ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
#witholding_tax
የገቢዎች ሚኒስቴር በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ መሰረት በእቃዎች እና አገልግሎት ግዢ ላይ ተግባራዊ የሚሆነው 3 በመቶ የቅድመ ግብር (withholding) ክፍያ ከነሐሴ 1 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን አሳውቋል።
በገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ቁጥር 1 ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ሥራ አስኪያጅ አቶ አቶ ሄኖክ በላይ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ ከነሐሴ 1 ጀምሮ ተግባራዊ በሚሆነው አሰራር ለአላስፈላጊ ወጪ እንዳትዳረጉ ሲል አሳስቧል።
ደብዳቤው አዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ጀምሮ ስራ ላይ እንዲውል በተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁን አስታውሶ በአዲሱ አዋጅ መሰረት ለውጥ ከተደረገባቸው መካከል የቀደመ ግብር (witholding tax) ይገኝበታል ብሏል።
በአዋጅ መሰረት ፡-
1. በእቃዎች ግዥ ላይ ከ 20,000 በላይ ሲከፈል 3% ቅደመ ግብር መያዝ እንዳለበት
2. በአገልግሎት ግዥ ላይ ከ 10,000 ብር በላይ ሲከፈል 3% ቅደመ ግብር መሰብሰብ እንዳለበት የተደነገገ በመሆኑ
ይኸውም " ተግባራዊ የሚደረገው ከ ነሀሴ 1 ቀን ጀምሮ በመሆኑ ላልተፈለገ ወጪ እንዳትዳረጉ ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንድታደርጉ አሳስባለሁ " ብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamliyAA
@tikvahethiopia
#Update
" እስካሁን አስክሬኖቹን ማግኘት አልተቻለም፤ ፍለጋው እንደቀጠለ ነዉ " - የደቡብ አሪ ወረዳ አስተዳደር
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሪ ዞን ደቡብ አሪ ወረዳ ከመር ቀበሌ በደረሰዉ የመሬት ናዳ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አምስት ሰዎች ከመሬት በታች ናዳዉ ተጭኖባቸዉ ለማዉጣት ዛሬ
ቀኑን ሙሉ ቢሞከርም እስካሁን አለመቻሉን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግዛዉ ሃይሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" የአስክሬን ፍለጋዉ ሂደት በሰው ሃይል መሆኑ ፍለጋዉን ከባድ አድርጎታል " ያሉት ዋና አስተዳዳሪው " ከክልሉ መንግስትና ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የማሽን ድጋፍ ብንጠይቅም እስካሁን አልደረሰልንም " ሲሉ አስረድተዋል።
የመሬት ናዳዉ ከ3 ሄክታር በላይ በሆነ ቦታ መከሰቱን አንስተው በናዳዉ እስካሁን የተለዩ አራት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መዋጣቸዉን ገልፀዋል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች መፈናቀላቸዉንና በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ አደጋ ዉስጥ ናቸዉ ብለዋል።
" የፍለጋዉ ሂደት እንደ ጎፋዉ አከባቢ ሌላ ናዳ እንዳያስከትል ሕብረተሰቡን ብናስጠነቅቅም ከአቅማችን በላይ ሆኗል " ያሉት አስተዳዳሪዉ " እስከ ምሽት ድረስ የአስክሬን ፍለጋዉ ሂደት በሰዉ ሃይል እየተካሄደ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ስራትና ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጋንታ ጋምኣ ደዉሎ የነበረ ሲሆን ፈቃደኛ ባለመሆናቸው መረጃ ማግኘት ሳይቻል ቀርቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamliyHawassa
@tikvahethiopia
#Tigray የትግራይ ክልል የኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ለመወያየት ወደ አዲስ አበባ መጥተዋል።
ጳጳሳቱ ባለፈው ሳምንት ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ለመወያየት ጥያቄ አቅርበው ነበር።
ለጥያቄ አወንታዊ ምላሽ በማግኘታቸው ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ሊጓዙ እንደቻሉ ተነግሯል።
ጳጳሳቱ ነገ ማክሰኞ ሀምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠቅላይ ሚንስትሩ ተገናኝተው ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ከቀናት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትግራይ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሸማግሌዎች ተቀብለው ስለ መምከራቸው ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamliyMekelle
ፎቶ፦ ድምጺ ወያነ
@tikvahethiopia
#ETHIOPIA🇪🇹
#GERD
" ግብፅ ግድቡን ታፈነዳዋለች " ሲሉ የነበሩት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት አሁን ግድቡ ሊመረቅ ሲቃረብ " ግድቡ የተሰራው በኛ ገንዘብ ነው " ማለት ጀምረዋል።
ከዚህ ቀደም በነበራቸው የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዚዳንትነት የስልጣን ዘመን ኢትዮጵያውያንን " ውሃ ወደ ናይል ወንዝ እንዳይፈስ የሚያቆም ግድብ ገነቡ (ታላቁ የሕዳሴ ግድብን ማለታቸው ነው) ፤ ግብጽ በዚህ ብትበሳጭ መኮነን የለባትም። ግብጽ ግድቡን ታፈነዳዋለች " በሚለው ንግግራቸው የሚታወቁት ዶናልድ ትራምፕ አሁን ደግሞ " ግድቡን በአብዛኛው የገነባነው እኛ ነን " እያሉ ደጋግመው እየተናገሩ ናቸው።
ዶናልድ ትራምፕ በዋይት ሐውስ ለሪፐብሊካን ሴናተሮች የእራት ፕሮግራም ባደረጉበት ምሽት የታላቁ ሕዳሴ ግድብን የሚመለከት ነገር ተናግረዋል።
በዓለም ላይ ያሉ ጦርነቶችን ሰላማዊ እልባት ለመስጠት አሜሪካ እያደረገችው ስላለው ጥረት ተናግረው " ግብፅ እና ኢትዮጵያ በሕዳሴ ግድብ እየተጣሉ መሆኑን ታውቃላችሁ " ብለዋል።
" ኢትዮጵያ ግድቡን የገነባችው በአሜሪካ ገንዘብ ነው፤ በአብዛኛው " ሲሉ ተደምጠዋል።
ትራምፕ አገራቸው መቼ ገንዘቡን እንደሰጠች ወይም በምን መልኩ እንደሆነ ምንም አልተናገሩም።
ፕሬዝደንቱ ዳግም ተመርጠው ስልጣን ላይ ከወጡ በኃላ በተደጋጋሚ አገራቸው ለሕዳሴ ግድብ የገንዘብ ድጋፍ መስጠቷን ሲናገሩ ነበር። በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንኳን ሁለት ጊዜ ተናግረዋል፤ የአሁኑ ሶስተኛቸው ነው።
ኢትዮጵያ እስካሁን ለፕሬዚዳንቱ ንግግር ይፋዊ ምላሽ አልሰጠቻቸውም።
ትራምፕ በመጀመሪያው የስልጣን ዘመናቸው " ውሃ ወደ ናይል ወንዝ እንዳይፈስ የሚያቆም ግድብ ገነቡ ፤ ግብጽ በዚህ ብትበሳጭ መኮነን የለባትም። ግብጽ ግድቡን ታፈነዳዋለች፤ ግብጽ እና ኢትዮጵያ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ አድርጌ ነበር ኢትዮጵያ ግን ጥላ ወጣች " ብለው ነበር።
ኢትዮጵያ አስገዳጅ ስምምነቱን ጥላ በመውጣቷ ብዙ ድጋፎች እንደተቋረጠባትም ገልጸው ነበር።
ፕሬዜዳንቱ አሁን ዳግም ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በግልጽ ለግብጽ ወገንተኛ የሆኑ አስተያየቶችን ከመስጠት ባለፈ ከ " ታፈነዳዋለች " አስተያየት " እኛ ነን የገነባነው " ወደማለት መጥተዋል።
#TikvahEthiopiaFamliyAA
@tikvahethiopia
ንብተራ ኦንላይን
ሁሉንም በአንድ ጥላ ሥር የሚያገኙበት!
ምቹ፣ ቀላል እና አስተማማኝ መተግበሪያ፡፡
***
ይሠሯል ከልብ እንደ ንብ!
