Youtube https://youtu.be/_0l6c0I7ouM 👉ስለ ግቢው ወቅታዊ መረጃ 📌ዲፓርትመንቶች ፡⚽️ስፓርት፡🎤ኪነጥበብ ምሽቶች ፡📄የጊቢ ማስታወቂያ ፡ ምልከታወችና ታሪክ ወግ ፡📷📷አስገራሚ ፎቶወች ፡ እውነታዎች እና መረጃወች📃 መፀሀፍት ፡ ሳይኮሎጂ ሁሉም ይዳሰሱበታል:: Contact
3 ቀን ብቻ ቀረው
ለብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ህትመት አቅርበን የነበረው ቅናሽ 3 ቀናት ብቻ ይቀሩታል።
የህትመት አገልግሎቱ ሁሌም የሚቀጥ ሲሆን ቅናሹ ግን እስከ ታህሳስ 1 ድረስ ብቻ ይቆያል።
ዲጂታል መታወቂያ ለምን ይጠቅማል?
👉እንደማንኛውም መታወቂያ ያገለግላል
👉በሃገር ውስጥ የሚከናወኑ ተቋማዊም ይሁን ግላዊ ክንውኖች ላይ ግዴታ እየሆነ ይገኛል
👉 አለም አቀፋዊ የሆኑ የኦንላይን ሳይቶችን ቬሪፋይ(ተቀባይነት ለማግኘት) ያገለግላል።
ህትመት አገልግሎት ለማድረግ ምን ያስፈልጋል
👉የተመዘገባችሁበት ስልክ በእጃችሁ ላይ መኖር ብቻ
ፋይዳ ቁጥር የጠፋበት መልሶ መላክ ስለሚቻል ጥያቄ ውስጥ አይገባም
ማስታወሻ፥ ይህን ዲጂታል መታወቂያ ህትመት ሲከናወንላችሁ Verified ካልሆነላችሁ ያለተጨማሪ ወጪ ድጋሜ ማውጣት እንደምትችሉ እንገልፃለን ።
ዋጋ- ኦርጂናል 350 250
ዲጂታል ኮፒ 150 100
ሽክረት ዲዛይን፣ህትመት እና ማስታወቂያ
ከዚህ በተጨማሪም ማንኛውም የህትመት፣የማስታወቂያ እና የስጦታ እቃዎች ህትመት ስራዎችን በድርጅታችን ይዘን ቀርበናል።
አድራሻ ፥ ደብረብርሃን ከተማ ከስላሴ ቤተክርስቲያን ቀጥሎ ያለው ህንፃ 1ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ 0940219376
:Telegram: @shikret07
@natiTg2
@DBU11
@DBU111
ለአዲስ ገቢ ሴት ተማሪዎች በሙሉ
ዛሬ ማለትም ማክሰኞ 24/03/2017 ልዩ የሴት ተማሪዎች ውይይት በሴቶች ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ተዘጋጅቷል።
ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት በብሎክ 14 ሁላችሁም እንድትገኙ ጥሪ ተላልፏል።
የሴቶች ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ
@DBU11
@DBU111
🚨 Huge Announcement from Techtonic! 🚨
We’re beyond excited to introduce Techtonic Labs, the latest evolution of the Techtonic Tribe community!
Techtonic Labs is your new home for innovation—a space where Tribe members and bootcamp graduates can:
🚀 Work on real-world projects
🎯 Build original products
🤝 Collaborate on exciting opportunities
👉 Join official Labs channel To Apply : Join Here!
