dbu11 | Unsorted

Telegram-канал dbu11 - DBU Daily News

14219

Youtube https://youtu.be/_0l6c0I7ouM 👉ስለ ግቢው ወቅታዊ መረጃ 📌ዲፓርትመንቶች ፡⚽️ስፓርት፡🎤ኪነጥበብ ምሽቶች ፡📄የጊቢ ማስታወቂያ ፡ ምልከታወችና ታሪክ ወግ ፡📷📷አስገራሚ ፎቶወች ፡ እውነታዎች እና መረጃወች📃 መፀሀፍት ፡ ሳይኮሎጂ ሁሉም ይዳሰሱበታል:: Contact

Subscribe to a channel

DBU Daily News

የስራ ማስታወቂያ👆

@Dbu 11
@dbu111

Читать полностью…

DBU Daily News

ለ10ሰዎች ነፃ የአይን ህክምና ተማሪዎች እድላችሁን ተጠቀሙ


ለደብረ ብርሀንና አካባቢው ነዋሪዎች በሙሉ:-
መጭውን የትንሳዔ በዓል ምክንያት በማድረግ እና ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የሀዋሪያትን እግር ያጠበበትን ዕለት በበጎ ተግባር አስበን ለመዋል ያክል በድርጅታችን አዲስ ቪዥን የዓይን ህክምና ክሊኒክ በዕለተ ሀሙስ/የጸሎተ ሀሙስ/ ማለትም ሚያዚያ 09/08/2017ዓ/ም ለ10 ሰዎች ነጻ የዓይን ህክምና አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅተናል🙏
በመሆኑም ይህንን ማስታወቂያ የተመለከታችሁ ሁሉ በተለይም አቅም ለሌላቸው እና ህክምና ለሚፈልጉ ሰዎች መረጃውን እንድታደርሱልን በትህትና እንጠይቃለን!

አድራሻችን:- ደብረ ብርሀን ከተማ ስላሴ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት አጼ ዘረያቆብ ህንጻ ስር እንገኛለን።
ለበለጠ መረጃ:-
-0913300229
-0913241929

@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

" ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ስልክ ይዘው እንዳይሄዱ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል " - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)

ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ስልክ የሚባል ነገር ይዘው እንዳይገቡ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ።

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በሚመሩት የትምህርት ዘርፍ ላይ ስለአፈጻጻምና ስለታቀዱ እቅዶች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በሰጡት ማብራሪያም በሚቀጥለው ሳምንት ከትምህርት ቢሮዎች ጋር ውይይት እንደሚካሄድ ጠቁመዋል።

በዚህም ወቅት ተማሪዎች ስልክ ትምህርት ቤት ይዘው እንዳይገቡ ለማድረግ ስለሚደረገው እንቅስቃሴ እንደሚመከር ገልጸዋል።

" የጋራ ስምምነት ላይ ከደረስን ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ገብተው ትምህርት መከታተል ነው እንጂ ከስልክ ጋር የሚጫወቱበት ሁኔታ እንዳይፈጠር ይደረጋል " ብለዋል።

via Tikvah Ethiopia


@dbu11
@dbu111

Читать полностью…

DBU Daily News

ሆሳዕና በአርያም  "ሁሉን በትሕትና ጀምሮ በትሕትና ፈጸመ:: በበረት ውስጥ ጀምሮ በአህያ ላይ ጨረሰ::
በቤተልሔም በበረት ውስጥ የነበረው በኢየሩሳሌም በአህያ ላይ ታየ"
                          
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ

ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች እንኳን ለሆሳዕና በዓል አደረሳችሁ።

@dbu11
@dbu111

Читать полностью…

DBU Daily News

በደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ሐኪም ግዛው ሆስፒታል የ2017 ዓ.ም የ9 ወር አፈፃጸም ግምገማ እና የማህበረሰብ ውይይት እያካሄደ ነው።

የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ
ግንቦት 1 ቀን 2014ዓ.ም  ስራ መጀመሩ ይታወቃል ።

ከ690 በላይ የሰው ሃይል፣128 አልጋዎች፣4 የቀዶ ጥገና ክፍሎች እና ልዩ ልዩ የህክምና አገልግሎት የሚሰጥናቸው በርካታ ክፍሎች ያሉት ነው ።
ደብረብርሃን፣ሰሜን ሸዋና ከኦሮሚያ አጎራባች ወረዳዎችን ጨምሮ  ከ3 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ህዝብ እያገለገለ ይገኛል ።
@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

..ከላይ የቀጠለ
በሚያስፈልገውን ድጋፍ እና እድሎች ማመቻቸቱን ለማስቀጠል ሁዋዌ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።


ቡድኑ ለዓለም አቀፋዊ ውድድር  እድል ያገኘው  በግንቦት 2016 ዓ.ም በኤሳውራ ሞሮኮ በተካሄደው የክፍለ አህጉራዊ የቴክፎርጉድ (Tech4Good)ውድድር ወቅት  ከ17 የአፍሪካ ሀገራት ከተውጣጡ 28 ቡድኖች ጋር ተወዳድሮ አንደኛ በወጣበት ወቅት መሆኑ ይታወሳል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ እ.ኤ.አ. በ2008 የተጀመረው የሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ፕሮግራም በአገር ውስጥ ያለውን ውድድር ከኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሚያዘጋጅ ሲሆን ለተሳታፊ ተማሪዎች ከውድድር ባለፈ የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት (AI)፣ ክላዉድ ኮምፒዉቲንግ፣5ኛ ትውልድ: ሳይበር ደህንነት፣ አይኦቲ እና ቢግ ዳታን ጨምሮ በቴክኖሎጂዎች ላይ አጠቃላይ ስልጠና የሚወስዱበት እድል ያመቻቻል።

