Youtube https://youtu.be/_0l6c0I7ouM 👉ስለ ግቢው ወቅታዊ መረጃ 📌ዲፓርትመንቶች ፡⚽️ስፓርት፡🎤ኪነጥበብ ምሽቶች ፡📄የጊቢ ማስታወቂያ ፡ ምልከታወችና ታሪክ ወግ ፡📷📷አስገራሚ ፎቶወች ፡ እውነታዎች እና መረጃወች📃 መፀሀፍት ፡ ሳይኮሎጂ ሁሉም ይዳሰሱበታል:: Contact
#developing story መሀል ሜዳ ካምፖስ
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ መሀልሜዳ ግቢ መምህራንና ሰራተኞች በተማሪዎች አቀባበልና መማር ማስተማር አጀማምር ዙሪያ ውይይት አደርገዋል ።
@DBU11
@DBU11
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ የተከታታይ ጤና ሙያ ማጎልበቻ ስልጠና (CPD) ዕውቅና ሰጪ ተቋም ሆኖ በድጋሜ ፈቃድ ማግኘቱን ቲክቫህ ዘግቦታል።
ካምፓሱ የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ አቅራቢዎች እና የስልጠና ኮርሶች ዕውቅና ሰጪ ተቋም (CPD Accreditor) ሆኖ እንዲያገለግል በድጋሜ ዕውቅና ከጤና ሚኒስቴር ማግኘቱን አሳውቋል።
በዚህም ካምፓሱ ለጤና ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት የሚያስችለው ሲሆን፤ ፈቃዱ ለሦስት ዓመት የሚቆይ መሆኑ ታውቋል።
በኢትዮጵያ ተከታታይ የጤና ሙያ ማጎልበቻ ስልጠና Continuing Professional Development (CPD) የሚሰጡ ከ250 በላይ ተቋማት እንዳሉ የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡
@dbu11
@dbu111
📌📌በእሳት አደጋው 13 ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል ።
በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር በመኪና ጋራዦች ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ የንብረት ውድመት ደረሰ።
ከለሊቱ 10:30 ገደማ የተነሳው እሳት 13 ተሽከርካሪዎችን ለውድመት ዳርጓል።
በእቴጌ ጣይቱ ክፍለከተማ አየማን መናፈሻ አቅራቢያ የነበሩ ሁለት ጋራዦች ላይ ነው የእሳት አደጋው የደረሰው። በአደጋው በጋራዦቹ ውስጥ ቆመው የነበሩ ተሽከርካሪዎች ናቸው ውድመት የደረሰባቸው።
የደብረ ብርሃን ከተማ እሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ታዬ ኀይለጊዮርጊስ የእሳቱ መነሻ ከጋራዦቹ ውስጥ ይሆናል ተብሎ የተገመተ ሲሆን አጠቃላይ መንስኤ እና የደረሰው ጉዳት ተጣርቶ ይገለፃል ሲሉ ለአሚኮ ተናግረዋል።
መረጃው የአሚኮ ነው
@DBU11
@DBU11
ማስታወቂያ ከተማሪዎች ሙያ ማሻሻያ ማዕከል ስልጠናውን አጠናቃችሁ ሰርተፍኬት ያልወሰዳችሁ ተማሪዎች በሙሉ👆👆👆👆
@dbu11
@dbu111
#AD
ምን ይፈልጋሉ? ምንስ ለመግዛት አስበው
አጥተዋል ?🤔🤔🤔
😊እንግዲያውስ Shop In DBU
የትም መሄድ እና ዞሮ መፈለግ😩ሳይጠበቅባችሁ 🤗
💁♀ የተለያዩ የሴት productochn ሙሉ በሙሉ
ማለት በሚቻል መልኩ
እንዲሁም 💁♂የወንድ ሽቶዎች
💪 ለ ጂም የሚሆኑ የውሃ ኮዳዎች
⏱ ብራንድ የ እጅ ሰዓቶች
😊 headset እና earpods
እንዲሁም የተለያዩ ዕቃዎችን....
