tikvahethiopia | Unsorted

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1531512

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Subscribe to a channel

TIKVAH-ETHIOPIA

#Tigray

" እንቅስቃሴው እጅግ አደገኛና የማያባራ ቀውስ የሚያዋልድ በመሆኑ በአስቸኳይ ይቁም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

" ' የሰራዊት አመራር ውሳኔ ' በሚል ህገ-ወጥ ጉባኤ ላካሄደ ቡድን ስልጣን ለማስረከብ የተጀመረ እንቅስቃሴ እንዲቆም " ሲል የትግራይ ክልል ጊዜዊ አስተዳደር ትእዛዝ ሰጠ።

ትእዛዙን የሰጡት የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ህገ-ወጥ ተግባሩ " አስነዋሪ ፣ ለውጥ አደናቃፊና እርባና ቢስ " ሲሉ አጣጥለውታል።

ፕሬዜዳንቱ በቀጥታ ለጊዚያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕሬዜዳንትና የሰራዊት አዛዥ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ የካቲት 26/2017 ዓ.ም በፃፉት ደብዳቤ ህገ-ወጥ ተግባሩ በአስቸኳይ እንዲቆም አዘዋል።

" ህገ-ወጥ ጉባኤ ያካሄደ ቡድን " ሲል የገለፁት የደብረፅዮኑ (ዶ/ር) ህወሓት የክልሉ ማእከላዊና ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን የጊዚያዊ አስተዳደር መዋቅሮች በሰራዊት በመታጠቅ መቆጣጠሩ አንስቷል።

ህገ-ወጥ ድርጊቱ በተቀሩት ምስራቃዊ ፣ ደቡባዊ ፣ ደቡብ ምስራቅና መቐለ ዞኖች ለመፈፀም ያለመ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነውም ብለዋል። 

አቶ ጌታቸው ፤ " ማንኛውም ጥያቄ አለኝ የሚል የሰራዊት አመራር በህጋዊ መንገድ ጥያቄው ማቅረብ የሚችልበት ስርዓት በመጣስ በቀበሌ ፣ በወረዳ እና በመንደር ሰራዊት እያሰማሩ የመንግስት መዋቅር ለማፍረስ ማህተም ለመቀማት የሚደረግ እንቅስቃሴ ከስርዓት አልበኝነት ውጪ የሚያመጣው ፋይዳ የለም " ብለዋል።

" በተወሰኑ የሰራዊት አመራር ስም ሰራዊቱ በማሰመራት የመንግስት መዋቅሮች ህገ-ወጥ ጉባኤ ላካሄደ ቡድን ለማስረከብ የሚደረግ እንቅስቃሴ እጅግ አደገኛና የማያባራ ቀውስ የሚያዋልድ በመሆኑ በአስቸኳይ ቆሞ ህገ-ወጥ ተግባሩ እንዲፈፀም ያዘዙ የሰራዊት አመራሮች እንዲጠየቁ " ሲሉም ፕሬዜዳንቱ በደብዳቤያቸው በአፅንኦት አሳስበዋል።

ለምክትል ፕሬዜዳንትና የሰራዊት አዛዥ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የተፃፈው ደብዳቤ ትእዛዙ በግልባጭ ለሰላም እና የፀጥታ ቢሮ ለከፍተኛ የሰራዊት አዛዦች ሜጀር ጀነራል ዮውሃንስ ወ/ጊዮርጊስ ፣ ሜጀር ጀነራል ማሾ በየነ አሳውቀዋል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
 
@tikvahethiopia            

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

🔴 “ የታሰሩት ተፈትተዋል፡፡ የመብት ጥያቄ በማቅረብችን ነው ያሰሩን፡፡ 10 ሠራተኞች ሥራ ተከልክለናል ” - የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች

➡️ “ ቅሬታ እንዳለባቸው አውቃለሁ፡፡ ያንን ማሰማት መብታቸው ነው፡፡ የሰሩት ወንጀል የለም ” - የከተማው ጸጥታ መምሪያ

በዛ ቢባል 1,100 ብር ደመወዝተኛ ለ20 ዓመታት ምገባና ሌሎች ሥራዎችን የሰሩ 800 የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ እንዲደረግላቸው ዩኒቨርሲቲውን ሲጠይቁ ‘እንዲያውም አሰናብታችኋላሁ’ እንዳላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቀናት በፊት ተናግረው ነበር።

ሠራተኞቹ ከዚያ በኋላ በገለጹት መሰረት፣ ቅሬታቸውን ለሚዲያ ለማቅረብ በሄዱበት ወቅት ደግሞ የተወሰኑት ሠራተኞች በፖሊስ እንደታሰሩ ነበር የነገሩን።

የሲዳማ ክልል ጸጥታ ቢሮ ጉዳዩን እንደሚያጣራና ሠራተኞቹ ደመወዝ ቢጨመርላቸውም እንደማይከፋው፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጉዳዩን እንደማያውቅ ስለጉዳዩ ከቲክቫህ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተው ነበር።

ታሰሩ የተባሉት ሠራተኞች ተፈቱ ?

የታሰሩት ሠራተኞች ትላንት ጠዋት በዋስ እንደተፈቱ፣ ገና ወደ ሥራ እንዳልገቡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ታስረው ከነበሩና ከቅሬታ አቅራቢ ሠራተኞቹ ገለጻ ለማወቅ ችሏል፡፡

ሠራተኞቹ በሰጡን ቃል፣ “የታሰሩት ተፈትተዋል፡፡ የመብት ጥያቄ በማቅረብችን ነው ያሰሩን፡፡ ከ10 በላይ ሠራተኞች ሥራ ተከልክለናል” ነው ያሉት።

የመብት ጥያቄ ለማቅረብ ከመሞከር ውጪ ጥፋት እንዳልፈጸሙ፣ ሆኖም በዩኒቨርሲቲ በሚገኘው 01 ቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ከቆዩ በኋላ በመታወቂያ ዋስ እንደተለቀቁ ሠራተኞቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል፣ ቅሬታ ካቀረቡት የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች መካከል 10 የሚሆኑት “ወደ ዩኒቨርሲቲው ለሥራ አትግቡ” ተብለው እንደተከለኩ ገልጸው፣ መብታቸው እንዲከበርላቸው በድጋሚ ጠይቀዋል፡፡

ታሳሪዎቹን በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጥ ሰሞኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲጠይቀው የነበረው የሀዋሳ ከተማ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ፣ ጉዳዩን አጣርቶ ምላሽ ለመስጠት ገልጾ ነበር፡፡

መምሪያው ትላንት በሰጠን ምላሽ፣ “ምንም የታሰረ አካል የለም፡፡ የተፈጠረ ነገርም የለምኮ ለምንድን ነው የሚያታሰሩት?” ብሏል።

“ ቅሬታ እንዳለባቸው አውቃለሁ፡፡ ያንን ማሰማት መብታቸው ነው፡፡ የሰሩት ወንጀል የለም፡፡ የሚያሳስራቸው ጉዳይም የለም ” ሲል ተናግሯል።

የተፈጠረ ነገርማ አለ፤ ሠራተኞች እንደታሰሩ ተናግረዋል፣ ለመሆኑ ከከተማው 01 ቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ ሄዳችሁ አጣርታችሁ ነበር ? ስንል ላቀረብለት ጥያቄ ደግሞ፣ “ ቼክ አድረገናል፡፡ ወንጀል የለባቸውም፡፡ ዩኒቨርሲቲውም ለኛ ያመለከተን ጉዳይ የለም ” ብሏል።

ሠራተኞቹ በበኩላቸው፣ “ እነርሱማ እውነት ነው አይሉም ” ሲሉ ወቅሰዋል።

(ክትትሉ ይቀጥላል)


#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ወጋገን ባንክ

እንኳን ለዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን አደረሳችሁ

ከመደበኛው ቁጠባ ከፍ ያለ ወለድ በሚያስገኘው ንጋት የሴቶች መደበኛ ወይም ንጋት ሙዳረባህ ትርፍ የሚያጋራ  ከወለድ ነፃ የሴቶች የቁጠባ ሂሳብ ስትቆጥቢ ያሰብሽዉን ታሳኪያለሽ!

ለበለጠ መረጃ የወጋገን ባንክ ማህበራዊ ሚዲያዎችን ከስር ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ!

https://linktr.ee/WegagenBank

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

እጅግ ፈጣንና ዘመናዊ የሆነውን የመኪና ባትሪ መሙያ ጣቢያ እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ይመልከቱ!!

🤖 በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የሚታገዝ
🔋 የባትሪ አቅም መፈተሽ የሚችል
🔌 በሰከንድ እስከ 1 ኪ.ሜ. መጓዝ የሚያስችል ኃይል የሚሞላ

ለ1 ኪሎ ዋት 10ብር ብቻ!

