tikvahuniversity | Unsorted

Telegram-канал tikvahuniversity - Tikvah-University

308824

Subscribe to a channel

Tikvah-University

የተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማሯቸውን ተማሪዎች ነገ የካቲት 8/2017 ዓ.ም ያስመርቃሉ።

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ፣ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ፣ ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ እና ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ነገ ተማሪዎቻቸውን ከሚያስመርቁ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ይገኙበታል፡፡

ተቋማቱ በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ ዲግሪ፣ በሦስተኛ ዲግሪ፣ በስፔሻሊት እና በሰብ-ስፔሻሊቲ ያስተምሯቸውን ተማሪዎች ያስመርቃሉ።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#UPDATE #ExitExamResult

“ ከዲሲፒሊን ጋር በተገናኘ 540 ተማሪዎች ተለይተዋል። ከዚህኛው ውጤት እስከ መሰረዝ፣ የሚቀጥለውንም ድጋሚ ያለመፈተንና እንቅፋታቸው ትልልቅ የሆኑም እስከነጨረሻውም የሚይፈተኑበት ጊዜ ሊኖር ይችላል ” - ትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

ሃገር አቀፉን የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ከሰዓታት በፊት መለቀቁን ትምትርት ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኅብረት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸውን ነግረናችኋል።

በወቅቱም የፈተናው ውጤት የሚታይበት ሊንክ ስንጠይቅ “ ለዩኒቨርሲቲዎች ተልኳል ” በመባሉ የተለዬ መመልከቻ ካለ እንደምናጋራችሁ ቃል ገብተንላችሁ ነበር።

በዚህም፣ የውጤት መመልከቻው ሊንክ የትኛው ነው ? ስንል የጠየቅናቸው አንድ የትምህርት ሚኒስቴር አመራር በሰጡን ቃል፣ “ ውጤት የሚታይበት ሊንክ ኖርማሊ ለዩኒቨርሲቲዎች ተልኳል። ከተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ውጪ ሁሉም ማዬት እንዲችሉ ተነግሯቸዋል ” የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።

“ ሊንኩ፦ ባለፈው ኦንላይን ሳፓርቲንግ የምንጠቀምበት ፔጅ ነበረ፤ እዛ ፔጅ ላይ ተለቋል። ያውቁታል እነሱ ፤ ከዚህ በፊት የተለቀቀ ሊንክ ነው ለኤግዚት ኤግዛም የተመዘገቡበት ሊንክ ላይ ውጤት ማየት ይችላሉ ” ሲሉ አስረድተዋል።

ስንት ተማሪዎች እንዳለፉና እንደወደቁ ጠይቀናቸው ገና እንዳልታወቀ በገለጹበት አውድ፣ “ አናላይስሱ አልተሰራም። አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ቅዳሜ እለት ስለሚያስመርቁ ለእነሱ ተብሎ ነው በችኮላ የተለቀቀው ” ብለዋል።

በሌላ በኩል፣ የዲሲፒሊን ጉድለት የታየባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የፈተና ውጤት አለመለቀቁንም እኝሁ አካል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

“ የዲሲፒሊን ግድፈት ጎልቶ የታየባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ውጤት አልተለቀቀም፤ ወደ 6 በሚሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች። ከዛ ውጪ ተለቋል። ስለዚህ አናላይሲሱ የ6ቱም ተጨምሮ ሲያልቅ ይሰራል ” ሲሉ ነግረውናል።

ስለዚህ የፈተናው ውጤት በተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች ነው የተላከው ማለት ነው ? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ ፣ “ የፈተና ኮራፕሽኑ፤ ስርቆቱ የጎላባቸው 6 ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ላይ ነው እንጂ ያልተለቀቀው ሁሉም ላይ ተለቋል ” የሚል ምላሽ ነው የሰጡን።

በፈተናው ወቅት የተፈጠረ ችግር ነበር ወይስ በሰላም ተጠናቋል ? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የአመራሩ ምላሽ፣ “ በዚህኛው ፈተናችን በሰላም ነው የተጠናቀቀው። የጎላ ቸግር አልነበረም ” የሚል ነው።

