሉ ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Ethiopia🇪🇹
#GERD💪
" አሜርካን ጨምሮ ሌሎች አገሮች በግድቡ ዙሪያ ለሚሰነዝሯቸው የሀሰት መረጃዎች ሁሉም እየተነሳ መግለጫ መስጠት የለበትም " - የግድቡ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት
የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት የግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ባለፉት 14 አመታት ከ84.4 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የጉልበትና የተፋሰስ ስራዎች መሰራታቸውን እና ግንባታው የተጠናቀቀው በራሷ አቅም ብቻ መሆኑን ገልጿል።
የጽህፈት ቤቱ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ፍቅርተ ታዕምር በተያዘው በጀት አመት እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ከቦንድ ግዥና ስጦታ፣ ከዲያስፖራው ማህበረሰብ፣ ከ8100A ሰብስክራይበር እና ከህብረተሰቡ ከ4.1 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ መሰብሰቡን ተናግረዋል።
የጽህፈት ቤቱ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ፍቅርተ ስለ ዶናልድ ትራምፕ ንግግር ምን አሉ ?
" የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በመንግስት እና በህዝብ ድጋፍ የተሰራ ነው። ማንም አካል እየተነሳ እኔ ነኝ የሰራሁት ቢሊ ያለምንም ማስረጃ ምንም ማድረግ አይችልም። ግድቡ ከተጀመረ ጀምሮ ምንም አይነት ከውጭ አገሮች የተገኘ እርዳታ የለም።
የአሜርካው ፕሬዝዳንት ከሰሞኑ ኢትዮጵያ ግድቡን የገነባችው በአብዛኛው በአሜርካ ገንዘብ ነው ሲሉ እየተናገሩት ላለው ነገር መንግስት በአርቆ አሳቢነት፣ በጥልቅ ዲፕሎማሲያዊ አሰራር ነው መልስ መስጠት ያለበት። ማንኛውም ሰው እየተነሳ ስለሀገር ጉዳይ የእራሱን እና የግል አስተያየቱን መስጠት አይችልም። እንደመንግስት ግልፅ እና የተብራራ መረጃ ወደ ፊት መሰጠት አለበት።
እኛ መያዝ ያለብን ግን ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ ሌሎች ሰዎች የፈለጉትን ስላሉ ሳይሆን ይህን አፍራሽ መልዕክት የሚመክት እውነታ ብቻ ነው የምንናገረው። እውነታ እና እውነታው ደግሞ በኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ብቻ ነው የተሰራው። ማለትም የሚገባንን ይሄን ነው፣ የፍርሀትም ሆነ የመሽቆጥቆጥ አይደለም።
ዲፕሎማሲ የመንግስት አሰራር አለው፣ መንግስት በራሱ ጊዜና በሚፈልገው አይነት መልስ ይሰጣል። እኛ ግን የህዝብ ተሳትፎን አስተባባሪ እንደመሆናችን መጠን ግድቡ የተሰራው በህዝባችን ላብ እና ደም ፈሶ ነው። ማንም ስላላ የእኛን ስራ የሚያፈርስበት ሁኔታ አለመኖሩን ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል።
በግድቡ ላይ ሀሳብ የሚሰነዝሩ አካላቶች ማስረጃ አለኝ የሚሉና ከሆነ የትኛውም አካል ማስረጃውን ያቅርብ፣ በወሬ አይደለም።
በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንድ ግንባታ ሲጠናቀቅ እንቅፋቶች ሊገጥሙ ይችላሉ ሲሉ የተናገሩትን ንግግር በተሳሳተ መንገድ በመገንዘብ የሰላም ችግር ያለ በማስመሰል የሚያናፍሱ አካላቶች አሉ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር እሳቤ ነው። እንጂ የሰላም ችግር ወይም እጦት አለ አላሉም።
አንጃ የሚነዙ ሰዎች ይኖራሉ። ነገር ግን በመጭው አመት መጀመሪያ ወር ላይ ዝናቡ ጋብ ሲል መንግስት እና ህዝብ ሪቫኑን ይቆርጣሉ። ከዚህ የሚያስቀረን አንዳችም ነገር የለም።
ግድቡ ቢጠናቀቅም ተጨማሪ ድጋፎች እየተሰበሰቡ ነው። ህዝቡ የግንባታው ምርቃት አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ የትኛውንም አይነት ድጋፍ የሚያደርጉበት ፕላትፎርም አለን። ይህ የሀብት አሰባሰብ በአዋጅና በደንብ የተቋቋመ ስለሆነ በአዋጁ እና በደንቡ ቆሟል ሲባል እናቆማለን። ምክንያቱም ሌላ ግድብ መስራት ያስፈልጋል። አሁንም በውጭም ሀገርም ሆነ በሀገር ውስጥ ከፍተኛ ቦንድ እየተሸጠ ነው። " ብለዋል።
የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) በበኩላቸው " የግብፆች ግፊት በየአቅጣጫው እንዳለ ግልፅ ነው " ብለዋል።
" ከ600 ዓ.ም ጀምሮ ጦርነት ሁሉ የከፈቱበት ወቅት ነበር። ስለዚህ ኢትዮጵያን ለማደናቀፍ የማያደርጉት ነገር የለም። ከአሜርካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሚመጡ አንዳንድ የተዛቡ ንግግሮች ከዚህ መዐዘን ማየት አስፈላጊ ነው " ሲሉ ጠቁመዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamliyAA
@tikvahethiopia
Calling all #Ethiopian Innovators!
The second round of the Immunisation Innovation Accelerator is now open - offering up to $100,000 in grants to solutions that improve #vaccine access.
