tikvahethiopia | Unsorted

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1527733

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Subscribe to a channel

TIKVAH-ETHIOPIA

“ ለውጪ አገር ዜጋ ቦታ ለመስጠት ብለው በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ለማፈናቀል እየተሯሯጡ ነው ” - 1400 አባላትን ያቀፈው ማኀበር

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው ' አጣና ተራ ' በተሰኘ ቦታ 1400 የሚሆኑ ሰዎች በተለያዩ ስራዎች የሚንቀሳቀስበትን ቦታ ያለ ምትክ “ ልቀቁ ” መባላቸውን ማኀበራቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቤቱታውን አሰማ።

“ ዜድቲኤም ማኀበር ” ከተመሰረተ 20 ዓመታትን እንዳስቆጠረ ገልጾ፣ “ ቦታው የሚሰጠው ለቻይናዊ ነው ተብሏል፤ ‘ለባለሃብት ተሰጥቷል ከቦታው ላይ ተነሱ’ ተብለናል ” ሲል ገልጿል።

“ ካሳም ሆነ ምትክ ቦታ አልተሰጠንም ” ያለው ማኀበሩ፣ “ መንግስት በሐምሌ ጨለማ ሜዳ ላይ አይጣለን፤ በሦስት ቀናት ውስጥ ወጥተን የት እንወድቃለን ? ” ሲል ጠይቆ፣ መንግስት አካባቢውን ለማልማት ጊዜ፣ ወይም ምትክ ቦታ እንዲሰጣቸው አሳስቧል።

ማኀበሩ በዝርዝር ምን አለ ?

“ ለውጪ አገር ዜጋ ቦታ ለመስጠት ብለው በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ለማፈናቀል እየተሯሯጡ ነው። የበላይ የመንግስት አካልም የሚያውቀው አይመስለንም። ከታች ያሉት አካላት አሻጥር እየሰሩ ህዝቡን በዚህ በሐምሌ ጨለማ ‘በሦስት ቀናት እቃህን ይዘህ ውጣ’ የሚል አሳዛኝ ድርጊት ነው እየተፈጸመ ያለው ” ብሏል።

ማኀበሩ፣ “ ትልቅ በደል ነው በህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው። ህዝቡ እያለቀሰ ነው፤ ምሳውን በልቶ እራቱን የማይደግም ህዝብ ነው ችግር ላይ እየወደቀ ያለው ” ሲልም ወቅሷል።

ቦታውን ከ50 ዓመት በፊት ጀምሮ ይሰሩበት እንደነበር የገለጸው ማኀበሩ፣ “ ነባር ቦታ ነው፤ ቤት ንብረት ተመስርቶ፣ በግለሰብም ተከራይቶ የሚኖርበት ቦታ ነው ” ብሏል።

“ አካባቢው ነባር መዘጋጃ ቤት ነው፤ በኃይለ ሥላሴ ጊዜ ተሰርቶ ለግለሰቦች የተከራየ ቤት ነው። በ1960 ዓ/ም የተያዘ ቦታ ነው። ከሱ ቤት ውስጥ ነው ውጡና ሜዳ ላይ ውደቁ የተባለው ” ሲልም አክሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታውን ይዞ ምላሽ የጠየቃቸው አንድ የክፍለ ከተማው አካል፣ “ ጉዳዩ አይመለከተኝም ” ብለው ስልክ ዘግተዋል፤ በድጋሚ ሲደወልም ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም፣ ተጨማሪ ጥረት ይደረጋል።
 
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ስያሜያችሁ ከብሔር ስም ጋር የተገናኘ ከሆነ መቀየር ይኖርባችኋል " - የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሀገሪቱ በሁሉም የሊግ እርከን የሚገኙ ክለቦች በ2018 የውድድር ዓመት ምዝገባ ወቅት የክለብ ስያሜያቸው ከብሔር ስም ጋር የተገናኘ ከሆነ በመቀየር ማስመዝገብ እንደሚኖርባቸው አዟል።

ከዚህም በተጨማሪ ክለቦች በኦፊሴላዊ መለያ (አርማ) ላይ ፖለቲካዊ እና የብሔር ይዘት ያላቸው መልዕክቶች እና ምስሎችን መጠቀም የተከለከለ መሆኑን ፌዴሬሽኑ አስገንዝቧል።

#Ethiopia🇪🇹

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#DStvEthiopia

🎬 በአቦል ቲቪ የሚተላለፉትን አዝናኝ እና አጓጊ ተከታታይ ድራማዎችን በ479 ብር ብቻ በጎጆ ፓኬጅ ላይ ይኮምኩሙ!

🌟 ፍርቱና- ዘወትር ሰኞ ከምሽቱ 2፡00
🌟 ግዛት- ከሰኞ-ረቡዕ ከምሽቱ 2፡30
🌟 ዕፀህይወት- ሀሙስ እና አርብ ከምሽቱ 2፡30
🌟 አፋፍ - ከሰኞ-አርብ ከምሽቱ 3፡30

ይህንን ሊንክ በመጫን የተለያዩ የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ያግኙ!
👇
https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/mabkg72w

#ሁሉምያለውእኛጋርነው

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ግብር

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱም የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅን በ5 ተቃውሞ፣ በ12 ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው ያፀደቀው።

በሕዝብ ተወካዮች ምር ቤት የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ የገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያው ከግብር ነጻ የሆነው ከመቀጠር የሚገኘ ገቢ ከፍ እንዲል የተደረገ በመሆኑ ፦
- ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ተቀጣሪዎች ላይ የግብር ጫናው እንደሚቀንስ፤
- የግብር መሰረቱ እንዲሰፋ፤
- መንግስት ከገቢ ግብር የሚያገኘው ገቢ በአንጻራዊ ሁኔታ ከፍ እንዲል አጋዥ መሆኑን አመልክተዋል።

በማሻሻያው ላይ ከበርካታ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እንደተደረገበት እና እንደ ቋሚ ኮሚቴም ሰፊ ጊዜ ተወስዶበት የተዘጋጀ ማሻሻያ ነው ብለዋል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ " ማሻሻያው ለረጅም ጊዜ ውይይት የተደረሀበት እና የሀገራት ልምድ የተወሰደበት ነው። ማሻሻያው ዘመኑን የዋጀ ነው " ሲሉ ተናገረዋል።

አዋጁን የተቃወሙ የምክር ቤት አባላት የገቢ ግብር ማሻሻያው የመንግስት ሠራተኛውን የኑሮ ሁኔታ ታሳቢ ያላደረገ ማሻሻያ በመሆኑ ምክር ቤቱ ማሻሻያውን በድጋሚ እንዲፈትሸው ጠይቀዋል፡፡

የገቢ ግብር አዋጁ ከዚህ ቀደም ሰፊ የክርክር ነጥቦች የተነሳባቸው ጉዳዮች ላይ ማስተካከያ ሳይደረግበት ነው በ5 ተቃውሞ ፣ በ12 ድምጸ ተዓቅዶ በአብላጫ ድምጽ የፀደቀው።

#HoPR🇪🇹
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#HoPR🇪🇹

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ እያካሄደ ባለው አስቸኳይ ስብሰባ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅ አጽዷል።

የተሻሻው አዋጅ በቀጣይ ዓመት ለሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ 26 አንቀፆች ላይ ማሻሻያ የተደረገበት ናው ተብሏል።

