Gaming PC (Core i9)
🔸Z-Book, Core i9
10th Generation
1TB Storage/ 32GB RAM
Nvidia RTX 5000 (16GB)
🔹HP OMEN, Core i9
13th Generation
1TB Storage/ 16GB RAM
Nvidia RTX 4060 (8GB)
🔸Nitro-5, Core i9
Core i9-13th Gen
1TB Storage /16GB RAM
Nvidia RTX 4060 (8GB)
Contact Us
0953964175 @heymobile
@heyonlinemarket
ከንአን ማርከነህ ግብ አስቆጥሯል !
በሊቢያ ሊግ ተሳታፊ ለሆነው አል መዲና ትሪፖሊ እግር ኳስ ክለብ የሚጫወተው ኢትዮጵያዊው የፊት መስመር ተጫዋች ከንአን ማርከነህ የመጀመሪያ ግቡን አስቆጥሯል።
የከንአን ማርከነህ ክለብ አል መዲና ትሪፖሊ ዛሬ ከአል አትሀድ ጋር ያደረገውን የሊቢያ ሊግ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር 3ለ1 ማሸነፍ ችሏል።
በጨዋታው ከንአን ማርከነህ 34ኛው ደቂቃ ላይ ለክለቡ የመጀመሪያው የሆነውን ግብ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
የከንአን ማርከነህን የመጀመሪያ ግብ በጎል ቻናላችን መመልከት ይችላሉ።
የጎል ቻናላችን 👉 /channel/+rbdEU4UaEdQxYWFk
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ማውንት ለምን ያህል ጊዜ ከሜዳ ይርቃል ?
እንግሊዛዊው የማንችስተር ዩናይትድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሜሰን ማውንት ለረጅም ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም አረጋግጠዋል።
ሜሰን ማውንት ማንችስተር ዩናይትድ ማንችስተር ሲቲን ባሸነፈበት ጨዋታ በጉዳት ምክንያት ተቀይሮ መውጣቱ የሚታወስ ነው።
" ማውንት መቼ እንደሚመለስ በግልጽ ቀኑን አላውቅም ነገርግን ለረጅም ጊዜ ከሜዳ ይርቃል “ ሲሉ ሩበን አምሪም የጉዳት ሁኔታውን አስረድተዋል።
25ዓመቱ ሜሰን ማውንት ባለፈው አመት አምስት ወራትን በጉዳት ሲያሳልፍ በዚህ አመትም ከሁለት ወራት ጉዳት በኋላ በቅርቡ ወደ ሜዳ ተመልሶ ነበር።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ደማቁ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ወደ ሜዳ ተመልሰዋል💥
ቶተንሃም ከሊቨርፑል በ ቶተንሀም ስታዲየም የሚያደርጉተን ደመቅ ጨዋታ በቀጥታ በSS Premier League Ch 223 በሜዳ ፓኬጅ በቀጥታ ይከታተሉ!