አክለው ደግሞ፣ “ የተለመዱ የዲሲፒሊን ችግሮች ናቸው የነበሩት፣ የተማሪዎች ከስርቆት ጋር በተገናኘ ያልተፈቀዱ እንደ ሞባይል ያሉ ኤሌክትሮኒክ ዲቫይሶችን ለመጠቀም ሙከራ ማድረግ፣ ወጣ ያለ ደግሞ ከዚህ በፊት የተፈተኑ ተማሪዎች ገብተው ለመፈተን ሙከራ ማድረግ፣ ናቸው እንጂ በጣም የጎላ ችግር አልታዬም ” ነው ያሉት።

ከዲሲፒሊን ግድፈት ጋር በተያያዘ ስንት ተማሪዎች ተገኝተዋል ? ለሚለው ጥያቄ በሰጡን ምላሽ፣ “ ከዲሲፒሊን ጋር በተገናኘ እስካሁን ድረስ ወደ 540 ተማሪዎች ተለይተዋል። የዚህኛው ራውንድ ውጤት እስከ መሰረዝ፣ የሚቀጥለውንም ድጋሚ ያለመፈተንና እንቅፋታቸው ትልልቅ የሆኑ እስከነጨረሻውም የማይፈተኑበት ጊዜ ሊኖር ይችላል ” ብለዋል።

“ እስካሁን ግን አልተወሰነም። ለጊዜው ግን የዚህኛው ውጤት ዲስኳሊፋይድ እንደሚደረግ ነው 54ዐ ተማሪዎች የተለዩት። ቁጥሩ ሊበልጥ ይችላል፤ ለጊዜው ግን ወደ 540 ተማሪዎች ተለይተዋል ” ሲሉም አክለዋል።

(ስንት ተፈታኞች እንዳለፉና እንዳላለፉ ውጤቱን ተከታትለን በቀጣይ የምናሳውቃችሁ ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

Tikvah-University

#ExitExamResult

" የፈተናው ውጤት ተለቆ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ተልኳል " - የትምህርት ሚኒስቴር አመራር

🔴" የፈተና ውጤት ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ጋር መጥቷል " -  የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኅብረት

የሀገር አቀፍ መውጫ ፈተና ውጤት ለዩኒቨርሲቲዎች መላኩን የትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት አጭር ቃል ፥ " ፈተናው ተለቆ ለዩኒቨርሲቲዎች ተልኳል " ብለዋል።

" በነገራችን ላይ ለዩኒቨርሲቲዎች ነው የሚላከው ሊንኩም ይላክላቸዋል። ውጤት ሁሉም ዩኒቨርሲቲ ጋር ደርሷል " ሲሉ ገልጸዋል።

ምን ያክል ተማሪ አለፈ ? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ " ውጤቱ አሁን ስለተለቀቀና ለተቋማት ስለተላከ አጠቃላይ ዳታውን የምናየው ነገ ነው " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኅብረት ቡኩሉ፣  " ውጤቱ ተለቋል። የሁሉም ዩኒቨርሲቲ መጥቷል " ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ውጤት መመልከቻ ሊንኩ ደርሷችኋል ? ስንል ላቀረብንለት ጥያቄ በሰጠን ምላሽ ደግሞ፣ " ዝም ብሎ ውጤቱ ነው የመጣው " የሚል አጭር ምላሽ ሰጥቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የፈተናው ውጤት በኦንላይ የሚታይበት መንገድ ካላ ጠይቆ ያቀርባል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

Tikvah-University

#Exit_Exam_Result

ሀገር አቀፍ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት እንደሚለቀቅ ይጠበቃል።

https//:result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት ExitExam የሚለውን በመምረጥና የራስዎን User Name በማስገባት ውጤትዎን መመልከት ይችላሉ።

በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም መሠጠቱ ይታወቃል።
▬▬▬▬▬▬

ዛሬ ከሰዓት 8:00 ላይ ማስፈንጠሪያው እየሠራ የነበረ መሆኑን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተመልክቷል (ከላይ የተያያዘው ምስልም ዛሬ የተወሰደ ነው።)

ይሁን እንጂ አሁን ላይ ማስፈንጠሪያው እየሠራ አለመሆኑን ተመልክተናል። በመሆኑም ማስፈንጠሪያው ክፍት ሆኖ መስራት እስከሚጀምር በትዕግስት እንድትጠብቁ ለመግለፅ እንወዳለን።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የበንሳ ዳዬ ካምፓስ የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ቅሬታ!

