tikvahethiopia | Unsorted

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1527734

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Subscribe to a channel

TIKVAH-ETHIOPIA

" ታግተው ተወስደው የነበሩት ሁለቱም ዛሬ ተገድለዋል፡፡ ገንዘብ ተሰብሶ የተወሰነውን ከወሰዱ በኋላ መልሰው ገደሏቸው " - የወረዳው ቤተ ክህነት

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ጀጁ ወረዳ ሶኮራ ቀበሌ ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ/ም የ "ሸኔ" ታጣቂ ቡድን ባደረሱት ጥቃት አባትና ልጅ በተገደሉበት ወቅት " ታግተው ተወስደዋል " ተብለው የነበሩ ሁለቱ ሰዎች የሚለቀቁበት ገንዘብ ተሰብሰቦ የተወሰነው ከተሰጠ በኋላ " ገድለዋቸዋል " ሲል የወረዳው ቤተ ክህነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ፡፡

ታጣቂ ቡድኑ በወቅቱ በአንድ ቤተሰብ አባላት ስላደረሰው ጥቃት ቤተ ክህነቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ " አንድ ካህንና ወንድሙ ሁለት ሰዎች ናቸው ታግተው የተወሰዱት፡፡ አንድ አባት እስከ ልጃቸው ተገድለዋል " ብሎ ነበር፡፡

ዛሬ ለቲክቫህ ኢትየጵያ በሰጠው ቃል ደግሞ፣ " ታግተው ተወስደው የነበሩት ሁለቱም ሰዎች ዛሬ ተገድለዋል፡፡ አምጥተው በአካባቢያቸው ገድለው ጥለዋቸው ሂደዋል " ብሏል፡፡

" ገንዘብ ተሰብሶ የተወሰነውን ከወሰዱ በኋላ መልሰው ገደሏቸው፡፡ ዛሬ ሌሊት ተገድለው አደሩ፤ ሜዳ ላይ አምጥተው ገድለው ጥለዋቸው ነው የሄዱት፡፡ ዛሬ ቀብራቸው ተፈጽሟል " ያለው ቤተ ክህነቱ፣ ሟቾቹ ካህንኑና ወንድሙ ከሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ/ም ጅምሮ ታግተው እንደቆዩ፣ አጋቾቹ ታጋቾቹን ለመልቀቅ ገንዘብ ጠይቀው እንደነበርና የተወሰነው ተሰብስቦ ከወሰዱ በኋላ የግድያ ጥቃቱን ማድረሳቸውን አስረድቷል፡፡

" የተገደሉትም ካህኑና ወንድሙ ናቸው፡፡ ስማቸውም ቄስ አድማሱ ጌታነህና ወገኔ ጌታነህ ነው የሚባለው " ሲል አስረድቶ፣ አሁንም በአካባቢው ያለው የታጣቂ ቡድኑ እንቅስቃሴ አስጊና አሳሳቢ መሆኑን ጠቁሞ፣ ከለላ እንዲደረግ አሳስቧል።

ተደጋጋሚ ጥቃቱን በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ የጠየቀው የኦሮሚያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ፣ ጥቃት ደረሰበት የተባለው ወረዳ ምላሽ እንዲሰጥ በመጠቆም ማብራሪያ ከመስጠት የተቆጠበ ሲሆን፣ ወደ ወረዳው የተደረገው ሙከራም ለጊዜው አልተሳካም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

“ በሰው የደረሰ የሞት አደጋ የለም፡፡ ሁለት ሰዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ እንስሳት ተጎድተዋል፤ ንግድ ሱቆችም ተቃጥለዋል ” - አፋር ክልል

በአፋር ክልል ዳሎል ወረዳ የተከሰተው፣ እስካሁን “መንስዔው ገና እየተጣራ ነው” የተባለው የእሳት አደጋ ከፍተኛ የንብረት ውድመት መከሰቱን የክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተገልጿል፡፡

የክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽ ኃላፊ አቶ መሐመድ አሊ፣ “ የእሳት አደጋው መንስዔ ገና እየተጣራ ነው፡፡ በሰው የደረሰ የሞት አደጋ የለም። ሁለት ሰዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ እንስሳት ተጎድተዋል፤ ንግድ ሱቆችም ተቃጥለዋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አደጋው የተነሳው ትላንት 11 ሰዓት ተኩል ገደማ መሆኑን፣ የአካባቢው ማህበረሰብ ጭምር እሳቱን ለማጥፋት ርብርብ እናዳደረገ የገለጹት ኃላፊው፣ “እሳቱ በቁጥጥር ሥር ውሏል” ብለዋል፡፡

በቃጠሎው የደረሰው የጉዳት መጠን ምን ያክል እንደሆነ ሲጠየቁም፣ “ ጉዳቱ ከፍተኛ ነው ከፍተኛ እሳት ነው የነበረው፡፡ አካባቢው ሞቃታማ ነው ቶሎ መቆጣጠር አይቻልም፡፡ ቦታውም ከሰመራ በጣም ሩቅና ገጠራማ አካካቢ ስለሆነ የእሳት አደጋ ተሸከርካሪ ቶሎ የሚደርስበት አይደለም፡፡ በባህላዊ መንገድ ነው እሳቱን ያጠፉት ” ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የጉዳት መጠኑን ለማወቅ ባለሙያዎች በጥናት መሰረት የሚያቀርቡትን መረጃ መጠበቅ የተሻለ እንደሆነና ሪፖርቱ ሲደርስ እንደሚገልጹ ጠቁመዋል፡፡

በጥቅሉ በአደጋው ሱቆች፣ ንግድ ቤቶች፣ የግለሰብ መኖሪያ ቤቶች በእሳቱ እንደተቃጠሉ፣ በአካባው የክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን እንደደረሰና የጉዳቱ መጠን እየተጣራ መሆኑም ገልጸዋል፡፡

“ሞት ባይኖርም በእሳት አደጋ ምክንያት የተፈናቀሉ አሉ፡፡ የስነ ልቦና ችግር ለደረሰባቸው ወገኖችንም የክልል ጤና ቢሮ የህክምና ባለሙያዎች ልዑካን ቡድን ተልኳል። የእሳር አደጋውን መነሻ ለማወቅ ፖሊስም እያጣራ ነው” ብለዋል።

“በዳሎል ለደረሰው የእሳት እና በአፍዴራ ለደረሰው ሰሞንኛ የንፋስ አደጋ ክልሉ ለተጎጅዎች የእለት ደራሽ ምግብ በማቅረብ፣ የህክምና አገልግሎት በመስጠት፣ ጊዜያዊም ቢሆን የመጠለያ ቁሳቁስ በመቅረብ ባለው አቅም በቦታው ደርሶ ህዝቡን የመታደግ ሥራ እየሰራ ነው፡፡ በቀጣይ የፌደራሉም የክሉም መንግስት የሚሰሩበት ይሆናል” ብለዋል አቶ መሐመድ።

ቲክቫህ ኢተዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update
#አርባምንጭ

ተከሳሾች ያቀረቡት የመከላከያ ማስረጃ ዉድቅ ተደርጓል።

የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ጠዋት ባካሄደዉ ችሎት የብሔራዊ ቡድን እግር ኳስ ተጫዋች በነበረው አለልኝ አዘነ የግድያ ወንጀል የተጠረጠሩት ባለቤቱና የባለቤቱ እህት ባል ያቀረቡትን የመከላከያ ማስረጃ ሙሉ በሙሉ ዉድቅ በማድረግ የፍርድ ዉሳኔ ለመስጠት ከሰዓት በኋላ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በርካታ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ችሎቱን ለመታደም ፍርድ ቤት መጥተዉ የነበረ ቢሆንም የችሎት አደራሽ ከልክ በላይ በመሙላቱ አብዛኛዉ ሰው ከግቢ ዉጪ በመሆን የፍርድ ውሳኔውን በመጠባበቅ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተመልክቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቦታው ተገኝቶ ችሎቱን እየተከታተለ ያለ ሲሆን መረጃዎችን ተከታትሎ የሚያደርስ ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አርባ ምንጭ
#TikvahEthiopiaFamliyArbaminch

