tikvahuniversity | Unsorted

Telegram-канал tikvahuniversity - Tikvah-University

308824

Subscribe to a channel

Tikvah-University

#MoH

በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ ምዝገባ ያጠናቀቃችሁ የጤና ባለሙያዎች ፈተና ከሚያዚያ 1-3/ 2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ጤና ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል፡፡

ሚኒስቴሩ የመፈተኛ ጣቢያዎች ዝርዝርን ይፋ አድርጓል። ተፈታኞች የመፈተኛ ጣቢያችሁን መመልከት ትችላላችሁ። (ከላይ ተያይዟል)

ምንሊክ ጤና ሳይንስ ኮሌጂ የመረጣችሁ ተመዛኞች፥ የመፈተኛ ማዕከላችሁ ወደ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተቀየረ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የሰብል መውቂያ እና መፈልፈያ የሠሩ ወጣቶች 👏

ታምራት አለሙ ከሌሎች ሰባት ወጣቶች ጋር በመሆን እንደ በቆሎ፣ ጤፍ፣ ማሽላ እና ሩዝ የመሳሰሉ ሳራማ እና አገዳማ እህሎችን ለመውቃት እና ለመፈልፈል የሚያስችል ማሽን ሰርተዋል፡፡

ማሽኑ በኤሌክትሪክ ወይም በጀነሬተር የመስራት አማራጭን የያዘ ሲሆን፤ በቀላሉ ለማንቀሳቀስ በሚያስችል መልኩ የተሠራ ነው፡፡

Multi-Crop Threshing Machine የተሰኘው ፈጠራው፤ በተለይ አነስተኛ ማሳ ያላቸው አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡

ወጪ ቆጣቢ እና ችግር ፈቺ የሆነው ማሽኑ፤ በኪራይ እና በሽያጭ አማራጮች ለገበያ መቅረቡ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

46ኛ ዙር የግራፊክ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኤዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ የፊታችን ሰኞ መጋቢት 29/2017 ዓ.ም በቀን መርሐግብር ይጀምራል።

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 Advanced Graphic + Video Editing + Motion Graphic + Digital Marketing በአንድ ላይ
👉 ከ50 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ

ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#HaramayaUniversity

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ኮሌጅ ተማሪዎች ቡድን በአሜሪካ፣ ዋሺንግተን ዲሲ JESSUP የምስለ ችሎት ውድድር ላይ ተሳትፏል፡፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ተማሪዎች ማህደር እንደሻው፣ አያንቱ ደቻሳ እና አብዱራዛቅ ነቢ ኢትዮጵያን በመወከል በውድድሩ የተሳተፉ ሲሆን፤ መምህር ወንድሜነህ በየነ እና ሀብታሙ ሲዋያ ተወዳዳሪዎቹን በአሰልጣኝነት መርተዋል።

ተማሪዎቹ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተወዳዳሪ ቡድኖችን በማሸነፍ በ2025 PHILIP C. JESSUP ዓለም አቀፍ የምስለ ችሎት ውድድር ላይ ለመሳተፍ መቻላቸው ተገልጿል።

JESSUP በዓለም ትልቁ የምስለ ችሎት ውድድር ሲሆን ከመላው ዓለም 700 ከሚሆኑ የሕግ ትምህርት ቤቶች የሚወከሉ ተማሪዎች በውድድሩ ይሳተፋሉ።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

🔥 ይጋብዙ፣ ይሸለሙ! 🔥
📣 አሁንም እንደቀጠለ ነው 📣

የቴሌግራም ቻናላችንን ያጋሩ!
💥 ትክክለኛውን ቦታችንን ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉ🎁

ከእናንተ የሚጠበቀው የሳፋሪኮም መስመራችሁን በመጠቀም የተጠቀሱትን ቅደም ተከተሎች መተግበር ነው🫰🏽

👉🏽 ያስተውሉ፣ በዕርስዎ ጋባዥነት የሚቀላቀለው ሰው ቁጥር ሲጨምር የሚያገኙት የአየር ሰዓት መጠንም እየጨመረ ይሄዳል። እንዲሁም ተጋባዦቻችሁ ገፁን ከተቀላቀሉ በኋላ “Back” የሚለውን ተጭነው “Check Subscription” እንዲያደርጉ ያሳስቡ 🔥