🖇 Join Our : Channel | Group | tech_tonic_tribe">Tik Tok | LinkedIn
ዛሬ ከ7:30 ጀምሮ ኦረንቴሽን ይሰጣል።
አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲያችን እንኳን ደህና መጣችሁ።
በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ እና በመማር ምስተማር ሂደት ዙሪያ ዛሬ አርብ 20/03/2017 ኦረንቴሽን ስለሚሰጥ በ7:30 በመመረቂያ አዳራሽ እምድትገኙ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ማስተባበሪያ ጥሪውን አስተላልፏል።
Join our channel | Join Our Discussion Group
❌ የተከለከሉ ስፍራዎች
ለነባር ተማሪዎች
አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ቅበላ ምክኒያት በማድረግ ብሎክ 1፣8፣9፣39፣40 መግባት የማይቻል መሆኑ ተገልፁአል።
@DBU11
@DBU111
2017 ለሚገቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ዶርም የሚያስረክቡ ሰራተኞች ስም እና ስልክ ቁጥር ዝርዝር
@DBU111
@DBU11
ለአዲስ ገቢ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች!
.
.
.
የደብረብርሃን ማህበረሰብ በባህሉ ሰው ወዳድ፣ እንግዳ ተቀባይ ማህበረሰብ ነው።
የምግቡን ነገር እንመልከት፦ ከካፌው ስንጀምር
የካፌው ምግብ ከአብዛኛው የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ካፌዎች ጋር ተመሳሳይ ነው። ነገር ግን የተለየ የጤና ችግር ያለባችሁ ከሆነና የህክምና ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ ከሆነ special cafe መመገብ ይፈቀድላችኋል። ከnormal cafe የተሻለ እዛ ይገኛል።
ከዛም በተጨማሪ በግቢው ውስጥ 3 lounge ታገኛላችሁ ዋጋቸውም ከ50-80 እንደምግብ አይነቱ ያወጣሉ። ከዛ በተሻለ እዛው ግቢ ውስጥ መገዘዝ እንዲሁም ማርካን የተባሉ የግል ካፌዎች አሉ። ዋጋቸውም ከ60-90 ያወጣሉ።
እነዚህም ተስማሚ ካልሆናችሁ ከግቢ አቅራቢያ የሚገኙ ግን ከግቢ ውጪ ምግብ ቤቶች አሉ። ዋጋቸውም በአማካኝ ከ70-120 እንደምግብ አይነቱ ያወጣሉ። በኮንትራት ከሆነ ደግሞ 10 ና 15 እንደየቤቱ ቅናሽ ያረጋሉ።
የአካባቢው የፀጥታ ሁኔታን ስንመለከት አሁን ላይ(ህዳር 2017)ከተማዋ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ስትሆን የባጃጅ አገልገሎት በከተማዋ ከ12 ሰዓት በኃላ አገልግሎት አይሰጡም። እንዲሁም ምንም አይነት መኪናዎች ከ2ሰዓት በኃላ አይንቀሳቀሱም። በተጨማሪም እግረኛ መንቀሳቀስ የሚችለው እስከ 4 ሰዓት ድረስ ነው።
ወደ እምነት ተቋማት ስናልፍ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንና ገዳማት በዩኒቨርስቲው አቅራቢያ ለማግኘት በጣም ቀላል ነው። እንዲሁም ከግቢው በስተጀርባ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዬች ቤተክርስቲያን እናም ለእስልምና እምነት ተከታዮች መስኪድ አሉ።
መልካም የትምህርት ዘመን!😊
@DBU11
@DBU111
#AD
እማዬ ሾርባ እና እስቲም ቡና ::
እንደተለመደው ጥራቱን የጠበቀ በተመጣጣኝ ዋጋ
