tikvahethiopia | Unsorted

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1527733

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Subscribe to a channel

TIKVAH-ETHIOPIA

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ስለ #ኢትዮጵያ 🇪🇹 ምን እያሉ ነው ?

ከሀገራቸው ጉዳይ ይልቅ ስለ ሰው ሀገር ጉዳዮች ሰፊ ጊዜ ወስደው በመናገርና በመተንተን የሚታወቁት የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትላንት ምሽት በሀገራቸው ብቸኛው ቴሌቪዥን በተላለፈ ቃለ መጠይቅ #የኢትዮጵያን ስም ደጋግመው ሲያነሱ ታይተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ከወራት በፊት በነበራቸው ቃለ መጠይቅ ከሀገራቸው ጉዳይ ይልቅ ስለ ኢትዮጵያ እና ቀጠናው ጉዳይ ትንታኔ ሲሰጡ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም። በወቅቱም ኢትዮጵያ ስሟን እያነሱ ለተናገሩት ነገር ሁሉ በቀጥታ አንዳችም ምላሽ ሳትሰጣቸው በዝምታ አልፋቸዋለች።

ትላንት በነበራቸው ቃለ መጠይቅ ደግሞ ንዴትን በቀላቀለ ሁኔታ በማይመጥኑ ቃላት የኢትዮጵያን ስም ሲያነሱ ነበር።

በተለይም ኢትዮጵያ ያነሳችውን የባህር በር ጥያቄ ሲያጣጥሉት ነው ያመሹት።

የኢትዮጵያን የወደብ እና የባህር በር ጥያቄ " የህጻን ጨዋታ ነው፣ ማሳሳቻ ነው፣ የረከሰ ውሸት ነው ፣ የውስጥ ጉዳይ ማዳፈኛ ነው ፣ ጀርባው የተባበሩት አረብ ኤሜራት የወደብ ማስፋፋት አጀንዳ ነው " የሚሉ ቃላቶችን በመጠቀም ኢትዮጵያን ለማጣጣል ሞክረዋል።

ኢትዮጵያ የባህር በርን ጉዳይ አለም አቀፍ አጀንዳ ማድረጓን ተከትሎ በርካታ ሀገራት ለጥያቄዋ ድጋፍ ማድረጋቸውም ፕሬዝዳንቱን እንዳላስደሰተ የሚጠቁም ንግግርም ሲናገሩ ነበር።

" ፈረንሳይ ከኛ ጋር ናት፣ አሜሪካ ፣ ኤማራት፣ አውሮፓ ህብረት ከኛ ጎን ናቸው ማለት ጭንቅ እንጂ የድል መንገድ አይደለም " በማለት " ኢትዮጵያውያን የውስጥ ችግራችሁን ፍቱ " ሲሉ ተደምጠዋል።

በኢትዮጵያ በኩል ሀገራቸው ላይ የጦርነት  ስጋትና ዛቻ እንዳለ በማመላከትም " እራሳችንን እንጠብቃለን " ሲሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ለባሕር ስትል ኤርትራንም ሆነ የትኛውንም ጎረቤት ሀገር የመውጋት አንዳችም ፍላጎት እንደሌላት በተደጋጋሚ ማሳወቋ ይታወሳል። ነገር ግን የባህር በር ጉዳይ ህልውናዋ መሆኑን ለዓለም ህዝብ አስረግጣ ተናግራለች።

ሌላው ፕሬዜዳንቱ ኢትዮጵያ ተመድ ሄዳ ከሳናለች (ክሱ ፦ ድንበር አካባቢ አሁንም የኤርትራ ጦር ግፍ እየፈጸመ ስለመሆኑ)  " ያሉም ሲሆን " ክሱ አስነዋሪና አሳፋሪ ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

ስለ ፕሪቶሪያ ስምምነትም ሲያነሱ ነበር።

ገና የትግራይን ጦርነት ያስቆመው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሲፈረም ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት እንዳሻከረች በይፋ የሚታወቅ ቢሆንም " ኤርትራን ከመክሰሳችሁ በፊት የፕሪቶሪያን ውል ተግብሩ ፤ የውስጥ ችግራችሁን መፍታት አስቀድሙ ፤ ለምን ስምምነቱ በቅን ልቦና አልተተገበርም ለምን ፋኖ ላይ ጦርነት ከፈታችሁ ? " የሚል ንግግርም ተናግረዋል።

ሌላው የፖለቲካ ፓርቲዎች የሌለባት ፣ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የማይታወቅባት ኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያን በተመለከተ ንግግራቸው " በኢትዮጵያ መታየት ጀምሮ የነበረው የለውጥ ተስፋ ጨልሟል ፤ የፖለቲካ ፓርቲ ብሎ የለም " የሚል ንግግር አሰምተዋል።

ያለአንዳች ተቀናቃኝ ከ30 ዓመት በላይ  ኤርትራን እየገዙ ያሉት ኢሳያስ አፈወርቂ እንደ ሁል ጊዜው የትላንት ምሽቱ ቃለ ምልልሳቸው ስለ ሀገራቸው ጉዳይ ሳይሆን ስለ ኢትዮጵያ እንዲሁም ስለ ሌሎች ሀገራት ጉዳይ በመተንተን ነው ያለፈው።

ከዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ተነሳሽነት በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ሰላም እንዲወርድ ከተደረገ በኃላ የትግራይን ጦርነት ያስቆመው የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እስኪፈረም ድረስ ኢትዮጵያን እና አስተዳደሯን ሲያሞካሹ እንደቆዩ በአደባባይ የሚታወቅ ሀቅ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamliyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ስኬት ባንክ በበጀት አመቱ አጠቃላይ የካፒታል መጠኑን 9.3 ቢሊዮን ብር አደረሰ!

ስኬት ባንክ በ2024/25 በጀት ዓመት አፈፃጸም እና 2025/26 ዕቅድ ላይ ከሐምሌ 18 -19/2025 የሁለት ቀናት ጉባኤ አካሂዷል፡፡

በውይይቱ ላይ እንደተገለፀው በ2024/25 በጀት ዓመት የባንኩ አጠቃላይ ካፒታል 9.3 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን 19.2 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ሀብት አስመዝግቧል፡፡

ባንኩ ብር 7.6 ቢሊዮን ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ የቻለ ሲሆን በዚህም ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 2.7 ቢሊዮን ብር ገቢ በማስመዝገብ ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማግኘት ችሏል።

የስኬት ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳምጠው አለማየሁ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት ባንኩ በጀት ዓመቱን በስኬት መጠናቀቁን ገልፀዋል፡፡

በአብዛኛዎቹ የሥራ አፈፃፀም መለኪያዎችም የላቀ አፈፃፀም መመዝገቡን በማንሳት፤ የባንኩን ስኬታማ ጉዞ በማስጠበቅ በእንዱስትሪው ተወዳዳሪ ሆኖ ለመስራት የሚያስችል የአምስት (5) ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ በመንደፍ ወደ ስራ የገባ ሲሆን ከተለያዩ የሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገር ከሚገኙ ተቋማት ጋር በቀጣይነት አብሮ ለመስራት የሚያስችል ስትራቴጂካዊ ስምምነቶችን እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ስኬት ባንክ የማህበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት አንፃር በተለያዩ ጊዜያት ሰፊ ስራዎችን የሰራ ሲሆን በበጀት ዓመቱም ከ56 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አበርክቷል፡፡

በመጨረሻም በ2024/25 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ዲስትሪክቶች፣ ቅርንጫፎች እና ሰራተኞች የዋንጫ፤ የምስክር ወረቀት እና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ስኬት ባንክ የስኬትዎ መሰረት!

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#OFC

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ መጀመሩን የህዝብ ግንኙነት ፅ/ቤቱ በላከልን መረጃ ገለጸ።

" በአገሪቱ ላይ የተደቀነውን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የፀጥታ ቀውስ ለመገምገም እና የፓርቲውን የወደፊት አቅጣጫ ለመቀየስ የሚያስችለውን ወሳኝ ስብሰባ ነው " ብሏል።

ዛሬ ስብሰበው በፓርቲው የውስጥ አቅም ግንባታና ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ላይ ያተኮረ እንደነበር አመልክቷል።

የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የፓርቲውን አመራርና ድርጅታዊ ብቃት ለማጠናከር ልዩ ሥልጠናዎችን እንደወሰዱና ሥልጠናው በፍጥነት በሚለዋወጥና ፈታኝ በሆነው የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ የኦፌኮን የወደፊት አቅጣጫ ለመቅረፅ ያለመ እንደሆነ ገልጿል።

ነገ ደግሞ ውይይቱ ትኩረት " በኦሮሞ ሕዝብ፣ በኢትዮጵያና በሰፊው የአፍሪካ ቀንድ ክልል ላይ በተደቀኑት ከባድ ፈተናዎች ላይ ይሆናል " ብሏል።

" በአጀንዳው ውስጥ በዋናነት የተካተቱት ጉዳዮች በቀጠለው ጦርነትና ማኅበረሰቡን ባወደመው ከፍተኛ የፀጥታ እጦት፣ በመንግሥት የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም የተባባሰው ከባድ የኢኮኖሚ ችግር፣ የተንሰራፋው የወጣቶች ሥራ አጥነት እና ስር የሰደደው ሥርዓታዊ ሙስና ናቸው " ሲል ገልጿል።