ከ Amharic tutorial class ገፅ የተወሰደ።

@dbu11
@dbu111

Читать полностью…

DBU Daily News

ለተመራቂ ተማሪዎች በመውጫ ፈተና ዙሪያ ገለፃ ተካሄደ/ጤና ሳይንስ
======================================
በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ለ2017 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች በመውጫ ፈተና ዙሪያ ገለፃ እና ውይይት ተካሄደ፡፡

ገለጻው እና ውይይቱ በዋነኛነት ትኩረቱን ያደረገው በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚሰጠው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና(Exit Exam) የሚወስዱ ተማሪዎች በስነ-ልቦና ከወዲሁ ዝግጁ ሆነው እንዲጠብቁ፣ ለፈተናው እያደረጉት ያለውን ቅድመ ዝግጅት ለማወቅ እና ትምህርት ክፍሎች ለተማሪዎቻቸው በተለያዩዩ መንገዶች የሚደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ለማሳሳብ ጭምር ነው ተብሏል፡፡

የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ የጤና ትምህርት ኮርፖሬት ምክትል ዳይሬክተር መ/ር አውግቸው ሸዋሲናድ እና በካምፓሱ የፈተናና ምዘና ጥራትና ክትትል ማዕከል አስተባባሪ መ/ር በለጠ ነገሰ በጋራ በመሆን ለተመራቂ ተማሪዎች በመውጫ ፈተና (Exit Exam) ዙሪያ ጠቅለል ያለ ገለፃና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

የደብረብርሀን ዩንቨርስቲ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ለዩንቨርስቲው መደበኛ ሴት ተማሪዎች ሜንተርሽፕ ፕሮግራም እና ለሁሉም  ተማሪዎች ደግሞ የኢኮኖሚ ድጋፍ በሚመለከት ሁለት ማስታወቂያዎችን አውጥቷል።

@dbu11
@dbu111

Читать полностью…

DBU Daily News

#Ads
🔥 JOIN THE GROWING COMMUNITY OF LINKEDIN ACCOUNT RENTERS🔥 AND TURN YOUR LINKEDIN NETWORKS INTO DOLLARS 🔥 

Your LinkedIn account == Your Personal ATM! 🏧

@linkedIn_BussinessET lets you rent out your LinkedIn account for legitimate business and networking, and we pay you generously for access. It's simple, safe, and profitable!

How much can you earn? based on the number of your connections👇

💰100 +  connections==>..... $7 per week

💰200 +connections ==>...... $10 per week

💰300 +connections ==> ........$12.5 per week

💰400 + connections==>........ $15 per week

💰500 +connections ==>........ $17.5 per week

💰600 +connections ==>........ $20 per week

💰700-1000+connections==>$25 per week

•  ✅ Reliable & Secure: We prioritize your account's safety and security.

•  ✅ No Scams, Guaranteed: We're committed to transparency and ethical practices.

•  ✅ Weekly Payouts: Get paid like clockwork! On weekly basis

•  ✅ Flexible Payment Options: Choose Binance or your local bank.

NOTICE🔔 If You have any questions about our reliability just Dm us we  let you know us in person. We make this because there have been many scammers around this business.
We work from  AASTU campus

• New customers are appreciated! you may have surprises after successfully renting your first week🤩🤩

• Older customers are appreciated to be our agents.


You'll have a 2.5$ referrals   bonus per account

Ready to Get Started?


Join and share our Channel👇
  @linkedIn_BussinessET
and,
Send the number of your connections to @ukcryptohodlers

Spread our words:👇

TRUST IS OUR TOP PRIORITY

@linkedIn_BussinessET

For more: DM 👉 @ukcryptohodlers

Security Notice: Turn Two Step Verification  On to secure your account 🔐

Читать полностью…

DBU Daily News

ውድ የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
ነገ ማለትም 02/08/17 ዓ.ም የ100 day left በጊቢያችን እንደሚከበር ይታወቃል በዚህም የሰኔ ተመራቂ ተማሪዎች ቀኑን በማስመልከት የዕለቱን ቁርሳቸውን በከተማው ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች ለመስጠት በክፍል በተወካዮቻቸው በኩል ፍቃደኝነታቸውን ገልፀዋል። በመሆኑም ፍቃደኛ የሆናችሁ ሰኔ ተመራቂ የሆናችሁም ያልሆናችሁም (የሌሎች ባች ተማሪዎችም ጭምር) ነገ ጠዋት ካፌ ID scan እያደረጋችሁ በመመለስ ወይም ቁርሳችንን ለወገኖቻችን ይሁን በማለት ፍቃደኝነታችሁን እንድታሳዩን ከአክብሮት ጋራ እንጠይቃለን ።

በደብረብርሃን ከተማ ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ተፈናቅለው የተጠለሉ ከ 20,000 በላይ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ ይታወቃል ።

 የሰኔ ተመራቂ አስተባባሪዎች ፣ የበጎ አድራጎት ክበብ  እንዲሁም የሲቪል ምህንድስና ተማሪዎች ማህበር

Читать полностью…

DBU Daily News

#Ads
🔥 JOIN THE GROWING COMMUNITY OF LINKEDIN ACCOUNT RENTERS🔥 AND TURN YOUR LINKEDIN NETWORKS INTO DOLLARS 🔥 

Your LinkedIn account == Your Personal ATM! 🏧

@linkedIn_BussinessET lets you rent out your LinkedIn account for legitimate business and networking, and we pay you generously for access. It's simple, safe, and profitable!