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በትንሹ ከ3-4 ሰዓት በላይ ነው የምንቆመው " - ነዋሪዎች

➡️ " መንገዱ እየተሰራ በመሆኑ ደስታ ቢሰማንም ፣ የአካባቢው አስተዳደር ፕሮጀክቱን ከመጀመሩ በፊት ሊከሰት የሚችል የመንገድ ችግርን ታሳቢ ያደረገ አማራጭ መንገድ እንዲመቻች ማድረግ ነበረበት ! "

ከዩኒሳ አደባባይ ወደ ዱከም መሄጃ ሸገር ከተማ ላይ እየተሰራ ካለ የመንገድ ስራ ጋር በተያያዘ አማራጭ መንገድ ባለመዘጋጀቱ ምክንያት ነዋሪዎች ከቤታቸው ወጥተው ወደ ከተማ ለስራ ሄዶ መመለስ ፈተና እንደሆነባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" የመንገዱ ስራ ቱቦ ቀበራ ላይ ናቸው። ዋናው መንገድ ፈርሷል። በግራ በኩል ያለው ገደል ሆኗል። የከባድ መኪናዎች መግቢያና መውጪያ ነው በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ነን። የመንግሥት አካላት ምላሽ እየሰጡ አይደለም " ሲሉ አንድ ነዋሪ ገልጸዋል።

" በትንሹ ከ2 እና 3 ሰዓት በላይ ነው የምቆመው ፤ ከሰሞኑን ለስራ ስንል በቢሾፍቱ ዞረን ነው በፈጣን መንገድ ገብተን ነው የምንወጣው። ከዛ ውጭ መንገዱ ስለሚዘጋጋ ማለፍ አይቻልም። የከባድ መኪና መግቢያቸው በዚህ ነው " ብለዋል።

ነዋሪዎች በአካባቢው ባለው የመንገድ ችግር እስከ እጅግ አምሽተው ቤታቸው ለመግባት እየተገደዱ መሆኑን አመልክተዋል።

የመፍትሄ ያለ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

ሌላኛው የገላን ክፍለ ከተማ የሸገር ከተማ ነዋሪ እንደሆኑ የገለጹ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል " ከዩኒሳ እስከ ሸገር ገላን ያለውን የመንገድ ችግር እውነት ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ችግሩ ከጀመረ ከአንድ ወር በላይ አልፎታል ከቀን ወደ ቀንም እየተባባሰ ነው። በአሁኑ ሰአት ከዩኒሳ ወደ ገላን በባጃጅ 20 ብር የነበረ መንገድ 100 ብር እንድንከፍል እየተገደድን ነው " ብለዋል።

" አብዛኛው የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ለስራ አዲስ አበባ ዉለን የምንገባ ሲሆን ለዚቹ መንገድ በቀን ከ200 ብር በላይ እያወጣን እንገኛለን። በዚህ መንገድ ለኑሮ (ሥራ) በየቀኑ የምንሄድ ሰዎች ሰዎች ላይ ያለውን ሸክም አስቡት " ሲሉ ገልጸዋል።

" ችግሩ እየተካሄደ ባለው የዋና መንገድ ግንባታ የተከሰተ ነው። መንገዱ እየተሰራ በመሆኑ ደስታ ቢሰማንም ፣ የአካባቢው አስተዳደር ፕሮጀክቱን ከመጀመሩ በፊት ሊከሰት የሚችል የመንገድ ችግርን ታሳቢ ያደረገ አማራጭ መንገድን ማመቻቸት ነበረበት ሆኖም ይህ ሳይደረግ በመቅረቱ ላሳሳቢ ችግር ተጋልጠናል " ብለዋል።

" ከዚህ ባለፈም የዝናብ ወቅት እንደመሆኑ ዝናቡ ችግሩን እያባባሰው ስለሆነ አሁንም ቢሆን ተገቢውን ትኩረት ሊሰጠው ይገባል " ሲሉ አሳስበዋል።

ሌላኛው የአካባቢው ነዋሪ በቪድዮ ጭምር አስደግፈው በላኩት የአቤቱታ መልዕክት አማራጭ መንገድ ባለመዘጋጀቱ ነዋሪዎች ከቤት ወጥተው እስከሚመለሱ ከምሽት 4 ሰዓት ሁሉ ሊያልፍ እንደሚችል ፤ አንዳንዶችም ያለው ችግር እስኪቀረፍ ሌላ ቦታ መኖር እንደመጀመር መገደዳቸውን አመልክተዋል።

" በቀኝ በኩል ሲኬድ መንገዱን ለማስፋት አማራጭ አለው ፤ መንገዱን የሚሰራው ኮንትራክተር መንገዱን ጠረግ ቢያደርገው መኪኖች ይተላለፋሉ ፤ ግን የመንገዱ ተቆጣጣሪዎች ትንንሽ መኪና እንኳን የያዙ ሰዎች ከባባድ መኪናዎች በሚሄዱበት የተቆራረጠ መንገድ ነው እንዲሄዱ የሚፈልጉት " ብለዋል።

" መንገዱ መውጫ መግቢያ ነው። ትልልቅ መኪኖች ከዱከም ኢንዱስትሪ ዞን ኮንቴነር ጭነው ፣ ከጅቡቲም የሚመጡ መኪኖች፣ ሲኖ ትራኮች ትልልቅ መኪኖች ናቸው የሚጠቀሙት መንገዱን " ያሉት ነዋሪው " ተቀያሪ መንገድ ጭራሽ ነው ያልታሰበበት " ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

" እኛ ሰፈር መግባት እየተቸገርን እና የሚጠፋው ጊዜ ብዙ ስለሆነ የዘመድ ቤት ለመግባት ተገደናል " ያሉ ሲሆን " ፍቃድ እየሞሉ ስራም የማይገቡ አሉ። የሚመለከታቸው አካላት መፍትሄ ይፈልጉለት " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሚመለከታቸውን አካላት በማነጋገር ምላሽ ይዞ ለመቅረብ ጥረት ያደርጋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamliyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" 4 አመታት በጥንቃቄ የተገነባውና ወደ 6 ሚልየን ብር ወጪ የተደረገበት በገዳሙ ዙሪያ የተገነባው የጎርፍ መከላከያ ግንብ ፈርሶብናል " - የገዳሙ አሰሪ ኮሚቴ

በሰሜን ወሎ ዞን በፍላቂት ገረገራ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው እና አሁን በመገንባት ላይ ያለው የገረገራ ቀራንዮ መድኃኔዓለም አቡነ ተክለ ሃይማኖት አባ ሳሙኤል አንድነት ገዳም ሰሞኑን በጣለው ከባድ ዝናብ  በገዳሙ  ዙሪያ ጎርፍን ለመከላከል ያስችላል ተብሎ የተገነባው ግንብ መፍረሱን የገዳሙ  አሰሪ ኮሚቴ አባል አቶ ዘላለም ሙላቱ ተናግረዋል።

