ወላይታ ድቻ ድል አድርገዋል !
በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሁለተኛ ሳምንት መርሐግብር ወላይታ ድቻ ከወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።
የወላይታ ድቻን የማሸነፊያ ግብ ካርሎስ ዳምጠው ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
የጦና ንቦቹ ሶስተኛ ተከታታይ ድላቸውን ማሳካት ችለዋል።
በሊጉ ግርጌ የተቀመጠው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ በውድድር አመቱ አስራ ሶስተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
4️⃣ ወላይታ ድቻ :- 33 ነጥብ
1️⃣8️⃣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ :- 9 ነጥብ
ቀጣይ መርሐግብር ?
ማክሰኞ - ወላይታ ድቻ ከ መቀለ 70 እንደርታ
ሐሙስ - ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ከ ፋሲል ከነማ
@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ስኬት ማጣትን የማይበት መንገድ ሌላ ነው “ አርቴታ
የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የፕርሚየር ሊጉ አሸናፊነት እድል በእጃችን አይደለም በማለት ተናግረዋል።
የሊቨርፑል አሸናፊነት እስከሚረጋገጥ የሊጉ እድል አለን ብለው ማሰባቸውን ቀጥለው እንደሆነ የተጠየቁት አርቴታ “ የሊጉ አሸናፊነት በእጃችን አይደለም " ብለዋል።
አክለውም “ አሁን ላይ ማድረግ የምንችለው ብቸኛው ነገር እያንዳንዱን ጨዋታ ለማሸነፍ ጥረታችንን መቀጠል እና የሚሆነውን ማየት ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
በዚህ አመት ዋንጫ አለማሸነፍ ለአርሰናል ስኬት ማጣት እንደሆነ ተያይዞ የተነሳላቸው አርቴታ “ ይህን ለማለት ገና አመቱ አላለቀም “ ብለዋል።
ጨምረው እንደገለፁትም “ ቢሆንም ስኬት ማጣትን እኔ ሰዎች በሚያስቡት መልኩ አላስበውም ግን አልናገርም “ ሲሉ ነው የተደመጡት።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
#wanawsportswear
🕯🕯🕯 ዜና እረፍት🕯🕯🕯
ከሰፈር እስከ ሀገር በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ ለዉጥ ለማምጣት መረጃ በመስጠት፣ ችግሮችን በመጠቆም፣ መፍትሄ በማሳየት የሚታወቀው ኑርሁሴን አሊ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን።
“በዳጉ ስፖርት” የስፖርት መረጃ አቅራቢው ወጣት ጋዜጠኛ ድንገተኛ ህልፈት ዋናው ስፖርት ለቤተሰቡ፣ ወዳጅ ዘመዶቹ እና ለመላው የእግር ኳስ ቤተሰብ መፅናናትን እንመኛለን።
ጋዜጠኛ ኑርሁሴን አሊ
ለእግር ኳስ ለሰጠህው ነገር ሁሉ እናመሰግንሀለን!Читать полностью…
“ ትልቅ ዋንጫ ማሸነፍ እፈልጋለሁ “ ዊሊያም ሳሊባ
ፈረንሳዊው ተከላካይ ዊሊያም ሳሊባ “ በአርሰናል ቤት ትልቅ ዋንጫዎችን ማሸነፍ እፈልጋለሁ “ ሲል ከነገው የፒኤስቪ ጨዋታ በፊት በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።
“ ምንም ትልቅ ዋንጫ ሳታሸንፍ አርሰናልን የምትለቅ ከሆነ የትኛውም ደጋፊ አያስታውስህም “ ሲል ሳሊባ አስተያየቱን ሰጥቷል።
አክሎም በቀጣይ አላማው ለአርሰናል ትልቅ ነገር በማምጣት ስኬታማ መሆኑ መሆኑን ተናግሯል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ልዩ ትዝታዎቼ ኦልድትራፎርድ ናቸው “ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን
የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ታሪክ አይሽሬ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ኦልድትራፎርድ ስታዲየም በርካታ ትዝታዎች ቢኖሯቸውም አዲስ መገንባቱን እንደሚደግፉ ገልጸዋል።
ኦልድትራፎርድ ስታዲየም የበርካታ ታሪክ ባለቤት መሆኑን ያስታወሱት ፈርጉሰን " ማንችስተር ዩናይትድ ሜዳ ላይ እና ከሜዳ ውጪ ጥሩ ነገሮችን መስራት አለበት " ብለዋል።
አክለውም “ ኦልድትራፎርድ በተለይ የእኔን በርካታ ልዩ ትዝታዎች ይዟል ነገርግን ለወደፊት የሚሆን አዲስ ስታዲየም መገንባት እና አዲስ ታሪክ መፃፍ አለብን “ ሲሉ ተናግረዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ በዛሬው ዕለት 100,000 ተመልካች መያዝ የሚችል አዲስ ስታዲየም ለመገንባት መወሰኑን ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ዩናይትድ ግዙፍ ስታዲየም ሊገነባ ነው !