👉እነዚህን ድንቅ ፍልሚያዎች ጨምሮ ሌሎች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይመልከቱ።
ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh
ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et
#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
" ከዩናይትድ ሽንፈት በኋላ ደስተኛ አልነበርኩም " ጋርዲዮላ
የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድናቸው ነገ ከአስቶን ቪላ ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ በፊት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
አሰልጣኙ በንግግራቸውም :-
- "በሚቀጥለው የጥር የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ማንችስተር ሲቲን የሚለቅ ተጨዋች የሚኖር አይመስለኝም።
- በማንችስተር ዩናይትድ ከደረሰብን ሽንፈት በኋላ ደስተኛ አልነበርኩም ስድስት ጊዜ ከወደቃችሁ ለሰባተኛ ጊዜ መነሳት አለባችሁ።
- በዚህ ሳምንት ጥሩ የልምምድ ጊዜ ነበረን ዛሬ ጥሩ ልምምድ ነበረን ተጨዋቾቹ ዝግጁ ናቸው አንድ ጊዜ ማሸነፍ ከጀመርን እንደምንሻሻል እርግጠኛ ነኝ።
- ጨዋታዎችን ማሸነፍ አለብን አሁን ባለንበት ሁኔታ ነጥብ ማግኘት እንደምንችል አውቃለሁ ቡድናችን ሙሉ ሲሆን በድጋሜ እንመለሳለን።
- አስቶንቪላ ምርጥ አሰልጣኝ አላቸው በሻምፒየንስ ሊግ ያላቸው ውጤት በራሱ ይናገራል ምርጥ ስራ እየሰሩ ነው።"ብለዋል
@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ለማሸነፍ ያለንን ሁሉ እንሰጣለን " ሀንሲ ፍሊክ
የባርሴሎናው ዋና አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ ቡድናቸው ነገ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ከባድ እንደሚሆን ገልጸዋል።
“ ጨዋታው ለእኛ በጣም አስፈላጊ ነው “ ያሉት አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ " 3️⃣ ነጥቡን ለማሳካት ሜዳ ላይ ያለንን ሁሉ እንሰጣለን " ብለዋለ።
አትሌቲኮ ማድሪድ ያለፉትን አስራ አንድ ተከታታይ ጨዋታዎች ማሸነፋቸውን ያስታወሱት አሰልጣኙ “ ከባድ ጨዋታ ይሆናል ነገርግን ዝግጁ ነን " በማለት ተናግረዋል።
አሰልጣኙ አክለውም የፊት መስመር ተጨዋቹ አንሱ ፋቲ ወደ ቡድኑ ስብስብ መመለሱን አረጋግጠዋል።
ሳውዝሀምፕተን አሰልጣኝ ለመሾም ተስማማ !
ከቀናት በፊት አሰልጣኝ ሩሴል ማርቲን ያሰናበተው የፕርሚየር ሊጉ ክለብ ሳውዝሀምፕተን አዲስ አሰልጣኝ በሀላፊነት ለመሾም ተስማምቷል።
ሳውዝሀምፕተን አሁን ላይ ክሮሽያዊውን አሰልጣኝ ኢቫን ጁሪች በሀላፊነት ለመሾም ከስምምነት መድረሳቸውን ዘ አትሌቲክ አረጋግጧል።
የ 49ዓመቱ አሰልጣኝ ኢቫን ጁሪች ከሮማ አሰልጣኝነታቸው ከ 5️⃣3️⃣ ቀናት በኋላ ከተሰናበቱ ወዲህ ያለ ሀላፊነት ይገኙ ነበር።
አሰልጣኙ በሳውዝሀምፕተን ቤት የአንድ አመት እና ግማሽ አመት ኮንትራት እንደሚፈራረሙ ተገልጿል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
"ልዩ የእንኳን ደህና መጡ ጉርሻ!
ደንበኛ ይሁኑ! ይወራረዱ! 100% ጉርሻ ያግኙ!
እንኳን ደህና መጡ! የመጀመሪያ ብቁ የሆነ ውርርድዎን ሲያደርጉ የተወራረዱበትን ገንዘብ መጠን እስከ 100% እንደ ጉርሻ ያገኛሉ።
አሁኑኑ Betika.et ላይ ቤቲካን ይቀላቀሉ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!"
" መልካም አስተዳደር የግድ መኖር ያለበት ጉዳይ ነው “ ሴባስቲያን ኮ
በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የፕሬዝደንት እና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ምርጫ ጋር እንዲሁም አጠቃላይ ከስፖርቱ ጋር በተያያዘ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ይነሳሉ።
ይህንን ጉዳይ በተመለከተ የአለም አትሌቲክስ ፕሬዝዳንት ሴባስቲያን ኮ የሚያውቁት ጉዳይ ካለ ከልዩ ስፖርት ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።
ፕሬዝዳንቱ በምላሻቸው ምን አሉ ?