📅 Application deadline: July 27
🔗 https://www.stc-accelerator.org/
#ChildHealth #InnovationInAction #HealthInnovation #Ethiopia
#Update
" ወታደር ስላሰማራህ አስተዳድረሀል ማለት አይደለም " - የትግራይ ደቡባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሃፍቱ ኪሮስ
" እኔን የወከለ አስተዳዳሪ የለም ፤ ህጋዊ የዞኑ አስተዳዳሪ እኔ ነኝ ፤ አላስፈላጊ ግጭትና ደም መፋሰስ ለማስቀረት በማሰብ ፅህፈት ቤቴን ለቅቄ ወጥቻለሁ " አሉ የትግራይ ደቡባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሃፍቱ ኪሮስ።
ዋና አስተዳዳሪው በጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) እውቀና ትእዛዝ ከትናንት ሀምሌ 14/2017 ዓ.ም " ሰላማዊ ሹምሽር ነው " የተባለው በዞኑ እየተከናወነ ያለው የአመራር ለውጥ ተቃውመዋል።
" በዞኑ የሚደረግ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ቀይ መስመር ነው ፤ ወታደር ስለአሰማራህ አስተዳድረሀል ማለት አይደለም " በማለት ገልፀዋል።
ዋና አስተዳዳሪው ዛሬ በሰጡት ቃል ፥ ከትናንት ሀምሌ 14 ከምሽቱ 3፡30 ጀምሮ የአድማ ብተና ፖሊስና ታጣቂ ሰራዊት ወደ ዞኑ መሰማራቱ አረጋግጠዋል።
" ለረጅም ጊዚያት እቅድና ዝግጅት ሲደረግበት የቆየ የዞኑ አስተዳደር የማፍረስ ተግባር እየተፈፀመ ነው " ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ፕሬዜዳንት ጀነራል ታደሰ የሰጡት ቃለመጠይቅ " እርስበራሱ የሚጋጭ አዲስ ቀውሰ አዋላጅ " በማለት አብጠልጥለውታል።
ጊዚያዊ አስተዳደሩ " ኃላቀርና ቆሞ ቀር " ሲሉ የገለፁት የህወሓት አመራር ቡድን መሳሪያ ሆኗል ሲሉም ከሰዋል።
ባለፈው የሚያዝያ ወር 2017 ዓ.ም የደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት ወደ የአከባቢውን አስተዳደር በራሱ ሰዎች ለመተካት መወሰኑን ተከትሎ ማይጨውና አላማጣ ጨምሮ በመላ የዞኑ ከተሞች የተቃውሞ ህዝባዊ ሰልፍ መካሄዱ አይዘነጋም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamliyMekelle
@tikvahethiopia
#Update
የእግር ኳስ ተጫዋች በነበረው አለልኝ አዘነ ግድያ የተከሰሱት ባለቤቱና የባለቤቱ እህት ባል የ16 እና 15 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደባቸው።
በአለልኝ አዘነ ጉዳይ የመጨረሻ ፍርድ ለመስጠት ዛሬ የተሰየመዉ የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተከሳሽ የአለልኝ ባለቤት አደይ ጌታቸዉና በእህቷ ባል ላይ የ16 እና 15 ዓመት ፅኑ እስራት ፈርዶባቸዋል።
ፍርድ ቤቱ ይህንን ዉሳኔ ያስተላለፈው መጋቢት 17/2016 ዓ/ም በተጋቡ በ15ኛ ቀን አለልኝ አዘነን ባለቤቱና የባለቤቱ እህት ባል መግደላቸውን በሰዉና በሰነድ ማስረጃዎች ካረጋገጠ በኋላ መሆኑን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል መረጃውን ከአርባ ምንጭ ልኳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አርባ ምንጭ
#TikvahEthiopiaFamliyArbaminch
@tikvahethiopia
#Hawassa
" ጉማሬዉ አስከሬኑን አልለቅ ብሎ በጥይት ተኩስ ነዉ አስክሬኑን ማውጣት የተቻለው " - የዐይን እማኞች
በሀዋሳ ሀይቅ ላይ አንድ አሳ አጥማጅን ጉማሬ ባደረሰበት ጥቃት ሕይወቱ ማለፉን የዐይን እማኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
በሀዋሳ ሀይቅ ዙሪያ ኑሯቸዉን ያደረጉ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ከትላንት በስቲያ በሀይቁ ላይ በአነስተኛ መንሳፈፊያ አሳ በማጥመድ ላይ የነበረ ወጣት በድንገት ጉማሬ ባደረሰበት ጥቃት ሕይወቱ ማለፉን ተናግረዋል።
ጉማሬ በሀዋሳ ሀይቅ በብዛት ባይኖርም ባለባቸዉ ጥቂት ቦታዎችም ቢሆን ከዚህ ቀደም እንደዚህ አይነት ጥቃት አድርሶ አያዉቅም ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ " ባልተለመደ መልኩ ልጁ አሳ ከሚያጠምድበት ገልብጦት እላዩ ቁጭ በማለት ሕይወቱ እንዲያልፍ ማድረጉን ጩኸት ተነስቶ በሄድንበት አጋጣሚ ተመልክተናል " ብለዋል።
በሀዋሳ ሀይቅ ከአሞራ ገደል በቅርብ ርቀት ይህ ክስተት መፈጠሩን የነገሩን ነዋሪዎቹ ጉማሬዉ ልጁን መልቀቅ ባለመቻሉ መሳሪያ ተተኩሶበት አስከሬኑ መውጣቱን አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሀዋሳ ከተማ ፖሊስ በጉዳዩ ላይ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamliyAA
@tikvahethiopia
#Afar
" በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የፌስቡክ ገጽ እየተላላፈ ያለው መልዕክት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽንንም የክልሉን መንግስትም አይወክልም " - አፋር ክልል