ባለፈው ሐሙስ ጥር 29/2017 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በንሳ ዳዬ ካምፓስ የተገኙ ተፈታኞች፥ "በካምፓሱ በተፈጠረ የኔትወርክ መቋረጥ ምክንያት" ፈተናውን ሳይወስዱ መቅረታቸውን ለቲክቫህ ተናግረዋል፡፡

የመውጫ ፈተናውን መውሰድ የሚችሉበት ሁኔታ እንዲመቻችላቸው የካምፓሱን አመራሮች ማነጋገራቸውን፣ ይሁን እንጂ ምንም አይነት መፍትሔ አለማግኘታቸውን ለቲክቫህ ገልፀዋል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የበንሳ ዳዬ ካምፓስ ኤክዚኪዩቲቭ ዳይሬክተር የሆኑትን ፍሬው ካሳ (ዶ/ር) ጠይቀናል፡፡

በተጠቀሰው ቀን የተሰጠውን የመውጫ ፈተና "በካምፓሱ ሦስት ትምህርት ክፍሎች ተማሪዎች የሆኑ ዘጠኝ ተፈታኞች" አለመውሰዳቸውን ዋና ዳይሬክተሩ አረጋግጠዋል፡፡

በዕለቱ ፈተናው መሰጠት ሊጀምር ሲል የኢንተርኔት መቋረጥ መከሰቱንና ችግሩን በቶሎ በመቅረፍ ፈተናውን ለመስጠት ጥረት መደረጉን ፍሬው (ዶ/ር) አስረድተዋል፡፡

ካምፓሱ በሚገኝበት አካባቢ ባለ የመንገድ ሥራ ምክንያት የኢንተርኔት መቋረጥ ማጋጠሙን የገለፁት ኃላፊው፤ ከአካባቢው የኢትዮ ቴሌኮም ቅርንጫፍ ጋር በመነጋገር ችግሩን ለመፍታት ጥረት ተደርጓል ብለዋል፡፡ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ጋር በመነጋገር ተፈታኞቹ ፈተናቸውን እንዲወስዱ ጥረት መደረጉንም ገልፀዋል፡፡

የተማሪዎቹን ዕጣፈንታ በተመለከተ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ውይይት መደገሩንም አንስተዋል፡፡ በዚህም ያልተፈተኑት ተማሪዎች ዘጠኝ ብቻ በመሆናቸውና ለነሱ ብቻ ሌላ ፈተና ማዘጋጀት የሚቻል ባለመሆኑ፣ ተፈታኞቹ በቀጣይ ሰኔ ወር ላይ ፈተናቸውን እንዲወስዱ መግባባት ላይ መደረሱን ገልፀዋል፡፡ ውሳኔው ለተማሪዎቹ እንደተነገራቸውም ኃላፊው ለቲክቫህ ተናግረዋል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም በአምስት የትምህርት መስኮች በፖስት ቤዚክ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም በግል ወይም በመንግሥት ስፖንሰርነት ትምህርታችሁን መከታተል የምትፈልጉ አመልካቾችን ይቀበላል፡፡

የማመልከቻ ጊዜ፦
እስከ የካቲት 20/2017 ዓ.ም

የትምህርት መስኮች፦

✍️ Comprehensive Nursing
✍️ Neonatal Nursing
✍️ Emergency & Critical Care Nursing
✍️ Midwifery
✍️ Medical Laboratory Technology

መስፈርቶች፡-
► ዲፕሎማ ወይም TVET ደረጃ-4 ከታወቀ ተቋም
► የሥራ ልምድ አይጠይቅም
► COC ወስዶ ያለፈ/ያለፈች
► ከሥራ ቦታ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
► የመግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል/የምትችል

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

"ከአማራ ክልል ተማሪዎች 60 በመቶ የሚጠጉት ከትምህርት ገበታ ውጭ ናቸው።" - የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር


በአማራ ክልል ከሚገኙ ተማሪዎች ውስጥ 59.8 በመቶ የሚሆኑት፤ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን “ከትምህርት ገበታ ውጭ” መሆናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ገልፀዋል።

