dbu11 | Unsorted

Telegram-канал dbu11 - DBU Daily News

14219

Youtube https://youtu.be/_0l6c0I7ouM 👉ስለ ግቢው ወቅታዊ መረጃ 📌ዲፓርትመንቶች ፡⚽️ስፓርት፡🎤ኪነጥበብ ምሽቶች ፡📄የጊቢ ማስታወቂያ ፡ ምልከታወችና ታሪክ ወግ ፡📷📷አስገራሚ ፎቶወች ፡ እውነታዎች እና መረጃወች📃 መፀሀፍት ፡ ሳይኮሎጂ ሁሉም ይዳሰሱበታል:: Contact

Subscribe to a channel

DBU Daily News

20 የሚደርሱ የትምህርት ክፍሎች ተዘግተዋል።


የአፕላይድ ዩኒቨርሲቲ የሆነው የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ  በ57 ፕሮግራሞች ላይ የስርዓተ ትምህርት ክለሳ በማድረግ ወደ 37 ፕሮግራዎች ዝቅ እንዲል አደርጓል፡፡

ገበያ ተኮር ፕሮግራሞችን ይዞ ተወዳዳሪና ተመራጭ መሆን ይገባል  ያሉት የዩኒቨርሲቲው  ፕሬዝዳንት መጪው ጊዜ ዩኒቨርሲቲዎች ከመንግስት የተማሪዎች ምደባ ወጥተው ወደ ተማሪዎች ቅበላ የሚሸጋገሩበት ዘመን ነው ብለዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የአማርኛ ቋንቋና የታሪክ ትምህርት በልዩ ሁኔታዎች እንዲቀጥሉ ማኔጅመንቱ ወስኗል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ 

👍መረጃውን ከዩኒቨርስቲው የፌስቡክ ገፅ ተመልክተነዋል

@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

✨✨
ቀደምት አባቶች እንደሚናገሩት በድሮ ጊዜ የኢትዮጵያ ንግስት የነበረችው ንግስት ሳባ ወደ እስራኤሉ ንጉስ ሰለሞን የጥበቡን ስፋት ለማየት ሄዳ ነበር።

ንግስቷ የንጉሱን ጥበብ ለመፈተን አንድ ፈተና ይዛ ንጉሱ ዘንድ ቀረበች።

ፈተናውም ሁለት ተመሳሳይ መልክና ቀለም ያላቸውን አበቦች ይዛ ሄዳ  ከሱም ራቅ ብላ በመቆም የተፈጥሮ የሆነውንና ያልሆነውን እንዲለይ ነበር።

ስትጠይቀውም  "አበባ አየህ ወይ?" ብላ እንደነበርና ከዛም የተነሳ በአዲስ አመት ልጆች ሲጫወቱ አበባዬሽ የሚሉት ከዚህ  ትውፊት ተነስተው እንደሆኘ ሊቃውንት አባቶች ይናገራሉ።

ንጉሱም መስኮቱን ክፈቺወና ንብ የቱ ላይ እንደሚያርፍ እንይ አላት ይባላል።

ለመላው የDBU DAILY CHANNEL  ቤተሰቦች እንኳን ለ2017ዓ.ም በሰላም አደረሳችው።

አዲሱ አመት ክፍውን ከደጉ የምንለይበት እንዲሆን ተመኘን።🌼🌼🌼

@dbu11
@dbu_entertainment

Читать полностью…

DBU Daily News

ለጤና ተማሪዎች የመግቢያ ቀን 👆 ተመልከቱት

@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

#update

ለቀናት ተራዝሞ የነበረው በ2017 የትምህርት ዘመን የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር የመግቢያ ፈተና (NGAT) አመልካቾች ምዝገባ ዛሬ ተጠናቋል።

ፈተናው ነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ም ይሰጣል።

ወደየተመደባችሁበት የፈተና ማዕከል ለፈተና ስትሔዱ የተሰጣችሁን User Name and Password እንዲሁም ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ መያዝ ይጠበቃባችኋል።

