ሳውዝሀምፕተን በይፋ አሰልጣኝ ሾመ !
ከቀናት በፊት አሰልጣኝ ሩሴል ማርቲን ያሰናበተው የፕርሚየር ሊጉ ክለብ ሳውዝሀምፕተን በይፋ አዲስ አሰልጣኝ በሀላፊነት ሾሟል።
ሳውዝሀምፕተን ክሮሽያዊውን አሰልጣኝ ኢቫን ጁሪች በሩሴል ማርቲን ምትክ በሀላፊነት መሾማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።
የ 49ዓመቱ አሰልጣኝ ኢቫን ጁሪች በሳውዝሀምፕተን ቤት የአንድ አመት እና ግማሽ አመት ኮንትራት መፈራረማቸው ተገልጿል።
አሰልጣኙ ከፊርማው በኋላ “ ሜዳ ላይ ተፋላሚ የሆነ ጠንካራ ቡድን እፈልጋለሁ “ ሲሉ ተደምጠዋል።
“ ቡድኑ በፍጥነት አስተሳሰቡን መቀየር አለበት “ ሲሉ ከወዲሁ ያሳሰቡት አሰልጣኙ “ በደንብ የሚያጠቃ ሀይል ያለው ቡድን እፈልጋለሁ የእኔ የእግርኳስ ፍልስፍና ይህ ነው “ ብለዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
#PremiereLeague 🏴
የእንግሊዝ ፕርሚየር መርሐግብሮች ሲካሄዱ ኒውካስል ኢፕስዊች ታውንን 4ለ0 እንዲሁም ኖቲንግሀም ፎረስት ብሬንትፎርድን 2ለ0 ማሸነፍ ችለዋል።
የኒውካስል ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች አሌክሳንደር አይሳክ 3x እና ጃኮብ ሙርፊ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።
ለኖቲንግሀም ፎረስት የድል ግቦችን አንቶኒ ኢላንጋ እና ኦላ አይና አስቆጥረዋል።
በሌላ ጨዋታ ዌስትሀም ዩናይትድ ከብራይተን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።
ኖቲንግሀም ፍረስት ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 3️⃣1️⃣ በማድረስ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ 3️⃣ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል።
ስዊድናዊው የፊት መስመር ተጨዋች አሌክሳንደር አይሳክ በኒውካስል ዩናይትድ የመጀመሪያ ሀትሪክ መስራት ችሏል።
አሌክሳንደር አይሳክ በውድድር ዘመኑ 1️⃣0️⃣ኛ የፕርሚየር ሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
የኢፕስዊች ታውኑ ተጨዋች ሳም ሞርሲ ቢጫ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ በቅጣት ምክንያት በቀጣይ የአርሰናል ጨዋታ የሚያመልጠው ይሆናል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !
2:30 ክሪስታል ፓላስ ከ አርሰናል
@tikvahethsport @kidusoyoftahe
“ አሁንም በፔፕ ጋርዲዮላ እምነት አለን “ ሀላንድ
የማንችስተር ሲቲው አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከገቡበት አስቸጋሪ ሁኔታ ለማውጣት መንገድ ይፈልጋሉ የሚል እምነት እንዳለው ተናግሯል።
“ በእርግጠኝነት ከዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መውጣት እንችላለን “ የሚለው ሀላንድ “ አሁንም በፔፕ ጋርዲዮላ እምነት አለን እሱ መንገድ ይፈልጋል " ሲል ተናግሯል።
ሀላንድ አክሎም “ የምናደርገው ነገር በቂ አይደለም ጠንክረን መስራት አለብን “ ሲል ቡድኑን አሳስቧል።
“ በቅድሚያ ራሴን መመልከት አለብኝ ማስቆጠር ያለብኝን አላስቆጠርኩም ማድረግ ያለብኝንም አላደረግኩም “ ሀላንድ
@tikvahethsport @kidusoyoftahe
ማንችስተር ሲቲ ሽንፈት አስተናግዷል !
በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐግብር ማንችስተር ሲቲ ከአስቶን ቪላ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።
የአስቶን ቪላን የማሸነፊያ ግቦች ጆን ዱራን እና ሞርጋን ሮጀርስ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ፎደን የማንችስተር ሲቲን ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል።
ማንችስተር ሲቲ በሁሉም ውድድሮች ባደረጋቸው ያለፉት አስራ ሁለት ጨዋታዎች ሀያ ሰባት ግቦች ተቆጥረውበታል።
የፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን ማንችስተር ሲቲ ካደረጋቸው የመጨረሻ አስራ ሁለት ጨዋታዎች በአስራ አንዱ ቢያንስ ሁለት ግቦች አስተናግዷል።
ማንችስተር ሲቲ ካለፉት አስራ ሁለት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንድ ጨዋታ ነው ዘጠኙን በሽንፈት አጠናቋል።
በሊጉ ስንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ?
