weperspective | Unsorted

Telegram-канал weperspective - Perspective

-

Subscribe to a channel

Perspective

#አዳም_ረታ

የአዳም ረታ ስምንት መጻሕፍት በሁሉም መጽሐፍ መደብር ይገኛሉ :: ስትገዙም ሽፋኑ ላይ ከታተመው ዋጋ ከ 250 እስከ 150 ብር ድረስ አስቀንሳችሁ መግዛት ትችላላችሁ :: እኔም የገዛሁት እንደዛ ነው ::

Читать полностью…

Perspective

🎯 የበረራ አስተናጋጆች ዋነኛ ስራ እና ጥቅም ምንድነው?

አዎን! የብዙ ሰው መልስ፣ ለመንገደኛው የምግብ እና መጠጥ አቅርቦት መስተንግዶ ነው የሚል እንደሆነ ይታወቃል፡፡

#Ethiopia | እውነታው ግን ዋነኛ ስራቸውና፣ በማንኛውም አየር መንገድ የስራ ኃላፊነታቸው ቁልፍ የሚሆንበት ምክንያት የመንገደኞች እና የአይሮፕላኑ ደህንነት በብዙ መንገድ እነሱን የሚመለከት በመሆኑ ነው፡፡

ከትናንት ወዲያ ንብረትንቱ የጃፓን አየር መንገድ የሆነ Airbus 350 አይሮፕላን 379 መንገደኞችን አሳፍሮ በርሮ ሊያርፍ ሲል በመንደርደርያው ላይ ከነበረ አነስተኛ አይሮፕላን ጋር ተጋጭቶ በተፈጠረ እሳት፣ በሚገርም ፍጥነት፣ እሳቱ በመላው የአይሮፕላኑ ክፍል ተዛምቶ፣ አይሮፕላኑን ወደ አመድነት ሲቀይረው ዓለም በቀጥታ ስርጭት እየተመለከተ ነበር፡፡

በ18 ደቂቃ ውስጥ፣ የ379 መንገደኞችን ህይወት ከዚያ በእሳት ከሚንቀለቀለው አይሮፕላን ውስጥ በፍጥነት፣ በአደጋ ጊዜ መውጫ በሮች በኩል ተንሸራተው አንድም ሰው ሳይጎዳ በሰላም እንዲወጡ ያደረገው ማንም ሳይሆን፣ የአይሮፕላኑ የበረራ አስተናጋጆች ናቸው፡፡

ከዚህ ሁሉ በላይ፣ አይሮፕላኑ ከተጋጨ በኋላ በእሳት መያያዙን እንኳን ለዋና አብራሪው የተናገረቸው፣ በኋለኛው የአይሮፕላኑ ክፍል ተመድባ ትሰራ የነበረችው የበረራ አስተናጋጅ ናት፡፡

ከምንም እና ከምንም በላይ፣ የበረራ አስተናጋጆች የቱንም ያክል ህይወታቸው አደጋ ላይ ቢሆን፣ የመጨረሻው መንገደኛ፣ ከአይሮፕላኑ ሳይወጣ በፊት ለነፍሳቸው ሳስተው፣ መንገደኛ ጥለው እንደማይሄዱ ታውቃላችሁ? የትኛው ስራ ነው በዚህ ያክል ራሱን ለሌሎች የሚያስቀድም?

አየር መንገዳችን፣ በየጊዜው የሚያሰለጥናቸው የበረራ አስተናጋጆቻችን፣ በስልጠናቸው በአጽንዖት የሚማሩትና፣ በምረቃቸውም ቃል የሚገቡት መሀላ፣ በማንኛውም ጊዜ ከራሳቸው አብልጠው የእኛን ደህንነት ለማስቀደም ነው፡፡

የበረራ አስተናጋጆች፣ ልክ በመስተንግዶአቸው ላይ፣ የሚመገቡትም ይሁን የሚያርፉት ከመንገደኞቻቸው በኋላ እንደሆነው ሁሉ፣ በእያንዳንዱ በረራቸው፣ የራሳቸውን ህይወት ደህንነት ከሁሉም መንገደኛ መጨረሻ ለማድረግ የወሰኑ እና በቤታቸው የሚቆርሱትም እንጀራ ከዚህ መስዋዕትነት በኋላ የተረፈውን ነው።

በሀገራችን፣ የአቪዬሽን ጉዳይ በአንድ ለእናቱ የአየር መንገዳችን ቅጥር ግቢ ውስጥ የተወሰነ ስለሆነ፣ በመሰል ጉዳዮች ላይ የተሟላ እና ትክክለኛ ዕውቀት ባይኖር የማንም ስህተት አይደለም፡፡ አሁን ግን ይህንን አጋራኋችሁ፡፡

በነገራችን ላይ፣ በአንድ አይሮፕላን በረራ ላይ የሚበሩ የበረራ አስተናጋጆች ቁጥር የሚወሰነው safety minimum and service minimum በሚል standard መለኪያ ነው። ይህም ማለት አንድ የበረራ አስተናጋጅ በመደበኛ በረራ ጊዜ ጥሩ መስተንግዶ እና በአደጋ ጊዜ ደግሞ፣ የደህንነት እገዛ የሚያደርግልን መንገደኞች ቁጥርን፣ የአይሮፕላኑን የአደጋ ጊዜ መውጫ በሮች እና አጠቃላይ አቅም ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ነው። በዚህ standard አንዳንድ ጊዜ የበረራ አስተናጋጆች እጥረት ሲያጋጥም፣ የመስተንግዶ minimum ቁጥርን በልዩ ሁኔታ compromise ሊያደርጉ ይችላሉ። ይሁንና በምንም ተዓምር የsafety minimum ቁጥርን compromise አያደርጉም።

በአጭሩ፣ በማንኛውም በረራ፣ የsafety minimum የሚሆነውን ቁጥር ያክል የበረራ አስተናጋጆች ከሌሉ፣ በረራው ሊደረግ አይችልም። ይህም የበረራ መስተንግዶ ስራ በዋነኝነት የሚያያዘው ከበረራ እና የመንገደኞች ደህንነት ጋር እንጂ ምግብና መጠጥ መስተንግዶ ጋር አለመሆኑን በውል ያሳያል።

በብዙ ሀገራት አየር መንገዶች፣ Low cost airlines የሚባሉ አየር መንገዶች አሉ። የምግብና መጠጥ አቅርቦትና መስተንግዶን ጨምሮ፣ በተለምዶ የምናውቃቸውን የመንገደኛ አገልግሎቶች በመቀነስ፣ ዋናውን የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ብቻ በማቅረብ በቅናሽ የሚያጓጉዙ አየር መንገዶች ናቸው። እነዚህን መሰል አየር መንገዶች፣ በአሜሪካና በአውሮፓ በጣም የታወቁና የተለመዱም ናቸው። ይህም የሚነግረን እውነት፣ የበረራ አስተናጋጆች ዋነኛ ጥቅም ምግብ እና መጠጥ ማቅረብ ሳይሆን በአደጋ ጊዜ የመንገደኞችን ደህንነት መጠበቅ መሆኑን ነው።

ከዛሬ ጀምሮ፣ የበረራ አስተናጋጆች ስራ ምንድነው ስትባሉ፣ የመንገደኞችን ደህንነት መጠበቅ እና ማስጠበቅ እንደምትሉ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ተስፋ አደርጋለሁ፣ ከዚህ በኋላ ለመንገደኛው ክብር እና ለሀገር ገጽታ ሲሉ ራሳቸውን አስውበው ከምታዩአቸው የበረራ አስተናጋጆቻችን ጀርባ፣ ለሌሎች ደህንነት የራሳቸውን ህይወት አስቀድመው ለመስጠት የተዋቡ ልቦቻቸውንም ጭምር እንደምናይ።

ልባዊ አክብሮት እና ምስጋና ለበረራ አስተናጋጆቻችን ሁሉ!

@Yonathan
ዮናታን መንክር ካሳ፣ ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ጸሐፊ፣ የግል አብራሪ እና የአየር ሜዳ የአቪዬሽን ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ ነው።

Читать полностью…

Perspective

የሁለተኛ ድግሪ በምማር ወቅት ከ #ሱማሌላንድ በዩኤን ዲ ፒ ስኮላር ተሰጥቷቸው ኢትዮጵያ መጥተው ይማሩ የነበሩ ጓደኞች ነበሩኝ። ስለ ሀገራቸው ሲናገሩ በጣም በኩራት ነበር "ሱማሌ" ባልኳቸው ቁጥር "ሱማሌላንድ" እንድል ያርሙኛል። "ዓለም እውቅና አለመስጠቱን አትመልከት በምስራቅ አፍሪካ የህዝብ ምርጫን ዲሞክራሲያዊ ብቻ ሳይሆን ዲጂታል አድርገን በመምራት እንታወቃለን" ይሉኛል።


በቅርቡ ኢትዮጵያና እና ሱማሌላንድ የወደብ ስምምነት ማድረጋቸው ተሰምቷል ታዲያ ስምምነት ማድረጓቸውን ተከትሎ የሚጠበቁ ምልልሶች ጀምረዋል (የሱማሌ "ግዛቴን ከመውረር ለይቼ አላየውም"፤ የአውሮፓ ህብረት "የግዛት ልዋላዊነት እንዳይረሳ"፤ የግብፅ "የሱማሌ የግዛት አንድነት እንዲጠበቅ አለሁ" ፤ ወዘተ)።


የኢኮኖሚ ስምምነቶች የጋራ ተጠቃሚነት ከተቻለ ይበልጡን የመጠቀም መርህን የተከተለ ነው። ለምሳሌ፦ ሱማሌላንድ 20ኪ.ሜ ለወደብ የቀረበ የየብስ መሬት ለ50ዓመት መነሻ ኪራይ በመስጠት ከኢትዮጵያ ቀልፍ አጋርነት፤ የሀገርነት እውቅና፤ የመሰረተ ልማት ተጠቃሚነት፤ የመብራት ሃይል አቅርቦት እንዲሁም ከግዙፍ የመንግስት የልማት ተቋማት ድርሻ የማገኘት ድርድር ሊኖራት ይችላል።


ስለዚህ ድርድሩ በመጪው 50 ዓመት የሚመጡ እድሎች እና ስጋቶችን የደመረ የቀነሰ ረዥም እንደሚሆን ግልፅ ነው። ስምምነት በሚደረስባቸው ጉዳዮች በሙሉ ኢትዮጲያም ልታሸንፍ ሱማሌላንድም ልታተርፍ ለቀጣይ 50 ዓመት አቅጣጫ ቀያሪ ውሳኔ ሊያሳልፉ ነው የሚገናኙት።


ወደብ ለኢትዮጵያ ለኢኮኖሚ ወሳኝ ነው። ይበልጥ በቀጣይ ለማደግ ለሚደረግ ፍጥነት ቀላል ድርሻ አይኖረውም። በተመሳሳይ ከእውቅና እስከ የለማ መሰረተ ልማት ተጠቃሚነት ለሱማሌላንድ ግዙፍ በረከት ነው።


ከ1991ጀምሮ የሱማሌላንድ የእውቅና ጥያቄ በዓለም ሀገራት የሚጣጣለው አንድም የሱማሌን መብት ከመግፋት ጋር በማቆራኘት ሲሆን በዋናነት ግን ራስ ገዝ የሆነ ግዛቶችን በቀላሉ የሀገርነት እውቅና በሰጡ ቁጥር ተመሳሳይ እልፍ ተሰነጣጣቂ ሀገራትን ላለመፍጠር ነው።


በኢትዮጵያ እና በሱማሌላንድ መካከል የተደረሰው ስምምነት ማንን ይበልጥ በዘላቂነት ሊጠቅም እንደሚችል ለማወቅ የስምምነቱ (ምን የመስጠት እና ምን የመቀበል) ጭብጥ በደንብ ሲቀርብ ለመወሰን ይቀላል። በመርህ ደረጃ ግን ሁለቱም እጅግ የሚያስፈልጋቸው ጉዳይ ላይ እንደተገጣጠሙ ይሰማኛል።


እንደዚህ አይነት ስምምነት በወደፊቱ በ2070ዎቹ ሳይቀር ሁለቱ ሀገራት ሊኖራቸው የሚችለውን ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታ ሳይቀር የሚወስን ነው።


ለሱማሌላንድ የሀገርነት እውቅና ከኢትዮጵያ ሀ ብሎ መጀመር እና በኢትዮጵያ በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ኢኮኖሚያዊ አቅም ከፈጠሩ የልማት ድርጅቶች ድርሻ ማግኘትን ከጨመረ ቀላል ጥምቅ አይኖረውም። ለኢትዮጵያ በተመሳሳይ ለመጪው ጊዜ የጦር መንደር ከማግኘት እስከ ነጠላ ክንፍ የወደብ ጥገኝነት (ጅቡቲ) ላይ ለተንጠለጠለው ኢኮኖሚ ሰፊ አማራጭ ማግኘቱ  ቀላል ፋይዳ አይኖረውም።

*
የኢኮኖሚ ባለሙያ ዋሲሁን በላይ

Читать полностью…

Perspective

አንጋፋ የኪነ-ጥበብ ምሽት

በታላቁ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ባህል ማዕከል የሚዘጋጀው የኪነ-ጥበብ መርሃ ግብር ስድስተኛ ምሽቱን ከፍ ባለ ዝግጅት ዕረቡ ታህሳስ 24 ያካሂዳል ። በእለቱም ቢተውን የሚሳካለት ፣ ቢያነብ የሚያምርበት ፣ ቢናገር የሚሰምርለት የመድረክ ንጉሱ ግሩም ዘነበ ( እያዩ ፈንገስ ) በመሀከላችን ይገኛል ! እንዲሁም ግጥሞች ፣ ወግ ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ተሰናድተው እናንተ ውድ ታዳሚዎቻችንን በባህል ማዕከል አዳራሽ ከቀኑ በ 11: 30 ጀምሮ ይጠብቃችኃል  ።

#ሼር ያድርጉ !

#ማስታወሻ :— ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም የምትፈልጉ በአሁን ሰዓት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የስነ ጽሑፍ አፍቃሪያን መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው ።

/channel/weperspective

Читать полностью…

Perspective

#ኪስህንን_ከሌባ_ጠብቅ_ብለህ_ስረቀው!