ምሽቱን በአፋር ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ኦፊሴላዊ የፌስቡክ ገጽ ላይ " የብልጽግና መንግስት የአፋርን ህዝብ ለሕወሓትና ኢሳ ቡድን አሳልፎ ሰጥቷል " በሚል መንግስትን በብርቱ የሚተች በኮሚሽኑ ገጽ ያልተለመደ መግለጫ ወጥቶ በማህበራዊ ሚዲያው በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ የተፈጠረው ነገር ምንድን ነው ? ሲል የአፋር ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ መሐመድ አሊን የጠየቀ ሲሆን፣ እሳቸውም " የፓሊስ ኮሚሽኑ የፌስ ቡክ ፔጅ ሐክ ተደርጎ ነው፣ ለመመለስ ጥረት እየተደረገ ነው " ብለዋል።
የክልል ፖሊስ ኮሚሽን የራሱ ማህበራዊ ሚዲያ እንዳለው የገለጹት ኃላፊው፣ " እዛው ውስጥ ይሰራ የነበረና ከተቋሙ የተባረረ፣ አሁን ተቋም ውስጥ የሌለ አዲሚን የነበረ ሰው ነው የማይገቡ መልዕክቶችን እያስተላለፈ ያለው " ሲሉ አስረድተዋል።
ይሄው አካል ሰሞኑን ከአፋር ወደ ሌላ ቦታ መኮብለሉን ገልጸው፣ " ፔጁን በፊት ይጠቀምበት ነበር፡፡ በኋላ ስልኩንም ከፔጁ ሪሙቭ አድርገው እሱንም አስወጥተው ነበር፡፡ በራሱ ኤሜል ስለከፈተው እንደገና ገብቶ ነው የማይገቡ መልዕክቶችን እያስተላለፈ ያለው " ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል፡፡
" አድሚኑ በዚህ ሰዓት አፋር ክልል ውስጥ የለም፡፡ በሌላ አገላለጽ ባንዳ ነው " ያሉት ኃላፊው፣ " ልጁ ከፍተኛ የዲሲፕሊን ችግርም ያለበት፣ ታማኝ ያልሆነ ልጅ ነው። እዚህ የለም ቢኖር እንደዚህ አያደርግም/አይችልም ነበር " ብለዋል።
ይህ የምሽቱ የተለየ መልዕክት በፖሊስ ኮሚሽኑ የፌስቡክ ገጽ ፖስት ከተደረገበት ሰዓት ጀምሮ በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የፌስቡክ ገጽ እየተላላፈ ያለው መልዕክት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽንንም የክልሉን መንግስትም የማይወክል መሆኑን ኃላፊው አሳውቀዋል፡፡
ስለዚህ " የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከዚህ በፊት በቀጥታ ተጠሪነቱ ለክልሉ ሰላምና ደህንነት ቢሮ የነበረ ቢሆንም ከዚህ በኋላ የአፋር ፖሊስ ኮሚሽን በቀጥታ ተጠሪነቱ ለክልሉ ርዕሰ መስትዳድር ጽሕፈት ሆኗል " በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ከፌስቡክ ገጹ ሐክ መደረግ ጋር በተያያዘ ነው ? ስንልም ኃላፊውን ጠይቀናል፡፡
እሳቸውም በምላሻቸው፣ " እሱ እኛ ጋ ብቻ አይደለም፣ ፌደራል ፖሊስም፣ የሌሎች ክልሎችም እንደዛ ነው፡፡ ዋናው ምክንያቱ ፔጁ ሐክ ተደርጎ ነው " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Update
ተስተካክሏል !
አዲስ አበባ አስኮ አዲስ ሰፈር ወደ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን መንገድ ላይ የእንጨት ኤሌክትሪክ ፖል ተንጋዶ ለመውደቅ እጅጉን መቃረቡን የአካባቢው ነዋሪዎች ጠቁመው ነበር።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መረጃ በጥቆማው መሰረት " የዘመመውን ምሰሶ አቃንተን ከአደጋ ነፃ አድርገናል " ሲል ገልጾልናል።
#እናመሰግናለን
@tikvahethiopia
" የሶስት ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል፤ ዝናብና አስቸጋሪዉ መልክአምድር ፈታኝ ቢሆንም የቀሪ አስከሬኖች ፍለጋ ቀጥሏል " - የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ
ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን በያዘዉ የአስክሬን ፍለጋ ከማለዳ ጀምሮ በሰዉና በማሽን ታግዞ የቀጠለ ሲሆን ረፋዱን የ3 ሰዎች አስክሬን መገኘቱን የደቡብ አሪ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግዛዉ ሃይሌ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ተጨማሪ የመሬት መሰንጠቅ አደጋዎች በአከባቢው መከሰታቸውን የገለፁት ዋና አስተዳዳሪዉ በዚህም ምክንያት የተፈናቃዮች ቁጥር ከ1 ሺህ ማለፉን አስረድተዋል።
አሁን ላይ ለተፈናቃዮችም ሆነ ጉዳት ለደረሰባቸው የአከባቢው ነዋሪዎች እየተደረገ ያለዉ እርዳታ በቂ አለመሆኑንና በአከባቢው ያለዉ ከፍተኛ የወባ በሽታ ስርጭት ተፈናቃዮች አከባቢ መገኘቱን ጉዳቱን የከፋ ሊያደርገዉ ይችላል ሲሉም አቶ ግዛዉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የክልሉን አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጋንታ ጋምኣን ለማነጋገር ቢሞክርም ኃላፊው ጉዳዩን ከሰሙ በኋላ ጆሯችን ላይ ስልክ በመዝጋት መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን እየተከታተለ መረጃ የሚያጋራ ይሆናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamliyHawassa
@tikvahethiopia
#MakeWay
በተዋልዶ ጤና አገልግሎቶች ላይ ድርብርብ ቀንበር ያለባቸው ወጣቶችን አካታች ያደረገ የማህበረሰብ ሀሳብ መስጫ ካርድ ምንድን ነው?