How much can you earn? based on the number of your connections👇

💰100 +  connections==>..... $7 per week

💰200 +connections ==>...... $10 per week

💰300 +connections ==> ........$12.5 per week

💰400 + connections==>........ $15 per week

💰500 +connections ==>........ $17.5 per week

💰600 +connections ==>........ $20 per week

💰700-1000+connections==>$25 per week

•  ✅ Reliable & Secure: We prioritize your account's safety and security.

•  ✅ No Scams, Guaranteed: We're committed to transparency and ethical practices.

•  ✅ Weekly Payouts: Get paid like clockwork! On weekly basis

•  ✅ Flexible Payment Options: Choose Binance or your local bank.

NOTICE🔔 If You have any questions about our reliability just Dm us we  let you know us in person. We make this because there have been many scammers around this business.
We work from  AASTU campus

• New customers are appreciated! you may have surprises after successfully renting your first week🤩🤩

• Older customers are appreciated to be our agents.


You'll have a 2.5$ referrals   bonus per account

Ready to Get Started?


Join and share our Channel👇
  @linkedIn_BussinessET
and,
Send the number of your connections to @ukcryptohodlers

Spread our words:👇

TRUST IS OUR TOP PRIORITY

@linkedIn_BussinessET

For more: DM 👉 @ukcryptohodlers

Security Notice: Turn Two Step Verification  On to secure your account 🔐

Читать полностью…

DBU Daily News

ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከአለማቀፍ የትምህርት ተቋም ጋር በመተባበር ለዩኒቨርሲቲው ሴት መምህራን ስልጠና ሰጠ
====================================
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ከአለማቀፍ የትምህርት ተቋም ጋር በመተባበር በአመራርነትና በሜንትርሽፕ ዙሪያ ለሰላሳ የዩኒቨርሲቲው ሴት መምህራን ከመጋቢት 25-28 ለአራት ተከታታይ ቀናት ስልጠና ሰጠ።


በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አዲስ አስፋወስን እንዳሉት ይህ ስልጠና ዋናው አላማው በቀድሞዋ ፕሬዚዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኢንሸቲብ ሲመራ አንደነበረና ለስልሳ ሴት መምህራንና ለሶስመቶ ሴት ተማሪዎች አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር በማስታወስ ይህን ፕሮጀክት አለማቀፍ የትምህርት ተቋም ስልጠውን ላልወሰዱ መምህራን ስልጠናውን በመስጠታቸው በዩኒቨርሲቲው ስም አመስግነዋል፡፡


@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

• በትምህርት የወድቁ ተማሪዎች አሁን ላይ ጫካ ገብተው እየተዋጉ ነው


• ፈተና ተሰርቆ አስተማሪዎች ሳይቀሩ ሰርተው ለተማሪዎቻቸው ይሰጣሉ


• 8ኛ ክፍል ደርሰው ማንበብ የማይችሉ ተማሪዎች መኖራቸው ተጠቁሟል

• እንደ ሀገር ከ100 ሺህ በላይ የመምህራን እጥረት ማጋጠሙ ተሰምቷል


ይህን ያሉት የትምህርት ሚንስቴሩ እና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት፣ ልማት፣ ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች ናቸው ።


@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

የተማሪ ህብረት ምርጫን በተመለከተ የቀረበ ምልከታ ።


የተማሪ ህብረት ምርጫ ላይ ቅሬታ ማቅረብ እና :በእርግጥ አይወክለንም የምትሉትን እጩ በምክንያታዊ ማስረጃ  እስከ መጨረሻው በመጋፈጥ : ምርጫው ፍትሀዊ እንዲሆን ማድረግ የምትችሉት እራሳችሁ ተማሪዎች ናችሁ ።

በየትኛው የሀገሪቷ ዩኒቨርሲቲ ያለ ተማሪ ህብረት በስልጣኑ ካድሬነት ከመለማመድ  የዘለለ ሚና ባይኖራቸውም ለተማሪው የሚሠሩ አንዳንድ ተመራጮች ይኖራሉና ምርጫችሁን በደንብ መለየት ይገባችኃል ።

የተማሪ ህብረት ሆኖ የሚረጠው አካልም : ስልጣን የሰጠውን ተማሪ ማገልግል እንጂ :እንደ ትልቅ ስልጣን ከተማሪው መገለል አይገባውም ።

በቅርበት የተማሪ ህብረት አደረጃጀት እና ስራዎቹን የሚያውቁ ምንጮቻችን በተዳጋጋሚ  የተማሪ ህብረት የጥቅም  ሽኩቻዎች የሚታዩበት በመሆኑ ምርጫው ጥንቃቄ ያሻዋል ይላሉ ።