- “ በጉዳዩ ዙሪያ በጥልቀት አስተያየት መስጠት አልችልም። ነገርግን ሁሉንም አባል ፌዴሬሽኖች የሚከታተል አለምአቀፍ የግንኙነት ክፍል አለን።
- ይህ ክፍል መሬት ላይ የሚሰራውን ስራ ፣ አስተዳደር አካባቢ፣ በአጠቃላይ የሁሉንም ፌዴሬሽኖች የስፖርት እንቅስቃሴ ይገመግማል።
- የመልካም አስተዳደር ጉዳይ ቢኖር ጥሩ ነው ሳይሆን ፤ የግድ መኖር ያለበት እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ነው።
- ጉዳዩ ከስፖርቱ ባሻገርም ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። አትሌቲክሱ ውስጥ በአጋርነት መስራት ለሚፈልጉ ተቋማት፤ አብረው እንዲቀጥሉ ለማድረግ መተማመንን የሚሰጥ ጭምር ነው።
- የተነሱት ስጋቶች የማስብባቸው ናቸው አባል ፌዴሬሽኖቻችን ውስጥ ችግሮች ሲኖሩ AIU(አትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት) በጣም ፈጣን ምላሽ ይሰጣል።" ሲሉ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።
ምንጭ -https://liyu-sport.com/article/54
@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ዋንጫ ማሸነፍ ችግራችንን አይፈታም " አሞሪም
የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ቡድኑ ዋንጫ ቢያሸንፍ ችግሮቹ ይፈታሉ የሚል እምነት እንደሌላቸው ገልጸዋል።
“ እንደ ቡድን እየተሻሻልን " ያሉት አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ዋንጫ ማሸነፍ ችግራችንን ሁሉ ይፈታል ብለን አናስብም ሲሉ ከምሽቱ ሽንፈት በኋላ ተናግረዋል።
“ የመጀመሪያ አላማችን የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫን ማሸነፍ ነው ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድብን ግን አላውቅም።" ሩበን አሞሪም
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የካራባኦ ካፕ ድልድል ምን ይመስላል ?
የእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ ሩብ ፍፃሜ ውድድር ባለፉት ሁለት ቀናት መካሄዱን ተከትሎ የግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚዎች ተለይተዋል።
በግማሽ ፍፃሜ የሚገናኙ ቡድኖች ከተደረገው የእጣ ማውጣት ስነስርዓት በኋላ ሲታወቁ
⏩ ቶተንሀም ከ ሊቨርፑል እንዲሁም
⏩ አርሰናል ከ ኒውካስል ዩናይትድ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ዩናይትድ ከካራባኦ ካፕ ውድድር ውጪ ሆነ !
ማንችስተር ዩናይትድ ከቶተንሀም ጋር ያደረጉትን የእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ 4ለ3 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።
የቶተንሀምን የማሸነፊያ ግቦች ዶምኒክ ሶላንኬ 2x ፣ ሰን ሁንግ ሚን እና ኩሉሴቭስኪ ማስቆጠር ችለዋል።
የማንችስተር ዩናይትድን ግቦች ዚርኪዜ ፣ አማድ ዲያሎ እና ጆኒ ኢቫንስ ከመረብ አሳርፈዋል።
ይህንንም ተከትሎ ቶተንሀም የካራባኦ ካፕ ግማሽ ፍፃሜውን ሲቀላቀል ማንችስተር ዩናይትድ ከውድድሩ ውጪ ሆነዋል።
ግማሽ ፍፃሜውን እነማን ተቀላቀሉ ?
