Youtube https://youtu.be/_0l6c0I7ouM 👉ስለ ግቢው ወቅታዊ መረጃ 📌ዲፓርትመንቶች ፡⚽️ስፓርት፡🎤ኪነጥበብ ምሽቶች ፡📄የጊቢ ማስታወቂያ ፡ ምልከታወችና ታሪክ ወግ ፡📷📷አስገራሚ ፎቶወች ፡ እውነታዎች እና መረጃወች📃 መፀሀፍት ፡ ሳይኮሎጂ ሁሉም ይዳሰሱበታል:: Contact
ሀገር አቀፍ የደም ልገሳ
ተስፋ አዲስ የካንሰር ሕሙማን ማዕከል ለሚገኙ ሕፃናት በሀገራችን በ20 ከተሞች ጥር 24 እና 25 2017 ዓ.ም 7ኛው ዙር የደም ልገሳ ፕሮግራም ይካሔዳል።
በከተማችን ደብረብርሀንም ቅዳሜ ጥር 24 2017 ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ለ2ኛ ዙር በከተማው በሚገኘው ደም ባንክ የልገሳ መርሀ ግብሩ ይደረጋል።
ስለሆነም ለግቢያችን ተማሪዎች እና ሰራተኞች በሙሉ የተስፋ አዲስ ቤተሰብ "ኑ በደማችን ታሪክ እንፃፍ የህፃናቱን ሕይወት እንታደግ" እያለ ጥሪውን ያቀርባል።
ለተጨማሪ መረጃ
0942169900
0913314264 ይደውሉ
@dbu
ለሬሚዲያል ተማሪዎች ጥሪ ተላልፏል 👆👆👆
የተመደባችሁበትን ግቢ ለማወቅ ማስታወቂያው ላይ የተገለፀውን ሊንክ ተጠቀሙ ።
tinyurl.com/dbu-rcp-2017
ለጓደኞቻችሁ ሼር አድርጉላቸው
@DBU11
@DBU11
በትላንትናው ዕለት የሆሄ ተስፋ የኪነ ጥበብ ቡድን የዓመቱ ሁለተኛ መድረኩን በደማቅ ሁኔታ አቅርቦ ዋለ።
የግቢያችን ብቸኛው የኪነጥበብ ቡድን ሆሄ ተስፋ የሁለተኛ መርሀ ግብሩን ለ18/05/2017 አሰናድቶ መጨረሱን አስታውቆ ለ19/05/2017 ማራዘሙ የሚታወስ ሲሆን በቀጠሮው መሰረት በትላንትናው ዕለትም እንደተለመደው ግጥም፥ ሙዚቃ፥ ተውኔት እና ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ የነበረው የውዝዋዜ ቡድን በአዲስ መልክ ስራ ጀምሮ የምጀመሪያ የመድረክ ስራውን አሳይቷል።
@dbu11
@dbu111
ማስታወቂያ:
ለደብረብርሃን ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በሙሉ
የ True Culture University Essay ውድድርን ይቀላቀሉ እና በፓን አፍሪካኒዝም ላይ ያለዎትን ግንዛቤ ያካፍሉ! የማሸነፍ እና የእውቅና እድል ለማግኘት እስከ አርብ ጥር 23 ድረስ ድርሰትዎን ያቅርቡ። እንዳያመልጥዎ - ለመሳተፍ ዝርዝሮችን እና መስፈርቶችን ይመልከቱ!
ፅሁፋን በ truecultureuniversity1@gmail.com ይላኩ
@dbu11
@dbu111
ዝግጅታችንን ጨርሰናል
ጥራትና ውበት ያላቸውን ባይንደሮች ሁሉንም ባማከለ ዋጋ ከ250 ብር ጀምሮ ከሽክረት ህትመትና ማስታወቂያ
በግልና በቡድን ማዘዝ ይችላሉ
ለበለጠ መረጃ
Telegram: @SHIKRET007
Phone: 0940219376
@DBU11
@DBU111
Notice
የፕሮግራም መተላለፍ !!
ሆሄ ተስፋ የኪነ-ጥበብ ቡድን በዚህ አመት ሁለተኛ ተወዳጅ የኪነ- ጥበብ ስራዎችን ሊያቀርብላችሁ ዝግጅቱን ጨርሶ ፕሮግራሞች ያቀርባል ተብሎ ታስቦ የነበረ ቢሆንም በግቢው ውስጥ ባጋጠመ የመብራት አለመኖር ምክንያት ፕሮግራሙ ለነገ 10 ሰዓት መተላለፉን ስናሳውቅ ከታላቅ ይቅርታ ጋር ነው፡፡
“ሆሄ ተስፋ የኪነ-ጥበብ ቡድን”
@DBU1
@DBU111
የመውጫ ፈተና እንደመድረሱም
Gemini
Copilot
ብዙዎቻችሁ ታውቋቸዋላችሁ የሚል ግምት ይኖረኛል። AI bot ናቸው።
ልዩነታቸው Copilot Creative bot ሲሆን ነገሮችን በራሱ አስቦ(ፈጥሮ) ሊመልስ ይችላል።
Gemini ደግሞ Analysis Bot በመሆኑ ነገሮችን ከያሉበት ቀራርሞ መልስ ያዘጋጃል።
ሁለቱም የየራሳቸው ድክመት አላቸው።
የፈተናው ጊዜ እንደመቅረቡም አሁን ጥያቄዎችን መዘጋጀት ይበልጥ ውጤታማ የሚያደርግ ይመስለኛል።
ሌላው እንደግል የምጠቁማችሁ ነገር ቢኖር ሞዴል ፈተና ላይ እና የዚህን ዓመት ፈተና እንደየዲፓርትመንታችሁ ከየትኛው ግቢ እንደሚወጣ በማጣራት ይበልጡን የዚያን የሞዴል ጥያቄዎች ብትሰሩ ይመረጣል።
መልካም የጥናት ጊዜ
@DBU11
@DBU111
የተማሪዎች ባይንደር ጨረታን በተመለከተ
የዘንድሮን አመት የባይንደር ስራ ማህሌት ህትመት (አዲስ አበባ) ጨረታውን በ300 ብር አሸንፏል።
በባለፈው ዓመት እና ከዚያ በፊት ያሉትን ዓመታት የዩኒቨርሲቲውን ባይንደር ሲሰራ የነበረው ካርል ማተሚያ ቤት (አዲስ አበባ) የ2016 ዓም ባይንደርን በጥራት ባለመስራቱ እና በወቅቱም ባለማድረሱ በጨረታው ሊሳተፍ አልቻለም።
የተማሪን አቅም ባገናዘበ ዋጋ በሽክረት ህትመትና ማስታወቂያ ማሰራት የምትፈልጉ ክታች የሚገኙትን አድራሻዎች መጠቀም ይችላሉ።
@shikret007
ወይም 0940219376
@DBU11
@DBU111
#well go DBU
በዛሬው ዕለት የዩንቨርስቲያችን (ደብረብርሀን ዩንቨርስቲ) የተማሪዎች ስፓርት ልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዩንቨርስቲ አስተናጋጅነት በሐገር አቀፍ የመንግስት ዩንቨርስቲዎች መካከል ለሚደረገው ስፓርታዊ ውድድር ወደ አዲስ አበባ አቅንቷል።
ሁሉም የመንግስት ዩንቨርስቲዎች ስፓርታዊ ውድድር ፌስቲቫሉ በሚያካትታቸው ስፓርቶች በሩጫ ከ100 -3000 ሜትር ፥በ ወንዶች እግርኳስ፥በ ወርልድ ቴክዋንዶ ፥ በባህላዊ ስፓርት እና ቼዝ የሚፋለሙ ነው የሚሆነው።
ውድድሩ ከ ጥር 17-27/05/2017 ዓ.ም ለተከታታይ 10 ቀናት ይካሔዳል ለዩንቨርስቲያችን ስፖርት ልዑክ መልካም ዕድል ተመኝተናል ሁላችንም በcomment መስጫ ሳጥን መልካም ምኞታችንን እናድርሳቸው ሰናይ ጊዜ ይሁንላችሁ።
@DBU11
@DBU111
📌ባይንደር ሪቫን እና መፅሔት
ደረጃውን የጠበቀ የመመረቂያ ባይንደር ሪቫንና መፅሔት ከሽክረት ህትመትና ማስታወቂያ በተመጣጣኝ ዋጋ ይዘን ቀርበናል።
📍ልምንሰራው ስራ ሙሉ የጥራት ዋስትና እንሰጣለን
በምትፈልጉት የጥራት እና የህትመት ደረጃ በግል እና በቡድን እናስተናግዳለን።
📌የአንድ ባይንደር ዋጋ 250 ብር ብቻ
ሪቫን ከ150 ብር ጀምሮ እስከ 300 ብር
yየመጽሔት ዋጋ በገጹ ብዛት ይወሰናል።
በባይንደሩ ላይ 👉 የግል ስም
👉ዲፓርትመንት
👉 የዩኒቨርሲቲው ስም እና ሎጎ
ይሰፍርበታል።
ሪቫን በተለያየ የህትመት እና የጨርቅ አማራጭ ይዘን ቀርበናል።
መፅሔት በሶፍት ኮፒ እና በሃርድ ፕሪንት እናዘጋጃለን።
በቅርቡ ደ/ብ ዩኒቨርሲቲ በር ላይ የሚገኘው ቢሯችን ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ
Telegram @shikret007
0940219376
0964765047
ወይም በዋና ቢሯችን በመምጣት ሊያገኙን ይችላሉ።
አድራሻ
ስላሴ ቤ/ክ ( ኬር ቁርጥ አጠገብ)
በመውጫ ፈተና ላይ ምንም የተቀየረ (የተራዘመ) ቀን የለም
የደ/ብ/ዩ/አካዳሚክ ዘርፍ በየካቲት ተመራቂዎች የፈተና ቀን ላይ ምንም ቅያሬ አለመደረጉን ገልፆ ተማሪዎች በቂ ዝግጅት እዲያደርጉ አሳስቧል።
@DBU11
@DBU111
የዲጂታል ላይብረሪ ማሳሰቢያን አውጥቷል።
በዚህ ወር የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና አስመልክቶ ኮምፒውተሮች ለፈተና ዝግጁ መደረግ ስላለባቸው ተማሪዎች በኮምፒውተሮች ላይ ያስቀመጣችሁት የግል ፋይል ካለ እንድትወስዱ ገልፁአል።
ዲጂታል ላይብረሪ
@DBU11
@DBU111
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2017 የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
DBUDAILY መልካም በዓል እንዲሆንላቹ ይመኛል።
@dbu11
@dbu111
#ማስታወቂያ
ከ ተማሪዎች ሙያ ማሻሻያ ማዕከል(CDC)።
ማዕከሉ በ Amref Health Africa/KEFETA ድጋፍ ለሚሰጠው የ ህይዎት ክህሎት ስልጠና የተመዘገባችሁ እና ተመዝግቦ ለመሰልጠን ፍላጎት ላላችሁ ተማሪዎች በሙሉ። የተያያዘውን የማስታወቂያ መልዕክት አንብቡ።
ለመመዝገብ ይኽንን ሊንክ ተጠቀሙ👉👇👇👇 https://courses.hetialliance.et/student.registration/
DBU11
DBU111
ጥምቀት [ደብረብርሃን]
የ2017 ዓም የጥምቀት በዓል በደብረብርሃን ከተማ ያሉ ሁሉም አድባራት በአንድ ቦታ እንደሚያከብሩ የሰሜን ሸዋ ሃገረስብከት ስራ አስኪያጅ መጋቢሃዲስ ነቅዓጥበብ አባቡ ገልፀዋል።
ከዚህ ቀደም በ2013 ዓም የሃገረስብከቱ ሊቀጳጳስ አቡነ ቀለሜንጦስ በዓሉ በአንድነት እንዲከበር ገልፀው የነበረ ቢሆንም በዓሉ ሲከበርበት የነበረው ዘርዓያዕቆን አደባባይ ለአድባራቱ ምዕመናን በበቂ ሁኔታ ስለማያስተናግድ ላለፉት ሁለት ዓመታት በዚህ መልኩ ሳይከበር ቆይቷል።
በመሆኑም ቤተክህነቱ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመነጋገር በቋሚነት ለጥምቀት በዓል ማክበሪያ በቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን አካባቢ 100ሺ ካሬ ሜትር ቦታ በመሰጠቱ የዘንድሮው የጥምቀት በዓል በከተማይቱ ያሉ አድባራት በአንድነት በመሆን የጥምቀት በዓልን ያከብራሉ።
@DBU11
@dbu111
ማስታወቂያ ከ ተማሪዎች ሙያ ማጎልበቻ ክበብ ለሁሉም የዩንቨርስቲያችን መደበኛ ተማሪዎች(Regular students) የፊታችን ቅዳሜ በቀን 24/05/2017 mindset,stress and time management በሚል ርዕስ በልዩ እንግዳ 2፡30 በመመረቃያ አዳራሽ ልዩ ስልጠና ይሰጣል።
@DBU11
@DBU111
ማስታወቂያ
ለAgricultur and FB college ለየካቲት ተመራቂዎች በሙሉ ከነገ ቀን 21/05/2017ዓ.ም ጀምሮ መውጫ ፈተና (exit exam)እስክትጨርሱ ድረስ ከድህረ ምረቃው(Post Graduate) ዲጂታል ላይብረሪ መጠቀም ትችላላችሁ ተብሏል።የደ/ብ/ዩ ቤተ-መፅሐፍትና ዲጂታል አግልግሎት ዳይሪክቶሬት ከተማሪዎች ህብረት አካዳሚክ ዘርፍ ተጠሪ ጋር በመሆን ሰለ ዲጂታል ላይብረሪ መጨናነቅ ተወያይቷል።ይህን መጨናነቅ አይቶ የተሻለ መፍትሄ ያለውን ለጊዜያዊም ቢሆን በሚለው ይህንን ሀሳብ ከጥቂት ማሳሰቢያዎች ጋር ይዞ መጥቷል።
ማሳሰቢያ
1.መጠቀም የምትችሉት ከጠዋቱ 1:30 እስከ ምሽቱ 2:30 ብቻ ነው
2. ሰባ Computers አሉ እነርሱ ከተያዙ መሰለፍም ሆነ እዛ አከባቢ መቀመጥ፣በቡድን ሆኖ ማውራት ተፈፅሞ የተከለከለ ነው
3. ID/መታወቂያ መያዝ የተጠበቀ ነው
4. የየካቲት ተመራቂ ብሎም ከሁለቱ ኮሌጆች ውጭ ለሌላው አልተፈቀደም
N.B :- "Exit exam" We have only six (6) days left!!!
"OUR REWARD IS STUDENTS HAPPINESS"
የደ/ብ/ዩ/ህ አካዳሚክ ዘርፍ ተጠሪ
NOTICE
ለሁሉም የግቢያችን ተማሪዎች በሙሉ ከትላንትናው እለት ጀምሮ መብራት መጥፋቱ ይታወቃል በመሆኑም የሲስተም ችግር ስለሆነ እስኪስተካክል ድረስ በትእግስት እንድጠብቁ ለማሳሰብ እንወዳለን።
የደ/ብ/ዩ/ተ/ህ ጠቅላላ አገልግሎት ዘርፍ
@dbu11
@dbu111
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ እግር ኳስ ቡድን የጋምቤላ አቻውን 1ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ
==========================
ዛሬ 3ኛ ቀኑን በያዘው የኢትዮጽያ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የስፓርት ፌስቲቫል በአቃቂ አድቬንቲስት ትም/ቤት ሜዳ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያውን ያደረገው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ እግር ኳስ ቡድን የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲን በናትናኤል አስራት ብቸኛ ግብ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፎ 3 ነጥብ ይዞ መውጣት ችሏል።
ናትናኤል ተቀይሮ ገብቶ ግብ ማስቆጠር የቻለ የተከላካይ መስመር ተጫዋች ነው። ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በነገው እለትም በተመሳሳይ ሰአት ወሎ ዩኒቨርሲቲን ካቻ መጫወቻ ሜዳ ላይ የሚገጥም ይሆናል።
@DBU11
@DBU11
እንኳን ደስ አላችሁ
============
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በወንዶች ቴኳንዶ ወርቅ አገኘ
=================================
ዛሬ ከሰአት በኋላ ከ80 ኩሎ በታች በተካሄደ የፍጻሜ የወንዶች ቴኳንዶ ውድድር ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ወርቅ አገኘ። በመጀመሪያ ማጣሪያ በፎርፌ ለፍጻሜ የደረሰው ፋሲል የሽዋስ ከሰአት በኋላ የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ታጋጣሚውን ተማም ሰኢድን በሁለት ዙር አሸንፎ ለደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያውን ወርቅ አምጥቷል። በትላንትናው እለትም በሴቶች ሀናን አብዲኑር የብር ሜዳሊያ ለቡድኗ ማምጣቷ የሚታወስ ነው።
@DBU11
@DBU11
ምላሽ (ከሽክረት ህትመት)
በዘንድሮ የባይንደር ህትመት ዙሪያ አንዳንድ ካሃላፊነት ውጪ በኮሚቴዎች እየተነሳ ላለው ስም ማጥፋት አንዳንድ ነገር ልል እገደዳለሁ።
የዘንድሮው የባይንደር ህትመት ለምን ሽክረት አልሰራም ተብሎ ለተነሳው ጥያቄ መልስ እንዲሆን አንዳንድ አካላት ያነሱት ምላሽ "የባለፈውን አመት ባይንደር በተሳካ ሁኔታ ባለማቅረቡ" የሚል ምላሽ ሲያቀርቡ ስለተመለከትኩ እውነታውን እንድታውቁት እወዳለሁ።
የባለፈውን አመት ባይንደር ያዘጋጀው ካርል ህትመት ድርጅት ይባላል። የተወሰኑ ስራዎችን ለመስፈርትነት ከቀረቡት ማቴሪያሎች ውጪ ማቅረቡም ይታወሳል። ይህን ጉዳይ በጂሲ ኮሚቴ ተወካይነት ስንከታተል የነበርን የተማሪዎች ህብረት እና የጂሲኮሚቴ አባላት በሰዓቱ ባለቀ ሰዓት ማስቀየር የምንችለው ነገር ባለመኖሩ የተሰራውን እንደነበር ለተማሪዎች አቅርበናል።
በዚህ አባልነት ውስጥ የአሁን የሽክረት ህትመት ድርጅት ባለቤት እንደ አንድ ኮሚቴ አባል ተገኝቼበታለሁ። ካርልድ ህትመት ድርጅት ባጠፋው ጥፋት ከተከፈተ አመት እንኳን ያልሞላውን ድርጅት ስም(ሽክረት) ማያያዝ እንደ ስም ማጥፋት ወንጀልም ስለሚቆጠር በዚህ ያልተገባ ድርጊት ውስጥ የምትገኙ አካላት ለሽርፍራፊ ጥቅም ብላችሁ ችግር ውስጥ ባትገቡ እመክራለሁ።
እናም በድርጅታችን ለሚሰሩ ማንኛውም የህትመት ስራዎች ሙሉ የጥራት ዋስትና የምንሰጥ መሆኑንና ያለመስፈርት የተሰሩ ስራዎች ኪሳራ ቢፈጠር ሙሉ በሙሉ የምንሸፍን መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለመግለፅ እወዳለሁ።
ሽክረት ህትመት
@DBU11
ማስታወቂያ
========
ቀን 16/05/2017
ለመ/ሜዳ ካምፓስ በተለያዩ የሥራ መደቦች ላይ ተወዳድራችሁ ከ70% የጽሑፍ ፈተና ወስዳችሁ 35 እና በላይ ውጤት ያመጣችሁ ቃለ መጠይቅ በ17/05/2017 ስለሚሰጥ በዋናው ግቢ ጧት 2:30 በብቃትና ሰው ሀብት አስተዳደር ቢሮ እንድትገኙ እናሳውቃለን፡፡
@dbu11
ታላቅ የኪነ- ጥበብ ምሽት ለኪነጥበብ አፍቃራያን
ሆሄ ተስፋ የኪነ-ጥበብ ቡድን በዚህ አመት ሁለተኛ ተወዳጅ የኪነ- ጥበብ ስራዎችን ሊያቀርብላችሁ ዝግጅቱን ጨርሶ በቀን 18/05/17 ዓ.ም በእለተ እሁድ ከቀኑ 8፡30 ጀምሮ በዕለቱ ግጥሞች፣ ወግ፣ በሙዚቃ፣ ውዝዋዜ የመፅሐፍ ጥቆማ እንዲሁም ሌሎች አዝናኝና አስተማሪ ፕሮግራሞች በዕለቱ ይቀርባሉ፡፡
“ሁላችሁም ተጋብዛችኋል”
“ሆሄ ተስፋ የኪነ-ጥበብ ቡድን”
@DBU1
@DBU111
#ማስታወቂያ 👆👆👆ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ለ ጥር እና ሰኔ ተመራቂ የኢኮኖሚ ድጋፍ ተጠቃሚ ተማሪዎች በሙሉ።
@DBU11
@DBU111
ባይንደር ሪቫን እና መፅሔት
ደረጃውን የጠበቀ የመመረቂያ ባይንደር ሪቫንና መፅሔት ከሽክረት ህትመትና ማስታወቂያ በተመጣጣኝ ዋጋ ይዘን ቀርበናል።
በምትፈልጉት የጥራት እና የህትመት ደረጃ በግል እና በቡድን እናስተናግዳለን።
በባይንደሩ ላይ 👉 የግል ስም
👉ዲፓርትመንት
👉 የዩኒቨርሲቲው ስም እና ሎጎ
ይሰፍርበታል።
ሪቫን በተለያየ የህትመት እና የጨርቅ አማራጭ ይዘን ቀርበናል።
መፅሔት በሶፍት ኮፒ እና በሃርድ ፕሪንት እናዘጋጃለን።
በቅርቡ ደ/ብ ዩኒቨርሲቲ በር ላይ የሚገኘው ቢሯችን ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ 0940219376
0964765047
ወይም በዋና ቢሯችን በመምጣት ሊያገኙን ይችላሉ።
አድራሻ
ስላሴ ቤ/ክ ( ኬር ቁርጥ አጠገብ)
ለሰኔ ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ
የፊታችን አርብ እና ቅዳሜ ማለትም በ 16 እና 17/05/2017ዓ.ም የደብረ ብርሀን ዩኒቨርስቲ ቱሪዝም ዲፓርትመንት ከከተማችን ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር በአይነቱ ለየት ያለ
የ Culture Day እና የ MICE EVENT ለማክበር ሽርጉዳቸዉን ጨርሰዋል ።
በመሆኑም ይህ “MICE EVENT’’ ፕሮግራም የ culture day ለማክበር አሪፍ አጋጣሚ ስለሚሆን ሁላችሁም የሰኔ ተመራቂ ተማሪዎች የባህል ልብስ በመልበስ የበዓሉ እና የፕሮግራሙ ተሳታፊ መሆን የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
👉በዚህም ዕለት ቁንጅት ፤ዕምር ፤ድምቅ ብላችሁ እንድትገኙ ተጋብዛቹአል.....
መልካም ቆይታ!
@DBU11
@DBU111
#AD
ክሪስፒ እርጥብ
የምርጦች ምርጥ የተባለለትን አቀራረብ ይዞ በልዩ ቅርፅ እርጥብ ማግኘት ይፈልጋሉ ?
🖊ስፔሻል እርጥብ (በእንቁላል ፣ ሠላጣ፣ አትክልትና ፣ካቻፕ)
🖊ኖርማል እርጥብ (በካቻፕ)
🖊ሻይ እንዲሁም ቡና እጅግ በሚማርክ መልኩ እናዘጋጃለን ።
📌በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲ ግቢ ድረስ እርጥብ ለምትፈልጉ ደንበኞቻችን Free delivery አዘጋጅተናል።
👉እንዳትሸወዱ በእርጥብ ቤታችን መተው ከተመገቡ በኋላ የሚሰጥ የfree card ዕድል አዘጋጅተናል፤ ዕድለኞች የተሰጣቸው Business card ላይ free የሚል ፅሁፍ ካገኙ ነፃ እርጥብ ከክሪስፒ ይኖራቸዋል።😄
የት ነው???🤔
ከዩኒቨርሲው ፊት ለፊት ከመስኪ ቡና እና ከአልሚ ምግብ ቤት መሃከል ላይ እንገኛለን።
ወይም
0901633031
0931512004 ይደውሉ።
@dbu11
@dbu111
# Cost sharing(ወጭ መጋራት)‼️
መንግስት በዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የወጪ መጋራት ክፍያ መጠን ጭማሪ ማድረጉ ተሰምቷል‼️
መንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች በወጪ መጋራት ፖሊሲ የሚከፍሉትን ክፍያ እስከ አምስት ዕጥፍ ገደማ አሳድጓል።
የወጪ መጋራት ክፍያ የተጨመረው፣ የአንድ ተማሪ የቀን የምግብ በጀት ከ22 ብር ወደ 100 ብር መጨመሩን ተከትሎ ነው ተብሏል። በአዲሱ ጭማሪ መሠረትም፣ ለአራት ዓመት የዩንቨርሲቲ ቆይታ አንድ ተማሪ ይከፍለው የነበረው ከ25 ሺሕ ብር የማይበልጥ ክፍያ ወደ 120 ሺሕ ከፍ ብሏል። 35 ሺሕ ብር ገደማ ይከፍሉ የነበሩት አምስት ዓመት የሚማሩ የህግ እና የምህንድስና ተማሪዎች ደግሞ ወደ 150 ሺሕ ብር አካባቢ እንዲከፍሉ ይደረጋል። ትምህርት ሚንስቴር አዲሱን የወጪ መጋራት ተመን ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገና ባይልክም፣ በቅርቡ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ መጠቀሱን አዩ ዘሐበሻ አስነብቦናል።
ምንጭ ፡- አዩ ዘሐበሻ
@DBU11
@DBU111
ጥምቀት [ደብረብርሃን]
የ2017 ዓም የጥምቀት በዓል በደብረብርሃን ከተማ ያሉ ሁሉም አድባራት በአንድ ቦታ እንደሚያከብሩ የሰሜን ሸዋ ሃገረስብከት ስራ አስኪያጅ መጋቢሃዲስ ነቅዓጥበብ አባቡ ገልፀዋል።
ከዚህ ቀደም በ2013 ዓም የሃገረስብከቱ ሊቀጳጳስ አቡነ ቀለሜንጦስ በዓሉ በአንድነት እንዲከበር ገልፀው የነበረ ቢሆንም በዓሉ ሲከበርበት የነበረው ዘርዓያዕቆን አደባባይ ለአድባራቱ ምዕመናን በበቂ ሁኔታ ስለማያስተናግድ ላለፉት ሁለት ዓመታት በዚህ መልኩ ሳይከበር ቆይቷል።
በመሆኑም ቤተክህነቱ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመነጋገር በቋሚነት ለጥምቀት በዓል ማክበሪያ በቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን አካባቢ 100ሺ ካሬ ሜትር ቦታ በመሰጠቱ የዘንድሮው የጥምቀት በዓል በከተማይቱ ያሉ አድባራት በአንድነት በመሆን የጥምቀት በዓልን ያከብራሉ።
@DBU11
@dbu111
#AD
ክሪስፒ እርጥብ
የምርጦች ምርጥ የተባለለትን አቀራረብ ይዞ በልዩ ቅርፅ እርጥብ ማግኘት ይፈልጋሉ ?
🖊ስፔሻል እርጥብ (በእንቁላል ፣ ሠላጣ፣ አትክልትና ፣ካቻፕ)
🖊ኖርማል እርጥብ (በካቻፕ)
🖊ሻይ እንዲሁም ቡና እጅግ በሚማርክ መልኩ እናዘጋጃለን ።
📌በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲ ግቢ ድረስ እርጥብ ለምትፈልጉ ደንበኞቻችን Free delivery አዘጋጅተናል።
👉እንዳትሸወዱ በእርጥብ ቤታችን መተው ከተመገቡ በኋላ የሚሰጥ የfree card ዕድል አዘጋጅተናል፤ ዕድለኞች የተሰጣቸው Business card ላይ free የሚል ፅሁፍ ካገኙ ነፃ እርጥብ ከክሪስፒ ይኖራቸዋል።😄
የት ነው???🤔
ከዩኒቨርሲው ፊት ለፊት ከመስኪ ቡና እና ከአልሚ ምግብ ቤት መሃከል ላይ እንገኛለን።
ወይም
0901633031
0931512004 ይደውሉ።
@dbu11
@dbu111