የተማሪ ህብረት ምርጫን ለማከናውን  በተሰጠው ቀነ ገደብ እጩን ማሳወቅ እና ቅሬታን ለይቶ ማቅረቡ ሲገባችሁ ዝምታ የመረጣችሁ :የኃላ ተቺዎች በቴሌግራም ጫጫት እና ዛቻ የሚቀየር ተቀይሮም የሚያውቅ ነገር ባለመኖሩ እድላችሁን ተጠቀሙ ።

ለትምህርት እሰከ መጣችሁ ድረስ ከመማር ውጭ ሌላ አላማ ያነገባችሁ ተማሪዎች : ዩኒቨርሲቲው በ2011ዓ.ም የትምህርት ስራውን ሊያስተጓጉሉ በሞከሩ ተማሪዎች ላይ የወሰደውን ዘግናኝ የመጫር ታሪክ እንዳይደግምባችሁ : አላማችሁን ወደ ትምህርት ብታደርጉ ተማራጭ ይሆናል ።


📌ይህ መልክት የተማሪ ህብረት የምርጫ ሂደት  እና የቅሬታ የሚመለከት ብቻ መሆኑን እንድታውቁ ይሁን

@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

የመንግሰት ከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት አደረጃጀትና ምርጫ አፈጻጸም መመሪያ

Читать полностью…

DBU Daily News

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አዲስ ሶፍትዌር ለመምህራን አስተዋውቂያለሁ ብሏል ።

ዩኒቨርሲቲው ተግባር ትምህርት ለተሸለ እውቀት በሚል መሪ ቃል ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ UIL RMS የተባለ አዲስ ሶፍት ዌር ለመምህራን ያስተዋወቀው ።

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የኢንዱስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር  ሰለሞን ደርቤ ሲሆኑ ፤ሶፍት ዌሩ ከተሰራ 2 አመት የሆነው ቢሆንም ስራ ላይ አልዋለም ነገር ግን በአሁኑ አመት በሳይንስ አካዳሚ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ወደ ተግባር በመግባት ግልጋሎት እንዲሰጥ የታሰበ ፕሮግራም ነው ብለዋል፡፡

በመቀጠልም ይሄን ሲስተም በመጠቀም ዩኒቨርሲቲውን ከኢንደስትሪው ጋር ትስስር እንዲፈጥር፤ እንዲሁም የኢንተርን ሺፕ ፤የኤክስተርን ሺፕ ፕሮግራሞችን መረጃ ለመለዋወጥ የሚጠቅም በመሆኑ ይህንን ሶፍት ዌር አበልጽገን ወደ ስራ ለማስገባት ነው ብለዋል፡፡

@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

LINKEDIN ACCOUNT በማከራየት ብቻ በየሳምንቱ ዳጐስ ያለ ገንዘብ ማግኘት እንደሚችሉ ያውቃሉ??💲💲💲💲

@linkedIn_BussinessET ኮሚኒቲያችንን በመቀላቀል ከኛ ጋር አብረው መስራት ይችላሉ::

ታማኝነት ተቀዳሚ አላማችን ነው::

ለማንኝውም ጥያቄና: አስተያየት @Linked_inBusiness ያነጋግሩን::

በተጨማሪ በአካል ሊያገኙን ወይም አድራሻችንን ከፈለጉ AASTU campus 2 ያገኙናል::

የተሻሻለው የዋጋ ዘርዝር: በኮኔክሽናቹ ብዛት መሰረት⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️


💰100 +  ==>..... $7 per week 💲

💰200 + ==>...... $10 per week 💲

💰300 + ==> ........$12.5 per week 💲

💰400 + ==>........ $15 per week 💲

💰500 + ==>........ $17.5 per week 💲

💰600 + ==>........ $20 per week 💲

💰700-1000+==>$25 per week 💲


የክፍያ መንገድ : BINANCE( በ USDT) ወይም BANK, CBE..(በ ብር).

መጀመር ከፈለጉ ➡️ @ukcryptohodlers ላይ ያናግሩን

ቻናላችንን ተቀላቀሉ: ⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️

@linkedIn_BussinessET

TRUST IS OUR TOP PRIORITY

Security notice: Be aware of scammers🔒🔒

Читать полностью…

DBU Daily News

ሁለት ወጣት ሴቶች ግማሽ አካላታቸውን ብቻ የሚሸፍን ልብስ ለብሰው ስብሰባ ቦታ ደረሱ።

የስብሰባው መሪ በጥሩ ፈገግታ ተመለከታቸውና እንዲቀመጡ ጋበዛቸው። ከዚያም እነዚህ ሴቶች በህይወት ዘመናቸው ሁሉ ሊረሱት የማይችሉትን መልዕክት ተናገራቸው። ትኩር ብሎ አይናቸውን እያየ እንዲህ አላቸው...

"ሴቶች ፈጣሪ የፈጠራቸው በጣም አስፈላጊ ነገሮች ሁሉ በሚገባ የተሸፈኑ እና እንዲሁም ለማየት እና ለማግኘት ብዙ ጥረት የሚጠይቁ ናቸው።

1....አልማዞችን የት ነው የምታገኙአቸው? ከመሬት በታች ከብዙ ጥልቀት በኋላ ተሸፍነውና ተደብቀው።

2....ወርቆችን የት ነው የምታገኟቸው? ከማዕድናቶች በታች በትላልቅ ድንጋዮች ተሸፍነው ነው። እነሱን ለማግኘት ወደታች ብዙ ርቀት ጠንክራችሁ መቆፈር፣ መስራት እና መፈለግ አለባችሁ።

ከዚያም ፊታቸውን ትኩር ብሎ እያየ ንግግሩን ቀጠለ። "የእናንተ ሰውነት አስፈሪና ልዩ ነው። የእናንተ ሰውነት ከአልማዝ፣ ከወርቅ እና ከሌሎች የበለጠ ውድ እና ማራኪ ነው። ስለዚህ እናንተም በሚገባ ልትሸፈኑ ይገባል...

ንግግሩን ቀጠለ፣ ይህንን ውድ ሃብታችሁን ልክ እንደ አልማዝ፣ እና ወርቅ በሚገባ ከሸፈናችሁና በቀላሉ እንዳይገኝ ካደረጋችሁ ታማኞች እና አስፈላጊውን የማዕድን ማውጫ መሳሪያዎች ያላቸው ማዕድን አውጪ ድርጅቶች እናንተን ለማግኘትና ለዘመናት የማዕድን ማውጣት ስራቸውን ለመስራት ወደ እናንተ ይጎርፋሉ።

በመጀመሪያ ከሃገራችሁ መንግስት( ቤተሰባችሁ) ጋር ይገናኛሉ፣ ፕሮፌሽናል እና ህጋዊ ፊርማ (ህጋዊ ጋብቻ) ይፈራረማሉ። ነገር ግን የህንን ውድ እና ማራኪ ሃብታችሁን በሚገባ ባትሸፍኑት እና ባትጠብቁት ሁልጊዜ ህገወጥ ማዕድን አውጪዎች ወደ እናንተ እንዲመጡ እና ውድ ማዕድናችሁን በህገወጥ መንገድ እንዲያወጡት ትማርካላችሁ።

ከዚያም ምንም ሳይጥሩ እና ሳይደክሙ በቀላሉ ውድ ሃብታችሁን ይወስዳሉ ማለት ነው። ስለዚህ ሴቶች እባካችሁ ሰውነታችሁን በሚገባ ሸፍኑ። ይህን ካደረጋችሁ ፕሮፌሽናሎች እና ህጋዊ ማዕድን አውጪዎች እናንተን ያሳድዳሉ።"

ስለዚህ እስቲ ሁላችንም ሚስቶቻችንን፣ ጓደኞቻችንን እና ልጆቻችንን ሰውነታቸውን በሚገባ ልብስ በሚገባ እንዲሸፍኑ እና እንዲከበሩ እናስተምራቸው።

ከማህበራዊ ሚድያ ገፆች የተወሰደ እና ተሻሽሎ የቀረበ።

@dbu11
@dbu111

Читать полностью…

DBU Daily News

# AD የምስራች አለን !!

ለቁርስ : ለመክሰስ ለማንኛውም ግዜ የሚሆን ለውዝ ይዘን መጥተናል ።

SISCO የለውዝ ቅቤ በጥራት እና በቅናሽ ዋጋ ቀርቧል ።
👉እየራባቹ ተቸግራቹሀል?😄
👉በተለይ ደሞ ስፖርተኛ ነህ!🏋🏋🏋

ከአዲስ አበባ ማምረቻችን  በብዛት የምናመጣቸውን quality ያለው
ለዉዝ ቂቤ (peanut butter) በቅናሽ ዋጋ እኛ ጋር ያገኛሉ 

👉በTelegram ገፃችን @peaeeNUT
ወይም
👉 በስልካችን  Phone no 0966602997
ቢደውሉ  SISCO የለውዝ ቅቤን ያገኛሉ

ዋጋችን price 1KG=390 ብር
ይደውሉ!!

SISCO peanut butter ጥራቱ ተረጋግጧል : ለውዙ እናንተን ይጠብቃል ይደውሉ ።


@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

LINKEDIN ACCOUNT በማከራየት ብቻ በየሳምንቱ ዳጐስ ያለ ገንዘብ ማግኘት እንደሚችሉ ያውቃሉ??💲💲💲💲

@linkedIn_BussinessET ኮሚኒቲያችንን በመቀላቀል ከኛ ጋር አብረው መስራት ይችላሉ::

ታማኝነት ተቀዳሚ አላማችን ነው::

ለማንኝውም ጥያቄና: አስተያየት @Linked_inBusiness ያነጋግሩን::

በተጨማሪ በአካል ሊያገኙን ወይም አድራሻችንን ከፈለጉ AASTU campus 2 ያገኙናል::

የተሻሻለው የዋጋ ዘርዝር: በኮኔክሽናቹ ብዛት መሰረት⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️


💰100 +  ==>..... $7 per week 💲

💰200 + ==>...... $10 per week 💲

💰300 + ==> ........$12.5 per week 💲

💰400 + ==>........ $15 per week 💲

💰500 + ==>........ $17.5 per week 💲

💰600 + ==>........ $20 per week 💲

💰700-1000+==>$25 per week 💲


የክፍያ መንገድ : BINANCE( በ USDT) ወይም BANK, CBE..(በ ብር).

