“ ዋንጫ ማሸነፍ እፈልጋለሁ “ ዳኒ ኦልሞ
ስፔናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዳኒ ኦልሞ በቀጣይ ዋንጫዎችን ማሸነፍ እንደሚፈልግ በሰጠው አስተያየት ገልጿል።
የተገባደደው 2024 ለእሱ የተለየ አመት እንደነበር የገለፀው ዳኒ ኦልሞ “ ከስፔን ጋር ዋንጫ የማሳካት እና በባርሴሎና ማለያ የመጫወት ትልቅ ህልማን ያሳካሁበት ነበር “ ብሏል።
ዳኒ ኦልሞ አክሎም በቀጣይ ከባርሴሎና እና ስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር ዋንጫ ማሸነፍ እንደሚፈልግ ተናግሯል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Ethiopia 🇪🇹
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሱዳን አቻው ጋር ያደረገውን የቻን አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።
የዋልያዎቹን ብቸኛ ግብ ብርሀኑ በቀለ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በደርሶ መልስ ውጤት 4ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፎ ለውድድሩ ማለፍ ሳይችል ቀርቷል።
የሱዳን ብሔራዊ ቡድን ኬንያ ፣ ታንዛኒያ እና ዩጋንዳ በጣምራ በሚያዘጋጁት የ 2025 ቻን አፍሪካ ዋንጫ ውድድር የሚሳተፍ ይሆናል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
65 '
ሱዳን 1-1 ኢትዮጵያ
⚽ ሙሳ ካንቴ
ድምር ውጤት :- 3-1
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
#እረፍት
ሱዳን 1-0 ኢትዮጵያ
⚽ ሙሳ ካንቴ
ድምር ውጤት :- 3-0
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
12 '
ሱዳን 0-0 ኢትዮጵያ
ድምር ውጤት :- 2-0
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !
11:00 ሱዳን ከ ኢትዮጵያ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ዩናይትድ የበዓል ዝግጅቱን በመሰረዙ ስንት አተረፈ ?
አዲሱ የማንችስተር ዩናይትድ ባለሀብት ሰር ጂም ራትክሊፍ የክለቡን የፋይናንስ ሁኔታ ለማስተካከል ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።
ክለቡ ወጪውን ለመቀነስ በማሰብ የተለያዩ አላስፈላጊ ያላቸውን ወጪዎች መቀነስን ጨምሮ ሰራተኞቹን ከስራቸው አሰናብቷል።
ማንችስተር ዩናይትድ በተጨማሪም የክለቡን ወጪ ለመቀነስ በማሰብ ክለቡ በየአመቱ የሚያዘጋጀውን ባህላዊ የገና በዓል ዝግጅት ሰርዟል።
የገና በዓል ዝግጅቱን የመሰረዙ ውሳኔ በማንችስተር ዩናይትድ ውስጥ ሁሉንም ሰው ያበሳጨ እንደነበር ተዘግቧል።
አሁን ላይ ማንችስተር ዩናይትድ የገና በዓል ዝግጅቱን በመሰረዙ 250,000 ፓውንድ ወጪ ለማትረፍ መቻሉን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ቫርዲ ለሊቨርፑል ጨዋታ ላይደርስ ይችላል !
ሌስተር ሲቲ ሐሙስ ከሊጉ መሪ ሊቨርፑል ጋር በሚያደርጉት ተጠባቂ መርሐግብር የጄሚ ቫርዲን ግልጋሎት ላያገኙ ይችላሉ።
ተጨዋቹ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት በጨዋታው መድረሱ አጠራጣሪ መሆኑን አሰልጣኝ ሩድ ቫን ኔስትሮይ አረጋግጠዋል።
ጄሚ ቫርዲ በውድድር አመቱ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ስድስት የሊግ ግቦችን በማስቆጠር ጥሩ የውድድር አመት በማሳለፍ ላይ ይገኛል።
በተጨማሪም በጉዳት ላይ የሚገኘው ግብ ጠባቂው ማድስ ሄርማንሰን በጨዋታው እንደማይመለስ አሰልጣኙ ጠቁመዋል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ኦስካር ወደ ቀድሞ ክለቡ ተመለሰ !
ብራዚላዊው የቀድሞ የቼልሲ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኦስካር ወደ ቀድሞ የልጅነት ክለቡ ሳኦ ፓውሎ መመለሱ ይፋ ተደርጓል።
የ 33ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኦስካር ከቻይናው ክለብ ሻንጋይ ፖርት ጋር ከሰባት የውድድር አመታት በኋላ መለያየቱ ይታወሳል።
ኦስካር አሁን ላይ ሳኦ ፓውሎን ለሶስት የውድድር አመታት ለመቀላቀል ፊርማውን ማኖሩ ተገልጿል።
" ባለፉት ጥቂት ቀናት በማህበራዊ ሚዲያ ለተሰጠኝ ፍቅር አመሰግናለሁ በቀጣይ በጋራ ትልቅ ነገሮችን እንድናሳካ የተቻለኝን አደርጋለሁ።“ ሲል ኦስካር ተናግሯል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ሲቲ ወደ ዋንጫ ፉክክሩ ይመጣል “ ማሬስካ
የሰማያዊዎቹ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ስለ ዋንጫ ፉክክር ያለማሰባቸው ምክንያት “ ጫና ሳይሆን እውነት ነው " በማለት ተናግረዋል።
የዋንጫ ፉክክር ውስጥ የለንም ማለታቸው ጫና በመፍራት አለመሆኑን ያነሱት ኢንዞ ማሬስካ “ እንደዚህ አይነት ጫናዎች መቋቋም እንፈልጋለን ነገርግን የተናገርነው እውነታ ነው “ ብለዋል።
ኢንዞ ማሬስካ አክለውም “ ማንችስተር ሲቲ በመጨረሻ ሰዓት ወደ ዋንጫ ፉክክሩ ይመጣል “ ሲሉ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
“ ማንችስተር ሲቲ ከዚህ በፊት ገጥሟቸው በማያውቅ ችግር ውስጥ እያለፉ ነው በየጨዋታው ጉዳት እያጋጠማቸው ነው አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ናቸው።“ ማሬስካ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ያልተጠበቁ ውጤቶች ያስተናገደው የዘንድሮ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አሁንም እንደቀጠለ ነው!
ቦክሲንግዴይ ፍልሚያ ደግሞ ታህሳስ 17 እና 18 ይካሄዳል! የሊጉ መሪ ሊቨርፑል የነጥብ ልዩነቱን ያሰፋል ወይስ ቼልሲ፥ አርሰናልና ማን ሲቲ ልዩነቱን ያጠቡታል?
ያጓጓል!
👉እነዚህን ድንቅ ፍልሚያዎች ጨምሮ ሌሎች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይመልከቱ።
ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh
ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et
#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
" አሁን ላይ ለእኛ ቀላል ተጋጣሚ የለም " ጋርዲዮላ
የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድናቸው ሐሙስ ከኤቨርተን ጋር ከሚያደርገው የሊግ መርሐግብር በፊት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ምን አሉ ?
- ኤቨርተን ቀላል ተጋጣሚ ነው ብለን አናስብም አሁን ባለንበት ሁኔታ ለእኛ ቀላል የሚባል ተጋጣሚ የለም።
- በጨዋታው ወደ አሸናፊነት መመለስ እንፈልጋለን ጊዜ ይወስዳል ነገርግን በቻልነው ፍጥነት ነጥብ ማግኘት አለብን።
- ኤቨርተን ጥሩ አቋም ላይ ሆኖ ነው የምንገጥመው ጥሩ መሆናቸውን ቁጥሮች እና እንቅስቃሴያቸው ያሳያል።
- ኤርሊንግ ሀላንድ ለእኛ ወሳኝ ተጨዋች ነው እሱን በጥሩ መንገድ ለመጠቀም የተሻሉ ነገሮችን ማድረግ አለብን።"ሲሉ ተደምጠዋል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ባርሴሎና ተጨዋቹ ጉዳት አጋጥሞታል !
የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የፊት መስመር ተጨዋቹ ፌራን ቶሬስ የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠመው ተገልጿል።
ስፔናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ፌራን ቶሬስ ባርሴሎና በአትሌቲኮ ማድሪድ በተሸነፈበት ጨዋታ ጉዳት እንዳጋጠመው ክለቡ አስታውቋል።
ባርሴሎና ተጨዋቹ ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ሜዳ የሚመለስበትን ጊዜ በግልጽ አላስቀመጠም።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ዴቪድ ኩት ይግባኝ መጠየቅ አይፈልጉም !
የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዳኛ የነበሩት ዴቪድ ኩት የፕርሚየር ሊጉ ፕሮፌሽናል ዳኞች ማኅበር ከስራቸው እንዳሰናበታቸው ይታወቃል።
ዋና ዳኞው በቅርቡ በተሰራጨ የቪዲዮ ቅጂ ሊቨርፑልን እና የቀድሞ አሰልጣኛቸውን የርገን ክሎፕን ሲሳደቡ እና ሲተቹ ተስተውለው እንደነበር ይታወሳል።
የ 49ዓመቱ ዳኛ ዴቪድ ኩት አሁን ላይ ከስራቸው የተባረሩበትን ውሳኔ ለመቀበል ማሰባቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።
ዋና ዳኛው ውሳኔውን ተተቃውመው ለእንግሊዝ ፕሮፌሽናል ተጨዋቾች ማኅበረ ይገባኝ መጠየቅ እንደማይፈልጉ ተነግሯል።
ይህንንም ተከትሎ ዋና ዳኛውን ከዚህ በኋላ በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች የማንመለከታቸው ይሆናል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ትኩረቴ ራሽፎርድን ማሻሻል ላይ ነው “ አሞሪም
የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ማርከስ ራሽፎርድ የሰጠውን ቃለምልልስ ወደ ጎን በመተው አቋሙ ላይ ብቻ እያተኮሩ መሆኑን ገልጸዋል።
“ አሁን ላይ ትኩረት እያደረኩ ያለሁት ራሽፎርድን ማሻሻል ላይ ብቻ ነው “ ያሉት ሩበን አሞሪም " እንደሱ አይነት ተሰጥኦ ያለው ተጨዋች ያስፈልገናል " ብለዋል።
" እሱ ያደረገውን ቃለምልልስ ረስቼ ሜዳ ላይ የማየውን ነገር ብቻ እየተመለከትኩ ነው “ ሲሉ ሩበን አሞሪም ተናግረዋል።
አሰልጣኙ አክለውም “ እንደ አሰልጣኝ ትኩረት የማደርገው የእሱ አቋም እና ልምምድ ላይ ነው ሌላው ጊዜው ሲደርስ ቢሆን ለእኔም ለክለቡም ጥሩ ነው።“ ብለዋል።
“ እንደዚህ አይነት ተጨዋቾች በዙሪያቸው ብዙ ሰዎች እንዳሉ እረዳለሁ አንዳንድ ጊዜ የራሳቸው ሀሳብ ያልሆነ ውሳኔም ይወስናሉ።“ ሩበን አሞሪም
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
#Wanaw
✨የነገው የኢትዩጵያ እግርኳስ ተስፈኞችን የሚያበቃው......ዋናው የስፖርት ትጥቅ አምራች!!!✨
ለበለጠ መረጃ
📞8️⃣2️⃣8️⃣9️⃣ ላይ ይደውሉ
ማህበራዊ ገጾቻችን
Instagram|Facebook |TikTok |X|wanawsportswear?si=TSJ9HZINs4MzMPj2">Youtube
🌍በአፍሪካውያን የተመረተ 🌍
🏅ዋናው ወደፊት»»»Читать полностью…
68 '
ሱዳን 2-1 ኢትዮጵያ
⚽ ሙሳ ካንቴ ⚽ ብርሀኑ በቀለ
⚽ መሐመድ አብዱልራህማን
ድምር ውጤት :- 4-1
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
62 '
ሱዳን 1-0 ኢትዮጵያ
⚽ ሙሳ ካንቴ
ድምር ውጤት :- 3-0
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
22 '
ሱዳን 1-0 ኢትዮጵያ
⚽ ሙሳ ካንቴ
ድምር ውጤት :- 3-0
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
“ በእኔ መፈረም የሚፀፀት የለም “ ምባፔ
የሪያል ማድሪዱ የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ በ 2025 አላማው ዋንጫ ማሸነፍ መሆኑን በሰጠው አስተያየት ገልጿል።
ስለ አዲሱ ክለቡ ሪያል ማድሪድ አስተያየቱን የሰጠው ኪሊያን ምባፔ “ ሪያል ማድሪድ ውስጥ ማንም ሰው በእኔ ፊርማ አይፀፀትም “ ሲል ተናግሯል።
ኪሊያን ምባፔ አክሎም “ በ 2025 ዋንጫ ማሸነፍ እፈልጋለሁ አላማዬ ይህ ነው “ ሲል በቀጣይ በክለቡ ስላለው እቅድ ገልጿል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
“ መሐመድ ሳላህ እንደ ማሽን ነው “ ሉዊስ ዲያዝ
የሊቨርፑሉ የፊት መስመር ተጨዋች ሉዊስ ዲያዝ መሐመድ ሳላህ በየቀኑ ራሱን ማሻሻል ለሚፈልግ ተጨዋች ትልቅ ምሳሌ መሆኑን ገልጿል።
“ ሳላህ ሁለት ወይም ሶስት ግቦችን ቢያስቅጥርም እንኳን በቀጣይ ቀን ስለ ሚቀጥለው ጨዋታ ነው የሚያስበው “ ሲል ሉዊስ ዲያዝ ተናግሯል።
“ መሐመድ ሳላህ ለእኔ እንደ ማሽን ነው “ የሚለው ዲያዝ እሱ በየቀኑ መሻሻል ለሚፈልግ ሰው ትልቅ ምሳሌ የሆነ ተጨዋች ነው ከእሱ ብዙ መማር ይቻላል ብሏል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
አታላንታ ቀዳሚው ክለብ ነው !
የጣልያን ሴርያው ክለብ አታላንታ በዘንድሮው የውድድር አመት ሶስት ተጨዋቾቹ ከአስር በላይ የሊግ ግቦችን ማስቆጠር ችለዋል።
ይህንንም ተከትሎ አታላንታ ከአምስቱ የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ሶስት ተጨዋቾቹ ከአስር በላይ ግብ ያስቆጠሩ ብቸኛው ክለብ አድርጎታል።
በውድድሩ ዘመኑ
- ሬትጉዮ :- 14 ግብ
- አዴሞላ ሉክማን :- 12 ግብ እንዲሁም
- ዴ ኬቴሌር :- 10 የሊግ ግቦችን ለአታላንታ አስቆጥረዋል።
በአሰልጣኝ ጂያን ፔሮ ጋስፔሪኒ የሚመራው አታላንታ በ 4️⃣0️⃣ ነጥብ ሴርያውን በመምራት ላይ ይገኛል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ቪክቶር ኦሲሜን ድጋፍ አድርጓል !
ናይጄሪያዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪክቶር ኦሲሜን ለገና በዓል ምግብ የመግዛት አቅም ለሌላቸው ሰዎች ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል።
ተጨዋቹ በሀገሩ ናይጄሪያ ትውልድ መንደሩ የመግዛት አቅም ለሌላቸው ሰዎች ምግብ ይዞ በመሄድ ማከፋፈሉ ተነግሯል።
“ ለእናቶቻችን ምግብ መከፋፈል አለበት ላደረጋችሁልነኝ ነገር እናንተን አመሰግናለሁ የምልበት ትንሽ መንገድ ይሄ ነው “ ሲል ቪክቶር ኦስሜን ተናግሯል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
🤩የቤቲካ ምርጥ የቀኑ አሸናፊዎች ! 🤩
🌟ደንበኞቻችን ተወራርደው በትልቁ አሸንፈዋል !
🥁ቀጣዩ የእናንተ ተራ ነው !
🌟አሁኑኑ Betika.et ላይ ይወራረዱ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
“ ጠንካራ መሆን አለብን “ ሩበን አሞሪም
የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ቡድናቸው ጥሩ ያልሆነ ጊዜ ላይ ቢሆንም ጠንካራ መሆን አለብን ሲሉ ገልጸዋል።
“ አሁን ያለንበት ሁኔታ ከክለባችን አስከፊ ጊዜያት አንዱ ሊሆን ይችላል “ የሚሉት ሩበን አሞሪም ጠንካራ መሆን እና ሁኔታውን መጋፈጥ አለብን ብለዋል።
“ አሁን ስለ በዓል አላስብም ጨዋታ ስለማሸነፍ ብቻ ነው ሀሳቤ ሙሉ ትኩረታችን ቀጣዩን ጨዋታ ስለማሸነፍ ብቻ ነው “ ሲሉ ሩበን አሞሪም ተናግረዋል።
“ ምቾት የሚሰማኝ ጊዜ ላይ አይደለሁም አስቸጋሪ ወቅት ላይ ነን ነገርግን ችግሮችን ቀስ በቀስ በመፍታት ለሁሉም ጥያቄዎች መልስ እናገኛለን።“ ሩበን አሞሪም
ሰለ ራሽፎርድ ሁኔታ ያነሱት አሰልጣኙ እሱ ቡድኑን ለማሻሻል ትልቅ ሀላፊነት አለበት “ እዚህ ብዙ አመት የቆዩ እና ትልቅ አቅም ያለባቸው ተጨዋቾች ትልቅ ሀላፊነት አለባቸው “ ብለዋል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
#wanaw_export
ዋናው የስፖርት ትጥቅ🧡የአፍሪካ ኩራት። ከላይቤሪያ እግርኳስ ቡድን በስተጀርባ አንድ ታላቅ ህዝብ አለ ዋናውን የተሻለ እንዲሰራ የሚያበረታ😊...በቅርቡ ተወዳጅ የአፍሪካ ጎረቤት ሀገርም ዋንውን ይወዳጃል!!
የትኘው ሀገር ይመስልዎታል❓❓❓
🏅ዋናው ወደፊት»»»Читать полностью…
ሲቲ የተጫዋቹን ግልጋሎት አያገኝም !
ማንችስተር ሲቲ ሐሙስ ከኤቨርተን ጋር በሚያደርገው የሊግ መርሐግብር የተጫዋቹን ግልጋሎት እንደማያገኝ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አረጋግጠዋል።
እንግሊዛዊው ተከላካይ ጆን ስቶንስ በጉዳት ምክንያት ከጨዋታው ውጪ መሆኑን አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።
ቡድናቸው ዛሬ የልምምድ መርሐግብር እንዳለው የገለፁት ፔፕ ጋርዲዮላ ምንያህል ተጨዋቾች ዝግጁ እንደሆኑ ገና አላወቅኩም ብለዋል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ቶተንሀም ተጨዋች ማስፈረም ይፈልጋል !
የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም በጥር የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት አዲስ ተጨዋቾች ማስፈረም እንደሚፈልግ አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ ተናግረዋል።
ቶተንሀም ወሳኝ ተጨዋቾቹ ቫን ዴቪን ፣ ክርስቲያን ሮሜሮ እና ግብ ጠባቂው ቪካርዮን ጨምሮ ሰባት ተጨዋቾቹ በጉዳት ላይ ይገኛሉ።
" በአንዳንድ የሜዳ ክፍሎች ስብስባችን የሳሳ ነው ቦታውን በጥር ማጠናከር አለብን " ሲሉ አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ ተናግረዋል።
ቶተንሀም በሊጉ ሀያ ሶስት ነጥቦችን በመሰብሰብ አስራ አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
አሌክስ ኢዎቢ በነፃ የሚያገለግል ሱቅ ከፍቷል !
ናይጄሪያዊው የፉልሀም የፊት መስመር ተጨዋች አሌክስ ኢዎቢ ለንደን ውስጥ በነፃ የሚያገለግል የራሱን ጊዜያዊ ሱቅ መክፈቱ ተገልጿል።
የቀድሞ የአርሰናል ተጨዋች አሌክስ ኢዎቢ በጊዜያዊ ሱቁ ለገና በዓል ምግብ ለመግዛት አቅም ለሌላቸው ሰዎች በነፃ ምግብ ማከፋፈሉ ተነግሯል።
“ የገና በዓልን ደስተኛ ሆነው እንዲያሳልፉ መርዳት ከቻልኩኝ ለምን አላደርገውም “ ሲል አሌክስ ኢዎቢ ሰዎችን በመርዳቱ ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል።
“ ሰዎች ቤተሰባቸውን ይዘው መጥተው የሚፈልጉትን ይዘው መሄድ የሚችሉበትን ቦታ መፍጠር እፈልጋለሁ “ አሌክስ ኢዎቢ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
🎁🎁 የቤቲካ የገና ስጦታዎች 🎁🎁
💰 የአቪዬተር የበአል ሽልማት 225,000 ብር ይዞ መቷል ! 💰
ብዙ ማባዣዎች(x) የሚሰበስቡ ደንበኞች 225,000 ብር ይካፈላሉ!
ታዲያ ምን ይጠብቃሉ?
ይወራረዱ፣በትልቁ ያሸንፉ፣ከስጦታ እና ጉርሻዎቹ የድርሻዎን ይውሰዱ።
ቤቲካ - የአሸናፊዎች ቤት