ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
#Update
አ/አ ከጋርመንት ወደ ጀሞ አንድ ሲኬድ መብራት ተሻግሮ (ቫርኔሮ የመኖሪያ መንደር አካባቢ) ዘመን ማደያ ጋር የመብራት ኮንክሪት ፖል ለመውደቅ ጫፍ ላይ መድረሱን በመጠቆም መፍትሔ ይፈለግለት ሲሉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች መጠየቃቸው ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በደረሰው መረጃ መሰረት ይህንን ፖል የመቀየር ሥራ በምሽት እየተሰራ ይገኛል።
" ባለሞያዎቻችን አሁንም እዛው ሳይት ናቸው " ሲል ጥገናው ምሽቱን እየተከናወነ መሆኑን የገለጸልን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፥ ፖሉ ተበልቶ ሳይሆን በመኪና ተገጭቶ ጉዳት ደርሶበት እንደነበር መረጃውን አጋርቶናል።
@eeuethiopia
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
" አንድ ካህንና ወንድሙ፤ ሁለት ሰዎች ናቸው ታግተው የተወሰዱት። አንድ አባት እስከ ልጃቸው ተገድለዋል " - የወረዳው ቤተ ክህነት
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ጀጁ ወረዳ ሶኮራ ቀበሌ የ"ሸኔ" ታጣቂ ቡድን በአንድ ቤተሰብ አባላት የግድያ እና እገታ ጥቃት መፈጸሙን የወረዳው ቤተ ክህነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ቤተ ክህነቱ የሆነውን ሲያስረዳ፣ " ሁለት ሰዎች ተገድለዋል፤ ትላንት 3 ሰዓት ከሩብ ላይ ነው ጥቃቱ የተፈጸመው ዛሬ የሟች አባትና ልጅ ቀብር ተፈጽሟል። ካህንና ምዕመን ወንድማማቾች ታግተው ተወስደዋል፤ የተወሰዱትም የሟች ወንድም ናቸው " ሲል ተናግሯል።
" አንድ ካህንና ወንድሙ፤ ሁለት ናቸው ታግተው የተወሰዱት። አንድ አባት እስከ ልጃቸው ተገድለዋል " ብሎ፣ ታጋች ካህን የሰኮራ ኪዳነ ምህረት አገልጋይ መሆናቸውን ገልጿል።
ቤተ ክህነቱ፣ " ህዝቡ ሁሌም በልቅሶ ነው፤ ሁሌ መገደል ነው ማን ይደርስለታል " ሲልም በአካባቢው በተደጋጋሚ የሚፈጸምን ጥቃት አስከፊነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቷል።
" ታጣቂ ቡድኑ 3 ሰዓት ይመጣል፤ ምሽት 11 ሰዓት ይመለሳል፤ በሌሊትም የፈለገውን ይፈጸሰማል" ብሎ " መንግስት የህዝቡ ድምጽ እንዲሰማና ህዝቡን እንዲጠብቅ አሳስቧል።
" መንግስት ቢደርስ ጥሩ ነው በወረዳው ከ2014 ዓ/ም ጀሞሮ ያለማቋረጥ ነው ግድያ እየተፈጸመ ያለው። ህዝቡ እየተፈናቀለ ነው፤ ተፈናቅሎም የሚገባበት የለም። ይህ የሆነው መንግስት ሃይ ባለማለቱ ነው " ሲልም ወቅሷል።
እናት ፓርቲ ባወጣው መግለጫ፣ በበዞኑ ሶኮራ ቀበሌ ሐምሌ 4/2017 ዓ/ም አባትና ልጅ በአሰቃቂ ሁኔታ እንደተገደሉ ገልጾ፣ " የሟች ወንድሞችና የአጥቢያው አገልጋይ ካህን ቄስ አድማሱ ጌታነህና ወገኔ ጌታነህ ታፍነው የተወሰዱ ሲሆን፣ የደረሱበት አልታወቀም " ሲል አስታውቋል።
" ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ የሚጠራው ኃይል በዞኑ በሁሉም አካባቢ በሚባል ደረጃ እየተንቀሳቀሰ ከፍተኛ ሰቆቃ የሚፈጽም ሲሆን፣ ከፌዴራሉም ሆነ ከክልሉ መንግሥት በኩል ነገሩን ከማድበስበስ ያለፈ እስካሁን ይህ ነው የሚባል እርምጃ ሲወስዱ አልታየም። ይህም ለሌላ ጥርጣሬ የሚጋብዝ ነው " ብሏል።
" ፓርቲያችን ግድያውን በጽኑ ያወግዛል፤ ታፍነው የተወሰዱ ካህንና ወንድማቸው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁ ይጠይቃል " ሲል ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#EFFORT
" ነባሩ ቦርድ ህጋዊ ነው ፤ በትእምት ስም የተካሄደው የምክር ቤት ጉባኤ ህጋዊ አይደለም " የሚል ውሳነ መሰጠቱ ተሰማ።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ታማኝ ምንጮች በላኩት መረጃ ነባሩ የትእምት ኢንቨስትመንት አመራር " ህገ-ወጥ የምክር ጉባኤ አካሂዶ ህገ-ያልተከተሉ አመራሮች መርጦ በተቋሙ ላይ የጀመረው ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ይታገድልኝ " ሲል ለክልሉ የፍትህ ቢሮ ያቀረበው ክስ ተቀባይነት አግኝቷል።
" በስራ ላይ ያለው ህጋዊ የትእምት ኢንቨስትመንት አመራር ነኝ " የሚል አካል ለፍትህ ቢሮ ያቀረበው ክስ ምን ይመስላል ?
በአቶ ቴድሮስ ሓጎስ የሚመራው የትእምት ባለ አደራ ቦርድ አመራር " በትእምት ስም የተካሄደው የምክር ቤት ጉባኤ ህገ-ወጥ ነው ፤ በጉባኤው የተመረጠ በኣብራሃም ተከስተ (ዶ/ር) የሚመራ ቦርድ በተቋሙ ላይ እያካሄደ የሚገኘው እንቅስቃሴም ህገ-ወጥ መሆኑ ተጣርቶ ይታገድልኝ " ሲል ለፍትህ ቢሮ አቤታቱ አቅርቧል።
ሦስት አጣሪ አባላት ያሉት ኮሚቴ በማቋቋም ላለፉት 10 ቀናት የቀረበለት አቤቱታ ሲመረምር የቆየው የፍትህ ቢሮ " በኣብራሃም ተከስተ (ዶ/ር) የሚመራ ቦርድ ህጋዊ አይደለም " በማለት በትእምት ላይ የሚያደርገው እንቅስቃሴ እንዲያቆም የእግድ ውሳኔ ሰጥቷል።
" የትእምት ምክር ቤት ባለፈው የካቲት 2017 ዓ.ም ባካሄደው ጉባኤ መርጦኛል " በሚል በመንቀሳቀስ ላይ ያለውና የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ በየነ መክሩ ህጋዊ ርክክብ ባላካሄዱበት ሁኔታ በላያቸው ላይ አዲስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ለመቅጠር በሚድያዎች እስከማስነገር የደረሰው በኣብራሃም ተከስተ (ዶ/ር) የሚመራው አካል " ህጋዊ አይደለህም " የሚል የፍትህ ቢሮ ውሳኔ ያከብር ይሆን ? የብዙዎች ጥያቄ ነው።
ባለፈው መጋቢት 2017 ዓ.ም በተፈጠረው የፓለቲካ ቀውስ ምክንያት የቀድሞ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከትግራይ መውጣታቸው ተከትሎ የትእምት ኢንቨስትመንት ዋና ስራ አስፈፃሚና የባለ አደራ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ በየነ መክሩና አቶ ቴድሮስ ሓጎስ ከክልሉ ውጪ ናቸው።
የትእምት ዋና ስራ ስፈፃሚ በየነ መክሩ በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ላዛ ትግርኛ ለተባለው ሚድያ ከአዲስ አበባ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ " ህገ-ወጥ ቡድኑ በሃይል ካስቀመጣቸው አመራሮች የተደረገ ርክክብ የለም ፤ ዋና ስራ አስፈፃሚና ቦርድ የነበረው ነው ያለው " ማለታቸው ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
" ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች አርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ተወስደው ሕክምና እየተደረገላቸው ይገኛል" - ፖሊስ
በጋሞ ዞን ቦረዳ ወረዳ የጅብ መንጋ በሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ።
የቦረዳ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ም/ኮማንደር ስምዖን ለንበቦ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ትናንት ምሽት 1 ሰዓት ገደማ የጅብ መንጋ በወረዳዉ ወይደ መላቶ ቀበሌ በሰዎች ላይ ጉዳት ሰንዝሮ ስድስት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።
በአከባቢው ከከተማ በቅርብ ርቀት ጥብቅ ደኖች መኖራቸውን የገለፁት ፖሊስ አዛዡ ጅቦች በጫካዉ ዉስጥ እንዳሉ ቢታወቅም እስካሁን በሰዉ ላይ ጉዳት አድርሰው እንደማያውቅና የትናንት ምሽቱ ጥቃት ድንገተኛ እንደሆነ ገልጸዋል።
በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ስድስት ሰዎች ወደ አርባ ምንጭ ሆስፒታል ተወስደዉ ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን አዛዡ ገልጸው ማምሻዉን ጥንቃቄና ጥበቃ ሲደረግ ማደሩንና ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ የፀጥታ አባላት ከአከባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን አሰሳ እያደረጉ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahethiopia
#Tinsae #IDEXX
ትንሳኤ ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ኢንተርፕራይዝ ከአይዴክስ (IDEXX) ላቦራቶሪስ ጋራ በጋራ በመሆን የውሃ ጥራት መመርመሪያ መሳሪያዎች ላይ ያተኮረ ዎርክሾፕ ከሰሞኑን አካሂዶ ነበር።
ወርክሾፑ ላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት እና የግል ተቋማት ተሳታፊ እንደነበሩ ድርጅቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
" መሳሪያዎቹ እጅግ በጣም ቀላል፣ ጊዜ ቆጣቢና በቀላሉ በአጭር ጊዜ ስልጠና በቀላሉ ለመስራት የሚያስችሉ " ናቸው ያለ ሲሆን " በተለይ Tecta B4 እና Teta B6 የተባሉት መሳሪያዎች እጅግ ዘመናዊ ከእጅ ንኪኪ ውጪ የሆኑ፣ ባንድ ጊዜ አራት ወይም ስድስት ናሙናዎችን ለመመርመር የሚያስችሉና ውጤቱንም በኢሜል ለሚመለከተው አካል የመላክ አቅም ያላቸው " ናቸው ሲል ገልጧል።
" ይኼንን የመሳሰሉት መሳሪያዎች በስፋት ወደ ስራ በሚገቡበት ጊዜ የሀገሪቱን የንፁህ ውሃ አቅርቦት እና ተደራሽነት ከፍ በማድረግ በተለይም በውሃ ወለድ የሚመጡ በሽታዎችን በከፍተኛ ደረጃ የሚቀንሱ ይሆናሉ " ብሏል።
ትንሳኤ ኢንተርናሽናል ከአይዴክስ (IDEXX) በተጨማሪ ሀክ (HACH) እና ሌሎች አለማቀፍ የውሃ መመርመሪያ አምራች ድርጂቶች ጋር ብቸኛ አቅራቢ በመሆን የረጅም ጊዜ ልምድ እንዳለውና በዚህ ረገድ በሃገሪቱ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ላይ የራሱን አሻራ እያሳረፈ ያለ ተቋም መሆኑም አመልክቷል።
@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia
በፈጣኑ እና በማይቆራረጠው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ BET-WiFi ከቤት እንስራ ውጤታማ እንሁን!