አቶ ዘላለም ሙላቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት ገዳሙ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰራ የቆየና ወደ 30 ሚልየን ብር ወጭ የፈጀ ሲሆን በሚቀጥለው አመት 2018ዓ.ም መጀመሪያ ላይ ለማስመረቅ እቅድ ተይዞ ነበር ብለዋል።

ነገር ግን ከሰሞኑ ሀምሌ 3 /2017ዓ.ም በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ጎርፍን ለመከላከል ያስችላል ተብሎ የተገነባው ግንብ በመፍረሱ ገዳሙ በአሁኑ ወቅት ምንም ባይሆንም ለቀጣይ የሚያሰጋው እንደሚሆን ነው የገለጹት።

ሰሞኑን በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት የፈረሰውና በገዳሙ ዙሪያ የተገነባው የጎርፍ መከላከያ ግንብ ላለፍት 4 አመታት በጥንቃቄ የተገነባና ወደ 6 ሚልየን ብር የፈጀ እንደነበርም አቶ ዘላለም አክለው ገልፀዋል።

የገረገራ ቀራንዮ መድኃኔዓለም አቡነ ተክለ ሃይማኖት አባ ሳሙኤል አንድነት ገዳም ከመሬት ወለል 2900 ከፍታ ባለው ተራራማ ስፍራ የተገነባ ነው።

የአካባቢው መሬት ተንሸራታች በመሆኑም ገዳሙ በተፈጥሮ አደጋ የመጋለጥ እድሉ ከፍተኛ ሲሆን ገዳሙ ሳይመረቅ በጎርፍ እንዳይወሰድ እና የፈረሰውን ግንብ መልሶ በመገንባት ሂደት ምዕምናን እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
#TikvahEthiopiaFamliyBahridar

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ፀሐይ ባንክ
ለሁሉ!


ሕንጻዎትን በቀላሉ የሚያስተዳድሩበት እጅግ ዘመናዊ መፍትሔ ከፀሐይ ባንክ! 👏👏

ዘመናዊነትን ይምረጡ፣ ጊዜዎንና ጉልበትዎን ይቆጥቡ፣ ትርፍዎን ያሳድጉ!

🔔 የፀሐይ ባንክ የሕንጻ አስተዳደር ሲስተም ተጠቃሚ ይሁኑ!

በርካታ ጥቅሞች ያሉትን ይህን ስርዓት በመጠቀም፥ የሕንጻዎን ደህንነት ይጠብቁ! ጠንካራ የተከራይ ግንኙነት ይፍጠሩ! የክፍያ እና የቁጥጥር ስርዓትዎን ያዘምኑ!

አስተማማኝ እንዲሁም ለአጠቃቀምና ለአከፋፈል ምቹ በሆነ ዘመናዊ ሲስተም ይጠቀሙ!

Telegram: /channel/tsehaybanksc
Facebook: https://www.facebook.com/tsehaybanksc

ፀሐይ ባንክ
ለሁሉ!

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የአለልኝ አዘነ ጉዳይ ነገ ትክክለኛ ፍትሕ ያገኛል ብለን እንጠብቃለን " - ወዳጆቹ

ከዓመት በፊት በመጋቢት 2016 ዓ/ም በድንገት ሕይወቱ ያለፈዉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና በተለያዩ የሀገራችን ክለቦች ተጫዉቶ ያለፈው ወጣቱ የአማካኝ ተከላካይ አለልኝ አዘነ ከአሟሟቱ ጋር በተያያዘ የትዳር አጋሩና የእህቷ ባል በቁጥጥር ስር ውለው ክስ የተመሰረተባቸው መሆኑ ይታወሳል።

የማጣራት፣ የምስክርና መከላከያ ማስረጃዎችን ሲያደምጥ የቆየዉ የአርባ ምንጭ ከተማ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በነገዉ ዕለት የፍርድ ዉሳኔ እንደሚያስተላልፍ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመረዳት ችሏል።

በ26 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው አለልኝ አዘነ የእግር ኳስ ሕይወቱን በአርባምንጭ ከተማ፣ በሀዋሳ ከተማ፣ በባህር ዳር ከተማ እንዲሁም በብሔራዊ ቡድን ያሳለፈ ሲሆን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርቲያን ስርዓት ጋብቻ በፈፀመ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተወልዶ ባደገበትና የእግር ኳስ ሕይወትን ሀ ብሎ በጀመረበት አርባ ምንጭ ከተማ በድንገት ሕይወቱ ማለፉን ተከትሎ " እራሱን አጠፋ " የሚሉና " በሰዉ ተገድሎ ነዉ " የሚሉ መረጃዎች ሲሰራጩ መቆየታቸው ይታወሳል።

ኋላም " እራሱን አላጠፋም " በሚል ስርዓተ ፍትሐት እንዲፈፀምለት ተደርጓል።

የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስም የትዳር አጋሩንና የእህቷን ባል (የሚስቱን እህት ባል) በቁጥጥር አውሎ ክስ እንዲመሰረት ያደረገ ሲሆን የግራ ቀኝ ምስክርና የመከላከያ ማስረጃዎችን ሲያደምጥ እንዲሁም መዝገቡን ሲመረምር የቆየዉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍርድ ዉሳኔ ለመስጠት ነገ ሀምሌ 11/2017 ዓ/ም ቀጠሮ ይዟል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በአርባምንጭ ከተማ ተገኝቶ ያነጋገራቸው የከተማዉ ነዋሪዎች እና የተጫዋቹ ወዳጆች ዉሳኔዉን በጉጉት እንደሚጠብቁ ገልፀው  " ነገ የአለልኝ ጉዳይ ፍትሕ ያገኛል፤ የኛም ልብ ያርፋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ውሳኔዉን በርካታ የእግር ኳስ ቤተሰቦች፣ የኳስ ተጫዋቹ ወዳጆችና መላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚጠብቀው በመሆኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቦታዉ ላይ በመገኘት መረጃውን ያደርሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አርባ ምንጭ
#TikvahEthiopiaFamliyArbaminch

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

በሁለት እንስቶች ላይ አሲድ በመድፋት አረሜናዊ ድርጊት የፈፀመው ተጠርጣሪ " እስካሁን በቁጥጥር ስር አልዋለም " ሲሉ የትግራይ እንዳስላሰ - ሽረ ከተማ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

" አሲድ የተደፋባቸው ወገኖች በከፍተኛ ስቃይ ላይ ይገኛሉ " ሲሉ አክለዋል።

አሲድ የተደፋባቸው እንስቶቹ ለተሻለ ህክምና ከእንዳስላሰ - ሽረ ወደ አክሱም ቅድስት ማርያም ሆስፒታል ሪፈር መባላቸውን ገልጸዋል።

ባለፈው ሀምሌ 7/2017 ዓ/ም እስካሁን ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ በአንድ መጠጥ ቤት በሁለት እንስቶች ላይ አሲድ በመድፋት ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ማድረሱ ይታወሳል።

የድርጊቱ ፈፃሚ ግለሰብና ?  አስቃቂ ተግባር የተፈፀመባቸው እንስቶች በምን ሁኔታ እንደሚገኙ ለማጣራት ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ኣባል ዛሬ ሀምሌ 10/2017 ዓ.ም ወደ ከተማዋ ፓሊስ ስልክ ደውሎ ነበር።

ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የከተማዋ ፓሊስ አመራር " በአካል ወደ ከተማችን ካልመጣችሁ በስቀር በስልክ መረጃ አንሰጥም " በማለት መረጃውን ከልክለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የከተማዋ ነዋሪ ከሆኑ ታማኝ ምንጮቹ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የጭካኔ ድርጊቱን የፈፀመው ግለሰብ የሚታወቅ የከተማዋ ነዋሪ ሆኖ እያለ እስካሁን በቁጥጥር ስር አለመዋሉ ሁኔታውን አሳሳቢ አድርጎታል።