በክልሉ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል 32 በመቶ የሚሆኑት ከመማር ማስተማር ተልዕኮዋቸው መስተጓጎላቸውንም በክልሉ ም/ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ተናግረዋል።

በክልሉ በአሁኑ ወቅት “በተጨባጭ በመማር ማስተማር ሂደት እየተሳተፉ” የሚገኙ ተማሪዎች ብዛት 2.78 ሚሊዮን እንደሆኑ ጠቅሰዋል።

በአማራ ክልል በዘንድሮው በጀት ዓመት ለመመዝገብ ታቅዶ የነበረው አጠቃላይ የተማሪዎች ብዛት 7.1 ሚሊዮን እንደሆነ የክልሉ ትምህርት ቢሮ መረጃ ያመላክታል።

በአማራ ክልል በ2017 በጀት ዓመት መደበኛ የመማር ማስተማር ተግባራቸውን ያከናወኑ ትምህርት ቤቶች ብዛት 7,444 መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው ጠቅሰዋል።

በአማራ ክልል ያሉት ትምህርት ቤቶች ብዛት 10,983 ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 32 በመቶ በሚሆኑት ትምህርት ቤቶች ከመማር ማስተማር ተልዕኳቸው ተስተጓጉለው መቆየታቸው ተገልጿል። #ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነጻ ከፍተኛ የትምህርት ዕድል በኢትዮጵያ ላገኙ ደቡብ ሱዳናውያን አሸኛኘት አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት 577 በመጀመሪያ ዲግሪ እና 67 በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም በድምሩ ለ644 ደቡብ ሱዳናውያን ተማሪዎች ነጻ ከፍተኛ የትምህርት ዕድል ለ2024/25 የትምህርት ዘመን ሰጥቷል፡፡

ከነዚህ ውስጥ 110 በቴክኒክና ሙያ ስልጠና የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ነጻ የትምህርት ዕድል ያገኙ ተማሪዎች በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡

ነጻ የትምህርት ዕድሉ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የአቅም ግንባታና የሰው ሃብት ልማት ትብብር እንደሚያጠናክር በጁባ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል መሐዲ ተናግረዋል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሪፌራል ሆስፒታል ቀጥሎ በተጠቀሱት ክፍት የሥራ መደቦች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል።

የምዝገባ ጊዜ፦
እስከ የካቲት 17/2017 ዓ.ም

የምዝገባ ቦታ፡-
ወለጋ ዩንቨርሲቲ ሪፌራል ሆስፒታል የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት የሥራ ሂደት ቢሮ ቁ. 85

➫ አመልካቾች የምታቀርቡት የሥራ ልምድ ከሥራ መደቡ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው መሆን እንዲሁም ደመወዝና ከመቼ እስከ መቼ እንዳገለገሉ የሚገልጽ መሆን አለበት።

➫ አመልካቾች የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውና የማይመለስ አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡

➫ አመልካቾች የምታቀርቡት የሥራ ልምድ ማስረጃ የመንግስታዊ መስሪያ ቤት ካልሆነ የገቢ ግብር መክፈላችሁን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

➫ ዜሮ ዓመት ለሚጠይቁ የሥራ መደቦች የምትወዳደሩ አመልካቾች የሥራ አጥ ካርድ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።

አስፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች መወዳደር ትችላላችሁ የተባለ ሲሆን፤ የፈተና ቀን በውስጥ ማስታወቂያ ይገለጻል ተብሏል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የጤና ተመራቂዎች የሙያ ብቃት ምዘና (COC) መቼ ይሰጣል?

የሙያ ብቃት ምዘና ለመውሰድ እየጠበቁ የሚገኙ የጤና ተመራቂዎች ምዘናው መቼ ይሰጣል የሚሉ በርካታ ጥያቄዎች ለቲክቫህ አድርሰዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ ጤና ሚኒስቴርን የጠየቅን ሲሆን፤ ምዘናውን ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

በትምህርት ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎችን ዝርዝር እየጠበቀ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር ለቲክቫህ ገልጿል።

የመውጫ ፈተና ውጤት መገለፅን ተከትሎ፥ COC የሚወስዱ አመልካቾች (በድጋሜ ተፈታኞችን ጨምሮ) ምዝገባ እንደሚደረግ ሚኒስቴሩ አረጋግጧል።

