272588
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ስፖርት ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የስፖርታዊ መረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። በዚህ ቻናል ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ የስፖርት መረጃዎች ይዳሰሱበታል። ለመረጃ እና ማስታወቂያ +251926797469
“ ሊጉን 🏆 እንደምናነሳ እርግጠኛ ነኝ “ - ሚኬል አርቴታ
“ የቆመ ኳስ ለእኛ ወሳኝ ነው “
የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በዚህ የውድድር አመት “ አላማችንን እናሳካለን “ ሲሉ ለደጋፊው ቃል ገቡ።
ለደጋፊው መልዕክት ያስተላለፉት አርቴታ “ ደጋፊዎች ብሩህ ተስፋ እንዲኖራቸው ጥሩ እንዲያስቡ እና ቡድኑን በጋለ ስሜት እንዲደግፉ መንገር እፈልጋለሁ “ ብለዋል።
አክለውም “ በዚህ አመት አላማችንን እንደምናሳካ እርግጠኛ መሆኔን ለደጋፊዎች ማረጋገጥ እፈልጋለሁ “ ሲሉ ቃል ገብተዋል።
አርቴታ ስለ ቆመ ኳስ ምን አሉ ?
“ የቆመ ኳስ ለቡድኔ ወሳኝ ነገር ነው በቆመ ኳስ አጨዋወት ብዙ ልምምድ እናደርጋለን “ ሲሉ ሚኬል አርቴታ ተናግረዋል።
“ በአሁኑ ሰዓት የቆመ ኳስ ጨዋታዎችን ለማሸነፍ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው " ያሉት አርቴታ አሁን ላይ 33% ጎሎች የተቆጠሩት በእሱ ነው ብለዋል።
“ ለእያንዳንዱ ዋንጫ መፎካከር የምትፈልግ ከሆነ የቆመ ኳስ ላይ ምርጥ ( ' ማስተር ' ) መሆን አለብህ “ ሚኬል አርቴታ
@tikvahethsport @YisakAH
የአለም ዋንጫ ትኬት ዋጋ ንሯል !
ፊፋ የ 2026 አለም ዋንጫ የመጨረሻ ዙር ትኬት ሽያጭ መጀመሩን አስታውቋል።
ይሁን እንጂ በአለም ዋንጫ ትኬት ዋጋው ለይ የተደረገው ከፍተኛ ጭማሬ ደጋፊዎችን ቅር አሰኝቷል።
የፍፃሜ ጨዋታው የመጀመሪያ ደረጃ ትኬት ዋጋ በአሁኑ ሰዓት 10,990 ዶላር መድረሱ ተገልጿል።
የትኬቱ ዋጋ መጀመሪያ ላይ ተጠቅሶ ከነበረው 1,550 ዶላር በሰባት እጥፍ የበለጠ ሆኗል።
የደረጃ ሁለት ትኬት 7,380 እንዲሁም የደረጃ ሶስት 5,785 ዶላር መድረሱ ሲገለፅ ከዋናው ዋጋ በሁለት አጥፍ ከፍ ብሏል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የማህበራዊ ሚዲያ ኮንተንት ክሪኤተር ነዎት?
ከዩቲዩብ እና ከሌሎች ማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎች የሚላክልዎ የማረጋገጫ ደብዳቤ፣ የክፍያ ማስታወቂያ ወይም ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶች በአድራሻ እጦት ምክንያት አልደርስ ብሎት ተጨንቀዋል? አሁን ግን መፍትሄ አለ!
የኢትዮጵያ ፖስታ የ“Virtual P.O. Box” (ሳጥን አልባ የመልዕክት አገልግሎት) አካላዊ ሳጥን ሳያስፈልግ ቋሚ የፖስታ አድራሻ ይሰጥዎታል። ወደ እርስዎ የሚላክ ማንኛውም ደብዳቤ ወይም ሰነድ በዲጂታል መንገድ ተመዝግቦ ባሉበት ይደርስዎታል።
በዘመናዊ መፍትሄ ህይወትዎን ያቅልሉ!
🔹 የተረጋገጠ እና ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት
🔹 መልዕክቶችዎን በማንኛውም ቦታ እና በማንኛውም ሰዓት ማግኘት የሚያስችልዎ
🔹 ፈጣን ማሳወቂያ እና ቀላል አስተዳደር
ሁሉንም በአንድ መተግበሪያ በእጅ ስልክዎ!