የቴሌግራም ቻናላችን 👉🏽
/channel/Safaricom_Ethiopia_PLC

የቴሌግራም ቦታችን 👉🏽
/channel/official_safaricomet_bot

መልካም ዕድል 🎁💥

#SafaricomEthiopia #1Wedefit
#FurtherAheadTogether

Читать полностью…

Tikvah-University

#WolaitaSodoUniversity

በ2017 ዓ.ም ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች ምዝገባ የሚካሄደው መጋቢት 29 እና 30/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ (በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስፖንሰር ለተደረጋችሁ)
➫ ከ8-12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ወረቀት እና ከ9-10ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት
➫ የመልቀቂያ ደብዳቤ ይሰሩበት ከነበረው ተቋም
➫ የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ሰርተፊኬት
➫ የመጀመሪያ ዲግሪ ኦፊሽያል ትራንስክሪፕት ለወላይታ ሶዶ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝ ሆስፒታል በፖ.ሳ.ቁ. 200 ማስላክ
➫ ሁለት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#BahirDarUniversity

በ2017 ዓ.ም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች የምዝገባ ጊዜ ሚያዚያ 2 እና 3/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ በቅጣት ምዝገባ፦ ሚያዚያ 6/2017 ዓ.ም

የምዝገባ ቦታ፦
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሬጅስትራር ጥበበ ጊዮን ካምፓስ

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

➫ ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በፖ.ሣ.ቁ. 79 ማስላከ፣ መድረሱን ማረጋገጥ እና "TRN" ቁጥር ማቅረብ
➫ የትምህርት ማስረጃዎች (ዋናው እና ኮፒው)
➫ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ
➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ (በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፎርም ተሞልቶ በስፖንሰር አድራጊው ተቋም የተፈረመ)

ለሁሉም ትምህርት ክፍሎች ገለጻ (Orientation) ሚያዚያ 7/2017 ዓ.ም ጠዋት 3፡00 ሰዓት ይሰጣል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

🔥 Code. Compete. Conquer!
Safaricom Talent Cloud Capstone Challenge!
🔥

Ready to push your limits? Safaricom Talent Cloud brings to you the Capstone Project. If you are in Addis Ababa, team up and turn your idea into an MVP in just 6 weeks.

💰 Win BIG! 💰
🥇 Grand Prize: ETB 140,000
🥈 Second Place: ETB 85,000
🥉 Third Place: ETB 50,000

🔔 Are you are skilled in one of the following?

● Mobile (Kotlin/Flutter)
● Frontend (React)
● Backend (Java/Node.js)
● Fullstack
● DevOps
● UX/UI
● Product Ownership/Scrum Master

Form Your Dream Team! 🤝
● Assemble your 4–6-member squad and let one person apply, registering everyone.
● Note: All applicants must complete the TestGorilla assessment which will be sent through email!
Guided by expert advisors, you will collaborate, innovate, and compete for the prize.

Apply Here

Deadline: April 07, 2025

Читать полностью…

Tikvah-University

#UniversityOfGondar

በጤና ሚኒስቴር የ'Maching Exam' ወስዳችሁ ያለፋችሁና ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች ምዝገባ የሚካሔደው መጋቢት 29 እና 30/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ትምህርት ሚያዝያ 1/2017 ዓ.ም የሚጀመር መሆኑ ተገልጿል፡፡

አዲስ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች የመጀመሪያ ዲግሪ ኦፊሺያል ትራንስክርፒት ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ዋናው ሬጅስትራር ፖ.ሣ.ቁ. 196 C/O CMHS ብላችሁ ማስላክ ይኖርባችኋል፡፡ እንዲሁም NGAT ማለፋችሁን የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