የCOC ምዘና አመልካቾች ምዝገባ በጊዚያዊነት ከየካቲት 10/2017 ዓ.ም በኋላ ለመጀመር መታቀዱን ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።

በዚህም ምዘናውን በየካቲት ወር መጨረሻ ወይም በመጋቢት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ለመስጠት በጊዚያዊነት መታቀዱን ከሚኒስቴሩ ሰምተናል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ቅመም Itel Proን ዛሬውኑ ገዝተን ያለ ባትሪ ስጋት በሽ በሽ እንበል! አሁኑኑ ወደ ሳፋሪኮም ሱቆች በማቅናት ስልካችንን ገዝተን ለ90 ቀናት በሚቆይ 5ጊባ ወር​ሃዊ ጥቅል እና 1000 የሳፋሪኮም ደቂቃ ጉርሻ እናግኝ!

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉 /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC

🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details...

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit #Furtheraheadtogether

Читать полностью…

Tikvah-University

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና በህክምና፣ በፋርማሲ እና በህክምና ላብራቶሪ ሳይንስ በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሦስተኛ ዲግሪ፣ በስፔሻሊት እና በሰብ-ስፔሻሊቲ ያስተምራቸውን ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ቅዳሜ የካቲት 8/2017 ዓ.ም ያስመርቃል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

7ኛ ዙር የኢንቴሪየር ዲዛይን (Interior Design) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!

👉 Sketch-Up, Revit, Rhino, 3D Max እና Lumion ሶፍትዌሮችን በአንድ ላይ
👉 ከንድፈ ሀሳብ እና ሶፍትዌር ስልጠና በተጨማሪ በተግባር በወርክሾፕም  የሚሰጥ

☎️  0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) የተመደቡለትን ተማሪዎች በመቀበል ላይ ይገኛል።

በ2017 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች የካቲት 3 እና 4/2017 ዓ.ም በአካል ሪፖርት እንዲያደርጉ ዩኒቨርሲቲው ይታወቃል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

🔔 ነጻ የሙያሎጂ ኮርስ ያሸነፉ!

#ሙያሎጂ በGreat Rift Valley Legacy Builders People's Choice አዋርድ ላይ ዕጩ ሆኗል። ይሄን ውድድር ማሸነፍ ደግሞ ሙያሎጂ ለሚፈጥረው ትውልድ ተኮር ተጽዕኖ ትልቅ ዕድል ነው።

ይሄን ለማሳካት 2 ደቂቃ በማይፈጅ ሂደት ድምጻችሁን ስጡን! ምስጋናችንን ለመግለጽ ቀድመው ድምጽ ለሚሰጡን 200 ሰዎች የሙያሎጂ ኮርስ በነጻ እንሰጣልን።

የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ በጣም ቀላል ነው፦

➫ መጀመሪያ ይሄንን ሊንክ https://vote.grvsummit.com ይጫኑ

➫ በመቀጠል Muyalogy ስር ያለችውን Vote የምትለዋን በተን ተጭኖ Gmail በመጠቀም ድምጻችሁን መስጠት

➫ በመጨረሻም በዚህ የቴሌግራም አካውንት /channel/muyalogy_cs የውስጥ መስመር Vote ያደረጋችሁበትን Screenshot እና Vote ያደረጋችሁበትን Email መላክ።

ለተነሳንበት አላማ ስለምታበረታቱን እናመሰግናለን!

Читать полностью…

Tikvah-University

የፊታችን እሑድ የካቲት 09/2017 ዓ.ም ጠዋት 2:00 በመገናኛ ካምፓስ የጋዜጠኝነት ስልጠና ተማሪዎች የመመረቂያ ፕሮጀክታቸውን ያቀርባሉ። ጋዜጠኛ ትዕግስቱ በቀለ በመርሐግብሩ ላይ በመገኘት ልምዱን የሚያካፍል ይሆናል።

በመርሐግብሩ ላይ በመገኘት የተመራቂ ተማሪዎቻችንን የመመረቂያ ሥራዎች እንዲከታተሉ እንዲሁም በልምድ ልውውጡ ላይ እንዲካፈሉ ጋብዘንዎታል።