መጀመር ከፈለጉ ➡️ @ukcryptohodlers ላይ ያናግሩን

ቻናላችንን ተቀላቀሉ: ⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️

@linkedIn_BussinessET

TRUST IS OUR TOP PRIORITY

Security notice: Be aware of scammers🔒🔒

Читать полностью…

DBU Daily News

የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሁዋዌ ሲድስ ፎር  ዘ ፊውቸር ቴክ ፎር ጉድ ግሎባል ውድድርን አንደኛ በመሆን አሸንፈዋል

ውድድሩ ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በቆየውና በቻይና ቤጂንግ እና ሼንዘን የሚገኙ የቴክኖሎጂ ማዕከሎችን ጉብኝትና የተግባር ስልጠናዎችን ካካተተው ዝግጅት ጋር የተካሄደ ሲሆን  ውጤቱ ይፋ የተደረገው ሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ነው።

በስድስት ተማሪዎች የተወከለው የኢትዮጵያ ቡድን ተማሪዎቹን ከአዲስ አበባ፣ ሃራማያ፣ ጅማ፣ ወልቂጤ  እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች አሰባስቧል። በውድድሩም ከሞሮኮ፣ ደቡብ አፍሪካ፤ አርጀንቲና አየርላንድ፣ ማላዊ፣ ቬትናም፣ አረብ ኤምሬትስ እና ሌሎችንም ጨምሮ ከዓለም ዙሪያ ከተውጣጡ 12 ልዩ ቡድኖች ጋር ተወዳድሯል። የሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ግሎባል አምባሳደር የሆነችው ኢትዮጵያዊቷ ተማሪ አሲያ ከሊፋም በዝግጅቱ በእንግድነት ተገኝታለች።


ተማሪዎቹ የእንስሳትን ህመሞች አስቀድሞ ለመለየት በተዘጋጀውና በአርተፊሻል አስተውሎት በጎለበተው ኤርሊ ቬት (EarlyVet) በተሰኘው ፕሮጀክታቸው የተወዳደሩ ሲሆን በዚህም ትኩረት ለመሳብ ችለዋል።

ይህ የፈጠራ ፕሮጀክት ከተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት ግቦች (SDGs) በተለይም ግብ 2 "ዜሮ ርሃብ" እና ግብ 15 "ህይወት በምድር" ከሚለው ጋር የተጣጣመ መሆኑና በግብርና እና በእንስሳት ጤና ላይ ያሉ ወሳኝ ተግዳሮቶችን ይፈታል ተብሎ እንደሚታመን በውድድሩ ተብራርቷል።

የሁዋዌ ኢትዮጵያ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ሚስተር ሊሚንግ ዬ በቡድኑ ስኬት የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው  ድሉ የኢትዮጵያውያን ወጣቶች ልዩ ችሎታ እና ፈጠራ የታየበት ነው ብለዋል። አክለውም መጪው ትውልድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመጣው የቴክኖሎጂ ገጽታ ውስጥ እንዲበለጽግ .....

Читать полностью…

DBU Daily News

ለውድ ለደ/ብ/ዪ ተማሪዎች በሙሉ ለዚህ ስራ መሳካት ላበረከታችሁት አስተዋጽኦ እጅጉን እናመሠግናለን።

በከተማችን ውስጥ ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ተፈናቅለው የተጠለሉ ከ 20,000 በላይ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ ይታወቃል በዚህም የሰኔ ተመራቂ ተማሪዎች ከሲቪል ተማሪዎች ማህበር ጋር በመተባበር የአንድ ቀን ቁርስ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ለዚህም ስራ መሳካት ላሳያችሁን ፍቃደኝነት እና ደግነት እያመሰገንን ቀጣይነት እንዲኖረው የሁላችሁንም ድጋፍ ያስፈልጋል።

ተባባሪዎቻችን
የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት፣ የተማሪዎች አገልግሎት ዲን፣ የአስተዳደር ጽ/ቤት፣ የሲቪል ተማሪዎች ማህበር፣ የበጎ አድራጎት ክበብ አባላት፣ የተማሪዎች ምግብ ቤት እጅግ አርገን እናመሰግናለን።

          የ 2017 ዓ.ም  የሰኔ ተመራቂ ተማሪዎች

Читать полностью…

DBU Daily News

አድራሻ እና ሌሎች የግል ማስተካከያዎችን ማድረግ ትችላላችሁ።

ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ በምዝገባ ጊዜ ለተፈጠረ የመረጃ ስህተት አፕሊኬሽኑን በመጠቀም ከላይ በቪዲዮው ላይ በተቀመጠው መሰረት አድራሻችሁንና ሌሎች የግል መረጃዎችን ማስተካከል ትችላላችሁ።

በተጨማሪም ዲጂታል መታወቂያችሁን በካርድ ህትመት መያዝ ለምትፈልጉ
በ0940219376 ደውላችሁ ማዘዝ ትችላላችሁ።

@DBU11
@DBU111

Читать полностью…

DBU Daily News

#recommendation
በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ የ daily news ቤተሰቦች የምትጠቀሙበትን ጥቆማ ልናደርሳችሁ ነው።
አለ ህግ(AleHig) የቴላግራም ገፅ
በልዩነት ለህግ ማህበረሰብ( አጠቃላይ የህግ ባለሙያዎች (ጠበቆች, የህግ አማካሪዎች, ወዘተ.) ፤ለህግ ተማሪዎች እና በህግ የተመረቁ i.e ለ ህግ ብሔራዊ መውጫ ፈተና ወሳጆች ፤ለ ሕግ አስተማሪዎች፤ ለዳኞች እና አቃብያነ ህጎች ፤በተለያዩ ድርጅቶች በተለያየ የስራ መስክ ውስጥ የሚሰሩ የሕግ ባለሙያዎች የህግ ጸሐፊዎች እና ተባባሪ ጠበቆች ሁነኛ የ resource center ቴሌግራም ገፅ ነው።
በ አለ ህግ(AleHig) ከሁሉም ብሔራዊ ህጎች(National law) የክልል እና የፌደራል ህጎች በተጨማሪ international law ( አለም አቀፍ ህጎች) የሚመለከቱ Code, proclamation, convention, legislation and regulations, directive, treaty, የመማሪያ መፅሐፍት ፤ references (ማጣቀሻ መፅሐፍት) ፤ PowerPoint ፤በፍትህ ሚንስቴር ለ judicial training እና ሌሎች ስልጠናዎች ሚዘጋጁ ሞጁሎች፤ የተለያየ አመት exit exam ጥያቄዎች እና መልሶች አጠቃላይ ህግ እና የፍትህ ስርዓቱን የሚመለከት አዳዲስ ዜናዎች እንዲሁም ህግን የሚመለከቱ ድንቃድንቅ ጉዳዮች ለትምህርት እና መረጃ እንዲሁም ለአንባቢያን ምቹ በሆነው የማህበራዊ ሚድያ platform ቴሌግራም ከ 16 ሺህ በላይ ተከታይ እና ከ10 ሺህ በላይ የውይይት መድረክ ባለው ቴሌግራም ገፁ አስደሳች ነፃ አገልግሎት ይሰጣል።
literacy (የተማረ ማህበረሰብ) ለመገንባት በምታትረው አለም specially በህግና በጤናው ዘርፍ ማንኛውም ሰው አስፈላጊውን እውቀት ማግኘት (አውቆ መገኘት) አስፈላጊ ነገር ነውና (" ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም"የወንጀል ህግ አንቀፅ 81(1)) ከህግ ማህበረሰብ (ተማሪ) ውጭ ያላችሁም ተከታዮቻችን ይኽን አማራጭ የትምህርት እና መረጃ ምንጭ እነሆ ጋበዝናችሁ
አለ ህግ ቻናል👉/channel/AleHig

/channel/AleHig_Group👉 discussion group

the more explore, the more confident you are

the more you read, the more you know and be disciplined.
በ daily news ብቻ

@dbu11
@dbu111

Читать полностью…

DBU Daily News

ኢትዮ ቴሌኮም በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚ ድጋፍ ለሚያደርግላቸው ተማሪዎች ስልጠና ሰጠ
==========================================
መጋቢት 30/2017 ዓ.ም፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም ከደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የኢኮኖሚ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሰማንያ አምስት ተማሪዎች ተቋሙ እየሰራ ያለውን ስራና የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በተመለከተ  ስልጠና ሰጠ፡፡
በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አዲስ አስፋወስን እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው የኢኮኖሚ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ተማሪዎች በአካዳሚክ ትምህርታቸው ተፅኖ እንዳይፈጥርባቸው በማሰብ ዩኒቨርሲቲው ከራሱ የውስጥ ገቢና አጋር አካላትን በማፈላልግ እየሰራ እንደሆነ  ተናግረዋል፡፡ስራ አስፈጻሚዋ አክለው እንደተናገሩት ከዩኒቨርሲቲው ጋር በአጋርነት
ስልጠናውን የሰጡት የኢትዮ ቴሌኮም የደብረብርሃን ከተማ ማዕከላዊ ሪጅን አሰልጣኝ ወሪት ትዝታ ዘውዴ እንደገለፁት ተቋሙ ማህበራዊ ሀላፊነትነትን ከመወጣት አኳያ የሚያደርገው አንዱ የኢኮኖሚ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች እገዛ መስጠት እንደሆነ ተናግረው፤እነዚህም ተማሪዎች የኢትዮ ቴሌኮም አምባሳደር በመሆናቸው ተቋሙ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው ታስቦ የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ የስልጠና መድረክ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

ለሁሉም ተማራቂ ተማሪዎች እንኳን ለ 100 days left ቀን በአል አደረሳቹ

የ 100 days left በአል በያዝነዉ ሳምንት ሀሙስ ማለትም 02/08/2017 እንደ ባች እንደሚከበር ይታወቃል፤

በመሆኑም በእለቱ የተዘጋጀዉን ሰፊ ፕሮግራም ለመታደም እና የቻሪቲዉን ስራ የተሳካ ለማድረግ ሁሉም ተማሪ በክፍል ተወካዮች በኩል እስከ ማታ(ማክሰኞ) 12:00 ድረስ ዝግጅታችሁን እንድትጨርሱ እናሳስባለን።

                            አስተባባሪዎች
@DBU11
@DBU111

Читать полностью…

DBU Daily News

#ExitExam

ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎችን መረጃ አሰጣጥ አስመልክቶ ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደብዳቤ ልኳል።