ከሰዎች የምትፈልገውን ነገር ለማግኘት መጀመሪያ የምትፈልገውን ነገር የት እንደደበቁት ለማወቅ ጥበብ መጠቀም ይኖርብሃል፤ የሌቦችን የኪስ ማውለቅ ጥበብ መቼም ሳታውቀው አትቀርም፡፡

ኪስ አውላቂዎች ይህንን አሪፍ አድርገው ይሰራሉ።

ኪስ የማውለቅ ቁልፉ የኪስ ቦርሳህን የያዘው የትኛው ኪስ እንደሆነ ማወቅ ነው።

ልምድ ያላቸው ኪስ አውላቂዎች ስራቸውን የሚሰሩት በአውቶቢስና ባቡር ጣቢያዎች እንዲሁም በሌሎች በግልጽ “ኪሳችሁን ከሌቦች ጠብቁ” የሚል ምልክት በተለጠፈባቸው ቦታዎች ነው።

ምክንያቱም ይህንን ምልክት የሚያዩ መንገደኞች# የኪስ_ቦርሳቸው_እንዳለ_እርግጠኛ_ለመሆን ኪሳቸውን ይዳብሳሉ።

ለመስረቅ አድፍጠው ለሚመለከቱት ኪስ አውላቂዎች፣ ይህ ጥሩ ምልክት ነው። እንዲያውም ኪስ አውላቂዎች የሚታወቁት የራሳቸውን “ኪሳችሁን ከሌባ ጠብቁ” የሚሉ ስኬታቸውን የሚያረጋግጡ ምልክቶች በማስቀመጥ ነው።

አንተም የተደበቀብህን ነገር ለማወቅና የምትፈልገውን ነገር ለማግኘት የደበቀብህ ሰው እራሱ በጥበብ እንዲያሳይህ አድርገው! እንዴት?

#የኃያልነት_ሕጎች መጽሐፍ ጥበቡን ያስተምርሃል።

🎀

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡

እይታ በአንድ ሰው ልምዶች ፣ እምነቶችና ስሜቶች ተጽዕኖ የሚደረግበት ግላዊ አመለካከት ነው ። ግለሰቦች ሁኔታዎችን እንዴት እንደሚገነዘቡ እና እንደሚተረጉሙ ይቀርፃል ፣ ይህም ብዙውን ጊዜ በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ የተለያዩ አመለካከቶችን ያስከትላል ። ይህም የግለሰብ እይታ ተቀባይነት ካገኘ የሀገር ብሎም የዓለም ይሆናል ::

መጽሐፍ ፣ ስዕል ፣ ሙዚቃ ...

/channel/weperspective

Читать полностью…

Perspective

ሰውዬው ድግስ ነበረበትና በሬውን አረደ
በ Zemelak Endrias
ከድግሱ እንዲቋደሱለት ዘመድ አዝማድ እና ጎረቤት መጋበዝ ፈልጎ ሴት ልጁን ጠርቶ "ሄደሽ ጎረቤቶቻችንን እና ወዳጆቻችንን እየዞርሽ ጥሪያቸው: ከእኛ ጋር ይብሉ ይጠጡ" አላት

ሴት ልጁም የሰፈሩ መስቀለኛ መንገድ ላይ ወጥታ "እባካችሁን ጎረቤቶቻችን ቤታችን በእሳት ተያይዞ እየነደደ ነው: እባካችሁን መጥታችሁ በማጥፋት አግዙን" ስትል ጮኸች

የተወሰኑ ሰዎች የልጅቷን ጥሪ ሰምተው እየሮጡ ወደ አባትየው ቤት ሄዱ: ሌሎች ደግሞ ሰምተው ዝም አሉ

ድግሱ ተጀመረ: ምግብ መጠጡ ቀረበ :ሁሉም መደሰት ጀመረ

ሰውዬው ቅርብ የሚላቸው ወዳጆቹ እና ጎረቤቶቹ ጋብዟቸው ባለመምጣታቸው ቅር ብሎታል

ሴት ልጁንም ጠርቶ "እዚህ የማያቸው ሰዎች በቅርቡ ወደ ሰፈራችን የመጡ ናቸው: አንዳንዶቹን ደግሞ ከነአንካቴው አላውቃቸውም:: ጎረቤቶቻችን እና የቅርብ ወዳጆቻችን የታሉ? አልጠራሻቸውም እንዴ" ሲል ጠየቃት

ልጅቱም እንዲህ አለችው

👇🏾

“እዚህ የምታያቸው ሰዎች ቤታችን ውስጥ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት እና እኛን ለመርዳት የመጡ ናቸው: ድግስ መኖሩን አያውቁም ነበር"

"ስለዚህ እነዚህ ናቸው ወዳጆቻችን እና ጎረቤቶቻችን: ከእነዚህ ጋር ነው ደስታችንን መካፈል እና ድግሳችንን መቋደስ ያለብን"

ምንጭ :- ሶሻል ሚዲያ

Читать полностью…

Perspective

#Ethiopia #Seaport

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከሶማሊለንድ ጋር ስለተፈረመው ስምምነት ምን አሉ ?

- ኢትዮጵያ የባህር በር ተጠቃሚ እንድትሆን በምክክር፣ በሰላማዊ መንገድ ብቻ በሰጥቶ መቀበል መርህ የተለያዩ የዲፕሎማሲ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል።

- ከሌሎች ጎረቤት ሀገራት ጋር ብዙ ሞክረን ያልተሳካው ከሶማሊላንድ ጋር በተመሳሳይ መንገድ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል።

- መንግሥት አቋሙን ይፋ ካደረገ በኃላ ያሉ ሃብቶችን ከመጋራት አንፃር የነበረው ጉዳይ ጥርቶ ከወጣ በኃላ ዝርዝር ውይይት ሲካሄድ ነው የቆየው።

- ጉዳዩ መልክ እስኪይዝ በተወሰነ በጠባብ ቡድን፣ በመሪዎች ደረጃ እና በተወሰኑ አካላት ደረጃ እንዲያዝ እየበሰለ ሲሄድ ደግሞ ሁለቱም አካላት የየራሳቸውን አመራር እያሳተፉ የሚሄዱበት ሁኔታ እንዲፈጠር ተደርጓል።

- የወደብ ስምምነት ተጠቃሚነት በሊዝ አማካኝነት የሚፈፀም ነው።

- ይህ የስምምነት ማዕቀፍ ሶማሌለንድ እና ኢትዮጵያ አንዳቸው ጋር ያለውን ሃብት ለመጋራት በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ እድል የሚያሰፋበት፣ በመከላከያና ደህንነት ዘርፍ ኢትዮጵያ ያላትን አቅምና ልምድ ለሶማሊላንድ የምታጋራበት ፤ የጋራ ጥቅማቸውን ማስጠበቅ የሚችሉበት አቅም ይገነባል።

- የስምምነቱ ማዕቀፍ ኢትዮጵያ ሶማሌላንድ ውስጥ Military base እና Commercial maritime ሰፈር እንዲኖራት ይፈቅዳል። ይህ #በሊዝ የሚታሰብ ይሆናል። ለ50 ዓመት እና ከዛ በላይ #በማራዘም የሚካሄድ እንዲሆን ያደርጋል።