26ኛ ዙር ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Modern Accountancy) ስልጠና ቅዳሜ መጋቢት 27/2017 ዓ.ም በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ይጀምራል። 

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 መሠረታዊ የአካውንቲንግ እና የኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1:
ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#MoH

የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከሚያዚያ 1-3/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።

ፈተናው ከስር በተገለፁት የጤና ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው ምዝገባ ላጠናቀቁ ተመዛኞች የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።

የፈተናው መርሐግብር

ሚያዝያ 1/2017 ዓ.ም
Nursing, Nutrition, Optometry, Pediatric and Child Health Nursing, Dental Medicine, Emergency and Critical Care Nursing, Environmental Health, Surgical Nursing, Anesthesia and Psychiatric Nursing

ሚያዝያ 2/2017 ዓ.ም
Pharmacy, Medical Radiology Technology, Midwifery

ሚያዝያ 3/2017 ዓ.ም
Medicine, Public Health and Medical Laboratory Science

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በግዕዝ ጥናት መስክ በዶክትሬት ዲግሪ ፕሮግራም ሰልጣኞችን መቀበል ሊጀምር ነው።

ዩኒቨርሲቲው ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማስተማር የሚያስችለውን ስርዓተ ትምህርት አዘጋጅቷል።

ዩኒቨርሲቲው የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት በማድረግና ስርዓተ ትምህርት በመቅረፅ ዝግጅት ሲያደረግ መቆየቱን፥ ትምህርቱን ለመጀመር በተዘጋጀ የምክክር አውደ ጥናት ላይ ተገልጿል።

የግዕዝ ቋንቋ ትምህርት በሰርተፊኬት እና በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ከሚሰጡ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ወሎ ዩኒቨርሲቲ፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ይጠቀሳሉ።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

Eid Mubarak!


ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ለእስልምና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የኢድ አል-ፈጥር በዓል ይመኛል።

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምትገኙና በዓሉን ከቤተሰቦቻችሁ ርቃችሁ እያከበራችሁ ላላችሁ ተማሪዎች መልካም የኢድ አል-ፈጥር በዓል ይሁንላችሁ።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማሪታይም አካዳሚ ሊከፈት ነው።

የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን እና አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማሪታይም አካዳሚ በዩኒቨርሲቲው ለመክፈት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የአካዳሚው መከፈት ባለሥልጣኑ ባህረኞችን አሠልጥኖ ለዓለም ገበያ ለማቅረብ ያስችለዋል ተብሏል።

አካዳሚው በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ስር የሚከፈተው መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን የሚያስተዳድራቸው ሁለት የማሪታይም ማሰልጠኛዎች ማለትም የኢትዮጵያ ማሪታይም ትሬኒንግ ኢንስቲትዩት እንዲሁም የባቦጋያ ሎጅስቲክስ እና ማሪታይም አካዳሚ እንዳሉት ይታወቃል። #EMA

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በኢንተርኔት የታገዘ የመስኖ መቆጣጠሪያ ሲስተም የሠሩ ወጣቶች 👏

የክህሎት ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ዙር ተወዳዳሪዎች የነበሩት ዘላለም እንዳለ እና ጓደኞቹ IoT Smart Irrigation Control and Monitoring System ቴክኖሎጂ አበልፅገዋል፡፡

ቴክኖሎጂው እስከ 10ኪሜ ርቀት ላይ ያሉ የመስኖ እርሻዎችን ለመከታተልና አስፈጊውን ግባዓት ለማቅረብ የሚረዳ ነው።

ሲስተሙ ከአፈር ውስጥ በሚሰበስበው መረጃ አስፈላጊውን የውሃ፣ የማዳበሪያ እና ሌሎች ግብዓቶችን ለመስጠት ይረዳል፡፡ ቴክኖሎጂው በዕለቱ ያለውን መረጃ ከመስጠት በተጨማሪ በቀጣይ ቀናት ያለው የግብርና ማሳ ወሳኝ መረጃ ትንበያ ያመለክታል፡፡ አውቶማቲክ ወይም ማንዋል ስልት ተገጥሞለታል፡፡