በተሻሻለው አዋጅ ሀገራዊ የፖለቲካ ፓርቲ ለመሆን የ6 ክልሎችን ድጋፍ ማግኘትን ያስገድዳል።

ምክር ቤቱ አዋጁን በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።

ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ስብሰባው ሰፊ ክርክር ሲነሳበት የነበረውን የፌደራል ገቢ ግብር ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ያጸድቃል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

የስታርት አፕ ረቂቅ አዋጅም ዛሬ ያጸድቃል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ጥቆማ
#ለሚመለከታችሁ_አካላት

" ይሄ የመብራት ፖል የመኖሪያ ቤት ላይ ወድቆ ጉዳት ሳያደርስ በፊት መፍትሄ ይፈለግለት " - ነዋሪዎች

ከላይ የተያያዘው ቪድዮ አዲስ አበባ፣ እንጦጦ ማርያምን በተለምዶ ' ሀሙስ ገበያ ' እየተባለ የሚጠራው አካባቢ ከሚኖሩ ነዋሪዎች የተላከ ነው።

በቪድዮው ላይ እንደሚታየው የመብራት ፖሉ ቤት ላይ ተንጋዶ ይገኛል።

አንድ የአካባቢው ነዋሪና የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል " የመብራት ፖሉ ቤት ተደግፎ ነው ያለው ፤ በተደጋጋሚ ለሚመለከታቸው አካላት ሄደን ብናመለክትም ምላሽ ሊሰጡን አልቻሉም " ብሏል።

" አሁን ከባድ ንፋስ እና ከባድ ዝናብ ስላለ አስጊ ሁኔታ ላይ ነው ያለው " ሲል ገልጿል።

" የሰው ህይወት እንዲሁም በንብረት ላይ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል ጥቆማውን ተመልክታችሁ የሚመለከታችሁ አካላት መፍትሄ እንድትወስዱ " በማለት ጥሪ አቅርቧል።

#TikvahEthiopiaFamliyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Oromiyaa

✅ 384,498 (78.7%) ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት አምጥተዋል !

የ2017 የኦሮሚያ ክልል 8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ይፋ ሆኗል።

በክልሉ ፈተናቸውን የወሰዱ ተማሪዎች ወንድ 251,120 ፤ ሴት 237,338 በድምሩ 488,458 ናቸው።

ከተፈተኑት ተማሪዎች መካከል ወንድ 205,113 (81.7%) ሴት 179,388 (75.6%) በድምሩ 384,498 (78.7%) ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት በማስመዝገብ ወደ ሚቀጥለው ክፍል ተዛውሯል።

ተማሪዎች ውጤት ለማየት oromia.ministry.et መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጿል።

መረጃው የተላከው ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ያጋጠመ ሞት የለም ! " - የአሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሰራተኞች

ዛሬ ምሸት በመቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ ምንድን ነው የተከሰተው ?

ባለቤትነቷ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነችው ET-A U Z አውሮፕላን ከአዲስ አበባ ተነስታ መቐለ አሉላ አባነጋ የአውሮፕላን ማረፍያ ከምሽቱ 1:52 ለማረፍ ስትል  ቀላል አደጋ አጋጥሟታል።

የአውሮፕላንዋ ዋናና ረዳት አብራሪ ፤ 2 ሰራተኞች እንዲሁም 49 ተጓዦች በአጠቃላይ 53 ሰዎች አሳፍራ ነበር። 

አውሮፕላንዋ በማረፍ ላይ እያለች በግራ ክንፋዋ በኩል አደጋ እንዳጋጠማትና የአደጋው መነሻ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ታውቀዋል። 

የአሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ ሰራተኞች ለድምፂ ወያነ ሚድያ በሰጡት መረጃ በአደጋው ያጋጠመ ሞት የለም። ተጓዦችም ወደየ ቤተሰቦቻቸው በሰላም እንደተሸኙ ገልጸዋል።

ሌሎች ያልተረጋገጡ ምንጮች ደግሞ በአደጋው የአውሮፕላንዋ ካፒቴን የሚገኙባቸው ጥቂት ተጓዦች ጉዳት ደርሶባቸው በመታከም ላይ መሆናቸውን ፅፈው አሰራጭተዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ጉዳዩን በተመለከተ ከሃኪሞች መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ለማግኘት ጥረት አድርጓል። ስለጉዳዩ ምላሽ የጠየቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ " እያጣራን ነው ያለነው፤ መግለጫ እናወጣለን " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

#TikvahEthiopiaFamliyMekelle
#TikvahEthiopiaFamliyAA

ፎቶው ፦ ድምፂ ወያነ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Ethiopia🇪🇹

" ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ የሚያደርጉ የአሜሪካ ፓስፓርት የያዙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ የሌሎች ሃገራት  ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች የኢትዮጵያን ቪዛ ለማግኘት ወደ አገራችን ሲመጡ ከተፈቀደላቸው የቆይታ ጊዜ በላይ በሀገራችን ሕግ መሠረት ቅጣት የሚያስከትል በመሆኑ ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግ ለማሳሰብ እንወዳለን " - አምባሳደር ነብያት ጌታቸው

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#MoE
#NationalExam🇪🇹

ትምህርት ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

የትምህርት ሚንስትሩ ፕ/ሮ ብርሃኑ ነጋ  " ባለፉት ሶስት አመታት በተወሰነ መልኩ ያጋጥሙ የነበሩ የጸጥታ ችግሮች፣ የፈተና ስርቆት ሙከራዎች፣ የፈተና ስርዓትና አስተዳደር የዲሲፒሊን ግድፈቶች በዘንድሮው አመት ቀንሰው ተገኝተዋል " ብለዋል።

ለዚህም " የበይነ መረብ የፈተና ሽፋን በአንድ አመት ውስጥ በአራት እጥፍ ማደጉ፤ የፈተና ግብረ ሀይሉ ያልተቆጠበ ጥረት፤ እንዲሁም ተማሪዎች ሰርቶ ውጤት ማምጣት አማራጭ የሌለው መፍትሄ መሆኑን መገንዘባቸው " ምክንያቶች ናቸው ሲሉ ገልጸዋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው " ፈተናው በ4 ዙሮች እንዲሠጥ ነው የተደረገው። በአራቱም ዙሮች የተሰጡ ፈተናዎች ተቀራራቢ (አቻ) ናቸው " ብለዋል።

በ2017 የትምህርት ዘመን በአጠቃላይ ከተመዘገቡ ተፈታኞች 608,742 መካከል 581,905 (95.6%) ፈተናውን እንደወሰዱ አመልክተዋል። ከነዚህም ውስጥ 134,828 (23.2%) በበይነ መረብ ብቻ የተፈተኑ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በአማራ ብሔራዊ ክልል ያሉ እና የተወሰኑ የህግ ታራሚዎች በድምሩ 4,966 ተፈታኞች ከነሐሴ
26-28/2017 ዓ/ም በሁለተኛ ዙር የተዘጋጀላቸውን ፈተና በወረቀት እንደሚወስዱ አመልክተዋል።

#MoE

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

" ዛሬ ወሬ የለም " - ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ

የሃይማኖት አባቶች ልዑክ በመቐለ !