ማንችስተር ዩናይትድ አዲስ ግዙፍ ስታዲየም ለመገንባት የመጨረሻ ውሳኔ ላይ መድረሱን በይፋ አስታውቋል።
ቀያዮቹ ሴጣኖች በቀጣይ 100,000 ተመልካቾችን መያዝ የሚችል አዲስ ግዙፍ ስታዲየም ለመገንባት ማሰባቸውን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል።
ክለቡ በቅርቡ ኦልድትራፎርድ ስታዲየምን ለማደስ ወይም አዲስ ለመገንባት በመምከር ላይ መሆኑ ሲገለፅ እንደነበር አይዘነጋም።
የስታዲየሙ ግንባታ ጊዜው አምስት አመት ሊወስድ እንደሚችል የተገለፀ ሲሆን ለግንባታው እስከ 2.4 ቢልዮን ዩሮ እንደሚያስፈልግ ተነግሯል።
አዲሱ የማንችስተር ዩናይትድ ስታዲየም በአለም ግዙፉ ስታዲየም ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተዘግቧል።
ክለቡ አዲስ የሚገነባው ስታዲየም በኦልድትራፎርድ ስታዲየም አቅራቢያ በሚገኝ የመሬት ይዞታው ላይ እንደሚያደርግ ተጠቁሟል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Wanawsportswear_March_8
ጥራት እና ዝነጣ በእያንዳንዱ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ውስጥ።🍀
እያንዳንዱ እርምጃ፣እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ሁሉም ድሎች - ትክክለኛውን የስፖርት ትጥቅ ከመምረጥ ይጀምራል🏆
የባለድሎች ምርጫ የሆነውን የስፖርት ትጥቅ
የካቲት 29(MARCH 8) የሚከበረውን የሴቶች ቀን ምክንያት በማድረግ እስከ መጋቢት 6 ድረስ በግማሽ ዋጋ ይሸምቱ❗️❗️
😄50% ቅናሽ
😄እስከ መጋቢት 6 ድረስ
😄ለሴቶች የስፖርት ቡድኖች ብቻ
😄በሁሉም የዋናው ምርቶች ላይ
📞ደውለው ይዘዙን
➡️8️⃣2️⃣8️⃣9️⃣
➡️+251901138283
➡️+251910851535
➡️+251913586742
🔗 ማህበራዊ ገጾቻችን🔗
Instagram|Facebook |TikTok |X|wanawsportswear?si=TSJ9HZINs4MzMPj2">Youtube
🌎በአፍሪካውያን የተመረተ 🌎
⭐️ ⭐️ ⭐️ ዋናው ወደፊት🔜🔜🔜Читать полностью…
" ከሳምንቱ የተሻለ እናደርጋለን " አርኔ ስሎት
የሊቨርፑሉ ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በዛሬው የፒኤስጂ ጨዋታ ቡድናቸው የተሻለ እንደሚንቀሳቀስ በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።
" ሰዎች በመጀመሪያው ዙር መጥፎ ጨዋታ እንዳደረግን ያስባሉ እኔ ግን አልስማማም ፒኤስጂ ጥሩ ስለተጫወተ ነው " ሲሉ አርኔ ስሎት ተናግረዋል።
አክለውም " ነገርግን ባለፈው ሳምንት ካሳየነው እንቅስቃሴ የተሻለ ነገር ማድረግ እንደምንችል እናውቃለን “ ብለዋል።
" ሊቨርፑልን ማሰልጠን የፈለኩት ክለቡ ባለው ታሪክ ፤ ተጨዋቾቹ ባላቸው ጥራት እና እናንተ ሊቨርፑል ለሁሉም ነገር እንዲፎካከር ስለምትጠብቁ ነው " አርኔ ስሎት
ኔዘርላንዳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኮዲ ጋክፖ ለጨዋታው ዝግጁ መሆኑን አሰልጣኝ አርኔ ስሎት አያይዘውም አረጋግጠዋል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች !
9:00 ኢትዮጵያ መድን ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
12:00 ወላይታ ድቻ ከ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
2:45 ባርሴሎና ከ ቤኔፊካ ( agg 1-0 )
5:00 ባየር ሌቨርኩሰን ከ ባየር ሙኒክ ( agg 0-3 )
5:00 ኢንተር ሚላን ከ ፊኖርድ ( agg 2-0 )
5:00 ሊቨርፑል ከ ፒኤስጂ ( agg 1-0 )
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
The National Finance Academy (NFA), the only accredited training institution for Insurance in the country, is pleased to announce the launch of its 4-month Professional Diploma Program in Insurance.
As part of our commitment to social responsibility, NFA offers FULL and PARTIAL scholarships in collaboration with Ethiopian Reinsurance Company, Africa Reinsurance Company, Association of Ethiopian Insurers, Ethio Life and General Insurance, Awash Insurance S.C, and Africa Insurance S.C.
Registrar Office: Around Magenagna infront of Ministry of Agriculture Tel: +251116661297 or +251945253515
“ ለቡድኑ የማይመጥኑ ተጨዋቾች አሉ “
የቀያይ ሴጣኖቹ ባለቤት ሰር ጂም ራትክሊፍ ማንችስተር ዩናይትድን የማይመጥኑ ተጨዋቾች " በቡድኑ አሉ “ በማለት ተናግረዋል።
" አንዳንድ ተጨዋቾች ለቡድኑ አይመጥኑም " ያሉት ባለሀብቱ “ ከሚገባቸው በላይ ገንዘብ የወጣባቸውም ተጨዋቾች አሉ " ብለዋል።
አክለውም “ አንዳንድ የሚደንቁ ተጨዋቾችም አሉን እንደ ብሩኖ ፈርናንዴዝ አይነት እሱ አስደናቂ እግርኳስ ተጨዋች ነው።“ ሲሉ ተደምጠዋል።
ስለ ሰራተኛ ቅነሳው ያነሱት ሰር ጂም ራትክሊፍ “ የሚገርመው በአመት 175,000 ፓውንድ የሚከፈለው የምልክት ቋንቋ አማካሪ ጭምር አግኝተናል “ ብለዋል።
“ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ስለ ክለቡ ሁኔታ ስናስረዳቸው ራሳቸው ናቸው ክለቡን በማስቀደም የአምባሳደርነት ሀላፊነታቸውን ለመልቀቅ የወሰኑት “ ራትክሊፍ
" የእኔ ብቸኛው ፍላጎት ማንችስተር ዩናይትድን በድጋሜ ታላቅ ማድረግ ነው " ሲሉ ባለሀብቱ ጨምረውም ተናግረዋል።
@Tikvahethsport @Kidusyoftahe
“ እዚህ ያለነው ለማሸነፍ ነው “ ቅቫራትስኬሊያ
የፒኤስጂው የፊት መስመር ተጨዋች ቅቫራትስኬሊያ ቡድናቸው ነገ ሊቨርፑልን ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ገልጿል።
" ሁለቱ ቡድኖች ተቀራራቢ ናቸው ነገርግን እኛ እዚህ ያለነው ለማሸነፍ ነው ፤ በለመድነው በራሳችን መንገድ እንጫወታለን “ ሲል ቅቫራትስኬሊያ ተናግሯል።
አክሎም “ የመጀመሪያው ሽንፈት ያበሳጭ ነበር በነገው ጨዋታ የትኛውንም ቡድን ማሸነፍ እንደምንችል ለአለም ማሳየት እንፈልጋለን “ ብሏል።
“ ነገ አስፈላጊው ነገር የቻልኩትን ሁሉ ማድረግ እና ጨዋታውን ማሸነፍ ነው ፤ ጨዋታው የአመቱ በጣም አስፈላጊ ጨዋታ ነው “ ቅቫራትስኬሊያ
@Tikvahethsport @Kidusyoftahe
ባየር ሌቨርኩሰን ተጫዋቹን በጉዳት አጣ !