በእነዚህ ውይይቶች ማዕከላዊው ጉዳይ ፓርቲው ለመጪው የ2018 አገራዊ ምርጫ ያለው ስትራቴጂ እንደሆነ አመልክቷል።

" ኦፌኮ ነፃ፣ ፍትሐዊ እና እምነት የሚጣልበት ምርጫ በማካሄድ እውነተኛ የዲሞክራሲ ሽግግርን ለማረጋገጥ መንግሥት እንደ ቅድመ ሁኔታ የፖለቲካ ምህዳሩን እንዲከፍት ተጨባጭና ሊረጋገጡ የሚችሉ እርምጃዎችን እንዲወስድ ጥያቄዎቹን በይፋ ያቀርባል " ብሏል።

ስብሰባው ከተጠናቀቀ በኃላ ፓርቲው ይፋዊ መግለጫ እንደሚያወጣ ጽ/ቤቱ በላከልን መረጃ አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamliyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በቱርካና ሀይቅ ሙላትና መስፋፋት ምክንያት የዳሰነች ወረዳ ዋና ከተማ ኦሞ ራቴ ወደ ሌላ ቦታ ይዋቀራል " - ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ

ዛሬ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ በአርባ ምንጭ ከተማ ሲካሄድ ውሏል።

በዚሁ ጉባኤ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ከምክር ቤት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

አቶ ጥላሁን ካነሷቸው ጉዳዮች አንዱ የዳሰነች ወረዳ ጉዳይ ነው።

በቱርካና ሀይቅ ሙላትና መስፋፋት ምክንያት የዳሰነች ወረዳ ዋና ከተማ የሆነዉ ኦሞ ራቴ ከተማ ወደ ሌላ ሊዋቀር መሆኑን አሳውቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በኢትዮጵያ ኬንያ ድንበር አከባቢ በሚገኘዉ የቱርካና ሀይቅና የኦሞ ወንዝ ሙላትን ተከትሎ ፦
- የወረዳዉ 66 በመቶ መሬት ፤ በርካታ ቀበሌዎች በዉሃ ሙላት መጥለቅለቁን
- ከ86 ሺህ ዜጎች በላይ መፈናቀላቸውን
- የወረዳዉን ዋና ከተማ ኦሞራቴን ጨምሮ ተፈናቃዮች የሚገኙባቸዉ መጠለያ ጣቢያዎች ስጋት ውስጥ መሆናቸውን የአካባቢውን ነዋሪዎች ዋቢ በማድረግ ተደጋጋሚ መረጃዎች ማጋራቱ ይታወሳል።

ይህ ጉዳይ ሰኔ 26/2017 ዓ/ም በነበረዉ 6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 42ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ቀርቦ ነበር።

ዛሬ ጉባኤውን ባካሄደው የክልል ም/ቤት ርዕሰ መስተሳደሩ፤ ዉሃ ሙላቱ ዋነኛው መንስኤ የቱርካና ሀይቅ የዉሃ መጠን መጨመርና መስፋፋት መሆኑን አንስተዋል።

በዳሰነች ወረዳ አከባቢ ያለዉ የዉሃ ሙላት የወረዳዉን ዋና ከተማ ኦሞ ራቴን ጭምር አደጋ ዉስጥ የጣለ መሆኑን ገልጸዋል።

" የኦሞ ራቴ ከተማን ሌላ ቦታ ለማስፈር ጥናት ተጠናቆ ወደ ትግበራ ሊገባ ስለሆነ የክልሉ ነዋሪዎች የአከባቢውን ነዋሪዎች በማቋቋም ረገድ የድርሻችሁን እንዲትወጡ " የሚል ጥሪ አቆርበዋል።

ተጨማሪ የክልሉ ምክር ቤት መረጃዎች : https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-07-19-2

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አርባ ምንጭ
#TikvahEthiopiaFamilyArbaminch

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update
#EFFROT

እነ አዲስአለም ባሌማ (ዶ/ር) ፣ ደብረጽዮን ገ/ማካኤል (ዶ/ር) ጨምሮ 12 ሰዎች እግድ ተጣለባቸው።

በትእምት ኢንቨስትመንት ዙሪያ ቀደም ሲል በፍትህ ቢሮ " ህጋዊ አይደላችሁም "  የተባሉ አካላት  ፍርድ ቤትም እንዳገዳቸው የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል መረጃውን ልኳል።

የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት እግድ የጣለው በኣዲስ ኣለም ባሌማ (ዶ/ር) የሚመራውና ባለፈው የካቲት ወር 2017 ዓ.ም ጉባኤ አካሂዶ የትእምት አመራር ለሚለው አካል ነው።

የትግራይ ፍትህ ቢሮ ነባሩ የትእምት አመራር በፅሁፍ ያቀረበለት " በኣዲስ ኣለም ባሌማ (ዶ/ር) የሚመራው አካል ያካሄደው ጉባኤ 'ህገ-ወጥና ቅቡልነት እንደሌለው ይረጋገጥልኝ " የሚል ክስ ከ10 ቀናት ማጣራት በኋላ ተቀባይነት ማግኘቱ መዘገባችን ይታወሳል።

የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት ሀምሌ 11/2017 ዓ.ም በፃፈው ትእዛዝ በስም የጠቀሳቸው ኣካላት ተለዋጭ ቀጠሮ እስኪሰጥ ድረስ በትእምት ኢንቨስትመንት ስም ማንኛውም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ የአግድ ትእዛዝ ጥሎባቸዋል።

ተከሳሾቹ እነማን ናቸው ?

1. ኣረጋዊ ገ/ሚካኤል(ዶ/ር)
2. ጀነራል ክንፈ ዳኘው
3. ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)
4. ኣብራሃም ተኸስተ  (ዶ/ር)
5. ወ/ሮ ኪሮስ ሓጎስ
6. አምባሳደር ሃይለኪሮስ ገሰሰ
7. ፃድቕ ኪ/ማርያም (ዶ/ር)
8. አቶ ሰናይ ካሓሰ
9. ኮ/ል ካሕሳይ ተኽሉ
10. ወ/ሮ ሸዊት አዲሱ
11. አቶ አታኽልቲ ገ/ሂወት
12. አምባሳደር አዲስ አለም ባሌማ (ዶ/ር)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamliyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ሴጅ_ማሰልጠኛ_ኢስቲትዩት

የሶስት ወር የበይነ መረብ (Online) ስልጠናዎች ሐምሌ 28/2017 ዓ.ም ይጀመራሉ።
የስልጠናዎቹ ዓይነት:
👉 Advanced Graphic, Video Editing, Motion  Graphic and Digital Marketing
👉 Computer  Programming and Database
👉MERN Stack Website and Mobile Application Development
👉Modern Accountancy (ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ)
👉 Import and Export
👉 Research Methods and Analysis
👉 Animation and Visual Effect
👉  Artificial Intellegence and Data Science
👉 Journalism
👉 Interior Design
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያናs ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram sage_training_institute">Tiktok Linkedin

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ንብተራ ኦንላይን

• ነባር ደንበኛችን ከሆኑ አሁኑኑ የንብ ሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያን "update/upgrade" ያድርጉ፣

• አዲስ ደንበኛችን ከሆኑ ደግሞ መተግበሪያውን በማውረድ አቅራቢያዎ ወደ ሚገኝ ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉና የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሁኑ፣

***
ይሠሯል ከልብ እንደ ንብ!

#Nib #nibmobilebanking #NibQR #nib #nibtera #nibbank

Facebook  / Instagram / linkedin / nibinternationalbank6204">X / nibinternationalbank6204">Youtube / nibinternationalbank">Tiktok / Website

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

ነዋሪነታቸው እንጦጦ ማርያም በተለምዶ ' ሀሙስ ገበያ ' የሆኑ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መኖሪያ ቤት ላይ የመብራት ፖል ተንጋዶ መተኛቱን በመጠቆም በክረምቱ ንፋስና ዝናብ ጉዳት ሳይደርስ በፊት የሚመለከታቸው አካላት እንዲያስተካክሉላቸው ትላንት ጠቁመው ነበር።

ጥቆማው የደረሰው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለሞያዎቹን በመላክ ጥገና አደርጎ ማስተካከሉን አገልግሎቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቋል።

" ለህብረተሰቡ እንዲሁም ለሚዲያችሁ ምስጋና እናቀርባለን፡፡ በቀጣይም በአገልግሎታችን ላይ ለሚሰጡን ጥቆማዎችና ቅሬታዎች በወቅቱ ለመፍታት እንሰራለን " ሲል ገልጿል።

ጥቆማውን ያደረሱ የአካባቢው ነዋሪዎች ዛሬ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለሙያዎች መጥተው ችግሩን ማስተካከላቸውን ገልጸው ምስጋናን አቅርበዋል።

ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፤ ከጋርመንት ወደ ጀሞ 1 መሄጃ መንገድ ላይ ' ዘመን ማደያ ' አካባቢ በመኪና የተገጨ እና በክረምቱ ዝናብና ንፋስ ቢወድቅ ጉዳት የሚያደርስ ኮንክሪት ፖል ጥቆማ በደረሰ ቀን እስከ ምሽት 4 ሰዓት በመስራት መቀየሩ ይታወሳል።