ዛሬውኑ መተግበሪያውን ከአፕስቶር ወይም ከፕሌይ ስቶር በማውረድ አልያም በ app.ethio.post በመግባት በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ይመዝገቡ። መልዕክቶችዎን በዘመናዊ እና ቀላል መንገድ ያስተዳድሩ — አንድም አስፈላጊ መልዕክት እንዳይዘገይ!
ሀሳብ ወይም አስተያየት ካልዎት https://forms.gle/7yw6mcxAi9tK2ean6
ለበለጠ መረጃ በነጻ የስልክ መስመር 8536 ይደውሉልን ወይም በቴሌግራም @etpccsbot ያግኙን።
#Ethiopost #virtual po box
Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | ethiopostal">TikTok |
“ ፊፋ እና አሜሪካ ኪሳችንን እያለቡ ነው “ ለአለም ዋንጫ ቤቱን የሸጠ ደጋፊ
አስር የአለም ዋንጫ ውድድሮችን የታደመው ታዋቂ የእንግሊዝ ደጋፊ አንዲ ሚሎን የአለም ዋንጫ ወጪዎች መጨመርን ተችቷል።
“ ፊፋ እና አሜሪካ ልክ ባልሆነ መንገድ ሌሎችን እያለቡ ገንዘብ ለመውሰድ እያደረጉ ያሉት ነገር በጣም አሳፋሪ ነው “ ሲል ደጋፊው ተናግሯል።
አክሎም “ ለመኪና ማቆሚያ 132 ዶላር መጠየቅ ምን ይሉታል " ያለው ደጋፊው “ የትራንስፖርት ወጪም በአራት አጥፍ አሳድገዋል “ ብሏል።
“ እዛ ያለ ሁሉም ሰው ከእኛ ገንዘብ ለመውሰድ ጥረት እያደረገ ነው " ሲል ያለውን ቅሬታ ገልጿል።
ደጋፊው ውድድሩን በአሜሪካ ለመመልከት መኖሪያ ቤቱን መሸጡ ተገልጿል።
@tikvahethsport @YisakAH
ናይጄሪያ ከፖርቹጋል ጋር ልትጫወት ነው !
የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ከፖርቹጋል ጋር የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያደርግ የሀገሪቱ እግርኳስ ፌዴሬሽን አሳውቋል።
የአቋም መለኪያ ጨዋታው ሰኔ 3/2018 ዓ.ም እንደሚደረግ ተገልጿል።
ናይጄሪያ በተጨማሪ ከፖርቹጋል ከመጫወቷ በፊት ከፖላንድ ጋር የአቋም መለኪያ ጨዋታ ታደርጋለች።
ጨዋታዎች የት እንደሚካሄዱ ገና እንዳልታወቀ ተዘግቧል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የጣልያን ብሔራዊ ቡድን ሀላፊዎች ሊለቁ ነው !
በሶስት ተከታታይ አለም ዋንጫ ውድድር መሳተፍ የተሳናት ጣልያን በርካታ ለውጦች ልታደርግ መሆኑ ተገልጿል።
የጣልያን እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ጋብሬል ግራቪና ከሀላፊነታቸው ለመልቀቅ መወሰናቸው ተገልጿል።
አሰልጣኝ ጅናሮ ጋቱሶ እንዲሁ በቀጣይ ሰዓታት ከአሰልጣኝነት ለመልቀቅ ማሰባቸውን የጣሊያን መገናኛ ብዙሃን አስነብበዋል።
በተጨማሪም የብሔራዊ ቡድኑ መሪ ጂያንሉጂ ቡፎን ከሀላፊነት እንደሚለቅ ተገልጿል።
ጣልያን በቀጣይ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንቺኒን ለመቅጠር ጥሪ ማቅረቧ ተሰምቷል።
አዲስ ፕሬዝዳንት ለመሾም ጊዜ እንደሚፈልግ ሲገለፅ በብሔራዊ ቡድኑ ስር ነቀል ለውጥ እየተደረገ መሆኑ ነው የተነገረው።
@tikvahethsport @YisakAH
የፕሪሚየር ሊጉ ከፍተኛ ተካፋዮች እነማን ናቸው ?
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከፍተኛ ተከፋይ አሰልጣኞች ደረጃን አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በበላይነት ይመራሉ።
የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ወርሀዊ 1.92 ሚልዮን ዩሮ ያገኛሉ።
እነማን ከፍተኛ ተከፋይ ናቸው ?
1️⃣ ፔፕ ጋርዲዮላ :- 1.92 ሚልዮን ዩሮ ( ወርሀዊ )
2️⃣ ሚኬል አርቴታ :- 1.25 ሚልዮን ዩሮ
3️⃣ ኡናይ ኤምሬ :- 770,000 ዩሮ
ከፕሪሚየር ሊጉ ተጨዋቾች ከፍተኛ ክፍያ የሚያገኘው ኤርሊንግ ሀላንድ ሲሆን በ ወር 2.63 ሚልዮን ዩሮ ይከፈለዋል።
እነማን ከፍተኛ ክፍያ ያገኛሉ ?
1️⃣ ኤርሊንግ ሀላንድ :- 2.63 ሚልዮን ዩሮ ( ወርሀዊ )
2️⃣ ሞሀመድ ሳላህ :- 2 ሚልዮን ዩሮ
3️⃣ ቫን ዳይክ እና ካሴሚሮ :- 1.75 ሚልዮን ዩሮ
4️⃣ ቡካዩ ሳካ እና ፈርናንዴዝ :- 1.5 ሚልዮን ዩሮ ያገኛሉ።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የኢብራሂማ ኮናቴ የሊቨርፑል ቆይታ ?
ሊቨርፑል የኢብራሂማ ኮናቴን ኮንትራት ለማራዘም የሚያደርጉት ድርድር መሻሻል #አለማሳየቱ ተገልጿል።
ኢብራሂማ ኮናቴ ሊቨርፑል በአዲሱ ውል ሳምንታዊ ከፍተኛ የደሞዝ ክፍያ እንዲከፍለው መጠየቁ ተነግሯል።
ተጨዋቹ በክለቡ ይከፈለው ከነበረው ሳምንታዊ 150,000 ፓውንድ ከፍተኛ ጭማሬ ጠይቋል።
ሪያል ማድሪድ ኮናቴን ለማስፈረም ያለውን ፍላጎት ሙሉ ለሙሉ ያቆመ ሲሆን ወደ ዝውውሩ ይመለሳል ተብሎም አይጠበቅም።
የሎስ ብላንኮዎቹ ፍላጎት ማጣት ኢብራሂማ ኮናቴ አሻግሮ የሚመለከተው አማራጭ እንዳሳጣው ነው የተገለጸው።
በዚህም ምክንያት ኮናቴ በሊቨርፑል ይቆያል የሚል እምነት እንዳላቸው ለክለቡ መልበሻ ቤት ቅርብ የሆኑ ምንጮች አስነብበዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ቶተንሀምን መረከብ ለእኔ ትልቅ ክብር ነው “
ጣልያናዊው አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ በአዲሱ ክለባቸው ቶተንሀም ተገኝተው ስራቸውን በይፋ ጀምረው።
አሰልጣኙ ለደጋፊዎቹ ባስተላለፉት መልዕክት “ እዚህ በመሆኔ ደስተኛ ነኝ ፤ የእናንተ አሰልጣኝ በመሆኔ እኮራለሁ “ ብለዋል።
“ ቶተንሀምን መረከብ ለእኔ ትልቅ ክብር ነው “ ያሉት አሰልጣኙ “ በዚህ ትልቅ ክለብ ውስጥ ለረጅም ጊዜ መቆየት እፈልጋለሁ “ ብለዋል።
ጥሩ ያልሆነ የውድድር ዘመን እያሳለፈ የሚገኘው ቶተንሀም በሊጉ 17ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ጣልያን ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ ይገጥማታል !
የጣልያን ብሔራዊ ቡድን ለ 2026 አለም ዋንጫ ውድድር ማለፍ ሳይችል መቅረቱ አይዘነጋም።
በስፖርታዊ ውጤቱ ባሻገር በዚህ ምክንያት የጣልያን እግርኳስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚያጣ ተገልጿል።
ጣልያን ለአለም ዋንጫ ማለፍ አለመቻሏ ቢያንስ 3️⃣0️⃣ ሚልዮን ዩሮ እንደሚያሳጣት ተነግሯል።
የጣልያን እግርኳስ ፌዴሬሽን ፊፋ ቃል የገባውን 10.5 ሚልዮን ዩሮ የተሳትፎ ክፍያ ያጣል።
እንዲሁም ቡድኑ ለአለም ዋንጫው ባለማለፉ ከአዲዳስ ማግኘት የሚገባውን 9.5 ሚልዮን ዩሮ ለማጣት ተገዷል።
በተጨማሪም ከ ቁሳቁስ ሽያጭ እና አዳዲስ ስፖንሰሮች ሊያገኝ የነበረውን 10 ሚልዮን ዩሮ ማጣቱ ተዘግቧል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የጨዋታ ቀን 🇪🇹
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ከሳኦ ቶሜ አቻው ጋር የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን ያደርጋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዛሬው ጨዋታ አረንጓዴ ማልያ፣ ቢጫ ቁምጣ እና ቀይ ካሶተኒ ለብሶ ወደ ሜዳ ይገባል።
የመልስ ጨዋታው በድሬዳዋ ስታዲየም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ላይ ይጀመራል።
ጨዋታውን ግብፃዊው ዳኛ ሞሀመድ ማሩፍ መንሱር ከሌሎች ግብፃዊያን ዳኞች ጋር በመሆን ይመሩት።
በጨዋታው 10,000 ደጋፊዎች ኤንዲታደሙ ፍቃድ መሰጠቱን ተከትሎ ጨዋታው ለተመልካች ክፍት ይሆናል።
ጨዋታው በምን ይተላለፋል ?
ድሬ ቲቪ ጨዋታውን በቀጥታ ስርጭት እንደሚያስተላልፈው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አሳውቋል።
ሞሮኮ ላይ የተደረገው የመጀመሪያው ዙር ጨዋታ በኢትዮጵያ የ 3ለ0 አሸናፊነት መጠናቀቁ አይዘነጋም።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ብሔራዊ ቡድኑን የሚለቅ ተጨዋች የክለቡን አንድ ጨዋታ መቀጣት አለበት “ አግቦላሆር
“ አርሰናል ልክ አይደለም “
የቀድሞ እንግሊዛዊ የአስቶን ቪላ ተጨዋች ጋብሬል አግቦላሆር የአርሰናል ተጨዋቾች ብሔራዊ ቡድናቸውን እየለቀቁ መሄዳቸው “ ልክ አይመስለኝም “ ሲል ገልጿል።
“ እኔ በፕሪሚየር ሊጉ ሀላፊነት ቦታ ብሆን በዚህ ጉዳይ አዲስ ህግ አስተዋውቅ ነበር “ ሲል ጋብሬል አግቦላሆር ተናግሯል።
አክሎም “ ብሔራዊ ቡድኑን የሚለቅ ተጨዋች የክለቡን ቀጣይ አንድ የሊግ ጨዋታ እንዲቀጣ አደርጋለሁ “ ሲል ተደምጧል።
“ ይህ ህግ ቢወጣ እና ቢተገበር አንድም ተጨዋች ለቆ እንደማይወጣ አረጋግጥላችኋለሁ “ ሲል ጨምሮ ተናግሯል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ሁሉም ተጨዋቾች ለቀናት ከሜዳ ይርቃሉ " ቶማስ ቱሄል
የሶስቱ አናብስት አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ከብሔራዊ ቡድኑ የለቀቁ ተጨዋቾች ለተወሰኑ ቀናት ከሜዳ እንደሚርቁ ገልጸዋል።
“ ሁሉም ተጨዋቾች መጫወት ፈልገው ነበር “ ያሉት ቶማስ ቱሄል “ ነገርግን አደጋውን ተጋፍጦ ማጫወት ምክንያታዊ አይደለም “ ብለዋል።
ኖኒ ማዱኬ በብሔራዊ ቡድኑ ህክምና ቡድን መገምገሙን የገለፁት አሰልጣኙ “ ውጤቱ ከሚሰማው ስሜት የተሻለ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
ቶማስ ቱሄል አያይዘውም ቡካዩ ሳካ እና ዴክላን ራይስ ወደ ክለባቸው የተመለሱት ለጥንቃቄ እንደሆነ ገልጸው “ ሶስቱም ለተወሰኑ ቀናት ከሜዳ ይርቃሉ “ ብለዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ማድሪድ ከተማን እወደዋለሁ “ ኢንዞ ፈርናንዴዝ
አርጀንቲናዊው የሰማያዊዎቹ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኢንዞ ፍናንዴዝ ማድሪድ ከተማን እንደሚወደው ተናግሯል።
አንድ ቀን በማድሪድ ከተማ ስለመኖር አስቦ ያውቅ እንደሆነ የተጠየቀው ኢንዞ ፈርናንዴዝ “ አዎ “ ሲል ምላሽ ሰጥቷል።
“ ማድሪድ ከተማን ወድጄዋለሁ " ያለው ኢንዞ ፈርናንዴዝ ከአርጀንቲና ከተማ ቦነስ አይረስ ጋር ተመሳሳይነት አለው " ሲል ተደምጧል።
አስቶን ቪላ ላይ ቅጣት ምት ካስቆጠረ በኋላ ለምን ማልያውን እንዳወለቀ ሲጠይቅ “ ሌላ ክለብ መቀላቀል ይፈልጋል ተብሎ ሲነገር ነበር እዚህ ነኝ የሚል ምላሽ ለመስጠት ነው “ ብሏል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ የአፍሪካ ዳኞች ከአለም ምርጥ ዳኞች መካከል ይመደባሉ “ ፓትሪስ ሞትሴፔ
የአፍሪካ እግርኳስ የበላይ ካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ የአፍሪካ ዳኞች ከአለም ምርጦች ውስጥ ይመደባሉ ሲሉ ተናግረዋል።
“ የአፍሪካ እግርኳስ ዳኞች ከአለም ምርጥ ዳኞች መካከል ይመደባሉ “ ሲሉ ፕሬዝዳንት ሞትሴፔ ተናግረዋል።
አያይዘውም “ እነሱን በደንብ ማሰልጠን አለብን በደንብ ልንከፍላቸውም ይገባል “ ሲሉ ሀላፊነት መውሰድ አለብን በስኬታችን እርግጠኛ ነኝ ብለዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ጂያንሉጂ ቡፎን ከሀላፊነት ለቀቀ !
ታሪካዊው ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ቡፎን በጣልያን ብሔራዊ ቡድን የነበረውን ሀላፊነት በፈቃዱ መልቀቁን አሳውቋል።
ጂያንሉጂ ቡፎን ባለፉት ሁለት አመታት ውስጥ የጣልያን ብሔራዊ ቡድን መሪ በመሆን አገልግሏል።
“ አላማው ጣልያንን ወደ አለም ዋንጫ መመለስ ነበር ማድረግ አልቻልንም “ ሲል ቡፎን የስንብት መልዕክቱን አስተላልፏል።
የጣልያን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጅናሮ ጋቱሶ በተመሳሳይ ከሀላፊነታቸው እንደሚለቁ ይጠበቃል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የጣልያን ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ስራቸውን ለቀቁ !
የጣልያን እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ግራቪና በፍቃዳቸው ከሀላፊነት መልቀቃቸው ይፋ ተደርጓል።
በፕሬዝዳንቱ የመሪነት ጊዜ ጣልያን በሁለት አለም ዋንጫ ውድድሮች መሳተፍ ሳትችል ቀርታለች።
የጣልያን ብሔራዊ ቡድን የውጤት ማጣት የገጠመው በመሆኑ የሀላፊዎች ለውጥ አያደረገ ይገኛል።
ብሔራዊ ቡድኑ በአለም ዋንጫው አለመሳተፉን ተከትሎ የጣሊያን መንግሥት ፕሬዝዳንቱ ለቀው እንዲሄዱ ማድረጉ ነው የተነገረው።
እግርኳስ ፌዴሬሽኑ በቀጣይ ሰኔ ወር አዲስ ፕሬዝዳንት ለመምረጥ ድምፅ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ትጥቆችን ማቅረብ ብቻ አይደለም ስራችን፤ከድሎች ጀርባ እንቆማለን።
እጅግ አስደናቂ በሆነ የጨዋታ የበላይነት 4 ለ 0 አሸንፎ ለወጣው የቡሩንዲ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን፣ ይፋዊ የትጥቅ አቅራቢ እና አጋር በመሆናችን ታላቅ ኩራት ይሰማናል።
ይህ ከውጤትም በላይ ነው።
ማረጋገጫ ነው።
🇪🇹 የኢትዮጵያ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ገና "እያደገ ያለ" ብቻ አለመሆኑን፤ ይልቁንም በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ በፅናት እየተወዳደረ፣ የላቀ ብቃቱን እያሳየ እና እያሸነፈ መሆኑን በተግባር ያረጋገጠበት ማሳያ ነው።
ዋናው ፣ ማንነት፣ ጥራት እና ከፍተኛ ብቃት የሚገናኙበትን አዲስ የጥራት መለኪያ ይወክላል።
ዋናው ወደፊት»»»
🔗ማህበራዊ ገጾቻችን🔗
Instagram|Facebook |wanawsportswear">TikTok |X|WANAWSPORTSWEAR">Youtube
⭐️|#Wanaw #MadeInEthiopia #ProudlyEthiopian #AfricanExcellence #SupportLocal #EthiopiaRisingЧитать полностью…
ጣልያን የአውሮፓ ዋንጫ አዘጋጅነቷ ሊነጠቅ ይችላል !
ጣልያን የ 2031 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር እንድታዘጋጅ በአውሮፓ እግርኳስ ማህበር መመረጧ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ የዩኤፋ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሴፈሪን የውድድሩን አዘጋጅነት ከጣልያን ሊነጥቁ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።
“ መሰረተ ልማቶች ዝግጁ እንደሚሆኑ ተስፋ አደርጋለሁ “ ያሉት ፕሬዝዳንቱ “ ካልሆነ ግን ውድድሩ በጣሊያን አይደረግም “ ብለዋል።
ስለ ጣልያን እግርኳስ ውድቀት ያነሱት ሴፈሪን “ ዋናው የእግርኳሱ ችግር በእግርኳስ ፓለቲካ እና በባህላዊ ፖለቲካ መካከል ያለው ግንኙነት ነው “ ሲሉ ገልጸዋል።
ሁሉም ሰው ለህጉ ቢገዛ “ ጣልያን በፍጥነት የአለም እና አውሮፓ ሻምፒዮን መሆን ትችላለች “ ሲሉ ተደምጠዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ እኔ ያማልን ብሆን ወደ ስፔን አልመለስም “ ሲሶኮ
ፈረንሳዊው የቀድሞ የፒኤስጂ ተጨዋች ሞሀመድ ሲሶኮ ላሚን ያማል ወደ ስፔን ብሔራዊ ቡድን እንዳይመለስ መክሯል።
“ እውነት ለመናገር እኔ ላሚን ያማልን ብሆን ወደ ስፔን ብሔራዊ ቡድን አልመለስም ነበር “ ሲል ሲሶኮ ተናግሯል።
“ ያደረጉት ነገር በጣም የሚያሳፍር ነው “ ያለው ተጨዋቹ ያማል ይሄ አይገባውም ነበር ለሞሮኮ መጫወት ይችል ነበር ብሏል።
“ እሱ ስፔንን መርጧል ስፔን አሁን የአለም ምርጥ ተጨዋች አላት ፤ በጣም ያሳዝናል ማህበረሰባችን ወደኋላ ቀርቷል።"ሲሶኮ
@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ አስደናቂ ጊዜ አሳልፌ ተመልሻለሁ “ ዮኬሬሽ
ባስቆጠራቸው ወሳኝ ጎሎች ስዊድን ወደ አለም ዋንጫ እንድታልፍ የረዳው ቪክቶር ዮኬሬሽ ወደ ክለቡ አርሰናል ተመልሷል።
ቪክቶር ዮኬሬሽ በብሔራዊ ቡድኑ ያሳለፈውን ጊዜ “ በጣም አስደናቂ ነበር “ ሲል ገልጿል።
“ የዛ አካል በመሆኔ ደስተኛ ነኝ “ ያለው ቪክቶር ዮኬሬሽ “ የፈለግነውን ነገር አግኝተናል በአለም ዋንጫ ገብተናል ህልማችን እውን ሆኗል “ ብሏል።
ቪክቶር ዮኬሬሽ ለስዊድን ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች አራት ጎሎችን አስቆጥሯል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ሊቨርፑልን በሊጉ ማየት አያዝናናም “ ጄራርድ
የቀድሞ የሊቨርፑል ታሪካዊ ተጨዋች ስቴቨን ጄራርድ ሊቨርፑልን በሊጉ መመልከት አያዝናናም በማለት ተናግሯል።
ከጋሪ ኔቭል ጋር ቆይታ የነበረው ስቴቨን ጄራርድ “ ሊቨርፑልን በሊጉ መመልከት አላዝናናኝም “ የለ ሲሆን “ መስተካከል ያለበት ብዙ ችግር አለባቸው “ ብሏል።
ሊቨርፑልን ስለማሰልጠን ያስብ እንደሆነ የተጠየቀው የቀድሞ ተጨዋቹ “ አዎ ህልሜ ነው “ ሲል ምላሽ ሰጥቷል።
“ ነገርግን አሁን ለተወሰነ ጊዜ ሀላፊነት ለመቀበል ዝግጁ ላልሆን እችላለሁ " ሲል ጄራርድ ተናግሯል።
የሊቨርፑል ምክትል አሰልጣኝ እንዲሆን ቢጠየቅ ይቀበል እንደሆነ የተጠየቀው ጄራርድ በምላሹ “ ለሊቨርፑል አደርገዋለሁ “ ነው ያለው።
ጄራርድ ስለ አርነ ስሎት ምን አለ ?
“ ፕሪሚየር ሊጉን ያሸነፈ አሰልጣኝ ችግሩን ነቅሶ በማውጣት እንዲያስተካክል ሙሉ የውድድር አመት መሰጠት ይገባዋል “ ጄራርድ
@tikvahethsport @YisakAH
“ ኢንዞ ፈርናንዴዝ ቼልሲ ከሰለቸው የፈለገበት ሊሄድ ይችላል “ ጆን ኦቢ ሚኬል
የቀድሞ የቼልሲ ታሪካዊ ተጨዋች ጆን ኦቢ ሚኬል ኢንዞ ፈርናንዴዝ የሰጠውን አስተያየት ተከትሎ ትችቱን ሰንዝሯል።
ኢንዞ ፈርናንዴዝ ከቀናት በፊት በማድሪድ መኖር እንደሚፈልግ ተናግሮ እንደነበር ይታወሳል።
ጆን ኦቢ ሚኬል በበኩሉ “ ከክለቡ በላይ አስፈላጊ የሆነ ማንም ተጨዋች የለም ለቼልሲ በመጫወቱ ማመስገን አለበት “ ብሏል።
አክሎም “ በቼልሲ መጫወት ሰልችቶት ከሆነ ግን እጁን ከፍ አድርጎ ሲዖል መግባት ይችላል “ ሲል ተናግሮታል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የአርሰናል የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የወርሀ መጋቢት የወሩ ምርጥ ተጨዋች እጩዎች ይፋ ተደርገዋል።
በዚህም መሰረት :-
⏩ ዴቪድ ራያ
⏩ ዴክላን ራይስ
⏩ ጋብሬል ማግሀሌስ እና
⏩ ኤቤሬ ኢዜ በእጩነት መቅረብ ችለዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ለአርሰናል መጫወት እፈልጋለሁ “
ብራዚላዊው የዜኒት የፊት መሰመር አጥቂ ሉዊዝ ሄንሪኬ ለፕሪሚየር ሊጉ ክለብ አርሰናል መጫወት እንደሚፈልግ ገልጿል።
“ ለአርሰናል መጫወት እንደምችል እና በሚኬል አርቴታ ስር የመጫወት እድል እንደማገኝ ተስፋ አደርጋለሁ “ ሲል ሉዊዝ ሄንሪኬ ተናግሯል።
ጋብሬል ማርቲኔሊ እና ማግሀሌስን እንዳነጋገረ የገለፀው ተጨዋቹ " አርቴታን ይወዱታል ተጨዋች የሚሰማ አሰልጣኝ መሆኑን ነግረውኛል “ ብሏል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ጋቶች ለቅሶ ላይ ሆኖ ሁሌም ስለ ሀገሩ ነበር የሚያስበው “ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ
የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ጋቶች ፓኖም ኀዘን ላይ ሆኖ ለሀገሩ ያሳየው ክብር ለሌሎች ተምሳሌት የሚሆን ነው በማለት ተናግረዋል።
ጋቶች ፓኖም ምንም እንኳን በወላጅ አባቱ ህልፈት ኀዘን ላይ ቢሆንም ከብሔራዊ ቡድኑ ጎን ነበር ሲሉ ገልፀዋል።
“ ጋቶች መልዕክት እየላከ ሲያበረታታን ነበር “ ያሉት ዮሐንስ ሳህሌ “ እሱ ለሌሎች አርኣያ የሚሆን ነው ትክክለኛ ፕሮፌሽናልነት ነው ያሳየው “ ሲሉ አድንቀዋል።
አክለውም “ ለእሱ ትልቅ ክብር ነው ያለኝ ሞሮኮ ባይሄድም ለቅሶ ላይ ሆኖ ሁልጊዜም ስለ ሀገሩ ነበር የሚያስበው “ ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ “ የጋቶችን ድርጊት ከጋዜጠኞች እንጠብቀው ነበር “ ሲሉ ወቅሰዋል።
“ ጋዜጠኞች መተቸት ብቻ ሳይሆን ጥሩ መመኘትም ይገባቸው ነበር ምክንያቱም ሀገራዊ ጉዳይ ነው “ ሲሉ አሳዝኖኛል ብለዋል።
የቡድኑ አምበል ጋቶች ፓኖም በነገው ጨዋታ መሰለፉን ከመጨረሻው ልምምድ በኋላ እንደሚወስኑ ጨምረው ተናግረዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ኖኒ ማዱኬ ለምን ያህል ጊዜ ከሜዳ ይርቃል ?
እንግሊዛዊው የአርሰናል የፊት መስመር ተጨዋች ኖኒ ማዱኬ በብሔራዊ ቡድኑ ጨዋታ ጉዳት እንዳጋጠመው ይታወሳል።
ከዩራጓይ በነበረ ጨዋታ ተቀይሮ የወጣው ማዱኬ ከጨዋታው በኋላ ጉልበቱን አስሮ ሲወጣ ታይቷል።
ማዱኬ በጉልበት ጉዳቱ ምክንያት አርሰናል ከስፖርቲንግ ሊዝበን በሚያደርገው የመጀመሪያ የሻምፒየንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ መድረሱ አጠራጣሪ ሆኗል።
ተጨዋቹ አርሰናል ቅዳሜ ከሳውዝሀምፕተን ከሚያደርገው የኤፌ ካፕ ጨዋታ ውጪ መሆኑ ተገልጿል።
ኖኒ ማዱኬ ምናልባት በመልሱ የስፖርቲንግ ሊዝበን ጨዋታ ወደ ሜዳ ሊመለስ እንደሚችል ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
@tikvahethsport @YisakAH
“ ሜዳ ላይ ደስታ መፍጠር ነው የምፈልገው “ ሼርኪ
ፈረንሳዊው የማንችስተር ሲቲ ተጨዋች ረያን ሼርኪ በእግርኳስ ሜዳ ላይ ደስታ መፍጠር እንደሚያስደስተው ገልጿል።
“ እንደ ፈጣሪ ተጨዋችነቴ አላማዬ የቡድን አጋሮቼ እየሳቁ ከሜዳ እንዲወጡ ማድረግ ነው “ ሲል ረያን ሼርኪ ተናግሯል።
አክሎም “ ጎል ባላስቆጥርም አመቻችቼ ባላቀብልም ሜዳ ላይ ደስታ መፍጠር ነው ፍላጎቴ " በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ዙቢሜንዲ የብሔራዊ ቡድኑን ስብስብ ለቀቀ !
ስፔናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማርቲን ዙቢሜንዲ የስፔን ብሔራዊ ቡድን ስብስብን መልቀቁ ተገልጿል።
ተጨዋቹ በጉልበቱ ላይ ምቾት ያልተሰማው በመሆኑ ለጥንቃቄ ሲባል ከብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ ውጪ መደረጉ ተነግሯል።
ይህንንም ተከትሎ ማርቲን ዙቢሜንዲ ወደ አርሰናል መመለሱ ተገልጿል።
አሁን ላይ 1️⃣1️⃣ የአርሰናል ተጨዋቾች ከብሔራዊ ቡድናቸው ስብስብ ለቀው ወደ ክለቡ ተመልሰዋል።
@tikvahethsport @YisakAH
ሴኔጋል የዋንጫ ድሏን እያከበረች ነው !
የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫውን በስታድ ዴ ፍራንስ ይዞ ቀርቧል።
የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች የዋንጫ ድላቸውን ከደጋፊዎች ጋር በማክበር ላይ ይገኛሉ።
ሞሮኮ የአፍሪካ ዋንጫው በስታዲየም እንዳይቀርብ አስጠንቅቃ እንደነበር የሚታወስ ነው።
ሴኔጋል ከፔሩ ጋር የወዳጅነት ጨዋታዋን ታደርጋለች።
@tikvahethsport @kidusyoftahe