📍 ከቦሌ ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ላይ ይገኛል!


#teleEvCharging
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #SmartAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" እሳቱ ከሰማይ እንደወረደ በማስመሰል የሚሰራጩት መረጃዎች የተሳሳቱ ናቸው " - ፖሊስ

በሀላባ እና ከንባታ አከባቢ " ሰማይ ላይ እሳት መሰል አካል ታየ " ተብሎ የሚሰራጨው መረጃ ትክክለኛ አይደለም ሲል የአከባቢው ፖሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

ከዚህ ቀደም በደቡብ ኢትዮጵያ ማዕከላዊ ቦታዎች እና በኦሮሚያ ክልል ጉጂና ቦረና አከባቢዎች የታየዉ አይነት በራሪ እሳት መሰል ብርሃናማ አካል ትላንት ሌሊት 6 ሰዓት ገደማ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ እና ከንባታ አከባቢዎች ዳግም መታየቱን በመግለፅ በርካቶች በማህበራዊ የትስስር ገፃቸዉ መረጃዎችን ሲያጋሩ ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን ለማጣራት የአከባቢውን የፀጥታ መዋቅሮች አነጋግሯቸዋል።

የከንባታ ዞን ዳንቦያ ወረዳ እና የሀላባ ዞን ወዠዌይራ ወረዳ ፖሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጹት ፤ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለዉ ይህ መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ገልጸዋል።

" ጉዳዩ የተከሰተበት ሠዓት እኩለ ሌሊት መሆኑንና በተለይም ከሀላባ ከተማ በኩል ሲታይ በረጅም ተራራ አናት ላይ በድንገት የተከሰተውን እሳት በሌሊት የተነሱት ፎቶዎች ከወራት በፊት በሰማይ ከታየው ብርሃናማ አካል ጋር በማያያዝ ትክክለኛ ያለሆነ መረጃ በርካቶች እንዲቀባበሉ ሳያደርግ እንዳልቀረ " ተናግረዋል።

በሀላባ ዞን ዌይራ ወረዳና በከንባታ ዞን ዳንቦያ ወረዳ አዋሳኝ አከባቢ በሚገኝ ተራራማ ስፍራ በትላንትናው ዕለት ሌሊት 6 ሰዓት አከባቢ እስካሁን ትክክለኛ መንስኤው ያልታወቀ የእሳት አደጋ ተከስቶ ከ7 ሄክታር በላይ ደን ማዉደሙን ገልፀዋል።

እሳቱ የተቀሰቀሰበት ሠዓት እኩለ ሌሊት አከባቢ መሆንና የመልክአምድሩ አስቸጋሪነት ከወቅቱ በጋ መሆን ጋር ተዳምሮ እሳቱን የማጥፋት ሂደት አዳጋች አድርጎት እንደነበር የገለፁት የሁለቱም አጎራባች ወረዳዎች ፖሊስ አዛዦች የእሳት አደጋውን ትክክለኛ መነሻና መንስኤ አጣርተን ለሕዝቡ እናሳዉቃለን ሲሉ ቃል ገብተዋል።

ከዚህ በዘለለ እሳቱ ከሰማይ እንደወረደ በማስመሰል መረጃዎች እያሰራጩ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

Got grit, guts, and a big idea? Jasiri Talent Investor is your ticket to building sustainable ventures—13 months, fully backed, and ready for you. Submit your application now!

👉Head to https://bit.ly/40Ai4oR and apply to join our 8th cohort today!

For more information @jasiri4africa

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ከጀርባዋ " ኤሌክትሮኒክ ቁስ ተሸክማ ስትበር ተያዘች " የተባለችው ወፍ ምንድነች ?

🔴 “ ምርመራ እየተደረገ ነው ፤ ገና አላለቀም ” - የቤንሻንጉል ክልል ፓሊስ ኮሚሽን

➡️ “ ምርመራ እየተደረገ ነው። ሲያልቅ እናሳውቃለን ” - የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን እና ሰላምና ጸጥታ ቢሮ 


በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ ጉሬ ቀበሌ “ በጀርባዋ ላይ ኤሌክቶርኒክስ ቁስ ተገጥሞባታል ” የተባለችና ከወትሮው ለየት ያለች ወፍ ስትበር መያዟን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአካባቢው ነዋሪዎች ሰምቷል።

በገለጻው መሠረት፣ ወፏ በጉሬ ቀበሌ ሰማይ ስር ስትበር የተገኘችው ከቀናት በፊት ሲሆን፣ ኤሌክትሮኒክስ ቁስ የተገጠመላት ከመሆኗ ባሻገር፣ ሙሉ አካሏ በአርቲፊሻል የተሞላ፣ በሁለት እግሯቿም ቀለበቶች እንዳላት ተመላክቷል።

እንዲህ አይነት ወፍ ከዚህ በፊት በአካባቢው ዝር ብሎ እንደማያውቅ የተናገሩት ነዋሪዎች በተለይ ወፏ እግር ላይ ያሉት ቀለበቶችና በጀርባዋ ተገጥሞላታል የተባለው ኤሌክትሮኒክ ቁስ “ ምን የያዘ ነው ? ” በሚል ስጋትን እንደደቀነባቸው ጠቁመዋል።

አንዳንዶችም ጉዳዩ “ ከህዳሴ ግድቡ ጋ ሊገናኝ ይችል ይሆን ? ” የሚል መላምት ሲያስቀምጡም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተመልክቷል።

በተለይም ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ወፏ ላይ ምርመራ ለማድረግ በጸጥታ አካላት ወፏ ወደ አሶሳ ከተማ ሳትወሰድ እንዳልቀረች ተነግሯል።

በዚህም ስለጉዳዩ የተጠየቅነው የአሶሳ ፓሊስ መምሪያ፣ ጉዳዩን እንደሰማ፣ ነገር ግን ሁነቱ ከከተማው ውጪ በመሆኑ ምርመራው እንደማይመለከተው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተጨማሪም፣ በማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ ሰማይ ስር ስትበር ታየች የተባለችው ቀለበትና ኤሌክትሮኒክ ቁስ በጀርባዋ እንዳላት የተነገረላት ወፍን ምንነት አውቀው እንደሆን የክልሉ ፓሊስ፣ ኮሚዩኒኬሽን፣ ሰላምና ጸጥታ ቢሮዎችን ጠይቋል።

አንድ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ፓሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራር በሰጡት ምላሽ፣ “ መከላከያ ጋር ነው፤ ምርመራ እየተካሄደ ያለው። ምርመራው ገና ለላለቀም ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። 

ስለጉዳዩ የጠየቅናቸው አንድ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አካል ደግሞ መረጃው እንደደረሳቸው ገልጸው፣ “ ምርመራ እየተደረገ ነው። ሲያልቅ እናሳውቃለን ” የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።

ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረብንለት የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ በበኩሉ፣ ወፏን በተመለከተ ምርመራ እየተደረገ እንደሆነ፣ ምርመራው ሲጠናቀቅ ማብራሪያ እንደሚሰጠን ቃል ገብቷል።


(ጉዳዩን ተከታትለን በቀጣይ መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Mekelle

🔴 " ህወሓት መዳን ከፈለገች መልሳ ጉባኤ ማድረግ አለባት የሚል እምነት አለኝ "- ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ 

⚫️ " ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እርምጃ ውሰድ ፤ ካልሆነ በራሳችን መንገድ እንሄዳለን " - የመቐለ ከተማ ወጣቶች


ዛሬ ለመቐለ ከተማ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር የመከሩ ወጣቶች የደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት "  ኋላቀር ለውጥ አደናቃፊ " ሲሉ  ወረፉ።

ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ዛሬ ከመቐለ 7 ከፍለ ከተሞች ከተወጣጡ ወጣቶች በፅህፈት ቤታቸው የተወያዩ ሲሆን ለተነሱላቸው ጥያቄዎች መልስና ማብራርያ ሰጥተዋል። 

ወጣቶቹ በመድረኩ ባቀረቡት አስተያየትና አካሄድ የደብረፅዮኑ (ዶ/ር) ህወሓት " ' እኔ ባልቀደስኩት መአድ ለመብላት እጅ መሰድድ አይታሰብም ' በሚል አካሄድ ተጠምደዋል " ሲሉ  ተችተዋል።