ተጨማሪ ይመልከቱ 👉 ለአማርኛ
👉 English
#MillenniumHall
ሚሊኒየም አዳራሽ ፈርሶ በአዲስ መልኩ ሊገነባ ነው።
በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር የሚገኘው ሚሊኒየም አዳራሽ በመባል የሚታወቀው አዲስ ፓርክ እና ማኔጅመንት ከታህሳስ 2018 ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ፈርሶ በአዲስ መልኩ እንደሚገነባ መገለጹን ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።
በ2000 ዓ.ም. አገልግሎት መስጠት የጀመረው ይህ ግዙፍ አዳራሽ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ታላላቅ አዳራሾች ግንባር ቀደሙ ነው።
አዲሱ ግንባታ የአዳራሹን አቅም እና ዘመናዊነት ይበልጥ ያሳድጋል የተባለ ሲሆን ለግንባታው የሚወጣው ኢንቨስትመንት መጠን እና የስራ ተቋራጩ ማንነት በቀጣይ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።
ሚሊኒየም አዳራሽ በ20 ሺህ ስኩዌር ሜትር ስፋት ላይ ያረፈ ሲሆን በአንድ ጊዜ እስከ 25,000 ሰዎችን የማስተናገድ አቅም አለው።
ይህ አዳራሽ ከትልልቅ ብሔራዊ ፕሮግራሞች፣ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች፣ ኤግዚቢሽኖች፣ ኃይማኖታዊ ፕሮግራሞች፣ የምርቃት ስነስርዓቶች በተጨማሪ፣ ታላላቅ ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ለሽኝት ስነስርዓቶች ጭምር ሚናውን ሲጫወት ቆይቷል።
በሰኔ ወር 2017 ምሽት ላይ ሚሊኒየም አዳራሽ የተለመደውን አገልግሎት እየሰጠ በነበረበት ወቅት ድንገተኛ የእሳት አደጋ እንደገጠመው ታውቋል። የዚህ ችግር ምንጭ ለጊዜው በሚመለከተው አካል እየተጣራ በመሆኑ ጊዜው ሲደርስ ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ከ17 ዓመታት በኃላ አዳራሹ ሙሉ በሙሉ ፈርሶ በአዲስ መልኩ መገንባት ለወደፊቱ ለተለያዩ ዝግጅቶች የተሻለ እና ዘመናዊ የመስተንግዶ አማራጭ እንደሚሰጥ ይጠበቃል ተብሏል።
#CAPITAL
@tikvahethiopia
" ትላንት በማሽን የታገዘ ቁፋሮ ስናደርግ ብንውልም አንድም አስክሬን ማግኘት አልቻልንም " - የደቡብ አሪ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ
የደቡብ አሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግዛዉ ሃይሌ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ሀምሌ 13 ቀን 2017 ዓ/ም ምሽት 2:30 ገደማ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ከናዳው ስር የሚገኝ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አምስት ሰዎች አስክሬን ለማግኘት ትላንት ለሁለተኛ ቀን ሙከራ ሲደረግ መዋሉን ተናግረዋል።
ሙከራው በማሽን የታገዘ እንደነበር ጠቁመዋል።
" ከትላንት በስቲያ በሰዉ ሃይል ቀኑን ሙሉ ፍለጋ ቢደረግም ድካም ብቻ ነበር " ያሉት ዋና አስተዳዳሪዉ " ትላንት በስካቫቴር ታገዘን አስከሬኑ አለ ተብሎ በሚታሰብበት አከባቢ የደረስን ቢሆንም በመምሸቱ ፍለጋዉን አቋርጠን ለመወጣት ተገደናል " ሲሉ ተናግረዋል።
ለተፈናቃዮች በቀይ መስቀልና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መጠነኛ የዕለት ደራሽ እርዳታ የቀረበ ቢሆንም ከተፈናቀሉት ነዋሪዎች እና ከአደጋው ስፋት አንፃር በቂ አለመሆኑን ገልፀዉ ለክልሉ መንግስት ይህንኑ ማድረሳቸውን ገልፀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamliyAA
@tikvahethiopia
ንብተራ ኦንላይ
ነባሩን የንብ ሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ አሁኑኑ "update/upgrade" በማድረግ የአዲሱ የንብተራ ኦንላይን ተጠቃሚ ይሁኑ፡፡
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!
@nibinternationalbanksc
#Nib #nibmobilebanking #NibQR #nib #nibtera #nibbank
Facebook / Instagram / linkedin / nibinternationalbank6204">X / nibinternationalbank6204">Youtube / nibinternationalbank">Tiktok / Website
" እስካሁን ድረስ በሰዎች የደረሰ ጉዳት የለም፤ ፍንዳታው ግን አለ " - ከኤርታሌ በቅርበት የምትገኘው ቀበሌ