የባየር ሌቨርኩሰኑ ጀርመናዊ የፊት መስመር ተጨዋች ፎሎሪያን ቨርትዝ በእግሩ ላይ ጉዳት እንዳጋጠመው መረጋገጡ ተገልጿል።
ጀርመናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ፎሎሪያን ቨርትዝ በጉዳቱ ምክንያት ለአራት ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ተነግሯል።
ይህንንም ተከትሎ ፎሎሪያን ቨርትዝ ከነገ ምሽቱ የባየር ሙኒክ የሻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ ውጪ መሆኑ ተረጋግጧል።
በተጨማሪም ጀርመን በቀጣይ ከጣልያን ጋር የምታደርገው የኔሽንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ የሚያመልጠው ይሆናል።
@Tikvahethsport @Kidusyoftahe
" ለሀኪሙ ማሸነፍ እንፈልጋለን " ሀንሲ ፍሊክ
⏩ “ ራፊንሀ ባሎን ዶር ሊያሸንፍ ይችላል “
የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ዋና አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ ከነገው የቤኔፊካ የሻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ በፊት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ ምን አሉ ?
- " የነገውን ጨዋታ ህይወታቸው ላለፈው የቡድኑ የህክምና ባለሙያ ስንል ማሸነፍ እንፈልጋለን
- ሮበርት ሌዋንዶውስኪ ተመልሷል ነገ ለመጫወት ዝግጁ ነው ቅዳሜ ዕለት ስሜት ነበረው አሁን በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው።
- ቤኔፊካ በጣም ጠንካራ ቡድን ነው አሰልጣኙ የተለየ ነገር እየሰሩ ነው ያላቸውን ፍልስፍና እና መጫወት የሚፈልጉበት መንገድ በግልጽ ይታያል።
- ቤኔፊካ ከሜዳው ውጪ ሲጫወት ብዙ ጨዋታዎችን አሸንፏል መጠንቀቅ አለብን።
- ቡድኑ በጥሩ ዝግጁነት ላይ ነው በትክክለኛው መንገድ ላይ ነን ጨዋታው ገና አልተጠናቀቀም።
- ሼዝኒ የበሰለ እና ልምድ ያካበተ ግብ ጠባቂ ነው እሱ በግሉ ብዙ ረድቶናል ብዙ ምርጥ ነገሮችን ሰርቷል።
- ራፊንሀ ምርጥ የውድድር ዘመን እያሳለፈ ይገኛል ቡድኑን በደንብ ረድቷል የባሎን ዶር እጩ ሊሆን ይችላል።" ብለዋል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
የማድሪድ ደርቢን ማን ይመራዋል ?
የፊታችን ረቡዕ በጉጉት የሚጠበቀውን የሪያል ማድሪድ እና አትሌቲኮ ማድሪድ የሻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።
ሪያድ ኤር ሜትሮፖሊታኖ ስታዲየም ላይ የሚደረገውን ተጠባቂ የመልስ ጨዋታ ፖላንዳዊው ዳኛ ሲሞን ማርሲንያክ በመሐል ዳኝነት እንደሚመሩት ይፋ ሆኗል።
ዋና ዳኛው ከዚህ በፊት በስምንት አጋጣሚዎች የሪያል ማድሪድን ጨዋታ ሲመሩ ሎስ ብላንኮዎቹ አራቱን አሸንፈው በሁለቱ ተሸንፈው በቀሪው አቻ ተለያይተዋል።
እንዲሁም ዋና ዳኛው ከዚህ በፊት ሁለቱ ቡድኖች የተገናኙበትን የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ዋንጫ የመሩ ሰሆን ጨዋታውን አትሌቲኮ ማድሪድ ማሸነፍ ችሏል።
የመጀመሪያው ዙር ጨዋታ በሪያል ማድሪድ የ 2ለ1 አሸናፊነት መጠናቀቁ አይዘነጋም።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !
2:45 ባርሴሎና ከ ቤኔፊካ ( agg 1-0 )
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
የአሸናፊነት ሳምንት ይሁንላችሁ!