" ' እኔ ብቻ ነኝ ፈላጭ ቆራጭ ' የሚል ፈሊጥ ያለንበት ወቅት የማይዋጅ ኋላቀር " ሲሉ በስሜት የተናገሩት ወጣቶቹ የደብረፅዮኑ (ዶ/ር) ህወሓት የጠቅላይነት መንገድና አካሄድ አይሰራም ብለዋል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት " ፀረ ለውጥ " ሲሉ በፈረጁት የደብረፅዮኑ ህወሓት ላይ እርምጃ ባለመወሰዱ አምርረው የነቀፉት ወጣቶቹ  " ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እርምጃ ውሰድ ፤ ካልሆነ በራሳችን መንገድ እንሄዳለን " በማለት ቁጣቸው አሰምተዋል።  

" መንግስት መንግስትን በመሆን የለውጥ ጥያቄያችን ይመልስ እኛ ወጣቶች ትዕግስታችን ተሟጠዋል " ሲሉም ገልጸዋል።

ህዝቡ የአስተማማኝ ሰላም ባለቤት እንዲሆን በምርጫ የሰየመው መንግስት ሊኖረው ይገባል ሲሉ ምላሽ የሰጡት ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ይህንን እውን እንዲሆን ከስሜት የፀዳ ትግልና አካሄድ ከወጣቱ ይጠበቃል ብለዋል። 

" ህወሓት ጠላት ነው " የሚል ነገር ስህተት እንደሆነ የገለፁት ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው  " ፓርቲው እንዲድን ከተፈለገ እንደ አዲስ አሳታፊ ጉባኤ ማካሄድ ይጠበቅበታል " የሚል ምክረ ሃሳብ አቅርበዋል። 

በትግራይ ያለው ችግር በህወሓት ብቻ ይፈታል ማለት ስህተት ነው ፤/ስለሆነም ላሉት ዘርፈ በዙ ችግሮች አሳታፊ ሁሉን አቀፍ ፓለቲካ ዋነኛ ተመራጭ መንገድ ነው ሲሉ አክለዋል።

ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የመቐለ ከተማ ያለ ከንቲባ ከሦስት ወራት በላይ መቆየት፣ የDDR መቋረጥ ፣ በክልሉ የሚታዩ በርካታ የፀጥታ ችግሮች በማስመልከት ከወጣቶች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስና ማብራርያ መስጠታቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

Photo Credit - Tigrai TV

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የሽግግር መንግሥት በተናጠል በክልል ደረጃ ሊመሠረት አይችልም " - የትብብር ፓርቲዎች

መኢአድ፣ ኢሕአፓ፣ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄና እናት ፓርቲ በጋራ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ አወጡ።

በዚህ መግለጫቸው የሰሞኑን የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ምክልር እና የተላለፈውን ውሳኔ ታቃውመዋል።

" እሳት ላይ ቤንዚን እንደማርከፍከፍ ይቆጠራል " ሲሉም ገልጸውታብ።

ፓርቲዎቹ " አገራችን የገባችበት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅል ወደ አገራዊ ቀውስ እያደገ ባለበትና ከዚህም ለመውጣት አገር አድን ርብርብ በሚያስፈልግበት በአሁኑ ወቅት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የደረሱበት ስምምነት በአመዛኙ እሳት ላይ ቤንዚን እንደማርከፍከፍ የሚቆጠርና ቀን አይቶ የመጣል አዝማሚያ ያለው ሆኖ አግኝተነዋል " ብለዋል።

" አሁንም ሰላም በአገራችን እንዲሰፍን ሁላችንም በጋራ መታገል ያለብን ወቅት ነው እንላለን " ያሉት ፓርቲዎቹ " ላለፉት 6 ዓመታት የመከራ ሕይወት እየገፋ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚቻለውን ሁሉ በማድረግ በጋራ ታግለን የሚናፍቀውን ሰላም እውን ማድረግ ይጠበቅብናል እንጂ በተናጠል ያውም በክልል ደረጃ ወርደን የሚመጣ ሰላም አይኖርም የአገራችንን አንድነትም ማስጠበቅ አይቻልም " ብለዋል።

" በአንድ ክልል ሊቋቋም የታሰበው ' የሽግግር መንግሥት ' አገራችን አሁን ከምትገኝበት ሁኔታ የበለጠ ያመሰቃቅላል፣ ችግሮችንም ያባብሳል እንጂ መፍትሄ ሊሆን እንደማይችል መገንዘብ ያስፈልጋል " ብለዋል።

" በሁሉም አካባቢ ሰላም ካልሰፈነ፣ ማንም ወገን ብቻውን ነፃ አይወጣም፣ የትኛውም ክልል ውስጥ በተናጠል ሰላም አይሰፍንም " ሲሉ አመልክተዋል።

" በተናጠል በኦሮሚያ ክልል ' የሽግግር መንግሥት ማቋቋም ' የሚለውን አስተሳሰብ አጥብቀን እንቃወማለን " ብለዋል። 

(የትብብር ፓርቲዎቹ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#DStvEthiopia

ብዙ ታሪክ ያየው የማን ዩናይትድ ሜዳ ኦልድትራፎድ ስታዲዮም እሁድ ከምሽቱ 01፡30 የዘመናት የኳስ ባላንጣዎቹ ማንቼ እና አርሴን ያስተናግዳል!

አርሰናል የኤፍኤ ካፕ ሽንፈቱን ለመበቀል ቋምጧል ማን ዩናይትድ ባላንጣውን አንገት ሊያስደፋ አሰፍስፏል!

ማን ያሸንፋል ? እሁድ የካቲት 30 ይለያል!
👉 ሁሉንም የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይመልከቱ።

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#MoE #NGAT

ትምህርት ሚኒስቴር የሶስተኛውን ዙር የ2017 ዓ.ም የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ ጊዜ ይፋ አደረገ።

ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) አመልካቾች ምዝገባ ከየካቲት 27 እስከ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም ማታ 12፡00 ሰዓት ድረሰ ብቻ በ
https://ngat.ethernet.edu.et/registration የመመዝገቢያ ሊንክ በኩል እንደሚከናወን አሳውቋል።

ከምዝገባው ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ በሥራ ሰዓት በኢሜል አድራሻ
ngat@ethernet.edu.et ወይም በስልክ ቁጥር 0920157474 እና 0911335683 ማብራሪያ መጠየቅ እንደሚቻልም አመልክቷል።

የመፈተኛ ' USER NAME ' እና " PASSWORD ' በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል ይላካል ያለው ሚኒስቴሩ የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 750 እንደሆነና በቴሌብር በኩል ብቻ እንደሚፈጸም ገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን በቀጣይ እንደሚያሳውቅ አመልክቷል። ተፈታኞች በፈተና ወቅት የተሰጣቸውን User Name እና Password፣ እንዲሁም ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል ብሏል።

#MoE

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

🔴 " ሙሉ ፓትሮል መኪና መጣብን፡፡ እኛ ሮጠን አመለጥን ሌሎች 5 ሰዎች ታስረዋል " - የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች

➡️ " እየለፉ እስከሆነ ድረስ ቢጨመርላቸው ደስ ይለናል " - የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ

⚫️ " የማውቀው ጉዳይ የለም " - የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን

ከማኀበራት ተውጣጥተው በሀዋሳ የኒቨርሲቲ በምገባና ሌሎች ስራዎች ለዓመታት ሰራን ያሉ ወደ 800 ሠራተኞች ደመወዝ እንዲጨመርና ቋሚ ቅጥረኛ እንዲሆኑ ጥያቄ በማቅረባቸው፣ ዩኒቨርሲቲው ከሥራ ሊያሰናብታቸው መሆኑን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አቤት ብለው ነበር።

ሠራተኞቹ ዛሬ በሰጡን ቃልስ ምን አሉ ?

“ ደመወዝን በተመለከተ ቅሬችንን ለመግለጥ ወደ ደቡብ ኤፍኤፍ እየሄድን በነበረበት የተወሰኑ ሰዎች ታስረዋል መብታቸውን ስለጠቁ ታስረዋል፡፡ አንዱ ታሳሪ ታሟል፡፡

ጠዋት ደቡብ ኤፍኤም ቀጥሮን ነበር፡፡ 2 ሰዓት ተኩል ወደ ጣቢያው ስንሄድ ሙሉ ፓትሮል መኪና መጣብን፡፡ እኛ ሮጠን አመለጥን ሌሎች 5 ሰዎች ታደስረዋል፡፡ ጠዋት ነው የታሰሩት አሁን ስንሄድ ቃላቸውን የሚቀበላቸው የለም። እኛንም እየፈለጉን ነው ካፓስ ውጪ ነን። 

ሰዎቹ የታሰሩት ሀዋሳ 01 ፖሊስ ጣቢያ ነው፡፡ ምንም አላጠፋንም፡፡ ‘ለምን ተሰባሰባችሁ’? ሲሉን የደመወዝ ጭማሪ አልደረሰንም፡፡ በ1,000 ብር ደመወዝ እየሰራን ኑሮ ውድነቱን መቋቋም አልቻልንም፡፡ መንግስት እንዲመለከተን ለሚዲያ ቃላችንን ልንሰጥ ነው የመጣነው አልናቸው፡፡

ከዚያ በኋላ ‘እንዴት ስማችን ይጠፋል? ለምንድን ነው የምታስተላልፉት’? ብለው ነው ወንዶቹን አተኩረው ያሰሯቸው። የታሰሩት ሠራተኞች እንጨት ሲፈልጡ ለትርፍ አንጀት በሽታ ተጋልጠው ቀዶ ጥገና የተሰሩ ናቸው፡፡ አንዱ መኪና ላይ ሲወረውሩት ራሱን አያውቅም።

መንግስት ይየን፡፡ ፍትህ ይደረግልን፡፡ የኑሮ ውድነት እኛን አልነካም? እኛ ልጆች የሉንም? ለምንድን ነው መንግስት የማያየን? የኑሮ ወድነቱን አልቻልንም፡፡ ተንከራተን ነው የምንኖረው፡፡ ልጆቻችን እየተራቡ፣ እየተጠሙ ነው፡፡

24 ሰዓት ነው ግቢ ውስጥ የምንሰራው፡፡ ከግቢ ወጥተን ሌላ ሥራ ለመስራትም ጊዜ የለንም፡፡ ሁሉም በችግር ላይ ነው። በዛ ላይ ወጥ የተደፋባቸው፣ እጃቸውን ማሽን የቆረጣቸው አሉ። አካል ጉዳተኞቹንም ለማሳየት ነበር ወደ ሚዲያ የሄድነው፡፡ ግን መብታችን ተረግጧል፡፡ ዲሞክራሲም የለም፡፡

አካል ጉዳተኞች 50 በላይ ይሆናሉ፡፡ እናቶች መንቀሳቀስ ስለማይችሉ ቤት ውስጥ ነው ያሉት፡፡ የሚያሰሩት ሰዎችን 600 ብር ቀጥረው ነው፡፡ መስራት ስላማችሉ፡፡ ከታሰረው እንዱ ራሱ ወጥ ተደፍቶበት እግሩ ተቃጥሏል፡፡

እንጨት ከጫካ ተሸክመን አምጥተን ፈልጠን በዬኩሽናው እናደርስ ነበር። እንደዚህ ደክሞን ውለን የምንታጠብበት ሳሙና አልነበረንም። ችግር ከትክሻችን አልወርድ አለ። 

ለሌሎች ደመወዝ ሲጨመር የኛስ ድካም ለምን አይታይም? ልጆች እናስተምራለን፣ የቤት ኪራይ አለብን። 'ደመወዝ ተጨምሯል' ሲባልም የቤት ኪራይ ተጨምሮብን 'ቅድሚያ ካልከፈላችሁ ውጡ’ እየተባልን ነው፤ ተጨንቀናል ” ሲሉ ቅሬታ አቅራቢዎች አማረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ የሠራተኞችን ቅሬታ ይዞ ፤ ሰዎቹ የመብት ጥያቄ ስላነሱ ለምን ታሰሩ ? ይህን ማድረግ አግባብ ነው ? ሲል የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮን ጠይቋል።

አንድ የቢሮው አካል በሰጡት ምላሽ፣ የደመወዝ ጭማሬና ቋሚ ሰራተኛ መሆንን በተመለከተ ዩኒቨርሲቲው የራሱ መተዳደሪያ ደንብ እንዳለው፣ ጭማሬው ለቋሚ ሠራተኞች እንጅ ለጊዜያዊ እንደማይሆን ገልጸዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ ለሰዎቹ ደመወዝ የመጨመርና ቋሚ ሠራተኛ ማድረግን የሚመለከተው ዩኒቨርሲቲው ሆኖ እያለ፣ ሠራተኞቹ የመብት ጥያቄ በማቅረባቸው መታሰታቸው አግባብ ነው ? ሲል ለእኝሁ አካል በድጋሚ ጥያቄ አቅርቧል፡፡

እሳቸው በምላሻቸው፣ ከክልል ይታሰሩ እንዳልተባለ ገልጸው፣ " አንተ እንዳልከው እኛ ደመወዝ ይጨመርላቸው፤ አይጨመርላቸው የመተዳደሪያ ደንብ ስላላቸው እነርሱ ናቸው የሚያስተካክሉት " ብለዋል፡፡

" ቢጨምሩላቸው እኛም ደስ ይለናል፡፡ እየለፉ እስከሆነ ድረስ ቢጨመርላቸው ደስ ይለናል፡፡ ግን እነዚህ ሰዎች ታስረዋል ? ማነው ያሰራቸው ? የሚለውን ለመጠየቅ እየሞከርኩኝ ነው፡፡ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ናቸው፡፡ ሲወጡ እንዴት ታሰሩ ? የሚለውን አጣራለሁ " ብለዋል፡፡

በተጨማሪም፣ ሠራተኞችን ለምን እንደታሰሩ ማብራሪያ  የጠየቅናቸው የሲዳማ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ካሳ ጩቦ በሰጡን ቃል፣ " የማውቀው ነገር የለም " የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።
 
(የክልሉ ፓሊስና ጸጥታ ቢሮ ተጨማሪ አጥጋቢ ምላሽ  ከሰጡን የምናቀርብ ሲሆን፣ ጉዳዩንም እስከ ጥግ እንከታተለዋልን)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

አቢሲንያ ባንክ

4ኛ ዙር እችላለሁ!  ማርች 8 እየደረሰ ነው ! ዝግጁ !    
                                                                                                                                                                                               
         የሴቶች የሥራ ፈጠራ፣ የሙዚቃና የቲክቶክ ቪዲዮ ውድድር !

ባንካችን በየአመቱ የሚከበረውን ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 ምክንያት በማድረግ እ.አ.አ ከማርች 3 ቀን እስከ ማርች 31 ቀን 2025 ድረስ በሁለት የተከፈሉ ውድድሮችን አዘጋጅቶ ለተሳታፊዎች ክፍት አድርጓል፡፡

1) የሙዚቃ ተሰጥዖ ውድድር
ባንካችን የሙዚቃ ተሰጥኦ ያላቸውን ሴት ተሳታፊዎችን በማወዳደር በባለሙያና በማህበራዊ ሚዲያ በሚሰጥ የህዝብ ድምጽ የተለዩ አሸናፊዎችን በየደረጃው ይሸልማል፡፡ አንደኛ ለምትወጣው የብር 100,000፣ ሁለተኛ ለምትወጣው የብር 75,000 እንዲሁም ሶስተኛ ለምትወጣው የብር 50,000 ሽልማት አዘጋጅቷል።
በሙዚቃው ዘርፍ ተሰጥኦዬን ያሳያል የምትሉትን ከሶስት (3) ደቂቃ ያልበለጠ የሙዚቃ ሥራ ያለ ሙዚቃ መሣሪያና የድምፅ ማዳመጫ (Earphone) ሳይደረግ በቪዲዮ ሰርታችሁ ከዚህ በታች በተቀመጠው ቴሌግራም መላክ ይኖርባችኋል፡፡ የቴሌግራም አድራሻ------------ 0919857373

2) የቲክቶክ ቪዲዮ ተሰጥዖ ውድድር
እንዲሁም በተመረጡ ቲክቶከሮች መካከል ባንካችን ለሴት ደንበኞቻችን ያዘጋጃቸውን አደይና ዘሃራ የቁጠባ ሂሳቦችን በተለየ መንገድ የማስተዋወቅ ውድድር ይካሄዳል፡፡በዚህም ውድድር አንደኛ ለምትወጣው የብር 100,000፣ ሁለተኛ ለምትወጣው የብር 75,000 እንዲሁም ሶስተኛ ለምትወጣው የብር 50,000 ሽልማት አዘጋጅቷል።

3) የሥራ ፈጠራ ውድድር
የሴት ሥራ ፈጣሪዎችን ለማበረታት ባንኩ ባሉት ዲስትሪክቶች የሥራ ፈጣሪ ሴቶችን በመምረጥ በአነስተኛ የወለድ ምጣኔን ካለመያዣ እስከ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) የብድር አገልግሎት ለመስጠት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ፍላጎቱ ያላችሁና መስፈርቶችን የምታሟሉ የሥራ ፈጣሪዎች አቅራቢያችሁ ባሉ ቅርንጫፎችና የዲስትሪክት ፅ/ቤቶች በመቅረብ ከየካቲት 19 ቀን እስከ መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓም. ባሉት ቀናት ብቻ በፁሑፍ ጥያቄያችሁን እንድታቀርቡ በአክብሮት እንጠይቃለን።