#Nib #nibmobilebanking #NibQR #nib #nibtera #nibbank
Facebook / Instagram / linkedin / nibinternationalbank6204">X / nibinternationalbank6204">Youtube / nibinternationalbank">Tiktok / Website
" የጉብኝት ቪዛ አመልካቾች ሁሉንም የማህበራዊ ትስስር ገጽ መለያቸውን ከግል ሴቲንግ ወደ ክፍት/ይፋዊ ሴቲንግ እንዲያስተካክሉ ይጠየቃሉ " - የአሜሪካ ኤምባሲ
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስደተኛ ባልሆኑ የቪዛ አመልካቾች ላይ የፖሊሲ ለውጥ ማድረጉን ማሳወቁ ይታወሳል።
የፖሊሲ ለውጡ ከሐምሌ 1/2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለኢትዮጵውያን የሚሰጠው ቪዛ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል እና የሦስት ወር ቆይታ ብቻ እንዲኖረው ያደረገ ሆኗል።
በኢትዮጵያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በአዲሱ መመሪያ መሠረት ወደ ሃገሪቱ በጊዜያዊነት ጉዞ ለማድረግ የቪዛ ጥያቄ የሚያመለክቱ ዜጎችን የበይነ መረብ (online) አጠቃቀም ላይ ሁሉን አካታች እና ጥልቅ የሆነ ማጣራት እንደሚያካሄድ አሳውቋል።
አምባሲው " በአዲሱ መመሪያ መሠረት በጉብኝት ቪዛ መደብ ውስጥ የF ፣ M እና J ሁሉም የተማሪ እና የልውውጥ (Exchange) ቪዛ አመልካቾችን የበይነ መረብ (online) አጠቃቀም ጨምሮ ሁሉን አካታች እና ጥልቅ የሆነ ማጣራት እናካሄዳለን " ብሏል።
ይህን የማጣራት ሥራ ለማቀላጠፍም ሁሉም የ F ፣ M እና J የጉብኝት ቪዛ አመልካቾች ሁሉንም የማህበራዊ ትስስር ገጽ መለያቸውን ከግል ሴቲንግ ወደ ክፍት/ይፋዊ ሴቲንግ (public setting) እንዲያስተካክሉ ጠይቋል።
የአሜሪካ መንግስት ወደ ሃገሪቱ ለመግባት የሚያመለክቱ ዜጎችን የጉዞ አላማ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በመመልከት በሃገሪቱ የስደተኞች ህግ መሰረት ምን አይነት ቪዛ እንደሚያስፈልግ ምድብ የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል።
ለጊዜያዊ ጉዳዮች እና በቋሚነት ወደ አሜሪካ ጉዞ ለሚያደርጉ ዜጎች በዩኤስ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ሲያመለክቱ ኦፊሰሮች በህጎች ላይ በመመስረት ቪዛ ለመቀበል ብቁ ሆነው ለተገኙ ዜጎች የትኛው የቪዛ ምድብ ለአመልካቹ ተገቢ እንደሆነ ይወስናሉ።
F፣ M እና J የተሰኙ የቪዛ ምድቦች ስደተኛ ያልሆኑ እና ለትምህርት ፣ ለአካዳሚክ ጉዳዮች እና ከተለመደው የቱሪስት ቪዛ ውጪ ለጉብኝት እንዲሁም ለልዩ ልዩ ጉዳዮች ወደ አሜሪካ በጊዜያዊነት ለመግባት ለሚያመለክቱ ዜጎች የሚሰጥ ቪዛን ያመለክታል።
° ኤፍ ቪዛ (F-1/F-2) ፡-
በዋነኛነት በዩኤስ ኮሌጆች፣ ዩኒቨርሲቲዎች ወይም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተቋማት የሙሉ ጊዜ ትምህርት ለሚከታተሉ የአካዳሚክ ተማሪዎች።
° M ቪዛ (M-1/M-2)፡
እንደ የቴክኒክ ክህሎት ስልጠና ላሉ፣ ለሙያ ፣ አካዳሚክ ያልሆኑ ወይም የሙያ ፕሮግራሞችን ለሚከታተሉ።
° ጄ ቪዛ (J-1/J-2)፡
ለተፈቀደላቸው የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብሮች፣ የሁለተኛ ደረጃ እና የዩኒቨርሲቲ ጥናቶች፣ የባህል ልውውጥ ፕሮግራሞችን ጨምሮ በስራ እና በጥናት ላይ የተመሰረተ የልምድ ልውውጦችን ለሚያደርጉ አካላት የሚሰጥ ቪዛን ያመላክታል።
በተጠቀሱት የቪዛ አይነቶች ጥያቄያቸው ያቀረቡ አመልካቾች የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ እና ሁሉን አካታች ማጣራት እንደሚያካሂድ ኤምባሲው አሳውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamliyAA
@tikvahethiopia
#OFC
" በሰላማዊ ትግል ለመቀጠል ቁርጠኛ ነኝ " - የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ)
🗳" በ2018 ሀገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ ቁልፍ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጠናል ! "
የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ለሁለት ቀናት ያካሄደውን መደበኛ ጉባኤ ዛሬ እንዳጠናቀቀ ገለጸ።
ፓርቲው በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ መግለጫ አውጥቷል።
" ሀገሪቱ የመንታ መንገድ ላይ ትገኛለች " ያለው ፓርቲው " ቀጣዩ ምርጫ 'በዲሞክራሲያዊ መታደስ ወይም በሀገር መፍረስ' መካከል የሚደረግ " ነው ብሏል።
" ያለፉት ሰባት ዓመታት 'የባከነ ተስፋ' የታየባቸው እንዲሁም የፖለቲካ፣ የጸጥታና የኢኮኖሚ ቀውሶች እርስ በርስ እየተመጋገቡ ወደ ከፋ ጥፋት ያመሩበት ጊዜ ነበር " ሲል ገልጿል።
" ለዚህ ሀገራዊ ውድቀት ዋነኛውን ምክንያት በሕብረ ብሄራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ላይ የተፈጸመ ስልታዊ ጥቃትና ሰላማዊ የፖለቲካ አማራጮች በሙሉ መዘጋታቸው ነው " ሲል አመልክቷል።
ፓርቲ በመጪው የ2018 ሀገራዊ ምርጫ ላይ የሚሳተፈው በቅድመ ሁኔታ እንደሆነ ገልጿል።
ኦፌኮ " 'ለተሰባበረ የፖለቲካ ሂደት' ሕጋዊ ዕውቅና አልሰጥም " ያለ ሲሆን " በምርጫው ፍተሃዊነትና ታዓማኒነት የሚረጋገጠው መንግሥት መሰረታዊ የሆነ ዳግም ማስተካከያ ሲያደርግ ብቻ ነው " ብሏል።
ፓርቲው " ቁልፍ " ያላቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ይፋ አድርጓል።
" እነዚህም ፦
1. በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ያለው ጦርነት በአፋጣኝና በዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በተረጋገጠ መልኩ እንዲቆም እና ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ውይይት እንዲጀመር።
2. ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ፤ ይህም ለሀገራዊ እርቅ መሰረት እንዲሆን። የፖለቲካ ነጻነቶች ሙሉ በሙሉ እንዲከበሩ፤ የታሸጉ የኦፌኮ ቢሮዎች እንዲከፈቱ እንዲሁም አፋኝ የሆኑ፣ የምርጫ ፣የሚዲያና የሲቪል ማህበረሰብ ሕጎች እንዲሻሩ።
3. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝብን አመኔታ መልሶ እንዲያገኝ በሁሉም ፓርቲዎች ሙሉ ስምምነት ላይ ተመስርቶ በአዲስ መልክ እንዲዋቀር። " የሚሉ ናቸው።
ኦፌኮ በማጠቃለያው " የኦሮሞ ህዝብ አንድነቱን እንዲያጠናክር " ሲል ጥሪ አቅርቦ " ከሌሎች የኦሮሞና የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር ቃልኪዳን ለዲሞክራሲ ለመፍጠር የትብብር እጁን መዘርጋቱን " አመልክቷል።
" ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በመንግሥት ላይ ተጨባጭ ጫና ያሳድር " ሲል ገልጿል።
ኦፌኮ ፥ በሰላማዊ ትግል ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆኑን አሳውቆ " ለዲሞክራሲ ምቹ ሁኔታን የመፍጠር ዋነኛው ኃላፊነት በገዥው ፓርቲ ላይ የሚወድቅ ነው " ሲል አቅጣጫ አስቀምጧል።
መረጃውን የላከው የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት ፅ/ቤት ነው።
#TikvahEthiopiaFamliyAA
@tikvahethiopia
“ አራት አመት ለፍተው ተምረዋል፣ ከተማሩ በኋላ ለፈተና ተቀምጠዋል፣ ውጤታቸውን የማየት ሙሉ መብት አላቸው ” - የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማኀበር
የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከወሰዱ ቢቆዩም ሁሉም ተማሪዎች ውጤታቸውን ባለማየታቸው መፍትሄ እንዲሰጣቸው በሰፊው ቅሬታ እያቀረቡ ይገኛሉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለጉዳዩ የጠየቀው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማኀበርም፣ “የተወሰኑት አይተዋል፤ የተወሰኑት ያላዩ አሉ። ብዙ ተማሪዎችም እየደወሉ 'ውጤት አልተልቀቀልንም' የሚሉ አሉ። የተሟላ አይደለም የውጤት አገላለጹ፤ ወጥነት የለውም። ከክፍያ ጋር የተያያዘ ጉዳይም አለው ” ብሏል።
ውጤት የሚያሳውቀውን ትምህርት ሚኒስቴርን ስለጉዳዩ መጠየቁን የገለጸው ማኀበሩ፣ ምክንያቱ ክፍያ ያልከፈሉ ተቋማት በመኖራቸው እንደሆነ፣ ክፍያውን ሲያጠናቅቁም በተናጠል ውጤት እየተለቀቁላቸው መሆኑን እንዳሳወቀው አስረድቷል።
ማኀበሩ፣ ተቋማትም በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ክፍያ አሟልተው መክፈል እንደሚጠበቅባቸው፣ ትምህርት ሚኒስቴርም ችግሮች ካሉ ቀድሞ ማሳወቅ እንደነበረበት አስረድቶ፣ “ ምዝገባው በጋራ እንደሚከናወነው ሁሉ ውጤቱም የመንግስት፣ የግል ሳይል ሁሉም በወጥነት መገለፅ አለበት ” ብሏል።
“ በወጥነት ካልተገለጸ በተማሪዎቹ ጥቅም ላይ በህዝቡ ላይ የራሱ ተጽዕኖ አለው። ተማሪዎቹ የዚሁ ዳፋ ተቀባይ መሆን የለባቸውም። ምክንያቱም አራት አመት ለፍተው ተምረዋል፣ ከተማሩ በኋላ ለፈተና ተቀምጠዋል፣ ውጤታቸውን የማየት ሙሉ መብት አላቸው። ከዚህ ውጭ ያሉት ነገሮች የተቋም ጉዳይ ናቸው፣ የተቋም ጉዳይ ደግሞ በተቋማት መፈታት አለበት ” ሲልም ገልጿል።
ማኀበሩ፣ “ለምንድን ነው ተማሪዎችን የጉዳቱ አካል የምናደርጋቸው? ”ሲል ጠይቆ፣ “ የሚመለከታቸው አካላት በአንክሮ ማሰብ አለባቸው። የግል ተቋማትም ክፍያውን በወቅቱ ለትምህርት ሚኒስቴር ማስገባት አለባቸው” ብሏል።
ክፍያ ያልፈጸሙት ስንት ተቋማት እንደሆኑ ሲጠየቅም፣ ውጤቱ ከተለቀቀ እንደቆዬ በዚህም ብዙ ተቋማት ከፍለው ሊሆን እንደሚችል ገልጾ፣ “ ያኔ ሲገለፅ የነበረበት ቁጥርና አሁን መውጫ ውጤቱ ከተለቀቀ በኋላ ክፍያቸውን ያጠናቀቁ ተቋማት ስለሚኖሩ የቁጥሩን ሁኔታ ከትምህርት ሚኒስቴር ነው በቀጥታ ማግኘት የሚሻለው ” ሲል መልሷል።
ምን ያክል ተማሪዎች እንዳለፉ፣ ምን ያክል እንደወደቁ እንዳላወቀ በመግለጽ፣ “ ትምህርት ሚኒስቴር ይህንን እንኳን ተደራሽ አላደረገም። የ2016 ዓ/ም ተጠቃሎ የተለቀቀው በአመቱ መጨረሻ ነው። የሁለቱ የመውጫ ፈተና ውጤት ” ብሏል።
“ በትምህርት ሚኒስቴር ፖርታል ከተለቀቀ በኋላ ነው የሚታወቀው ” ያለው ማኀበሩ፣ “ ባለው የፀጥታው ሁኔታ የኔትወርክ ችግር ያለባቸው አካባቢዎች አሉ። ደውሎ ስንት አሳለፋችሁ ለማለት አስቸጋሪ ነው። ብዙ ጥረት አድርገን ነበር የተወሰኑ ተቋማት ናቸው ውጤታቸውን ተደራሽ ያደረጉት ” ሲልም ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ጥቆማ
#ለሚመለከታችሁ_አካላት
" ህጻናትና ሌሎችም ነዋሪዎች ላይ ጉዳት ሳያደርስ መፍትሄ ይሰጠው ! " - ነዋሪዎች
አዲስ አበባ ቃሊቲ 08 ቀበሌ ወደጃቴ ኪዳነ ምህረት ቤ/ክርስቲያን በሚወስደው እሳት አደጋው አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች በአካባቢዎች ወደ መሬት ሊወድቅ ያለ የእንጨት መብራት ፖል መኖሩን በመጠቆም እንዲስተካከልላቸው ጠይቀዋል።
ነዋሪዎቹ " የመብራት ፖሉ ወደቆ መሬት ለመንካት ትንሽ ነው የቀረው ፤ በሰፈሩም ብዙ ህጻናት የሚጫወቱበት ቦታ ነው። ከመሸ በኋላ አዋቂዎችንም ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው። በመሆኑ የሚመለከታችሁ አካላት አስቸኳይ መፍትሄ ስጡት " ብለዋል።
ወቅቱ ክረምት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ያለው ኃይለኛ ዝናብና ንፋስ ፖሉን ጥሎት አደጋ ሳይደርስ መፍትሄ እንዲፈለግ በነዋሪዎች ተጠይቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamliyAA
@tikvahethiopia
#ጥናት🤖
" የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት (AI) መሳሪያዎች የሰዎችን የማመዛዘን ብቃት እየቀነሱት ነዉ " - ጥናት
በቅርቡ የካርኔጊ ሜሎን ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ማይክሮሶፍት በጋራ የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት (AI) በሰዎች የማገናዘብ አቅም ላይ ስለሚኖረዉ ተፅዕኖ አንድ ጥናት አድርገዉ ነበር።
ይህ ጥናት ከፈረንጆቹ 2024 እስከ 2025 የተካሄደ ሲሆን ባለፈው ሚያዚያ ወር በጃፓን ዮኮሀማ በተካሄደ ኮንፍረንስ ላይ በይፋ ለህዝብ የቀረበ ነው።
319 ሰዎችን ያካተተዉ ይህ ጥናት ስራቸዉ ጥልቅ የሆነ ማሰብን ይጠይቃል የተባሉ ሰዎችን አካቷል።
የጥናቱ የተገኙ ግኝቶች ምንድን ናቸው ?
በዚህ ጥናት በዋናነት ሶስት ግኝቶች ተቀምጠዋል።
1ኛ. ጥናቱ ከተደረገባቸው ሰዎች አብዛኞቹ ነገሮች ላይ በጥልቀት ማሰብ እና ትኩረት ማድረግ ላይ እንደሚቸገሩ የጥናቱ ውጤት ያሳያል።
" የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት (AI) መሳሪያዉ ይመልሰዋል " ብለዉ ስለሚያስቡ ነገሮችን በጥልቀት የመመርመር ፍላጎት መቀነስም ታይቶባቸዋል።
2ኛ. ከመጠን ያለፈ እምነት በሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት (AI) መሳሪያዎች ላይ መጣል ሲሆን ጥናቱ የተደረገባቸው ሰዎች ከመሳሪያዉ የሚገኙ ዉጤቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ መተማመን እንዳላቸዉ ያሳያል።
ውጤቶቹንም እውነተኛነታቸዉን ለማረጋገጥ ሌላ ተጨማሪ ምንጮችን በማየት ለማረጋገጥ እንደማይሞክሩ ውጤቱ ያመለክታል።
3ኛ. የጥናቱ ውጤት ሰዎች ጥልቅ እና የተወሳሰቡ የሚመስሉ ነገሮችን ከማሰብ እና ምክንያታዊ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ከሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት (AI) መሳሪያዎች የሚወጡ ቀላል እና መሰረታዊ ስህተቶችን በማረም ላይ ያተኩራሉ ብሏል።
እንዲሁም የራሳቸዉን አስተሳሰብ በጥቂቱ ስለሚያቀርቡ የግለሰቡን ሀሳብ የማመንጨት ተፈጥሯዊ ብቃቱን እንደሚያሳጣዉ ጥናቱ ይገልጻል።
በጥናቱ መሰረት ከመረጃ ጋር የተያያዙ ስራዎች ከሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መሳሪያዎች ጥቅም ላይ መዋል በኋላ መረጃን ከመሰብሰብ ወደ ማረጋገጥ መዞራቸውን ያነሳል።
ችግር ፈቺ በሆኑ የሥራ ቦታዎችም ቀጥታ ችግሩን ከመፍታት የሰው ሰራሽ አስተውሎት ምክሮቸን ወደመቀበል ዞረዋል ተብሏል።
በጥናቱ ከተሳተፉ 319 ሰዎች ውስጥ 83 ያህሉ በሰው ሰራሽ አስተውሎት መሳሪያዎች ላይ ያላቸው መተማመን የማገናዘብ አቅማቸውን እንዳዳከመው አምነዋል።
ከዚህ በተጨማሪ 72 ሰዎች ከሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ያገኙት ምላሽ ስህተት እያለው እንኳን ለማረም እንደማይችሉ በጥናቱ ተመላክቷል።
በአጠቃላይ የጥናቱ ማጠቃለያ ሰዎች በስራ ቦታ ላይ ያላቸዉ የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት (AI) መሳሪያዎች አጠቃቀም የሰዎችን ምክንያታዊ የአስተሳሰብ አቅም እየቀነሰዉ መምጣቱን ያሳያል።
ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ተጠቃሚዎች ከሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት መሳሪያዎች በሚመነጩ መልሶች ላይ መተማመናቸው ነው።
በተጨማሪም ከመተንተን ይልቅ ከሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት የሚገኙ ውጤቶችን ወደ ማረጋገጥ ፣ ማቀናጀት እና መሰረታዊ ሰህተቶችን ወደ ማረም መዞራቸው መሆኑን ጥናቱ ያሳያል።
#TikvahEthiopiaFamliyAA
Via @TikvahethMagazine
#Ambulance🚑
በዚህ ዓመት ብቻ 184 እናቶች ከወሊድ ጋር በተያያዘ መሞታቸውን የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ።
ቢሮው ይህን ያለው ባፈላለገው ፈንድ በኢትዮጵያና የዓለም ቀይ መስቀል ማህበራት ቅንጅት የተገዙ 200 አምቡላንሶች ለዞኖች ርክክብ በተደረገበት ወቅት ነው።
የቢሮው ሃላፊ ዶ/ር አማኒኤል ሃይለ ፤ ጦርነት በወለደው ጦስ ምክንያት የአምቡላንስ እጥረት በማጋጠሙ የእናቶች እና የህፃናት ሞት እጅግ እንዳሻቀበ ተናግረዋል።
በዚህ ዓመት ብቻ 184 እናቶች ከወሊድ ጋር በተያያዘ መሞታቸውን ጠቁመዋል።
" ከጦርነቱ በፊት በትግራይ 310 አምቡላንሶች ነበሩ ከጦርነቱ በኃላ ከ82 በታች ነው " የቀሩት ያሉት ሃላፊው " በዚህ ምክንያት የክልሉ የህክምና ዘርፍ 25 ዓመት ወደ ኃላ ተመልሷብምል ፤ የእናቶችና የህፃናት ሞት ተበራክቷል " ብለዋል።
በጦርነቱ ምክንያት እጅግ የተጎዳው የክልሉ ጤና ዘርፍ መልሶ እንዲያገግም አገራዊና ዓለም አቀፋዊ እገዛ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።
ኃላፊው አሁን የተለገሱት 200 አምቡላንሶች ጠቀሜታቸው ከፍተኛ እንዳሆነ ገልጸዋል። ግን የክልሉን ፍላጎት ለሟሟላት 400 አምቡላንሶች እንደሚቀሩ ጠቁመዋል።
አምቡላንሶቹ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ የነዳጅ አቅርቦት ሊታሰብበት እንደሚገባ አመላክተዋል።
200 አምቡላንሶቹን የትግራይ 7 ዞኖች ተወካዮች ከክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) እጅ ቁልፍ ተረክበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamliyMekelle
@tikvahethiopia
#UoG
ጎንደር ዩኒቨርስቲ ትልቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ 14 የቀድሞ ምሩቃን ልዩ ዕውቅና ሰጠ !
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለትም በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን 2500 ተማሪዎችን አስመርቋል።
ዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ተማሪዎች ማህበር ምስረታን በትላንትናው ዕለት የፋ ሲያደርግ በዛሬው ዕለት ደግሞ በ13 ዘርፎች ለ14 የቀድሞ ምሩቃን ልዩ ዕውቅና ሰጥቷል።
የዩኒቨርስቲው ፕረዚዳንት ዶክተር አስራት አፀደወይን ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ባደረጉት ቆይታ ዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያውን ምረቃ ያካሄደው ሰኔ 30 ቀን 1949 ዓ.ም እንደነበር እና ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 66 ዓመታት 107 ሺ 860 ሙህራንን ማፍራቱን አስታውሰዋል።
ከእነዚህ ሙህራን መካከል በ13 ዘርፎች በሙያቸው በጎ ትፅዕኖ የፈጠሩ 14 ሙህራንን ዩንቨርስቲው ዕውቅና ለመስጠት መወሰኑን አስረድተዋል።
ጎንደር ዩኒቨርስቲ በምን ዘርፍ ለየትኞቹ የቀድሞ ተመራቂዎች ልዩ ዕውቅና ሰጠ ?
1. የፕሬዚዳንታዊ ሌጋሲ ከፍተኛ ሽልማት ዘርፍ
- ፕ/ር መንገሻ አድማሱ (የቀድሞው የዩኒቨርስቲው ፕረዚዳንት)
- ፕ/ር ያሬድ ወንድምኩን (የመጀመሪያው የዩኒቨርስቲው ፕረዚዳንት)
2. የማኅበረሰብ ተጽዕኖ የላቀ ሽልማት (Community Award)
- ፕ/ር ብሩክ ላጲሶ
3. ዓለም አቀፋዊ የመሪነት ዘርፍ (Global Leadership Award)
- ዶ/ር ከሰተብርሃን አድማሱ (የቀድሞ የኢፌዴሪ ጤና ጥበቃ (ጤና) ሚኒስትር
4. ወጣት ሥራ ፈጣሪና ተጽዕኖ ፈጣሪ ዘርፍ
- አቶ ጃለታ ሙላቱ
5. በጎንደር ዩኒቨርስቲ ድጋፍ እና አጋርነት ዘርፍ
- ዶ/ር ካሱ ከተማ
6. በትምህርት እና ምርምር ልኅቀት ዘርፍ
- ዶ/ር ኤርሚያስ ዲኖ
7. በህዝባዊ አገልግሎት ዘርፍ (Public Service Award)
- ዶ/ር ተዋበች ቢሻው (የመጀመሪያዋ ሴት ጤና መኮንን)
8. በህይወት ዘመን አበርክቶ ዘርፍ
- ፕ/ር ጉታ ዘነበ
9. በጤናና ሰብዓዊ አገልግሎት ዘርፍ
- ዶ/ር ፈቀደ አጉዋር
10. በባህል፤ በመገናኛ ብዙኀን እና ኪነ-ጥበብ ዘርፍ
- አቶ ስለሺ ግርማ ( በአሁኑ ወቅት የቱሪዝም ሚኒስትር ሚ/ዴኤታ)
11. በሥራ ፈጠራና ኢንቨስትመንት ዘርፍ
- ዶ/ር ግርማ አባቢ
12. በዲያስፖራ አምባሳደርነት ከፍተኛ ተሸላሚ
- ዶ/ር ኑሩ አብሲኖ
13. ልዩ የሰብዓዊ አገልግሎት ሽልማት (Social Humanitarian Impact Award)
- ወጣት ዳዊት አየነው
እጩዎችን የማሰባሰብ እና ድምጽ የማሰባሰብ ሥራ ተሰርቶ ተሸላሚዎቹ መለየታቸውን ዩኒቨርስቲው አስታውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
#TikvahEthiopiaFamliyBahirdar
@tikvahethiopia
" ብቃት ያላቸውን አሽከርካሪዎችን አይቶና መዝኖ ለብቃት የሚያበቃቸውን መንጃ ፍቅድ መስጠት ነው እንጂ ገንዘብ ስለከፈለ ብቻ መስጠት ተገቢ አይደለም " - የሀረሪ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን
የመንጃ ፈቃድ ብቃት ላላቸው አሽከርከርካሪዎች እንዲሰጥ፣ አሽከርካሪዎችም በጥንቃቄ እንዲያሽከክሩ፣ እግረኞችም የእግረኛ መንገድ ጠብቀው እንዲጓዙ የሀረሪ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሳስቧል።
የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ጣሰው ቻለው ይህን ያሉት ትላንት በክልሉ ሀረር ከተማ የደረሰውን የመኪና አደጋ በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ገለጻ ነው።
በከተማው አራተኛ ተብሎ በሚጠራው መንገድ በደረሰው አደጋ ስለደረሰው ጉዳት ማብራሪያ ስንጠይቃቸው፣ " የሞተ ሰው የለም፤ 8 ሰዎች ናቸው ጉዳት የደረሰባቸው፤ አራቱ ከባድ እና አራቱ ቀላል ጉዳት ነው " ሲሉ አስረድተዋል።
አደጋው የተከሰተው ውሃ የጫነ ቦቴ ከአራተኛ መንገድ ወደ ስቴዲየም ሲጓዝ ፍሬን በጥሶ፣ ከሁለት ባጃጆችና ከአንድ ፒካፕ ጋር በመጋጨቱ መሆኑ ተመልክቷል።
ኮማንደር ጣሰው ባስተላለፉት መልዕክት፥ " እንደ ሀገር የትራፊክ አደጋ ከፍተኛ የሰውን ልጅ ሕይወት የሚቀጥፍ ነው በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው " ብለዋል።
" እንደ ሀገር ከፍተኛ የሆነ ጥፋት ነው እያደረሰ ያለው " ያሉት ኮማንደር ጣሰው፣ " ስለዚህ ትልቁ ነገር፥ ብቃት ያላቸውን አሽከርካሪ አሰልጥኖ ማውጣት ነው። ይሄ ደግሞ የማሽከርከሪያ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ትልቅ ኃላፊነት ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
" በዚህ ጉዳይ ትኩረት መሰጠት አለበት ዝም ብሎ መንጃ ፈቃድ መስጠት ብቻ ሳይሆን ለሰው ሕይወት፣ ለሀገር ማሰብ ተገቢ ነው አሽከርካሪዎቹም በአግባቡ ማሽከርከር፣ ለሰው ሕይወት ማሰብ አለባቸው " በማለት አስገንዝበዋል።
" ብቃት ያላቸውን አሽከርካሪዎችን አይቶና መዝኖ ለብቃት የሚያበቃቸውን መንጃ ፈቅድ መስጠት ነው እንጂ ገንዘብ ስለከፈለ ብቻ መስጠት ተገቢ አይደለም። ይሄ ትልቅ ኃላፊነት የሁላችንም ስለሆነ ጥንቃቄ መድረግ አለበት፤ ህብረተሰቡም የእግረኛውን መንገድ በአግባቡ ጠብቆ መሄድ አለበት " ሲሉ አሳስበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia
በማይቆራረጥ ኢንተርኔት የLive ያጧጡፉ!
በBET-WIF ሁሉም ኮንተንት ክሬተር የሚያስፈልገውን ፈጣን እና የማይቆራረጥ ኢንተርኔት ከቤቶ ሆነው ያግኙ።
#Update
“ ተራራው እየተደረመሰ ወደ ታች ወደ እሳተ ገሞራው እየገባ ነው፡፡ በፍንዳታው የሚወጣው ሰልፈርዳይ ኦክሳይድም የመተንፈሻ አካል ላይ ክፍተኛ ጉዳት ያስከትላል ” - ሰመራ ዩኒቨርሲቲ
የአፋር ክልሉ የኤርታሌ እሳተ ገሞራ ፍንዳታ እንዳልቆመ፣ እሳተ ገሞራው ሲወጣ መሬቱ እየተደረመሰ ወደ ውስጥ እየገባ ከመሆኑም ባሻገር የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ መሆኑን በቦታው ተገኝቶ የነበረው ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የዩኒቨርሲቲ የጂኦሎጅ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ኖራ ያኒሚኦ ጉዳዩ ያለበትን ሁኔታውን ሲያስረዱን፣ “ትላንት በቦታው ነበርን፤ በኤርታሌ በጣም ከፍተኛ የሆነ አቧራ እየወጣ ነው፡፡ በሁለት ቦታዎች ላይ ደግሞ ትንሽ ጭስና እሳት ታይቷል፡፡ ግን ትንሽ ጭስ ከመውጣት ውጪ ሌላ ነገር የለውም” ብለዋል፡፡
“በፎቶ የተሰራጨው በጣም ከፍተኛ አቧራ ሲወጣበት የነበረው ቦታ ግን ትላንት ራሱ ከቀኑ 11 እስከ ማታ 2 ሰዓት ድረስ ከፍተኛ አቧራ እየወጣበት ነው የነበረው፡፡ አቧራው ከመውጣቱ በፊት ዝቅተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር፡፡ መሬት መንቀጥቀጡ ከእሳተ ገሞራ ፍናዳታው ጋር የተያያዘ ነው” ሲሉም አስረድተዋል፡፡
አክለው፣ “የሚወጣው አቧራ ደግሞ ሰርፈርዳይ ኦክሳይድ ኮንቴነቱ ከፍተኛ ስለሆነ ከፍተኛ የሰልፈር ሽታ አለው፡፡ መሬቱም እተሰነጠቀ ነው፡፡ አስቸጋሪ ሆነ ሁኔታ ነው ያለው” ብለዋል፡፡
“እየተሰነጠቀ ያለው መሬት ደግሞ የእሳተ ገሞራው ላቫ ወደ መሬት በሚወጣት ወቅት ሶሊድፋይድ ይሆናል፤ ስለዚህ ሶሊድፋይ የሆነውና ላቫና ክቧ ተራራ የሚገናኙት ቦታ ላይ ነው፡፡ በመሆኑም ተራራው እየተደረመሰ ወደ ታች ወደ እሳተ ገሞራው እየገባ ነው” ሲሉም የአደጋውን በአሳሳቢነት አስረድተዋል፡፡
ተመራማሪው፣ “በፍንዳታው የሚወጣው ሰልፈርዳይ ኦክሳይድ የመተንፈሻ አካል ላይ ክፍተኛ ጉዳት ያስከትላል፡፡ በዓይንም ሆነ አፍንጫ ሲገባ በጣም ነው የሚያቃጥለው” ብለው፣ በኤርታሌ በጣም በቅርበት የሚኖሩ ነዋሪዎች ባይኖሩም ብናኝ የሚድርሰባቸው ነዋሪዎችም ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አስገንዝበዋል፡፡
ርቀት ቦታ ላይ በሚገኙ እንደ አፍዴራ ባሉ አካካቢዎች ብናኙ እየደረሰ መሆኑን ጠቁመው፣ “የሚወጣው አቧራ የመተንፈሻ አካል ላይ ጉዳት ሊያስከትል ስልሚችል ማህበረሰቡ የአፍንጫ ጭምብል ሊጠቀም ይገባል” ሲሉም አሳስበዋል፡፡
በኤርታሌ ከዚህ ቀደም እንደዚህ አይነት አደጋ አጋጥሞ እንደማያውቅ ገልጸው፣ “ አሁን ግን ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ ወደ ኤክስክሎሲቭ ኢራፕሽን እየተሸጋገረ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች አሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ነገር ብዙም ኤርታሌ ላይ የተለመደ አይደለም፡፡ እስከዛሬ ማግማው ወደ ላይ ከመምጣት ውጭ የኤክስክሎሲቭ ምልክት አያሳይም ነበር ” ነው ያሉት፡፡
ፎቶ ለማንሳትና ቪዲዮ ለመቅረጽ ወደ ቦታው የሚሄዱ ሰዎች እንዳሉ ገልጸው፣ እሳተ ገሞራው በሚወጣበት ወቅት ከፍትኛ የሆነ መሬት መንቀጥቀጥ ስላለ፣ ተራራውም እየተናደ ስለሆነ (ትላንት የነበሩበት ቦታ እንደተናደ ጠቁመዋል) በርቀት ካልሆነ በስተቀር ሰዎች ወደ ቦታው ቀርቦ ከመቅረጽ እንዲታቀቡ በአጽንኦት አስጠንቅቀዋል፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiafamilyAA
ፎቶ፦ ፋይል
@tikvahethiopia
#Alert🚨
" በጥቆማው መሰረት መድኃኒቱ ችግር ያለበት መሆኑን በመታወቁ ከሁሉም ተቋማት እንዲወገድ ተደርጓል " - የምግብ እና መድኃኒት ባለሥልጣን
የኢትዮጵያን ምግብ እና መድኃኒት ባለሥልጣን " NURATION (10mg Thiamine monohydrate+3mg Pyridoxine Hydrochloride+15mcg Cyanocobalamin) sugar coated tablet supplement " የተሰኘ መድኃኒት ከደረጃ በታች ሆኖ በመገኘቱ ማህበረሰቡ እንዳይጠቀመው አሳስቧል።
ይህ ከደረጃ በታች የሆነ ፕሮዳክት የ ሦስት (ቢ 1 ፣ቢ 6 እና ቢ 12 የተሰኙ) ቫይታሚኖች ስብጥር ሲሆን የቫይታሚን እጥረት እና የነርቭ ችግር ላለባቸው ሰዎች የሚታዘዝ መድኃኒት መሆኑን ባለሥልጣኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።
ባለሥልጣኑ " በህጋዊ መንገድ የተመዘገበው መድኃኒት ገበያ ላይ አለ ነገር ግን በማመሳሰል የተሰራው እና ማህበረሰቡ እንዲያውቀው ያልነው መድኃኒት ከህጋዊው መድኃኒት ጋር በይዘት (Content) በማመሳሰል ገበያ ላይ የወጣውን ነው " ብሏል።
ሃሰተኛው መድኃኒት ማሸጊያ ላይ " Zhejiang Medicine and Health care product " የሚል ጽሁፍ ስለመኖሩም አሳውቋል።
በኢትዮጵያ የምግብ እና መድኃኒት ባለሥልጣን የመድኃኒት ደህንነት እና ማርኬቲንግ ሰርቬላንስ ዴስክ ሃላፊ አቶ ተሽታ ሹቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?
" ይህ ቫይታሚን ከፍተኛ የሆኑ የ ይዘት (Content) ችግር አለበት።
የተቀመጡት ቫይታሚኖች መጠንም :-
° ' ቫይታሚን ቢ 1 ' 100 mg መሆን ሲገባው የያዘው 10 mg ነው።
° ' ቫይታሚን ቢ 6 ' 200 mg መሆን ሲገባው የያዘው 3 mg ነው።
° ' ቫይታሚን ቢ 12 ' 1000 micro gram መሆን ሲገባው የያዘው 15 micro gram ብቻ ነው።
ይህ ከፍተኛ የሆነ የይዘት ልዩነት ከመኖሩም በላይ መድኃኒት ነው ብለን መጥራትም አንችልም።
እስካልተመዘገበ እና ፈዋሽነቱም እስካልተረጋገጠ ድረስ በአናሳ ሚሊ ግራምም ቢሆን መድኃኒት ነው ብለን የምንቀበልበት ምክንያት የለም።
ህብረተሰቡ መድኃኒት ነው ብሎ እንዳይጠቀም፣ ጤና ባለሞያዎችም እንዳያዙ፣ የክልል ተቆጣጣሪዎችም የራሳቸውን እርምጃ እንዲወስዱ በሚል አሳውቀናል።
ይህንን ያሰራጨው አቅራቢ የብቃት ማረጋገጫው ተሰርዞበታል በህጋዊ መንገድም ፍርድ ቤት ይቀርባል።
ራስ ደስታ ሆስፒታል በጨረታ ከአቅራቢው እነዚህን መድኃኒቶች ወስዶ እየተጠቀመው ነበር።
መድኃኒቱ በ ጴጥሮስ ሆስፒታል ላይ እጥረት ባጋጠመበት ወቅት በመንግስት ሆስፒታሎች መካከል የመድኃኒቶች የውስጥ ዝውውር ስለሚፈቀድ ከራስ ደስታ ሆስፒታል የተጠቀሰው መድኃኒት ወደ ጴጥሮስ ሆስፒታል በሄደበት ወቅት ከጴጥሮስ ሆስፒታል ለ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ መድኃኒቱ ችግር ያለበት ስለመሆኑ ጥቆማ ደርሷል።
በጥቆማው መሰረት መድኃኒቱ ችግር ያለበት መሆኑን በመታወቁ ከሁሉም ተቋማት እንዲወገድ ተደርጓል።
በአቅርቦት ሰንሰለቱ ውስጥ ሌላ ቦታ የተጠቀሰው ፕሮዳክት አለ ወይ የሚል ማጣራት ተደርጓል ባጣራነው መሰረትም መድኃኒቱን አላገኘንም በሁለቱ ሆስፒታሎች የነበረውም እንዲወገድ ተደርጓል።
አቅራቢውም በፍርድ ቤት ለመጠየቅ እየተንቀሳቀስን ነው " ብለዋል።
NB. ህጋዊው እና ህገወጥ መድኃኒቱ ስላላቸው ልዩነት ከተያያዘው ምስል ላይ ይመልከቱ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamliyAA
@tikvahethiopia
#Update
" በመካከል የ12ኛ ክፍል ፈተና ስንጀምር ወደ አርካይቭ መቀየር ነበረብን ወደ አርካይቭ ስናስገባው ፕላትፎርሙ ተዘጋና ማየት አልቻሉም፤ እኛም ማየት አልቻልንም፤ በቅርብ ይለቀቃል " - ትምህርት ሚኒስቴር
የመውጫ ፈተና ውጤት " ሁሉም ተፈታኞች አላዩም " በሚል እየቀረበ ላለው ቅሬታ ሰሞኑን ምላሽ የጠየቅነው የግል ከፍተኛ ተቋማት ማኀበር ትምህርት ሚኒስቴርንና ክፍያ ያልከፈሉ ተቋማትን ተጠያቂ አድርጓል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ተማሪዎቹ ውጤታቸውን ማየት ያልቻሉት ምን ተፈጥሮ ነው ? ሲል ዛሬ የጠየቀው የትምህርት ሚኒስቴር፣ " ከ12ኛ ክፍል ፈተና በፊት ነው ውጤት የተቀቀው፤ ተቋሙም እንዲያይ ተማሪዎቹም እንዲያዩ አድርገናል " ብሏል።
" ነገር ግን መካከል ላይ የ12 ክፍል ፈተና ስንጀምር ወደ አርካይቭ መቀየር ስለነበረብን ወደ አርካይቭ ስናስገባው ፕላትፎርሙ ተዘጋና ማየት አልቻሉም ሰዎች፤ እኛም ማየት አልቻልንም ለጊዜው። በቅርብ ይለቀቃል፤ እየተነጋገርን ነው " ሲሉ አንድ የተቋሙ አመራር ተናግረዋል።
ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውጤት እንደላኩ አስታውሰው፣ “" አንዳንድ ያላኩላቸውም ክፍያ ላይ የዘገዩ ተቋማት ስለነበሩ እነርሱም አላዩም እንለቀዋለን። ግን 'አላየንም' የሚለው የሚያስኬድ አይደለም ልጆችም ተቋማትም በጊዜ ገብተው ማየት ይችሉ ነበር፤ ያን ማድረግ ስላልቻሉ ነው አሁንም ይለቀቃል " ብለዋል።
ብዙዎች ተቋማት ክፍያ እያጠናቀቁ መሆኑን አስረድተው፣ " በተቀመጠላቸው ጊዜ የኤግዚት ተፈታኝ ስለማይከፍሉ ነው ብዙዎቹ የሚዘገይባቸው። ሁለት፣ ሦስት ተቋማት ናቸው አሁን የቀሩት። ከዛ ውጪ ያሉት ግን ፕላትፎርሙ አክቲቭ ሲሆን ማየት ይችላሉ፤ ያኔም ያላዩት ስለዘገዩ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
ለፈተና ከመቀመጣቸው በፊት አይደለም እንዴ ክፍያ መጠናቀቅ የነበረበት ? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄም በምላሻቸው፣ ቅድሚያ መክፈል እንደነበረባቸው አምነው፣ " ግን አይከፍሉም። እኛ ፈተና ከመጀመሩ በፊት ሳይሆን ከዛ በፊት ነው ደብዳቤ የሰጠናቸው፤ ግን ብዙ ከፍተኛ ተቋማት ፈተና ሳይቀመጡ ተማሪዎቹ ከፍለው እንዲጨርሱ ብናሳስባቸውም አያደርጉም " ነው ያሉት።
" እኛም ደግሞ ተማሪዎቹ ለፈተና ተዘጋጅተው ተቋሙ አልከፈለምና አትፈተኑም ማለት አልፈለግንም። ከተፈተኑ በኋላ ተቋማቱ ቢያንስ ከፍለው ውጤቱ እንዲያዩ ነው የምናደርገው፤ ተማሪዎቹም ማገድ አስቸጋሪ ነው " ሲሉ መልሰዋል።
እንዲህ አይነት ኬዝ ያለበት ውጤትስ ታዲያ መቼ ይለቀቃል ? ለሚለው ጥያቄም '' የመንግስት የግል የሚባል ነገር የለም። አሁን ፕላትፎርሙ አይሰራም " ብለው፣ " ቢበዛ ነገ የሁሉም ይለቀቃል፤ ተነጋግረናል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvqhEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia
⚡️ በሳምንታዊ የዳታ ጥቅሎች ዘና ፈታ እንበል! 🥳
በልዩ ልዩ አማራጮች የቀረበልንን የሳፋሪኮም የኢንተርኔት ጥቅል አሁኑኑ እንግዛ! በፈጣን ዳታ እንንበሽበሽ!
#1wedefit
#Furtheraheadtogether
" በአደጋው የአንድ ቤተሰብ ሙሉ አባላት ህይወት ነው ያለፈው " - አሪ ወረዳ
በደቡብ አሪ ወረዳ በኮመር ቀበሌ ሞልሽር ልማት ቡድን ትላንት እሁድ 10:00 አከባቢ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ከምሽቱ 2:30 ላይ በተከሰተእ ናዳ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል።
በተከሰተው ናዳ ምክንያት የአንድ ቤተሰብ ሙሉ አባላት ህይወት እንዳለፈ ወረዳው ገልጿል።
አቶ ተረቱ ካይቲ የተባሉ አባት ከ2 ወንድ ልጆች ፣ 1 ሴት ልጅ እና ከልጆቻቸው እናት ጋር ህይወታቸው ህይወታቸው አልፏል።
ሶስት ቤቶች ሁለት ቆርቆሮ ቤት እና አንድ ሳር ቤት ከቤት እንስሳት እና አትክልት ጋር በናዳው ጉዳት ደርሶባቸዋል።
200 ሰዎችም ተፈናቅለዋል።
@tikvahethiopia
ኢትዮጵያ የአፍላ ወጣቶችን እርግዝናቅነሳ ፍኖተ ካርታ (2025–2030) ተግባራዊ አድርጋለች።
ጠንካራ ሀገራዊ ጥረቶች ለተሻሻለ የልጃገረዶች ሁለንተናዊ ከለላ፣ትምህርት እና የማህበረሰብ ጤና!
ተጨማሪ ይመልከቱ
ለአማርኛ English
#MakeWay #VSO #RTG
" የጣና ሀይቅና በዙሪያው ያሉ ደሴቶች የዓለም ቅርስ ሆነው ሊመዘገቡ ነው " - የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ
የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ጣና ሐይቅ እና በዙሪያው ያሉ ደሴቶች ተፈጥሮዊም ባህላዊም የዓለም ቅርስ ሆነው እንዲምዘገቡ መወሰኑን የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ።
በቢሮው ምክትል ኃላፊ አየለ አናውጤ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል " ዩኔስኮ በጣና ሀይቅ ዙሪያ ያሉ ደሴቶችን ጨምሮ በ3600 ኪ.ሜትር ስፋት ርቀት ያለውን የሐይቁን አካባቢ በተፈጥሮዊና በባህላዊ የዓለም ቅርስ አድርጎ እንደሚመዘግበው በኢሜል አረጋግጧል " ብለዋል።
የቢሮው ምክትል ኃላፊ አየለ አናውጤ ( ዶ/ር) በዝርዝር ምን አሉ ?
" ላለፍት ሁለት ዓመታት ሀይቁን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ሰፊ ሥራ ሲሰራ ቆይቷል። በቅርቡም ተቀባይነት ማግኘቱን ከድርጅቱ ለቢሮው የኢሜል መልዕክት ተልኳል።
በአሁኑ ወቅት ሀይቁ ያለበት ትክክለኛ ገፅታ የሚያሳይ ፎቶ ግራፎችና ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ላኩ ተብሎ ተልኳል። በሚቀጥለው መስከረም ወር ላይ የድርጅቱ አጥኝ ቡድን በአካል ተገኝቶ የተላከውን ፎቶና ቪዲዪ መሬት ላይ መኖሩን ይገመግማል።
ከግምገማው በኃላም በሚቀጥለው ዓመት ጥር ወር ላይ ማለትም በአዲሱ የፈረንጆቹ 2026 ዩኔስኮ በሚያካሂደው 48ኛ ጉባኤ ላይ እንደሚፀድቅ ድርጅቱ ገልጿል።
ለድርጅቱ በተላከው ዶክመንት ላይም የሐይቁን ስፋትና በውስጡ ስላሉ ተፈጥሮ ውበት ማለትም ፦
- በሀይቁ ውስጥ የሚኖሩ የአሳ ዓይነቶች፤
- በሀይቁ ዙሪያ ያሉ የአዕዋፋት ዓይነቶች፤
- በሀይቁ አባይና ጣና የሚገናኙበት ቦታ፤
- የአባይ መነሻ እንዲሁ። በባህላዊ ቅርሱ ደግሞ በደሴቶቹ ውስጥ ያሉ ገዳማት፤ ኪነ ህንፃዎቹ፤ የሀይማኖት መዛግብቱ፤ የነገስታት መቃብሮችን ያጠቃለለ ሲሆን በዚህ ምክንያት በሁለት መልኩ በተፈጥሮአዊና ባህላዊ ቅርስነት ይመዘገባል።
ይህ በዮኔስኮ አሰራር አልተለመደም። በዓለም ሁለቱንም የያዘ ቅርስ የተመዘገበ የለም ይህም በዓለም አንደኛ እንዲሆን ያደርገዋል።
ሐይቁና በሐይቁ ዙሪያ ያሉ ደሴቶች በዓለም ቅርስነት መመዝገብ የዓለምን ቅርስ ለመጎብኘት የሚመጣው ቱሪስት ቁጥር ይጨምራል።
እንዲሁም ሐይቁን ራሱን የሚያስተዳድር ተቋም በአዋጅ እንዲቋቋም ዩኔስኮ ያስገድዳል ይህ ሆነ ማለት ሐይቁ በደለል፤ በእርሻ፤ በእምቦጭ እንዳይጠቃ የውሃ መጠኑ እንዳይቀንስ ጥበቃ ያደርጋል።
ሐይቁ ተጎዳ ብለን ሪፖርት ብናደርግ እንኳን ድርጅቱም በቴክኒክም በገንዘብም እገዛ ያደርጋል በአጠቃላይ ህልውና እንዲጠበቅም ያደርጋል፤ ያግዛልም " ሲሉ ነግረውናል።
በጣና ሀይቅ በቋጥኝ እና በደን የተሸፈኑ ከ37 በላይ ደሴቶች የሚገኙ ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ 19ኙ ታሪካዊ ገዳማትን እና አድባራትን ይዘዋል፡፡
ጣና ሐይቅ በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ በአማራ ክልል የሚገኝ ሐይቅ ሲሆን፤ በስፋቱም በኢትዮጵያ ቀዳሚ ሐይቅ ነው።
ይህ ሀብት በዩኔስኮ የሚመዘገብ ከሆነ ከሰሜን ብሔራዊ ፓርክ ቀጥሎ ሁለተኛ የተፈጥሮ ሀብት ሆኖ በክልሉ ይመዘገባል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
#TikvahEthiopiaFamilyBahirdar
@tikvahethiopia
የንብረት ግብር ተፅዕኖውና ጥቅሙ በባለሙያ አይን !
" የንብረት ግብር ማስከፈል በሌሎች ሀገራት የተለመደ አሰራር ነው፡፡ የመንግስትን የገቢ ምንጭ የሚጨምር ስለሆነ ይህ ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን መንግስት በምላሹ ለህብረተሰቡ የሚሰጠው አገልግሎት ምን ያህል ነው ? የሚለው በአግባቡ መታየት አለበት፡፡ በሰበሰበው ግብር ልክ፣ ለህብረተሰቡ አገልግሎት ይሰጣል ወይ ? የሚለው መጠየቅ ያለበት ነገር ነው " - አረጋ ሹመት (ዶ/ር)
የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ በሚቀጥለው አመት ማለትም በ2018 ዓ.ም ክልሎች የንብረት ግብርን ማስከፈል እንደሚጀምሩ ከዚህ ቀደም መናገራቸው ይታወሳል።
ሚኒስትሩ በሚቀጥለው በጀት ዓመት የንብረት ታክስ በክልሎች ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጀመር ነው የገለጹት።
በንብረት ግብር ምንነትና ተፅዕኖ ዙርያ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ እንዲሰጡን የጠየቃቸው በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር፣ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት አረጋ ሹመት (ዶ/ር) ይህ አሰራር በሌሎች ሀገራት የተለመደና በኢትዮጵያም መጀመሩ አግባብ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ሆኖም ግን፣ መንግስት ከህዝቡ በሚሰበስበው ግብር ለህዝቡ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዳለበት አብሮ መታየት ይኖርበታል ብለዋል፡፡ እርምጃው የሸቀጦች የዋጋ ግሽበትን ሊያስከትል እንደሚችልም ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡
አረጋ ሹመት (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በዝርዝር ምን አሉ ?
" የንብረት ግብር ወይም ፕሮፐርቲ ታክስ ከማይንቀሳቀስና ከሚንቀሳቀስ ንብረት የሚከፈል ግብር ነው፡፡ የሚንቀሳቀስ ንብረት ሲባል ለምሳሌ መኪናን ሊያካትት ይችላል፡፡ ለዚህ ንብረት የሚከፈል ግብር ይኖራል ማለት ነው፡፡
በሌሎች ሀገራት ሌሎች አይነት ንብረቶችን ሊያከካትት ይችላል፡፡ ለምሳሌ በሀገረ ሶማሊያ ከከብቶች/የቤት እንስሳት የንብረት ግብር እንዲከፈል የቀረበ ምክረሀሳብ እንዳለ አውቃለሁ፡፡ የማይንቀሳቀሰስ ንብረት የሚባለው ደግሞ ህንፃዎችንና መሬትን ያካትታል፡፡ በሌሎችም ሀገራት የንብረት ግብር ማስከፈል የተለመደ ነገር ነው፡፡
የዚህ ግብር አይነት አዎንታዊ ጎኑ የመንግስትን ገቢ ይጨምራል፡፡ አሁን የተያዘው በጀት በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ 1.9 ትሪሊዮን ብር በጀት መንግስት ከዬት ሊያመጣው ይችላል፣ ግብር ካላስከፈለ፡፡ ስለዚህ የመንግስትን የገቢ ምንጭ ያሰፋል፡፡ ይህ አንድ ጠቀሜታ ነው፡፡ ሌላው ጠቀሜታ ደግሞ፣ አካሔዱ አንዳንድ ንብረቶችን ወደ ምርት ሊቀይራቸው ይችላል፡፡ ስራ ፈትቶ የነበረ ንብረት፣ ምርታማ እንዲሆን ያደርጋል ይህ እርምጃ፡፡
ለምሳሌ የማይከራይ ህንፃ፣ ተጀምሮ የቆመ ህንፃ፣ ተዘግቶ የተቀመጠ ቤት፣ ታጥሮ የተቀመጠ መሬት ካለ፣ የንብረት ግብር መክፈል ስትጀምር ጥቅም ላይ እንዲውል ይደረጋል ማለት ነው፡፡ ንብረቱ መንቀሳቀስ ይጀምራል ማለት ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ተመሳሳይ የመሬት ስፋት ላይ ያረፉ የተለያየ መጠን ያላቸው ህንፃዎች፣ ለመንግስት የተለያየ ግብር እንዲከፍሉ/እንዲያስገቡ ይደረጋል፡፡ በዚህም በኩል ጥቅም አለው፡፡
አንድ ትልቅ ህንፃና አንድ ትንሽ ህንፃ እኩል የመሬት ስፋት ላይ ቢያርፉም፣ የሚሰጡት የአገልግሎት ብዛትና አይነት ግን የተለያየ ነው፡፡ ከመንግስት የሚያገኙት አገልግሎትም እንደዚሁ የተለያየ ነው፡፡ ስለዚህ ግብሩ የሚከፈለው፣ በመጠናቸውና በሚሰጡት አገልግሎት ልክ ነው እንጂ ባረፉበት መሬት መጠን አይሆንም፡፡ እንደ ንብረቱ ትልቅነት ነው ግብር የሚከፈለው፡፡
በእኛ ሀገር የንብረት ግብር አዲስ ስለሆነ የሚያስከትለው ተፅዕኖ ይኖራል፡፡ የህንፃና የቤት ኪራይ ሊጨምር ይችላል፡፡ እነዚህ ንብረቶች ላይ ግብር ስለሚጣል ማለት ነው፡፡ እንደዚሁም መኪና ላይ ግብር ስትጨምር፣ ቀጥታ የትራንስፖርት ዋጋ ይጨምራል፡፡ አንዳንድ ሸቀጦች ላይም ዋጋቸው ሊጨምር ይችላል፡፡
በህንፃዎችና በመኪኖች ላይ ኪራይ ሲጨምር፣ የሸቀጦች ዋጋ ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ ይፈጥራል፡፡ ህንፃዎቹን ተከራይተው የሚሰሩ ነጋዴች፣ በትራንስፖርት የሚያጓጉዙ ነጋዴዎች የንብረት ግብሩ እነሱ ላይ ተፅዕኖ ስለሚኖረው፣ በሸቀጦች ላይና በሚሰጡት አገልግሎት ላይ ዋጋ ይጨምራሉ፡፡ ተፅዕኖው ህብረተሰቡ ላይ ያርፋል፡፡
መንግስት ግብር መሰብሰብ አለበት፣ ትክክል ነው፡፡ ግን እዚህ ጋ መነሳት ያለበት ጥያቄ፣ በሰበሰበው ግብር ለህብረተሰቡ ምን ያህል አገልግሎት ይሰጣል የሚለው ነው፡፡
ከማህበረሰቡ ወስዶ፣ ለማህበረሰቡ የሚሰጠው አገልግሎት በቂ ነው ወይ የሚለው መታየት አለበት፡፡ መንግስት በሰበሰበውን ግብር ለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት ይሰጣል ወይ የሚለው በአግባቡ መታየት አለበት፡፡
ህዝቡ በሀገሪቱ ከአንዱ ጫፍ ወደ ሌላው ጫፍ ተንቀሳቅሶ እንዲሰራ የሚያስችል የሰላም ዋስትና ይሰጠዋል ወይ የሚለው መታየት አለበት፡፡ እኔ ለመንግስት በሰጠሁት ግብር፣ ይህን አገልግሎት እንዲሰጠኝ ነው የምመኘው፣ የምፈልገው፡፡
መንግስት ይህን ግብር እያስከፈለ፣ ህብረተሰቡ ደግሞ እንደልቡ ቀንም ሆነ ማታ ተንቀሳቅሶ እንዲሰራ የሚያስችል ሁኔታ መፍጠር አለበት፡፡
ህዝቡን አላሰራ ያለውን የሰላም እጦት፣ አላሰራ ያለውን ቢሮክራሲ እንዲሁም ሙስናውን መቀነስና ማስወገድ አለበት፡፡ በከፈልነው ግብር ልክ የተሻለ አገልግሎት ቢሰጠን መልካም ነው፡፡ ካልሆነ ግን፣ ህብረተሰቡ እንደ ልብ ተንቀሳቀሶ የማይሰራበት ሁኔታ እያለ ይህንን ግብር መጨመር ማለት ዝም ብሎ ተጨማሪ ጫና መፍጠር ነው፡፡
በመንግስት ኢንቨስትመንት ለማህበራዊ ልማት ቅድሚያ ቢሰጥ ጥሩ ነው፡፡ የመዝናኛ ስፍራዎች እየተሰሩ ናቸው፡፡ ግን እኔ እየራበኝ በዚህ ስፍራ ላይ ተዝናና ብትለኝ እንዴት ይሆናል፡፡ ህብረተሰቡ እቤቱ ውሀና መብራት ሳይኖረው፣ መንገድ ላይ ውሀና መብራት ቢያይ ምንድነው ትርጉሙ፡፡ ይህንን ማህበራዊ ልማት ልትለው አትችልም፡፡ መንግስት ኢንቨስት ሲያደርግ ይህ ለህብረተሰቡ ቅድሚ የሚሰጠውና ቀጥተኛ ጥቅም የሚያመጣ ነውን ብሎ መጠየቅ አለበት፡፡
የመንግስት ኢንቨስትመንት ከህዝቡ ቀጥተኛ ጥቅም ጋር መያያዝ አለበት፡፡ እያንዳንዱን ኢንቨስትመንት ከማህበራዊ ጠቀሜታ አኳያ ሳይሆን ከፖለቲካዊ ጥቅም አኳያ ብቻ የሚታይ ከሆነ አስቸጋሪ ነው " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamliyAA
@tikvahethiopia
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ስለ #ኢትዮጵያ 🇪🇹 ምን እያሉ ነው ?
ከሀገራቸው ጉዳይ ይልቅ ስለ ሰው ሀገር ጉዳዮች ሰፊ ጊዜ ወስደው በመናገርና በመተንተን የሚታወቁት የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትላንት ምሽት በሀገራቸው ብቸኛው ቴሌቪዥን በተላለፈ ቃለ መጠይቅ #የኢትዮጵያን ስም ደጋግመው ሲያነሱ ታይተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ከወራት በፊት በነበራቸው ቃለ መጠይቅ ከሀገራቸው ጉዳይ ይልቅ ስለ ኢትዮጵያ እና ቀጠናው ጉዳይ ትንታኔ ሲሰጡ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም። በወቅቱም ኢትዮጵያ ስሟን እያነሱ ለተናገሩት ነገር ሁሉ በቀጥታ አንዳችም ምላሽ ሳትሰጣቸው በዝምታ አልፋቸዋለች።
ትላንት በነበራቸው ቃለ መጠይቅ ደግሞ ንዴትን በቀላቀለ ሁኔታ በማይመጥኑ ቃላት የኢትዮጵያን ስም ሲያነሱ ነበር።
በተለይም ኢትዮጵያ ያነሳችውን የባህር በር ጥያቄ ሲያጣጥሉት ነው ያመሹት።
የኢትዮጵያን የወደብ እና የባህር በር ጥያቄ " የህጻን ጨዋታ ነው፣ ማሳሳቻ ነው፣ የረከሰ ውሸት ነው ፣ የውስጥ ጉዳይ ማዳፈኛ ነው ፣ ጀርባው የተባበሩት አረብ ኤሜራት የወደብ ማስፋፋት አጀንዳ ነው " የሚሉ ቃላቶችን በመጠቀም ኢትዮጵያን ለማጣጣል ሞክረዋል።
ኢትዮጵያ የባህር በርን ጉዳይ አለም አቀፍ አጀንዳ ማድረጓን ተከትሎ በርካታ ሀገራት ለጥያቄዋ ድጋፍ ማድረጋቸውም ፕሬዝዳንቱን እንዳላስደሰተ የሚጠቁም ንግግርም ሲናገሩ ነበር።
" ፈረንሳይ ከኛ ጋር ናት፣ አሜሪካ ፣ ኤማራት፣ አውሮፓ ህብረት ከኛ ጎን ናቸው ማለት ጭንቅ እንጂ የድል መንገድ አይደለም " በማለት " ኢትዮጵያውያን የውስጥ ችግራችሁን ፍቱ " ሲሉ ተደምጠዋል።
በኢትዮጵያ በኩል ሀገራቸው ላይ የጦርነት ስጋትና ዛቻ እንዳለ በማመላከትም " እራሳችንን እንጠብቃለን " ሲሉ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ለባሕር ስትል ኤርትራንም ሆነ የትኛውንም ጎረቤት ሀገር የመውጋት አንዳችም ፍላጎት እንደሌላት በተደጋጋሚ ማሳወቋ ይታወሳል። ነገር ግን የባህር በር ጉዳይ ህልውናዋ መሆኑን ለዓለም ህዝብ አስረግጣ ተናግራለች።
ሌላው ፕሬዜዳንቱ ኢትዮጵያ ተመድ ሄዳ ከሳናለች (ክሱ ፦ ድንበር አካባቢ አሁንም የኤርትራ ጦር ግፍ እየፈጸመ ስለመሆኑ) " ያሉም ሲሆን " ክሱ አስነዋሪና አሳፋሪ ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።
ስለ ፕሪቶሪያ ስምምነትም ሲያነሱ ነበር።
ገና የትግራይን ጦርነት ያስቆመው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሲፈረም ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት እንዳሻከረች በይፋ የሚታወቅ ቢሆንም " ኤርትራን ከመክሰሳችሁ በፊት የፕሪቶሪያን ውል ተግብሩ ፤ የውስጥ ችግራችሁን መፍታት አስቀድሙ ፤ ለምን ስምምነቱ በቅን ልቦና አልተተገበርም ለምን ፋኖ ላይ ጦርነት ከፈታችሁ ? " የሚል ንግግርም ተናግረዋል።
ሌላው የፖለቲካ ፓርቲዎች የሌለባት ፣ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የማይታወቅባት ኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያን በተመለከተ ንግግራቸው " በኢትዮጵያ መታየት ጀምሮ የነበረው የለውጥ ተስፋ ጨልሟል ፤ የፖለቲካ ፓርቲ ብሎ የለም " የሚል ንግግር አሰምተዋል።
ያለአንዳች ተቀናቃኝ ከ30 ዓመት በላይ ኤርትራን እየገዙ ያሉት ኢሳያስ አፈወርቂ እንደ ሁል ጊዜው የትላንት ምሽቱ ቃለ ምልልሳቸው ስለ ሀገራቸው ጉዳይ ሳይሆን ስለ ኢትዮጵያ እንዲሁም ስለ ሌሎች ሀገራት ጉዳይ በመተንተን ነው ያለፈው።
ከዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ተነሳሽነት በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ሰላም እንዲወርድ ከተደረገ በኃላ የትግራይን ጦርነት ያስቆመው የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እስኪፈረም ድረስ ኢትዮጵያን እና አስተዳደሯን ሲያሞካሹ እንደቆዩ በአደባባይ የሚታወቅ ሀቅ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamliyMekelle
@tikvahethiopia
ስኬት ባንክ በበጀት አመቱ አጠቃላይ የካፒታል መጠኑን 9.3 ቢሊዮን ብር አደረሰ!
ስኬት ባንክ በ2024/25 በጀት ዓመት አፈፃጸም እና 2025/26 ዕቅድ ላይ ከሐምሌ 18 -19/2025 የሁለት ቀናት ጉባኤ አካሂዷል፡፡
በውይይቱ ላይ እንደተገለፀው በ2024/25 በጀት ዓመት የባንኩ አጠቃላይ ካፒታል 9.3 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን 19.2 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ሀብት አስመዝግቧል፡፡
ባንኩ ብር 7.6 ቢሊዮን ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ የቻለ ሲሆን በዚህም ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 2.7 ቢሊዮን ብር ገቢ በማስመዝገብ ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማግኘት ችሏል።
የስኬት ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳምጠው አለማየሁ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት ባንኩ በጀት ዓመቱን በስኬት መጠናቀቁን ገልፀዋል፡፡
በአብዛኛዎቹ የሥራ አፈፃፀም መለኪያዎችም የላቀ አፈፃፀም መመዝገቡን በማንሳት፤ የባንኩን ስኬታማ ጉዞ በማስጠበቅ በእንዱስትሪው ተወዳዳሪ ሆኖ ለመስራት የሚያስችል የአምስት (5) ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ በመንደፍ ወደ ስራ የገባ ሲሆን ከተለያዩ የሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገር ከሚገኙ ተቋማት ጋር በቀጣይነት አብሮ ለመስራት የሚያስችል ስትራቴጂካዊ ስምምነቶችን እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
በሌላ በኩል ስኬት ባንክ የማህበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት አንፃር በተለያዩ ጊዜያት ሰፊ ስራዎችን የሰራ ሲሆን በበጀት ዓመቱም ከ56 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አበርክቷል፡፡
በመጨረሻም በ2024/25 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ዲስትሪክቶች፣ ቅርንጫፎች እና ሰራተኞች የዋንጫ፤ የምስክር ወረቀት እና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
ስኬት ባንክ የስኬትዎ መሰረት!