ቴክሎጂው በፀሐይ ኃይል የሚሠራ መሆኑ ሌላው ልዩ የሚያደርገው ነው፡፡ በማሳ ውስጥ የውሃን ብክነትን በ50% የሚቀንስ፣ ምርትን በ30% የሚያሳድግ እና የአፈር ማዳበሪያን ፍጆታን የሚቀንስ ፈጠራ ነው፡፡

ቴክኖሎጂውን ለማበልፀግ 1.4 ሚሊዮን ብር እንደፈጀ የሚናገሩት ወጣቶቹ፤ ከ1.6-1.8 ሚሊዮን ብር ለገበያ መቅረቡን ገልፀዋል፡፡ ወጣቶቹ የፋይናንስ ድጋፍ ቢያገኙ በሰፊው በማምረት ወደ ገበያ ለማቅረብ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ #PMOEthiopia
ተጨማሪ፦ https://web.facebook.com/share/v/16JAnn9uDV/

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#BahirDarUniversity

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዲጂታል ትምህርት እና ምርምር በተደራጀ መልኩ ለመስጠት የሚያስችል ዘመናዊ የድምጽ እና ምስል ሰቱዲዮ ሥራ አስጀምሯል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ጂኦስፓሺያል ዳታ እና ቴክኖሎጂ ማዕከል ውስጥ የተመረቀው ስቱዲዮው፤ በስትራቴጂክ አጋርነት ከኔዘርላንድሱ ትዌንቴ ዩኒቨርሲቲ ትብብር የተገነባ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ስቱዲዮው ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠውን የዲጂታል ትምህርት፣ ምርምር እና ማኅበረሰብ ጉድኝትን ለማስፋት ያስችላል ተብሏል፡፡

የስቱዲዮው ሥራ መጀመር ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርት በመስጠት ቀዳሚ ከሆኑ የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ ለመሆን የሚያደርገውን ጥረት የሚደግፍ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

🌐 እጅግ ፈጣን ዋይፋይ በአዲስ ቅመም! ሊያውም ከጉርሻ ጋር! 🤗

💨⚡️ እስከ 6 ሰዓት የሚቆይ የባትሪ አቅም ያለውና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ትሩፋቶችን ይዞ በአንዴ እስከ 8 ሰው ድረስ የሚያስጠቅመውን ልዩ ቅመም MIFI ‘ን ገዝተን ፈጣን 4G ኢንተርኔት እንጠቀም!

🍰 ለ30 ቀን ከሚቆይ ነጻ 30ጊባ ዳታ ጉርሻ ጋር

ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት⚡️

#SafaricomEthiopia

Читать полностью…

Tikvah-University

#MoE

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ለአንድ ዓመት እንዲያስተምሩ ሊገደዱ ነው።

ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ማኅበረሰቡን ለአንድ ዓመት በቅድሚያ እንዲያስተምሩ ወይም እንዲያገለግሉ የሚያደርግ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን አስታወቀ።

ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት ዝቅተኛ የሆነበትን መንስዔ በተመለከተ ጥናት አቅርበዋል።

ውይይት ሲደረግ ነበር።

በዚህም ወቅት በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ስለተያዘው እቅድ አብራርተዋል።

ላለፉት ዓመታት (እሳቸው በኃላፊነት ከተሾሙ ጀምሮ) ፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት በከፍተኛ ደረጃ ዝቅተኛ እንዲሆን ካደረጉ መንስዔዎች መካከል፣ የመምህራን ብቃትና የተነሳሽነት ማነስ ተጠቃሽ መሆናቸው ጠቁመዋል።

ችግሩን በአጭር ጊዜ ለመፍታት እንዲቻል የተለያዩ ተግበራት እየተሰሩ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

'' የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ '' የሚል መጠሪያ የተሰጠው አሠራር ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ዕቅድ የተያዘ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ " በአራት ዓመት የሚመረቅ ተማሪ፣ የሦስተኛ ዓመት ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ወደ አስተማረው ማኅበረሰበብ ተመልሶ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ይሰጥና (ማኅበረሰቡን እንዲያገለግል ይደረግና) እንዲመረቅ ይደረጋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ይህም ሲሆን የተማሪዎቹ መሠረታዊ ወጪ የሚሸፈን እንደሚሆንም አክለዋል።

ይህ አሰራር ለተማሪዎች ለራሳቸው የተግባር ትምህርት እንደሚሆንና የበለጠ እንዲበስሉ እንደሚያደርጋቸውም ተናግረዋል።

ተማሪዎች የመምህርነትን ሙያ ተላብሰው በዚያው ወደ ሙያው እንዲያመሩ ዕድል በመፍጠር ለጊዜውም ቢሆን በዘርፉ እየቀነሰ የመጣውን ወደ ሙያው የሚገባ የአስተማሪን ቁጥር ለማሳግ እንደሚረዳም ሚንስትሩ አብራርተዋል።

በቅርቡ በመምህራን ላይ በተደረገ ግምገማ ፣ 100,000 የሚደርስ የመምህራን ዕጥረት መኖሩ መታወቁን የተናገሩት ብርሃኑ (ፕሮፌሰር)፣ አሰራሩ በከፍተኛ ደረጃ ያለውን የመምህራን ዕጥረት እንዲቀንስ የበኩልን እንደሚወጣ አስረድተዋል።

ወደ መምህርነት ሙያ የሚገቡ ሰዎችን ክፍተት ለማስተካከል ከተያዙ ዘርፈ ብዙ የማትጊያ ሥርዓቶች አንዱ፣ መምህራን በአገሪቱ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ የራሳቸው ድርሻ እንዲኖራቸውና የኑሮ ውድነቱን እንዲቋቋሙ ለማድረግ፣ " የመምህራን ባንክ " ማቋቋም አንዱ እቅድ መሆኑን አንስተዋል።

ባንኩ " በአንድ ዓመት ውስጥ ወደ ሥራ ይገባዋል ብለን እንጠብቃለን " ያሉት ሚኒስትሩ፣ በ2019 ዓ.ም ደግም በእርግጠኝነት ወደ የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ አሰራር እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

Tikvah-University

#TVTI

በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ውስጥ የፋሽን ስልጠና ማዕከል ሊከፈት ነው።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ከማፊ ፋሽን አካዳሚ ባለቤት ዲዛይነር ማህሌት አፈወርቅ (ማፊ) ጋር በኢንስቲትዩቱ ውስጥ የፋሽን ስልጠና ማዕከል ለመክፈት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የፋሽን ማሰልጠኛ ማዕከሉ የአጭር እና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎችን እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#የሥራ_ዕድል_ጥቆማ

የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢንስቲትዩት ብቁ የሕክምና መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

➤ የሥራ መደብ፦ የሕክምና መምህራን
➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 10
➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ በሕክምና የመጀመሪያ ዲግሪ
➤ የሥራ ቦታ፦ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢንስቲትዩት

መስፈርቱን የምታሟሉ ባለሙያዎች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር የሥራ ቀናት በዩኒቨርሲቲው የሰው ሃብት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 02 በመገኘት ወይም በኦንላይን humanresourcemgt@dadu.edu.et ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

(ዝርዝር የሥራ ማስታወቂያው ከላይ ተያይዟል፡፡)

ለተጨማሪ መረጃ፦ 0575553618

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የፊታችን እሑድ መጋቢት 28/2017 ዓ.ም የአካውንቲንግ እና ፋይናንስ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) የሦስት ወር ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ይጀምራል።

🔔 ፈጥነው ይመዝገቡ!