#EthiopianElectricUtility

#TikvahEthiopiaFamliyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

ፍርድ ቤቱ አለልኝ አዘነ በሰዉ እጅ ስለመገደሉ አረጋግጦ ባለቤቱንና የባለቤቱን እህት ባል ጥፋተኛ ብሎ ብይን ሰጥቷል።

በእግር ኳስ ተጫዋቹ አለልኝ አዘነ ግድያ ላይ ዛሬ በሁለት ፈረቃዎች የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት የተሰየመው የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ የአለልኝ ባለቤት እና 2ኛ ተከሳሽ የባለቤቱ እህት ባል መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ/ም ከሌሊቱ 5፡30 እስከ 8 ሰዓት ገደማ ባለዉ ጊዜ በአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ነጭ ሳር ቀበሌ ልማት ሰፈር ' ሃይላንድ ' ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በተቀነባበረ ሁኔታ የ26 አመቱን ወጣት አለልኝ አዘነን በመግደል እራሱን ያጠፋ እንዲመስል በማድረግ የግዲያ ወንጀል መፈፀማቸው በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች በመረጋገጡ ጥፋተኛ እንዳላቸው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል መረጃውን ልኳል።

ዛሬ ከሰዓት በኋላ የፍርድ ድሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ይዞ የነበረዉ የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መደበኛ ችሎት የዐቃቤ ሕግና የተከሳሾችን ጠበቃ የቅጣት አስተያየት ካደመጠ በኋላ ዉሳኔዉን ወደ ሀምሌ 15/2017 ዓ/ም አሸጋግሯል።


ምን የሚሉ የቅጣት አስተያየቶች ተሰጡ ?

የተከሳሾች ጠበቃ (የቅጣት ማቅለያ) ፦
👉 ተከሳሾች የወንጀል ሪከርድ የሌለባቸው መሆኑን
👉 የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸዉንና
👉 1ኛ ተከሳሽ የሟች አለልኝ አዘነ ባለቤት የአስም ታማሚ መሆኗ በቅጣት ማቅለያነት አቅርቧል።

የጋሞ ዞን ከፍተኛ ዐቃቤ ሕግ (የቅጣት ማክበጃ) ፦
ዐቃቤ ሕግ የወንጀል አወሳሰን መመሪያ ማንዋል 03/2017ዓ/ም እና የወንጀል ሕጉን አንቀፅ 84 (1) ለ፣ ሐ፣ ሠ በመጥቀስ
➡️ የአገዳደሉ አደገኛነት
➡️ ወንጀል ፈፃሚዎች ለወንጀል ድርጊቱ የመረጡት ሰዓት አሳቻና ሰዎች የማይደርሱበትን ሰዓት መሆኑን
➡️ በዘመድ ላይ የተፈፀመ የጭካኔ ወንጀል መሆኑን በመግለፅ እንዲሁም ሟቹ አለልኝ አዘነ ለብሔራዊ ቡድኑ (ለሀገር) ሲሰጥ የነበረዉን ግልጋሎት ከግምት ዉስጥ በማስገባት ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን እንዲያከብድ ጠይቋል።

የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ያደመጠዉ ፍርድ ቤት የፍርድ ቅጣት እርከኑን ለመወሰን ለሀምሌ 15/2017 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ከስፍራው መረጃውን ልኳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አርባ ምንጭ
#TikvahEthiopiaFamliyArbaminch

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የጋሞ ዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት በእግር ኳስ ተጫዋቹ አለልኝ አዘነ ግድያ ዙሪያ ፍርድ ለመስጠት ለሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ የቅጣት ማክበጃ እና ማቅለያ የሰማ ሲሆን የመጨረሻውን የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት ለሐምሌ 15 ቀጥሯል።

ውድ ቤተሰቦቻችን ቲክቫህ ኢትዮጵያ የፍርድ ቤቱን ውሎ ዝርዝር መረጃ ከደቂቃዎች በኃላ ይልክላችኋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አርባ ምንጭ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ኢትዮጵያ🇪🇹

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ፥ " በአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች የሚደረግ ምክክርና እርቀ ሰላም ፍሬው ጣፋጭ ነው " አሉ።

ትናንት ሀምሌ 10/2017 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ያቀኑት የትግራይ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሸማግሌዎች ዛሬ ሀምሌ 11/2017 ዓ.ም ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) መክረዋል።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ከትግራይ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሸማግሌዎች ስለተካሄደው የሰላም ውይይት አስመልከተው በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው በትግርኛ ባጋሩት መረጃ " የኢፌዲሪ መንግስት በሽምግልና እና ምክክር ችግሮች እንዲፈቱ ቅድምያ ሰጥቶ እንደሚሰራ በተለያዩ ጊዚያት በተግባር አሳይቷል " ብለዋል። 

" በረጅሙ የአገሪቱ የአገረ መንግስት ስርዓት አገራዊ እርቅ ፣ አገራዊ ምክክር ፣ ፓለቲካዊ ውይይት የሚሉ ማህበራዊ አምዶች በኢትዮጵያ ፓለቲካ ውይይት በይፋ እንዲተገበሩ ያደረገው የአሁኑ መንግስት መሆኑ መካድ የለበትም " ብለዋል።
  
" ግጭት ሌላ ግጭት እየወለደ በችግር አዙሪት ከመኖር ያለፈ ሌላ ፋይዳ የለውም " ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ " በውይይትና መግባባት ችግሮቻችን በመፍታት ሰላምን በፅኑ መሰረት እናኑር " ብለዋል። 

" ከተለያዩ የትግራይ የማህበረሰብ ክፍሎች ከተውጣጡ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ አካላት ለቀጣይ መደረክ ምቹ መደላድል የሚፈጥር ውይይት አካሂደናል " ሲሉ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተካሄደው ጥልቅ ውይይት በጥያቄና መልስ የታጀቡ በርካታ ጉዳዮች እንደተነሱ ገልጸዋል።

በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አተገባበር ያሉት ተግዳሮቶች እንዴት መታረም አለባቸው ፣ ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ ንግግሮች መቆምና መታረም እንዳለባቸው በተለይ የተፈናቃዮችና ትግራይን መልሶ መገንባት ጉዳይ የምክክሩ ዋነኛ ነጥቦች ነበሩ ብለዋል።

የትግራይ ህዝብና ልሂቃን በአገሪቱ ፓለቲካና ኢኮኖሚ በብርቱ ተዋናይ የሚሆኑበት ሁኔታ መፍጠር እጅግ አስፈላጊ እንደሆነና ሌሎች ጉዳዮች ተነስው መግባባት ተደርሶባቸዋል ብለዋል።

" የፌደራል መንግስት ከህዝብ ፣ ከጊዚያዊ አስተዳደሩና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በፓለቲካ በፀጥታና ኢኮኖሚ እንዲሁም በትግራይ መልሶ ግንባታ ዙሪያ ተቀራርበን እንደምንሰራ ደገመን እረጋግጠንላችኋለን " ብለዋል።

የትግራይ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሸማግሌዎች ትናንት ሀምሌ 10/2017 ዓ.ም በመቐለ ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ከተወያዩ በኋላ ወደ አዲስ አበባ በማቅናት ነው ዛሬ ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር ) ጋር ውይይት ያደረጉት ሲል የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamliyAA

ፎቶ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

🔥 ከወር እስከ ወር ያለገደብ!

ወሩን ሙሉ ያለገደብ መደወል የሚያስችሉ ወርኃዊ ፕሪሚየም የድምጽ ጥቅል ካልተገደበ ነጻ የመልዕክት አገልግሎት ጋር!

❇️ በ979 ብር ብቻ!

💁‍♂️ በቴሌብር ሱፐርአፕ፣ በማይ ኢትዮቴል፣ በአርዲ ቻትቦት እንዲሁም በ*999# ይግዙ፣ ወሩን ሙሉ ያለሐሳብ ይጠቀሙ!


#MonthlyUnlimitedVoicePackage
#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ስምረት

በእነ አቶ ጌታቸው ረዳ የተቋቋመው ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) የፓለቲካ ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤቱ በመቐለ ከፈተ።

በተጨማሪም ፓርቲድ የመቐለ እና ደቡባዊ ምስራቕ ዞን ቅርንጫፍ ቢሮዎች ከፍቷል።

ፓርቲው እንዳስታወቀው ዋና ፅህፈት ቤቱ በመቐለ በመክፈት የፓለቲካ ስራውን በግልፅ ጀምሯራ።

ፓርቲው በሁሉም የትግራይ የዞን ፣ የወረዳና ከተሞች ፓለቲካዊ ፅህፈት ቤቶች መክፈት እንደሚቀጥል አስታውቋል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ታማኝ የመረጃ ምንጮች እንዳሉት ከአንድ ወር በፊት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ  የምርጫ ቦርድ ቅድመ እውቅና ያገኘው ስምረት ፓርቲ ለምስረታ ብቁ የሚያደርጉት አባላት መልምሎ ጨርሷል።

የክልል ፓርቲ ለመመስረት የሚስፈልገው 4 ሺህ በላይ መስራች አባላት መልምሎ ለይፋዊ ምስረታ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የመረጃ ምንጮቹ ተናግረዋል።

ስምረት ፓርቲ በቀጣዩ የነሀሴ ወር 2017 ዓ.ም በትግራይ ይፋዊ ምስረታ በማከናወን ከቅድመ እውቅና ወደ ሙሉ እውቅና እንደሚሸጋገር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamliyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Save_the_Children #GSK

Calling all #Ethiopian Innovators!