ደንበኞች በሳምንታዊ ጃክፖት ሚሊየነር እየሆኑ ነው። ተራው የእርስዎ ነው!
ሚሊየነርነት እዚህ ይጀምራል https://betika.com.et/et/jackpot
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
ኢትዮጵያ መድን መሪነቱን አጠናክሯል !
በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።
የኢትዮጵያ መድንን የማሸነፊያ ግቦች አለን ካይዋ እና አቡበከር ሳኒ ሲያስቆጥሩ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኪቲካ ጅማ ከመረብ አሳርፏል።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
1️⃣ ኢትዮጵያ መድን :- 41 ነጥብ
1️⃣0️⃣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ :- 28 ነጥብ
ቀጣይ መርሐግብር ምን ይመስላል ?
ሐሙስ - ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮጵያ መድን
ቅዳሜ - ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ሲዳማ ቡና
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
“ አርሰናል ውስጥ መቀጠል እፈልጋለሁ “ ሳሊባ
የመድፈኞቹ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ዊሊያም ሳሊባ በቀጣይ በአርሰናል ቤት መቀጠል እንደሚፈልግ ተናግሯል።
“ እዚህ በጣም ደስተኛ ነኝ በአርሰናል መቀጠል እፈልጋለሁ “ ሲል ዊሊያም ሳሊባ አስተያየቱን ሰጥቷል።
ውሉን ለማራዘም እስካሁን ንግግር እንዳልጀመረ ያረጋገጠው ዊሊያም ሳሊባ “ እዚህ ደስተኛ ነኝ አያስቸኩልም “ ሲል ገልጿል።
ፈረንሳዊው ተከላካይ ዊሊያም ሳሊባ በስፔኑ ሀያል ክለብ ሪያል ማድሪድ እንደሚፈልግ ታማኝ የመረጃ ምንጮች ማስነበባቸው አይዘነጋም።
መድፈኞቹ ዊሊያም ሳሊባን በቀጣይ በክለቡ ማቆየት እንደሚፈልጉ መዘገቡ የሚታወስ ነው።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የስፖርት ጋዜጠኛው ህይወቱ አለፈ !
በማህበራዊ ሚዲያ የታችኛውን የሀገር ውስጥ እግርኳስ ውድድሮች ሽፋን በመስጠት የሚታወቀው የዳጉ ስፖርት ማህበራዊ ሚዲያ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ኑርሁሴን አሊ ህይወቱ አለፈ።
የሰመራ ዩኒቨርስቲ እግር ኳስ ክለብ የጨዋታ መርሐግብር ለማድረግ በሚጓዝበት ወቅት አሳዛኝ የመኪና አደጋ እንዳጋጠመው ታውቋል።
የዳጉ ስፖርት አዘጋጅ ጋዜጠኛ ኑርሁሴን አሊ መደበኛ የዘገባ ስራውን ለመስራት ከቡድኑ ጋር ሲጓዝ እንደነበር ተገልጿል።
ጋዜጠኛ ኑርሁሴን አሊ ትኩረት ያልተሰጣቸውን የታችኛው ሊግ የሀገር ውስጥ እግርኳስ ውድድሮችን ሽፋን በመስጠት ለስፖርቱ እድገት የራሱን አሻራ በማስቀመጥ ላይ የነበረ ታታሪ ወጣት ነበር።
ቲክቫህ ስፖርት ለቤተሰቦቹ ፣ ወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለመላው የእግር ኳስ ቤተሰብ መፅናናትን እንመኛለን።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የአውሮፓ የሻምፕየንስ ሊግ ምርጥ 16 ጥሎ ማለፍ ሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ይጀመራሉ!
ሁሉንም የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎችን እና ምርጥ ምርጥ መዝናኛዎችን ያካተቱ ከ125 በላይ በአዲሱ ሜዳ ስፖርት ፓኬጅ!
🎊 ከጥር 5 እስከ መጋቢት 22 ባሉት ቀናት አሁን ካሉበት ከቤተሰብ ፓኬጅ ወደ ሜዳ ከፍ ሲሉ… እኛ ሜዳ ስፖርት ፓኬጅን እንመርቅሎታለን!
