ተጀመረ
ማንችስተር ዩናይትድ 0-0 አርሰናል
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሰማያዊዎቹ ድል አድርገዋል !
በፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቼልሲ ከሌስተር ሲቲ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
የሰማያዊዎቹን የማሸነፊያ ግብ ማርክ ኩኩሬላ ማስቆጠር ችሏል።
ሌስተር ሲቲ ሰባተኛ ተከታታይ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።
በሌላ ጨዋታ ቶተንሀም ከበርንማውዝ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።
የቶተንሀምን ግቦች ሰን ሁንግ ሚን እና ሳር ሲያስቆጥሩ ለበርንማውዝ ታቬርኔር እና ኢቫኒልሰን ከመረብ አሳርፈዋል።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
4️⃣ ቼልሲ :- 49 ነጥብ
1️⃣9️⃣ ሌስተር ሲቲ :- 17 ነጥብ
ቀጣይ መርሐግብር ?
እሁድ - አርሰናል ከ ቼልሲ
እሁድ - ሌስተር ሲቲ ከ ማንችስተር ዩናይትድ
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የዩናይትድ ደጋፊዎች ተቃውሟቸውን አሰሙ !
የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ከአርሰናል ጨዋታ በፊት በክለቡ ስታዲየም አቅራቢያ ተቃዋሚዎችን በማቅረብ ላይ ናቸው።
ደጋፊዎቹ የክለቡን ባለቤት የግሌዘር ቤተሰቦች በመቃወም መፈክሮችን ሲያሰሙ ተስተውለዋል።
በተቃውሞ ሰልፉ የተገኙ የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች በቀረበላቸው ጥሪ መሰረት ጥቁር ለብሰው ታይተዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
62 '
ቼልሲ 1-0 ሌስተር ሲቲ
⚽ ኩኩሬላ
ቶተንሀም 1-2 በርንማውዝ
⚽ ሳር ⚽ ታቨርኔር
⚽ ኢቫኒልሰን
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ተጠናቀቀ | ሄታፌ 2-1 አትሌቲኮ ማድሪድ
⚽⚽ አራምባሪ ⚽ ሶርሎት
- የአሰልጣኝ ዲያጎ ሲሞኒው ቡድን አትሌቲኮ ማድሪድ በመጨረሻ ደቂቃዎች በተቆጠሩበት ሁለት ግቦች ሊሸነፍ ችሏል።
- በጨዋታው አንሄል ኮርያ ቀይ ካርድ የተመለከተ ሲሆን ከእሱ መውጣት በኋላ በተቆጠሩ ግቦች አትሌቲኮ ማድሪድ ተሸንፏል።
- አትሌቲኮ ማድሪድ መሸነፉን ተከትሎ የሊጉን መሪነት ከባርሴሎና የሚረከብበትን እድል ሳይጠቀም ቀርቷል።
- አትሌቲኮ ማድሪድ ከባርሴሎና ሀምሳ ስድስት ነጥቦችን በመሰብሰብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
እረፍት
ቼልሲ 0-0 ሌስተር ሲቲ
ቶተንሀም 0-1 በርንማውዝ
⚽ ታቨርኔር
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ቀመረኛው!!
ዛሬም የሚያሸንፉባቸው የእለቱ የውርርድ ጥቆማዎች እነሆ!
አሁን ነው ማሸነፍ እድሜ ለቀመረኛው!!
ቀመረኛው - በቤቲካ ብቻ!
የሊቨርፑል እና ፒኤስጂን ጨዋታ ማን ይመራዋል ?
የፊታችን ማክሰኞ በሊቨርፑል እና ፒኤስጂ መካከል የሚደረገውን ተጠባቂ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።
ማክሰኞ ምሽት 5:00 የሚደረገውን ተጠባቂ የመልስ ጨዋታ ሮማኒያዊው ዳኛ እስቴቫን ኮቫችስ በመሀል ዳኝነት እንደሚመሩት ተገልጿል።
ዋና ዳኛው ባለፈው አመት ፒኤስጂ ባርሴሎናን በሜዳው 4ለ1 ያሸነፈበትን የሻምፒየንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ መርተዋል።
ፒኤስጂ የመጀመሪያውን ጨዋታ በሜዳው 3ለ2 ተሸንፎ ባርሴሎናን በሜዳው 4ለ1 በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀላቸው አይዘነጋም።
የመጀመሪያውን ዙር ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ሊቨርፑል ከሜዳው ውጪ1ለ0 በማሸነፍ መመለሳቸው ይታወቃል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
አርሰናል ሀላፊ ለመሾም ተስማማ !
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በኤዱ ጋስፐር ምትክ አዲስ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ለመሾም ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል።
መድፈኞቹ የቀድሞውን የአትሌቲኮ ማድሪድ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር አንድሬ ቤርታ በሀላፊነት ለመሾም ከስምምነት መድረሳቸውን ዘ አትሌቲክ አረጋግጧል።
አንድሬ ቤርታ ከተለያዩ ክለቦች ጥያቄዎች ቢቀርቡላቸውም ለአርሰናል ቅድሚያ በመስጠት ክለቡን ለመቀላቀል መስማማታቸው ተነግሯል።
ጣልያናዊው ስፖርቲንግ ዳይሬክተር አንድሬ ቤርታ በአትሌቲኮ ማድሪድ ቤት ከአሰልጣኝ ዲያጎ ሲሞኒ ጋር ለአስራ ሁለት አመታት ሰርተዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
Can PlayStation
PlayStation 5 Packed jestic በ 11,000ብር
ብዛት አቅርበናል
ለክፍለ ሀገር እናቀርባለን ይደውሉ
በቅናሽ PlayStation ይግዙ
ከ Can PlayStation
PlayStation 4 Dubai jestic=3500
Ps4 Dubai Used Orginal jestic=5000
PlayStation 5 Packed jestic=11,000
🤝Tanks for choice
አድራሻ፦
ቁጥር 1 መገናኛ ሱቅ የአድራሻ ለውጥ በቅርቡ ስለምናደርግ ከመምጣቶ በፊት አስቀድመው ይደውሉ
ቁጥር 2 ቦሌ Celavi burger አጠገብ ዘንባባ ህንፃ ምድር ላይ
ስልክ፦ 0910529770 ወይም 0977349492
0914646972 ይደውሉ
ለአዳዲስ መረጃ Telegram channel join ይበሉ ፦
/channel/CanPlaystation
👍Update Your Life
#TeamEthiopia 🇪🇹
የኢትዮጵያ ከ 17ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከካሜሩን ጋር ያደረገውን የአለም ዋንጫ ማጣርያ ሁለተኛ ዙር የመጀመርያ ጨዋታ 5ለ2 ተሸንፏል።
ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች የመልሱን ጨዋታ በሚቀጥለው ሳምንት ቅዳሜ አዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ይደረጋል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
የባርሴሎና ጨዋታ ተራዘመ !
የባርሴሎና ኤና ኦሳሱና የሊግ መርሐግብር ለሌላ ጊዜ መራዘሙን የስፔን እግርኳስ ፌዴሬሽን በይፋ አስታውቋል።
ጨዋታው የተራዘመው በባርሴሎና መልበሻ ክፍል ያለ የተጨዋቾቹ ቅርብ ሰው ህይወቱ ማለፉን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል።
ለክለቡ ቅርብ የሆኑ የመረጃ ምንጮች ህይወታቸው ያለፈው ግለሰብ የዋናው ቡድን ሀኪም መሆናቸውን ገልጸዋል።
ተጨዋቾቹ ጨዋታው እንዲራዘም መጠየቃቸው ሲገለፅ የስፔን እግርኳስ ፌዴሬሽን እና ላሊጋውም መስማማታቸው ተነግሯል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ይገምቱ ይሸለሙ
የባርሴሎና እና ኦሳሱናን ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።
የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?