የአጃ ሾርባ
የአትክልት ሾርባ(ministrone)
እስቲም ቡና
አዲስ ሻይ
ሞርንጋ ሻይ
ግሪን ሻይ
ሚንት ሻይ
ከሞሜላ ሻይ
ብላክ ሻይ ወ.ዘ.ተ
ድንች ቅቅል
ድንች ቅቅል በአቮካዶ
እንቁላል ቅቅል
እና ሌሎችንም ከ ነፃ WIFI ጋር እኛ ጋር ያገኛሉ ።
አድራሻ ዩኒቨርሲቲ በር ከአልሚ ምግብ ቤት ጎን።
አማራጮችን ተጠቀሙ
በኖርኩበት 5 ዓመታት የግቢ ቆይታ ከሰዓታት ያለፈ የውሃ ችግርን አስተውዬ አላውቅም።
ዩኒቨርሲቲያችን ያልለመደበትን ውሃ ተቋርጦበታል።
እንደ አማራጭ
የህግ ኮሌጅ አካባቢ
pr አዳራሽ ላውንች ስር
ሶሻል ላይብረሪ አካባቢ ያሉት ቧንቧዎች ጋር ችግሩ እስኪቀረፍ መጠቀም ትችላላችሁ።
የውሃ አቅርቦቱ እስከ ንጋት ድረስ ሊፈታ እንደሚችል ከተማሪዎች ህብረት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
@DBU11
@DBU111
ለደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ ዘናጭ ተማሪዋች በሙሉ
StayleAura Collection በማይታመን ቅናሽ ዋጋ ጥራት ያላቸው ልብሶችን ከ 300 ብር ጀምሮ ከነፃ Delivery አገልግሎት ጋ ይዞላችሁ ቀርቧል።
ይደውሉ ያሉበት እናደርሳለን
+251710754440
+251946178499
Contact us
@Mworkacc
@Birhansg
@mulushimels
Telegram channel
Join በማረግ ይዘዙን ያሉበት እናደርሳለን
👇👇👇👇👇👇
/channel/StyleAuraCollection
𝑬𝑻𝑺𝑼𝑩 𝑭𝑰𝑵𝑫𝑺 𝑶𝑵𝑳𝑰𝑵𝑬 𝑺𝑯𝑶𝑷𝑷𝑰𝑵𝑮 🛍
ሰላም 👋 እንዴት ናቹህ 🤗
Trendy እንዲሁም BEST 🗣 አልባሳት ጫማ ሁዲ ቲሸርት ሽቶ Human hair ኤሌክትሮኒክስ ..... 🥵 ብቻ ምን አለፋቹ የምትፈልጉት ሁሉ በእጃችሁ በደጃቻቹህ
ከእናንተ የሚጠበቀው ኢችን ጠቅ
👇👇👇👇
/channel/etsubfindsonlineshop
👆👆👆👆
ሁሉም በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ ቤተሰብ ይሁኑን
ቤተሰብ +
/channel/etsubfindsonlineshop
መልካም ቀን 🙌
🚀 Join TechtonicTribe’s Opening Event at Debre Birhan University!
This Saturday, we’re launching a new chapter for tech enthusiasts and innovators. Join us as we explore fresh opportunities, connect with like-minded peers, and embark on a community-driven journey into the future of tech!
📅 Date: 7/03/2017
⏰ Time: 2:00 PM - 5:30 PM
📍 Location: PR hall, DBU
🎙️ Speakers: Meet inspiring industry leaders, including
Bereketab H/eyesus,
Amare Terefe,
and Abrham Assefa!
Be part of something bigger. Let’s code the future together! 🌍💻
🖇 Join Our : Channel | Group | tech_tonic_tribe">Tik Tok | LinkedIn
ማስታወቂያ
የደ/ብ/ዪ/ አንደኛ አመት ተማሪዎች በሙሉ፡፡
የላይፍ እስኪል ስልጠና ስለሚሰጥ በቀን 28/3/2017 ከጠዋቱ 2.30 በመመረቂያ አዳራሽ እንድትገኙ ስንል እንገልፃለን፡፡
የሴቶችናማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራአስፈፃሚ፡፡
@dbu111
@dbu11
#ADVERTISING
◍ 📣 እንኳን ደህና መጡ 📣 📣 📣
🌴ጉሊት ገበያ 🌴🌴
/channel/aronium0224
/channel/gulitgebeya02
የተለያዩ የሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ ምርት የሆኑ መዋቢያዎችንና መገልገያዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ይሸምቱ
✨ የተለያዩ ንፅህና ውበት መጠበቂያዎች
🌴ማንኛውም በሃኪም የሚታዘዙ የ ቆዳና የፀጉር መጠበቅያዎች አሉን
🌴 ኦሪጅናል የ ቆዳ ውበት መጠበቅያ
-የብጉር ፣ ጠባሳ ፣ማድያት ማጥፊያ
🌴 የ ፀጉር ማሳደግያና ውበት መጠበቅያ በኦይል፣ስፕረይና በ ክሬም
🌴ቋሚ የ ፎፎርና የሽበት ማጥፊያ
🌴የተለያዩ የሰውነት ክብደት መጨመርያና መቀነሽያ ሰፕልሜንቶች አስገብተናል
እኛ ጋር ከመጡ ማንኛውንም ዕቃ ያገኛሉ
👣 ሁሉም ምርቶቻችን ኦሪጅናል ናቸው
አድራሻ ፦ ደ/ብርሃን ጠባሴ ዩንቨርስቲ ሰፈር
👣ከ ደ/ብ ውጭ ለክልል ከተሞች በ ወኪሎቻችን በኩል እናደርሳለን
ይደውሉልን☎️0931648720
☎️0716518723
🗣🗣ለጥያቄ ያናግሩን @aroncoin7
ቴሌግራም
/channel/aronium0224
/channel/gulitgebeya02
ለአጭር ጊዜ ብቻ የሚቆይ ቅናሽ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ለማንኛውም አገልግሎት (Verification Access) መዋል የሚችል ኦርጂናል ህትመት
በሽክረት ህትመትና ማስታወቂያ ድርጅት መጥተው ህትመት ሲያሰሩ እስከ ህዳር ወር መጠናቀቂያ ብቻ የተማሪ መታወቂያችሁን በማሳየት ለተማሪ በተደረገው ቅናሽ
ኦርጂናል በ250 ብር እንዲሁም
ዲጂታል ኮፒ 100 ብር
ብቻ የቅናሽ አገልግሎታችን ተጠቃሚ ይሁኑ።
አድራሻ - ደብረብርሃን ከተማ ስላሴ ቤተክርስቲያን/ ኬር ቁርጥ አጠገብ
ለበለጠ መረጃ 0940219376 ይደውሉ
Telegram @natiTg2
ሽክረት ዲዛይን፣ህትመትና ማስታወቂያ ድርጅት
@DBU11
@DBU111
የላይብረሪ ጉዳይ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ደርሷል
በጉዳዩ የላይብረሪ ባለድርሻዎችና የተማሪ ህብረት ጽ/ቤት በቀን 12/03/2017 ምክክር አድርገውበታል።
በዚህ ምክክር እስካሁን ድረስ በተማሪም ሆነ በሰራተኛ ሲፈጠሩ የነበሩ የቤተ-መፃህፍት ህግና ደንብ የጣሱ ክፍቶች በያዝነው የትምህርት ዘመን እንደማይኖሩ እንዲሁም ለመማር ማስተማር ሂደቱ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንደሚወታ ስምምነት ላይ ተደርሷል ።
በዚህ ጉዳይ የኛ ቻናል ጋዜጠኞች ከተማሪ ህብረት አካላት ጋር በመሆን በሃላፊነት ካሉ ሰዎች ጋር ባሳለፍነው ዓመት በተመሳሳይ መልኩ ስምምነት ላይ ደርሰን እንደነበር ይታወቃል።
በየአመቱ የስነምግባር ስምምነት የውልድ እድሳት የሚፈልግ አይመስለኝም። ቦታው የፀጥታና ለጥናት ምቹ መሆን ያለበት ስፍራ ነው። በትኩረት ሊሰራበት ይገባል።
ይህን እና መሰል ለተማሪ ምላሽ ያልተሰጠባቸውን ጥያቄዎች ይዘን እንመለሳለን!
@DBU11
@DBU111
እንኳን ደህና መጣችሁ!
ከዛሬ ቀን 17/03/2017 ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲያችን ለምትቀላቀሉ አዲስ ገቢ ተማሪዎች እንኳን ደህና መጣችሁ!