መልካም ዕድል

@dbu11

Читать полностью…

DBU Daily News

የግቢያችን የሆሄ ተስፋ የኪነ-ጥበብ ቡድን አባላት የተሳተፉበት ታሪካዊ መፅሐፍ

'ክንፋም ከዋክበት'

እነሆ የመጀመሪያው ምዕራፍ ተጠናቀቀ
እንኳን  ደስ ያለን ያላችሁ

ነገ መጪው ትውልድ ሲጠይቅ ዘመኔ እንዲህ ተጠቦ ነበር ብለው ሚመሰክሩበት
ታሪክ ነው።

አዲሱ ትውልድ እና የግጥም ጣዕም የገባቸው፤ 100 የሚሆኑ ወጣቶች ሥራዎቻቸውን በጋራ ለማሳተም ቅድመ ምልከታ ሲደረግ የቆየ ሲሆን።ለአዲሱ ዓመት መቀበያ ፤ የ50 ገጣሚያን ሥራዎች ተመርጠው ለንባብ በቁ።

 
የመጀመሪያው ምዕራፍ ገጣሚያን እንኳን ደስ አላችሁ።
 
መጽሐፋን የመመረቅ፣ አንጋፋዎቹን ለበዓል የመጠየቅ መሰናዶ ከፊት ይጠብቀናል።
እርስዎ ደግሞ የዚህ ደስታ እና ባለ ታሪክ እንዲሆኑ በክብር ጋብዘናል።

እነሆ ቅድመ ሽያጭ ጀምረናል።
የመጽሐፉ ዋጋ 300:ብር ሲሆን
እነዚህን ከዋክብትን እና መጪዎቹን ለማበርታት አብረውን ይጓዙ። እናመሰግናለን።

1000420583528 ሰይፉ ወርቁ
1000143312244 ጌታቸው ዓለሙ  ደረሰኙን ይላኩልን። መጽሐፋን ባሉበት እንልካለን።

+251 924 913036
+251 911 125788

Читать полностью…

DBU Daily News

ደብረብርሃን ባጃጆች ከጠዋቱ 12:00 ሰአት እስከ ምሽቱ 12:00 ሰአት ብቻ እንዲሰሩ ተወሰነ።

የደብረ ብርሃን ከተማ  የጸጥታ ምክር ቤት  ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባጃጅ ተሽከርካሪን በመጠቀም በማህበረሰቡ ላይ ስርቆትን ጨምሮ የተለያዩ ወንጀሎችን ለመከላከል ለባጃጅ አሽከርካሪዎች የተለያዩ ክልከላዎችን አስቀምጠ።

በዚህ ወንጀል የተሠማሩ አካላት የባጃጅ ተሽከርካሪዎቹን ማሟላት ያለባቸውን ህጋዊ ሰውነት ተሽከርካሪዎቹ ሳያሟሉ እንደሚያሽከረክሩም የጸጥታው ምክር ቤት እንደደረሰባቸው አንስቷል።

ለህዝብ ሰላም ሲባል የጸጥታ ምክር ቤቱ ህግና ስርአት ለማስከበር ያመች ዘንድ ማንኛውም የባጃጅ አሽከርካሪ በተሽከርካሪው ላይ ስቲከር መለጠፍ ፣ መጋረጃ መጠቀም እንደማይቻል በክልከላው ገልጿል።

ያለስምሪት ፣ የጎን ቁጥርና ታርጋ  ሳይጠቀሙም ማሽከርከር በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን፣

ከዛሬ 4:00 ጀምሮ የባጃጅ ተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ከጠዋቱ 12:00 ሰአት እስከ ምሽቱ 12:00 ሰአት ብቻ ማሽከርከር  እንደሚቻል፣

ከዚህ ሰአት ውጭ ወይም ከላይ መደረግ ያለባቸውን ያላሟላ ባጃጅ ሲንቀሳቀስ ቢገኝ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ በባጃጅ አሽከርካሪውና ባለንብረቱ ላይ እንደሚወሰድ ከከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አገኘውት ያለው ኢትዮ መረጃ የኢንፎርሜሽን ቻናል ነው ።

@dbu11

Читать полностью…

DBU Daily News

ለ2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ ትምህርት ፕሮግራም ፈላጊዎች በሙሉ ከአስራት ወልደየስ የጤና ሳይንስ ካምፓስ የወጣ የትምህርት ማስታወቂያ

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN

Читать полностью…

DBU Daily News

ለመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች :ሀምሌ 22 ወደ ዩኒቨርሰቲው ግቡ ተብሏችኃል ።

@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

ክፍት የስራ ቦታ

ሞክሩት 📌
🔊 Paid Internship Opportunity

Organization: Center of Excellence International Consult

Eligible applicants: Fresh graduates who have a degree and/or interest in the stated position.

Positions:
🎯Marketing
🎯Accounting
🎯Sociology
🎯Statistics
🎯Gender studies

🖍How to apply: Send your CV and Cover letter to the email address  awaqiyouth@gmail.com with the subject "Center of Excellence International Consult"

📅 Duration: 3 months
💰 Paid Internship
📈 Benefit: Employment opportunity based on performance.

@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

የደብረብርሐን ዩንቨርስቲ Route finding system application ነው።

በዩንቨርስቲው ውስጥ ያሉትን አድራሻዎች ሙሉ በሙሉ የያዘ የቦታ(መዳረሻ) ጠቋሚ
ሲሆን ከተወሰኑ የ ትምህርት ክፍል አድራሻ (ብሎክዎች) ቅያሪ ውጭ ማንንም መጠየቅ ሳያስፈልገን በትክክል የፈለግነው ቦታ ለመሔድ እጅጉን የሚያገለግል አፕልኬሽን ነው
ተጠቀሙበት።

አፕልኬሽኑ በአጋጣሚ የሌላችሁ ቤተሰቦች አውርዳችሑ መጠቀም ትችላላችሁ ለጓደኞቻችሁም አጋሯቸው።
አፕልኬሽኑ በአማርኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋ አማራጮች ሲኖሩት አማራጩን አፕልኬሽኑን እንደከፈታችሁ Top right corner(በስተቀኝ የራስጌ ማዕዘን) ላይ extra የሚለውን icon ስትነኩት ታገኙታላችሑ።



@DBU11
@DBU_entertain

Читать полностью…

DBU Daily News

እንኳን ደስ አለን!

#Internet

ለረጅም ወራት በአማራ ክልል ተቋርጦ የነበረው ኢንተርኔት ከዛሬ ጀምሮ በቋሚነት ተለቋል!

@DBU11
@DBU_entertain

Читать полностью…

DBU Daily News

#ማጭበርበር

እየተከናወነ ያለው ተመራቂ ተኮር ሌብነት ምን ይመስላል?

ይህም ሰራ ፈጠራ መሆኑ ነው እንግዲህ..

በተቀናጀ መልኩ የስራ ማስታወቂያዎችን በማውጣት በ0 ዓመት የስራ ልምድ ለስራ እናወዳድራለን በሚል ውሸት ብዙ ተመራቂ ስራ ፈላጊ ተማሪዎች እየተሸወዱ እንደሆነ ይስተዋላል።

ውድ ስራ ፈላጊ ተመራቂዎች ስራ ለመወዳደር የምትገኙበትን ቦታ እና ቀጣሪዎቻችሁን በውል ሳታረጋግጡ ክፍያን አትክፈሉ።

@Dbu11

Читать полностью…

DBU Daily News

ለክረምት ነባር ተማሪዎች
@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ስለ ግቢው :ስለ ፈተናው ገለፃ ተደርጎላቸዋል ።

መልካም ዕድል ለተፈተኞች

@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ

የጋዜጠኝነት ፍላጎት ያላችሁ እና በሶሻል ትምህርቶች ዲግሪ ያላችሁ ሞክሩት ።

ፎርቹን የእንግሊዘኛ ቢዝነስ ጋዜጣ ላይ

መስፈሥርቱን በደንብ ተመልከቱት

@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

🌼እንኳን አደረሳችሁ!

እመጓ ህትመት እና ተያያዥ ስራዎች ድርጅት
🤫ከበዓል ጀምሮ በየሳምንቱ የሚቀጥል ልዩ ስጦታ ይዞላችሁ ቀርቧል።

የሽልማት መስፈርት የሚሆነው በሚለቀቁት የቲክቶክ ቪዲዮዎች ስር ገብቶ ኮሜንት መስጠት እና  like ማድረግ ብቻ ነው።

በኮሜንቱ ስር 100 , 50 , እና 30 like ያገኙትን ሁሉንም የ የሽልማቱ ተጋሪ  ይሆናሉ።

የቲክቶክ ፔጅ ሊንክ👇
https://vm.tiktok.com/ZMhemW6Eq/

መልካም ዕድል!

Читать полностью…

DBU Daily News

የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ የግብርና ካምፖስ በ2017 ተማሪዎችን ይቀበላል ተባለ ።

👍ዩኒቨርስቲው ላለፉት ሁለት አመታት  በግንባታ ነበር ። በመንዝ መሀልሜዳ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው የግብርና ካምፓስ በ2017 ዓ.ም ተማሪዎችን ተቀብሎ የመማር ማስተማር ስራውን በይፋ እንደሚጀምር ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።

👍የዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመናዊ ኢትዮጵያን በመገንባትና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ትልቅ ቦታ እንድትደርስ ያበረከቱትን አስተዋፅኦ የሚዘክር በትውልድ ቦታቸው አንጎለላ ቀበሌ በ150 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ በምስራቅ አፍሪካ ተመራጭ የምርምር ማዕከል ሊሆን የሚችል የቴክኖሎጂ ካምፓስ እየተገነባ እንደሚገኝ ተገልፆል ።

@dbu11
@dbu_entertain

Читать полностью…

DBU Daily News

Urgent 🖍

አሁን በደረሰን መረጃ .............


@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

የመግቢያ ፈተና ምዝገባ መራዘምና የፈተና ግዜን ስለማሳወቅ

Читать полностью…

DBU Daily News

ግቢ ውስጥ ለሚገኙ ሱቆች ጨረታ ወጣ :
@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

#notice

ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ የ2017 መደበኛ ተማሪዎች መግቢያ ቀን እስኪሁን በይፋ አላስታወቀም።

ዩኒቨርስቲው የመግቢያ ቀን ይፋ ሲያደርግ ታማኝ በሆነው ቻናላችን በፍጥነት የምናሳውቅ ይሆናል።

እስከዛው ባልተረጋገጡ የመግቢያ ቀን ተብለው በሚወጡ መረጃዎች አትወዛገቡ።

@dbu11

Читать полностью…

DBU Daily News

#Notice

የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ ጊዜ ከሐምሌ 24 ይጀምራል ።

ትምህርት ሚኒስቴር በ2017 የትምህርት ዘመን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ላላቸው አመልካቾች የሚሰጠው የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና  (NGAT) ምዝገባ የሚካሄደው ከሐምሌ 24 - ነሐሴ 05/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

፨ የመመዝገቢያው ቅጽ ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በሟሟላት በ https://NGAT.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

@dbu11

Читать полностью…

DBU Daily News

''ለክረምት ተማሪዎች ከተጠቀሰው ቀን ዘይግይቶ የሚመጣ ተማሪን አላስተናግድም 'ዩኒቨርሲቲው

ሙሉ መረጃው በምሰሉ ላይ ተያይዟል 👆👆
@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ና የታሪክ ትምህርት ክፍል እንዲመልሱ ወሰነ ።

የደብረ ብረሃን ዩኒቨርስቲ የባህል፣ የታሪክና የቋንቋ ማዕከል እንደገና መደራጀቱን አስታወቀ። ብዙ ወዝግቦችና የትችት አስተያየቶች ሲሰጡበት የነበረው የዩኒቨርሲቲው ውሳኔ ፣በበርካቶች ዘንድ መነጋገሪ እንደ ነበር ያትወሳል ።

ከዚህ ቀደም ዩኒቨርሲው የትምህርት ሚኒስቴር በሰጠው አቅጣጫና ተልኮ መሰረት በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ አራት ኮሌጆች ውስጥ ያሉ 18 የትምህርት ክፍሎች እንዲዘጉ መወሰኑን ይታወቃል ።ዩኒቨርሲቲው ወሳኔውን ዳግም በማጤን የታሪክንና የአማርኛ ቋንቋን በማካተት አንድ ማዕከል ማቋቋሙን አስታወቋል ። የትምህርት ክፍሎቹ ዝቅተኛ የተማሪ ቁጥር ማሟላት የሚችሉ ከሆነ በመጀመሪያ፣ ሁለተኛና ሦስተኛ ድግሪ እንዲማሩ ይደረጋል ሲል ዩኒቨርሲቲው በማህበራዊ ድህረ ገጹ ላይ አስፍሯል ።

የዐማራ ክልል የመንግሥትዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማኅበርም፣ “ውሳኔው፥ ፖለቲካዊ ተጽእኖ ያለበት ነው ሲል መቃወሙ ይታወሳል።
@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

ደብረብርሃን ዩኒቨርሲተ ለ2016 ዓ.ም የ2ኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ገለጻ አደረገ።

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከሰሜን ሸዋ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ለመጡ የ2ኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎችን 6-8/11/2016 ዓ.ም ተቀብሎ ሀምሌ 08/2016 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ስለሚሰጡ አገልግሎቶችና አጠቃላይ ስለፈተናው ሂደት ገለጻ አደረጓል፡፡

በገለፃው ላይ የተገኙት የደብረ ብርሃን ከተማ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት እንዳሉት ተፈታኝ ተማሪዎች በዚህ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ሆናችሁ ለፈተና በመቅረባችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ካሉ በኋላ ለዚህ ስኬት ያበቋችሁ ወላጆች፣መምህራንና የትምህርት አመራሮች ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

አያይዘውም የነገው ሃገር ተረካቢ ትውልድ በመሆነችሁ ራሳችሁን አረጋግታችሁ ትኩረታችሁን ፈተናው ላይ በማድረግ የሀገሪቷን ከፍተኛ ውጤት እንደምታስመዘገቡ ምኞቴ ነው በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡

ለተፈታኝ ተማሪዎች  በዋናነት ስለ በመብትና ግዴታቸው፣ስለጊዜ አጠቃቀም፣የፈተና ወረቀት አጠቋቆር እንዲሁም የተከለከሉ ነገሮችንና ተዛማጅ ጉዳዮችን አስመልክቶ የፈተና ማዕከል አስተባባሪ አቶ አማን ወርጂ  ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በአጠቃላይ በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ከ8000 በላይ የ12ኛ ክፍል የማህበራዊና የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ሀገር አቀፍ ፈተና እንደሚወስዱ ታውቋል፡፡

ሐምሌ 2016

@dbu11

Читать полностью…

DBU Daily News

#Alert

ማጣት ለማጣት ምክኒያት አይሁን!

ከትንንሽ ገቢ፣ወይም ከቤተሰብ ድጋፍ ላይ የምንቀራርማት ሳንቲም ላይ አሰፍሳፊው ብዙ ሆኗል

ለጥንቃቄ እንዲሆናችሁ ዛሬ የቅርብ ጓደኞቼ ጋር ለማጭበርበር የደረሳቸውን Scam ላስተዋውቃችሁ።

ዌብሳይቱ registers.infinitypowersvip.com ነው። እንሰራለን የሚሉበት መንገድ የሆነ ያህል ሺ ብሮችን ከእናንተ ኢንቨስት እንድታደርጉላቸው እና ኢንቨስት ባደረጋችሁላቸው ብር መጠን በ% ታስቦ ትርፋችሁ እንደሚደርሳችሁ ያሳውቋችኋል።

ለመተማመን እንዲሆን የመጀመሪያዎቹን ዙሮች በእርግጠኝነት ትርፍ ልታዩ ትችላላችሁ። ከተወሰኑ ዙሮች በኋላ ግን የምትመድቧቸው ብሮች አይመለሱም።ተጠንቅቃችሁ ከሰራችሁ ሳይቀድሟችሁ ልትቀድሟቸውም ትችላላችሁ።

እንድታውቁ ምፈልገው ግን ስካም ነው!

እስኪ ለማረጋገጥ አንዳንድ የ ስካም ቼክ መንገዶችን ላሳያችሁ።

ማረጋገጫ
  Trust Score (የእምነት ውጤት) በ scamadviser.com እይታ መሰረት የእምነት መጠኑ ዝቅተኛ የሚባል ነው።


Source Code and Registry:  The algorithm scans the source code, terms, conditions, and registry information to assess legitimacy


Negative Highlights:
ማንኛውንም site whoIs (xxxx) x ቦታ ማረጋገጥ የምትፈልጉትን አስገብታችሁ ሰርች ብታደርጉ የዚያን ሳይት ትክክለናነት ታረጋግጣላችሁ.

በተጨማሪም scam-detector.com  ላይ በቀጥታ ስካም ነው የሚል ሜሴጅ አለው።

The Tranco rank (traffic) is low.

በዚህ ሳይት ላይ  iframe ወይም inline frame ተገኝቶበታል። ይህ ማለት እናንተ ከምትጠቀሙት ገጽ በተጨማሪ የምትጋሩት ገጽ አለ ማለት ነው። ይህ መጥፎ ነገር ባንለውም  ግን በስካም ስራ ውስጥ የመጀመሪያው መንገድ ተጠቃሚውን ያለፍቃዱ ወደሌላ ገጽ መክተት ነው።

Consumer Reviews:
   የተጠቃሚዎች ምላሽ በሚታይበት ሰዓትም whatsapp ላይ በተሰራው ጥናት መሰረት ከፍተኛ የተካዱ ፈንዶች ፈጻሚ ስር ተካቷል።

በአጠቃላይ እንዲህ አይነት ስካም ሳይቶች የበዙ በመሆናቸው እያንዳንዳቸውን ጠቅሶ ማረጋገጥ ስለሚታክት በራሳችሁ መንገድ ጥናት ብታደርጉባቸው እና ከዘራፊዎች እንድትጠበቁ ምክራችን ነው።

ደሞ እናንተ ማን ስለሆናችሁ ነው ምንም ሳትሰሩ ብር ምትጠብቁት ... እ

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN

Читать полностью…

DBU Daily News

ፈተናው በሰላም ተጠናቋል!

በደብረ ብርሃን ዩንቨርስቲ ሐምሌ ከሀምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ለ3 ቀናት ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ማጠቃለያ ፈተና በስኬት፣በሰላምና በጥሩ ስነ-ምግባር ተጠናቋል፡፡ከሁሉም ወረዳዎች የመጡ ተፈታኝ ተማሪዎች ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡

ሐምሌ 06/2016 ዓ.ም

@dbu11

Читать полностью…

DBU Daily News

Student Portal

የሁሉም ተማሪ መረጃ የሚካተትበት የተማሪዎችን User name እና password የያዘ ፋይል ከላይ ተያይዞላችኋል።

በID ሊስት ስር የራሳችሁን user name ካገኛችሁ በኋላ https://studentportal.dbu.edu.et/ በመግባት የራሳችሁን መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።

እንደ password የምትጠቀሙት username በSmall latter በማድረግ እና በመጨረሻም ከusername በኋላ ከሚገኘው ቁጥር ቀጥሎ # በማስገባት ነው።

ለምሳሌ
user name= Dbu612673
Password= dbu612673#

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN

Читать полностью…

DBU Daily News

ለኢንጂነሪንግ ተመራቂዎች

በ0 አመት ለኢንጂሪንግ ተማሪዎች : በደቡብ ክልል ለምትገኙ እና የከፋ ዞን ለሚቀርባችሁ ተመራቂዎች የወጣ ማስታወቂ ።

ዝርዝሩን በጥንቃቄ ከማስታወቂያው ላይ ይመልከቱ

@DBU11
@DBU11

Читать полностью…

DBU Daily News

ቻናላችን በተጨማሪ ገፅታ


መረጃ ማቅረብ የሚታወቁ DBU Daily news ከዚህ በኃላ በተጨማሪነት በዜሮ አመት የስራ ልምድ ና የትርፍ ሰአት ስራ ማስታወቂያዎችን ለእናንተ ማድረስ ይጀምራል ።

@DBU11
@DBU11

Читать полностью…
Subscribe to a channel