√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።
√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 5:00 ሰዓት ብቻ ነው።
🔴 ይነበብ
አንድ የቤተሰባችን አባል ግምት ማስቀመጥ የሚችለው #አንዴ ብቻ ነው። ከአንድ ጊዜ በላይ የመለሰ ቤተሰባችን ሽልማት አይደርሰውም።
መልካም ዕድል !
@tikvahethsport
31 '
ካሜሩን 3 - 1 ኢትዮጵያ
ጨዋታውን በተከታዩ ሊንክ መከታተል ይቻላል።
በቀጥታ ለመከታተል https://web.facebook.com/allezleslionscmr/videos/1294875474907638
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ሊቨርፑል መቼ አሸናፊ መሆኑን ያረጋግጣል ?
የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ከሳውዝሀምፕተን ድል በኋላ ፕርሚየር ሊጉን በአስራ ስድስት ነጥቦች ልዩነት መምራት ጀምሯል።
ሀያ ዘጠኝ የሊግ መርሐ ግብሮችን ያደረገው ሊቨርፑል ሊጉን ለማጠናቀቅ ቀሪ #ዘጠኝ ጨዋታዎች ይቀሩታል።
ሊቨርፑል በቀጣይ ከቀሪ ዘጠኝ ጨዋታዎች ስድስቱን የሚያሸንፍ ከሆነ በይፋ የሊግ አሸናፊነቱን የሚያረጋግጥ ይሆናል።
ሊቨርፑል ተከታታይ ስድስት ጨዋታዎችን የሚያሸንፍ ከሆነ ከቼልሲ ጋር በሚያደርገው የሊግ ጨዋታ ሻምፒዮንነቱን ያረጋግጣል።
በሌላ በኩል በሊጉ ፉክክር ውስጥ የሚገኙት መድፈኞቹ ቀሪ ሁለት ጨዋታዎቻቸውን የሚያሸንፉ ከሆነ የነጥብ ልዩነቱን ወደ አስር ማጥበብ ይችላሉ።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
" ለማሸነፍ እንፋለማለን " አሞሪም
የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ቡድናቸው አርሰናልን ለማሸነፍ እንደሚፋለም ገልጸዋል።
" ከምርጥ ቡድን ጋር ትልቅ ጨዋታ ነው ያሉት ሩበን አሞሪም ጨዋታው ለደጋፊው ምን ማለት እንደሆነ እናውቃለን ለማሸነፍ እንፋለማለን " ብለዋል።
አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በበኩላቸው " ትልቅ ጨዋታ ነው የምናደርገው ትልቅ አድል ነው ፣ ጨዋታችንን ተጫውተን ጥሩ ውጤት ይዘን መውጣት አለብን " ብለዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
86 '
ቼልሲ 1-0 ሌስተር ሲቲ
⚽ ኩኩሬላ
ቶተንሀም 2 - 2 በርንማውዝ
⚽ ሳር ⚽ ታቨርኔር
⚽ ሰን ⚽ ኢቫኒልሰን
@tikvahethsport @kidusyoftahe
73 '
ቼልሲ 1-0 ሌስተር ሲቲ
⚽ ኩኩሬላ
ቶተንሀም 1- 2 በርንማውዝ
⚽ ሳር ⚽ ታቨርኔር
⚽ ኢቫኒልሰን
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ይገምቱ ይሸለሙ
የማንችስተር ዩናይትድ እና አርሰናልን ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።
የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?
√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።
√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 1:30 ሰዓት ብቻ ነው።
🔴 ይነበብ
አንድ የቤተሰባችን አባል ግምት ማስቀመጥ የሚችለው #አንዴ ብቻ ነው። ከአንድ ጊዜ በላይ የመለሰ ቤተሰባችን ሽልማት አይደርሰውም።
መልካም ዕድል !