#SafaricomEthiopia
ጥያቄያችን ካልተመለሰ ወደ ቤት አንገባም ያሉ ነዋሪዎች !
" መንግስት መጥቶ ጥያቄያችንን ካለመለሰልን ወደ ቤት ላለመመለስ ወስነን ሜዳ ላይ ተሰብስበናል " - ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ
" ሰሚ እስክናገኝ ወደ ቤታችን አንመለስም ! "
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ የዶሬ ባፋኖ አከባቢ ነዋሪዎች " በአዲስ የመዋቅር ጥናት እና ልማታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የወረዳዉ መንግስት እንዲያነጋግን ብንጠይቅም ተገቢዉን ምላሽ ባለማግኘታችን በአደባባይ ወጥተን ድምፃችንን ለማሰማት ተሰብስበናል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የአከባቢዉ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሀዋሳ ከተማ አዲስ የመዋቅር አደረጃጀት ጋር በተያያዘ የተናገሯቸው መረጃዎችን መነሻ በማድረግ ሕዝቡ የወረዳው መንግስት ምላሽና ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቋል።
ነገር ግን የሚያናግር አካል ባለመምጣቱ 18 የሚሆኑ የሀገር ሽማግሌዎች እና የአከባቢው ባለሃብቶችን ያካተተ የሕብረተሰቡ ተወካዮች ተሰይመዉ በየደረጃው የመንግስት አካላትን እንዲያነጋግሩ ቢላኩም ተገቢው ምላሽ ስላልተሰጣቸው ሕዝቡ ሜዳ ላይ ተሰብስቦ መዋሉን አስረድተዋል።
የህዝቡ መሰረታዊ ጥያቄ " ከሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ዶሬ ባፋኖ አከባቢ ያሉ አምስት ቀበሌያት በአዲስ መልክ ይዋቀራል በተባለዉ የሀዋሳ አንድ ክፍለ ከተማ ስር ተካተዋል " መባሉ ነዉ ያሉ አንድ አስተያየት ሰጪ " ይህ የወረዳዉን አቅም ያዳክመዋል የሚል ቅሬታ ሕዝቡ ዘንድ ፈጥሯል " ሲሉ ተናግረዋል።
" በዛሬዉ ዕለትም ' የሚያናግራችሁ የመንግስት አመራር ይመጣል ' ተብለን ቀኑን ሙሉ ብንጠበቅም እንደተባለው ባለመምጣቱ ሕዝቡ በነቅስ ወደ ወረዳ አስተዳዳሪዉ ቢሮ ሄዷል ' አመራሩ ተነጋግሮ ያነጋግራችኋል ' ተብለን ምላሽ ባለመምጣቱ ሕዝቡ ' የሚያነጋግረን የመንግስት አካል እስኪመጣ ወደ ቤታችን አንመለስም ' በማለት ምሽቱንም በአንድ ቦታ ላይ ተሰባስቦ ይገኛል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ ለማግኘት ባደረገዉ ሙከራ የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊን በስልክ አግኝቷቸው ነበር። ግን " የወረዳ አስተዳዳሪ አነጋግሩ " በማለታቸዉ ወደ አስተዳዳሪዉ የእጅ ስልክ ደጋግመን ብንደዉልም ምላሽ ማግኘት ባለመቻሉ ምላሻቸው ሳይካተት ቀርቷል።
ምላሻቸውን እንዳገኘን የምናካትት ይሆናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
“እስከ ወረዳ ድረስ ቡድን ተዋቅሮ ችግር ያለባቸው ግንባታዎች ተለይተዋል፡፡ ከተለዩት 2681ግንባታዎች 1157 ብቻ ናቸው ትንሹን መስፈርት የሚያሟሉት” - ባለስልጣኑ
➡️ከ2015 እስከ ሰኔ 24/2017 ዓ/ም በሥራ ላይ የ142 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተጠቁሟል!
የአዲስ አበባ ከተማ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ከ2015 እስከ 24/10/2017 ዓ/ም ድረስ በመዲናዋ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች 121 ወንዶች፣ 21 ሴቶች በድምሩ 142 ሰዎች በህንጻ ሥራ ላይ እያሉ በተለያዩ ምክንያቶች ህይወታቸው ማለፉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል፡፡
42 ወንዶችና 10 ሴቶች በድምሩ 52 በለሚኩራ፤ 15 ወንዶችና 2 ሴቶች በድምሩ 17 በንፋስ ስልክ፤ 15 ወንዶችና 2 ሴቶች በድምሩ 17 በቦሌ፤ 13 ወንዶችና አንዲት ሴት በድምሩ 14 ሰዎች በቂርቆስ፣ ቀሪዎቹ ደግሞ በሌሎቹ ክፍለ ከተሞች ህወታቸው ማለፉን የባለስልጣኑ መረጃ በዝርዝር ያስረዳል፡፡
ባለስልጣኑ ህንፃች አሁን ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ፣ “እስከ ወረዳ ድረስ ቡድን ተዋቅሮ ችግር ያለባቸው ግንባታዎች ተለይተዋል፡፡ ከተለዩት 2681ግንባታዎች 1157 ብቻ ናቸው ትንሹን መስፈርት የሚያሟሉት” ብሏል፡፡
ባለፉት አስር አመታት በአዲስ አበባ ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎች በስፋት እየተገነቡ እንደሚገኙ፣ ለአብነትም በ2017 ዓ/ም በከተማዋ 11 ሺሕ 748 አዳዲስና 12 ሺሕ 322 ነባር ግንጻዎች ክትትል እንደተደረገባቸው፣ ግንባታዎቹ ከ581 ቢሊዮን ብር በላይ ግምት እንዳላቸው የባለሥልጣኑ መረጃ ይገልጻል፡፡
በከተማዋ በግንባታ ሳይቶች ላይ በተደጋጋሚ የሚታዩ የአደጋ መንስኤዎች እና ስጋቶች ምንድን ናቸው?