ውድ ተማሪዎች
በጉዞ ሂዲት እንደባለፉት ዓመታት ተማሪዎችን የሚቀበል በዩኒቨርሲቲው የተመደበ መኪና አለመኖሩን አውቃችሁ ከአጭበርባሪዎች ራሳችሁን እንድትጠብቁም በዚሁ አጋጣሚ ልንገልፅ እንወዳለን!
@DBU11
@DBU111
ለአዲስ ገቢ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች!
ደብረ ብርሃን ምን አይነት ጊቢ ነው? የከተማው አየሩ ፀባይስ? እውነት እንደሚባለው ቀዝቃዛ ነው? ማህበረሰቡስ? ምግብስ የጊቢውና የውጪው እንዴትነው? ዋጋውስ? የአካባቢው ጊዜያዊ ፀጥታ ሁኔታ? የእምነት ተቋማት አሉ ወይ? እያላችው እያሰባችሁ እንደሆነ አንጠራጠርም ።
እነዚህን ጥያቄዎች DBUDAILY ከሞላ ጎደል ሊመልስላችሁ ወደደ።
ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ በ1999ዓ.ም ከተቋቋሙት ሁለተኛ ትውልድ አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ነው። ግቢው አሁን ላይ በሁለት ካምፓስ (ጤና ካምፓስ እና ዋና ካምፓስ ) ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል።
በግቢው ውስጥ 3 ላይብረሪዎች አሉ። የሴቶች ላይብረሪ /ለሴቶች ዶርም በጣም ቅርብ የሆነና ብዙ ጊዜ በሴቶች ተመራጭ ላይብረሪ ነው።/፣ከበደ ሚካኤል ላይብረሪ (የsocial ተማሪዎች ላይብረሪ በመባል ይታወቃል።) ፣ተስፋገብረስላሴ ላይብረሪ (ዋና ላይብረሪ) በስፋቱም በይዘቱም ከሌሎቹ
የተሻለ ነው።
ይቀጥላል ...
@dbu11
@dbu111
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 9/2017 እስከ ህዳር 12/2017 ዓ.ም በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሃምሳ አራት ለሚደርሱ መምህራንና ለቤተ መጽሃፍት ሰራተኞች የተመሳሳይነት ማረጋገጫ (Turnitin plagiarism / similarity checker) ሶፍተዌር ስልጠና ሰጥቷል፡፡
ስልጠናው የረጅም አመት ልምድ ባላቸው የቴክኖሎጅ ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን በስልጠናው ድህረ ምረቃ መምህራን(አሰልጣኞች)፥ተመካሪ ተማሪዎች ያላቸው መምህራን(research advisor) እና የቤተመፅሐፍ ሰራተኞች ተሳትፈዋል።
ከአዲስ አበባ በመጡ ምሁራን የተሰጠው ይህ የ software ቴክኖሎጅ ስልጠና የተማሪዎች የመመረቂያ ጽሁፍ ኩረጃን በተወሰነ መልኩ ለማስቀረት፤የምርምር ማእከሉን ለማዘመን ፤ ጥራት ያላቸው በርካታ መጽሃፍትን የሚጠቀሙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለማፍራት እና በአለም አቀፍ ጥራት ያላቸው መጽሃፍት ማሳተምና ለውድድር የማብቃት ግንዛቤን የሚያስጨብጥ ጠቀሜታ እና አላም እንዳለው ተገልጿል።
ሰልጣኞች ከላይ የተጠቀሱትን እና ተጨማሪ ግንዛቤዎችን እንዳገኙ መናገራቸውን ዩንቨርስቲው በ ይፋዊ ማህበራዊ ሚድያ ገፁ ገልጿል።
@dbu11
@dbu111
ችግሩን ለመቅረፍ እየተሰራ ነው
ዉድ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በሙሉ ዛሬ በቀን 12/03/17 ዓ.ም በግቢያችን ውስጥ የውሀ አገልግሎት መቋረጡ ይታወቃል ይህም የተፈጠረው የዩኒቨርስቲው የዉሀ ጉድጓድ ብልሽት ስላጋጠመው በመሆኑ ነዉ ፤ ዉሀዉ ከተቋረጠበት ጊዜ አንስቶ ባለ ሙያዎች የቻሉትን ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ተገንዝባችሁ እስከ ንጋት ድረስ በትዕግሥት እንድትጠብቁን እና የተለመደው ትብብራችሁ እንዳይለየን በትህትና እንጠይቃለን።
የተማሪ ህብረት ጽ/ቤት
@DBU11
@DBU111
🎉 A Day to Remember at Techtonic Tribe 2017! 🎉
The energy, the innovation, the incredible connections—we’re still buzzing from today’s opening event! 🚀
From insightful discussions to inspiring moments, your presence made it all extraordinary. 💡
Check out some snapshots from the day below! 📸
Let’s keep this momentum going all year long!