@tikvahethsport
" ጠንካራ ድጋፍ ያስፈልገናል " ማሬስካ
የሰማያዊዎቹ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የክለቡ ደጋፊዎች በዛሬው የሌስተር ሲቲ ጨዋታ ጠንካራ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
“ ደጋፊዎቻችን ዘጠና ደቂቃ ያስፈልጉናል “ ያሉት አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ጨዋታውን ማሸነፍ በጣም ያስፈልገናል በማለት ገልጸዋል።
“ ጨዋታውን ማሸነፍ የምናልመውን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ቦታ ለማግኘት አንድ እርምጃ ይወስደናል “ ሲሉ ኢንዞ ማሬስካ ተናግረዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የየእለቱን የቲክቫህ ዜናዎችን በSMS እናግኝ! 🗞📲
ከሳፋሪኮም ቁጥራችን 'A’ ብለን ወደ 30000 SMS አሁኑኑ በመላክ ወይም ወደ *799# በመደወል የቲክቫህ ትኩስ መረጃዎችን እናግኝ!
በቀን 1ብር ብቻ! ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት ⚡️
🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
" ሬንስ የበለጠ ፈትኖናል " ኤንሪኬ
የፒኤስጂው ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ትላንት ምሽት ከሬንስ ጋር ያደረጉት የሊግ ጨዋታ ከሻምፒየንስ ሊጉ ጨዋታ የበለጠ ፈታኝ ሆኖብን ነበር በማለት ተናግረዋል።
ፒኤስጂ ትላንት ምሽት ባደረገው የሊግ መርሐ ግብር ሬንስን 4ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል።
ከጨዋታው በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት የፒኤስጂው አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ " ሬንስ ከአንድ አንድ የሻምፒየንስ ሊግ ቡድኖች በበለጠ ፈትኖን ነበር።" ብለዋል።
የፒኤስጂ ተጨዋቾች ከሊቨርፑል ይልቅ በሻምፒየንስ ሊጉ የገጠሟቸው አርሰናል እና ባየር ሙኒክ “ ከባድ ናቸው “ ብለው እንደሚያምኑ ተገልጿል።
በፒኤስጂ ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው ሊቨርፑልን አንፊልድ ላይ አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር እንደሚያልፉ እርግጠኛ መሆናቸው ተነግሯል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች !
9:00 ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና
10:00 ሄታፌ ከ አትሌቲኮ ማድሪድ
11:00 ቼልሲ ከ ሌስተር ሲቲ
11:00 ቶተንሀም ከ በርንማውዝ
11:00 ናፖሊ ከ ፊዮሬንቲና
12:00 ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ስሑል ሽረ
12:15 ሪያል ማድሪድ ከ ራዮ ቫዬካኖ
1:30 ማንችስተር ዩናይትድ ከ አርሰናል
2:00 ኢምፖሊ ከ ሮማ
4:45 ጁቬንቱስ አታላንታ
🔴የዛሬው የይገምቱ ሽልማታችን የቼልሲ ፣ ሪያል ማድሪድ እና ማንችስተር ዩናይትድ ከአርሰናል ጨዋታዎች ናቸው።
🔴 የዛሬ ሽልማቶቻችን 9:30 ፣ 11:00 ፣ 12:00 ሰዓት ላይ ወደ ቤተሰቦቻችን የሚደርሱ ይሆናል።
⏩ ያንብቡ
🔴 መገመት የሚቻለው በተጠቀሱት ሰዓቶች ላይ ብቻ ነው።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
The National Finance Academy (NFA), the only accredited training institution for Insurance in the country, is pleased to announce the launch of its 4-month Professional Diploma Program in Insurance.
As part of our commitment to social responsibility, NFA offers FULL and PARTIAL scholarships in collaboration with Ethiopian Reinsurance Company, Africa Reinsurance Company, Association of Ethiopian Insurers, Ethio Life and General Insurance, Awash Insurance S.C, and Africa Insurance S.C.