- አርሰናል
- ሊቨርፑል
- ኒውካስል ዩናይትድ እና
- ቶተንሀም የግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚ መሆናቸውን ያረጋገጡ ክለቦች ናቸው።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
90 '
ቶተንሀም 4-3 ማንችስተር ዩናይትድ ( ካራባኦ ካፕ )
⚽⚽ ሶላንኬ ⚽ ዚርኪዜ
⚽ ኩሉሴቭስኪ ⚽ አማድ ዲያሎ
⚽ ሰን ⚽ ኢቫንስ
ቼልሲ 5-1 ሻምሮክ ሮቨርስ ( ኮንፈረንስ ሊግ )
⚽⚽⚽ ጉዩ ⚽ ፖም
⚽ ዴውስቡሪ
⚽ ኩኩሬላ
@tikvahethsport @kidusyoftahe
82 '
ቶተንሀም 3-2 ማንችስተር ዩናይትድ ( ካራባኦ ካፕ )
⚽⚽ ሶላንኬ ⚽ ዚርኪዜ
⚽ ኩሉሴቭስኪ ⚽ አማድ ዲያሎ
ቼልሲ 5-1 ሻምሮክ ሮቨርስ ( ኮንፈረንስ ሊግ )
⚽⚽⚽ ጉዩ ⚽ ፖም
⚽ ዴውስቡሪ
⚽ ኩኩሬላ
@tikvahethsport @kidusyoftahe
65'
ቶተንሀም 3-1 ማንችስተር ዩናይትድ ( ካራባኦ ካፕ )
⚽⚽ ሶላንኬ ⚽ ዚርኪዜ
⚽ ኩሉሴቭስኪ
ቼልሲ 5-1 ሻምሮክ ሮቨርስ ( ኮንፈረንስ ሊግ )
⚽⚽⚽ ጉዩ ⚽ ፖም
⚽ ዴውስቡሪ
⚽ ኩኩሬላ
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ይቅናዎት!
ኦዶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍ ተደርገዋል።
ታዲያ ምን ይጠብቃሉ? ለማሸነፍ በተመቻቹ ኦዶች ይወራረዱ!
አሁኑኑ Betika.et ላይ ብቻ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
“ ትልቅ ዋንጫዎችን ማሸነፍ እንፈልጋለን “ አርቴታ
በክለቡ ሀላፊነት አምስት አመት የሆናቸው የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በቀጣይ ትልቅ ዋንጫዎችን ማሸነፍ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
“ በዚህ ክለብ ውስጥ ማሳካት የምንፈልገው ነገር ግልጽ ነው " ያሉት ሚኬል አርቴታ ምንም አይነት ጨዋታ ሳንሸነፍ ትልቅ ዋንጫዎችን ማንሳት እንፈልጋለን ብለዋል።
በጉዳት ላይ ስለሚገኙ ተጨዋቾቻቸው የተናገሩት አርቴታ ዴክላን ራይስ እና ሪካርዶ ካላፊዮሪ ለነገው የክሪስታል ፓላስ ጨዋታ ይደርሳሉ ሲሉ አረጋግጠዋል።
በሌላ በኩል አሌክሳንደር ዚንቼንኮ እና ቶሚያሱ ለጨዋታው የመድረስ እድል ሊኖራቸው እንደሚችል አሰልጣኙ ጠቁመዋል።
ቡድናቸው በጥር ማርከስ ራሽፎርድን ያስፈርም እንደሆነ የተጠየቁት ሚኬል አርቴታ “ ስለ ሌላ ክለብ ተጨዋች መናገር አልችልም “ ሲሉ መልሰዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ የአመቱ ምርጥ ስፖርተኛ ተባለ !
የአስቶን ቪላው ግብ ጠባቂ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ የአርጀንቲና የ 2024 የአመቱ ምርጥ አትሌት በመሆን መመረጡ ይፋ ተደርጓል።
ከሶስት አመታት በኋላ ከሊዮኔል ሜሲ ውጪ ሌላ ስፖርተኛ ሽልማቱን ሲያሸንፍ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።
ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ በ 2024 ምን አሳካ ?
- ከ 41 አመታት በኋላ አስቶንቪላ ሻምፒየንስ ሊግ እንዲሳተፍ አገዘ
- ከአርጀንቲና ጋር ኮፓ አሜሪካ አሳካ
- የ ባሎን ዶር የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ
- የፊፋ የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ
@tikvahethsport @kidusyoftahe
📽 😍 የምርጥ አስሩን ቆይታ እንከታተል!
የ#1Wedefit ዲጂታል የሙዚቃ ውድድር ኮከቦቻችን ያደረጉትን አስደሳች ቆይታ የመጀመሪያው ክፍል በYouTube ቻናላችን ላይ እንድትከታተሉ እንጋብዛችኋለን! 👉🏾 https://youtu.be/akPYilRmFME?si=CSq0ihl5s9qq3lkT
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#FurtherAheadTogether #DigitalMusicChallenge
ሲቲ ተጨዋቾቹ ወደ ሜዳ ይመለሳሉ !