በዚህም መሠረት በመርሃ-ግብሩ መሳተፍ የምትፈልጉ ሴት ተወዳዳሪዎች አስቀድማችሁ የአቢሲንያ ባንክ የፌስቡክ ገፅን https://www.facebook.com/BoAeth/ መወዳጀት ይኖርባችኋል፡፡
ዝርዝር የብድር እንዲሁም የመወዳደሪያ መስፈርቶችን ለመመልከት ከታች የሚገኘውን የቴሌግራም ሊንክ መጠቀም የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ /channel/BoAEth

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#USA

" ቀጣዩ የግብር ቅነሳ ነው ፤ ከገቢ ግብር፣ ከቲፕ ገንዘብ እና ከትርፍ ሰዓት ክፍያ ላይ ግብር አነሳለሁ " - ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ትላንት ምሽት በአሜሪካ የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገው ነበር።

በዚህም ንግግራቸው " አሜሪካ ተመልሳለች " ያሉ ሲሆን የሪፐብሊካን ሕግ አውጪዎች " ዩ ኤስ ኤ" በሚል ዝማሬ አጅበዋቸዋል።

ትረምፕ ንግግራቸውን ከጀመሩ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ በምክር ቤቱ አዳራሽ ከተሰበሰቡ ሰዎች በተሰማ የስላቅ ድምፅ ንግግራቸው ተስተጓጎሎ ነበር።

የተወካዮች ምክርቤቱ አፈ-ጉባኤ ማይክ ጆንሰን የምክርቤቱ ሥነ ስርዐት አስከባሪዎች፣ በቴክሳስ ዲሞክራት ፓርቲን ወክለው ለምክርቤት አባልነት የተመረጡትን አል ግሪን ከምክርቤቱ እንዲያስወጧቸው አዘዋል።  ሌሎች የምክር ቤቱ አባላትም ሥነ-ስርዐት እንዲከተሉ አሳስበዋል።

ግሪን ከምክርቤቱ አዳራሽ ከወጡ በኋላ ትረምፕ ንግግራቸውን ቀጥለዋል።

ትረምፕ በዚሁ ንግግራቸው " የመጀመሪያው ወር የፕሬዝደንትነት ዘመኔ፣ በሀገራችን ታሪክ እጅግ ስኬታማው መሆኑን ብዙዎች ገልጸውታል " ብለዋል።

ገና በጥቂት ሳምንታት አሳካው ያሏቸውን ስኬቶች አብራርተዋል።

ከነዚህ አንዱ በህገወጥ ስደተኞች ላይ የወሰዱትን እምርጃ ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም የፌደራል ቅጥር ሂደቶች እና የውጭ ርዳታዎች ላይ እግድ መጣላቸውን ገልጸዋል።

የፌደራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ቁጥር እና ሠራተኞችን ለመቀነስ፣ በምፅሃረ ቃሉ 'ዶጅ' በመባል የሚጠራ በኢላን መስክ የሚመራ ተቋም መመስረታቸውን የተናገሩት ትረምፕ በቢሊየኖች የሚቆጠር የመንግሥት ገንዘብ እያዳነ መሆኑንም አመልክተዋል።

ትረምፕ በንግግራቸው በ48 ዓመት ውስጥ ያልታየውን የዋጋ ግሽበት ለማስተካከል ከወሰዷቸው ርምጃዎች መካከል " ወርቃማ ፈሳሽ " ሲሉ የጠሩትን የነዳጅ ጋዝ ቁፋሮ እያካሄዱ መሆኑን ተናግረዋል።

" የወሳኝ እና ብርቅዬ ማዕድናት ምርት ይፋጠናል " ሲሉም ገልጸዋል።

" ቀጣዩ የግብር ቅነሳ ነው " ያሉት ትራምፕ፣ ከገቢ ግብር፣ ከቲፕ ገንዘብ እና ከትርፍ ሰዓት ክፍያ ላይ ግብር እንደሚያነሱ ተናግረዋል።

ትረምፕ ከዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮለድሚር ዜለንስኪ ጋራ ያደረጉትን ኃይለቃል የተሞላበት ውይይት ተከትሎ አሜሪካ ለዩክሬን የምትሰጠውን ወታደራዊ ርዳታ አቋርጣለች።

" አውሮፓውያን ዩክሬንን ከመደገፍ ይልቅ ከሩስያ ለሚገዙት ነዳጅ እና ዘይት የበለጠ አውጥተዋል " ያሉት ትራምፕ የዩክሬን ፕሬዝደንት ለሰላም ዝግጁ መሆናቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ እንደፃፉላቸው አመልክተዋል።

ትረምፕ አክለው " በተመሳሳይ ጊዜ ከሩሲያ ጋራ ጠንከር ያለ ውይይት አድርገን ለሰላም ዝግጁ መኾናቸውን የሚያሳይ ምልክቶች አግኝተናል " ብለዋል።

መረጃው የቪኦኤ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የኢትዮጵያውያን አንድነት ዳግም የታየበት የካራማራ ድል !


የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ/ም የሱማሊያን ዚያድባሬ ጦር ለመመከት በካራማራ ጀግኖች የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የህይወት መሰዋዕትነት ከፍለው ወራሪውን ጦር ከሀገር ያባረሩበት እና የሀገራቸውን ሰንደቅ ያውለበለቡበት ቀን ነው።

በሶቪየት ህብረት ከፍተኛ የሆነ ድጋፍ የመጣው የዚአድባሪ ጦር የእናት ሀገር ጥሪ እያለ በተሰበሰበው የኢትዮጵያ ጦረኛ "  ካራማራ " ላይ ድባቅ ተመትቶ ወደ መጣበት ተመልሷል።

በጦርነቱ መጀመሪያ ሶቪየት ህብረት ሶማሊያን ስትደግፍ ነበር በኃላ ላይ ወደ ኢትዮጵያ አዘንብላ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ እገዛ አድርጋለች ፤ ከኢትዮጵያ ጋር ጥሩ ግንኙነት የነበራት አሜሪካ ደግሞ ወደ ሶማሊያ ፊቷን አዙራ ነበር።

በጦርነቱ ኩባ፣ ሰሜን ኮሪያ፣ የመን እና ምሥራቅ ጀርመንን ጨምሮ ሌሎች አገራት አጋርነታቸውን ለኢትዮጵያ አሳይተዋል።

ከ16,000 በላይ የኩባ ወታደሮች በውጊያው እንደተሳተፉ መዛግብት ያሳያሉ። ደቡብ የመንም ጦሯን
#ለኢትዮጵያ አሰልፋ ነበር።

በተለያየ የፖለቲካ የትግል ሁኔታ፣ በተለያየ ቅራኔ ውስጥ የነበሩ የኢትዮጵያ ሀይሎች ሁሉ ስለ ሀገር አንድ ሆነው የዚያድባሬን ጦር የመከቱበት የካራማራ ጦርነት የኢትዮጵያ አንድነት ዳግም በጉልህ የታየበት ስለመሆኑ ይነገርለታል፡፡

በየአመቱ የካቲት 26 ቀን የሚታሰበው የ " ካራማራ ድል " ዘንድሮም ለ47ኛ ጊዜ እየታሰበ ይገኛል፡፡

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ከቢሊ ግራሀም ኢቫንጀልስቲክ አሶሴሽን ጋር በጋራ በመሆን ያዘጋጀው ፤ " መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ " የተሰኘው መረሃ ግብር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እየተካሄደ ይገኛል።

#EvangelicalMediaCouncil

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#MPESAEthiopia

ከUAE ገንዘብ በM-PESA እንቀበል 10% ስጦታ እና 1 ጊ.ባ ኢንተርኔት ተጨማሪ አሁኑኑ እናግኝ! ቪዛ ፣ ማስተርካርድ ወይም አሜክስ ካርድ በመጠቀም በካሽ ጎን በኩል እንላክ።

በምንዛሬ ተመን
1 AED = 34.5 ብር

ካሽ ጎን ይህንን ሊንክ ተጠቅመን ማውረድ እንችላለን፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bankofabyssinia.cashgo

ገንዘቦን በዳሽን ባንክ እለታዊ ምንዛሬ ያግኙ + 10%ስጦታ ።

#MPESASafaricom

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#እንድታውቁት

ነገ ቅዳሜ እና እሁድ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ።


የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ከቢሊግርሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን ጋር በመተባበር የካቲት 29 እና 30 ቀን 2017 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ የሚያደረገው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት መርሀ ግብር ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ የሚዘጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሠረት በሁለቱም ቀናት ከቀኑ 5:00 ሠዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስኪጠናቀቅ ድረስ፦

➡️ ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)
➡️ ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት (ጥላሁን አደባባይ ላይ)
➡️ ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ (ለገሃር መብራት)
➡️ ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድየም (ቴሌ ማቋረጫ ላይ)
➡️ ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ (ሀራምቤ መብራት ላይ )
➡️ ከብሔራዊ ቤተ መንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ (ብሔራዊ ቤተመንግሥት ላይ)
➡️ ከቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ወደ መስቀል (ባምቢስ መቅረዝ ሆስፒታል መታጠፊያ) ላይ የሚዘጋ መሆኑ ተገልጿል።

አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ አሳስቧል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ ! "

ነገ ቅዳሜ እና ከነገ በስቲያ እሁድ ከቀኑ 7 ሠዓት ጀምሮ በመስቀል ዐደባባይ " መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ " በሚል መሪ ሐሳብ የጀማ ወንጌል ስብከት እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡

መርሐ-ግብሩን ያዘጋጁት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ከቢሊ ግራሃም የወንጌል ማኅበር ጋር በመተባበር ነው፡፡

የቢሊ ግራሃም የወንጌል ማኅበር ፕሬዚዳንትና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቄስ ፍራንክሊን ግራሃም መርሐ-ግብሩን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ " ውብና ጠንካራ ሀገር ወደ ሆነችው ኢትዮጵያ በመምጣቴ ደስ ብሎኛል " ብለዋል።

መርሐ-ግብሩ የጸሎት፣ የወንጌል ስብከት እና የዝማሬ ፕሮግራምን ያካተተ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ፀሐፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ በበኩላቸው፤ እንደ ሀገር ፈጣሪን የምናዳምጥበት፣ ስለ ኢትዮጵያና በምድሪቷ ስለሚኖሩ ሰዎች የምንፀልይበት ጊዜ ነው ብለዋል፡፡

ቢሊ ግራሃም የወንጌል ማኅበር በ1952 ዓ.ም በወንጌላዊ ቢሊ ግራሃም በአዲስ አበባ የወንጌል ስብከት ያከናወኑ ሲሆን፤ በንጉሡ ቤተ-መንግስት ተጋብዘው በዐጼ ኃይለ ሥላሴ ሽልማት ተበርክቶላቸው ነበር።

ልጃቸው ፍራንክሊን በ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል ዐደባባይ የሚያከናወኑት የጀማ ወንጌል ስብከት አባታቸው ወንጌልን ከሰበኩ ከ65 ዓመታት በኋላ መሆኑ ተጠቁሟል።


ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኤፍ ኤም ሲ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ሕብረት ባንክ እንኳን ለ1446 ዓ.ሒ የሐጅ ጉዞ በሰላም አደረሳችሁ እያለ፤ የሐጅ ጉዞ ክፍያዎን በአቅራቢያዎ በሚገኙ ቅርንጫፎቻችን በልዩ መስተንግዶ እንዲፈጽሙ በአክብሮት ይጋብዛል፡፡

በዚህ አጋጣሚ የሸሪዓውን መርህ መሰረት ያደረገ  ሕብር ሀቅ የተሰኘ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎታችን ተጠቃሚ ይሁኑ፡፡

ሐጀን መብሩር!

ሕብር ሀቅ
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update #HealthAlert

" የሟቾች ቀጥር ከ30 በልጧል " - ዞን ጤና መምሪያ

በጋምቤላ ክልል በኑዌር ዞን በተከሠተው የኮሌራ ወረርሽኝ፣ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ30 በላይ እንደደረሰ የዞኑ ጤና መምሪያ ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጠው ቃል አሳውቋል።

በዞኑ ከ1 ሺሕ በላይ የሚደርሱ ሰዎች በበሽታው መታመማቸው ተመላክቷል።

የኑዌር ዞን ጤና መምሪያ ሓላፊ አቶ ጋትቤል ግርማ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፤ ወረርሽኙ ቀድሞ የተከሠተባቸው ዋንታዎ እና አኮቦ ወረዳዎች፣ አሁንም ስርጭቱ ከፍተኛ እንደሆነ ጠቅሰው፣ መድኃኒትም በበቂ ሁኔታ አልቀረበም ብለዋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ በምን ክሶች ጥፋተኛ ተባሉ ?

ከ1 ዓመት በላይ ማረሚያ ቤት ሆነዉ ጉዳያቸውን እየተከታተሉ የሚገኙት የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ፀጋዬ ቱኬ በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀረቡባቸው ሁለት ክሶች ጥፋተኛ ተብለዋል።

አቶ ጸጋዬ ፕሮጀክቶችን " በህገ ወጥ አግባብ መርተዋል " በሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።

" የህዝብ እና የመንግስት ሀብት ጉዳት እንዲደርስ በማድረግ " እና " ስልጣንን ያለአግባብ በመገልገል " በሚል ዐቃቤ ህግ በአቶ ጸጋዬ ላይ የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦባቸው ነበር። 

በዚህ ክስ ቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ በፍርድ ቤት " ጥፋተኛ " ተብለዋል።

አቶ ጸጋዬ በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ የተባሉበት ሌላው ጉዳይ በመንግስት የመኖሪያ ቤት ተሰጥቷቸው እያለ ከስልጣን እስከተነሱበት ጊዜ ድረስ " የቤት ኪራይ ገንዘብ ይቀበሉ ነበር " የሚለው ነው። 

የቀድሞው ከንቲባ ለቤት ኪራይ በወር 10 ሺህ ብር በድምሩ 260 ሺህ ብር " ያልተገባ ጥቅም አግኝተዋል " በሚል በዐቃቤ ህግ የቀረበባቸውን ክስ የመረመረው ፍርድ ቤቱ፤ አቶ ጸጋዬን " ጥፋተኛ ናቸው " ብሏል።

የሀዋሳ ከተማ ፍርድ ቤት በትላንቱ ውሎው፤ አቶ ጸጋዬ ላይ ከቀረቡ ሶስት ክሶች በአንደኛው " ነጻ መሆናቸውን " ውሳኔ አስተላልፏል።

የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ በአቃቤ ህግ የቅጣት ማክበጃ እንዲሁም የሚቀርብ የቅጣት ማቅለያን ለመስማት ለረቡዕ መጋቢት 3/ 2017 ተለዋጭ ቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል። 

አቶ ፀጋዬ ቱኬ ፤ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሀዋሳ ማዕከል ቀርቦባቸው ከነበሩ ሁለት ሌሎች ክሶች " ነጻ ናቸው " መባላቸው ይታወሳል። 

ያንብቡ :
https://telegra.ph/Ethiopia-Insider-03-06

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገጽ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በስም ከተለዩት ግለሰቦች መካከል ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ዜጎችም ይገኙበታል " -የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ የታክስ ዕዳ ያለባቸው 62 ግብር ከፋዮች ከሀገር እንዳይወጡ የእግድ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ገልጿል፡፡

እግድ የተጣለባቸው 62 ግለሰቦች በተደጋጋሚ ጥሪ ቢደረግላቸውም ዕዳቸውን ለመክፈል  ፈቃደኛ ያልሆኑ ናቸው ተብሏል።

" በስም ከተለዩት ግለሰቦች መካከል ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ዜጎችም ይገኙበታል ዕዳቸውን የማይከፍሉ ከሆነም አዋጁ በሰጠን ሥልጣን መሰረትም በቀጣይ የንብረት እግድ እና ንብረታቸውን በሃራጅ የመሸጥ እርምጃዎች ይወሰዳሉ " ሲሉ የቢሮው የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቢሮው በታክስ አስተዳደር አዋጅ 983/2008 አንቀፅ 44 ንዑስ አንቀፅ ከ1-3 ለተቋሙ በተሰጠ ስልጣን መሰረት ከሀገር እንዳይወጡ እግድ የተጣለባቸው ግለሰቦች ስም ዝርዝር ለፌዴራል የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ማስተላለፉን አሳውቋል፡፡

የ62ቱ ግለሰቦች ስም ዝርዝር ለፌዴራል የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተላከው በትላንትናው ዕለት ነው።

አቶ ሰውነት " በህጉ መሰረት የተቀመጠ ቀነ ገደብ አለ በአዋጁ በተቀመጠው ቀነ ገደብ መሰረት መጥተው እስካልከፈሉ ድረስ ለእዳው ማካካሻ በሚሆን መሰረት ንብረታቸው በሃራጅ ተሽጦ እዳው ይሸፈናል " ብለዋል።

ቢሮው የግብር ዕዳቸውን ሳይወጡ የሚሰወሩ ግብር ከፋዮችን በመከታተል ግዴታቸውን እንዲወጡ ለማስቻል የዕዳ ክትትልና አስተዳደር የስራ ክፍልን በ2017 በጀት ዓመት እንደ አዲስ አዋቅሯል።

በዚህም መሰረት ባለፉት 6 ወራት ከ 6.4 ቢሊዮን ብር በላይ የታክስ እዳ መሰብሰቡን አቶ ሰውነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#SafaricomEthiopia

ቀን ተቆርጧል አንዳትቀሪ !
መጋቢት 7 ለአንደኝነት እና ደስታ ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5Km ሩጫ አዘጋጅቷል፣ ቲሸርትሽን በM-PESA ግዢ! እንጠብቅሻለን ፣ እንዳትቀሪ!

ከM-PESA ጋር አብረን አንፍጠን!
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

#SafaricomEthiopia #Andegna #1Wedefit #FurtherAheadTogether

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

🔹 "እጆች ይናገራሉ፣ አይኖች ያዳምጣሉ" - መስማት ለተሳናቸው ታዳጊ ሴቶች ድምጽ ነን! 🔹

ይህ መልዕክት ለዓመታት መስማት ለተሳናቸው ዜጎችን ለመደገፍ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ ጉልህ ድርሻ ያለው ነው። 🌍✨

ሩትስ ኤንደ ዊንግስ ከማላላ ፈንድ ባገኘው ድጋፍ፣ መስማት የተሳናቸው ታዳጊ ሴቶችን ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኙ፣ መብታቸው እንዲጠበቅ እና እኩል እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየሰራ ይገኛል።

📢 ለኅብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫዎችን መስራት፤
✊ ለአካታች ሥርዓት መታገል፤
📚 ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኙ ማገዝ ላይ እየሰራን እንገኛለን።

ቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል የምልክት ቋንቋ  እንደ ሌሎች ቋንቋዎች እኩል መደመጥ የሚችል ቋንቋ መሆኑንና የዚህ ቋንቋ ተናጋሪ ታዳጊ ሴቶች እንደ ሌሎች እኩዮቻቸው ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኙ ያግዙን! 

ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 /channel/RWethiopia 

#HandsSpeakEyesListen #DeafGirlsMatter 

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተቋቋሙበትን ዓላማ እንዲያስፈፅሙ አሳሰበ።

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፥ * የኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተቋቋሙበትን ዋና ዓላማ መዘንጋት የለባቸውም " ሲሉ አሳሰቡ።

ሚኒስትሩ ይህን ማሳሰኒያ የሰጡት ዛሬ ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ ማሕበረሰብ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ነው።

" ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ችግር ፈቺ ሥራዎችን መሥራት ይጠበቅባቸዋል " ያሉት ፕ/ር ብርሃኑ ፥ ተቋማቱ በአካባቢ ሳይታጠሩ ለተመሠረቱበት ዓላማ መኖር አለባቸውም ብለዋል፡፡

- የሙስና መንሰራፋት፣
- ግብረ-ገብነት ማጣት
- ዕውቀት የመቀያየር ባሕል በምሁራን ዘንድ መቀዛቀዙን አንስተዋል

እነዚህ ችግሮች ከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት የዕውቀት ማዕከል እንዳይሆኑ አድርገዋል ብለዋል።

" ሀገራችን በዘርፈ-ብዙ ችግሮች ውስጥ በመሆኗ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን የመፍትሔ ሐሳብ ማመንጨት ይጠበቅባቸዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ዩኒቨርሲቲዎች የዕውቀት እና የእውነት ማዕከል እንዲሆኑየሪፎርም ሥራ እየተከናወነ ነው " ሲሉም አመልክተዋል።

ተቋማቱ፤ ጥራት ባለው ትምሕርት ትውልድን መቅረጽ እና የማሕበረሰቡን ችግሮች መቅረፍ የሚያስችሉ ምርምሮችን በማድረግ ሀገራዊ ግዴታቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸውም በአጽንኦት አሳስበዋል።

Credit -
#FMC

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#SafaricomEthiopia

🎁 ስድስት ወር ሙሉ ዳታ እንደልብ! ለረጅም ጊዜ የሚቆዩትን ሜጋ የኢንተርኔት ጥቅሎች በM-PESA በመግዛት እስከ 1,000 ብር የሚደርስ ቅናሽ አግኝተን ሶሻል ሚዲያዉን ፏ ፏ እናድርግ! 🌐🤳 ከሳፋሪኮም አስተማማኝ ኔትወርክ ጋር ወደፊት!⚡️

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

#MPESASafaricom #1Wedefit
#Furtheraheadtogether

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#AddisAbaba

በተደመሰሰ፣ በታጠፈ እና በማይታይ የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ቁጥር ሲገለገሉ የተገኙ ከ1,000 በላይ አሽከርከሪዎችን ቀጥቻለሁ ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለጸ።

ቁጥራቸው ቀላል የማይባል አሽከርካሪዎች የተቀባ፣ የታጠፈ ፣ የተፋፋቀ፣ የተቆራረጠ እና በአጠቃላይ ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳን በመጠቀም ደምብ ሲተላለፉ ቆይተዋል ሲል ፖሊስ አስታውሷል፡፡

አንዳንዶቹ እንደውም ወንጀል ሲፈፅሙ ተገኝተው ምርመራ እየተጣራባቸው ነው ብሏል፡፡

ከየካቲት 16 እስከ የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም በተደረገ  ቁጥጥር  1,587 ተሽከርካሪዎች  ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳን ለጥፈው ተገኝተዋል ተብሏል፡፡

የተፋፋቀ፣ የደበዘዘ፣ የታጠፈ እና የማይታይ የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ቁጥር መጠቀም፣ ከሰሌዳ መብራት ውጪ ሌሎች ዓይነቶችን አብረቅራቂ መብራቶችን መጠቀም፣ ሰሌዳውን በማይታይ ቦታ መለጠፍ እና ሆን ብለው ሰሌዳን አጥፎ መንቀሳቀስ በቁጥጥሩ ወቅት የተገኙ ጥፋቶች ናቸው ሲል ፖሊስ አስረድቷል፡፡

በጥፋት ውስጥ ከተገኙት ውስጥ ኮድ-1 ወይም ታክሲ 216፣ ኮድ-2 ወይም የቤት መኪና 320፣ ኮድ-3 የሆኑ 1,037 እና ሌሎች ተሽከርካሪዎች 14 መሆናቸውን በአዲስ አበባ ፖሊስ የትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ ጠቅሷል፡፡

ቁጥጥር ከተደረገባቸው መካከል  አብዛኛዎቹ  የፊት ወይም የኋላ ሰሌዳ ሳይኖራቸው የተገኙ  ናቸው፡፡  ቀሪዎቹ 633ቱ ደግሞ  የተቆረጠ ወይም ለዕይታ ግልጽ ያልሆነ ሰሌዳ ሲጠቀሙ የተገኙና ሰሌዳውን በማይታይ ቦታ ያሰሩ፣ የተሸፈኑና የተለያየ ቀለም የተቀቡ ሰሌዳዎች መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡

#AddisAbabaPolice #ShegerFM

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#የሠራተኞችድምጽ🔈

🔴 “ የምናደርገው አጥተን ነው ተማረን በእንባ የወጣነው። 3 ልጆች አሉኝ  በ1,000 ብር ደመወዝ ነው የምተዳደረው፤ አሁን የት እንውደቅ ? ” - የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች

➡️ “ ፕሬዚዳንቱ ተስፋ አስቆረጠን። 'እናንተን ዩንቨርሲቲው እንጂ የቀጠራችሁ የመንግስት ሰራተኞች አይደላችሁም' አለን ” - የ1,100 ብር ደሞዝተኛ

እስከ 20 ዓመታት ' አገለገልን ' ያሉ ከ800 በላይ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምገባና የሌሎች ሠራተኞች " ዩኒቨርሲቲው ከሥራ ሊያሰናብተን ነው " ሲሉ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ስሞታ አሰሙ።

ሠራተኞቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል በዝርዝር ምን አሉ ?