- ኢትዮጵያ አማራጭ ወደብን እድል ለማግኘት በርበራ ኮሊደርን የምታሰፋበት ፣ የመከላከያ አቅሟን አዲስ በምትከራየው ቦታ የምታጠናክርበት እድል ይሰጣል።

- ኢትዮጵያ ለሊዝ ተጠቃሚነቷ ቴሌኮም ይሁን፣ አየር መንገድ ይሁን ጥቅም በሚያስገኙ መሰረተ ልማቶች ላይ ድርሻ ትሰጣለች። ምን ያህል ነው ? የሚለው የሚከፈለው ሊዝም ምን ያህል ይሆናል ? የሚለው በዝርዝር ውይይቶች ይወሠናል።

- በጤና፣ በትምህርት ፣ በመከላከያ የሚሰሩት ዝርዝር ስምምነቶች በተናጠል ውይይት ይካሄድባቸዋል። ወደ ፓርላማ ሄደው የሚፀድቁ በርካታ ስምምነቶች ከዚህ ይፈልቃሉ።

- የጋራ የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱ አጠቃላይ ማዕቀፍ ሁለቱ አካላት በጋራ ተባብረው የሚያድጉበትን ማዕቀፍ ነው የሚያስቀምጠው። ዋና ዋና አንጓዎች ተቀምጠዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር የምታገኝበትን ዕድል በተጨባጭ ወደመሬት ለማውረድ እድል ይሰጣል።

- ስምምነቱ በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ሂደቱ ያልቃል / ወደ ተግባር / ስራ ይገባል።

- ከሌሎች ሀገራት ጋር የጀመርናቸው አሉ #ከኤርትራ ጋር በዝርዝር ውይይት ተጀምሮ የሆነ ቦታ ላይ ነው የቆመው።

- ኢትዮጵያ አንድ ወደብ ፣ ሁለት ወደብ ፣ ሶስት ወደብ ሳይሆን ፤ ኢትዮጵያ አሁን ባለው ሁኔታ እያደገች ከሄደች ሁሉም ቀጠናዎች የሁሉም ጫፎች የኢትዮጵያን ምርቶች የሚያስገቡበት በር ያስፈልጋል።

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በማብራሪያቸው በስምምነቱ ሶማሊያ ልዓላዊ ግዛቴ ናት ለምትለው ራስ ገዟ #ሶማሌላንድ በይፋ የነፃ ሀገርነት እውቅናን ትስጠ እንደሆነ የተናግሩት አንዳች ነገር የለም።

ምንጭ @tikvahethiopia

Читать полностью…

Perspective

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በውጭ ሀገር በስፋት የምንሰማው ራስን የማጥፋት (suicide) ተግባር በሀገራችን በተለይም አንዲት እንስት 'ብንሄድ ይሻላል' ብላ Facebook ከለጠፈች እና ራሷን ካጠፋች ብኋላ በሀገራችን በተለይም በወጣቱ ዘንድ እንደተስፋፋ ግልፅ ነው።

ከዚህ ቀደም በሚዲያ አንሰማው ይሆናል እንጂ ይህ ራስን የማጥፋት ድርጊት በዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ የትምህርት እና ስራ ቦታዎች ላይ ሲከሰት ነበር።

ምናልባትም ይህንን በራሳችን ላይ ለመፈፀም የሚያስገድዱ ሁኔታዎች ውስጥ ያለፍን ልንኖር እንችላለን። ሰው ነፍሱን በራሱ ለማጥፋት ምክንያት የሚሆኑ በጥቂቱ ብንጠቅስ ፦

ሕይወት ፊቷን ስታዞር እና ቀን ሲጨልምበት
በሚያመነው ሰው ሲከዳ እና ተስፋውን ሲያጣ
የኑሮ ፈተና ሲበዛ እና መውጫ መንገድ ሲጠፋበት በሚያሰበው ልክ ነገሮች ሳይከናወኑለት ሲቀሩ
በሚያየው ሁሉ ነገን ኣሻግሮ ማየት ሲያቅተው
በቤቱ በትዳሩ ክብርን እና ተቀባይነት ሲነፈግ ወ.ዘ.ተ ናቸው።

በርግጥ በግለሰቡ ሁኔታ እና ጫማ ውስጥ ሆነን ነገሩን መመልከት እስካልቻልን ድረስ ስለዚህ ሁኔታ በድፍረት መናገር አንችልም።

የራስን ማጥፋት ውሳኔ ቅፅበታዊ ነው። ጥቂት ሰከንዶች ሺህ ዘመን መስለው ይታያሉ። ስቃይ እና ፈተና ዘላለማዊ ይመስልና አዕምሯችን ለውሳኔ እንድንጣደፍ ሆርሞኖችን ይቀሰቅሳል። ከዚያ ነገሮች ያበቃሉ። ሰዎች የሰዎችን ሁኔታ አያዩም እንጂ በርካቶች ለተመሳሳይ ወጥመድ ተጋልጠው በተዓምር ይሁን በራሳቸው ብርታት አምልጠዋል። ለዚህ ምስክሮችን መጥራት አያስፈልግም።

በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ራሳችንን እንዳናገኝ እነዚህ ነገሮችን ብንተገብር መልካም ነው ብዬ አስባለው።

1. ከእምነት ተቋማት አለመራቅ። ሀይማኖታዊነትን መላበስ በራሱ የመንፈስ ጥንካሬ ይሰጣል ብዬ አምናለው።

2. Multi-Professional-Friends ሊኖሩን ይገባል። በአንድ ሙያ መስክ ብቻ የተሰማሩ ጓደኞች አይኑሯችሁ። ሕይወትን ከተለያዩ አቅጣጫዎች ሊያስመለክቱ የሚችሉ ወዳጆችን መፍጠር ያስፈልጋል።

3. በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ የምክር አገልግሎት የሚሰጡ -Counselling and Guidance Service ተቋማትን መጎብኘት ያስፈልጋል። በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚገኙ እነዚህ ተቋማት በመሰል ማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ቦታዎች በየከተማው ላይ መስፋፋት አለባቸው።

ራሳቸውን ላጠፉ ፈጣሪ እዝነቱን ያድርግላቸው !

Credit: Workineh Gebeyehu Gomera

@weperspective

Читать полностью…

Perspective

ስለደራሲ በዓሉ ግርማ በጥቂቱ ...