#TechtonicTribe2017 #EventHighlights #TechInnovation
🖇 Follow Us On : Channel | Group | tech_tonic_tribe">Tik Tok | LinkedIn | Instagram
የህግ ተማሪዎች ቅሬታ
እኛ የ2013 ባች የህግ ተማሪዎች አሁን በያዝነው የትምህርት ዘመን (2017) ዓ.ም የህግ ትምህርት (LL. B curriculum) ትምህርታችንን እንደምናጠናቅቅ እናውቅ የነበረ እንዲሁም ቃል ተገብቶልን የነበረ ሲሆን ይህንንም ከዳር ለማድረስ በ 2015 የትምህርት ዘመን ሶስት ሴሚስተር፤ በ 2016 ደግሞ ከ የካቲት 23- ሰኔ 27 ባሉት አራት ወራት ሁለት ሴሚስተር ወስደን ያጠናቀቅን ሲሆን ፤ በተጨማሪም ለዚህ ይረዳን ዘንድ ባለፈዉ የክረምት ወቅት የመመረቂያ ፅሁፍ (Research) ተሰጥቶን በማጠናቀቅ ላይ እንገኛለን።
ይህ በእንዲህ እንዳለ እኛ ተማሪዎች ለመውጫ ፈተና እራሳችንን በስነልቦና እያዘጋጀን በምንገኝበት በዚህ ወቅት የፈተናም ሆነ የመመረቂያ ጊዜያችን ወደ ጥር 2018 የተራዘመ እንደሆነ ተነግሮናል
፤ በመሆኑም ይህ የፕሮግራም መቀየር እና ቃል የተገባልን የጊዜ ሠሌዳ አለመተግበሩ ለከፍተኛ እና ተደራራቢ ችግርች ተጋላጭ ያደርገናል ፤ ከነዚህም መካከል፦
1ኛ. እኛ የህግ ተማሪዎች ከህግ ትምህርት ቤት ተመርቀን ስንወጣ ወደ ስራ ለመግባት የምንወስደው የፌደራልም ይሁን የየክልሎቹ የፍትህ ቢሮዎች የሚያወጡት የዳኝነት ስልጠና (judicial training) መውሰድ የምንችለው እና ማስታወቂያ የሚወጣው በየአመቱ መጀመሪያ በመሆኑ ይህ ውሳኔ ስልጠናውን የምንወስድበትን ጊዜ በአንድ አመት በማራዘም ወደ 2019 ይወስደዋል። ከዚህም አለፍ ሲል በዛው አመት (2018) ለሚመረቁ ተማሪዎች ቅድሚያ የመወዳደር እድል የሚሰጥ በመሆኑ የአመታት ልፋታችን ውጤት ለፍሬ እንዳይበቃ ያደርገዋል ፤ ይህም ምን ያህል ኢኮኖሚያዊና ስነ ልቦናዊ ጫና እንደሚያስከትል እሙን ነው።
2ኛ. ከላይ ከተዘረዘሩት ነጥቦች በተጨማሪ የመውጫ ፈተና (exit exam) ላይ ከሚመጡ ኮርሶች ውስጥ የቀሩን ሁለት ብቻ ሲሆኑ እነሱንም አሁን ባለንበት ሴሚስተር በማካተት ለፈተናው ዝግጁ ማድረግ መቻሉ እና በ2018 ጥር ወር ላይ ለመመረቅ በየጊዜው ከሚያገረሸው የሠላም እጦት የተነሳ በየትኛው ወር ላይ ጥሪ እንደሚደረግልን አለመታወቁ ውድ ጊዜያችንን ከማራዘም (ከማቃጠል) ውጭ ከዚህ የተሻለ ጊዜ እንደማይኖረን አመላካች ነው።