5️⃣ አስቶን ቪላ :- 28 ነጥብ
6️⃣ ማንችስተር ሲቲ :- 27 ነጥብ
ቀጣይ መርሐግብር ምን ይመስላል ?
ሐሙስ - ማንችስተር ሲቲ ከ ኤቨርተን
ሐሙስ - ኒውካስል ዩናይትድ ከ አስቶን ቪላ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
89 '
አስቶን ቪላ 2 - 0 ማንችስተር ሲቲ
⚽ ዱራን
⚽ ሮጀርስ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
63 '
አስቶን ቪላ 2 - 0 ማንችስተር ሲቲ
⚽ ዱራን
⚽ ሮጀርስ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
የእረፍት ሰአት !
በአስራ ሰባተኛ ሳምንት የፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር አስቶን ቪላ ከማንችስተር ሲቲ ጋር እያደረጉ የሚገኙትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት እየመሩ ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል።
የአስቶን ቪላን የመሪነት ግብ ጆን ዱራን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
🟨 የቢጫ ካርድ የተመለከቱ ተጫዋቾች እነማን ናቸው ?
- በመጀመርያው አጋማሽ ማቲ ካሽ በአስቶን ቪላ በኩል የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክተዋል።
⚽ የጨዋታው የኳስ ቁጥጥር ምን ይመስላል ?
- በመጀመርያው አጋማሽ ማንችስተር ሲቲ 67% - 33% የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ወስዷል።
@tikvahethsport @kidusoyoftahe
27 '
አስቶን ቪላ 1 - 0 ማንችስተር ሲቲ
⚽ ዱራን
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
1 '
አስቶን ቪላ 0 - 0 ማንችስተር ሲቲ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
9:30 አስቶን ቪላ ከ ማንችስተር ሲቲ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ቶተንሃሞች ሊቨርፑልን አሸንፈው ለከተማ ተቀናቃኞቻቸው ውለታ ይውላሉ? በዕለታዊ 1.1 ጊባ የዳታ ጥቅል የኳስ ጨዋታውን ከዳር እስከ ዳር በሚገኘው በሳፋሪኮም ኔትወርክ ላይ በDSTV በቀጥታ እንከታተል!
በM-PESA ላይ ስንገዛ
እለታዊ 1.3 ጊባ በ30 ብር ብቻ!
🔗የM-PESAን ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
የቴሌግራም ቦታችንን /channel/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!
የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉/channel/Safaricom_Ethiopia_PLC
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit
#Furtheraheadtogether
ይገምቱ ይሸለሙ
የማንችስተር ሲቲ እና አስቶን ቪላን ን ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።
የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?
√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።
√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 8:00 ሰዓት ብቻ ነው።
🔴 ይነበብ
አንድ የቤተሰባችን አባል ግምት ማስቀመጥ የሚችለው #አንዴ ብቻ ነው። ከአንድ ጊዜ በላይ የመለሰ ቤተሰባችን ሽልማት አይደርሰውም።
መልካም ዕድል !
@tikvahethsport
ሲቲ ወደ ዝውውር ገበያው ይወጣሉ !
ማንችስተር ሲቲዎች በሚቀጥለው ጥር ወር የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ መዘጋጀታቸው ተገልጿል።
ማንችስተር ሲቲ በጥር ወር እስከ ሶስት ተጨዋቾች ለማስፈረም ማሰቡን የዝውውር ጉዳዮችን የሚከታተለው ጋዜጠኛ ፋብሪዝዮ ሮማኖ ተናግሯል።
በውጤት ማጣት ውስጥ የሚገኘው ማንችስተር ሲቲ በዝውውር መስኮቱ የተከላካይ ፣ የመሐል እና የፊት መስመር ክፍሉን ለማጠናከር ማሰቡ ተነግሯል።
ማንችስተር ሲቲ ከያዘው የተጨዋች ዝርዝር ውስጥ የኒውካስሉ ብሩኖ ጉማሬሽ የሪያል ሶሴዳዱ ማርቲን ዙብሜንዲ እንደሚገኙበት ተገልጿል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሬስ ጄምስ ወደ ልምምድ ተመልሷል !