#OFC
የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ መጀመሩን የህዝብ ግንኙነት ፅ/ቤቱ በላከልን መረጃ ገለጸ።
" በአገሪቱ ላይ የተደቀነውን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የፀጥታ ቀውስ ለመገምገም እና የፓርቲውን የወደፊት አቅጣጫ ለመቀየስ የሚያስችለውን ወሳኝ ስብሰባ ነው " ብሏል።
ዛሬ ስብሰበው በፓርቲው የውስጥ አቅም ግንባታና ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ላይ ያተኮረ እንደነበር አመልክቷል።
የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የፓርቲውን አመራርና ድርጅታዊ ብቃት ለማጠናከር ልዩ ሥልጠናዎችን እንደወሰዱና ሥልጠናው በፍጥነት በሚለዋወጥና ፈታኝ በሆነው የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ የኦፌኮን የወደፊት አቅጣጫ ለመቅረፅ ያለመ እንደሆነ ገልጿል።
ነገ ደግሞ ውይይቱ ትኩረት " በኦሮሞ ሕዝብ፣ በኢትዮጵያና በሰፊው የአፍሪካ ቀንድ ክልል ላይ በተደቀኑት ከባድ ፈተናዎች ላይ ይሆናል " ብሏል።
" በአጀንዳው ውስጥ በዋናነት የተካተቱት ጉዳዮች በቀጠለው ጦርነትና ማኅበረሰቡን ባወደመው ከፍተኛ የፀጥታ እጦት፣ በመንግሥት የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም የተባባሰው ከባድ የኢኮኖሚ ችግር፣ የተንሰራፋው የወጣቶች ሥራ አጥነት እና ስር የሰደደው ሥርዓታዊ ሙስና ናቸው " ሲል ገልጿል።
በእነዚህ ውይይቶች ማዕከላዊው ጉዳይ ፓርቲው ለመጪው የ2018 አገራዊ ምርጫ ያለው ስትራቴጂ እንደሆነ አመልክቷል።
" ኦፌኮ ነፃ፣ ፍትሐዊ እና እምነት የሚጣልበት ምርጫ በማካሄድ እውነተኛ የዲሞክራሲ ሽግግርን ለማረጋገጥ መንግሥት እንደ ቅድመ ሁኔታ የፖለቲካ ምህዳሩን እንዲከፍት ተጨባጭና ሊረጋገጡ የሚችሉ እርምጃዎችን እንዲወስድ ጥያቄዎቹን በይፋ ያቀርባል " ብሏል።
ስብሰባው ከተጠናቀቀ በኃላ ፓርቲው ይፋዊ መግለጫ እንደሚያወጣ ጽ/ቤቱ በላከልን መረጃ አሳውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamliyAA
@tikvahethiopia
" በቱርካና ሀይቅ ሙላትና መስፋፋት ምክንያት የዳሰነች ወረዳ ዋና ከተማ ኦሞ ራቴ ወደ ሌላ ቦታ ይዋቀራል " - ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ
ዛሬ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ በአርባ ምንጭ ከተማ ሲካሄድ ውሏል።
በዚሁ ጉባኤ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ከምክር ቤት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።
አቶ ጥላሁን ካነሷቸው ጉዳዮች አንዱ የዳሰነች ወረዳ ጉዳይ ነው።
በቱርካና ሀይቅ ሙላትና መስፋፋት ምክንያት የዳሰነች ወረዳ ዋና ከተማ የሆነዉ ኦሞ ራቴ ከተማ ወደ ሌላ ሊዋቀር መሆኑን አሳውቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በኢትዮጵያ ኬንያ ድንበር አከባቢ በሚገኘዉ የቱርካና ሀይቅና የኦሞ ወንዝ ሙላትን ተከትሎ ፦
- የወረዳዉ 66 በመቶ መሬት ፤ በርካታ ቀበሌዎች በዉሃ ሙላት መጥለቅለቁን
- ከ86 ሺህ ዜጎች በላይ መፈናቀላቸውን
- የወረዳዉን ዋና ከተማ ኦሞራቴን ጨምሮ ተፈናቃዮች የሚገኙባቸዉ መጠለያ ጣቢያዎች ስጋት ውስጥ መሆናቸውን የአካባቢውን ነዋሪዎች ዋቢ በማድረግ ተደጋጋሚ መረጃዎች ማጋራቱ ይታወሳል።
ይህ ጉዳይ ሰኔ 26/2017 ዓ/ም በነበረዉ 6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 42ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ቀርቦ ነበር።
ዛሬ ጉባኤውን ባካሄደው የክልል ም/ቤት ርዕሰ መስተሳደሩ፤ ዉሃ ሙላቱ ዋነኛው መንስኤ የቱርካና ሀይቅ የዉሃ መጠን መጨመርና መስፋፋት መሆኑን አንስተዋል።
በዳሰነች ወረዳ አከባቢ ያለዉ የዉሃ ሙላት የወረዳዉን ዋና ከተማ ኦሞ ራቴን ጭምር አደጋ ዉስጥ የጣለ መሆኑን ገልጸዋል።
" የኦሞ ራቴ ከተማን ሌላ ቦታ ለማስፈር ጥናት ተጠናቆ ወደ ትግበራ ሊገባ ስለሆነ የክልሉ ነዋሪዎች የአከባቢውን ነዋሪዎች በማቋቋም ረገድ የድርሻችሁን እንዲትወጡ " የሚል ጥሪ አቆርበዋል።
ተጨማሪ የክልሉ ምክር ቤት መረጃዎች : https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-07-19-2
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አርባ ምንጭ
#TikvahEthiopiaFamilyArbaminch
@tikvahethiopia
#Update
#EFFROT
እነ አዲስአለም ባሌማ (ዶ/ር) ፣ ደብረጽዮን ገ/ማካኤል (ዶ/ር) ጨምሮ 12 ሰዎች እግድ ተጣለባቸው።
በትእምት ኢንቨስትመንት ዙሪያ ቀደም ሲል በፍትህ ቢሮ " ህጋዊ አይደላችሁም " የተባሉ አካላት ፍርድ ቤትም እንዳገዳቸው የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል መረጃውን ልኳል።
የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት እግድ የጣለው በኣዲስ ኣለም ባሌማ (ዶ/ር) የሚመራውና ባለፈው የካቲት ወር 2017 ዓ.ም ጉባኤ አካሂዶ የትእምት አመራር ለሚለው አካል ነው።
የትግራይ ፍትህ ቢሮ ነባሩ የትእምት አመራር በፅሁፍ ያቀረበለት " በኣዲስ ኣለም ባሌማ (ዶ/ር) የሚመራው አካል ያካሄደው ጉባኤ 'ህገ-ወጥና ቅቡልነት እንደሌለው ይረጋገጥልኝ " የሚል ክስ ከ10 ቀናት ማጣራት በኋላ ተቀባይነት ማግኘቱ መዘገባችን ይታወሳል።
የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት ሀምሌ 11/2017 ዓ.ም በፃፈው ትእዛዝ በስም የጠቀሳቸው ኣካላት ተለዋጭ ቀጠሮ እስኪሰጥ ድረስ በትእምት ኢንቨስትመንት ስም ማንኛውም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ የአግድ ትእዛዝ ጥሎባቸዋል።
ተከሳሾቹ እነማን ናቸው ?
1. ኣረጋዊ ገ/ሚካኤል(ዶ/ር)
2. ጀነራል ክንፈ ዳኘው
3. ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)
4. ኣብራሃም ተኸስተ (ዶ/ር)
5. ወ/ሮ ኪሮስ ሓጎስ
6. አምባሳደር ሃይለኪሮስ ገሰሰ
7. ፃድቕ ኪ/ማርያም (ዶ/ር)
8. አቶ ሰናይ ካሓሰ
9. ኮ/ል ካሕሳይ ተኽሉ
10. ወ/ሮ ሸዊት አዲሱ
11. አቶ አታኽልቲ ገ/ሂወት
12. አምባሳደር አዲስ አለም ባሌማ (ዶ/ር)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamliyMekelle
@tikvahethiopia
#ሴጅ_ማሰልጠኛ_ኢስቲትዩት
የሶስት ወር የበይነ መረብ (Online) ስልጠናዎች ሐምሌ 28/2017 ዓ.ም ይጀመራሉ።
የስልጠናዎቹ ዓይነት:
👉 Advanced Graphic, Video Editing, Motion Graphic and Digital Marketing
👉 Computer Programming and Database
👉MERN Stack Website and Mobile Application Development
👉Modern Accountancy (ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ)
👉 Import and Export
👉 Research Methods and Analysis
👉 Animation and Visual Effect
👉 Artificial Intellegence and Data Science
👉 Journalism
👉 Interior Design
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያናs ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram sage_training_institute">Tiktok Linkedin
ንብተራ ኦንላይን
• ነባር ደንበኛችን ከሆኑ አሁኑኑ የንብ ሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያን "update/upgrade" ያድርጉ፣
• አዲስ ደንበኛችን ከሆኑ ደግሞ መተግበሪያውን በማውረድ አቅራቢያዎ ወደ ሚገኝ ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉና የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሁኑ፣
***
ይሠሯል ከልብ እንደ ንብ!
#Nib #nibmobilebanking #NibQR #nib #nibtera #nibbank
Facebook / Instagram / linkedin / nibinternationalbank6204">X / nibinternationalbank6204">Youtube / nibinternationalbank">Tiktok / Website
#Update
ነዋሪነታቸው እንጦጦ ማርያም በተለምዶ ' ሀሙስ ገበያ ' የሆኑ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መኖሪያ ቤት ላይ የመብራት ፖል ተንጋዶ መተኛቱን በመጠቆም በክረምቱ ንፋስና ዝናብ ጉዳት ሳይደርስ በፊት የሚመለከታቸው አካላት እንዲያስተካክሉላቸው ትላንት ጠቁመው ነበር።
ጥቆማው የደረሰው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለሞያዎቹን በመላክ ጥገና አደርጎ ማስተካከሉን አገልግሎቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቋል።
" ለህብረተሰቡ እንዲሁም ለሚዲያችሁ ምስጋና እናቀርባለን፡፡ በቀጣይም በአገልግሎታችን ላይ ለሚሰጡን ጥቆማዎችና ቅሬታዎች በወቅቱ ለመፍታት እንሰራለን " ሲል ገልጿል።
ጥቆማውን ያደረሱ የአካባቢው ነዋሪዎች ዛሬ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለሙያዎች መጥተው ችግሩን ማስተካከላቸውን ገልጸው ምስጋናን አቅርበዋል።
ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፤ ከጋርመንት ወደ ጀሞ 1 መሄጃ መንገድ ላይ ' ዘመን ማደያ ' አካባቢ በመኪና የተገጨ እና በክረምቱ ዝናብና ንፋስ ቢወድቅ ጉዳት የሚያደርስ ኮንክሪት ፖል ጥቆማ በደረሰ ቀን እስከ ምሽት 4 ሰዓት በመስራት መቀየሩ ይታወሳል።
#EthiopianElectricUtility
#TikvahEthiopiaFamliyAA
@tikvahethiopia