ከአዲስ አበባ ተነስቶ በጥዋቱ ትግራይ ክልል መቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ የደረሰው የሃይማኖት አባቶች ልዑክ ከሁሉም የሃይማኖት ተቋማት የተወጣጣ ሲሆን አጠቃላይ ልዑኩ ከ20 በላይ አባላት አሉት።

የሰላም ልኡኩ ከአውሮፕላን ማረፍያ በቀጥታ ወደ መቐለ ፕላኔት ሆቴል አዳራሽ በማመራት በፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ከሚመራው የጊዚያዊ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት ጋር #በዝግ ተወያይቷል።

ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጄነራል) ከሰላም ልኡካኑ ጋር የነበራቸውን ቆይታ አጠቃልለው ሲወጡ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የሚገኙባቸው የጋዜጠኞች ቡድን መረጃ ፍለጋ ተጠግተው ነበር።

ፕሬዝዳንቱ በሳቅ ታጅበው " ዛሬ ወሬ የለም " በማለት ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

የሰላም ልኡኩ በሆቴሉ ጥቂት ደቂቃዎች እረፍት ወስዶ መልሶ በተመሳሳይ አዳራሽ ከትግራይ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ተወካዮች ጋር ተወያይቷል።

በዚሁ ወቅት በቦታው ላይ የነበሩ ጋዜጠኞች ውይይቱን ለመከታተል ጥያቄ ቢያቀርቡም መከታተል ይቅርና አዳራሹ ውስጥ እንዳይዘልቁና ፎቶም እንዳያነሱ ተከልክለዋል።

ከሰዓት በኃላ ከውይይቱ ተሳታፊዎች በተገኘው መረጃ የሰላም ልኡካኑ በመጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ተፈናቃዮች ጎብኝተው የማወያየት ፕሮግራም የነበራቸው ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት ይሄ ፕሮግራም ሳይካሄድ ቀርቷል።

የሰላም ልኡኩ ቀጥሎ ከህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ነው የተወያየው። ውይይቱ እንደ ጠዋቱ
#በዝግ መካሄዱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተረድቷል።

የድርጅቱ / የህወሓት ልሳን የሆነው የወይን ጋዜጣ ጋዜጠኞችም ጭምር ወደ ስብሰባው አዳራሽ እንዳይገቡ ተከልክለው ነው ውይይቱ የተካሄደው።

ከአዲስ አበባ የተጓዘው የሰላም ልኡክ ያካሄዳቸው የውይይቱ ርእሰ ጉዳዮች አልታወቁም። ከግምት ባሻገር የተሰጠ ይፋዊ መረጃ የለም። 

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ የሰላም ልኡኩ ቀኑን ሙሉ ከተለያዩ አካላት ጋር ያካሄደውን ውይይት በማስመልከት የሚሰጥ ጋዜጣዊ መግለጫ ይኖር እንደሆነ ለጊዚያዊ አስተዳደሩ የሚድያ ዴስክ ጠይቆ ያገኘው አመርቂ መልስ የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

ፎቶ፦ ትግራይ ቴሌቪዥን

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ኮደርላብ የ2025 የክረምት ካምፕን ይቀላቀሉ - ተማሪዎችን እናበቃ!

የኮደርላብ 2025 የክረምት ካምፕ ተማሪዎችን ዲጂታል ችሎታዎች፣ ኮድ ማድረግ፣ ሮቦቲክስ፣ የwebsite development እና ሌሎችንም ለማስተማር ዝግጅቱን ጨርሷል!

🚀 ከ6 እስከ 18 አመት ለሆኑ ተማሪዎች ክፍት ነው።

📅 የሚፈጀው ጊዜ፡- 4 ሳምንታት project based learning ( games , animations , python projects and website development)

🎓 የፕሮጀክት ማሳያዎችን፣ የቡድን ስራን እና የምስክር ወረቀቶችን ያካትታል

ክፍያ ለአጠቃላይ 4 ሳምንት ስልጠና 6000 Birr

📲አሁኑኑ በhttps://forms.gle/HcjfaWrmC9PWmzGM7 ይመዝገቡ
ወይምበ+251907945085 ይደውሉልን

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

በ2018 ዓ.ም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የጥራት ቁጥጥር እንደሚጀመር ታውቋል።

የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን፣ በመጪው አመት 2018 ዓ.ም በመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ የጥራት ቁጥጥር እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡

የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ውብሸት ታደለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃለመጠይቅ፣ በአሁን ወቅት በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ እየተካወነ ያለው ዳግም ምዝገባና ምዘና ስራ ሲጠናቀቅ ይኸው እንቅስቃሴ በመንግስት ኮሌጆች፣ የማሰልጠኛ ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች ላይም በቀጣዩ አመት እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

አቶ ውብሸት ታደለ በዝርዝር ምን አሉ ?

" አሁን እየተከናወነ ያለውን የመጀመሪያው ዙር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ምዝገባና ግምገማ እንደጨረስን፣ በሁለተኛውና በሶስተኛው ዙር የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን እንመዘግባለን፣ እንገመግማለን፡፡ በፌደራልና በክልሎች የተከፈቱ ኮሌጆችና የማሰልጠኛ ተቋማት አሉ፡፡ መጀመሪያ የምናየው እነሱን ነው፡፡ ቀጥለን ደግሞ ሁሉንም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን እናያለን፡፡

እስካሁን የግል ተቋማት ላይ ያተኮርነው፣ እዚህ ዘርፍ ላይ የነበረው ችግር ሰፊ ስለሆነ ነው፡፡ ያለንን የሰው ሀይልና ሀብት ወደዚህ ዘርፍ በማዞር ቅድሚያ ሰጥተናል፡፡ ሁሉንም አንድ ላይ ማየት አንችልም፡፡ አሁን የግሎቹን ተቋማት ካጠናቀቅን በኋላ፣ ወደ መንግስት ትምህርት ተቋማት ግምገማ እንገባለን፡፡

የመንግስት የትምህርት ተቋማት በመሰረተልማት በኩል ችግር የለባቸውም፡፡ የራሳቸው ህንፃና ግቢ አላቸው፡፡ ስለዚህ እነሱ ጋ ትኩረት የምናደርገው ጥራት ላይ ነው፡፡ ለምሳሌ ፕሮግራሞቹ/ትምህርቱ በበቂ መምህራንና አኳሀን መሰጠቱን እናያለን፡፡ አካዳሚያዊ የድርጊት መርሀግብራቸው ትክክል መሆኑን እንፈትሻለን፡፡

የተገቢነትና አስፈላጊነት ጥያቄ የሚነሳባቸው፣ ዝም ብለው ያለ በቂ ጥናት የሚከፈቱ ፕሮግራሞች አሉ፡፡ የትምህርት ግብአት እና የላቦራቶሪ ቁሳቁሶች፣ እንዲሁም የዳታ ማዕከላቸው ይታያል፡፡ ለተማሪዎችና ለአስተማሪዎች የሚቀርቡት አገልግሎቶች ደረጃቸውን የጠበቁ ናቸው ወይ የሚለውን እናያለን፡፡

ቀደም ብለው የተቋቋሙት ነባሮቹ ዩኒቨርሲቲዎች የዚህ አይነት ችግር ላይኖርባቸው ይችላል፡፡ አዳዲሶቹ ዩኒቨርሲቲዎች ግን በነዚህ መስፈርቶች በኩል ክፍተት ይኖሩባቸዋል፡፡