ወደ እኛ የ ቴሌግራም channel ብቅ በማለት አልያም የሚፈልጉትን ወይም ያሻዎትን አማርጠው ኦርደር በማድረግ መሸመት ይችላሉ ስንል በታላቅ ደስታ ነው 🤗
💸ዋጋችን ተማሪን ያማከለ ስለሆነ ፈጥነው ይደውሉ 👇
ቴሌግራም channel 👉 @dbu_shoping or @Dbu_shopin
☎️ 0987393989
☎️ 0933261810
አልያም በ Inbox👉 { @hanlia228 ሊያገኙን ይችላሉ::
# መሀል ሜዳ ካምፖስ
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መሃል ሜዳ ካምፓስ ተማሪዎችን አቀባበልን ተከትሎ የመ/ሜዳና አካባቢው ነዋሪዎች ተማሪዎችን ለመቀበል ተዘጋጅተዋል ።
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መሃል ሜዳ ካምፓስ ግንባታው ተጠናቆ በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራው በማጠናቀቅ ከየካቲት 6 እስከ 7/2017 ዓ.ም ተማሪዎችን ተማሪዎችን ለመቀበል የቅድመ ዝግጅት ስራውን አጠናቋል።
የታሪከ ባለቤት ፣እንግዳ ተቀባይነት፣ሰው አክባሪነት፣በፍቅር አዋቂነት የማይታማው የመንዝ ህዝብ እንኳን ደህና መጣችሁ ይላል ።
@DBU11
@DBU11
የፈተና ሰዓት ተቀይሯል
ነገ ማለትም አርብ ይሰጥ የነበረው የመውጫ ፈተና ሰዓት 5:30 ይሰጥ የነበረው ወደ 7:30 እንዲሁም 8:30 ይሰጥ የነበረው ወደ 10:30 ተሸጋግሯል።
@DBU11
@DBU111
ከመዲናዋ በ.135 ኪሎ ሜትር ርቀት እና ተመሳሳይ ከፍታ ላይ የሚገኙት ደብረብርሀኖቹ 2 🥇ወርቅ + 3 🥈ብር
ከ 49 ዩንቨርስቲዎች 8 ተኛ ደረጃ🏆 ምርጥ 10 ውስጥ በመግባት አጠናቀዋል።💪🙏
say well come back (ዘማች ሲመለስ) ድጋፋችሁን አሳዩአቸው፤ ብዙ ተማሪዎች ዳሸን ቢራ ድረስ ሔደው በመቀበል ወደ ግቢ እያመሩ ነው ።
@dbu11
@dbu111
ከመዲናዋ በ135 ኪሎ ሜትር ርቀት እና ተመሳሳይ ከፍታ ላይ የሚገኙት ደብረብርሀኖቹ
2 ወርቅ🥇 + 3 ብር🥈💪🙏
ከ 49 ዩንቨርስቲዎች ስምንተኛ ደረጃ ። 🏆 ምርጥ 10 ውስጥ ገብተው አጠናቀዋል።
say well come back (ዘማች ሲመለስ) ድጋፋችሁን አሳዩአቸው ፤በዙ ተማሪዎች ዳሸን ቢራ ድረስ ሔደው ለመቀበል ወደዚያው እያመሩ ነው ።
ለመሃል ሜዳ ካምፓስ ለወጣው የቅጥር ማስታወቂያ የተወዳደራችሁ ውጤታችሁን ከዚህ በላይ ባሉት ምስሎች ተያይዘው ታገኛላችሁ።
@DBU11
@dbu111
ለተመራቂዎች
የወጪ መጋራት መረጃ ለማሟላት 2 ጉርድ ፎቶ ይዛችሁ እንድትቀርቡ የሬጅስትራል ጽ/ቤት አስታውቋል።
@dbu11
@dbu111
#EXITEXAM #Note
ከትምህርት ሚንስቴር ቴሌግራም ገፅ ያገኘነው መረጃ 👇👇👇
ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመራቸው ስራዎች አንዱ የሆነ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከጥር 26 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ይሰጣል።
🌀በፈተና ወቅት ከተፈታኝ ተማሪዎች ምን ይጠበቃል ?
👉🏾 ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ክፍል ሲመጡ ማንኛውም አይነት ስልክ፣ ስማርት ሰዓት ፣ ታብሌት ፣ ላፕቶፕና ... ወዘተ ተመሳሳይ ኤክትሮኒክ ቁሳቁስ መያዝ በፍፁም የተከለከለ ነው። (ይዞ የተገኘ ፈተናው /ውጤቱ ተሰርዞበት በቀጣይ ጊዜ እንዲቀመጥ ይደርጋል)
👉🏾 ፈተና ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት መፈተኛ ክፍል መገኘት አለባቸው ይህም ማለት ከጥዋቱ 2፡00 በፊት ፤ ከሰዓት ደግሞ ከ8፡00 በፊት ተፈታኞች መገኘት አለባቸው።
👉🏾 ተፈታኞች ለፈተና ሲመጡ ID መያዝ ያለባቸው ሲሆን User Name እና Password lower-case and upper-case ፊደላትን ለይተው በጥንቃቄ መያዝ አለባቸው።
👉🏾 ተፈታኞች ፈተና ከተጀመረ በኃላ ከ30 ደቂቃ በፊት ከፈተናው ክፍል መውጣት የለባቸውም።
👉🏾 ተፈታኞች ፤ ፈተናውን የሚያስፈትኑ መምህራን በሚያሳዩት ቦታ ብቻ መቀመጥ አለባቸው።
👉🏾 ሁሉም ተፈታኝ እንዲቀመጥ የተመደበበት የራሱ ኮምፒውተር ላይ ብቻ ተቀምጦ መክፈትና መጠቀም አለበት።
👉🏾 በፈተና ክፍል ውስጥ መነጋገር እና ከቦታ ቦታ መዘዋወር በፍፁም የተከለከለ ነው። እንዲሁም ማንኛውም ተፈታኝ ከጎኑ ያለውን ተማሪ ኮምፒውተር በፍፁም ማየት የለበትም።
👉🏾 ምንም ዓይነት ወረቀት ወደ መፈተኛ ክፍል ይዞ መምጣት አይቻልም።
👉🏾 ተፈታኞች በምንም ሁኔታ መኮርጅም ሆነ ማስኮርጅ ተግባር ላይ ቢሳተፉ እርምጃ ይወሰድባቸዋል።
👉🏾 ሁሉም ተፈታኞሽ ለፈታኝ መምህራንና ለአስተባባሪዎች መታዘዝ ያለባቸው ሲሆን የፈተናው ደንብ እና ስርዓት ተገዢ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
👉🏾 በድጋሚ ተፈታኞች የፈተና መግቢያ ትኬት (Exit Exam Entry Ticket) መያዝ ይጠበቅባቸዋል።
NB. ሁሉም ተፈታኞች ወደ መፈኛ ክፍል ተፈትሸው እንዲገቡ የሚደረግ ሲሆን ማንኛውም ተፈታኝ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በፍተሻ ወቅት ይሁን ሥርዓት ለማስያዝ በሚደረግ እንቅስቃሴ እንቅፋት ሆኖ ከተገኘ ከመፈተኛ አከባቢ እንዲገለል ተደርጎ በቀጣዩ የመውጫ ፈተና መስጫ ወቅት እንዲቀመጥ ይፈቀድለታል።
🌀 ከፈታኝ መምህራን የሚጠበቅ
👉🏾 የተፈታኝ ተማሪዎችን ID በአግባቡ በማረጋገጥ ወደ ክፍል እንዲገቡ ማደረግ ይጠበቅባቸዋል።
👉🏾 ተፈታኝ ተማሪዎችን በሥም ዝርዝራቸው መሠረት ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
👉🏾 ፈታኝ መምራህን የተማሪዎችን አቴንዳንሰ ይወስዳሉ ፤ ተማሪዎችን ፊርማ ያስፈርማሉ።
👉🏾 በፈተና ክፍል ውስጥ ደምጽ እንዳይሰማ፣ ተማሪዎች ከቦታ ቦታ እንዳይዘዋወሩ ተገቢውን ቁጥጥር ማድረግ አለባቸው።
👉🏾 የፈተናው አጠቃለይ ሂደት በትኩረት መከታተል አለባቸው።
👉🏾 በህመም ምክንያት ተማሪዎች ከክፍል መውጣት ቢፈልጉ ከሱፐርቨዘር ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን እርዳታ ያደርጋሉ።
👉🏾 ተማሪዎች በጎናቸው ያለውን ሌላ ኮምፒውተር እንዳይመለከቱ መቆጣጠር አለባቸው።
👉🏾 ተማሪዎች ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በፊት እንዳይወጡ መቆጣጠር ይጠበቅባቸዋል።
👉🏾 ሲኮርጂ ወይንም ሲያስኮርጅ የተገኘ ተማሪ ከመፈተኛ ክፍል እንዲወጣ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
👉🏾 ፈተናው ከጀመረ 15 ደቂቃ በኃላ የሚመጣ ተማሪ እንዲገባ ማድረግ የላባቸውም።
👉🏾 የፈተና አፈጻጸም ሪፖርት ለሱፐርቨዘር ማቅረብ
@dbu11
@dbu111
መልዕክት ከተማሪዎች ህብረት
ውድ ተማሪዎቻችን ሰሞኑን በተከሰተዉ የእንጀራ ብልሽት ይቅርታ እየጠየቅን ችግሩን ለማስተካከል ሲባል አዲስ ዱቄት ተፈጭቶ በአዲስ ተጋግሮ እንዲቀርብ ከፍተኛ ጥረት እያደረግን ስለሆነ ዛሬ ምሳ ሰዓት ዳቦ እንዲሁም እራት ሰዓት ላይ አዲሱን ቡኮ ተጋግሮ /አፍለኛ/ ከ አማራጭ ዳቦ ጋር ስለሚቀርብ ችግሩ እስኪፈታ ድረስ የቀረበዉን አማራጭ በቅን ልቦና እንድንጠቀምና ችግሩ እስኪፈታ በትዕግስት እንድትጠብቁን ስንል በትህትና እንጠይቃለን፡፡
የደ/ብ/ዩ/ተ/ህ ጽ/ቤት
@dbu11
@dbu111
"ኑ በደማችን ታሪክ እንፃፍ የህፃናቱን ሕይወት እንታደግ"
ብለው የተስፋ አዲስ ቤተሰቦች ባቀረቡት ጥሪ መሰረት ዛሬ የዩንቨርስቲያችን ተማሪዎች ደብረብርሀን ደምባንክ ተገኝተው ደማቸውን ለግሰዋል።
Tesfa Addis parents children cancer organisation ( TAPCCO) የሚገኙ ህፃናት በካንሰር ሕመም ተጠቅተው ከሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ተሰባስበው በማዕከል ውስጥ ሕክምናቸውን እየተከታተሉ ያሉ ህፃናት ናቸው። የደም ልገሳው በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ7ኛ ዙር እየተደረገ ያለ ሲሆን በከተማችን ደግሞ ለ2ኛ ዙር ተለግሷል።
የደም ልገሳው በዛሬው ዕለት በተመሳሳይ ሰዐት በ20 ከተሞች የተደረገ ሲሆን በተወሰኑ ከተሞች ነገም የሚቀጥል መሆኑን ገልፀዋል።
@dbu11
@dbu111
True Culture University የ2017 የመጀመሪያ የሆነዉን ፕሮግራም በ ጥር 25 ለማቅረብ ዝግጁ ነው። በፕሮግራሙ የፍሬሽማን ተማሪዎችን እንዲሁም አዲስ የTCU አባላት ምዝገባ ይካሄዳል።
📌 ምን ተዘጋጅቷል?
✅ የፍሬሽ ተማሪ አቀባበል ክፍለ ጊዜ
✅ አመታዊ TCU ሪፖርት
✅ መዝናኛ (ግጥም እና ዘፈኖች)
✅ ድርሰት ውድድር
✅ የጥያቄ እና መልስ ክፍለ ጊዜ
✅ የአባልነት ምዝገባ
📅 ቀን፡ እሁድ ጥር 25 ቀን 2017
⏰ ሰአት፡ 8፡00-9፡00 ሰአት
📍 ቦታ፡ PR አዳራሽ ከLH 4 ጀርባ
ዓለም አቀፋዊ እድሎችን ለመዳሰስ፣ ጠቃሚ ግንኙነቶችን ለመገንባት እና ፓን አፍሪካኒዝምን ለማወቅ ይህንን እድል እንዳያመልጥዎት!
@DBU11
@DBU111
ለመሀል ሜዳ ካምፖስ ተማሪዎች አቀባበል ሊደረግ ነው ።
የደ/ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መ/ሜዳ ካምፓስ ተማሪዎችን በታላቅ ድምቀት ለመቀበል የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ እና መ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ቅድመ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል።
ለክብር እንግዶችና ተማሪዎችመ የምሳ ግብዣ ለማድረግ በጣፋጭነቱ በደ/ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ልዩ ብራንድ የተሰጠውን የመንዝ በግ እና ሰንጋ የወረዳው አመራሮች ለዩኒቨርሲቲው አመራሮች ስጦታ አበርክተዋል።
ተማሪዎች እንደቤታቸው የሚደሰቱበት፣እንደ ቤተሰብ የሚንከባከባቸው ማህበረሰብን የሚቀላቀሉበት፣መንዝን በፍቅር የሚናፍቁበት እለት በመድረሱ በርካታ የአቀባበል ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት በጉጉት እየተጠበቁ ነው።
@DBU11
@DBU11
የ2017 ዓ.ም የካቲት ወር የእጩ ተመራቂዎች የዋንጫ ውድድር(GC cup 🏆) የፊታችን ቅዳሜ ይጀምራል።
ውድድሩ በሁለት ምድብ የሚካሔድ ሲሆን 16 ቡድኖች (ትምህርት ክፍሎች) ይሳተፉበታል።
የእግርኳስ ዋንጫ ፍልሚያው ከአዲግራት-ደብረብርሀን ህግ ትምህርት ክፍል ውጭ በ2013 ባች መካከል ሚካሔድ ነው ሚሆነው ከፍተኛ ፉክክር እንደሚኖርም ግምት ተሰጥቶታል።ዋንጫውን ማን ያነሳው ይሆን ቀድማችሁ ግምታችሁን በመልዕክት መስጫ ሳጥን ማስቀመጥ ትችላላችሁ።
dbu11
dbu111
ለምርቃት የሚሆኑ ደረጃቸውን የጠበቁ ሪቫን ስካርቮችን ከሽክረት ህትመትና ማስታወቂያ
ይጎብኙን
አድራሻ ደብረብርሃን ከተማ ስላሴ ቤ/ክ አጠገብ
ለበለጠ መረጃ
Call us 0940219376
@Shikret_channel
@shikret_group
Inbox @shikret007
አጭር መረጃ ስለ መሀል ሜዳ ከተማ
የመሀል ሜዳ ከተማ ከአዲስ አበበ ከ280ኪ.ሜ ርቀት በላይ የሚገኝ ሲሆን ከደብረብርሃን ከተማ ደግሞ በ150ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል ።
የማዓከላዊ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታዎች ከሚገኙበት የመንዝ አከባቢ ዋነኛው ሲሆን የአየር ሁኔታው ቀዝቃዛ ነው ማለት ይቻላል ። ከባህር ጠለል በላይ 3ሺህ ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል።
የማህበረሰብ ጥብቅ ስፍራዎች የሚገኝበት የመንዝ አከባቢ : በብዛት የቱሪስቶች መነሀሪያ ነው ማለት ይቻላል ።
NB: የተጠቀምነው የመሀል ሜዳ ካምፖስ በግንባታ ላይ እያለ የሚያሳይ ምስል ነው
@DBU11
@DBU11
ለዲጅታል ቤተ መጻሕፍት ተጠቃሚዎች በሙሉ ከተማሪዎች ህብረት ባገኘነው መረጃ
በቀን 1/6/2017 ዓ/ም በሁሉም ቤተ መጻሕፍት ያሉ የዲጅታል መጠቀሚያ ኮምፒውተሮች በExit Exam ምክንያት ከጠዋት ሽፍት አገልግሎት የማይሰጡ መሆኑን አውቃችሁ ሌሎች አማራጮችን እንድትጠቀሙ እናሳውቃልን።
ቤተመፅሀፍቱ
የእጩ ተመራቂዎች የዩንቨስስቲ መውጫ ፈተና መጠናቀቁን ተከትሎ በሚቀጥሉት ቀናት ውጤት እንደሚገለፅ የተለያዩ ምንጮች እየገለፁ ነው።
176 ሺህ ተፈታኞች በ 86 የፈተና ማዕከላት ፈተናውን መውሰዳቸው ይታወሳል።
@dbu11
@dbu111
well come back vibe on the road 😎😎😎😎👍
@dbu11
@dbu111
ከመዲናዋ በ135 ኪሎ ሜትር ርቀት እና ተመሳሳይ ከፍታ ላይ የሚገኙት ደብረብርሀኖቹ
2 ወርቅ🥇 + 3 ብር🥈💪🙏
ከ 49 ዩንቨርስቲዎች ስምንተኛ ደረጃ ። 🏆 ምርጥ 10 ውስጥ ገብተው አጠናቀዋል።
say well come back (ዘማች ሲመለስ) ድጋፋችሁን አሳዩአቸው ፤በዙ ተማሪዎች ዳሸን ቢራ ድረስ ሔደው ለመቀበል ወደዚያው እያመሩ ነው ።
Good job DBU!
@dbu11
#አቀባበል
ደብረብርሀን ዩንቨርስቲ ስፖርት ልዑክ በ2017 የኢቲዮዽያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስፖርት ፌሲቲቫል (ውድድር) ዩኒቨርስቲያችን ደብረብርሃን በተፋለመባቸው ውድድሮች ላይ 5 ሜዳልያዎችን በማሸነፍ እና ስምንተኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ዩንቨርስቲያቸው እየተመለሱ ነው።
ተማሪዎች አቀባበል ለማድረግ ሁለት ባሶች አስተዳደር ህንፃ አካባቢ ተዘጋጅተዋል እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት አቀባበል አድርጉላቸው።
dbu11
dbu111
ለመሃል ሜዳ ካምፓስ ለወጣው የቅጥር ማስታወቂያ የተወዳደራችሁ ውጤታችሁን ከዚህ በላይ ባሉት ምስሎች ተያይዘው ታገኛላችሁ።
@DBU11
@dbu111
ለተማሪዎች የማስጠንቀቂያ መልዕክት
ከሰሞኑን ለfinal እንዲሁም የexit ጥናትን ተከትሎ ሌሊት ላይ ከቤተ መፅሃፍት አምሽታችሁ የምትወጡ ተማሪዎች ወደ ዶርም ስትገቡ አልያም ከ ዶርም ወደ ቤተ መፅሃፍት ስትሄዱ በተቻላችሁ መጠን ሁለትና ሶስት እየሆናችሁ አካባቢያችሁን በንቃት እየቃኛችሁ እንድትሄዱ ስንል እናሳስባለን።
👉እንደ earphones,airpod የመሳሰሉ የአካባቢ ድምፆችን ከመስማት የሚከለከክሉ ነገሮችንም ከመስማት ተቆጠቡ።
በሌላ በኩል የወንዶች ብሎክ ላይ የስርቆት ስራዎች (መስኮት ሰብሮ መግባትን ጨምሮ ለምሳሌ ብሎክ 34 ና 41 )ተበራክተዋል ።
👉ተማሪዎች በተለይም የታችኛው ወለል( Ground ) ላይ የምትገኙ ስልካችሁን በአቅራቢያችሁ እንድታደርጉ እንዲሁም በራቹንና መስኮታችሁን ከመተኛታችሁ ፤ከመውጣታችሁ በፊት መዝጋታችሁን እንድታረጋግጡ ስንል በአፅንኦት እናሳስባለን።
👉ከዚህ በተጨማሪ ጨለማን ተገን አድርጋችሁ ወንጀል የምትሰሩ ተማሪዎች ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እያስጠነቀቅን ከድርጊታችሁ ለማትቆጠቡ ተማሪዎች ግን ከፍተኛ ክትትል እያደረግን እንደሆነ ልናሳውቃችሁ እንወዳለን።
ይህንን ተግባር የሚፈፅሙ አካላትን ያያችሁ ፣የምታውቁ ተማሪዎች ሠላም ለሁላችንም ነውና ተጠርጣሪዎቹን ለሚመለከታቸው አካላት እንድታሳውቁ ስንል እናሳስባለን ።
የደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ ሰላምና ደህንነት ስራ አስፈፃሚ
@dbu11
@dbu111
ይህን ፖስት ከለቀቅንበት ሰዓት ጀምሮ 18 ሰዓታት ብቻ ይቀራሉ
የመጀመሪያው (first session examinees)ሀገር አቀፍ የዩንቨርስቲ መውጫ ፈተናቸውን ለመውሰድ ነገ 2:30 AM local time exam room ይቀመጣሉ።
በነገው ዕለት የሚጀምረውን መውጫ ፈተና ሚወስዱት በተለያየ መሰናክል ውስጥ ያለፉ
ከአዲግራት ዩንቨርስቲ ህግ ትምህርት ቤት በዝውውር የዩንቨርስቲው ህግ ተማሪዎች የሆኑት ህግ ተማሪዎችን ጨምሮ በተከለሰው ስርዓተ ትምህርት አራት አመት የትምህርት ዘመን የዩንቨርስቲ ቆይታ ያላቸው 2013 ባች ተማሪዎች ናቸው።
ደብረብርሀን ዩንቨርስቲ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲን በመቅደም ከጅማ ዩንቨርስቲ ቀጥሎ 2248 holding capacity በመያዝ የመጀመሪያው ፈተና ላይ ሚቀመጡት Accounting and finance ትምህርት ክፍልን በአንድ session ያስፈትናል።በአጠቃላይ 3516 ተማሪዎችን የሚያስፈትን ሲሆን።በ 1086 የተማሪ ብዛት ከፍተኛውን ቁጥር የሚወስደው ትምህርት ክፍል Management ነው።
daily news መልካም እና ጥሩ ውጤት ምታስመዘግቡበት ፈተና ይሆን ዘንድ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።
@dbu11
@dbu111
ደብረብርሃን የከተማ ውስጥ ትራንስፖርት
የተሻሻለው የታክሲ ትራንስፖርት ታሪፍ ከላይ የሚመለከተውን ይመስላል።
@DBU11
@DBU111
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና የሰዓት ቅንጅት ከላይ የተቀመጠውን ይመስላል።
@DBU11
@DBU111
በኢትዮጵያ የዩንቨርስቲ ታሪክ ለብዙ በሚሊዎን ለሚቆጠሩ ተማሪዎች Freshman course video በአማርኛ በማቅረብ ባለውለታ የሆነው
A+ Ethiopia እነሆ አንደኛ አመቱን በማስመልከት 50ሺ Subscribers የመግባት Challenge ተጀምሯል 🥰
ለዚህም 10ሺ ብር ተዘጋጅቷል 😙 #ሰብስክራይብ በማድረግ እንዲሁም ለመጨረሻ ግዜ በተለቀቀው Logic chapter 5 በአማረኛ video ላይ Comment በማድረግ ብቻ 10ሺ ብር ተሸላሚ መሆን ትችላላችሁ🙌
ሽልማቱ በሚቀጥለው ወር በ 21 በ ቀጥታ ስርጭት ይወጣል ።
ለመሳተፍ
ዩቱብ 🔗🔗🔗🔗 👇👇👇
https://youtu.be/crJ4mQTGvZs?si=gxjGA_Mpd12EoZj9
በቴሌግራም ለመቀላቀል 10ሺ + 👇👇
👉 @AplusEthiopia
👉 @AplusEthiopia
👉 @AplusEthiopia
@dbu11
@dbu1111