" ተጠርጣሪ ወንጀለኛው እስካሁን በከተማዋ ተደብቆ እንደሚገኝ የሚሰሙ ጭምጭምታዎች አሉ " ያሉት የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንጮች ፤ ፓሊስ የጭካኔ ድርጊቱ የፈፀመው ግለሰብ አድኖ በመያዝ ህግ እንዲያስከብር አደራ ብለዋል።

የከተማዋ ነዋሪ ተጥርጣሪውን ለፓሊስ አሳልፎ በመስጠት ዜግነታዊ ሃላፊነቱ እንዲወጣም ነዋሪዎቹ ጥሪ አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የእንዳስላሰ - ሽረ ከተማ ፓሊስ ለሚድያ የሚፈቀድ መረጃ በመስጠት እንዲተባበር እየጠየቀ ጉዳዩ ተከታትሎ መዘገቡ እንደሚቀጥል ቃል ይገባል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamliyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ጳጉሜ ወር ላይ ይፋ ይደረጋል " - ትምህርት ሚኒስቴር

➡️ " መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ/ም ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ይቀበላሉ ! "


የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ጳጉሜ ወር 2017 ዓ/ም ላይ ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴር ትላንት በሰጠው መግለጫ ላይ ለመስማት ተችሏል።

ትምህርታቸውን በሰላምና ደህንነት ምክንያት ዘግይተው በጀመሩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ያሉ ተማሪዎች እንዲሁም የተወሰኑ የህግ ታራሚዎች ፈተናውን ነሀሴ ወር ላይ እንደሚወስዱ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አሳውቀዋል።

አጠቃላይ ፈተናውን የሚወስዱት 4,966 ተፈታኞች ሲሆኑ ፈተናውን ከነሐሴ 26 - 28/2017 ዓ/ም ድረስ በወረቀት እንደሚወስዱ ተገልጿል።

እንዚህ ተማሪዎች ፈተናቸውን ከወሰዱ በኃላ አጠቃላይ የሁሉም የ2017 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ጳጉሜ ወር ላይ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ/ም ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች እንደሚቀበሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

#MoE

#TikvahEthiopiaFamliyAA
@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" 75 ሚሊዮን ብር ከህጋዊ አደን ገቢ ተገኝቷል " - የኦሮሚያ ክልል ደን እና ዱር እንስሳት ድርጅት

በ2017 በጀት ዓመት በኦሮሚያ ክልል በተደረጉ ከህጋዊ አደን 75 ሚሊዮን ብር ገቢ መግኘቱን የክልሉ ደን እና ዱር እንስሳት ድርጅት የዱር እንስሳት ልማት እና አጠቃቀም ባለሙያ የሆኑት አሸናፊ መንግስቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

በክልሉ ባሌ ፤ አርሲ እና ሀራርጌ ዞኖች ውስጥ በበጀት ዓመቱ ማርጀታቸው የተረጋገጠ 250 የተለያዩ የዱር እንስሳቶች ለህጋዊ አዳኞች ለመሸጥ ታቅዶ 176 የሚሆኑት ተሽጠው ከነዝህ ውስጥ 147 በህጋዊ መንገድ ታድነዋል ብለዋል።

ለአደን ከተሸጡት ውስጥ 22ቱ የደጋ አጋዘን ሲሆኑ አንድ የደጋ አጋዘን በአስራ አምስት ሽህ ዶላር እንደታደነም አቶ አሸናፊ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አዳኞቹም የደጋ አጋዘን ካደኑ በኋላ ቀንዱን እና ቆዳውን እንደሚወሰዱ የገለፁት ባለሙያው አዳኞቹ በስህተት ያላረጁ ዱር እንስሳት ከገደሉ ከዋጋው በእጠፍ እንዲከፍሉ ቅጣት ተቀምጧል ብለዋል።

ከተሸጡት ውስጥም ያልታደኑ መኖራቸውንም ነው ያነሱት።

ከአደን ከተገኘው ገቢ ውስጥ 11 ሚሊየን የሚሆነው ገንዘብ ለፌደራል ደን እና ዱር እንስሳት የሚሰጥ ሲሆን ቀሪው ለክልሉ ደን እና ዱር እንስሳት ድርጅት እና በፖርኮቹ አካባቢ በማኅበር ተደራጅተው ለሚሰሩ ስዎች ገቢ ይደረጋል ብለዋል።

የተገኘው ገቢም ለመሰረተ ልማት ማሟያ ፤ለአዳኞች ምቹ የሆኑ የመቆያ ስፍራዎችን ማመቻቸት፤ በፓርኩ ውስጥ ላሉ የተለያዩ እንስሳቶች ለመንከባከብያ ይውላል ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነቀምቴ
TikvahEthiopiaFamilyNekemte

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#National_ID_Program

ተጨማሪ የመረጃ ማስተካከያ ጣቢያዎች

የመረጃ ስህተት ሲገጥም እንዲሁም መረጃ መቀየር ቢያስፈልግዎ በአቅራቢያዎ የሚገኝ የመረጃ እድሳት አገልግሎት ሰጪ ጣቢያ መሄድ እንደሚችሉ ያውቃሉ?

እነዚህን እና ተጨማሪ የምዝገባ ጣቢያዎች ለማግኘት id.gov.et/updatecenters ይመልከቱ። ነገር ግን በምዝገባ ቅጽ ላይ የሞሉት መረጃ በመዝጋቢ ባለሙያ በስህተት ከተመዘገበ መረጃዎን ለማስተካከል በአካል መሔድ ሳይጠበቅብዎ id.gov.et/update ላይ ወይም "Fayda ID" የሞባይል መተግበሪያን በመጠቀም በቤትዎ ሆነው የተሳሳተ መረጃዎን እንዲስተካከል መጠየቅ ይችላሉ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #አካታች

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

የፌደራል ገቢ ግብር አዋጅ ፀደቀ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል ገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አፀደቀ።

ረቂቅ አዋጁ በአብላጫ ድምጽ ነው የፀደቀው።

ረቂቅ አዋጁ ላይ ሰፊ ክርክር ሲነሳበት እንደነበር ይታወቃል። በተለይ የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማሕበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) ረቂቅ አዋጁ ላይ የደመወዝ ገቢ ግብር መነሻ ተብሎ የተቀመጠው 2,000 ብር ወደ 8,324 ብር ከፍ እንዲል ፤ አጠቃላይ አዋጁ የኑሮ ውድነቱንና ጫናውን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንዲታረም ሲወተውት ነበር።

ከ0 ጀምሮ 10% ፣ 15% ፣ 20% ፣ 25% ፣ 30% ፣ 35% ይቀጥል የነበርው የግብር ምጣኔም በረቂቅ አዋጁ 10% ከመሃል ወጥቶ ከ0 ጀምሮ ቀጥታ ባከፍተኛው 15% መጀመሩንም ታቃውሞ ነበር።

ሌላው 14,100 በላይ የሚያገኝ ሰው 35% ግብር ይከፍላል በሚለው ላይም ጥያቄ ተነስቶ ነበር።

በአሁኑ የኑሮ ውድነት ሰራተኛው በእያንዳንዱ ነገር በምግብ ዋጋ፣ በሚገዛው እቃ 15% ይጨምራል ይሄ በ35% ላይ ሲደመር 50% ይመጣል፤ 7% የጡረታ አለ ሲደመር 57% ከደመወዙ ላይ ይሄዳል በቀረችው 43% ልጆች ያስተምራል ፣ ምግብ ይበላል ፣ ልብስ ይገዛል ፣ ቤት ይከራያል ምንድነው የሚያደርገው ? የሚል የሰራተኛውን ጥያቄ በማንሳት ረቂቁ እንዲታረም ጠይቆ ነበር።

ኮንፌዴሬሽኑ ፤ " መኖር ከማይችል እና በልቶ ከማያድር ሰው ግብር አይሰብሰብም " ብሎም የነበረ ሲሆነ " እንደ ሀገር ግብር መሰብሰብና ልማትም መቀጠል አለበት ፤ የሰው ህይወትም ግን መቀጠል አለበት ፤ ሰው እየተራበ መስራት አይችልም ምርታማ መሆን አይችልም " በማለት ረቂቁ እንዲታረም ብርቱ ጥያቄ አቅርቦ ነበር።

ሌሎችም አካላት ሰፊ ክርክር ሲያደርጉበት የነበረው ረቂቅ አዋጅ በዛሬው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአብላጭ ድምጽ ፀድቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamliyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የመፍረስ አደጋ የተጋረጠበት ተቋም !