ደራሲ በዓሉ ግርማ በኢሉባቦር ክፍለ ሀገር ሱጱ በምትባል ሥፍራ በ1928 ዓ.ም ተወለዱ ። ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዘነበወርቅ ትምህርት ቤት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በጄኔራል ዊንጌት አጠናቀዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም በፓለቲካል ሳይንስና ኢንተርናሽናል ሪሌሽን የቢኤ ዲግሪ ያገኙ ሲሆን በዚሁ ተመሳሳይ መስክ ከአውሮፓ የማስተር ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።

በዓሉ ግርማ በተለይ በልብ-ወለድ ፈጠራ የስነ-ጽሑፍ ስራዎች ከታወቁት የኢትዮጵያ የዘመኑ ደራሲዎች መካከል ተወዳጅነትና ዝናን ካተረፉ እውቅ ደራሲ አንዱ ነበሩ ። ከጻፉቸው በርካታ ድርሰቶቻቸው ውስጥ ከአድማስ ባሻገር የተሰኘው መጽሐፋቸው በሩሲያ ቋንቋ ተተርጉሞ ሶቭየት ሕብረት ቀርቧል። በተጨማሪም በጋዜጠኝነት ሙያም ስማቸውን ያስጠሩ ሙያቸውንም ያስከበሩ ነበሩ።

የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ፣ የመነን መፅሔት ፣ የአዲስ ሪፓርት መጽሔት ፣ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በመሆን ከመሥራታቸውም ባሻገር ብዙ ወጣት ጋዜጠኞችን ለማፍራት ጥረት አድርገዋል። አዲስ ሪፓርት የተባለውን መጽሔትም ደረጃው ከፍ እንዲልና በኢንተርናሽናል ደረጃ እንዲገመገም አድርገዋል። እንዲሁም በኢትዮጵያ ሬድዮ ሠርተዋል።

ደራሲ በዓሉ ግርማ ለኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ከፍተኛውን አስተዋጽኦ ያበረከቱና ብዙ ሥራዎችን ያቀረቡ ሲሆን የመጨረሻው ጽሑፋቸው "ኦሮማይ" በመባል የሚታወቅ ሲሆን በወቅቱ በነበረው የመንግስት የነበሩ ባለስልጣናትን ክፉኛ ተችቷል በማለት ጥርስ ተነከሰበት :: በዚህ መጽሐፍ ምክንያት በ1976 ዓ.ም ለደራሲው ሕይወት መጥፋት መንስኤ ሆኗል ።

የደራሲው ስራዎች :-

ከአድማስ ባሻገር
ሀዲስ
የቀይ ኮከብ ጥሪ
ደራሲው
የህሊና ደወል
ኦሮማይ

@weperspective

Читать полностью…

Perspective

አቶ ጃዋር መሐመድ በ2023 ካነበባቸው ጠቃሚ እና ጥሩ ያላቸው 25 መጽሐፎች።

1. The Wise Men by Evan Thomas & Walter Isaacson

2. The Loom of Time by Robert D Kaplan

3. Napoleon by Andrew Roberts
4. MBS by Ben Hubbard

5. For Profit by William Magnuson

6. China after Mao by Frank Dikotter

7. The Age of Strongman by Gideon Rachman

8. Leadership by Henry Kissinger

9. How Civil War Start by Barbara F Walter

10. Why We Fight by Christopher Blattman

11. Chip War by Chris Miller

12. Capital in Twenty-First Century by Thomas Piketty

13. If We Burn by Vincent Bevins

14. How States Think by John J
Mearshemer

15. Seeing Like a State  by James  C Scott

16. Conflict by David Petraeus

17. Landscape of History  by John Lewis Gaddis

18. On Politics by Alan Ryan

19. The Epic Split by Johan Nylander 

20. Founding Partisans  by H.W. Brands

21. Theory of Irregular War by  Jonathan W Hackett 

22. The Coming Wave by Mustafa Suleyman

23. Power and Progress by Daron  Acemoglu

24. Identity and Violence by Amartya Sen

25. How China Escaped the Poverty Trap by Yuen Yuen Ang


/channel/weperspective

Читать полностью…

Perspective

ዘወትር እሁድ የሚጠብቁት የሪፖርተር ጋዜጣ የተለያዩ መረጃዎችን ይዞ በገበያ ላይ ይገኛል
በድረገጻችን https://www.ethiopianreporter.com/ ላይም ያገኙታል።
----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com

Join us on 👇/channel/weperspective

Читать полностью…

Perspective

ሲፈለግ የነበረው የሕግ መጽሐፍ
በሁለት ቅጽ ተከፋፍሎ ታትሟል

የተጠቃሰሱ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ሰበር ሰሚ ችሎት
ከቅጽ 1-25 የታተሙ እና ከ2006 እስከ 2015 የተሰጡ ያልታተሙ ዉሳኔዎች

በመላከ ጥላሁን( LLB/LLM)

ይህን በዋጋ ሊተመን የማይችል የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የታተሙ እና ያልታተሙ ዉሳኔዎችን በአንድ ላይ አጠቃሎ የያዘ መጽሃፍ ላይ አስተያየት የመስጠት እድል አግኝቻለሁ፡፡

ይህ ስራ ዳኛ መላከ ጥላሁን ትጋት እና ብቃት የተሞላበት ስራ በመስራት እነዚህን ለበርካታ ዓመታት ያልታተሙ ዉሳኔዎችን ጭምር በጥንቃቄ ሰብስቦ እና የታተሙትን ዉሳኔዎች አጠቃልሎ በጉዳዮች ዓይነት ከፋፍሎ በማቅረብ በቀላሉ ተደራሽ እንዲሆኑ የተደረገበት ነዉ፡፡

ይህ ጥንቅር ለጠበቆች፤ዳኞች እና ለምሁራን ጠቃሚ ግብዓት ነዉ፡፡የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ የሕግ ትርጉም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ዳሰሳ ተደርጎ የሚሰጥበት ነዉ ተብሎ የሚገመት ሲሆን በመጽሐፉ ጉዳዮች በደንብ የተደራጁ እና በዉሳኔዉ እልባት ያገኘዉን የሕግ ጭብጥ በቀላሉ ለማግኘት የሚረዳ እንዲሁም ማጠቃለያዎቹ አጭር እና መረጃ ሰጪ ናቸዉ፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሚሰጣቸዉን ዉሳኔዎች ለማናቸዉም ሥራ መመርመር እና መጠቀም ለሚፈልግ ማንኛዉም ሰዉ ይህን ጥንቅር እንዲጠቀም እመክራለሁ።

አልማው ወሌ
የቀድሞ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ስበር ሰሚ ዳኛ
አሁን ጠበቃና የሕግ አማካሪ

4ኪሎ ምኒልክ ት/ቤት ፊት ለፊት ከሮሚና ዝቅ ብሎ።
ሥልክ፦ 0912735000
            0905222224

ይህ የእነሆ መጻሕፍት የቴሌ ግራም ቻናላችሁ ነው የተለያዩ አዳዲስ መጻሕፍት ይተዋወቁበታል። የእነሆ መጻሕፍት ግብዣችን ጥቆማ ይቀርብበታል።

/channel/enhobooks

Читать полностью…

Perspective

#ፍርሃትህን_ተጋፈጠው!!!

የወደቅከው በፍርሃት የተነሳ ነው እንጂ አቅም አንሶ ወይም ስለማትችል አይደለም።

ፍርሃት አቅምህ አሽመድምዶ እራስህ አሳንሰህ እንድታይ ያደርግሀል። ነገርግን እውነታው ያ አይደለም። ፍርሃት እንዳይሰማ የማይቻል ቢሆንም ፍርሃትህ የህይወት መሪ አለማድረግ እና አለማደመጥ የአንተ ድርሻ ነው።

ፍርሃቱ እያለብህ ማድረግ የለብህ ነገር መፈፀም አለብህ። ልጅ እያለን ትምህርት ቤት የምናውቀውን ነገር ፊት ላይ ወጥተን ለሌሎች አቅርቡ ስንባል  ፍርሃት እና ብርክ ብርክ ይለን ነበር። ከዚህም አልፎ የምናውቀው ነገር ሁሉ ይጠፋብን ነበር።  ፈርተን ስናወራ እና ሲስቁብን የበሰ ከዚህ በኃላ ሰው ፊት ወጥቼ አናወራም እንል ነበር። እናም አሁን በህይወታችን ብዙ ነገሮች መሞከር አቆምን፤ ምክንያቱም በልጅነታችን እንደተሳቀብን አሁን ብንወድቅ ወይም ብንሳሳት ይስቁብኛው ብለን ስለምናስብ።

ፍርሃትህን አሸንፈው። ምክንያቱም ብዙ ህልሞች የሞቱት በፍርሃት መሆኑን እወቅ። ሩቅ የሚያስጉዝ አቅም አሳስሮ የሚያስቀምጥህ ፍርሃት የተበለ ነቀዝ ነው። ምን ይሉኝ ይሆን ብለህ አትስብ፤ የሚሉትን ይበሉ፤ ግን መኖር አለብኝ ብለህ የምታስበው ኑር። ደፋር ሁን፤  ፍርሃት እንኳን  ዙሪያህ ቢከብህም። አንተ የሚወቅስህ እና አትችልም የሚልህ አብዛኛው ጊዜ ምንም ነገር ሞክሮ የማያወቅ የመቀመጥ ንጉስ፣ የጥላቻ አለቃ የሆነ ሰው ነው። ተዋቸው ያሉትን ይበሉ። ዛሬ እኳ ነው ዳዴ የምትለው ከሆነ ጊዜ በኃላ ምን ያህል እርቀት ከእነሱ  እንደሚኖርህ አስብ።

በህልምህ አትቀልድ፤ በህልምህ አታሹፍ፤ መከፈል የለበት ዋጋ ከፍለህ መድረስ የለብህ ነገር ጋር ድረስ። ፍርሃት ተጋፈጠው፤  እንደምትችል እመን። አሁን ጀመሪ ነህ። ማንንም አልሰማህ ሲልህ አይዞህ ሁሉም ከመውደቅ ነው መራመድ ቀላል የሆለት። ምን ይሉኛ የሚለው ፍርሃት ከብዙ ነገር ወደኃላ እንዳስቀረህ ስታስብ ልትቆጭ ይገባል። ዋናው ፈጣሪ የሚከብርበት ሰው የማይጎዳ ነገር ከሆነ ለምን ብለህ ነው የምትሳቀቀው። ሰው ፊት ወጥተህ ማቅረብ ስትጀምር ስትንቀጠቀጥ፣ የሌለብህ መንተባታብ ስንተተባተብ፤ አይገርም ነገሩ ሳታውቀው ቀርታህ አይደለም። ነገር ግን ፍርሃት ስላለሸንፈከው ነው።

አየህ ትክክል ነው ወይ  ያልኩት ብለህ ስትጨነቀ የባሰ ምንም እንደማያውቀው ሰው ትሆናለህ። እና ፍርሃት ያስመለጠህ ብዙ ዕድሎች እንዳሉ አይሰማህም። ስለዚህ ፍርሃት ህልምህ ከመግደሉ በፊት አንተ ተጋፈጠው።

✍️ህልመኛው

📕📕📕

(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)

ቴሌግራም- /channel/teklu_tilahun
ፌስቡክ ገጽ 1- https://bit.ly/3sNq5Kd
ፌስቡክ ገጽ 2- https://bit.ly/3sJcsMa

Читать полностью…

Perspective

Ethiopia in Theory - Elleni Centime Zeleke

የ1966 አብዮት እና በአብዮቱ ዙሪያ የነበሩ ኀልዮቶች (Theories) በድህረ አብዮት ዓመታት ፣ በቅድመ እና ድኅረ ምርጫ-97 እና የቅርብ ዘመን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ስላሳደሩት ተጽዕኖ በሚዳስሰው መጽሐፍ ዙሪያ የኢትዮጵያ ቡክ ፎረም አሰናኞችና ተሳታፊዎች ውይይት ያደርጋሉ።

የውይይቱ ሊንክ:

https://www.clubhouse.com/invite/b36S0GJWq9Dw60GN5AEpeoykRDpRFOVD53R:sfyjXXKaDs0wd5CtxvyEbYqvTLkHZJWRDgO6EF1K4RQ

Читать полностью…

Perspective

#ዛሬ_የሕይወታችሁ_የመጀመሪያው_ቀን_ቢሆን!

እንደምን አደራችሁ የሃገሬ ሰዎች፡፡

“ዛሬ የሕይወታችሁ የመጀመሪያው ቀን ነው!” ብትባሉ . . . 

•  ምን በማድረግ ቀኑን ትጀምራላችሁ?

•  ምንስ በማቆም ቀናችሁን ትጀምራላችሁ?

•  የትኛውን ነገር በመርሳትና ወደኋላ በመተው ሕይወታችሁን ትጀምራላችሁ?

•  ከየትኛው መርዛማ ግንኙነት በመለየት ወደፊት ለመሄድ ውሳኔን ታስተላልፋላችሁ?

•  ለወደፊቱስ ምን አይነት እቅድ ታወጣላችሁ?

•  እስካሁን ተጨንቃችሁ ምንም ለውጥ ያላመጣችሁትን የትኛውን ጭንቀት ለመተው ትወስናላችሁ?

በሉ እንግዲያው፣ “ዛሬ ለተቀረው ዘመናችሁ የመጀመሪያው ቀን ነው”!

“Today Is The First Day Of The Rest Of Your Life” - Charles Dederich

መልካም ቀን ይሁንላችሁ!

ዶ/ር ኢዮብ ማሞ

/channel/weperspective

Читать полностью…

Perspective

#በዓሉ_ግርማ

ገበያ ላይ ብትፈልጉ የምታገኟቸው የበዓሉ ግርማ መጽሐፎች :: መጽሐፎቹን በትክክለኛው ዋጋ የምትገዙበትን ብር መጠን እና መጽሐፍ ቤቱቹን አድራሻ ጽፌላቹሃለሁ ::

ስለመጽሐፍ ጉዳይ ጥያቄ ካላችሁ ኮሜንት ላይ ጠይቁኝ ::

Читать полностью…

Perspective

የአሌክስ አብርሃም ስድስት ስራዎች

Читать полностью…

Perspective

በስራዎ ሲበዛ Busy ናችሁ ማለት ምርታማና ትርፋማ ናችሁ ማለት አይደለም ::

Читать полностью…

Perspective

" መንገድ ስጡኝ ሰፊ " በገብረክርስቶስ ደስታ Pdf

ይህን የግጥም ስብስብ በመጽሐፍ መሸጫዎች መደብር አታገኙትምና ይህን Pdf File ተጠቀሙበት ::

እይታ በአንድ ሰው ልምዶች ፣ እምነቶችና ስሜቶች ተጽዕኖ የሚደረግበት ግላዊ አመለካከት ነው ። ግለሰቦች ሁኔታዎችን እንዴት እንደሚገነዘቡ እና እንደሚተረጉሙ ይቀርፃል ፣ ይህም ብዙውን ጊዜ በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ የተለያዩ አመለካከቶችን ያስከትላል ። ይህም የግለሰብ እይታ ተቀባይነት ካገኘ የሀገር ብሎም የዓለም ይሆናል ::

መጽሐፍ ፣ ስዕል ፣ ሙዚቃ ...

/channel/weperspective

Читать полностью…

Perspective

10 Lessons from 12 Rules for Life: An Antidote to Chaos

1. Stand Up Straight with Your Shoulders Back: This seemingly simple act fosters confidence and a sense of power, improving your mood and posture, and projecting assertiveness to the world.

2. Treat Yourself Like Someone You Are Responsible for Helping: Embrace self-care and cultivate compassion towards yourself. Take care of your physical and mental health, make responsible choices, and strive to become your best self.

3. Befriend People Who Want the Best for You: Surround yourself with positive and supportive individuals who uplift and inspire you. Avoid those who drag you down or undermine your aspirations.

4. Compare Yourself to Who You Were Yesterday, Not to Who Someone Else Is Today: Focus on personal growth and progress, not external comparisons. Celebrate your own achievements and measure your steps, not someone else's finish line.

5. Do Not Let Your Children Do Anything That Makes You Dislike Them: Set clear boundaries and expectations for your children's behavior. Encourage responsibility and positive choices, and avoid indulging behaviors that lead to resentment.

6. Set Your House in Order Before You Criticize the World: Focus on improving your own life and personal conduct before attempting to fix larger problems or criticizing others. Personal responsibility should come first.

7. Pursue What Is Meaningful, Not What Is Expedient: Prioritize activities that align with your values and long-term goals, even if they seem more challenging than quick fixes or temporary satisfactions.

8. Tell the Truth – Or, at Least, Don't Lie: Honesty is fundamental in building trust and healthy relationships. Avoid deception and strive for open communication, even when difficult.

9. Assume That the Person You Are Listening to Might Know Something You Don't: Approach conversations with humility and a willingness to learn. Actively listen and be open to different perspectives, even if they contradict your own.

10. Be Precise in Your Speech: Use clear and concise language to avoid misunderstandings and communicate effectively. Choose your words with care and strive to express yourself accurately and authentically.

Please Join and share others

👍👍👍 /channel/weperspective

Читать полностью…

Perspective

12 books to make you healthier, wealthier and wiser in 2024

January 2, 2024 by @weperspective
With four highly recommended books in each of the key areas of health, personal finance, and personal growth, this diverse reading list offers practical insights to help you start the new year off strong.

Healthier:

1. How Not to Die by Michael Greger
Cut your risk of chronic disease by optimizing your diet using whole plant foods to maximize nutrition and avoid animal products linked to higher mortality.

2. Why We Sleep by Matthew Walker

Sleep at least 7 hours per night and follow basic sleep hygiene to boost learning, lower disease risk, and improve your mood and energy.

3. Spark by John Ratey

Exercise daily, even moderately, to grow new brain cells, sharpen thinking, regulate mood, and delay cognitive decline decades into life.

4. 10% Happier by Dan Harris

Reduce stress and increase calm by establishing a simple, non-dogmatic mindfulness meditation practice amidst the distractions of modern life.

Wealthier:
5. Principles for Navigating Big Debt Crises by Ray Dalio

Financial markets naturally cycle through booms and busts, so manage risk by balancing conservative and aggressive investments, and watch leveraged bubbles.

6. The Psychology of Money by Morgan Housel

Wealth is created through frugality, time, and avoiding irrational financial thinking, not chasing overnight riches or spending to impress others.

7. The Intelligent Investor by Benjamin Graham

Build long-term wealth by focusing on consistent value investing principles rather than emotions, following a patient, disciplined approach to the market.

8. Your Money or Your Life by Vicki Robin


Achieve financial independence by cutting unnecessary spending, saving and investing the difference, then aligning work with purpose rather than money alone.

Wiser:
9. Man's Search for Meaning by Viktor Frankl

Discover deep inner meaning and purpose even amidst suffering by taking responsibility to shape your response to unavoidable hardship.

10. Meditations by Marcus Aurelius

Find tranquility and wisdom for ruling your own life through practicing Stoic principles of virtue, self-control, and accepting the present moment.

11. Essentialism by Greg McKeown

Escape chaos and accomplish more by purposefully pursuing only the vital few priorities that truly matter, rather than trying to have it all.

12. The Art of War by Sun Tzu

Outthink opponents by laying flexible plans, strategically assessing strengths and weaknesses, and skillfully responding to changing conditions.

More book recommendations: /channel/weperspective

Читать полностью…

Perspective

"Man's Search for Meaning" by Viktor E. Frankl chronicles his experiences as a Holocaust survivor and psychiatrist.

The book explores the importance of finding meaning and purpose in life, especially in the face of extreme suffering and adversity.

Frankl emphasizes that individuals can find meaning in their lives, even in the most difficult circumstances, by focusing on inner strength, resilience, and the freedom to choose their attitudes and responses to challenges.

Through poignant anecdotes and profound insights, Frankl's work serves as a powerful reminder of the human capacity to find hope, meaning, and resilience, regardless of the circumstances.

Here are 10 lessons from the book:

1. Finding Purpose: Frankl argues that finding meaning in life, even amidst suffering, is essential for resilience and survival. Having a sense of purpose gives life meaning, no matter the circumstances.

2. Freedom of Attitude: While circumstances may be beyond our control, we have the freedom to choose our attitude toward those circumstances. This internal freedom allows us to find meaning in any situation.

3. The Search for Meaning: The quest for meaning is individual and unique. What brings meaning to one person might differ for another. It is a deeply personal journey.

4. Resilience Through Suffering: Frankl observed that those who endured suffering with a sense of meaning were more resilient. Finding purpose helped individuals endure hardship and emerge stronger.

5. Mindset and Response: Our attitudes and responses to challenges and adversity shape our experiences. By choosing our responses, we can find strength and meaning even in difficult times.

6. Importance of Relationships: Human connections and relationships play a significant role in finding meaning. Love, compassion, and connection with others contribute to a sense of purpose.

7. Living with Intention: Frankl emphasizes living with intention and consciousness, making deliberate choices aligned with one's values and beliefs.

8. Embracing Responsibility: Taking responsibility for our actions and choices is crucial. It empowers us to create meaning and make a positive impact despite circumstances.

9. Hope and Resilience: Even in the darkest moments, holding onto hope and maintaining resilience are powerful forces for survival and finding meaning.

10. Transcending Suffering: Through finding meaning, individuals can transcend suffering. This doesn't negate the pain but allows one to rise above it.

"Man's Search for Meaning" is a testament to the human spirit and the resilience that comes from finding purpose, even in the most challenging circumstances.

Frankl's lessons offer guidance on how individuals can find meaning, resilience, and hope in their own lives, irrespective of their circumstances.

ARE YOU INTERESTED in joining our telegram channel @weperspective

Читать полностью…

Perspective

https://www.youtube.com/watch?v=-xZxZUhulmY

Читать полностью…

Perspective

ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም

https://youtu.be/Sp4EQ4rpRxo?si=QZUv5cwbdpswEKvb

Читать полностью…

Perspective

#ተራራ_የሆነብህ_ምንድነው?

ምናልባት የአንተ ተራራ ሱስ፣ ከመጠን በላይ የሆነ የሰውነት ክብደት፣ ግንኙነቶች፣ ስራ፣ መነሳሳት አለመቻል ወይም የገንዘብ እጥረት ሊሆን ይችላል። ምናልባት ደግሞ ተራራህ ምን እንደሆነ አታውቅም ይሆናል።

ምናልባት ድንግዝግዝ ያለ የጭንቀት፣ በራስ ያለመተማመን፣ የፍርሃት ወይም በሁሉም ነገሮችህ ላይ የሚታይ አጠቃላይ የደስታ ማጣት ስሜት ሊሆን ይችላል። ተራራው በአብዛኛው፣ በፊት ለፊት ሲታይ ብዙም ችግር ያልሆነ፣ ነገር ግን የሕይወትህን እያንዳንዱን ክፍል የሚቀይር በውስጥህ ያለ ችግር ነው።

ብዙውን ጊዜ ከሁኔታ ጋር የተያያዘ ችግር ሲያጋጥምህ የምትጋፈጠው የሕይወትን እውነታ ሲሆን፣ ስር የሰደደ ችግር ሲያጋጥምህ ግን የምትጋፈጠው ከራስህ እውነታ ጋር ነው። ብዙ ጊዜ ተራራ በድንገት የሚከሰት የሕይወት ከባድ ሁኔታ እንደሆነ ታስባለህ፤እውነታው ግን ተራራ ሁልጊዜ ማለት ይቻላል ባሳለፍካቸው ዓመታት ያጋጠሙህን ጥቃቅን ጉዳቶች፣ ልማዶችና የመቋቋሚያ ዘዴዎች በማከማቸት ምክንያት የመጣ መሆኑ ነው።

#ተራራህ በአንተና ለመኖር በምትፈልገው ሕይወት መካከል ያለ እንቅፋት ነው። ወደ ነጻነትና መሆን ወደምትፈልገው ለመድረስ ብቸኛው መንገድ ደግሞ እርሱን መጋፈጥ ነው። እዚህ ያለኸውም ለለውጥ የሚያነሳሳህ ነገር ቁስልህን ስላሳየህ ነው። ያየኸው ቁስልህ መንገድህን ያሳይሃል፣ መንገድህ ደግሞ ወደ እጣ ፈንታህ ይመራሃል።

#ተራራው_አንተ_ነህ መጽሐፍ በገበያ ላይ

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡

📕📕📕

(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)

ቴሌግራም- /channel/teklu_tilahun
ፌስቡክ ገጽ 1- https://bit.ly/3sNq5Kd

Join us on telegram 👇👇👇

/channel/weperspective

Читать полностью…

Perspective

"ትውልድ የሚቀጥለው በሴት ኃላፊነት ነው!" ዓለማየሁ ገላጋይ

Читать полностью…

Perspective

" እነሆ ከዚህ ያማረ ስፍራ ሆኜ ወደ ጥሞና ዓለም ነጎድኩኝ :: ከኔዋ ሴት ርቄ በውጥን ውስጥ ወደራሴ የትውስታ ማሕደር ተጓዝኩኝ :: ከዕድሜዬ ማለዳ ጀምሮ ጥያቄዎች ነበሩኝ :: ግን ለምን እናቴ ጠላቺኝ ?! ለምንስ በኔ ላይ ፈርዳ በሐሰት መሰከረች ?! በእናቴ ዕዳ ለምንድናው የምቀጣው ብዬ ስባዝን ከረምኩኝ ::

  የኋላ ኋላ ድህነት ክፉ መሆኑን ተረዳሁ :: ድሃ ለመኖር ሲል ክብሩንና ስሙን አውልቆ ሊጥል ይችላል :: በተለይ አግኝቶ ማጣት ደስታን ያመሻል :: እናቴ ላይም አልፈርድ ዘንድ ራሴን ገሰጽኩኝ :: አብሬ ያልኖርኩትንና  ፈተናውን ያልተጋራሁት ሰው ላይ እፈርድ ዘንድ እኔ ማነኝ ? ዛሬ በሁለት እግሬ ስቆም ለኔ ከዳዴ ጀምሬ ቀና ለማለቴ ጎንበስ ያሉ ሰዎች መኖራቸውን አልረሳሁም :: "

★★★

አርምሞ
በኤልያስ ገብሩ አዕምሮ
አስራስድስተኛ ዕትም
ገጽ / 239

ጃዕፈር መጻሕፍት
መጽሐፉ ገበያ ላይ ይገኛል !!

Читать полностью…

Perspective

ትዘታ ዘ አራዳ :- በኢትዮጵያ ተማሪዎች ትግል ደማቅ ስም ስለነበረው  ጥላሁን ግዛው - በተፈሪ ዓለሙ ታህሳስ 20፣2016

https://youtu.be/o1Pes2fAQPY?si=ypqDzlqIRpLnYEil

#Ethiopia #ShegerFM #Tizitazearada #TillahunGizaw

Читать полностью…

Perspective

ተማጽኖ
(በእውቀቱ ስዩም)

አቤቱ
የጠፈር ባለቤቱ
በየብስ ነህ፥ በባህር፥ በምድር ነህ በሰማይ?
በቅጡ ለማናውቅህ ፥ በድንግዝግዝ ለምናይ

አቤቱ የፍጥረት አባት
ከሰማኸኝ ምናልባት
ኮረብታውን ሜዳ አድርገው ፤ ኮረኮንቹን አለስልሰው
የፎይታየን አድራሻ፥ ርቀቱን ቀንሰው
አልልህም!

ጽናት ስጠኝ ፤ ብርቱ አድርገኝ! በየርምጃው እንዳይደክመኝ
ከቀንበሮች ሁሉ መርጠህ፥ ምችለውን አሸክመኝ

አቤቱ! የጠፈሮች ሁሉ መስራች
አፈራርቀህ የምትሰጥ፥ መርዶና የምስራች !
ተወስነህ የማትገኝ ፤ በጊዜና በቦታ
ወሰን የሌለህ ዝምታ
እኔ ልጅህ-ሲመቸኝ ፤ ሲመቸኝ አማኝ
ባይመችህም ስማኝ

ካደፈጠው እዳ ሁሉ፥ በየበስ፥ ባየር በቀላይ
ከአውሎ ነፋስም በላይ
ከመሬት መራድም ይልቅ
ሰው ነው ሰውን ሚያሳቅቅ
ሰው ነው የሰው አደጋ
ደግሞ በሌላ ገጹ፥ ሰው ነው ለሰው ልጅ ጸጋ
ከስጦታው አካፍለኝ ፥ ካደጋው አስመልጠኝ
አልሳሳት አልልህም፥ የሚታረም ስህተት ስጠኝ !

Читать полностью…

Perspective

The Everyday Hero Manifesto

Читать полностью…
Subscribe to a channel