3ኛ. ከእኛ ዩንቨርስቲ ጋር ተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሌሎች ዩንቨርስቲዎች ማለትም ደብረ ማርቆስ፥ ወሎ፥ ፥ ጎንደር ፥ ደባርቅ እና ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የኛ ባች (2013 entry) ተማሪዎችን ለማስመረቅ የሚያስችል ፕሮግራም አውጥተው ተማሪዎቻቸውን በማስተማር ላይ ይገኛሉ። ይህም ከሌሎች አቻዎቻችን ጋር እኩል ወደ ስራው አለም የምንቀላቀልበት እና ላሉት ውስን ክፍት የስራ ቦታዎች እኩል ተወዳዳሪ እንዳንሆን በማድረግ ለኛም ፥ ላስተማረን ቤተሰብም ሆነ ማህበረሰብ ውሳኔው እጅግ ተስፋ የሚያስቆርጥ አድርጎታል።
ከላይ ከተዘረዘሩት ነጥቦች እና ከሚያስከትሏቸው ተጓዳኝ ችግሮች በመነሳት ይህንኑ ጥያቄ ለሚመለከተው የዩኒቨርስቲው አካል ማለትም ለ ፕሬዘዳንት ፅ/ቤት እና ለዩኒቨርስቲው ሴኔት በዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ህብረት እና በዩኒቨርስቲው የህግ ማህበር በኩል ያቀረብን ቢሆንም አጥጋቢ ምላሽ ሳናገኝ ቀርተናል። በመሆኑም የሚመለከታቸው የዩኒቨርስቲው አካላት ተማሪዎችን በማወያየት እና ሌሎች መሰል ዩኒቨርስቲዎች እየተከተሉ ያሉትን አስቻይ ሁኔታዎች በአፅንኦት በመመልከት እንዲሁም የደረሰብንን እና ሊደርስብን የሚችለውን ከባድ ጉዳት እና ጫና ከግምት ውስጥ በማስገባት ውሳኔውን በድጋሚ እንዲመለከቱት ስንል በትህትና እንጠይቃለን።
@DBU11
@DBU111
የተሳሳተ መረጃ
የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ መደበኛ እና ሬሚዲያል ተማሪዎችን በተመለከተ እየተዘዋወረ ያለው የጥሪ ማስታወቂያ ትክክለኛ አለመሆኑን እንድታውቁ እና ጥሪ በሚደረግበት ጊዜ በዚሁ ገጽ የምናጋራ መሆኑን እንገልፃለን።
@DBU11
@DBU111
ለወንድ ተማሪዎች በሙሉ የተማሪዎች መኝታ አገልግሎት (students dormitory service) ባወጣው ማስታወቂያ ማንኛውንም አገልግሎት( i.e የመውጫ ፈቃድ ወረቀት )የተማሪ ህብረት ህንፃ ኮሪደር (ground) ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት እንደምትችሉ ገልፃጿል።
@DBU11
@DBU11
ትልቅ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ዕድል በዩኒቨርስቲአችን!
የእንግሊዝኛ ቋንቋችሁን ማዳበር የምትፈልጉ ተማሪዎች በግቢያችን ደብረ ብርሃን የEnglish language improvement center (ELIC) ያዘጋጀው የውይይት፣ንባብ፣ፅሁፍ እንዲሁም የተለያዩ የቋንቋ ችሎታን የሚያዳብሩ ነገሮች ላይ እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
የምዝገባ ቦታ= SE02 F1 ELIC OFFICE
የምዝገባ ጊዜ =ከህዳር 2-21-2017/በሁሉም ስራ ቀናት
@dbu11