ፓኬጅዎን ያሳድጉ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh
#ChampionsLeagueAllonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET #StepUp
“ አማራጫችን ማሸነፍ ብቻ ነው “ ኤንሪኬ
የፒኤስጂው ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ቡድናቸው በዛሬው ጨዋታ ያለው አማራጭ ማሸነፍ ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።
“ አላማችን ሁልጊዜም አንድ ነው ከተጋጣሚያችን ተሽለን መገኘት እንፈልጋለን “ ያሉት ሉዊስ ኤንሪኬ " ዛሬ ያለን አማራጭ ማሸነፍ ብቻ ነው “ ብለዋል።
" ከጨዋታው መጀመር አንስቶ ምንም ማሰብ አያስፈልግም በጣም ቀላል ነው ማሸነፍ ብቻ ነው በውስጣችን የሚኖረው " ሲሉ ሉዊስ ኤንሪኬ ተናግረዋል።
" አንፊልድ ልዩ ስታዲየም ነው ተጨዋቾቹ እዛ መጫወት ይፈልጋሉ ፤ ያለንን ሁሉ ሰጥተን እንድንጫወት ያነሳሳናል ፤ እዛም ምርጥ ጨዋታ እንደምንጫወት ማሳየት እንፈልጋለን " ኤንሪኬ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ሊቨርፑልን አሸንፈን ዋንጫውን እናነሳለን “ ብሩኖ ጉማሬስ
የኒውካስል ዩናይትዱ ተጨዋች ብሩኖ ጉማሬስ ቡድናቸው በሳምንቱ መጨረሻ ከሊቨርፑል የሚያደርገውን የካራባኦ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ ማሸነፍ እንደሚችል ተናግሯል።
ትላንት ምሽት ዌስትሀምን 1ለ0 ካሸነፉበት ጨዋታ በኋላ አስተያየቱን የሰጠው ጉማሬስ “ ዌምብሌይ ላይ ዋንጫውን እንደምናሸንፍ እርግጠኛ ነኝ " ብሏል።
“ ሰዎች በእኛ ተጠራጥረዋል ነገርግን እኛ በራሳችን አንጠራጠርም ፣ ዋንጫው ለእኛ የአለም ዋንጫ ነው ምክንያቱም ታሪክ መስራት እንፈልጋለን “ ጉማሬስ
የካራባኦ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ እሁድ ምሽት 1:30 በዌምብሌይ ስታዲየም ይካሄዳል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
Can PlayStation
PlayStation 5 Packed jestic በ 11,000ብር
ብዛት አቅርበናል
ለክፍለ ሀገር እናቀርባለን ይደውሉ
በቅናሽ PlayStation ይግዙ
ከ Can PlayStation
PlayStation 4 Dubai jestic=3500
Ps4 Dubai Used Orginal jestic=5000
PlayStation 5 Packed jestic=11,000
🤝Tanks for choice
አድራሻ፦
ቁጥር 1 መገናኛ ሱቅ የአድራሻ ለውጥ በቅርቡ ስለምናደርግ ከመምጣቶ በፊት አስቀድመው ይደውሉ
ቁጥር 2 ቦሌ Celavi burger አጠገብ ዘንባባ ህንፃ ምድር ላይ
ስልክ፦ 0910529770 ወይም 0977349492
0914646972 ይደውሉ
ለአዳዲስ መረጃ Telegram channel join ይበሉ ፦
/channel/CanPlaystation
👍Update Your Life
አል ነስር ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቀለ !
በእስያ ሻምፒዮንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ አል ነስር ከኢራኑ ክለብ ኢስቴግሀል ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።
የአል ነስርን የማሸነፊያ ግቦች ጆን ዱራን 2x እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።
አል ነስር ጨዋታውን በድምር ውጤት 3ለ0 በማሸነፍ ሩብ ፍፄሜውን ተቀላቅለዋል።
ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእስያ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ሰባተኛ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።
@Tikvahethsport @Kidusyoftahe
“ ሩበን አሞሪም ለረጅም ጊዜ ይቆያል “ ራትክሊፍ
“ ቴንሀግን ማቆየት ስህተት ነበር “
የማንችስተር ዩናይትድ አነስተኛ ድርሻ ባለቤት ሰር ጂም ራትክሊፍ በክለቡ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ አስተያየታቸውን ሰጥተው ነበር።
እንግሊዛዊው ቢሊየነር ሰር ጂም ራትክሊፍ በአስተያየታቸው አሰልጣኝ ሩበን አሞሪምን “ ምርጥ ወጣት አሰልጣኝ “ ሲሉ አሞካሽተዋቸዋል።
አክለውም “ ለረጅም ጊዜ እዚህ የሚቆይ ይመስለኛል “ ሲሉ በአሰልጣኙ ያላቸውን እምነት ተናግረዋል።
ባለሀብቱ ምን አሉ ?
