tikvahethiopia | Unsorted

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1527734

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Subscribe to a channel

TIKVAH-ETHIOPIA

" የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲያሟሉዋቸው የተቀመጡት መስፈርቶች በጣም ዝቅተኛ ናቸው ! "  - ባለስልጣኑ

" የግል ትምህርት ተቋማትን ስጋት ላይ የጣለው አዲሱ መመሪያ ምን ይላል " በሚለው ከዚህ ቀደም በቀረበው ዘገባችን፣ የዘርፉ ተዋናዮችን ቅሬታዎች አቅርበናል፡፡

የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ደግሞ ለቅሬታዎቹ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ውብሸት ታደለ፣ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃለመጠይቅ፣ በትምህርት ተቋማቱ የዳግመ ምዝገባና የመስክ ምልከታው የሚታዩት ዋና ዋና የሚባሉት መስፈርቶች ናቸው ብለዋል፡፡ የትምህርት ተቋማቱ፣ ትውልድን ለማስተማር በትንሹ ምን ማሟላት አለባቸው የሚለውን ነው የምናየው በማለትም ተናግረዋል፡፡

አቶ ውብሸት ታደለ በዝርዝር ምን መለሱ ?

" አንድ የትምህርት ተቋም ስናስብ የራሱ የሆነ ድባብ ሊኖረው ይገባል፡፡ አንዳንዶቹ ተቋማት የሆነ ህንፃ ላይ አንድና ሁለት ወለል ብቻ ተከራይተው ከቡቲኩና ከካፌው ጋር እየተጋፉ ነው የሚሰሩት፡፡ ይህ ትክክል አይደለም፡፡ የኮሌጅነት ቅርፅ እንዲኖራቸው የሚያስችሉ መስፈርቶች መቀመጥ አለባቸው፡፡ ግን ደግሞ የተቀመጡትን ሁሉንም መስፈርቶች በሙሉ እንተግብር አላልንም፡፡ በጣም መሰረታዊ የሚባሉትን ብቻ እንዲያሟሉ ነው እያደረግን ያለነው፡፡ በጣም በዝቅተኛ መስፈርት ነው እየተመዘኑ ያሉት፡፡ እነዚህን ዝቅተኛ መስፈርቶችስ ምን ያህሎቹ ተቋማት ያሟላሉ የሚለውን ደግሞ ሪፖርቱ ሲለቀቅ የምናየው ይሆናል፡፡   

መስፈርቶቹ ምንድናቸው ካልን አንደኛው የመማሪያ ህንፃን የሚመለከት ነው፡፡ ከአምስት ፕሮግራሞች በላይ ያላቸው ተቋማት የራሳቸው ግቢና ህንፃ እንዲኖራቸው ተደንግጓል፡፡ ተከራይተውም ቢሆን፣ የራሳቸው ግቢና ህንፃ ይኑራቸው፣ ከሌሎች የንግድ ስራዎች ጋር ሊዳበሉ አይገባም ነው፣ ይህ አንድ መሰረታዊ መስፈርት ነው፡፡

ግን ደግሞ በአብዛኞቹ ኮሌጆች ዘንድ መስፈርቶቹን ለማሟላት ስለሚቸገሩ ለድርድር እያቀረብናቸው ነው፡፡ ለምሳሌ ከአምስት ፕሮግራሞች በታች የሚሰጡ ጀማሪ ባለሀብቶች፣ የራሳቸው ህንፃና ግቢ እንዲኖራቸው አናስገድድም፡፡ እነሱ ከሌሎች ቢዝነሶች ጋር ተዳብለው መስራት ይችላሉ ብለናል፣ እስኪጠናከሩ ድረስ፡፡ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ተረድተን ነው በዚህ ደረጃ መስፈርቱን አውርደን እየሰራን ያለነው፡፡ መስፈርቶቹ በምንም መልኩ ሊሟሉና ሊተገበሩ አይችሉም የሚባሉ አይደሉም፡፡ 

ሁለተኛው መስፈርት ለማስያዣነት የሚያስቀምጡት ገንዘብ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር፣ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ መቼ ገብተው መቼ እንደሚወጡ አይታወቅም ነበር፡፡ በተለይም አወጣጣቸው ስርዓት ስላልነበረው፣ መቼ እንደወጡ እንኳን ማወቅ አይቻልም ነበር፡፡ ይህን ስርዓት ለማስያዝ ነው 500 ሺህ ብር ማስያዣ እንዲያስቀምጡ የጠደነገገው፡፡ ከእንግዲህ፣ ማንኛውም ተቋም ከገበያው ሲወጣ፣ አወጣጡ ስርዓት ያለው ይሆናል፣ የጠራ መረጃም ይኖረናል ማለት ነው፡፡

ሶስተኛው መስፈርት የሰው ሀይሉን የሚመለከት ነው፡፡ ከበፊቱ መመሪያ ብዙም የተጨመረ ነገር የለውም፡፡ አንድ ነገር ነው ብቻ ነው ያሻሻልነው፡፡ የማስተርስ ተማሪ ፒኤችዲ ዲግሪ በሌለው ረዳት ፕሮፌሰር መሰልጠን የለበትም የሚል ነው፡፡ የአስተማሪው የትምህርት ደረጃ ከሚያሰለጥነው የትምህርት ደረጃ አንድ እርከን ከፍ ይበል ነው፡፡ ለምሳሌ የዲግሪ ተማሪ ማስተርስ ዲግሪ በያዘ መምህር፣ የማስተርስ ዲግሪ ተማሪ ደግሞ የዶክትሬት/ፒኤችዲ ዲግሪ ባለው መምህር መሰልጠን አለባቸው፡፡ አሁን ግን ፒኤችዲ ዲግሪ ሳይኖራቸው ረዳት ፕሮፌሰር የሚል ማዕረግ ያላቸው አስተማሪዎች ናቸው ከነሱ ጋር አቻ የሆነን የማስተርስ ዲግሪ ስልጠና የሚሰጡት፡፡ ማስተርን በማስተር ማለት ነው፡፡ ይህ ሊሆን አይችልም ብለናል በመስፈርቱ፡፡

ከዚያ ውጭ፣ በግል ኮሌጆች ድጋፍ ሰጪ ሰራተኛውም፣ የአስተዳደር ሐላፊዎችም ፒኤችዲ ዲግሪ ይኑራቸው አልተባለም፡፡ ይህ ስህተት ነው፡፡ ዲኖቻቸው/ የተቋማቱ ሐላፊዎች እንኳን ፒኤችዲ ከሌላቸው ብለን ጥብቅ ቁጥጥር አናደርግም፣ እውነት ለመናገር፡፡ ትኩረታችን አስተማሪዎቹና ትምህርቱ ላይ ነው፡፡ በሒደት ደግሞ ወደ ስታንዳርዱ እናስገባቸዋለን የሚል እሳቤ ነው ያለን፡፡

አራተኛው መስፈርት መምህራንን መዋዋስ በተመለከተ ነው፡፡ ሁሉንም ትምህርቶች በትርፍ ሰዓት/ፓርታይም መምህር አታስተምሩ ነው እንጂ ሁሉም አስተማሪዎቻችሁ የሙሉ ሰዓት ተቀጣሪዎች/ፉልታይም መምህራን ይሁኑ አላልንም፡፡ ትምህርት ብዙ ማንበብ፣ መጣርና ማማከር የሚያስፈልገው፣ የምርምር ስራ የሚያስፈልገው ስራ ነው፡፡ ይህንን ሁሉ ስራ የሆነች ሰዓት ላይ ብቻ አስተምሮ በሚሔድ በትርፍ ሰዓት ብቻ በሚሰራ መምህር ልታስኬደው አትችልም፡፡ መምህሩ ሶስት አራት ቦታ ላይ ከተጠመደ እንዴት ነው የምርምር ስራውን የሚሰራውና የሚያሰራው፡፡ የተወሰኑ የራሳችሁ ቋሚ መምህራን ይኑሩዋችሁ፣ ሌሎችን ደግሞ በፓርታይም መምህራን መሸፈን ትችላላችሁ ነው ያልነው፡፡ 

አምስተኛው መስፈርት፣ አንድ ተቋም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ቢያንስ 25 በመቶ ካላሳለፈ ይዘጋል የሚል ነው፡፡ አንድ ተቋም አራት አመት ካስተማራቸው 100 ተማሪዎች ቢያንስ 25ቱን ማሳለፍ ካልቻለ መዘጋት ነው ያለበት፡፡ ተማሪዎችን ካላሳለፈ እኮ እያስተማረ አይደለም፣ የሀገር ሀብት እያባከነ ነው ያለው፡፡