ማንችስተር ሲቲ በጉዳት ላይ የሚገኙ ተጨዋቾቹ ወደ ሜደ ሜዳ እንደሚመለሱለት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አረጋግጠዋል።
ሁለቱ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋቾች " ማኑኤል አካንጂ እና ጆን ስቶንስ በጥሩ ሁኔታ ላይ ናቸው ወደ ቡድኑ ተመልሰዋል " ሲሉ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ሩበን ዲያስ እስከ አንድ ወር ለሚደርስ ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ ፔፕ ጋርዲዮላ አረጋግጠዋል።
ብራዚላዊው ግብ ጠባቂ ኤደርሰን በበኩሉ በነገው የአስቶን ቪላ ጨዋታ መድረሱ አጠራጣሪ መሆኑን ፔፕ ጋርዲዮላ ገልጸዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ማድሪድ የቪኒሰስን ሽልማት ያከብራል !
ሪያል ማድሪድ እሁድ ከሲቪያ ጋር ከሚያደርጉት የሊግ መርሐግብር በፊት የቪኒሰስ ጁኒየርን የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማት እንደሚያከብሩ ተገልጿል።
ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪኒሰስ ጁኒየር የፊፋ የ 2024 የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን ለመጀመሪያ ጊዜ ማሸነፉ ይታወሳል።
ሎስ ብላንኮዎቹ ከሲቪያ ጨዋታ በፊት በሳንቲያጎ በርናቦ ለቪኒሰስ ጁኒየር ዝግጅት ማድረጋቸውን "Diario AS" ዘግቧል።
ቪኒሰስ ጁኒየር በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም የፊፋ የአመቱ ምርጥ ሽልማቱን ለደጋፊው እንደሚያስመለክት ተነግሯል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ዩሮፓ ሊግ ላይ የቶተንሀም ደጋፊ ነኝ " አርኔ ስሎት
የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት እሁድ ከቶተንሀም ጋር ከሚያደርጉት ጨዋታ በፊት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
አሰልጣኙ ካነሷቸው ሀሳቦች መካከልም :-
- " በካራባኦ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ የቀሩ ቡድኖች ጠንካራ ናቸው ቀላል የሚባል ቡድን የለም ነገርግን ድልድሉ አስደስቶናል።
- ቶተንሀም ጥሩ ስራ እየሰሩ ነው ዋንጫ ቢያሸንፉ ደስ ይለኛል ነገርግን የካራባኦ ዋንጫን አይደለም የዩሮፓ ሊግ ነው እዛ ላይ የእነሱ ደጋፊ ነኝ።
- ፌዴሪኮ ኬሳ ጠንካራ እየሆነ እና እየተሻሻለ ነው ፤ ጠንካራ ወደሆነ ሊግ ነው የመጣው ለመላመድ ረጅም ጊዜ ወስዶባታል።"ሲሉ ተደምጠዋል።
አሰልጣኙ በንግግራቸው ወቅት ከብራድሌይ እና ኢብራሂም ኮናቴ ውጪ ሁሉም ተጨዋቾቻቸው ለእሁዱ የቶተንሀም ጨዋታ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
📦 #Wanaw_Products 📦
በዋናው ቤት አርብ ልዩ ቀን ነው!!!
ዋናው ወደፊት»»»Читать полностью…
" በምናደርገው እንቅስቃሴ ደስተኛ ነኝ " ማሬስካ
የሰማያዊዎቹ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ቡድናቸው እያሳየ በሚገኘው እንቅስቃሴ መደሰታቸውን ከምሽቱ ድል በኋላ ገልፀዋል።
“ ቡድኑ ባደረገው እንቅስቃሴ እና ባስመዘገበው ውጤት ደስተኛ ነኝ በጣም አሰፈላጊ ውጤት ነበር “ ሲሉ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ተናግረዋል።
ብዙ ጊዜ ለቡድኖች ቀላል ግምት እንደሚሰጥ የገለፁት ኢንዞ ማሬስካ ጨዋታዎችን በትኩረት እንደምንመለከት እና ለተጋጣሚ ክብር እንዳለን በተደጋጋሚ አሳይተናል ብለዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የኮፓ ኢጣልያ ተጋጣሚዎች ታውቀዋል !