-ከከፍታ ላይ መውደቅ
-የኤሌክትሪክ አደጋ
-የእቃ መውደቅ
-የግንባታ መዋቅር ችግር
-የሠራተኞች በቂ ስልጠና አለመውሰድ
-የግል ደህንነት መጠበበቂያ መሳሪያዎች ያለመጠቀም
-የቁጥጥር ችግር፣ የበጅት እጥረት
-ህግ የማስከበር ችግር ዋና ዋናዎቹ ናቸው ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ “በአስር አመት አማካኝ የኢንዱስትሪው እድገት 10%"፣ “በቀጥታና በተዘዋዋሪ በየዓመቱ በአማካኝ የሚፈጠረው የሥራ እድል 1.2 ሚሊዮን” መሆኑን የጠቀሰው ባለስልጣኑ፣ “በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ፈጣን ኢንዱስትሪው እድገት በሠራተኞች የሥራ ላይ ደንነነት ተመሳሳይ ለውጥና መሻሻል እየታየበት አይደለም” ብሏል፡፡
“አልሚዎች ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ፣ በአነስተኛ ወጭ ለመጨረስ በሚያደርጉት ጥረት የሥራ ላይ ደህንነት ትኩረት በመሆኑ አደጋና ጉዳት እየጨመረ ይገኛል” ብሎ፣ የኮንስትራክሽን እድገት በአጭር ጊዜና በዝቅተኛ ዋጋ ግንባታዎችን ለመጨረስ የሥራ ላይ ደህንነትን አቀናጅቶ መተግበር እንደሚገባ አሳስቧል።
(ዝርዝር መረጃ ከላይ የተያያዘ ሲሆን፣ ተጣለ የተባለውን ቅጣት የተመለከተ ተጨማሪ አለን)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
ባለንበት ሆነን ወርሃዊ የውሃ ፍጆታችንን በቀላሉ በቴሌብር በመክፈል ጊዜያችን መቆጠብ እንችላለን።
ቴሌብር ሱፐርአፕ ➡️ ክፍያ ➡️ የውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ➡️ ክፍያ
*127# ደውለን ወይም ቴሌብርን በስልካችን በዚህ ሊንክ https://bit.ly/telebirr_SuperApp ጭነን ስንመዘገብ እንዲህ ነን!
#ደንበኛ_ስንሆን_እንዲህ_ነን
#ስንመዘገብ_እንዲህ_ነን
#ስንጭን_እንዲህ_ነን
#ስናስጀምር_እንዲህ_ነን
#Ethiopia🇪🇹
ከዩቲዩብ ፣ ቲክቶክና ከሌሎች የዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር ሊጣል ነው።
በኢትዮጵያ ለ9 ዓመታት ስራ ላይ የቆየውን የገቢ ግብር አዋጅ ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ፣ ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ በሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር ለመጣል የሚያስችል ንዑስ አንቀጽ ተካቷል።
በታቀደው የአዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ መሰረት፣ ከማህበራዊ ሚዲያ የሚገኝ ገቢ ለምሳሌ ፦
- ከዩቲዩብ፣
- ፌስቡክ፣
- ኢንስታግራም፣
- ቲክቶክና ሌሎችም መድረኮች
- በኢንተርኔት ከሚሰራጩ መረጃዎች
- በኢንተርኔት ከሚፈፀሙ ግብይቶች፣
- ከስፖንሰርሺፕ ከመሳሰሉት የዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ ግብር እንደሚጣልባቸው በዝርዝር ያስቀምጣል።
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዉይይት እየተደረገበት የሚገኘዉ ይህ ረቂቅ አዋጅ ፤ እነዚህ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች በመደበኛነት የሚከናወኑ ከሆነ፣ የሚገኘው ገቢ በንግድ ስራ ገቢ ስር የሚመደብ ሲሆን፣ የንግድ ስራ ገቢ ግብርም የሚከፈልበት መሆኑን ይገልጻል።
ሆኖም፣ በአዋጁ የተቀመጡትን መስፈርቶች የማያሟላ ከሆነ፣ ገቢው " ሌሎች ገቢዎች " በሚለው ስር ተመድቦ ከጠቅላላ ገቢው ላይ 15% (አስራ አምስት በመቶ) ግብር እንዲከፈልበት ይደረጋል ይላል።
ከዚህ በተጨማሪም፣ ለዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ክፍያ የሚያመቻቹ መድረኮች ለእያንዳንዱ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪ የተከፈለውን ገንዘብ የሚያሳይ ሪፖርት ለታክስ ባለስልጣን የመላክ ግዴታ እንደሚኖርባቸው ያስቀምጣል።
ይህን ተከትሎም፣ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የማውጣት ፣ ገቢያቸውን የማስታወቅ እና ሌሎች የታክስ ከፋይ ግዴታዎችን የመወጣት ሃላፊነት እንደሚጠበቅባቸው ያስገድዳል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የካፒታል ጋዜጣ ነው። #CAPITAL
@tikvahethiopia
" በአነስተኛ ጀልባዎች ለመሻገር የሚደረጉ ሙከራዎች ከንቱ ይሆናሉ "- የዩናይትድ ኪንግደም ጠ/ሚ
ዩናይትድ ኪንግደም ከፈረንሳይ በአነስተኛ ጀልባዎች ወደ አገሪቱ የሚገቡ ስደተኞችን በሳምንታት ጊዜ ውስጥ አዲስ በተወጠነ እቅድ መሰረት መመለስ እንምትጀምር ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታመር መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
በእቅዱ መሰረት አገር ውስጥ የሚገቡ አንዳንድ ስደተኞች ወደ ፈረንሳይ ሲመለሱ፤ ዩናይትድ ኪንግደም ደግሞ ተመጣጣኝ ቁጥር ያላቸውን ጥገኛ ጠያቂዎች የደኅንነት ፍተሻ አድርጋ ትቀበላለች።
የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለሦስት ቀናት የሥራ ጉብኝት ለንደን ይገኛሉ።
መሪዎቹ በጋራ በሰጡት መግለጫ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ስታመር " በአነስተኛ ጀልባዎች ለመሻገር የሚደረጉ ሙከራዎች ከንቱ ይሆናሉ " ብለዋል።
እቅዱ በሳምንት እስከ 50 የሚደርሱ ሰዎች እንዲመለሱ እንደሚያደርግ የተዘገበ ቢሆንም፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን አሃዙን አላረጋገጡም።
" ለውጥ አምጪው " እቅድ የሰዎች ዝውውር ላይ የተመለደውን አካሄድ ለመስበር የሚያግዝ እና ውጤታማ ከሆነ በስፋት የሚሰራበት ነውም ብለዋል።
ሕገ-ወጥ ስደት " ዓለም አቀፍ ቀውስ፣ የአውሮፓ ሕብረት ቀውስ እና የሁለቱ አገሮቻችን ቀውስ ነው " ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
መረጃው የቢቢሲ ነው።
@tikvahethiopia
" ሦስት 5Lሚኒባሶች ናቸው የተወሰዱት ፤ ሦስት ሆነው ነበር ያደሩት አንዱ ጥበቃ አብሮ ጠፍቷል " - ባለንብረቶቹ
ትላንት (ረቡዕ ለሐሙስ) ከሌሊቱ 9 ሰዓት ገደማ ፓርክ ከተደረጉበት ሦስት 5L ሚኒባሶች እንደተወሰዱባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጹ ባለንብረቶች ተሽከርካሪዎቹን ያየ ሁሉ እንዲጠቁማቸው በአጽንኦት ተማጽነዋል።
ባለንብረቶቹ " ሦስት 5L ሚኒባሶች ናቸው የተወሰዱት፤ ሦስት ሆነው ነበር ያደሩት አንዱ ጥበቃ አብሮ ጠፍቷል። ሁለቱ 'ተኝተን ነበር' አሉ። ከተቀጠረ ሦስት ቀናት የማይሞላው ጥበቃ ነው ከተሽከርካሪዎቹ ጋር አብሮ የጠፋው " ሲሉ ሁነቱን አስረድተዋል።
" ጥበቃው የተቀጠረው በኤጀንሲ ነበር። ኤጄንሲው ተመሳጥሮ እንዳይሆን የሚል ጥርጣሬ አለን። ምክንያቱም ኤጀንሲው የተሟላ ዶክሜንት አልያዘም ጥቃውን ሲቀጥረው፤ ዋስትና አልያዘም 'መጣል' በሚል" ብለዋል።
አክለው፣ "ኮሚቴዎች ደግሞ 'አይቻልም' ብለው ሲመልሱ አማላጅ ፓሊስ ጠርቶ 'ፓሊሱ እኔ ኃላፊነቱን እወስዳለሁ፤ በሦስት ቀናት ያመጣል ይስራ' እንዳላቸው ነው ኮሚቴዎቹ የነገሩን። የኤጀንሲው ሰውም፣ ፓሊሱም፣ ሁለቱ ጥበቃዎችም ተይዘዋል" ነው ያሉት።
ሦስቱም ተሽከርካሪዎች ከአንድ ፓርኪንግ ከቆሙበት እንደተወሰዱ፣ የተወሰዱትም ቃሊቲ ቶታል ጨፌ ኮንዶሚኒየም እንደሆነ፣ አንዱ መኪና ኦሮ ኮድ 03 34021 መሆኑን ተናግረዋል።
ሌላኛው የጠፋው ተሽከርካሪ ኦሮ ኮድ 03 ኦሮ 41867 እንደሆነ፣ ከጠፉት ከሦስቱ አንዱ እንደተገኘ በዚህ ዘገባ ታርጋቸው የተገለጹት እንዳልተገኙ ገልጸው፣ ተሽከርካሪዎቹን ያየ በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች እንዲጠቁማቸው ተማጽነዋል።
የባለንብረቶቹ ስልክ ቁጥሮች 0912049042፤ 0965206720 ናቸው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አዲስ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ግብር
" የቤተክርስቲያን ወሳኝ አካል የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ሊመለከተው ይገባል " - አባቶች
➡️ የሃይማኖት ተቋማት ከተቋቋሙበት ዓላማ ባሻገር የገቢ ማስገኛ ሥራዎች ላይ ሲሳተፉ ታክስ መክፈል እንዳለባቸው መወሰኑ ይታወቃል !