አንድ አባት ፥ “ ከ2004 ዓ/ም ጀምሮ ከከተማው ተደራጅቼ በመስተንግዶና ሁለገብ ሥራ ግቢው እንደፈለገ ነው የምሰራው። የአባቶች እግራቸው ተሰብሯል፤ ጥርሳቸው ወልቋል፤ እጃቸው በእሳት ተቃጥሏል ” ብለዋል።

“ የዩኒቨርሲቲ ዋናው ፕሬዚዳንት ‘መንግስት መዋቅር እያስተካከለ ነው። ይህ ሂደት ካለቀ በኋላ ማኀበራትን ሁሉ ያሰናብታል። መንግስት ከዚህ ግቢ አያውቃችሁም’ ብሏል። እንደ አሮጌ እቃ ቆጥረውናልና መፍትሄ የሚሰጠን የህግ አካል መጥቶ ይመልከተን ” ሲሉም ተማጽነዋል።

ልላኛው አባት፣ “ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከ16 ዓመታት በላይ ከባልደረቦቻችን ጋር እንጨት እየፈለጥን እየተሸከምን ብዙ የሥራ ጫና ነበረብን ” ሲሉ ገልጸዋል።

“ ወድቄ ከተሰበርኩ ከአንድ ዓመት በላይ ሆኖኛል፤ ነገር ግን ህክምና አላገኘሁም። ሦስት ልጆች አሉኝ በ1000 ብር ደመወዝ ነው የምንተዳደረው። አሁን የት እንውደቅ ? የት እንግባ ? ” ሲሉም ጠይቀዋል።

ሌላኛው ቅሬታ አቅራቢም፣ “ 9 ቤተሰብ የቤት ኪራይ እየከፈልኩ አስተዳድራለሁ። እኔ ራሴ መማር እፈልጋለሁ። ግን በገንዘብ ማነስ ምክንያት አልቻልኩም። 1,100 ብር ነው የሚከፈለኝ። ይቺን 1100 ብር ታዲያ ወስጄ ምንድን ነው የማደርጋት ? ” ሲሉ ጠይቀዋል።

ሌላኛዋ እናት፣ “ ለፍተን እየሰራን ቆይተን አሁን ሁለት ፀጉር አብቅለን በሽተኛ ከሆንን በኋላ ጅብ ይብላችሁ ጎዳና ውጡ ተብለናል።  አራት፣ አምስት ወራት የቆዩትን ቋሚ አድርጎ 20 ዓመት በላይ ቆይታ እያለን ምንም አንዳልጠቀምን ተደርገናል ” ብለዋል።

“ 7 ልጆች አሉኝ ደመወዜ 1000 ብር ነች ከሌሎቹ እኩል አድርጉን እኛም ኢትዮጵያዊ ነን፤ አዋጁ ይመለከተናል፤ ይጨምርልን ስላልን ነው ‘ውጡ’ የተባልነው አንዲያውም አረጋውያን ይደገፉ እንጂ ይጣሉ አይባልም ነበር ” ሲሉም ወቅሰዋል።

ሌላኛዋ ቅሬታ አቅራቢ፣ “ 17 ዓመት ከጅብ ጋር እየተጋፋን እንደ ሻማ ቀልጠን አገልግለናል። ደመወዝ ጭማሪ ስንጠይቅ ‘እንዲያውም እስካሁን አገልግላችኋል አንፈልጋችሁም’ ተባልን ” የሚል ወቀሳ አቅርበዋል።

አክለው፣ “ እኔስ ቆሜ በሚዲያ ተናገርሁ ስንቱ ነው እግሩ የተቀደደው! ስንቱ ነው ሰባራ ሆኖ በየቤቱ ያለው። ቋሚ ሰራተኛ አድርጉን አላልንም ደመወዝ ይጨመርልን ነው የኛ ጥያቄ ” ነው ያሉት።

ሌላኛዋ እናት፣ “ ሙሉ 30 ቀናት ነው አፈር ግጠን የምንሰራው። ስንቀጠር 330 ብር ነበር ትንሽ፣ ትንሽ እየተጨመረልን 1100 ደረሰ። በኋላ ይጨመረናል ብለን ስንጠብቅ አዲሱ ፕሬዚዳንት ጭራሽ ተስፋ አስቆረጠን። ‘እናንተን ዩንቨርስቲው ነው እንጂ የቀጠራችሁ የመንግስት ሠራተኞች አይደላችሁም’ አለን ” ሲሉ ገልጸዋል።

“ ዩኒቨርስቲው ትንሽ፣ ትንሽ እየጨመረ ቆይቷል፤ አሁንስ ለምን አይጨምርም? ኑሮ ውድነቱ በኛስ አልጨመረም ወይ? ብለን ስንጠይቅ፥ ‘እናንተን አናወቃችሁም። እንዲያውም ተንሳፋፊ ሰራተኛ ተመድቦ ይሰራል። እናንተን እናስወጣለን ብዙ ስላገለገላችሁ ይበቃችኋል’ አለን ” ብለዋል።

አክለው፣ “ የምናደርገው አጥተን ነው ተማረን በእንባ የወጣነው ” ያሉ ሲሆን፣ ልላኛው አባትም፣ “ ከ2002 ጀምሬ ነው ዩኒቨርሲቲ ላይ በመስተንግዶ የሰራሁት። በሳምንት፤ በሁለት ሳምንታት ህክምና ለልዩ ልዩ ነገሮች ይኖራሉ። ሁሉን ትተን እየሰራን ቆይተናል ” ብለዋል።

“ ልጆች እናስተምራለን፤ የቤት ኪራይ አንከፍላለን በወር 1,100 በቀን 33 ብር እየተከፈለው በዚህ ኑሮ ውድነት ሰው እንዴት ይኖራል? ብለን ጥያቄ ስናቀርብ ‘በኔ በኩል ጨርሻለሁ ወደ ሚመለከተው ሂዱ የምታመጡት ነገር የለም’ ነው ያለን ፕሬዝዳንቱ ” ሲሉም አማረዋል። 

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቅሬታው ምላሽ ለመጠየቅ ወደ ዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንትና ምክትል ፕሬዜዳንት ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም ለጊዜው ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።

(ጥረቱ ይቀጥላል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ ወንዝ ላይ የጣለ ግለሰብ 500 ሺህ ብር ይቀጣል " - የወንዞች ዳርቻ ልማትና ብክለት መከላከል ደንብ

በአዲስ አበባ ወደ ተግባር የገባው የወንዞች ዳርቻ ልማትና ብክለት መከላከል ደንብን መተላለፍ የሚያስከትለው ቅጣት ስንት ነው ?

➡️ በባህሪው አደጋኝነት የሆነ ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ በወንዝ ዳርቻ ያሰወገደ ድርጅት አንድ ሚሊዮን ብር ይቀጣል።

➡️ ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ ወንዝ ላይ የጣለ ግለሰብ 500 ሺህ ብር ይቀጣል።

➡️ ፍቃድ የወሰዱም ሆነ ሳይወስዱ ፍሳሽን ቀጥታ በወንዞች ዳርቻ ሲያስወግዱ ቢገኙ 100 ሺህ ብር  ይቀጣሉ።

➡️ በወንዝ ዳርቻና አካባቢ መጸዳዳት ሁለት ሺህ ብር ያስቀጣል።

➡️ የፈሳሽ ማጣሪያ ሳይኖር በወንዝ ዳርቻና አካባቢ ተሽከርካሪ ማጠብ 400 ሺህ ብር ያስቀጣል።

➡️ እንስሳትን ማሰማራት፣ ማስገባት ከተፈቀደው ውጪ ተሽከርካሪ ማሽከርከር 30 ሺህ ብር ያስቀጣል።

➡️ ለመዝናኛ፣ ለመናፈሻና ለፖርክ ከተፈቀደ ውጪ ግንባታ መገንባት 200 ሺህ ብር ያስቀጣል።

➡️ ከአምራችና አገልግሎት ሰጪ  ተቋማት ማንኛውም ያልታከመ ቆሻሻ መልቀቅ 300 ሺህ ብር ያስቀጣል።

➡️ ኬሚካል ነክ ቆሻሻዎችን የማከሚያ ዘዴ ሳይጠቀም የለቀቀ ግለሰብ 50 ሺህ፤ ድርጅት 300 ሺህ ብር ይቀጣሉ።

➡️ ማንኛውም በካይ ቆሻሻ ከተፈቀደ የፈሳሽ ማጠራቀሚያ ውጪ ያፈሰስ ግለስብ 50 ሺህ ፤ ድርጅት 400 ሺህ ብር ይቀጣል።

➡️ የአትክልትና ፍራፍሬ ተረፈ ምርቶችን በወንዝ ዳርቻ ማስወገድ ግለሰብ 20 ሺህ፣ ድርጅት 100 ሺህ ይቀጣሉ።

➡️ ዘይት፣ ጨዋማ ፈሳሽ፣የሞተር ዘይት፣ ነዳጅ ሳሙና ነክ ነገሮችን በወንዝ ዳርቻ ያስወገደ 400 ሺህ ብር ይቀጣል።

➡️ ማንኛውም ያልተጣራ ቆሻሻ ወደ ወንዝ መልቀቅ ግለሰብ 150 ሺህ ድርጀት 300 ሺህ ይቀጣል።

➡️ ፍቃድ ሳይሰጠው ያልታከመ ቆሻሻን ወደ ወንዝ ያስወገደ ግለሰብ 15 ሺህ ብር ድርጅት 40 ሺህ ብር ይቀጣል።

(የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)

@tikvahethiopia

Читать полностью…
Subscribe to a channel