ከሐምሌ 8/2017 ዓ/ም ጀምሮ የተከሰተው የአፋር ክልሉ የኤርታሌ እሳተ ገሞራ ፍንዳታ እስካሁን እንዳልቆ፣ መሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ መሆኑን የኩስራዋድ ወረዳና ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ከኤርታሌ 25 ኪሎ ሜትር የምትገኘው የኩስራዋድ ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ ሐጂ አሊ፣ " የእሳተ ገሞራ ፍንዳታው አልቆመም፡፡ አንዳንዴም ይንቀጠቀጣል፤ ጭስም አለው፡፡ እስካሁን በሰዎች የደረሰ ጉዳት የለም፤ ፍንዳታው ግን አለ " ሲሉ ነግረውናል፡፡
ከፍተኛ የፍንዳታ ድምጽ እንደሚሰማ፣ መሬቱ እየተናደ ወደ ውስጥ መግባቱም እንደቀጠለ መሆኑን አስረድተው፣ " አንድ ቀን ይቆማል፣ ሁለት ቀን ይፈነዳል መሬቱ እየሰጠመ እየጨመረ ሂዷል " ሲሉ ክስተቱ ያለበትን ሁኔታ ገልጸዋል፡፡
የፍንዳታው ቦታ ከመኖሪያ ቦታ ርቀት ቢኖረውም በቅርብ ርቀት ያሉ ነዋሪዎች ንብረታቸውን ትተው መሄድም ፈተና ስለሆነባቸው እንጂ በፍንዳታው ስጋት እንዳደረባቸው ሊቀመንበሩ አስረድተዋል፡፡
የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የጂኦሎጂ መምህርና ተመራማሪ ኖራ ያኒሚኦ በበኩላቸው፣ አደጋው ባለመቆሙ አሁንም ብናኝ እየወጣ፣ የመሬት መንቀጥቀጡም እየተከሰተ ስለመሆኑ ከአካባቢው ባለስጣናት መረዳታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ሰሞኑን በቦታው ተገኝተው በነበረበት ወቅትም ከፍተኛ የአመድ ብናኝ እነወጣ እንደነበር ገልጸው፣ " ብናኞቹ መጀመሪያ ቀይና ጥቁር ሆነው ነው የሚወጡት፤ እየቆየ በሄደ ቁጥር ደግሞ ወደ ነጭ እየተቀየረ ነበር። ከስር ተራራውን እየበላው ሲያልቅ ከላይ ያለው እንዳለ ኮላብስ ነው የሚያደርገው " ብለዋል።
በፍንዳታው የሚወጣው ብናኝ አንዳንዴ የተወሰነ ደቂቃ፤ አንዳንዴ ደግሞ ለረጅም ሰዓት እንደሚቆይ ገልጸው፣ በቦታው በነበርሩበት ወቅት አንድ ቀን " ከቀኑ 11 ሰዓት እስከ 2 ሰዓት ድረስ ሳያቋረጥ በጣም ከፍተኛ የሆነ ጭስ ነው ሲወጣ የነበረው " ሲሉ አስታውሰዋል።
" ፍንዳታው በዚህ የሚቀጥል ከሆነ የአስጊነቱን ደረጃ ከፍ ሊያደርገው ይችላል " ያሉት ተመራማሪው፣ " ከኤርታሌ የወጣው አሽ እስከ አፍዴራ 'ይሸት ነበር' ሲሉ የነገሩን ሰዎች አሉ " ነው ያሉት ተመራማሪው።
እሳተ ገሞራ ፍንዳታ ሲፈጠር ከአደጋው ባሻገር ይዞት የሚመጣ በረከት አለ ይባላል ? ይህ ከምን አንፃር ነው ? ለሚለው ጥያቄም፣ " ትክክል ነው፤ እሳተ ገምራ ወደ ላይ ሲወጣ የተለያዩ ማዕድናትን ይዞ ሊወጣ ይችላል። ስለዚህ አንዳንዴ በረከትም ይሆናል " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
TikvahEthiopiaFamilyAA
ፎቶ፦ ፋይል
@tikvahethiopia
" የፍርድ ውሳኔውን ተከትሎ እንደ አዲስ ለቅሶ ተቀምጠናል " - የአለልኝ አዘነ ቤተሰቦች
➡" ' እራሱን አጠፋ ' ከተባለበት ጉዳዩን መርምሮ ለዚህ ዉሳኔ ማብቃት ትልቅ ውጤት ነው ፤ ይግባኙን በተመለከተ የዐቃቤ ሕግ ቡድኑ በፖናል የሚወስነው ይሆናል" - ፍትሕ መምሪያ
የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና የባሕር ዳር ከተማ ተጫዋች በነበረው አለልኝ አዘነ ግድያ የዞኑ ከፍተኛ ዐቃቤ ሕግ ልዩ ልዩ ወንጀሎች ቡድን በባለቤቱ አበይ ጌታቸውና የባለቤቱ እህት ባል ሉንጎ ሉቃስ ላይ በመሰረተው ክስ የፍርድ ዉሳኔ ማስተላለፉ ይታወቃል።
ውሳኔዉን ተከትሎ የአለልኝ ቤተሰቦች ፣ ጓደኞችና ፍትህ ተጓድሏል ያሉ ወጣቶች ቅሬታቸዉን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሰምተዋል።
የፍርድ ሂደቱን ከመነሻው ጀምሮ ሲከታተል የነበረ የአለልኝ አዘነ የቅርብ ጓደኛ የሆነ እግር ኳስ ተጫዋች ቃሉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥቷል።
ከፍርድ ሂደቱና በፍርድ ቤት ሲነበብ በሰማው ግድያው እንዴት ሊፈጸም እንደቻለ በአጭሩ አስረድቷል።
" አሌ ብቻውን ቤት ውስጥ ነበር ፤ ከዛም ስልኩን ተቀበሉት ማንም እንዳይረዳው ፤ በአጥር ዘሎ ቢወጣም ማንቁርቱ ላይ በቦክስ ተመቶ አጥንቱ ወደ ውስጥ ይሰነቀራል ፤ ከዛም የስልክ እንጨት ፖል ላይ አራት ወይም አምስት ጊዜ በማንጠልጠል በአንገቱ ሽቦ በመጠቅለል ራሱን አንቆ እንደገደለ ለማስመሰል ተሞክሯል " ሲል በፍርድ ሂደቱ የተነበበውን ገልጿል።
" አንደኛ ተከሳሽ የአለለኝ አዘነ ባለቤት አይዳ ጌታቸው ሁለተኛ ተከሳሽ የሆነውን የእህቷን ባል ሉንጎ ሉቃስን ደውላ በመጥራት ነው የግድያ ወንጀሉ እንዲፈጸም በዋናነት ያቀናበረችው " የሚለውን ከፍርድ ሂደቱ መስማቱን አስረድቷል።
ግድያውን የተፈጸመሙት ሆን በለውና አቅደው አለልኝ ማንም ሰው እንዳይረዳው ሆኖ ከምሽቱ 5:30 እስከ ለሊት 8:00 ባለው ጊዜ እንደሆነ መስማቱንም ጠቁሟል።
" ሂደቱ ቀጥሎ ፍርድ ቤቱ አለልኝ በሰው እጅ መገደሉን በማረጋገጥ ዛሬ የፍርድ ሰጥቷል። እሷ ላይ 16 ዓመት ፤ የእህቷ ባል ላይ 15 ዓመት ፅኑ እስራት ፈርዷል " ብሏል።