👉 ስልጠናው በተመረጡ የዩኒቨርሲቲ መምህራን የሚሰጥ ነው።
👉 በስልጠናው ሁሉም በፈተና ላይ የሚመጡ ኮርሶች ላይ ክለሳ ይደረጋል።
👉 ከ1000 በላይ ጥያቄዎችን በመስራት ለፈተናው ብቁ የምትሆኑበት።

☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ

ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

🌟 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#WolloUniversity

በ2017 ዓ.ም ወሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች የምዝገባ ጊዜ መጋቢት 29 እና 30/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
ወሎ ዩኒቨርሲቲ ልዕለ ህክምና ካምፓስ (ጢጣ)

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

➫ የትምህርት ማስረጃዎች (ዋናው እና ኮፒው)
➫ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ
➫ የድኅረ-ምረቃ መግቢያ (NGAT) ሰርትፍኬት

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

50ሜባ ስጦታ በየቀኑ! በ Opera Mini አስተማማኙ የሳፋሪኮም ኔትወርክ ላይ ኢንተርኔት እየተጠቀምን በየቀኑ 50 ሜባ በነጻ እናግኝ! ከዳር እስከ ዳር በፈጣን ኢንተርኔት!

🔗 የ Opera Mini መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ 👉 https://opr.as/Ethiopia

#SafaricomEthiopia
#OperaMini

Читать полностью…

Tikvah-University

የኤሌክትሪክ ብስክሌት የሠራው ወጣት 👏

አብርሃም እሸቱ የክህሎት ኢትዮጵያ 1ኛ ዙር ተወዳዳሪ ነው፡፡ ወጣቱ የሚሰራበት የመኪና ማምረቻ ኩባንያ የተለያዩ ብስክሌቶችን ያመርታል፡፡ በፔዳል የሚሰሩ፣ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ፣ ባለ ሦስት እግር እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች የሚሆኑ ብስክሌቶችን ያመርታሉ፡፡

ወጣት አብርሃም የሠራው የኤሌክትሪክ ብስክሌት ከ80-85 በመቶ ግብዓቶቹ ከሀገር ውስጥ ምርት የሚሰራ ሲሆን፤ ሊቲየም ባትሪ እና ዲናሞ ብቻ ከውጭ የሚመጣ መሆኑን ገልጿል፡፡

በሀገር ውስጥ የሚመረተው የኤሌክትሪክ ብስክሌቱ፤ የሀገሪቱን መልክዓ ምድር ከግምት በማስገባት የሚሠሩ እና በነዳጅ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ የሚያግዙ መሆናቸውን ጠቁሟል።

የብስክሌቶቹ መለዋወጫ በሀገር ውስጥ በቀላሉ የሚገኙ ሲሆን፤ ዋስትናም ያላቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኤሌክትሪክ ብስክሌቶቹ በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ መቅረባቸውን የገለፀው ወጣቱ ሥራ ፈጣሪ፤ ዝቅተኛው የአንድ የኤሌክትሪክ ብስክሌት ዋጋ ከ25,000 እስከ 32,000 መሆኑን ተናግሯል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ተጨማሪ

የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከሚያዚያ 1-3/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል።

ሁሉም ተፈታኝ ማክሰኞ መጋቢት 30/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ (Orientation) መከታተል፣ የመለማመጃ ጥያቄዎችን መስራት እና የመፈተኛ ክፍሉን መለየት ይኖርበታል።

ተመዛኞች ወደ ፈተና ጣቢያ ስትሔዱ ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መግቢያ (ስሊፕ) መያዝ ስለሚኖርባችሁ Print አድርጋችሁ መያዝ ያስፈልጋል።

ተመዛኞች ወደ ፈተና ጣቢያ ከመሔዳችሁ በፊት በጤና ሚኒስቴር የተለቀቀውን የመረጣችሁትን የፈተና ጣቢያ መመልከት ይኖርባችኋል። ስማቸው ከተጠቀሰበት የመፈተኛ ጣቢያ (ተቋም) ውጪ ፈተናውን መውሰድ አይፈቀድም፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#Y12HMC