አራት አመት ሙሉ ካስተማራቸው ተማሪዎች 75 ከመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች ከወደቁ፣ ያንን ሁሉ ሀብት ያባከነው ለምንም ነው ማለት ነው፡፡ ያ ተቋም ለምን ይቀጥላል፡፡እንዳይዘጋ ከፈለገ በደንብ አሰልጥኖ ተማሪዎቹን አብቅቶ የመውጫ ፈተናን ማሳለፍ ነው ያለበት፡፡ እንደገና ደግሞ 25 በመቶ ካላሳለፈ የሚባለው በኮሌጅ ደረጃ ሳይሆን በፕሮግራም ደረጃ ነው፡፡ ለምሳሌ 25 በመቶ ያላሳለፈው የአካውንቲን ትምህርት ከሆነ፣ ያ ትምህርት ነው የሚዘጋው እንጂ ተቋሙ አይደለም የሚዘጋው፡፡

ይህንን አሰራር ደግሞ በአንዴ ተግብሩ አላልንም፡፡ የእፎይታ ጊዜ ሰጥተናቸዋል፡፡ ይህ አሰራር የሚተገበረው መመሪያው በፀደቀበት በ 2015 ዓ.ም ትምህርት በጀመሩ ተማሪዎች ላይ ነው፡፡ ያኔ አንደኛ አመት የነበሩ ተማሪዎች በ 2019 ዓ.ም የሚመረቁ ናቸው፣ በነዚህ ላይ ህጉ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ ድንገት ተነስተን ዘንድሮ ቢያንስ 25 በመቶ አስመርቅ አላልንም፡፡ ለ 2019 ዓ.ም ካስተማርካቸው ተማሪዎች 25 በመቶውን ለማሳለፍ ተዘጋጅ ብሎ የቤት ስራ መስጠት የተጋነነ አይደለም፡፡ "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በትግራይ ላይ የሚታሰብና የሚደረግ የውክልና ግጭት (Proxy Conflict) ተቀባይነት የለውም " አሉ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጄነራል)።

" በዓፋር እንጂ በትግራይ ነፃ (ሓራ) መሬት ብሎ የለም " በማለትም ተናግረዋል።

ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ትላንት በመቐለ የሰማእታት ሀውልት አዳራሽ በተካሄደው 36ኛው የሰማእታት ቀን የማጠቃለያ ፕሮግራም ተገኝተው እንዳሉት " ነፃ (ሓራ) መሬት ተብሎ ትግራይ ላይ ለሚቃጣ ማንኛውም ዓይነት ጥቃት ተጠያቂዎቹ የፌደራል እና የዓፋር ክልል መንግስታት ናቸው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ነፃ (ሓራ) መሬት ብሎ በትግራይ የለም " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " በዓፋር ክልል ያለው የትግራይ ታጣቂ በፌደራልና በዓፋር ክልል መንግስታት እውቅና እገዛ የሚንቀሳቀስ ነው " ሲሉ ተናግረዋል። 

" በዓፋር በኩል ያሉ ታጣቂዎች ትግራይ ላይ የሚቃጡት ማንኛውም ዓይነት ጫናና ግጭት ጊዚያዊ አስተዳደሩ የፌደራልና የዓፋር መንግስታት ፍላጎት እንጂ የነሱ አድርጎ አይመለከተውም "  ብለዋል።

" እዚያ ካሉት ታጣቂዎች ያለው ማንኛውም ዓይነት ልዩነት ከውይይት ውጪ ሊፈታ አይችልም " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " የፌደራልና የዓፋር መንግስታት ጉዳዩ ሰላማዊ እልባት እንዲኖረው ማገዝ አለባቸው " ብለዋል።

" የትግራይ ቁጥር አንድ ጥያቄ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት እንዲተገበር ነው ፤ ከዚህ ውጪ የውክልና ግጭት (proxy Conflict) እንዲካሄድ የሚደረገው ጥረት ተቀባይነት የለውም የሚሳካም አይደለም " ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ንብተራ ኦንላይን!
ሁሉንም በአንድ ጥላ ስር የሚያገኙበት!

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ

***
ይሠሯል ከልብ እንደ ንብ!

#Nib #nibmobilebanking #NibQR #nib #nibtera #nibbank

Facebook  / Instagram / linkedin / nibinternationalbank6204">X / nibinternationalbank6204">Youtube / nibinternationalbank">Tiktok / Website

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ለወላጆች

ፋይዳ ለትምህርት ቤት አስፈላጊ መታወቂያ ነው።

ወላጆች ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ያልተመዘገቡ ልጆቻቸውን በትምህርት ቤታቸው ሆነ በማንኛውም የፋይዳ ምዝገባ ባለበት ቦታ (ቴሌና ባንክን ጨምሮ) ወስደው ማስመዝገብ እንደሚችሉ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት አሳውቋል።

በተለይ ከ10 ዓመት በታች ላሉ ህፃናት ከጣቶቻቸው ማነስ እና በትግስት ካለመቀመጥ ጋር ተያይዞ በቀላሉ መረጃቸውን ማሽን ላይ ለመመዝገብ ዕክል ሊያጋጥም እንደሚችል ጠቁሟል።

ለተሻለ ምዝገባ ያለው አማራጭ ምንድነው ?

1. ጣቶቻቸውን ሲያስቀምጡ በስሱ ጫን በማለት አሻራ እንዲሰጡ ማድረግ። ካልተያዘም ደጋግሞ መሞከር።

2. የሚቀመጡበትን ወንበር ወደ አሻራ መስጫው ማሽን ቀርበው እንዲሰጡ ማመቻቸት።

3. ለማንኛውም ለሚያጋጥም ችግር በተጨማሪ የተመደበው የምዝገባ ባለሙያን እገዛ መጠየቅ።

ጽ/ቤቱ " ከፋይዳ በስልክዎ መልዕክት ካልደረሰዎ በስተቀር ከአንድ ግዜ በላይ መመዝገብ አይቻልም " ሲል አስገንዝቧል።

#ፋይዳለተማሪ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

Freelance Ethiopia Afriwork

ስልካችሁን ብቻ በመጠቀም ከቤታችሁ በመሆን ለስራ አፕላይ ያርጉ! ✨

✅ ከ70 ሺ በላይ ቅጥሮችን ያሳካ
✅ ከ15 ሺ በላይ ቀጣሪዎች የሚገኙበት
✅ ከ300 ሺ በላይ ደንበኞች ያሉት

አሁኑኑ ቻናላሽንን በመቀላቀል ➡️➡️ /channel/+bOAJV6PZV9s2ZjRk ወይም afriworket.com ላይ በመሄድ ለርሶ እና ለቤተሰቦ የለውጥ መጀመሪያ ይሁኑ!

የህልሞ ስራ ከኛ ጋር!

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ተቀጣሪው ሰራተኛ በቀን አንድ ጊዜ በልቶ መዋል አልቻለም ምክንያቱም በርካታ ወጪዎች አሉበት ፤ ... ህክምና ሄዶ መታከም የማይችልበት ሁኔታ ላይ ደርሷል !! " - ኢሰማኮ

➡️ " ልማት ያለ ሰው ሰው ያለ ልማት ሊኖሩ አይችሉም !! "

🔴 " የኢትዮጵያ ሰራተኞች ኑሮን አልቻሉም፤ ቋሚ ኮሚቴው ፍቃደኛ ከሆነ ከስራ ሲውጡ ፌስታል ይዘው ሆቴል አካባቢ ቆመው የሚለምኑ ሰራተኞችን አብረን ማየት እንችላለን !! "

የኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሰማኮ) ፓርላማው ፍቃደኛ ከሆነ በስራ መውጫ ስዓት ፌስታል ይዘው ከሆቴል ተመላሸ ምግብ የሚለምኑ ሰራተኞች መኖራቸውን ማሳየት እንደሚችል ተናገረ፡፡

ይህን ያለው በቅርብ ይጸድቃል ተብሎ በሚጠበቀው የፌዴራል ገቢ ግብር ማሻሽያ ረቂቅ አዋጅ  ላይ ዛሬ/በህ/ም/ቤት የፕላን በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡

የኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ዋና ፕሬዘዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ምን አሉ ?

" ከገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከሰራተኛው ለመቁረጥ የቀረበው ሃሳብ ውስብስብ የዋጋ ንረትን እና የድህነት መጠንን ያላገናዘብ ከመሆኑም በላይ ማጭበርበር ሳይኖር በአግባቡ ከደሞዙ ግብር የሚከፍለውን ሰራተኛ ከችግር የሚውጣ ሳይሆን ችግር ውስጥ የሚከት ነው።

ሰራተኛው በቀን አንድ ጊዜ በልቶ መዋል አልቻለም ምክንያቱ ደግሞ በርካታ ወጪዎች ስላሉበት ነው።

ተቀጣሪው ሰራተኛ ህክምና ሄዶ መታከም የማይችልበት ሁኔታ ላይ ደርሷል። እውነት ለመናገር አንድ ሰው በ5 ሺ ብር ደሞዝ ቤት ኪራይ ይከፍላል ፣ ይበላል ? ፣ ልብስ ይለብሳል ? ፣ ህክምና ይሄዳል ?