" ከደመወዝና ሰራተኞች ጥቅማጥቅም ባሻገር የዚህ አንጋፋ ተቋም ህልዉና አደጋ ዉስጥ መሆን ያሳስበናል " - የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ሠራተኞች


የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ከቀድሞዉ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መፍረስ በኋላ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዉ እየተዳከመ መጥቶ አሁን ላይ ፦
- የሰራተኞች ደመወዝ ፣
- የደሞዝ ማሻሻያ (Back Payment)፣
- የደረጃ ዕድገትና ሌሎችም ጥቅማጥቅሞች መክፈል አለመቻልን ጨምሮ የመፍረስ አደጋ እንደተጋረጠበት የተቋሙ ሠራተኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ስማቸዉ እንዲገለፅ ያልፈለጉ አንድ የድርጅቱ አንጋፋ ጋዜጠኛ ፥ " ተቋሙ አሁን ላይ የተጋረጠበት አደጋ በወር ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም አለመኖር ብቻ የሚመዘን ሳይሆን የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦች ድምፅ በመሆን ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት  በልማት፣ መልካም አስተዳደደርና በደሞክራሲ ግንባታ ረገድ ጉልህ አበርክቶ ያለዉ ከመሆኑም በላይ ለሀገራችን የሚዲያዉ ኢንዱስትራ በርካታ ባለሙያዎችን ያፈራ አንጋፋ ተቋም እንደመሆኑ በዚህ ልክ አስታዋሽ ያጣ መሆን አልነበረበትም " ብለዋል።

ሌሎች ሰራተኞች በበኩላቸው " የደመወዝና ስራ ማስኬጃ በጀት ከአራቱ ክልሎች እየተዋጣለት እስካሁን የቆየዉ ድርጅቱ ባለቤት አልባ፣ ተቆርቋሪ እና ጠያቂ ያጣ ስለመሆኑ ማሳያ የሚሆነዉ እስካሁንም ዋና ስራ አስፈፃሚዉን ጨምሮ የተቋሙ አመራሮች በዉክልና ለረጅም ጊዜ የቆዩ መሆናቸው ነው " ብለዋል።

" ግምገማ ኦዲትና የቅርብ ክትትል የሚያደርግ አካልም ባለመኖሩ ከደመወዝና ሰራተኞች ጥቅማጥቅም ባሻገር የዚህ አንጋፋ ተቋም ህልዉና አደጋ ዉስጥ እንደሆነ ይሰማናል " ሲሉ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው ከዚህ ቀደም በተቋሙ የሰሩ በአሁኑ ወቅትም በሀገራችን ትልልቅ የሚዲያ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎች " ከ48 ቋንቋዎች በላይ ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ የሚደርሰዉ ይህ አንጋፋ ተቋም በዚህ ልክ ትኩረት መነፈጉና ለበርካቶች ድምፅ መሆን የቻሉ ጋዜጠኞችና የሚዲያ ባለሙያዎች በዚህ ልክ ትኩረት ተነፍገዉ ማየት በጣም ያሳዝናል " ሲሉ ሃሳባቸዉን ገልፀዋል።

" የፌደራል መንግስት ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላትም ለዚህ ተቋም መጠናከር የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል" ሲሉ ባለሙያዎቹ አክለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamliyHawassa

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ሴጅ_ማሰልጠኛ_ኢንስቲትዩት

የሁለት ወር የኢንቴሪየር ዲዛይን (Interior Design) የክረምት ስልጠና ሐምሌ 14/2017 ዓ.ም ይጀመራል።

👉 Sketch-Up, Revit, Autocad, 3D Max እና Lumion ሶፍትዌሮችን በአንድ ላይ
👉 ስልጠናውን ልዩ የሚያደርገው ከንድፈ ሀሳብ እና ሶፍትዌር ስልጠና በተጨማሪ በተግባር በወርክሾፕም  የሚሰጥ በመሆኑ ነው።

የበለጠ ይጠብቁ ...

☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
Tiktok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
Linkedin: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምን አለ ?

" በመንገደኞቻችን ላይ ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም፤ በሁለት የበረራ ሰራተኞች ላይ መጠነኛ ጉዳት አጋጥሞ ህክምና ተደርጎላቸው ወደ ሆቴል ተመልሰዋል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ


የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET-298 በዛሬው ዕለት ከአዲስ አበባ ተነስቶ መቐ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ካረፈ በኋላ ከአውሮፕላን መንደርደሪያው መጠነኛ የመንሸራተት እክል እንዳጋጠመው አየር መንገዱ ገልጿል።

አውሮፕላኑ በሚያርፍበት ጊዜ ዝናብ እየዘነበ እንደነበረም አመልክቷል።

አየር መንገዱ እስካሁን ባለው መረጃ በመንገደኞቻችን ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰና በሰላም ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ እንደተደረገ ገልጿል።

በሁለት የበረራ ሰራተኞች ላይ ግን መጠነኛ ጉዳት በማጋጠሙ ለተጨማሪ የህክምና ዕርዳታ በአቅራቢያ ወደሚገኝ የህክምና መስጫ ተቋም ተወስደው ከታከሙ በኋላ ወደ ሆቴል እንዲሄዱ መደረጋቸውን አሳውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው የደንበኞች መጉላላት ይቅርታ ጠይቋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

ፍርድ ቤቱ አለልኝ አዘነ በሰዉ እጅ ስለመገደሉ አረጋግጦ ባለቤቱንና የባለቤቱን እህት ባል ጥፋተኛ ብሎ ብይን ሰጥቷል።

በእግር ኳስ ተጫዋቹ አለልኝ አዘነ ግድያ ላይ ዛሬ በሁለት ፈረቃዎች የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት የተሰየመው የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ የአለልኝ ባለቤት እና 2ኛ ተከሳሽ የባለቤቱ እህት ባል መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ/ም ከሌሊቱ 5፡30 እስከ 8 ሰዓት ገደማ ባለዉ ጊዜ በአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ነጭ ሳር ቀበሌ ልማት ሰፈር ' ሃይላንድ ' ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በተቀነባበረ ሁኔታ የ26 አመቱን ወጣት አለልኝ አዘነን በመግደል እራሱን ያጠፋ እንዲመስል በማድረግ የግዲያ ወንጀል መፈፀማቸው በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች በመረጋገጡ ጥፋተኛ እንዳላቸው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል መረጃውን ልኳል።

ዛሬ ከሰዓት በኋላ የፍርድ ድሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ይዞ የነበረዉ የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መደበኛ ችሎት የዐቃቤ ሕግና የተከሳሾችን ጠበቃ የቅጣት አስተያየት ካደመጠ በኋላ ዉሳኔዉን ወደ ሀምሌ 15/2017 ዓ/ም አሸጋግሯል።


ምን የሚሉ የቅጣት አስተያየቶች ተሰጡ ?