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ አዲስ የተመደባችሁ የሬዚደንሲ ሰልጣኞች ምዝገባ መጋቢት 29 እና 30/2017 ዓ.ም መሆኑን ኮሌጁ አሳውቋል።

ትምህርት ሚያዝያ 6/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

➫ የትምህርት ማስረጃዎች ኮፒ (ዲግሪ እና ስቱደንት ኮፒ)
➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ (በዩኒቨርሲቲ ስፖንሰር ለተደረጋችሁ)
➫ የመልቀቂያ ደብዳቤ ይሰሩበት ከነበረው ተቋም
➫ የመጀመሪያ ዲግሪ ኦፊሽያል ትራንስክሪፕት ለኮሌጁ በፖ.ሳ.ቁ. 257 ማስላክ
➫ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች መግቢያ ፈተና ሰርተፊኬት
➫ ሁለት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ነገ ማክሰኞ መጋቢት 23/2017 ዓ.ም 2ኛ ዙር የሞባይል ጥገና (Advanced Mobile Maintenance) ስልጠና በቀን መርሐግብር በመገናኛ ካምፓስ ይጀምራል።

👉 ንድፈ ሀሳብን ከተግባር ጋር በማዛመድ የሚሰጥ ስልጠና
👉 Hardware እና Software ጥገና ክፍሎችን በከፍተኛ ደረጃ (Advanced Level) የሚሰጥበት

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#EidAlFitr

የዒድ አልፈጥር በዓል ነገ እሁድ ይውላል።

ዛሬ የሸዋል ወር ጨረቃ በመታየቷ 1446ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ነገ እሁድ ተከብሮ ይውላል።

ዒድ ሙባረክ !

#Haramain

@tikvahethiopia

Читать полностью…

Tikvah-University

#የፌሎውሺፕ_ጥቆማ

በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የ Obstetrics and Gynecology ትምህርት ክፍል ብቃት ያላቸው አመልካቾችን ለ2025 የትምህርት ዘመን ፌሎውሺፕ ፕሮግራም መቀበል ይፈልጋል፡፡

የፌሎውሺፕ ፕሮግራሙ ክፍት የሆነባሀቸው መስኮች
➫ Maternal and Fetal Medicine - ሁለት
➫ Urogynaecology - ሁለት

መስፈርቶች፦


➫ ዕውቅና ካለው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በሕክምና የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው/ያላት
➫ በ'Obstetrics and Gynecology' የሬዚደንሲ ስልጠና ያጠናቀቀ/ያጠናቀቀች
➫ ለሁለት ዓመት በ'Obstetrics and Gynecology' የገለገለ/ያገለገለች
➫ የኮሌጁን የቅበላ ሒደት (የመግቢያ ፈተናን ጨምሮ) ማጠናቀቅ የሚችል/የምትችል
➫ በኢትዮጵያ በ'Gynecology and Obstetrics' ሙያተኝነት የተመዘገበ እና ፈቃድ ያለው/ያላት
➫ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ያለፈ/ያለፈች

የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦
ሚያዝያ 01/2017 ዓ.ም

(ስታመለክቱ ልታሟሏቸው የሚገቡ ሰነዶችና ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

Join us this coming Monday, 31 March, 2025 at 8:10 PM EAT on Fana FM 98.1 for a vital discussion on "Expanding Learning Opportunities for Out-of-School Youth."

This edition, supported by the Mastercard Foundation, features Abel Ababu, Co-Founder & General Manager at Think Hub ET Innovations; Abdi Abraham, Co-founder and Managing Director of Enkoy Technologies and E-learning Developer; and Nardos Amde, Senior E-Learning Designer and Developer at Bank of Abyssinia.

Moderated by Rediet Meshesha (Ethio FM), the program explores how EdTech, combined with community initiatives, can empower youth.

#EdTechEthiopia #MastercardFoundation #YouthEmpowerment

Читать полностью…
Subscribe to a channel