ህክምናውን እንተው እየጸለየ ይኑር ፤ ቤት ኪራይውንም እንተወው በበረንዳ በሰዎች ላይ በጥገኝነት ይኑር ግን በቀን አንድ ጊዜ እየበላ መኖር የለበትም ወይ ?

አንድ ድርጅት ከትርፉ 35 በመቶ ግብር ይከፍላል ፤ ሰራተኛውም 35 በመቶ ይከፍላል ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል ?

ነጋዴውም፣ ድርጅቱም ከትርፉ ነው እኮ 35 በመቶ የሚከፍለው ሰራተኛው ግን ከትርፉ ሳይሆን ከሚበላው ላይ ነው የሚከፍለው ይህ እንዴት ነው ? እኩል የሚሆነው።

ስለሰዎች ስናስብ ልማት ለማስቀጠል ነው ልማት ያለ ሰው ሰው ያለ ልማት ሊኖሩ አይችሉም።

ስለዚህም የሰራተኛውንም ጫና የመንግስትን ዓላማ ታሳቢ ያደረገ የግብር ምጣኔ መጣል አለበት።

አሁን በማሻሻያው የግብር መነሻ 2000 ሺ ብር ሲሆን ምን ታሳቢ ተደርጎ ነው ?  አንድ ስልት ሲሰራ ሰውን ማኖር አለበት ይህ መነሻ ግን ታሳቢ አልተደረገም።

ቋሚ ኮሚቴው እንደገና ከሚመለከታቸው ሰዎች ጋር ቢመካከር ይሻላል።

የኢትዮጵያ ሰራተኞች ኑሮን አልቻሉም፤ ቋሚ ኮሚቴው ፍቃደኛ ከሆነ ከስራ ሲውጡ ፌስታል ይዘው ሆቴል አካባቢ ቆመው ሲለምኑ አብረን ማየት እንችላለን። "

የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ፍቃዱ ሆረታ ምን አሉ ?

" አዋጁ በይድረስ ይድረስ የተዘጋጀ ሳይሆን ሁለት ዓመት ጥናት ተሰርቶበት የተዘጋጀ ማሻሻያ ነው።

2000 ብር መነሻ የተደረገበት ምክንያት የመክፈል አቅማችን ዝቅተኛ ስለሆነ ነው።

መነሻን ከዚህ ከፍ ለማድረግ ቢፈለግ አገሪቱ ያላት ገቢ አይፈቅድም ወደፊት ገቢው እያደገ ሲሄድ ግን መነሻን ከፍ ማድረግ ይቻላል።

የኑሮ ውድነቱ ግብር በመክፍል ብቻ የመጣ አይደለም። በኢትዮጵያ ብቻም ያለ ችግር አይደለም።

ከውጭ የምናስገባቸውን መዳበሪያ ፣ ነዳጅ እና መሰል ግብዓቶች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በሰዎች ላይ ጫና ይፍጥራል።

ይህን ችግር ለመፍታት ደግሞ መንግስት ደሞዝ ጨምሯል። መንግስት አቅም በፈቀደ መሰረት ድጋፍ አድርጓል።

በገቢ ግብር ላይ ያለውም ጫናውን መቀነስ ነው እንጂ ማጥፋት አይደለም። በነባሩ አዋጅ ላይ መነሳት ብናመለከት 600 ነው ወደ 2000 ያደገው በውይይት ተደርጎበት ነው።

በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና የሞያ ማህበራት ተሳትፎ የተደረገ ማሻሻያ እንጂ ዝም ብሎ የመጣ ቁጥር አይደለም።

የግብር መነሻው ከተቀጣሪ ሰራተኛ አሁን ካቀረብነው ከፍ ካለ መንግስት ከፍተኛ ገቢ ያጣል። በተለይ በክልሎች ገቢ ላይ የበረታ ጫና ያሳድራል። "

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ኢትዮጵያ🇪🇹

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ፣ የኑሮ ውድነትን ታሳቢ በማድረግ የገቢ ግብር መነሻ ገቢ ከ2,000 ብር ወደ 5,000 ብር ከፍ እንዲል ጠንካራ ጥያቄ ቀርቧል።

ጥያቄው የቀረበው የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ በፓርላማው የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ ባደረገዉ ዉይይት ላይ ነው።

በአሁኑ ረቂቅ አዋጅ መሰረት፣ ከ2,000 ብር በላይ በሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር እንዲከፈል የሚለው ሀሳብ ቀርቧል።

ይህ የገቢ ግብር አዋጅ ከዘጠኝ ዓመታት በላይ ስራ ላይ መዋሉ የተገለጸ ሲሆን፣ አሁን በማሻሻያው ከግብር ነፃ የሚሆነው ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ በ300% በማሳደግ ወደ 2,000 ብር ከፍ እንዲል ተደርጓል።

በተጨማሪም፣ ከፍተኛው የማስከፈያ መጣኔ የሆነው 35% ግብር የሚያርፍበት ገቢ ደግሞ ወደ 14,000 ብር ከፍ እንዲል ሆኗል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ፣ የአዋጁ መሻሻል መንግስት ግብር በመሰብሰብ የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ እንደሚረዳ ገልጸዋል።

ከግብር ከፋዩ ህብረተሰብ የሚነሱ " ግብር በዝቷል ይቀነስ " የሚሉ ሀሳቦች ሚዛናዊ በሆነ መልኩ እንደሚታዩም አክለዋል።

በውይይት መድረኩ ከተነሱት አስተያየቶች መካከል፣፦
- የገቢ ግብር መነሻው ከአምስት ሺህ ብር ጀምሮ እንዲሆን፣
- ለአካል ጉዳተኞች በተለየ መልኩ ግብር እንዲቀነስ፣
- በተለያዩ የሙያና የንግድ ዘርፎች አንፃር በደንብ እንዲታይ የሚሉ ሀሳቦች ቀርበዋል።

የመረጃው ባለቤት የካፒታል ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ከ3 ጊዜያት በላይ ሲራዘም የቆየዉ ቶምቦላ ሎቶሪ ዛሬ ይወጣል ተባለ።

የሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታን ለማጠናቀቅ ታስቦ ለሽያጭ የቀረበዉ ቶምቦላ ሎተሪ ከሶስት ጊዜያት በላይ ሲራዘም ቆይቶ ዛሬ በብሔራዊ ሎተሪ አደራሽ እንደሚወጣ የሀዋሳ ከተማ የሕብረተሰብ ተሳትፎ ልማት ፈንድ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘሪሁን ቃሚሶ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቀዋል።

አስቀድሞ ጥር ‎20/2017 ዓ/ም ከዚያም ሚያዚያ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ሌላ ጊዜ ደግሞ ሰኔ 30/2017 ዓ/ም ዕጣዉ እንደሚወጣ ተገልፆ ሲራዘም የቆየዉ ሎተሪ 500 ሺህ ትኬቶች ለገበያ የቀረቡ ሲሆን 1 መቶ ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብም ዕቅድ ተይዞበት ነበር።

" ሶስቱንም ዙሮች ትኬቶቹ በበቂ ሁኔታ ስላልተሸጡና በተለያዩ አከባቢዎች የተሰራጩ የቲኬት ወረቀቶችም ተሰብስበዉ ስላላለቁ " በሚል መውጫው ሲራዘም ነበር ተብሏል።

250 ካ.ሜ ለንግድ እና 200 ካ.ሜ ለመኖሪያ የሚሆን መሬትን ጨምሮ ኩዊት ባጃጅ፣ ሞተር፣ ቴሌቪዥን፣ ፍሪጅ ዕጣ የሚወጣባቸው ሲሆኑ 14 ዕድለኞች ይታወቃሉ።

#Update ዕጣው ወጥቷል።

በዚህ መሰረት፦
‎1ኛ ዕጣ 0189833 ➡️ 250 ካሬ ለንግድ አገልግሎት የሚሆን መሬት
‎2ኛ  ዕጣ 0385625 ➡️ ለመኖሪ አገልግሎት የሚሆን መሬት
‌‎3ኛ ዕጣ 0122191 ➡️ ኪዉ ባጃጅ
‎4ኛ ዕጣ 0274157 ➡️ ባለ 3 እግር ባጃጅ
‌‎5ኛ ዕጣ 0043656 ➡️ አፓች ሞተር ሣይክል
‎6ኛ ዕጣ 0116134 ➡️ ኤል (ሊፋን) ሞተር ሣይክል
‎7ኛ ዕጣ 0176687 ➡️ ማቀዝቀዣ ፍሪጅ
‎8ኛ ዕጣ 0185323 ➡️ HP Cori i5 ላፕቶፕ
‎9ኛ ዕጣ  0367397 / 0023129 ➡️ ለሁለት ሰዎች 54 ኢንች ቴሌቪዥን
‎10ኛ ዕጣ 0480480 ፣ 0263409፣  0041937፣ 0208319፣ 0273773 ➡️ ለ5ቱ ለእያንዳንዳቸው ሞባይል ቀፎ

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamliyHawassa

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Mesebo

የመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ከሁለት ወራት በላይ ከስራ ገበታ ውጪ ሆኗል። ስራ ባቆመባቸው ቀናት 400 ሺህ ቶን ስሚንቶ ሳያመርት ቀርቷል።

ፋብሪካው ከማምረት ውጪ ሊሆን የቻለው ጥሬ እቃ ከሚያገኝበት አከባቢ ከሚኖር ማህበረሰብ ጋር  በተፈጠረ አለመስማማት ነው።

የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ ክብረኣብ ተወልደ ምን አሉ ?