- " ሩበን አሞሪም የተለየ አሰልጣኝ ነው ጊዜ ሊሰጠው ይገባል እሱ ለረጅም ጊዜ እዚህ እንደሚቆይ አስባለሁ።
- ሩበን አሞሪም ብዙ ከሚከፈላቸው ተጨዋቾች መካከል ግማሹን እያገኘ አይደለም ብዙ ጉዳቶችም አለበት እሱ ይህ ሁሉ ሆኖ ምርጥ ስራ እየሰራ እንደሆነ ይሰማኛል።
- ኤሪክ ቴንሀግ እንዲቀጥል ማድረግ ስህተት ነበር ብዙ ክርክሮች ነበሩ በዚህ ጉዳይ ደጋፊዎች ይደግፉት ነበር ነገርግን ውሳኔያችን ስህተት ነበር።
- ሩበን አሞሪም ወጣት አሰልጣኝ ነው ቡድን እንዲገነባ እና እንዲላመድ እድል መስጠት አለብን “ ብለዋል።
@Tikvahethsport @Kidusyoftahe
“ ውጤቱን መቀልበስ እንችላለን “ ዣቢ አሎንሶ
የባየር ሌቨርኩሰኑ ዋና አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ቡድናቸው ነገ ባየር ሙኒክን በማሸነፍ ውጤቱን መቀልበስ እንደሚችል ገልጸዋል።
“ እኛ ምንም ሳንሸነፍ ቡንደስሊጋውን ያሸነፍን ነን “ ያሉት አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ነገ ውጤቱን ከመቀልበስ የሚከብደው ይሄ ይመስለኛል ብለዋል።
" ቡድኑ ከባድ ነገሮችን ማድረግ ይችላል ተጨዋቾቹ ይሄንን ያውቃሉ ይሰማቸዋል አስፈላጊው ነገር ይህ ነው " ሲሉ አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ተናግረዋል።
ባየር ሙኒክ የመጀመሪያውን ዙር ጨዋታ 3ለ0 ማሸነፉ የሚታወስ ሲሆን የመልስ ጨዋታው ነገ ምሽት 5:00 ሰዓት በባየር ሌቨርኩሰን ሜዳ ይደረጋል።
@Tikvahethsport @Kidusyoftahe
የጣና ሞገዶቹ ወሳኝ ድል አሳክተዋል !
በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባሕርዳር ከተማ ከሀድያ ሆሳዕና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።
የባሕር ዳር ከተማን የማሸነፊያ ግብ ፍቅረሚካኤል አለሙ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
የደረጃ ሰንጠረዡ ምን ይመስላል ?
2️⃣ ባሕር ዳር ከተማ - 33 ነጥብ
4️⃣ ሀድያ ሆሳዕና - 32 ነጥብ
ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?
ረቡዕ - ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሀድያ ሆሳዕና
አርብ - ባሕርዳር ከተማ ከ ስሑል ሽረ
@Tikvahethsport @Kidusyoftahe
የደጋፊዎች የወሩ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !
በሊቨርፑል መሪነት የቀጠለው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የወርሀ የካቲት የደጋፊዎች የወሩ ምርጥ ተጨዋች ይፋ ተደርጓል።
ይህንንም ተከትሎ ግብፃዊው የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ሳላህ የደጋፊዎች የወሩ ምርጥ ተጨዋች በመሆን በአብላጫ ድምፅ መመረጥ ችሏል።
መሐመድ ሳላህ በወሩ ባደረጋቸው የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ስድስት ግቦችን ሲያስቆጥር አራት አመቻችቶ አቀብሏል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ቀመረኛው!!
ዛሬም የሚያሸንፉባቸው የእለቱ የውርርድ ጥቆማዎች እነሆ!
አሁን ነው ማሸነፍ እድሜ ለቀመረኛው!!
ቀመረኛው - በቤቲካ ብቻ!