ቤተ ክርስቲያን የተጨማሪ ገቢ ግብር መክፈል እንዳለባት በተላለፈ ውሳኔ ላይ ውይይት መደረጉን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገለጸች።
ውይይቱ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የተካሄደ ሲሆን፦
- ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣
- ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የደቡብ ምስራቅ ትግራይና የራያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣
- ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስአበባ እና የሐድያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣
- ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ ዩንቨርስቲ ፕሬዘዳንትና የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሊቀ ጳጳስ ተገኝተው ነበር።
ከመንግሥት በኩል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገቢዎች ቢሮ የሥራ ኀላፊዎች እና መጋቢ ታምራት የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሐፊ በውይይቱ ተካፍለዋል።
የሃይማኖት ተቋማት ከተቋቋሙበት ዓላማ ባሻገር የገቢ ማስገኛ ሥራዎች ላይ ሲሳተፉ ታክስ መክፈል እንዳለባቸው የሚደነግገውን አዋጅ ላይ በከተማ አስተዳደሩ የተጋበዙ የሥራ ኀላፊዎች ዝርዝር ማብራሪያ አቅርበዋል።
ከቤተክርስቲያን ወገን የተገኙ መሪዎችና የሥራ ኃላፊዎች ፤ ጉዳዩ ዙሪያ መለስ ውጤቶችን ከግምት ባስገባ መልኩ ተጨማሪ ምክክር ሊደረግበት የሚገባ መሆኑን አሳውቀዋል።
በተጨማሪ የቤተክርስቲያን ወሳኝ አካል የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ሊመለከተው እንደሚገባ መጠቆማቸውም ተገልጿል።
ውይይቱ ቀጣይነት እንዳለው ተጠቁሟል።
መረጃው የመንበረ ፓትርያርክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።
@tikvahethiopia
" የትልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክት ማሽን ጭነን ቅድሚያ ስጡን ብለን ብንጠይቅም የሚሰማን አላገኘንም ፤ ተሰልፈን መንገድ ላይ ለማደር ተገደናል " - አሽከርካሪዎች
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ቀደም ሲል በቤንዚን ላይ ብቻ ይስተዋል የነበረው ሰልፍ ከቅርብ ጊዜያት ወዲ በናፍጣ ላይ ጎልቶ መታየት የጀመረ ሲሆን ቲክቫህ ኢትዮጵያም አሽከርካሪዎች አነጋግሯቸዋል።
ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን የሚሰሩ የተለያዩ ማሽነሪዎችን ጭነዉ በነዳጅ ሰልፉ ላይ የነበሩ አሽከርካሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል " ማሽነሪዎቹ በየመንገዱ ባደሩ ቁጥር የሚሰራዉ ፕሮጀክት ከመጓተቱም በላይ የክረምት የጎርፍ ሙላት ፕሮጀክቱን ያበላቸዋል ይህን ለማደያ ባለሙያዎች ብንገልፅም ከሰልፉ ወጪ ለመቅዳት የንግድ ቢሮ ትዕዛዝ እንደሚያስፈልግ ነግረውናል " ብለዋል።
" በከተማ ሁሉም ማደያዎች ለመንግስት አምቡላንሶች እንጂ ለሌሎች የሕክምና ተቋማት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ቅድሚያ እየተሰጠ አይደለም " ያሉ ሌሎች አሽከርካሪዎች ደግሞ " ይህ ተገቢነት የለዉም " ብለዋል።
በአንድ ማደያ የናፍጣና ቤንዚን ረጃጅም ሰልፎች በተመሳሳይ ሰዓት መመደባቸዉ ለእግልታችን ሌላኛዉ ምክንያት ነዉ ያሉት በሰልፉ ላይ ያነጋገርናቸው አሽከርካሪዎች " የከተማ አስተዳደሩ ንግድ መምሪያ ጉዳዩን በአግባቡ መምራት አለመቻሉንና እንደዉም በተቃራኒው ምሳ ሰዓት ዘግቶ በመዉጣት ለሚፈጠሩ መጨናነቆች ምክንያት እየሆነ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።
" ተመዝግበዉ ያደሩ ናቸዉ " በሚል በየሰልፉ መሃል እንዲገቡ የሚደረጉ ተሽከርካሪዎች አሽከርካሪዎች እርስ በርስ እንዲጋጩ እያደረገ ስለመሆኑ አሽከርካሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" በነዳጅ ማደያዎች ሀዋሳ ከተማን የሚመጥን መስተንግዶ አላገኘንም " ሲሉም ወቅሰዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽና ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ የእጅ ስልክ ደጋግሞ ቢደውልም ስልክ ባለመነሳቱ ምላሽ ማግኘት አልተቻለም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
" በተማሪነትም ሆነ በቱሪስት ቪዛ ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ዜጎቻችን ከተፈቀደላቸው የቪዛ ቆይታ ጊዜ በላይ በአሜሪካ መቆየት በአሁኑ ወቅት ተቀባይነት የሌለውና ከፍተኛ ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑን መገንዘብ ያሻል " - አምባሳደር ነብያት ጌታቸው
ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የአሜሪካ ቪዛ የያዙ ኢትዮጵያውያና የሌላ አገር ዜግነት ያላቸው ዜጎች ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ከቆዩ ቅጣት እንደሚከተላቸው የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ይህን ያሉት ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነው።
በዚህም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአሜሪካ መንግስት የቪዛና አገልንሎትና ኢምግሬሽን ጉዳዮችን በሚመለከት አዳዲስ አሰራሮችንና አካሄዶችን ይፋ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው ለዜጎች ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።
"በተማሪነትም ሆነ በቱሪስት ቪዛ ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ዜጎቻችን ከተፈቀደላቸው የቪዛ ቆይታ ጊዜ በላይ በአሜሪካ መቆየት በአሁኑ ወቅት ተቀባይነት የሌለውና ከፍተኛ ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑን መገንዘብ ያሻል" ሲሉ ተናግረዋል።
"ወደፊትም ለትምህርትም ሆነ ለጉብኝት ወደ አሜሪካ የመጓዝ እድል ያላቸው ዜጎች እነኝህን የተቀመጡ የቪዛ ቆይታ ጊዜዎች ካላከበሩ ለተለያዩ ችግሮች ሊጋለጡ የሚችሉ በመሆኑ ተገቢውን ጥንቃቄ እንደረግ ማሳሰብ እንፈልጋለን" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ወደ አሜሪካ ለመጓዝ፣ ቪዛ ለማግኘት ለአሜሪካ ኤምባሲ ማመልከቻ የሚያስገቡ ከመንግስትም ሆነ ከግል ተቋማት የሚመነጩ ሰነዶች ትክክል ስለመሆናቸው እያረጋገጡ እንዲሆን አሳስበዋል።
በአጠቃላይ የአሜሪካ መንግስት የቪዛ አገልግሎትን የኢምግሬሽን ጉዳዮችን የሚያወጣቸውን አዳዲስ አሰራሮች በመከታተል ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል።
አምባሳደሩ፣ "ከአሜሪካም ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ የሚያደርጉ የአሜሪካ ፓስፓርት የያዙ ኢትዮጵያውያን፣ የሌሎች ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች የኢትዮጵያን ቪዛ ለማግኘት ወደ አገራችን ሲመጡ ከተፈቀደላቸው የቆይታ ጊዜ በላይ በሀገራችን ሕግ መሠረት ቅጣት የሚያስከትል በመሆኑ ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግ ለማሳሰብ እንወዳለን" ሲሉም ተናግረዋል።
አምባሳደር ነብያት፣ "ይህ አሰራር የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ያልያዙትን ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ይጨምራል" ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvaEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" ባለቤቴንና አምስት ልጆቼን ነው ያጣሁት " - ተጎጂ አባት