" የላይምስቶን ጥሬ እቃ የሚያገኝበት አከባቢ የሚኖረው ህዝብ በተደጋጋሚ የሚያነሳው ጥያቄ  በጊዜ ባለመመለሱ የተነሳ ፋብሪካው ላለፉት 65 ቀናት አላመረተም። 

ባለፉት 65 ቀናት ውስጥ 400 ሺህ ቶን ስሚንቶ ማምረት ይችል ነበር በመጋዘን የነበረው ክምችት ባለፉት 30 ቀናት ተሽጦ አልቋል።

ፋብሪካው ማምረት በማቆሙ የስሚንቶ መወደድ አስከትሏል። ጥሬ እቃ ከሚያገኝበት አከባቢ ከሚኖር  ህዝብ የተፈጠረው አለመግባባት ተፈትቶ ፋብሪካው በቅርቡ ወደ ስራ ይመለሳል። " #DemtsiWeyane

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

🤙🏽ከሳፋሪኮም ወደ የቴሌ የሚያስደውሉ የድምፅ ጥቅሎች በመጠቀም ከ07 ➡️ 09 መስመር በእጥፍ ጉርሻ በሽ በሽ ብለን እንደዋወል! ከሳፋሪኮም ጋር በአብሮነት አንድ ወደፊት⚡️

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ATTENTION🚨

ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው መልዕክት !

በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች ለአብነትም አዋሽ ወንዝን ተከትሎ የሚኖሩ ከመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍል ከኦሮሚያ ክልል ከደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወረዳዎች ጀምሮ እስከ ታችኛው አዋሽ አካባቢዎች በተለይም ፦
- በአፋር ክልል በአዋሽ ወንዝ ዳር የሚገኙ ወረዳዎች፣
- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዳሰች ወረዳ ሆሞራቴ ከተማን ጨምሮ፣
- በጋምቤላ ክልል ጋምቤላ ከተማ እና ሌሎች በባሮ ወንዝ ተጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉት ወረዳዎች፣
- በዋቤ ሸበሌ ወንዝ ሊጠቁ የሚችሉ የሶማሌ ክልል ወረዳዎች፣
- በአማራ ክልል በጣና ሀይቅ አቅራቢያ የሚገኙ አንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች በዚህ የክረምት ወቅት ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ እና የተጎጂ ይሆናሉ ተብሎ ተለይቷል፡፡

በተጨማሪም የክረምት ወቅት ዝናብ ተጠቃሚ የአገሪቱ አከባቢዎችና ከተሞች በሙሉ ከባድ ዝናብ በሚኖርበት ወቅት በየትኛዉም ጊዜ በቅፅበታዊ ጎርፍ አደጋ ሊጠቁ የሚችሉ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎች ባልታሰቡ ክስተቶች እና ትናንሽ ወንዞች ምክንያት የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ይችላል፡፡

የ2017 ክረምት ወቅት የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት እና ዓለም አቀፍ ትንበያዎች እንደሚያመለክቱት በእነዚህ ክልሎች እና ሌሎችም ከመደበኛ በላይ የሆነ ዝናብ የሚጠበቅ ነዉ፡፡

የጎርፍ አደጋ ስጋት ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች የትኞቹ ናቸው ?

➡️ በተፋሰስና ወንዝ ዳርቻ (አዋሽ ፣ ዋቤ ሸበሌ፣ ተከዜ፣ ባሮ፣ ኦሞ፣ የከተሞች ወንዞች፣ ወ.ዘ.ተ….)፣

➡️ በግድቦች ማስተንፈሻ አካባቢዎች (ተንዳሆና ቀሰም፣ ግልገል ጊቤ ፣ ተከዜ፣ ገናሌ፣ ዳዋ ፣ ፊንጫ፣ ቆቃ ወ.ዘ.ተ...)፣

➡️ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆነ አከባቢዎችና ከተሞች ሙሉ በሙሉ ከባድ ዝናብ በሚኖርበት ወቅት በየትኛዉም ጊዜ ቅፅበታዊ ጎርፍ ሊጠቁ ይችላሉ።

ማህበረሰቡ፣ የሚመለከታቸው ተቋማት እና የአስተዳደር መዋቅሮች አስፈላጊውን ጥንቃቄና በክትትል ላይ ተመሰረተ እርምጃዎች እንዲወስዱ የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አሳስቧል።

(ዝርዝር መረጀዎች ከላይ ተያይዟል)

⚠️መልዕክቱን ለሌሎች ያጋሩ!

#EDRMC

#TikvahEthiopiaFamliyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ሞሐመዱ ቡሃሪ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

የ82 ዓመቱ ቡሃሪ በብሪታኒያ ዋና ከተማ ለንደን በሚገኝ ክሊኒክ ውስጥ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለዩ የቀድሞ ቃል አቀባያቸው ገርባ ጋሹ ገልጸዋል።

ሁለት የፕሬዝዳንታዊ የሥልጣን ዘመን ያገለገሉት ቡኻሪ ሥልጣን ያስረከቡት እኤአ በ2023 ነበር።

በናይጄሪያ ታሪክ ቡሃሪ በምርጫ በሥልጣን ላይ የሚገኝ ፕሬዝደንት ያሸነፉ የመጀመሪያው የተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩ ነበሩ። እኤአ 2015 ሥልጣን የያዙት የቀድሞውን ፕሬዝደንት ጉድላክ ጆናታን በምርጫ አሸንፈው ነው።

ይሁንና ናይጄሪያን የመሩባቸው ዓመታት በጤና ዕክል ምክንያት አሉባልታ በብዛት ይናፈስባቸው ነበር።

ቡሃሪ ራሳቸውን ዴሞክራሲያዊ አድርገው ከመቀየራቸው በፊት በ1980ዎቹ ጠንካራ አምባገነን ሆነው ናይጄሪያን መርተዋል።

ቡሃሪ ከሦስት ያልተሳካ ሙከራ በኋላ ጉድላክ ጆናታንን አሸንፈው ፕሬዝዳንት ሲሆኑ በናይጄሪያ ፖለቲካ የለውጥ ዕድል ተፈጠረ ተብሎ ተስፋ ተሰንቆ ነበር።

ይሁንና በስልጣን ዘመናቸው በናይጄሪያ የበረታውን ሙስና እና የመረጋጋት እጦት መቅረፍ ተስኗቸዋል። የሥልጣን ዘመናቸው ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እና የጤና ዕክል የበረታባቸው ነበሩ። መንግሥታቸው በተቃዋሚዎች ላይ በወሰዳቸው ርምጃዎች ከፍተኛ ትችት ይሰነዘርባቸው ነበር።

በሰሜናዊ እና ደቡባዊ ናይጄሪያ ከፍተኛ ፉክክር ባለባት ሀገር ቡሃሪ የትውልድ አካባቢያቸውን ሰዎች እና ዘመድ አዝማዶቻቸውን ለከፍተኛ የመንግሥት ሥልጣን በመሾም አለመተማመን እና ጥርጣሬ እንዲነግስ አድርገዋል እየተባሉ ይተቻሉ።

Credit - DW

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#AddisAbaba

በመዲናዋ የተመረጡ የመንግሥት ተቋማት እስከ እሁድ ግማሽ ቀን ድረስ አገልግሎት ሊሰጡ ነው።

በአዲስ አበባ ከተማ በተመረጡ የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ላይ መደበኛ የሥራ ቀናት መራዘሙን የከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው እንዳሳወቀው፥ አገልግሎት ፈላጊዎች በተመረጡ ተቋማት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 እና እሁድ እስከ ቀኑ 6፡30 ድረስ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ነው የገለጸው።

አገልግሎቱም ከማዕከል መስሪያ ቤቶች ጀምሮ ክ/ከተማ እና ወረዳዎች ድረስ የሚዘልቅ መሆኑን አስታውቋል።

በተጠቀሱት ቀናት አገልግሎት የሚሰጡ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ ተቋማት የትኞቹ ናቸው ?

- ንግድ ቢሮ፣

- ገቢዎች ቢሮ፣

- መሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ፣

- መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ፣

- ግንባታ ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን፣

- ህብረት ስራ እና የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ እና ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ላይ በተጠቀሰው መሰረት አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን አሳውቋል።

@TikvahethMagazine @tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ንብተራ ኦንላይን መተግበሪያን ይፋ አደረገ !

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አዲስ ይፋ ባደረገው የሦስት ዓመት ስትራቴጂ ዕቅድና የአምስት ዓመት ፍኖተ ካርታ ውስጥ ካቀዳቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል አንዱ የሆነውን ንብተራ ኦንላይን መተግበሪያ የማብሰሪያ መርሐ ግብር አካሄደ፡፡

ይህ ለደንበኞች የተሟላ፣ ምቹ፣ ቀላልና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለው ንብተራ ኦንላይን ሱፐር አፕ መተግበሪያ ከሐምሌ 05 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡

መተግበርያው ደንበኞች ከባንክ አገልግልት በተጨማሪ ግብይቶችንና ክፍያዎችን በቀላሉ የእጅ ስልካቸውን ብቻ በመጠቀም መፈጸም እንደሚያስችላቸው በዚሁ የማብሰሪያ መርሃ ግብር ላይ ተገልጻል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሔኖክ ከበደ ባስተላለፉት መልዕክት ባንኩ ለደንበኞቹ ዘመኑ የሚፈልገውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በውጤት የታጀበ አገልግልት ለመስጠት ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹ ሲሆን አዲሱ የሦስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድም ከባለድርሻ አካላትና ከመላው ደንበኞቹ ጋር በመሆን የላቀ ውጤት የሚመዘገብበት ይሆናል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ይህ በውስጥ አቅም በልጽጎ ወደ ተግባር የገባው ንብተራ ኦንላይን መተግበሪያና አዲሱ የሶስት አመት ስትራቴጂክ ዕቅድ በአጭር ጊዜ ውስጥ በማበልፀግና ወደ ሥራ እንዲገባ ላደረጉ የባንኩ ሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች ምሰጋና ያቀረቡት የባንኩ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሊ/መንበር አቶ ሺሰማ ሸዋነካ አዲሱ የስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ምክክር አድርገውበትና ጸድቆ ወደ ሥራ መግባቱን አመልክተዋል፡፡

በይፋዊ የንብተራ ኦንላይን መተግበሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የባንኩ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት፣ ደንበኞች፣ የባንኩ የስራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- https://www.nibbanksc.com/wp-content/uploads/2025/07/Press-release-NIB-Tera.pdf

ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

#Nib #DigitalBanking #Nibinternationalbank #nibbank #nibtera #nibsuperapp

Facebook  / Instagram / linkedin / X / Youtube / Tiktok / Website

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በፈርንጆቹ 2026 ሁለት በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ትናንሽ አውሮፕላኖች እናስመጣለን "-የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኢትዮጵያዊ አየር መንገድ መጋቢት 17/2017 ዓም ላይ አርቸር አቪዬሽን ከተሰኘ አለም አቀፍ ተቋም ጋር ስምምነት መፈራረሙ ይታወሳል።

ስምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና አርቸር አቪዬሽን በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውሮፕላኖችን በአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ለማዋል ሲሆን በመኪና ከ60-90 ደቂቃ የሚወስድ ጉዞን ወደ 10 ደቂቃ ዝቅ የሚያደርግ እንደሆነ በወቅቱ ተገልጾ ነበር።

የዚህ ስምምነት ትግበራ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ጥያቄ አቅርቧል።

ዋና ስራ አስፈጻሚ በሰጡት ምላሽ " በፈርንጂዎቹ 2026 ሁለት በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ትናንሽ አውሮፕላኖች እናስመጣለን በዋነኛነት የቱሪስት መዳረሻዎች ላይ እንጠቀምባቸዋለን ብለን አቅደናል " ብለዋል።

የኢ-ኮሜርስ ንግድን ከማስፋፋት አኳያ አየር መንገዱ ከአለም አቀፎቹ አማዞን እና አሊባባ እንዲሁም ከሃገር ውስጡ " ዘመን ገበያ " ጋር በአጋርነት ለመስራት አስቧል ወይ ? ምን አይነት እንቅስቃሴዎችንስ እያደረገ ይገኛል ? የሚል ጥያቄ ያነሳንላቸው አቶ መስፍን ፤ አየር መንገዱ የተወሰነ እንቅስቃሴዎች እያደረገ እንደሚገኝ ነገር ግን ገና በሚባል ደረጃ ላይ ያለ መሆኑን ጠቁመዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን በተጨማሪ ምን አሉ ?

"እኛ እስካሁን ድረስ ኢ-ኮሜርስን በአለም አቀፍ ደረጃ ለመስራት የሚያስችለንን ፋሲሊቲ ገንብተናል።

ይህ ፋስሊቲ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አካሉን ብቻ ነው የሚሰራው እኛ ኢ-ኮሜርስ ውስጥ አንገባም ኢ-ኮሜርስ ንግዱን የሚሰሩት ሌሎች ድርጅቶች ናቸው እኛ ትራንስፖርቱን ነው የምናቀላጥፈው።

ከመነሻው ማጠናቀቁን እና መዳረሻውን ላይ ደግሞ የመጨረሻውን ከሚያከፋፍሉ ድርጅቶች ጋር ተቀናጅተን ቦሌ ኤርፖርት ካርጎ ተርሚናላችንን ተጠቅመን ይህንን ለማሳለጥ ነው የምንሰራው የተወሰነ የተጀመረ ስራ አለ ነገር ግን ገና መሰራት ያለበት ነው " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamliyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#NationalExam🇪🇹

በአገር አቀፍ ደረጃ በወረቀትና በበይነ-መረብ ሲሰጥ የቆየው የ2017 ትምህርት ዘመን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂ (12ኛ ክፍል) ፈተና መጠናቀቁ ተገልጿል።

ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8/ 2017 ዓ.ም  በመላ አገሪቱ በወረቀትና በበይነ-መረብ ሲሰጥ የቆየው የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መለቀቂያ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል፡፡

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ኮደርላብ የ2025 የክረምት ካምፕን ይቀላቀሉ - ተማሪዎችን እናበቃ!

የኮደርላብ 2025 የክረምት ካምፕ ተማሪዎችን ዲጂታል ችሎታዎች፣ ኮድ ማድረግ፣ ሮቦቲክስ፣ የwebsite development እና ሌሎችንም ለማስተማር ዝግጅቱን ጨርሷል!

🚀 ከ6 እስከ 18 አመት ለሆኑ ተማሪዎች ክፍት ነው።

📅 የሚፈጀው ጊዜ፡- 4 ሳምንታት project based learning ( games , animations , python projects and website development)

🎓 የፕሮጀክት ማሳያዎችን፣ የቡድን ስራን እና የምስክር ወረቀቶችን ያካትታል

ክፍያ ለአጠቃላይ 4 ሳምንት ስልጠና 6000Birr

📲 አሁኑኑ በhttps://forms.gle/HcjfaWrmC9PWmzGM7 ይመዝገቡ

ወይም በ +251 907 945085 ይደውሉልን

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የአውሮፕላን ነዳጅ መቆጣጠሪያዎች በጥብቅ ይፈተሹ " - ህንድ

ከአንድ ወር በፊት ህንድ ውስጥ በደረሰ የቦይንግ 787-8  አውሮፕላን መከስከስ አደጋ የ260 ሰዎች ህይወት መቀጠፉ ይታወሳል።

የአደጋው መንስዔ የቦይንግ አውሮፕላኑ ከተነሳ ከሰኮንዶች በኋላ የነዳጅ መቆጣጠሪያዎች ጠፍተው ወደ ሞተሩ የሚደርሰው ነዳጅ መቋረጡ መሆኑን በህንድ የአውሮፕላን አደጋ የምርመራ ቢሮ (AAIB)  ይፋ የተደረገ ቅድመ ሪፖርት አሳይቷል።

አውሮፕላኑ ከተነሳ በሰከንዶች ውስጥ የነዳጅ መቆጣጠሪያ ማብሪያና ማጥፊያዎች ደህነንት ጠፍተው ነዳጅ ተቋርጦ ነበር ተብሏል።

መቆጣጠሪያዎቹ ከመብራት ወደ መጥፋት በመቀየራቸው ወደ ሞተሩ የሚወስደው ነዳጅ መቋረጡ ተመላክቷል። በዚህም አውሮፕላኑ ሊከሰከስ ችሏል።

ሪፖርቱን ተከትሎ ህንድ አየር መንገዶች የአውሮፕላን ነዳጅ መቆጣጠሪያዎችን በጥብቅ እንዲፈትሹ መመሪያ አወጥታለች።

የአገረቱ ሲቪል አቪዬሽን የህንድ እና አለም አቀፍ አየር መንገዶች በነዳጅ መቆጣጠሪያዎች ላይ የራሳቸውን ፍተሻ አድርገው ሪፖርት እንዲያቀርቡ መመሪያው እንደወጣ ገልጿል።

አየር መንገዶች የቦይንግ አውሮፕላኖች የነዳጅ መቆጣጠሪያዎች ማብሪያና ማጥፊያዎችን እስከ ሐምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ፈትሸው እንዲያጠናቅቁ ጠይቋል።

" የተቀመጠውን ቀነ ገደብ በጥብቅ መከተል የመብረር ብቃት እና የአፕሬሸኖችን ደህንነት ለማረጋገጥ መሰረታዊ ጉዳይ ነው " ብሏል።

የአሜሪካ የፌደራል አቪዬሽን ባለስልጣን ይፋ የተደረገውን ሪፖርት ተከትሎ " የቦይንግ የነዳጅ መቆጣጠሪያዎች ማብሪያና ማጥፊያዎች ደህንነታቸው የተጠበቀ ነው " ብሏል። መቆጣጠሪያዎቹ በሚቆለፍ መልኩ የተገጠሙ መሆኑን አመልክቷል።

የህንድ አየር መንገድ ፓይለቶች ማህበር ከአደጋው ጋር ተያይዞ በአውሮፕላኑ ፓይለቶች ላይ የሚሰነዘረውን የስም ማጉደፍ ተከላክሎ መግለጫ አውጥቷል።

ማህብሩ " አብራሪዎች በፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ማድረግ ያለባቸውን በስልጠናቸው እና በተሰጣቸው ኃላፊነት መሰረት እርምጃ ወስደዋል " ብሏል።

አደጋውን ተከትሎ ከኮክፒት የተገኘ የድምጽ ቅጂ አንደኛው ፓይለት " ለምን አቋረጥከው ? " ሲል የሚሰማ ሲሆን ሌላኛው አብራሪ ደግሞ " አኔ አላቋረጥኩትም " ሲል ይደመጣል።

በህንዱ የአውሮፕላን አደጋ በተአምር ከተረፈው አንድ ሰው በስተቀር ሌሎች ተሳፋሪዎች እና የበረራው አባላት ሁሉ መሞታቸው ይታወሳል።

መረጀው ከቢቢሲ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" መሬታችን ለቀማኛ አንሰጥም ፤ ህይወታችን ለመሬታችን እንክፍላለን " - የማይቅነጣልና የቀይሕ ተኽሊ ነዋሪዎች

➡️ " ህዝብ ያልተቀበለው ባለሃብት አናስተናግድም ፤ የህዝቡ ጥያቄ ተቀብለን እርምጃ ወስደናል" - የወረዳዎቹ አመራሮች


በትግራይ ክልል ማእከላዊ ዞን በመቶዎች የሚቆጠሩ የማይቅነጣልና የቀይሕ ተኽሊ ተምቤን ወረዳ ነዋሪዎች " አከባቢያችንን ይበክልብናል ! በራሳችንና በእንስሶቻችን ህይወት ላይ አደጋ ያስከትልብናል " ያሉት ተግባር ተቃወሙ።

ተቃውሟቸው የመኪና መንገድ እስከ መዝጋት የደረሰ ነው።

ነዋሪዎቹ ቅዳሜ ሐምሌ 6/2017 ዓ.ም ባሰሙት ተቃውሞ ' ወርዒ ' ተብሎ በሚጠራው ወደ ተከዜ የሚፈስ ታላቅ ወንዝ ላይ የተጀመረው ህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን የማጣራት ተግባር ተቃውመዋል።

ነዋሪዎቹ ባሰሙት የተቃውሞ ድምፅ
- መሬታችን አንሰጥም !!
- ለመሬታችን ይቀላል አንገታችን !!
- ወንዛችን በአደገኛ ኬሚካል አይበከልም !!
ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ሐምሌ 7/2017 ዓ.ም ወደ ወረዳዎቹ አመራሮች ደውሎ በሰጡት ቃል የህዝቡ ጥያቄ ልክ መሆኑ በመቀበል የአከባቢው ህዝብ ሐምሌ 6/2017 ዓ.ም በቁጣ ተነሳስቶ " ለሰዓታት የመኪና መንገድ ዘግቶ ነበር " ብለዋል።

" ህዝብ ያልተቀበለው ልማትና ባለሃብት የመንግስት አመራር አያስተናግድም " ያሉት አስተዳዳሪዎቹ " ለህዝብ ቁጣ መነሻ የሆነው በወንዝ ዳር የወርቅ ማዕድን የማጣራት ስራ በተሳተፈው ባለሃብት ላይ እርምጃ ተወስዷል " ብለዋል።

" ባለሃብቱ ለስራ ያሰማራቸው ማሸነሪዎች ከአከባቢው እንዲያነሳና ስራው እንዲያቆም ፈጣን አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል " ሲሉ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በትግራይ ከጦርነቱ በኋላ በተለይ ደግሞ በሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ከህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ስራ ጋር ተያይዞ እስከ ሞት የሚያደርሱ ግጭቶችና ችግሮች በመከሰት ላይ መሆናቸውን መረጃ መስጠታችን ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ሥራን በክብር
ግብርዎን በቴሌብር!


ከሥራዎ ገበታ ሳይነሱ ምቾትዎ እንደተጠበቀ ባሉበት ሆነው ግብርዎን በቀላሉ በቴሌብር ይክፈሉ!

👉 በቴሌብር ሱፐርአፕ https://bit.ly/telebirr_SuperApp ወይም *127#

ቴሌብር ሱፐርአፕ ➡️ ክፍያ ➡️ ግብርና የመንግሥት አገልግሎት ➡️ የግብር ክፍያ


ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#TaxPayment
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

በአዲስ አበባ በፒኤስጂ እና ቼልሲ መካከል የተደረገውን የዓለም የክለቦች ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በዲኤስቲቪ ሲመለከቱ የነበሩ ደጋፊዎች በነበሩበት ሆቴል በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት አለፈ።

ትላንት ምሽት በአሜርካ ኒው ጀርሲ በሚገኘው ሜትላይፍ ስታዲየም በፒኤስጂ እና ቼልሲ መካከል የተደረገውን የዓለም የክለቦች ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ " ለቡ " አካባቢ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ በዲኤስቲቪ እየተመለከቱ በነበሩ ተመልካቾች መካከል በተፈጠረ ግጭት የአንድ ለጋ ወጣት ህይወት አልፏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በለቡ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በመገኘት የሟቹ ወጣት የቀብር ስነስርዓት ሲፈፀም ተመልክቷል።

በቀብር ስነስርዓቱ ላይ የተገኙ የሟቹ ወዳጆች ፣ ጓደኞች " አሟሟቱ እጅግ የሚያሳዝን ነው " ያሉ ሲሆን " ግለሰቡም ተይዟል " ብለዋል።

" እስከ ምሽት 3:00 ሰአት ድረስ ከቤተሰቦቹ ጋር ካመሸ በኋላ ከጓደኞቼ ጋር ትንሽ ልዝናና ብሎ ሆቴሉ እንደገባ ነው ክስተቱ የተፈጠረው " ሲሉ ተናግረዋል።

በአሟሟቱ ቤተሰቦቹ እጅግ ከፍተኛ ሀዘን ውስጥ እንደሚገኙ ለመመልከት ችለናል።

" ወጣቱ ከኳስ ስሜታዊነት መቆጠብ ወይም የእግር ኳስ ጨዎታዎችን ተሰባስቦ ከማየት መቆጠብ አለበት ካልሆነ ግን የቤተሰብን ሀዘን ማብዛት ነው " ሲሉ ያነጋገርናቸው ለቀስተኞች ተናግረዋል።

" ወጣቶች እባካችሁ ለቤተሰቦቻችሁ ሀዘን አታብዙ፣ ሁሉን በማስተዋል አድርጉ፣ ማታ ማታ አታምሹ፣ በአጭሩ እየተቀጫችሁ ሃዘናችንን አታብዙት " የሚሉ እና ሌሎች ልብ የሚነኩ ሃሳቦች ሲሰነዘሩ እንደነበር ቲክቫህ ኢትዮጵያ በስፍራው ተገኝቶ ተመልክቷል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በስልክ ቃላቸውን የሰጡ አንድ እናት ሟቹን ወጣት እንደሚያውቁት ገና በ22 ዓመቱ በተፈጠረው ፀብ እንደተቀጠፈ ገልጸዋል።

" በውጭ ኳስ ምክንያት የለጋ ወጣት ህይወት መጥፋቱ እጅግ ያሳዝናል። ሁሉም ወጣቱ ከስሜታዊነት መራቅ አለበት፣ የሚመለከታቸው አካላትም እንዲህ ያለው ነገር እንዳይፈጠር የራሳቸውን ድርሻ መወጣት አለባቸው " ሲሉ እናታዊ መልዕክታቸውን በሀዘን ስሜት አስተላልፈዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ከ116 ግለሰቦች ላይ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ በሞባይል ባንኪግ በማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ 80 ግለሰቦች ላይ ክስ መመስረቱ ተነገረ።

‎የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ  በሞባይል ባንኪንግ አማካኝነት ከ116 ግለሰቦች ላይ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ በሞባይል ባንኪግ በማጭበርበር ወንጀል በተጠረጠሩ 80 ግለሰቦች ላይ ወንጀል ምርመራ በማጣራት ለፌደራል ዐቃቤ ህግ በማስተላለፍ ክስ እንዲመሰረት ማድረጉን አመልክቷል።

‎ተከሳሾቹ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ከሌሎች የግል ባንኮች የሚደውሉ በማስመሰል እንዲሁም የኮምፒውተር ስርዓትን በመጠቀም አሳሳች መረጃዎችን በማሰራጨት ወንጀሉን እንደፈጸሙ ፖሊስ ገልጿል።

‎የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት የቀረበው ክስ እንደሚያብራራው፣ ተጠርጣሪዎቹ ማንነታቸውን በመሰወር፣ ሀሰተኛ ሰነዶችን እና መታወቂያዎችን በማዘጋጀት እና በመጠቀም የተበዳዮችን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው  ማዋላቸው በምርመራ ተረጋግጧል።

‎በተጠርጣሪዎቹ ላይ የቀረበው ክስ በዋናነት በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ እና የኮምፒዩተር ወንጀል አዋጅ ቁጥር 958/2008ን እንዲሁም የብሄራዊ የክፍያ ስርዓት አዋጅ ቁጥር 718/2003ን የተላለፉ መሆናቸውን ይገልጻል።

‎ለወንጀል ድርጊቱ ማስፈጸሚያነት ሲጠቀሙባቸው የነበሩ ፦
- በርካታ የባንክ አካውንቶች፣
- የሞባይል ቀፎዎች፣
- ሲም ካርዶች እና ኮምፒውተሮች የተያዙ ሲሆን፣ ጉዳዩን ለማጣራት ተጨማሪ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

ፖሊስ ፥ ህብረተሰቡ ከማያውቋቸውና አጠራጣሪ ከሆኑ የስልክ ጥሪዎችና መልዕክቶች ራሱን እንዲጠብቅ አሳስቧል።

(በክሱ ከተጠቀሱት ተጠርጣሪዎች መካከል የተወሰኑት ስም ዝርዝራቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ለጥንቃቄ
#ጥቆማ_ለሚመለከተው_አካል!

አዲስ አበባ ጎተራ አካባቢ በሚገኘው የኢሚግሬሽ እና ዜግነት አገልግሎት አካባቢ ከሰሞኑን የሜትር ታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ በማስመሰል የዘረፋ ተግባር ላይ በተሰማሩ ሰዎች የተሞከረባትን የዘረፋ ሙከራ አንድ የቤተሰባችን አባል ለጥንቃቄ አጋርታለች።

የጎተራው አገልግሎት መ/ቤት የውጭ ዜጎች አገልግሎት ፣ የቪዛም አገልግሎት የሚገኝበት በመሆኑ ብዙ ከውጭ ሀገር የሚመጡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውን ለአገልግሎት ይሄዳሉ።

በባለፈው ሳምንት ለዚሁ የውጭ አገልግሎት የሄደች አንዲት ከአሜሪካ የመጣች የቤተሰባችን አባል የዘረፉ ሙከራ ተፈጽሞባታል።

ነገሩ እንዲህ ነው ...

ቦታው እንደልብ ትራንስፖርት የማይገኝበት እና ጭር ያለ ነው።

ልክ ከአገልግሎቱ መ/ቤቱ ስትወጣ በቦታው ቀድሞውንም የነበሩ የሜትር ታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ የሚመስሉ ሰዎች " ይኸው ነይ የሜትር ታክሲ አገልግሎት " ይሏት።

እሷም ወደ መኪናው ትገባለች።

ብዙ ሳይጓዙ መኪናውን የሚያሽከረክረው ሰው መኪናውን ያቆመውና አንድ ሰው ገቢና ይጨምራል።

" ለምን ሰው ትጨምራለህ ? " ብትለውም " ምን አገባሽ ዝም ብለሽ ቁጭበይ " የሚል መልስ ይሰጣታል።

ነገሩ ያላማራት ይህች እህታችን ሁኔታውን በንቃት መከታተል ትጀምራለች።

አሁንም ትንሽ ከተጓዙ በኃላ መኪናውን አንድ ግብረአበራቸው ጋር ያቆሙና እሷ በተቀመጠችበት በር በኩል እንዲገባ ይነግሩታል።

በዚህ ወቅት እሷ " እኔ አልከፍትም በዛኛው ተቃራኒ በኩል ከፍቶ ይግባ " የሚል ምላሽ ትሰጣለች። ልክ ሰውየው በዛኛው በር ለመግባት ሲሄድ የነበረችበትን በር በመክፈት ወርዳ ወደ ኃሏ ሩጣ ማምለጥ ችላለች።

ሰዎቹ መንገዱ ወደፊት እንጂ ወደኃላ መመለስ የማያስችል በመሆኑ ሊከተሏት አልቻሉም።

በኃላም አካባቢው ግር ስላለባት በጎተራ ድልድይ አድርጋ ወደ ሳሪስ አቅጣጫ በእግር እየሮጠች ራሷን አትርፋለች።

በሩጫ በምታመልጥበት ወቅት ሰዎቹ " ነቃሽብን አይደል " እንዳሏት ታስታውሳለች።

ታርጋውን ለማየት ባትችልም የመኪናው ቀለም ' ብሉብላክ ' ቶዮታ ቪትዝ እንደነበር አስተውላለች።

አካባቢው ጭር ያለም ስለሆነ ብዙ ከውጭ የሚመጡ ሰዎች የሚስተናገዱበት በመሆኑ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ መከታተል ይገባል።

የሜትር ታክሲ አገልግሎት የምትጠቀሙም " ኑ ታክሲ ይኸው " ብትባሉ እንዳትገቡ። ይልቁም ወደ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶቹ ስልክ በመወደል እና የተመዘገበ ህጋዊ መኪና ወደእናተ እንዲመጣ ማስደረግ አለባችሁ።

በማንኛውም ሁኔታ ስልካችሁ ባልተመዘገበበት እና ባለመኪናውም በድርጅት በህጋዊነት የተመዘገበ መሆኑን ሳታረጋግጡ ትራንስፖርት ለመጠቀም አትሞክሩ።

መንገድ ላይ የምትገቡም ከሆነ ስልካችሁን የግድ አስመስግባችሁ መልዕክት ሲመጣላችሁ ብቻ ተንቀሳቀሱ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamliyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ዓባይ ባንክ የተመሰረተበትን 15ኛ ዓመት በይፋ ማክበር ጀመረ
-------------------------------------------
ዓባይ ባንክ አ.ማ የኢትዮጵያ የግል ባንክ ዘርፍ በመቀላቀል የተሟላ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት የተመሰረተበትን 15ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በይፋ ማክበር ጀመረ፡፡

ባንኩ የተመሰረተበትን 15ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በይፋ ማክበር መጀመሩን አስመልክቶ በሀያት ሪጀንሲ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ የኋላ ገሠሠ እንደገለጹት፣ ባንኩ በተመሰረተ አጭር ጊዜ ውስጥ በሁሉም የሥራ አፈፃፀም መለኪያዎች እጅግ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን እና ለተገኘው ሁለንተናዊ የሥራ ስኬት የባንኩ ደንበኞች፣ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት፣ ባለአክሲዮኖች፣ የሥራ አመራር አባላት፣ ሠራተኞች እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የነበራቸው ሚና ከፍተኛ እንደነበረ አውስተዋል፡፡   የምስረታ በዓሉ በአጠቃላይ ለደንበኞች እና ለመላ የባንኩ ቤተሰቦች መሆኑን የጠቆሙት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ብሩህ አጀማመራችንን የሚዘክር እና የከፍታ መዳረሻችንን የሚያመላክትም ይሆናል ብልዋል፡፡  

ባንኩ በ823 መስራች ባለአክሲዮኖች በብር 125 ነጥብ 8 ሚሊዮን የተከፈለ ካፒታል ሥራ የጀመረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ እድገት በማስመዝገብ የባለአክሲዮኖችን ቁጥሩ 4 ሺህ 500 እንዲሁም የተከፈለ ካፒታሉን ብር 7 ቢሊዮን ማድረስ መቻሉ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተገልጿል፡፡

ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ!

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#AAiT

Announcement of Professional Training Programs

Python Programming + Data Analytics and Visualization

By: Addis Ababa University,
College of Technology and Built Environment,
School of Electrical & Computer Engineering

Registration Deadline: July 24, 2025

Training Starts on: July 26, 2025

Online Registration Link: https://forms.gle/M1DPS1zFP4K9QT4V6

Telephone: +251-913-574525/ +251-940-182870

Email: sece.training@aait.edu.et

For more information: https://forms.gle/M1DPS1zFP4K9QT4V6  

Telegram Channel: /channel/TrainingAAiT

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ሸዉደዉናል 5ዐ ሰዉ መርጣችሁ ስጡን ብለዉ ካስነሱን በኋላ የተወከሉትን ስብሰባ ጠርተዉ አስፈራርተዋል " - ነዋሪዎች

➡️ " የኛ ጥያቄ የወረዳውን የተወሰኑ ቀበሌያት ወደ ሀዋሳ ከተማ ክፍለ ከተማነት ለማጠቃለል መወሰኑ ተገቢነት የለዉም የሚል ነው ! "


የሲዳማ ክልል ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ የዶሬ ባፋኖ  አከባቢ ነዋሪዎች ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር አዲስ ተዋቀረ በተባለው የክፍለ ከተማ አደረጃጀት ከሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ 5 ቀበሌያትን ብቻ ነጥሎ መወሰዱን በመግለፅ ቅሬታ እንዳደረባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵየ ገልጸው ነበር።

ነዋሪዎቹ የተመረጡት ቀበሌያት ምርታማና የተሻለ የኢኮኖሚ አቅም ያላቸዉ በመሆኑ የወረዳዉን የመልማት አቅም ያዳክመዋል፤ ከዚህ ቀደም የተገባልንም ቃል ተግባራዊ አልተደረገም ሲሉ አደባባይ በመዉጣት " ጥያቄያችን እስኪመለስ ወደ ቤታችን አንመለስም " ማለታቸው አይዘነጋን።

" በዕለቱ ሕዝቡ ከሜዳ ላይ አልነሳ በማለቱ ምሽት ከ2 ሰዓት በኋላ የዞንና የወረዳ አመራሮች መጥተዉ 'ለነገ 50 ተወካዮችን መርጣችሁ ዉይይት እናድርግ' ብለዉ ሕዝቡ እንዲበተን ካደረጉ በኋላ በማግስቱ የተመረጡትን ተወካዮች ሰብስበዉ አስፈራርተዋቸው ስብሰባዉን ረግጠዉ ወጥተዋል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" አመራሮች ሸዉደዉናል 50 ሰዎችን መርጣችሁ ወክሉና እናንተ ወደ ቤት ተመለሱ እነሱ ነገ ከኛ ጋር ይወያዩ ብለው በሽማግሌዎች በኩል ሕዝቡ እንዲበተን ካደረጉ በኋላ በማግስቱ የተወከሉትን ሰዎች ' እናንተ ናችሁ ሕዝቡን የሚታሳምፁት ' ብለዉ በማስፈራራት ስብሰባዉን ጭምር ረግጠዉ ወጥተዋል " ሲሉ ገልፀዋል።

ዶሬ ባፋናና አከባቢዉ ያሉ ሌሎች ቀበሌዎች ከዚህ ቀደም በሀዋሳ ከተማ ስር ከመካለል ጋር ተያይዞ አንድ ላይ ዉሳኔው ያለ ልዩነት ተግባራዊ እንደሚደረግ እየተነገራቸዉ የቆየ ቢሆንም አሁን ላይ በወረዳው የተሻለ አቅም ያላቸው የተባሉ 5 ቀበሌያትን ብቻ ነጥሎ ' በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሀዋሳ ላንጋኖ ክፍለ ከተማ ' በሚል ሊደራጅ እንደሆነ መነገሩ ሕዝቡን ማስቆጣቱን ነዋሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገዉ ሙከራ የወረዳዉ አስተዳዳሪ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሳይሳካ ቀርቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamliyHawassa

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የታርጋ ቁጥሩ ኮድ3-48279 አ.አ የሆነ ተሽከርካሪ ተሰርቆብናል " - ድርጅቱ

ሮሜል ጀነራል ትሬዲንግ የተሰኘ ድርጅት ጃፓን ሰራሽ 5L የ2002 ሞዴል ታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3-48279 አ.አ የሆነ ሚኒባስ መኪና መሰረቁን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

መኪናው ሀምሌ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ አዲስ አበባ ከኡራኤል ወደ ወሎ ሰፈር በሚወስደው አዲሱ አስፓልት ላይ ' ሰላም አደባባይ ' ከመድረሱ በፊት ባለው ቦታ ከቆመበት በሌቦች እንደተሰረቀ አመልክቷል።

ድርጅቱ ይህንን በዕለቱ ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እንዳመለከተ ገልጿል።

" የመኪናው ልዩ ምልክት ዕቃ ለመጫን እንዲመች ከገቢና ቀጥሎ ያለው ወንበር ብቻ ያለው ሲሆን ሌላው የተፈታ ነው " ብሏል።

" መኪናችን ያለበትን ለጠቆመ ወይም ለያዘ ወረታ እንከፍላለን " ያለው ድርጅቱ " ለጥቆማ ስልክ ቁጥሮቻችን +251930078032 ፣ 0913324134 እና +251115620212 ናቸው " ሲል አመልክቷል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" አንዱ መኪና ተገኝቷል " - ባለንብረቶች

ከቀናት በፊት ለሊት 9 ሰዓት ላይ አዲስ አበባ ቃሊቶ ቶታል ኮንዶሚየም ግቢ ውስጥ የቆሙ ሶስት 5L ሚኒባስ ተሽከርካሪዎች በአንድ ጊዜ እንደተወሰዱ፣ አንደኛው እንደተገኘ ሌሎቹን ያየ ሰው እንዲቆጥማቸው ባለንበረቶቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች አሳውቀው ነበር።

መልዕክቱ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ከወጣ በኋላ አንዱ መኪና ማለትም ኦሮ ኮድ 03 34021 ጀሞ 2 አካባቢ መገኘቱን ገልጸዋል።

" መረጃዉን አይቶ ለደወለልን ግለሰብ እንዲሁም ለአቃቂ ቃሊቲ ፖሊስ አባላት ምስጋናችንን አድርሱልን " ብለዋል።

አሁን ላይ ተሽከርካሪውን በእጃቸው ለማድረግ ከፖሊስ እየጠበቁ መሆናቸውን አመልክተው " ተሽከርካሪዎቹን ይወስዳሉ ተብለው የተጠረጠሩት አልተያዙም ክትትል እየተደረገ ነው " ሲሉ ጠቁመዋል።

አሁንም ቀሪ አንዱን ተሽከርካሪ ኦሮ ኮድ 03 41867 ያየ እንዲጠቁማቸው ተማጽነዋል።

ከዚህ ቀደም ባለንብረቶቹ በጥበቃና ቀጣሪ ኤጀንሲው ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው ገልጸው የነበረ ሲሆን በዚህ ላይ ገና ፖሊስ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamliyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

Calling all #Ethiopian Innovators!

The second round of the Immunisation Innovation Accelerator is now open - offering up to $100,000 in grants to solutions that improve #vaccine access.

📅 Application deadline: July 27
🔗 https://www.stc-accelerator.org/

#ChildHealth #InnovationInAction #HealthInnovation #Ethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ቅሬታችንን ለዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት አስገብተናል " - የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ

የ‎ሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ከኢትዮጵያ ዋንጫ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያስተላለፈዉን ዉሳኔ በመቃወም ለዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት (CAS) የይግባኝ ደብዳቤ ማስገባቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታዉቋል።

ክለቡ ቅሬታዉን በየደረጃ ለፌዴሬሽኑም አስገብቶ ምላሽ ባለማግኘቱ ወደ ስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት ማለፉን የገልጿል።

ሲዳማ ቡና ከወላይታ ዲቻ ጋር ባደረጉት የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍፃሜ ጫወታ የሲዳማ እግር ኳስ ክለብ 2ለ1 አሸንፎ ዋንጫዉን ቢያነሳም " ያለ አግባብ ተጫዋቾችን አሰልፏል " በሚል ፌዴሬሽኑ ቡድኑ የወሰደዉን ዋንጫ ለወላይታ ዲቻ ተመላሽ እንዲያደርግ የሚል ዉሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

‎@tikvahethiopia

Читать полностью…
Subscribe to a channel