☎️  0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

የመውጫ ፈተና ውጤት ለዩኒቨርሲቲዎች ሬጅስትራር መላኩን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ኅብረት ፕሬዝዳንት ሃየሎም ስዩም ለቲክቫህ ገልጿል።

የሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተፈታኞች ከነገ ጀምሮ በየካምፓሳቸው በመገኘት ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል።

"ለኮሌጅ ተማሪዎች እንዲሁም ለየኮሌጆቻቸው ውጤታቸው ይደርሳል፤ ተፈታኞች በየካምፓሳቸው ከነገ ጀምሮ ማየት ይችላሉ" ሲል የኅብረቱ ፕሬዝዳንት ገልጿል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ቅዳሜ የካቲት 8/2017 ዓ.ም ያስመርቃል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የመውጫ ፈተና ዛሬ ከሰዓት በኃላ ይፋ እንደሚደረግ ከትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ማግኘቱን የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት አሳውቋል።

NB. መረጃው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንት እና የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት ፕሬዜዳንት ሃየሎም ስዩም ነው።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

🔔 ባሉበት በማንኛውም ሰዓት በተመጣጣኝ ዋጋ ያለገደብ የፈለጉትን ሙያ ይማሩ!

በአጭር ግዜ የተዋጣለት መባለሙያ የሚያደርግዎትን የተለያዩ ኮርሶችን በሙያሎጂ ይውሰዱ!

➡️ ቢዝነስ በኢትዮጵያ ኮርስ
➡️ እንግሊዝኛ ቋንቋ
➡️ ኢንቴሪየር ዲዛይን
➡️ ግራፊክ ዲዛይን እና አዶቤ ፎቶ ሾፕ
➡️ ዌብ ዴቨሎፕመንት
➡️ ዲጅታል ማርኬቲንግ
➡️ ፊልም ሜኪንግ እና አዶቤ ፕሪሚየር
➡️ ሥራ ፈጠራ
➡️ ኪሮሽ ሥራ

✔️ በዘርፉ ዕውቅና እና ልምድ ባካበቱ ባለሙያዎች ተግባራዊና ወቅታዊ ዕውቀትን ይቅሰሙ፡፡
✔️ ኮርሱ የሚሰጠው ኦንላይን ሲሆን፤ በፈለጉት ሰዓት ደግመው መመልከት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ላይቭ ሴሽን እና ፊዚካል ወርክሾፕ ይኖረዋል።
✔️ ኮርሱን ላጠናቀቁ ሰልጣኞች ሰረተፍኬት እንሰጣለን፣ የስራ ዕድል እናመቻቻለን።

📣  አሁኑኑ www.muyalogy.com ላይ ገብተው በመመዝገብ የ 20% ቅናሽ ተጠቃሚ ይሁኑ!

☎️    0904135555

Читать полностью…

Tikvah-University

2ኛ ዙር የዓለም አቀፍ ግብይት (Import and Export Business) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!

🔔 ፈጥነው ይመዝገቡ!

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ አሰራሮች የሚተነተኑበት  
👉 በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች የሚሰጥ

☎️  0906777799 / 0906777755
አድራሻ
፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ የተከታታይ ጤና ሙያ ማጎልበቻ ስልጠና (CPD) ዕውቅና ሰጪ ተቋም ሆኖ በድጋሜ ፈቃድ አጊኝቷል።

ካምፓሱ የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ አቅራቢዎች እና የስልጠና ኮርሶች ዕውቅና ሰጪ ተቋም (CPD Accreditor) ሆኖ እንዲያገለግል በድጋሜ ዕውቅና ከጤና ሚኒስቴር ማግኘቱን አሳውቋል።

በዚህም ካምፓሱ ለጤና ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት የሚያስችለው ሲሆን፤ ፈቃዱ ለሦስት ዓመት የሚቆይ መሆኑ ታውቋል።

በኢትዮጵያ ተከታታይ የጤና ሙያ ማጎልበቻ ስልጠና Continuing Professional Development (CPD) የሚሰጡ ከ250 በላይ ተቋማት እንዳሉ የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

🔔 ነጻ የሙያሎጂ ኮርስ ያሸነፉ!

#ሙያሎጂ በGreat Rift Valley Legacy Builders People's Choice አዋርድ ላይ ዕጩ ሆኗል። ይሄን ውድድር ማሸነፍ ደግሞ ሙያሎጂ ለሚፈጥረው ትውልድ ተኮር ተጽዕኖ ትልቅ ዕድል ነው።

ይሄን ለማሳካት 2 ደቂቃ በማይፈጅ ሂደት ድምጻችሁን ስጡን! ምስጋናችንን ለመግለጽ ቀድመው ድምጽ ለሚሰጡን 200 ሰዎች የሙያሎጂ ኮርስ በነጻ እንሰጣልን።

የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ በጣም ቀላል ነው፦

➫ መጀመሪያ ይሄንን ሊንክ https://vote.grvsummit.com ይጫኑ

➫ በመቀጠል Muyalogy ስር ያለችውን Vote የምትለዋን በተን ተጭኖ Gmail በመጠቀም ድምጻችሁን መስጠት

➫ በመጨረሻም በዚህ የቴሌግራም አካውንት /channel/muyalogy_cs የውስጥ መስመር Vote ያደረጋችሁበትን Screenshot እና Vote ያደረጋችሁበትን Email መላክ።

ለተነሳንበት አላማ ስለምታበረታቱን እናመሰግናለን!

Читать полностью…

Tikvah-University

የፊታችን እሑድ የካቲት 09/2017 ዓ.ም ጠዋት 2:00 በመገናኛ ካምፓስ የጋዜጠኝነት ስልጠና ተማሪዎች የመመረቂያ ፕሮጀክታቸውን ያቀርባሉ። ጋዜጠኛ ትዕግስቱ በቀለ በመርሐግብሩ ላይ በመገኘት ልምዱን የሚያካፍል ይሆናል።

በመርሐግብሩ ላይ በመገኘት የተመራቂ ተማሪዎቻችንን የመመረቂያ ሥራዎች እንዲከታተሉ እንዲሁም በልምድ ልውውጡ ላይ እንዲካፈሉ ጋብዘንዎታል።

☎️  0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የ2017 ትምህርት ዘመን የአጋማሽ ዓመት የተማሪዎች የምረቃ መርሐግብር እሑድ የካቲት 9/2017 ዓ.ም ያካሒዳል።

በዚህም የተቋሙ የጤና ሳይንስ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች፣ የእንስሳት ህክምና ሳይንስ ተማሪዎች እንዲሁም የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት ይከናወናል ተብሏል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

🔔 ነጻ የሙያሎጂ ኮርስ ያሸነፉ!

#ሙያሎጂ በGreat Rift Valley Legacy Builders People's Choice አዋርድ ላይ ዕጩ ሆኗል። ይሄን ውድድር ማሸነፍ ደግሞ ሙያሎጂ ለሚፈጥረው ትውልድ ተኮር ተጽዕኖ ትልቅ ዕድል ነው።

ይሄን ለማሳካት 2 ደቂቃ በማይፈጅ ሂደት ድምጻችሁን ስጡን! ምስጋናችንን ለመግለጽ ቀድመው ድምጽ ለሚሰጡን 200 ሰዎች የሙያሎጂ ኮርስ በነጻ እንሰጣልን።

የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ በጣም ቀላል ነው፦

➫ መጀመሪያ ይሄንን ሊንክ https://vote.grvsummit.com ይጫኑ

➫ በመቀጠል Muyalogy ስር ያለችውን Vote የምትለዋን በተን ተጭኖ Gmail በመጠቀም ድምጻችሁን መስጠት

➫ በመጨረሻም በዚህ የቴሌግራም አካውንት /channel/muyalogy_cs የውስጥ መስመር Vote ያደረጋችሁበትን Screenshot እና Vote ያደረጋችሁበትን Email መላክ።

ለተነሳንበት አላማ ስለምታበረታቱን እናመሰግናለን!