Registrar Office: Around Magenagna infront of Ministry of Agriculture Tel: +251116661297 or +251945253515
#Update
የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የዋናው ቡድን ሀኪም የነበሩት ካርልስ ሚናሮ ጋርሽያ ዛሬ ምሽት ህይወታቸው ማለፉን በይፋ አስታውቋል።
በዚህም ምክንያት ባርሴሎና ዛሬ ምሽት ከኦሳሱና ጋር ሊያደርገው የነበረው የሊግ መርሐግብር ለሌላ ጊዜ ተራዝሟል።
የባርሴሎና መልበሻ ቤት ከህክምና ባለሙያው ህልፈተ ህይወት በኋላ መረበሹን የሚወጡ ዘገባዎች አመላክተዋል።
የህክምና ባለሙያው በባርሴሎና መልበሻ ቤት ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው እና በሁሉም የሚወደዱ ባለሙያ እንደነበሩ ተዘግቧል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
72 '
ካሜሩን 4 - 1 ኢትዮጵያ
ጨዋታውን በተከታዩ ሊንክ መከታተል ይቻላል።
https://www.facebook.com/share/v/1BCkVmzM9d/?mibextid=wwXIfr
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ኤሲ ሚላን ወደ ድል ተመልሰዋል !
በጣልያን ሴርያ የሀያ ስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኤስ ሚላን ከሊቼ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።
የኤሲ ሚላንን የማሸነፊያ ግቦች ክርስቲያን ፑልሲች 2x እና አንቶኒኖ ጋሎ ከመረብ ሲያሳርፉ ክርስቶቪች ለሊቼ አስቆጥሯል።
ኤሲ ሚላን ከሶስት ተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ ወደ ድል መመለስ ችለዋል።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
8️⃣ ኤሲ ሚላን :- 44 ነጥብ
1️⃣6️⃣ ሊቼ :- 28 ነጥብ
ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?
አርብ - ጂኖኣ ከ ሊቼ
ቅዳሜ - ኤሲ ሚላን ከ ኮሞ
@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Ethiopia 🇪🇹
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከካሜሩን ጋር እያደረገ የሚገኘውን ጨዋታ በተከታዩ ሊንክ መከታተል ይቻላል።
በቀጥታ ለመከታተል https://web.facebook.com/allezleslionscmr/videos/1294875474907638
21 ' ካሜሩን 1-1 ኢትዮጵያ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ሊቨርፑል መሪነቱን አጠናክሯል !
የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ከሳውዝሀምፕተን ጋር ያደረገውን የሊግ መርሐ ግብር 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች መሐመድ ሳላህ 2x እና ዳርዊን ኑኔዝ ሲያስቆጥሩ ለሳውዝሀምፕተን ስሞልቦን ከመረብ አሳርፏል።
ግብፃዊው ተጨዋች መሐመድ ሳላህ በውድድር ዘመኑ ሀያ ሰባተኛ የሊግ ግቡን አስቆጥሯል።
መሐመድ ሳላህ በ 2️⃣4️⃣3️⃣ ግቦች በታሪክ የሊቨርፑል ሶስተኛው ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን አዲስ ታሪክ ፅፏል።
መሐመድ ሳላህ በሊቨርፑል ታሪክ በአንድ የውድድር አመት አርባ አራት የግብ ተሳትፎ ያደረገ የመጀመሪያው ተጨዋች ሆኗል።
በሌሎች ጨዋታዎች
- ብራይተን ፉልሀምን 2ለ1 ሲያሸንፍ
- ክሪስታል ፓላስ ኢፕስዊች ታውንን 1ለ0 ማሸነፍ ችለዋል።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
1️⃣ ሊቨርፑል :- 70 ነጥብ
2️⃣0️⃣ ሳውዝሀምፕተን :- 9 ነጥብ
ቀጣይ መርሐ ግብር ?
ረቡዕ - ሊቨርፑል ከ ኤቨርተን
ቅዳሜ - ሳውዛምፕተን ከ ዎልቭስ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe