Youtube https://youtu.be/_0l6c0I7ouM 👉ስለ ግቢው ወቅታዊ መረጃ 📌ዲፓርትመንቶች ፡⚽️ስፓርት፡🎤ኪነጥበብ ምሽቶች ፡📄የጊቢ ማስታወቂያ ፡ ምልከታወችና ታሪክ ወግ ፡📷📷አስገራሚ ፎቶወች ፡ እውነታዎች እና መረጃወች📃 መፀሀፍት ፡ ሳይኮሎጂ ሁሉም ይዳሰሱበታል:: Contact
የመውጫ ፈተና መመዝገቢያ ጊዜ ተራዘመ📌📌
በ2017 ዓ.ም በሰኔ ወር የሚሰጠው የመውጫ ፈተና መመዝገቢያ ጊዜ እስከ ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ብቻ የተራዘመ መሆኑን እየገለጽን፡-
1. እስከ አሁን ያልተመዘገባችሁ የድጋሚ ተፈታኞች (resitters) ከዚህን በፊት ለምዝገባ በተከፈተውና በተገለጸው መመዝገቢያ ፕላትፎረም (registration link) በኩል ገብታችሁ ምዝገባችሁን እንድታጠናቅቁ፣
2. ለመጀመሪያ ጊዜ ለመውጫ ፈተና የምትቀመጡ ተፈታኞች በተቋሞቻችሁ በኩል መመዝገባችሁን እንድታረጋግጡ እያሳሰብን፤
3. ፈተናው የሚሰጠው ከሰኔ 2-10/2017 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ማሳሰቢያ
ለፈተናው የምታመለክቱ አመልካቾች ለመመዝገብ የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ ሊኖራችሁ ይገባል፡፡
ከግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ቦኋላ ምዝገባ አይስተናገድም፡፡
የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር
@DBU11
@DBU11
መልካም ዜና ለተመራቂ ተማሪዎች❗
🎀ከ 100 በላይ የ2017(ጥር) የቀድሞ ተመራቂ ተማሪዎችን የወንዶች መመረቂያ ሱፍ (suit) በብቃት ሰርቶ ያስመረቀው ዮሐንስ ዘመናዊ የወንዶች ልብስ ስፌት ጨርቃጨርቅ እና ዲዛይን ኑ በእርካታዎ የሚመሰክሩለትን ሱፍ (suit) ያሰሩ ይላችሗል።
🎇DBU daily news ነው የላከን ብላችሁ ከመጣችሁ ከ ሌሎች ደምበኞች የ 1000 ብር ልዩነት እንደ ፍላጎታችሁ በምትመርጡት ጨርቅ ቅናሽ ያደርግላችሗል።
🚀የ daily news ጋዜጠኛ በስራ ጥራቱ እና ብቃቱ ተማምኖበት ዮሐንስ ዘመናዊ የወንዶች ልብስ ስፌት ጨርቃጨርቅ እና ዲዛይን ጋር ያሰራል፤ ለእናንተም መረጃውን ያጋራችሁ አስደሳች አገልግሎት እንደምታገኙ ሙሉ ዕምነት ስላለው ነው።
🎀ምን ይሔ ብቻ በአግራሞት እና አድናቆት ያጨበጨብንለት በ 44 A+ (በተለምዶ charge) በማምጣት የዩንቨርስቲውን ዋንጫ ያነሳው የ marketing ተመራቂው ተማሪ አስማማው መድረክ ላይ ደምቆ የታየበት suit የስራ ውጤት ባለቤት ነው ዮሐንስ ዘመናዊ የወንዶች ልብስ ስፌት ።
🎋ኑ በቤተሰቦቻችሁ ዘመድ ጓደኞቻችሁ ባለውለታዎቻችሁ መምህራኖቻችሁ እና ተመልካቾቻችሁ ፌት የምትደምቁበትን suit እኛ ጋ ያግኙ ይላችሗል ዮሐንስ ዘመናዊ የወንዶች ልብስ ስፌት ጨርቃጨርቅ እና ዲዛይን ።
👔🎖️ከላይ ያያዝናቸውን የሱፍ ጨርቆች ይጎብኙ እንደፍላጎት እና ምርጫችሁ በሁሉም አይነት quality እና ምርጫ አለ።ብለብዙ አመታት ባካበትነው ልምዳችን(experience) የሚያረካ አገልግሎት ልንሰጥዎ ዝግጁ ነን። በሚፈለገው ሰዓት እናደርሳለን።
📞
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0974602023
0911858707
0793128088
መደወል ይችላሉ።
@dbu11
@dbu111
#ማስታወቂያ ከ ሴቶች ማህበራዊ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ለመደበኛ የዩንቨርስቲው ሜንተርሽፕ ስልጠና ለመውሰድ የተመዘገቡ ሴት ተማሪዎች በሙሉ👇👇👇👇👇
ለሁሉም ከአንደኛ አመት እስከ አራተኛ አመት ላሉ የግቢው ሴት ተማሪዎች በሙሉ የሜንተርሽፕ ፕሮግራም ለመከታተል ያመለከታችሁ እና ስማችሁ ከላይ የተገለፀ በቀን 7/09/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 በዋናው ግቢ PR አዳራሽ እንድትገኙ እንገልጻለን።
@db11
@dbu111
✨ you want to get a job, you want to get a wife 😁 you want to impress your parents so we allies you we allies students we are here because we want impress you ....…🌟 speech from the Safaricom CEOS.
ታላቅ Event❗ Safaricom Ethiopia ከደብረብርሀን ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር የእግርኳስና የሙዚቃ ድግስ አሰናድቷል‼️
ከ ደቂቃዎች በሗላ በዛሬው ዕለት ግንቦት5/09/2017 ኑ ተጋብዛችሗል የዩንቨርስቲ ትዝታዎን ያስቀምጡ !
🚀ልብ በሉ! የሳፋሪኮም ካርድ እና unlimitedና መሰል ጥቅል ሽልማቶችን ጨምሮ ሌሎችም አጓጊ ሽልማቶችን አሰናድቷል።
🚀i.e safaricom ማይፋይ (safaricom wifi) ተንቀሳቃሽ የሳፋሪኮም ዋይፋይ ከነፃ የ 6 ወር ፓኬጅ ስጦታ ጋር። የተለያዩ ያልተገደበ እና mega package ም አለ።
ልዩ ድባብ❗አስቸኳይ መረጃም አለን👇
ነገ ግንቦት 5/2017 ከ ጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከደብረብርሀን ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው event ልዩ የሚያዝናኑ ትዕይንቶችን አሰናድቶ ይጠብቀናል።
💺የሳፋሪኮም ከፍተኛ አመራሮች እና ማናጀሮች፤ የዩንቨርስቲው አመራሮች እና ድምፃዊያንም ይገኛሉ።
🎁award ማይፋይ(Mifi) ተንቀሳቃሽ ሳፋሪኮም ዋይፋይ ከነፃ የ ግማሽ አመት ፓኬጅ ስጦታ ጋር ፤ ይታደሙ የተለያዩ safaricom package ጥቅሎችን ይሸለሙ።
🎇ከሙዚቃ ጨዋታ በተጨማሪ በ ተማሪ ህብረት ስራ አስፈፃሚ አባላት እና በመምህራን መካከል የሚደረገው የእግርኳስ ፍልሚያ በጉጉት ይጠበቃል፤ ገመድ ጉተታ ውድድርም አለ።
🎙️እያዝናና በሽልማት እያንበሸበሸ safaricom ቀናችሁን ያደምቃል ኑ በክብር ተጋብዛችሗል።
ነጠላ ተቀያይሮበኛል የሚል ወንድም በዚህ ስልክ 0985427235 ደውሉልኝ ብሏል ።
@DBU11
@DBU11
በአማራ ክልል ባለው ግጭት ሳቢያ በርካታ ት/ቤቶች የዘንደሮውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እንደማያስፈትኑ ተገለፀ።
የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናውን የሚያስፈትኑ ትምህርት ቤቶች 470 ብቻ ናቸው የተባለ ሲሆን
በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ግጭት ምክንያት ትምህርት ያልጀመሩና ተማሪዎቻቸውን የማያስፈትኑ በርካታ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ እየሩስ መንግሥቱ መግለፃቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡
በክልሉ በአጠቃላይ 685 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚገኙ የገለጹት ኃላፊዋ ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት የዘንድሮውን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የሚያስፈትኑ ትምህርት ቤቶች 470 ብቻ ናቸው ብለዋል፡፡
አክለውም ሰላም ባለባቸው አከባቢዎች በሚገኙ ት/ቤቶች የሚገኙ 99ሺህ 880 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ ተመዝግበዋል ሲሉ ገልጸዋል።
አንድ በሰሜን ጎጃም ዞን የሚገኝ የ12ኛ ክፍል ተማሪ በበኩሉ በክልሉ ሠላም እስኪመጣ አማራጭ ያለውን ሥራ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግሯል።
@dbu11
@dbu111
የ2017 ትምህርት ዘመን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ / የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት መርሃ ግብር ይፋ ተደርጓል።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ይፋ ባደረገው መርሃ ግብር ፈተናው ከሰኔ 23/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ/ም የሚሰጥ ይሆናል።
በወረቀት የሚፈተኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 21 እና 22/2017 ዓ/ም እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 29 እና 30/2017 ዓ/ም ወደሚፈተኑበት ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ይሆናል፡፡
በበይነ መረብ የሚፈተኑ ተፈታኞች ከመኖሪያ ቤታቸው በየቀኑ እየተመላለሱ በተመደቡበት መፈተኛ ማዕከል የሚፈተኑ ሲሆን ዝርዝር መርሃ ግብሩ ከላይ ተያይዟል።
የፈተናው ይዘት በተማሪው መጽሐፍ ላይ ያተኮረ በመሆኑ እያንዳንዱ ተፈታኝ በትምህርት ቤቱ የተማረበትን የተማሪ መጽሐፍ መሠረት አድርጎ ተገቢ የሆኑ አጋዥ መጽሐፍትን ለበለጠ እውቀትና መረዳት በመጠቀም እንዲዘጋጅ አገልግሎቱ ጥሪውን አስተላልፏል።
በፈተና ወቅት ለፈተና ስርቆትና ኩረጃ የሚውሉ ማንኛውንም ቁሳቁሶች መጠቀም የተከለከለ ነው ተብሏል።
via TIKVAH
@DBU11
@DBU11
ኢያቄም ወሀና ወለዱ ሰማየ
ሰማዮሙኒ አስረቀት ፀሃየ!ሀና እና ኢያቄም ሰማይን ወለ፤ሰማይም ፀሃይን አስገኘች!
ለመላው ኦርቶዶክሳውያን መልካም የልደት በዓል!
@DBU11
@DBU111
From the community to the community
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ የተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ውስጥ እንደሚካተት ተገለፀ ።
በጤና፣ በኢንጅነሪግ እና ሌሎችም የሙያ ዘርፎች ተቀብሎ በማስተማር ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ምልመላ ማድረግ ጀምሯል።
ዩኒቨርሲቲው ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን መልምሎ ለማስተማር በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶችን በማካሔድ ላይ ይገኛል።
በዚህም ከመንግሥት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር እንቅስቃሴ ዙሪያ ውይይት አካሒዷል።
የወራቤ ዩኒቨርሲቲ እና የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ቅበላና ምልመላ ዙሪያ ገለጻ ከተደረገላቸው ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ይጠቀሳሉ።
በወታደራዊ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በፈጠራ ክህሎት ልዩ አቅም ያላቸው ተማሪዎች በውድድር ዩኒቨርሲቲውን መቀላቀል እንደሚችሉ ተጠቁሟል።
@DBU11
@DBU11
#መፍትሔ እንፈልጋለን !ችግሩን መፍታት ይቻላል! እርዱን!
በልዩነት ትምህርት ክፍላችን(ህግ ትምህርት ክፍል) እነዚያ ብዙ እገዛዎችህ እርዳታዎችህ እና ጥረቶችህ እንዳይባክኑ እነዚህን ኮርሶች አስጨርሰን።
...🪗አድራሻችን ፋሲል ሆቴል ፊት ለፊት 100 ሜትር ገባ ብሎ ወይም ደንበኛ አክባሪ ነንና ሰማያዊ ህንፃ ከደረሱ በዚህ ስልክ 👉0911858707 ቢደውሉ መጥተን እንቀበላችሗለን።
Читать полностью…በነገው ዕለት ግንቦት 6 የደብረብርሀን ዩንቨርስቲ ህግ ትምህርትቤት(ትምህርት ክፍል) አምስተኛ ዕጩ ተመራቂ ህግ ተማሪዎቹን MOC(model exam) ፈተና ሊፈትን ነው።
ህግ ትምህርት ቤት በ GC cup( ዕጩ ተመራቂዎች እግርኳስ ዋንጫ) ሚያነሱ ከተጠበቁ ቡድኖች ቀዳሚ ነው። እሁድ ከ አካውንቲንግ አቻው ጋር የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደርጋል።
በብዙ መሰናክሎች መሐል እያለፋችሁ እንደሆነ ተመልክተናል ህጎች ከትምህርት ክፍላችሁ ጋር እጅ እና ጓንት ሆናችሁ ወንዙን እንደምትሻገሩት ምኞታችን ነው መልካም ዕድል እንመኛለን DBU daily news 👍
@dbu11
@dbu111
CEO told you that 👉🎙️talk to your friend, talk to your parents talk to everybody and spread the word that "safaricom is here to give you good quality very affordable internet and voice service for everybody in the university and around ...🌐"
🌟strange vibes from footsal stadium come on here 🌟❗
Читать полностью…Event ቱ እየተካሔደ ነው ሳፋሪኮም ደግሞ እየጠራችሁ ነው ከስታድየሙ አጠገብ በትንሿ ስታድየም(ፉትሳል ሜዳ)
"DBU daily news" አምስት አመታትን በአገልግሎት !
✨በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ የ daily news ቤተሰቦች በዚህ ሳምንት DBU daily news አገልግሎቱን መስጠት ከጀመረ አምስተኛ አመቱን ያስቆጣራል።
✨ታማኝ እና ተደራሽ የመረጃ ምንጭ በመሆን ሲያገለግላችሁ የቆየው ገፃችሁ(DBU daily news) በዚህ ሳምንት አምስተኛ አመት ምስረታውን ያከብራል።
✨Daily news በአምስት ዓመት ቆይታው የማይረሱ ትዝታዎችን የበጎ ፈቃድ ስራዎችን በመስራት እና በማስተባበር ከእናንተ ጋር አሳልፏል።
ለትውስታ የወንድማችን ለገሰ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና ከ daily news ጋር ያደረጋችሁት በጎ ተግባር አይረሳም።
ክፉ እና ጥሩ ግዜያቶችን አሳልፈናል። እስኪ የእናንተን ትዝታ በመልዕክት መስጫ ሳጥን (comment) ላይ አስቀምጡልን።
✨ከ 14 ሺህ በላይ community
👉 የዩንቨርስቲው መደበኛ እና extension ተማሪዎች፤ መምህራን፤ የዩንቨርስቲው አስተዳደር አካላት እና የከተማው ህዝብ እንዲሁም የተማሪ ወላጅችም ጭምር የሚከታተሉት የቴሌግራም ገፅ ነው።
የመወያያ ጥያቄ(መረጃ) እርስ በእርስ ወይም ከቻናሉ መጠየቂያ ዕርዳታ መጠየቂያ ግሩፕም አለው ይህ ሊንኩ ነው 👉 @dbu111 ።
🌟አምስተኛ አመቱን ሲያከብር ጥያቄዎችን ወደ እናንተ ይለቃል ለአሸናፊዎች የተለያዩ ሽልማቶችን የሚያደርስ ይሆናል።🎁
⚠️UPDATE‼️
ዛሬ ከተከናወነው የጂሲ ካፕ የምድብ ድልድል የእጣ ማውጣት በኋላ ዘግይተው የመጡት የኢንጅነሪንግ ዲፓርትመንት ተማሪዎች እንደገና ወደ ውድድሩ ገብተው መሳተፋቸው በጂሲ ኮሚቴ ስራ አስፈፃሚዎችና የየክላሱ የጂሲ ተወካዮች ዘንድ ቅሬታን አስነስቷል።
በዚህም ምክንያት የጂሲ ኮሚቴ ስራ አስፈፃሚና የተማሪ ህብረት በጋራ በተደረገው ስብሰባ መሰረት፦
1. የኢንጀነሪንግ ተማሪዎች ተመራቂ አለመሆናቸው
2. ካለን ጊዜ አንፃር እንደ አዲስ ሌላ ድልድል ማውጣት ስለማንችል
3. ድልድሉን ማውጣት ቢቻል እንኳን በተሳታፊ ቡድኖች ላይ የሚያመጣውን ችግር እና የጨዋታ ስነልቦና ማጣት
እነዚህንና ሌሎች አሳማኝ ምክንያቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ወደ ጂሲ ካፑ ገብተው የነበሩት የኢንጀነሪንግ ዲፓርትመንቶች አሁን ከሚደረገው የጂሲ ካፕ ውድድር እንዲቀሩና ጥር 2018 ላይ እነሱ ተመራቂ በሚሆኑበት ወቅት ለነሱ አመቺ በሆነ መልኩ ጂሲ ካፕ በማዘጋጀት እንዲወዳደሩ ተወስኗል።
በዚህም ምክንያት ቀድሞ ወጥቶ የነበረው የጂሲ ካፕ የጥሎ ማለፍ ድልድል በነበረበት የሚቀጥል ይሆናል።
ማኔጅመንትም ቀድሞ በእጣ ወደ ሩብ ፍፃሜው ተሻግሮ እንደነበረው በዛው የሚቀጥል ይሆናል። ሌሎች ጨዋታዎችም በወጣላቸው ድልድል መሰረት ይከናወናሉ።
ወደሩብ ፍፃሜው ለመግባት የሚደረጉ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች
1. Computer science vs soft ware
2. Information technology vs sociology
3. Information system vs Biotechnology, Geology and psychology
4. Marketing vs NARM and Agroeconomics
5. Law vs Accounting
6. Economics vs Geography
7. Tuorism and logistics vs Sport and Biology
ጨዋታዎቹ ከቅዳሜ ጀምሮ እንደሚከናወኑ ቀደም ሲል መግለፃችን የሚታወስ ነው።
መረጃው በቀጥታ ከተማሪዎች ህብረት የተወሰደ ነው
@DBU11
@DBU111
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አካደሚክ ካላንደር በትምህርት ሚኒስቴር ፕሮግራም መሰረት እንደሚደረግ ተገለጸ።
በዚህም መሰረት ብሔራዊ የዩንቨርስቲዎች መውጫ ፈተና ከ ሰኔ 2-10 የሚሰጥ ይሆናል። ሙሉ academic schedule ከላይ በፎቶ ተያይዞላችሗል።
በተያያዘ ዜና ዘንድሮ 608 ሺህ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የመልቀቂያ ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል።
ፈተናውን በወረቀት የሚወስዱ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ በዩኒቨርሲቲዎች የሚፈተኑ ይሆናል።
ፈተናውን በበይነ መረብ የሚወስዱት ደግሞ በዩኒቨርሲቲዎች፣ በመንግሥት እና በግል ትምህርት ቤቶች፣ በጤና እና መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ ባሉ ኮምፒዩተሮች ይፈተናሉ ተብሏል።
@dbu11
@dbu111
''የመምህራን ስልጠና በስርአት አለመከወኑ የትምህርት ጥራቱ ላይ ችግር ፈጥሯል '' የደ/ብ ዩኒቨርስቲ የጥናት ውጤት
የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ 7 አውደ ጥናቶችን በመጀመሪያና በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራንና ጠቃላይ የትምህርት መሪዎች ላይ አካሂዷል ።
በአውደ ጥናቱም የመምህራን ስልጠና በስርአት አለመከወኑ የትምህርት ጥራቱ ላይ ችግር መፍጠሩን እና በፓሊሲ ደረጃና በት/ቤት ደረጃ የታዩ ክፍተቶች መኖራቸውን አመላክቷል ።
በትም/ሚኒስቴርና በተለያዩ ምሁራኖች የተጠኑ ጥናቶች የሚያሳዩት በትምህርት ስርአቱ ውስጥ የመምህራን የብቃት ክፍተት ለተማሪዎች የውጤት ማሽቆልቆል እንደ ምክንያት የሚጠቀስ በመሆኑ በመድረኩ ተገልጿል ። ለትምህርት ስርአቱ መሻሻል እና የተጠኑ ጥናቶች አጋዥ መሆናተውን የትምህርት ሚንስቴር ተወካይ በገልፀዋል ።
በመድረኩ የትምህርት ሚንስቴር ሀላፊዎች የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሰቲ ሙሁራን እና የትምህር ቤቶች ሀላፊና መምህራን ተገኝተዋል ።
@DBU11
@DBU11
የለውጥ መሳሪዎችን በመጠቀም የተገልጋዮች እርካታ ማረጋገጥ ይገባል ተባለ
==============================================
በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ የሀኪም ግዛው ሆስፒታል ወርሃዊ የስራ አፈጻጸም ግምገማ የካምፓሱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ቴዎድሮስ ክፍለዮሐንስን ጨምሮ የሆስፒታሉ የህክምና አገልግሎት ኮርፖሬት ም/ዳይሬክተር፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ የዴስክ ኃላፊዎች እና የሚመለከታቸው በአስተዳደር ዘርፍ ላይ ያሉ ሀላፊዎች በተገኙበት ሚያዚያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ግምገማ አካሄደ፡፡
የካምፓሱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ቴዎድሮስ ክፍለዮሐንስ እንዳሉት የለውጥ መሳሪያዎችን እንደ EBC /Evidence Based Care/ እና SBFR /System Bottleneck Focused Reform/ ያሉትን በመጠቀም የሆስፒታሉን ተገልጋዮች እርካታ በሚያረጋግጥ መልኩ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡ በሀኪም ግዛው ሆስፒታል የሚሰጠውን የተሻለ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት የሚመጡ ተገልጋዮች ቁጥር እየጨመረ በመሄዱ እነዚህን ተገልጋዮች የሚያረካ አገልግሎት መስጠት የሁሉም ስራ ክፍሎች ርብርብና ተናቦ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
በሀኪም ግዛው ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት ኮርፖሬት ም/ዳይሬክተር ዶ/ር ዘመድ ገለታ በበኩላቸው አገልግሎታችን ተቋማችንን መሰረት በማድረግ ለተገልጋዮች ትኩረት መስጠትና ለስራችን ኃላፊነት መውሰድ ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም የምንሰጠው የህክምና አገልግሎት የቡድን ስራ በመሆኑ የስራ ኃላፊዎች በስራ ክፍላቸው የሚገኙ ሰራተኞችን በኃላፊነት መንፈስ፣ በጥልቅ የስራ ዲስፕሊን ሊመሩና ሊቆጣጠሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
@DBU11
@DBU11
የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማግኘት ከግንቦት 15/2017 ዓ.ም ጀምሮ የፋይዳ መታወቂያ እንደሚጠይቅ አሳውቋል።
የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ አገልግሎት ለማግኘት የሚፈልጉ የባለሥልጣኑ ተገልጋዮች የፋይዳ መታወቂያ ቁጥር ሊኖራቸው እንደሚገባም ተገልጿል።
@DBU11
@DBU11
ክፍት የስራ ማስታወቂያ
ኤርሞን ኢንጅነሪንግ ድርጅታችን ከዚህ በታች በተገለፀው ክፍት የስራ መደብ ላይ ብቁ የሆኑ ባለሞያዎችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል።
የስራ መደብ፥ አርክቴክት
የትምህርት ደረጃ - በአርክቴክቸር የመጀመሪያ ዲግሪ
ልምድ- አንድ ዓመት እና ከዚያ በላይ
አድራሻ ደብረብርሃን
ደሞዝ - በድርጅቱ ስኬል
2 በድራፍቲንግ (Draft Man)
የት/ት ደረጃ፥ ብድራፍቲንግ በሌቭል የተመረቀ/ች
ችሎታ- AutoCAD በቂ እውቀት ያለው/ያላት የአርክቴክቸራል ድራፍቲንግ ስራዎችን መስራት የሚችል/የምትችል።
ልምድ- 1 ዓመትና ከዚያ በላይ
ደሞዝ - በድርጅቱ ስኬል
አድራሻ ደብረብርሃን
ኤርሞን ኢንጅነሪንግ- የሽክረት ዲዛይን ህትመትና ማስታወቂያ አጋር
ለበለጠ መረጃ
+251911158287
🆕አዲስ ነገር ከ @linkedIn_BussinessET
LINKEDIN ACCOUNT በማከራየት ብቻ በየሳምንቱ ዳጐስ ያለ ገንዘብ ማግኘት እንደሚችሉ ያውቃሉ??💲💲💲💲
@linkedIn_BussinessET ኮሚኒቲያችንን በመቀላቀል ከኛ ጋር አብረው መስራት ይችላሉ::
ታማኝነት ተቀዳሚ አላማችን ነው::
ለማንኝውም ጥያቄና: አስተያየት @ukcryptohodlers ያነጋግሩን::
በተጨማሪ በአካል ሊያገኙን ወይም አድራሻችንን ከፈለጉ AASTU campus 2 ያገኙናል::
የተሻሻለው የዋጋ ዘርዝር: በኮኔክሽናቹ ብዛት መሰረት⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
💰100 + ==>..... $7 per week 💲
💰200 + ==>...... $10 per week 💲
💰300 + ==> ........$12.5 per week 💲
💰400 + ==>........ $15 per week 💲
💰500 + ==>........ $17.5 per week 💲
💰600 + ==>........ $20 per week 💲
💰700-1000+==>$25 per week 💲
TRUST IS OUR TOP PRIORITY
ከላይ ይቀጠለ
judicial training (የስራ አለም ከመግባት በፊት የሚወሰድ ስልጠና) አብዝሐኞቹ በበጀት አመቱ የመጀመሪያ ወራቶች ላይ ይሰጣሉ i.e መስከረም።
ቤተሰቦቻችን እንደምንመረቅ እንደምንጨርስ ነው የሚያውቁት ዝግጅቶችን እያደረጉ ነው ምክንያቱም ከ17 ዓመት የትምህርት ዓለም ቆይታ በሗላ ልጃቸው የመጀመሪያ ድግሪውን ሊይዝ ነው በምን አይነት መንገድ ብናስረዳቸው ነው የሚረዱን እንዴት ነው የምንነግራቸው ጨንቆናል።
#3 ተማሪዎቹ የዩንቨርስቲው ጥሩ ውጤት ተወዳዳሪዎች የዋንጫ ተፋላሚ ተማሪዎች ብዙ የማዕረግ ተሸላሚዎች አሉ እናም ትምህርት ክፍሉ ያስመሰግናል የእነዚህ ውጤታማ ተማሪዎች ሞራልን ይጠብቃል።
የዩንቨርስቲያችን ዓላማ አምራች እና ተወዳዳሪ (ውጤታማ) ትውልድ ማፍራት እንደመሆኑ በሚገባው ሰዓት አላስፈላጊ resource (ጊዜ፥ ገንዘብ፥ ጉልበት፥ future ) ሳይባክን በሚገባው ሰዓት ለህዝባችን ወደ ገበያ እንዲያስገባን (መርቆ እንደሚያስወጣን ፅኑ ዕምነት አለን)።
"from the community to the community"
አምስተኛ አመት ሁለተኛ ሴሚስተር የተግባር ልምምድ (apparent) ለመውጫ ፈተና እየተዘጋጀን እየሰራን ነው በመሆኑም አምተኛ አመት 3 ሴሚስተር እንድንማር መደረግ አግባብ አይደለም ትምህርት ክፍላችን መልካም ውሳኔህን i.e ምቹ የትምህርት አካባቢ ስትፈጥር እንደነበረው የተለመደ እገዛህን እንፈልጋለን።
@dbu11
@dbu111
በታሪፍ ጭማሪ ምክንያት ከደብረ ብርሀን አዲስ አበባ የትራንስፖርት መጉላላት እየደረሰ ነው ።
ከደብረብርሃን ከተማ ወደ አዲስ አበባ መኪና ባለመኖሩ ጠዋት አራት ሰዓት ጀምሮ በርካታ ሰው እየተጉላላ መሆኑን የደረሰኝ ጥቆማ ያመላክታል።
ውጪ ላይ ታሪፉን እጥፍ በማድረግ 500 ብር የሚጭኑ እንዳሉም ሰምተናል።
ትኬት ቆራጭ ማህበራት ቢኖሩም መኪኖች የሉም ያሉ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ችግሩን መቀረፍ ይኖርበታል።
የደብረብርሃን ከተማ መናኸሪያ የትኬት ቆራጭ ማህበራትን በማስገባት ህበረተሰቡን በተወሰነ መልኩም ቢሆን ከተጨማሪ ክፍያ ያዳነ ቢሆንም እንደዚህ ያሉ ጊዚያዊ ችግሮች ሲከሰቱ ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል።
በተለይ ከመናኸሪያ ውጪ ላይ ለመጫን የሚሞክሩ ሰዎች በህጋዊ መንገድ መናኸሪያ ውስጥ በሚጭኑ ሰዎች ላይ ጫና እያሳደሩ ስለሆነ እርምጃ ቢወሰድ ጥሩ ነው ሲሉ ተሳፋሪዎች ገልፀዋል።
ምንጭ አዩ ዘሀበሻ
@DBU11
@DBU11