" ፍርዱ እኛ ጓደኞቹን ጨምሮ ቤተሰቦቹን እጅግ አሳዝኗል ፤ አስከፍቷል። የአለልኝ እናት በውሳኔው እጅግ የመረረ ሀዘን ተሰምቷቸው ብቻቸውን በሀዘን ነው ከፍርድ ቤት የወጡት " ሲል ገልጿል።
" በተጨማሪ በውሳኔው ደስ ያልተሰኙ ነዋሪዎች ተቃውሞ አሰምተዋል " ሲል አክሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአለልኝ ቤተሰቦች ጋርም ቆይታ አድርጓል።
አንድ የአለልኝ ቤተሰብ አባል " አለልኝን እነሱ ያኔ ገደሉት ፍርድ ቤቱ ደግሞ ዛሬ ገደለው " ሲሉ በሃዘን ሃሳባቸውን ገልጸዋል።
" ዛሬ እንደ አዲስ ቤታችን ለለቅሶ ቁጭ ብለናል ሰዎችም ለቅሶ እየደረሱ ነው " ብሏል።
" ሚስቱ የወንጀል ድርጊቱን በመምራት በተባባሪዋ የእህቷ ባል አማካኝነት ካስገደለችው በኋላ የስልክ ገመድ በአንገቱ ላይ በማስገባት ' አለልኝ እራሱን አጠፋ ' በማለት ፍትሐት እንዳያገኝ አድርጋለች " ሲል ገልጿል።
" የጀመሩትን የጭካኔ ተግባር የሃይማኖት አባቶችን ጭምር በማሳሳት ' ሚስቱ ነፍሰጡር ነች ' እያሉ በማስወራት የሕዝቡን ልብ ካራሩ በኋላ ፖሊስና ዐቃቤ ሕግ ባደረጉት ጠንካራ ምርመራ አለልኝ እራሱን አለማጥፋቱና እነሱ መግደላቸዉን ፍርድ ቤቱ አረጋግጦና ያቀረቡትን የቅጣት ማቅለያም ወድቅ አድርጎ ሲያበቃ ፍርድ ቤቱ ያስተላለፈው ያልተጠበቀ ውሳኔ ቤተሰቡን አሳዝኗል " ብሏል።
" የስርቆትና አንድ ማንኛውንም ወንጀል በፈፀመ ወንጀለኛ ላይ የሚተላለፍ የፍርድ ውሳኔ ለሀገር ብዙ ያደርግ ለነበረ ተስፈኛ ወጣት ግድያ ወንጀል መሰጠቱ አሳዝኖናል " ሲል አክሏል።
" አለልኝ ላይ በተቀነባበረ መልኩ የግድያ ወንጀል ፈፅመዉ፣ ሕግን ህዝብንና ሃይማኖትን ለማታለል በሞከሩ ጨካኞች ላይ ፍርድ ቤቱ ያስተላለፈው ድሳኔ በጣም የሚያሳዝን ነው " ሲልም ቅሬታቸዉን አሰምተዋል።
ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ነዋሪዎችም " ፍርድ ቤቱ ሚስቱና የእህቷ ባል አለልኝን መግደላቸውን አረጋግጦ ጥፋተኛ ካለ በኃላ የወሰነው ውሳኔ እጅግ አሳዛኝ ነው " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጉዱዩ ጋር በተያያዘ የጋሞ ዞን ዐቃቤ ሕግ መምሪያ ኃላፊ አቶ ጤናሁን ጨርቆስን አነጋግሯል።
" ' የአለልኝ ጉዳይ እራሱን አጠፋ ተብሎ ተስፋ ተቆርጦ ከተተወበት የፍትህ መዋቅሩ ከፖሊስ ጋር በመሆን ጉዳዩን ከምንም አንስተው ለዚህ በማድረስ ተጠርጣሪዎችን ጥፋተኛ ማስባል በራሱ ትልቅ እርምጃ ነው " ብለዋል።
ይግባኝን በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላነሳላቸዉ ጥያቄ " የከፍተኛ ዐቃቤ ህግ ቡድኑ በፖናል ተነጋግሮ የሚወስነድ ይሆናል " ሲሉ ገልጸዋል።
የቲክክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ በስፍራው ተገኝቶ እንደተመለከተው ከፍርድ ዉሳኔዉ በኋላ የአለልኝ ቤተሰቦች ወዳጅ ዘመዶችና የአከባቢው ነዋሪዎች እንደ አዲስ ለቅሶ ተቀምጠዋል።
በሌላ በኩል በአርባ ምንጭ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የኑርሁሴን መታሰቢያ የክረምት እግር ኳስ ውድድር ዛሬ የነበረው መርሃግብር ተሰርዟል።
በርካታ የአርባ ምንጭ ከተማ ወጣቶችም የፍርድ ውሳኔን የሚቃወሙ ፅሑፎችን በመያዝ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አርባ ምንጭ
#TikvahEthiopiaFamliyArbaminch
@tikvahethiopia
#Ethiopia🇪🇹
#GERD💪
" ውሃውን እና አፈሩን በብቸኝነት ለመጠቀም የማያደርጉት ነገር የለም " - አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር)
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) ፥ በግድቡ ጉዳይ ኢትዮጵያን ከየአቅጣጫው የሚጎነትላት እንዳልጠፋ ገልጸዋል።
" የግብፆች ግፊት በየአቅጣጫው እንዳለ የታወቀ ነው። ከድሮ ጀምሮ ውሃውን ለብቻቸው ለመጠቀም ጦርነት ጭምር የከፈቱበት ወቅቶች ነበሩ፣ ከ640 ዓ.ም ጀምሮ በአዶሊስ ድረስ መጥተው ነበር " ሲሉ ተደምጠዋል።
" ስለዚህ በተለያየ አቅጣጫ ኢትዮጵያን ነፃ ከሆነ የልማት ጉዞዋ ለማደናቀፍ ውሃውን እና አፈሩን ደግሞ በብቸኝነት ለመጠቀም የማያደርጉት ነገር የለም። ከውስጥም ለመቦርቦር ይሞክራሉ ከውጭም እንደዛው " ሲሉ ገልጸዋል።
" ከወደ ትራምፕ በኩል የሚመጣው የተዛቡ ንግግሮች ከዚህ ማዕዘን ማየት አስፈላጊ ነው " ያሉት አረጋዊ (ዶ/ር)፣ " በአጭሩ ይሄ ግድብ በመንግስት ጥሩ ጥረት እና በህዝብ ቆራጥ ተሳትፎ ነው ተጠናቆ ለምረቃ እየተንደረደረ ያለው " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
✨🎁 በቴሌብር ሱፐርአፕ ይሙሉ፤ በየቀኑ 30% ተጨማሪ ስጦታ ያግኙ!
በቴሌብር ሱፐርአፕ https://bit.ly/telebirr_SuperApp የ100 ብር ካርድ ሲሞሉ ተጨማሪ የ30 ብር የአየር ሰዓት ስጦታ እናበረክትልዎታለን፡፡
👉 በዕለቱ በድጋሚ ካርድ ከሞሉ 25% ተጨማሪ ስጦታ ያገኛሉ!
💥 የአየር ሰዓትዎን በቴሌብር ሱፐርአፕ ይሙሉ፤ በየዕለቱ ተጨማሪ ስጦታ ያግኙ!
🗓 እስከ ጳጉሜ 05 ቀን 2017 ዓ.ም
ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia
" 10 ሰዎች ተገድለዋል፤ ከ10 በላይ ሰዎች ቆስለዋል " - የቤሩ ወረዳ አስተዳዳሪ
በጋምቤላ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል አዋሳኝ ዲማ እና ቤሩ አከባቢዎች በተነሳ ግጭት የሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ባለስልጣናት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለፁ።
በጋምቤላ ክልል የአኙዋሃ ብሔረሰብ ዞን ዲማ ወረዳ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የምዕራብ ኦሞ ዞን ቤሩ ወረዳ አዋሳኝ አከባቢዎች በወርቅ ቁፋሮ ቦታ ምክንያት በተነሳ ግጭት ከ10 ሰዎች በላይ መሞታቸውን ባለስልጣናት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።
የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኦጉላ ኡጁሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት በዲማ ወረዳ የወርቅ ማምረት ስራ ላይ ፈቃድ ወስደዉ የተሰማሩ ባለሃብቶችንና በሳይት ጥበቃ ላይ የነበሩ ሚሊሻዎችን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ምዕራብ ኦሞ ዞን በኩል አስረዉ መወሰዳቸውን ተከትሎ ግጭቱ መከሰቱን አስታውቀዋል።
" በግጭቱ ምክንያት ሁለቱም በኩል የሰዉ ሕይወት ጠፍቷል " ሲሉ ገልፀዋል።
" የሟቾችን ቁጥር እስካሁን አልለየንም " ያሉት ኮሚሽነሩ መረጃዉ ተጣርቶ ሲደርስ እንደሚያሳዉቁም ገልፀዋል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ምዕራብ ኦሞ ዞን የቤሩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገመዳ ከይዳዴ በበኩላቸው " ድንበር አልፈዉ የወርቅ ቁፋሮ ሲያካሂዱ የነበሩ 11 ግለሰቦችንና 1 የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር አዉለን ተገቢውን ማጣራት እያደረግን ባለንበት ወቅት ከጋምቤላ ክልል በኩል ተኩስ ተከፍቶ 2 የአድማ ብተና አባላት፣ 1 መደበኛ ፖሊስ እና ሴቶች ጨምሮ 7 በወርቅ ቁፋሮ ስራ ላይ የነበሩ ንፁሃን ዜጎች በድምሩ 10 ሰዎች ተገድለዋል፤ ከ10 በላይ ሰዎች ቆስለዋል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
በግጭቱ ምክንያት ከ20 ሺህ ነዋሪዎች ተፈናቅለዉ እንደነበር የገለፁት ዋና አስተዳዳሪዉ ከማምሻ ጀምሮ የፌዴራል ፖሊስ እና የሀገር መከላከያ ሠራዊት አከባቢውን በመቆጣጠሩ ተፈናቃዮችን ወደ ቦታቸዉ የመመለስ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
በአሁኑ ሰዓት በአካባቢው ግጭት መቆሙንና የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የሁለቱም ክልል ባለስልጣናት ሕዝቡን የማረጋጋት ስራ እየሰሩ ስለመሆኑ ከሁለቱም ክልሎች በኩል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ማረጋገጥ ችሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamily
@tikvahethiopia
#አለልኝ_አዘነ
ከአለልኝ አዘነ ግድያ ጋር በተያያዘ በባለቤቱ አደይ ጌታቸው እና በባለቤቱ እህት ባል ሉንጎ ሉቃስ ላይ የተላለፈው የፍርድ ውሳኔ " አንሷል " ሲሉ የተጫዋቹ ቤተሰቦች እና የቅርብ ጓደኞች ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአለልኝ አዘነ ጉዳይ የመጨረሻ ፍርድ ዛሬ የሰጠ ሲሆን በተከሳሽ የአለልኝ ባለቤት አደይ ጌታቸዉና በእህቷ ባል ሉንጎ ሉቃስ ላይ የ16 እና 15 ዓመት ፅኑ እስራት ፈርዶባቸዋል።
የፍርድ ጊዜዉም ከዛሬ ጀምሮ የሚቆጠር እንደሆነ የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ያመላክታል።
የተጫዋቹ ቤተሰቦችና የቅርብ ጓደኞች " የፍርድ ዉሳኔዉ አንሷል " በሚል ቅሬታቸዉን እያሰሙ እንደሚገኝ የፍርድ ሂደቱን የተከታተለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ገልጿል።
አለልኝ አዘነ ጋብቻውን በፈጸመ በጥቂት ቀናት ውስጥ ነው በባለቤቱና በባለቤቱ እህት ባል በተቀነባበረ ሁኔታ የተገደለው።