እንግሊዛዊው የሰማያዊዎቹ የመስመር ተጨዋች ሬስ ጄምስ ከጉዳቱ በማገገም ወደ ልምምድ መመለሱ ተገልጿል።
በቅርቡ በድጋሜ ባጋጠመው መጠነኛ ጉዳት ከሜዳ ርቆ የቆየው ሬስ ጄምስ አሁን ላይ ልምምድ መስራት መጀመሩን በማህበራዊ ትስስር ገፁ አሳውቋል።
አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ተጫዋቹን በተመለከተ በሰጡት አስተያየት ሬስ ጄምስ በዚህ ሳምንት ወደ ሜዳ ላይመለስ እንደሚችል ገልጸዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ራሂም ስተርሊንግ ጉዳት አጋጥሞታል !
የመድፈኞቹ የፊት መስመር ተጨዋች ራሂም ስተርሊንግ ጉዳት እንዳጋጠመው አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አረጋግጠዋል።
ተጨዋቹ በልምምድ ወቅት እንደተጎዳ የተናገሩት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ዛሬ ከጨዋታው ውጪ የሆነውም በዚሁ ምክንያት ነው ብለዋል።
" ትላንት በልምምድ ወቅት የጉዳት ስሜት ተሰምቶት አቋርጧል ሁኔታውን ለመረዳት በቀጣይ የህክምና ምርመራ ይደረግለታል።" ሲሉ ሚኬል አርቴታ ተናግረዋል።
@tikvahethsport @kidusoyoftahe
#TikvahGoal
በአሁን ሰዓት እየተካሄዱ የሚገኙ ጨዋታዎች እና ግቦችን በጎል ቻናላችን መከታተል ይችላሉ።
የጎል ቻናላችን 👉 /channel/+rbdEU4UaEdQxYWFk
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ይገምቱ ይሸለሙ
የአርሰናል እና ክሪስታል ፓላስን ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።
የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?
√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።
√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 2:30 ሰዓት ብቻ ነው።
🔴 ይነበብ
አንድ የቤተሰባችን አባል ግምት ማስቀመጥ የሚችለው #አንዴ ብቻ ነው። ከአንድ ጊዜ በላይ የመለሰ ቤተሰባችን ሽልማት አይደርሰውም።
መልካም ዕድል !
@tikvahethsport
“ ወደ አቋማችን መመለሳችን አይቀርም “ ጋርዲዮላ
የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ወደ ቀደመ አቋማችን የመመለሻ መፍትሔው “ የተጨዋቾቻችን መመለስ ነው “ ሲል ከሽንፈቱ በኋላ ተናግረዋል።
በዛሬው ጨዋታ “ ከስህተታችን ውጪ በመጀመሪያው አጋማሽ ጥሩ ተጫውተናል " ሲሉ የተደመጡት አሰልጣኙ በሁለተኛው አጋማሽ አቋማችን ወርዶ ነበር ብለዋል።
“ በጨዋታው ያደረግነው ጫና ውጤታማ አልነበረም በተለይ በቀኝ በኩል “ ሲሉ ስለ ጨዋታው ተናግረዋል።
“ ወደ አቋማችን የመመለሻ መፍትሄው የተጨዋቾቻችን መመለስ ነው “ የሚሉት ጋርዲዮላ አንድ የመሐል ተከላካይ ነው ያለን ይሄ የበለጠ አስቸጋሪ አድርጎብናል ብለዋል።
“ ባሉኝ ተጨዋቾች ትልቅ እምነት አለኝ አብዛኞቹ ተጨዋቾች ወደ አቋማችን ለመመለስ ይፈልጋሉ ይዋል ይደር እንጂ ቀስ በቀስ ወደ አቋማችን ለመመለስ መንገድ እንፈልጋለን።“ ጋርዲዮላ
@tikvahethsport @kidusoyoftahe
90+3'
አስቶን ቪላ 2 - 1 ማንችስተር ሲቲ
⚽ ዱራን ⚽ ፎደን
⚽ ሮጀርስ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
78 '
አስቶን ቪላ 2 - 0 ማንችስተር ሲቲ
⚽ ዱራን
⚽ ሮጀርስ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
50 '
አስቶን ቪላ 1 - 0 ማንችስተር ሲቲ
⚽ ዱራን
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
41 '
አስቶን ቪላ 1 - 0 ማንችስተር ሲቲ
⚽ ዱራን
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
17 '
አስቶን ቪላ 1 - 0 ማንችስተር ሲቲ
⚽ ዱራን
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
" የጦርነት ያህል መፋለም አለብን " ጋርዲዮላ
የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድናቸው ወደ አቋሙ ለመመለስ በትልቅ ደረጃ መፋለም እንዳለበት ገልጸዋል።
አሰልጣኙ ሲናገሩም " ወደ ቀድሞ ውጤታማነታችን ለመመለስ የጦርነት ያህል መፋለም አለብን " ሲሉ ተደምጠዋል።
ካይል ዎከር እና ኬቨን ዴብሮይን ተጠባባቂ ስለሆኑበት ምክንያት የተጠየቁት ጋርዲዮላ “ በእረፍት ምክንያት አይደለም በምንጫወትበት አጨዋወት ምክንያት ነው " ብለዋል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
የጀርመን ቡንደስሊጋ ተጎጂዎችን ያስባል !