በአጠቃላይ ግን ጥራትን እናምጣ ካልን፣ ሁሉንም የመንግስት ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎችን መፈተሽ አለብን፡፡ በዳግመ ምዝገባችን፣ በተቋማቱ የሚሰጡትን ሁሉንም ፕሮግራሞቻቸውን እናያለን፡፡ ፋይሎቻቸውን እንዲያስገቡ አድርገን እያንዳንዱን ፕሮግራም እንመዝናለን፡፡ አያስፈልጉም የምንላቸውን ፕሮግራሞች እንዲዘጉ፣ ያስኬዳሉ የምንላቸውን ደግሞ እንዲያስቀጥሉ እናደርጋለን፡፡

የመንግስት ተቋማትን ከግሎቹ በበለጠ ጠንከር ያለ ምዘና እናደርጋለን፡፡ ጠበቅ አድርገን ለማየት እንሞክራለን፡፡ የግሎቹን እንደጨረስን፣ በየክልሉ ያሉትንና በፌደራል ደረጃም ያሉትን ኮሌጆችና የማሰልጠኛ ተቋማትን እናያለን፡፡ ከዛም ወደ ዩኒቨርሲቲዎች እንሔዳለን፡፡ ይህ ስራ በ 2018 ዓ.ም የሚጀመር ይመስለኛል " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

Addis Ababa University

Announcement of Professional Training Programs

Python Programming + Data Analytics and Visualization

By: Addis Ababa University,
College of Technology and Built Environment,
School of Electrical & Computer Engineering

Registration Deadline: July 24, 2025

Training Starts on: July 26, 2025

Online Registration Link: https://forms.gle/M1DPS1zFP4K9QT4V6

Telephone: +251-913-574525/ +251-940-182870

Email: sece.training@aait.edu.et

For more information: https://forms.gle/M1DPS1zFP4K9QT4V6  

Telegram Channel: /channel/TrainingAAiT

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" እሳተ ገሞራው እንደፈነዳ መረጃው ደርሶናል፣ ከዚህ በፊት ያልነበረ በጣም ከፍተኛ አቧራ እየወጣ ነው " - ሰመራ ዩኒቨርሲቲ

በአፋር ክልል የኤርታሌ እሳተ ገሞራ እየፈነዳ መሆኑን ሰመራ ዩኒቨርሲቲና አንድ የዘርፉ ባለሙያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የጂዖሎጂ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ኖራ ያኒሚኦ በሰጡን ገለጻ፣ እሳተ ገሞራው መፈንዳቱን ከአካባቢው ማህበረሰብ ማረጋገጣቸውን ገልጸው፣ ለነዋሪዎቹ የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፈዋል።

" እሳተ ገሞራው እንደፈነዳ መረጃው ደርሶናል፣ ከዚህ በፊት ያልነበረ በጣም ከፍተኛ አቧራ እየወጣ ነው " ያሉት ተመራማሪው፣ " በአካባቢው በሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳት ሊያስከትል ስለሚችል ቢያንስ እዛ አካባቢ ያለውን ህዝብ ማራቅ የሚቻልበት መንገድ ቢፈጠር ጥሩ ነው " ሲሉ አስገንዝበዋል።

" ኤርታሌ በቀን በጣም ብዙ ሰው የሚጎበኘው ቦታ ስለሆነ ወደዚያ የሚሄዱ ጎብኝዎች ጥንቃቄ ያድርጉ፣ ምክንያቱም የሚፈጠረው ነገር አይታወቅም " ሲሉም ተናግረዋል።

" ከዚህ በፊት ኤርታሌ ላይ እንደዚህ አይነት ነገር የተለመደ አልነበረም፣ እሳት ገሞራ ከመፍሰስ ውጭ፣ አሁን ግን ብናኞቹ ወደሰማይ እየወጡ ስለሆነ ጉዳትም ሊያስከትል ይችላል " ያሉት አቶ ኖራ፣ ክስተቱ እስከሚረጋጋ ድረስ ወደ አካባቢው ቀርበው ፎቶ የሚያነሱ ሰዎች እየተስተዋሉ በመሆኑ ከዚህ ተግባር እንዲታቀቡ አሳስበዋል።

አክለው፣ " አንድ ልጅ በጣም ተጠባብሶ ፎቶ እያነሳ ነበር " ሲሉ የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ተጨማሪ ማብራሪያ የጠየቅናቸው አንድ የዘርፉ ባለሙያ በበኩላቸው፣ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታው እንደተከሰተ ገልጸው፣ ጉዳዩን ይበልጥ ለማጣራት በውጭ ሀገራት ከሚገኙ ባለሙያዎች ጋር እየተነጋገሩ እንደሆነ፣ መረጃውን አጣርተውም ተጨማሪ ማብራሪያ እንደሚሰጡን ነግረውናል።

ግን እሳተ ገሞራው ተከስቷል መባሉ ትክክል ነው ? ስንል  ላቀረብንላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽም "እውነት ነው። እየፈነዳ እንደሆነ ሰምቻለሁ፣ ፎቶግራፎችም ደርሰውኛል " ብለዋል።

" ዛሬ ምሳ ሰዓት አካባቢ እንደተከሰተ ነግረውኛል፤ ከአፋር ክልልም ደውየ አጣርቻለሁ " ብለው፣ " የሳተላይት መረጃዎችን እያጠናከርን ነው " ሲሉም ተናግረል።

በአካባቢው ላለፉት በርካታ ዓመታት ተደጋጋሚ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ያስተናገደ ሲሆን፣ በተለይም ከ2017 ዓ/ም ጀምሮ ከፍተኛ ፍንዳታዎችን እንደታዩ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ በስፋት እንደተከሰተ ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ጳጉሜ ወር ላይ ይፋ ይደረጋል " - ትምህርት ሚኒስቴር

➡️ " መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ/ም ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ይቀበላሉ ! "


የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ጳጉሜ ወር 2017 ዓ/ም ላይ ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴር ትላንት በሰጠው መግለጫ ላይ ለመስማት ተችሏል።

ትምህርታቸውን በሰላምና ደህንነት ምክንያት ዘግይተው በጀመሩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ያሉ ተማሪዎች እንዲሁም የተወሰኑ የህግ ታራሚዎች ፈተናውን ነሀሴ ወር ላይ እንደሚወስዱ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አሳውቀዋል።

አጠቃላይ ፈተናውን የሚወስዱት 4,966 ተፈታኞች ሲሆኑ ፈተናውን ከነሐሴ 26 - 28/2017 ዓ/ም ድረስ በወረቀት እንደሚወስዱ ተገልጿል።

እንዚህ ተማሪዎች ፈተናቸውን ከወሰዱ በኃላ አጠቃላይ የሁሉም የ2017 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ጳጉሜ ወር ላይ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ/ም ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች እንደሚቀበሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

#MoE

#TikvahEthiopiaFamliyAA
@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" 75 ሚሊዮን ብር ከህጋዊ አደን ገቢ ተገኝቷል " - የኦሮሚያ ክልል ደን እና ዱር እንስሳት ድርጅት

በ2017 በጀት ዓመት በኦሮሚያ ክልል በተደረጉ ከህጋዊ አደን 75 ሚሊዮን ብር ገቢ መግኘቱን የክልሉ ደን እና ዱር እንስሳት ድርጅት የዱር እንስሳት ልማት እና አጠቃቀም ባለሙያ የሆኑት አሸናፊ መንግስቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

በክልሉ ባሌ ፤ አርሲ እና ሀራርጌ ዞኖች ውስጥ በበጀት ዓመቱ ማርጀታቸው የተረጋገጠ 250 የተለያዩ የዱር እንስሳቶች ለህጋዊ አዳኞች ለመሸጥ ታቅዶ 176 የሚሆኑት ተሽጠው ከነዝህ ውስጥ 147 በህጋዊ መንገድ ታድነዋል ብለዋል።

ለአደን ከተሸጡት ውስጥ 22ቱ የደጋ አጋዘን ሲሆኑ አንድ የደጋ አጋዘን በአስራ አምስት ሽህ ዶላር እንደታደነም አቶ አሸናፊ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አዳኞቹም የደጋ አጋዘን ካደኑ በኋላ ቀንዱን እና ቆዳውን እንደሚወሰዱ የገለፁት ባለሙያው አዳኞቹ በስህተት ያላረጁ ዱር እንስሳት ከገደሉ ከዋጋው በእጠፍ እንዲከፍሉ ቅጣት ተቀምጧል ብለዋል።

ከተሸጡት ውስጥም ያልታደኑ መኖራቸውንም ነው ያነሱት።

ከአደን ከተገኘው ገቢ ውስጥ 11 ሚሊየን የሚሆነው ገንዘብ ለፌደራል ደን እና ዱር እንስሳት የሚሰጥ ሲሆን ቀሪው ለክልሉ ደን እና ዱር እንስሳት ድርጅት እና በፖርኮቹ አካባቢ በማኅበር ተደራጅተው ለሚሰሩ ስዎች ገቢ ይደረጋል ብለዋል።

የተገኘው ገቢም ለመሰረተ ልማት ማሟያ ፤ለአዳኞች ምቹ የሆኑ የመቆያ ስፍራዎችን ማመቻቸት፤ በፓርኩ ውስጥ ላሉ የተለያዩ እንስሳቶች ለመንከባከብያ ይውላል ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነቀምቴ
TikvahEthiopiaFamilyNekemte

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#National_ID_Program

ተጨማሪ የመረጃ ማስተካከያ ጣቢያዎች

የመረጃ ስህተት ሲገጥም እንዲሁም መረጃ መቀየር ቢያስፈልግዎ በአቅራቢያዎ የሚገኝ የመረጃ እድሳት አገልግሎት ሰጪ ጣቢያ መሄድ እንደሚችሉ ያውቃሉ?

እነዚህን እና ተጨማሪ የምዝገባ ጣቢያዎች ለማግኘት id.gov.et/updatecenters ይመልከቱ። ነገር ግን በምዝገባ ቅጽ ላይ የሞሉት መረጃ በመዝጋቢ ባለሙያ በስህተት ከተመዘገበ መረጃዎን ለማስተካከል በአካል መሔድ ሳይጠበቅብዎ id.gov.et/update ላይ ወይም "Fayda ID" የሞባይል መተግበሪያን በመጠቀም በቤትዎ ሆነው የተሳሳተ መረጃዎን እንዲስተካከል መጠየቅ ይችላሉ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #አካታች

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

የፌደራል ገቢ ግብር አዋጅ ፀደቀ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል ገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አፀደቀ።

ረቂቅ አዋጁ በአብላጫ ድምጽ ነው የፀደቀው።

ረቂቅ አዋጁ ላይ ሰፊ ክርክር ሲነሳበት እንደነበር ይታወቃል። በተለይ የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማሕበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) ረቂቅ አዋጁ ላይ የደመወዝ ገቢ ግብር መነሻ ተብሎ የተቀመጠው 2,000 ብር ወደ 8,324 ብር ከፍ እንዲል ፤ አጠቃላይ አዋጁ የኑሮ ውድነቱንና ጫናውን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንዲታረም ሲወተውት ነበር።

ከ0 ጀምሮ 10% ፣ 15% ፣ 20% ፣ 25% ፣ 30% ፣ 35% ይቀጥል የነበርው የግብር ምጣኔም በረቂቅ አዋጁ 10% ከመሃል ወጥቶ ከ0 ጀምሮ ቀጥታ ባከፍተኛው 15% መጀመሩንም ታቃውሞ ነበር።

ሌላው 14,100 በላይ የሚያገኝ ሰው 35% ግብር ይከፍላል በሚለው ላይም ጥያቄ ተነስቶ ነበር።

በአሁኑ የኑሮ ውድነት ሰራተኛው በእያንዳንዱ ነገር በምግብ ዋጋ፣ በሚገዛው እቃ 15% ይጨምራል ይሄ በ35% ላይ ሲደመር 50% ይመጣል፤ 7% የጡረታ አለ ሲደመር 57% ከደመወዙ ላይ ይሄዳል በቀረችው 43% ልጆች ያስተምራል ፣ ምግብ ይበላል ፣ ልብስ ይገዛል ፣ ቤት ይከራያል ምንድነው የሚያደርገው ? የሚል የሰራተኛውን ጥያቄ በማንሳት ረቂቁ እንዲታረም ጠይቆ ነበር።

ኮንፌዴሬሽኑ ፤ " መኖር ከማይችል እና በልቶ ከማያድር ሰው ግብር አይሰብሰብም " ብሎም የነበረ ሲሆነ " እንደ ሀገር ግብር መሰብሰብና ልማትም መቀጠል አለበት ፤ የሰው ህይወትም ግን መቀጠል አለበት ፤ ሰው እየተራበ መስራት አይችልም ምርታማ መሆን አይችልም " በማለት ረቂቁ እንዲታረም ብርቱ ጥያቄ አቅርቦ ነበር።

ሌሎችም አካላት ሰፊ ክርክር ሲያደርጉበት የነበረው ረቂቅ አዋጅ በዛሬው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአብላጭ ድምጽ ፀድቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamliyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የመፍረስ አደጋ የተጋረጠበት ተቋም !

" ከደመወዝና ሰራተኞች ጥቅማጥቅም ባሻገር የዚህ አንጋፋ ተቋም ህልዉና አደጋ ዉስጥ መሆን ያሳስበናል " - የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ሠራተኞች


የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ከቀድሞዉ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መፍረስ በኋላ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዉ እየተዳከመ መጥቶ አሁን ላይ ፦
- የሰራተኞች ደመወዝ ፣
- የደሞዝ ማሻሻያ (Back Payment)፣
- የደረጃ ዕድገትና ሌሎችም ጥቅማጥቅሞች መክፈል አለመቻልን ጨምሮ የመፍረስ አደጋ እንደተጋረጠበት የተቋሙ ሠራተኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ስማቸዉ እንዲገለፅ ያልፈለጉ አንድ የድርጅቱ አንጋፋ ጋዜጠኛ ፥ " ተቋሙ አሁን ላይ የተጋረጠበት አደጋ በወር ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም አለመኖር ብቻ የሚመዘን ሳይሆን የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦች ድምፅ በመሆን ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት  በልማት፣ መልካም አስተዳደደርና በደሞክራሲ ግንባታ ረገድ ጉልህ አበርክቶ ያለዉ ከመሆኑም በላይ ለሀገራችን የሚዲያዉ ኢንዱስትራ በርካታ ባለሙያዎችን ያፈራ አንጋፋ ተቋም እንደመሆኑ በዚህ ልክ አስታዋሽ ያጣ መሆን አልነበረበትም " ብለዋል።

ሌሎች ሰራተኞች በበኩላቸው " የደመወዝና ስራ ማስኬጃ በጀት ከአራቱ ክልሎች እየተዋጣለት እስካሁን የቆየዉ ድርጅቱ ባለቤት አልባ፣ ተቆርቋሪ እና ጠያቂ ያጣ ስለመሆኑ ማሳያ የሚሆነዉ እስካሁንም ዋና ስራ አስፈፃሚዉን ጨምሮ የተቋሙ አመራሮች በዉክልና ለረጅም ጊዜ የቆዩ መሆናቸው ነው " ብለዋል።

" ግምገማ ኦዲትና የቅርብ ክትትል የሚያደርግ አካልም ባለመኖሩ ከደመወዝና ሰራተኞች ጥቅማጥቅም ባሻገር የዚህ አንጋፋ ተቋም ህልዉና አደጋ ዉስጥ እንደሆነ ይሰማናል " ሲሉ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው ከዚህ ቀደም በተቋሙ የሰሩ በአሁኑ ወቅትም በሀገራችን ትልልቅ የሚዲያ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎች " ከ48 ቋንቋዎች በላይ ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ የሚደርሰዉ ይህ አንጋፋ ተቋም በዚህ ልክ ትኩረት መነፈጉና ለበርካቶች ድምፅ መሆን የቻሉ ጋዜጠኞችና የሚዲያ ባለሙያዎች በዚህ ልክ ትኩረት ተነፍገዉ ማየት በጣም ያሳዝናል " ሲሉ ሃሳባቸዉን ገልፀዋል።

" የፌደራል መንግስት ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላትም ለዚህ ተቋም መጠናከር የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል" ሲሉ ባለሙያዎቹ አክለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamliyHawassa

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ሴጅ_ማሰልጠኛ_ኢንስቲትዩት

የሁለት ወር የኢንቴሪየር ዲዛይን (Interior Design) የክረምት ስልጠና ሐምሌ 14/2017 ዓ.ም ይጀመራል።

👉 Sketch-Up, Revit, Autocad, 3D Max እና Lumion ሶፍትዌሮችን በአንድ ላይ
👉 ስልጠናውን ልዩ የሚያደርገው ከንድፈ ሀሳብ እና ሶፍትዌር ስልጠና በተጨማሪ በተግባር በወርክሾፕም  የሚሰጥ በመሆኑ ነው።

የበለጠ ይጠብቁ ...

☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
Tiktok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
Linkedin: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምን አለ ?

" በመንገደኞቻችን ላይ ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም፤ በሁለት የበረራ ሰራተኞች ላይ መጠነኛ ጉዳት አጋጥሞ ህክምና ተደርጎላቸው ወደ ሆቴል ተመልሰዋል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ


የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET-298 በዛሬው ዕለት ከአዲስ አበባ ተነስቶ መቐ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ካረፈ በኋላ ከአውሮፕላን መንደርደሪያው መጠነኛ የመንሸራተት እክል እንዳጋጠመው አየር መንገዱ ገልጿል።

አውሮፕላኑ በሚያርፍበት ጊዜ ዝናብ እየዘነበ እንደነበረም አመልክቷል።

አየር መንገዱ እስካሁን ባለው መረጃ በመንገደኞቻችን ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰና በሰላም ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ እንደተደረገ ገልጿል።

በሁለት የበረራ ሰራተኞች ላይ ግን መጠነኛ ጉዳት በማጋጠሙ ለተጨማሪ የህክምና ዕርዳታ በአቅራቢያ ወደሚገኝ የህክምና መስጫ ተቋም ተወስደው ከታከሙ በኋላ ወደ ሆቴል እንዲሄዱ መደረጋቸውን አሳውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው የደንበኞች መጉላላት ይቅርታ ጠይቋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ግብር

" መኖር ከማይችል ሰው ግብር አትሰበስብም ፤ በልቶ ከማያድር ሰው ግብር አትሰበስብም ! " - አቶ ካሳሁን ፎሎ


➡️ " እንደ ሀገር ግብር መሰብሰብ አለበት ልማትም መቀጠል አለበት ፤ የሰው ህይወትም መቀጠል አለበት ፤ ሰው እየተራበ መስራት አይችልም ምርታማ መሆን አይችልም ! "


የኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ዋና ፕሬዘዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ስለ ገቢ ግብር አዋጁ ምን አሉ ?

" የደመወዝ ገቢ ግብር ከዚህ በፊት መነሻው 600 ብር ነው፤ አሁን በረቂቁ የቀረበው 2,000 ሆኖ ነው።

በመሰረቱ 600 በሆነበት ሰዓት አንደኛ ገንዘብ የመግዛት አቅሙ ትልቅ በመሆኑ ፣ 1 ዶላርም 20 ብር ነበር ያኔ የዛሬ 10 ዓመት አካባቢ ነው ይሄ ነገር የተሻሻለው ፤ ሁለተኛ የመንግሥት ሰራተኞች መነሻ ደመወዝ 600 ነበር ያኔ 600 ለአንድ ሰው ለአንድ ወር ቢያንስ ምግብ መብላት ብቻ ይበቃዋል በሚል ታሳቢ አማካይ ተወስዶ ነው 600 የተባለው።

አሁን ግን 300% ፣ 200% ጨመርን (ማለትም 2000 ብር አደረግን) እሱ አይደለም ዋናው መነሻው ስንት ነው አሁን ? በአጭሩ ፤ እንኳን የኑሮ ውድነቱን ታሳቢ ያደረገ መንግሥት እራሱ ሰራተኛው በ600 ብር ሊያኖረው አይችልም ፤ የኑሮ ውድነቱ ከሚታሰበው በላይ በተለይም በሪፎርሙ መንግሥት በይፋ ያረጋገጠው ታችኛው የሰራተኛ ክፍል ጎድቶታል፤ ' ሊቋቋመው አይችልም ' በሚል መነሻ ደመወዙን ከፍ አድርጓል ፤ መነሻ ደመወዝን ከፍ ሲያደርግ ይሄን ታሳቢ አድርጓል።

አሁንም ቢሆን እነዚህ ሰዎች መኖር ከማይችል ሰው ግብር አትሰበስብም ፤ በልቶ ከማያድር ሰው ግብር አትሰበስብም። በቀን 2.15 ዶላር የሚያገኝ ሰው ድሃ ነው ከዚያ በታች የሚያገኝ በሙሉ ድሃ ነው ፤ እኛ ደግሞ እዛ ሁሉ አልደረስንም።

እኛ እያቀረብን ያለነው ሃሳብ 8,324 መነሻ ይሁን ነው። እንኳን የኛ ሀሳብ የመንግሥት እራሱ ያስቀመጠው መነሻ ላይ እንኳን አልደረሰም።

ሌላው በፊት የግብር ምጣኔው ከ0 ጀምሮ 10% ፣ 15% ፣ 20% ፣ 25% ፣ 30% ፣ 35% ይቀጥል ነበር አሁን 10%ን ከመሃል አወጡና ከ0 ጀምረው ቀጥታ 15% ነው የገቡት። አሁን ቀጥታ ከ15 ከከፍተኛው ነው ሲጀምር የጀመሩት። ይሄ ትክክል አይደለም።

35% ከየት ጀመረ 14,100 በላይ የሚያገኝ ሰው 35% ግብር ይከፍላል ፤ 35% ከሰራተኛ በአሁኑ የኑሮ ውድነት 15% በእያንዳንዱ በምግብ ዋጋም፣ በሚገዛው እቃም 15% ይጨምራል ይሄ ሲደመር 50% ይመጣል፤ 7% የጡረታ አለ ጡረታ የሚያገኘው ከ60 ዓመት በኃላ አሁን ግን 57% ከደመወዙ ላይ ይሄዳል በቀረችው 43% ፦
- ልጆች ያስተምራል
- ምግብ ይበላል
- ልብስ ይገዛል
- ቤት ይከራያል ምንድነው የሚያደርገው ?