በወቅቱም " ራሱን አጠፋ " ነበር የተባለው።
ነገር ግን ባለቤቱ (አደይ ጌታቸው) እና የባለቤቱ እህት ባል (ሉንጎ ሉቃስ) በአለልኝ ግድያ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉና ክስም ከተመሰረተ በኃላ የጋሞ ዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት ጉዳዩን ሲከታተለው ቆይቶ ዛሬ በተከሳሾቹ ላይ የ16 እና 15 ዓመት ፅኑ እስራት ፈርዶባቸዋል።
ቤተሰቦች እና የተጫዋቹ የቅርብ ጓደኞች ግን የፍርድ ውሳኔው አላስደሰታቸውም። ከተፈፀመው የግፍ ተግባር አንጻር የፍርድ ውሳኔው " አንሷል " የሚል ቅሬታ አላቸው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አርባ ምንጭ
#TikvahEthiopiaFamilyArbaminch
@tikvahethiopia
#Tigray
በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን የጊዚያዊ አስተዳደሩ ትእዛዝ በሰጠው አድማ በታኝ ፓሊስ የተደገፈ የስልጣን ሹምሽር እየተካሄደ መሆኑ ተሰምቷል።
ከትናንት ሀምሌ 14/2017 ዓ.ም ጀምሮ ነው ከመቐለ ወደ ማይጨው ከተማ በተላከ የአድማ ብተና ፓሊስ ጥብቅ ቁጥጥር ስር የስልጣን ሹምሽር እየተካሄደ ያለው።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጄ) የስልጠን ሹም ሽሩ " ሰላማዊ ነው " ቢሉም የቀድሞ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ጨምሮ በርካቶች ድርጊቱ " በሀይል የሚደረግ ግጭት ቀሰቃሽ የስልጣን ንጥቂያ " ብለውታል።
የዞኑ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ በወርሃ መጋቢት 2017 ዓ.ም ከትግራይ ከወጡበት ጀምሮ የአመራር ለውጥ ያልተደረገበት አከባቢ ሆኖ ቆይቷል።
የዞኑ አስተዳደር አመራሮች ባለፉት ወራት ህወሓት እንደማይወክላቸው የሚገልፅ ሰፋፊ ህዝባዊ ህዝባዊ ሰልፎች ማካሄዳቸው መዘገባችን ይታወሳል።
ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) በደቡባዊ ዞን እየተደረገ ነው ስላሉት የስልጣን ሹምሽር ዛሬ ሀምሌ 15/2017 ዓ.ም ለሚድያ በሰጡት መግለጫ ምን አሉ ?
- ከዞኑ የአመራር ቦታ የሚነሱ ሀላፊዎች በክልል የሃላፊነት ቦታ ተዘጋጅቶላቸዋል።
- የስልጣን ሽምሹሩ እንዲተገበር የሚያሳልጥ ፓሊስ ወደ አከባቢው ተልኳል።
- በዞኑ የለውጥ አመራር ለማድረግ ያስፈለገበት ምክንያት ቀጣይ አደጋዎች ለማስቀረትና የክልሉ የፀጥታ ችግር ለመፍታት በማለም ነው።
- መንግስት በዞኑ በግድ ማድረግ ያለበት ነው እያደረገ ያለው ስለሆነም ሂደቱ ማደናቀፍ አይቻልም።
- የአከባቢው ህዝብ ፣ ወጣቶች ፣ ሚልሻና ሌሎች ለውሳኔው ውጤታማነት ተባባሪ መሆን አለባቸው።
ሲሉ ተናግረዋል።
በትግራይ ደብባዊ ዞን እየተከናወነ ያለውን ጉዳይ" በዞኑ ህዝብ ላይ የተጫነ አስገዳጅ የስልጣን ንጥቂያ ነው " በማለት ብርቱ ትችት አዘል ፅሁፍ ካጋሩት በርካቶች አንዱ አቶ ጌታቸው ረዳ ናቸው።
አቶ ጌታቸው " ' ኃላቀር ቡድን ' ሲሉ የገለፁት የህወሓት አመራር በክልሉ ደቡብና ደብባዊ ዞኖች ወታደራዊ ዘመቻ በማካሄድ ሌላ ቀውስ እንዲፈጠር እየሰራ ነው " ሲሉ ከሰዋል።
በዚህ ምክንያት ለሚፈጠር ማንኛውም ጥፋት ' ኃላቀር ቡድን ' ሲሉ የገለፁት የህወሓት አመራር ፣ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮችና በተለይ ፕሬዜዳንቱና የጊዚያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ተጠያቂ መሆናቸውን አስጠንቅቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamliyMekelle
@tikvahethiopia
🎓 በወጋገን ኢ-ስኩል የመማር ማስተማር ስራን ወደላቀ ውጤታማነት ያሸጋግሩ!!
ወላጆች ካሉበት ቦታ ሆነው የልጆችዎን የትምህርት ክፍያ በወጋገን ባንክ የዲጂታል አማሪጮች እና ወኪሎችን በመጠቀም በቀላሉ ይፈፅሙ!
🎒 በተጨማሪም ከመዋዕለ ህፃናት እስከ ዩኒቨርሲቲ ላሉ የትምህርት ተቋማት:-
•የትምህርት ቤት ክፍያዎችን ዝርዝር መግለጫ በቀላሉ ማግኘት፣
•ደህንነቱ እና ምስጢራዊነቱ የተጠበቀ የተማሪዎች መረጃ አያያዝ ስርዓት መተግበር፣
•አውቶሜትድ በሆነ መልኩ የተማሪዎችን መታወቂያ ማዘጋጀት፣
•የተማሪዎችን ውጤት መሙላትና ሪፖርት ማዘጋጀት እንዲሁም ሰርተፊኬት ማተም
•በተደራጀ መልኩ የተማሪዎችን አቴንዳንስ መከታተል እና የተረጋገጠ የክፍያ ደረሰኝ ማግኘት
• ለተማሪዎች ልዩ ድጋፍ በማድረግ የመማር ማስተማር ስራን ማቀላጠፍ ይችላሉ!
ለበለጠ መረጃ በ866 ነፃ የስልክ መስመር ወደ ደንበኞች ግንኙነት ማዕከል ይደውሉ፣ ይስተናገዱ
📲 ሊንኩን በመጫን የማህበራዊ ሚዲያዎቻችንን ይቀላቀሉ
╰➤ https://linktr.ee/WegagenBank