የጀርመን ቡንደስሊጋ በቀሪ የአስራ አምስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ትላንት በጀርመን ማግዴቡርግ በደረሰ ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች እንደሚያስብ ተገልጿል።
ትላንት በጀርመን ማግዴቡርግ በተዘጋጀ የገና ገበያ ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ ጥቃት የአራት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካቶች መጎዳታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ገልጸዋል።
ይህንንም ተከትሎ የጀርመን ቡንደስሊጋ ቀጣይ ቀሪ ጨዋታዎች ከመጀመራቸው አስቀድሞ የህሊና መታሰቢያ ፀሎት በማድረግ እንደሚያስብ አስታውቋል።
በተጨማሪም ተጨዋቾች በእጅ ክንዳቸው ላይ ጥቁር ጨርቅ አጥልቀው ወደ ሜዳ በመግባት ተጎጂዎችን እንደሚያስቡ ተገልጿል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
🏆 #Wanaw_Eth_PL
⚡️የእረፍት ቀናት ሳምንቱን
በሙሉ ሃይል ለደከሙበት ነው....💯
📞 ይደውሉልን!
8289
+251901138283
+251910851535
+251913586742
ማህበራዊ ገጾቻችን
Instagram|Facebook |TikTok |X|wanawsportswear?si=TSJ9HZINs4MzMPj2">Youtube
🌍በአፍሪካውያን የተመረተ 🌍
ዋናው ወደፊት»»»Читать полностью…
ፒኤስጂ ከተጫዋቹ ጋር ሊለያይ ነው !
የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ከፈረንሳዊው ተጨዋች ራንዳል ኮሎ ሙኣኒ ጋር በጥር የዝውውር መስኮት መለያየቱ አይቀሬ መሆኑን ፋብሪዝዮ ሮማኖ ዘግቧል።
ስፔናዊው አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ራንዳል ኮሎ ሙኣኒን በቡድናቸው እንደማይፈልጉት ተገልጿል።
ተጨዋቹ ባለፉት ጨዋታዎች ከፒኤስጂ ስብስብ ውጪ እንደነበር የሚታወስ ነው።
ራንዳል ኮሎ ሙኣኒ ስሙ ማንችስተር ዩናይትድን ጨዋታ ከተለያዩ ክለቦች ጋር እየተያያዘ ይገኛል።
ፒኤስጂ በቀጣይ ለተጨዋቱ የሚቀርቡ የዝውውር ጥያቄዎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸው ተዘግቧል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ዩናይትድ አንቶኒን ማሰናበት አለበት “
የቀድሞ እንግሊዛዊ የፊት መስመር ተጨዋች ትሮይ ዲኒ ማንችስተር ዩናይትድ አንቶኒን መሸጥ እንዳለበት በሰጠው አስተያየት ገልጿል።
ትሮይ ዲኒ ስለ አንቶኒ ሲናገርም “ አንቶኒን ሜዳ ውስጥ ሲጫወት ስመለከተው ያበሳጨኛል “ ሲል ተደምጧል።
የቀድሞ የዋትፎርድ ተጨዋች ትሮይ ዲኒ አክሎም “ ማንችስተር ዩናይትድ አንቶኒን ማሰናበት አለበት “ በማለት ተናግሯል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች !
9:30 አስቶን ቪላ ከ ማንችስተር ሲቲ
12:00 ኢፕስዊች ታውን ከ ኒውካስል ዩናይትድ
12:00 ዌስትሀም ዩናይትድ ከ ብራይተን
2:00 ጂኖኣ ከ ናፖሊ
2:30 ክሪስታል ፓላስ ከ አርሰናል
5:00 ባርሴሎና ከ አትሌቲኮ ማድሪድ
🔴 የዛሬው የይግምቱ ሽልማቶቻችን የማንችስተር ሲቲ ፣ አርሰናል እና ባርሴሎና ጨዋታዎች ናቸው።
🔴 የዛሬ ሽልማታችን 8:00 ፣ 1:00 ሰዓት ፣ 4:00 ላይ ወደ ቤተሰቦቻችን የሚደርስ ይሆናል።
🔴 መገመት የሚቻለው በተጠቀሰው ሰዓት ላይ ብቻ ነው።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe