14224
Youtube https://youtu.be/_0l6c0I7ouM 👉ስለ ግቢው ወቅታዊ መረጃ 📌ዲፓርትመንቶች ፡⚽️ስፓርት፡🎤ኪነጥበብ ምሽቶች ፡📄የጊቢ ማስታወቂያ ፡ ምልከታወችና ታሪክ ወግ ፡📷📷አስገራሚ ፎቶወች ፡ እውነታዎች እና መረጃወች📃 መፀሀፍት ፡ ሳይኮሎጂ ሁሉም ይዳሰሱበታል:: Contact
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ 216 ተማሪዎችን በሸዋ ቃል ኪዳን ቤተሰብ አስተሳሰረ።
የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት አስማረ መለሰ (ዶ.ር) በመርሐ ግብሩ ላይ እንደገለጹት ዩኒቨርስቲው በሸዋ ቃል ኪዳን ቤተሰብ 216 ተማሪዎችን ትስሰር መፍጠሩን አስታውቀዋል።
ዓላማው ከተለያዩ ሩቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ወደ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ተመድበው የመጡ ተማሪዎች በደብረ ብርሃን ሁለተኛ የቃልኪዳን ቤተሰብ እንዲኖራቸው ማድረግ።
ወደ ዩኒቨርስቲው ሲመጡ ወደ ቤታቸውና ወደ ቤተሰቦቻቸው እንደሚመጡ ያህል የመንፈስና የአዕምሮ መረጋጋት ስሜት እንዲያዳብሩ፤ዩኒቨርስቲውንና ከተማው እንዲወዱት ማድረግ ነው ብለዋል።
በተጨማሪ በልዩ ሌዩ በዓላትና የዕረፍት ጊዜያቸው ተማሪዎች ከደብረ ብርሃን ቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለው ጊዜያቸውን በደስታ እንዲያሳልፉ ማስቻል፤ ከስጋ ቤተሰቦቻቸውና እዚህ ካሉ ቤተሰቦቻቸው መካከል ጥብቅና ዘላቂ ግንኙነትና ወዳጅነት እንዲፈጠር ማስቻል እንደኾነም አብራርተዋል።
@DBU11
@DBU111
በዝውውር ለመጣችሁ ሬሜዲያል ተማሪዎች ከመሀል ሜዳ ካምፖስ የወጣ ማስታወቂያ
Читать полностью…
2018 ዓ.ም የHalf life ፕሮግራም አስመልክቶ
መላው የግቢያችንን ተማሪዎች የዓርብ ቁርሳችንን ለበጎ ፈቃድ አውለን ቀኑን በተለየ መልኩ ለማክበር ሰለታሰበ ውድ ተማሪዎቻችን የተለመደውን አስፈላጊ ትብብራችሁን እንድታደርጉልን ሰንል በትህትና እንጠይቃለን በዕለቱ ቲክ እያደረጋችሁ በመመለስ እንድትተባበሩ ስንል በትህትና እንጠይቃለን ።
ከ Half Life ዝግጅት አስተባባሪዎች
@dbu11
@dbu111
ከሰላምታ ጋር
አዘጋጅ half life ኮሚቴ
Ads
በአዲስ መልክ እናንተን ለማገልገልና ቀልጣፋ መስተንግዶን ለእናንተ ለማድረስ ይረዳን ዘንድ አዲሱን የከስተመር ሰርቪስ ቁጥራችንን ተዋወቁት ...🙋
0901633037
ክሪስፒ ፋስት ፉድ በሳምንት ለ7 ቀናት በወር ለ30 ቀናት በፈለጉት ሰአት ቢመጡ ወይንም ሀሎ ቢሉን በፍቅር በታጀበ እና እጅግ በተቀላጠፈ መስተንግዶ ልናስተናግዶት ዝግጁ ነን ....
በልዩነት የምናቀርበውን እርጥባችንን ቀኑን ሙሉ እንደሚያገኙት ስንገልጽ በደስታ ነው .....😻
#ክሪስፒ_ፋስት_ፉድ
በጥፍጥናው ይለዩታል !!!
🎈 ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ ፊት ለፊት ታክሲ ተራው ጋር ....
◆ tiktok.com/@crispyfastfood
◆ 0901633037
◆ Google Map address
https://maps.app.goo.gl/gfAsBBeZvG72MJJw6?g_st=atm
የደብረ ብርሀን ዩንቨርስቲ የህግ ትምህርት ቤት በህግ ባለሙያና መምህር መለሰ መሪነት በ5ኛ አመት የህግ ተማሪዎች መካከል የ Mock trial exercises event አካሄደ።
የህግ ትምህርት ቤት ማህበሩም የህግ ትምህርት በመሰረታዊነት ከፅንሰ ሀሳብ በዘለለ የተግባር ትምህርት በመሆኑ እንደዚህ አይነት ተማሪዎች አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ የሚያግዙ የተግባር ልምምዶች መከናወናቸው ለእኛ ለተማሪዎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው በመግለፅ የህግ ባለሙያና የኮሌጁ የህግ መምህር መምህር መለሰ ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋናውን አድርሷል።
@dbu11
@dbu111
ቤተልሄምን _እናድናት
ቤተልሄም ንጉሴ ትባላለኝ። የደብረብርሀን ከተማ ነዋሪ ናት። በከተማዋ ላይ በሚዘጋጁ የኪነጥበብ ስራዎች ላይ ስትተውን፣ ግጥሞቿን ስታቀርብ፣ ስታስተባብር በጣም ተወዳጅ ነበረች። የሚያውቃት ሁሉ ነገዋን በተስፋ የሚጠብቅላት የሚሳሳላት ወጣት ነበረች።
'ነበረች' ያልነው አሁን የአልጋ ቁራኛ ሆና ከምትወደውና ከምትናፈቅበት ስፍራ ስለሌለች ነው።
ቤቲ የመኪና አደጋ ደርሶባት ምንም መንቀሳቀስ ባለመቻሏ ቤቷ ከተቀመጠች ብዙ ወራት አለፉ። ከህመሟ ለማገገም ህክምና ስትከታተል ብትቆይም ትንሽ ተስፋ ባየችበት ጊዜ በገንዘብ እጥረት ህክምናውን አቋርጣ ቤቷ ተቀምጣለች።
ወደ እናንተ ከመምጣታቸን በፊት የቻልነውን አድርገናል። አሁን ግን አልቻልንምና እባካችሁ ጓደኛችንን አድኑልን።
ይህ የባንክ አካውንት የወንድሟ የአቶ ሽመልስ ንጉሴ ነው። እባካችሁ የቻላችሁትን አድርጉልን
የዛሬ_ቁርሳችሁም_ለቤቲ_ህክምና_ላኩልኝ🙏
1000711719095
via melaku demise
@DBU11
@DBU111
የተማሪዎች የሥነ ምግባር ረቂቅ መመሪያ በውስጡ ምን ምን አካቷል ?
መመሪያው በመንግስት ፣ መንግስታዊ ባልሆኑ ፣ የግል ፣ በኃይማኖት ተቋማት የሚተዳደሩ ትምህርት ቤቶችና ከኢትዮጵያ ውጪ ባሉ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት በሚማሩ ተማሪዎች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል።
በመመሪያው የተማሪዎች መብትና ግዴታዎች ሲቀመጡ በተማሪዎች ግዴታ ስር ፀጉርን በአግባቡ መሰራት/ማሳጠር፣ ከተፈጥሯዊ ጸጉራቸው ውጪ እንዳይጠቀሙ ተቀምጧል።
የሴቶቾ የትምህርት ቤት የደንብ ልብስ ቀሚስ ቁመት ከባት በታች መሆን ያለበት ሲሆን ከአካባቢው ባህል ጋር የማይቃረን ልብስ መልበስ የሚለውም ተካቷል።
በመመሪያው ከተከለከሉ ተግባራት ሞባይልና የሙዚቃ ማዳመጫዎችን ወደ ትምህርት ቤት ይዞ መምጣት ይገኙበታል።
በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ኃይማኖታዊ አምልኮ ስርዓትና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን ማከናወንም በመመሪያው ተከልክሏል።
በመመሪያው ሀገራዊ እሴት ያልሆኑ መጤ ነገሮችን በሰውነት ላይ መነቀስ ሲከለከል፤ ሴት ተማሪዎች የጥፍር፣ የፀጉርና የከንፈር ቀለም ከመቀባትና ከመኳኳል እንደዚሁም አላስፈላጊ ጌጥ ከማድረግ ይከለክላል።
በተጨማሪም በረቂቁ በትምህርት ቤት ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑ የኢትዮጵያዊነት ባህልን የማይገልፁ ያላቸውን ድርጊቶች ፦
• Crazy Day,
• Gentle Day,
• Olds Day,
• Baby Day,
• Fruit Day,
• Tomato Day,
• Valentine Day,
• April the full,
• Color Day,
• Pyjama Day…etc መፈጸም፤ እና ሌሎችም አላስፈላጊ የሆኑ ባህልን የማይገልፁ ድርጊቶችን ማክበር እንደማይቻል ተገልጿል።
የተከለከሉ ተግባራትን በሚፈፅመት ላይ የተለያያ የእርምት እርምጃዎች ሲቀመጡ ቀላል እርምጃ ሊያስወስዱ በሚችሉ ጥፋቶች ስር ከፀጉር ጋር የተያያዙ እና ሌሎች ቀላል ጥፋቶች ተካተዋል።
የትምህርት ቤት ፕላዝማና ኮምፒውተር ለሌላ አላማ መጠቀም፣ በአጥር መዝልና መሽሎክ፣ ከላይ የተጠቀሱ አላስፈላጊ ባህሎችን ማክበር፣ አሉታዊ ምልክቶችን መነቀስ፣ ድብድብ እንደዚሁም ኃይማኖታዊ ስርዓት መፈፀምና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግ በከባድ ጥፋት ውስጥ ተካተዋል።
የቅጣት እርከኑ እንደ ተማሪዎች የትምህርት ደረጃና ጥፋቱ ሲለያይ ለከባድ የስነ ምግባር ግድፈት በመደበኛ ህግ መሰረት የህግ ተጠያቂነት ይኖራል።
መመሪያው የዲሲፕሊን ክስ አመሰራረት፣ የዲስፕሊን ኮሚቴ ስብጥር እንደዚሁም ተግባርና ኃላፊነትን በዝርዝር አስቀምጧል።
ከዚህ ባለፈ ፦
• ትምባሆ (ሲጋራ፣ ሺሻ)
• ጫት
• አልኮል
• የናርኮቲክ እና ሳይኮትሮፒክ ዝርያ ያላቸው አደገኛ ህገ ወጥ መድኃኒቶችና ሱስ አስያዥ ዕፆች በትምህርት ቤቶችና አካባቢ መገኘት፣ መጠቀም፣ መሸጥ፣ ማብቀል፣ ማምረት ወይም መለወጥ የተከለከለ እንደሆነ መመሪያው ላይ ተቀምጧል።
ትምህርት ሚኒስቴር በመመሪያው ላይ ምክረ ሃሳብ ያላቸው ሰዎች በ https://forms.gle/R72ai6EiMnzZtGsC6 እንዲያቀርቡ ጠይቋል።
Via Tikvah
@DBU11
@dbu111
ማስታወቂያ
ለደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች
1. ነገ አርብ ከሰአት 8:00 ጀምሮ በፍትሐብሔር case
2.በቀን 15/18 ማለትም ሰኞ በወንጀል case ጠዋት 2:30 ጀምሮ
በህግ ባለሙያ እና መምህር መለሰ መሪነት በ PR አዳራሽ በ5ኛ ዓመት የህግ ተማሪዎች ለሁሉም የህግ ተማሪዎች እጅግ ደስ የሚል የ Mock Exercise event ስላለ በሁለቱም ቀናት በተባለው ሰአት PR አዳራሽ ተገኝታችሁ መከታተል ትችላላችሁ።
''ፍሎር ላይ ኤርፎን ማይጠቀሙ ተማሪዎች ላይ የዲሲፕሊን እርምጃ እወስዳለሁ'' የአስራት ወልደየስ ጤና ካምፓስ
በዶርም አካባቢ ዋይፋይ ለምትጠቀሙ የተሰጠ ማሳሰቢያ
@DBU11
@DBU111
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ በ2019 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።
ለመምህራን የሚቀርበው ጥቅማጥቅምና ደመወዝ በቂ አለመሆን ለመምህራን እጥረት ምክንያት እንደሆነ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለምክር ቤት አባላት ተናግረው ይህም አዲስ መምህራንን በበቂ ሁኔታ ለማፍራት አስቸጋሪ እንዳረገው ገልፀዋል።
የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ግለሰቦች የአንድ ዓመት የማስተማር ዘዴ (Pedagogy) ኮርስ በመውሰድ ለመምህርነት ብቁ መሆን እንደሚችሉ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በዚህም የመምህራንን ቁጥር ለማሳደግ ይቻላል ብለዋል።
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ሲሰጡ፣ የበለጠ የመምህነነት ሙያ ፍቅር ሊያጎለብቱ እንደሚችሉም ገልፀዋል።
ባለፈው ዓመት ከቅድመ-መዋዕለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል በሀገሪቱ አጠቃላይ የመምህራን ቁጥር 625,000 የነበረ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ቁጥሩን ወደ 700,000 ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።
@DBU11
@DBU111
ለደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የስነ-ምግባርና ፀረሙስና ክበብ አባላት በሙሉ
@DBU11
@DBU111
https://forms.gle/hq9uU83TLMfB1YRf9
በፈረንሳይ መንግስት ስፖንሰር የተደረገ ለ14 ሳምንታት በነፃ የሚሠጥ የጋዜጠኝነት ስልጠና አዲስ አበባ ለምትገኙ በማንኛውም ፊልድ ለተመርቃችሁ ይሆናል ።
👍ሰርተፍኬት አለው
👍ሚዲያ ውስጥ ለመስራት አጋዥ ነው
ሞክሩት ለመመዝገብ ሊንኩን ይጫኑ
@DBU11
@DBU111
ለ1ኛ ዓመት Non-Cafe መሆን ለምትፈልጉ እና በተለያየ ምክኒያት ላልሞላችሁ ተማሪዎች በሙሉ
ከህዳር 2/2018 እስከ ህዳር 4/2018 ዓ.ም ድረስ በተማሪዎች ምግብ ቤት ቢሮ በመገኘት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን የተማሪዎች ምግብ ቤት ገልፁአል።
ለመመዝገብ ስትመጡ
•የንግድ ባንክ አካውንት የተከፈተበት ደብተር ኮፒ
•ID Card
•ስሊፕ (የሌላችሁ ግሬድ ሪፖርት)
መያዝ እንዳትረሱ
@DBU11
@DBU111
#Ads
ውድ የ ትሩ ቢንጎ (true Bingo) ተጫዋቾቻችን እንኳን በደህና ጥራቱን ወደ ጠበቀው ብሎም በአፍሪካ ተወዳዳሪ ወደሆነው እና የውጪ ባለ ሙያዎች ጭምር የተሳተፉበት የመጫወቻ መደላድል በሰላም መጡ::
ትሩ ቢንጎ (true bingo) ከወዳጅ ዘመድዎ ጋር ከስራ በሁዋላ በሀላፊነት ዘና የሚሉበት ተመራጭ መደላደል (telegram bot) ነው::
ስለሆነም ለእርስዎ ብዙ ማራኪ ስጦታወችን እና እድሎችን ያቀረብንልዎ መሆኑን ስንገልፅ በደስታ ነው::
በዚህ ሳምንት የመጀመሪያዉን እና ማራኪ የሆነውን የማስታወቂያ ስጦታችንን የምናቀርብ ሲሆን ቅድሚያ ለተመዘገቡ እና ገንዘብ አስገብተው ለሚጫወቱ ከ 10 ብር ጀምሮ እስከ 10,000 ብር ለድለኞች የምናበረክት መሆኑን በደስታ እየገለፅን በሚከተለው ሊንክ ቴሌግራም ላይ ገብተው ይመዝገቡ @truebingobot ለበለጠ
መረጃ እና አስተያየት @Truebingoethiopa መልክት ይላኩልን (text)
በኃላፊነት ይጫወቱ::
አንቺ አበባ ሆይ
በድምጻዊ ሳሙኤል መስፍን ከብዕር ክሬቲቭ ጋር የተዘጋጀው አዲስ የጎንደር ነጠላ ዜማ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ በደብረብርሃን ከተማ በእምዬ ምኒሊክ አዳራሽ የቪዲዮክሊፕ ምርቃት እየተካሄደ ይገኛል።
ሳሙኤል መስፍን እንኳን ደስ አለህ!
የመግቢያ ዋጋ ነጻ በመሆኑ ሁላችሁም መሳተፍ ትችላላችሁ
@DBU11
@DBU111
የደብረ ብርሀን ከተማ ደም ባንክ ከፍተኛ የሆነ የደም እጥረት አጋጥሞታል ደም እንለግስ
ነገ ጠዋት :DSTV ጀርባ
@DBU11
@DBU11
ለሬሜዲያል ተማሪዎች ጥሪ ተላልፏል
'share' እያደረጋችሁ ለሌሎች ተማሪዎች አድርሷቸው
NB :''የ2017 የ12ተኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የወሰዳችሁ ''
@DBU11
@DBU111
ማስታወቂያ
ለሁሉም የደ/ብ/ዩ ተማሪዎች በሙሉ ነገ በቀን 17/03/18 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በሴኔት ደረጃ በሴኔት አዳራሽ ፕሮግራም ስለሚካሄድ ከ3:00 ጀምሮ የተለያየ አካባቢ ባህላዊ ልብስ ያላችሁ ለብሳችሁ ደምቃችሁ እንድትሳተፋ እየጋበዝን የሌላችሁ እና መሳተፍ የምትፈልጉ ደግሞ ወደ ተማሪዎች ህብረት ቢሮ እየመጣችሁ እንድታሳውቁ እና ማክበር እንደምትችሉ የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት አስታውቋል።
@DBU11
@DBU111
ለሬሚዲያል ተማሪዎች
በዝውውር ከሌላ ዩኒቨርሲቲ የመጣችሁ የደ/ብ ዩኒቨርሲቲ ሬሚዲያል ተማሪዎች ምድባችሁ መሃልሜዳ ካምፓስ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ጽ/ቤት አስታውቋል።
@DBU11
@DBU111
ስለ ማርበርግ ቫይረስ ቁልፍ መረጃዎች:-
1. የመተላለፊያ መንገድ በንክኪ (ከሕመምተኛ ሰውነት ፈሳሾች ጋር ንክኪ ሲፈጠር)
2. የተሳሳተ ግንዛቤ
እንደ ኮሮና ቫይረስ በአየር አይተላለፍም!
3. የሞት ምጣኔ
ከ24% እስከ 88% ድረስ ይደርሳል (ከኮቪድ እጅግ የከፋ ነው)
4. ከህመም በኋላ :
ቫይረሱ በወንድ የዘር ፈሳሽ ውስጥ እስከ አንድ ዓመት ሊቆይ ይችላል።
5. ለዳኑ ሰዎች ማስጠንቀቂያ
ከህመሙ ያገገሙ ወንዶች ለአንድ አመት ልቅ የሆነ የግብረስጋ ግንኙነት ከመፈጸም መቆጠብ አለባቸው።
6. ተገቢው ክትትል እና ህክምና ተደርጎለት የዳነ ሰው ከቫይረሱ የፀዳ ከሆነ በሽታውን ማስተላለፍ አይችልም።
የወቅቱ ስታቲስቲክስ
* የተመረመሩ ሰዎች: 46
* በሽታው የተገኘባቸው (Confirmed Cases): 8 ሰዎች
* በሽታው ህይወታቸውን የቀጠፋቸው: 4 ሰዎች
* በህክምና ላይ ያሉ (በህይወት ያሉት): 3 ሰዎች
ይህ መረጃ ይፋ የሆነው የጤና ሚኒስቴር ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ለሚዲያ ባለሙያዎች ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ ነው።
ለጤንነትዎ ሲባል ይህንን ጠቃሚ መረጃ ያጋሩ!
@DBU11
@DBU111
ማስታወቂያ
ለደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች
1. ነገ አርብ ከሰአት 8:00 ጀምሮ በፍትሐብሔር case
2.በቀን 15/18 ማለትም ሰኞ በወንጀል case ጠዋት 2:30 ጀምሮ
በህግ ባለሙያ እና መምህር መለሰ መሪነት በ PR አዳራሽ በ5ኛ ዓመት የህግ ተማሪዎች ለሁሉም የህግ ተማሪዎች እጅግ ደስ የሚል የ Mock Exercise event ስላለ በሁለቱም ቀናት በተባለው ሰአት PR አዳራሽ ተገኝታችሁ መከታተል ትችላላችሁ።
@DBU11
@dbu11
ለዩንቨርሲቲው መምህራንና ለአስተዳድር ሰራተኞች አነስተኛ የዲጂታል ብድርን የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ አቀረበ ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አነስተኛ የዲጂታል የብድር ለደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ ለአስተዳደር ሰራተኞችና ለመምህራን የብድር አገልግሎቱ ለመስጠት ከስምምነት አስሯል ።
የዲጂታል አነስተኛ ብድሩ በተለያየ ምክንያት የአቅም እጥረት (ጫና )በሚያጋጥምበት ወቅት ከአጭር ጊዜ እስከ አንድ አመት የሚቆይ እና የደመወዝ ስኬልን መሰረት ያደረገ ነው ተብሏል ።
ብድሩን ለማመቻቸት ዩኒቨርሲቲው ሃላፊነት መውሰዱንና ውል መያዙን ተገልጿል ።
የስምምነቱን ፊርማውን የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አስማረ መለሰ(ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረብርሃን ዲስትሪክት ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ዳኜ ነጋሽ ተፈራርመዋል
@DBU11
@DBU111
የፀደቀ የአንድ አመት ጭማሪ ፕሮግራም የለም❗
Ethiopian university student union president.
ትምህርት ሚንስቴር ባለፈው አመት የዩንቨርስቲ ተማሪዎች የ 3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያዝ መመሪያ መውጣቱ ይታወሳል። በዚህ ሳምንት መመሪያው በ2019 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል የሚል ዜና መሰማቱን ተከትሎ በተለያዩ የሐገሪቱ ዩንቨርስቲዎች የተቃውሞ ድምጾች መሰማታቸውን ተከትሎ የደብረብርሀን ዩንቨርስቲ የተማሪዎች ህብረት የኢትዮጵያ ዩንቨርስቲዎች ህብረት ፕሬዝዳንትን በምንጭነት ጠቅሶ ፕሬዝዳንቱ በፌስቡክ ገፁ እንዳሰፈረው
ይህ መመሪያ በሀሳብ ደረጃ የቀረበ እንጂ በምን መልኩ እንደሚተገበር እና ዝርዝር መመሪያው የፀደቀ ነገር የለም።
እስካሁን ድረስም ከትምህርት ሚኒስቴር ለዩንቨርሲቲዎች የተላከ ምንም አይነት መመሪያ እንደሌለ ልናሳውቃችሁ እንወዳለን።
እስከዛው ግን ዝርዝር መመሪያው እስቀሚወጣና መረጃው ይፋ እስከሚደረግ ድረስም ተማሪዎች በትግስት እንድትጠብቁ ስንል እናሳስባለን።
የደብረ ብርሐን ዩኒቨርስቲ መሐል ሜዳ ግቢ የሸዋ ብርሃን የቃል - ኪዳን ቤተሰብ የትውውቅ ፕሮግራም አደረገ!
=========================================
የደብረ ብርሐን ዩኒቨርስቲ መሐል ሜዳ ግቢ የሸዋ ብርሐን ቃል - ኪዳን ቤተሰብ ከአራቱም የከተማ ቀበሌዎች ከመጡ ቤተሰቦችና በግቢው ተመድበው ከሚማሩት የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ጋር በግቢው ውስጥ የትውውቅ ፕሮግራም አድርጓል::
@DBU11
@DBU111
ለNetworking ትምህርት ፈላጊዎች
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲው CISCO Networking Academy በዘንድሮ አመት ቀጥሎ በተዘረዘሩት የትምህርት ዘርፎች ትምህርት ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቆ ይጠብቃችኋል። ያሉን ቦታዎች ውስን ስለሆኑ ቀድመው ይመዝገቡ።
* CCNA Routing and Switching
* CCNA Security
* IT Essential ( PC hardware and software maintenance)
ማሳሰቢያ:- ስልጠናውን ላጠናቀቀ ተማሪ certificate of completion የምንሰጥ ይሆናል።
@DBU11
@DBU11
ይህ በምስሉ ላይ የምታዩት ወንድማችን ብናልፈው ታረቀኝ እውነቴ ይባላል።
ትላንት ከቀኑ 6:00 በአርባምንጭ ከተማ የመኪና አደጋ ስለደረሰበት እና ቤተሰብም ሆነ ፈላጊ ጓደኛ ስላልተገኘለት የአርባምንጭ ፖሊስ አድራሻውን እና ቤተሰቦቹን የምታውቁ ካላችሁ ጥሪ አስተላልፏል።
አደጋው የደረሰበት ግለሰብ በያዘው መታወቂያ መሰረት ደብረብርሃን ነዋሪነትን የሚገልፅ መረጃ ተመላክቷል
የምታውቁት በዚህ ስልክ መረጃ ማድረስ ትችላላችሁ።
0920122932 ሶፎንያስ ፈንቴ
0918965382 በላይ ፈረደ
@dbu11
@dbu111
የኢትዮጵያ ዩንቨርሲቲዎች ስፖርት ፌስቲቫል በሁሉም የስፖርት አይነቶች ለመወዳደር ለተመዘገባችሁ በሙሉ ነገ ማክሰኞ ቀን 02/03/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ ዋናው ሜዳ(ስቴድየም) እንድትገኙ ስንል እናሳስባለን።
የደ/ብ/ዩ/ተማ/ህ ጽ/ቤት
@DBU11
@DBU111
እሁድን ከሆሄ ተስፋ የኪነ-ጥበብ ቡድን ጋር!
በቀጠሮ አክባሪነቱ የሚታወቀው የሆሄ ተስፋ የኪነ ጥበብ ቡድን የዓመቱ የመጀመሪያ መድረኩን በትላንትናው እለት በደማቅ ሁኔታ አቅርቧል።
የግቢያችን ብቸኛው የኪነጥበብ ቡድን ሆሄ ተስፋ የመጀመሪያ በሆነው ዝግጅቱ ላይ እንደተለመደው ድንቅ ድንቅ ግጥሞች፥ ወግ፥ ሙዚቃዎች (live music) ፥ ተውኔት እና ስነ-ስዕል (live painting) ስራዎቹን አሳይቷል።
@dbu11
@dbu111