Читать полностью…

Tikvah-University

የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ያስተምራቸውን ዕጩ ተመራቂዎች ቅዳሜ የካቲት 8/2017 ዓ.ም ያስመርቃል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የመውጫ ፈተና ውጤት ከሁለት ቀናት በኋላ ይፋ ይደረጋል፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር

ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በ87 የፈተና ማዕከላት መሰጠቱ ይታወቃል፡፡

ከፈተናው ጋር በተያያዘ በርካታ ቅሬታዎች ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ደርሰዋል፡፡ በተለይ የComprehensive Nursing ተፈታኝ ተማሪዎች፥ ፈተናው ከBlue Print ውጪ የተዘጋጀ እንደነበር በመግለፅ ትምህርት ሚኒስትር ለቅሬታቸው አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

የመውጫ ፈተና ውጤት ከሁለት ቀናት በኋላ ይፋ እንደሚደረግ ከትምህርት ሚኒስቴር መስማቱን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት ለቲክቫህ ገልጿል፡፡

ሚኒስቴሩ ከComprehensive Nursing የመውጫ ፈተና ጋር ተያይዞ የቀረበ ቅሬታን እያጣራ እንደሚገኝ ለህብረቱ አስረድቷል፡፡

በዚህም ከሁለት ቀናት በኋላ (ረቡዕ/ሐሙስ) አጠቃላይ የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ እንደሚደረግ ሚኒስቴሩ አሳውቋል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#TVTI_Exit_Exam

የመውጫ ፈተና የምትወስዱ የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ሰልጣኞች በኦንላይን ምዝገባ አድርጉ!

ተከታዩን ማስፈንጠሪያ በመጫኑ የምታገኙትን ቅፅ በመሙላት ምዝገባ ያድርጉ 👇
https://forms.office.com/r/3KgnK1esuc

ኦንላይን መመዝገብ የማትችሉ በዋናው ግቢ በአካል በመገኘት በየትምህርት ክፍላችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል።

የምዝገባ ጊዜ የሚያበቃው፦
የካቲት 10/2017 ዓ.ም

የመውጫ ፈተናውን #በድጋሜ የምትወስዱ ተፈታኞች ፈተናው በኢንስቲትዩቱ ዋና ግቢ እና በአዲስ አበባ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

የመዝገባ ብር 500 በኢንስቲትዩቱ የንግድ ባንክ አካውንት በማስገባት ክፍያ በመፈፀም ደረሰኝ መያዝ ይጠበቅባችኋል።

የምዝገባ ጥሪው በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የጋርመንት ቴክኖሎጂ ሰልጣኞችንም ይመለከታል።

የመውጫ ፈተናው ከመጋቢት 6-11/2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ እንደሚሰጥ ኢንስቲትዩቱ ገልጿል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ባለፈው ሳምንት ከተሰጠው ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ የ Comprehensive Nursing ተፈታኝ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አቅርበዋል፡፡

ፈተናው ከBlue Print ውጪ መዘጋጀቱን እንዲሁም የጥያቄ መደጋገም መኖሩን የገለፁት ተፈታኞቹ፤ ትምህርት ሚኒስትር ቅሬታቸውን በማየት በአፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

ከነርሲንግ ተማሪዎች ጋር ተያይዞ የትምህርት ሚኒስቴር እስካሁን ያለው ነገር የለም፡፡ ቲክቫህ ጥያቄውን ለሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራር ያቀረበ ሲሆን፤ የሚሰጡንን ምላሽ የምናቀርብ ይሆናል፡፡

በሌላ በኩል "ፈተናዎቹ ዘግይተው መሰጠት በመጀመራቸው የሰዓት ዕጥረት እንዲፈጠር ማድረጉ" እንዲሁም "የኔትወርክ እና የመብራት መቆራራጥ ችግሮች" ሌሎች በፈተናው ወቅት የታዩ ችግሮች እንደነበሩ ተፈታኝ ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ገልፀዋል፡፡

እንደ ተንቀሳቃሽ ስልክ ያሉ የተከለከሉ ነገሮችን ወደ ፈተና ጣቢያ ይዞ ለመገባት መሞከር በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ማጋጠሙን መግለፃችን ይታወሳል፡፡

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሞባይል ስልክ ሲጠቀሙ የተያዙ እና በመፈተኛ ክፍሎች ሞባይል ስልኮችን ይዘው የተገኙ 128 ተማሪዎችን ከፈተና ማዕከሉ እንዲሰናበቱ ማድረጉንና ውጤታቸው እንዲሰረዝ ማድረጉን አሳውቋል፡፡

የሀገር አቀፍ መውጫ ፈተና ውጤት ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ጥቂት ቀናት ይፋ እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡

ምስል፦ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity

Читать полностью…
Subscribe to a channel