➡️ " ጥቃቱን ያደረሱት ጽንፈኛ የሚባሉ በዚሁ በወሰን አከባቢ ሸምቀው ያሉ ታጣቂዎች ናቸው ! " - የአካባቢው ነዋሪ
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ቆንዳላ ቀበሌ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ 14 ሰዎች ተገደሉ።
ጥቃቱ ከትናንት በስቲያ ሃሙስ ሃምሌ 03 ቀን 2017 ዓ.ም. ምሽት ነው የተፈጸመው።
የታጠቁ አካላት በመደዳው አንድ መንደር ላይ አነጣጥረው የዘፈቀደ ጥቃት ማድረሳቸው ነው የተገለጸው፡፡
ብርሃኑ ሸምሰዲን የተባሉ ተጎጂ በጥቃቱ ሙሉ የቤተሰቦቻቸውን አባል አጥተዋል፡፡
ባለቤታቸውን እና አምስት ልጆቻቸውን ድንገት ከቤት በወጡበት አጋጣሚ አልቀው ማግኘታቸውን ተናግረዋል። አደጋው ዱብ እዳ እንደሆነባቸው በደከመና በሚቆራረጥ ድምፅ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ተናግረዋል።
" ምሽት አንድ ሰዓት ተኩል አከባቢ ነው ስድስት የቤተሰቤ አባላት በሙሉ የጨረሱብኝ፡፡ የሁለት ዓመት ጨቅላ ህጻንና ባለቤቴን ጨምሮ ሶስት ወንድ ልጆቼን እና ሁለት ሴት ልጆቼ አልቀውብኛል " ብለዋል።
" የአምስት ዓመት፣ የ11 እና 12 ዓመት እንዲሁም የ14 ዓመት እድሜ ልጆች ናቸው ያለቁብኝ፡፡ ገዳዮች ከኔ የተለየ ቂም የላቸውም፤ #ጽንፈኛ የሚባሉ በአከባቢያችን የደቡብ ክልል አዋሳኝ አከባቢ ሸምቀው ያሉ መሆናቸው ብቻ ነው የተነገረን " ሲሉ አክለዋል።
" በመንደራችን በመደደው በተወሰደብን ድንገተኛው ጥቃት እንደ እኔ ሙሉ ቤተሰቦቻቸው አልቆባቸው ባይጎዱም እንደ እኔ ሁሉ ዉዶቻቸውን ያጡ አራት ቤቶች ግድም ጎረቤቶቼም አሉ " ብለዋል።
ጥቃቱ ድንገተኛና ምንም በማያውቁ ንጹሃን ላይ ያነጣጠረ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ይህ ሁሉ አደጋ በመላው ቤተሰቦቻቸው ላይ የደረሰው እሳቸው ድንገት ለጉዳይ ወደ ጎረቤት ብቅ ባሉበት ሰዓት መሆኑን ገልጸዋል።
" ጥቃቱ የተፈጸመው ሁሉም በማታው ቤቱ ቁጭ ባለበት ሰዓት ነው፡፡ አንዳንዶቹ እራት እየበሉ ሌሎችም ቴሌቪዢን እየተመለከቱ ባሉበት ነው ድንገት ገብተውባቸው የጥይት እሩምታ በማዝነብ ህጻናት እና ሴት ሳይሉ ያገኙትን ሁሉ የገደሉዋቸው " ብለዋል።
" የተኩሱን ድምጽ ሰምቼ ከነበርኩበት ጎረቤት ቤት ልወጣ ስል በግድ አስቀመጡኝ፡፡ በኋላ ሮጬ ቤቴ ስደርስ ግን አንድም የተረፈልኝ የለም፤ ስድስት የቤተሰቤ አባላት በሙሉ አልቀው ጠበቁኝ " ሲሉ ሀዘናቸው መሪር መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
ጥቃቱ የተፈጸመበት ቦታ የምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳን ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ጋር በምታዋስን ቆንዳላ ቀበሌ ዳርጌ ከተማ ነው ያሉት የአይን እማኝየአከባቢው ነዋሪ፤ በተለይ ይህ ጥቃት የተፈጸመው በከተማዋ ዳር ላይ በሚገኙ መንደሮች ነው ብለዋል፡፡
ለደህንነታቸው ስባል ስማቸውን ሳይገልጹ አስተያየታቸውን ብቻ ያጋሩን እኚህ አስተያየት ሰጪ፤ " በሰዓቱ ሁላችንም በዚያችው ከተማ ውስጥ ነበርን፡፡ ጥቃቱ በደረሰበት በዚያ አከባቢ የከባባድ መሳሪያዎች ድምጽ ጨምር ስንሰማ ስለነበር ተኩሱ ሲቆም 2፡30 አከባቢ ወደ ቦታው ስናመራ ብዙ አስከሬን አገኘን " ብለዋል።
" የተጎዱትን ወደ ሆስፒታል ብንወስዳቸውም ሆስፒታልም ደርሰው ያለፉብን አሉ፡፡ አሁን ባጠቃላይ 14 ሰዎች ስሞቱ ሶስት ሰዎች በከባድ ሁኔታ ሆስፒታል እየታከሙ ይገኛሉ " ሲሉ ገልጸዋል።
" ሰላማዊ ሰዎች ላይ ነው በር እየከፈቱ እየገቡ የአንድ ዓመት ህጻን ጨምሮ አዛውንትና ሴት ሳይሉ ያገኙት ሁሉ ላይ ጥይት አርከፍክፈው የወጡት " ብለዋል፡፡
በወቅቱ የከተማዋን ጸጥታ የሚያስጠብቁ የፀጥታ አካላት በቦታው እንደሌሉ የገለጹት አስተያየት ሰጪው ነዋሪ ጥቃቱን ያደረሱ ታጣቂዎች ወደ 40 የሚጠጉ ናቸውም ብለዋል፡፡
" የፀጥታ መዋቅር በሰዓቱ ወደ ሌላ ስፍራ ተንቀሳቅሶ ነበር ነው የሚባለው፡፡ ይህን ክፍተት በመጠቀም ይመስላል ታጣቂዎቹ ዘልቀው ገብተው እንዲህ ያለ ዘግናኝ ጥቃት ያደረሱት፡፡ ጥቃቱን ያደረሱት ጽንፈኛ የሚባሉ በዚሁ በወሰን አከባቢ ሸምቀው ያሉ ሲሆን ከተማ ውስጥ ገብተው ጥቃቱን ያደረሱም በቁጥር ከ35 እስከ 40 እንደሚሆኑ ከጥቃቱ የተረፉ ነግረውናል፡፡ መሰል ድርጊቶች በዚህ ቀበሌና አከባቢው ተደጋግሞ የተፈጸመ ሲሆን አሁንም ልቆም አልቻለም " ሲሉ የችግሩን አሳሳቢነት ገልጸዋል፡፡
አከባቢው አሁን ተረጋግቶ እንደሆነ የተጠየቁት አስተያየት ሰጪው ነዋሪ፤ " ለአሁኑማ ምን መረጋጋት አለ፤ ሰው የሞተበትን ቀብሮ ሀዘን ተቀምጠዋል፡፡ የህግ አካላትም መጥተው ' ድርጊቱን የፈጸመውን አካል እያደንን ነው ' ብለዋል " ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።
መረጃው የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።
@tikvahethiopia
#ዙሪያ
ንግድ ላይ የተሰማሩ ዜጎች ይዘዋቸው የምናያቸውን በርካታ ፖስ ማሽኖች በማስቀረት ወደ አንድ የተቀናጀ ስርአት እንዲገቡ ያስችላቸዋል የተባለ ሲስተም ይፋ ተደርጓል።
ኢትዮ ቴሌኮም፣ ከዳሽን ባንክ እና ኤታ ሶሉሽንስ በአጋርነት በጋራ በመሆን የቀረበው "ዙሪያ" የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲስተም በአስመጪና ላኪ፣ በማኑፋክቸሪንግ እና ችርቻሮ ንግድ ዘርፍ ለተሰማሩ ድርጅቶችና ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጣቸውን ለማዘመን ያግዛቸዋል ተብሏል።
"ዙሪያ" የኢ.አር.ፒ (ERP)፣ የፒ.ኦ.ኤስ (POS) እና ካሽ ሬጂስተር (Cash Register) አገልግሎቶችን በአንድ ላይ ለመስጠት የሚያስችል የቢዝነስ አውቶሜሽ ሶሉሽን የያዘ ሲስተም ነው፡፡
መተግበሪያው የተለያየ ንግድ ላይ የተሰማሩ ዜጎች ይዘዋቸው የምናያቸውን በርካታ ፖስ ማሽኖች በማስቀረት ወደ አንድ የተቀናጀ ስርአት እንዲገቡ የሚያስችል ነው።
"ዙሪያ" ሁሉንም የሀገር ውስጥና አለም አቀፍ ካርዶች መቀበል እንደሚችል የተገለጸ ሲሆን በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ኮሚሽን ዕውቅና እንደተሰጠው ይፋ በማድረጊያ ስነ ስርአቱ ላይ ተገልጿል።
ይህ ሲስተም የሂሳብ ምዝገባ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ነጋዴዎች የሚያንቀሳቅሱትን ሃብት ለማስተዳደር እና ማንኛውንም የክፍያ መረጃዎች በአንድ ያካተተ ደረሰኝ ለማግኘት ያስችላል ነው የተባለው፡፡
አገልግሎቱን ለማቅረብ ኢትዮ ቴሌኮም የቴሌክላውድ (TeleCloud) መሠረተ ልማት በማቅረብ የተሳተፈ ሲሆን ለዚህ አገልግሎት የሚውለውን ማሽን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት በማመቻቸት ዳሽን ባንክ አስተዋጽኦ ማድረጉን ተነግሯል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" አካባቢው ላይ ያሉ ገበሬዎች ተነስተው የሚሰፍሩበት ቦታ ግንባታ በሰፊው እየተከናወነ ነው መስከረም ውስጥ ለማጠናቀቅ እየሰራን ነው " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ አቡሴራ አካባቢ አዲስ ለሚያስገነባው ግዙፉ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ 2,500 አባወራዎች እንደሚነሱ መገለጹ ይታወሳል።
3,500 ሔክታር መሬት ላይ የሚያርፈው አዲሱ የአየር ማረፊያ ስራ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አየር መንገዱ አሳውቋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በአሁኑ ሰአት ለ2,500 አባውራዎች መኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ መሆኑን እና በመስከረም ወር ለማስረከብ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ስለ አዲሱ አየር መንገድ እና በሃገር ውስጥ ያሉ መዳረሻዎችን ለማስፋት እየተሰራ ስላለው ስራ በዝርዝር ምን አሉ ?