The second round of the Immunisation Innovation Accelerator is now open - offering up to $100,000 in grants to solutions that improve #vaccine access.

📅 Application deadline: July 27
🔗 https://www.stc-accelerator.org/

#ChildHealth #InnovationInAction #HealthInnovation #Ethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Bahirdar

በአማራ ክልል መዲና ባሕርዳር ከተማ ተጥለው ከነበሩ ክልከላዎች ከፊሎቹ መነሳታቸውን የከተማው የጸጥታ ም/ቤት ዛሬ ምሽት አሳወቀ።

ምክር ቤቱ ፤ ማንኛውም የንግድ እንቅስቃሴ ያለገደብ 24 ሰዓት ክፍት በማድረግ እንዲሰሩ ወስኗል።

ከባጃጅ እና ከሞተር ሳይክል ውጭ ሁሉም ተሽከርካሪዎች ያለገደብ እንዲንቀሳቀሱም ውሳኔ አሳልፏል።

በተጨማሪ ማንኛውም ሰው ያለምንም የሰዓት ገደብ እንዲንቀሳቀስ የጸጥታ ም/ቤቱ ወስኗና።

ምክር ቤቱ ማሻሻያ ያልተደረገባቸውና አሁንም የተጣሉ ግዴታዎች እንዳሉ አስገንዝቧል።

➡️ ማንኛውም ተሽከርካሪ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ የፊት ለፊትና የኋላ ሰሌዳ አሟልቶ መንቀሳቀስ እንዳለበት ይህንን ሳያደርግ ተገኝቶ በጸጥታ ሀይሉ ለሚወሰደው ማንኛውም ህጋዊ እርምጃ ሀላፊነቱን ራሱ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

➡️ ማንኛውም እግረኛ ሲንቀሳቀስ ማንነቱን የሚገልጽ የቀበሌ የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት አለበት ብሏል።

➡️ የጸጥታ ሀይሉና በሚኖሩበት ቀበሌ ወይም ቀጠና ወይም ብሎክ ብቻ መሳሪያ ይዘው እንዲንቀሳቀሱ ከፈቀደላቸው መሳሪያ ፈቃድ ኩፖን ከተሰጣቸው ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በፍጹም የተከለከለ መሆኑ አስገንዝቧል።

➡️ የባጃጅ ተሽከርካሪ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት በኋላ ይዞ መንቀሳቀስ ክልክል መሆኑን አሳውቋል።

➡️ ባለ 2 እግር ሞተር በማንኛውም ሁኔታ ይዞ መንቀሳቀስ በፍጹም የተከለከለ እንደሆነ አስጠንቅቋል።

#BahirdarCity

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ጥቆማ
#ለሚመለከታችሁ_አካላት

" ህጻናትና ሌሎችም ነዋሪዎች ላይ ጉዳት ሳያደርስ መፍትሄ ይሰጠው ! " - ነዋሪዎች

አዲስ አበባ ቃሊቲ 08 ቀበሌ ወደጃቴ ኪዳነ ምህረት ቤ/ክርስቲያን በሚወስደው እሳት አደጋው አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች በአካባቢዎች ወደ መሬት ሊወድቅ ያለ የእንጨት መብራት ፖል መኖሩን በመጠቆም እንዲስተካከልላቸው ጠይቀዋል።

ነዋሪዎቹ " የመብራት ፖሉ ወደቆ መሬት ለመንካት ትንሽ ነው የቀረው ፤ በሰፈሩም ብዙ ህጻናት የሚጫወቱበት ቦታ ነው። ከመሸ በኋላ አዋቂዎችንም ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው። በመሆኑ የሚመለከታችሁ አካላት አስቸኳይ መፍትሄ ስጡት " ብለዋል።

ወቅቱ ክረምት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ያለው ኃይለኛ ዝናብና ንፋስ ፖሉን ጥሎት አደጋ ሳይደርስ መፍትሄ እንዲፈለግ በነዋሪዎች ተጠይቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamliyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ጥናት🤖

" የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት (AI) መሳሪያዎች የሰዎችን የማመዛዘን ብቃት እየቀነሱት ነዉ " - ጥናት

በቅርቡ የካርኔጊ ሜሎን ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ማይክሮሶፍት በጋራ የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት (AI) በሰዎች የማገናዘብ አቅም ላይ ስለሚኖረዉ ተፅዕኖ አንድ ጥናት አድርገዉ ነበር። 

ይህ ጥናት ከፈረንጆቹ 2024 እስከ 2025 የተካሄደ ሲሆን ባለፈው ሚያዚያ ወር በጃፓን ዮኮሀማ በተካሄደ ኮንፍረንስ ላይ በይፋ ለህዝብ የቀረበ ነው።

319 ሰዎችን ያካተተዉ ይህ ጥናት ስራቸዉ ጥልቅ የሆነ ማሰብን ይጠይቃል የተባሉ ሰዎችን አካቷል።

የጥናቱ የተገኙ ግኝቶች ምንድን ናቸው ?

በዚህ ጥናት በዋናነት ሶስት ግኝቶች ተቀምጠዋል። 

1ኛ. ጥናቱ ከተደረገባቸው ሰዎች አብዛኞቹ ነገሮች ላይ በጥልቀት ማሰብ እና ትኩረት ማድረግ ላይ እንደሚቸገሩ የጥናቱ ውጤት ያሳያል።

" የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት (AI) መሳሪያዉ ይመልሰዋል " ብለዉ ስለሚያስቡ ነገሮችን በጥልቀት የመመርመር ፍላጎት መቀነስም ታይቶባቸዋል።

2ኛ. ከመጠን ያለፈ እምነት በሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት (AI) መሳሪያዎች ላይ መጣል ሲሆን ጥናቱ የተደረገባቸው ሰዎች ከመሳሪያዉ የሚገኙ ዉጤቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ መተማመን እንዳላቸዉ ያሳያል።

ውጤቶቹንም እውነተኛነታቸዉን ለማረጋገጥ ሌላ ተጨማሪ ምንጮችን በማየት ለማረጋገጥ እንደማይሞክሩ ውጤቱ ያመለክታል።

3ኛ. የጥናቱ ውጤት ሰዎች ጥልቅ እና የተወሳሰቡ የሚመስሉ ነገሮችን ከማሰብ እና ምክንያታዊ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ከሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት (AI) መሳሪያዎች የሚወጡ ቀላል እና መሰረታዊ ስህተቶችን በማረም ላይ ያተኩራሉ ብሏል።

እንዲሁም የራሳቸዉን አስተሳሰብ በጥቂቱ ስለሚያቀርቡ የግለሰቡን ሀሳብ የማመንጨት ተፈጥሯዊ ብቃቱን እንደሚያሳጣዉ ጥናቱ ይገልጻል።

በጥናቱ መሰረት ከመረጃ ጋር የተያያዙ ስራዎች ከሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መሳሪያዎች ጥቅም ላይ መዋል በኋላ መረጃን ከመሰብሰብ ወደ ማረጋገጥ መዞራቸውን ያነሳል።

ችግር ፈቺ በሆኑ የሥራ ቦታዎችም ቀጥታ ችግሩን ከመፍታት የሰው ሰራሽ አስተውሎት ምክሮቸን ወደመቀበል ዞረዋል ተብሏል።

በጥናቱ ከተሳተፉ 319 ሰዎች ውስጥ 83 ያህሉ በሰው ሰራሽ አስተውሎት መሳሪያዎች ላይ ያላቸው መተማመን የማገናዘብ አቅማቸውን እንዳዳከመው አምነዋል።

ከዚህ በተጨማሪ 72 ሰዎች ከሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ያገኙት ምላሽ ስህተት እያለው እንኳን ለማረም እንደማይችሉ በጥናቱ ተመላክቷል።

በአጠቃላይ የጥናቱ ማጠቃለያ ሰዎች በስራ ቦታ ላይ ያላቸዉ የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት (AI) መሳሪያዎች አጠቃቀም የሰዎችን ምክንያታዊ የአስተሳሰብ አቅም እየቀነሰዉ መምጣቱን ያሳያል።

ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ተጠቃሚዎች ከሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት መሳሪያዎች በሚመነጩ መልሶች ላይ መተማመናቸው ነው።

በተጨማሪም ከመተንተን ይልቅ ከሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት የሚገኙ ውጤቶችን ወደ ማረጋገጥ ፣ ማቀናጀት እና መሰረታዊ ሰህተቶችን ወደ ማረም መዞራቸው መሆኑን ጥናቱ ያሳያል።

#TikvahEthiopiaFamliyAA

Via @TikvahethMagazine

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Ambulance🚑

በዚህ ዓመት ብቻ 184 እናቶች ከወሊድ ጋር በተያያዘ መሞታቸውን የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው ይህን ያለው ባፈላለገው ፈንድ በኢትዮጵያና የዓለም ቀይ መስቀል ማህበራት ቅንጅት የተገዙ  200 አምቡላንሶች ለዞኖች ርክክብ በተደረገበት ወቅት ነው።

የቢሮው ሃላፊ ዶ/ር አማኒኤል ሃይለ ፤ ጦርነት በወለደው ጦስ ምክንያት የአምቡላንስ እጥረት በማጋጠሙ የእናቶች እና የህፃናት ሞት እጅግ እንዳሻቀበ ተናግረዋል።

በዚህ ዓመት ብቻ 184 እናቶች ከወሊድ ጋር በተያያዘ መሞታቸውን ጠቁመዋል።

" ከጦርነቱ በፊት በትግራይ 310 አምቡላንሶች ነበሩ  ከጦርነቱ በኃላ ከ82 በታች ነው " የቀሩት ያሉት ሃላፊው " በዚህ ምክንያት የክልሉ የህክምና ዘርፍ 25 ዓመት ወደ ኃላ ተመልሷብምል ፤ የእናቶችና የህፃናት ሞት ተበራክቷል " ብለዋል።

በጦርነቱ ምክንያት እጅግ የተጎዳው የክልሉ ጤና ዘርፍ መልሶ እንዲያገግም አገራዊና ዓለም አቀፋዊ እገዛ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።

ኃላፊው አሁን የተለገሱት 200 አምቡላንሶች ጠቀሜታቸው ከፍተኛ እንዳሆነ ገልጸዋል። ግን የክልሉን ፍላጎት ለሟሟላት 400 አምቡላንሶች እንደሚቀሩ ጠቁመዋል።

አምቡላንሶቹ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ የነዳጅ አቅርቦት ሊታሰብበት እንደሚገባ አመላክተዋል።

200 አምቡላንሶቹን የትግራይ 7 ዞኖች ተወካዮች ከክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) እጅ ቁልፍ ተረክበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamliyMekelle

@tikvahethiopia            

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#UoG

ጎንደር ዩኒቨርስቲ ትልቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ 14 የቀድሞ ምሩቃን ልዩ ዕውቅና ሰጠ !

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለትም በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን 2500 ተማሪዎችን አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ተማሪዎች ማህበር ምስረታን በትላንትናው ዕለት የፋ ሲያደርግ በዛሬው ዕለት ደግሞ በ13 ዘርፎች ለ14 የቀድሞ ምሩቃን ልዩ ዕውቅና ሰጥቷል።

የዩኒቨርስቲው ፕረዚዳንት ዶክተር አስራት አፀደወይን ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ባደረጉት ቆይታ ዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያውን ምረቃ ያካሄደው ሰኔ 30 ቀን 1949 ዓ.ም እንደነበር እና ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 66 ዓመታት 107 ሺ 860 ሙህራንን ማፍራቱን አስታውሰዋል።

ከእነዚህ ሙህራን መካከል በ13 ዘርፎች በሙያቸው በጎ ትፅዕኖ የፈጠሩ 14 ሙህራንን ዩንቨርስቲው ዕውቅና ለመስጠት መወሰኑን አስረድተዋል።

ጎንደር ዩኒቨርስቲ በምን ዘርፍ ለየትኞቹ የቀድሞ ተመራቂዎች ልዩ ዕውቅና ሰጠ ?

1. የፕሬዚዳንታዊ ሌጋሲ ከፍተኛ ሽልማት ዘርፍ
- ፕ/ር መንገሻ አድማሱ (የቀድሞው የዩኒቨርስቲው ፕረዚዳንት)
- ፕ/ር ያሬድ ወንድምኩን (የመጀመሪያው የዩኒቨርስቲው ፕረዚዳንት)

2. የማኅበረሰብ ተጽዕኖ የላቀ ሽልማት (Community Award)
- ፕ/ር ብሩክ ላጲሶ

3. ዓለም አቀፋዊ የመሪነት ዘርፍ (Global Leadership Award)
- ዶ/ር ከሰተብርሃን አድማሱ (የቀድሞ የኢፌዴሪ ጤና ጥበቃ (ጤና) ሚኒስትር

4. ወጣት ሥራ ፈጣሪና ተጽዕኖ ፈጣሪ ዘርፍ
- አቶ ጃለታ ሙላቱ

5. በጎንደር ዩኒቨርስቲ ድጋፍ እና አጋርነት ዘርፍ
- ዶ/ር ካሱ ከተማ

6. በትምህርት እና ምርምር ልኅቀት ዘርፍ
- ዶ/ር ኤርሚያስ ዲኖ

7. በህዝባዊ አገልግሎት ዘርፍ (Public Service Award)
- ዶ/ር ተዋበች ቢሻው (የመጀመሪያዋ ሴት ጤና መኮንን)

8. በህይወት ዘመን አበርክቶ ዘርፍ
- ፕ/ር ጉታ ዘነበ

9. በጤናና ሰብዓዊ አገልግሎት ዘርፍ
- ዶ/ር ፈቀደ አጉዋር

10. በባህል፤ በመገናኛ ብዙኀን እና ኪነ-ጥበብ ዘርፍ
- አቶ ስለሺ ግርማ ( በአሁኑ ወቅት የቱሪዝም ሚኒስትር ሚ/ዴኤታ)

11. በሥራ ፈጠራና ኢንቨስትመንት ዘርፍ
- ዶ/ር ግርማ አባቢ

12. በዲያስፖራ አምባሳደርነት ከፍተኛ ተሸላሚ
- ዶ/ር ኑሩ አብሲኖ

13. ልዩ የሰብዓዊ አገልግሎት ሽልማት (Social Humanitarian Impact Award)
- ወጣት ዳዊት አየነው

እጩዎችን የማሰባሰብ እና ድምጽ የማሰባሰብ ሥራ ተሰርቶ ተሸላሚዎቹ መለየታቸውን ዩኒቨርስቲው አስታውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
#TikvahEthiopiaFamliyBahirdar

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ብቃት ያላቸውን አሽከርካሪዎችን አይቶና መዝኖ ለብቃት የሚያበቃቸውን መንጃ ፍቅድ መስጠት ነው እንጂ ገንዘብ ስለከፈለ ብቻ መስጠት ተገቢ አይደለም " - የሀረሪ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን

የመንጃ ፈቃድ ብቃት ላላቸው አሽከርከርካሪዎች እንዲሰጥ፣ አሽከርካሪዎችም በጥንቃቄ እንዲያሽከክሩ፣ እግረኞችም የእግረኛ መንገድ ጠብቀው እንዲጓዙ የሀረሪ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሳስቧል።

የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ጣሰው ቻለው ይህን ያሉት ትላንት በክልሉ ሀረር ከተማ የደረሰውን የመኪና አደጋ በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ገለጻ ነው።

በከተማው አራተኛ ተብሎ በሚጠራው መንገድ በደረሰው አደጋ ስለደረሰው ጉዳት ማብራሪያ ስንጠይቃቸው፣ " የሞተ ሰው የለም፤ 8 ሰዎች ናቸው ጉዳት የደረሰባቸው፤ አራቱ ከባድ እና አራቱ ቀላል ጉዳት ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

አደጋው የተከሰተው ውሃ የጫነ ቦቴ ከአራተኛ መንገድ ወደ ስቴዲየም ሲጓዝ ፍሬን በጥሶ፣ ከሁለት ባጃጆችና ከአንድ ፒካፕ ጋር በመጋጨቱ መሆኑ ተመልክቷል።

ኮማንደር ጣሰው ባስተላለፉት መልዕክት፥ " እንደ ሀገር የትራፊክ አደጋ ከፍተኛ የሰውን ልጅ ሕይወት የሚቀጥፍ ነው በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው " ብለዋል።

" እንደ ሀገር ከፍተኛ የሆነ ጥፋት ነው እያደረሰ ያለው " ያሉት ኮማንደር ጣሰው፣ " ስለዚህ ትልቁ ነገር፥ ብቃት ያላቸውን አሽከርካሪ አሰልጥኖ ማውጣት ነው። ይሄ ደግሞ የማሽከርከሪያ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ትልቅ ኃላፊነት ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" በዚህ ጉዳይ ትኩረት መሰጠት አለበት ዝም ብሎ መንጃ ፈቃድ መስጠት ብቻ ሳይሆን ለሰው ሕይወት፣ ለሀገር ማሰብ ተገቢ ነው አሽከርካሪዎቹም በአግባቡ ማሽከርከር፣ ለሰው ሕይወት ማሰብ አለባቸው " በማለት አስገንዝበዋል።

" ብቃት ያላቸውን አሽከርካሪዎችን አይቶና መዝኖ ለብቃት የሚያበቃቸውን መንጃ ፈቅድ መስጠት ነው እንጂ ገንዘብ ስለከፈለ ብቻ መስጠት ተገቢ አይደለም። ይሄ ትልቅ ኃላፊነት የሁላችንም ስለሆነ ጥንቃቄ መድረግ አለበት፤ ህብረተሰቡም የእግረኛውን መንገድ በአግባቡ ጠብቆ መሄድ አለበት " ሲሉ አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#SafaricomEthiopia

በማይቆራረጥ ኢንተርኔት የLive ያጧጡፉ!

በBET-WIF ሁሉም ኮንተንት ክሬተር የሚያስፈልገውን ፈጣን እና የማይቆራረጥ ኢንተርኔት ከቤቶ ሆነው ያግኙ።

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

“ ተራራው እየተደረመሰ ወደ ታች ወደ እሳተ ገሞራው እየገባ ነው፡፡ በፍንዳታው የሚወጣው ሰልፈርዳይ ኦክሳይድም የመተንፈሻ አካል ላይ ክፍተኛ ጉዳት ያስከትላል ” - ሰመራ ዩኒቨርሲቲ

የአፋር ክልሉ የኤርታሌ እሳተ ገሞራ ፍንዳታ እንዳልቆመ፣ እሳተ ገሞራው ሲወጣ መሬቱ እየተደረመሰ ወደ ውስጥ እየገባ ከመሆኑም ባሻገር የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ መሆኑን በቦታው ተገኝቶ የነበረው ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የዩኒቨርሲቲ የጂኦሎጅ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ኖራ ያኒሚኦ ጉዳዩ ያለበትን ሁኔታውን ሲያስረዱን፣ “ትላንት በቦታው ነበርን፤ በኤርታሌ በጣም ከፍተኛ የሆነ አቧራ እየወጣ ነው፡፡ በሁለት ቦታዎች ላይ ደግሞ ትንሽ ጭስና እሳት ታይቷል፡፡ ግን ትንሽ ጭስ ከመውጣት ውጪ ሌላ ነገር የለውም” ብለዋል፡፡

“በፎቶ የተሰራጨው በጣም ከፍተኛ አቧራ ሲወጣበት የነበረው ቦታ ግን ትላንት ራሱ ከቀኑ 11 እስከ ማታ 2 ሰዓት ድረስ ከፍተኛ አቧራ እየወጣበት ነው የነበረው፡፡ አቧራው ከመውጣቱ በፊት ዝቅተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር፡፡ መሬት መንቀጥቀጡ ከእሳተ ገሞራ ፍናዳታው ጋር የተያያዘ ነው” ሲሉም አስረድተዋል፡፡

አክለው፣ “የሚወጣው አቧራ ደግሞ ሰርፈርዳይ ኦክሳይድ ኮንቴነቱ ከፍተኛ ስለሆነ ከፍተኛ የሰልፈር ሽታ አለው፡፡ መሬቱም እተሰነጠቀ ነው፡፡ አስቸጋሪ ሆነ ሁኔታ ነው ያለው” ብለዋል፡፡

“እየተሰነጠቀ ያለው መሬት ደግሞ የእሳተ ገሞራው ላቫ ወደ መሬት በሚወጣት ወቅት ሶሊድፋይድ ይሆናል፤ ስለዚህ ሶሊድፋይ የሆነውና ላቫና ክቧ ተራራ የሚገናኙት ቦታ ላይ ነው፡፡ በመሆኑም ተራራው እየተደረመሰ ወደ ታች ወደ እሳተ ገሞራው እየገባ ነው” ሲሉም የአደጋውን በአሳሳቢነት አስረድተዋል፡፡

ተመራማሪው፣ “በፍንዳታው የሚወጣው ሰልፈርዳይ ኦክሳይድ የመተንፈሻ አካል ላይ ክፍተኛ ጉዳት ያስከትላል፡፡ በዓይንም ሆነ አፍንጫ ሲገባ በጣም ነው የሚያቃጥለው” ብለው፣ በኤርታሌ በጣም በቅርበት የሚኖሩ ነዋሪዎች ባይኖሩም ብናኝ የሚድርሰባቸው ነዋሪዎችም ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አስገንዝበዋል፡፡

ርቀት ቦታ ላይ በሚገኙ እንደ አፍዴራ ባሉ አካካቢዎች ብናኙ እየደረሰ መሆኑን ጠቁመው፣ “የሚወጣው አቧራ የመተንፈሻ አካል ላይ ጉዳት ሊያስከትል ስልሚችል ማህበረሰቡ የአፍንጫ ጭምብል ሊጠቀም ይገባል” ሲሉም አሳስበዋል፡፡

በኤርታሌ ከዚህ ቀደም እንደዚህ አይነት አደጋ አጋጥሞ እንደማያውቅ ገልጸው፣ “ አሁን ግን ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ ወደ ኤክስክሎሲቭ ኢራፕሽን እየተሸጋገረ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች አሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ነገር ብዙም ኤርታሌ ላይ የተለመደ አይደለም፡፡ እስከዛሬ ማግማው ወደ ላይ ከመምጣት ውጭ የኤክስክሎሲቭ ምልክት አያሳይም ነበር ” ነው ያሉት፡፡

ፎቶ ለማንሳትና ቪዲዮ ለመቅረጽ ወደ ቦታው የሚሄዱ ሰዎች እንዳሉ ገልጸው፣ እሳተ ገሞራው በሚወጣበት ወቅት ከፍትኛ የሆነ መሬት መንቀጥቀጥ ስላለ፣ ተራራውም እየተናደ ስለሆነ (ትላንት የነበሩበት ቦታ እንደተናደ ጠቁመዋል) በርቀት ካልሆነ በስተቀር ሰዎች ወደ ቦታው ቀርቦ ከመቅረጽ እንዲታቀቡ በአጽንኦት አስጠንቅቀዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiafamilyAA

ፎቶ፦ ፋይል

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ታግተው ተወስደው የነበሩት ሁለቱም ዛሬ ተገድለዋል፡፡ ገንዘብ ተሰብሶ የተወሰነውን ከወሰዱ በኋላ መልሰው ገደሏቸው " - የወረዳው ቤተ ክህነት

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ጀጁ ወረዳ ሶኮራ ቀበሌ ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ/ም የ "ሸኔ" ታጣቂ ቡድን ባደረሱት ጥቃት አባትና ልጅ በተገደሉበት ወቅት " ታግተው ተወስደዋል " ተብለው የነበሩ ሁለቱ ሰዎች የሚለቀቁበት ገንዘብ ተሰብሰቦ የተወሰነው ከተሰጠ በኋላ " ገድለዋቸዋል " ሲል የወረዳው ቤተ ክህነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ፡፡

ታጣቂ ቡድኑ በወቅቱ በአንድ ቤተሰብ አባላት ስላደረሰው ጥቃት ቤተ ክህነቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ " አንድ ካህንና ወንድሙ ሁለት ሰዎች ናቸው ታግተው የተወሰዱት፡፡ አንድ አባት እስከ ልጃቸው ተገድለዋል " ብሎ ነበር፡፡

ዛሬ ለቲክቫህ ኢትየጵያ በሰጠው ቃል ደግሞ፣ " ታግተው ተወስደው የነበሩት ሁለቱም ሰዎች ዛሬ ተገድለዋል፡፡ አምጥተው በአካባቢያቸው ገድለው ጥለዋቸው ሂደዋል " ብሏል፡፡

" ገንዘብ ተሰብሶ የተወሰነውን ከወሰዱ በኋላ መልሰው ገደሏቸው፡፡ ዛሬ ሌሊት ተገድለው አደሩ፤ ሜዳ ላይ አምጥተው ገድለው ጥለዋቸው ነው የሄዱት፡፡ ዛሬ ቀብራቸው ተፈጽሟል " ያለው ቤተ ክህነቱ፣ ሟቾቹ ካህንኑና ወንድሙ ከሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ/ም ጅምሮ ታግተው እንደቆዩ፣ አጋቾቹ ታጋቾቹን ለመልቀቅ ገንዘብ ጠይቀው እንደነበርና የተወሰነው ተሰብስቦ ከወሰዱ በኋላ የግድያ ጥቃቱን ማድረሳቸውን አስረድቷል፡፡

" የተገደሉትም ካህኑና ወንድሙ ናቸው፡፡ ስማቸውም ቄስ አድማሱ ጌታነህና ወገኔ ጌታነህ ነው የሚባለው " ሲል አስረድቶ፣ አሁንም በአካባቢው ያለው የታጣቂ ቡድኑ እንቅስቃሴ አስጊና አሳሳቢ መሆኑን ጠቁሞ፣ ከለላ እንዲደረግ አሳስቧል።

ተደጋጋሚ ጥቃቱን በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ የጠየቀው የኦሮሚያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ፣ ጥቃት ደረሰበት የተባለው ወረዳ ምላሽ እንዲሰጥ በመጠቆም ማብራሪያ ከመስጠት የተቆጠበ ሲሆን፣ ወደ ወረዳው የተደረገው ሙከራም ለጊዜው አልተሳካም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

“ በሰው የደረሰ የሞት አደጋ የለም፡፡ ሁለት ሰዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ እንስሳት ተጎድተዋል፤ ንግድ ሱቆችም ተቃጥለዋል ” - አፋር ክልል

በአፋር ክልል ዳሎል ወረዳ የተከሰተው፣ እስካሁን “መንስዔው ገና እየተጣራ ነው” የተባለው የእሳት አደጋ ከፍተኛ የንብረት ውድመት መከሰቱን የክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተገልጿል፡፡

የክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽ ኃላፊ አቶ መሐመድ አሊ፣ “ የእሳት አደጋው መንስዔ ገና እየተጣራ ነው፡፡ በሰው የደረሰ የሞት አደጋ የለም። ሁለት ሰዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ እንስሳት ተጎድተዋል፤ ንግድ ሱቆችም ተቃጥለዋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አደጋው የተነሳው ትላንት 11 ሰዓት ተኩል ገደማ መሆኑን፣ የአካባቢው ማህበረሰብ ጭምር እሳቱን ለማጥፋት ርብርብ እናዳደረገ የገለጹት ኃላፊው፣ “እሳቱ በቁጥጥር ሥር ውሏል” ብለዋል፡፡

በቃጠሎው የደረሰው የጉዳት መጠን ምን ያክል እንደሆነ ሲጠየቁም፣ “ ጉዳቱ ከፍተኛ ነው ከፍተኛ እሳት ነው የነበረው፡፡ አካባቢው ሞቃታማ ነው ቶሎ መቆጣጠር አይቻልም፡፡ ቦታውም ከሰመራ በጣም ሩቅና ገጠራማ አካካቢ ስለሆነ የእሳት አደጋ ተሸከርካሪ ቶሎ የሚደርስበት አይደለም፡፡ በባህላዊ መንገድ ነው እሳቱን ያጠፉት ” ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የጉዳት መጠኑን ለማወቅ ባለሙያዎች በጥናት መሰረት የሚያቀርቡትን መረጃ መጠበቅ የተሻለ እንደሆነና ሪፖርቱ ሲደርስ እንደሚገልጹ ጠቁመዋል፡፡

በጥቅሉ በአደጋው ሱቆች፣ ንግድ ቤቶች፣ የግለሰብ መኖሪያ ቤቶች በእሳቱ እንደተቃጠሉ፣ በአካባው የክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን እንደደረሰና የጉዳቱ መጠን እየተጣራ መሆኑም ገልጸዋል፡፡

“ሞት ባይኖርም በእሳት አደጋ ምክንያት የተፈናቀሉ አሉ፡፡ የስነ ልቦና ችግር ለደረሰባቸው ወገኖችንም የክልል ጤና ቢሮ የህክምና ባለሙያዎች ልዑካን ቡድን ተልኳል። የእሳር አደጋውን መነሻ ለማወቅ ፖሊስም እያጣራ ነው” ብለዋል።

“በዳሎል ለደረሰው የእሳት እና በአፍዴራ ለደረሰው ሰሞንኛ የንፋስ አደጋ ክልሉ ለተጎጅዎች የእለት ደራሽ ምግብ በማቅረብ፣ የህክምና አገልግሎት በመስጠት፣ ጊዜያዊም ቢሆን የመጠለያ ቁሳቁስ በመቅረብ ባለው አቅም በቦታው ደርሶ ህዝቡን የመታደግ ሥራ እየሰራ ነው፡፡ በቀጣይ የፌደራሉም የክሉም መንግስት የሚሰሩበት ይሆናል” ብለዋል አቶ መሐመድ።

ቲክቫህ ኢተዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update
#አርባምንጭ

ተከሳሾች ያቀረቡት የመከላከያ ማስረጃ ዉድቅ ተደርጓል።

የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ጠዋት ባካሄደዉ ችሎት የብሔራዊ ቡድን እግር ኳስ ተጫዋች በነበረው አለልኝ አዘነ የግድያ ወንጀል የተጠረጠሩት ባለቤቱና የባለቤቱ እህት ባል ያቀረቡትን የመከላከያ ማስረጃ ሙሉ በሙሉ ዉድቅ በማድረግ የፍርድ ዉሳኔ ለመስጠት ከሰዓት በኋላ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በርካታ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ችሎቱን ለመታደም ፍርድ ቤት መጥተዉ የነበረ ቢሆንም የችሎት አደራሽ ከልክ በላይ በመሙላቱ አብዛኛዉ ሰው ከግቢ ዉጪ በመሆን የፍርድ ውሳኔውን በመጠባበቅ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተመልክቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቦታው ተገኝቶ ችሎቱን እየተከታተለ ያለ ሲሆን መረጃዎችን ተከታትሎ የሚያደርስ ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አርባ ምንጭ
#TikvahEthiopiaFamliyArbaminch

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በትንሹ ከ3-4 ሰዓት በላይ ነው የምንቆመው " - ነዋሪዎች

➡️ " መንገዱ እየተሰራ በመሆኑ ደስታ ቢሰማንም ፣ የአካባቢው አስተዳደር ፕሮጀክቱን ከመጀመሩ በፊት ሊከሰት የሚችል የመንገድ ችግርን ታሳቢ ያደረገ አማራጭ መንገድ እንዲመቻች ማድረግ ነበረበት ! "

ከዩኒሳ አደባባይ ወደ ዱከም መሄጃ ሸገር ከተማ ላይ እየተሰራ ካለ የመንገድ ስራ ጋር በተያያዘ አማራጭ መንገድ ባለመዘጋጀቱ ምክንያት ነዋሪዎች ከቤታቸው ወጥተው ወደ ከተማ ለስራ ሄዶ መመለስ ፈተና እንደሆነባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" የመንገዱ ስራ ቱቦ ቀበራ ላይ ናቸው። ዋናው መንገድ ፈርሷል። በግራ በኩል ያለው ገደል ሆኗል። የከባድ መኪናዎች መግቢያና መውጪያ ነው በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ነን። የመንግሥት አካላት ምላሽ እየሰጡ አይደለም " ሲሉ አንድ ነዋሪ ገልጸዋል።

" በትንሹ ከ2 እና 3 ሰዓት በላይ ነው የምቆመው ፤ ከሰሞኑን ለስራ ስንል በቢሾፍቱ ዞረን ነው በፈጣን መንገድ ገብተን ነው የምንወጣው። ከዛ ውጭ መንገዱ ስለሚዘጋጋ ማለፍ አይቻልም። የከባድ መኪና መግቢያቸው በዚህ ነው " ብለዋል።

ነዋሪዎች በአካባቢው ባለው የመንገድ ችግር እስከ እጅግ አምሽተው ቤታቸው ለመግባት እየተገደዱ መሆኑን አመልክተዋል።

የመፍትሄ ያለ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

ሌላኛው የገላን ክፍለ ከተማ የሸገር ከተማ ነዋሪ እንደሆኑ የገለጹ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል " ከዩኒሳ እስከ ሸገር ገላን ያለውን የመንገድ ችግር እውነት ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ችግሩ ከጀመረ ከአንድ ወር በላይ አልፎታል ከቀን ወደ ቀንም እየተባባሰ ነው። በአሁኑ ሰአት ከዩኒሳ ወደ ገላን በባጃጅ 20 ብር የነበረ መንገድ 100 ብር እንድንከፍል እየተገደድን ነው " ብለዋል።

" አብዛኛው የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ለስራ አዲስ አበባ ዉለን የምንገባ ሲሆን ለዚቹ መንገድ በቀን ከ200 ብር በላይ እያወጣን እንገኛለን። በዚህ መንገድ ለኑሮ (ሥራ) በየቀኑ የምንሄድ ሰዎች ሰዎች ላይ ያለውን ሸክም አስቡት " ሲሉ ገልጸዋል።

" ችግሩ እየተካሄደ ባለው የዋና መንገድ ግንባታ የተከሰተ ነው። መንገዱ እየተሰራ በመሆኑ ደስታ ቢሰማንም ፣ የአካባቢው አስተዳደር ፕሮጀክቱን ከመጀመሩ በፊት ሊከሰት የሚችል የመንገድ ችግርን ታሳቢ ያደረገ አማራጭ መንገድን ማመቻቸት ነበረበት ሆኖም ይህ ሳይደረግ በመቅረቱ ላሳሳቢ ችግር ተጋልጠናል " ብለዋል።

" ከዚህ ባለፈም የዝናብ ወቅት እንደመሆኑ ዝናቡ ችግሩን እያባባሰው ስለሆነ አሁንም ቢሆን ተገቢውን ትኩረት ሊሰጠው ይገባል " ሲሉ አሳስበዋል።

ሌላኛው የአካባቢው ነዋሪ በቪድዮ ጭምር አስደግፈው በላኩት የአቤቱታ መልዕክት አማራጭ መንገድ ባለመዘጋጀቱ ነዋሪዎች ከቤት ወጥተው እስከሚመለሱ ከምሽት 4 ሰዓት ሁሉ ሊያልፍ እንደሚችል ፤ አንዳንዶችም ያለው ችግር እስኪቀረፍ ሌላ ቦታ መኖር እንደመጀመር መገደዳቸውን አመልክተዋል።

" በቀኝ በኩል ሲኬድ መንገዱን ለማስፋት አማራጭ አለው ፤ መንገዱን የሚሰራው ኮንትራክተር መንገዱን ጠረግ ቢያደርገው መኪኖች ይተላለፋሉ ፤ ግን የመንገዱ ተቆጣጣሪዎች ትንንሽ መኪና እንኳን የያዙ ሰዎች ከባባድ መኪናዎች በሚሄዱበት የተቆራረጠ መንገድ ነው እንዲሄዱ የሚፈልጉት " ብለዋል።

" መንገዱ መውጫ መግቢያ ነው። ትልልቅ መኪኖች ከዱከም ኢንዱስትሪ ዞን ኮንቴነር ጭነው ፣ ከጅቡቲም የሚመጡ መኪኖች፣ ሲኖ ትራኮች ትልልቅ መኪኖች ናቸው የሚጠቀሙት መንገዱን " ያሉት ነዋሪው " ተቀያሪ መንገድ ጭራሽ ነው ያልታሰበበት " ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

" እኛ ሰፈር መግባት እየተቸገርን እና የሚጠፋው ጊዜ ብዙ ስለሆነ የዘመድ ቤት ለመግባት ተገደናል " ያሉ ሲሆን " ፍቃድ እየሞሉ ስራም የማይገቡ አሉ። የሚመለከታቸው አካላት መፍትሄ ይፈልጉለት " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሚመለከታቸውን አካላት በማነጋገር ምላሽ ይዞ ለመቅረብ ጥረት ያደርጋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamliyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" 4 አመታት በጥንቃቄ የተገነባውና ወደ 6 ሚልየን ብር ወጪ የተደረገበት በገዳሙ ዙሪያ የተገነባው የጎርፍ መከላከያ ግንብ ፈርሶብናል " - የገዳሙ አሰሪ ኮሚቴ

በሰሜን ወሎ ዞን በፍላቂት ገረገራ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው እና አሁን በመገንባት ላይ ያለው የገረገራ ቀራንዮ መድኃኔዓለም አቡነ ተክለ ሃይማኖት አባ ሳሙኤል አንድነት ገዳም ሰሞኑን በጣለው ከባድ ዝናብ  በገዳሙ  ዙሪያ ጎርፍን ለመከላከል ያስችላል ተብሎ የተገነባው ግንብ መፍረሱን የገዳሙ  አሰሪ ኮሚቴ አባል አቶ ዘላለም ሙላቱ ተናግረዋል።

አቶ ዘላለም ሙላቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት ገዳሙ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰራ የቆየና ወደ 30 ሚልየን ብር ወጭ የፈጀ ሲሆን በሚቀጥለው አመት 2018ዓ.ም መጀመሪያ ላይ ለማስመረቅ እቅድ ተይዞ ነበር ብለዋል።

ነገር ግን ከሰሞኑ ሀምሌ 3 /2017ዓ.ም በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ጎርፍን ለመከላከል ያስችላል ተብሎ የተገነባው ግንብ በመፍረሱ ገዳሙ በአሁኑ ወቅት ምንም ባይሆንም ለቀጣይ የሚያሰጋው እንደሚሆን ነው የገለጹት።

ሰሞኑን በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት የፈረሰውና በገዳሙ ዙሪያ የተገነባው የጎርፍ መከላከያ ግንብ ላለፍት 4 አመታት በጥንቃቄ የተገነባና ወደ 6 ሚልየን ብር የፈጀ እንደነበርም አቶ ዘላለም አክለው ገልፀዋል።

የገረገራ ቀራንዮ መድኃኔዓለም አቡነ ተክለ ሃይማኖት አባ ሳሙኤል አንድነት ገዳም ከመሬት ወለል 2900 ከፍታ ባለው ተራራማ ስፍራ የተገነባ ነው።

የአካባቢው መሬት ተንሸራታች በመሆኑም ገዳሙ በተፈጥሮ አደጋ የመጋለጥ እድሉ ከፍተኛ ሲሆን ገዳሙ ሳይመረቅ በጎርፍ እንዳይወሰድ እና የፈረሰውን ግንብ መልሶ በመገንባት ሂደት ምዕምናን እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
#TikvahEthiopiaFamliyBahridar

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ፀሐይ ባንክ
ለሁሉ!


ሕንጻዎትን በቀላሉ የሚያስተዳድሩበት እጅግ ዘመናዊ መፍትሔ ከፀሐይ ባንክ! 👏👏

ዘመናዊነትን ይምረጡ፣ ጊዜዎንና ጉልበትዎን ይቆጥቡ፣ ትርፍዎን ያሳድጉ!

🔔 የፀሐይ ባንክ የሕንጻ አስተዳደር ሲስተም ተጠቃሚ ይሁኑ!

በርካታ ጥቅሞች ያሉትን ይህን ስርዓት በመጠቀም፥ የሕንጻዎን ደህንነት ይጠብቁ! ጠንካራ የተከራይ ግንኙነት ይፍጠሩ! የክፍያ እና የቁጥጥር ስርዓትዎን ያዘምኑ!

አስተማማኝ እንዲሁም ለአጠቃቀምና ለአከፋፈል ምቹ በሆነ ዘመናዊ ሲስተም ይጠቀሙ!

Telegram: /channel/tsehaybanksc
Facebook: https://www.facebook.com/tsehaybanksc

ፀሐይ ባንክ
ለሁሉ!

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የአለልኝ አዘነ ጉዳይ ነገ ትክክለኛ ፍትሕ ያገኛል ብለን እንጠብቃለን " - ወዳጆቹ

ከዓመት በፊት በመጋቢት 2016 ዓ/ም በድንገት ሕይወቱ ያለፈዉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና በተለያዩ የሀገራችን ክለቦች ተጫዉቶ ያለፈው ወጣቱ የአማካኝ ተከላካይ አለልኝ አዘነ ከአሟሟቱ ጋር በተያያዘ የትዳር አጋሩና የእህቷ ባል በቁጥጥር ስር ውለው ክስ የተመሰረተባቸው መሆኑ ይታወሳል።

የማጣራት፣ የምስክርና መከላከያ ማስረጃዎችን ሲያደምጥ የቆየዉ የአርባ ምንጭ ከተማ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በነገዉ ዕለት የፍርድ ዉሳኔ እንደሚያስተላልፍ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመረዳት ችሏል።

በ26 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው አለልኝ አዘነ የእግር ኳስ ሕይወቱን በአርባምንጭ ከተማ፣ በሀዋሳ ከተማ፣ በባህር ዳር ከተማ እንዲሁም በብሔራዊ ቡድን ያሳለፈ ሲሆን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርቲያን ስርዓት ጋብቻ በፈፀመ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተወልዶ ባደገበትና የእግር ኳስ ሕይወትን ሀ ብሎ በጀመረበት አርባ ምንጭ ከተማ በድንገት ሕይወቱ ማለፉን ተከትሎ " እራሱን አጠፋ " የሚሉና " በሰዉ ተገድሎ ነዉ " የሚሉ መረጃዎች ሲሰራጩ መቆየታቸው ይታወሳል።

ኋላም " እራሱን አላጠፋም " በሚል ስርዓተ ፍትሐት እንዲፈፀምለት ተደርጓል።

የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስም የትዳር አጋሩንና የእህቷን ባል (የሚስቱን እህት ባል) በቁጥጥር አውሎ ክስ እንዲመሰረት ያደረገ ሲሆን የግራ ቀኝ ምስክርና የመከላከያ ማስረጃዎችን ሲያደምጥ እንዲሁም መዝገቡን ሲመረምር የቆየዉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍርድ ዉሳኔ ለመስጠት ነገ ሀምሌ 11/2017 ዓ/ም ቀጠሮ ይዟል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በአርባምንጭ ከተማ ተገኝቶ ያነጋገራቸው የከተማዉ ነዋሪዎች እና የተጫዋቹ ወዳጆች ዉሳኔዉን በጉጉት እንደሚጠብቁ ገልፀው  " ነገ የአለልኝ ጉዳይ ፍትሕ ያገኛል፤ የኛም ልብ ያርፋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ውሳኔዉን በርካታ የእግር ኳስ ቤተሰቦች፣ የኳስ ተጫዋቹ ወዳጆችና መላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚጠብቀው በመሆኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቦታዉ ላይ በመገኘት መረጃውን ያደርሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አርባ ምንጭ
#TikvahEthiopiaFamliyArbaminch

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

በሁለት እንስቶች ላይ አሲድ በመድፋት አረሜናዊ ድርጊት የፈፀመው ተጠርጣሪ " እስካሁን በቁጥጥር ስር አልዋለም " ሲሉ የትግራይ እንዳስላሰ - ሽረ ከተማ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

" አሲድ የተደፋባቸው ወገኖች በከፍተኛ ስቃይ ላይ ይገኛሉ " ሲሉ አክለዋል።

አሲድ የተደፋባቸው እንስቶቹ ለተሻለ ህክምና ከእንዳስላሰ - ሽረ ወደ አክሱም ቅድስት ማርያም ሆስፒታል ሪፈር መባላቸውን ገልጸዋል።

ባለፈው ሀምሌ 7/2017 ዓ/ም እስካሁን ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ በአንድ መጠጥ ቤት በሁለት እንስቶች ላይ አሲድ በመድፋት ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ማድረሱ ይታወሳል።

የድርጊቱ ፈፃሚ ግለሰብና ?  አስቃቂ ተግባር የተፈፀመባቸው እንስቶች በምን ሁኔታ እንደሚገኙ ለማጣራት ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ኣባል ዛሬ ሀምሌ 10/2017 ዓ.ም ወደ ከተማዋ ፓሊስ ስልክ ደውሎ ነበር።

ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የከተማዋ ፓሊስ አመራር " በአካል ወደ ከተማችን ካልመጣችሁ በስቀር በስልክ መረጃ አንሰጥም " በማለት መረጃውን ከልክለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የከተማዋ ነዋሪ ከሆኑ ታማኝ ምንጮቹ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የጭካኔ ድርጊቱን የፈፀመው ግለሰብ የሚታወቅ የከተማዋ ነዋሪ ሆኖ እያለ እስካሁን በቁጥጥር ስር አለመዋሉ ሁኔታውን አሳሳቢ አድርጎታል።

" ተጠርጣሪ ወንጀለኛው እስካሁን በከተማዋ ተደብቆ እንደሚገኝ የሚሰሙ ጭምጭምታዎች አሉ " ያሉት የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንጮች ፤ ፓሊስ የጭካኔ ድርጊቱ የፈፀመው ግለሰብ አድኖ በመያዝ ህግ እንዲያስከብር አደራ ብለዋል።

የከተማዋ ነዋሪ ተጥርጣሪውን ለፓሊስ አሳልፎ በመስጠት ዜግነታዊ ሃላፊነቱ እንዲወጣም ነዋሪዎቹ ጥሪ አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የእንዳስላሰ - ሽረ ከተማ ፓሊስ ለሚድያ የሚፈቀድ መረጃ በመስጠት እንዲተባበር እየጠየቀ ጉዳዩ ተከታትሎ መዘገቡ እንደሚቀጥል ቃል ይገባል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamliyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…
Subscribe to a channel