ይሄና ይሄ ብቻ ስላልሆነ ነው ዝም ያልን እንጂ ይሄም ከፍ ብሎ እኮ ይበቃል ማለት አይደለም።

ግን እንደ ሀገር ግብር መሰብሰብ አለበት ልማትም መቀጠል አለበት ፤ የሰው ህይወትም መቀጠል አለበት ፤ ሰው እየተራበ መስራት አይችልም ምርታማ መሆን አይችልም። "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamliyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#HoPR🇪🇹

ነገ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ያካሂዳል።

በዚህም ስብሰባ ሰፊ ክርክር ሲካሄድበት ብዙ ሃሳቦች ሲሰነዘሩበት የነበረውን የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ ያጸድቃል።

ረቂቅ አዋጁ በንግዱ ማህበረሰብና በተቀጣሪ ሠራተኞች ላይ ሊጣል የታሰበው የግብር ምጣኔ ከፍተኛ ነው የሚል ቅሬታ ሲነሳበት ቆይቷል።

አሁን ካለው የኑሮ ውድነትና የዋጋ ንረት አኳያ፣ እስከ 35 በመቶ የሚደርሰው የገቢ ግብር መጠን መቀነስ እንዳለበት ሲጠቆም ነበር።

የገቢ ግብር መነሻው 2,000 ብር ተብሎ የተቀመጠው ዝቅተኛ በመሆኑ መጠኑ ከፍ እንዲል ሲጠየቅ ነበር።

ለአካል ጉዳተኞች የግብር መጠኑ በተለየ መልኩ እንዲቀነስ እና ከተለያዩ የሙያና የንግድ ዘርፎች አንጻር የአዋጁ ድንጋጌዎች በደንብ ታይተው መስተካከል እንዳለባቸው ሲጠየቅ ነበር።

መንግስት ሲሰጥ የነበረዉ ማብራሪያ ደግሞ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተደርጎ የታክስ ፍትሀዊነትን እና የኢኮኖሚ ልማት እንዲሁም እድገትን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ እንደሆነ ገልጿል።

ም/ቤቱ ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን እንዲሁም የስታርታፕ ረቂቅ አዋጅን ያፀድቃል።

መረጃው ከህ/ተ/ም/ቤት እና ካፒታል ጋዜጣ የተውጣጣ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ፎቶ፦ በአፋር ክልል አፍዴራ ወረዳ ትናንት በነበረ ዝናብ አዘል ከባድ ነፋስ የሰው ህይወት ጠፍቷል ፤ በንብረት ላይም ከባድ ጉዳት መድረሱን የአፋር ክልል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ገልጿል።

በአደጋው የ1 ሰው ሕይወት አልፏል።

በተጨማሪም በ32 ሰዎች ላይ ከባድ ፤ በ22 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት መደረሱ ተመላክቷል።

አደጋው በ3 ባንኮች፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና በኢትዮ ቴሌኮም መሠረተ ልማቶች እንዲሁም በ5 የጨው ፋብካዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

ትምህት ቤቶች እና ጤና ጣቢያዎችን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት በአደጋው ተጎድተዋል።

በዚህ ዝናብ በቀላቀለ ከባድ ነፋስ በከተማው ጉዳት ያልደረሰበት አንድም ቤት የለም ተብሏል።

የዚህ መረጃ ባለቤት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Sidama

🔴 የሲዳማ ክልል ም/ቤት አቶ ዳዊት ዳንግሳን የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አድርጎ ሾመ።

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ምርጫ ዙር 4ኛ ሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ላለፉት ሶስት ቀናት በ11 አጀንዳዎች ላይ ሲወያይ ቆይቷል።

በዚህም የ2018 ዓ/ም በጀት፣ የተለያዩ ሹመቶችን እንዲሁም አዳዲስ አዋጆች በማፅደቅ ተጠናቋል።

በጀትን በሚመለከተ ፦

የክልሉን የ2018 ዓ.ም በጀት 32 ቢሊዮን 823 ሚሊዮን 357 ሺህ 21 ብር እንዲሆን አፅድቋል።

ከበጀቱ 19 ቢሊዮን 336 ሚሊዮን 298 ሽህ 596 ብር ከክልሉ የውስጥ ገቢ የሚሰበሰብ እንደሆነም ተመላክቷል።

ሹመትን በሚመከተ ፦

ምክር ቤቱ በርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ደስታ ሌዴሞ የቀረቡ ሹመቶችን ተቀብሎ ያፀደቀ ሲሆን በዚሁ መሰረት :-

➡️ አቶ ዳዊት ዳንግሳ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ (በዚህ ቦታ የነበሩት አቶ አለማየሁ ጢሞቲዮስ በወንጀል ተጠርጥረው መታሰራቸው ይታወሳል)
➡️ አቶ ፍቅሬኢየሱስ አሸናፊ የመሬት አስተዳደር እና ኢንቨስትመንት ቢሮኃላፊ
➡️ አቶ ቢንያም ሰለሞን በጠቅላ ፍርድ ቤት የፍርድ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት
➡️ አቶ ገነነ ሹኔ በጠቅላይ ፍርድ ቤት የአስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነዉ ተሹመዋል።

ፍትሕን በሚመለከት ፦

በክልሉ በ2017 በጀት ዓመት በወንጀል እና ፍትሐብሔር መዝገቦች 43 ሺህ 653 አዳዲስ የክስ መዝገቦች የቀረቡ እንዲሁም 1 ሺህ 480 መዝገቦች ከካለፈው ዓመት የዞሩ በድምሩ 45 ሺህ 133 የክስ መዝገቦች ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን  44 ሺህ 307 መዝገቦች ውሳኔ ማግኘታቸውንና ቀሪዎቹ 826 መዝገቦች ለቀጣይ ዓመት መዘዋወራቸዉ በጉባኤዉ ላይ ተገልፆል።

ኦዲትን በሚመለከት ፦

ለምክር ቤቱ በቀረበዉ ልዩ ልዩ የኦዲት ሪፖርቶች በሲዳማ ክልል የበጀት አስተዳደር፣ ውሎ አበል፣ በነዳጅ ክፊያና በፕሮጀክቶች አፈፃፀም እና ጥራት ላይ የታዩ ክፍተቶቾ ለምክር ቤቱ ቀርበዋል።

በምክር ቤቱ ከተነሱ የኦዲት ሪፖርቶች መካከል ፦
° ያለ አግባብ የተከፈለ የአበል ብር 2,567,732,09 /ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ስልሳ ሰባት ሺ ሰባት መቶ ሰላሳ ሁለት ብር ከዘጠኝ ሳንቲም/ ፤

° ያላግባብ የተከናወነ የነዳጅ ግዢ ብር 60,940,354,58 /ስልሳ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አርባ ሺ ሶስት መቶ ሃምሳ አራት ብር ከሃምሳ ስምንት ሳንቲም/ ይገኙበታል።