በዘንድሮው የውድድር አመት የኮፓ ኢጣልያ ሩብ ፍፃሜ ተጋጣሚዎች ትላንት ምሽት ከተደረገው የኢንተር ሚላን እና ዩዲኔዜ ጨዋታ በኋላ ተለይተዋል።
ኢንተር ሚላን ትላንት ምሽት ከ ዩዲኔዜ ጋር ያደረገውን ጨዋታ በአርናቶቪች እና አሴላኒ ግቦች 2ለ0 በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል።
በኮፓ ኢጣልያ ሩብ ፍፃሜ
- ኤሲ ሚላን ከ ሮማ
- ላዚዮ ከ ኢንተር ሚላን
- ጁቬንቱስ ከ ካግሊያሪ
- ቦሎኛ ከ አታላንታ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።
ሁሉም ጨዋታዎች በየካቲት ወር ውስጥ እንደሚካሄዱ ተገልጿል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
-Mackbook Air M3 (2024)
16GM RAM
256GB SSD Storage
175,000 birr
Contact us :
0953964175 @heymobile
Facebook |Instagram |Telegram
@Heyonlinemarket
ሰማያዊዎቹ ድል አድርገዋል !
በአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ስድስተኛ ጨዋታ ቼልሲ ከአየርላንዱ ክለብ ሻምሮክ ሮቨርስ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 5ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
የቼልሲን የማሸነፊያ ግቦች ማርክ ጉዩ 3x ፣ ኩኩሬላ እና ዴውስቡሪ ሀል ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።
ቼልሲ በአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ያደረጋቸውን ስድስት ጨዋታዎች በአሸናፊነት መወጣት ችሏል።
ይህንንም ተከትሎ ቼልሲ የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ደረጃ ሰንጠረዥን በበላይነት በማጠናቀቅ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅለዋል።
በውድድሩ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?
1️⃣ ቼልሲ :- 18 ነጥብ
1️⃣1️⃣ ሻምሮክ ሮቨርስ :- 11ነጥብ
@tikvahethsport @kidusyoftahe
88 '
ቶተንሀም 4-2 ማንችስተር ዩናይትድ ( ካራባኦ ካፕ )
⚽⚽ ሶላንኬ ⚽ ዚርኪዜ
⚽ ኩሉሴቭስኪ ⚽ አማድ ዲያሎ
⚽ ሰን
ቼልሲ 5-1 ሻምሮክ ሮቨርስ ( ኮንፈረንስ ሊግ )
⚽⚽⚽ ጉዩ ⚽ ፖም
⚽ ዴውስቡሪ
⚽ ኩኩሬላ
@tikvahethsport @kidusyoftahe
72'
ቶተንሀም 3-2 ማንችስተር ዩናይትድ ( ካራባኦ ካፕ )
⚽⚽ ሶላንኬ ⚽ ዚርኪዜ
⚽ ኩሉሴቭስኪ ⚽ አማድ ዲያሎ
ቼልሲ 5-1 ሻምሮክ ሮቨርስ ( ኮንፈረንስ ሊግ )
⚽⚽⚽ ጉዩ ⚽ ፖም
⚽ ዴውስቡሪ
⚽ ኩኩሬላ
@tikvahethsport @kidusyoftahe
61'
ቼልሲ 5-1 ሻምሮክ ሮቨርስ ( ኮንፈረንስ ሊግ )
⚽⚽⚽ ጉዩ ⚽ ፖም
⚽ ዴውስቡሪ
⚽ ኩኩሬላ
ቶተንሀም 3-0 ማንችስተር ዩናይትድ ( ካራባኦ ካፕ )
⚽⚽ ሶላንኬ
⚽ ኩሉሴቭስኪ
@tikvahethsport @kidusyoftahe