የተከሳሾች ጠበቃ (የቅጣት ማቅለያ) ፦
👉 ተከሳሾች የወንጀል ሪከርድ የሌለባቸው መሆኑን
👉 የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸዉንና
👉 1ኛ ተከሳሽ የሟች አለልኝ አዘነ ባለቤት የአስም ታማሚ መሆኗ በቅጣት ማቅለያነት አቅርቧል።

የጋሞ ዞን ከፍተኛ ዐቃቤ ሕግ (የቅጣት ማክበጃ) ፦
ዐቃቤ ሕግ የወንጀል አወሳሰን መመሪያ ማንዋል 03/2017ዓ/ም እና የወንጀል ሕጉን አንቀፅ 84 (1) ለ፣ ሐ፣ ሠ በመጥቀስ
➡️ የአገዳደሉ አደገኛነት
➡️ ወንጀል ፈፃሚዎች ለወንጀል ድርጊቱ የመረጡት ሰዓት አሳቻና ሰዎች የማይደርሱበትን ሰዓት መሆኑን
➡️ በዘመድ ላይ የተፈፀመ የጭካኔ ወንጀል መሆኑን በመግለፅ እንዲሁም ሟቹ አለልኝ አዘነ ለብሔራዊ ቡድኑ (ለሀገር) ሲሰጥ የነበረዉን ግልጋሎት ከግምት ዉስጥ በማስገባት ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን እንዲያከብድ ጠይቋል።

የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ያደመጠዉ ፍርድ ቤት የፍርድ ቅጣት እርከኑን ለመወሰን ለሀምሌ 15/2017 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ከስፍራው መረጃውን ልኳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አርባ ምንጭ
#TikvahEthiopiaFamliyArbaminch

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የጋሞ ዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት በእግር ኳስ ተጫዋቹ አለልኝ አዘነ ግድያ ዙሪያ ፍርድ ለመስጠት ለሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ የቅጣት ማክበጃ እና ማቅለያ የሰማ ሲሆን የመጨረሻውን የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት ለሐምሌ 15 ቀጥሯል።

ውድ ቤተሰቦቻችን ቲክቫህ ኢትዮጵያ የፍርድ ቤቱን ውሎ ዝርዝር መረጃ ከደቂቃዎች በኃላ ይልክላችኋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አርባ ምንጭ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ኢትዮጵያ🇪🇹

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ፥ " በአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች የሚደረግ ምክክርና እርቀ ሰላም ፍሬው ጣፋጭ ነው " አሉ።

ትናንት ሀምሌ 10/2017 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ያቀኑት የትግራይ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሸማግሌዎች ዛሬ ሀምሌ 11/2017 ዓ.ም ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) መክረዋል።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ከትግራይ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሸማግሌዎች ስለተካሄደው የሰላም ውይይት አስመልከተው በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው በትግርኛ ባጋሩት መረጃ " የኢፌዲሪ መንግስት በሽምግልና እና ምክክር ችግሮች እንዲፈቱ ቅድምያ ሰጥቶ እንደሚሰራ በተለያዩ ጊዚያት በተግባር አሳይቷል " ብለዋል። 

" በረጅሙ የአገሪቱ የአገረ መንግስት ስርዓት አገራዊ እርቅ ፣ አገራዊ ምክክር ፣ ፓለቲካዊ ውይይት የሚሉ ማህበራዊ አምዶች በኢትዮጵያ ፓለቲካ ውይይት በይፋ እንዲተገበሩ ያደረገው የአሁኑ መንግስት መሆኑ መካድ የለበትም " ብለዋል።
  
" ግጭት ሌላ ግጭት እየወለደ በችግር አዙሪት ከመኖር ያለፈ ሌላ ፋይዳ የለውም " ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ " በውይይትና መግባባት ችግሮቻችን በመፍታት ሰላምን በፅኑ መሰረት እናኑር " ብለዋል። 

" ከተለያዩ የትግራይ የማህበረሰብ ክፍሎች ከተውጣጡ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ አካላት ለቀጣይ መደረክ ምቹ መደላድል የሚፈጥር ውይይት አካሂደናል " ሲሉ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተካሄደው ጥልቅ ውይይት በጥያቄና መልስ የታጀቡ በርካታ ጉዳዮች እንደተነሱ ገልጸዋል።

በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አተገባበር ያሉት ተግዳሮቶች እንዴት መታረም አለባቸው ፣ ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ ንግግሮች መቆምና መታረም እንዳለባቸው በተለይ የተፈናቃዮችና ትግራይን መልሶ መገንባት ጉዳይ የምክክሩ ዋነኛ ነጥቦች ነበሩ ብለዋል።

የትግራይ ህዝብና ልሂቃን በአገሪቱ ፓለቲካና ኢኮኖሚ በብርቱ ተዋናይ የሚሆኑበት ሁኔታ መፍጠር እጅግ አስፈላጊ እንደሆነና ሌሎች ጉዳዮች ተነስው መግባባት ተደርሶባቸዋል ብለዋል።

" የፌደራል መንግስት ከህዝብ ፣ ከጊዚያዊ አስተዳደሩና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በፓለቲካ በፀጥታና ኢኮኖሚ እንዲሁም በትግራይ መልሶ ግንባታ ዙሪያ ተቀራርበን እንደምንሰራ ደገመን እረጋግጠንላችኋለን " ብለዋል።

የትግራይ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሸማግሌዎች ትናንት ሀምሌ 10/2017 ዓ.ም በመቐለ ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ከተወያዩ በኋላ ወደ አዲስ አበባ በማቅናት ነው ዛሬ ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር ) ጋር ውይይት ያደረጉት ሲል የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamliyAA

ፎቶ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

🔥 ከወር እስከ ወር ያለገደብ!

ወሩን ሙሉ ያለገደብ መደወል የሚያስችሉ ወርኃዊ ፕሪሚየም የድምጽ ጥቅል ካልተገደበ ነጻ የመልዕክት አገልግሎት ጋር!

❇️ በ979 ብር ብቻ!

💁‍♂️ በቴሌብር ሱፐርአፕ፣ በማይ ኢትዮቴል፣ በአርዲ ቻትቦት እንዲሁም በ*999# ይግዙ፣ ወሩን ሙሉ ያለሐሳብ ይጠቀሙ!


#MonthlyUnlimitedVoicePackage
#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ስምረት

በእነ አቶ ጌታቸው ረዳ የተቋቋመው ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) የፓለቲካ ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤቱ በመቐለ ከፈተ።

በተጨማሪም ፓርቲድ የመቐለ እና ደቡባዊ ምስራቕ ዞን ቅርንጫፍ ቢሮዎች ከፍቷል።

ፓርቲው እንዳስታወቀው ዋና ፅህፈት ቤቱ በመቐለ በመክፈት የፓለቲካ ስራውን በግልፅ ጀምሯራ።

ፓርቲው በሁሉም የትግራይ የዞን ፣ የወረዳና ከተሞች ፓለቲካዊ ፅህፈት ቤቶች መክፈት እንደሚቀጥል አስታውቋል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ታማኝ የመረጃ ምንጮች እንዳሉት ከአንድ ወር በፊት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ  የምርጫ ቦርድ ቅድመ እውቅና ያገኘው ስምረት ፓርቲ ለምስረታ ብቁ የሚያደርጉት አባላት መልምሎ ጨርሷል።

የክልል ፓርቲ ለመመስረት የሚስፈልገው 4 ሺህ በላይ መስራች አባላት መልምሎ ለይፋዊ ምስረታ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የመረጃ ምንጮቹ ተናግረዋል።

ስምረት ፓርቲ በቀጣዩ የነሀሴ ወር 2017 ዓ.ም በትግራይ ይፋዊ ምስረታ በማከናወን ከቅድመ እውቅና ወደ ሙሉ እውቅና እንደሚሸጋገር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamliyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Save_the_Children #GSK

Calling all #Ethiopian Innovators!

The second round of the Immunisation Innovation Accelerator is now open - offering up to $100,000 in grants to solutions that improve #vaccine access.

📅 Application deadline: July 27
🔗 https://www.stc-accelerator.org/

#ChildHealth #InnovationInAction #HealthInnovation #Ethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Bahirdar

በአማራ ክልል መዲና ባሕርዳር ከተማ ተጥለው ከነበሩ ክልከላዎች ከፊሎቹ መነሳታቸውን የከተማው የጸጥታ ም/ቤት ዛሬ ምሽት አሳወቀ።

ምክር ቤቱ ፤ ማንኛውም የንግድ እንቅስቃሴ ያለገደብ 24 ሰዓት ክፍት በማድረግ እንዲሰሩ ወስኗል።

ከባጃጅ እና ከሞተር ሳይክል ውጭ ሁሉም ተሽከርካሪዎች ያለገደብ እንዲንቀሳቀሱም ውሳኔ አሳልፏል።

በተጨማሪ ማንኛውም ሰው ያለምንም የሰዓት ገደብ እንዲንቀሳቀስ የጸጥታ ም/ቤቱ ወስኗና።

ምክር ቤቱ ማሻሻያ ያልተደረገባቸውና አሁንም የተጣሉ ግዴታዎች እንዳሉ አስገንዝቧል።

➡️ ማንኛውም ተሽከርካሪ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ የፊት ለፊትና የኋላ ሰሌዳ አሟልቶ መንቀሳቀስ እንዳለበት ይህንን ሳያደርግ ተገኝቶ በጸጥታ ሀይሉ ለሚወሰደው ማንኛውም ህጋዊ እርምጃ ሀላፊነቱን ራሱ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

➡️ ማንኛውም እግረኛ ሲንቀሳቀስ ማንነቱን የሚገልጽ የቀበሌ የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት አለበት ብሏል።

➡️ የጸጥታ ሀይሉና በሚኖሩበት ቀበሌ ወይም ቀጠና ወይም ብሎክ ብቻ መሳሪያ ይዘው እንዲንቀሳቀሱ ከፈቀደላቸው መሳሪያ ፈቃድ ኩፖን ከተሰጣቸው ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በፍጹም የተከለከለ መሆኑ አስገንዝቧል።

➡️ የባጃጅ ተሽከርካሪ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት በኋላ ይዞ መንቀሳቀስ ክልክል መሆኑን አሳውቋል።

➡️ ባለ 2 እግር ሞተር በማንኛውም ሁኔታ ይዞ መንቀሳቀስ በፍጹም የተከለከለ እንደሆነ አስጠንቅቋል።

#BahirdarCity

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

“ ለውጪ አገር ዜጋ ቦታ ለመስጠት ብለው በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ለማፈናቀል እየተሯሯጡ ነው ” - 1400 አባላትን ያቀፈው ማኀበር

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው ' አጣና ተራ ' በተሰኘ ቦታ 1400 የሚሆኑ ሰዎች በተለያዩ ስራዎች የሚንቀሳቀስበትን ቦታ ያለ ምትክ “ ልቀቁ ” መባላቸውን ማኀበራቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቤቱታውን አሰማ።

“ ዜድቲኤም ማኀበር ” ከተመሰረተ 20 ዓመታትን እንዳስቆጠረ ገልጾ፣ “ ቦታው የሚሰጠው ለቻይናዊ ነው ተብሏል፤ ‘ለባለሃብት ተሰጥቷል ከቦታው ላይ ተነሱ’ ተብለናል ” ሲል ገልጿል።

“ ካሳም ሆነ ምትክ ቦታ አልተሰጠንም ” ያለው ማኀበሩ፣ “ መንግስት በሐምሌ ጨለማ ሜዳ ላይ አይጣለን፤ በሦስት ቀናት ውስጥ ወጥተን የት እንወድቃለን ? ” ሲል ጠይቆ፣ መንግስት አካባቢውን ለማልማት ጊዜ፣ ወይም ምትክ ቦታ እንዲሰጣቸው አሳስቧል።

ማኀበሩ በዝርዝር ምን አለ ?

“ ለውጪ አገር ዜጋ ቦታ ለመስጠት ብለው በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ለማፈናቀል እየተሯሯጡ ነው። የበላይ የመንግስት አካልም የሚያውቀው አይመስለንም። ከታች ያሉት አካላት አሻጥር እየሰሩ ህዝቡን በዚህ በሐምሌ ጨለማ ‘በሦስት ቀናት እቃህን ይዘህ ውጣ’ የሚል አሳዛኝ ድርጊት ነው እየተፈጸመ ያለው ” ብሏል።

ማኀበሩ፣ “ ትልቅ በደል ነው በህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው። ህዝቡ እያለቀሰ ነው፤ ምሳውን በልቶ እራቱን የማይደግም ህዝብ ነው ችግር ላይ እየወደቀ ያለው ” ሲልም ወቅሷል።

ቦታውን ከ50 ዓመት በፊት ጀምሮ ይሰሩበት እንደነበር የገለጸው ማኀበሩ፣ “ ነባር ቦታ ነው፤ ቤት ንብረት ተመስርቶ፣ በግለሰብም ተከራይቶ የሚኖርበት ቦታ ነው ” ብሏል።

“ አካባቢው ነባር መዘጋጃ ቤት ነው፤ በኃይለ ሥላሴ ጊዜ ተሰርቶ ለግለሰቦች የተከራየ ቤት ነው። በ1960 ዓ/ም የተያዘ ቦታ ነው። ከሱ ቤት ውስጥ ነው ውጡና ሜዳ ላይ ውደቁ የተባለው ” ሲልም አክሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታውን ይዞ ምላሽ የጠየቃቸው አንድ የክፍለ ከተማው አካል፣ “ ጉዳዩ አይመለከተኝም ” ብለው ስልክ ዘግተዋል፤ በድጋሚ ሲደወልም ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም፣ ተጨማሪ ጥረት ይደረጋል።
 
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ስያሜያችሁ ከብሔር ስም ጋር የተገናኘ ከሆነ መቀየር ይኖርባችኋል " - የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሀገሪቱ በሁሉም የሊግ እርከን የሚገኙ ክለቦች በ2018 የውድድር ዓመት ምዝገባ ወቅት የክለብ ስያሜያቸው ከብሔር ስም ጋር የተገናኘ ከሆነ በመቀየር ማስመዝገብ እንደሚኖርባቸው አዟል።

ከዚህም በተጨማሪ ክለቦች በኦፊሴላዊ መለያ (አርማ) ላይ ፖለቲካዊ እና የብሔር ይዘት ያላቸው መልዕክቶች እና ምስሎችን መጠቀም የተከለከለ መሆኑን ፌዴሬሽኑ አስገንዝቧል።

#Ethiopia🇪🇹

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#DStvEthiopia

🎬 በአቦል ቲቪ የሚተላለፉትን አዝናኝ እና አጓጊ ተከታታይ ድራማዎችን በ479 ብር ብቻ በጎጆ ፓኬጅ ላይ ይኮምኩሙ!