አዋጆችን በተመለከተ ፦

የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 50/2017 ዓ/ም ፣ የአስፈጻሚ አካላት ማቋቋሚያ፣ ስልጣንና ተግባር  ለመወሰን የወጣ የአዋጅ ቁጥር 51/2017 ዓ/ም፤ የፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባርን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 52/2017 ዓ/ም እና የሀዋሳ ከተማ መዋቅራዊ የዉስጥ አደረጃጀትን መልሶ ለማዋቀር የቀረበ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 53/2017 ዓ/ም ቀርቦ ዉይይት ከተደረገባቸው በኋላ ፀድቀዋል።

የክልሉን ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አደረጃጀት ስልጣንና ተግባርን ለመወሰን እንዲሁም የክልሉን መንግስት አስፈፃሚ አካላት ማቋቋሚያ እና ስልጣንና ተግባርን ለመወሰን የወጡ አዋጆችንም አፅድቋል።

በአዋጁ መሠረት የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተጠሪነቱ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዲሆንና በክልል መዋቅር ያሉ 20 ቢሮዎች ሰምና መጠሪያ ማሻሻያ የተደረገባቸዉን ጨምሮ በርዕሰ መስተዳድሩ ሰብሳቢነት የመስተዳድሩ ምክር ቤት አባላት እንደሆኑ አዋጁ ይደነግጋል።

በሌላ በኩል የሀዋሳ ከተማ መዋቅርን መልሶ ለማደረጃት የቀረበዉ ረቂቅ አዋጅ ከዚህ ቀደም የነበረዉን የክፍለ ከተማ ብዛት ስያሜ ላይ ለዉጥ በማድረግ በ5 ክፍለ ከተሞችና በ26 ቀበሌዎች ዳግም እንዲዋቀር በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

ፎቶ፦ የክልሉ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#SafaricomEthiopia

የየእለቱን ዜናዎችን በSMS እናግኝ! 🗞📲
ከሳፋሪኮም ቁጥራችን 'A’ ብለን ወደ 30000 SMS አሁኑኑ በመላክ ወይም ወደ *799# በመደወል የቲክቫህ ትኩስ መረጃዎችን እናግኝ! በቀን 1ብር ብቻ! ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት ⚡️

#1Wedefit
#Furtheraheadtogether

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Tigray

ከሁሉም የሃይማኖት የቋማት የተወጣጡ እና በሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተመሩ አባቶች መቐለ ከተማ ይገኛሉ።

የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ከሁለት ሳምንት በፊት ባካሄደበት ወቅት የተገኙት የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በትግራይ ክልል ለዳግም ግጭት ቅስቀሳ የሚያደርጉ አካላት ስለመኖራቸው ያመላከተ መላሽ መስጠታቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ለተነሳላቸው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ በፌደራሉ መንግስት እና ማንነታቸውን ባልጠቀሷቸው በክልሉ የሚንቀሳቀሱ አካላት መካከል መቃቃር ስለመኖሩ አመላካች ሆኗል።

ለጥያቄው በሰጡት ምላሽም " የሁሉም እምነት አባቶች እዚህ ተወካዮች አላችሁ፣ ሌላ ምንም ስራ የላችሁም በፍጥነት ትግራይ ወደ ግጭት፣ ወደ ጦርነት እንዳይገባ ስራችሁን አሁን ጀምሩ፣ ከተጀመረ ወዲያ ብትናገሩ ዋጋ የለውም " ብለው ነበር።

" ባለሃብቶች፣ ምሁራን፣ ኤምባሲዎች ውጊያ እንዳይጀመር አሁን ሚናችሁን ተወጡ ምክንያቱም ከተጀመረ ከዚህ በፊት እንደምናቀው አይደለም ነገር ይበላሻል " ማለታቸውም የሚታወስ ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትሩን መልእክት ተከትሎ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በማግስቱ ለአስቸኳይ ስብሰባ ተቀመጦ እንደነበር ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።

በወቅቱ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ሃላፊ ፓስተር ይታገሱ ሃይለ ሚካኤል ተቋሙ እያደረገ ስላለው ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል " በቅርብ ጊዜ የሚደረጉ ነገሮች እንደሚኖሩ ተስፋ እናደርጋለን አሁን በውይይት ደረጃ ላይ ነው ያሉት ምን ይደረግ፣ እንዴት እናድርግ ውጤታማ የምንሆነው እንዴት ነው በሚለው ላይ መክረዋል በቅርብ ጊዜ ተግባራዊ የሆነ እንቅስቃሴ ውስጥ ይገባሉ " ብለው ነበር።

የስብሰባው አላማም የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልእክት ነገሩን በአጽንዖት መያዝ እንደሚያስፈልግ ጠቋሚ በመሆኑ መሆኑን ፓስተር ይታገሱ አስታውቀዋል።

መደረግ ባለባቸው ጉዳዮች ላይ ተከታታይ ውይይት ያደረጉት አባቶች በዛሬው ዕለት ወደ መቀሌ አቅንተዋል።

በመቐለ የሚገኙት አባቶች በምን በምን ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ተጨማሪ መረጃ ከተቋሙ እንዳገኘን የምናጋራቹ ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

ፎቶ፦ ድምጺ ወያነ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ንብተራ ኦንላይን!
ሁሉንም በአንድ ጥላ ስር የሚያገኙበት!

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ

***
ይሠሯል ከልብ እንደ ንብ!

#Nib #nibmobilebanking #NibQR #nib #nibtera #nibbank

Facebook  / Instagram / linkedin / nibinternationalbank6204">X / nibinternationalbank6204">Youtube / nibinternationalbank">Tiktok / Website

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ሰኞ ሀምሌ 7/2017 ዓ.ም በትግራይ እንዳስላሰ - ሽረ ከተማ ሁለት እንስቶች አሲድ ተደፍቶባቸው ጉዳት እንደደረሰባቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመስማት ችሏል።

ለጊዜው ስሙ ይፋ ያልተደረገ አንድ ግለሰብ በከተማዋ በሚገኘው አንድ መጠጥ ቤት በሚሰሩ ሁለት እንስቶች ላይ አሲድ በመድፋት ከባድ የአካል ጉዳት አድርሶባቸዋል።

ድርጊቱ በርካቶችን አስደንግጧል።

የተፈጠረው ምንድነው ? በማለት ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ወደ ከተማዋ የፓሊስ ምንጮች ደውሏል።

" የወንጀል ተግባሩ መነሻና አፈፃፀም እየተጣራ ነው " ሲሉ መልሰዋል።

የጭካኔ ድርጊቱ የመጠጥ ቤቶች በስፋት በሚገኙበት 03 ቀበሌ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ መፈፀሙ ያረጋገጡ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንጮች " ማንኛውም መነሻ ይኑረው አስነዋሪ እርምጃው ከሰብአዊነት ያፈነገጠ ጭካኔ የተሞላበት ነው " በማለት ገልፀውታል።

ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ደግሞ አሲድ በላያቸው ላይ የተደፋባቸው እንስት  አህቶች ለህይወት አስጊ በሆነ ሁኔታ ይገኛሉ ብለዋል።

" በሴቶች ላይ የሚፈፀመው ይህን መሰል አስነዋሪ ጥቃት ማስቆም ካቃተን እንደ ህዝብ የመቀጠል ዕጣ ፈንታችን ጥያቄ ውስጥ ይወድቃል " ሲሉ በአፅንኦት ተናግረዋል። 

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…
Subscribe to a channel