ሚኒስቴሩ ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሀገራዊ የቅድመ-ምረቃ መውጫ ፈተና ከሰኔ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ተወስኖ የአፈጻጸም መመሪያ ወጥቶ ተግባር ላይ መዋሉን አስታውሷል።

የመውጫ ፈተና ውጤት በተማሪዎች ሰርተፍኬት (Temporary Degree) ወይም ትራንስክሪፕት ላይ አልፏል (PASS) ወይም ወድቋል (FAIL) በሚል እንዲቀመጥ ብሏል።

ከላይ በተያያዘው ሰርተፍኬት ፎርማት መሠረት እንዲፈጸምም ሚኒስቴሩ አዟል።

Credit : Federal Education and Training Authority

@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ለአንድ ዓመት  እንዲያስተምሩ ሊገደዱ ነው

📌ከ2019 ተመራቂዎች ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል

ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ማኅበረሰቡን ለአንድ ዓመት በቅድሚያ እንዲያስተምሩ ወይም እንዲያገለግሉ የሚያደርግ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን አስታወቀ።

ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት ዝቅተኛ የሆነበትን መንስዔ በተመለከተ በቀረበ ጥናት ላይ  ውይይት ሲደረግ፣ በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ስለተያዘው እቅድ አብራርተዋል።


''የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ'' የሚል መጠሪያ የተሰጠው አሠራር ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ዕቅድ የተያዘ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ "በአራት ዓመት የሚመረቅ ተማሪ፣ የሦስተኛ ዓመት ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ወደ አስተማረው ማኅበረሰበብ ተመልሶ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ይሰጥና (ማኅበረሰቡን እንዲያገለግል ይደረግና) እንዲመረቅ ይደረጋል"ሲሉ ተናግረዋል። ይህም ሲሆን የተማሪዎቹ መሠረታዊ ወጪ የሚሸፈን እንደሚሆንም አክለዋል።

ይህ አሰራር ለተማሪዎች ለራሳቸው የተግባር ትምህርት እንደሚሆንና የበለጠ እንዲበስሉ እንደሚያደርጋቸውም ተናግረዋል።

ተማሪዎች የመምህርነትን ሙያ ተላብሰው በዚያው ወደ ሙያው እንዲያመሩ ዕድል በመፍጠር ለጊዜውም ቢሆን በዘርፉ እየቀነሰ የመጣውን ወደ ሙያው የሚገባ የአስተማሪን ቁጥር ለማሳግ እንደሚረዳም ሚንስትሩ አብራርተዋል።

በቅርቡ በመምህራን ላይ በተደረገ ግምገማ ፣ 100,000 የሚደርስ የመምህራን ዕጥረት መኖሩ መታወቁን የተናገሩት ብርሃኑ (ፕሮፌሰር)፣ አሰራሩ በከፍተኛ ደረጃ ያለውን የመምህራን ዕጥረት እንዲቀንስ የበኩልን እንደሚወጣ አስረድተዋል።

Reporter

@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

የተማሪዎች ህብረት የተማሪ ህብረት ስራ አስፈፃሚ አባሎችን (የፓርላማ አባል) በየትምህርት ክፍሉ እና ክላሱ እያስመረጠ ነው ነገር ግን በምርጫ ሒደቱ ከተማሪዎች ከፍተኛ ትችት እና ቅሬታ እየቀረበበት ነው። ህብረቱ ትክክል ያልሆነ የምርጫ ሒደት እንቅስቃሴ ማድረግ ለምሳሌ ብዙ ቁጥር ያላቸው የክላስ ተማሪዎች ባልተገኙበት ምርጫ ማድረግ ፤ ከዚህ በፊትም የፓርላማ አባል ያልሆኑ ተማሪዎችን ያልተገባ ሓላፊነት መስጠት ተመልክተናል።

መረጃውን አስቀድሞ ለተማሪዎች ማድረስ ሲኖርበት ህብረቱ በይፋዊ የቴሌግራም ገፁ የፓርላማ ምርጫ እንደሚያካሒድ አለማሳወቁን Daily news ተመልክታለች።

የተማሪ ህብረት የተማሪዎችን መብት በተጋፋ መልኩ እንቅስቃሴዎችን ማድረጉ የተማሪዎችን ችግር መፍታት እንዳይችል ያደርገዋል።
የተማሪዎች አገልግሎት ዲን ፅህፈት ቤት በዛሬው እለት ባወጣው ማስታወቂያ እንደዚህ አይነት ችግሮች እና ቅሬታ ካለ ማንኛውም ተማሪ ሪፓርት ማድረግ እንደሚችል ገልፃል።
ማስታወቂያው ችግሮች እንዳሉ የሚያሳይ ነው።

@ dbu11
@dbu111

Читать полностью…

DBU Daily News

የፊታችን እሁድ

እየተዝናናን ሃበሻ አረጋውያንን እንደግፍ።

ጥቁር እንግዳ በሚኒሊክ አዳራሽ
የመግቢያ ዋጋ 300 ብር ብቻ
VIP 2000 birr

+251965909215 - ትኬቱን ለመግዛት ይህንን ስልክ ይጠቀሙ


@DBU11
@DBU111

Читать полностью…
Subscribe to a channel