🌟 ፍርቱና- ዘወትር ሰኞ ከምሽቱ 2፡00
🌟 ግዛት- ከሰኞ-ረቡዕ ከምሽቱ 2፡30
🌟 ዕፀህይወት- ሀሙስ እና አርብ ከምሽቱ 2፡30
🌟 አፋፍ - ከሰኞ-አርብ ከምሽቱ 3፡30

ይህንን ሊንክ በመጫን የተለያዩ የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ያግኙ!
👇
https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/mabkg72w

#ሁሉምያለውእኛጋርነው

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ግብር

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱም የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅን በ5 ተቃውሞ፣ በ12 ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው ያፀደቀው።

በሕዝብ ተወካዮች ምር ቤት የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ የገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያው ከግብር ነጻ የሆነው ከመቀጠር የሚገኘ ገቢ ከፍ እንዲል የተደረገ በመሆኑ ፦
- ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ተቀጣሪዎች ላይ የግብር ጫናው እንደሚቀንስ፤
- የግብር መሰረቱ እንዲሰፋ፤
- መንግስት ከገቢ ግብር የሚያገኘው ገቢ በአንጻራዊ ሁኔታ ከፍ እንዲል አጋዥ መሆኑን አመልክተዋል።

በማሻሻያው ላይ ከበርካታ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እንደተደረገበት እና እንደ ቋሚ ኮሚቴም ሰፊ ጊዜ ተወስዶበት የተዘጋጀ ማሻሻያ ነው ብለዋል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ " ማሻሻያው ለረጅም ጊዜ ውይይት የተደረሀበት እና የሀገራት ልምድ የተወሰደበት ነው። ማሻሻያው ዘመኑን የዋጀ ነው " ሲሉ ተናገረዋል።

አዋጁን የተቃወሙ የምክር ቤት አባላት የገቢ ግብር ማሻሻያው የመንግስት ሠራተኛውን የኑሮ ሁኔታ ታሳቢ ያላደረገ ማሻሻያ በመሆኑ ምክር ቤቱ ማሻሻያውን በድጋሚ እንዲፈትሸው ጠይቀዋል፡፡

የገቢ ግብር አዋጁ ከዚህ ቀደም ሰፊ የክርክር ነጥቦች የተነሳባቸው ጉዳዮች ላይ ማስተካከያ ሳይደረግበት ነው በ5 ተቃውሞ ፣ በ12 ድምጸ ተዓቅዶ በአብላጫ ድምጽ የፀደቀው።

#HoPR🇪🇹
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#HoPR🇪🇹

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ እያካሄደ ባለው አስቸኳይ ስብሰባ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅ አጽዷል።

የተሻሻው አዋጅ በቀጣይ ዓመት ለሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ 26 አንቀፆች ላይ ማሻሻያ የተደረገበት ናው ተብሏል።

በተሻሻለው አዋጅ ሀገራዊ የፖለቲካ ፓርቲ ለመሆን የ6 ክልሎችን ድጋፍ ማግኘትን ያስገድዳል።

ምክር ቤቱ አዋጁን በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።

ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ስብሰባው ሰፊ ክርክር ሲነሳበት የነበረውን የፌደራል ገቢ ግብር ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ያጸድቃል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

የስታርት አፕ ረቂቅ አዋጅም ዛሬ ያጸድቃል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ጥቆማ
#ለሚመለከታችሁ_አካላት

" ይሄ የመብራት ፖል የመኖሪያ ቤት ላይ ወድቆ ጉዳት ሳያደርስ በፊት መፍትሄ ይፈለግለት " - ነዋሪዎች

ከላይ የተያያዘው ቪድዮ አዲስ አበባ፣ እንጦጦ ማርያምን በተለምዶ ' ሀሙስ ገበያ ' እየተባለ የሚጠራው አካባቢ ከሚኖሩ ነዋሪዎች የተላከ ነው።

በቪድዮው ላይ እንደሚታየው የመብራት ፖሉ ቤት ላይ ተንጋዶ ይገኛል።

አንድ የአካባቢው ነዋሪና የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል " የመብራት ፖሉ ቤት ተደግፎ ነው ያለው ፤ በተደጋጋሚ ለሚመለከታቸው አካላት ሄደን ብናመለክትም ምላሽ ሊሰጡን አልቻሉም " ብሏል።

" አሁን ከባድ ንፋስ እና ከባድ ዝናብ ስላለ አስጊ ሁኔታ ላይ ነው ያለው " ሲል ገልጿል።

" የሰው ህይወት እንዲሁም በንብረት ላይ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል ጥቆማውን ተመልክታችሁ የሚመለከታችሁ አካላት መፍትሄ እንድትወስዱ " በማለት ጥሪ አቅርቧል።

#TikvahEthiopiaFamliyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Oromiyaa

✅ 384,498 (78.7%) ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት አምጥተዋል !

የ2017 የኦሮሚያ ክልል 8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ይፋ ሆኗል።

በክልሉ ፈተናቸውን የወሰዱ ተማሪዎች ወንድ 251,120 ፤ ሴት 237,338 በድምሩ 488,458 ናቸው።

ከተፈተኑት ተማሪዎች መካከል ወንድ 205,113 (81.7%) ሴት 179,388 (75.6%) በድምሩ 384,498 (78.7%) ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት በማስመዝገብ ወደ ሚቀጥለው ክፍል ተዛውሯል።

ተማሪዎች ውጤት ለማየት oromia.ministry.et መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጿል።

መረጃው የተላከው ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ያጋጠመ ሞት የለም ! " - የአሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሰራተኞች

ዛሬ ምሸት በመቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ ምንድን ነው የተከሰተው ?

ባለቤትነቷ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነችው ET-A U Z አውሮፕላን ከአዲስ አበባ ተነስታ መቐለ አሉላ አባነጋ የአውሮፕላን ማረፍያ ከምሽቱ 1:52 ለማረፍ ስትል  ቀላል አደጋ አጋጥሟታል።

የአውሮፕላንዋ ዋናና ረዳት አብራሪ ፤ 2 ሰራተኞች እንዲሁም 49 ተጓዦች በአጠቃላይ 53 ሰዎች አሳፍራ ነበር። 

አውሮፕላንዋ በማረፍ ላይ እያለች በግራ ክንፋዋ በኩል አደጋ እንዳጋጠማትና የአደጋው መነሻ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ታውቀዋል። 

የአሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ ሰራተኞች ለድምፂ ወያነ ሚድያ በሰጡት መረጃ በአደጋው ያጋጠመ ሞት የለም። ተጓዦችም ወደየ ቤተሰቦቻቸው በሰላም እንደተሸኙ ገልጸዋል።

ሌሎች ያልተረጋገጡ ምንጮች ደግሞ በአደጋው የአውሮፕላንዋ ካፒቴን የሚገኙባቸው ጥቂት ተጓዦች ጉዳት ደርሶባቸው በመታከም ላይ መሆናቸውን ፅፈው አሰራጭተዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ጉዳዩን በተመለከተ ከሃኪሞች መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ለማግኘት ጥረት አድርጓል። ስለጉዳዩ ምላሽ የጠየቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ " እያጣራን ነው ያለነው፤ መግለጫ እናወጣለን " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

#TikvahEthiopiaFamliyMekelle
#TikvahEthiopiaFamliyAA

ፎቶው ፦ ድምፂ ወያነ

@tikvahethiopia

Читать полностью…
Subscribe to a channel