" አካባቢው ላይ ያሉ ገበሬዎች ተነስተው የሚሰፍሩበት ቦታ ግንባታ በሰፊው እየተከናወነ ነው መስከረም ውስጥ ለማጠናቀቅ እየሰራን ነው እንደተጠናቀቀ ወደ ተሰራላቸው ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች ይዘዋወራሉ ስራቸውንም በአዲስ መልክ ይጀምራሉ።
ቦታው ሲለቀቅልን የግንባታ ስራ እንጀምራለን የአየር መንገዱ ዲዛይንም በብዙ አድቫንስ አድርጓል እየቆራረጥን በቅደም ተከተል ነው የምንሰራው የመጀመሪያውን ዙር ስራ ህዳር ውስጥ ለመጀመር እቅድ ይዘናል።
የሃገር ውስጥ በረራን ለማስፋት እና የአገልግሎት ጥራቱን ከፍ ለማድረግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት ጥቂት አመታት በርካታ ስራ ሲሰራ ቆይቷል።
ከስራዎቹ መሃል ዛሬ ላይ ያሉን የአውሮፕላን ጣቢያዎች ማሻሻል ነው የአውሮፕላን መንደርደሪያው ጥሩ ካልሆነ እሱን በአዲስ መልክ መስራት።
መንገደኞች የሚስተናገዱባቸው ተርሚናሎችም አንዳንዶቹ ደረጃቸውን ያልጠበቁ እና አሮጌ ፣ ወይም በቆርቆሮ የተሰሩ ነበሩ እነሱን እያፈረስን በዘመናዊ መንገድ እየሰራን ነው ሁሉንም በአንድ ጊዜ ስለማይቻል በቅደም ተከተል ነው የምንሰራው።
ባለፈው አንድ አመት ውስጥ ብቻ እንደ ጎዴ እና ጂንካ ያሉ 3 ተርሚናሎችን ሰርተን ስራ ላይ አውለናል።
አገልግሎቱን ለማስፋትም አዳዲስ ኤርፖርቶችን በመስራት ላይ እንገኛለን በአሁኑ ሰአት ስድስት ተርሚናሎች እየተሰሩ ይገኛሉ አንዳንዶቹ ለምረቃ ደርሰዋል።
ለምሳሌ ፦ ያቤሎ መንደርደሪያው አልቋል በሁለት ወር ውስጥ በረራ እምጀምራለን እሱ 23ኛው የሃገር ውስጥ መዳረሻችን ይሆናል ማለት ነው።
ነገሌ ቦረና፣ መቱ ፣ሚዛን አማን እና ደብረ ማርቆስም በመገንባት ላይ ናቸው በሚመጡት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃል " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ጥቆማ
(ለሚመለከተው አካል - አዲስ አበባ)
" በሰውና መኪና ላይ ወድቆ ጉዳት እንዳይደርስ መፍትሄ ይፈለግለት ! "
" ይህ በቪድዮው ላይ የምትመለከቱት የመብራት ኮንክሪት ፖል ታቹ ተበልቶ አልቆ ለመውደቅ ጫፍ ላይ ደርሷል። ከጎኑ ትራንስፎርመርንም አለ።
ቦታው ከጋርመንት ወደ ጀሞ አንድ ሲኬድ መብራት ተሻግሮ (ቫርኔሮ የመኖሪያ መንደር አካባቢ) ዘመን ማደያ ጋር ነው ሲሆን ብዙ ሰው የሚመላለስበት መኪናም የሚንቀሳቀስበት ነው።
ፖሉ ወድቆ በሰው እና በመኪና ጉዳት ሳያደርስ በፊት መፍትሄ ይፈለግለት። ወቅቱም ክረምት በመሆኑ ዝናቡና ንፋሱ ኃይለኛነውና ፈጣን መፍትሄ ይፈለግለት። " - ዮሴፍ (ከአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል)
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ሴጅ_ማሰልጠኛ_ኢንስቲትዩት
የሁለት ወር የጋዜጠኝነት የክረምት ስልጠና የፊታችን ሰኞ ሐምሌ 07/2017 ዓ.ም ይጀመራል።
በስልጠናው፦
👉 መሠረታዊ የጋዜጠኝነት መርሖች
👉 የመዝናኛ ፕሮግራም ጋዜጠኝነት፣ የፕሮግራም ዝግጅት እና ዶክመንተሪ ዝግጅት
👉 የሞባይል ጋዜጠኝነት እና YouTube Journalism አካቷል፡፡
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram sage_training_institute">Tiktok Linkedin
#SouthEthiopia
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የማሽንጋ ወንዝ በመሙላቱ በተከሰተ ጎርፍ የሁለት ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን የወላይታ ዞን አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኃላፊ አቶ ዳዊት ደሳለኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ወደ ገበያ እየሄዱ የነበሩ አራት አርሶአደሮችን የዉሃ ሙላቱ ወስዷቸዉ እንደነበር የገለፁት አቶ ዳዊት ሁለቱ በሕይወት መትረፋቸውን ሁለቱ ደግሞ ህይወታቸው ማለፉን ገልፀዋል።
በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች በመሬት ናዳ ሰዎች እንደሞቱ ተደርጎ እየተሰራጨ ያለዉ መረጃ ከእዉነት የራቄ ነዉ ያሉት ኃላፊዉ ከሰሞኑ በዞኑ በየትኛውም ቦታ በመሬት ናዳ የሞተ ሰዉ አለመኖሩን ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ፤ በዛው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ አሪ ዞን ሳላማጎ ወረዳ ዲሜገሮ ቀበሌ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ምሶሶ ለመትከል በቁፋሮ ላይ የነበሩ ሰራተኞች ላይ አፈር ተደርምሶ ሦስት ወጣቶች ወዲያውኑ መሞታቸውን የወረዳዉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዳጁ ጨነቀ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አደጋዉ የደረሰዉ በአከባቢው የከፍተኛ ኤሌክትሪክ መስመር ተሸካሚ ታዎር ለመትከል DCGG በተባለ ኮንትራክተር አማካኝነት በተቆፈሩ ጉድጓዶች የዝናብ ዉሃ መሙላቱን ተከትሎ ዉሃዉ በጄኔሬተር ፓንፕ እንዲወጣ ተደርጎ ሰራተኞች ግንባታ እየሰሩ በነበረበት የአፈር መደርመስ ተከስቶ እንደሆነ አስረድተዋል።
በአደጋው ሦስት ወጣቶች ሲሞቱ በሁለቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን አስታዉቀዋል።
የሦስቱ ወጣቶች አስከሬን በእስካቫተር ተቆፍሮ መዉጣቱንም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
ያለፈቃድ የግንባታ ዲዛይን ማስፋፊያ ለሚያደርጉ አካላት በየእርከኑ የ100 ሺሕ ብር ቅጣት ተጣለ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ባደረገው የቅጣት ማሻሻያ በሕንፃ ግንባታ ህግጋት መሰረት በተጣለው የህንፃ ደህንነትና ተያያዥ ቅጣት በተለያዩ ተግባራት ከ15 ሺሕ እስከ 100 ሺሕ ብር ቅጣት መጣሉን ገልጿል።
ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰው የባለስልጣኑ መረጃ እንዲሚያስረዳው፥ የማስፋፊያ ሥራ የዲዛይን ማሻሻያን ስለሚፈልግ፣ ያልተፈቀደ ግንባታ የዲዛይን ጥራት ስለሚጎድለው የመደርመስ አደጋ ስለሚያስከትል ያለፈቃድ የማስፋፋት ሥራ ማከናወን (በየእርከኑ) 100 ሺሕ ብር ያስቀጣል።
እንዲሁም፣ ጥራት ያለው ስካፎልዲንግ፣ ሾርኒንግና መሰል መሳሪያዎችን አለመጠቀም ለአደጋ የሚያጋልጥ መሆኑን የጠቀሰው ባለስልጣኑ፣ በግንባታ ወቅት እነዚህን መስፈርቶች ለማያሟሉ አካላት (በእርከን) 50 ሺሕ ብር ቅጣት መጣሉን አመልክቷል።
ቅጣቱ "በየእርከኑ" ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ባለስልጣኑ ሲያስረዳም፣ "ለምሳሌ አንድ G+10 ህንጻ 26 የክትትል እርከኖች ይኖሩታል፤ 26*50,000=1,300,000 ይሆናል" ሲልም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ያለተቆጣጣሪ ማሰራት ለአደጋ አጋላጭ በመሆኑ የግንባታ ስራዎችን ያለተቆጣጣሪ የሚያሰሩ አካላት (በየእርከኑ) 25 ሺሕ ብር እንደሚቀጡም ተጠቁሟል።
ስቶር፣ ልብስ መሸጫ፣ መመገቢያና ሌሎች የቅድመ ግንባታ መስፈርቶችን ሳያዘጋጁ ሥራ ለሚጀምሩ አካላት የ15 ሺሕ ብር፤ በሚሰጥ የማስታወቂያ ትዕዛዝ መሰረት ተረፈ ምርትን በወቅቱ ለማያነሱ 15 ሺሕ ብር ቅጣት መጣሉን የደረሰን የባለስልጣኑ መረጃ ያሳያል።
ሕጋዊ ተጠያቂነትን በተመለከተ የማማከር ኃላፊነትን በአግበባቡ አለመወጣት ከ5 እስከ 15 ዓመታት የእስራትና ከ30 እስከ 50 ሺሕ የገንዘብ፤ ደረጃውን ያልጠበቀ ግንባታ ማከናወን ከ5 እስከ 15 ዓመታት የእስራትና ከ50 እስከ 100 ሺሕ የገንዘብ ቅጣቶች መጣላቸው ተመልክቷል፡፡
እንዲሁም፣ ግባታውን በህዝብ ደህንነት አደጋ በሚጥል ሁኔታ ያከናወነ ከ5 እስከ 10 ዓመታት የእስራት እና ከ20 እስከ 50 ሺሕ የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልበት የተገለጸ ሲሆን፣ ጥፈተኛ ሆኖ የተገኘ አማካሪ/ሥራ ተቋራጭ ከ15 ዓመት እስከ ከፍተኛ የእስር ጊዜው ፈቃዱ ይታገዳል ተብሏል፡፡
(የቀድሞው እና የተሻሻለውን ቅጣት፤ የመፍትሄ ሀሳቦችን የያዘው የባለስልጣኑ መረጃ ከላይ ተያይዟል)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#AmazonFashion
ሙሉ ልብስ ሽያጭና ኪራይ የአመቱ የማጣሪያ ሽያጭና ታላቅ ቅናሽ ሙሉ ልብስ(ሱፍ) ሽያጭ ከ 12 ሺ -15 ሺ ብቻ፤ በርካታ አማራጭ ስላለን ለብዛት ፈላጊዎች ለሚዜዎች ለተመራቂ ተመራቂዎች በብዙ አማራጭ አለን። በተጨማሪም የሙሉ ልብስ ኪራይም በሌላኛው ብራንቻችን አለን።
አድራሻ: ፒያሳ downtown ህንፃ ምድር ላይ
☎️ 0919339250 / 0911072936 /0939721321
https://t.me/joinchat/AAAAAEc8iQJX1Zjgepjq1w
#Update
የእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል !
በእንስት ዘውዱ ሃፍቱ የጭካኔ የግድያ የተከሰሱት ተጠርጣሪዎች ጥፋተኞች ተብለው የፍርድ ውሳኔ ተላለፈባቸው።
ተከሳሾቹ ለፍርድ ውሳኔ ማቅለያ ይሆነናል በማለት " የቆየ ህመም አለብን " ቢሉም የመቐለ ዓይደር ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ሃኪሞች የምርመራ ማስረጃ " የቆየ ህመም የለባቸውም " ሲል ምላሽ ሰጥቷል።
የመቐለ ማእላዊ ፍርድ ቤት በእንስት ዘውዱ ሃፍቱ አሰቃቂ ግድያ የመጨረሻ የፍርድ ውሳኔ ውሎ ምን ይመስል ነበር ?
የተጠርጣሪ ጠበቆች ትናንት ሀምሌ 3 " ደምበኞቻችን የቆየ ህመም አለባቸው ይህንን ለማረጋገጥ የህክምና ማስረጃ ለአርብ ሀምሌ 4 እናቀርባለን " ብለው ነበር።
ፍርድ ቤቱ ይህን ተቀብሎ ለዛሬ የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት ቀነ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር።
ዛሬ አርብ ሀምሌ 4/2017 ዓ.ም ከመንግስት ሰራተኞች የስራ ሰዓት በፊት ቤተሰብ የሚገኙባቸው የሚድያና የሴቶች መብት ተቆርቋሪዎች በፍርድ ቤቱ በራፍ ደርሰው ተሰባስበዋል።
ተከሳሾች ለውሳኔ ማቅለያ ይሆነናል ብለው የጠየቁት የህክምና ማስረጃ የቆየ ህመም እንደሌለባቸው አረጋግጧል።
ዳኞችም ይህን ካረጋገጡ በኋላ በተከሳሾች ላይ ውሳኔ ሰጥተዋል።
አንደኛና ሁለተኛ ተከሳሾች ያሬድ ገብረስላሰ በላይ እና ኣንገሶም ሃይለማርያም በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።
በፍርድ ቤቱ ውሳኔ አለመርካታቸው የገለፁት አስተያየት ሰጪዎች የወንጀል ደርጊቱን ከማጠራት እስከ ምርመራና ውሳኔ ድረስ በችግሮች የተተበተበ እንደነበር በመግለፅ ማረሚያ ቤት የፍርድ ውሳኔውን በጥብቅ እንዲተገብረው ጠይቀዋል።
" የጭካኔ ግድያው የሞት ፍርድ ያሰጥ ነበር " ያሉ ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች ደግሞ " የተበዳይ ቤተሰቦች ወደ ቀጣዩ የፍርድ ቤት ይግባኝ ይጠይቁ " ብለዋል።
ከነሀሴ 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሀምሌ 4/2017 ዓ.ም የተጓዘው የእንስት ዘውዱ ሃፍቱ ግድያ በዚሁ ተቋጭቷል ሲል የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መረጃውን ልኳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ የእንስቷን ግድያ ከመነሻው እስከ ፍርድ ሂደቱ ሲከታተል ቆይቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
አዲሱ የዩትዩብ ሞኒታይዤሽን መመሪያ ምን ይዟል ?
ከፊታችን ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ዩትዩብ፤ ዩትዩብን ተጠቅመው ገቢ በሚያስገቡ ላይ ጥብቅ መመሪያ አውጥቷል።
መመሪያው ምን ይላል ?
- ከአሁን በኋላ ዩትዩብ ክፍያ የሚፈጽመው አዲስና የራሳቸው ፈጠራ ብቻ ለሆኑ ፤ በብዛት ወይም በድጋሚ በዩትዩብ ላይ ላልዋሉ ስራዎች ነው።
- ክፍያ የሚፈጸምላቸው ቪድዮዎች እውነት እና የራስ ስራ ላይ የተመሰረቱ ብቻ መሆን አለባቸው።
- አርተፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ተጠቅመው የሚሰሩ ሰዎች ክፍያ አይከፈላቸውም።
- በድምፅና ትንሽ የቪድዮ ስራ ብቻ ተጨማምሮባቸው የሚቀርቡ የሌላ ሰዎች ስራዎች ክፍያ አያገኙም።
- በተለያዩ ተንቀሳቃሽ ቪድዮዎች ወይም የሰው ቪድዮዎች ላይ reaction መስጠት እና የሰው ቪድዮዎችን እየሰበሰቡ ማቅረብ ከዩትዩብ ክፍያ ውጭ ይደረጋሉ።
- የራሳቸው ስራ ያልሆነ ቪድዮ ማለትም እዛው ዩትዩብ ላይ በሌሎች የተሰሩ ቪድዮ የሚያቀርቡ ሰዎች የራሳቸውን ሃሳብ እንዲጨምሩና እንዲሰሩ የሚጠየቁበት መንገድ ቢኖርም ያለማስጠንቀቂያም ሊታገዱ ይችላሉ።
ዩትዩብ በአዲሱ መመሪያው ኦሪጅናል ለሆኑ እና ሰዎች በራሳቸው ጥረት ለሰሯቸው ስራዎች ክፍያ ይከፍላል። ክፍያ ለማግኘት የራስን የፈጠራ ስራ ዩትዩብ ላይ መጫን ግዴት ይሆናል።
ዩትዩብ ይህን ወደማድረግ የገባው ሰዎች የራሳቸውን የፈጠራ ስራ እንዲሰሩ ለማበረታታ ነው።
ዩትዩብ ክፍያ ለመክፈል ከዚህ ቀደም ያስቀመጠው አስገዳጁ 1 ሺህ ሰብስክራይበር እንዲሁም 4,000 የዕይታ ሰዓት በ12 ወራት ውስጥ ማግኘት አሁንም እንደ ግዴታ ይቀጥላል ተብሏል።
#YouTube #TheVerge
@tikvahethiopia
💎 ትልቁ ይገባዎታል!
በፀሐይ ባንክ "ዳይመንድ የቁጠባ ሒሳብ" ተጠቃሚ ይሁኑ!
ከ 9.5% እስከ 10% የሚደርስ የወለድ መጠን የሚያስገኝ ልዩ የቁጠባ ሒሳብ!
እርስዎ በርትተው ይቆጥቡ፤ እኛ ዳጎስ ባለ የወለድ ምጣኔ እንደግፍዎታለን! አሁኑኑ የፀሐይ ባንክ "ዳይመንድ የቁጠባ ሒሳብ" ይክፈቱ!
ለበለጠ መረጃ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ የፀሐይ ባንክ ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ ወይም ወደ 921 ነጻ የጥሪ ማዕከላችን ይደውሉ፡፡
ፀሐይ ባንክ
ለሁሉ!
የፀሐይ ባንክ የቴሌግራም ገጽን ይቀላቀሉ 👇 /channel/tsehaybanksc
" አንድ ሃገር ለመብረር ፈቃድ ያስፈልጋል ያንን ፈቃድ ጠይቀን ሲፈቀድልን ነው የምንበረው " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቬትናም የሚያደርገውን የመጀመሪያውን በረራ በዛሬው ዕለት ምሽት ያስጀምራል።
አየር መንገዱ አፍሪካን ከ ኤዥያ ጋር ያገናኘው የዛሬ 52 አመት እ.ኤ.አ በ 1973 ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቻይናዋ ከተማ ሻንጋይ በመብረር እንደነበር የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ይፋ በማድረጊያ ስነ ስርአቱ ላይ ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤዢያ 27 መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን ወደ ቬትናም ሃኖይ ከተማ የሚያደርገው በረራ 28 ኛው መዳረሻው ይሆናል።
አቶ መስፍን " 190 በረራዎች በሳምንት ወደ ኤዢያ እናደርግ ነበር የአሁኑ በረራ በሳምንት ለ አራት ቀናት የሚከናወን በመሆኑ በአህጉሩ በሳምንት የምናደርገውን በረራ ወደ 194 ከፍ አድርገነዋል " ብለዋል።
ሃኖይ ለንግድ እና ለቱሪዝም የምትመረጥ መዳረሻ በመሆኗም የቀጥታ በረራ በመጀመሩ 120 የሚሆኑ አፍሪካውያን በዛሬው ምሽት ወደ ቬትናም ሃኖይ እንደሚጓዙ ተገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው " አየር መንገዱ በየጊዜው የሚጨምራቸው መዳረሻዎች በምን መስፈርት የተመረጡ ናቸው ? አፍሪካን እርስ በእርስ የማገናኘት ሥራስ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው ? " ሲል ጠይቋል።
ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው ምን ምላሽ ሰጡ ?
" ወደ አንድ ሃገር እና ከተማ የበረራ መስመር ከመክፈታችን በፊት የአዋጭነት ጥናት እናካሄዳለን።
አዋጭነት ማለት ገበያው አለ ወይ በረራ ብንጀምርስ በቂ መንገደኛ እናገኛለን ወይ የሚለው ላይ ጥናት እናካሂዳለን።
ያ ጥናት በቂ መንገደኛ አለ ሲለን በረራውን እንጀምራለን።
እድገት የሚመጣው አዳዲስ የበረራ መስመሮችን በመጨመር ወይም ባሉት ላይ የበረራ ምልልሱን በመጨመር ነው።
አፍሪካ ውስጥ በአሁኑ ሰአት በ 40 ሃገራት ወደ 61 ከተሞች እንበራለን።
ወደ ፊት እያየን የምንበርባቸው ሃገሮች ተጨማሪ ከተሞችን አዋጭ ሆነው ስናገኛቸው ፈቃዱን እንዳገኘን እንበራለን።
በተጨማሪም የማንበርባቸው ሃገሮችም ፈቃድ እንዳገኘን አዋጭነት እያየን እንበራለን በዚህ መንገድ አፍሪካ ውስጥ መዳረሻችንን እና የበረራ ምልልሱን እንጨምራለን።
አንድ ሃገር ለመብረር ፈቃድ ያስፈልጋል ያንን ፈቃድ ጠይቀን ሲፈቀድልን ነው የምንበረው " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba
ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ
@tikvahethiopia
#Update
የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት በእንስት ዘውዱ ሃፍቱ የግድያ ወንጀል ጉዳይ ላይ የመጨረሻ ያለውን ቀነ ቀጠሮ ሰጠ።
ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም በእስር የሚገኙ ተከሳሽ ተጠርጣሪዎች ለውሳኔ ማቅለያ የሚሆን የህክምና ማስረጃ እናቀርባለን ባሉት መሰረት ለዛሬ ሀምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።
ይሁን እንጂ ዛሬ ችሎት ላይ የቀረቡት የተከሳሽ ጠበቆች " የመቐለ ዓይደር ሰፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነገ አርብ ሀምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም የህክምና ማስረጃ ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቶናል " ብለዋል።
ፍርድ ቤቱም ይህን አድምጦና ተቀብሎ የመጨረሻ ቀነ ቀጠሮ ለነገ ሰጥቷል።
በእንስት ዘውዱ ሃፍቱ የግድያ ወንጀል ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል በሚል ዛሬ በመቐለ ማእከላይ ፍርድ ቤት የተበዳይና ተከሳሽ ቤተሰቦች ፣ በርካታ ሚድያዎች ፣ በሴት ጥቃት መከላከል ዙሪያ የሚሰሩ ስቪክ ማህበራት አመራሮችና አባላት ተገኝተው ነበር ።
ሁለት አመት ያስቆጠረው የእንስት ዘውዱ ሃፍቱ አሰቃቂ የግድያ ወንጀል ነገ ሀምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም የመጨረሻ መቋጫ የፍርድ ውሳኔ ያገኝ ይሆን ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የችሎቱን ውሳኔ ተከታትሎ ያቀርባል።
ቲክቫህ ኢትጵዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
#DStvEthiopia
ከ32 ቡድን 2 ብቻ ቀሩ! የዓለም ምርጡ ክለብ ማነው?
⏰ እሁድ ሀምሌ 6 ከምሽቱ 04፡00 ሰዓት
Chelsea vs PSG
📺 Channel 223 SS FIFA Club World Cup በጎጆ ፓኬጅ
⚽️ አንድም የጨዋታውን ደቂቃ እንዳያመልጥዎ ሁሉንም ጨዋታዎች በጎጆ ፓኬጅ ላይ በቻናል 223 ይመልከቱ! 📺✨
📣 አዲሱን የዲኤሲቲቪ ስጦታ እየተጠቀማችሁ ነው?
🎊 እስከ ሐምሌ 24 ድረስ ባሉት ቀናት በመረጡት የዲኤስቲቪ ፓኬጅ የአንድ ወር ሙሉ ክፍያ ሲከፍሉ ዲኤስቲቪ ያለተጨማሪ ክፍያ ከፍ ወዳለው ፓኬጅ ከተጨማሪ ቻናሎች ጋር በስጦታ ያገኛሉ!
ደንበኝነትዎን አሁኑኑ አራዝሙ ስጦታ ያግኙ!
⬇️
https://mydstv.onelink.me/vGln/xepsjmo7
ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው!
#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #FIFACWC
#USA #VISA
" የቪዛው የቆይታ ጊዜ ወደ ሦስት ወር አጥሯል ፤ በአንድ ቪዛ ተደጋጋሚ ወደ አገሪቱ መግባትም ተከልክሏል " - ኤምባሲው
የአሜሪካ ኤምባሲ ለኢትዮጵያውያን የሚሰጠው ቪዛ የቆይታ ጊዜ ወደ ሦስት ወር ማጠሩን አስታውቋል።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስደተኛ ባልሆኑ የቪዛ አመልካቾች ላይ ባደረገው የፖሊሲ ለውጥ ምክንያት ውሳኔው መተላለፉን ኤምባሲው ገልጿል።
በአዲሱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፖሊሲ መሠረት፤ " ከሐምሌ 1/2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለኢትዮጵውያን የሚሰጠው ቪዛ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል እና የሦስት ወር ቆይታ " እንደሚኖረው አስታውቋል።
ኤምባሲው ከሐምሌ 1/2017 ዓ.ም. በፊት የተሰጡ ቪዛዎች ባሉበት እንደሚቀጥሉ ገልጿል።
ለንግድ እና ለጉብኝት ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን የሚያገኙት ቪዛ "B1" እና "B2" በሚለው ምድብ ውስጥ ይካተታል።
እስካሁን በነበረው አሰራር በዚህ ምድብ ውስጥ የሚገቡ ተጓዦች የሚያገኙት ቪዛ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ነበር። በተጨማሪም የቪዛው የቆይታ ጊዜ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በተደጋጋሚ ወደ አገሪቱ እንዲገቡ ያስችል ነበር።
አሁን ይፋ የተደረገው ፖሊሲ የቪዛውን የቆይታ ጊዜ ወደ ሦስት ወር ከማሳጠር በተጨማሪ በአንድ ቪዛ ተደጋጋሚ ወደ አገሪቱ መግባትን ከልክሏል።
በአዲሱ ፖሊሲ ቪዛ የሚያገኙ ተጓዦች የቆይታ ጊዜ ባይጠናቀቅም እንኳ ከአሜሪካ ከወጡ በኋላ በዚያው ቪዛ ተመልሰው መግባት አይችሉም።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተለያዩ አፍሪካ አገራትን ቪዛ የቆይታ ጊዜን ወደ ሦስት ወራት ማሳጠሩን ትላንት ይፋ አድርጓል። ይህ ውሳኔ ከተላለፈባቸው ሀገራት መካከል ናይጄርያ እና ጋና ይገኙበታል።
#USEmbassyAddisAbaba #BBCAmharic
@tikvahethiopia